Professional Documents
Culture Documents
የዜጎች ቻርተር
Citizen Charter
2005 ዓም
2013
0
ማውጫ
መግቢያ፣............................................................................................................................................2
የቻርተሩ ዓላማ፡-.................................................................................................................................2
የመ/ቤቱ ተልዕኮ፤ ራዕይ፤ እሴቶች..........................................................................................................3
የመ/ቤቱ ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት..................................................................................................3
የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ድንጋጌዎች...........................................................................4
የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ሥልጣንና ተግባር፤............................................................................................4
ስለኦዲት ሥርዓት ወሰንና የጊዜ ገደብ....................................................................................................6
የኦዲት ተደራጊዎች ግዴታ...................................................................................................................6
የመተባበር ግዴታ.................................................................................................................................6
የማስታወቅ ግዴታ...............................................................................................................................7
ዋናው ኦዲተር መ/ቤት የሚያከናውናቸው የኦዲት ዓይነቶች....................................................................7
ዋናው ኦዲተር መ/ቤት የሚከተለው አሰራር-..........................................................................................8
ኦዲቱን ለማከናወን የተቀመጠ ስታንደርድ............................................................................................10
የሙያ ስነ ምግባር ስታንዳርድ.............................................................................................................10
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤የሚከናወኑበት ቦታ፤ክንውኑ የሚወስደው ጊዜ........................................11
የፋይናንሻል ኦዲት ዋና እና ዝርዝር ተግባራት የሚከናወኑበት የጥራት ስታንዳርድ.......................................13
ለክዋኔ ኦዲት ዋና ዋና ተግባራት የተቀመጠላቸው የጥራት ስታንዳርድ.....................................................20
የተገልጋዮች መብት...........................................................................................................................20
ከኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች........................................................................20
አገልግሎቱ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት.......................................................................................21
አስተያየት የሚሰጥባቸውና ተሳትፎ የሚደረግባቸው ሁኔታዎች..............................................................22
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስነ ሥርዓት..............................................................................................22
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮችን አስመልክቶ ካሣና የተለያዩ ማካካሻዎችን ለማድረግ
የሚወሰዱ ኃላፊነቶች........................................................................................................................23
የክትትልና ግምገማ ሥርዓት...............................................................................................................23
የመረጃ ሥርጭትና ግብረ መልስ..........................................................................................................24
1
1 መግቢያ፣
የደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የሚሰጠውን የኦዲት
አገልግሎት ቀልጣፋና የተገልጋዮችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት የሚያረካ ለማድረግ፤ በዋናው ኦዲተር
መ/ቤት እና በኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች መካከል ያሉትን የሥራ ግንኙነት ለማሻሻል እንዲሁም ኦዲት ተደራጊ
መ/ቤቶች ስለ ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ተግባር፣ሥልጣንና ኃላፊነት ያላቸው ግንዛቤ ለማሳደግና ለኦዲት ሥራ
ተባባሪ እንዲሆኑ ይረዳ ዘንድ ይህ የዜጎች ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡
በመሆኑም ቻርተሩ የደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት
ከኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች ጋር የሚያደርገውን የሥራ ግንኙነት ግልጽ ቀልጣፋና ስኬታማ እንዲሆን
ለሚያደርገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡ በተጨማሪም ቻርተሩ የደቡብ
ብሔሮች፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ
ኦዲቶች፤ ስለኦዲቶቹ ደረጃና የኦዲት ስልቶች /Auditing Procedures/ ለኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች
ለማስታዋወቅ፤ እንዲሁም ከመ/ቤቶቹ የሚጠበቁትን ትብብሮች ለማሳወቅ እንደሚረዳ ይታመናል፡፡
2 የቻርተሩ ዓላማ፡-
2.1 ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለማስፈን፤
2.2 ተገልጋዮች ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሚያገኙትን አገልግሎት አውቀውና የሚጠበቅባቸውን
ቅድመ ሁኔታ ተረድተው የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል፤
2.3 የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ተልዕኮውን እንዳይወጣ ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን ከተገልጋዮች ጋር
በመመካከርና በመተባበር በጋራ ለመቅረፍ፤
2.4 በኦዲት ሥራ ላይ ተገልጋዮችና አገልግሎት ሰጪዎች የባለቤትነት ስሜት እንዲፈጥሩ ለማስቻል፤
2.5 የፋይናንሻል /ሕጋዊነት/ እና የክዋኔ ኦዲት ዋና ዋና የአሠራር ሂደቶችን ግልጽ ለማድረግ እና
2.6 ዋናው ኦዲተር መ/ቤት የልዩ ኦዲት ወይም ምርመራ ሥራ እንዲሠራ በሚጠየቅበት ጊዜ ጥያቄዎችን
ለማስተናገድ የሚጠቀምባቸውን መመዘኛዎችንና የአሠራር ስልቶችን ለመግለጽ ነው፡፡
3.1 ተልዕኮ
በክልሉ የኦዲት ስርዓትን በማጠናከር የክልሉ መንግስት መ/ቤቶች ተግባራቸዉን በወጡ ህጎች፤ ደንቦችና
መመሪያዎች መሰረት ስለማከናወናቸዉ እንዲሁም የሚጠበቅባቸዉን ግብ ለሟሟላት በቅልጥፍናና
ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ ስለመፈጸማቸዉ ተቀባይነት ያላቸዉን የኦዲት ደረጃዎች በመጠቀም ቀልጣፋ
የኦዲት አገልግሎት በመስጠት ለክልሉ ም/ቤትና ለሚመለከታቸዉ አካላት ነጻና አስተማማኝ መረጃ
ማቅረብ፡፡
3.2 የመ/ቤቱ ራዕይ
2
በ 2017 ዓ.ም ለክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገትና መልካም አስተዳደር መስፈን አስተዋጽኦ የሚያደርግ የኦዲት
አገልግሎት የሚሠጥ ሞዴል ተቋም ሆኖ ማየት፡፡
3.3 የመ/ቤቱ እሴቶች
የመ/ቤቱ የአሠራር ባህል የሚገልጹ እሴቶች
ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ማስፈን መሠረታዊ የተልዕኮአችን መገለጫ ነው፡፡
ሙያዊ ነፃነትና ብቃት ማጐልበት የሥራዎቻችን ጥራት ማረጋገጫ ነው፡፡
በመማማርና በመደጋገፍ መልካም የሥራ ግንኙነት መመስረት መሠረታዊ የጋራ አመለካከታችን ነው
መልካም የሙያ ሥነ-ምግባር እሴቶች መላበስ የሥራዎቻችን አፈፃፀም ጥራት መለኪያችን ነው፡፡
ደንበኞቻችንን በቅንነት፤ በትህትናና በታማኝነት ማገልገል ልዩ መለያችን ነው፡፡
3
4.1.3 የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤትን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች
ያስገኙት ውጤት ሕጉን የተከተለ፣ ኢኮኖሚያዊ በሆነ አሠራር የተፈጸመ መሆኑንና ተፈላጊውን ግብ
መምታቱን ለማረጋገጥ እንደ አስፈላጊነቱ የክዋኔ ኦዲት ያደርጋል፤ ያስደርጋል፤
4.1.4 የክልል መንግሥት ከብር 5 ዐዐ,ዐዐዐ /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሚጠይቅ ሥራ የግል ሥራ
ተቋራጮች እንዲሠሩ በውል የሰጠ እንደሆነ ይህንኑ መንግሥት ነክ የሆነ የግል ሥራ ተቋራጮች ሂሣብ
ይመረምራል፡፡ ሆኖም የማጭበርበር ድርጊት ለመፈጸሙ ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ፍንጭ ያገኘ እንደሆነ
ሥራው የሚጠይቀው ገንዘብ ከብር 500000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በታች ቢሆንም የመንግስት
ሥራ ነክ የሆነ የተቋራጮች ሂሳብን ይመረምራል፤ያስመረምራል፤
4.1.5 በክልል ምክር ቤት ጥያቄ፤በመደበኛ የኦዲት ሥራ ጊዜ የዋናው ኦዲተር መ/ቤት በሂሳቡ ላይ ተንኮል
ለመሰራቱ ፍንጭ ከታየ፤ በፍርድ ቤቶች አግባብ ያለው ትዕዛዝ ሲቀርብና እንዲሁም በጉዳዩ ክብደት
ላይ ተመስርቶ ከመንግስት መ/ቤቶች፤ ከድርጅቶችና ከህብረተሰቡ በሚቀርበው ጥያቄና ጥቆማ
በመነሳት ከመደበኛ ኦዲት ውጭ የልዩ ኦዲት ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያስደርጋል፤
4.1.6 ከዚህ በላይ በሰፈሩት ድንጋጌዎች መሰረት ያከናወነውን የኦዲት ሥራ ውጤት አግባብ ላለው
የመንግስት መ/ቤት ወይም ለድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ያሳውቃል፡፡ የኦዲት ውጤቱ ወንጀል መፈጸሙን
የሚያሳይ ሆኖ ሲገኝ ለሚመለከተው አካል ወዲያውኑ ሪፖርት ያደርጋል፣
4.1.7 ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች እንዲሁም ከፌደራልና ከሌሎች ክልል የኦዲት
መ/ቤቶች ጋር በመመካከር የኦዲት ደረጃ /ስታንዳርድ/ እና የአሰራር ሥርዓት መወሰኛ መመሪያዎችን
ያወጣል፤
4.1.8 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለውስጥ
ኦዲተሮች ተገቢውን ስልጠናና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክርነት ይሰጣል፤ እንደ አስፈላጊነቱም
የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲቀርብለት ሊያደርግ ይችላል፤
4.1.9 አንድ ሂሣብ ወንጀል ባለበት ሁኔታና ታማኝነት በጎደለው አኳኋን መያዙን ለማመን ምክንያት ያለው
እንደሆነ ይህንኑ ሂሣብ የሚመለከቱ ጽሑፎች፣ መዘክሮች፣ መዝገቦች፣ ሰነዶችና ሌሎች ተያያዥነት
ያላቸው መረጃዎች ላይ ያሽጋል፤
4.1.10 የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ስለገንዘብና የሂሣብ አጠባበቅ በሚያዘጋጀው ህግና ደንብ
ረቂቆች ላይ አስፈላጊውን ምክርና አስተያየት ይሰጣል፣
4.1.11 ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል መንግስታት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሂሣብ አያያዝ እና
የኦዲት ሙያ ትክክለኛውን ፈር ይዞ እንዲዳብር ጥረት ያደርጋል፤
4.1.12 በክልሉ ውስጥ በኦዲት ሙያ ለሚሰማሩ ኦዲተሮችና የሂሳብ አያያዝ ሥራ ለሚያከናውኑ የሂሳብ
አዋቂዎች በስራው መስክ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ያድሳል፤
ያግዳል፤ ይሰርዛል፤
4
4.1.13 ከፌደራል መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጋር በመተባበር የኦዲተሮችንና የሂሳብ አያያዝ
ባለሙያዎችን የብቃት ማረጋገጫ የምስክርነት ወረቀት ለመስጠት፤ ለማደስ፤ለማገድ እና ለመሰረዝ
የሚያስችል ወጥነት ያለው ደረጃ ያወጣል፤
4.1.14 የምሥክር ወረቀት በሚሰጥበትና በሚያድስበት ጊዜ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን ዋጋ
ያስከፍላል፤
4.2 ዋናው ኦዲተር ያከናወነውን የምርመራ ውጤት ለተመርማሪው መስሪያ ቤት/ድርጅት/ኃላፊ ያሳውቃል፡፡
የተመርማሪ መ/ቤትና ድርጅት የበላይ ኃላፊ በምርመራ ውጤት ላይ የሚሰጠውን
አስተያየት፤የሚያቀርበው ተቃውሞ አጥጋቢ ያለመሆኑን ዋና ኦዲተሩ የገመተ እንደሆነ የተሰጠውን
አስተያየትና የቀረበውን ተቃውሞ መ/ቤቱ በሚያቀርበው ዓመታዊ ሪፖርት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
5
4.4.4 የኦዲት ተደራጊ መ/ቤትን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ እንዲቻል በሕግ ጥላ ሥር የሚገኝ ጉዳዩ
የሚመለከተው ግለሰብ በሚጠይቅበት ጊዜ ለማስመርመር ግዴታ አለበት፡፡
6
የክዋኔ ኦዲት የክልሉ መንግስት መ/ቤቶች ዕቅዶች፣ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ኢኮኖሚያዊ፤ ውጤታማና
ብቃት ያለው አፈጻጸም እንዲኖራቸው የሚያስችል ግብዓት ለመስጠት የሚከናወን የኦዲት ዓይነት ነው፡፡
ኦዲቱ አራት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን ደረጃዎቹም፤
የቅድመ ኦዲት ሥራዎች( pre-engagement activities)
የዳሰሳ እና የአዋጭነት ጥናት (Overview & Feasibility study)
ዝርዝር የኦዲት ዕቅድ ማዘጋጀትና ኦዲት ማድረግ (Detail Planning & execution)
ሪፖርቲንግ (reporting) ናቸው፡፡
ኦዲቱ የዋና ኦዲተር መ/ቤት በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የኦዲት ሥራ ዕቅድ ወይም በክልል ም/ቤት ጥያቄ
መሰረት በማንኛውም ጊዜ ተጀምሮ ሊከናወን ይችላል፡፡
5.3 ልዩ ኦዲት (Investigation)፡-
ከክልል ምክር ቤት፤ ከስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን፤ ከፍርድ ቤቶች፤ ከኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች እና
ክህብረተሱ በሚቀርብ ኦዲት ይደረግልን ጥያቄና ጥቆማ መሰረት የሚከናወን ኦዲት ሲሆን የኦዲት ሥራውም
እንደጉዳዩ ዓይነት የሚለያይ ነው፡፡
የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሚቀርብለትን የልዩ ኦዲት ጥያቄ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ውሣኔ ላይ ከመድረሱ
በፊት ጥያቄው አምሰት መመዘኛዎችን ማሟላቱን ያረጋግጣል፡፡
መመዘኛዎቹም የሚከተሉት ናቸው
5.3.1 ጥያቄው ለዋናው ኦዲተር መ/ቤት በአዋጅ ከተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት ጋር የሚጣጣም መሆኑን፤
5.3.2 ሥራውን ለመሥራት የሚያስችል ብቃትና ግብዓት መኖሩን፤
5.3.3 ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ጥያቄውን ቢቀበል በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸው መደበኛ የኦዲት ሥራዎችንም
ማጠናቀቅ መቻል አለመቻሉን፤
5.3.4 እንዲሠራ የተጠየቀው ኦዲት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መሥራት የሚቻል መሆን
አለመሆኑን፤
5.3.5 የዋናው ኦዲተር መ/ቤት የሙያ ነፃነትን የማይነካ እንዲሁም የዋናው ኦዲተር መ/ቤት የኦዲት
ደረጃዎችን ለመተግበር ማስቻል አለማስቻሉ የሚሉ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ከመ/ቤቶቹ የተጠየቁት የኦዲት/የምርመራ ይደረግልን ጥያቄዎች፣ መመዘኛዎቹን ቢያሟሉም
እንኳ በአንድ ጊዜ ከተለያዩ አካላት በርካታ ጥያቄዎች ከቀረቡ ሁሉንም መቀበል ስለማይቻል የቀረበው ጥያቄ
ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ወይም የንብረት ምዝበራን የሚመለከት ከሆነ ቅድሚያ ሊሰጠው ይችላል፡፡
7
6 ዋናው ኦዲተር መ/ቤት የሚከተለው አሰራር-
6.1 የኦዲት ሪፖርቶች በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረቱ፤ ሚዛናዊና የኢትዮጵያ መንግስት የኦዲት
ደረጃዎችን (Ethiopian government auditing standards) እና ዓለም አቀፍ የመንግስት ኦዲት
ደረጃዎችን (International government auditing standards) ያሟሉ ይሆናሉ፡፡
6.2 ኦዲቶች ሲካሄዱና ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያ መንግስት የኦዲት ደረጃዎችን (Ethiopian government
auditing standards) እና ዓለም አቀፍ የመንግስት ኦዲት ደረጃዎችን (International government
auditing standards) ያሟሉ እንዲሆኑ በየደረጃው ተገቢውን የጥራት ቁጥጥር (quality control)
ያደርጋል፡፡
6.3 ኦዲት ከመጀመሩ በፊት የትብብር ደብዳቤ ለክዋኔና ለፋይናንሻል ኦዲት፤ በተጨማሪም
የኢንጌጅመንት ደብዳቤ(engagement letter) ለፋይናንሻል ኦዲት ይልካል፡፡
6.4 የኦዲት ቡድን ኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች እንደደረሰ የትብብርና የኢንጌጅመንት ደብዳቤ
ይሰጣል፤የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የመግቢያ (entrance) ስብሰባዎችን በማድረግ ስለኦዲቱ
አጠቃላይ ሁኔታ ማብራሪያ ይሰጣል፤
6.5 ከላይ በተራ ቁጥር 6.4 የተገለጸው ቢኖርም ለማከናወን የታሰበው ልዩ ኦዲት ከሆነና ስለ ኦዲቱ
መጀመር በቅድሚያ ማሳወቅ በሥራው ሂደትና ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሎ
ከታሰበ ስለኦዲቱ መጀመር በቅድሚያ ላይገለጽ ይችላል፡፡
6.6 የፋይናንሻል /ሕጋዊነት/ ተከታታይ ኦዲት የመጀመሪያ ዙር እንደተጠናቀቀ ረቂቅ የማኔጅመንት
ደብዳቤ (draft management letter) ተዘጋጅቶ ለኦዲት ተደራጊው ይሰጣል፡፡
6.7 የሚከናወኑ ኦዲቶች /ምርመራዎች/ በኢንጌጅመንት ደብዳቤው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ
እንዲጠናቀቁ ያደርጋል፤
6.8 የተከታታይ ኦዲቱ 2 ኛ ዙር የኦዲት ሥራ ሲጠናቀቅ፤ የክዋኔ እና በተከታታይ ኦዲት የማይሸፈኑ
መ/ቤቶች የፋይናንሻል ኦዲት እንደተጠናቀቀ የመውጫ ስብሰባ ይደረጋል፡፡ የስብሰባው ዓላማ ኦዲቱ
በተከናወነበት ጊዜ የተገኙት ግኝቶችና ግኝቶቹም በተሟላ ማስረጃ የተደገፉ መሆኑን የኦዲት ተደራጊ
መ/ቤቶች እንዲያውቁት ለማድረግ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኦዲቱ ወቅት የተገኙትን ችግሮች
/ግኝቶች/ ለመፍታት ያስችላሉ ተብለው በቀረቡት የማሻሻያ ሀሣቦችና የተደረሰባቸው
መደምደሚያዎች በስብሰባው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡ በስብሰባው ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው
የኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች እና ሥራው የሚመለከታቸው የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊዎች
ይገኛሉ፡፡ በስብሰባው ወቅት ኃላፊዎቹ የሚሰጡት አስተያየት በቃለ ጉባኤ ከተያዘ በኋላ ተፈርሞበት
አስተያየቱ በመጨረሻው ሪፖርት ውስጥ እንዲካተት ይደረጋል፡፡
8
6.9 በክልል ምክር ቤት፣ በፍርድ ቤቶች፣ በሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተጠይቆ ለሚካሄዱ የልዩ
ኦዲት ሥራዎች የመውጫ ስብሰባ ላይደረግ ይችላል፡፡ ኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች በተገኙ ግኝቶችና
በተደረሰባቸው ድምዳሜዎች ላይ አስተያየት አንዲሰጡ ላይጠየቁ ይችላሉ፡፡
6.10 የፋይናንሻልና ክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ለኦዲት ተደራጊ መ/ቤት ይላካል፣ የልዩ ኦዲት ሪፖርት ለጠየቀው
አካል ይላካል፣ እንደአስፈላጊነቱ ግልባጭ ለሚደረግላቸው አካላት ይልካል፡፡
6.11 ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ለሥራው የሰበሰባቸውን መረጃዎች በተለይም በከፍተኛ ጥንቃቄ መጠበቅ
የሚገባቸውን በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡ መረጃውን የሰጠው መ/ቤት የሚጠይቀውን
የመረጃ አጠባበቅ ሥርዓት ለማሟላትም ዋናው ኦዲተር መ/ቤት የተቻለውን ጥረት ያደርጋል፡፡ ሆኖም
ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ጥንቃቄ የሚያስፈልገውን መረጃ ለማግኘት የመፈረም ወይም ከኦዲት
ተደራጊው መ/ቤት ጋር የተለየ ስምምነት የማድረግ ግዴታ የለበትም፡፡
6.12 ከተለያዩ አካላት የሚቀርብ የልዩ ኦዲት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ ሥራው መቼ እንደሚጀመር
ተቀባይነት ካላገኘ ደግሞ ምክንያቱን በ 1 ዐ የሥራ ቀናት ውሰጥ ጥያቄውን ላቀረበው መ/ቤት
ይገልጻል፡፡
6.13 ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ከክልል ምክር ቤት በጽሁፍ ከተጠየቀ ሪፖርታቸው ለህዝብ ይፋ ለሆኑ
ኦዲቶች ደጋፊ የሆኑ ኦዲቱ በተከናወነበት ወቅት የተዘጋጁ ሰነዶችንና መረጃዎችን ለምክር ቤቱ
ሊሰጥ ይችላል፡፡ ሥራው በሂደት ላይ ያለ ኦዲት ወይም ምርመራ በሚከናወንበት ወቅት የተያዙ
የኦዲት መረጃዎች ለማንኛውም አካል አይሰጥም፡፡
9
7.1.5 *Ç=}` Y^¨<” uT>ÁŸ“¨<”uƒ Ñ>²? ¾Y^ ኃ Lò’~” uSÖkU u*Ç=ƒ }Å^Ñ>‹ Là }Ñu= ÁMJ’
Ý“ SõÖ` ¾KuƒU'
7.1.6 *Ç=}` *Ç=ƒ ŸT>ÁÅ`Ѩ< S/u?ƒ wÉ` SÖ¾pU J’ S¨<cÉ ¾KuƒU::
7.1.7 *Ç=}` *Ç=ƒ ¾T>ÁÅ`Óuƒ ¾H>Xw c’Ê‹“ Ÿ*Ç=ƒ }Å^Ñ>‹ ¾}cÖ<ƒ” ¾Y^ SX]Á‹
በታማ˜’ƒ Öwq Y^¨<” እ”ÇÖ“kk SSKc Õ`u ታ M::
7.1.8 *Ç=}` ¾S”ÓYƒ” Y^ c¯ƒ u›Óvu< KS”ÓYƒ Y^ TªM ›Kuƒ :
7.1.9 ¾*Ç=}` ª“ ƒŸ<[ƒ uÓ˜„‡ Là єu=“ ¾Te}"ŸÁ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ›e}Á¾ƒ KSeÖƒ
እ”Í= eI}ƒ ðLÑ> w‰ SJ” ¾KuƒU::
7.1.10 *Ç=}` ¾Se]Á u?~” SM"U eU ¾T>Öwp“ ¾›c^` vIM እንዲዳብር ¾T>Ø` SJ” ›Kuƒ::
7.1.11 *Ç=}` uY^ ›Ò×T> ¾Á³†¨<” T”—¨<U óÃM T>eÖ=^©’ƒ SÖup ›Kuƒ::
7.1.12 *Ç=}` *Ç=ƒ eKT>Å[Ѩ< Se]Á u?ƒU J’ W^}— Ÿ›ÉKA©’ƒ ’é J• S[Í uTcvcw ƒ¡¡K—
ÉUÇT@ LÃ K=Å`e ÃÑvM::
10
ተ.ቁ ዋና እና ዝርዝር ተግባራት አንድ ክንውን የሚወስደው ጊዜ በሰዓት
ስራዎች ስራዎች
የሚሰሩበት የሚሰሩበት
ቦታ ወቅት ዝቅተኛ መካከለኛ ከፍተኛ
ስጋት ስጋት ስጋት
1 የቅድመ ኦዲት ሥራዎች ( pre- በኦዲት ዋናሥ/ሂ ከነሐሴ-ሰኔ 24 30 30
engagement activities) ቢሮ ውስጥ
2 የዳሰሳ እና የአዋጭነት ጥናት ከነሐሴ-ሰኔ 859 998 1343
(Overview & Feasibility መስክ ላይ
study)
3 ዝርዝር የኦዲት ዕቅድ ማዘጋጀትና ከሐምሌ-ሰኔ 1334 1508 1794
ኦዲት ማድረግ (Detail መስክ ላይ
Planning& ececution)
4 ሪፖርቲንግ (reporting) በኦዲት ከሐምሌ-ሰኔ 314 358 392
ዋና/ሥ/ሂ/ ቢሮ
ውስጥ
ድምር 2531 2894 3559
11
መለያ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
Completed by Reviewed
by
12
መለያ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
Completed by Reviewed
by
P20 ለእያንዳንዱ ኦዲት ፕሮግራም የኦዲት ናሙና ኦዲተር ቡድን መሪ
መወሰን( determine the sample size for each audit (Auditor) (Team
procedure and sample source leader)
13
መለያ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
Completed by Reviewed
by
የሂሳብ መግለጫዎች ማዘጋጀት ቡድን መሪ ማናጀር/ma
(Team leader) nager/
በጀት ማመዛዘን /budget analysis ኦዲተር ቡድን መሪ
(Auditor) (Team
leader)
15
መለ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
ያ Completed by Reviewed by
LEVEL
P14 አጠቃላይ የኦዲት ስትራቴጂ ማዘጋጀት OVERALL AUDIT ቡድን መሪ ማናጀር/man
STRATEGY (Team leader) ager/
P16 የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት መግለጫ /system description for ኦዲተር ቡድን መሪ
audit components/ ማዘጋጀት (Auditor) (Team
leader)
16
መለ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
ያ Completed by Reviewed by
E9 የኦዲት ማስታወሻ (audit query) ኦዲተር ቡድን መሪ
(Auditor) (Team
leader)
17
መለ ዋናና ዝርዝር ተግባራት ማጠናቀቅ መከለስ
ያ Completed by Reviewed by
ረቂቅ የኦዲት ሪፖርት(specimen audit report) ማናጀር ዳይሬክተር
/manager/ (director)
8 የተገልጋዮች መብት
8.1 ተገልጋይ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ፤በፆታ፤ በብሔር፤ በቋንቋና በመሳሰሉት ጉዳዮች ልዩነት ሳይደረግ
አገልግሎት ማግኘት
8.2 ቅሬታ የማቅረብና ምላሽ የማግኘት
18
9.2.4 አናሊቲካል (Analytical) ማስረጃ በኦዲት ተደራጊው መ/ቤት ወይንም በዋና ኦዲተር
መ/ቤት ኦዲተሮች የተዘጋጁ መረጃዎችን በመተንተን የሚገኙ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ኦዲት
ተደራጊ መ/ቤቶች አራቱንም ዓይነት ማስረጃዎች በተፈለገው ጊዜ በተጠየቀ በ 3 ቀን ውስጥ
መስጠት፡፡ በተለይም ከመ/ቤቶቹ የሥራ አመራር አባላት ብቻ ሊገኝ የሚችል ማስረጃ
በሚፈለግበት ጊዜ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በተገቢው ጊዜ የመስጠት ኃላፊነት
አለባቸው፡፡
9.3 ለኦዲተሮች ሥራ ተስማሚ የሆነ ቢሮ የሥራ ጊዜ ሳይባክን አዘጋጅቶ መስጠት፤
9.4 የኦዲት መግቢያና መውጫ ስብሰባዎች በኢንጌጅመንት ደብዳቤ (engagement letter) ውስጥ በተመለከቱት
ቀነ ገደቦች ለማካሄድ እንዲቻል ሁኔታዎች ማመቻቸት እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በተጠቀሱት
ስብሰባዎች መገኘት፤
9.5 ለኦዲት ሥራ የሚያስፈልጉትን መረጃዎች የሚያውቅና ለኦዲት ሥራ የሚያስፈልጉትን ስብሰባዎችን
የሚያመቻች እንዲሁም ልዩ ልዩ ከኦዲቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለማስፈፀም የሚችል ኃላፊ ( focal person)
መመደብ፡፡
9.6 በረቂቅ የፋይናንሻል (የሕጋዊነት) እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቶች ላይ ያላቸውን አስተያየት በመውጫ ስብሰባ
ወቅት መግለጽ ይኖርባቸዋል፤
9.7 በፋይናንሻል ኦዲት ረቂቅ የማኔጅመንት ደብዳቤ መሰረት በግኝቶቹና በተሰጡ የማሻሻያ ሀሳቦች ላይ እርምጃ
መወሰዱን ወይም የሚወሰድ ስለመሆኑ ለሥራ አመራር ደብዳቤ (management letter) የጽሁፍ ምላሽ ከ 1
እስከ 3 ቀናት ጊዜ ውስጥ መስጠት፤
9.8 ኦዲት ተደራጊ መ/ቤቶች በተሰጣቸው ረቂቅ የሥራ አመራር ደብዳቤና በመውጫ ስብሰባ ወቅት መግባባት
በተደረሰባቸው ግኝቶች ላይ ዋናውን ሪፖርት እስከሚደርስ ሳይጠብቁ የማስተካከያ እርምጃ መወሰድ
ይጠበቅባቸዋል፡፡
19
11.2 የመ/ቤቱና ኃላፊዎች አድራሻ
11.2.1 የመ/ቤቱ ስም የደቡብ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ሲሆን
አድራሻው፤ ሀዋሳ ከተማ ፤ ሐይቅዳር ክፍለ ከተማ፤ ጉዱማሌ ቀበሌ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 66 E-mail
auditorgeneralsouth@yahoo.com
11.2.2 የመ/ቤቱ ኃላፊዎች አድራሻ፤
ተቁ የሥራ አድራሻ
ስልክ ፋክስ ኢሜይል
የኃላፊ ስም ኃላፊነት
1 አቶ ሣህሌ ገብሬ ዋና ኦዲተር 0462201525 0462206138 Gebre_40@yahoo.com
2 አቶ ሲንቦ ሽብሩ ም/ዋና 0462201860 0462204600 ssinbo@yahoo.com
ኦዲተር
20
ሀሰተኛ መሆኑን እያወቀ ወይም እውነተኛ መሆኑን ለማመን ምክንያት ሳይኖረው ማንኛውንም
መረጃ ለዋናው ኦዲተር መ/ቤት ወይም ኦዲተሮች ወይም ለወኪሎች የሰጠ፤
የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ሥራውን በሚገባ እንዳያከናውን ያሰናከለ፤
በቂ ህጋዊ ምክንያት ሳይኖረው ከዋናው ኦዲተር መ/ቤት በቀረቡ ኦዲት ሪፖርቶች ላይ በተሰጡ
የማሻሻያ አስተያየቶችና ሀሳቦች መሰረት ወቅታዊና አጥጋቢ እርምጃ ያልወሰደ፤
ማንኛውም አገልግሎት ተቀባይ የዋናው ኦዲተር መ/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ እና የዚህ ቻርተር
ድንጋጌዎችን እንዲፈጽም በተጠየቀ ጊዜ ፈቃደኛ ሆኖ ያልተገኘ እንደሆነ ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት
ሊደርስ በሚችል እስራት ወይም እስከ ብር 10000.00 /አስር ሺህ ብር/የገንዘብ መቀጫ ወይም
በሁለቱም ይቀጣል፡፡
21
የማስተዋወቅ ተግባር ይከናወናል፡፡ የዜጎች ቻርተርን ክትትልና ግምገማ በማድረግ የተገኙ ውጤቶችን፤
የታዩ ችግሮችን፤ የተወሰዱ እርምጃዎችንና የተደረጉ ማሻሻያዎችን በተመለከተ ግብረ መልስ በጽሁፍ
ይሰጣል፡፡
22