Professional Documents
Culture Documents
ሪፖርት
1 መግቢያ
የክልሉ ዋናው ኦዲተር መ/ቤት” እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 83/1996 በተሰጠው ስልጣንና
ተግባር መሰረት በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሰት በደቡብ ኦሞ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ 2002 በጀት
ዓመት ሂሣብ ኦዲት አድርገናል፡፡
2 የሥራ አመራሩና የዋና ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊነት
ወቅታዊ የሆኑ የሂሣብ መግለጫዎችን አዘጋጅቶ ማቅረብ የኦዲት ተደራጊው መ/ቤት የሥራ አመራር ኃላፊነት
ሲሆን፣ ¾H>dw SÓKÝ‹” ኦዲት uTÉ[Ó S<Á© ¾*Ç=ƒ አስተያየት መስጠት ደግሞ የክልሉ ዋናው
ኦዲተር መ/ቤት ኃላፊነት ነው፡፡
3 የኦዲቱ ወሰንና ኃላፊነት
ኦዲቱ የተከናወነው ዓለም አቀፍ የኦዲት ደረጃዎችን መሰረት ያደረገው የኢትዮጵያን የመንግስት ሂሳብ የኦዲት ደረጃዎች
በመከተል ነው፡፡ እነዚህን የኦዲት ደረጃዎች መከተል ኦዲቱን በሚገባ አቅደን በመስራት በተዘጋጁት የሂሳብ መግለጫዎች
ላይ አጥጋቢ የሆነ ማረጋገጫ / የኦዲት አስተያት / ለመስጠት ያስችለናል፡፡
ኦዲታችን የሚያካትተው፡-
4 የኦዲት ግኝት፣
1 በሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ ያልተመዘገበ ብር 171,648.29 በሌጀር ያልተመዘገበ ብር 446.56 የገቢ
ሂሳብ ተገኝቷል፤
2 በማነስ ወደ ገቢ ሂሳብ ሪፖርት የተላለፈ የገቢ ሂሳብ ብር 318,278.92 ተገኝቷል፤
3 በታጠፈ የወጪ ማስመስከሪያ የተመዘገበ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት የተላለፈ የወጪ ሂሳብ ብር 3849.00
ተገኝቷል፤
4 ትክክለኛ ባልሆነ የሂሳብ መደብ የተመዘገበና ሪፖርት የተደረገ የወጪ ሂሳብ ብር 993.60 ተገኝቷል፤
5 በሂሳብ እንቅስቃሴ በወጪ ከተመዘገበው ሂሳብ በማነስ ብር 126,684.35 እና በመብለጥ ብር
123,689.35 በወጪ ሂሳብ ሪፖርት የተላለፈ መሆኑ ታውቋል፤
6 ወደ ተሰብሳቢ ሂሳብ መቀየር ሲገባው ያልተቀየረ የሠነድ ሂሳብ ብር 9,532.84 የበጀት ዓመቱ እና ብር
742,749.20 ውዝፍ ተገኝቷል፤
7 ያለአግባብ የተከፈለ የውሎ አበል ሂሳብ ብር 164.50 ተገኝቷል፤
8 የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት የወጪ ሂሳብ ብር 5012.00 ተገኝቷል፤
9 አግባብ ያለው የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት ወጪ ብር 27,322.70 ተገኝቷል፤
10 የንብረት መዝገብ ያልተቋቋመ እና ምዝገባ የማይከናወን መሆኑ ታውቋል፤
11 የንብረት ቆጠራ እየተደረገ ከመዝገብ ከወጪ ቀሪ ጋር የማይመሳከር መሆኑ ታውቋል፤፤
5 አስተያያት
ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ምክንያቶች በሂሳብ ሪፖርቶች ላይ የሰፈሩት አሀዞች ጉልህ ከሆኑ መዛባቶች የጸዱ
መሆናቸውን፣ ዝርዝር የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች በክልሉ መንግስት በወጡት አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት
መከናወናቸውን፤ የተዘጋጁት የሂሳብ መግለጫዎች የክልሉን መንግስት የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት በመከተል የተዘጋጁ
መሆኑን፤ የመንግስት ንብረት አስተዳደር በክልሉ መንግስት በወጡ ህጎች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት መከናወኑን
በአጥጋቢ ሁኔታ አያሳይም፡፡