You are on page 1of 58

የውስጥ ኦዲት ትርጉም እና ዓላማ

የውስጥ ኦዲት ማለት

ለመንግስት መ/ቤት ተጨማሪ እሴት በሚፈጥር እና የመንግስት መ/ቤቱ የሥራ


እንቅስቃሴ ማሻሻል በሚያስችል አኳኋን የሚቀረጽ ነፃና ገለልተኛ የሆነ
በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ ማረጋገጫና የምክር አገልግሎት
ለመስጠት እንዲያስችል ታስቦ የሚከናወን ተግባር ነው።

2
yWS_ åÄ!T ዓላማ

የውስጥ ኦዲት ዓላማ የመ/ቤቱ ሥራ አመራርና ሠራተኞች ኃላፊነታቸውን


በብቃት መወጣት እንዲችሉ በተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትና በወጡት
የፋይናንስ አሰተዳደር አዋጆች፣ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአሰራር ሥርዓቶች
መሠረት ሥራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን ኦዲት አድርጎ ማረጋገጥ ነውÝÝ

3
የቀጠለ..

በአሁኑ ጊዜ ኦዲት ማለት ነፃና ገለልተኛ በመሆን በእውነተኛ


መረጃዎች ላይ ብቻ ተመሥርቶ ሙያዊ ትንተና በማድረግ
የቀረቡ የሂሳብ መግለጫዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት
መሠረት መከናወን አለመከናወናቸውን አረጋግጦ
ለተጠቃሚው አካል አስተያየት የማያቀረብ ነው፡፡

4
ኦዲት ምን ምን አገልግሎቶችን ይሰጣል?

1. 1.1. የማረጋገጥ /Assurance Service/ተግባር፣

2.2. ነፃና ገለልተኛ የሆነ ሙያዊ የምክር አገልግሎት

/ consulting services/ ይሰጣል ።

“ከምን ዓንጻር”

5
 ጠንካራ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱንና መተግበሩን
ከማረጋገጥ አንጻር፣
 ሥራዎች በህግ፣ ደንብና መመሪያዎችን ተከትለው የተሰሩ
መሆናቸውን ከማረጋገጥ አንጻር፣
 ሥራዎች ኢኮኖሚያዊ፣ ብቃት ባለውና ውጤታማ በሆነ
ሁኔታ መሠራታቸውን ከማረጋገጥ አንጻር ነው።
6
የውስጥ ኦዲተር የሚያከናውናቸው ተግባራት…
የቀጠለ

 በመ/ቤቱ የተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት የመ/ቤቱን ዓላማ በማሳካት


ረገድ ውጤታማ እንዲሆኑ እገዛ ማድረግ
 ማጭበርበርና ስህተትን መከላከል፣
 ማጭበርበርና ስህተት ተፈጥሮ ሲገኝ የማስተካከያ ሀሳብ መስጠት እና ህጋዊ
እና አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ አስተያየት መስጠት፤
 ነፃና ገለልተኛ የሆኑ አስተያየቶች፣ የአሰራር ማሻሻያ ሀሳቦችን ለመ/ቤቱ
ኃላፊ መስጠት፡፡
7
ኦዲተሩ የሚያከናውናቸው የኦዲት አይነቶች

 የፋይናንሻያል ኦዲት /Financial Audit/


 የህግ መከበር ኦዲት/Compliance Audit/
 የክዋኔ ኦዲት/ Performance /Operational Audit/
 ልዩ ኦዲት/Special Audit /

8
የፋይናንስ ኦዲት/Financial Audit/

ኦዲተሮች የሂሳብ መግለጫዎችን /financial statements/


በመመርመር የሂሳብ መግለጫዎቹ በትክክል የመ/ቤቱን
የፋይናንስ አቋም መሆናቸውን
የሚያሳዩ ወይም የማያሳዩ
በማረጋገጥ የኦዲት አስተያየታቸውን የሚሰጡበት የኦዲት
አይነት ነው፡፡

9
ኮምፒሊያንስ ኦዲት/Compliance Audit/

ኦዲተሮች ኦዲት ተደራጊ አካላት ተግባራቶቻቸውን


ሲያከናውኑ ፓሊሲዎችን ፣ህጎችን፣ ደንብ እና መመሪያዎችን
ተከትለው ስለማከናወናቸው የሚያረጋግጡበት የኦዲት
አይነት ነው፡፡

10
የፋይናንስ እና ኮምፒሊያንስ ኦዲት በጣምራ ይሰራሉ፡-

 በገቢ ደረሰኞች /RV/ በተሰበሰበ ገቢ ላይ


 በገንዘብ ዝዉዉርና የክፍያ ማስመስከሪያ/PV/ ፣በሂሳብ
ምዝገባ ማዛዣ /JV/ እና በሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ /TR/
ወይም IBEX ምዝገባ ላይ፣
 በሂሳብ መግለጫዎች ላይ አስተያየት መሰጠትን፣
 የህጎች ፣ደንቦች እና ስርአቶች መከበርን ፣
11
ነገርግን /

 ከላይ የተገለጹት የኦዲት አይነቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-


 የተጠበቀው ውጤት መገኘቱን፣
 የሀብት ብክነት መኖሩን እና
 የሀብት አጠቃቀሙ በብቃት መፈጸሙን፣

"መረጃዎች አይሰጡም "

12
የክዋኔ ኦዲት ትርጉም
/Definition of performance
auditing/

ክዋኔ ኦዲት ማለት የኢኮኖሚ፣ ብቃትና ውጤታማነት ኦዲት


ሲሆን ኦዲት ተደራጊ አካላት ውስን ሀብታቸውን በመጠቀም
አላማቸውን ማሳካታቸውን ለማረጋገጥ የሚካሄድ ኦዲት ነው ፡፡

ወይም "ኦዲት ተደራጊ አካላት ትክክለኛ ስራ በተሻለ መንገድ


እየሰሩ መሆኑን ማረጋገጥ ነው።

13
ልዩ ኦዲት /Special Audit/

አንድ የተለየ ጉዳይ ሲገጥም /በተለይ የህግ ነክ የሆኑ


ጉዱዳዮቸን /ለማጣራት በተለየ ትእዛዘ የሚደረግ የኦዲት
ምርመራን የሚጠይቅ ስራ ሲሆን ከላይ 1-3 የተገለጹትን
የኦዲት ዓይነቶች በተናጥልም ይሁን በጣምራ ኦዲተሩ ሊጠቀም
ይችላል፡

"ማጭበርበር፣ኪራይና ጥቆማ ሲኖር"


14
የውስጥ ኦዲተሮች ከውጪ ኦዲተሮች ጋር
በሚከተሉት ምክንያቶች እየተመካከሩ /ተናበው/
ይሰራሉ

15
ከውጭ ኦዲተሮች ጋር የሚናበቡበት ምክንያት

1. አላስፈላጊ የስራ መደጋገምን ለመቀነስ ወይም የስራ


መዘዘለል እንዳይከሰት፣ በተለይ የውጪ ኦዲተሮች
በውስጥ ኦዲተሮች የተሰራውን ስራ በመገምገም
ደረጃውን የጠበቀ ከሆነ ስራውን በመቀበል አስተያየት
መስጠት እንዲችሉ በማድረግ የኦዲት ሽፋንን ለማሳደግ
ይሰራሉ፤
16
የቀጠለ…

2. መሰረታዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመለዋወጥ፣ ለምሳሌ


የመ/ቤቱ የስጋት አካባቢዎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ በውስጥ
ኦዲቱ ያልተሸፈኑ የስራ ዘርፎች ለይቶ ኦዲት ለማድረግ
እንዲረዳ፣

17
የቀጠለ…

3. በውስጥ ኦዲተሮች አስተያየት የተሰጠባቸው ነገር ግን በስራ


አመራሩ ችላ የተባሉ የኦዲት ግኝቶች በወጪ ኦዲተሮች
ማጠናከሪያ አስተያየት በመስጠት እንዲስተካከል
ለማድረግ እና የክትትል ስራን ምቹ ለማድረግ በጋራ
ይሰራሉ፣

18
የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት

19
የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ትርጉም

 የውስጥ ቁጥጥር የመ/ቤቱን ዓላማና ግብ ለማሳካት እንዲቻል በሥራ


አመራሩ የሚወሰድ ማንኛውም ርምጃ ነው።
 የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት የድርጅቱ የስራ አካል ሆኖ በድርጅቱ ሥራ
አመራር እና ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የድርጅቱን ሥራ

ለመቆጣጠርና የድርጅቱ ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን ክትትል


የሚደረግበት ለመሆኑ ተመጣጣኝ ማረጋገጫ እንዲሰጥ
የተዘረጋ ሥርዓት ነው።
20
የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ጠንካራ ለመባል ሶስት
መሠረታዊ መመዘኛዎችን ማሟላት ይኖርበታል

1. ተገቢ/ትክክለኛ ቁጥጥር በትክክለኛው ቦታ እና ለሥጋት


ተመጣጣኝ የሆነ፣

2. ለተባለው ጊዜ ያለማቋረጥ መሥራቱ፣

3. በወጪ አኳያ ውጤታማ መሆን የውስጥ ቁጥጥሩን


ለመተግበር የወጣው ወጪ ከጥቅሙ መብለጥ የለበትም።

21
የቀጠለ..

• የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ሲዘረጋ ዓላማ


ሊኖረው ይገባል
• የውስጥ ቁጥጥር ሲዘረጋ ዓላማ ከሌለው
የቀጥጥር ሥርዓቱ ጥቅም የለውም

22
የውስጥ ቁጥጥር ዓላማዎች

ሀ. ሥራዎችን በተደራጀ አኳኋን በሥነ-ምግባር በቁጠባ በውጤታማነት


ብቃት ባለው መንገድ ማከናወንን፣

ለ. የተጠያቂነት ግዴታዎችን ማሟላትን፣

ሐ. አግባብነት ያላቸውን ህጎችና ግዴታዎች ተከትሎ መስራትን፣

መ. ሀብትን ከስርቆት አላግባብ ከመጠቀምና ከብልሽት መጠበቅ ናቸው።

23
የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትን እና የውስጥ ኦዲት በሚመለከት
የመንግስት መስሪያ ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ኃላፊነት

1. የመስሪያ ቤቱን በልዩ ልዩ ክፍሎችና ተግባራት እንደየ ባህሪያቸው ከፋፍሎ

የማደራጀት፣ የውስጥ ቀጥጥር ሥርዓትን የመዘርጋት፣

2. የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ኃላፊነቱን በሚገባ ለመወጣት የሚረዳው ዋንኛው

መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ሥርዓቱን የመቅረጽ፣ በሥራ ላይ የማዋልና

በሚፈለገው መንገድ እየተሰራበት መሆኑን የመከታተል፣

3. የተዘረጉ የውስጥ ቁጥጥሮች ፣የወጡትን መመሪያዎችና ደንቦች ውጤታማ

ለማድረግ የሚያስችል አመራር የመስጠትና አቅጣጫ የማስያዝ ኃላፊነት

አለባቸው።
24
4. የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱን በየጊዜው ለመገምገምና የሚታዩ ችግሮችን፣
ሰነዶችንና ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል ግልጽ ዕቅድ የመዘርጋት፣

5. የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱን በተመለከተ በሚደረጉ ግምገማዎች


የሚደረስበትን አጠቃላይ ውጤት መሰረት በማድረግ ተገቢውን
የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ፣
6. የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትን በማስከበሩ ተግባር ላይ ሁሉም የመስሪያ ቤቱ
ሠራተኞች ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን የማመቻቸት
ኃላፊነት አለበት፣
25
የቀጠለ…

7. የኦዲት ሪፖርት እንደደረሰ የሚመለከታቸው የሥራ ሂደቶች


የእርምት እርምጃ ወስደው ውጤቱን እንዲያቀርቡ
የማድረግ ፣

8. የኦዲት ሪፖርት መሠረት የተወሰደውን የእርምት እርምጃ


ውጤት በ15 ቀናት ውስጥ ለቢሮው የማሳወቅ ኃላፊነት
አለበት ፣
26
የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ድክመቶች /limitations of
Internal Control Systems

 የሥራ አመራሩ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትን አለማክበር ፣


 ሥልጣንና ኃላፊነትን አለአግባብ መጠቀም፣
 በሁለትና በሶስት ሠራተኞች መካከል የሚደረግ የሚስጥር
ስምምነት /ሌሎችን ለማታለል ሲባል/ ፣
 ከመ/ቤት ውጪ ከሚገኙ ግለሰቦች ጋር ለጥቅም ሲባል
የሚደረግ የሚስጥር ስምምነት ፣
27
የኦዲት አፈጻጸም

28
የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ኦዲት

የጥሬ ገንዘብ ትርጉም

ጥሬ ገንዘብ ማለት የወረቀት ገንዘብ፣ በባንክ የተመሰከለት ቼክ


/ሲፒኦ/ ፣ በገንዘብ ያዦች እጅ ወደ ባንክ ገቢ የተደረጉ
ዝውውሮች ፣ በዕለት ገቢ ሰብሳቢዎች ፣ በፒቲ ካሸሮች እና
በዕቃ ግዥ ኦፊሰሮች እጅ የሚገኝ ገንዘብን ያጠቃልላል።

29
የጥሬ ገንዘብ ኦዲት ዓላማዎች

 መሰብሰብ የሚገባው ገንዘብ በሙሉ መሰብሰቡንና መመዝገቡን


በመጨረሻም የጥሬ ገንዘብና የባንክ ከወጪ ቀሪ በማጠቃለያ የሂሳብ
ቋቶች በትክክለኛው መጠን መገለጻቸውን ማጣራት፣
 ተገቢ ያልሆኑ ክፍያ አለመፈጸሙን ለማጣራት ፣
 የተሰበሰቡና የተከፈሉ ሂሳቦች በወቅቱና በትክክል መመዝገባቸውን
ለማጣራት ፣
 በጥሬ ገንዘብና በባንክ ከወጪ ቀሪ ሂሳብ ላይ ብክነትና ማጭበርበር
ተፈጽሞ ከሆነ ፈልጎ ለማግኘት ፣
 አጥጋቢ የሆነ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር እና ቁጥጥርና ሥርዓት
መኖሩን ለማረጋገጥ ነው።
30
የጥሬ ገንዘብ አያያዝ

የመንግስት መ/ቤቶች በካዝና እንድይዙ የሚፈቀድላቸው


የጥቃቅን ወጪዎች መሸፈኛ የገንዘብ መጠን እንደ መ/ቤቱ
የስራ ስፋትና እንቅስቃሴ በማየት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ባለበት ርዕሰ ከተማ ከፍተኛው ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ
ብር/ዝቅተኛው ብር 2,000.00/ሁለት ሺህ ብር/ነው።

31
የጥሬ ገንዘብ አያያዝ የቀጠለ…

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሌለበት ርዕሰ ከተማ ከፍተኛው ብር


100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ዝቅተኛው 20,000.00/ሃያ ሺህ
ብር/ ይሆናል።
 በመ/ቤቱ የስራ በህሪይ ምክንያት የተፈቀደው የጥቃቅን ወጪዎች
መሸፈኛ የገንዘብ መጠን ከፍ እንዲል ካስፈለገና መ/ቤቱ ለቢሮው
ጥያቄውን ሲያቀርብ ዝርዝር ሁኔታው ታይቶ በልዩ ሁኔታ ሊፈቀድ
ይችላል ።
32
የጥሬ ገንዘብ አያያዝ የቀጠለ…

የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ከመ/ቤቱ የሥራ እንቅስቃሴ አኳያ


ለጥቃቅን ወጪዎች መሸፈኛ ገንዘብ መያዝ አስፈላጊ
መሆኑንና አለመሆኑን ከላይ ከተፈቀደው መጠን ሳያልፍ
በሳጥን ሊያዝ የሚገባው ጥሬ ገንዘብ መጠን ሊወስን ይችላል።

33
የጥሬ ገንዘብ አያያዝ የቀጠለ…

 መ/ቤቱ ለጥቃቅን ወጪዎች መሸፈኛ ከሳጥን ከሚያዘው ገንዘብ


የሚከፈለው ወጪ እስከ 2,000.00/ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ ለጥቃቅን
ወጪዎች መሸፈኛ በሳጥን ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ በአንድ ሰነድ
ለአንድ ጊዜ ክፍያ የሚፈጸም መሆኑን ማረጋገጥ፣
 ከብር 2,000.00/ሁለት ሺህ ብር በላይ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄ
ወጪዎች በቼክ ከባንክ የሚፈጸም መሆኑን ማረጋገጥ፣

34
የጥሬ ገንዘብ አያያዝ የቀጠለ…

 ለጥሬ ገንዘብ አጠባበቅ ተስማሚ ቢሮና ካዝና መኖሩን ማረጋገጥ፣


 የጥሬ ገንዘብ ገቢና ወጪ መከታተያ መዝገብ /Cash Register Book /
በየቀኑ በአግባቡ የሚመዘገብ መሆኑ ማረጋገጥ
 በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኞችና ማጠቃለያዎች ላይ ቀን፣የከፋይ
ስም፣የክፍያ ምክንያት፣አጣቃሽ ማዘዣ ደብደቤዎች፣የገንዘብ ተቀባይ
ስምና ፊርማ በትክክል በተዘጋጀው ቦታ መጻፉን ማረጋገጥ ፣

35
የዋና ገንዘብ ያዥ የሳጥን መጠባበቂያ

የሳጥን ክፍያ ወርሃዊ ክፍያ


የመንግት ባንክ ባለበት አካባቢ ለሚገኙ ብር 150.00
የመንግት ባንክ በሌለበት አካባቢ ብር 250.00
በፑል ያልታቀፉና ክልል ተቋማት የመንግስት ባንክ ባለበት
የሚገኙ ብር 75.00
በፑል ያልታቀፉና ክልል ተቋማት የመንግስት ባንክ በሌለበት
የሚገኙ ብር 100.00
የመንግስት መ/ቤቶች ከላይ ለተጠቀሰው ክፍያ መጠባበቂያ

36 በጀት መያዝ አለባቸው


የሳጥን መጠባበቂያ በጀት የክፍያ አፈጻጻም

 የሳጥን መጠባበቂያ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ክፍያ የሚፈጸመው


በዓመቱ መጨረሻ ያሳጥን ጉድለት አለመኖሩ ተረጋግጦ ከምስክር
ወረቀት ጋር በዓመት አንድ ጊዜ የሚሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የበጀት ዓመቱ ሳይጠናቀቅ በሥራ ምክንያት ከገንዘብ ያዥነት
የሚለቁ ካሉ የገንዘብ ጉድለት አለመኖሩ ተረጋግጦ የሰሩበት ወራት
ታስቦ ይከፈላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣

37
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ

1. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የሚሰጠው ቼክ ከመስራቱ


በፊት በሞዴል 19 በመ/ቤቱ ገቢ የተደረገ መሆኑን ማረጋገጥ፣

2. ቼክ እንድይዝ ለተወከለው የክፍያ ሠራተኛ በስሙ ወጪ


እንዲደረግ ከስራ ሂደቱ በሚሰጠው ደብዳቤ ከንብረት ክፍል
ወጪ አድርጎ በጥንቃቄ በመያዝ ሥራ ላይ እንዲውል የተደረገ
መሆኑ ማረጋገጥ፣።
38
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ የቀጠለ…

3. ቼክ በሚሰራበት ጊዜ በራሪው /ለባንክ በመሄደው/ የክፍያ

ማዘዣ ላይ የተጻፈ መረጃ በሙሉ በቀሪ /ጉራጅ/ ላይ

የተጻፈ መሆኑን ማረጋገጥ፣

4. በክፍያ ማዘዣ ደረሰኝ ላይ የቼክ ቁጥር የተጻፈ መሆኑን

ማረጋገጥ፣
39
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ የቀጠለ…

4. የቼክ ፈራሚዎች በቀሪውም ጉርድ ቼክ ላይ ፊርማቸውን

ማኖራቸውን ማረጋገጥ፣

5. የቼክ ተቀባይ በጉራጁ ቼክ ጀርባ ላይ የወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር


በመጻፍ ስለመቀበሉ ስም ፣ፊርማና ቀን መጻፉን ማረጋገጥ፣

6. ቼክ በፈራሚዎች እጅ ያልተያዘ መሆኑን ማረጋገጥ፣

40
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ የቀጠለ…

7. ባልተሰራበት ቼክ ላይ አስቀድሞ በኃላፊዎች ያልተፈረመበት መሆኑን


ማረጋገጥ፣

8. ያለቀ ቼክ በሞዴል 42 ተዘርዝሮ ቼኩን የሚይዘው ባለሙያ ለሰነድ


ክፍል የተላለፈ መሆኑን ማረጋጥ

9. በሰነድ ክፍል የሚገኙ ቼኮች ለኦዲት ቀርበው ይመረመራል


በመጨረሻም የገቢና የወጪ ቼኮች ሚዛን በኦዲተሮች ይስራል።
41
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ የቀጠለ…

10. ያልተሰራና የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ ወይም የባንክ ሂሳቡ


እንቅስቃሴ እንዲዘጋ በሚደረግበት ጊዜ የተሰራና ያልተሰራ
በዝርዝር ላባንክ የተላከ መሆኑ፣ባንኩ የሰጠው መረጃ ተያይዞ
በሰነድነት እንዲቀመጥ የተደረገ መሆኑ ማረጋገጥ፣

11. ቼክ ካለው ዋጋ አንጻር በአግባቡ ተቆልፎ ጥንቃቄ ባለበት ስፍራ


የተያዘ መሆኑን ማረጋገጥ፣

42
የቼክ አስተዳደርና የባንክ ሂሳብ የቀጠለ…

12. የተፈረሙ ቼኮች ወዲያውኑ ወጪ መደረግ አለባቸው ካልሆነም አስተማማኝ


በሆነ ቦታ የተቀመጡ መሆኑን ማረጋገጥ፣

13. የባንክ ሂሳብ መዝገብ አጠቃላይ የባንክ ሌጀር የሂሳብ ሪፖርት ድምርና ከወጪ
ቀሪ ትክክለኝነት ማጣራት፣

14. የባንክ ሂሳብ ማሰታወቂያው የተመለከተውን ከወጪ ቀሪ ባንክ ከላከው


ማረጋገጫ ጋር ማነጻጸር

14. የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ በየወሩ መዘጋጀቱና በሌላ ተቆጣጣሪ አካል


43 መጣራቱን ማረጋገጥ፣
ተሰብሳቢ ሂሳብ

ተሰብሳቢ ሂሳብ ትርጉም ፦

በመንግስት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት መሠረት የተሰብሳቢ ሂሳብ


በፋይ/ኢ/ል/ቢሮ ወይም በአንድ የመንግስት መ/ቤት
ከሌላ የመንግስት መ/ቤት ወይም ከመንግስታዊ ካልሆነ
ድርጅት ወይም ግለሰቦች የሚሰበሰብ ማናቸውም
የገንዘብ መጠን ተብሎ ትርጉም ተሰጥቶል።
44
ተሰብሳቢ ሂሳብ የቀጠለ…
 የእያንዳንዱ ግለሰብ የሂሳብ ቋት ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ኦዲተሩ
የሚከተሉትን ሁኔታዎች ለማረጋገጥ በቂና አግባብ ያለው የኦዲት መረጃ
ለማሰባሰብ ዓላማው እድርጎ መነሳት አለበት
h) መኖር (Existence) በተሰብሳቢ ሂሳብ ተመዝግበው የሚገኙት ሂሳቦች
ወርሃዊ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ቀን በእርግጠኝነት መኖራቸውን
ማረጋገጥ፣
l) መብትና ግዴታ (Rights & Obligations)# ተሰብሳቢ ሂሳብ በመ/ቤቱ
ሊሰበሰብ የሚችል (መ/ቤቱ ሂሳቡን ለመሰብሰብ መብት ያለው) መሆኑ፣
ሐ) ሙሉዕነት (completeness)፦ በመ/ቤቱ የሚሰበሰበው ሂሳብ በሙሉ
የተመዘገበ መሆኑ፣

45
የተሰብሳቢ ሂሳብ ኦዲት አፈጻጸም
 የተሰብሳቢ ሂሳብ ከተቀጽላ ቋት የደበኞችን ሂሳብ የምዝገባ ድምርና የሚዛኑ
ትክክለኝነት ማጣራት፣
 ለረጅም ጊዜ ሳይሰበሰቡ የቆዩ ሂሳቦች መኖራቸውን መለየት ምክንያቱን
ማጣራት ፣
 የተሰብሳቢ ሂሳብ ክምችት እንዳይፈጠር ቁጥጥር የሚደረግ መሆኑ ማረጋገጥ፣
 ተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመናቸዉ በዝርዝር መረጃዉን በአግባቡ የተመዘገ
መሆኑና በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ እንዲወዳደቅ ክትትል የሚደረግ
መሆኑን ማረጋገጥ፣
46
ተከፋይ ሂሳቦች ኦዲት

ተከፋይ ሂሳብ ማለት፦ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ወይም ከተቀበሉት


ገንዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸው ወደፊት የሚከፈሉ ግዴታዎች ናቸው።
ማናቸዉንም ወደፊት ክፍያ የሚፈፀምባቸዉ ሂሳቦች ተከፋይ
ሂሳብነታቸዉ የሚያረጋገጥ በቂ ማስረጃ ያላቸው መሆቡን ማረጋገጥ፣
 መስሪያ ቤቶች ከተለያዩ አካላት ቀንሰዉ የሚያስቀሩትን ተቀናናሾች
ለሚመለከተዉ ግብር አስገቢ አካል ወቅቱን ጠብቀዉ ማስተላለፋቸውን
ማረጋገጥ፣

47
ተከፋይ ሂሳቦች ኦዲት የቀጠለ…

 የተከፋይ ሂሳቦች በትክክለኛ ሙሉ ለሙሉ መመዝገባቸውን እና የተመዘገቡትን


ዕዳዎች ህጋዊነት ማረጋገጥ
 ወርሃዊ /ዓመታዊ የተከፋይ ሂሳቦች ሪፖርት በመቀበል ማረጋገጥ
 የተከፋይ ሂሳቦች ድምር ትክክለኝነት ማረጋገጥ
 ለእያንዳንዱ ሂሳብ ሌጀር በመጠየቅ የሌጀር ባላንስ ከተከፋይ ሂሳቦች ሪፖርት ጋር
መስማማቱን በማጣራት በሁለቱ መካከል ለሚታዩ ማናቸውም ልዩነቶች ማጣራት
  የተከፋይ ሂሳቦች ተቀጽላ ሌጀሮችን በመደመር
ከመቆጣጠሪያ ሌጀሮች ድምር ጋር ማገናዘብ፣
48
የወጪ ኦዲቱ ዓላማዎች

የወጪ ሂሳብ ኦዲት መሠረታዊ ዓላማዎች የጥሬ ገንዘብም


ሆነ የቼክ ክፍያዎች በሙሉ በአግባቡ በባለስልጣን የፀደቀ፣
ወጪው የተመዘገበ፣ እና የተከፈለው ገንዘብም መ/ቤቱ
ለአገኘው አገልግሎት ወይም ለገዛውና ለተረከበው ዕቃ
ለመሆኑ በቂ የሆነ ማረጋገጫ ለማግኘት ነው።

49
የወጪ ሂሳብ የቀጠለ…

ይህንን መሠረታዊ ዓላማ ከግቡ ለማድረስ


 ክፍያው አግባብ ባለው ባለስልጣን እየተፈፈቀደ የሚፈጸም መሆኑን
ማረጋገጥ፣
 ክፍያው ለተገቢው አካል ወይም ባለጥቅም ለመፈጸሙ
 ክፍያው ለታሰበውና ለተፈለገው ዓለማና ሥራ መፈጸሙን ማረጋገጥ፣
 ክፍያው ኦዲት የሚደረገውን በጀት ዓመት የሚመለከተው ለመሆኑ
 ከክፍያ ቫውቸሮች ጋር አግባብ ያላቸው ደጋፊ ማስረጃዎች በሙሉ

50 መያያዛቸውን ማረጋገጥ
በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኞች የተቀመጠ ቀላል ቅጣት

1. ከተለያዩ ምንጮች የሚገኝ ገቢ ህጋዊ በሆነ መንገድ


እንዲሰበስቡ ኃላፊነት ለተሰጠው ለተፈቀደው መ/ቤት
ለሥራ የወጣው የገቢ ደረሰኝ ተመላሽ መደረጉ
ሳይረጋገጥ ተጨማሪ ደረሰኝ ወጪ እንዲሆን የፈቀደ
የሥራ ክፍል ኃላፊ እና ወጪ ያደረገው ባለሙያ
ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸውና የተዘረጋው የአሰራር
ሥርዓት በመጣሳቸው እያንዳንዳቸ በአንድ ወር ደመወዝ
ይቀጣሉ

51
ቀላል ቅጣት

2. መደበኛ የግብርና የታክስ እንዲሁም ታክስ ያልሆኑ ገቢዎችን


እንዲሰበስቡ በህግ ሥልጣን ከተሰጣቸውና ከተፈቀደላቸው
መ/ቤቶች በቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመምሪያው ከጽ/ቤቱ
በስሙ የገቢ ደረሰኝ ወጪ አድርጎ በመውሰድ ገቢ ሰብስቦ ገቢ
ሳያደርግ ኃላፊነቱን ሳይወጣ የቀረና የመንግስት ገቢ እስከ
አምስት ቀን በእጁ ያቆየና የተዘረጋው የአሰራር ሥርዓት
52 በመጣሱ በአንድ ወር ደመወዝ ይቀጣል።
ቀላል ቅጣት…የቀጠለ

3. ከመደበኛው ሥራው ጋር በተያያዘ ባለበጀት መ/ቤቶች


የሚሰበስቡትን የአገልግሎት ክፍያ ገቢዎች በስሙ ሰብስቦ እስከ
አምስት በእጁ ያቆየ ባለሙያ የአንድ ወር ደመወዙ ይቀጣል
4. የመደበኛ ታክስ እንዲሁም ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች እንዲሰበስቡ በህግ
ሥልጣን የተሰጣቸውን ገቢ እንዲሰበስቡ ውክልና የተሰጣቸው
መ/ቤቶች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት በስሙ ከመምሪያው
ወይም ከጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ወጪ አድርጎ በመውሰድ ደረሰኙ
ካለቀ በኋላ ለመምሪያው ወይም ለጽ/ቤቱ ተመላሽ ሳያደርግ
ከአምስት ቀን በላይ ያዘገየ ባለሙያ በአንድ ወር ደመወዝ ይቀጣል

53
ከባድ ቅጣት

 የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በስሙ ወጪ በማድረግ


የመንግስትን ጥቅም ለመጉዳት በራሪና ቀሪ ደረሰኝ
ያበላለጠ ባለሙያ አግባብነት ባለው ህግ የሚጠየቀው
እንደተጠበቀ ሆኖ ያበላለጠው ገንዘብ መጠን በልዩነት
በ10/በአስር እጥፍ/ ተባዝቶ ይከፍላል

54
ከባድ ቅጣት….የቀጠለ

 በስሙ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወጪ በማድረግ ከወሰደ


በኋላ ከውስጡ ከአንድ እስከ አምስት ቅጠል የበጨቀ
ወይም የቀደደ ወይም የተበጨቀውን የሰወረ ወይም ያጠፋ
ወይም ከአገልገሎት ውጭ እንዲሆን ያደረግ ባለሙያ
አግባብነት ባለው ህግ የሚጠየቀው እንደተጠበቀ ሆኖ
ከተቀደደው ጥራዝ አስቀድሞ ባለው ጥራዝ የተሰበሰበው
የገንዘብ መጠን ተደምሮ በሁለት እጥፍ እንዲከፍል
ይደረጋል

55
ከባድ ቅጣት….የቀጠለ

 በስሙ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወጪ በማድረግ ከወሰደ


በኋላ ከውስጡ አንድ ቅጠል የበጨቀ ወይም የቀደደ
ወይም የተበጨቀውን የሰወረ ወይም ያጠፋ ወይም
ከአገልገሎት ውጭ እንዲሆን ያደረግ ባለሙያ አግባብነት
ባለው ህግ የሚጠየቀው እንደተጠበቀ ሆኖ በቀሪው 49
ቅጠሎች የተሰበሰበው ገንዘብ ተደምሮ እንዲከፍሉ
ይደረጋል።

56
ከባድ ቅጣት….የቀጠለ

 በስሙ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወጪ በማድረግ ከወሰደ በኋላ


ከውስጡ ከአምስት ቅጠል በላይ የበጨቀ ወይም ሙሉ በሙሉ
ጥራዙን ያጠፋ ባለሙያ አግባብነት ባለው ህግ የሚጠየቀው
እንደተጠበቀ ሆኖ አስቀድሞ ባለው ጥራዝ የተሰበሰበው የገንዘብ
መጠን ተደምሮ በጠፋው ጥራዝ መጠን እየተባዛ ለአንድ ጥራዝ አራት

እጥፍ እንዲከፍል ይደረጋል።

57
58

You might also like