You are on page 1of 14

ማውጫ ገጽ

ክፍል - 1........................................................................................................................................... 3
1. ጭንቅላት ................................................................................................................................. 3
1.1. ጭንቅላት ላይ የሚቀመጡ መናፍስት .................................................................................... 3
1.2. መናፍስት ጭንቅላት ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች ............................................................ 4
1.3. መፍትሔው ...................................................................................................................... 5
ክፍል - 2........................................................................................................................................... 6
2. ዓይን ....................................................................................................................................... 6
2.1. ዓይን ላይ የሚቀመጡ መናፍስት .......................................................................................... 6
2.2. መናፍስት ዓይን ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች .................................................................. 7
2.3. መፍትሔው ...................................................................................................................... 8
ክፍል - 3........................................................................................................................................... 9
3. ጆሮና አንደበት ......................................................................................................................... 9
3.1. ጆሮና አንደበት ላይ የሚቀመጡ መናፍስት .......................................................................... 10
3.2. መናፍስት ጆሮና አንደበት ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች .................................................. 10
3.3. መፍትሔው .................................................................................................................... 11
ክፍል - 4......................................................................................................................................... 12
4. እጅና እግር ............................................................................................................................ 12
4.1. እጅና እግር ላይ የሚቀመጡ መናፍስት ............................................................................... 12
4.2. መናፍስት እጅና እግር ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች ....................................................... 13
4.3. መፍትሔው .................................................................................................................... 13

2
መናፍስትና የአካል ክፍሎቻችን
ክፍል - 1
ርኩሳን መናፍስት በሰውነታችን ውስጥ እንደሚቀመጡበት የሰውነት አካልና ስፍራ ላይ ልዩ ልዩ ሥራዎችን፣
ተልዕኮችንና ምሪቶችን ባረፉበት ቦታ መሠረት እያደረጉ ይፈጽማሉ፡፡

በሰውነት ሥጋችን አንድ የሆነ አካል ላይ መናፍስት አረፉ ሲባል፤ በሁለት አይነት የሚገለጽ ነው የሚሆነው።
እነርሱም፦

➢ አንደኛው በዛ በተለየ የሰውነት አካላችን ላይ የመንፈሱ ሠራዊቶች ተሰብስበው በመቀመጥ የሚያከናውኑት


ጥፋት አሊያም የሚያደርሱት ጫና ሲሆን፤
➢ ሁለተኛው መንፈሶቹ በአንድ አካል ተለይተው መቀመጣቸውን ሳይሆን የስምሪት አቅጣጫን የሚጠቁም ገለጻ
ሊሆንም ይችላል፡፡

እስኪ ከላይኛው የሰውነት ክፍላችን ከጭንቅላታችን ጀምረን፤ መሠረታዊ የሚባሉ መናፍስቱ


የሚቀመጡባቸውን ቦታዎችና የሚኖረውን ምልክት ከውጊያ ስልቶቻቸው ጋራ አጠር አድርገን እንመልከት፡፡

1. ጭንቅላት
ክፉ መናፍስት ጭንቅላት ላይ ተቀመጡ ሲባል፤ አንደኛው ከላይ እንደተጠቀሰው፤ መንፈሶቹ ተሰብስበው
የራስ ቅል ላይ ሠራዊታቸውን ይዘው ተቀመጡ ማለት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ መሪ(የጭፍራ አለቃ) የሚሆኑ
መንፈሶች ሥራቸውን የሚመሩበትና ለወጠኑት ግብ እንደ መሣሪያ የሚጠቀሙት የስምሪት መንገዳቸው ጭንቅላት
ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ መንፈሶቹ ግዴታ ጭንቅላት ላይ ላይቀመጡ ይችላሉ፡፡

1.1. ጭንቅላት ላይ የሚቀመጡ መናፍስት


መናፍስት በመሠረቱ በሰውነታችን ውስጥ ሲቀመጡ ልክና ሥርዓት ሠርተውበት የሚያርፉበት የአካል ክፍል
የለም፡፡ ረቂቃን ፍጡር እስከመሆናቸው ድረስ፤ እንደ ግዙፍ አካል በአንድ ክፍተት(space) ተወስነው ልዩ ቦታ
አይይዙም፡፡ ነገር ግን ማድረስ እንደሚፈልጉት የጉዳት አይነትና ሊገልጡት እንደሚፈልጉት የክፋት ድርጊት፤
ራሳቸውን ቅርጽና መጠን እያስያዙ ሰውነት ላይ ያደፍጣሉ፡፡ በሌላውም ደግሞ አንዳንድ ጊዜ መናፍስቱ ከስምሪታቸው
ውጪ አፈንግጠው ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የዛር መንፈስ እንደ ዓይነጥላ ዕድል ላይ አይሠራም፡፡ የመተት
መንፈስ ከተላከበት ዓላማ ውጪ የፍልስፍና መንፈሶችን ሥራ አይሠራም፡፡ ይሄ የስምሪት አቅጣጫቸው ግን እንደ
ግለሰቡ የውጊያ ሂደትና ጥንካሬ እየተዘመነ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡ ማለትም ዕድል ላይ ያለውን ዓይነጥላ ለይተን
ስንዋጋው፤ ሌሎቹ መንፈሶች ባልደረባቸውን ለማገዝ ያለ አሠራራቸው ዕድልን የማምከን አቅጣጫ ላይ ሊሰለፉ
ይችላሉ፡፡ የአየር አጋንንቶችም ውስጥ ሳይገቡ ባሉበት ቦታ እገዛ እንዲያደርጉ በመናበብ ይጠየቃሉ፡፡ በመሆኑም
ከታች ከተዘረዘሩት ውጪ ማንኛውም አይነት መንፈስ ጭንቅላት ላይ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ መቁጠሪያ ስትጠቀሙ፤
ለየብቻ እንደ ጥፋታቸው "ይሄን ይሄን ያደረክ" እያላችሁና ደግሞ "አጠቃላይ ሁላችሁም ሕይወቴ ውስጥ
ያደፈጣችሁ" እያላችሁ ቀጥቅጡ የሚለው መረጃ የተላለፈው ለዚህ ነው፡፡

❖ ጠቋር
❖ ዓይነጥላ (ከጭንቅላት አይጠፋም ብዙውን ጊዜ)
❖ ከልከልዮስ (የመቃብሩ መንፈስ)
❖ ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ያላቸው አብሮሆት ላይ የሚሠሩ መናፍስት እንደ ሉሲፈር፣ ባፎሜት፣ አባዶን

3
❖ የፍልስፍና፣ የክሕደት እና የሥነ አመክንድ መናፍስት እንደ ራምፓ፣ ኦሾ፣ ኤቲስትስ(ኢ-አማያን) የሚያደርጉ
በንባብ፣ በመስማትና በማየት የገቡ መናፍስት
❖ ትምህርት፣ እውቀትና ዕድል አበላሹ አሊያ ንጠቁ የተባሉ የመተት ወይንም የድግምት መናፍስት
❖ ሌላ ሰው ላይ እያለ ጭንቅላት ላይ ይሠራ የነበረ ቡዳ (አንዳንዴም ልክፍት)

1.2. መናፍስት ጭንቅላት ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች


➢ አንገት ሁለተኛ የራስ ቅል የተሸከመ እስኪመስል ድረስ የጭንቅላት መክበድ (በአቀማመጥ)
➢ ጭንቅላታችንን ስንነካው ከውስጡ ምንም የሌለው አይነት እንደ ቅርፊት ግዑዝ እቃ ድርቅ ማለት፣ ወይንም
በአንጻሩ ከውስጡ የቆሰለ ቦታ እንዳለ ሁሉ ሕመም መሰማት (በአቀማመጥ)
➢ የተለያየ መጠን ያለው ራስ ምታት ወይንም የውጋት ስሜት (በአቀማመጥና በስምሪት)
➢ ከፊታችን ክፍል በተለይ ግንባርና ጸጉር ላይ የሚርመሰመሱ ነፍሳት እንዳሉ አይነት የአንዳች ነገር መሯሯጥ
(በአቀማመጥ)
➢ ማስተዋል ማጣት፤ በተለይም ቃለ እግዚአብሔርን በመከታተል ጊዜ (በአቀማመጥና በስምሪት)
➢ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ማለትም ገሐድ ምንጭ የሌለው ጭንቅትና ውጥረት በተደጋጋሚ ማስተናገድ
(በስምሪት)
➢ የስሜት ቶሎ ቶሎ መለዋወጥ፤ በአንድ የቀን ሰዓት ውስጥ አንዴ ድብርተኛ አንዴ ደስተኛ እየሆኑ መቀያየር
(በስምሪት)
➢ በአንዳንድ ቀናት ላይ ደግሞ ፍዝዝ ብሎ ለረጅም ሰዓት መቆየት፤ በቤት ውስጥ ከክፍል ወደ ክፍል መንቀሳቀስ
እስኪያቅት ድረሰ በአእምሮ መዛልና መድከም (በአቀማመጥና በስምሪት)
➢ አሳብን መቆጣጠር አለመቻል፤ በአንድ ቅጽበት ውስጥ ዝብርቅርቅ ያሉ አሳቦችን ማስተናገድ፤ ከራስ ጋር የውስጥ
ንግግር በማድረግ ያሉበትን እስኪረሱ ድረስ በምናብ እልም ብሎ መጥፋት (በአብዛኛው በስምሪት)
➢ እንቅልፍ ሳይተኙ በቁም እያሉ መቃዠትና መበርገግ (በስምሪት)
➢ በእንቅልፍ ውስጥም እያሉ በአስፈሪ፣ አስጨናቂ፣ ፍጹም ግራ አጋቢ ሕልሞች እየተቸገሩ ማደር፤ (በስምሪት)
➢ የትምህርትና የሥራ ዕድል በተደጋጋሚ መበላሸት፤ እውቀትን መዝግቦ ማቆየት የሚችል ኃይል በማጣት ቶሎ
ቶሎ መርሳት (በአቀማመጥና በስምሪት)
➢ ክፉ ክፉው ነገር ላይ ንቃተ ሕሊና ማግኘት፤ ውስብስብ የኃጢአትን መንገድ በቀላሉ መረዳት፤ የጥፋት አሳቦችን
በረቀቀ እቅድና ስልት የመንደፍ ችሎታ (በስምሪት)
➢ አሰቃቂ መዝናኛዎችን፣ የወንጀል ገድሎችን፣ የወሲብ ትዕይንቶችንና ተመሳሳይ መረጃዎችን በመውደድ
መከታተል (በአቀማመጥና በስምሪት)

እነዚህና የመሳሰሉት ምልክቶች በአንድ ግለሰብ ላይ ብቻ እንደ ባሕሪዩና የአኗኗር ልማዱ ሊከሰቱ ይችላሉ።
በነገራችን፥ እዚህ የተዘረዘሩትን አይነት ሌሎች ምልክቶችን በሕይወታችንና በሰዎች ላይ ማስተዋል የኛ ፋንታ ነው።
እንደ ቅንነታችንና ለማወቅ ያለን ፍላጎት ልክ ተጨማሪ ምልክቶችን መንፈስ ቅዱስ በብዙ መንገድ ያስታውቀናል።

4
1.3. መፍትሔው
✓ በጸለይንበትና በባረክነው መቁጠሪያ ጭንቅላታችንን መናፍስቱን እየገሰጽን በደንብ መቀጥቀጥ
✓ የአምልኮት ስግደት በሚሰገድበት ጊዜ መናፍስቱ ከጭንቅላት ወጥተው ወደ ግንባር መጥተው እንዲታሰሩና
አብረው እንዲሰግዱ አዝዞ፤ ግንባርን ስዕለ ቅዱሳን አሊያም መስቀል እያስነኩ መስገድ
✓ እንዲሁ ግንባር ላይ አስሮ ቅባዕ ዘይት፣ እምነትና ጸበል መቀባት
✓ በጸሎት ወቅት ላይ በተለየ ኃይል የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲዋጋልንና የመናፍስቱን ጫና ከጭንቅላት
እንዲያነሳልን ለብቻ ጉዳይ ሰጥቶ በእምነት ማሳሰብ
✓ በእምነት በጠየቅንበት ሰሞን ውጊያው ከጭንቅላት ላይ ካልበረደ፤ እግዚአብሔር እንድናስተካክለው እየጠቆመን
ያለ አስተሳሰብ፣ እንድናቆም የፈለገው መረጃ(በማንበብ፣ በማየትና በመስማት ያለውን መረጃ)፣ እንድንለውጥ
የፈለገው የዝንባሌ ሁኔታ(ውሎና ዙሪያችን ያለው የሰው ተጋቦት) እና ሦስተኛው ጭንቅላታችን የጸጋ ባለቤት
ሲሆን ትግሉ ያንን ስጦታ እንድንቆፍር ይረዳልና ከፍልሚያው እንድንማር አምላክ ዝም ይላል(ለኛ የማይገባንን
ቀጥተኛ ያልሆነ መፍትሔ ይሰጣል)
✓ የእግዚአብሔር ኃይል ጭንቅላታችንን እንዲባርክ፣ እንዲቆጣጠርና እንዲመራ ቅዱስ ቁርባንን በርዕስ መውሰድ
ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚታይ ለውጥና ዘላቂ መፍትሔ ይሰጠናል ("ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤"
የሚለው የወንጌል ተስፋ የኛም ነው፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 24፥45))

5
ክፍል - 2
2. ዓይን
"የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤" (የማቴዎስ
ወንጌል 6፥22)

እንደሚታወቀው ዓይን ከውጪው ገሐድ ዓለም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የምንፈጥርበት እጅግ ውዱ የአካል
ክፍላችን ነው፡፡ የሚታዩ መረጃዎችንና ሁነቶችንም ወደ አእምሮአችን በማቀበል ሰውነታችን ብርሃንን እንዲለይና
እንዲያውቅ ትልቁን አገልግሎት ዓይን ትሰጣለች፡፡

ከሥጋዊው ዓይን በተጨማሪ ደግሞ የሰው ልጆች ሁለተኛ መንፈሳዊ ዓይን አላቸው፡፡ ለምሳሌ "እይታው
ጥሩ ነው" በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያለው አውዳዊ ፍቺ፤ አስተሳሰቡ ጥሩ ነው፣ አመለካከቱ ጥሩ ነው፣ ነገሮችን
የሚለካበት ሚዛን ጥሩ ነው፣ የመረዳት አቅሙ ጥሩ ነው እንደማለት ነው፡፡ ይሄንን ወደ ሃይማኖታዊ ቋንቋ ስናመጣው፤
በግዙፍ ሥጋ የማይዳሰሰውን ዳስሶ የሚያይ የነፍስ ዓይን አለ ማለት ነው፡፡

"መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።" የሚለው የማቴዎስ ወንጌል


13፥14 ቃልም የሚያረጋግጥልን ከሥጋዊ ዓይን በተጨማሪ ያለውን ውሳጣዊ ዓይንንና ጆሮን ነው፡፡ "ማየትም
ታያላችሁና አትመለኩትም" ሲል በሥጋ የዓይን ብርጭቆ ማየቱንስ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ያያችሁትን ብርሃን ከነፍስ
ዓይን ጋር(ከመንፈሳዊ ቃልና ከመንፈሳዊ እውነት ጋር) አስተባብራችሁ ስለማታዩ አትመለከቱም ነው የንግግሩ
አንድምታ፡፡

ስለዚህ መናፍስት በዓይን ላይ ተቀመጡ ሲባል፤ ሁለቱንም የዓይን ክፍሎች(ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን)


ያስቧል፡፡ መናፍስቱ የተቀመጡት ሥጋዊው ዓይን ላይ ሲሆን የሚታዩት ምልክቶችም ሥጋዊ ናቸው፡፡ የነፍስ ዓይንን
ሲጋርዱ ደግሞ የመናፍስቱ አሠራር ስምሪትን የጠበቀ ሆኖ ምልክቱም በሥጋ የማይሰተዋል ረቂቅ ነው፡፡

2.1. ዓይን ላይ የሚቀመጡ መናፍስት


❖ ዓይን ላይ ጉዳት እንዲያስከትል የተላከ የመተት፣ የአረማዊ ደብተራና የድግምት መንፈስ (ሥጋዊ ዓይን ላይ
ከውስጥም ከውጪውም ይቀመጣሉ)
❖ የዓይን በሽታን ውርስ እያደረገ በቤተሰብ ትውልድ የሚያስተላልፍ የዘር መንፈስ (ሥጋዊ ዓይን ላይ ከውስጥም
ከውጪውም ይቀመጣሉ)
❖ የዓይንን ውበት አይቶ የመጣ የቡዳ መንፈስ (ሥጋዊ ዓይን ላይ በብዛት ከውስጥ ይቀመጣሉ)
❖ ምስሎችን፣ ጽሑፎችን፣ ቁሳዊ ነገሮችንና ሰውን(አለባበሱን፣ አኳኋኑን፣ እንቅስቃሴውን፣ አነጋገሩን) በማየት ጊዜ
በዓይን የሚገቡ መንፈሶች ፦ የዝሙት መንፈስ፣ የጂኒ መንፈስ፣ የቡዳ መንፈስ፣ የልክፍት መንፈስ፣ የሱስ መንፈስ፣
የዓይነጥላ መንፈስ፣ የቁራኛ መንፈስ፣ የሩሐንያ አባድ መንፈስ(የግብረ ሰዶማውያን መንፈስ)፣ የሔርሜት መንፈስ፣
የሜሜት መንፈስ፣ የአፈዝ አደንግዝ ሰላቢ መንፈስ፣ የመስተፋቅር መንፈስና ወዘተ... (ሲቀመጡ ሥጋዊ ዓይን
ላይ ሆኖ ምልክቶቹ ግን መንፈሳዊም ሊሆኑ ይችላሉ)
❖ ማስተዋልን የሚሸፍኑ ጭንቅላት ላይ የሚቀመጡ መናፍስት በዓይን በኩል የሚገቡ መለኮታዊ ትምህርቶችንና
የውጊያ መረጃዎችን ለመከላከል ዓይን ላይ ተቀምጠው ከውስጠኛው አካል ወደ ውጪኛው ዓለም አብረው
ያያሉ (ሥጋዊውም መንፈሳዊውም ዓይን ላይ ይቀመጣሉ)
❖ የአስተሳሰብ አድማስን ለማጥበብና ለማስፋት በሩን በመቆጣጠር በሚፈልጉት አቅጣጫ ላይ ለመምራት የነፍስ
ዓይን ላይ ይቀመጣሉ፦ የመናፍቁ መንፈስ፣ የርዕዮተ ዓለም መንፈስ(የማርኪስትና የሌኒስት አምላክ የለሽ ፍልስፍና

6
ጀርባ ያሉ መናፍስት)፣ ከክሕደት የሳይንስና የምርምር መድረክ በስተኋላ የሚገኙ መናፍስት(ሰው ከዝንጀሮ መጣ
የሚሉት አይነት ንድፈ አሳብ አቀንቃኞች)፣ የሚስጥር ማሕበራት የሲዖል መናፍስት(የኢሉምናቲ አይነት
ድርጅቶች ጋር ባለ ግንኙነት የሚመጡ) (መንፈሳዊ ዓይን ላይ ይቀመጣሉ)

2.2. መናፍስት ዓይን ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች


➢ ሥጋዊ የሆነ የዓይን ሕመም (የዛርና የመተት መናፍስት)
➢ የዓይን እይታ ችግሮች (አተኩሮ አለማየት፣ ከሩቅና ከቅርብ የማየት እከል፣ እንደ ሞራ ያለ የእይታ ግርዶሽ፣
የእንባ አዘወትሮ መፍሰስ)
➢ የዓይንና የአከባቢው ድንገተኛ የውበት መበላሸት እንደ የዓይን ጸጉር መርገፍ፣ ባዕድ እብጠትና የቆዳ መቆጣት፣
የዓይን መደፍረስ፣ መቆጥቆጥ፣ ማሳከክና አለ ምክንያት ማቃጠል፣ የቅንድብ ጸጉር መበላሸት፣ ወዘተ... (የቡዳና
የልክፍት መናፍስት)
➢ በዓይን ሱስ የመውደቅ ዝንባሌዎች (የዝሙት፣ የወሲብ ፊልም፣ የሱስና የቁራኛ መናፍስት)
➢ ዓይንን ሕሊናን ከሚያስወቅስ የኃጢአት እይታዎች ለመከልከል መቸገር (የዓይነጥላ፣ የወሲብ ትዕይንት ልክፍት
መንፈሶች፣ የሔርሜትና ሜሜት መናፍስት)
➢ በዓይን በጎውን፣ የተቀደሰውን፣ የተባረከውን መለኮታዊ መንፈስ ያለበትን ሁሉ ለማየት መጥላትና መሸሽ (ለምሳሌ
ቤተክርስቲያን፣ ስዕለ አድኖ፣ መንፈሳዊ መጽሐፍ)
➢ ደም ሲፈስ(የእንስሳትም)፣ ጸብ ሲጋጋል፣ መከራ ሲገጥም፣ ውድቀት ሲከሰት ማየት መውደድ (የዛር መናፍስት)
➢ የእግዚአብሔርን ሕልውናና እውነት የሚጥሉ ተጨባጭ መረጃዎችን በፊልምና በመጽሐፍ አብዝቶ መከታተል
(የርዕዮት፣ የፍልስፍና፣ የክሕደትና የርኩሰት አብርሆት መናፍስት)
➢ መንፈሳዊ መረጃዎችንና ቃለ እግዚአብሔርን አይቶ ለመረዳት አለመቻል ሲሆንም ማወሳሰብና ለማጣጣል
ምክንያት መፈለግ (የነፍስ ዓይን ላይ የሚቀመጡት መናፍስት)
➢ የአስተሳሰብ ጨለምተኝነት "ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል።" (የማቴዎስ ወንጌል
6፥23) (የነፍስ ዓይን ላይ የሚቀመጡት መናፍስት)
➢ በዓይን አይቶ ክፉኛ ሰው ላይ መቅናት፣ በሰው ዕድል መበሳጨት፣ ጉዳት ለማድረስ መነሳሳት፣ የሰውን ችግር
ማባባስ፣ የሌላውን መከራ በቸልተኝነት ማለፍ፣ ድሆችን መገላመጥ፣ መናቅና መግፋት (የሥጋም የነፍስ ዓይን
ላይ ሲቀመጡ)
➢ የሕይወት ዘይቤን በሚገርም ፍጥነት መለዋወጥና ጭራሽ የማይስማሙ የአመለካከት ልዩነቶችን በተለያየ ጊዜ
ማንጸባረቅ፤ የራስን አመለካከት በሌሎች ለመጫን እልህና ትዕቢትን መጠቀም፤ ግልፍተኛ፣ ችኩልና በስሜታዊነት
መመራት (የነፍስ ዓይን ላይ ሲቀመጡ)
➢ እንደዚህ አይነት የመናፍስቱን ሚስጢር የሚያወጡ መረጃዎችን ከማየት በኋላ የስሜት መለዋወጥ፣ መናደድ፣
መቆጣት፣ ማልቀስ፣ መቆጨት፣ መጮኽ፣ መቆዘም፣ በአሳብ ዥው ብሎ መጥፋት፣ የእንባ በተደጋጋሚ መውረድ፣
ማዛጋት፣ የዓይን መቃጠል፣ ጥርስ መንከስ፣ የተቃርኖ ድምፇችን ማሰማት

በነገራችን፥ መንፈስ ከሰባት ዓመት ቆይታ በኋላ ያለበት ግለሰብ ላይ ቡዳ በመሆን ወደ ሌሎች ሰዎች
ሠራዊት መላክ እንደሚጀምር (እንደሚበላ) እንዳንረሳ፡፡ ለምሳሌ የዛሩ መንፈስ ሳይነቃበት ከሰባት ዓመት በላይ ከቆየ፤
ዛር ቡዳ ሆኖ ሌሎችን ይበላል፡፡

7
2.3. መፍትሔው
✓ "ከሥጋዬም ከነፍሴም ዓይን የተቀመጣችሁ" ብሎ በመጥራት በመቁጠሪያ መቀጥቀጥና በአስማተ ቅዱሳን አስሮ
ማሰገድ
✓ እምነት፣ የጸሎት ውኃና ቅባዕ ዘይትን ዓይን ላይ መጨመርና መቀባት
✓ የእንባ ጸሎትና ምስጋና ዓይን ላይ ያሉ ስውር ጠላቶችን ያቃጥላል (በእርግጠኝነት መናፍስቱ እንዲቃጠሉልኝ
ብላችሁ ማልቀስ አትችሉም፡፡ ብትችሉም አትደጋግሙትም፡፡ እንባ ከእግዚአብሔር ፍቅርና ከልብ ንጽሕና ጋር
ሲያያዝ ግን፤ አይደለም የራስ የሌሎች ሰዎችን መንፈስ ያነድዳል፥ ያሸሽማል)
✓ በዓይን በኩል ለሰኮንዶችም ቢሆን የሚገቡ ነገሮችን ልዩ ኃላፊነት ወስዶ መቆጣጠር
✓ ከቤት ከመውጣት በፊት መናፍስቱ በመናበብና ሠራዊት በመሳብ ጭፍራ በዓይን በኩል ስበው እንዳያመጡ
ግንባር ላይ ማሰርና በመንገድም፣ በሥራም ቦታና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ጸሎቶችን በለሆሳስ ማድረስ
መለማመድ (የዳዊት መዝሙራትን፣ ድርሳናትን፣ አቡነ ዘበሰማያትን፣ ሰላም ለኪንና ወዘተ...)
✓ አብዛኛውን የዓይን እይታ ለመንፈሳዊ ጊዜ መስጠት (ዓለማዊ እይታዎችን ባራቅን ቁጥር ዓይን ላይ የሚቀመጡ
መናፍስት አቅጣጫ የሚያስለውጡበት፣ የእምነት ሞራል የሚያቀዘቅዙበት፣ የጽድቅ መሻትን የሚያበርዱበት ዕድል
ያንስባቸዋል፡፡ በተቃራኒው ዓለማዊው ሰዓት የበዛ ከሆነ ግን መናፍስቱ ይበረታሉ፡፡ ለምሳሌ ዘፈንና ፊልም የሚያይ
ዓይን፤ ከደቂቃዎች በኋላ ለጸሎት መዘጋጀት ጣር ይሆንበታል፡፡
✓ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ያልከውን ቃል አሳየኝ መድኃኒት ክርስቶስ ሆይ ብሎ ስለ ነፍስ ዓይን መጨለም ጸልዮ
መቁረብ (ርዕስ አንድ)
✓ "ኤፍታህ" ያልከውን ቃል በኔም አመለካከት ላይ አሰማኝ፤ ውስጣዊ እይታዎቼን ባርክልኝ፤ ጠላቴ የዘጋውን
ማስተዋል ክፈትልኝ ብሎ መቁረብ (ርዕስ ሁለት)
✓ ቅዱስ መንፈስ የሥጋም ሆነ የነፍስ ዓይን ላይ ይቀመጥ ዘንድ ይሁንልኝ ብሎ "ለምኑ ይሰጣችሁማል" ያለውን
ቃል ከክርስቶስ ጋር የፍቅር ሙግት መግጠሚያ ጸሎት አድርጎ መቁረብ (ርዕስ ሦስት)

8
ክፍል - 3
3. ጆሮና አንደበት
"ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ።" (የማርቆስ ወንጌል 7፥35)

ክርስቶስ በመጣበት በሐዲስ ኪዳንም ዘመን መከፈት ሲገባቸው የተዘጉ በሮች አሉ፡፡ እነዚህ በሮች በአካላችን
ላይ የሰውነት ክፍል ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ በምሳሌም ስንጠቅስ የጆሮንና የአንደበትን በር ለዚህ አንቀጻችን መደገፊያ
ምስክር እናደርጋቸዋለን፡፡

እነዚህን ሁለት በሮች በሥጋዊው አእምሮ በኩል እንዲሁ ቀጥታ ስናጤናቸው፤ "ምናቸው ነው ተዘጋ
የሚያሰኘው?" የሚል ግርታ ይፈጠራል፡፡ ሆኖም ነገራችንን በእምነት መነጽር ለማየት ፈቃደኛ ሆነን አሳባችንን
ደግመን በደንብ ስናጤነው፤ "ተዘጉ" የሚለው ገለጻ ለጆሮና ለአንደበት የተሰጠው በምን ብያኔ ላይ ቆመን እንደሆነ
ማስቀመጥ ይቻለናል፡፡

ሁላችን ተገንዝተን የምንመራባቸው እንጀራ ተኮር ንድፈ አሳቦች እና በተለይም በአሁኑ በኛ ዘመን ከሰማይ
በታች በአራቱም ማዕዘነ ዓለም ተቆጣጥሮ ያለው የአስተሳሰብ ርዕዮት፤ ሰዎች መንፈሳዊ እውነትን እንዳይሰሙም ሆነ
እንዳይናገሩ ሲሉ በራሳቸው ሚስጢራዊ መንገድ የሚዋጉ መሆናቸውን ከጥቂቶች በስተቀር ብዙዎቻችን ገና
አልነቃንባቸውም፡፡

ጉዳዩን በየግል ሕይወታችን ሚዛን ላይ በማስቀመጥ ግንዛቤያችን ክብደት እንዲያገኝ እስቲ እንርዳው፡፡
የዕድሜ ልኬታችን ሆነው እያለፉ በሚገኙት ሰዓቶቻችን ውስጥ፤ ምን ያህል የእግዚአብሔር የሆነውን ሰማን? ምን
ያህልስ የእግዚአብሔር የሆነውን አወራን? እያልን ራሳችንን ከዕለት የኑሮ ውዥንብር ገለል አድርገን ስንጠይቅ፤
የምናገኘው ነባራዊ ምላሽ፤ የተዘጉ የመስሚያና የተዘጉ የመናገሪያ በሮች በእርግጥም ስለመኖራቸው የተጨበጠ
ማስረጃ ያለው ድምዳሜ ላይ ያደርሰናል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ፦ "ከሕዝቡ አንዱ መልሶ። መምህር ሆይ፥ ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ
አምጥቼአለሁ፤ በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፥ ጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልም፤
እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፥ አልቻሉምም አለው። ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ
ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ። አባቱንም። ይህ ከያዘው
ስንት ዘመን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤ ...ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ
ርኵሱን መንፈስ ገሠጸና። አንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ፥ እኔ አዝሃለሁ፥ ከእርሱ ውጣ እንግዲህም አትግባበት አለው።
" (የማርቆስ ወንጌል 9፥ 17-25)

"እግዚአብሔር የለም!" የሚል አዲስ የፍልስፍና ጽንፍን ለአገር ፖሊሲና ለእድገት ፍኖት መተዳደሪያ ቅርጽ
አድርጎ የተቀበለው የ1960'ዎቹ ትውልዳችን፤ በዚህ አኳኋን ላይ አኗኗሩን በባዕድ አመለካከት መሥርቶ ልጆችን
ሲወልድ፤ ከልጅነታቸው ጀምረው "የእግዚአብሔርን የማይሰሙና የእግዚአብሔርን የማይናገሩ" ትውልዶችን ተተኪ
አድርጎ አፈራ፡፡ (የለም ተብሎ ስለተፈረደበት መለኮታዊ እውነት ምን ሊሰሙ፥ ምንስ ሊናገሩ ይችላሉ?)

ስለዚህ "ከሕፃንነት ጀምሮ" ሃይማኖታዊ አንድምታዎች፣ መንፈሳዊ ዕሴቶች፣ ክርስቲያናዊ ቋንቋዎችና


ማሕበረሰባዊ የእምነት ግንባታዎች ላይ ዝም ያለው አስተዳደጋችን፤ "ዲዳና ደንቆሮ መንፈስ" የባሕሪይው አንድ
ክፍል ሆኖ ተቆራኝቶ ስለያዘው፤ ስለ ፍቅር፣ ስለ ጽድቅ፣ ስለ እውነት፣ ስለ በጎነት፣ ስለ ምሕረት፣ ስለ ክብር፣ ስለ
ጸጋ፣ ስለ ሞገስ፣ ስለ ቃልኪዳን፣ ስለ አንድነትና ወዘተ... ማድመጥም ሆነ መናገር አይቻለውም፡፡

9
3.1. ጆሮና አንደበት ላይ የሚቀመጡ መናፍስት
❖ ሁሉም አብረው ተወልደው ያደጉ መናፍስት(ዛር) እና ሌሎችም ረጅሙን ጊዜ ባሕሪይን ተለማምደው የቆዩ
መናፍስት ጆሮና አንደበት ላይ [በየቀኑ] ይቀመጣሉ፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ ሰማያዊ ድምፆችን የሚሰማበትና
የሚናገርበት ዕድል ከሌለው ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት አጋጣሚም የለውም ማለት ነው፡፡ (መንፈሳዊ
ነገርን መናገር ጸሎትን እንደሚጨምር ልብ ይሏል!)
❖ በሌላውም ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃላት ከማስደመጥና ከማስነገር ለመከልከል ብቻ ሳይሆን፤ መናፍስቱ
የራሳቸውን ፍቃድ ለመናገርና በዓለም ውስጥ የሚሰራጨውን የኃጢአት ቃል ለማስደመጥ እንዲችሉ በአብዛኛው
ከጆሮና ከአንደበት ላይ አይነሡም፡፡ በየቤታችን፣ በየመሥሪያ ቤቱና በየኑሮ ዘርፉ ከሰዎች ጋር አንድ ቋንቋ
እየተነጋገርን ማንግባባው ለዚህ ነው፡፡ (ነገሩን በጥሬ ገለጻ ስናስቀምጠው የአምልኮት ልምምድ በሌለው ሰው ላይ፤
መንፈሶቹ ከጆሮና ከአንደበት አይለዩም፡፡ ለዚህ ነው ከጽንሰት አንስቶ ያለውን የዲዳና የደንቆሮ መንፈስ
የጠቀስነው፦ የሚወጣው በጾም በጸሎት ነው ተብሎአል ፦በዕለት አምልኮት ማለት ነው!)
❖ አፍዝ አደንግዝ ተብለው የተላኩ የመተት፣ የድግምትና የምዋርት መናፍስት
❖ ተሳዳቢ የእርግማን መንፈሶች (አንደበት ላይ)
❖ በቆንጆ ቃላት የተቀመሙ ንግግሮችን በማድረስ መናፍስታዊ ስበትን የሚፈጥሩ ከሳይኮሎጂ፣ ፍልስፍናና ርዕዮት
ጀርባ የሚደበቁ መናፍስት (አንደበት ላይ)
❖ እንደ እሳት የሚንቀለቀል አንደበትን የሚሰጠው የመናፍቁ መንፈስ (ቅድሚያ ጆሮ ይዘጋል ቀጥሎ አንደበት
ይከፍታል) "እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።
" (የዮሐንስ ራእይ 13፥6)
❖ የእግዚአብሔር ቃል በሚሰበክበት ጊዜ የልቦና ክፍተትን የሚዘጋው የዓይጥላ መንፈስ (ጆሮ ላይ)
❖ ዝምተኛ ወይንም ተናጋሪ ሰው ቡዳ ሲበላን የመንፈሱ ሠራዊት የአዋራሹን ጸባይ ያዋርሳሉ፤ ማለትም መጀመሪያ
ቡዳው የነበረበት ግለሰብ አንደበት ላይ ተቀምጠው ለፍላፊ አድርገው ከነበረ፤ በተዋራሹም አንደበት ላይ
ተቀምጠው እንዲሁ ያደርጋሉ

3.2. መናፍስት ጆሮና አንደበት ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች


➢ ለቅድስና ቃልና ለመንፈሳዊ ሕይወት ዲዳና ደንቆሮ የሚያደርገው መንፈስ፤ ያለ ጾም ጸሎት ከቆየ፤ የያዘውን
ግለሰብ የማይሰማ፥ የማይለማ አድርጎ ያስቀምጠዋል፡፡

[ብዙዎቻችን ሥጋዊ ቃላትንና የቁስ አካላትን ድምፅ ስለምንሰማ ብቻ ጆሮአችን እንደሚሰማ ደምድመናል።
ደንቆሮ ነው ብለን በተለምዶ የምናስበውም ሥጋዊ የመስማት እከል የገጠመውን ነው፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ግን እጅግ
በጣም በቁጥር የበዛን ሰዎች ለመንፈሳዊው ቃል ደንቆሮ መሆናችንን እንኳን አናውቀውም፡፡ ቀላል ምሳሌ እናስቀምጥ።
በአገራችን እንደሚታወቀው በተለያየ መንገድ የእግዚአብሔር ቃል ይሰበካል፡፡ በየቀኑ ንስሐ ግቡ ይባላል፡፡ በተደጋጋሚ
መንፈሳዊ ትምህርቶችንም የመስማት አጋጣሚው አለን፡፡ ግን አልተለወጥንም፡፡ ይሄ ማለት፤ አብረው የሚሰሙ
መናፍስት የመለወጫውን ልቦና ሸብበውታል ማለት ነው፡፡

ቃለ እግዚአብሔር ሕይወት ነው፡፡ ቃለ- ሕይወት ያሰማልኝ የምንለው ስለዚህም ነው፡፡ በትክክል ካደመጥነው
ሕይወታችንን ይለውጣል፡፡ ቃሉን በሰማውና ባልሰማው መካከል ያለው ትልቁና ዋነኛው ልዩነት ለውጥ ነው፡፡ በዚህ
መሠረት ለውጡ አልመጣም ካለ፤ ያልተለወጠው ሰው እየሰማ አይደለም ማለት ነው፡፡ ጌታ በተደጋጋሚ "ጆሮ ያለው
ይስማ" እያለ የሚናገር የነበረው ይህንን ነው፡፡ በጣም የሚደንቀው ደግሞ መናፍስቱ እንዲህ እንደሚያደርጉ
እየተነገረንም አሁንም አንሰማም፡፡ አለመስማታችንም አያስጨንቀንም፡፡ አምርረን አናለቅስለትም፡፡ ምን ይሻላል?]

10
➢ ጆሮና አንደበቱ በመናፍስት ቁጥጥር የወደቁበት ሰው ከራሱ አሳብ ውጪ ማስተናገድ አይወድም፡፡ ንግግሩንም
በጫናና በግድ ለማሳመን ግፊት ይጠቀማል፡፡
➢ አንደበት ላይ የሚሆኑ የዛር መናፍስት፤ የስድብ ቃላትን፣ ክፉ ቃላትን፣ የምዋርት ቃላትንና የእርግማን ቃላትን
ያሰማሉ
➢ በስሜታዊነት በምንናጥበት የብስጭት፣ የንዴት፣ የተስፋ መቁረጥ፣ የቁጣና ወዘተ... ደቂቃዎች ላይ በአብዛኛው
መናፍስቱ ጆሮና አንደበት ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ቅጽበታዊ ክስተቶች ወደ ወንጀል፣ አደጋና ጸብ የሚቀየሩበት
ሚስጢራዊ ገጽታ ይሄ ነው
➢ በቤተሰብና በቅርብ ወዳጆች መካከል የሚፈጠረው መንፈሳዊ መቋሰልም ይኸው የመናፍስቱ አቀማመጥ ነው
(መቋሰል በሚል ርዕስ የተጻፈውን ወደ ታች ገጽ ወርደው ይመልከቱ!)
➢ አስገራሚው የመናፍስቱ አሠራር ደግሞ፤ በተለይ ጆሮን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሲዘጉት፤ ዓለማዊው ቦታ ላይ
በአንጻሩ በጣም ይከፍቱታል፡፡ በሌላ አገላለጽ አብረው በትኩረት ይሰማሉ፡፡ ክፉ ክፉው ነገር ቶሎ ልቦናችን
ውስጥ የሚታተምበት ምክንያት ይሄ ነው፡፡

3.3. መፍትሔው
✓ "ጀሮዬና አንደበቴ ላይ ተቀምጣችሁ ያላችሁ" ብሎ በመጥራት በመቁጠሪያ መቀጥቀጥና በአስማተ ቅዱሳን አስሮ
ማሰገድ
✓ የተጸለየበትን የጸሎት ውኃ ወይንም ጸበል ጆሮ ውስጥ በመጠን መጨመርና እምነት ከቅባዕ ዘይት ጋር መቀባት
✓ መንፈሳዊ ቃልን ከመስማትና ከማውራት በፊት ማድመጣችንና መናገራችን በእግዚአብሔር ኃይል እንዲጎበኝ
መጸለይ
✓ ለመናፍስቱ የሚስማሙ ቃላትን ከመስማትና ከመናገር ራስን መታገል "በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ
አንስተውምና።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥11) ..."አንስተውምና" ነበረ የሚለው፤ እኛ ሐሜትና ውሸት
የዲያብሎስ አሳብና ባሕሪይ እንደሆነ ግን ጭራሽ ዘንግተናል፡፡ ሁለቱም እጅግ በአንደበታችን የተለመዱ
በመሆናቸው የየዕለት ቀናቶቻችን አንድ አካል ሆነዋል)
✓ ከእኛ አካል ውጪ ያሉ መናፍስት በሰው ላይ ሆነው ወደኛ መጠጋታቸው የማይቀር ነውና፤ "ወደኔ የምታዩ፣
ጆሮ የምትጥሉና በሰው አንደበት የምትናገሩ መንፈሶች ታስራችኋል" እያልን አዲስ ሰዎችን ባገኘን ቁጥር
መጸለይ [የመናፍስት መናበብንና ሠራዊት መሳብን ይቆጣጠራል]
✓ ጌታችን ጆሮና አንደበቱ የተዘጋውን ሰው "ኤፍታህ" ብሎ መክፈቱን ከነፍስ አምነን ይዘን፤ ጠላቴ የዘጋውን
ክፈትልኝ ብሎ መቁረብ (ርዕስ አንድ)
✓ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ እንኪያስ፥ መናፍስቱ እያሉም እንኳ በፍቅር የምንሰማው ይደመጠናል፡፡ በፍቅር
የምንናገረው ይደመጣል፡፡ ስለዚህ መለኮታዊ ፍቅር መላ ሕዋሳችን ላይ እንዲታተም ስለ ፍቅር ብንቆርብ፤ ፍቅር
የሆነው የእግዚአብሔር ኃይል መስማታችንንና መናገራችንን ይባርካል (ርዕስ ሁለት)

11
ክፍል - 4
ከዚህ በፊት በነበረው ክፍል ሦስት ትምህርታችን መናፍስት ጆሮና አንደበት ላይ ሲቀመጡ ምን አይነት
ምልክቶችን እንደሚያሳዩ በቅንጭቡ ዳስሰናል፡፡ እነዚህንም መናፍስት ለመዋጋት የምንወስደውን መፍትሔ አይተን
ጨርሰን ነበር፡፡ እንዲሁ ቀጣዩን ደግሞ እንመለከታለን፡፡

4. እጅና እግር
"ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ
አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።" (መዝሙረ ዳዊት 14፥6)

በመጀመሪያው ክፍለ ትምህርት እንደተነጋገርነው መናፍስት የሰውነት አካል ላይ ተቀመጡ(አደሩ) ስንል


ሁለት አይነት መልክ እንዳለው አንስተናል፡፡ አንደኛው በዛ ሥጋዊ አካል ላይ የመንፈሱ ሠራዊቶች ቅርጽና ይዞታ
ይዘው ሲያርፉ ሲሆን፤ ሁለተኛው ግን ሥጋዊ አካሉ ላይ ሳይቀመጡ ያ የሰውነት አካል የሚሠራውን ሥራ ሲያበላሹ፣
ሲያስታጉሉና ሲያጠፉ የመናፍስቱን አቀማመጥ በስምሪት ነው እንለዋለን፡፡ ለምሳሌ የአየር አጋንንት የሚባሉት
መናፍስት በአብዛኛው ሥጋዊ አካል ላይ አይቀመጡም፡፡ ግን የአዙሪት ሹክሹክታን በመጠቀም አሳብን ይበርዛሉ፡፡ ያ
ማለት ጭንቅላት ላይ በስምሪት ሆነው እየተዋጉ ነው ማለት ነው፡፡ እንዲሁ እጅና እግርም ላይ አደፈጡ ስንል በተለይ
ሁለተኛውን የስምሪት አካሄድ ስውራኑ መናፍስት ይከተላሉ፡፡

4.1. እጅና እግር ላይ የሚቀመጡ መናፍስት


❖ ሁሉም መናፍስት ለእነርሱ የሚስማማውን ለማሠራትና ወደነርሱ አቅጣጫ ለመጠምዘዝ ሲፈልጉ እጅና እግር
ላይ ይቀመጣሉ፡፡ (የመዝሙረ ዳዊት መልእክቱ ሊነግረን የፈለገው ይህንኑ ነው)
❖ በተመሳሳይ የሚፈልጉትን በግፊት ለማስደረግ ብቻ ሳይሆን የማይፈልጉትንም ለመከልከል ሲሉ እጅና እግር ላይ
ይቀመጣሉ፡፡ ለምሳሌ እጅ ለጸሎት እንዳይዘረጋ፣ ምጽዋት እንዳይሰጥ፣ ዐሥራት እንዳይወጣ፣ ጉልበት
እንዳይንበረከክ፣ ስግደት እንዳይሰገድ፣ መንፈሳዊ ቦታ እንዳይኬድ አካላዊና ስምሪታዊ ተጽዕኖ በእጅና በእግር
ላይ ይፈጥራሉ
❖ አደጋ አድርስ፣ አስነክስ፣ ጉልበት ስበር፣ አብር፣ አንክርት፣ አባክን፣ ከአገር አጥፋ፣ አሳስረህ አስቀምጥ፣ መንገድ
አበላሽ፣ ዕድል አደናቅፍ(ኮቴ አድርቅ)፣ ወዘተ... ተብለው የሚላኩ የመተትና የድግምት መንፈሶች (እግር ላይ)
❖ ክንድ ስበር፣ እጅ አጣምም፣ ጣቶችን ቆላልፍ፣ ሥራ አበላሽ፣ በረከት አሳጣ፣ ገንዘቡን በትን፣ ግርማ ሞገስ ግፈፍ፣
ማዕረጉን ሻር፣ ወዘተ... ተብለው የሚላኩ የመተትና የድግምት መንፈሶች (እጅ ላይ)
❖ እጅ ላይ በሚጠለቁ ስጦታዎች(ቀለበት፣ አምባር፣ ሰዓት፣ ጥፍር ቀለምና የመሳሰሉት)፣ ቁሳቁስ በመቀበልና ደንቃራ
በመነካካት የገቡ መናፍስት (እጅ ላይ)
❖ ሱሉስ የጦስ ዝውውር እንዲሆኑ ተበጥብጠው የተደፉ፣ የተጣሉ፣ የተረጩ፣ የተቀበሩ የምግብ ተረፎችን፣ የእንስሳት
ቅሪቶችን፣ ብስባሾችንና ወዘተ.. በእግር በመርገጥ ጊዜ የሚቆራኙ መንፈሶች (እግር ላይ)
❖ ለስልብና የሚመቹ መናፍስትን እጅ ላይ አዋርሶ በመጨበጥ፣ በመዳበስ አሊያ በማስነካት ወደ ሰውነት ያለፉ
አፍዝ መናፍስት (እጅ ላይ)
❖ ገንዘብን በአልባሌ አሊያ አላስፈላጊ ዕቃዎች ግዢ የሚጨርስ ዓይነጥላ (እጅ ላይ)
❖ የጣት ውበትንና የሰውነት ተክለ ቁመናን አይቶ የመጣ የልክፍትና የቡዳ መንፈስ (እጅም እግርም ላይ)

12
4.2. መናፍስት እጅና እግር ላይ ሲቀመጡ የሚታዩ ምልክቶች
➢ በሥጋዊ አካል ላይ መናፍስቱ በቀጥታ ሲቀመጡ ሥጋዊ ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ የእጅና የእግር
በሽታዎች፣ እብጠት፣ የቆዳ መበላሸት፣ የአጥንት ጉዳት፣ ቁርጥማት፣ የአካል መድረቅና እንቅስቃሴ አልባ መሆን፣
ቶሎ ቶሎ መዛል ወይንም መደንዘዝ
➢ መናፍስት እጅ ላይ ተቀምጠው አብረው በሚሠሩበት ጊዜ የነኩት፣ የጀመሩት፣ የተጓዙበት፣ የፈለጉትና ያቀዱት
ክንውን ይበላሻል(አመድ አፋሽ መሆን)፣ የተገነባው ይፈርሳል፣ በሂደት ጫፍ ላይ የተደረሰው ከዳር ይመለሳል
(በሥጋም በስምሪትም እጅ ላይ መቀመጥ)
➢ የበረከት ማጣት፣ የትምህርትና የሥራ ዕድል መጣመም፣ የገንዘብ ወጪ መብዛት አሊያም የሐብት ብክነት
(በስምሪት እጅ ላይ መቀመጥ
➢ መንቀዥቀዥ፣ መራወጥ፣ አለ ምክንያት መንከራተት፣ መኖሪያ፥ መሥሪያና መማሪያ ቦታ በፍጥነት መቀያየር፣
ሲዞሩ መዋል፣ ከመንደርና ከቀዬ ብን እያሉ መጥፋት (በሥጋም በስምሪትም እግር ላይ መቀመጥ)
➢ በአንጻሩ ብዙ መቀመጥ፣ ብዙ መተኛት፣ እንቅስቃሴ መጥላት፣ ከቤት ለመውጣት መጫጫን፣ ለቀላሉም ለከባዱም
ድርጊት ዝግምተኛ(ቀሰስተኛ) መሆን (በሥጋም በስምሪትም እግር ላይ መቀመጥ
➢ ወደ ሱስ መዝናኛዎች ወይንም ልማድ ወደሆኑ የኃጢአት መንገዶች በተደጋጋሚ መጓዝ (በስምሪት የእግር
መዳፍ ላይ መቀመጥ)
➢ ለቤተክርስቲያንና አጠቃላይ ለመንፈሳዊ ሥራዎች የሚሆን ጉልበት ማጣት፣ የበጎ ነገር ልምሾ መሆን፣ የእምነት
ምግባር [እንደ ስግደት ያሉትን] ለመፈጸም ሲያስቡ ቀድሞ መድከም (በስምሪት ጉልበት ላይ መቀመጥ)
➢ የትከሻ መክበድና መጫጫን፣ የሞገስ ጥላ መገፈፍ፣ የክብር ማዕረግ ማጣት (በስምሪት ትከሻ ላይ መቀመጥ)
➢ ከልግስና መራቅ፣ ምጽዋትን መሸሽ፣ አይበቃኝም በሚል ስስታምነት እርዳታን መንፈግ፣ ለዐሥራት በኩራት ሰበብ
መደርደር (በስምሪት የእጅ መዳፍ ላይ መቀመጥ)
➢ የስርቆት አመል፣ አታልሎ ወይንም አደንዝዞ የመንጠቅ ጠባይ፣ የሰውን የመቀማት ፍቃድ፣ ሁሉንም ወደ ራስ
ብቻ የመስብሰብ አዝማሚያ (በሥጋም በስምሪትም እጅ ላይ መቀመጥ)

4.3. መፍትሔው
✓ እጅን ለጸሎት እግርን ለስግደት ማሰልጠንና ማትጋት
✓ ከትከሻ ጀምሮ እጅንና ከወገብ አንስቶ እግርን በመቁጠሪያ መቀጥቀጥ
✓ መናፍስቱ በሥጋ ላይ እንደተቀመጡ ከሚስተዋሉ ምልክቶች ከተገነዘብን፤ ከዚያ የሰውነት አካል ላይ "ሠራዊት
ሳቡና ግንባር ላይ ታሰሩ" ተብለው መታዘዝ አለባቸው፡፡ በስምሪት ተቀምጠው ከሆነ ደግሞ፤ በተዘረዘሩት
ምልክቶች መሠረት "እንዲህ እንዲህ የምታደርጉ መንፈሶች ሥራችሁን አቁሙ" እያሉ በሰማያዊ ስሞች
ሥልጣናቸውን መሻር
✓ ከቤት ከመውጣት በፊት ሰውነትን የተባረከ የወይራ ዘይት፣ የጸሎት ውኃና እምነት በመቀባት መዝሙር 90(91)ን
መጸለይ "(ክፉ ነገር ወዳንተ አይቀርብም፡፡መቅሠፍትም ወደቤትህ አይገባም፡፡ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ
መላእክቱን ስላንተ ያዝዛቸዋልና"የሚለው የተስፋ ቃል ፍልስፍና አሊያ ንድፈ ሐሳብ አይደለም፡፡ በሕይወት፣
በነፍስና በዘመን የሚተረጎም ሕያው እውነት ነው)
✓ ማንኛውንም ሥራ ከመጀመር በፊት በእግዚአብሔር ስም መባረክ፣ መዝሙር 22(23)'ን መድገምና የሂደቱን
ኃላፊነት የእግዚአብሔር መንፈስ እንዲረከብ በእምነት መጀመር
✓ በመንገድና በቤት ደጃፍ የሚጣሉ ደንቃራዎችን በሰውነት ሳይነኩ ጸበል አርከፍክፎ መዝሙር 90(91)ን እየጸለዩ
ማቃጠል

13
✓ ተልከው የሚገቡ አሊያም ቡዳ ሆነው የሚገቡ መናፍስት ቀደም ሲል ያልነበረ አዲስ ጠባይን ይገልጻሉና ከላይ
የተጠቀሱትን አይነት ባሕሪይ በራስ ላይ በተመለከቱ ጊዜ በመንቃት፤ "ይህንን ባሕሪይ ያመጣህ መንፈስ" ብሎ
በርዕስ ጸሎት፣ በርዕስ ስግደትና በርዕስ ቁርባን መታገል ይገባል
✓ የመልአክትን [እና የቅዱሳንን] መልክአ በምንጸልይበት ጊዜ፤ የመልአኩ ቅዱስ መንፈስ በኛም አካል ላይም
እንዲያርፍ ማሳሰብ፤ እንዲሁም በአንጻራዊ ውጊያ በዛው መንፈሱን እንዲያጠቃልን ማመልከት (ለምሳሌ
ለአእዳዊከ፤ የሚል የእጅን መልክአ ስንጸለይ የኛ እጅ እንዲባረክና የመንፈሱ እጅ በተቃራኒ ከክፋት ሥራ
እንዲቆጠብ መልክአ ጸሎቱን ከመጀመር በፊት መልአኩን በዚህ ርዕስ ማነጋገር)
✓ ምንም አይነት ቁሳቁስ ከሰዎች ስንረከብና ስንገዛ በእግዚአብሔር ስም መባረክ
✓ ቅዱስ ቁርባን አንዱ የሚወስድበት ምክንያት በረከት ነው፡፡ ሥራው ሲዘጋ፣ የትምህርቱ ዕድል ሲዛባ፣ መንገዱ
ሲጨልም ሥጋና ደሙን እንወስዳለን፡፡ በዚህ ጊዜ በስምሪት ተሰልፈው የሚዋጉ መንፈሶች መንገድ ሲዘጋ የኛ
ደግሞ ይከፈታል
✓ ዐሥራት ማውጣት፣ ድሆችን ማብላት ማጠጣትና ማልበስ፣ የታሰረን መጠየቅ፣ የተንገዳገደን መደገፍ የመንግሥተ
ሰማያት ጎዳናዎች ናቸው፡፡ በዚህ አቅጣጫ ላይ የማይሰማራ እጅና እግር ለክፉው አገልግሎት ቢውል እንደምን
ይደንቃል? (ግን የኛ ችግር እንዲወገድ አቅደን አይደለም የሌሎችን ችግር የምንቸገረው፡፡ ፍቅር አስቸግሮን
ነው የሰዎችን ችግር መፍትሔ መስጠት ያለብን፡፡ ከነፍስ በሚፈልቅ ርኅራኄ ነው መለገስ የሚገባው፡፡ ከባሕሪይ
በሚነሣ የቸርነት ስሜት ስናግዝ ነው መንፈሳዊ አንድምታ ያለው፡፡)

ማስታወሻ፦ ከዚህ ባሻገር ያሉት የሰውነት አካላት በአብዛኛው በሥጋዊ ሕመምና ጫና የሚገለጡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ
ኩላሊት ላይ ሲቀመጡ የኩላሊት በሽታ ይሆናሉ፡፡ ወገብ ላይ ሲሆኑ እንዲሁ የወገብ በሽታና ተጽዕኖ
ይፈጥራሉ፡፡ ማኅፀን ላይ ሲቀመጡ የተለያየ ደዌ በመፍጠርና ጽንስ እንዳይቋጠር በማድረግ ይፋለማሉ፡፡
ጨጓራ ላይም እንዲሁ ያንን ቦታ ማዕከል ያደረገ ችግር ይኖራል፡፡ እያንዳንዱን የአካል ክፍል ብንዘርዝር
አንጨርሰውምና አስቀድሞ በተማርናቸው መሠረት የመናፍስቱን አሠራር ማጤንና መወጋት ለእናንተ
የተተወ ክፍት ቦታ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሙሉት፡፡

አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው!

--------------------------------//--------------------------------

14

You might also like