You are on page 1of 1

5 ኛ ክፍል ሂሳብ ወርክሽት

I. ትክክል የሆነውን እውነት ስህተት የሆነውን ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ::


1. ጠሪው ከቆጣሪው የሚበልጥ ወይም እኩል የሆነ ክፍልፋይ ደግሞ ኢ-መደበኛ ክፍልፋይ ይባላል።

2. ኢ-መደበኛ ክፍልፋይን ወደ ድብልቅ ቁጥር ለመቀየር ጠሪውን ለቆጣሪው ማካፈል ነው።

3. ጠሪዎቻቸው እና ቆጣሪዎቻቸው የተለያዩ ክፍልፋዮችን ለማወዳደር ቆጣሪዎቻቸውን ተመሳሳይ በማድረግ ጠሪዎቻቸውን ማወዳደር ነው።
4. የተለያዩ ቆጣሪዎች ያሏቸውን ክፍልፋዮችን ለመደመር መጀመሪያ ተመሳሳይ ቆጣሪ እንዲኖራቸው ማድረግ ተገቢ ነው።
5. ብዜታቸው 1 የሆኑ ሙሉ ቁጥሮች አንዱ ለሌላኛው ተገላቢጦሽ ይባላል።

6. ቆጣሪያቸው የ10 ርቢ የሆኑ ክፍልፋዮች አስርዮሻዊ ክፍልፋዮች ይባላሉ፡፡

7. አስርዮሽ ቁጥር ላይ ከአስርዮሾች በፊት ዜሮ መጨመር የቁጥሩን ዋጋ አይለውጠውም፡፡


8. ተለዋዋጭ ማለት ቋሚ ያልሆነ ዋጋው የሚቀያየር ማለት ነው፡፡
9. ተለዋዋጮቻቸው ተመሳሳይ እና የተለዋዋጮች አርቢዎች አንድ ዓይነት የሆኑ ቁሞች ሁሉ ተመሳሳይ ቁሞች ይባላሉ፡፡

10. 46 የቁጠር 23፣ 50% ፐርሰንት ነው ፡፡


II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ::
1 23 21 21 51
11. 5 4 ን ወደ ኢ-መደበኛ ክፍልፋይ ሲቀየር ___________________________ ነው። ሀ ለ ሐ መ
20 20 4 4
6 21 6 21 123 27
12. + = _____ ሀ ለ ሐ መ
5 3 3 3 15 15
230 2304 2304 230
13. 23.04 ወደ ክፍልፋይ ሲቀየር _______ ነው ፡፡ ሀ ለ ሐ መ
100 100 1000 1000

14. 37.92+153.685= _______ ሀ. 191.605 ለ. 191.562 ሐ 119.603 መ 219.235

15. አንድ ተማሪ በአንድ የሂሳብ ትምህርት የሙከራ ፈተና ከ10 ጥያቄዎች ውስጥ 9 ቢመልስ በፐርሰንት ስንት ይሆናል?

ሀ. 20% ለ 12 % ሐ 31% መ 90%


III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ፡፡
16. የአንድ ቁጥር 3% እና 7% ድምር 26 ቢሆን፣ ቁጥሩ ስንት ነው?

17. 25 የ60 ስንት ፐርሰንት ነው?


18. የሚከተሉትን አስርዮሽ ቁጥሮች በፐርሰንት ግለጿቸው፡፡
ሀ. 0.22 ለ. 3.4 ሐ. 0.324 መ. 0.08
19. ወደ ክፍልፋይ በመለወጥ አስሉ፡፡
ሀ. 4.7 + 0.3 ለ. 38.6 - 5.7
20. የሚከተሉትን አስርዮሽ ቁጥሮች ከትንሹ ወደ ትልቁ በቅደም ተከተል አስቀምጡ፡፡
ሀ. 0.38 ፣ 0.37 ፣ 0.038 ፣ 0.079 ፣ 0.111 ለ. 9.995 ፣ 10.97 ፣ 21.034 ፣ 12.306 ፣ 19.983

You might also like