You are on page 1of 1

6 ኛ ክፍል ሂሳብ ወርክሽት

I. ትክክል የሆነውን እውነት ስህተት የሆነውን ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ::


1. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ10 ተከፋይ የሚሆነው የቁጥሩ የአንድ ቤት ሆሄ 0 ከሆነ ብቻ ነው፡፡
2. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ3 ተከፋይ የሚሆነው የሙሉ ቁጥሩ ሆሄያት ድምር ለ3 ተከፋይ ሲሆን ነው፡፡
3. 0 የማንኛውም ሙሉ ቁጥር ብዜት ነው፡፡
4. ትንሹ ተተንታኝ ቁጥር 2 ነው፡፡
5. የ2 ብዜት የሆነው ብቸኛ ቁጥር 2 ብቻ ነው፡፡
6. ማንኛውም ከ1 የበለጠ ሙሉ ቁጥር ቢያንስ ሁለት ተካፋዮች አሉት፡፡
7. የ10 እና 100 ብዜት የሆነ ሙሉ ቁጥር ሁሉ ለ10 እና ለ5 ተከፋይ ይሆናሉ፡፡
8. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ5 ተከፋይ የሚሆነው የቁጥሩ የአንድ ቤት ሆሄ 0 ወይም 5 ከሆነ ብቻ ነው፡፡
9. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ9 ተከፋይ የሚሆነው የሙሉ ቁጥሩ ሆሄያት ድምር ለ9 ተከፋይ ከሆነ ነው፡፡
10. አንድ ሙሉ ቁጥር ለ3 ተከፋይ ከሆነ ለ9 ተከፋይ ይሆናል::
II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል ምረጡ::
11. ከየሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች ውስጥ ለ8 ተከፋይ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. 7,395,624 ለ. 685,218 ሐ. 685,216 መ. 64,207

12. በ20 እና በ30 መካከል የሚገኙ የሁለት ብቸኛ ቁጥሮች የማባዛት ውጤት ነኝ፡፡ እኔ ማን ነኝ?

ሀ. 667 ለ. 23 ሐ. 29 መ. 374

13. የሁለት ቁጥሮች ት.ጋ.አ 1 እና ት.ጋ.ብ ደግሞ 24 ቢሆን ሁለቱን ቁጥሮች ከ24 እና ከ1 የተለዩ ቢሆኑ ቁጥሮቹ እነማን ናቸው?

ሀ. 3 እና 4 ለ. 4 እና 6 ሐ. 8 እና 10 መ. 4 እና 8

14. 8.634 ወደ ሁለት አስርዮሽ ቤት ሲጠጋጋ __________ ነው፡፡ ሀ. 8.63 ለ. 8.75 ሐ. 8.60 መ. 8.614
15. ከሚከተሉት ሙሉ ቁጥሮች መካከል ከ27,452 ላይ ተደምሮ ቁጥሩን ለ3 ተከፋይ የሚያደርገው ሙሉ ቁጥር የቱ ነው?
ሀ. 1 ለ. 2 ሐ. 5 መ. 9
III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ስጡ፡፡
16. የ27ን አብዥዎች (ተካፋዮች) ዘርዝሩ፡፡

17. ከ0 በስተቀር ከሁለት በላይ አብዥዎች ያሏቸው ሙሉ ቁጥሮች _________________ ቁጥሮች ይባላሉ፡፡
18. ለሚከተሉት ጥንድ ቁጥሮች የቁጥሮችን ብዜት በመዘርዘር ትንሹን የጋራ ብዜት ፈልጉ፡፡

ሀ. 60፣ 36 ለ. 12፣ 40
19. የሁለት ቁጥሮች ት.ጋ.አ 4 እና ት.ጋ.ብ ደግሞ 60 ነው፡፡ አንዱ ቁጥር 12 ቢሆን ሌላኛው ቁጥር ማን ነው?
2 ሸ
20. የ ዝቅተኛ ሂሳባዊ ቃል ቢሆን የ “ሸ” ዋጋ ስንት ነው?
5 25

You might also like