ManaBarnootaaHaayiliigi
ሃይሊግትምህርትቤት
Heilig School
'0221124055 *1045 Adama, Ethiopia E-mail: heiligschool@gmail.com
Grade_6__ Subject: maths
Date:-20/09/2013 -30/09/2013 E.C. 4th Quarter Note: 1
ምዕራፍ 5
መስመራዊ የእኩልነት ዓ/ነገሮች፣ መስመራዊ ያለእኩልነት ዓ/ነገሮች እና ወደረኝነት
1. መስመራዊ የእኩልነት ዓ/ነገሮች
በ “ ሀጠ + ለ = 0 መልክ ሊገለፅ የሚችል የዕኩልነት ዓረፍተ ነገር መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር ተብሎ ይጠራል፡፡
ምሳሌ ፡-
3ጠ+8=0
7 ቀ − 20 = 0
ዘ+5=0
63 − ከ = 0 - - - - ወ.ዘ.ተ መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡
መስመራዊ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮችን መፍታት
የአንድ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር የመፍትሄ ስብስብ እውን ስብስብ ይባላል፡፡
የእኩልነት ዓረፍተ ነገር አንድ የመፍትሄ ስብስብ ብቻ ይኖረዋል፡፡
እውን ስብስብ ለመፈለግ ዓረፍተ ነገሩን አመቺ ወደ ሆነ ሌሎች ተመጣጣኝ ዓረፍተ ነገር መለወጥ ያስፈልጋል ፡፡
የመነሻ መስኩ ሙሉ ቁጥር ለሆነ የእኩልነት ዓረፍተ ነገር የመፍትሄ ስብስብ የለውም፡፡ ስለዚህ የመፍትሄ ስብስቡ ባዶ
ስብስብ ነው፡፡
ምሳሌ
የሚከተሉትን የእኩልነት ዓ/ነገሮች የመፍትሄ ስብስብ ፈልጉ
ሀ. 5 ጠ − 14 = 16
5 ጠ − 14 + 14 = 16 + 14
5 ጠ − 0 = 30
5 ጠ = 30
5 ጠ 5 = 30 5
ጠ=6
ስለዚህ የመፍትሄ ስብስቡ { 6 } ነወ፡፡
ሀ. ጠ + 44 = 83
ጠ + 44 − 44 = 83 − 44
ጠ − 0 = 127
ጠ = 127
ስለዚህ የመፍትሄ ስብስቡ { 127 } ነው፡፡
መስመራዊ የእኩልነት አረፍተ ነገር ተመጣጣኝ ወደ ሆነው መስመራዊ የእኩልነት አረፍተነገር የመቀየር ደንብ
ሁለት መስመራዊ የእኩልነት አረፍተ ነገሮች በተሰጠው የመነሻ መስክ አንድ አይነት መፍትሔ ካላቸው
ተመጣጣኝ የእኩልነት ዐረፍተ ነገሮች ይባላሉ
ምሳሌ፡- ጠ-6 = 9 እና ጠ =15 ተመጣጣኝ የእኩልነት ዐረፍተ ነገሮች ናቸው፡፡
ምክንያቱም የመፍትሔ ስብስባቸው { 15 } ነው፡፡
መስመራዊ የእኩልነት አረፍተ ነገር ተመጣጣኝ ወደሆነው መስመራዊ የእኩልነት አረፍተ ነገር የመቀየር ደንብ::
አንድ የተሠጠ የእኩልነት አረፍተ ነገርን ግራና ቀኝ እኩል የሆነ ቁጥር ብትደር የሚገኘው የእኩልነት አረፍተ ነገር መጀመሪያ
ከተሠጠው የእኩልነት አረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል:: ይህም ማለት ጠ = ሀ ብንወስድ ጠ + ለ = ሀ + ለ ( ‹ ለ ›
ማንኛውም ቁጥር ነው፡፡
አንድ የተሠጠ የእኩልነት አረፍተ ነገርን ግራና ቀኝ እኩል የሆነ ቁጥር ብትቀንሱ የሚገኘው የእኩልነት አረፍተ ነገር፣
መጀመሪያ ከተሠጠው የእኩልነት አረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል::
ይህም ማለት ጠ = ሀ ብንወስድ ጠ − ለ = ሀ − ለ (‹ ለ › ማንኛውም ቁጥር ነው፡፡)
አንድ የተሠጠ የእኩልነት አረፍተ ነገርን ግራና ቀኝ እኩል በሆነ ግን ዜሮ ባልሆነ ቁጥር ብናባዛ የሚገኘው የእኩልነት አረፍተ
ነገር መጀመሪያ ከተሠጠው የእኩልነት አረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል::
ይህም ማለት ጠ = ሀ እና ለ 0 ብንወስድ ጠ x ለ = ሀ x ለ ( ‹ ለ › ማንኛውም ቁጥር ነው፡፡)
አንድ የተሠጠ የእኩልነት አረፍተ ነገርን ግራና ቀኝ እኩል በሆነ ግን ዜሮ ባልሆነ ቁጥር ብናካፍል የሚገኘው የእኩልነት አረፍተ
ነገር መጀመሪያ ከተሠጠው የእኩልነት አረፍተ ነገር ጋር ተመጣጣኝ ይሆናል::
ይህም ማለት ጠ = ሀ እና ለ 0 ብንወስድ ጠ ለ = ሀ ለ ( ‹ ለ › ማንኛውም ቁጥር ነው፡፡)
ምሳሌ
ጠ − 1 = 10
ጠ − 1 + 1 = 10 + 1 - - - በሁሉም ጎኖች 1 መደመር ጠ = 11
ስለዚህ ፡- "ጠ − 1 = 10" እና "ጠ = 11" ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓረፍተ ነገሮች ናቸው ፡፡
ምሳሌ
2ቀ+3=5
2 ቀ + 3 – 3 = 5 − 3 ---------- ከሁሉም ጎኖች 3 መቀነስ
2 ቀ = 2 ቀ = ------------- ከሁሉም ጎኖች ለ 2 ማካፈል
ቀ=1
ስለዚህ፡- ተመጣጣኝ የእኩልነት ዓ/ነገሮች ናቸው፡፡
መልመጃ
የሚከተሉትን የእኩልነት ዓ/ነገሮች በተሰጠው መስርያ ክልል ውስጥ ፍቱ፡፡
ሀ. 8 + ሸ = 65 ፣ ሸ ∈ ሙ
ለ. ሸ − 58 = 8 ፣ ሸ ∈ ድ
ሐ. ጠ – 1 = 7 ፣ ጠ ∈ ን
መ. ቀ = 0.18፤ቀ ∈ ን
ሠ. ወ = 57 ፣ ወ ∈ ሙ
ረ. 48 − ቀ = 98 ፣ ቀ ∈ ን
2. የሚከተሉትን የቃላት ፕሮብሌሞች በእኩልነት ዓ/ነገሮች ከገለፃችሁ በኋላ ፍቱ፡፡
ሀ. ከአንድ ቁጥር ላይ 35 ተደምሮበት ውጤቱ 207 ይሆናል ፡፡
ለ. የአበበ እና የሠሎሞን እድሜ ድምር 48 ነው፡፡ አበበ ሠሎሞንን 4 አመት ይበልጠዋል፡፡
i. የሠሎሞን እድሜ ስንት ነው?
ii. ii. የአበበ እድሜ ስንት ነው?
መ. በአንድ ክፍል ውስጥ 64 ተማሪዎች አሉ፡፡ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ከወንዶቹ በ 13 ያንሳል፡፡
i. የወንድ ተማሪ ቁጥር ስንት ነው?
ii. የሴት ተማሪ ቁጥር ስንት ነው?
2. መስመራዊ ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮች
መስመራዊ ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮች የሚባሉት ከሚከተሉት በአንዱ ፎረምልክት የተገለፀ ከሆነ ነው፡፡
ጠ+በ<0
ጠ+በ≤0
ጠ + በ> 0
ጠ+በ≥0
ጠ+በ≠0
መስመራዊ ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮች መፍታት
መስመራዊ ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮችን እውነት የሚያደርጉ ከአንድ በላይ መፍትሔዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ
3ሸ+6≥0
መፍትሔ
3ሸ+6≥0
3ሸ≥0−6
3ሸ≥−6
ሸ ≥ −2
ሸ ≥ −2 በቁጥር መስመር ሲገለፅ፡- ስለዚህ ማንኛውም ከ −2 የሚበልጥ ወይም እኩል የሆኑ ቁጥሮች የተሠጠው
ያለእኩልነት ዓ/ነገሩ መፍትሄ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የመፍትሄ ስብስቡ {−1 ; 0 ; 1; 2 ; … … … … . } ነው፡፡
የያለ እኩልነት ዓረፍተ ነገር ከአንድ በላይ የመፍትሄ ስብስብ ይኖረዋል፡፡
ምሳሌ
−4 ጠ < 12
መፍትሔ
−4 ጠ < 12 ጠ ˂ − ----------------- በሁሉም ጎን በ −4 ማካፈል ጠ < −3
ስለዚህ በ −4 ስለ ተካፈለ ምልክቱ ይዞራል ፡፡ በመሆኑም ጠ > −3
ምሳሌ
2−ሸ≥4፣ሸ∈ድ
መፍትሔ
2 − ሸ ≥ 4 ፣ ሸ ∈ ድ 2 − 2 − ሸ ≥ 4−2 -በሁሉም ጎኖች ላይ 2 መቀነስ፡፡
−ሸ ≥ 2 −1 x (−ሸ ) ≤ 2 x (−1) -ሁሉም ጎኖች በ−1 ማባዛት፡፡
ሸ ≤ −2 ------- ምልክቱ ይዞራል ፡፡
የዓ/ነገሩ መስርያ ክልል የድፍን ቁጥሮች ስብስብ ስለሆነ ዕ.ስ = {- - - −4 ፣ −3 ፣ −2}
መልመጃ
1. የሚከተሉትን መስመራዊ ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮች ፍቱ ፡፡
ሀ. 5 በ +7 < 11
ለ. ጠ + 5 ≥ 8
ሐ. ጠ + 2 ≥ 9
2. የሚከተሉትን ያለ እኩልነት ዓ/ነገሮች በተሰጠው መስርያ ክልል ፍቱ ፡፡ የመፍትሔ ስብስቡን በቁጥር መስመር አመልክቱ፡፡
ሀ. ሸ 3 ≤ 5 ፣ ሸ ∈ ሙ
ለ. 6 − ሸ ≤ ሸ + 8 ፣ ሸ ∈መ
ሐ. ጠ + 9 > 7 ፣ ጠ ∈ ድ
መ. 5 + 3 ጠ ≤ 9 ፣ ጠ ∈ ን
3. ውቅሮች
ተከታታይ ጥንድ ቁጥሮችን ለማመልከት የምንጠቀምበት ሥርዓተ ውቅር ይባላል፡
ስርዓተ-ውቅር ለመመስረት ሁለት መስመሮችን እንጠቀማልን ፡፡እነሱም፡-
ዋና አግዳሚ ጠ-መስመር /ጠ-ፈርጅ ወይም x-axis/
ዋና ቋሚ የ-መስመር /ጠ-ፈርጅ ወይም y-axis/ ናቸው ፡፡
ሁለት መስመሮች ሲቋረጡ አንግል ይፈጥራሉ፡፡
የሚቋረጡበት ቦታ (0 ፣ 0) ላይ ሲሆን መነሻ ነጥብ / ኦርጅን ወይም origin / ይባላል፡፡
ማስታወሻ በ "ጠ" አግድም ከመነሻ ነጥቡ በስተቀኝ በኩል አዎንታ ድፍን ቁጥሮች ሲቀመጡ ከመነሻ ነጥቡ በስተግራ በኩል
አሉታ ድፍን ቁጥሮች ይቀመጣሉ፡፡
በ "የ" ቁም ከመነሻ ነጥቡ በላይ አዎንታ ድፍን ቁጥሮች ሲቀመጡ፣ ከመነሻ ነጥቡ በታች ደግሞ አሉታ ድፍን ቁጥሮች
ይቀመጣሉ ፡፡
በማንኛውም ስርዓተ-ውቅር ማንኛውም ነጥብ በተከታታይ ጥንድ (ሀ ፣ ለ) ይወከላሉ፡፡ በዚህ ጥንድ ሀ ፡- አብሲሳ ወይም ጠ-
ኮርዲኔት ሲባል ለ ፡- ኦርድኔት ወይም የ-ኮርዲኔት ይባላል፡፡
አስተውሉ፡- ጠ - አግድም መስመር እና የ - ቁም መስመር የጠለል ክፍልን ከአራት እኩል ቦታ ይከፍሉታል፡፡ እያንዳንዱ ክፍል
ሩቤ ወይም ኳድራንት ይባላል፡፡ ሩቤዎች እንደሚከተለው ይወከላሉ ፡፡ 1 ኛ ሩቤ ፣ 2 ኛ ሩቤ ፣ 3 ኛ ሩቤ ፣ 4 ኛ ሩቤ
ናቸው፡፡
ሁለት ጥንድ ቁጥሮችን በስርዓተ ውቅር ማመልከት ይቻላል፡፡
በስርዓተ ውቅር ላይ የ ጠ - ፈርጅ መጀመሪያ ሲሆን የ የ - ፈርጅ ሁለተኛ ወይም ከ ጠ - ፈርጅ ተከትሎ
ይመጣል፡፡
1 ኛ ሩቤ (+ ፣ +) 2 ኛ ሩቤ (− ፣ +) 3 ኛ ሩቤ (− ፣ −) 4 ኛ ሩቤ (+ ፣ −)
ውቅር አንድ እና ውቅር አራት ተቃራኒ ሲሆኑ ውቅር ሁለት እና ውቅር አራት ተቃራኒ ናቸው፡፡
መልመጃ
ከዚህ በታች ያሉትን ጥንድ ቁጥሮች በስርዓተ ውቅር አሳዩ ፡፡
ሀ. (−5 ፣ 5)
ለ. (−4 ፣ −2)
ሐ. (0 ፣ −6 )
መ. (7 ፣ 0)
ሠ. (2 ፣ 4)
2. የሚከተሉትን ነጥቦች በየትኛው ሩቤ እደሚገኙ ግለፁ ፡፡
ሀ. (4 ፣ −3)
ለ. (-2 ፣ -3)
ሐ. (0 ፣ 5)
መ. (5 ፣ 1)
ሠ. (-3 ፣ 0)
ረ. (-3 ፣ 7)
3. ከሚከተሉት ነጥቦች ውስጥ የትኞቹ ጥንድ ቁጥሮች "የ = ጠ − 3" ን እውነት እንደሚያደርጉ ለዩ፡፡
ሀ. (0 ፣ −3)
ለ. (3 ፣ 0)
ሐ. (1 ፣ 2)
መ. (5 ፣ 2)
4 ወደረኛነት
ወደረኝነት የአንድን ነገር ከሌላ ነገር ጋር ያለው ንፅፅር ወይም ሚዛናዊነት ነው ፡፡
ይኸውም ፡- የ = 7 ጠ ቢሆን የ ’’የ‘’ ዋጋ የ ’’ጠ’’ ዋጋ መሠረት ያደርጋል፡፡
ማለትም ፡- የ ’’ጠ’’ ዋጋ ሲለወጥ የ ’’የ’’ ዋጋ ይለወጣል ፡፡
ሁለት አይነት ወደረኛነት አሉ ፡፡ እነሡም ፡-
ሀ. ርቱዕ−ወደረኝነት
ለ. ኢ - ርቱዕወደረኝነት
ርቱዕ ወደረኛነት
በሁለት ነገሮች መካከል የአንደኛው መጠን ሲጨምር የሌላኛው መጠን በተመጣጣኝ የሚጨምር ከሆነ ወይም የአንደኛው
መጠን ሲቀንስ የሌላኛው መጠን በተመጣጣኝ የሚቀንስ ከሆነ ዝምድናው ርቱዕ ወደረኛ ይባላል ፡፡
የ እና ጠ የርቱዕ ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው የ ጠ › ተብለው ይፃፋል::
የ = ከጠ እውነት ከሆነ "ከ" የወደረኝነት ትንትን ይባላል ፡፡ "ጠ" ሲጨምር "የ" ይጨምራል፡፡
ምሳሌ
ጊዜ(ጊ) በሠዓት 1 2 3 4 5 6
ርቀት(ር) በኪ.ሜ 20 40 60 80 100 120
ርቱዕ ወደረኛ ነው ፡፡ ምክንያት ር/ጊ/ = 60 ወይም ር = 60 × ጊ
የወደረኝነት ትንትን 60 ነው ፡፡
አሥተውሉ፡-የ ጠ ከሆነ እና ጠ 1 እና ጠ 2 የጠ ዋጋ፣ እንዲሁም የ 1 እና የ 2 የየ ዋጋ ከሆኑ
የ1 የ2 ጠ1 ጠ 2
= ወይም =
ጠ1 ጠ2 የ1 የ 2
ኢ - ርቱዕ ወደረኝነት
"ጠ" እና "የ" ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት አላቸው የምንለው ከዜሮ የተለየ ቁጥር "ከ"ን ወስደን
"ጠየ = ከ" ወይም "የ = ከ ጠ"ን እውነት የሚያደርግ ቁጥር ሲገኝ ነው ፡፡
"ከ" የወደረኛነት አዊት ይባላል ፡፡
"ጠ" እና "የ" ኢ-ርቱዕ ወደረኝነት በምልክት ሲገለፅ " የ α ጠ " በማለት ይፃፋል፡፡
"ጠ እና የ" ኢ - ርቱዕ ወደረኛ ከሆኑ፤"ጠ" ሲጨምር "የ" በተመጣጣኝ ይቀንሳል፤ "ጠ" ሲቀንስ "የ" በተመጣጣኝ
ይጨምራል፡፡
አሥተውሉ፡- ጠ 1 እና ጠ 2 የጠ ዋጋ፣ እንዲሁም የ 1 እና የ 2 የየ ዋጋ ከሆኑ የተለያዩ የየ ዋጋ ብንል:: ጠ እና የ የኢ-ርቱዕ
ወደረኝነት ዝምድና ካላቸው ጠ 1 × የ 1 = ጠ 2 × የ 2
ከ
ፍንጭ ፡- የ =
ጠ
የ ወደረኝነት ያዊት ከ = የጠ ይሆናል፡፡
ምሳሌ ፡-
ጠ 3 5 8 6 4
የ 10 6 6 8 12
ጠ 1 × የ 1 = ጠ 2 × የ 2 ስለዚህ ዝምድናው ኢ - ርቱዕ ወደረኛ ነው፡፡
መልመጃ
1."የ እና ጠ" ኢ - ርቱዕ ወደረኛ ናቸው፡፡ የ = 40 ፣ ጠ = 5 ቢሰጡ፡-
ሀ. የ"ጠ እና የ" ዐ.ነገር በማዛመድ ፃፉ፡፡
ለ. ይህንን ሂሳባዊ አገላለፅ በመጠቀም የ = 100 ከሆነ የ"ጠ" ዋጋ ፈልጉ ፡፡
ሐ. ይህንን ሂሳባዊ አገላለፅ በመጠቀም ጠ = 20 ከሆነ "የ" ስንት ነው ?
2. 10 ሠዎች 12 ቀን የሚፈጅባቸውን ስራ 6 ሰዎች ስንት ቀን ይፈጅባቸዋል?