You are on page 1of 7

አቤኔዘር ት/ቤት

(ከአፀደ ህፃናት እስከ ኮሌጅ መሰናዶ)


ቢሾፍቱ
የ2012 የተቀናጀ ሳይንስ ለ5ኛ ክፍል የተዘጋጀ ማስታወሻ

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች
 ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ደቂቅ ዘአካላት በአይን የማይታዩ በሽታ አምጪ ኣካላት ናቸው።

እነዚህ ደቂቅ ዘአካላት እንዲራቡ እና በሽታን እንዲያመጡ የሚያደርጉ ጎጂ ድርጊቶች የሚከተሉት


ናቸዉ።

 ጥሬ ስጋ እና አሣን መብላት

 ያልተፈላ ወተት መጠጣት

 ንፅህና የሌለውን ዉሃ መጠጣት

 በየቦታው መፀዳዳት

 ቆሻሻን በየቦታዉ መጣል ወዘተ ነዉ።

 ጥሬ ስጋ እና ያልተፈላ ወተት ለበሽታ አምጭ ጎጂ ዘኣካላት ምቹ መራቢያ ስለሆኑ ስጋዉን አብስለን


ወተቱን አፍልተን መጠቀም አለብን።

 ቆሻሸን በየቦታዉ መጣል እና በየቦታው መፀዳዳት ጉዳቶችን ያስከትላል።

 የአከባቢዉ ሽታ ወደ መጥፎነት ይቀይራል።

 በሽታ አምጪ ለሆኑ ጎጂ ነፍሳት መራቢያ ይሆናል።

 ቆሻሻዉ ወደመሬት ዘልቆ ዉሃን እና የእንሰሳትን ምግብ ይበክላል።

 በሚከሰተዉ በሽታ የተነሳ ሰዎች ይታመማሉ፣ ከፍተኛ ለሆነ የህክምና ወጪ ይዳረጋል።

o ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለመከላከል፦

 ቆሻሻን በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ መድፍት

 በሽንት ቤቶች መጠቀም

 ዉሃን በማፍላት ወይም የውሃ ማከሚያ መድሃኒት በመጨመር መጠጣት ያስፈልጋል።

ሳይንስ ገፅ 1
ኤች አይ ቪ እና ኤድስ(HIV and AIDS)

 ኤች አይ ቪ/ኤድስ፥የተገኘዉ ከሰላሳ ዓመት በፊት ነዉ። በነዚህ አመታት በአለም ላይ በሚሊዮኖች


የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

 ኤች አይ ቪ ቫይረስ ሲሆን ኤድስ ደግሞ በቫይረሱ የሚመጣዉ በሽታ ነዉ።

 ኤች አይ ቪ የሰዎችን የበሽታ ተከላካይ የሆነዉን ነጭ የደም ህዋስ(White blood cell)


የሚያጠቃ ቫይረስ ነዉ።

 ሰውነታችንን ከበሽታ የሚከላከለዉን ነጭ የደም ህዋስ ቁጥር በመቀነስ በሽታ የመከላከል


አቅምን በማሳጣት ለተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ እንድንጋለጥ ያደርጋል።

የኤች አይ ቪ መተላለፊያ መንገዶች፦

 በግብረ ስጋ ግንኙነት

 በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ

 በደም ንክኪ በሚፈጥሩ ስለታም እና ሹል ነገሮች ለምሳሌ፦ምላጭ እና መርፌ በሽታዉ ከያዘዉ


ህመምተኛ ጋር በጋራ በመጠቀም በመነቀስ እና ጆሮን በመበሳት ይተላለፋል።

 የጥርስ ብሩሽ በጋራ በመጠቀምም ይተላለፋል።

የኤች አይ ቪ የመከላከያ መንገዶች፦

 ራስን ማስተማር፦ ስለ በሽታው ምንነት እና መተላለፊያ መንገዶች ስለ ኤች አይ ቪ የተፃፉ


ፅሑፎችን ማንበብ ያስፈልጋል።

 ለኤች አይ ቪ ከሚያጋልጡ ልዩ ልዩ ተግባራት እራስን መጠበቅ

 ከጋብቻ በፊት የግብረ ስጋ ግንኙነት አለማድረግ እና ከጋብቻ በውኋላ በኣንድ መወሰን

 ስለታም ነገሮችን እና የጥርስ ቡርሾችን በጋራ አለመጠቀም

 የፀጉር መቁረጫ ማሽንን በደንብ ሳይፀዳ አለመጠቀም

ኤድስን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕይወት ክህሎቶች

 ከቤተሰብ እና ከመምህራን ጋር ስለበሽታዉ ምንነት እና መተላለፊያ መንገዶችን በደንብ


መወያየት

ሳይንስ ገፅ 2
 በራስ የመተማመን ስሜትን ማዳበር

 ራስን ለኤች አይ ቪ ከሚያጋልጡ ድርጊቶች መጠበቅ

 በበሽታዉ የተያዙ ሰዎችን አለማግለል

 ሰዎች በሚፈጽሟቸዉ መጥፎ ድርጊቶች አለመሳባ

 የቤተሰብን እና የመምህርን ምክር መስማት ወዘተ።

ምዕራፍ ስድስት

ሥርአተ ፀሀይ
 መሬት ኣንዷ ፕላኔት ናት። ለሰው መኖሪይ ከሁሉም ፕላኔቶች በላይ ምቹ ናት።መሬት ህይወት
ያላቸዉን እና ህይወት የሌላቸዉንነገሮች በሙሉ በውስጧ ትይዛለች።

ሥርአተ ፀሃይ፦

 ፀሃይ ኮከብ ሳትሆን የራሷ የሆነ ብርሃን ሙቀት አላት።

 ፀሃይ ለመሬት ዋና የጉልበት ምንጭ ናት

 የፀሃይ ክብደት የመሬትን ክብደት በሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ እጥፍ ይበልጣል

ሥርአተ ፀሃይ ማለት፦ ፀሃይ እና በፀሃይ ዙሪያ የሚዞሩ ኣካላትን የያዘ ስብስብ ማላት ነዉ። በዚህ
ስርአተ ፀሃይ ዉስጥ ፕላኔቶች፣ የየፕላኔቶቹ ጨረቃዎች፣ አስትሮይዳች፣ ሜትዪሮች
እና ኮሜቶች ናቸዉ።

6.1 ፕላኔቶች

 ስምንት(8) ታላላቅ ፕላኔቶች አሉ። እነሱም፦ ሜርኩሪ፣ ማርስ፣ ቬነስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ዩራኑስ፣
እና ኔፕቲዩን ናቸው።

 ሶስቱ(3) ትናንሽ ፕላኔቶች ደግሞ፦ፑሉቶ ፣ኤርስ፣ ሴርስ ናቸዉ።

አስትሮይዶች (Asteriods)

 ብዙ የድንጋይ ስብርባሪዎች ሲሆኑ በማርስ እና ጁፒተር መካከል ሆነዉ ፀሃይን ይዞራሉ።

ተዘዋዋሪ ኮከቦች Meteors

 በፀሃይ ዙሪያ የሚዞሩ ትናንሽ ተወርዋሪ አካላት ናቸው።

ጅረታማ ከዋክብት (Comets)

 ጅረታማ ክዋክብት የበረዶ ቁርጥራጮች የአቧራዎች እና የጋዞች ድብልቆች ናቸዉ።


ሳይንስ ገፅ 3
 በፀሃይ ዙሪያ የሚዞሩበት ምህዋር በጣም ሞላላ ነዉ።

6.2 የፀሃይ አቀማመጥ

ፀሃይ የሥርአተ ፀሐይ መሃል ስትሆን የተቀሩት ፕላኔቶች በፀሃይ ዙሪያ ምህዋራቸዉን ጠብቀዉ ይዞራሉ።

ፀሃይ ለጉልበት ምንጭ፦ከፀሃይ የሚገኘዉ የጉልበት ምንጭ ወደ መሬት የሚመጣዉ በጨረር አማካይነት
ነው። ከፀሃይ የሚገኘዉ ጉልበት (Solar energy) የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት።

 ዉሃን ለማፍላት (Solar boiler)

 በፀሃይ ጉልበት የሚሰራ ካልኩሌተር

 በፀሃይ ጉልበት ለሚሰራ መኪና

 ለብርሃን ምንጭነት

 ተክሎች ምግባቸዉን እንዲያዘጋጂ

 ለዝናብ መኖር ይጠቅማል

ፀሃይ ባትኖር ኖሮ?

o እፀዋት አይኖሩም። እፀዋት ከሌሉ ደግሞ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች ሁሉ አይኖሩም። ምክንያቱም
እፀዋት ምግባቸዉን የሚያዘጋጁት በፀሃይ ብርሃን አማካኝነት ስለሆነ ነዉ።

የፕላኔቶች ስም፦ የፕላኔቶች ስም ከፀሃይ ባለ ርቀት፦

1. ሜርኩሪ 5. ጁፒተር

2. ቬነስ 6. ሳተርን

3. መሬት 7. ዩራኑስ

4. ማርስ 8. ኔፕቲዩን

የሚከተሉትን አስታዉሱ፥

 ትልቁ ፕላኔት ጁፒተር ነዉ

 ከፀሃይ በርቀት ነሚገኘዉ ፕላኔት ኔፕቲዩን ነው

 በፀሃይ ዙሪያ አንድ ጊዜ ለመዞር ብዙ አመት የሚፈጅባት ፕላኔት ኔፕቲዩን ነዉ።

 ፕላኔቶች የራሳቸው የሆነ ብርሃን አያመነጩም።

ሳይንስ ገፅ 4
ትናንሽ ፕላኔቶች፦ ትናንሽ ፕላኔት የሚባሉት፡-

 ኤሪስ

 ፕሉቶ እና

 ሴርስ ናቸው።

 የሰዎች እዉቀት እያደገ በሄደ ቁጥር የፕላኔቶች ብዛት እየጨመረ ይሄዳል። በአሁን ወቅት
የተረጋገጡ ስምንት(8) ትላልቅ እና ሶስት(3) ትናንሽ ናቸዉ በአጠቃላይ አስራ አንድ(11) ናቸው።

 ፕላኔቶች ባላቸዉ ለፀሐይ ቅርብ የሆኑት ዉስጣዊ ፕላኔት ሲባሉ የራቁት ደግሞ ዉጫዊ ይባላል።
ሜርኩሪ ፣ መሬት እና ቬነስ ውሰጣዊ ሲሆኑ ጅፒተር ፣ ሳተርን ፣ ኡራኑስ እና ኔፕቲዪን ወጫዊ
ፕላኔቶች ናቸዉ።

መልመጃ

ከሚከተሉት አማራጮች ትክክለኛዉን መልስ ምረጡ።

1. ፀሐይ በአብዛኛዉን የተገነባችዉ ከምንድነዊ?

ሀ, ከሀይድሮጂን እና ከኦክስጂን ሐ,ከሃይድሮጂን እና ናይትሮጂን

ለ, ከሂሊየም እና ከሃይድሮጂን መ, ከሂሊየም እና ናይትሮጂን

2,ከሚከተሉት አንዱ ትንሽ ፕላኔት ነዉ። የትኛዉ ነዉ?

ሀ, ፑሉቶ ሐ,ሳተርን

ለ, ቬነስ መ, ሜርኩሪ

3, ከከዋክብት ሁሉ ለመሬት ቅርብ የሆነችው የትኛዋ ናት?

ሀ, ተወርዋሪ ኮከብ ሐ, ጅረታማ ኮከብ

ለ, ፀሃይ መ, የንጋት ኮከብ

4, ለመሬት ዋነኛ የጉልበት ምንጭ የሆነችዉ ከሚከተሉት የትኛዋ ናት?

ሀ, ፀሃይ ሐ,ያጥቢያ ኮከብ

ለ, ጨረቃ መ, ሁሉም መልስ ናቸዉ

ሳይንስ ገፅ 5
5, ደካማ የግለት አስተላላፊ ነው፡፡

ሀ, መስታወት ሐ, ቆርቆሮ

ለ, መዳብ መ, ወርቅ

6, የሰዉ ልጅ ስንት ኩላሊቶች አሉት?

ሀ, 2 ሐ, 3

ለ, 4 መ. 6

የሚከተሉትን ጥያቄዎች አዛምድ

ሀ ለ

1, የኤች አይ ቪ መከላከያ መንገዶች ሀ, ሙቀት በጠጣር ዉስጥ ሲያል

2, ከኤች አይ ቪ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ለ, ሙቀት በፈሳሽ ዉስጥ ሲያልፍ

3, የውሃን እጥረት ለመቅረፍ ሐ, ሙቀት በወና ዉስጥ ሲያልፍ

4, የኤች አይ ቪ መተላለፊያ መንገዶች መ, ጠንክሮ በጋራ መስራት

5, ድርቅን ለመቋቋም ሠ,ስለታም ነገሮችን በጋራ አለመጠቀም

6, ጨረራ ረ, እንክብካቤ እና ድጋፍ ማድረግ

7, ፍልክልክታ ሰ, በዝናብ ወራት ዉሃን ማጠራቀም

8, አስተላልፎሽ ሸ, የግብረ ስጋ ግንኙነት

9, ሙቀት አስተላላፊ ቀ, መጨባበጥ

10, ሙቀት የማያስተላልፍ በ,ጎማ

ተ, ብረት

ሳይንስ ገፅ 6
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛዉን መልስ ስጡ

1. በኤች አይ ቪ/ኤድስ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህፃናት ምን መደረግ አለበት?

------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------

2. ቆዳ ሁለት ዋናዋና ክፍሎች አሉት እነሱም?

----------------------------------------------------------------------------

----------------------------------------------------------------------------

3. የፅድጃ አካላት የሚባሉት የትኞቹ ናቸዉ?

------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------------------------------

አዘጋጅ፡- መ/ር ሙሴ

ስልክ ቁጥር፡- 09 22 66 43 78

ሳይንስ ገፅ 7

You might also like