You are on page 1of 37

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

KARA KALE HEYWET CHURCH


ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለሚመለከተው ሁሉ

ወንጌላዊ አስፈራቸው ጳውሎሰ ከየካቲት 1/2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 2/2015 ድረስ በአዲስ አበባ ካራ
ቃ/ሕ/ቤ በታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን በእነዚህ በአምስት አመታት ቆይታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማርና በመስበክ፤
የመጽሃፍ ቅዱስ ቡድኖችን በማዋቀር፤ ወራሃዊ የህያው እንጀራ ጽሁፍ በየወሩ በማዘጋጀት፤ የቤተሰብ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት
በማዘጋጀት፤ የቤተክርስቲያን የትምህርት ቀን ከፍተው ምዕመናንን በማስተማር፤ የተለያዩ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርቶችን
በእሁድ አምልኮ በማቅረብ፤ በመዝሙር አምልኮ በመምራትና መዝሙር በመዘመር፤ ሌሎችንም ለምዕመናን መንፈሳዊ ህይወት
የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን በማዋቀርና በመምራት ቤተክርስቲያናችንን ለማሳደግ ታላቀ አስተዋጾ ያበረከቱ አገልጋይ ናቸው፡፡
ከዚህ ለሚቀጥለው አገልግሎት ዘመናቸው ሁሉ የጌታ ጸጋ እንዲበዛላቸው እየተመኘን በየትኛውም አገልግሎት ዘርፍ ቢሳተፉ
ፍርያማ እንደሚሆኑ፤ የሚሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚችሉና ለመንፈሳዊ አገልግሎት የተሰጡ መሆናቸውን
እንመሰክራለን፡፡
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለአዲስ አበባ እና አከባቢው ቀጠና ጽ/ቤት


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የድጋፍ ድብዳቤ ስለመስጠት ይሆናል፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው በቀን 4/13/2014 ዓም በደብዳቤ ቁጥር አ/አ/ቀ/ጽ/12/14 በተጻፈው
ደብዳቤ መሠረት ሥራ አጥ ወጣቶች በ (International youth fellowship) በተዘጋጀው ስልጠና ለመሳተፍ
ታማኝነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ማምጣት እንዳለባቸው የሚጠይቅ
በመሆኑ ከታች በስም የተጠቀሱ ወጣቶች የቤተክርስቲያናችን ታማኝ አባልና አገልጋይ እንዲሁም ሥራ የሌላቸው
መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡ ስለምታደርጉት ቀና ትብብር ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

1. አቤነዘር ተስፋዬ
2. ልደት ታቦሬ
3. ዮሴፍ ገዛኽኝ
4. አማኑኤል ጌታሁን
5. አዩብርሃን ናስር

የጌታ ጸጋ ይብዛላችሁ!!!
ከሰላምታ ጋር

አቶ ናስር ሻንቆ
የቤተክርስቲያንቱ የአስተዳዳር ሽማግሌዎች ም/ሰብሳቢ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ዋና ጽ/ቤት


አዲስ አባባ
ጉዳዩ፡- ደረሰኝ ለመግዛት ስለመጠየቅ

የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የገንዘብ መጠየቂያ ደረሰኝ የቼክ መክፈያ ሰነድ ስላለቀብን የገንዘብ መቀበያ
ደረሰኝ 20 (ሃያ) ጥራዝ እንድንገዛ ይፈቀድልን ዘንድ በትህትና እናመለክታለን፡፡

አቶ ናስር ሻንቆ

የቤተክርስቲያን ም/ሰብሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለወረገኖ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ጉዳዩ ፡- መሸኛ ደብዳቤ ስለመስጠት ይሆናል፡፡

አቶ ታምራት ማኖ የቤተክርስቲያናችን አባል ሲሆኑ አሁን ግን ከቦታ ርቀት የተነሳ የመሸኛ ደብዳቤ
እንዲሰጣቸው በቀን 20/09/2014 ዓም በጻፉት ደብዳቤ ጠይቀውናል፡፡ ስለሆነም በመንፈሳዊ ሕይወታቸው
እንድታሳድጓቸው አደራ በማለት ጭምር ይህንን የመሸኛ ደብዳቤ ስጥታለች፡፡

ከሰላምታ ጋር

አቶ ተሰማ ጫሚሶ
የቤተክርስቲያንቱ የአስተዳደር ሽማግሌዎች ሰብሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለአቶ ደምሴ አቢዴ


አዲስ አበባ

በቤተክርስቲያን በኩል ባለው የይዞታ ድንበር ማስተካከያ እንዲደረግ ስለማሳሰብ፡-

የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሽማግሌዎች ቦርድ ተከታታይ ስብሰባዎችን በማድረግ በ 13/09/14 ዓ.ም
ባደረገው ስብሰባ የድርጅቱን አጠቃላይ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን ውሳኔዎች
አስተላልፏል፡፡

ቤተክርስቲያኒቱ ካላት የመንፈሰዊ አገልግሎት በተጨማሪ ከወረዳ 12 ጋር በመተባበር በአከባቢው ካለው


ኅብረተሰብ መካከል የደሃ ደሃ የተባሉ ከ 300 በላይ ልጆችን በመመልመል ሁለንተናዊ እርዳታ በማድረግ ላይ ያለች
መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ እነዚህ ልጆች ወደ ቤተክርስቲያን ግቢ ለማጠናከሪያ ትምህርትና የተለያዩ እርዳታዎችን
ለመቀበል ሲመጡ ደህንነታቸው በሚገባ መጠበቅ እንዳለበት ይታወቃል ፤ ቤተክርስቲያኒቱም ከተለያዩ ችግሮችና
አደጋዎች የመጠበቅ ኃላፊነት አለባት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቤተርስቲያኒቱ የራሷ የሆኑ መገልገያና የቢሮ ንብረት
ያላት በመሆኑ ለጥበቃ በሚያመች ሁኔታ ይዞታዋን አጥራ ለሥራና ለአገልግሎት አመቺ ማድረግ አስፈላጊ
በመሆኑ፡-

1. ልጆችና ሕዝቡ ሽንት ቤት ለመጠቀም በሚንቀሳቀሱበት መንገድ ላይ ያጠሩት አጥር ወድቆ መንገድ
የዘጋ በመሆኑ ከቤተክርስቲያን ይዞታ ወደ ራስዎ ይዞታ አጥር አንስተው እንዲያጥሩ

2. በቤተክርስቲን ይዞታና ግቢ ውስጥ መመላለስ ለጥበቃና ለልጆች ደህንነትም አደገኛና አስቸጋሪ


በመሆኑ በራሶ ይዞታ በኩል በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ መውጫ እንዲያዘጋጁ እያሳሰብን በድንበር
በኩል ለድርጅቱ ደህንነት ሲባል አጥር ለማጠር በዝግጅት ላይ መሆናችንን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ከሰላምታ ጋር
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለከራ ደማሚት አከባቢ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን

ጉዳዩ፡- መሸኛ መስጠትን ይመለክታል


ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

አቶ አፈወርቅ ወሌቦ በቀን ለቤተክርስቲን በጻፉት ደብዳቤ የመሸኛ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው ጠይቀውናል፡፡
በዚህም መሠረት አቶ አፈወርቅ ወሌቦ የአዲስ አበባ የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን አባል ናቸው፡፡

አሁን ግን ከቦታ ርቀት የተነሳ ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር በሚቀርባቸው ቤተክርስቲያን ጌታን ለማገልገል እና
ለማምለክ ስለፈለጉ በጌታ ፍቅር እንድትቀበሏቸው እና እና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው አንድታሳድጓቸው በጌታ
ፍቅር እንጠይቃለን፡፡

የጌታ ኢየሱስ ሠላሙ እና ጸጋው ይብዛላችሁ!!!

አቶ ተሰማ ጫሚሶ
የቤተክርስያንቱ ሽማግሌዎች ሰብሳቢ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለሚመለከተው ሁሉ
ጉዳዩ፡- የድጋፍ ደብዳቤ መስጠትን ይመለከታል

የቤተክርስቲያናችን አባል የሆኑት ምንዳ እሸቴ በ 14/05/14 የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ጠይቀዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከላይ በስም የተጠቀሱ ወንድም በቤተክርስቲያናችን ወጣቶችን ፤ልጆችን በማስተማር
፤ፕሮግራም በመምራትና በመስበክ የሚያገለግሉና ጌታን የሚወዱ ታማኝና ታታሪ አገልጋይ መሆናቸወን እየገለጽን
ለሚደረግላቸው ማንኛውም ትብብር እናመሰግናለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አቶ ተሰማ ጫሚሶ
የቤተክርስቲንቱ ሽማግሌዎች ሰብሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ማስታወቂያ ለሥራ ፈላጊዎች


 የስራ ቦታ ካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
 የስራ ዓይነት የማታ ጥበቃ
 የትምህርት ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል የተማረ
 ቢያንስ ለሁለት ዓመት የጥበቃ ልምድ ያለው
 የቀበሌ መታወቂያ ያለው
 በቂ አድራሻና ሥራ ያለው ተያዥ ማቅረብ የሚችል
 ፆታ ወንድ ቢሆን ይመረጣል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 3 ቀናት ድረስ የቤተክርስቲያን ጽ/ቤት በመቅረብ ማመልከት
የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለአቶ ገመቺስ ተሾመ ተሲሳ


አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በሥራ ቦታ አለመገኘተዎን ስለማሳወቅ

ከጥቅምት ወር 2009 ዓም ጀምሮ የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የማታ ጥበቃ ሠራተኛ ሆነው መቀጠርዎ ይታወቃል፡፡ ሆኖም
ባላተወቀ ምክንያት ከ 16/02/2014 ዓም ጀምሮ በሥራ ቦታዎ አልተገኙም በመሆኑም ይህ ደብዳቤ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ በሁለት
ቀናት ልዩነት እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ድረስ ሪፓርት እንዲያደርጉ እያሳወቅን በተሰጠዎት የጊዜ ገደብ በሥራ ቦታ ካልተገኙ
ድርጅቱ በቦታዎ ሌለ የጥበቃ ሠራተኛ የሚቀጥር መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ከሠላምታ ጋር

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለከራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ለኢት-172 የልጆች ልማት ፕሮጀክት


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የተወከሉ የፕሮጀክት አባላትን ስለማሳወቅ ይሆናል፡፡

በ 09/01/14 በተደረገው የሽማግሌዎች ስብሰባ በ 12/12/2013 ዓም የአገልግሎት ጊዜ ለስድስት ዓመታት በማገልገል የጨረሱ
አባላት ምትክ የፕሮጀክት ልማት ከሚቴ አባላትን መርጣ ቤተክርስቲያን እንዲትመድብ በተጠየቀው መሠረት
1. አቶ ሳሙኤል ተክሉ የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች ተወካይ
2. ወ/ሮ መስከረም ከበደ ከቤተክርስቲያን አባላት ተወካይ
ሆነው ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት እንዲያገለግሉ የተመረጡ ስለሆነ መመሪያዎችን በማስተዋወቅ የአገልግሎት ሥልጠናዎችን
በመስጠትና ልምድ በማካፈል ልጆችን በሁለንተናዊ አገልግሎት የማሳደግ ሃላፊነትን በትጋና በሕብረት እንዲትወጡ ከታላቅ አደራ ጋር
እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ

ግልባጭ
ለካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጽ/ቤት
ለወ/ሮ መስከረም ከበደ
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ለኢት 172 የልጆች ልማት ፕሮጅት በኮሚቴ አባልነት እንዲያገለግሉ መመረጥዎን ስለማሳወቅ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

በ 09/01/14 በተደረገው የሽማግሌዎች ጉባኤ ስብሰባ አገልግሎት በጨረሱ የኮሚቴ አባላት ምትክ ከቤተክርስቲያን ተመርጠው
እንዲተኩ በ 12/12/2013 በፕሮጀክቱ አስተባባሪ በተጻፈ ደብዳቤ የተጠየቅን በመሆኑ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምጽ እርሶ
እንዲወከሉ ተመርጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በዚህ ትውልድ በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ የማሳደግ ተልዕኮ ጊዜዎን ዕውቀትዎንና ሌላ የሚጠበቅቦትን የሃላፊነት
አገልግሎት በቅንነት በታማኝነት በትጋት ከቤተክርስቲያንና ከእግዚአብሔር የተቀበሉትን አደራ እንዲወጡ ከታላቅ አደራ ጋር እናሳስባለን፡፡

አገልግሎትዎን ጌታ ይባርክ!

ተሰማ ጫሚሶ
የሽምግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ

ግልባጭ
ለካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጽ/ቤት
ለአቶ ሳሙኤል ተክሉ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ለኢቲ 172 የልጆች ልማት ፕሮጀክት የኮሚቴ አገልግሎት ከሽማግሌዎች ጉባኤ መወከልዎን ስለማሳወቅ፤
በ 09/01/14 በተደረገው የሽማግሌዎች ጉባኤ ስበሰባ አገልግሎት በጨረሰ የኮሚቴው የሽማግሌዎች ተወካይ ምትክ ሌላ የኮሚቴ አባል
እንዲተካ በቀን 12/12/2013 በፕሮጀክቱ አስተባባሪ በተጻፈ ደብዳቤ የተጠየቅን በመሆኑ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምፅ
እርሶ እንዲወከሉ ተመርጠዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በዚህ ትውልድን በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ የመሳደደግ ተልዕኮ ጊዜዎን ዕውቀቶንና ሌላ የሚጠበቅበትን የሃላፊነት
አገልግሎት በቅንነት በታማኝነትና በትጋት ከቤተክርስቲያንና ከእግዚአብሔር የተቀበሉትን አደራ እንዲወጡ ከታላቅ አደራ ጋር
እናሳስባለን፡፡
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

አገልግሎት ጌታ ይባርክ!

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ

ግልባጭ
ለካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጽ/ቤት
ለቦሌ አራብሳ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክስቲያ
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- መሻኛ ስለመስጠት ይሆናል፡፡

ወንድም ሰይድ የሱፍ የቤተክርስቲያናችን አባልና አገልጋይ በ 13/12/13 በፃፈው ደብዳቤ በመኖሪያ ቦታ ርቀት ምክንያት
በቤተክርስቲያን ማምለክም ሆነ ማገልገል አለመቻሉን በመግለጽ በአቅራቢያው ለምትገኘው ቤተክርስቲያናችሁ መሸኛ ደብዳቤ እንዲጻፍ
ጠይቋል፡፡
በዚሁ መሠረት ወ/ም ሰይድ የሱፍ ከ 2009 ጀምሮ የቤተክርስቲያናችን አባል ከመሆኑ በተጨማሪ በቃል ፕሮግራም በመምራትና
በፀሎት ከሚቴ መሪነት በታማኝነትና በትጋት ጌታን እያገለገለ የነበረ ወንድም መሆኑን እየገለጽን በእናንተም በኩል አስፈላጊውን
ትብብር ሁሉ እንዲደረግለት በጌታ ፍቅር እናሳስባለን፡፡

ጌታ አገልግሎታችሁን ይባርክ!

ተሰማ ጫሚሶ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ

ግልባጭ
ለካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ጽ/ቤት

ለዘፀአት የለውጥ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ/ሥ/ ማህበር


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የድጋፍ ደብዳቤ ስለመስጠጥ ይሆን፡፡


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ወ /ሪት ሩት መርጊያ በዘፀአት የለውጥ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ /ሥ/ ማህበር አባል ሆነው
ለመቆጠብ የድጋፍ ደብዳቤ እንድንጽፍላቸው በቀን 05- 12- 2013 ዓም በጻፉልን ደብዳቤ ጠይቀውናል፡፡

ስለሆነም ወ/ሪት ሩት መርጊያ የቤተክርስቲያናችን አባል እና ታማኝ አገልጋይ መሆናቸውን እየገለጽን በእናተ በኩል አስፈላጊውን
ትብብር ሁሉ እንዲደረግላቸው በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን፡፡
ከሰላምታ ጋር

አቶ ናስር ሻንቆ
የቤተክርስቲያንቱ የሽማግሌዎች ቦርድ ም/ሰቢሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለውልና ማስረጃ አገልግሎት ቢሮ


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ውክልና ስለመስጠት

የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ያላትን አነስተኛ ለንግድ ሥራ የሚሆኑ ቤቶችን ለማከራየት የአከራይ ተከራይ ውል
ቤተክርስቲያንቱን ወክላ እንድታስፈጽም የቤተክርስያናችን አባልና አገልጋይ እንዲሁም የሽማግሌ ቦርድ አባል የሆኑትን ወ /ሮ መስከረም
ውብሸትን የወከልናቸው መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለአዲስ አበባና አከባቢዋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ኅብረት ጽ/ቤት


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የመሪ አገልጋዮች ምርጫ ቀን ስለማሳወቅ

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በየሶስት ዓመቱ የሚደረገው (የሚካሄደው) የመሪ አገልጋዮች
ምርጫ በ 2013 ዓም የሚካሄድ መሆኑን ከኅብረቱ ጽሕፈት ቤት በደብዳቤ ተገልጾልና፡፡
በዚሁ መሰረት ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቅን በመሆኑ ከኅብረቱ ጽ /ቤት ተወካዮችን በመላክ ቀደም ብለን ባስያዝነው የጊዜ ሰለዳ መሰረት
ስኔ 13, 2013 ዓም ጠዋት በመገኘት ምርጫ እንድታስፈጽሙ በታላቅ ትህትና እንጠይቃን፡፡
ከመንፈሳዊ ሰላታ ጋር

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለአዲስ አበባና አከባቢዋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ኅብረት


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- መዘመራንን ስለመላክ፤

በ 13/05/2013 ዓም በተጻፈ ደብዳቤ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ብሔራዊ የወጣቶች አገልግሎት ክፍል ከአዲስ አበባ
አጥቢያ ቤተክርሰቲያናት ህብረት ጋር በመተባበር የኅብረት መዘመራን ለማደራጀት ዝግጅት ላይ ስለሚገኝ ለሚቋቋመው የመዘመራን
አገልግሎት አባል የሚሆኑ መስፈርትን የሚያሟሉ ሁለት መዘመራን እንድንልክ በተጠየቅነው መሠረት በኳይርና በአምልኮ ዝማሬ መሪነት
በታማኝነት አገልጋዮች የሆኑን
1. ልደት ታቦሬ እና
2. የሰፍ ገዛኽኝን የላክን መሆኑን እየገለጽን ለሚደረግላቸው ትብብር ሁሉ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

ጌታ አገልግሎታችሁን ይባርክ!

ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ጉባዔ ሰብሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለኢትዮጵያ ኒው ሚሌኒየም 2000 ፕሬየር ቼይን

ጉዳዩ፡- በአርባ ቀናት ፆም ፀሎት እንድሳተፉ የላክናቸውን ሰዎች ስለማሳወቅ ይሆናል፡፡

በቅድምያ የከበረውን መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው በቀን
3/5/2013 ዓም በተጻፈልን ድብዳቤ መሠረት ከዚህ በታች በስም የተጠቀሱ ግለሰቦች ከቤተክርስቲንቱ ጋር ጤናማ
ግንኙነት ያላቸው እና ታማኝ አገልጋዮች መሆናቸውን እየገለጽን በጸሎቱ ቢሳተፉ ለቤተክርስቲናችን እና ለሃገር
በረከት የሚያመጡ መሆናቸው ስለታመነበት በጾም ፀሎት እንዲሳተፉ ቤተክርስንቱ ፈቅዳለች፡፡

1. ወ/ዊት ወርቅነሽ ረጂ
2. ወ/ዊ ዳልጌ ዳንቻ
3. ወ/ሮ ሙሉ ላቀው
4. ወ/ሮ ትንሳኤ ተረዳ
5. ወ/ሮ ታደለች አሰፋ
6. ወ/ሮ ጀንበሬ ናስር
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

7. ወ/ሮ እተነሽ ንጉሱ


8. ወ/ሮ ሸግቱ ፍልታ
9. ወ/ሮ ለምለም አበራ

ከሠላምታ ጋር
አቶ ተሰማ ጫሚሶ

የቤተክርቲያንቱ አስተዳር ሽማግሌዎች ቦርድ ሰብሳቢሰ


ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ኣዋሽ ባንክ አባዶ


መስቀለኛ ቅርንጫፍ
የመ.ሳ.ቁ 12638
አዲስ አበባ

ጉዳዩ ፡- የመሥርያ ቤታችን ሠራተኛ መሆናቸውን ስለመግልጽ ይሆናል፡፡

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ወ/ዊ ዳልጌ ዳንቻ በቀን2/6/2013 ዓ.ም በጠየቁት
ደብዳቤ ዋስ ለመሆን ለዮሰፍ ጽግረዳ እና ጓደኞቻቸው የዳልጋ ከብት ማልማት ህ/ሽ/ማህበር የወር
ደሞዛቸው ተጠቅሶ እንድንጽፍላቸው ጠይቀውናል፡፡

በዚህም መሠረት ሠራተኛችን በወር 4517/ አራት ሺህ አምስት መቶ አሥራ ሰባት ብር ከፈላቸው
እንዲሁም የመንግሥት የሥራ ግብር የሚከፍሉ በመሆናቸው ዋስ መሆን የሚችሉ መሆቸውን እና
ግለሰቡ መሥሪያ ቤታችንን ሲለቁ የምንገልጽላችሁ መሆኑን በትህትና እንገልጽላችኋለን፡፡

ከሠላምታ ጋር
አቶ ናስር ሻንቆ

የቤተክርስቲያንቱ የሽማግሌዎች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ለአንድኛ ሶሳ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን


ሙዱላ፡-

ከሁሉ በማስቀደም የከበረውን ሰላምታችንን እያቀረብን ወንድም መሀሩ ብርሃኑ በ 27/03/2013


ዓም በጻፈው ማመልከቻ በዚህ ዓመት ከ/ወሪት መድኃኒት አበበ ጋር በትዳር ለመጣመር
መስመማታቸውን ገልጾ የጋብቻ ትምህርት ለመማር እና የጋብቻ ሥርዓትም ለመፈጸም ወደ
ቤተክስቲያናችሁ እንደሚሄድ በመግለጽ የትብብር ደብዳቤ እንዲጻፍለት ጠይቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ወንድም መሀሩ ብርሃኑ የቤተክርስቲያናችን አባል እና በ‹‹ሀ ›› ኳይር አገልጋይ
መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የጋብቻ ትምህርት ተስጥቷቸው በቤተክርስቲያን ሥርዓት መሰረት
ጋብቻቸውን እንዲፈጽሙ በእናንተ በኩል አስፈላጊው ትብብር ሁሉ እንድታደርጉ እየጠየቅን
በመጨረሻም ውጤቱን በደብዳቤ እንድታሳውቁን እናሳስባለን፡፡

ጌታ አገልግሎታችሁን ይባርካችሁ
አቶ ተሰማ ጫሚሶ

የቤተክርስቲያንቱ የሽማግሌዎች ቦርድ ሰብሳቢ


ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

በኢትጵያ ንግድ ባንክ ለገጂዳ ቅርንጫፍ


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የባንክ ፈራሚ ስለመቀየር ይሆናል፤


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገጂዳ ቅርንጫፍ ላላት የቁጠባና
ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ፈራሚ በነበሩት በአቶ ዲታ ዱሜ ምትክ አቶ አበራ መስቀሎ አንዲሆኑ የተወሰነ
ስለሆነ ይህ ታውቆ ተግባራዊ አንዲደረግ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አቶ ተሰማ ጫሚሶ
የሽማግሌዎች ቦርድ ሰቢሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለሚመለከተው ሁሉ

ካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶችም ሆነ በህብረተሰቡ ዘንድ


ለሚኖራት ጉዳይ እንዲሁም የእዳ እገዳ፣ የፕላን ስምምነትንና የግንባታ ፈቃድ በኃላፊነት
እንዲያስጨርሱ የቤተክርስያኒቱ ሽማግሌዎች ቦርድ አባል የሆኑትን አቶ ኃይሉ ዳራጎን ጉዳዩን
እንዲያስፈጽሙ የወከልናቸው መሆኑን በታላቅ ትህትና እናሳውቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አቶ ናስር ሻንቆ
የሽማግለዎች ቦርድ /ሰብሳቢ

ግልባጭ፣
ለአቶ ኃይሉ ዳራጎ
አዲስ አበባ

ለሚመለከተው ሁሉ

ጉዳዩ፡- የኤች አይ ቪ ምርመራ ውጤት አሽጋችሁ እንድትሰጡን ይሆናል፡፡

ከሁሉ በማስቀደም የከበረውን ሰላምታችንን እያቀረብን ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው


የቤተክርስቲያናችን አባላት የሆኑት አቶ ታምራት ማኖ እና ወ/ሪት እመቤት አሰፋ ጋብቻቸው
ሥነ-ሥርዓት ለሚፈጸመው የተስማሙ ስለሆነ ቤተክርስቲያንቱ ይህንን መንፈሳዊ ሥርዓት
ለመፈጸም የኤች አይ ቪ ምርመራ ውጤት ስለሚያስፈልጋት የምርመራ ውጤታቸውን በፖስታ
አሽጋችሁ እንድትሰጡን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ ስለምታደርጉልንን መልካም ትብብር ሁሉ ከልብ
እንመሰግለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
አቶ ናስር ሻንቆ
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

የቤተክርስቲያንቱ ም/ሰብሳቢ

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገጂዳ ቅርጫፍ


ጉዳዩ፡- የቦንድ ግዥ ይመለከታል
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ቤተክርስቲያናችን የአምስት ሺህ (5000) ብር ቦንድ ለመግዛት የወሰነች በመሆኑ ግዥው
በወ/ሮ ሙሉነሽ ላቀው አማካኝነት እንዲፈጸም የወሰንን በመሆኑ በእናንተ በኩል አስፈላጊው ትብብር ሁሉ እንዲደረግ በትህትና
እንጠይቃለን፡፡
ከመንፈሳዊ ሠላምታ ጋር
አቶ ተስፋዬ ሽጉጠ

የሽማግለዎች ቦርድ ጻሐፊ


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

በየካ ክፈለ ከተማ ለወረዳ 12 ገቢዎች ጽ/ቤት

ጉዳዩ፡- የሠራተኞች የሥራ ግብርና ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ክፍያ ይመለከታል፡፡

የቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ማንኛውንም ግልጋሎት የሚያገኙት


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሥራ ፈቃድ እና ግብር መክፈያ
ሲሆን የአገር ውስጥ ገቢ ከ 2012 ዓም ጀምሮ የግብር መቀበያ አሠራሩን የለወጠ
በመሆኑና የተለወጠው አሠራር ደግሞ ሁሉንም አጥቢያዎችን ማስተናገድ ባለመቻሉ
አገር ውስጥ ገቢዎችን ስናናግር ለጊዜው የሰጡን ሃሳብ ጉዳዩ እስከሚስተካከል
ድረስ አጥቢያዎች ባሉበት ወረዳ እንዲከፍሉ ብታደርጉ የሚል ስለሆነ የቃለ ሕይወት
ዋና ጽ/ቤት ያለንበትን ወረዳ በደብዳቤ በመጠየቅ መክፈል እንዲንችል በደብዳቤ
ያሳሰበን በመሆኑ አጥቢያ ቤተክርስቲያናችን የሥራ ግብርና ዊዝ ሆልድንግ በወረዳ
12 ገቢዎች ጽ/ቤት ክፍል መክፈል እንድትችል እንዲመቻችልን በታላቅ
ትህትና እንጠይቃለ፡፡

ከሠላምታ ጋር

አቶ ናስር ሻንቆ
የቤተክርስቲያንቱ ም/ሰብሳቢ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳዳር ገቢዎች በለስልጣን ለየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች
ቅርጫፎች ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ትብብር ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡


የካራ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሠራተኛ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተሾሜ ግብር ከፋይ ስለሆኑ
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ለማወጣት አሻራ በመቀበል እንድትተባበሩ በትህትና
እንጠይቃለን፡
ከሠላምታ ጋር
አቶ ናስር ሻንቆ

የቤ/ክ ሽማግለዎች ም/ሰብሳቢ


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

/ / /
ለኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ የተ የግ ማህበር

አዲስ አበባ

የመሥሪያ ቤታችን ሠራተኛ የሆኑት አቶ ገመቺስ ተሾመ ለወሮ ገላኔ ዳኜ ዋስ መሆን እንዲችሉ ደሞዛቸው ተገልጾ
እንዲጻፍላቸው በቀን 15/1/2013 ዓም በማመልከቻ ጠይቀውናል፡፡ በመሆኑም ከላይ በስም የተጠቀሰው ግለሰብ 1150 (አንድ
ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ) ብር በወር የሚከፈላቸው የመሥሪያ ቤታችን ቋሚ ሠራኛ መሆናቸውን እየገለጽን ሠራተኛው በተለያዩ
ምክንያቶች ሥራ ቢለቁ ለድርጅታችሁ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጽላቸዋለን፡፡

ከሰላምታ ጋር
አቶ ናስር ሻንቆ

የሽማግሌዎች ቦርድ ም/ሰብሳቢ


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

ቀን ………………….

/ // /
ለካራ ቃ ሕ አ ቤ ን
አዲስ አበባ

ከሁሉ በማስቀደም የከበረውን ሰላምታ እያቀረብኩ እኔ አቶ ገመችስ ተሾሜ ለባለቤተ ገላኔ ዳኜው ዋስ ለመሆን ስለሚፈልግ
ቤተክርስቲያንቱ የደሞዝ መጠን ጠቅሳ ለኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ /የተ/የግ/ማህበር የድጋፍ ደብዳቤ እንድትጽፍልኝ በትህትና
አጠይቃለሁ፡፡

ከሠላምታ ጋር
አቶ ገመችስ ተሾሜ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቀን-------------------------
ቁጥር-----------------------

ለኤም & ኤስ ቡትክ


ጉዳዩ ፡- የመሥሪያ ቤታችን ሠራተኛ መሆናቸውን ስለመግለጽ ይሆናል፡፡

ከሁሉ አስቀድመን የከበረውን ሰላምታችንን እያቀረብን ወ/ዊ አስፈራቸው ጳውሎስ በወር 5000 ብር የሚከፈላቸው
የቤተክርስቲያናችን ቋሚ እና ታማኝ ሠራተኛ እንዲሁም የሠራተኛ ግብር ለመንግሥት የሚከፍሉ በመሆናቸው ተያዥ ለመሆን
የሚችሉ መሆናቸውን እና ሠራተኛው መሥሪያ ቤቱን በሚለቁበት ጊዜ እንደምናሳውቃችሁ በትህትና እንገልጽላችኋለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

አቶ ናስር ሻንቆ

ለገርጂ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ የድጋፍ ደብዳቤ ስለመስጠት

የቤተክርስቲያናችን አባላት የሆኑት ወጣት ኢያሱ አለሙና ውጣት ቃልኪዳን ወዬሳ


በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምስራቅ አዲስ አበባ የካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
KARA KALE HEYWET CHURCH
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

ቁጥር------------------
ቀን---------------------

በቤተክርስቲያናችሁ የቃልኪዳን ስርአት ለመፈፀም የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው

በ 01/05/15 በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ወጣቶቹ የቤተክርስቲያናችን ታማኝና ታዛዥ አገልጋዮች ከመሆናቸው
በተጨማሪ በክርስትናዊ ጋብቻ ለመጣመር መተጫጨታቸውን በመግለፅ ለቤተክርስቲያኒቱ ሽማግሌዎች ቦርድ አሳውቀው
አስተማሪ ተመድቦላቸው እየተማሩ ያሉ እጅግ የምንወዳቸውና የምናከብራቸው ወጣቶች መሆናቸውን እየገለፅን ለሚደረግላቸው
ትብብር በሙሉ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

ጌታ አገልግሎታችሁን ይባርክ!!

ተሰማ ጫሚሶ

የሽማግሌዎች ጉባኤ ሰብሳቢ

You might also like