You are on page 1of 94

የህይወት ክህሎት ስልጠና

ጥር/2005ዓ.ም

ደረጀ ካህሳይ
በስልጠናው የሚካተቱ
ተ.ቁ አርዕስት

1 ግንኙነትን መመሥረት

2 የተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ

3 የተሳታፊዎች ደንቦች

4 በቡድን መሥራት

5 የህይወት ክህሎት ምንነትና ዓላማዎች

6 የህይወት ክህሎት ትምህርት መርሆዎች

7 የክህሎት ዓይነቶች

8 የህይወት ክህሎት ትምህርት ጥቅሞች

9 እሴቶች

10 ሥነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎት


10.1 ራስን ማወቅና እራስን ከማወቅ ጋር የተዛመዱ ክህሎት
10.2 ራስን ማወቅ
10.3 ራስን መገምገም
10.4 ግብ ማስቀመጥ
10.5 አድናቆታዊ ጥያቄዎች
10.6 ስሜትን የመቆጣጠር ክህሎት
10.7 ሥነ ልቦናዊ ጫናን መቋቋም
11 ማህበራዊ ክሕሎት
ተ.ቁ አርዕስት

11.1 ውጤታማ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ

11.2 በጥሞና ማድመጥ

11.3 ልበ ሙሉነት ፣ ለዘብተኝነትና ሞገደኛነት

11.4 የአቻ ግፊትን መለየትና መቋቋም

11.5 ግጭትን መፍታት

11.6 አሳቢነት ወይም ሀዘኔታ

11.7 መደራደር

12 የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎት

12.1 በጥልቀት ማሰብ

12.2 አዲስ ነገርን ለመፍጠር የሚያስችል አስተሳሰብ

12.3 ችግሮችን መፍታት

12.4 ውሣኔ የመስጠት


1. ግንኙነት መመስረት
1.1 ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ
ዓላማ፣
 ተሳታፊዎችና አመቻቾች እርስ በርስ እንዲተዋወቁና በውይይቱ ሂደት ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ
ነው፡፡

የሥልጠና ዘዴ
 በጣምራ ውይይትና በመድረክ ገለፃ
 የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ካርዶች፣ ደብተርና እስክሪብቶ

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 አመቻቾች እያንዳንዱ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ከማያውቀው ሰው ጋር ሁለት ሁለት ሆነው እንዲቀመጡ ይጠይቃሉ፡፡
ሁለት ሁለት ሆነው የተጣመሩትን ሰዎች
 ስማቸውን
 የመጡበትን አካባቢና የሥራ ድርሻ
 ጠንካራ ጐኖች /ስለራሳቸው የሚወዱትን ነገር/
 በአውደ ጥናቱ ወቅት ሊጠሩበት የሚፈልጉትን ስም ይጠያየቃሉ፣
 እነዚህን መረጃዎች ከተለዋወጡ በኋላ እያንዳንዱ ሰው አብሮት ያለውን/ ያላችውን ሰው ለጉባኤው ያስተዋውቃሉ፡፡
 በተዘጋጁት ቁርጥራጭ ካርዶች ላይ ስማቸውን በመጻፍ ደረታቸው ላይ ይለጥፋሉ፡፡
1.2 የተሳታፊዎች ደንቦች
ዓላማዎች
 ተሳታፊዎች በአውደ ጥናቱ ወቅት ሊከበሩ የሚፈልጓቸውን ሕግጋትና ተገቢ አካሄዶች ጊዜ
ወስደው በአንክሮ እንዲያስቡባችው ማድረግ ፣
 በአውደ ጥናቱ ወቅት ሊደነገጉና ሊከበሩ የሚገባቸው ሕጐች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ፣
 ተሳታፊዎች ለሚያሳዩአችው ምግባሮችና ለሚፈጽሟቸው ማንኛውም ዓይነት ድርጊ ድርጊቶች
የርስበርስ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችሉ ደንቦች ላይ መስማማት ፣

የሥልጠና ዘዴ፣
 የቡድን ውይይት፣
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣


 አመቻቾች በሥልጠና ወቅት የርስበርስ መከባበር መንፈስ ይሰፍን ዘንድ ሰዎች ድርጊታቸውንና
ባህሪያቸውን በሥርዓት መቃኘት የሚችሉባቸው መንገዶች ላይ የመሰማማት አስፈላጊነት ላይ
ከተሳታፊዎች ጋር መወያየት፣
…የቀጠለ

 ደንቦችና ሕግጋት በሰዕል መልክ እንዲቀርቡ በማስረዳት ምሳሌ ሰጥ /ለምሳሌ


በወርክሾፑ ጊዜ ሰዎች ማጤስ እንደማይኖርባቸው ለማስገንዘብ የሲጋራ ስዕል በመሳል
ላዩ ላይ የx ምልክት አኑርበት/ ፣
 ተሳታፊዎች በቡድኖች ይደራጁ፣
 ለያንዳንዱ ቡድን ወረቀትና ስዕል መንደፍ የሚችሉባቸው ማርከሮች መስጠት ፣
 ቡድኖቹ በአንድነት ሲሰበሰቡ እያንዳንዱ ቡድን ስዕሎቻቸውን እንዲያሳዩና ሊከበሩ
የሚፈልጓቸውን ሕጐች እንዲያብራሩ መጠየቅ፣
 ሌላኛው ቡድን ተመሳሳይ ስዕል ስሎ ከሆነ ከተሳታፊዎች ጋር ሆኖ የትኛው ስዕል
እንደሚሻል ተነጋግሮ መወሰን፣
 በቀረቡት ደንቦች ላይ ስምምነት ከደረሳችሁ በኋላ ስዕሉን ግድግዳ ላይ መለጠፍ፣
 ተሳታፊዎች፣ ሕጐች ሳይከበሩ ሲቀሩ ሕጉን የማስታወስ ኃላፊነት የሚኖረው የፍትህ
ሚኒስትር ምረጡ፡፡ ምናልባትም ጊዜ ጠባቂ መሾምና ይህን ኃላፊነት ለተለያዩ
ተሳታፊዎች በዑደት ማሸጋገርም ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ክፍለ
ጊዜውን ማጠቃለል፣
1.3 በቡድን መሥራት
ዓላማ
 ተሳታፊዎች የህይወት ክህሎቶችን ለማዳበር በጋራ መሥራት ወሳኝ መሆኑን እንዲረዱና
እንዲተገብሩት ለማስቻል ነው፡፡
የሥልጠና ዘዴ፣
 በጥሞና ማሰብና የቡድን ሥራ

የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት


 ተሳታፊዎችን በቡድን መክፈል
 ለእያንዳንዱ ቡድን ፍሊፕ ቻርት ወረቀት እና ማርከር መስጠት ፣
 እያንዳንዱ የቡድን አባል በግሉ በሚቀጥሉት 3 ደቂቃዎች ውስጥ መሳል የሚፈልገውን እንስሳ
በአእምሮው እንዲያስብ ማድረግ፣
የአመቻቾች ማስታወሻ፣ የሥልጠና ሥልቶች

የቡድን ሥራዎች
 የቡድን ሥራዎች የሚከናወኑት ተሳታፊዎችን አነስተኛ ቁጥር ወደ ያዙ ትንንሽ ቡድኖች በመክፈል
በተሰጣቸው ሃሳብ ላይ እንዲወያዩና የጋራ ሃሳባቸውን በአቅርቦት መልክ ወይም ደግሞ
በጭውውቶችና በድራማዎች መልክ አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው፡፡ የቡድን ሥራዎች
የሥልጠና ሂደቱን ይበልጥ አሳታፊ ለማድረግና ሁሉም ተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ
ለማገዝ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
በግል የሚከናወኑ ሥራዎች
 በሥልጠናው ሂደት ተሳታፊዎች በህይወት ክህሎት ዙሪያ ጠለቅ ብለው እንዲያስቡና
ከገጠመኞቻቸው ጋር እንዲያገናዝቡ ለማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ለተሳታፊዎች በግል የሚከናወን
ሥራ ይሰጣል፡፡
አጫጭር ድራማዎች
 አመቻቹ በመመሪያው ውስጥ በተለያዩ ርዕስ ጉዳዬች ዙሪያ የተቀመጡ ታሪኮች በተሳታፊዎች
በድራማ መልክ ተዘጋጅተው እንዲቀርቡ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ከተነሣው
ሃሳብ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ታሪኮችን መሠረት በማድረግ ከአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ
በመነሳት ተሳታፊዎች አጫጭር ድራማዎችን እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፡፡
ስዕሎች
 አመቻቹ ከሥልጠና በፊት ጠቃሚ መልዕክቶችን በስዕል መልክ ለማስተላለፍ
የተለያዩ ሥዕሎችን እንደየአስፈላጊነቱ ያስባስባል ይጠቀማል፡፡ ከዚያ
በተጨማሪም ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን በስዕል መልክ እንዲገልጹ ያደርጋል፡፡
ትረካ
 አንድ ሃሳብ ለተሳታፊዎች በቀላሉ ሊገባ በሚችል እና አዝናኝ በሆነ መልኩ
ለማስተላለፍ በአካባቢው የተፈፀመውን ነገር ወይም ሊፈፀም የሚችል እውነታን
በትረካ መልክ ይቀርባል፡፡ ይህም አስቀድሞ ታሳቦ በጥንቃቄ የሚዘጋጅ ነገር
ይሆናል፡፡
ጥያቄዎች
 ተሳታፊዎችን ሊያመራምሩ የሚችለና በርካታ ምላሾችን ሊያስከትሉ የሚችሉ
ጥያቄዎችን በየርዕሰ ጉዳዬቹ ላይ በማንሳትና ለሁሉም ተሳታፊዎች ለውይይት
በማቅረብ ይከናወናል፡፡
ጨዋታዎች
 ጠቃሚ መልዕክት ያላቸውንና ተሳታፊዎችን እያዝናኑ ሊያስተምሩ የሚችሉ ቀልዶችና
ጨዋታዎችን በየመሀሉና በየርዕሰ ጉዳዬቹ ሥር ጣልቃ በማስገባት ይከናወናል፡፡
መዝሙርና ግጥሞች
 መዝሙሮችና ግጥሞች አጠር ባለ መልኩ ግልጽና አዝናኝ የሆኑ መልዕክቶችን
ለማስተላለፍ ይጠቅማሉ፡፡ ይህም ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት ተሳታፊዎች
በቀላሉ እንዲይዙትና እንዲያስታውሱት ያግዛል፡፡
 በተለይ ዕድሜያቸው ከ5-13 የሆኑ ተሳታፊዎችን ለመድረስ ይበልጥ እንጠቀማለን፡፡
ክርክር
 ተሳታፊዎችን በቡድን በመክፈል በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ጎራ ለይተው
እንዲከራከሩ ማድረግ በሂደቱም ላይ አመቻቹ ሥነሥርዓት በማስከበርና መደማመጥ
እንዲኖር ያደርጋል፤ ተከራካሪዎች ለሚያነሷቸው የክርክር ሃሳቦች ነጥብ በመስጠት
አሸናፊውን ወገን በመለየት ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት ይቋጫል፡፡
…የቀጠለ
 ቀጥሎ የቡድን አባላት እርስ በርስ ሳይነጋገሩ በዝምታ ሆነው ማርከሩን በመቀባበል
የሚያስቡትን እንስሳ መሳል እንዲጀምሩ ማድረግ
 የሚሳለው ስእል አንድ ብቻ መሆኑን መግለጽ እና ለዚህም የቡድን አባላት ያለውን
ማርከር ተራ በተራ እየተቀባበሉና አንዱ ከቆመበት ስፍራ /በመስመር በመቀጠል
ስእሉን እንዲያጠናቅቁ ማድረግ፡፡
 በመቀጠልም በፊሊፕ ቻርቱ በሌላኛው ጐን በጋራ ተነጋግረውና ተስማምተው
የመረጡትን አንድ የእንስሳ ሥዕል በወኪላቸው አማካኝነት ይሥላሉ፡፡
 ተሳታፊዎች በቡድን የሳሉትን እንስሳ ስም እንዲሰጡ እና በግድግዳ ላይ
እንዲለጥፉት ማድረግ
 በመጨረሻም በቡድን ደረጃ የተሰራውን ሥራ ለጠቅላላው አባላት ማቅረብ፣
/የመወያያ ጥያቄዎች፣ ምን ተሰማችሁ ?/
 አመቻቹ ሂደቱን በጋራ ከመሥራት ጋር ያለው ተዛምዶ በማብራራት በቀጣዩ ሂደት
የህይወት ክህሎትን ለማዳበር በጋራ እንዲቆሙ በማስታወስ ክፍለ ጊዜውን
ያጠቃልላል
የህይወት ክህሎት ምንነትና ዓላማዎች፣
ዓላማ፣
 ተሳታፊዎች የህይወት ክህሎትን ትርጉምና ዓላማዎች ይረዳሉ
የሥልጠና ዘዴ፣
 ጥያቄና መልስ

የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣


 አመቻቾች ተሳታፊዎቹ ተራ በራራ የየግል ክህሎቶቻቸውን እንዲናገሩ በማድረግ መልሶቻቸውን በፊሊፕ
ቻርት ላይ ይጽፋሉ፤
 ተሳታፊዎቹ ክህሎቶቻቸውን እንዴት ሊያገኙና ሊያዳብሩ እንደቻሉ እየጠየቁ ሀሳባቸውን ይጽፋሉ፤
 ተሳታፊዎቹ ክህሎቶቻቸውን እንዴት የራሳቸውና የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታትና ለኑሮአቸው
መጠቀሚያ እንዳዋሏቸው ይጠይቃሉ/
 በተሳታፊዎቹ ሃሳብ ላይ ተመስርቶ የውይይቱን ሃሳብ በማጠናከርና የአመቻቾች ማስታወሻን በመጠቀም ክፍለ
ትምህርቱን ያጠናቅቃሉ፡፡
የህይወት ክህሎት
የህይወት ክህሎት ሰዎች ለዕለት ተዕለት ኑሮአቸው የሚያስፈልጋቸውን
ፍላጐት ለማሟላትና የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች በአዎንታዊ መልኩ
ለመፍታት የሚጠቀሙበት አቅምና ብቃት ነው፡፡
የህይወት ክህሎት የሰውን ልጅ ባህሪ በመለወጥና በማሳደግ ላይ መሠረት
ያደረገ ልምምድና ተከታታይ ትምህርት በመስጠት የሚገኙ ሲሆን ሂደቱ
ዕውቀትን፣ አመለካከትንና ክህሎትን በተመጣጠነ ሁኔታ በማሳደግ ላይ
ያተኩራል፡፡
የህይወት ክህሎት ሊዳብሩና ሊያድጉ ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል፡፡
የዕለት ከዕለት የማህበረሰብ የአኗኗር ዘዴዎች ፣
የህይወት ገጠመኞች ፣
በአንድ ተግባር ላይ ደጋግሞ በመሳተፍ፣
ተከታታይ የሆነ ሥልጠናና ትምህርት ናቸው፡፡
የህይወት ክህሎት ትምህርት ዓላማዎች፣

 ወጣቶች እራሳቸውንም ሆነ ማህበረሰባቸውን በተገቢው መንገድ ተገንዝበው


ጤናማ ህይወት ለመኖር የሚያስችላቸውን እውቀትና ችሎታ ማስረጽ፣
 አዎንታዊና ውጤታማ የሆኑ አማራጮችን በመውሰድ ጤናማ እና በጐ
ባሕሪያትን እንዲያዳብሩ ማድረግ፣
 በመረጃ፣ በዕውቀትና በክህሎት ላይ መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን የመወሰን
ብቃት እንዲያዳብሩ ማድረግ፣
 በሕይወት የሚያጋጥሙ የተለያዩ ፈተናዎችንና ለአደጋ የሚያጋልጡ ጐጂ
ባህሪያትን ለይተው በማወቅ ችግሮችን ለማስወገድ የሚጠቅም ዕውቀት
ክህሎት ማስጨበጥ፣
 ወጣቶች እራሳቸውን ከኤች አይ ቪ /ኤድስ ለመከላከል እንዲችሉ በቂ
እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ ማድረግ፣
የህይወት ክህሎት ትምህርት መርሆዎች
ዓላማ
 ተሣታፊዎች የህይወት ክህሎት ትምህርትን ዓላማ ተረድተው በተግባር እንዲተገብሩት ማድረግ
ነው፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
 ጥያቄዎችን በማቅረብ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች፣
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት


 በማስታወሻ ስር የተዘረዘሩትን የህይወት ክህሎት ትምህርት መርሆዎች አንድ በአንድ በፊሊፕ
ቻርት ላይ በመፃፍ ተሣታፊዎች እንዲወያዩባቸው መጠይቅ፣
 ተሣታፊዎች በመርሆዎቹ ላይ መስማማታቸው ይጠየቁ፣
 ሁሉም ስለመስማማታቸው እርግጠኛ መሆናቸውን ሲያውቁ ፊሊፕ ቻርቱን ጠረጴዛ ላይ
አንጥፈው የጋራ መርህ መሆኑን ለመግለጽ የክብር ፊርማቸውን እንዲያኖሩበት በማድረግ
ለሁሉም በሚታይበት ሥፍራ ይለጠፍ፡፡
የህይወት ክህሎት ትምህርት መርሆዎች
አሳታፊነት
 ተሳታፊነትን የማበረታታት፣ የመደማመጥ፣ የሌሎችን አመለካከት
የማክበርና በመግባባት ሀሳብን የመግለጽነፃነትን ማረጋገጥ፣
በጐ ፈቃደኝነት፣
 የህይወት ክህሎትን ሥልጠና የሚከታተል ወጣት /ግለሰብ ክህሎቱን
በብቃት ለመጨበጥ ሙሉ ፍላጐት ያለውናፈቃደኛ መሆን ይገባዋል፡፡
ሥርዓተ ፆታ ተኮርነት፣
 ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ በሚደርስባቸው የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣
ማህበራዊና ባህላዊ ተጽዕኖዎች የተነሳከወንዶች የበለጠ ለተለያዩ ችግሮች
የተጋለጡ ናቸው፡፡ ስለሆነም የሚደርስባቸውን ችግሮች
ለመቋቋምናእራሳቸውን እንዲከላከሉ ለማድረግ የሕይወት ክህሎት
ትምህረት ስርዓተ ፆታ ተኮርነት ባህርይ ያለው መሆንይገባዋል፡፡
ባህርይ ተኮርነት፣
ከተለያዩ አደገኛና ጐጂ የህይወት ልምዶች ማላቀቅ የሚቻለው በተለያዩ
የማስተማሪያ ስልቶች በመጠቀም የባህሪለውጥ ማምጣት ሲቻል ነው፡፡
ስለሆነም የህይወት ክህሎት ትምህርት አሰጣጥ በባህርይ ለውጥ ላይ
ያተኮረመሆን አለበት፡፡
የማህበረሰብ እሴቶችን መሠረት ማድረግ፣
ማህበረሰቡ ለኑሮውና ለህይወቱ ጠቃሚና ይበጃሉ ያላቸውን እሴቶች
ተገንዝቦ በእነዚህ እሴቶች ላይ የተመሠረቱክህሉቶችን ማዳበር፡፡
የክህሎት ዓይነቶች

ዓላማ፣
 የህይወት ክህሎት አይነቶችን ይረዳሉ ፣ ያስረዳሉ
የሥልጠና ዘዴ፣
 ጥያቄና መል
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች፣
 ካርዶች፣ ፈሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 አመቻቾች በርካታ ካርዶች በማዘጋጀት ለተሳታፊዎቹ ያከፋፍላሉ፣
 ተሳታፊዎች በተረዱት የሕይወት ክህሉት ትርጉም ላይ በመመስረት እያንዳንዳቸው አንድ ክህሎት ብቻ በአንድ
ካርድ ላይ እንዲጽፋ ያደርጋሉ / ከአንድ በላይ ክህሎት የሚጽፍ ካለ ተጨማሪ ካርድ መጠቀም ይችላል/፡፡
 ተሳታፊዎቹ የክህሎት ዓይነቶችን ከጻፋ በኋላ አመቻቾች አመቺ ቦት መርጠው ለሁሉም በሚሰማ መልኩ
እያነበቡ እንዲያስቀምጡ ወየም እንዲለጥፋ ያደርጋሉ፡፡
 አመቻቾች የክህሎት ዓይነቶች ተብለው በተሳታፊዎች የቀረቡት ዝርዝርሮች ክህሎት መሆን አለመሆናቸውን
እንዲነጋገሩና ክህሉት ያልሆኑትን ለይተው እንዲያወጡ ወይም ክህሎት በመሆናቸው እንዲስማሙ ያደርጋሉ፡፡
 ክህሎቶቹን በምድብ ከለዩ በኋላ የአመዳደብ መስፈርቶቻቸውን እንዲገልጹ ይጠይቋቸዋል፡፡
…የቀጠለ

 አመቻቾች መስፈርቶቻቸውን ካዳመጡ በኋላ ቀድሞ በፊሊፕ ቻርት ላይ ጽፈው ያዘጋÍቸውን አራት ዋና
ዋና የክህሎት ምድቦችን በግድግዳ ላይ ይለጥፋሉ፡፡
 አመቻቾች ተሳታፊዎቹ ቀደም ብለው በተለያዩ ምድቦች ያስቀመጧቸው የክህሎት ዓይነቶች በአራቱ ዋና ዋና
ክህሎት ሥር አቀናጅተው እንዲያስቀምጡ ያደርጋሉ፡፡
 ተሳታፊዎቹ አጨቃጫቂ የሆኑና የት እንደሚመድቧቸው ግራ ያጋቦቸውን የክህሎቶች ዓይነቶች ለብቻ
እንዲያስቀምጡ ያደርጋል፡፡
 አመቻቾች የአራቱን ዋና ዋና የክህሎት ምድቦች ትርጉም በምሳሌ እያስደገፈ ለተሳታፊዎቹ ያስረዳል፡፡
 አመቻቾች ተሳታፊዎቹ ቀደም ብለው በአራቱ ዋና ዋና የክህሎት ምድቦች ሥር የተደለደሉትንና ለምደባ
የተቸገሩባቸውን ክህሎት እንደገና እንዲያዩና ምናልባት የምድብ ቦታ ያላገኙላቸውን ወይም ምድባቸው
መለወጥ አለበት ብለው ያሰቧቸውን እንዲያስተካክሉ ያደርጋሉ፡፡
 አመቻቾች ለምደባ የተቸገሩባቸውን ክህሎት በማመልከት ለምን ለመመደብ እንደተቸገሩ ይጠይቋቸዋል፡፡
 አመቻቾች ምክንያታቸውን ከሰማ በኋላ አራቱ ዋና ዋና የክህሎት ምድቦች እርስ በእርሳቸው ያላቸውን
ተያያዥነት ያስረዳሉ ፡፡
 አመቻቾች ተሳታፊዎቹ ቀደም ብለው በአራቱ ዋና ዋና የክህሎት ምድቦች ሥር የተደለደሉትንና ለምደባ
የተቸገሩባቸውን ክህሎት እንደገና እንዲያዩና ምናልባት የምድብ ቦታ ያላገኙላቸው ወይም ምድባቸው
መለወጥ አለበት ብለው ያስቧቸውን እንዲያስተካክሉ ያደርጋሉ፡፡
 አመቻቾች ለምደባ የተቸገሩባቸውን ክህሎት በማመልከት ለምን ለመመደብ እንደተቸገሩ ይጠይቋቸዋል፡፡
 አመቻቾች ምክንያታቸውን ከሰማ በኋላ አራቱ ዋና ዋና የክህሎት ምድቦች እርስ በእርሳቸው ያላቸውን
ተያያዥነት ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ ለምን እንደተቸገሩና እያንዳንዱ የክህሎት ዓይነት ብቻውን
መቆም እንደማይችል አስረድተው ያጠቃልላሉ፡፡
የክህሎት ዓይነቶች
በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ ፡፡ እነርሱም ፣

1.አካላዊ ክህሎት ፣
 ሰዎች በአካላዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት ልዩ ልዩ ተግባራትን ለማከናወን
የሚያስችላቸው ብቃት ነው፡፡
 ክህሎቶቹ ከልምድና ከሥልጠና ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ምሳሌ እርሻ፣ ሩጫ፣ ጭፈራና
እስክስታ ወዘተ… ፣
2. አዕምሮአዊ ክህሎት፣
 ሰዎች በማህበረሰብ ውስጥ ሲኖሩ በልዩ ልዩ ጉዳዬች ላይ ውሳኔ ላይ ለመድረስ
የሁኔታዎችንና የክስተቶችን ልዩ ልዩ ገጽታዎች የሚያመዛዝኑበት ችሎታ ነው፡፡
 እነዚህ ክህሎቶች አኗኗርን ለማሻሻል፣ ችግሮችን ለመፍታትና ተፈጥሯዊና
ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመቋቋም ያስችላሉ ፡፡
 እነዚህ የክህሎት ዓይነቶች በህይወት ልምድ፣ በትምህርትና በሥልጠና የሚገኙና
የሚዳብሩ ናቸው፡፡
3.ቴክኒካዊና ሙያዊ ክህሎት፣
 የቁሳዊ ነገሮችና የመገልገያ መሳሪዎችን ጠባይ ጠንቅቆ በመረዳት ሥራዎችን
ለማከናወን የሚያስችሉ አቅሞች ናቸው፡፡
 ክህሎቶቹ እንደ አካላዊ ክህሎቶች በተሞክሮ ወይም በሥልጠና የሚገኙና
የሚዳብሩ ናቸው ፡፡
ምሳሌ ፣ አናፂነት፣ መካኒክነት፣ ሸክላ ሥራ ባልተናና እደጥበብ፣
4. ሥነልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎት ፣
 በግላዊና ማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ግጭቶችን፣ቅራኔዎችንና
ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ክህሎቶች ናቸው፡፡
 እነዚህ የክህሎት ዓይነቶች ከቤተሰብ ጋር በሚፈጠር ስብዓዊና ማህበራዊ
ትስስር እንዲሁም ከማህበረሰቡ ከሚወረሱ ልዩ ልዩ ወጐች ፣ ልማዶችና
የአኗኗር ስርዓቶች ሊመነጩ የሚችሉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በትምህርትና
በሥልጠና የሚዳብሩ ናቸው፡፡
 ምሳሌ ፣ በራስ መተማመን ፣ የአቻ ግፊትን መቋቋም ፣ መደራደር ፣ ውሳኔ
መስጠትና ችግርን መፍታት፣
ሥነልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎቶች በሶስት ዋና ዋና ፈርጆች ይከፈላሉ፡፡
እነርሱም፡-
እራስን ማወቅና እራስን ከማወቅ ጋር የተዛመዱ ክህሎት
ሌሎች ሰዎችን የማወቅና ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ የመኖር ክህሎትና
የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎት ናቸው፡፡
የህይወት ክህሎት ትምህርት ጥቅሞች

አላማ፣
 ተሣታፊዎች የህይወት ክህሎት ትምህርትን ጥቅሞች ይረዳሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ፣
 ጥያቄዎችን በማቅረብ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት
 አመቻቾች በማስታወሻ ስር የተዘረዘሩትን የህይወት ክህሎት ትምህርት
ጥቅሞች አንድ በአንድ በፊሊፕ ቻርት ላይ በመፃፍ ተሣታፊዎች በዝርዝር
እንዲወያዩበት ይጠይቃሉ፡፡
 ሁሉንም ጥቅሞች በማቅረብ ውይይት እንዲደረግበት በማድረግ ተሣታፊዎች
በጥቅሞቹ መስማማታቸውን ይጠይቃሉ፡፡

የህይወት ክህሎት ትምህርት ጥቅሞች
የጤና ጥቅሞች፣
 የህይወት ክህሎት ትምህርት ሰዎች ጤናቸውን ሊጎዱ ከሚችሉ አደገኛ ባህሪያት እራሳቸውን
እንዲጠብቁ ብቃትን ይሰጣቸዋል፡፡
ለምሳሌ በስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች፣ ኤች አይ ቪ /ኤድስ እና ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች
ሊያጋልጡ ከሚችሉ ሁኔታዎች እንዲጠበቁ እና ጤናማ ባህሪያት እንዲያጎለብቱ የህይወት
ክህሎት ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
ማህበራዊ ጥቅሞች
 የህይወት ክህሎት ትምህርት፣ መልካም ማህበራዊ ግንኙነትን ለመመስረት ከማስቻሉም ሌላ
ወጣት ጥፋተኝነትን ፣ ሥራ አጥነትን እና ሌሎችንም የማህበራዊ ቀውሶች ለመቀነስ በጣም
አስፈላጊ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡
ባህላዊ ጥቅሞች ፣
 የህይወት ክህሎት የተለያየ ባህል እና ልምድ ባላቸው ማህበረሰብ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች
ልዩነቶችን አውቀው እርስ በእርስ በመከባበር እና በመቻቻል አብሮ የመኖር ጥበብን
እንዲያጎለብቱ ይረዳሉ፡፡
 በተጨማሪም በሰለጠነ ማህበረሰብ ውስጥ የሚያድጉ ወጣቶች ፍላጎታቸውን ግልጽ
በማድረግ በትውልድ መካከል ሊፈጠሩ የሚችሉ ልዩነቶች በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ
ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ፣
 ሰዎች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ ውጤታማ እና አትራፊ በሆነ መልኩ
እንዲንቀሳቀሱ የህይወት ክህሎቶች ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ፖለቲካዊ ጥቅሞች ፣
 የህይወት ክህሎት ሰዎች ፍላጎታቸውን እና መብታቸውን ለማስከበር
በሚያደርጉት ሂደት ውሰጥ የሌሎች ሰዎችን መብት ሳይነኩ እና ግጭት
ሳይፈጥሩ ሰላማዊ በሆነ አካሄድ ሃሳባቸውን መግለጽ የሚችሉበትን ጥበብ
እና ብቃት እንዲያሳድጉ ይረዷቸዋል፡፡
ትምህርታዊ ጥቅሞች
 የህይወት ክህሎት ሰዎች በትምህርታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን ብቃት
ከማሳደጉም በላይ በአሰተማሪ እና በተማሪ መካከል ጤናማ ግንኙነት
እንዲፈጠር ይረዳሉ፡፡ በሌላ በኩልም አሳታፊ የመማማሪያ መንገዶችን
ማእከል ያደረገ አቀራረብ በህይወት ክህሎት ትምህርት ውስጥ ከፍተኛ
ስፍራ ስለሚሰጠው ውጤታማ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴንም
ያስተዋውቃል፡፡
የባህርይ ለውጥ ድልድይ ሞዴል
ዓላማዎች
 ተሳታፊዎች በመረጃና በባህሪ ለውጥ መካከል ያለውን ልዩነትና ግንኙነት በድልድይ ሞዴል ምሳሌነት ያስረደሉ፡፡
 ከመረጃ ወደ ባህሪ ለውጥ ለመሸጋገር የሚረዱ የህይወት ክህሎትን የብራራሉ፡፡
 ጤናማና አወንታዊ ህይወት እንዲኖራቸው የሚረዱ የህይወት ክህሎትን በማዳበር በዕለት ከዕለት
እንቅስቃሴያቸው ያንፀባርቃሉ፡፡

የሥልጠና ዘዴ፣
 አስመስሎ ጫወታ ፣ የመድረክ ውይይት ፣

የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፍሊፕ ቻርት ፣ ማርከር ፣

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 አመቻቾች የባህሪ ለውጥ ሞዴልን ለማብራራት የሚረዳ አስመስሎ ጫዋታ ቀደም ብለው ያዘጋጃሉ፡፡
 አሥመስሎ ጫዋታውን የሚተውኑ ሶስት ተሣታፊዎችን / ሁለት ሴትና አንድ ወንድ መርጦ የተዘጋጀውን
አስመስሎ ጫዋታ እንዲዘጋጁበት አድርጉ ፡፡ /በአስመስሎ ጫዋታ የሚሳተፋ ስዎች ቁጥር አመቻቾች
እንዳዘጋጁት ተውኔት ሊለያይ ይችላል/ ፡፡
…የቀጠለ

 የሚከተለውን አስመስሎ የጫዋታ ጭብጥ ለሶስቱ ተሣታፊዎች በቅድሚያ ይሰጣቸው፣


አለምፀሐይ አካል ጉዳተ ስትሆን ከእርግዝና፣ ከኤች አይ ቪና ተዛማጅ ችግሮች ሊጠብቃት
የሚያስችል በቂ መረጃ ቢኖራትም ለእርግዝናና ለአባላዘር በሽታ ተጋልጣለች ፣ ሰናይትና
አለምፀሐይ የሚዋደዱ የረጅ ጊዜ ጓደኛሞች ሲሆኑ ዘወትር ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ
ጉዳዬች ዙሪያ መረጃ ይለዋወጣሉ፣ አለምፀሐይና ሰናይት አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥም
ኮንዶም መጠቀም ብልህነት መሆኑን በጋራ የተስማሙበት ሁኔታ ነበር ፣ አስቻለው
የአለምፀሐይ ጓደኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ የወሲብ ጥያቄ በማቅረብ ምላሹን ይጠባበቅ ነበር፡፡
ምላሹን ለማግኘትም የተለያዩ ማግባቢያ ስጦታዎችን ያቀርብላት ነበር፣ አንድ ቀን ግን
አለምፀሐይ ጥያቄው ስለበዛባትና የአስቻለው ስጦታም ይሉኝታ ስላሳደረባት ለጥያቄው
ምላሷን በመስጠት ከአስቻለው ጋር ያለኮንዶም ወሲብ ፈፀመች ፣ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ
አለምፀሐይ እንዳረገዘችና የአባላዘር በሽታ እንደያዛት አረጋገጠች፡፡ አስመሥሎ ጫዋታው
አስፈላጊውን መረጃ እንዲያስተላልፍ ተደርጐ መዘጋጀቱ ሲረጋገጥ ለተሣታፊዎች
እንዲቀርብ አድርጉ፡፡ አመቻቾች በቀረበው ጭውውት ላይ በመንተራስ ተሣታፊዎችን
ለማወያየት የሚረዱ ቀጥተኛ ጥያቄዎችን በማቅረብ ሁኔታዎችን በጥልቀት እንዲወያዩ
አድርጉ፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄወች በምሣሌነት መውሰድ ይቻላል፡፡
…የቀጠለ

 በጫዋታው ውስጥ የቀረበው ሃሳብ እውነተኛና በማህበረሰቡ ውስጥ ልናየው


እንችላለን?
 ዓለምፀሐይ ከአስቻለው ጋር ወሲብ መፈጸም ሊያስከትል የሚችለው አደጋ /ችግር/
በትክክል የተገነዘበች ይመስላችኋል ?
 ወሲብ መፈጸም ሊያስከትል የሚችለውን ችግር በሚገባ ከተገነዘበች እና በቂ መረጃም
ካላት ለምን ወሲብ ፈጸመች ?
 አስቻለው ዓለምፀሐይ ከእርሱ ጋር ወሲብ እንድትፈጽም ለመገፋፋት የተጠቀመባቸው
ማሳመኛ ነጥቦች ምን ይመስላችኋል?
 ዓለምፀሐይ ሰናይት እንደትጠቀም የሰጠቻትን ኮንዶም ላለመጠቀም በቂ ምክንያት
ነበራት ?
 አሁን ዓለምፀሐይ ላይ ምን ችግር ሉደርስባት ይችላል ?
 እርሷ እና በአስቻለው መካከል ምን ሊከሰት ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
 በአስመስሎ ጫዋታው በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ በቂ ውይይት ከተደረገ በኋላ
በፍሊፕ ቻርት ያዘጋጃችሁትን ድልድይ ሞደል ለተሳታፊዎች በግልጽ በሚታይበት
ስፍራ በመስቀል የጋራ ውይይት ይደረግበት፡፡
የባህርይ ለውጥ ድልድይ ሞዴል

የባህሪ ለውጥ ሞዴል


ከመረጃ ወደ ባህሪ ለውጥ እንዴት አድርገን ድልድይ /መሸጋገሪያ/ እንገነባለን
የአልኮል መጠጦችና
የአደንዛዥ እፆች ተጠቃሚ
መሆንና ራስን መጥላት
ባህላዊ እምነቶች እርግዝናን በአባላዘር በሽታዎች
መፍራት
ስለ በሌብነት
ኤች አይ ቪ/ኤድስ እስር ቤት ተስፋ መቁረጥ
መረጃና እውቀት መግባባት አዎንታዊና ጤናማ
ከትምህርት ህይወት
ቤት መቅረት
ስለ አባላዘር ያልተፈለገ ስራ ማጣት
በሽታዎች እርግዝና
እውነታዎች
እምነቶች በሰው እጅ መሞት
ቤተሰቦች /ወላጆች/
ከልጆቻቸው
የሚጠብቋቸው
ነገሮች
እሴቶች
እሴቶች ማወቅና መለየት
ዓላማዎች ፣
 ተሳታፊዎች ስለ እሴት ምንነት ያውቃሉ ማስረዳት ይችላሉ፡፡
 በማህበራዊም ሆነ በግል ህይወት ውስጥ እሴተች ያላቸውን ጠቀሜታ መግለፅ ይችላሉ፡፡
 የሌሎችን እሴቶች ማክበርና ጠቃሚም ሆኖ ሲያገኙት መቀበልና የራሳቸውን እሴቶች
ከሌሎች ጋር ሊቻቻል እንደሚቻል ማስረዳት ይችላሉ፡፡
 ቅድሚያ የሚሰጧቸውን እሴቶች በደረጃ ለይተው ማሳየት ይችላሉ፡፡
የሥልና ዘዴ፣
 በቡድን ውይይትና የግል ውሣኔ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ካርዶች ፣ ፍሊፕ ፣ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣
 አመቻቾች ተሳታፊዎች በአነስተኛ ቡድኖች እንዲቧደኑ ያደርጋሉ፡፡
 እያንዳንዱ ቡድን ለሚከተሉት ጥያቄዎች በሃያ ደቂቃዎች ውስጥ ምላሹን ያዘጋጃል፡፡
…የቀጠለ

ጥያቄዎች፣
ማህበራዊ እሴት በአካባቢው ቋንቋ ምን ይባላል
በምትኖሩበት አካባቢ ማህበረሰቡ በጐ ናቸው የሚላቸውን አራት ድርጊቶችንና
መጥፎ የሚላቸውን አራት ድርጊቶችን ዘርዝሩ፡፡
ማህበረሰቡ በጐ ያላቸውን ድርጊቶች ለምን እንደሚያበረታታና መጥፎ የሚላቸውን
ደግሞ ለምን እንደሚያወግዝ አስረዱ ፡፡
ማህበረሰቡ በጐ ናቸው የሚላቸውን ድርጊቶች ማበረታታቱና መጥፎ የሚላቸውን
ማውገዙ ያለውን ጠቅምና ጉዳት ይግለፁ፡፡
የተዘረዘሩት እሴቶች የማህበረሰቡን አሳሳቢ ጉዳዬችና ችግሮች ለመፍታት በምን
አይነት ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፡፡
እያንዳንዱ ቡድን በተወካዬቹ አማካኝነት ሥራውን ለጠቅላላ ተሳታፊዎች
እንዲያቀርብ ይሰጠዋል፡፡
የቡድን ሥራዎች ከቀረቡ በኋላ በማህበረሰብ ውስጥ የአንድን የድርጊት
በጐነትና መጥፎነት የሚወስነው አስተሳሰብ እሴት መሆኑን በመግለጽ
እሴቶች
 እሴት አንድ ማህበረሰብ ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችና የማህበረሰቡ
አባላት አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን በበጐ ወይም በመጥፎነት ፈርጀው
የሚያበረታቱበትን ወይም የሚያወግዙበትን የአሰተሳሰብ ስርዓት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
 ደግነትን፣ ቅንነትን በበጐ ተግባራት ፈርጀው ማበረታታትና ስስትንና ፈሪነትን በክፋ
ፈርጆ ማውገዝ የማህበረሰብ እሴቶች መገለጫ ነው፡፡

 ማህበረሰባዊ እሴቶች ማለት ሰዎች በህብረተሰባቸው ውስጥ እርስ በእርሳቸው


የተቆራኘ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማህበራዊ አንድነትና አቅም እንዲፈጥርላቸው
የሚያግዙ ደምቦች እና እነዚህም የታቀፋበትን ተቋማት የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
 የአንድን ማህበረሰብ ማህበራዊ እሴቶች ለማወቅ ማህበረሰቡ በጐ ናቸው ብሎ
የሚቀበላቸውን ወይም መጥፎ ናቸው ብሎ የሚያወግዛቸውን ድርጊቶች የሰዎች
ጠባዬችንና የሥነ ምግባር ገጽታዎችን ማወቅ ያሻል፡፡

ለምሳሌ በኢትዬጰያውያን ዘንድ ደግነት፣ ለጋስነት ጀግንነት ማህበረሰቡ በጐ ናቸው


ስለ እሴቶች በጥልቀት ማሰብ
ዓላማዎች
 ጠቃሚና ጎጁ የሆኑ እሴቶችን ይለያሉ ያብራራሉ
 ጠቃሚ እሴቶችን ይበልጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋሉ ጎጆቹን ደግሞ በሂደት ያስወግዳሉ፣
 በማህበራዊም ሆነ በግል ህይወት ውስጥ እሴቶች ያላቸውን ጠቀሜታ መግለጽ ይችላሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ
 በቡድን ፣ ውይይትና የግል ውሣኔ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ካርዶች፣ ፍሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣
 አመቻቾች ተሳታፊዎች ከሶስት እስከ አምስት አባላት ባሏቸው ቡድኖች እንዲቧደኑ
ያደርጋሉ፡፡
 ከቡድኖቹ መካከል ግማሹ ከዚህ በታች በፊደል ሀ ምድብ በፊደል መ ምድብ ያሉትን
በመከፋፈል የማህበረሰቡን እሴቶች የሚገልጽ አባባሎች ጠቃሚነት ወይም ጐጂነት
ከነምክንያታቸው እንዲገለፅና አባሎቹ በበጐነት ወይም በመጥፎነት የሚገልጿቸውን
ድርጊቶች ጽፈው በማዘጋጀት ይሰጧቸዋል፡፡
ስለ እሴቶች በጥልቀት ማሰብ
 ማህበረሰባዊ እሴቶች እንደ የማህበረረሰቡ የግል ሥነልቦና የሚወሰኑ በመሆናቸው
እንደ አካባቢው ተቀባይነት ያላቸውና የሚበረታቱ ተግባራት በሌሎች አካባቢዎች
ላይበረታቱ ይችላሉ ተቀባይነት ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ በእሴቶች ላይ ያለ ልዩነት
የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ያስቸግራል፡፡

ለእሴቶች ድምጽ መስጠት


“ ሀ” “ለ”
 ልጅና ፊት አይበርደውም ሴትን ያመነና ጉም የዘገነ
 ዝምታ ወርቅ ነው ሲሾም ያለበላ ሲሻር ይቆጨዋል
 የሰው ወርቅ አያደምቅ ደፋርና ጪስ መውጫ አያጣም
“ ሐ” “መ”
 ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እውነትን ተናግሮ የመሸበት ማደር
 ጋብቻ ክብር ነው ኩራት እራት ነው
 ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ያለአቻ ጋብቻ
ለእሴቶች ድምጽ መስጠት
ዓላማ
 በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንዳንድ እሴቶች በማህበረሰቡ እኩል ተቀባይነት ላይኖራዠው እንደሚችል ያውቃሉ፣
ያብራራሉ
የሥልጠና ዘዴ፣
 በቡድን ውይይትና የግል ውሣኔ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች፣
 ካርዶች ፣ ፍሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣
 አመቻቾች ከዚህ በታች በተገለጸው አባባል ተሳታፊዎች እንዲከራከሩ ያቀርባሉ፡፡
 ከጋብቻ በፊት የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈጸም ተገቢ አይደለም፡፡
 አመቻቾች ከላይ የተጠቀሱትን የመከራከሪያ ርዕሶች ጐላ ብለው እንዲታዩ በሰሌዳ ላይ ይጽፋሉ፡፡
 አባባሉ ላይ ድምጽ ከመስጠቱ በፊት የሚከተሉት አስተያየትቶች የተፃፋባቸውን ሶስት ካርዶች ውይይቱ በሚካሄድበት
ክፍል ግድግዳ ላይ ይለጥፋሉ፡፡
 እስማማለሁ
 አልስማማም
 እርግጠኛ አይደለሁም
 በአባባሉ ላይ ድምጽ የሚሰጡት ተሳታፊዎች ምርጫቸው ወደ ተፃፈበት ካርድ አጠገብ እንዲቀመጡ ይደረጋል፡፡
 በየምርጫው ካርድ አጠገብ የተሰበሰቡት ተሳታፊዎች ቡድን መስርተው ለምርጫቸው ምክንያት የሆነውን ሃሳብ
ተወያይቶ በተወካዬቹ አማካኝነት ለጠቅላላ ተሳታፊዎች ያቀርባሉ፡፡ በአጋጣሚ አንድ ተሳታፊ ብቻ ያለበት ምርጫ ካለም
ሃሳቡን እንዲያቀርብ ይደረጋል፡፡
 የየቡድኑ ሃሳብ ከቀረበ በኋላ አመቻቾች ስለ እሴት የቀረቡትን አስተያየቶች በማጠቃለል ሁሉም የማህበረሰቡ አባላት
በእሴቶች ላይ ልዩነት የሌለበት ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚያስቸግራቸው በመግለጽ ውይይቱን ያጠቃልላሉ፡፡
ሥነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎት
 ራስን ማወቅና እራስን ከማወቅ ጋር የተዛመዱ ክሕሎቶች ፣
 ራስን ማወቅ

ዓላማዎች
 ተሳታፊዎች ራስን ማወቅ እና መቀበል ምን ማለት እንደሆነ ይረዳሉ
 ራስን ለማወቅና ለማግኘት የሚረዱ ሥልቶችን ይለማመዳሉ
 ራሳቸውን በማወቅና በመቀበል በዕለት ከዕለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ፈተናና
የሚያስፈልጋቸውን ፍላጐት ለማሟላት የሚረዳ በራስ የመተማመንና ለራስ ከፍተሃ ግምት
የሚሰጡት ሁኔታን ያዳብራሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ
 ትረካ፣ የቡድንና የግል ልምምድ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፡-
 ፊሊፕ ቻርት ፣ ደብተርና ስክሪብቶ፣
በየደረጃው የሚከናወወኑ ተግባራት ፣
 ተሳታፊዎችን አነስተኛ ቁጥር በያዙ ቡድኖች ማከፋፈል፣
 ከቡድን አባላት መካከል የተዘጋጀውን ትረካ የሚያቀርቡ አንድ አንድ ተሳታፊ በመለየት
ትረካውን ለተሳታፊዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ሥነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎት
ራስን ማወቅና እራስን ከማወቅ ጋር የተዛመዱ ክሕሎቶች
1. ራስን ማወቅ
ትረካ አንድ
ኤሊና የሁለት ቁራዎተ ጓደኝነት ፣
አንድ ኤሊና ሁለት ቁራዎች ጓደኝነት መሰረቱ፡- ጓደኝነታቸው በጣም
ጠንክሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ይወያዩ ጀመር ፡፡ አንድ ቀን ኤሊ እንደ
ጓደኞቿ መብረር አማራትና ለምን አልበርም ስትል ራሲን ጠየቀች ፡፡ ጓደኞቿ
ከዋሉበት እንደመጡ እሷም እንደነርሱ መብረር እንዳለባት አሳመነቻቸው ፡፡
ግን በራሷ አቅም መብረር ስለማትችል ሁለቱ ቁራዎች በአፋቸው አንድ
እንጨት ይዘው ኤሊን መሀል በማስገባት እንጨቱን በአፏ አስይዘው መብረር
ጀመሩ፡፡ ከዚያም ኤሊ መሬት ላሉት ኤሊዎች እናንተ ደካመች ፣ እንደ እኔ
አትበሩም ልትል ፈልጋ አፏን በመክፈቋ እንጨቱን ለቃ ተከሰከሳ ሞተች፡፡
 ይህ ትረካ ራስን ማወቅና መቀበል ከሚለው ሀሳብ ጋር ያለው ተያያዥ ነት
ምንድነው?
 ራስን አውቆ አለመቀበል እንዴት ሊጎዳ ይችላል ?
 ራስን አውቆ መቀበል ምን ጥቅም አለው ?
ስለራስህ አስብና ሶሶት ደካማና ሶስት ጠንካራ ጐኖችህን ዘርዝር፣
ስለራስህ አስብና ልሠራ እችላለሁ የምትላቸውን ሶስት ሥራዎች ጻፍ ሥራዎቹን
ሊያስሩህ የሚችሉትን ክህሎቶች ግለጽ ፣
ስለራስህ አስብና ልሰራቸው እፈልጋለሁ ግን አልችልም የምትላቸውን ሶስት
ሥራዎች ጻፍ ወደፊት እነዚህን ሥራዎች እንድትሰራ ምን ማድረግ እንዳለብህ ዘርዝር

ተሳታፊዎች በየግላቸው በሚፈልጉት ሥፈራ ሆነው በጥሞና በማሰብ እነዚህን
ጥያቄዎች በመመለስ በማስታወሻ ደብተራቸው ያሰፍራሉ ፡፡
ተሳታፊዎች ወደየቡድናቸው ተመልሰው በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ይወያያሉ፡፡
ስለራሳችሁ ጠንካራና ደካማ ጐኖች እየጻፋችሁ ምን ተሰማችሁ? ለምን?
እዚህ ሙከራ ምን ተማራችሁ?
ቡድኖች በተወካዬቻቸው አማካኝነት ስለ ውይይታቸው ለጠቅላላ ተሳታፊዎች
ከገለጹ በኋላ አመቻቾች ክፍለ ጊዜውን ያጠቃሉ፡፡
 ራስን ማወቅ አንድ የስነ ልቦናዊና ማህበራዊ ክህሎት አካል እንደ መሆኑ
በህብረተሰብ ውስጥ አዎንታዊና ንቁ ህይወት ለመኖር ያስችላል፡፡
 ራስን ማወቅ በጥልቀት በማሰብ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ፡፡ ይህም
የህይወት ውጣ ውረዶችን ለመጋፈጥ እንዲቻል ምን ማድረግ እንደሚገባ ፣
ተገቢውን ውሳኔ ለመወሰንና ለችግሮችም ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት
ያስችላል ፡፡ ችግርን ለመቋቋምም ሆነ ለመደራደር፣ ለልዩ ልዩ አስቸጋሪ
የህይወት ሁኔታዎች ራስን ዝግጁ ለማድረግ መነሻ የሆናል፡፡
 ራስን ማወቅ ለራስ ከፍተኛ ግምት ወደ መስጠት ያመራል፡፡
 ሰዎች ስለችሎታቸውና በማህበረሰብ ውስጥ ስላላቸው ቦታ ሊያውቁ
ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት ይጨምራል፡፡ በጥልቀት ከማሰብ የመነጨ
ለራስ የተሰጠ ከፍተኟ ግምት የራስን ጠንካራና በጎ ጎን መረዳትን ይጨምራል
ይህም በራስ የመተማመን ስሜትን ያዳብራል፡፡
 ራሳቸውን የተቀበሉ ሰዎች ህይወታቸውን በእውነታ ላይ ተመስርተው ይመራሉ፡፡
በእውነታ ላይ ተመስርተው ከህይወት ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ይህም በኑሯቸው ስኬታማ
እንዲሆኑ ይረዳቸዋል፡፡
 አንድ ሰው ያለው በራስ የመተማመን ስሜት በማህበራዊ ግንኙቱ ላይ ማህበራዊ
ግንኙቱም በራስ የመተማመን ስሜቱ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ግለሰቦች
በማህበረሰባቸው ውስጥ ያላቸው አዎንታዊ ግንኙነት በራስ የመተማመን ስሜታቸውን
ሊያጎለብተው ይችላል፡፡
 በራስ መተማመን ወጣቶች ደስተኞች እንዲሆኑና ሰብእናንና ጤናን ከሚጎዱ ተግባራት
እንዲርቁ ያደርጋቸዋል፡፡ ዝቅተኛ የሆኑ በራስ የመተማመን ባህሪያት ጤናማ ያልሆኑ
አማራጮችና ባህሪያትን ያበረታታሉ፡፡
 ራስን ማወቅ፣ ለራስ ግምት መስጠትና በራስ መተማመን ራስን ማክበርንና ራስን መቀበልን
ያስከትላል፡፡ የራሳቸውን ቤተሰባዊና ማህበራዊ ሁኔታ የተገነዘቡ፣ ችሎታቸውንና
ውሱንነታቸውን ያወቁ ሰዎች ለራሳቸው ግምት ይሰጣሉ፤ በራሳቸው ይተማመናሉ፤
ራሳቸውን የከብራሉ፡፡ ራስን ማክበርም የራስን ማንነት ለመቀበል ያስችላል፡፡
 ራሳቸውን የተቀበሉ ሰዎች በክህሎቶቻቸው ይኮራሉ፤ ይጠቀሙባቸዋል፤ ያልሆኑትን
ለመምሰል አይሞክሩም፡፡ ራሳቸውን በትክክለኛው ማንነታቸው የገልጻሉ፡፡ እውነተኛ
ባህሪያቸውን አይደብቁም፡፡
 ራሳቸውን የተቀበሉ ሰዎች ህይወታቸውን በእውነታ ላይ ተመስርተው ይመራሉ፡፡
ራስን መገምገም፣
ዓላማዎች
 ራሳቸውን እንዴት መገምገም እንደሚችሉ ክህሎት ያገኛሉ፣
 ራስን የመገምገም ልምድን ያዳብራሉ
የሥልጠና ዘዴ ፣
 በግል የሚደረግ ክንውንና በጥያቄዎች ፣
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ድርጊቶች ፣
 አመቻቾች ራስን የመገምገም ጽንሰ ሃሳብና ጥቅሞቹን ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
 አመቻቾች ራስን የመገምገሚያ ጥያቄዎችን በፊሊፕ ቻርት በማዘጋጀት ተሳታፊዎች በሚያዩበት ቦታ ይለጥፉ፡፡
 ራስን የመመዘኛ/ መገምገሚያ / ጥያቄዎች
 ስለራስህ በማሰብ ጠንካራና ደካማ ጉኖችህንና እንዲሁም ስለራስህ የምትወዳቸውን ነገሮች ዘርዝር ፣
 በህይወትህ በተፈጥሮህና በአቅምህ መለወጥ የምትችላቸውን ነገሮችና መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮች ለይተህ
ለሁለት በመክፈል ዘርዝራቸው፣
 ስለነዚህ ነገሮች ማድረግ አለብኝ ወይም እችላለሁ የምትለውን ውሳኔዎችህን ከእያንዳንዱ ጐን አስፍር፣
 ውሳኔዎቹን እንዴት በዘላቂነት መተግበር እችላለሁ ?
 ተሳታፊዎች በሚመቻቸው ቦታ ላይ በመሆን ከጥያቄዎቹ አንፃር ራሳቸውን በመገምገም ምላሻቸውን
በማስታወሻቸው ላይ እንዲያስፍሩ ይደረጋል፡፡
 የሚያስፈልገው ጊዜ ፣
ራስን መገምገም፣

ራስን የመመዘኛ/ መገምገሚያ / ጥያቄዎች


ስለራስህ በማሰብ ጠንካራና ደካማ ጉኖችህንና እንዲሁም ስለራስህ
የምትወዳቸውን ነገሮች ዘርዝር ፣
በህይወትህ በተፈጥሮህና በአቅምህ መለወጥ የምትችላቸውን ነገሮችና
መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮች ለይተህ ለሁለት በመክፈል
ዘርዝራቸው፣
ስለነዚህ ነገሮች ማድረግ አለብኝ ወይም እችላለሁ የምትለውን
ውሳኔዎችህን ከእያንዳንዱ ጐን አስፍር፣
ውሳኔዎቹን እንዴት በዘላቂነት መተግበር እችላለሁ ?
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን የሚገመግሙት ሰዎች ስለነሱ ባላቸው
አመለካከትና በሚሰጧቸው አስተያየቶች በመነሣት ነው፡፡
ይህ ደግሞ ጠቃሚ ቢሆንም ራስን ለመገምገምና ለራስ በምንሰጠው ግምት
ዙሪያ እንደ መሠረታዊ ነገር ተቆጥሮ መወሰድ የለበትም፡፡
አንድ ሰው ስለራሱ በማወቅ በሚያደርገው ጥረት ችሎታ የለኝም ወደሚል
መደምደሚያ ከመድረሱ በፊት አንዳንድ ሁኔታዎችን ተመልሶ ለብቻ ማጤን
ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ራሱን በመገምገም ሂደት ክህሎቱን አዳብሮ ከፍ
ካለ ደረጃ ማድረስ ይችላልና ነው፡፡
ራስን የመገምገም ሂደትም ቀጣይነት ያለውና በዘላቂነት የሚደረግ ተግባር
ነው፡፡
ግብ ማስቀመጥ
 ጋሻዬ
ዓላማ
 ተሳታፊዎተ የግል ሕይወታቸውን በማሰላሰል በተለያዩ ጊዚያት ሊደርሱባቸው የሚፈልጉባቸውን ደረጃዎች
ያስቀምጣሉ
የሥልጠና ዘዴ፣
 የግልና የቡድን ሥራዎች
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር፣
በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት ፣
 አመቻቾች ከዚህ በታች የተሳለውን ሥዕል በፍሊፕ ቻርት ላይ በመሣል አጭር ገለፃ ያድርጉ
 እያንዳንዱ ተሣታፊ በጋሻው ውስጥ የተካተቱትን አራቱን ጥያቄዎች በሚፈልጉት ሥፍራ ቁጭ ብለው በጥሞና በማሰብ
የየራሣቸውን ጋሻ እንዲሠሩ የ1ዐ ደቂቃ ጊዜ ይሰጣቸው፡፡
 አራቱ ወይም አምስት ፈቃደኛ ተሣታፊዎች መልሶቻቸውን በፍሊፕ ቻርት ወይም በደብተር ወረቀት ላይ ጽፈው
እንዲያቀርቡ ይደረግ፡፡
 ጠቅላላ ተሣታፊዎች በፊቃደኛ ተሣታፊዎች የቀረቡትን መልሶች መሠረት በማድረግ ውይይት ያካሂዱ፡፡
 የቀረቡትን መልሶች በጥሞናና በጥልቀት በማሰብ ጋሻዬ ላይ ተመስርተው ስለመዘጋጀታቸው ተሣታፊዎች ምላሽ ይስጡ
፡፡
 ሁሉም ተሳታፊ ያዘጋጀውን የግል ጋሻ በመሰብሰብ በአዳራሹ ውስጥ ሁሉም ሊያዩት በሚችሉበት ቦታ በመለጠፍ የጋሻዬ
ጋለሪ ይዘጋጃል፡፡
 አመቻቾች በውይይቱ የተነሱ ጉዳዬችን ከስነልቦናና ማህበራዊ ክህሎት ባህሪያት ጋር በማዛመድና የአመቻቹን ማስታወሻ
በመጠቀም ክፍለ ጊዜው ይቋላሉ፡፡
ግብ ማስቀመጥ

እኔ ማነኝ በህይወት ዘመኔ ልደርስበት የምሻው ደረጃ ምንድን ነው፡፡

ከአሁን ጀምሮ ከሞት በኋላ


ለሚቀጥሉት ሰዎች በምን
አሥር ዓመታት እንዲያስታውሱኝ
ምን መሆን እፈልጋለሁ?
እፈልጋለሁ?

ስዕል፡- ጋሻየ /የራስን ስብዕና ለመገንባት ራስን ማወቅና ግብ ማስቀመጥ/


የግብ ምንነትና ጠቀሜታ
ዓላማዎች ፣
 የግብን ምንነት ያስረዳሉ
 የህይወት ግቦችን ያስቀምጣሉ
የሥልጠና ዘዴ፣
 የግልና የቡድን ሥራዎች
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፍሊፕ ቻርትና ማርከር ፣
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት፣
 አመቻቾች ተሳታፊዎች ስለግብ ምንነት የሚያውቁትን የሚያስቡትንና የተረዱትን እንዲገልፁ ያደርጋሉ፡፡
 ከግብ ጋር ተመሳሳይ ወይም አንድ አይነት ትርጉም ያላቸውን ቃላቶችና ሐረጎችን በፍሊፕ ቻርት ላይ
ይጽፋሉ፡፡
 በተለይ ቃላቶችና ሐረጎች ዙሪያ ያለውን አንድነትና ልዩነት በማወያየት ያጠቃልላሉ፡፡
 በመቀጠል ተሳታፊዎችን በቡድን በመከፋፈል በሚከተሉት ጥያቄዎች ዙሪያ እንዲወያዩ ያደርጋሉ፡፡
 የግብ ዋና ዋና ባህሪያት ምን ምን ናቸው ?
 ግብ ማስቀመጥ ለምን ይጠቅማል ?ቢያንስ አምስት ጥቅሞች ጥቀሱ
 ግብን ለማሳካት ምን ማድረግ ያስፈልጋል? ቢያንስ አምስት ጉዳዬችን ጥቀሱ
 ቡድኖች በተወካዬቻቸው አማካኝነት የቡድኑን መልሶች ለጠቅላላው መድረክ ያቀርባሉ፡፡
 አመቻቾች በቡድኖች የቀረቡትንና የአመቻቾችን ማስታወሻ በመጠቀም ክፍለ ጊዜውን ያጠቃሉ፡፡
የግብ ምንነትና ጠቀሜታ
 ግብ አንድ ግለሰብ የተወሰኑ ተግባሮችን በመፈፀም ሊደርስበት የሚሻው
ውጤት ነው፡፡
 ግብን ማስቀመጥ አንድ ሰው በተወሰኑ ጉዳዬች ላይ በማተኮር ወደ ውጤት
እንዲያመራ ያግዘዋል፡፡
 ግብን ማስቀመጥ አንድ ሰው በተሰጦውና በክህሎቶቹ ለመጠቀም
ያስችለዋል፡፡ ለምሳሌ መካኒክ የመሆን ግብ ያለው ወጣት የቴክኒክና የሙያ
ክህሎቶችን ለማዳበርና ውጤታማ ለመሆን ይጥራል፡፡
 በዓመታት በሚቆጠር ጊዜ ውስጥ የሚደርስበት ግብ ያለው ወጣት ግቡን
ሊደርስበት ይችላል፡፡
 የተለያዩ ግቦች አስቀምጦ ስኬታማ መሆን በራስ መተማመንን ያሳድጋል፡፡
ያልተሳኩ ግቦች የራስን ድክመቶች ለማረምና ለማስተካከል ይጠቅማሉ፡፡
 ግብ ማስቀመጥ ስለራስ ማንነትና የወደፊት እቅድ ለመገለጽ አቅም
ይፈጥራል፡፡
አድናቆታዊ ጥያቄ
ዓላማዎች
 የውይይት ተሳታፊዎች በችሎታቸው፣ በጥንካሬዎቸቸውና በክህሎቶቻቸው ላይ እንዲያንፀባርቁ ለማድረግ
 ተሳታፊዎች አንዱቸው ከሌላቸው ልምድና ስኬት እንዲማማሩ ለማድረግ
 ተሳታፊዎች ከዚህ ቀደም ችግሮቻቸውን ለማስወገድ የተጠቀሙአቸው ዘዴዎች ወይም ክህሎቶች
የማሕበረሰቡን አሳሳቢ ጉዳዬች ከመፍታት አንጻር ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ለማስገንዘብ
የሥልጠና ዘዴ፣
 የቡድን ስራ
 የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፍሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣
 ተሳታፊዎች በቡድን ሆነው እርስ በርሳቸው ስለ ገጠመኞቻቸውና አስቸጋሪ ጉዳዬችን ስለተወጡበት መንገድ
እንዲወያዩ ማድረግ
 በቡድን የተወያዩትን ለጠቅላላ ተሳታፊዎች ማቅረብና ውይይት ማድረግ
 የቡድን ሥራ ጥያቄዎች
 ያላችሁ ጠንካራ ጐን ምን እንደሆነ ለሌሎች አካፍሉ
 በህይወታችሁ ያጋጠማችሁን አስቸጋሪ ወይም ፈታኝ ነገር ለማለፍ የተጠቀማችሁበትን ዘዴ ለሌሎች አካፍሉ
 የተጠቀማችሁት ዘዴ አሳሳቢ ጉዳዬችን ከመከላከል አንጻር ያለውን ፋይዳ በቡድን ተወያዩ
 የቡድን ሃሳባችሁን ለአጠቃላይ ውይይት አቅርቡ
አድናቆታዊ ጥያቄ

አድናቆታዊ ጥያቄ ሰዎች ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ስኬትና


ያጋጠማቸውን ችግር የፈቱበትን መንገድ እንዲያስታውሱ እና እርስ
በርሳቸው ልምድ እንዲለዋወጡ የማድረግ አካሄድ ነው፡፡
ስሜትን የመቆጣጠር ክህሉት

ዓላማዎች
በህይወት ክህሎት መጐልበት ላይ ተጽዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ በርካታ
ስሜቶችን መዘርዘር ይችላሉ፡፡
ስሜትን በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስልቶችን መለየት
ይችላሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
የስሜት ቁጥጥር ኤግዚቭሽን ጉብኝት
የድልድይ ሞዴል
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
ሰፊ ዝርግ ወረቀት / ፊሊፕ ቻርት / ወይም ሰሌዳ
ማርከር ወይም እስክርፕቶ
ማጣበቂያ
…የቀጠለ

ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 /2ዐ ደቂቃ / ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ድርጉቶች
 የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ፣
 በሰፊ ወረቀቶች ለመለጠፍ እንዲያመች የክፍሉን ግድግዳዎች ባዶ በማድረግ ማዘጋጀት፣
 ስለ “ድልድይ ሞዴል” በመጥቀስ የአንድን ሰው ስሜቶችን በመቆጣጠርና አደገኛ
ባህሪያትን በማስወገድ መካከል ያለውን ተዛማጅነት /ተያያዥነት/ በሚመለከት ውይይት
እንዲካሄድ ሁኔታዎችን አመቻቹ ፣
 እያንዳንዱ ተሳታፊ “ስሜት” የሚለውን ቃል ትክክለኛ ትርጓሜ መረዳቱን አረጋግጡ ፣
ተሳታፊዎች የቃሉን ትርጉም በመስጠት መልሱን በሰፊ ወረቀት /ፊሊፕ ቻርት/ ወይም
ሰሌዳ ላይ እንዲጻፍ አድርጉ፣
 በኦ፣አበበ መልመጃ አማካኝነት ስሜቶች የሚለውን አስተሳሰብ /ጽንሰ ሃሳብ / በአጭሩ
ለተሳታፊዎች አስተዋውቋቸው፡፡ ተሳታፊዎች በሙሉ ክብ ሰርተው እንዲቆሙ ጠይቋቸው
 የሰውነት እንቅስቃሴና ድምጽን ጨምሮ ሃሳብ ለመለዋወጥ የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች
መኖራቸውን ለተሳታፊዎች አስታውሷቸው፡፡
 ይህ እንቅስቃሴ የሚያሳየው በሰውነታችንና በድምፃችን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ መልዕክቶችን
ለሰዎች ለማስተላለፍ እንደምንችል መሆኑን አስረዱ፡፡
 ኦ፣አበበ፣ የሚለውን ሃረግ በተለያዩ ሁኔታዎች ውሰጥ ለምሳሌ የቁጣ፣ የደስታ፣ የሳቅ የፍርሃት ፣ ስሜቶችን
በሚያንፀባርቅ መልኩ ልንለው /ልንገልጸው/ እንደምንችል አሳዩአቸው፡፡
 በክብ ቀርጽ በመሥሪት የቆሙት ተሳታፊዎችም ኦ፣ አበበ፣ የሚለውን ቃል የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን
/የሰውነት ቋንቋዎችን / ፣ የድምጽ አወጣጥንና የፊት ገጽታን በመጠቀም የተለያዩ ስሜቶችን እንዲያስተላልፉ
/ኮሙኒኬት እንዲያደርጉ/ በማድረግ መልመጃው ህይወት ያለው /አስደሳች እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡
 እያንዳንዱ አባል አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከተሳተፉ በኋላ በልምምድ የተንፀባረቁትን ልዩ ልዩ ስሜቶች በፊሊፕ
ቻርት /በሰፊ ዝርግ ወረቀት / ወይም በሰሌዳ ላይ ይፃፉ፡፡
 በዚህ ሁኔታ የተንፀባረቁት ስሜቶች የሚከተሉትን ያካተቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ሀዘን ጥርጣሬ ስቃይ ቅናት ጥፋተኝነት
 ስብጭት መፈንደቅ ግራመጋባት ጭንቀት መከፋት
 ፍርሃት መውደድ መጨመት መጐሳቆል ደስታ
ሀዘን ስብጭት ፍርሃት ኮስት
ጥርጣሬ መፈንደቅ መውደድ ፍቅር
ስቃይ ግራመጋባት መጨመት ቆጣ
ቅናት ጭንቀት መጐሳቆል ፀፀት
ጥፋተኝነት መከፋት ደስታ ሳቅ
የስሜት ቁጥጥር ኤግዚብሽን ጉብኝት /አንድ ስዓት
ከላይ የተዘረዘሩት ስሜቶች እንዴት ወደ አደገኛ ባሕሪ ሊቀየሩ
እንደሚችሉ ለመወያየት ጥቂት ጊዜ ውሰድ፣
መፈንደቅና ደስታ የመሳሰሉት አንዳንድ ስሜቶች ከሌሎች በተሻለ
መልኩ በግልጽ ሊገለጹ ይችላሉ ይሆናል፣
ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ “ባህል” በግልጽ እንዲንፀባረቁ ወይም
እንዲደበቁ ግድ የሚለው የትኞቹን ስሜቶች ነው ?
በባሕሉ መሠረት አንድ ሰው በግልጽ ሊያንፀባርቃቸው አይገባም
ተብለው ከሚታመንባቸው ስሜቶች ፊት ምልክት ይደረግባቸው፡፡

…የቀጠለ

?
 ስሜትን መቆጣጠር መቻልን መማር በምን መልኩ አደገኛ ባህሪያትን ይቀንሳል ?
 በጣም ጠንካራ የሆኑትን ለምሳሌ ቁጣ፣ ፍቅር /እርካታ/ ፣ የወሲብ ስሜት ወይም
ቅናትን የመሳሰሉ ስሜቶችን መቆጣጠር ቀላል አይደለም፡፡ እነዚህነ ስሜቶች
ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስልቶችን ማጐልበት አስፈላጊና ወሳኝም ነው፡፡
 አሁን ስሜታችንን ለመቆጣጠር በሚያስችሉን ስልቶች ላይ ለመወያየት /ሃሳብ
ለመለዋወጥ/ ጥቂት ጊዜ እንሰጣለን፡፡
 በፊሊፕ ቻርት /በሰፊው ዝርግ ወረቀት / ላይ የቀረበውን ቦታ ተሳታፊዎች
“ልንቆጣጠራቸው ይገባሉ” የሚሏቸውን ስሜቶች ይጻፉባቸዋል፡፡
 እነዚህ ስሜቶች የተፃፉባቸው ወረቀቶች በክፍሉ ውስጥ በግድግዳው ላይ ይለጠፉ
 በዚህም መሠረት የሚከተሉትን መሰል ሀረጐች የሚነበቡባቸው ሰፋፊ ወረቀቶች
በክፍሉ የተለያዩ ማዕዘናት ይታያሉ፡፡
 ንዴትህን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
 ብስጭትህን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
 የወሲብ ፍላጐትህን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
…የቀጠለ

 ተሳታፊዎቹ እንዴት ልንቆጣጠራቸው እንደምንችል መማር ይገባናል ብለው ያመኑባቸው ስሜቶችና ፍላጐቶች ብቻ
ያቅርቡ፡፡
 ተሳታፊዎች ከክፍሉ ውሰጥ እየተዟዟሩ በእያንዳንዱ ወረቀት ላይ የሰፈረውን ስሜት ለመቆጣጠር ይጠቅማሉ ያሏቸውን
ቴክኒኮች ወየም ስልቶች ይፃፉ ፡፡ ይህም ተግባር ከአሰራ አምስት እስከ ሃያ ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ይቀጥል፡፡
 ተሳታፊዎች የፃፏቸውን ሥልቶች / ቴክኒኮች ይዘት የሚከተለውን ሊመስል ይችላል፡፡
 እስከ አስር መቁጠር ፣
 አካባቢውን ለቆ በመሄድ ትንሽ ቆይቶ መምጣት፣
 ቆም ብዬ ምን እንዳናደደኝ ማሰብ፣
 ሁኔታው ከሌላኛው ሰው አንፃር ማየትና ማሰብ፣
 መፀለይ፣
 አስቂኝ ታሪክ ማሰብ ፣
 በጥልቀት ማሰብ፣
 ሁኔታውን በሰላም ለመፍታት መወያየት ፣
 ሊቀርቡ ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው ሃሳቦች በሙሉ ከቀረቡ በኋላ ተሳታፊዎች በክፍል ውሰጥ የኤግዚብሽን ጉብኝት
በሚመሰል መልኩ በመዘዋወር በእያንዳንዱ ሰፊ ወረቀት ላይ የተፃፉትን ሃሳቦች ያነባሉ፡፡ በእዚህም ስሜትን በመቆጣጠር
ረገድ የቀረቡትን የተለያዩ አመለካከቶች ያጠናሉ፡፡
 ከጉብኝቱ በኋላ ተሳታፊዎች በጋራ ቁጭ ብለው ልምምዱን ያጠኑታል፡፡
 ስሜትን ለመቆጣጠር ሊረዱ የሚችሉ ጥሩ ሃሳቦች የትኞቹ ናቸው ?
 ሊረዱን የማይችሉትስ የትኞቹ ናቸው?
 በተግባርስ የተተረጐመ አለን ብለው ይወያዩበታል፡፡
ስሜትን የመቆጣጠር ክህሉት ፣

ሀዘን ጥርጣሬ ስቃይ ቅናት ጥፋተኝነት


ስብጭት መፈንደቅ ግራመጋባት ጭንቀት መከፋት
ፍርሃት መውደድ መጨመት መጐሳቆል ደስታ
ኮስት ፍቅር ቆጣ ፀፀት ሳቅ
 ንዴትህን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
 ብስጭትህን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
 ደስታን እንዴት ትቆጣጠራለህ/ሽ ?
ስነ ልቦናዊ ጫናን መቋቋም
ዓላማዎች
 የሥነ ልቦና ጫና ዓይነቶችን /ምልክቶችን መዘርዘር ይችላሉ
 የሥነ ልቦና ጫና ምንጮችን ያውቃሉ ለሌሎችም ማስረዳት ይችላሉ
 የተለያዩ የጫና መቆጣጠሪያ / መቋቋሚያ ዘዴዎችን ያውቃሉ ለሌሎችም ያስረዳሉ
የሥልጠና ዘዴ ፣
 የቡድን ውይይት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ማርከርና ፊሊፕ ቻርት
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ድርጊቶች
 አመቻቾች ተሳታፊዎችን በቡድን ይከፋፍላሉ፡፡
 ቡድኖቹ ለኤች አይ ቪ/ኤድስ የሚያጋልጡ የሥነልቦና ጫናዎችን በመለየት የጫናዎቹን ምንጭና
የመቋቋሚያ ዘዴዎች ዘርዝረው ፊሊፕ ቻርት ላይ ይፃፉ
 ቡድኖቹ የሠሩትን በተወካዬቻቸው አማካኝነት ለተሳታፊዎች እንዲያቀርቡ ይደረግ፡፡
 በቀረቡት የቡድን ሥራዎች ላይ ተሳታፊዎች እንዲወያዩ ይደረግ፡፡
 አመቻቾች የተነሱ ነጥቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ማጠቃለያ ይሰጣሉ፡፡
ስነ ልቦናዊ ጫናን መቋቋም
ሥነልቦናዊ ጫና ልናስወግደው የማንችለው እውነታ ስለሆነ ማንኛውንም
ሰው ሊያጋጥመው የሚችል ችግር ነው፡፡
የሥነልቦና ጫና ምልክቶች በተለያየ መልኩ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡
ስሜት ፡- መጨነቅ ፣ ፍርሃት፣ ምቾት ማጣት
አስተሳሰብ ፡- ለመወሰን መቸገር፣ አለመረጋጋት፣ ሥፋት ፣ መርሳት ፣
ሰለአንድ ጉዳይ ያለማቋረጥ ማሰብ፣
ፀባይ/ባሕርይ፡- ማልቀስ፣የንዴት ሳቅ፣ በጥፊ መምታት፣
አካላዊ፡- የጡንቻ መኮማተር፣ እጅን ማላብ ፣ ራስምታት፣
ብዙውን ጊዜ ጭንቀትን ሊያመጡ ከሚችሉ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉት
ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
 የዘመድ ወይም የጓደኛ መሞት
 የሥራ ማጣት
 ፍቅር
 ከፈተና መውደቅ
 የኑሮ አለመመቻቸት
 የገንዘብ ችግር
 ያልተፈለገ እርግዝና
 የሥነ ልቦና ጫናን ለመቋቋም ከምናደርጋቸው ጥረቶች የሚከተሉት በዋንኛነት ሊጠቀሱ
ይችላሉ፡፡
 የሥነ ልቦና ጫና ምንጭና የምንሰጠው ምላሽ በዝርዝር መፃፍ፣
 የሥነ ልቦና ምንጭና ምላሽ ከተለየ በኋላ እንዴት ባህሪያችንን ልንለውጥ እንደምንችል
ማወቅ
 የሥነ ልቦና ጫና የመቋቋሚያ ዘዴዎችን መጠቀም፣
 አካላዊ፣
 አዕምሯዊ
 ራስን የማዝናናት ዘዴዎች ፣
ማህበራዊ ክህሎት ፣
ውጤታማ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ
ዓላማ
 ተሳታፊዎች የኮሚኒኬሽን ምንነትና ምን ምን ነገሮችን እንደሚያካትት ማስረዳት ይችላሉ፡፡
 ቀን ተቀን የምንገለገልባቸዉን የኮሚኒኬሽን ዓይነቶችን መዘርዘር ይችላሉ፡፡
 ውጤታማ የሆነ የኮሚኒኬሽን ባህሪያቶችን መዘርዘር ይችላሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
 በግል የሚከናወን ሥራ
የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች፣
 ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ጥቂት ወረቀቶች
 በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣
 አመቻቾች አራት ተሳታፊዎችን በመምረጥ በተሳታፊዎች ፈት ወጥተው ወደ ተሳታፊዎቹ ፊታቸውን አድርገው እንዲቆሙ ያደርጋሉ፣
 ሌሎች ተሳታፊዎች መመልከት እንጂ መናገር የለባቸውም ከፊት ለፊት ያሉትን አራት ተሳታፊዎች ለመምራት መሞከር የለባቸውም፣
 በተሳታፊዎቹ ፊት ለቆሙት አራት ተሳታፊዎች አንዳንድ ገጽ ወረቀት ይሰጣቸዋል፡፡ እነዚህ ተሳታፊዎች ማክበር የሚገባቸው ደንብ ይገለጽላቸዋል፡፡ ይህም አንደኛ
መልመጃው መጠናቀቁ እስኪገለጽላቸው ድረስ አይናቸውን መክፈት ክልክል መሆኑንና ሁለተኛው ደግሞ የሚነገሩትን መመሪያዎች በጥሞና አዳምጦ መፈፀም እንጂ
ጥያቄ መጠየቅ ያለመቻሉን፣
 የሚከተሉትን ትዕዛዞች ማቅረብ፣
 የያዛችሁትን ወረቀት ለሁለት አጠፉት
 በወረቀቱ የታችኛው ክፍል በስተቀኝ የሚገኘው ማዕዘን ቀዳችሁ ጣሉ
 እንደገና ወረቀቱን ለሁለት እጠፉ
 በወረቀቱ የላይኛው ክፍል በስተቀኝ የሚገኘውን ማዕዘን ቀዳችሁ ጣሉ
 እንደገና ወረቀቱን ለሁለት እጠፉ
 በታችኛው የግራ እጅ አቅጣጫ የሚዐኘውን ማዕዘን ቀዳችሁ ጣሉ ፣
 አይናቸውን እንዲገልጡና የያዙትን ወረቀት እርስ በርስ እንዲያስተያዩና ለመላው ተሳታፊዎች እንዲያሳዩ የደረግ ፡፡
 የትኞቹን ትዕዛዛት ተሳታፊዎቹ በተለያየ መንገድ ተረዷዠው ትዕዛዞቹን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻል ነበር ?
ማህበራዊ ክህሎት
 ውጤታማ የሆነ የሃሳብ ልውውጥ

የሃሳብ ልውውጥ መረጃን የመስጠት ወየም የመቀበል ሂደት ሲሆን ይህ


ሂደት በሁለት ግለሰቦች መካከል ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች
መካከል የሚካሄድና ግቡም የጋራ መረዳት ላይ መድረስ ነው፡፡
የሃሳብ ልውውጥ ግቡ የሆነውን የጋራ መረዳት ሲያመጣ ውጤታማ
ኮሚኒኬሽን ቁልፉ በጥሞና ማድመጥ ነው ፡፡
ከላይ የቀረበው መልመጃ ቀላል የሚመስሉ ትዕዛዞችን እንኳን የተለያዩ
ሰዎተ በተለያየ መንገድ እንደሚረዱ ለማመልከት ያስችላል ፡፡
በጥሞና ማድመጥ

 በጥሞና ማድመጥ

ዓላማዎተ
 በጥሞና ማዳመጥ በግንኙነት ወቅት ወሳኝ ክህሎት መሆኑን ያስረዳሉ በተግባርም ያሳያሉ፣
የሥልጠና ዘዴ
 የቡድን ሥራ
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ማርከርና ካርድ

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 አመቻቾች ተሳታፊዎችን በሶስት ቡድኖች እንዲቧደኑ ያደርጋሉ፣
 የሚከተሉትን ሶስት የመከራከሪያ ርዕሰ ጉዳዬች እያንዳንዳቸውን በተለያየ ካርድ ላይ በመፃፍ ማዘጋጀት
 ሴት ልጅ ወንድን ለፍቅር ጓደኝነት ወይም ለትዳር መጠየቅ እና ሽማግሌ መላክ ትችላለች ወይስ አትችልም
 ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት መጀመር /ማድረግ/ ለትዳር ዝግጅት ጠቃሚ ነው ወይስ አይደለም
 አመቻቾች በሶስት ካርዶች ላይ የተዘጋጁትን መከራከሪያዎች ለአንድ ቡድን አንድ የመከራከሪያ ርዕሰ ጉዳይ
የያዘ ካርድ በመስጠት ክርክሩን ያመቻቻሉ፡፡
 አመቻቾች በየቡድኑ በመዘዋወር ክርክሩን በመከታተል በጥሞና የሚድመጥ ሁኔታ መኖር ያለመኖሩን
ይቃኛሉ፡፡
 ክርክሮቹ ከተጠናቀቁ በኋላ በጥሞና ማድመጠ ለውጤታማ ኮሚኒኬሽን ወሳኝ ተግባር መሆኑን በማስረዳት
ያጠቃልላሉ፡፡
በጥሞና ማድመጥ
 ማንኛውም የኮሚኒኪሽን ዓይነት የሃሳብ ልውውጥ/አምስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህም
 ላኪ፣
 መልዕክት ፣
 መልዕክት መላኪያ ዘዴ፣
 ተቀባይና
 የተቀባዩ ምላሽ ናቸው፡፡
 ኮሚኒኬሽን የተዋጣ እንዳይሆን የሚያስናክሉ በመላኪያ በተቀባይ መካከል ሊከሰቱ
የሚችሉ አምስት አብይት ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነሱም ተሰሚነት ለማግኘት መፎካከር፣
ቋንቋ፣ የእድሜ ልዩነት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶች፣ የባህሪና /የእምነት ሁኔታዎች
ናቸው፡፡
 የተዋጣ ኮሚኒኬሽን እንዲኖር የሚያስችሉ ዋና ዋና መርሆዎች ሰባት ሲሆኑ እነሱም
 አስተማማኝ
 የመልእከት ምንጭ
 አስተማማኝ መልዕክት ተቀባይ
 ሰለተቀባዩ ፣ በቂ እውቀት፣
 መልዕክቱን ግልጽ አድርጐ ማደራጀት
የሃሳብ ልውውጦች አራት ደረጃዎች ያላቸው ሲሆን እነሱም፣
ከራስ ጋር መነጋገር
በግለሰቦች መካከል ያለ የሃሳብ መለዋወጥ
በቡድን የሚደረግ የሃሳብ መለዋወጥና
በአካልና በሰሜት በጊዜና በቦታ የተለዩ ሰዎች ጋር የሚደረግ ናቸው፡፡
አራቱ የግንኙነት ደረጃዎች ከሚያሳትፉት ሰው ብዛትና ከሚኖራቸው
የቦታና የጊዜ እርቀት አንፃር በስዕል የማመልከት ከዚህ በታች ያለውን
የጥሩንባ ቅርጸ መጠቀም ይቻላል፡፡
ልብ ሙሉነት ፣ ለዘብተኝነትና ሞገደኛነት
ዓላማ ፣
ተሳታፊዎች ከስልጠናው በኋላ እራሳቸውን በልበ ሙሉነት የመግለጽን ክሕሎት
ይለማመዳሉ ይገብራሉ፣ የለዘብተኝነትን ፣ የልበ ሙሉነትንና የሞገደኝነት
ምንነት አውቀው በኑሯቸው ውስጥ ልበሙሉነትን ለማዳበር ይተጋሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
ትረካ የቡድን ውይይትና ጭውውት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
ማርከሮችና ፊሊፕ ቻርቶች
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት፣
ተሳታፊዎች ቡድን ይመሰርታሉ ፣
ከቡኑ አባላት መካከል አንድ አንድ ተሳታፊዎች በምረጥ ያሚከተለውን ትረካ
እንዲያነቡ አድርጉ፣
ልብ ሙሉነት ፣ ለዘብተኝነትና ሞገደኛነት
ዘሀራ በአንድ ድርጅት ውሰጥ በጊዜያዊ ፀሐፊነት ተቀጥራ የምትሠራ የ2ዐ ዓመት ወጣት
ነች ፡፡ አንድ ቀን አለቃዋ ለተከታዩ ቀን ስብሰባ የሚደርስ በርካታ ሥራዎችን
በአስቸኳይ እንድትሠራ አዘዛት ፡፡ ተቀብላ እንዳትሰራ ከሥራ መውጫ ስዓቷ
ደርሷል፡፡
ስለዚህ ባለው አጭር ጊዜ ሥራውን መጨረስ እንደማትችል ለአለቃዋ ገለፀች አለቃዋም
ሥራው አስቸኳይ መሆኑን በአፅንኦት በመናገር ሁለት አማራጮችን ሰጣት ፣
 አምሽታ ሥራውን እንድትጨርሰው፣
 ቤቱ ሄዳ በግል ኮምፒውተሩ እንድትሠራ ፣
ይህን ማድረግ የማትችል ከሆነ ከሥራ እንደምትሰናበት አስታወቃት፡፡ ዘሀራ ምን
ታድርግ? አልሠራም ካለች ከሥራ ተባራ ራሷንና ቤተሰቧን ትጎዳለች ፡፡ የተሰጧትን
አማራጮች ከተቀበለች ተገዳ በመደፊር በኤች አይ ቪ እና የአባላዘር በሽታዎች
ልትጋለጥ ትችላለች ምን ታድርግ ?
 ለዘብተኝነትና ቁጡነት ከልበሙሉነት ጋር ተፃራሪነት ያላቸው ሁለት
በተቃራኒ ፅንፍ ላይ የሚገኙ ባህሪያት ናቸው፡፡ ለዘብተኝነት አንድ ሰው
ተገቢ ያልሆኑ የሌሎች ሰዎች ሀሳቦችን ወይም ድርጊቶችን በቸልታ
እንዲቀበል ወይም እንዲመለከት የሚያደርግ ከዝቅተኛ የመግባባት ክህሎት
ወይም ከፍርሃት የሚመነጭ ባህሪ ነው፡፡ ለዘብተኛ ሰው ሰህተቶች
ሲፈፀሙ የማረሚያ ሀሳብ ከማቅረብ ይቆጠባል፡፡ ትችቶችን ለመሰንዘርና
የማረሚያ ሀሳብ ለማቅረብ ድፍረት የለውም ለዘብተኛ ሰው በደል
ቢፈፀምበት እንኳ ሆድ ይፍጀው ብሎ መቀበልን ይመርጣል፡፡
 ቁጡነት ከለዘብተኝነት የሚለይ ቢሆንም በመግባባት ላይ የተመሰረተ
ውጤትን ለማምጣት የሚያስችል ጥቅም የለውም፡፡ መቆጣት በብስጭትና
ስሜትን መቆጣጠር ካለመቻል የሚመጣ ግልፍተኝነት በመሆኑ በሰዎች
መካከል የሚፈጠር አለመግባባትን ለመፍታት ወይም የመግለጽና ሌሎችን
የማስረዳት እንዲሁም የሌሎችን ሀሳብ የመረዳት አቅም በማዳከም ጐጂ
ውጤት ሊያስከትል ይችላል፡፡
ልበሙሉነት ማስተዋልና በራስ መተማመን ላይ የተመሰረተ ፣ ሀሳብንና
አቋምን ያለምንም ጥርጣሬና ፍርሃት በተረጋጋ መንፈስ የመግለጽ ችሎታ
ነው፡፡ ልበ ሙሉ ሰው ስህተቶች ሲፈፀሙና ጥርጣሬና ፍርሃት በተረጋጋ
መንፈስ የመግለጽ ችሎታ ነው፡፡
ልበ ሙሉ ሰው ስህተቶች ሲፈፀሙና መብቱ ሲጣስ በቸልታ
አይመለከትም፡፡ ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት አይቆጣ ሊሆን የሚችል ጥረት
ያደርጋል፡፡ መግባባትን ለመፍጠር ይደራደራል፡፡ በድርድር ሂደት የሰዎችን
ሀሳብ ይቀበላል፣ የራሱንም ሀሳብ እንዲቀበሉት ያደርጋል፡፡ ልበ ሙሉነት
በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ክህሎት ነው፡፡
ተነሳሽነት የማጣት ባህሪ መገለጫዎች
ለሌሎች ፍላጎት መሽነፍ፣ አንድ ሰው የሚፈልገውን ነገር ሳይጠይቅ
ለማግኘት መመኘት /መፈለግ/
መብትን ለማስከበር ምንም እርምጃ ያለመውሰድ
ራስን በመጉዳት የሌሎችን ጥቅም ማስቀደም
ሌሎች የሚፈልጉትን ማድረግ
አንድ የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥም በዝምታ መያዝ
አብዝቶ /ደግሞ ደጋግሞ/ ይቅርታ መጠየቅ
ተሸናፊነት፣ ለምሳሌ በዝግታ መናገር፣ የጭንቀት ሳቅ፣ ትከሻ መስበቅ፣
ክርክሮችን /ያለመግባባትን/ ማስወገድ፣ ፊትን በእጅ መሸፈን
ልብ ሙሉነት ፣ ለዘብተኝነትና ሞገደኛነት
ዓላማ ፣
ተሳታፊዎች ከስልጠናው በኋላ እራሳቸውን በልበ ሙሉነት የመግለጽን
ክሕሎት ይለማመዳሉ ይገብራሉ፣ የለዘብተኝነትን ፣ የልበ ሙሉነትንና
የሞገደኝነት ምንነት አውቀው በኑሯቸው ውስጥ ልበሙሉነትን ለማዳበር
ይተጋሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
ትረካ የቡድን ውይይትና ጭውውት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
ማርከሮችና ፊሊፕ ቻርቶች
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት፣
ተሳታፊዎች ቡድን ይመሰርታሉ ፣
ከቡኑ አባላት መካከል አንድ አንድ ተሳታፊዎች በምረጥ ያሚከተለውን ትረካ
እንዲያነቡ አድርጉ፣
 ትረካ
 ዘሀራ በአንድ ድርጅት ውሰጥ በጊዜያዊ ፀሐፊነት ተቀጥራ የምትሠራ የ2ዐ
ዓመት ወጣት ነች ፡፡ አንድ ቀን አለቃዋ ለተከታዩ ቀን ስብሰባ የሚደርስ
በርካታ ሥራዎችን በአስቸኳይ እንድትሠራ አዘዛት ፡፡ ተቀብላ እንዳትሰራ
ከሥራ መውጫ ስዓቷ ደርሷል፡፡ ስለዚህ ባለው አጭር ጊዜ ሥራውን
መጨረስ እንደማትችል ለአለቃዋ ገለፀች አለቃዋም ሥራው አስቸኳይ
መሆኑን በአፅንኦት በመናገር ሁለት አማራጮችን ሰጣት ፣ አምሽታ ሥራውን
እንድትጨርሰው፣ ቤቱ ሄዳ በግል ኮምፒውተሩ እንድትሠራ ፣ ይህን
ማድረግ የማትችል ከሆነ ከሥራ እንደምትሰናበት አስታወቃት፡፡ ዘሀራ ምን
ታድርግ? አልሠራም ካለች ከሥራ ተባራ ራሷንና ቤተሰቧን ትጎዳለች ፡፡
የተሰጧትን አማራጮች ከተቀበለች ተገዳ በመደፊር በኤች አይ ቪ እና
የአባላዘር በሽታዎች ልትጋለጥ ትችላለች ምን ታድርግ ?
 በትረካው ስር ለቀረበው ጥያቄ እራሣቸውን የታሪኩ አካል በማድረግ
ለቡድኑ ምላሻቸውን በየተራ ይሰጣሉ፡፡ መልሶቻቸው በፀሐፊዎች በኩል
ይመዘገባል፡፡ በቡድን አጠቃላይ ውይይት ይደረጋል፡፡
 በውይይቱ በለዘብተኝነት፣ በልበሙሉነትና በሃይለኝነት የተንኀባረቁ ሃሳቦች
ተለይተው ይቀርባሉ፡፡
 ከተሳታፊዎች መካከል ሁለት ሁለት ሆነው /ወንድና ሴት / ሶስት ቡድን
ይመሰርታሉ፡፡
 እነዚሁ በሶስት ቡድን የተከፈሉ ተሳታፊዎች ከጋብቻ በፊት በአቻ ግፊት
ምክንያት ስለሚቀርብ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ጥያቄ ጭውውት ያቀርባሉ፡፡
 ጭውውቶቹን አንደኛው ቡድን በለዘብተኝነት እራስን በመግለጽ ሁኔታ
ሁለተኛው ቡድን በልበ ሙሉነት እራስን በመግለጽ ሁኔታ ሶስተኛው ቡድን
በሞገደኝነት እራስን በመግለጽ መልክ ጭውውት ያቀርባሉ፡፡
 በቀረበው ጭውውት ላይ በሁሉም ተሳታፊዎች ውይይት ይደረጋል፡፡
 በጭውውቱ ዙሪያ የጋራ ግምገማ ይካሄዳል፡፡
ልበ ሙሉነት ራስን የመግለጽ ባህሪያት (Assertive behavior)
ማስፈራራት በማይመለስ ወይም እብሪት ባልተሞላበት መልኩ በትክክል
ምን እንደምትፈልግ ወይም እንደምትፈልጊ ሌሎች በገልጽ እንዲያውቁት
መንገር፡፡
የሌሎችን መብት ሳይነኩ የራስን መብት ለማስከበር ታጥቆ መነሳት ለዚህም
መቆም
ራስንና ሌሎችንም ማክበር
ዮሚገባ ማዳመጥና መናገር
አዎንታዊና አሉታዊ ስሜቶችን በአግባቡ መግለጽ
ሌሎችን ሳይገፋፉ በራስ የመተማመን ሁኔታን ማንፀባረቅ
ሚዛናዊ አቋም መያዝ፡- ምን ማለት እንደምትፈልግ አውቀህ
“እንደሚመስለኝ” በማለት ፈንታ “እንደሚሰማኝ” በማለት ግልጽ መሆን ፡፡
“እኔ” በማለት ፤ፊት ለፊት እያዩ መናገር፣ ያለማንጓጠጥና ያለማሽሟጠጥ፤
እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ቋንቋን መጠቀም፣ ለያዙት አላማና አቋም
በጽናት መቆም ፣ አቋምን ማንፀባረቅ
የቁጡነት / ሞገደኛ ባህሪ (Aggressive behavior)
ሌሎችን በመጫንና በማስፈራራት መልኩ የራስን ስሜትና አስተሳሰብ
መግለጽ
ለሌሎች ሰዎች መብት መከበር ምንም ትኩረት ሳይሰጡ የራስን መብት
ለማስከበር መጣር
በሌሎች ኪሳራ ራስን አስቀድሞ መገኘት
ሌሎችን ከሰልጣን ስር ለማዋል መሞከር
በሌሎች ኪሳራ ከራስ ግብ ለመድረስ መጣር
መጫን፡- ለምሳሌ መጮህ ፣አምጡ ስጡኝ ብሎ መጠየቅ ፣ ሌሎችን
ያለማዳመጥ፣ ሌሎችን ተሳስታችኋል ማለት፣ ሌሎች ላይ ማፍጠጥ፣ ዝቅ
አድርጎ ማየት ፣ በሌሎች ላይ ጣት መቀሰር ወይም መዛት ፣ ማስፈራራት
ወይም መደባደብ፡፡
የአቻ ግፊትን መለየትና መቋቋም

ዓላማዎች፣
 ተሳታፊዎች ከአቻዎቻቸው የሚሰነዘሩ የአቻዎችን ግፊት ይረዳሉ፡፡
 የአቻዎችን ግፊት ሁኔታ ተረድተው ተገቢን እርምጃ በመጠቀም እራሣቸውን ከአሉታዊ ተጽዕኖዎች
ይከላከላሉ፣
የሥልጠና ዘዴ፣
 በግል ማሰላሰልና የቡድን ውይይት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፊሊፕ ቻርት ፣ማርከር፣ ደብተርና እስክሪብቶ፣
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት
 ተሳታፊዎች በአነስተኛ ቡድን በመክፈል ክብ ሰርተው እንዲቀመጡ አድርጉ
 የአቻዎችን ግፊት ለማሳየትና ለመረዳት እንዲችሉ ልምምድ እንደሚሰሩ ይነገራቸው፡፡
 እያንዳንዱ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ከአቻዎቻቸው ጋር በነበራቸው ግንኙነት ያዩትን፣ የተማሩትን እና
የተገበሩትን አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ባህሪ አመለካከትና ድርጊት በግላቸው እንዲዘረዝሩ አድርጉ፡፡
 አዎንታዊ አሉታዊ


 ለምሳሌ ፣ አዲስ ቃላቶች ወይም አባባሉች የአለባበስ ዓይነቶች የተለያዩ ልምዶች
ወዘተ…
 በግል የገለጿቸውን ነገሮች ከአቻዎቻቸው እንደዴት እንደተማሩ እንዲያብራሩ
ጭምር ይገልጽላቸው፣
 በግል ያስላስሉትንና የፃፉትን በመያዝ በክብ ለተቀመጡ ጓደኞቻቸው በመግለጽ
ውይይት ያደርጋሉ፡፡
 የቡድን ውይይቱ እንደተጠናቀቀ ተሳታፊዎች በቡድን ወኪሎቻቸው አማካኝነት
ለመድረክ በማቅረብ ይወያያሉ፡፡
 አመቻቾች ውይይቱን ለማጠቃለል የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠቀም
 ከአቻዎቻችሁ በተማራችኋቸው ነገሮች ተደነቃችሁ? ለምን?
 ከአቻዎቻችሁ ለሚደርስባች ጫና ወቅታዊ ምላሽ ሰጥታችሁ ነበር ?
 የተማራችኋቸውን ነገሮች ስታስቡ ምን ተሰማችሁ?
 ከአቻዎቻችሁ ምን ጥሩ ነገር ተማራችሁ?
 ከአቻቻቻችሁ የወሰዳችሁት ግን ልታስወግዱት የሚገቡ ነገሮች ምን ምን ናቸው ?
 በነዚህ ዙሪያ በማወያየት ፕሮግራሙን አጠቃሉ?
ግጭትን መፍታት

ዓላማዎች፣
 በማህበረሰባቸው ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን በመለየት ግንዛቤ ያገኛሉ፡፡
 ግጭትን ለመፍታት የሚጠቅሙ ክህሎቶችን ተረድተው መጠቀም ይጀምራሉ፡፡
 ግጭትን በመፍታት ላይ ያላቸውን ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፣
 የቡድን ሥራ እና የግል ክንውን
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፍሊፕ ቻርትና ማርከር
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት
 ድርጊት አንድ፣ የቡድን ሥራ
 አመቻቾች ተሳታፊዎችን በቡድን በመክፈል በህብረተሰባቸው ውስጥ የሚታዩ የግጭት ዓይነቶችን ለይተው
በማውጣት፣ ለግጭቶቹ መፍጠር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን፣ በህብረተሰባቸው ውሰጥ ያሉ የግጭት
መፍቻ ዘዴዎችንና ግጭቶቹን ለመፍታት ማህበረሰቡ የሚጠቀማቸው ዘዴዎች ላይ እንዲወያዩ ያደርጋሉ፡፡
 ተሳታፊዎች የተወያዩቡትን ርዕሰ ጉዳዬች በፊሊፕ ቻርት ላይ በማስፈር በተወካየቻቸው በኩል ለሁሉም
እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡
 በቀረቡት ላይ አጠቃላይ ውየይት ይደረጋል፡፡
 አመቻቾች ከተሳታፊዎች የቀረቡትን ሃሳቦች ላይ አፅንኦት በመስጠት የማጠቃለያ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡
 የአመቻቾች ማስታወሻ
 ግጭቶች በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በማንኛውም የዕድሜ ክልል በሚገኙ ሰዎች መካከል መፈጠራቸው
የማይቀር ቢሆንም ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ኑሮን አፍራሽ የሆነ ችግር ሳያስከትሉ ለማስወገድ
ይረዳል፡፡
 ግጭቶችን በመፍታት ሂደት ውስጥ በሥራ ላይ የሚውሉ አራት የግጭት መፍቻ ዘዴዎች አሉ፡፡
እነሱም አስታራቂነት፣ ቁጣን ማብረድ፣ መደራደርና አማላጅነት ናቸው፡፡ እነዚህ አራት ዘዴዎተ
እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉና ግጭትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፍታት ደረጃ በደረጃ ሥራ ላይ
የሚውሉ ናቸው፡፡
 ገጭቶች ተካረው ወደ አምባጓሮና ኃይልን ወደ መጠቀም ሲያመሩ ቁጣን የማብረድ ዘዴ ሊያገለግል
ይችላል፡፡ ዘዴው ስሜታቸውን መቆጣጠር ያቃታቸውን ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ
አዕምሯቸው ተመልሰው ከኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ ለማድረግ የሚያገለግል ነው፡፡
 ቁጣን የማብረድ ተግባር በሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት የሚፈፀም ሊሆን ይችላል፡፡ በግጭት ውስጥ
ባሉ ወገኖች ተነሳሽነትም ይፈጽማል፡፡
 አማላጅነት በግጭት ውስጥ ካሉ ወገኖች የአንደኛውን ፍላጎት በውክልና ወደ ሌላው ወገን ሄዶ
በማማለድ ግጭትን ለመፍታት ሥራ ላይ የሚውል ዘዴ ነው፡፡ ይህ በተለይ በደል ፈጽሜያለሁ ብሎ
የሚያምን ወገን ወደ ሌላው ወገን የይቅርታ ጥያቄ የሚያቀርብበት መንገድ ነው፡፡
አሳቢነት ወይም ሀዘኔታ

ዓላማዎች ፣
 ለሌሎች አሳቢነት ወይም ሀዘኔታን በተውኔት መልክ መግለጽ ይችላሉ፡፡
 በዕለት ከዕለት ሕይወታቸው ውሰጥ የአሳቢነት ወይም ሀዘኔታን (Empathy ) ጠቀሜታ ይረዳሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ
 ጭውውት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፍሊፕ ቻርትና ማርከር
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት፣
 የተግባር ልምምድ ፣ ክፍል አንድ
 ሁሉም ተሳታፊዎች ወደ መሃል እንዲመጡ ማድረግ ፣
 ሁሉም የቀኝ እግር ጫማቸውን አውልቀው እንዲያስቀምጡ ማድረግ ፣
 ያወለቁትን ጫማዎች በመደባለቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ከራሳቸው ጨማ ውጭ የሌላ ሰው ጫማ እንዲያደርጉ
ትዕዛዝ መስጠት ፣
 ሁሉም ተሳታፊ የሌላ ሰው ጫማ አድርጐ ሲንቀሳቀስ የተስማቸውን ስሜት እንዲገልጽ ማድረግ፣
 ተሳታፊዎች ከዚህ ጨዋታ ምን እንደተማሩ መጠየቅ፣
 ተሳታፊዎች የሌላ ሰው ጫማ አድርገው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ሁሉም ምቾት በሌለው ሁኔታ እንደነበሩ
ሊገልጽ ይችላል ፡፡ ምን አልባትም የሌላ ሰው ጫማ ማድረግም የማይፈልግ ተሳታፊ ሊኖርም ይችላል፡፡ አዘኔታ
ወይም ርህራሄ የምንለው የተቸገረ ሰው ስናይ በውስጣችን የሚፈጠረውን ስሜት ነው፡፡ የተቸገረ ሰው አይተን
ውስጣችን ርህራሄ ተሰምቶን ችግረኛውን ሰው ለመርዳት ዋ ገእስከመክፈል ድረስ ልንሄድ እንችላለን ፡፡ ይህም
ነገር ልክ እንደ ጫማው ጨዋታ አስደሳች ላይሆን ይችላል፡፡
የተግባር ልምምድ ፣ ክፍል ሁለት
 በዚህ ክፍለ ጊዜ ተሳታፊዎች በአዘኔታ/ በርህራሄ ስሜት የተለያዩ ሰብአዊ አገልግሎት ለመስጠት እንዴት እንደሚችሉ
አጫጭር ተውኔት በመስራት ሊለማመዱ ይችላሉ፡፡
 ለምሰሌ፣
 ሣራ እናቷን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ያጣች ወጣት ተማሪ ነች ሁልጊዜ የእናቷ ስቃይና ህመም በህሊናዋ እየመጣባት ትጨነቃለች
፣ ታስባለች ፡፡ ከእዚህም የተነሳ የምግብ ፍላጐቷ ቀንሷል፣ የሰውነት ክብደቷም ቀንሷል፡፡ ጐረቤትና የትምህርት ቤት ጓደኞቿ
ግን ሣራ እራሷ የኤች አይ ቧ ቫይረስ በደሟ ውስጥ አለ በማለት አግልለዋታል፡፡ ሣራ ግን ተመርምራ ኤች አይ ቪ እንደሌለባት
ታውቃለች፡፡፡ እናንተ የሣራ እውነኛ ጓደኛ ብትሆኑ በእንዴት አየነት ሁኔታ ሣራን ልትረዷት እንደምትችሉ አስመስላችሁ
ተጫወቱ፡፡
 አዘኔታ/አሳቢነት

ትምህርታዊ ጨዋታ
 ሶስት ተሳታፊዎች ወደ መድረክ እንዲወጡ ማድረግ፣
 ከተሳታፊዎቹ አንዱ ድንገት እንዲወድቅ ማድረግ፣
 አብረውት ያሉት የሚያደርጉትን እርዳታ መመልከት፣
 ከተመልካቹ መሀል ለእርዳታ ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነት እንዲሄዱ ማድረግ፣

የመወያያ ነጥቦች
 ሁሉም ተሳታፊ ስለወደቀው ልጅ ምን ተሰማቸው ?
 ተሳታፊዎች ከዚህ ጨዋታ ምን እንደተማሩ መጠየቅ?
 የወደቀውን ልጅ ለመርዳት ጓደኞቹ እና ሌሎች ምን ያህል ደነገጡ ?አዘኔታ ወይም ርናራሄ ተሰምቶን ችግረኛውን ሰው
ለመርዳት ምን ያህል ተሳተፍን ?
መደራደር
ዓላማዎች
 ተሳታፊዎች መደራደር ምን ማለት እንደሆነ ግንዛቤ ያገኛሉ
 ውጤታማ ድርድር ለማካሄድ የሚረዱ አስፈላጊ ነጥቦችን ያውቃሉ ለሌሎችም ያስረዳሉ
 የተለያዩ ችግሮችን በመደራደር ለመፍታት የሚያስችላቸውን ብቃት ያዳብራሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ፣
 ድራማ
የሚያስፈልጉ ማቴሪሎች፣
 ማርከርና ፊሊፕ ቻርት
ደረጃ በደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት
 አመቻቾች ተሳታፊዎችን ደረጃ በደረጃ ይከፋፍሉ፣
 የመከራከሪያ ነጥቦች ለየቡድኖቹ ይስጡ፣
 ቡድኖች ዋና ተደራዳሪዎቻቸውን ይምረጡ
 ዋና ተደራዳሪዎች ወደ መድረክ እንዲወጡ በማድረግ ድርድር ያድርጉ
 በድርድሩ ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ ይደረግ፣
 የተነሱ ነጥቦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አመቻቾች ማጠቃለያ ይስጡ
አመቻቾች ማስታወሻ
መደራደር በሰዎች መካከል የሚኖር ግንኙነትና የአንድን ሰው መርህ
ሳይነኩ ወይም ሳይጋፉ እንደአስፈላጊነቱ ለመለወጥ ዝግጁ መሆንን
ያጠቃልላል፡፡
አለመግባባት ምናልባት አደገኛ፣ አስፈሪና ብቀላን ሊያመጣ ይችላል፡፡
በምንደራደርበት ጊዜ በሚገባ መገንዘብ ያለብን ነገር
ልበ ሙሉ መሆን
እሴቱን ማወቅ
እምነትን ማወቅ
የሕይወት መመሪያን ማወቅ
ሌላውን ሰው ማክበር አለመናቅ
አዘኔታና ርህራሀ ሊኖረን ይገባል፡፡
የውሳኔ አሰጣጥ ክሕሎት

በጥልቀት ማሰብ
ዓላማዎች
 በጥልቀት የማሰብ ዘዴ ምንነትና ጠቀሜታ ይረዳዩ፣
 የጥልቀት የማሰብ ክህሎት ያዳብራሉ፣
 የጥልቀት የማሰብ ክህሎት ኤች አይ ቪ/ኤድስ ነክ እና ሌሎች ተዛማጅ ችግሮችን ለመፍታት ይጠቀሙበታል
የሥልጠና ዘዴ፣
 በጥያቄና በጥሞና ማሰላሰል
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣
 አመቻቾች ፣ በጥቁር ሠሌዳ/ፊሊፕ ቻርት ላይ ዘጠኝ ነጥቦች በሚቀጥለው መልኩ ይሰላሉ፡፡
ተሳታፊዎች በሚከተሉት መመሪያዎች መሠረት ዘጠኙን ነጥቦች ያያይዛሉ፡፡
 እስክሪፕቶ፤ ማርከር በመጠቀም በመረጡት አንዱ ነጥብ ላይ ያሳርፋሉ፣ ካሳረፋ በኋላ እጃቸውን ማንሳት/ ማንቀሳቀስ
የለበቸውም፤
 አንድ ጊዜ በየትኛውም አቅጣጫ ማስመር ከጀመሩ፤ በመስመሩ ላይ ወደ ኋላ መመለስ አይችሉም፤
 መስመር ቀጥተኛ እና ከአራት መስመር መብለጥ የለበትም፤
 አመቻቾች ታሳታፊዎቹ ነጥቦቹን ለማገናኘት ከተለመዱት አካሄዶች ወጣ ብለው እንዲያስቡና የራሳቸውን ፈጠራዊ
አስተሳሰብ እንደያጎለብቱና እንዲጠቀሙ ማበረታታት አለባቸው፡፡
 ፈጠራን እንዲያጎለብቱና እንዲጠቀሙ ማበረታታት አለባቸው፡፡
የውሳኔ አሰጣጥ ክሕሎት
 በጥልቀት ማሰብ

ዓላማዎች
በጥልቀት የማሰብ ዘዴ ምንነትና ጠቀሜታ ይረዳዩ፣
የጥልቀት የማሰብ ክህሎት ያዳብራሉ፣
የጥልቀት የማሰብ ክህሎት ኤች አይ ቪ/ኤድስ ነክ እና ሌሎች ተዛማጅ
ችግሮችን ለመፍታት ይጠቀሙበታል
አዲስ ነገርን ለመፍጠር የሚያስችል አስተሳሰብ

ዓላማዎች
ተሳታፊዎች ፊጠራዊ የማሰብ ክሂል ምን ጠቀሜታ እንዳለው ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
ተሳታፊዎች ፈጠራዊ የማሰብ ክሂል በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ያለውን ጠቀሜታ
መዘርዘር ይችላሉ፡፡
የሥልጠና ዘዴ ፤
የቡድን ውይይት
የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች ፣
 ፊሊፕ ቻርትና ማርከር
በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣
ተሳታፊዎችን በቡድን ማደራጀት
ከቡድን አባላት መካከል አንዳንድ ተሳታፊ በመምረጥ የሚከተለው ትረካ
እንዲያቀርቡ አድርጉ ፡፡
አዲስ ነገርን ለመፍጠር የሚያስችል አስተሳሰብ

 ትረካ …
 የርግብና የማሰሮ ውሃ
ርግቧ በከረረው ፀሐይ በጣም ውሃ ጠምቷት ነበር፡፡ ውሃ ለማግኘት
በአካባቢዋ ከሚገኙ ሰዎች መኖሪያ አካባቢ ብትሄድም ምንም ልታገኝ
አልቻለችም፡፡ ይናንን ውሃ ለመጠጣት ወደ ማሰሮው ቀረበች በማሰሮው
አፍ ላይ ሆና አፏን ወደ ውሃው አቀረቀረች፡፡ አፏ ወሃው ጋር ሊደርስ
አልቻለም በተደጋጋሚ ሞከረች ልትደርስ የቀራት ጥቂት እንደሆነ
ተረዳች፡፡ ከዚያም ውሃውን እስኪበቃት መጠጣት ቻለች፡፡
 ይህ ትረካ የፈጠራ ክሂል ከሚለው ጋር ምን ተካምዶ አለው
 የፈጠራ ክሂል ማዳበር ምን ጥቅም ያስገኛል ?
የርግብና የማሰሮ ውሃ

. ………………...
ఝఝఝఝఝఝ
ఝఝఝఝఝఝ
ఝఝఝఝఝఝ
ఝఝఝఋయయ
యయఝఝఝఝ
መልመጃ ሁለት
 አመቻቾች የሚከተለውን የፈጠራ ክህሎት መልመጃ እንደሚከተለው በፊሊፕ ቻርት
በመጻፍ ተሳታፊዎች በግላቸው እንዲመልሱ ያደርጋሉ
 አንድ እናት ከገበያ 8 ሊትር የሚይዝ የገዙትን የምግብ ዘይት ከጐረቤታቸው ጋር
እንድካፍላቸው ጠየቀቻቸው፡፡ ዘይቱ እኩል አራት አራት አራት ሊትር ለማካፈል
ፈለጉ ይሁን እንጂ ይህንን ለማከፈል የሚረዳ ማከፋፈያ ዕቃ አልነበራቸውም
በቤታቸው የነበራቸው ባለ 5 ሊትርና ባለ 3 ሊትር ጀሪድኖች ብቻ ነበሩ፡፡ ታዲያ
እንዴት አድርገው እነዚህን ሶስት ጄሪካኖች ብቻ በመጠቀም እኩል ሊከፍሉ
ይችላሉ፡፡

8 ሊትር 5 ሊትር 3 ሊትር


ችግሮችን የመፍታት ክህሎት

ዓላማዎች፣
 ሠልጣኞች ችግሮችን በዝርዝር ያሳያሉ
 የችግር ማስወገጃ መንገዶችንና ደረጃ ያውቃሉ
 ችግሮችን በተገቢ ሁኔታ ለማሥወገድ የሚያስችል ክህሎት ያዳብራሉ

የሥልጠና ዘዴ፣
 የቡድን ውይይት

የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች
 ፍሊፕ ቻርትና ማርከር

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት፣


 ተሳታፊዎችን በአነስተኛ ቡድን ማዋቀር
 የቡድኑ አባላት በሚሃሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ጎልተው የሚታዩ አምስት ችግሮች ዘርዝሩ
 የችግሮቹን ምንጮች ተራ በተራ ለመረዳት ይሞክሩ
 ችግሮቹ በግልም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ የሚያስከትሉትን ጉዳት በአጭር በአጭሩ ያብራሩ
 ችግሮቹን እንደአሳሳቢነታቸው በደረጃ ይለዩ
 ችግሮቹን ለመፍታት ምን መደረግ እንደሚያስፈልግ ይዘርዝሩ
 ቡድኖቹ በተወካዬቻቸው አማካኝነት ለጥያቄዎቹ የሰጧቸውን መልሶች ለጠቅላላ ተሣታፊ ያቅርቡ
 አመቻቾች የአመቻቹን ማስታወሻ በመጠቀም ቡድኖቹ ባቀረቧቸው መልሶች ላይ በቂ ገለፃ በማድረግ ክፍለ ጊዜውን ያጠቃሉ፡፡
ችግሮችን የመፍታት ክህሎት
 ችግሮችን የመፍታት ክህሎት
 ችግሮችን የመፍታት ክህሎት የሰው ልጅ በኑሮ ሂደት ውስጥ ባዳበራቸው መሠረታዊ ክህሎቶች
አንዱ ነው ከቀላል እስከ ከባድ የኑሮ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ማድረግ ሰዎች ለመኖር
የሚያደርጉት ትግል አካል ነው፡፡
 ደረጃው ይለያያል እንጂ ሰዎች ሁሉ ችግሮች ይኖሯቸዋል፡፡ ከችገሮቹ ለመውጣትም የማያቋርጥ
ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ችግሮቹ የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን መፍትሄዎቻቸውም የሚጠየቀው
ጊዜና አቅም ይለያያል
 ችግርን በመፍታት ሂደት ልንከተለው የሚገባ መሠረታዊ አካሄድ፣
 ችግሩን ለይቶ ማወቅና መረዳት
 ለችግሩ መከሰት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በጥልቀት መለየት
 ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል አማራጭ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መንደፍና መወሰን
 የችግሩን ሥር/ምንጭ ለማስወገድ የሚያስችል አቅምና ሃብት ማሰባሰብ
 ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ችግሩን መፍታት ሂደቱን በመገምገም መማር
 የሥራ አጥነት ችግርን በመፍታት ሴተኛ አዳሪነትን መቀነስ፣ ሴቶችንና ወንዶችን ከተረጂነት
ማላቀቅ፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስን ሥርጭት መግታት ይታላል፡፡
 የማህበረሰቡን ችግሮች በመፍታት ሂደት ውስጥ አንገብጋቢ የሆኑትንና መፍትሄ ሊሰጣቸው
የሚችሉትን ለይቶ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡
 ችግሩን የመፍታት ክህሎትን ማበልጸግ፣ ወጣቶች ለራሣቸውና ለህብረተሰባቸው ችግሮች መፍትሄ
ውሣኔ መስጠት
ዓላማዎች
 የውሣኔን ምንነት ይረዳሉ
 ውሣኔ ለመስጠት የሚረዱ ደረጃዎችን ይረዳሉ
 ውጤታማ የሆኑ ውሣኔዎችን ለመወሰን የሚያስችሉ ክህሎት ያዳብራሉ

የሥልጠና ዘዴ፣
 በጥሞና ማሰላሰልና የቡድን ውይይት

የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች፣
 ፍሊፕ ቻርት፣ ማርከርና ካርዶች፣

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ፣


 ተሣታፊዎችን በአነስተኛ ቡድን ማዋቀር ፣
 ተሣታፊዎች ለሚከተሉት ጥያቄዎች በግላቸው መልስ እንዲሰጡ በጥሞ የማሰላሰያ ጊዜ ይሰጣቸው፣
 ውሣኔ ምንድ ነው
 ውሣኔ ላይ እንዴት ይደረሳል
 እስከዛሬ ውሣኔዎችን ስንወስን ምን ምን ነገሮችን እንጠቀም ነበር
 ባሳለፍነው ውሣኔ ተጸጽተን እናውቅ ይሆን ለምን
 በጥሞና ጊዜ ያገኙትን ውጤት ይዘው በየቡድናቸው ውይይት በማድረግ ሃሳባቸውን በፍሊፕ ቻርት ያዘጋጃሉ፡፡
 አመቻቾች ለየቡድኑ በካርድ ላይ ጽፈው ያዘጋጁትን የውሣኔ ነጥብ ለየቡድኑ ያድሉ፡፡
 የቡድን አባላት በጉዳዩ ላይ እንዲወያዩና ውሣኔ ለመስጠት ምን ምን ደረጃዎች ሂደቶችን እንደሚከተሉ ተወያይተው እንዲመዘግቡ ያደርጋሉ
 በየቡድኑ ሊከተሉ ያሰቡትን ደረጃዎች ሂደቶች በፍሊፕ ቻርት ላይ በዝርዝር ውሣኔ እንዲያሣልፍ ያደርጋሉ፡፡
 በቡድን ተወካዬች አማካኝነት ለጠቅላላ ተሣታፊ እንዲቀርብ በማድረግ አመቻቾች የአመቻቹን ማስታለሻ በመጠቀም ክፍል ግዜውን ያጠቀልሉ፡፡
ውሣኔ መስጠት
 ውሳኔ የሰው ልጅ በዕለት ከዕለት ኑሮው ውስጥ የሚያጋጥሙት ችግሮችና ምርጫዎች ለመፍታት የምንጠቀምበት አንድ የህይወት
ክፍል አይነት ነው፡፡

ውሳኔ ለመስጠት ክህሎት የሚዳብረው የሚከተሉትን ነጥቦች በየደረጃው በመተግበርና ልምድ አድርጐ በመውሰድ ይሆናል፡፡
 ውሣኔ ለመስጠት የፈለግነውን ጉዳይ መለየትና በጥልቀት መገንብ ፣
 በቂ ጊዜ መውሰድ፣
 ስለ ጉዳዩ በጥልቀት ማሰብ
 ከሌሎች ምክር መጠየቅ፣
 የሚሰጠውን ምክር በጥንቃቄ ማዳመጥ ፣ በጉዳዩ ዙሪያ በቂ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣
 መጸለይ/እረፍት መውሰድ፣
 የቤተሰብና የማህበረሰብ እሴቶችን ከግንዛቤ ማሰገባት፣
 ውሣኔው ለመወሰን ያሉትን አማራጮች ሁሉ በዝርዝር ለይቶ ማውጣት
 እያንዳንዱ ለመወሰን ያሉትን አማራጮች ሁሉ በዝርዝር ለይቶ ማውጣት፣
 እያንዳንዱ አማራጭ የሚያመጣውን ውጤትና የሚያሳድረውን ተጽዕኖ መገመት ማወዳደር፣
 ውሣኔው በሰዎች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ መገንዘብ
 ጥሩ የምትለውን ምርጫ ምረጠ፣
 ውሣኔህን ስጥ
 ውሣኔህን ተግባራዊ አድርግ
 ውሣኔን ተከትሎ የሚመጡ ማንኛውንም ጉዳት በኃላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ይሁን

You might also like