You are on page 1of 1

።።።የልብስ ስፌት መኪና ጉዞ!

።።።

ሠላማችሁ ብዝት ይበልልኝ ውዶቼ! የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ከጀመረ ከሁለት ሺ አስራ ዘጠኝ አመታት በላይ ሆነ
ለማለት ድፍረት የሚያጣ ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም የሀገራት ምስረታ የማይታሰብበት ዘመንን ሳይጨምር፣
የአውሮፓውያን የጨለማ ዘመን የሚል ስያሜ የተሰጠው አመታትን ሳይካትት፣ የእነ አብረሃምና ሙሴ ዘመን በቁጥር
ስሌት ማእቀፍ ሳይደመር፣ ... ... አውሮፓውያን ቀን መቁጠር ከጀመሩ ሁለት ሺ አስራ ዘጠኝን አገባደዋል። አረቦች
የዝሆን አመት (አመል ፊል) በሚል የቆጠሩትን እርግፍ አርገው ትተው በስደት (በሂጅራ) አቆጣጠር አንድ ብለው መቁጠር
ከጀመሩ እራሱ አንድ ሺ አራት መቶ ሰላሳ አራትን ተሻግረዋል። ሚስኪኗ የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ፣ የአሁኗ የውራ ውራ
ሀገራችን ኢትዮጵያ እራሷ ከሁለት ሺ አስራ አንድ መገባደጃ ድረስ መቁጠር ችላለች። ለመሆኑ በስልጣኔ የቀደመችባቸው
ጊዜያት ላይ ቀን አትቆጥርም ነበር እንዴ? ስለምን ቆጠራዋ ከአውፓውያኑ ሇላ ቀረ? እሱስ ብዙ ምክንያት አለው።
እነንጉስ ቁስጢንጢኖስ ከአንድም ሁለቴ አቆጣጠራቸውን በምክክር አሻሽለው የለ!።

የሆነው ሆኖ በዘመን ቆጠራዋ ሇላ መቅረቷ ይሁንና በስልጣኔዋ አሁን ከጀርባ የመገኘቷ እውነት ሚስጥሩ ምንድን ነው?
እዚጋ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የፃፉት የታሪክ እውነት ሃሳቡን ልጠቀም። "የጣሊያን ጠላት ጦር በተባበረ ክንድ
በስለትና በአህያ አንገት ያስደፉ አባቶች ነበሩ። ከሰላሳ ሶስት አመት በሇላ የጠላት ጦር በአየርና በመርዝ ጋዝ ጦሩን አዘምኖ
ለበቀል ሲመለስ የኢትዮጵያውያን ጦር እንደ ቀደመው በስለትና በአህያ ነበር ጠብቆ የገጠመው። ሰላሳ ሶስት አመት
ምንም አልሰራንም ማለት ነው። በተመሳሳይ በአንድ ወጥ ድንጋይ ሀውልት፣ አብያተ ክርስቲያን፣ መስጊድና ፍልፍል ዋሻ
የሰሩ የኪነ ህንፃ ጠበብት ልጆች ባለቤት ብትሆንም ኢትዮጵያ፣ ጥበቧን አዘምነው የሚያስቀጥሉ ልጆችና መሪዎች
አልታደለችም።“

እንደኔ እንደኔ እኛ ኢትዮጵያውያን ጉዞአችን እንደ ልብስ ስፌት መኪና ጉዞ በተወሰነ ርቀት ሇላና ፊት መመላለስ
ይመስለኛል። በተሰራ ነገር ላይ እየተመላለሱ ጉድለትን መጥቀም። ሳት ሲለውም ክሩን እየዘለለ በመርፌው ብቻ ጠቅጥቆ
በቀዳዳ ላይ ቀዳዳ መደመር።

እኔ እላለሁ ጉዞአችንን ከልብስ ስፌት መኪና ጉዞ አላቀን፣ ባለበት ረግጦ ከመመላለስ ተሻግረን፣ የነበረውን በማዘመን
ካልደረሰ እንደማይመለሰው የመንኮራኩር ጉዞ አይነት ፈጣን አድርገን በጋራ ታሪክ እንስራ እላለሁ። የነበረን፣ የተሰራን
ከመለጣጠፍ የልብስ ስፌት መኪና ጉዞ ተላቀን አሻሽሎ የሚሰራ በመሆን ስልጣኔያችንን ወደ ፊት እናራምድ እላለሁ።
ቸር ያሰማን! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ልጆቿን አብዝቶ ይባርክ!።

ጉራጌ ዞን፣ ወልቂጤ፣ ኢትዮጵያ!

#መ.ጀማል (ለመኖር ትግሉ)

You might also like