You are on page 1of 146

ደብረብርሃን ዩንቨርሰቲ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሁፍ (አማርኛ) ትምህርት ክፍል

የድህረምረቃ መርሃግብር

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡ የቃል ግብረመልሶች


ትንተና

(በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ

ትዕግስት አሰፋ

መስከረም 2012 ዓ.ም

ደብረብረሃን
በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡ የቃል ግብረመልሶች
ትንተና

(በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

ደብረብርሃን ዩንቨርሰቲ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሁፍ (አማርኛ) ትምህርት ክፍል

የድህረምረቃ መርሃግብር

ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያነት የቀረበ ጥናት

ትዕግስት አሰፋ

የጥናቱ አማካሪ ፡- ከበደ ይመር (ዶ/ር)

መስከረም 2012 ዓ.ም

ደብረብረሃን
«በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርቡ የቃልግብረመልሶች ትንተና፣
በ9ኛ ክፍል ተተኮሪነት» በሚል ርዕስ ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያነት በትዕግስት አሰፋ
የቀረበው ይህ ጥናት፣ የዩኒቨርስቲውን የጥራትና ወጥነት መስፈርት ስለማሟላቱ
በፈታኞች ተረጋግጦ ተፈርሟል፡፡

የፈታኞች ቦርድ አባላት፣

አማካሪ………………………………. ፊርማ……………….ቀን………………..

የውስጥ ፈታኝ ……………………… ፊርማ……………….ቀን………………..

የውጭ ፈታኝ…………………………ፊርማ……………….ቀን………………..

I
ማረጋገጫ

“በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርቡ የቃል ግብረመልሶች ትንተና፣


በ9ኛ ክፍል ተተኳሪነት” በሚል ርዕስ፣ በደ/ብርሃን ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ
ስነ- ስብ ኮሌጅ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሑፍ ትምህርት ክፍል የድህረምረቃ
መርሃግብር ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ ባቀረቡኩት ይህ ጥናት፣ከዚህ በፊት
በማንኛውም አካል ያልተሰራ የራሴ ወጥ ስራ መሆኑን፣ የተጠቀምኩባቸው
ድርሳናትም በትክክል ዋቢ መሆናቸውንና ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲም የጥናት ህጋዊ
ባለቤትነት ያለው መሆኑን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

ስም ………………………………

ፊርማ .…………………………….

ቀን ……………………………….

II
ምስጋና

በቅድሚያ ርማት በመስጠትና የአሰራር ስልቶችን በመጠቆም ክትትል ላደረገልኝ


አማካሪዬ ከበደ ይመር (ዶክተር) ምስጋናዬ የላቀ ነው፡፡እንዲሁም በሞራልና
ፅሁፉን በመተየብ ለተባበሩኝ ባለቤቴና ቤተሰቦቼ ምስጋና ይድረሳቸው፡፡ እንዲሁም
ለጥናቱ መሳካት መረጃ በመስጠት ፍቃደኛ ሆነው ለተባበሩኝ ለአንኮበር የከፍተኛ
ትምህርት መሰናዶና አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አማርኛ መምህራን
ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡በመቅረፀምስል የተቀረፀውን ምስል በማስተካከል ምስሎቹን
በቅደምተከተል በማስቀመጥ ለተባበሩኝ ለአንኮበር ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ባለሙያዎች
ምስጋናዬ ይድረስ፡፡ በመጨረሻም ጥናታዊ ፅሁፉን የተሳካ ለማድረግ
የሚያስችለኝን የገንዘብ ድጋፍ ላደረገልኝ የደ/ብርሃን ዩንቨርስቲ ምስጋና ይሁን፡፡

III
የይዘት ማውጫ

ምስጋና ................................................................................................................. III


አህፅሮተ ጥናት……………………………………………………………………………….VIII

ምዕራፍ አንድ ........................................................................................................ 1


1.1. የጥናቱ ዳራ ................................................................................................ 1
1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት............................................................................. 4
1.3. የጥናቱ ዓላማ .............................................................................................. 5
1.4. የጥናቱ ጠቀሜታ ........................................................................................ 6
1.5. የጥናቱ ወሰን .............................................................................................. 6
1.6. የቁልፍ ቃላት ፅንሰ ሃሳባዊ ፍቺ.................................................................. 7
ምዕራፍ ሁለት፣ የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት .............................................................. 8
2.1. የግብረመልስ ምንነት .................................................................................. 8
2.1.1. የቃል ግብረመልስ ምንነት ....................................................... 11
2.2. የቃል ግብረመልስ ዓይነቶች ከዓላማ አንፃር .............................................. 11
2.2.1. ገምጋሚ የቃል ግብረመልስ...................................................... 11
2.2.2. የማስተካከያ የቃል ግብረመልስ................................................ 12
2.2.3. ገላጭ የቃል ግብረመልስ ......................................................... 12
2.3. የግብረመልስ ዓይነቶች ከባህሪይ አንፃር .................................................... 12
2.3.1. አዎንታዊ ባህሪ ያለው ግብረመልስ .......................................... 12
2.3.2. አሉታዊ ባህሪ ያለው ግብረመልስ............................................. 13
2.4. የቃል ግብረመልስ ዓይነቶች ከቋንቋ አጠቃቀም አንፃር ............................. 13
2.5. የቃል ግብረመልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች .............................................. 14
2.5.1. እንደገና ማሰራት ..................................................................... 15
2.5.2. ግልፅ ርማት መስጠት .............................................................. 15
2.5.3. ፈጣን ምላሽ መስጠት .............................................................. 15
2.5.4. መድገም .................................................................................. 15
2.5.5. ማነሳሳት .................................................................................. 15
2.6. የቃል ግብረመልስ ሲሰጥ ሊስተዋሉ የሚገባቸው ነጥቦች ............................ 16

IV
2.7. የስኬታማ ግብረመልስ ባህሪያት ................................................................ 17
2.8. የቃል ግብረመልስ ለቋንቋ ትምህርት ያለው ጠቀሜታ .............................. 17
2.9. የቃል ግብረመልስ በማን ይሰጣል?........................................................ 19
2.9.1 የጓደኛ /የብጤ / የቃል ግብረመልስ ........................................ 19
2.9.2. የመምህራን የቃል ግብረመልስ ................................................ 20
2.10. ግብረመልስ የሚሰጥባቸው ጊዜያት .......................................................... 20
2.11. ንድፈሀሳባዊ ፍልስፍና........................................................................... 21
2.13. የቀደምት ስራዎች ቅኝት ........................................................................ 24
ምዕራፍ ሶስት፣ አጠናን ዘዴ ................................................................................. 26
3.1. የጥናቱ ዘዴ.................................................................................................. 26
3.2. የናሙና አመራረጥ ዘዴ ............................................................................ 28
3.2.1. የትምህርት ቤት ናሙና አመራረጥ .......................................... 28
3.2.2. የክፍል ደረጃ አመራረጥ ......................................................... 28
3.2.3. የተማዎች ናሙና አመራረጥ .................................................. 29
3.2.4. የመምህራን ናሙና አመራረጥ ............................................... 29
3.3. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ........................................................................... 29
ምልከታ .............................................................................................. 29
3.4. የመረጃ አሰባሰብ ሂደት ........................................................................... 30
3.5. የመረጃ አተናተን ዘዴ ........................................................................... 32
ምዕራፍ አራት፣መረጃ ትንተና፣የውጤት ማብራሪያና ትርጎማ ................................ 33
4.1. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት በመምህራንና በተማሪዎች የሚሰጡ
ግብረመልሶች ምን ዓይነት ናቸው?................................................................... 33
4.1.1. አወንታዊ ግብረመልስ.............................................................. 33
4.1.2. አሉታዊ ግብረመልስ .............................................................. 36
4.1.3. የማስተካከያ ግብረመልስ .......................................................... 39
4.1.4. ገምጋሚ ግብረመልስ................................................................ 43
4.1.5. ገላጭ ግብረመልስ.................................................................... 44
4.1.6. ውጫዊ ግብረመልስ ................................................................. 45
4.1.6.1. ከፊልና ሙሉ ግብረመልስ............................................................ 45

V
4.1.6.2. ይዘታዊና ቅርፃዊ ግብረመልስ ...................................................... 46
4.2. የቃል ግብረመልስ የሚቀርቡባቸው ስልቶች ምንምን ናቸው? ................... 50
4.2.1. እንደገና ማሰራት ..................................................................... 50
4.2.2. ግልጽ ርማት መስጠት ............................................................. 53
4.2.3. መድገም .................................................................................. 54
4.2.4. ማነሳሳት .................................................................................. 56
4.3. በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል ግብረመልስ ምን
አይነት ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ አለው?........................................ 59
4.3.1. የግብረመልስ ትምህርታዊ አስተዋጽኦ ...................................... 59
4.3.1.1. የቃል ክፍሎች ............................................................................. 59
4.3.1.2. የሀረግ ምስረታ ............................................................................. 61
4.3.1.3. የቃላት ንበት የሚያስከትለውን የትርጉም ለውጥ .......................... 64
4.3.1.4. የስርዓተ ነጥብ አገባብ .................................................................. 65
4.4.1.5. ዓ.ነገር .......................................................................................... 66
4.3.1.6. ስነ- ጽሁፋዊ ሃሳቦች ..................................................................... 69
4.3.1.7. የቃላት ንበት (የሆሄያት ግድፈት) ................................................ 71
4.3.2. የግብረመልስ ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ ........................................ 72
4.3.2.1. ቃላት በትክክል እንዲጠሩ መፈለግ .............................................. 72
4.3.2.2. የተባለውን በትክክል አለማዳመጥ ወይም ማረጋገጫ መሻት ......... 73
4.3.2.3. ተጨማሪ ማብራሪያ መፈለግ ........................................................ 75
4.3.2.4. የጠፉ ሀሳቦችን የሚገልጹ ዲስኩር አመልካች ቃላት...................... 77
4.4. የጥናቱ ግኝት ማብራሪያ ........................................................................... 79
4.4.1. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለ ጊዜያት በመምህራኑና
በተማሪዎች የሚቀርቡ የቃል ግብረ መልስ ዓይነቶች .......................... 79
4.4.2 የቃል ግብረ መልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች ............................ 81
4.4.3. በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል ግብረመልስ
ያለው ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋጽኦ ....................................... 82
ምዕራፍ አምስት፣የጥናቱ ማጠቃለያና አስተያየት.................................................. 83
5.1. ማጠቃለያ ................................................................................................. 83
5.2. አስተያየት................................................................................................. 85

VI
ዋቢፅሁፎች……………………………………………………………………………87

አባሪ አንድ ምዝግብ መረጃ አንድ ....................................................................... 90


አባሪ ሁለት ምዝግብ መረጃ ሁለት..................................................................... 100
አባሪ ሶስት ምዝግብ መረጃ ሶስት....................................................................... 106
አባሪ አራት ምዝግብ መረጃ አራት .................................................................... 111
አባሪ አምስት ምዝግብ መረጃ አምስት ............................................................... 122
አባሪ ስድስት ምዝግብ መረጃ ስድስት ................................................................ 127

VII
አሕጽሮተ ጥናት
የጥናቱ ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት በተማሪዎችና መምህራን
የሚቀርቡ የቃል ግብረመልሶችን ከተግባቦታዊና ከሥነትምህርታዊ ፋይዳቸው አኳያ
መተንተን ነው፡፡ የጥናቱ መሪ ጥያቄዎችም በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት
የሚቀርቡ የቃል ግብረመልስ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው? የቃል ግብረመልሶቹ
የሚቀርቡባቸው ስልቶች ምን ምን ናቸው? የቃል ግብረመልሶቹ ያላቸው
ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ ምንድነው? የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህን
ጥያቄዎች ለመመለስ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ የንግግር ልውውጥ
ትንተና አቀራረብ ተግባራዊ ሲሆን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴው ደግሞ ምልከታ
ነው፡፡ በምልከታ የተገኘው መረጃ ወደ ምዝግብ መረጃ ከተቀየረ በኋላ በንግግር
ልውውጥ ዘዴ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎች በአንኮበር የከፍተኛ
ትምህርት መሰናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2011 ዓ.ም ያሉት የዘጠነኛ
ክፍል ተማሪዎችና የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ሲሆኑ በዚሁ ት/ቤት በመማር ላይ
ከሚገኙት የ9ኛ ክፍል ምድቦች ውስጥ በቀላል ዕጣ ናሙና የተመረጡ ሁለት
ምድቦችና በሁለቱ ምድቦች ውስጥ የሚያስተምሩ ሁለት የአማርኛ መምህራን
በጠቅላይ ናሙና ተመርጠው ተካተዋል፡፡ በቀጥተኛ ምልከታ የተገኘው መረጃ ወደ
ምዝግብ መረጃ ተለውጦ ከቃል ግብረመልስ ዓይነቶች፣ ስልቶች፣ ከተግባቦታዊና
ትምህርታዊ አስተዋፅኦ አኳያ ተለይተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤቶችም
መምህራን በክፍል ውስጥ ከአይነት አንፃር አዎንታዊ ፣ አሉታዊ፣ የማስተካከያና
ቅርፃዊ ግብረመልሶችን እንደሚጠቀሙ ለይዘታዊና ለገምጋሚ ግብረመልሶች
ትኩረት እንደማይሰጡ፣ ከስልት አንፃርም እንደገና ማሰራት፣ ግልፅ ርማት መስጠት፣
መድገምና ማነሳሳትን እንደሚጠቀሙ አመላክተዋል፡፡ በይበልጥም እንደገና
ማሰራት፣ ማነሳሳትና ግልፅ ርማት መስጠት እንደሚተገበሩ፣ ግብረመልሶቹ
ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተመልክቶ በንዑሳን ክፍሎች
ተዘርዝረዋል፡፡ ትምህርታዊ አስተዋፅኦቹ ከቋንቋው ሰዋሠው ጋር የተዛመዱ ሲሆኑ
የቃል ክፍሎችን፣ ሀረጋትንና ዐ.ነገሮችን እንዲለዩና እንዲያዋቀሩ ማድረግ፣ የቃላት
ንበት የሚያስከትለውን ለውጥ መለየትና ስነ-ፅሁፋዊ ስያሜዎችን በትክክል መለየት
የሚሉት ናቸው፡፡ ተግባቦታዊ አስተዋፅኦዎቹም በትክክል አለማዳመጥን መቅረፍ፣
ተጨማሪ ማብራሪያ መሻትና ቃላትን በትክክል አለመጥራትን ማስወገድ የሚሉ
ናቸው፡፡ የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግም አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

VIII
ምዕራፍ አንድ
የዚህ ምዕራፍ ዓላማ የጥናቱን ምንነት ማስተዋወቅ ሲሆን በመጀመሪያ ከርዕሰጉዳዩ
ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ሃሳቦችን መነሻ በማድረግ የጥናቱ ዳራ ቀርቧል፡፡ ቀጥሎም
ለጥናቱ አነሳሽ የሆነው ምክንያት ከጥናቱ መሪ ጥያቄዎችም ተካቷል፡፡ የጥናቱ
ዋናና ዝርዝር ዓላማዎች ከተገለፁ በኋላ የጥናቱ ወሰን ከጊዜና ከቦታ አኳያ ተወስኖ
ቀርቧል፡፡

1.1. የጥናቱ ዳራ

የአፍ መፍቻም ሆነ የሁለተኛ ቋንቋን ትምህርት ዓላማ፣ተማሪዎች የቋንቋ ክሂሎችን


እንዲያዳብሩ፣በሥነ-ፅሁፍ፣በሠዋሰውና በቃላት በኩልም እውቀት እንዲጨብጡ
ማድረግ ነው፡፡ባገኙት እውቀት ተጠቅመውም ተፈላጊውን የተግባቦት ብቃት
በማዳበር ተግባቦታቸው የተሳካ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ ለዚህም መሠረቱ
ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚማሩት የቋንቋ ትምህርት ሲሆን ትምህርቱ በሚሰጥበት
ጊዜ ከመምህሮቻቸው እና ከአቻ ጓደኞቻቸው የሚያገኙት ግብረመልስ ተማሪዎች
ደጋግመው እንዲለማመዱና ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ብሎም በትምህርታቸው
ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ቋንቋን በመማር ሂደት፣ ተማሪዎች ሲማሩ
ስህተቶችን ይፈፅማሉ፡፡ ምንም እንኳ በመማር ሂደት ስህተት መስራት የሚከሰት
ቢሆንም ስህተቶች በወቅቱ ካልታረሙ በተማሪዎቹ ችሎታና ተግባቦት ላይ ተፅዕኖ
ያሳድራሉ፡፡ ነገርግን ስህተቶች በየክፍለጊዜያቱ በግብረመልስ ከታረሙ ችግሮቹ
በቀላሉ ሊቀርፉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም አንዱ ብልሃት የቃል ግብረመልስ ነው፡፡

እንደ Barbra (2002) እንደሚያስረዱት የቃል ግብረመልሶች ወይም ያልተፃፉ


አስተያየቶች ለተማሪዎች መሻሻል አስፈላጊ ናቸው፡፡ምክንያቱም የቃል
ግብረመልሶች ስህተቱ በተከሰተበት ጊዜ የሚከናወኑ በመሆናቸው በተማሪዎች
አዕምሮ በቀላሉ የመቀረፅ እድል አላቸው፡፡እኚህ ምሁር አያይዘውም ቃላዊ
ግብረመልሶች ውጤታማ ቢሆኑም ብዙ መምህራን ጊዜ ይጨርሳል በሚል ምክንያት
እምብዛም እንደማይተገብሯቸው ያስረዳሉ፡፡

1
እንደ John እና Helen (2007) ገለፃ ደግሞ መምህራን የተማሪ ቁጥር በመማሪያ
ክፍል በመብዛቱ ምክንያት በመምህር ተኮር ዘዴ ሲያስተምሩ ይታያሉ::
የተማሪዎችን የቋንቋ ተግባቦት በማሻሻል ረገድ የሚያከናውኑት የክፍል ውስጥ
ተግባር ስለሌለ ለቃል ግብረመልስ እንብዛም ቦታ አይሰጡም፡፡

ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ምሁራን ፣ እንደገለፁት መብዛት አመቺ እንዳልሆነ ምቹ


ሁኔታ ቢፈጠርም መምህራን እንብዛም ለግብረመልስ ትኩረት እንደማይሰጡ
መረዳት ይቻላል፡፡

እንደ Susan (2008) ገለፃ ግብረመልስ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን ጠቀሜታ


ያለው ተግባር ነው፡፡መምህራን ሲያስተምሩ ተማሪዎች ከሚሰጡት ምላሽ
የትምህርቱ ዓላማ ምን ያህል እንደተሳካ የሚረዱበት ሲሆን ተማሪዎች ደግሞ
ስህተት የሆኑትን ለመለየት እና ለማስተካከል ትክክል የሆኑትን ለማዳበር
ይረዳቸዋል በማለት ያስረዳሉ፡፡

Barbara (2002) ልማዳዊ ከሆነው በእያንዳንዱ ተማሪ ወረቀት ወይም ደብተር ላይ


ከሚፃፈው ግብረመልስ ይልቅ በቃል በየክፍለጊዜያቱ የሚሰጡት ግብረመልስ የተሻለ
ጠቃሚ ነው፡፡ምክንያቱም ተማሪዎች ፅሁፋዊ ግብረመልስ ሲሰጣቸው ጭራሽም
ላያዩት ይችላሉ፡፡ ግብረመልስ ከተሰጣቸው በኋላ ትኩረት ስለማይሰጡት አብዛኞቹ
ሲተገብሩና በቀጣይ ስራቸው ላይ ማስተካከያ ሲያደርጉ አይታይም በማለት
ይገልፃሉ፡፡ስለዚህ የፅሁፍ ግብረመልስ በቃል ከሚሰጠው ጋር ሲነፃፀር ስራቸው
እየደከመ እንዲሄድ የሚያደርግ እንጂ ለውጤት የሚያበቃ አይደለም በማለት
ያስረዳሉ፡፡በተጨማሪም ቃላዊ ግብረመልስ ተማሪዎች በቀጥታ ከመምህራቸው
የሚገናኙበት በቋንቋ ትምህርት መለማመጃዎችና የክፍል ውስጥ ተግባራት ላይ
የሚሰጥና ጉድለታቸውንም ሆነ ጥንካሬያቸውን የሚያሳይ የመማርና የማስተማር
ተግባር ነው በማለት ያብራራሉ፡፡

በምሁራኑ እንደተገለፀው ቃላዊ ግብረመልስ ተማሪዎች ወዲያውኑ ርማት


የሚወስዱበት የተማሪዎችን ስራ ለማሻሻል የሚረዳ ከመፃፍ ግብረመልስ የተሻለ
ተግባር ነው፡፡እንደ Keh (1990) ገለፃ ደግሞ የቃል ግብረመልስ መስጠት
የተማሪዎችን የጥረት ደረጃ ለመለየት፣ ተማሪዎች የሰሩት ስራ ለማድነቅና

2
ለማበረታታት ፣ በተግባራቸው ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚያስችል ተግባር
ነው፡፡መምህራን ለተማሪዎቻቸው ለግብረመልስ እድል መስጠትና የራሳቸውንም ሆነ
የጓደኞቻቸውን ተግባር የሚገመግሙበትን ሁኔታ መፍጠር አለባቸው፡፡ በዚህም
የተማሪዎች በራስ መተማመን ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል በማለት ያስረዳሉ፡፡

ከላይ እንደተገለፀው ግብረመልስ ከመማር ማስተማሩ ተግባር ጋር ጥብቅ ቁርኝት


አለው፤ ለተማሪዎች ስራ አዎንታዊ እና አሉታዊ ምላሽም ያስገኛል፡፡ ስለሆነም
መምህራን በክፍል ውስጥ ከተማሪዎቻቸው ጋር ጥብቅ የሆነ የመማር እና
የማስተማር ቁርኝት ከሚፈጥሩባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡

እንደ Ellis (2009) ገለፃ መምህራን በተለያየ ሁኔታ ከተማሪዎች ጋር ያላቸውን


ግንኙነት ከሚያጠናክሩባቸው መንገዶች አንዱ ቃላዊ ግብረመልስ ሲሆን የቃል
ግብረመልስ ተግባቦትን የሚፈጥር፣1ቀጥተኛ በሆነም ሆነ በኢ-ቀጥተኛ መንገድ
ተማሪዎችን ለማረምና ግልጽነትን ለመፍጠር የሚያስችል ተግባር ነው ፡፡

እንደ Nsw Government (2015) የቃልግብረመልስ ተማሪዎች ምላሽ ሲሰጡ


በሽልማት፣ በማነሳሳት፣ ስህተትን በመጠቆምና በመንቀፍ ሊቀርብ ይችላል፡፡

እንደ Anne (2013) ገለፃ ደግሞ የቃል ግብረመልስ የሚያተኩረው ጉድለት


በሚታይበት እውቀት ወይም ክህሎት ላይ ነው፡፡ ስለሆነም ግብረመልስ በተማሪዎች
የቋንቋ አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ስህተቶችን የሚጠቁም ተግባር ነው፤ ስለዚህ ግልፅ
ርማት በመስጠትና በማበረታታት ሊቀርብ ይችላል፡፡ባጭር አገላለፅ ግብረመልስ
ለተማሪዎች የቋንቋ ክሂል እና ዕውቀት መዳበር ወሳኝ ነው፡፡ በክፍለጊዜው የሚሰጡ
የቃል ግብረመልሶች በፍጥነት የሚከናወኑ በመሆናቸው ተማሪዎች ስህተታቸውን
ወዲያው ተረድተው እንዲያስተካክሉ ላቅ ያለ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ ስለዚህ
በመማሪያ ክፍል ውስጥ በመምህራን እና በተማሪዎች የሚከናወነውን የቃል
የግብረመልስ አቀራረብ ስልት በቀጥታ ምልከታ በማጥናት የሚሻሻልበትን መንገድ
ማንፀባረቅ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

1
ቀጥተኛ ግብረመልስ ተማሪው የሚሰራውን ስህተት በቀጥታ ማስተካከል ነው (Ferris
2002)፡ኢ-ቀጥተኛ ግብረመልስ በተማሪው ስራ ላይ ስህተት እንዳለ በመጠቆም ስህተቱን
ራሱ እንዲያርም ማድረግ ነው (Ferris 2002) ፡፡

3
ይህ የመማር እና የማስተማር ተግባር በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ እሮሮ እየቀረበበት
ያለውን የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ረገድ አስተዋጽኦ አለው፡፡

1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት


የቃል ግብረመልስ በክፍል ውስጥ ሲቀርብ የተማሪዎችን ሁኔታ ለመከታተል
ያስችላል፡፡ የቃል ግብረመልስ ለቋንቋ ትምህርት ያለው አስተዋፅኦ የላቀ ቢሆንም
ይህንን የሚያጠናክሩ የሀገር ውስጥ ጥናቶች አልተሰሩም፤ በግብረመልስ ዙሪያ
የተሰሩ ጥናቶች ቢኖሩም ትኩረታቸው በፅሁፋዊ ግብረመልስ ላይ ነው፡፡ እታለማሁ
(2006) የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎቻቸው የፅሁፍ መለማመጃ ላይ
የሚሰጡት ፅሁፋዊ ምጋቤምላሽ በሚል ርዕስ ያጠናች ሲሆን ባለባት የጊዜ እጥረት
የቃል ግብረመልስን ያላካተተች መሆኑን ገለፃ ትኩረት ተሰጥቶት ቢጠና የተሻለ
መሆኑን ጠቁማለች፡፡ አስካል (2001) ተማሪዎች ለሚፅፏቸው ድርሰቶች
በመምህራን የሚሰጡ ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማሻሻል
ረገድ ያላቸውን ተጽዕኖ መፈተሽ በሚል ርዕስ የፅሁፍ ግብረመልስን መሰረት
በማድረግ ያጠናች ሲሆን ትኩረቷ ሙሉ በሙሉ በፅሁፍ ግብረመልስ ላይ ነው፡፡
ፋንታዬ (1998) ደግሞ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ቃላዊ ምጋቤምላሽ ስልቶች
ፍተሻ የሚል ጥናት ያቀረበ ሲሆን የቃል ግብረመልስን ቢያጠናም ትኩረቱ ግን
በስልት ላይ ብቻ ስለነበር የቃል ግብረመልስ በተለያዩ መልኮች ቢጠናም ውጤታማ
እንደሚሆን በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡በመሆኑም ከላይ የቀረቡት ጥናቶች ለቃል
ግብረመልስ የሰጡት ትኩረት አናሳ መሆኑ አጥኝዋን ይህን ርዕስ ለማጥናት
እንድትነሳሳ አድርጓታል፡፡በተጨማሪም ከበደ (2009) kobayshi & kobyshi
(2004) በመጥቀስ እንደሚገለፀው የወቅት የቋንቋ ንድፈሃሳብ የመማሪያ ክፍል
ዲስኩር ከማህበረባህላዊና ከመስተጋብር አንፃር እንዲጠና ያነሳሳል በማለት
ይገልፃል፡፡ይህም ንድፈሃሳብ አጥኝዋን አነሳስቷታል፡፡

አጥኚዋ ይህን ጥናት እንድታጠና ያነሳሳት ሌላው ምክንያት በአስራሁለት ዓመት


የማስተማር ልምዷ የተማሪዎች የቋንቋ ችሎታ አናሳ መሆኑን በጥልቀት ስለታዘበች
ነው፡፡ የዚህ ጥናት ተተኳሪ ተማሪዎች በቋንቋው አፈፈት ቢሆኑም በክፍል ውስጥ
ሀሳባቸውን ለመግለፅ ሲቸገሩ በማስተዋሏ በክፍል ውስጥ የሚሰጡ ግብረመልሶች
አይነታቸውና ስልታቸው ምን ያህል እንደሆነ ለመተንተን እና ለማወቅ

4
ተነሳስታለች፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ጊዜ ከአቻ መምህራን ልምድ ልውውጥ
ለማድረግ በተለያዩ ክፍሎች በተገኘችባቸው አጋጣሚዎች መምህራን የሚሰጧቸው
የቃል ግብረመልሶች እምብዛም መሆናቸውን ተመልክታ መምህራን ለቃል
ግብረመልሶች የሚሰጡትን ትኩረትም ለመተንተን በመፈለጓ ጥናቱን ለማድረግ
ተነሳስታለች፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት ጥያቄዎች እንድታነሳ አድርጓታል፡፡

1. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት መምህራንና ተማሪዎች ምን ዓይነት


የቃል ግብረመልስ ይሰጣሉ?

2. ግብረመልሶቹ የሚቀርቡባቸው ሥልቶች ምን ምን ናቸው?

3.በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል ግብረመልስ ምን ምን

ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋጽኦ አለው?

1.3. የጥናቱ ዓላማ


የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡትን የቃል
ግብረመልሶች ዓይነት፣ የአቀራረብ ስልት እና ምክንያት በመተንተን የቃል
ግብረመልስ ያለውን ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ መመርመር ነው፡፡የጥናቱ
ዝርዝር ዓላማዎችም፡-

- መምህራንና ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት


ምን ዓይነት ግብረመልሶች እንደሚሰጡ መለየት
- የመምህራኑና የተማሪዎቹ ግብረመልሶች የቀረቡባቸው ስልቶችን
መለየት
- በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል
ግብረመልስ ምን ምን ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋጽኦ
እንዳለው መመርመር

5
1.4. የጥናቱ ጠቀሜታ
ይህ ጥናት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታመናል፡፡
ጠቀሜታዎቹም ከባለድርሻ አካላት አኳያ ቀጥሎ ቀርበዋል፡፡

ሀ. ለቋንቋ መምህራን፡- ጥናቱ በክፍል ውስጥ የሚካሄደውን የግብረመልስ አቀራረብ


ስልት በቀጥታ ምልከታ ስለሚያጠና እና ስለሚያንጸባርቅ መምህራን ጉድለታቸውን
እንዲያሻሽሉ ሞዴል በመሆን ሊያገለግል ይችላል፡፡

ለ. መምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት፡- ጥናቱ የመምህራን የግብረመልስ አሰጣጥ

ጉድለት ስለሚያንጸባርቅ ለማሠልጠኛ ተቋማቱ የሥልጠና የትኩረት አቅጣጫ


የሚጠቁም መረጃ ይሰጣል፡፡

ሐ. ለመማሪያ መሣሪያ አዘጋጆች፡- ይህ ጥናት የግብረመልስ አሰጣጥ ዓይነቶችን


እና የሚቀርቡበትን ስልቶች ስለሚተነትን የመማሪያ መሣሪያ አዘጋጆች
ከግብረመልስ አንፃር መሣሪያዎችን እንዲያዘጋጁ ሊጠቅም የሚችል መረጃ
ይሰጣል፡፡

መ.ለጥናት አድራጊዎች፡- በግብረመልስ አሰጣጥ ላይ ጥናት ማድረግ ለሚሹ


እንደመነሻ በመሆን ሊያገለግል ይችላል፡፡

1.5. የጥናቱ ወሰን

ይህ ጥናት ከይዘት አንፃር በግብረመልስ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአማርኛ ቋንቋ


ትምህርት ክፍለጊዜያት በሚሰጠው የቃል ግብረመልስ ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡
የፅሁፍ ግብረመልስንም ሆነ ከክፍለጊዜ በኋላ የሚሰጡ ግብረመልሶችን
አያካትትም፡፡በክፍለጊዜያቱ በመምህራንም ይሁን በአቻ ተማሪዎች የሚሰጠውን
የቃል ግብረመልስ ዓይነት፣ ስልት በመተንተን የክፍል ውስጥ የቃል ግብረመልስ
ያለውን ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅአ ያሳያል፡፡ከቦታ አንፃር ደግሞ ይህ
ጥናት የተካሄደው በአማራ ክልል፣ በሰሜንሸዋ ዞን በአንኮበር ከፍተኛ ትምህርት
መሰናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ ጥናቱ ትኩረት ያደረገው በዘጠነኛ
ክፍል ላይ ነው፡፡

6
1.6. የቁልፍ ቃላት ፅንሰ ሃሳባዊ ፍቺ
በዚህ ክፍል የጥናቱን ፅንሰሃሳብ የሚገልፁ ቁልፍ ቃላት ከፍቺያቸው ጋር
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1.ግብረመልስ፡- እነ Keh (1990) ፣ Anne (2013) እንደሚገልፁት ተማሪዎች


በሰሯቸው ስራዎች አስተያየትና እርማት ለመስጠት፣ ተማሪዎችን ለማበረታታትና
ለማድነቅ የሚያስችል ተግባር ነው ፡፡በዚህ ጥናትም ይህንኑ ይጠቁማል፡፡

2.የቃል ግብረመልስ፡- ሃይማኖት (2011) ከተማሪዎች ጋር ፊትለፊት በመገናኘት


በተግባራቸው ላይ በቃል አማካኝነት የሚሰጥ ምላሽን ያመለክታል፡፡በዚህ ጥናትም
በክፍል ውስጥ በየክፍለጊዜያቱ በቃል የሚቀርብ ግብረመልስን ያመለክታል ፡፡

3.የግብረመልስ አሰጣጥ ስልት፡- John (2007) መምህራን በክፍል ውስጥም ሆነ


ከክፍል ውጪ ለተማሪዎች ጥቆማዎችን ለመስጠት የሚጠቀሙባቸውን መንገዶች
ያሳያል፡፡ይህ ጥናት ግን በክፍል ውስጥ ስልቶች ላይ ብቻ ያተኩራል ፡፡

4.ትምህርታዊ አስተዋፅኦ፡- John (2007) እንደሚገልፀው በቋንቋ ትምህርት ውስጥ


ሰዋሰዋዊ ህግን ለማስገንዘብ የሚሰጥ የቃል ግብረመልስን ያመለክታል፡፡ በዚህ
ጥናትም ይህንኑ ያሳያል፡፡

5.ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ፡- እንደ John (2007) ገለፃ በቋንቋ መማሪያ ክፍል


በመምህራንና ተማሪዎች መካከል በተለያየ ምክንያት የመግባባት ችግር ሲያጋጥም
ተግባቦቱን ለማስቀጠል የሚቀርብ የቃል ግብረመልስን ያመለክታል፡፡ በዚህ
ጥናትም ይህንኑ ያመለክታል፡፡

7
ምዕራፍ ሁለት፣ የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት
የዚህ ምዕራፍ ዓላማ ከጥናቱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ጽሁፎች ከልሶ ማቅረብ
ነው፡፡ ተዛማጅ ጽሁፎቹ ስለ ቃል ግብረመልስ ምንነት፣ዓይነት፣ባህርያት፣ስልትና
አቀራረብን የሚያስረዱ ሀሳቦች ተገምግመዋል፡፡ በተጨማሪም በርዕሱ ዙሪያ የተሰሩ
ቀደምት ጥናቶች ቀርበዋል፡፡

2.1. የግብረመልስ ምንነት

እንደ Ur (1996) ገለፃ ግብረመልስ በክፍለጊዜ ሙሉ በተለያየ ሁኔታ የሚፈጠር


ተግባር ነው፡፡ በተግባራት ላይ የሚሰጡ ትክክለኛ ግብረመልሶች ተማሪዎችን
ለመገምገም ያስችላሉ፡፡ ግብረመልስ የተማሪዎችን ማዳመጥ መገምገም፣ አስተያየት
መስጠት፣ ሀሳብ እንዲቀርብ መገፋፋት፣ በቡድን የሚሰሩ ስራዎችን ማድነቅ፣
ለስራዎች በአጠቃላይ ዋጋ ለመስጠት በቋንቋ ክፍል ውስጥ የሚቀርብ ማበረታቻ
ነው፡፡ በጥቅሉ በማስተማር ስራ ውስጥ ግብረመልስ ማለት ስለ ተማሪዎች
በትምህርታዊ ተግባራት ላይ ባላቸው አተገባበር መሰረት የሚሰጣቸው መረጃ ነው፡፡
እንደ Ur (1996) ገለፃ አብዛኛውን ጊዜ የቋንቋ ትምህርትን አላማ መሠረት
ተደርገው የሚሰጡ የክህሎት ማዳሪያ ምላሾች ግብረመልስ ይባላሉ፡፡ ተማሪዎች
ጥያቄ ሲመልሱ በፈተና ጊዜ ሰባ ፐርሰንት የሚሆነውን ሲያገኙ ወ.ዘ.ተ፣ ትክክል
ወይም አዎ በመባል ሲበረታቱ ወይም ስህተት ለሆኑ ተግባራት በአይን እንቅስቃሴ
ምላሽ ሲሰጡ ግብረመልስ ተብሎ ይጠራል፡፡ እንደ wajnryb (1991) ግብረመልስ
በተማሪዎች በኩል በጽሁፍ ወይም በንግግር የፈለቁ መልሶችን የቋንቋ መምህሩ
ካዳመጡ ወይም ካነበቡ በኋላ በመልሳቸው ትክክለኛነት ወይም የስህተት ገጽታ ላይ
የሚሰጡት ርማት ወይም አስተያየት ነው፡፡ ፋንታዬ (1998) crystal (1997)
Weaver (1993) ን በመጥቀስ እንደሚገልፁት በተራዘመ የቋንቋ መግባባት ሂደት
አድማጩ ከተናጋሪው ግለሰብ በኩል ስለተላለፈው ሀሳብ የተረዳውና ያልተረዳውን
ለተናጋሪው መልሶ የሚያመለክትበት የንግግርና ንግግር አልባ ስልቶችን አጠቃሎ
የሚይዝ የተግባቦት ሂደት ዋንኛ መሳሪያ ግብረመልስ ይባላል፡፡

ፋንታዬ (1998) wajnryb (1991)ን በመጥቀስ በጥናታቸው እንዳመለከቱት


ያጭርና የረዥም ጊዜ ውስን የትምህርት አላማዎችን የያዙ ልምምዶችን ከግብ

8
በማድረስ ሂደት አብዛኛውን ጊዜ የቋንቋ መምህሩና ተማሪዎቹ በመማሪያ ክፍል
ውስጥ ሃሳባቸውን በንግግር እንደሚለዋወጡ ይታወቃል፡፡ በዚህ መስተጋብር ሂደት
በመምህሩ በኩል ለተጠየቀ የጽንሰ ሃሳብ ወይም የክህሎት ማጎልበቻ በመልመጃ
ተማሪ ተገቢ የሆነ መልስ፣ የመፍትሄ ሀሳብ ሊሆን ይችላል ብሎ ያመነበትን ሃሳብ
ለመምህሩና ለተማሪዎቹ ለማቅረብ ሞክራል፡፡ መምህሩም በተራው ተማሪው
ባቀረበው መልስ ላይ ትክክል መልስ አቅርበሀል (ሻል) መልስህ (ሽ) ስህተት ነው
ወ.ዘ.ተ በማለት አስተያየት ሊሰጥ ይችላል፡፡ መምህሩ የተማሪዎችን መልስ አዳምጦ
የተማሪው መልስ ትክክለኛ ወይም ስህተት ነው ብሎ ለተማሪው በጥቅሉ ፍንጭ
የሰጠበት ቋንቋው ግብረመልስ ይሰኛል፡፡

Richard & Lockhart (1996) ደግሞ አላማ ባለው ክንውን ውስጥ መምህሩ ወይም
የመማሪያ መፅሀፉ በትምህርትነት ባቀረበው ፅንሰሀሳብ ዙሪያ ተማሪውን ጥያቄ
ሊጠይቁት ይችላሉ፤ ተማሪውም መልስ ይሰጣል፡፡ በዚህ ወቅት መምህሩ አዎ!
በርግጥም ትክክል ብለሀል! ብለሻል ወይም አይደለም አሁን የተናገርከው
(የተናገርሽው) መልስ በክፍል ውስጥ ቀድማችሁ የተማራችሁትን የአሰራር ሂደትና
ቀመር ያልተከተለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ሀረጎችን ከማፍለቅ በተጨማሪ የተማሪዎችን
መልስ ለምን ስህተትና ትክክል እንደሆኑ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በመምህሩ፣
ተማሪዎቹ ባዳበሩትና ባልተገነዘቡት የአሰራር ግድፈትና ብቃት ደረጃ ላይ
የተናገራቸው በሙሉ ግብረመልስ በመባል ይጠራሉ በማለት ይገልፃሉ፡፡ በቋንቋ
መማር ተግባር ውስጥ የቀረቡላቸውን ልምምዶች ተማሪዎቹ በምንያህል ደረጃ
ስኬታማ በሆነ መንገድ በትክክል ማከናወን እንደቻሉና እንዳልቻሉ ፍንጭ
ለመስጠት የቋንቋ መምህሩ ለተማሪዎቻቸው አስተያየት ይሰነዝራሉ፤ይህም
ግብረመልስ ይሰኛል በማለት ይገልፃሉ፡፡ እንደ Kathleen (2017) ገለፃ ግብረመልስ
ማለት የአንድን ተማሪ የተግባር አፈፃፀም በተመለከተ በሌላ አካል መረጃ የመስጠት
ድርጊት ነው፡፡ ግብረመልስ በተግባርና በባህርያት ላይ የሚሰጥ መረጃ ሲሆን
መረጃው ለግለሰብ ወይም ለቡድኖች የሚሰጥ ነው፡፡ በመማር ሂደት ደግሞ
በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊ ሁኔታ የሚሰጥ ነው፡፡ ተማሪዎች በሰሩት ስራ
የሚዳኙበት ነው፡፡ ግብረመልስ ተማሪዎች ለነሱ ስራ በቂ ትኩረት እንደተሰጠው

9
እንዲያስቡ የሚያደርግ ስለተማሪዎች ስራ በዝርዝር መግለጫ የሚሰጥና የሚያሳይ
ነው፡፡

እንደ Anne (2013) ገለፃ በተለይ የቃል ግብረመልስ በትምህርት ወይም በስልጠና
ፕሮግራም አስፈላጊ ክፍል ሲሆን ተማሪዎች አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የሚረዳ
ድክመትና ጥንካሬያቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እንዲሁም ተማሪዎችን በቀጥታ
ከተሳሳተ ተግባር የሚያወጣና ለመሻሻላቸው መሠረት የሆነ ተግባር ነው፡፡
ግብረመልስ ምክር ሳይሆን ግምገማና ሽልማትን የሚያካትት አንድ ተማሪ
ተግባራትን ያከናወነበትን ሁኔታ እንዲሁም ግቡን ማሳካትና አለማሳካቱን
የሚጠቁም ነው፡፡

እንደ Brookhart (2008) ገለፃ የቃል ግብረመልስ ለተማሪዎች መሻሻል ወሳኝ


ነው፡፡ የቃል ግብረመልስ የተማሪዎችን ስህተት እንዲሁም ሂደታዊ መሻሻላቸውን
የሚያሳይ ግብረመልስ ነው፡፡ ይህ ግብረመልስ ተማሪዎች ትክክል የሆኑትን
በፍጥነት በመለየት ለማበረታታት እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖራቸው
ለማድረግ የሚረዳ ነው፡፡ የቃል ግብረመልስ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው በጊዜ
ተግባር ወይም የክፍል ውስጥ ተግባራት በሚከናውንበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ
ግብረመልስ ውጤታማና አስተማሪ የክፍል ውስጥ እንቅሰቃሴን የሚፈጥር የመማሪያ
ዘዴ ነው፡፡ እንደ Macdonald (1991) ገለፃ የቃል ግብረመልስ የሂደታዊ ምዘና
ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ አንድ ተግባር እንዴት እንደተሰራና እንዴት መሻሻል
እንዳለበት የሚጠቁም፣ በክፍል ውስጥ ውጤታማና የተግባር ጥራትን የሚያሳይ
ግብረመልስ ነው፡፡ የቃል ግብረመልስ በተማሪዎች አፈፃፀም ላይ በክፍል ውስጥ
ወዲያውኑ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን ተማሪዎች ባሳኩት ነገር ላይ ብቻ ሳይሆን
ክፍተታቸውን ለይቶ ለመረዳት የሚያስችል የመማር ማስተማር አንድ ክፍል ነው፡፡
እንደ Ur (1996) ግብረመልስ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም፡-ግምገማና
ርማት ናቸው፡፡

ግምገማ ፡-ተማሪዎች አተገባበራቸው ታይቶ ጥሩ ወይም መጥፎ ተብሎ ተግባራቸው


የሚመደብበት ነው፡፡ በአማካኝ (በፐርሰንት) ውጤት የሚሰጥበትም ነው፡፡

10
ርማት፡- ለተማሪዎች ክህሎት ዝርዝር መረጃ የሚሰጥበት ሲሆን ገለፃ ወይም አካላዊ
እንቅስቃሴን ይጠቀማል፡፡ ተማሪዎች በትክክል የሰሩትንም ሆነ ያልሰሩትን
በመመስረት መረጃ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ለምን ስህተት እንደሆኑ ጭምር
ይጠቁማቸዋል፡፡ Ur (1996) እንደሚገልፁት መምህራን ርማትንም ሆነ ግምገማን
በእኩል ደረጃ ይጠቀማሉ፡፡

2.1.1. የቃል ግብረመልስ ምንነት

ሀይማኖት (2011) Hyl& (2003) ን በመጥቀስ እንደገለፁት የቃል ግብረመልስ


አንዱ የግብረመልስ መግለጫ መንገድ ነው፡፡ በመሆኑም በይዘት አደረጃጀትና
በቋንቋ አጠቃቀም በመሳሰሉት ስህተቶች ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የቃል
ግብረመልስ ከእያንዳንዱ ተማሪ ጋር ፊትለፊት በመገናኘት ለተወሰነ የጊዜ ቆይታ
ተግባራዊ የሚደረግ የማስተማሪያ ዘዴ ነው፡፡ የቃል ግብረመልስ በስህተት ወይም
በድክመት ላይ ትኩረት በማድረግ የይዘቱን አደረጃጀትና የቋንቋ አጠቃቀም
መሰረት በማድረግ ሊሰጥ ይችላል፡፡ የቃል ግብረመልስ በመጠየቅ፣ በትዕዛዝ፣
በማድነቅና አስተያየት በመስጠት ይቀርባል፡፡ አቀራረቡም በምልልስ ነው፡፡

2.2. የቃል ግብረመልስ ዓይነቶች ከዓላማ አንፃር

እንደ Namara (1999) ገለፃ ከአላማ አንፃር ሶስት ዓይነት የቃል ግብረመልሶች
አሉ፡፡ እነዚህም፡- የማስተካከያ የቃል ግብረመልስ ፣ ገምጋሚና ገላጭ የቃል
ግብረመልሶች ናቸው፡

2.2.1. ገምጋሚ የቃል ግብረመልስ


እንደ Namara (1999) ገለፃ ገምጋሚ የቃል ግብረመልስ ጥቅል አስተያየቶች
የሚሰጥበት ነው፡፡ ተማሪዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ የሚጠቁም ሳይሆን በውጤት
ላይ የተመሰረተ ግብረ መልስ ነው፡፡እንደ Jhon (2007) ገለፃ ገምጋሚ ግብረመልስ
የተሻሉ ተማሪዎችን (ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ፤ ዝቅተኛ አፈፃፀም
ያላቸው ደግሞ መጥፎ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው፡፡ምናልባትም እነዚህ
ተማሪዎች ስራቸውን መቼም ማሳካት እንደማይችሉ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡በዚህ
ግብረመልስ አሰጣጥ ተማሪው ጥሩ ሰርተሃል ወይም ሰርተሻል በማለት ይገልፃሉ፡፡

11
2.2.2. የማስተካከያ የቃል ግብረመልስ

ይህ ግብረመልስ የተማሪዎችን ስህተት በቀጥታ በመጠቆም ለማስተካከል የሚረዳ


ግብረመልስ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በንግግር ሂደት ከንግግር አቀራረብ መመሪያ
ተማሪዎች ያልተገበሩትን በመጠቆም እንዲተገብሩ ማድረግ ነው፤ በሀረግና
ዓረፍተነገር ምስረታ ወቅት ተማሪዎች የተሳሳቷቸውን ገላጮች ወይም ቃላት
በመጠቆም ትክክለኛውን መተኪያ ቃል ወይም ገላጭ በመንገር ማስተካከል ነው፡፡

2.2.3. ገላጭ የቃል ግብረመልስ

እንደ Namara (1999) ገለፃ ገላጭ የቃል ግብረመልስ የተማሪዎችን ጉድለት ወይም
ስህተት የሚጠቁም ሲሆን ተማሪዎች በቀጣይ ስራቸው ላይ መሻሻል እንደሚችሉም
የሚያሳይ ግብረመልስ ነው፡፡ ተማሪዎች በስራቸው ሀላፊነት እንዲወሰዱና ራሳቸውን
ገምግመው እንዲያርሙ እድል የሚሰጥ ሲሆን ራሳቸው ምንድነው የሰራሁት?
እንዴትስ ማሻሻል አለብኝ? የሚለውን ጥያቄ እንዲጠይቁ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ፡-
መምህሩ በንግግር ጊዜ ጥሩ መግቢያ እንደሰጡና እንዴት ሊያስፋፉት እንደሚችሉ
ሊጠቁማቸው ይችላል፡፡

2.3. የግብረመልስ ዓይነቶች ከባህሪይ አንፃር

እንደ Anne (2013) ገለፃ ግብረመልስ ሁለት ዓይነት ባህሪያትን የያዘ አተገባበር
አለው፡፡ እነዚህም፡- አዎንታዊ ባህሪና አሉታዊ ባህሪ ናቸው በማለት ያብራራሉ፡፡

2.3.1. አዎንታዊ ባህሪ ያለው ግብረመልስ

አወንታዊ ባህሪ ያለው ግብረመልስ የተማሪዎች ስራ ተገቢ መሆኑን ትክክለኛ ስራ


ያቀረቡ መሆኑን የሚያመላክት ግብረመልስ ነው፡፡ ይህ ግብረመልስ በባህሪው
በጠንካራ ጎናቸው ላይ ስለሚያተኩር ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ተሳትፏቸው የተሻሉ
እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው፡፡ Cole & Lorna (1994) Richard & Lockhart (1996)
ደግሞ አዎንታዊ ግብረመልስ የተማሪው ተግባር ተገቢነት ያለው መሆኑን፣ ተማሪው
ትክክለኛ መልስ ለማቅረብ መሞከሩን ወይም በትክክለኛ መንገድ እየተጓዘ መሆኑን

12
የሚጠቁም ግብረመልስ ነው፡፡ አዎንታዊ ግብረመልስ ብዙውን ጊዜ የተማሪውን
የመማር ሂደት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በማለት ይገልፃሉ፡፡

2.3.2. አሉታዊ ባህሪ ያለው ግብረመልስ

ተማሪዎች በቀጥታ በተግባራቸው ውስጥ ስህተት እንደፈፀሙ፣ አገላለፃቸው የቃላት


አጠቃቀማቸው ወይም ምላሻቸው ትክክል እንዳልሆነ የሚነገርበት ነው፡፡ይህ ዓይነቱ
ግብረመልስ ተማሪዎች ተስፋ እንዲቆርጡና ምንም ሙከራ እንዳያደርጉ የሚገፋፋ
ግብረመልስ ነው ቢሆንም እንደ Anne (2013) ገለፃ አሉታዊ ግብረመልስ
በተማሪዎች ተግባር ላይ ተፅእኖ የሚያሳድር ቢሆንም ተማሪዎች ስህተታቸውን
በሚገባ እንዲረዱት ከተደረገ የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሳደግ አስተዋፅኦ ያደርጋል
በማለት ያስረዳሉ፡፡ Richard & Lockhart (1996) Cole & Lorna (1994)
እንደሚገልፁት አሉታዊ ግብረመልስ የቋንቋ ተማሪዎችን ተግባር፣ ምላሽ፣ የባህሪ
ለውጥ ወ.ዘ.ተ ተገቢነት የሌለው የተሳሳተ መንገድን የተከተለ መሆኑን ለመጠቆም
ሲፈለግ ባገልግሎት ላይ ይውላል፡፡አሉታዊ ግብረመልስ ዋንኛ ጠቀሜታው ተማሪው
የስህተት አይነቱንና ደረጃውን ለይቶ እንዲያውቅ ችግሩን ወደኋላ ተመልሶ
እንዲቃኝ እንዲሁም ስህተቱን ለማስተካከል ፍንጭ እንዲያገኝ ማድረግ ይሆናል፡፡
Richard & Lockhart (1996) ፣ Cole & lorna (1994) ፣ Anne (2013) መምህራን
አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጡት ግብረመልስ አሉታውን እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

2.4. የቃል ግብረመልስ ዓይነቶች ከቋንቋ አጠቃቀም አንፃር

እንደ Cole & Lorna (1994) ገለፃ ከመምህሩ የሚሰጡ ግብረመልሶች ከቋንቋ
አጠቃቀማቸው አንፃር ውስጣዊና ውጫዊ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡

ውስጣዊ ግብረመልስ፡- ተማሪው መምህሩ ወይም ባጠገቡ የሚገኘው ጓደኛው


ስለመማር ሂደቱ ምንም አይነት ግብረመልስ ሳይሰጠው የሚማረውን ትምህርት
በትክክል መከወን አለመከወኑን ከራሱ የድርጊት ሁኔታ የሚረዳበት ነው፡፡

ውጫዊ ግብረመልስ፡- Cole & Lorna (1994) እንደሚገልፁት ይህ ግብረመልስ


ስለተማሪው ጠንካራና ደካማ ጎን ወይም ተግባር ከመምህሩ፣ ከክፍል ተማሪዎች
ወይም ከሌላ ሰው የሚቀርቡ አስተያቶችን ጠቅልሎ ይይዛል፡፡

13
የውጫዊ ግብረመልስ ዓይነቶች

ሂደታዊና ማጠቃለያ ግብረመልስ ፋንታዬ (1998) Cole & Lorna (1994) ን


በመጥቀስ እንደገለፁት ሂደታዊ ግብረመልስ በመማር ተግባር ሂደት ውስጥ
የሚከናወነው ድርጊት ወዲያውኑ በተማሪው ከፍፃሜ መድረሱ በሚታመንበት ወቅት
የሚቀርብ ሲሆን የማጠቃለያ ግብረመልስ ደግሞ ተማሪዎቹ ተከታታይነት ያላቸው
ሶስት ወይም አራት ልምምዶች በተደራራቢነት አከናውነው ከፈፀሙ በኋላ
በመጨረሻ የሚሰጥ ግብረመልስ ነው፡፡

ከፊልና ሙሉ ግብረመልስ፡- የተማሪው ምላሽ በምን በምን ትክክል ነው? በምን


በምን ደግሞ ትክክል አይደለም? በማለት ደረጃ በደረጃ በጥልቀት ነጣጥሎ ሙሉ
በሙሉ በተማሪው ስራ ላይ ግብረመልስ የሚሰጥ ከሆነ ግብረመልሱ ሙሉ ይባላል፤
መምህሩ በተቃራኒው ተማሪው በመለሰው ሀሳብ በከፊል ተግባር ላይ ተንተርሶ
በተወሰኑ ነገሮች ግብረመልስ ከተሰጠ ከፊል ግብረመልስ ተብሎ ይፈረጃል በማለት
ፋንታዬ (1998) ይገልፃሉ፡፡

ይዘታዊና ቅርፃዊ ግብረመልስ፡- ፋንታዬ (1998) Harmar (1991) ን በመጥቀስ


የመምህራን ግብረመልስ መስጫ ቋንቋ ይዘታዊና ቅርፃዊ ተብሎ ሊከፈል ይችላል፡፡
በማለት ይጠቁማሉ፡፡

ይዘታዊ ግብረመልስ፡- ተማሪው በመማር ሂደቱ መከናወን የሚገባውን ጉዳይ


ትርጉም ባለው መንገድ ከመግለጽ አኳያ ታይቶ አስተያየት የሚሰጥበት ሂደት
ነው፡፡

ቅርፃዊ ግብረመልስ፡- ተማሪዎች የሚማሩትን ቋንቋ ሰዋሠዋዊ ስርዓትን


በተግባቦታዊ ተግባር ውስጥ በትክክል ማዋቀርና ማፍለቅ መቻላቸው ላይ ትኩረት
በመስጠት ግብረመልስ የሚሰጥበት ስልት ነው (ፋንታዬ 1998)፡፡

2.5. የቃል ግብረመልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች

እንደ John (2007) ገለፃ የቃል ግብረመልስ በሚከተሉት ስልቶች ሊቀርብ


ይችላል፡፡ ዋናዋና ታዋቂ ስልቶች የሆኑት ግን እንደገና ማሰራት፣ግልፅ እርማት
መስጠት፣ መደገምና ማነሳሳት ናቸው፡፡

14
2.5.1. እንደገና ማሰራት
መምህራን እንደገና የሚያሰሯቸው በቋንቋው ውስጥ የተማሪዎችን የቃላት
አጠቃቀም ለማስተካከል፣የሰሩትን ስህተት ለመቀነስ በሚል ነው፡፡

2.5.2. ግልፅ ርማት መስጠት


ቀድሞ ከቀረበው እንደገና ማሰራት ከሚለው ስልት ጋር በመጠኑ የሚመሳሰል ሲሆን
ተማሪዎች ምን ዓይነት ስህተት እንደሰሩ በግልፅ የሚጠቆምበት ነው፡፡ ትክክል
እንዳልሆነ ይነገራቸዋል፡፡ በዚህ ስልት ስነ ልቦናዊ ፍንጭ መስጠት፣ አሰራርን
ግልፅ ማድረግ ጥያቄዎችንና አጠያየቅን ግልፅ ማድረግ ይገኙበታል፡፡ ግልፅ ርማት
መስጠት ተማሪዎች ትክክለኛውን መንገድ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡

2.5.3. ፈጣን ምላሽ መስጠት


ቀጥተኛ ፈጣን ውሳኔ ሰጭ ሲሆን መምህራን ወዲያውኑ ለተማሪዎች ስህተት ምላሽ
የሚሰጡበት ነው፡፡ በአሉታዊ ጎን ላይ ብቻ ያተኮረ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ይህ
የግብረመልስ ስልት በቋሚነት በክፍል ውስጥ የሚታይ ነው፡፡

2.5.4. መድገም
ስህተት የሆኑ ቃላትን ወይም ዓረፍተነገሮችን በመድገም ተማሪዎች ስህተታቸውን
ራሳቸው እንዲረዱ የሚያደርግ ስልት ነው፡፡

2.5.5. ማነሳሳት
ተማሪዎች የውስጣቸውን እንዲገልፁ ማድረግ ሲሆን ስለአንድ ነገር ያላቸውን ግምት
እንዲገልፁ፣ አስተያየት እንዲሰጡ በማነሳሳት ወይም ማበረታታት የሚቀርብ ስልት
ነው፡፡እንደ Cole & Lorna (1994) ገለፃ ደግሞ ግብረመልስ በተለያዩ ስልቶች
ሊቀርብ ይችላል፡፡እነዚህም፡- ወደ ትክክለኛ የአሰራር ሂደት ሊያደርሱ የሚያስችሉ
ፍንጮችን በአማራጭ መስጠት ፣ ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ተጨማሪ
መልመጃዎች በማዘጋጀት ፣ ተማሪዎች ደጋግመው እንዲለማመዱባቸው እድል
መስጠት ፣ ተማሪዎቹ በቀላሉ ሊረዱት ያልቻሉትን የትምህርት ክፍል እንዲሁም
አዳዲስ ይዘቶችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንደገና በቀላል ዘዴና ምሳሌ
በማስተማርና ማስታወሻ በመስጠት ለተማሪው ስራ ግብረመልስ መስጠት ናቸው፡፡

15
Richards & Lockhart (1996) ደግሞ የክፍል ውስጥ የቃል ግብረመልስ
በሚከተለው መልኩ ሊቀርብ ይችላል በማለት ይገልፃሉ፡፡እነዚህም፡- ደገማ፣
ማጠቃለያ መስጠት፣ ጨመቃ፣ መጠየቅና አስፋፍቶ ርማት ናቸው፡፡

2.6. የቃል ግብረመልስ ሲሰጥ ሊስተዋሉ የሚገባቸው ነጥቦች

እንደ susan (2008) ገለፃ ግብረመልስ ሲሰጥ የሚከተሉትን ነጥቦች ማስተዋል


ያስፈልጋል፡፡

ጊዜ፡- መቼና ምንያህል ጊዜ መሰጠት አለበት? ጥሩ ግብረመልስ በፍጥነት የሚሰጥ


መሆን አለበት፤ (ወዲያውኑ ትክክል ወይም ስህተት መሆናቸውን ማሳወቅ አለበት)
የዘገየ ግብረመልስ በተማሪዎች ላይ የሚያሳየው ለውጥ የለም፡፡ ማንኛውም
ግብረመልስ ተማሪዎች ተግባራዊ የሚያደርጉበትን እድል መፍጠር አለበት፡፡

መጠን፡- ምንያህል ግብረመልስ ሊሰጥ ይችላል? (ምንያህል ነጥቦችን መያዝ


አለበት?) ግብረመልሱ መስጠት ያለበት ከመማር ግቡ ጋር በጥብቅ የተዛመዱ
ከሆኑት ተግባራት ጋር መሆን አለበት፡፡ ተማሪዎችን የመረዳት አቅም መሰረት
ያደረገ መሆን አለበት፡፡

ዘዴ(አይነት)፡- ግብረመልስ በቃል ፣ በፅሁፍ ፣ በገለፃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሊተላለፍ


እንደተፈለገው መልዕክት ተገቢውን ዘዴ መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ ነገርግን
ከተማሪዎች ጋር ፊት ለፊት በመገናኘት ማውራት ወይም ቃላዊው መንገድ የተሻለ
ዘዴ ነው፡፡ ለፅሁፍ ስራዎች ፅሁፋዊ ግብረመልስ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ተማሪዎች
እንዴት መስራት እንዳለባቸው ለማሳየትና ምሳሌዎችን ለመስጠት ገለፃና የቃል
ግብረመልስ ሊቀርብ ይችላል፡፡

አድማጭ (ግብረመልስ ሰጪ)፡- መምህሩ ወይም ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር ሊቀርብ


ይችላል፡፡ ግብረመልስ መምህሩ ለተማሪዎች ስራ ምን ያህል ዋጋ እንደሰጠ
ያመለክታል፡፡ የክፍሉ ተማሪዎች ግብረመልስ ሲሰጡ ምናልባት ሁሉም ተማሪዎች
ያጡትን (ያልተረዱትን) ሀሳብ የሚያሳዩበትና እንደገና ለመማማር እድል
የሚፈጥርበት ይሆናል፡፡

16
እንደ Susan (2008) ገለጻ ግብረመልስ ተማሪዎች ቀጣይ ግባቸውን እንዲወስኑ
ይረዳል፡፡ እንደ Nunan (1996) ገለጻ ደግሞ ግብረመልስ በተማሪዎች የራስ
መተማመን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ግልፅ ቀጥተኛ ግብረመልስ የተማሪዎችን
በራስ መተማመን ሲጨምር ግልፅ ያልሆነ ግብረመልስ መስጠት የተማሪዎችን በራስ
መተማመን ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ ግብረመልስ ሲሰጥ የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት
ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል በማለት ይገልፃሉ፡፡ እነዚህም፡- የትኞቹ ስህተቶች
መታረም አለባቸው? ስህተቶች መቼ ይስተካከሉ? ስህተቶች እንዴት ይታረሙ?
(በራስ፣ ጓደኛ ወይስ በመምህሩ ትክክለኛ መልስ ይሰጥ) የሚሉት ናቸው፡፡

2.7. የስኬታማ ግብረመልስ ባህሪያት

Susan (2008) በቋንቋ መማር ሂደት በቀረበላቸው ልምምዶች ላይ ብቻ ተወስኖ


የሚቀርብ መሆን ስልቱን በተማሪው የክህሎት ብቃት ላይ የተስተዋሉ ተገቢነት
ያላቸውን ግድፈቶች ብቻ የሚያርም፣ ተማሪው ስህተት ቢሰራ እንኳ ስህተቱን
እንዲያቃና ከማገዝ ውጭ ለምን ስህተት ተናገርክ ብሎ ዘለፋ የማይሰነዝር መሆን
መምህሩ ሁሉንም ጉዳይ በበላይነት ሳያርም ተማሪዎችም በግብረመልሱ
እንዲታሳተፉ እድል የሚሰጥ መሆን የማያሻማ ፍንጭ የሚሰጥ መሆን ማለትም
የተማሪውን ትክክለኛነትና ስህተትነት በግልጽ የሚጠቁም መሆን አለበት፡፡

2.8. የቃል ግብረመልስ ለቋንቋ ትምህርት ያለው ጠቀሜታ

Lyster & saito (2010) በጥናታቸው እንደጠቆሙት ግብረመልስ ለሁለተኛ ቋንቋ


ተማሪዎች የቃል ግብረመልስ እንደ ሂደታዊ መገምገሚያ ያገለግላል፡፡
ተከታታይነት ያለው የቃል ግብረመልስ ታላሚውን ቋንቋ ለማስረፅ
ይረዳል፡፡ይበልጥ የሚተገበረው ግብረመልስ አዎንታዊ የሚባለው ሲሆን ተማሪዎችን
በስራቸው ለማድነቅ የሚቀርብ ነው፡፡ Lyster & saito (2010) አሉታዊ
ግብረመልስ ግን ለተማሪዎች ጭንቀት ስለሚፈጥር ባይቀርብ የተሻለ ነው ይላሉ፡፡
Cole & Lorna (1994) የመምህሩ ግብረመልስ ተማሪዎች በመልሶቻቸው
ያቀረቧቸው ሀሳቦች በየት ቦታ ላይ ትክክለኛና የተሳሳተ ሙከራ እንደተናገሩ
ወደኋላ መለስ ብለው እንዲረዱ ያደርጋል በማለት ይገልፃሉ፡፡ Cole & Lorna
(1994) ጠቅሰው እንደሚገልፁት የመምህር ግብረመልስ በተማሪ በኩል በአንድ

17
የትምህርት መርሃ ግብር ለተዘረዘሩ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ የቀረቡ ልምምዶች
ወይም ጥያቄዎች እስከምን ድረስ በትክክል ማከናወን ችያለሁ? የቀረቡልኝን
ልምምዶች በአንፃራዊነት አሟልቼ የማከናወን ብቃትን በውስጤ ለማዳበር የጎደሉኝ
ነገሮች ምን ምን ናቸው? ወ.ዘ.ተ ለሚሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት
ፋይዳ አለው ይላሉ፡፡ ትክክለኛ የአሰራር ሂደትን የማስለመድ ጠቀሜታው የላቀ
ነው፤ ፋንታዬ (1998) rowntree (2000) ን በመጥቀስ እንደሚገልፁት ተማሪዎች
ከመምህራቸው ወይም ከብጤዎቻቸው የሚሰጣቸው ግብረመልስ በመልሶቻቸው
ያቀረቧቸው ሀሳቦች በየት ቦታ ላይ ትክክለኛና የተሳሳተ ሙከራ እንደተናገሩ ወደ
ኋላ መለስ ብለው በአፅዕኖት እንዲመረምሯቸው እድል ይሰጣል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን
በአሰራር ሂደታቸው የፈፀሟቸውን ስህተቶች እንደገና አቃንተው ትክክለኛ መልስ
የመስጠት ልምድን በሂደት እንዲያዳብሩ የማድረግ ፋይዳ አለው፡፡ ሌላው የቃል
ግብረመልስ ተለጣጣቂ ተግባራትን በጥሞና ለመስራት ያስችላል፤ የግብረመልስ
ዋንኛ አላማ የቋንቋ ተማሪዎቹ የመማር ሂደታቸው እውን መሆን ለቀረበላቸው
ተግባራት ተገቢነት ያላቸውን መልሶች አስበው እንዲያፈልቁ ሁኔታዎችን
ማመቻቸት ይሆናል፡፡

Richards & Lockhart (1996) በአንድ የቋንቋ ትምህርት መርሃ ግብር ተሳታፊ
የሚሆኑ ተማሪዎች የመማር ሂደታቸውን ከውጤት ለማድረስ ተብሎ ለሚታሰቡ
ልምምዶች ለሰነዘሯቸው ትክክለኛም ሆነ ስህተት ሙከራዎች፣ ለተነሱ ችግሮች
መፍቻ የሚሆኑ ሀሳቦችን በሚያፈልቁበት ወቅት መምህሩ ለስራቸው ተመጣጣኝ
የሆነ ግብረመልስ ከሰጣቸው ተማሪዎቹ ወደፊት ያሉትን ልምምዶች ሰፊ ጊዜ
ወስደው ለጥያቄዎች መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን አስበው የማደራጀት ልምድን
ሊስገኝላቸው እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡ የቃል ግብረመልስ ቋንቋ ተማሪውን የመማር
ስሜት የማነቃቃት፣ የማነሳሳት፣ ፍይዳ እንዳለው Cole & Lorna (1994)
ጠቁመዋል፡፡ ፋንታዬ (1998) የግብረመልስ ጠቀሜታን ሲገልፁ የቃል ግብረመልስ
የተማሪውን የመማር ግስጋሴ የማፋጠን ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም የቃል
ግብረመልስ ተማሪው በመማር ሂደቱ ለምንና በምን አጋጣሚ ስህተት እንደፈፀመ
መረጃ ይሰጣል፤ ተማሪው ትክክል በመለሳቸው መልሶች ላይ ተጨማሪ መልሶችን
እንዲያፈልቅ፣ ግድፈት ያለበትን ያሰራር ሂደት አቃንቶ እንዲያቀርብ ያደርጋል፤

18
ተማሪዎች ጥራት ያለው የአሰራር ሂደት እየለመዱ እንዲሄዱ እድል ይሰጣል፤
በቀጣይነት በተከታታይ የሚመጡ ተግባራትን ጊዜ ወስደው በአፅዕኖት
እንዲያከናውኑ የማድረግ ትልቅ ሚና አለው፡፡እንደ Michael (2011) ገለፃ ደግሞ
ግብረመልስ በተለይ ለቋንቋ ትምህርት አስፈላጊ የሆነ የትምህርቱ አካል
ነው፡፡ይኸውም የተማሪዎችን የቋንቋ አቅም የሚያሳድግ መሻሻላቸውን ለመለየት
የሚያስችል ተግባር ነው፡፡በተለይ የቃል ግብረመልስ በክፍል ውስጥ በሚቀርብበት
በጊዜ እያንዳንዱን የተግባር ክፍል ለማረም ያስችላል፡፡ለተማሪዎች ስራ
ግብረመልስ የማይሰጥ ከሆነ ሁሉም ተግባራቸው ልክ እንደሆነና ስህተት
እንደሌለባቸው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡በመሆኑም ግብረመልስ ተማሪዎች ከተሳሳተ
ተግባርና ባህሪ የሚያወጣ ዋነኛ መንገድ ነው በማለት ይገልፃሉ፡፡

2.9. የቃል ግብረመልስ በማን ይሰጣል?

Michael (2011) እንደሚያስረዱት ግብረመልስ የሚሰጠው ሰዎችን ለማጥቃት


ሳይሆን በተግባር ለማሻሻል ነው፡፡ ይህም ሰዎች ግብረመልስ ሲሰጡ አሉታዊና
አዎንታዊ ምላሽን ለማግኘት ነው፡፡ ማስታወስ ያለብን ግብረመልስ ሁልጊዜ
አዎንታዊ ላይሆን ይችላል፡፡ እንደ John & Helen (2007) ገለፃ የቃል ግብረመልስ
በመምህራን ወይም በአቻ ጓደኛ ሊቀርብ ይችላል፡፡

2.9.1 የጓደኛ /የብጤ / የቃል ግብረመልስ

John & Helen (2007) በጥናታቸው እንደገለፁት የጓደኛ ግብረመልስ በቋንቋ


ትምህርት ውስጥ ተማሪዎች በሰሩት ስራ ላይ ርስበርስ አንዱ ለሌላው የሚሰጠው
ርማትና አስተያየት ነው፡፡ የጓደኛ ግብረመልስ ለሁለተኛ ቋንቋም ሆነ ለአፍ መፍቻ
ቋንቋ ትምህርትና ለተማሪዎች መሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ አለው በማለት
ያስረዳሉ፡፡ ተማሪዎች ርስበርስ እንዲማማሩ እድል የሚፈጥር ነው ፡፡
Rollinson (2005) እንደሚገልፁት ደግሞ የጓደኛ ግብረመልስ ከክፍል ጓደኞቻቸው
የሚቀበሉት አስተያየት ነው፡፡ ለተማሪዎቹ ተመሳሳይ ልምድ ባላቸው አቻዎቻቸው
ስለሚቀርብ በቀላሉ የሚረዱት ግብረመልስ ነው በማለት ይገልፃሉ፡፡ በተጨማሪም
ተማሪዎች በጋራ የመተባበር መንፈስ ላይ ተመስርተው ተግባሮቻቸውን
እንዲያርሙ ሲደረግ ተማሪው ፈጣን ምላሽ ነገር ግን መምህራን አላማውንና

19
ጠቀሜታውን ባለመረዳትና ጊዜ ይሻማል በሚል ምክንያት በክፍል ውስጥ እንብዛም
አይተገብሩትም በማለት ያብራራሉ፡፡ ተማሪዎችም ቢሆኑ ከጓደኞቻቸው ጠቃሚ
ሀሳብ የሚያገኙ አይመስላቸውም፡፡ እንዲሁም ተማሪ ሊማር የሚገባው ጥልቅ
እውቀት ባላቸው በሙያው በሰለጠኑ ሰዎች (መምህራን) ብቻ ነው የሚል ሀሳብ
እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡ Rollinson (2005) እንደሚገልፁት የአቻ ግብረመልስ
የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነዚህም፡- የአስተያየት ሰጪዎቹን በጥልቀት
የማሰብ ችሎታን ያዳብራል፡፡ ስለ ጓደኞቻቸው መልሶችና ስራዎች ትክክለኛነቱን
እንዲያረጋግጡ ማስተዋል እንዲኖራቸው ያደርጋል፤ ተማሪዎች ከመምህራቸው
በተለየ ሁኔታ በቀላል ቋንቋ ግብረመልስ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ በራሳቸው
የመገምገሚያ መስፈርቶች እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፤ ግብረመልስ የመስጠትና
የመቀበል ልምዳቸውን ያዳብራል፤ ርስበርስ የመስጠትና የመቀበል ልምዳቸውን
ያዳብራሉ በማለት የጓደኛ የቃል ግብረመልስ ያለውን ጠቀሜታ ያስረዳሉ፡፡

2.9.2. የመምህራን የቃል ግብረመልስ

Michael (2011) እንደሚገልፁት ተማሪዎች በተማሩበት ላይ እንዴት ተግባራትን


ማስኬድና መቀጠል እንዳለባቸው በየክፍለጊዜያቱ በተግባራት ክንውን ወቅት
የሚሰጥ አስተያየት ሲሆን ጥያቄዎች ግልጽ ማድረግ ፣ተግባራት እንዴት
እንደሚከናወኑ የሚያሳዩ ቅደም ተከተሎችን ፣ለጥያቄዎች ትእዛዝና ማብራሪያ
መስጠት የሚሉትን ያካትታል፡፡ የመምህራን ግብረመልስ የተማሪዎችን ጠንካራና
ደካማ ጎን በመለየት የቋንቋ ችሎታቸውን ለማሻሻል የሚረዳ እቅድ ለመንደፍ
ያስችላል በማለት ይገልፃሉ፡፡ Lorna (2008) በጥናታቸው እንደሚገልፁት
መምህራን የተደራጀና በተማሪዎች የቋንቋ መሻሻል ላይ የሚያተኩር ግብረመልስ
መስጠት፣ ውጤታማ የሆነ ግብረመልስ የሚሰጡበት ሁኔታ ማመቻቸትና ተማሪዎች
ተገቢ ግብረመልስ እንዲሰጡ እድል መስጠት ለሚሉት ጉዳዮች ትኩረት መስጠት
አለባቸው፡፡

2.10. ግብረመልስ የሚሰጥባቸው ጊዜያት

እንደ John & Helen (2007) ገለፃ ግብረመልስ በጊዜ ተግባር እና በድህረ ተግባር
ሊሰጥ ይችላል ፡፡

20
ጊዜ ተግባር ግብረመልስ፡- በጊዜ ተግባር የሚሰጥ ግብረመልስ ተማሪዎች ወዲያውኑ
ሂሳቸውን እንዲለዩና ማሻሻል ያለባቸውን እንዲያሻሽሉ ያደርጋል፡፡ይህ ግብረመልስ
አዋጭና ውጤታማ የመማር ልምዶችን የሚያስገኝ ግብረመልስ ሲሆን ዝርዝር
መለኪያዎች የያዘና በተጨማሪም አይረሴነት ያለው የቋንቋ ችሎታን የሚያዳብር
ነው፡፡

ድህረ ተግባር ግብረመልስ፡- እንደ John & Helen (2007) ገለፃ ተማሪዎች
ወዲያውኑ የሚሻሻሉበትን መንገድ አይጠቁምም፡፡ ከተግባራት በኋላ የሚሰጥ
በመሆኑ ብዙ ጊዜ በጽሁፍ ይቀርባል፡፡ ለዚህ አይነት ግብረመልስ ተማሪዎች
ትኩረት ስለማይሰጡ መምህራንን ለተደጋጋሚ ርማት ይዳርጋል በማለት
ያብራራሉ፡፡ ርማቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሰጥበት ምክንያት ተማሪዎች ርማቱን
ወዲያው እንዲወስዱ ሳይሆን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን በቀጣይ እንዲያሻሽሉ
ለማድረግ ነው፡፡እንደ (John & Helen 2007) ገለፃ አስተያየቱን አይተው ርማት
ለሚወስዱ ጠንካራ ተማሪዎች አዋጭ ሲሆን ሁልጊዜም እንዲጥሩ እድል
ይፈጥራል፡፡ ደከም ለሚሉ ተማሪዎች ግን (የመማር ችሎታቸው በማዳመጥ ላይ
ለተመሰረቱ ተማሪዎች) አሰልቺ ግብረመልስ ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች በቋንቋ
ለመዳበራቸው ጊዜ ተግባር ግብረመልስ ጥሩና ተቀባይነት ያለው መሆኑን (John &
Helen 2007) ያስረዳሉ፡፡

2.11. ንድፈሀሳባዊ ፍልስፍና


እንደ Creswell (2014) ገለፃ የተለያዩ የጥናት ፍልስፍናዎች አሉ፡፡ለዚህ ጥናት
ተስማሚ የሆነው ፍልስፍና ግን የግንባታውያን ነው፡፡ በግንባታዊያን ፍልስፍና
መምህሩም የተማሪዎችን ክፍተት የሚሞላ፣ የሚያደንቅና ለተማሪዎች ጥያቄ ምላሽ
የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ፍልስፍና ተማሪዎች ከመምህራን፣ ከጓደኞቻቸውና
ከወላጆቻቸው በሚያገኙት መልስ ይቀየራሉ፡፡ ከሌሎች ጋር በሚፈጠሩት
መስተጋብር ይማራሉ፡፡ መማር የልምድ ማካበት ስራ ነው፡፡በቋንቋ ትምህርት
ወቅት በልምምድ ጊዜ የሚሰጥ ግብረመልስ የተፈለገውን ዓይነት ሆኖ ሲገኝ
የመማር ግስጋሴን ያፋጥናል፡፡ ይህም ማለት ልምምዱ እየጎለበተ ሊመጣ የሚችለው
በግብረመልሱ አማካኝነት ነው፡፡ Guerrero & Villamil (2000) እንደሚገልፁት
ደግሞ በዚህ ፍልስፍና መሰረት በጎ ምላሽ ወይም አሉታዊ ምላሽን በመጠቀም

21
ክሂሎችን ማጎልበትና ስህተቶችን መቀነስ ያስችላል፡፡ የዚህ ንድፈሀሳብ ቀማሪ
የሆነው ቪጎትስኪ ሲሆን በእሱ እይታ ተማሪዎች በመስተጋብር አማካኝነት
አዕምሯቸውን ያሳድጋሉ፡፡ በቋንቋ መማሪያ ክፍል ውስጥ ግብረመልስን መተንተን
ለቋንቋ ግብዓት ይሆናል፡፡ ይህ ጥናትም በመማሪያ ክፍል ውስጥ በሚሰጡ
የማስተካከያና የማነቃቂያ ምላሾች (ግብረመልሶች) ላይ ስለሚያተኩር ይህ ፍልስፍና
ይስማማዋል፡፡

Creswell (2014) እንደሚገልፀው በአወንታዊና አሉታዊ ምላሽ ምክንያት


የሚፈጠረውን መስተጋብራዊ ሁኔታ ይተነትናል፡፡ይህ ጥናት የሚከተለው
የግንባታውያንን ፍልስፍና ነው፡፡ እንደ Creswell (2014) እና Wolf (2010) ገለፃ፣
ይህ ፍልስፍና በመማር ማስተማር ሂደት ለተማሪዎች አዕምሯዊ ግንባታ አዳዲስ
ነገሮች ማግኘት ወሳኝ ነው፡፡ መምህሩም የተማሪዎችን ክፍተት የሚሞላ፣
የሚያደንቅና ለተማሪዎች ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ፍልስፍና
ተማሪዎች ከመምህራን፣ ከጓደኞቻቸውና ከወላጆቻቸው በሚያገኙት ግብረመልስ
ራሳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ከሌሎች ጋር በሚፈጥሩት መስተጋብር ይማራሉ፤ በአዕምሮ
ያድጋሉ፡፡ የመማር ማስተማር ተግባር ትብብር፣ ተግባቦትና መስተጋብርን ማካተት
ይኖርበታል፡፡እነዚህ ተግባራት የክፍል ውስጥ ክንውኑን ማህበራዊነት ያላብሱታል፡፡
በተጨማሪም ግብረመልስ ለክሂላቸው መዳበር ከፍተኛ እገዛ አለው በማለት
ይገልፃሉ፡፡ Guerrero & Villamil (2000) እንደሚገልፁት በግለሰቦች መካከል
የሚከናወኑ እርስበርሳዊ እና አዕምሯዊ ተግባራት በመጨረሻ ላይ ሂደቱ ወደ
ግለሰባዊ አዕምሯዊ ተግባራት በመሸጋገር ወይም በመቀየር የግለሰቡን ልምድ
ያዳብራሉ፡፡ እንዲሁም መስተጋብራዊ ሂደቱም መከናወን የሚኖርበት በተማሪዎችና
ከተማሪዎች የተሻለ ችሎታ ወይም ሙያ ባላቸው (መምህራን) መካከል መሆን
አለበት በማለት ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናት በተማሪዎችና በመምህራን
መካከል የሚካሄዱ የቃል ግብረመልሶችን የሚያጠና በመሆኑ ፍልስፍናው
ይስማማዋል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ጥናት በመስተጋብርና በግብረመልስ ላይ ያተኮረ በመሆኑ


ከፍልስፍናው ጋር ይዛመዳል፡፡ ተማሪዎች ከመምህራቸውና ከክፍል ጓደኞቻቸው
በሚኖራቸው መስተጋብር ሳቢያ የቋንቋ ትምህርቱን የሚያስኬዱበትን ሁኔታ

22
ያሳያል፡፡ግብረመልስን ማግኘት በተማሪዎች ክሂል ላይ ያለውን አስተዋፅኦ
ይተንትናል፡፡

2.12. የተማሪዎችና የመምህራን አተያይ (በቃል ግብረመልስ ላይ)

የቋንቋ ተማሪዎችና መምህራን በተማሪዎች የመማር ብቃት ላይ ተንተርሶ


ግብረመልስ መስጠትና መቀበል ይገባል አይገባም በሚለው ሀሳብ ላይ ተመሳሳይ
የሆነ አመለካከት እንደማያራምዱ ድርሳናት ይጠቁማሉ በማለት ፋንታዬ (1998)
ይገልፃሉ፡፡ በሰዎቹ መካከል ያለው የአመለካከት ልዩነት በሁለት በኩል ተከፍሎ
ይታያል፡፡ አንደኛው ወገን ግብረመልስ መስጠት የተማሪውን የመማር አቅም
በማጠናከር በኩል ምንም ሚና የለውም፤ በመሆኑም የተማሪው ስራ በተለይም
ስህተት የሆነው ሙከራው መታረም የለበትም የሚለውን ሀሳብ ያራምዳሉ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ግብረመልስ የተማሪውን የመማር ፍጥነት ስለሚጨምር ለተማሪው
ሁልጊዜም ተገቢ የሆነ ርማት መስጠት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ በመርህ ደረጃ መምህሩ
ለተማሪው ስራ ርማትን ደጋግሞ የሚሰጠው ተማሪው በመማር ሂደቱ
የሚፈጽማቸውን ስህተቶች እየቀነሰ ትክክለኛውን የአሰራር ሂደት እንዲከተል ነው
ሲሉ Ur (1989) ይገልፃሉ፡፡ይሁን እንጂ Richards & Lockhart (1996)
እንደሚገልፁት (Cohen & Robins 1976) ባጠኑት ጥናት በአንድ ዩንቨርስቲ ውስጥ
እንግሊዘኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የሚማሩ ተማሪዎች በፃፏቸው ድርሰቶች ላይ
የተሰጡ ተከታታይ ርማቶች ተማሪዎቹ ስህተትን ደጋግመው ከመፈፀም
እንዳላገዳቸው ማመልከቱ ግብረመልስ መስጠት የተማሪውን ስህተት ሊቀንስለት
እንደማይችል ጠቋሚ ሆኗል በማለት ይገልፃሉ፡፡

Wajnryb (1991) ሁለቱም አመለካከቶች ተገቢ ናቸው ይላሉ፡፡ግብረመልስ መስጠት


ተገቢ አይደለም በሚለው ጎራ ሀሳብ ሲያስቀምጡ አዋቂ ለሆኑ ተማሪዎች
ሙከራቸው ትክክል መሆን አለመሆኑን በግልጽ ብናሳውቃቸውም ባናሳውቃቸውም
በተማሪዎቹ ሂደት ላይ ምንም ተጽዕኖ አያሳድርም ነገር ግን ለሁለተኛ ደረጃ
ተማሪዎች ምን በትክክል እንደተማሩና እንዳልተማሩ ግልጽና የተብራራ
አወንታዊና አሉታዊ ግብረመልስ መስጠት ይገባል ይላሉ፡፡ Nunan (1988) ም
ግብረመልስ ተማሪዎች ነገሩን በትክክል ወይም በስህተት መንገድ የተረዱት

23
መሆኑን መረጃ የሚሰጥ ስለሆነ እና የተማሪውን የመማር አቅም የሚጨምር ስለሆነ
ሁልጊዜም ለተማሪው ስራ ግብረመልስ መስጠት ይገባል በማለት ይገልፃሉ፡፡

2.13. የቀደምት ስራዎች ቅኝት

ይህ ክፍል ከዚህ ጥናትጋር ተቀራራቢ የሆኑ ስራዎች የሚነሱበት ነው፡፡ከዚህ


በፊት ግብረመልስን የተመለከቱ ስራዎችን ስንመለከት እታለማሁ (2006)
ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ያቀረበችው ጥናት ላይ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን
በተማሪዎቻቸው የጽሁፍ መለማመጃ ላይ የሚሰጡት ጽሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ
ፍተሻ በሚል ርዕስ የፅሁፍ ግብረመልስን መሰረት ያደረገ ጥናት ያቀረበች ሲሆን
የጥናቱ ዓላማ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎች የጽሁፍ ልምምድ ላይ
የሚሰጡትን የጽሁፍ ግብረመልስ መፈተሽ ሲሆን በመደምደሚያውም መምህራን
የሚሰጡት ግብረመልስ አይነትን፣ ስልት፣ ትኩረት እና ባህሪ ለመለየት ችላለች፤
በጥናቷም የቃል ግብረመልስ ለቋንቋ ትምህርት ያለው አስተዋፅኦ የላቀ ቢሆንም
ባላባት የጊዜ እጥረት አኳያ የቃል ግብረመልስን አለማካተቷንና ቢጠና የተሻለ
መሆኑን ጠቁማለች፡፡ አስካል (2001) ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ባቀረበችው ጥናት
ላይ ተማሪዎች ለሚጽፏቸው ድርሰቶች በመምህራን የሚሰጡ ምላሾች
የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸው ተፅዕኖ በሚል
ርዕስ የፅሁፍ ግብረመልስን መሰረት ያደረገ ጥናት ያቀረበች ሲሆን የጥናቱ
አላማ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተማሪዎቻቸው ለሚጽፏቸው ድርሰቶች
የሚሰጣቸውን ግብረመልሶች የመፃፍ ችሎታቸውን በማዳበር በኩል ያለውን
ተፅእኖ መፈተሽ ሲሆን ለመረጃ መሰብሰቢያነት የዋለውም ሰነድ ፍተሻ፣ የፅሁፍ
መጠይቅና ቃለ መጠይቅ ሲሆኑ መምህራን ትክክለኛውን የግብረመልስ አሰጣጥ
ሂደት ስለማይከተሉ የሚሰጡት ግብረመልስ ለመፃፍ ክሂል መዳበር ያለው
አስተዋፅኦ አናሳ እንደሆነ ገልፃለች ፤ጥናቱ በፅሁፍ ግብረመልስ ላይ ብቻ
ያተኮረ ነው፡

ዳዊት (2008) ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባቀረበው ጥናት ላይ የመምህር ተማሪ


ምክክርና የመምህር የጽሁፍ ግብረመልስ በተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ላይ
ያላቸው ተጽእኖ በሚል ርዕስ የጽሁፍ ግብረመልስን መሠረት ያደረገ ጥናት
አቅርቧል፡፡ የጥናቱ ዓላማም የመምህር ተማሪ ምክክርና የመምህር የጽሁፍ
ግብረመልስ በተማሪዎች የመፃፍ እድገት ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ መመርመር
ሲሆን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴው ፈተና ነው፡፡ በመደምደሚያው የጽሁፍ
ግብረመልስና የተማሪና መምህር ምክክር በተለይም ለሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች
የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው አመላክቷል፡፡ ይህም ጥናት ስለግብረመልስ

24
ቢያጠናም አስተዋፅኦው ለሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች እንደሆነ እንጂ ለአፈፈት
ተማሪዎች ያለውን አስተዋፅኦ አላመለከተም፡፡ ሶስቱም ጥናቶች የሚያተኩሩት
በጽሁፍ ግብረመልሶች ላይ ሲሆን ይህ ጥናት ግን በአማርኛ ትምህርት
ክፍለጊዜያት የሚሰጡ የቃል ግብረመልሶችን መተንተን ላይ የሚያተኩር
በመሆኑና ሁለቱም ጥናቶች የመረጃ መሰብሰቢያቸው ሰነድ ፍተሻ፣ ቃለ
መጠይቅና የጽሁፍ መጠይቅ መሆኑና የዳዊት ጥናት ደግሞ መረጃ
መሰብሰቢያው ፈተና እና ቃለመጠይቅ መሆኑ ፣ የዚህ ጥናት ዋነኛ መረጃ
መሰብሰቢያ ደግሞ ምልከታ መሆኑ እንዲለይ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም በጊዜና
በቦታ ይለያያል፡፡

ሀይማኖት (2011) የድርሰት መለማመጃዎች ላይ የሚሰጡ የቃልና የፅሁፍ


ግብረመልሶች ትንተና በሚል ያቀረበችው ጥናት አላማው ተማሪዎች በፃፏቸው
ድርሰቶች ላይ መምህራን የሚሰጧቸውን ግብረመልሶችን መተንተን ሲሆን
መረጃ መሰበሰቢያዋም ምልከታ ፣ የተማሪ ወረቀቶች እና ቃለመጠይቅ ናቸው፡፡
በግኝቷም መምህራን አዘውትረው ትዕዛዛዊና ገምጋሚ ግብረመልሶችን
እንደሚጠቀሙ አመላክታለች፤ በተጨማሪም መምህራን የሚሰጡትን
ግብረመልስ ተገቢነት ለማመልከት የተሰሩ ጥናቶች ስለሌሉ ተጨማሪ ጥናቶች
ቢሰሩ መልካም እንደሆነ ጠቁማለች፡፡ ጥናቱ በግብረመልስ ላይ ማተኮሩ ከዚህ
ጥናት ጋር ቢያመሳስለውም የሃይማኖት ጥናት ያተኮረው በቃልም በፅሁፍም
ግብረመልስ ላይ ሲሆን ይህ ጥናት ያተኮረው በቃል ግብረመልስ ላይ ብቻ
መሆኑ እንዲለይ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም የዚህ ጥናት መረጃ መሰብሰቢያ
ምልከታ ብቻ መሆኑ እንዲለይ አድርጎታል፡፡ ፋንታዬ (1998) የአማርኛ
መምህራን ቃላዊ ምጋቤምላሽ አሰጣጥ ስልቶች ፍተሻ በሚል ርዕስ ያቀረቡት
ጥናት አላማው ስኬታማና ስኬታማ ያልሆኑ ቃላዊ ምጋቤምላሾችን መለየት
ሲሆን መረጃ መሰብሰቢያው ቃለመጠይቅ፣ ምልከታና የፅሁፍ መጠየቅ ናቸው፡፡
በውጤቱም የመምህራኑ ምጋቤምላሾች ወጥነት የሌላቸውና ጊዜን ያልጠበቁ
መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ይህ ጥናት በቃል ግብረመልስ አቀራረብ ስልቶች ላይ
ብቻ ያተኮረ በመሆኑ የቃል ግብረመልስ ከሌሎች መልኮች አንፃር ቢጠና
መልካም መሆኑን ተጠቁሟል፡፡ በቃልግብረመልሶች ማተኮሩ ከዚህ ጥናት ጋር
ቢያመሳስለውም በዓላማውና በመረጃ መሰብሰቢያው ይለያል፡፡

25
ምዕራፍ ሶስት፣ አጠናን ዘዴ

የዚህ ምዕራፍ ዓላማ በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡ የቃል


ግብረመልሶችን ዓይነት፣ ስልትና ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ መተንተን
ነው፡፡ ይህን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ተግባራዊ የተደረገው ያጠናን ዘዴ፣ የናሙና
አመራረጥ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ፣ የመረጃ አሰባሰብ ሂደቱ የመረጃ መተንተኛው
ዘዴ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

3.1. የጥናቱ ዘዴ
ይህ ጥናት የሚከተለው የግንባታውያንን ፍልስፍና ነው፡፡ ይህ ጥናት ተንታኝ ሲሆን
ዓይነታዊ ምርምር ስልትን የተከተለ ነው፡፡ ጥናቱ ሁኔታዎችን የሚዳስስና
አጠቃላይ ግንዛቤ የሚሰጥ ሲሆን አሁን ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ገለፃ ለማድረግ
የተከናወነ ጥናት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናት በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት
የሚሰጡ የቃል ግብረመልስ ዓይነቶችን፣ ስልቶችና ግብረመልሱ ያለውን
ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ በንዑሳን ክፍሎች ከፋፍሎ አሳይቷል፡፡
ለጥናቱ ዋነኛ መረጃ መሰብሰቢያ የሆነው የክፍል ውስጥ ምልከታ ሲሆን አጥኝዋ
በተከታታይ ክፍለጊዜያት ምልከታ በማድረግና በምልከታው ወቅት የክፍል ውስጥ
የቃል ግብረመልሶችን በመቅረፀ ምስል በመቅረፅ የተገኘው መረጃ ወደምዝግብ
መረጃ ተቀይሮ በዓይነታዊ መረጃ መተንተኛ ዘዴ በትረካዊ መንገድ በጥንቃቄ
ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ይህ ጥናት የሚከተሉትን ንድፎች ተጠቅሟል፡፡ አንደኛው ከበደ
(2009) Rymens (2008) እና Ten Have(2008) ን በመጥቀስ ካዘጋጀው የተወሰደ
የጥናት ንድፍ ነው፤ይህም የቃል ግብረመልስን ለመተንተን እውነተኛ የመማሪያ
ክፍል የቃል ግብረመልስ መቅረፅ፣ ምዝግብ መረጃ ማዘጋጀት፣ ከምዝግብ መረጃው
የተመረጡትን መረጃዎች መተንተንና ጥናቱን መዘገብ የሚሉት ናቸው፡፡ ይህ
ጥናት በተግባር ላይ ሲውል ከአንደኛው ሂደት ወደ ሌላኛው ሂደት በቅደምተከተል
ጥናቱ ተከናውኗል፡፡

26
እውነተኛ የመማሪያ ክፍል የቃል ግብረመልስን መቅረፅ

ምዝግብ መረጃ ማዘጋጀት

ከምዝግብ መረጃው የተመረጡት የቃል ግብረመልስ መረጃዎች መተንተን

ጥናቱን መዘገብ

ሥዕል1፣ የከበደ (2008፡62) የጥናት አከዋወን ንድፍ መሰረት በማድረግ በአጥኚዋ የተዘጋጀ
ንድፍ

ሌላኛው ንድፍ ያለው (2004፡424) ማይልስና ሁበርማን (1994፡12) ን ጠቅሶ


ዓይነታዊ መረጃ ትንተና ክፍሎችን ቀጥሎ የተገለፀውን ዓይነት ተራክቧዊ ሞዴል
እንዳላቸው ይገልፃል፡፡ እነሱም፡- መረጃ ስብሰባ፣ መረጃ ቅነሳ፣ መረጃ ማሳየትና
ማጠቃለያ መስጠት ናቸው፡፡

መረጃ መሰብሰብ

መረጃ ቅነሳ

ማጠቃለያ መስጠት

መረጃ ማሳየት

ሥዕል 1 .ያለው (2004፡424) የመረጃ ትንተና ተራክቧዊ ንድፍ መሰረት በማድረግ


በአጥኚዋ ተሻሽሎ የቀረበ

አጥኚዋ ይህን ንድፍ መሰረት በማድረግ መረጃው ከተሰበሰበ በኋላ የተሰበሰበው


መረጃ የመማሪያ ክፍል የቃል ልውውጥ መረጃ ሁሉም ስለማይቀርብ በትንተናው
ወቅት አስፈላጊ ምሳሌዎችን የያዙ ቀረፃዎችን በመጠቀም የመረጃ መጠንን
ለመቀነስ ሞክራለች፡፡ ከዚያም መረጃን ማሳየት ቀጣዩ የመረጃ ትንተና ሂደት ነው፡፡

27
የቃል ግብረመልስን በተመለከተ የተገኘው መረጃ በመልክ በመልክ በማደራጀት
በተለያየ መንገድ በቀጥታ ለአንባቢ ቀርቧል፡፡ መረጃው መምህራንና ተማሪዎች
ርስበርስ የተለዋወጡትን የቃል ግብረመልስ ለማሳየት በቅደምተከተል ማብራሪያ
በመስጠት ተተንትኗል፡፡ በመጨረሻ ማጠቃለያ ላይ በመድረስ በጥናቱ ዝርዝር
ዓላማዎች መሰረት ከትንተናዎች የተገኙት ውጤቶች ማጠቃለያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

3.2. የናሙና አመራረጥ ዘዴ

ይህ ንዑስ ክፍል የጥናቱ ናሙና እንዴት እንደተመረጠ ያስረዳል፡፡ስለዚህ የጥናቱ


ቦታና የጥናቱ ተሳታፊዎች በምን ዓይነት የንሞና ዘዴ እንደተመረጡ ያሳያል፡፡

3.2.1. የትምህርት ቤት ናሙና አመራረጥ

ይህ ጥናት የተካሄደው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር ወረዳ በሚገኘው


አንኮበር የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ላይ ነው፡፡ አንኮበር ወረዳ ከደብረብርሃን 42 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በስተምስራቅ
ይገኛል፡፡ በዚህ ወረዳ ሁለት የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና አጠቃላይ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ፡፡በወረዳው ከሚገኙት ሁለቱ ትምህርት
ቤቶች አንኮበር ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በአመቺ ናሙና ዘዴ ተመርጧል፡፡ ተመራጭ የሆነበትም ምክንያትም አጥኝዋ
ለምትኖርበት አካባቢ ቅርብ በመሆኑና በዚሁ ትምህርት ቤት የምታስተምር
በመሆኗ ወጪ ስለሚቀነስና በዚሁ ትምህርት ቤት መምህርት በመሆኗ ከት/ቤቱ
የአማርኛ ቋንቋ ከመምህራን ጋር ባላት ቀረቤታ መረጃዎችን በቀላሉ የማግኘት
እድሏን የሰፋ ስለሚያደርገው ነው፡፡

3.2.2. የክፍል ደረጃ አመራረጥ

በጥናቱ የተመረጠው ትምህርት ቤት ከዘጠነኛ እስከ አስራ ሁለተኛ የክፍል


ደረጃዎችን የያዘ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የዘጠነኛ ክፍል በአላማ ተኮር የናሙና
አመራረጥ ዘዴ ተመርጧል፡፡ የዘጠነኛ ክፍል የተመረጠበት ምክንያትም የዓመቱ
የትምህርት ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ በትምህርት ገበታቸው ላይ ስለሚገኙ በቂ
መረጃ ለማግኘት ይረዳል በሚል ነው፡፡ በብሄራዊ ፈተና ምክንያት ዓመቱን ሙሉ
በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙት የአስረኛና አስራሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች

28
ለጥናቱ አልተመረጡም፡፡ የአስራአንደኛ ክፍልም ካለባቸው የትምህርት ጫና
አንፃር ክፍሉ አልተመረጠም፡፡ በዘጠነኛ ክፍል ደረጃ ከሚገኙት ስድስት ምድቦች
ውስጥ ሁለቱ ምድቦች በቀላል የእጣ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ ምክንያቱም የጥናቱን
ናሙና ለመመጠን አመቺ ስለሆነ ነው፡፡

3.2.3. የተማዎች ናሙና አመራረጥ


በቀላል የእጣ ናሙና የተመረጡት የክፍል ምድቦች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች
በጠቅላይ ናሙና ተወስደው በጥናቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

3.2.4. የመምህራን ናሙና አመራረጥ


የዚህ ጥናት ተሳታፊዎች በአንኮበር ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና አጠቃላይ
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ናቸው፡፡
በናሙናነት በተመረጠው ክፍል ውስጥ ሁለት ሴት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ያሉ
ሲሆን ሁለቱም በጠቅላይ ናሙና ተመርጠው የጥናቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

3.3. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ


ይህ ጥናት አላማው በአንኮበር ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና አጠቃላይ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡ የቃል
ግብረመልሶችን መተንተን ነው፡፡የዚህ ጥናት ዋና አላማ ይሳካ ዘንድም የክፍል
ውስጥ ቀጥተኛ ምልከታ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሆኖ አገልግሏል፡፡

 ምልከታ

ምልከታ የጥናቱ ዋነኛ መረጃ መሰብሰቢያ መንገድ ነው፡፡እንደ ያለው (2009) ገለፃ፣
ምልከታ መረጃ ሰብሳቢው ከተጠኝዎች ጋር ወይም አካባቢ በመሆን
የሚያደርጉትንና የሚናገሩትን ነገር እያየና እየሰማ በመዘገብ መረጃ የሚሰበሰብበት
ዘዴ ነው፡፡ ተመራማሪው ተጠኝዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመሆን በዚያ ወቅት ምን
እንደሚሰሩ፣ እንዴት እንደሚሰሩ፣ እርስ በርሳቸው እንዴት እንደሚራከቡ፣ ምን
እንደሚናገሩ መረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናት በክፍል ውስጥ
በመገኘት በክፍለጊዜያቱ የሚሰጡ የቃል ግብረመልሶችን በቀጥታ በቪዲዮ ካሜራ
በመቅረጽ ምልከታውን አከናውና መረጃውን ሰብስባለች፡፡

29
3.4. የመረጃ አሰባሰብ ሂደት
በመረጃ ስብሰባው ወቅት መምህራንም ሆኑ ተማሪዎች ምልከታው በመቅረፀ ምስል
መቀረፁን ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር፡፡ ነገርግን አጥኚዋ መረጃው ለምን ዓላማ
እንደሚውል በማስረዳቷና ከአጥኚዋ በስተቀር መረጃውን የሚያየውም ሆነ
የሚጠቀመው እንደሌለ በማስገንዘቧ ፍቃደኛ ሆነው ቀረፃው ተካሂዷል፡፡ ቀረፃው
በሌላ መምህር የተካሄደ ሲሆን በምልከታው ወቅት አጥኚዋ በመማሪያ ክፍል
በመገኘት የመማር ማስተማሩን ሂደት ተከታትላለች፡፡ ይህም በመቅረጸምስል
የተገኘውን መረጃ ወደምዝግብ መረጃ ስትቀይር አግዟታል፡፡ቀረፃው ቀጥሎ
በተዘረዘሩት ቀናት ተግባራዊ ሆኗል፡፡

ሰንጠረዥ 1 ቀረፃ የተካሄደበትን መረሀ ግብር የሚያሳይ ሰንጠረዥ

መምህር የክፍል ምድብ ክፍለጊዜ ቀናት

ሀ ሀ 8:06-8:48 01/08/2011

ሀ ሀ 9:45-10:27 04/08/2011

ለ ሠ 4:21-5:03 17/08/2011

ለ ሠ 5:45-6:27 18/08/2011

ለ ሠ 4:21-5:03 30/08/2011

ሀ ሀ 9:03-9:45 01/09/2011

ሠንጠረዥ 3.1

በመቀጠልም አባሪ የሚሆኑ ምዝግብ መረጃዎችን ለማዘጋጀት ያገለገሉ አህፅሮተ


ቃላትና ምልክቶች ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ከበደ (2009) እንደሚገልፀው
በንግግር ልውውጥ ጥናት ለትንተና የሚሆነው ጥሬ መረጃ የሚገኘው ከምዝግብ
መረጃው ነው፡፡ይህም መረጃውን ለትንተና ዝግጁ ለማድረግ ይጠቅማል በማለት
ይገልፃል፡፡ ከበደ (2009) Jeffrson (2004) ን በመጥቀስ የምዝግብ መረጃ
አዘገጃጀት ደንብና ምልክቶችን ባስቀመጠው መሰረት በዚህ መሰረት ለዚህ ጥናት
ይመች ዘንድ አጥኚዋ በምልከታ ወቅት በመቅረፀ ምስል ለተገኙ መረጃዎች ከበደ
(2009) የተጠቀመውን Jeffrson (2004) ደንብ መሰረት በማድረግ በምዝግብ
መረጃው ላይ ላሉ ቁጥሮችና ምህጻረ ቃላት የሚከተለውን መግለጫ አስቀምጣለች፡፡
ከዚህ በታች የቀረቡት ምልክቶች የምዝግብ መረጃው ሲዘጋጅ የተለዋወጡትን የቃል
ግብረመልስ ለማመልከት ለመምህራንና ለተማሪዎች የተሰጡ ኮዶች

30
ናቸው፡፡የእያንዳንዱ ተናጋሪ ዐ.ነገር ሲመዘገብ በቅድሚያ የመጀመሪያ ሆሄ ወይም
ሁለት ሆሄዎች እንዲጻፉ ተደርጓል፡፡

ሠንጠረዥ 2 ፡- የምዝግብ መረጃ ምልክቶችና መግለጫ

ምልክት መግለጫ ምሳሌ

ተ1 እነዚህ ከቁጥር ጋር የተቀመጡት ተ1፡አንቺ ምድር


ምህፃረቃላት ተማሪ አንድ (ተ1) ፍረጂኝ ዘይቤ
፣ተማሪ ሁለት (ተ2) የሚለውን
ለማመልከት የገቡ ናቸው፡፡ ተ2፡ፈሊጥነው፡፡
ተ2…

01 እነዚህ ቁጥሮች ተማሪና መምህር ሀሳብ 01 መ፡ስማዊ ሀረግ


02 ሲለዋወጡ የመናገር ተራቸውን የሚመሰርትልኝ?
03… ያሳያሉ፡፡
02 ተ1፡አዋቂ ልጅ

ተጋ ተማሪዎች በጋራ የሰጡትን ግብረመልስ 01መ፡በባለፈው ምን


ያሳያል፡፡ ተማርን?

02 ተጋ፡ ስለ ሰዋሠው

መ/ርት መምህራንን ያሳያል፡፡ 01 መ/ርት፡የተማሪ እ?

መተ መምህራንና ተማሪዎች የሰጡትን የቃል 01 መ/ርት፡የህፃን እ?


ግብረመልስ ያሳያል፡፡
02 ተጋ፡ብልጥ

ክ መረጃው የተወሰደበትን ክፍል ያሳያል፡፡ ክፍል ሀ

ም ምዝግብ መረጃን ይገልፃል፡፡ ምዝግብ መረጃ 1

ክ/ጊዜ ምልከታ የተደረገበትን ክፍለጊዜ ክፍለጊዜ 1


ያሳያል፡፡

አ ምሳሌው የተወሰደበትን አባሪ ቁጥር አባሪ 1


ያሳያል፡፡
ሠንጠረዥ 3.2

31
3.5. የመረጃ አተናተን ዘዴ

የጥናቱ ዓይነት ተንታኝ ሲሆን ዓይነታዊ ዘዴን በመከተል የጥናቱ መረጃ የተተነተነ
ሲሆን የመተንተኛ ስልት ሆኖ የተመረጠውም የዲስኩር ትንተና ነው፡፡ ከበደ
(2009) Mazland (2006) ን በመጥቀስ እንደሚገልፀው የዲስኩር ልውውጥ ትንተና
በንግግር አማካኝነት ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጥናት ይረዳል፡፡ዓላማው
ተሳታፊዎቹ የግብረመልስ አሰጣጥ ሂደታቸው ምን ይመስላል? የሚለውን መግለፅ
ነው፡፡በተፈጥሮ የሚከሰተውን እውነተኛ ንግግር መሰረት በማድረግ ተሳታፊዎቹ
የሚያከናውኑትን ድርጊትና ባህሪይ ይመረምራል፡፡ በዚህ ጥናት በመረጃ መተንተኛ
ስልትነት ተግባራዊ የሆነው የዲስኩር ትንተና አቀራረብ ነው፡፡ ይህን አቀራረብ
መሰረት በማድረግ የቃል ግብረመልስ አሰጣጥ ሂደቱ በጥናቱ መሪ ጥያቄዎች አንፃር
ትንተናው ቀርቧል፡፡

32
ምዕራፍ አራት፣መረጃ ትንተና፣የውጤት ማብራሪያና ትርጎማ
የዚህ ምዕራፍ ዋና ዓላማ የጥናቱን መረጃ ትንታኔ፣ የውጤት ማብራሪያና ትርጎማ
በቅደም ተከተል ማቅረብ ነው፡፡የጥናቱ መሪ ጥያቄዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
ክፍለጊዜያት መምህራንና ተማሪዎች ምን ዓይነት ግብረመልስ ይሰጣሉ?
ግብረመልሶቹ የሚቀርቡባቸው ስልቶች ምን ምን ናቸው? የሚቀርበው የቃል
ግብረመልስ ምን ምን ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፆኦ አለው? የሚሉት
ናቸው፡፡በእያንዳንዱ የጥናት ጥያቄ ሥር በክፍል ውስጥ ምልከታ ከተሰበሰቡት
መረጃዎች ለናሙና የተመረጡ መረጃዎች በማቅረብ ተተንትነዋል፡፡ ስለሆነም
የመረጃ ትንተናው የጥናቱ መሪ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ ተደራጅቶ ቀርቧል፡፡

4.1. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት በመምህራንና በተማሪዎች


የሚሰጡ ግብረመልሶች ምን ዓይነት ናቸው?
መምህራን ከባህሪይ አንፃር አዎንታዊና አሉታዊ፣ የማስተካከያ፣ ገምጋሚና ገላጭ
ግብረመልሶችን ይሰጣሉ፡፡ከቋንቋ አንፃር ደግሞ ይዘታዊና ቅርፃዊ ግብረመልሶችን
ይሰጣሉ፡፡በናሙናነት በተመረጡት የመማሪያ ክፍሎች የሚሰጡት ግብረመልሶች
ደግሞ እንደሚከተለው ተተንተነው ቀርበዋል፡፡

4.1.1. አወንታዊ ግብረመልስ


አወንታዊ ግብረመልስ የተማሪዎችን ስራ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ለማሳየት
የሚቀርብ ነው፡፡ይህ ግብረመልስ በጠንካራ ጎን ላይ የሚተኩር ነው፡፡በቋንቋ
ትምህርት ወቅትም መምህሩ የተማሪዎችን ትክክለኛ መልስ መመለሳቸውን
ለማሳየት ይገለገሉበታል፡፡ወይም ጥሩ ሙከራ ማድረጋቸውን ያበረታቱበታል፡፡

ምሳሌ 1

60 መ/ርት፡ ልጅቷ ላሚቷን አለበች፡፡ እህ…

61 ተ16፡ ልጅቷ የሚለው ባለቤት፣ላሚቷ የሚለው ደግሞ

ተሳቢ ሲሆን አለበች የሚለው ማሰሪያ አንቀፅ

62 መ/ርት፡ ማሰሪያ … አንቀፅ በጣም ጥሩ …

(ም 2፣ ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 2፣አ 2)

33
ከዚህ በላይ በምሳሌ 1 በቀረበው የሀሳብ ልውውጥ እንደሚታየው ተማሪ
አስራስድስት የዐ.ነገሩን ክፍል በሚገባ ስለገለፀች መምህርቷ “በጣም ጥሩ” የሚል
ለትክክለኛነቷ ማረጋገጫ የሚሆን አወንታዊ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡መምህርቷ
ይህን ቃል በመጠቀማቸው ምላሽ የሰጠችው ተማሪ ጥሩ ስሜት እንዲሰማትና
ሌሎችም ተማሪዎች ለቀጣይ መልስ እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል፡፡

ምሳሌ 2

99 ተ20፡ ብልህ

100 መ/ርት፡ ብልህ …እሺ አሁን አንቺ ያሰብሽው ቅድም

ይመስለኛል፡፡ሀረግ አርጊው እስኪ ብልህን

የቅድሟን አቀናጂና፡፡ሀረግ አርጊው፡፡አይዞሽ

101 ተ19፡ (ለአፍታ ዝም አለች)

102 መ/ርት፡ የተማሪ ብለሻል አይደል?

103 ተ19፡ አዎ

104 መ/ርት፡ ቀኝ መሪው ብልህ ተሰጥቶናል፡፡ቅፅል አንድ ላይ

አቀናጂና ቅፅላዊ ሀረግ አድርጊው

105 ተ19፡ የተማሪ ብልጥ

106 መ/ርት፡ ጎበዝ የተማሪ ብልህ ለማለት ነበር ያሰብሽው

መጀመሪያ የተማሪ ያልሽኝ

(ም 1፣ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 1፣አ 1)

በምሳሌ ሁለት በቀረበው የንግግር ልውውጥ እንደተመለከትነው ተማሪ አስራዘጠኝ


የቃል ክፍል ለመምረጥ ብትቸገርም ሀረጉን በትክክል አቀናጅታ ስለመሰረተች
“ጎበዝ” የሚል የማበረታቻ ቃል በመንገር ትክክለኛ ሙከራ ማድረጓን የሚያሳይ
አዎንታዊ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ ተማሪዋም አወንታዊ ግብረመልሱን በማግኘቷ
ቀድማ የመረጠችውን ቃል ባትጠቀምም በሌላ ቃል ተጠቅማ ሀረጉን በትክክክል
እንድትመሰርት አስችሏታል፡፡

34
ምሳሌ 3

46 ተ15፡ ህብረ ቃሉ የሚለው እንዳያት እንዳያት

47 መ/ርት፡ ህብረቃላችን እንዳይት እንዳት ነው፡፡

48 ተ15፡ ሰሙ ደሞ አኳኋኗ ሁሉ እንዳያት ነው

49 መ/ርት፡ እንዳያት ነው፡፡

50 ተ15፡ አዎ…ወርቁ ደሞ ምንድነው?እንዳያት እንዳያት

ትፈልጋለች ወይም እንድመለከታት ትፈልጋለች

ማለት ነው፡፡

51 መ/ርት ፡ በጣም አሪፍ ፡፡

(ም 3 ፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ3፣አ 3)

በምሳሌ ሶስት እንደተመለከተው ተማሪ አስራአምስት የህብረቃሉን ሰምና ወርቅ


በትክክል መመለሱን ለማሳየት “በጣም አሪፍ” የሚል ቃል ተጠቅመው ሙሉ በሙሉ
ትክክለኛ መልስ መመለሱን መምህርቷ አረጋግጠዋል፡፡መምህርቷ ይህን ቃል
መጠቀማቸው ተማሪዎቹ ትክክለኛ መልስ መመለሳቸውን እርግጠኛ እንዲሆኑ
ያደርጋል፡፡

ምሳሌ 4

53 ተ17፡ ደረቅ እንጨት ሰበሰበና ክብሪት ተጠቅሞ እሳቱን

አቃጠለ ነው የሚለው አቀጣጠሉ፡፡

54 መ/ርት፡ እሺ…አቀጣጠለ ትክክል ናት?

55 ተጋ፡ አዎ

56 መ/ርት፡ ትክክል ናት፡፡ደረቅ እንጨት ሰበሰበና ክብሪት ተጠቅሞ

እሳቱን ምን አለ? አቃጠለ ሳይሆን አቀጣጠለ፡፡

(ም 1፣ ክ ሠ፣ ክ/ጊዜ 1፣አ 4)

ምሳሌ አራት እንደሚያሳየው ተማሪዋ እንድትሞላ የተፈለገው ለዐ.ነገሩ ተስማሚ


ቃል ነው፡፡ ዐ.ነገሩን በማስታወስ ደረቅ እንጨት ሰበሰበና ክብሪት ተጠቅሞ እሳቱን

35
አቃጠለ፡፡ማሰሪያ አንቀፅ ተገቢነት የሌለው መሆኑን ያሳያል፡፡ተማሪ አስራሰባትም
ትክክለኛውን ቃል አቀጣጠለ በሚል ስትመልስ መምህርቷ ትክክለኛነቱን ተማሪዎች
እንዲያረጋግጡ አድርጋ ተማሪዎችም “አዎ” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡መምህርቷም
በድጋሚ «ትክክል ናት»በማለት አረጋግጠዋል፡፡ ተማሪዎች አዎንታዊ ግብረመልስ
ሲሰጣቸው ትክክለኛ መልስ መመለሳቸውን እርግጠኛ እንዲሆኑና ጥሩ ስሜት
እንዲሰማቸው ያግዛል፡፡ስለዚህ አዎንታዊ ግብረመልስ የሚሰጥባቸው ቃላትና
ሀረጋት ተማሪዎች በክፍላቸው በትክክል የመደቧቸውና በትክክክል ያዋቀሯቸው
መሆናቸውን የመረጃ ትንተናው አመላክቷል፡፡

በአጠቃላይ በምሳሌ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስትና አራት የቀረቡት መረጃዎች


እንደሚያሳዩት ተማሪዎች አዎንታዊ ግብረመልስ በሚያገኙበት ጊዜ
ትክክለኛነታቸውን እንዲያረጋግጡና ለሌላ መልስ እንዲነሳሱ ያደርጋቸዋል ይህ
ግብረመልስም በይበልጥ ተተግብሯል፡፡

4.1.2. አሉታዊ ግብረመልስ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለክተው ይህ ግብረመልስ ተማሪዎች በቀጥታ
በተግባራቸው ውስጥ ስህተት እንደፈፀሙ፣አገላለፃቸው፣የቃላት አጠቃቀማቸው ወይም
ምላሻቸው ትክክል እንዳልሆነ የሚነገርበት ነው፡

ምሳሌ 5

14 ተ5፡ አበበ በጣም ተጫዋች ነው

15 መ/ርት፡ እ?

16 ተ5፡ አበበ በጣም ተጫዋች ነው፡፡

17 መ/ርት ፡ እ…እ…ትክክል ነው እንዴ?

18 ተጋ፡ አደለም፡፡

(ም1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ1፣አ 1)
ከዚህ በላይ በቀረበው የጥያቄና መልስ ልውውጥ እንደተመለከትነው ተማሪ አምስት
በቃል ክፍሎች በመጠቀም ዐ.ነገር እንዲመሰርት ሲደረግ ተጫወተ የሚለውን ቃል
ተጫዋች ብሎ ቀይሮ ዐ.ነገሩን በመስራቱ መምህርቷና ተማሪዎች ግብረመልስ

36
ሰጥተዋል፡፡መምህርቷ ትክክል ነው እንዴ?ብለው ሲጠይቁ ተማሪዎቹ አደለም
የሚል አሉታዊ ምላሽ ሠጥተዋል፡፡ስለዚህ አሉታዊ ግብረመልሱ ተማሪው
የተጠቀመው ቃል ማሰሪያአንቀጽ እንዳልሆነ ለማሳየት አገልግሏል፡፡ነገርግን
ተማሪዎቹ አይደለም ካሉ በኋላ መምህርቷም ሆኑ ተማሪዎቹ የቃል ክፍሉን
አልተናገሩም፡፡የቃል ክፍሉን ቢናገሩ ተማሪዎቹ ማሰሪያአንቀፅ የሚሆኑ ቃላት
በየትኛው የቃል ክፍል ውስጥ የሚገኙ ቃላት እንደሆኑ ለመረዳት ይችሉ ነበር፡፡

ምሳሌ 6

158 መ/ርት፡ አንቺ ምድር ፍረጂኝ ምን ዓይነት ዘይቤ ነው?

159 ተ4፡ ፈሊጥ ነው፡፡

160 መ/ርት፡ ፈሊጥ ወይስ ዘይቤ?

161 ተ2፡ ዘይቤ ነው፡፡

162 መ/ርት፡ ዘይቤ ነው፡፡ምን ዓይነት ዘይቤ ነው?ምን ዓይነት

ዘይቤ?

163 ተ3፡ ተምሳሌት ዘይቤ

164 መ/ርት፡ ተምሳሌት ዘይቤ? አይደለም፡፡

(ም 1፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ 1፣አ1)

ከላይ በቀረበው የጥያቄና መልስ ልውውጥ እንደተመለከትነው ተማሪ ሶስት


የዘይቤውን ዓይነት ተምሳሌት ዘይቤ ብሎ ለሰጠው ምላሽ ቃሉን በመድገም
“አይደለም” የሚል ቃል በመጠቀም አሉታዊ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡በዚህም
የተማሪው ምላሽ ትክክል እንዳልሆነ በቀጥታ ተነግሮታል፡፡የተሰጠው አሉታዊ
ግብረመልስ ተማሪው የዘይቤውን ዓይነት በመሳሳቱ የተሰጠ ሲሆን ተማሪዎቹ
የዘይቤውን ዓይነት በድጋሚ እንዲፈልጉ ያነሳሳል፡፡
ምሳሌ 7
41 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ

ቀልጣፎች ናቸው፡፡ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች

ናቸው፡፡እሱ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

42 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ እስከምን ድረስ ነው?ጠዋት ጠዋት

37
እስከሚለው?

43 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

44 መ/ርት፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እስከሚለው ድረስ ነው ትላለች

እስቲ ሌላስ?

45 ተ4፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ እዚህ ጋር

ድረስ ስማዊ ሀረግ ነው፤ቀልጣፎች ናቸው ይህ ደግሞ

ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

46 መ/ርት፡ እሺ … ትክክል አይደለም፡፡ እስቲ?

47 ተ19፡ ጓደኛችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት እስከሚለው ስማዊ

ሀረግ፣ ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው፡፡ ግሳዊ ሀረግ

48 መ/ርት፡ እሺ …ሌላስ ትክክል አይደለችም፡፡ እህ…

49ተ5፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ

የሚለው ስማዊ ሀረግ ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ቀልጣፎች ናቸው፡፡

50 መ/ርት፡ እ…ሺ ሌላስ?ትክክል አይደለም፡፡

(ም3፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

ከዚህ በላይ በቀረበው ምሳሌ እንደተመለከትነው ከመናገር ተራ አርባሶስት እስከ


መናገር ተራ አርባዘጠኝ ድረስ ተማሪ አስራአንድ፣ ተማሪአራት፣ ተማሪ አስራዘጠኝና
ተማሪ አምስት የዐ.ነገሩን ስማዊ ሀረግና ግሳዊ ሀረግ ሲተነትኑ ስህተት
ሠርተዋል፡፡መምህርቷም ተማሪ አስራ አንድን ደጋግመው ጠይቀዋታል፡፡
ተማሪዋም ያለችውን በመድገም ስትገልፅ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እስከሚለው
ድረስ ነው ትላለች በማለት በግልፅ ባይጠቁሙም ሌሎቹን ለመልስ አነሳስተው
ተማሪ አራት ቀጥላ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ መምህርቷም ለተማሪዋ የሰጠችው ምላሽ
«ትክክል አይደለም» የሚል አሉታዊ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ተማሪ አስራዘጠኝና
ተማሪ አምስትም ይህንኑ ዐ.ነገር ቢሰሩም መልሳቸው ትክክል ስላልሆነ መምህርቷ
ተማሪ አስራዘጠኝንም ተማሪ አምስትንም «ትክክል አይደለችም» የሚለውን
በመጠቀም አሉታዊ ግብረመልስ ሠጥተው ምላሻቸው ስህተት መሆኑን
አሳይተዋል፡፡ስለዚህ አሉታዊ ግብረመልሱ ተማሪዎች የዐ.ነገር ክፍሎችን ሲተነትኑ

38
ትክክል አለመሆናቸውን ለማሳየት ተሰጥቷል፡፡በምሳሌ ስድስትና ሰባት የተመረጡት
መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሉታዊ ግብረመልሱ ተማሪዎች ስነፅሁፋዊ ሃሳቦችንና
የዓ.ነገር ክፍሎችን ሲሳሳቱ ስህተት መሆናቸውን ማሳያ ናቸው፡፡

4.1.3. የማስተካከያ ግብረመልስ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለከተው ይህ ግብረመልስ የተማሪዎችን ስህተት
መጠቆም ለምሣሌ፡- ከመመሪያዎች ውስጥ ያልተገበሩትን ማሳየት፣ በሀረግና ዓ.ነገር
ምስረታ ወቅት የተሳሳቷቸውን መጠቆም እንዲሁም ትክክለኛውን መንገር መሆኑ
ተጠቁሟል፡፡ይህንንም በክፍል ውስጥ ምልከታ የተወሰነውን በመጥቀስ
እንመልከት፡፡

ምሳሌ 8

81ተ10፡ ብልጥ

82 መ/ርት፡ ብልጥ እሺ… ይህን ሀረግ የሚያደርግልኝ ብልጥ እህ

83 ተ4፡ ብልጥ ልጅ

84 መ/ርት፡ እሺ…ተመልከቱ አሁን ብልጥ … ልጅ ብለን ስንፅፍ

እኛ መፅሀፋችን ላይ የታዘዝነው ምናዊ ሀረግ

እንድንመሰርት ነው፡፡

85 ተጋ፡ ቅፅላዊ ሀረግ

86 መ/ርት፡ ቅፅላዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ቅፅላዊ ሀረግ

ስንመሰርት ደግሞ ቀኝ መሪው ምን መሆን አለበት?

ቅፅል፡፡አንተ ግን የነገርከን «ብልጥ ልጅ» ስንል ቀኝ

መሪያችን ማነው? ልጅ ነው፡፡ ልጁ ደግሞ የቃል ክፍሉ

ምንድነው?ስም ነው፡፡ አሁን ይህ ስማዊ ሀረግ እንጂ

ቅፅላዊ ሀረግ አልሆነልንም፡፡ የመፀሀፋችን ትዕዛዝ ግን

ቅፅል መርጠን ምናዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው?

ቅፅላዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ ሌላ እስኪ ይችን

የሚያስተካክላት…ሌላ…እስቲ?

39
87ተ1፡ የሰው ብልጥ

88 መ/ርት፡ የሰው ብልጥ አሁን ልዩነቱ ገብቶሀል? ቅድም ቀኝ

መሪያችን ስም ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቀኝ መሪያችን

ምን ሆነ? ቅፅል መሪያችን ቅፅል ሲሆን ሀረጉ ምን

ይሆናል? ቅፅላዊ….

89 መተ፡ ሀረግ

(ም 1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ1፣አ 1)

ከዚህ በላይ በቀረበው ምሣሌ እንደሚታየው የተሰጣቸው ጥያቄ የቃል ክፍሎችን


በመጠቀም ሀረግ መመስረት ሲሆን ብልጥ በሚለው ቃል በአርባ ስድስተኛው
የመናገር ተራ ተማሪ አራት ብልጥ ልጅ የሚል ሀረግ መስርቷል፡፡መምህርቷም
ማብራሪያ በመስጠት የታዘዙት ምን አይነት ሀረግ እንደሚመሰርቱ እንደሆነ
ተማሪዎች ማስተካከያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡ተማሪዎችም በጋራ ቅፅላዊ ሀረግ
በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡መምህርቷ ተማሪ አራት የመሰረተው ሀረግ ቀኝ መሪው
ስም እንደሆነ በማሳየት ሌላ ተማሪ የተስተካከለ ሀረግ እንዲመሰርት በማድረግ
የማስተካከያ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ይህ ግብረመልስ ተማሪዎች የቃላቱ ቦታ
መቀያየር የሀረጉን ዓይነት እንደሚለውጠው ለመረዳት የሚያስችል ሥነትምህርታዊ
አገልግሎት አለው፡፡

ምሳሌ 9

130 ተ26፡ የተናደደ ሰው አደጋ ሊያደርስ ይችላል፡፡ የተናደደ

የሚለው ቅፅል

131መ/ርት፡ የተናደደ ሰው አደጋ ሊያደርስ ይችላል፡፡ነው የሚለው

ቅፅል ነው፡፡ብላለች ሌላ

132 ተ27፡ ግስ፡፡

133 መ/ርት፡ ግስ ነው፡፡

134ተ28፡ መስተዋድድ

135 ተጋ፡ ግስ ነው

136 መ/ርት፡ እህ… አዎ… የተናደደ የሚለው በራሱ ግስ ነው፡፡

40
ምሣሌ ዘጠኝ እንደሚያሳየው የተናደደ የሚለውን ቃል ቅፅል ብላ ስትናገር
መምህርቷ ተማሪዋ የተናገረችውን በመድገም ስህተት እንደሆነ ባይገልፁም ለሌላ
ተማሪ እድል በመስጠት እንዲሞክርና ማስተካከያ እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡ነገርግን
በመቶሠላሣ ሁለተኛው የመናገር ተራ ተማሪ ሀያሰባት ግስ ብሎ ሲመልስ
መምህርቷም ግስ ነው በማለት ተማሪ ሀያስድስት ለሰራው ስህተት የማስተካከያ
ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ ነገርግን በመቶ ሠላሣአራተኛው የመናገር ተራ ላይ ተማሪ
ሀያስምንት መልሱን ባለማዳመጥ ይሁን በመምህሯ አነጋገር ተማሪ ሀያስምንት
መስተዋድድ በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡በመቶ ሠላሣ አምስተኛው በሁለት መቶ
አስራ አራተኛው የመናገር ተራ ተማሪዎች በጋራ ግስ ነው በማለት የማስተካከያ
ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡መምህርቷም የተናደደ የሚለው በራሱ ግስ ነው በማለት
በድጋሚ ተማሪ ሀያ ስድስትና ተማሪ ሀያ ስምንት የሰሩትን ስህተት ለማረም
የሚያስችል የማስተካከያ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡

ምሳሌ 10

364ተ2፡ በዚህ ዘመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንደጥንታዊ

ግሪካውያን ዴስሞን

መ/ርት፡ ዴሞስቴን … ዴሞስቴን

365ተ2፡ ተገልሎ ለብቻ መለማመድ አስፈላጊ ይሆናል

ምክንያቱም ብቻውን ከተለማመደ የተለያዩ መድረኮችና

ሸንጐዎች ላይ ሲቀርብ ምንም የሚያቅተው ነገር የለም

ስለዚህ … አዎ

(ም3፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ3፣አ 6)

በምሣሌ አስር ላይ በሦስት መቶ ስልሣ አራተኛው የመናገር ተራ ተማሪ ሁለት


ግሪካውያን ተናጋሪ ዴስሞን ብላ ስትጠራ መምህርቷ ዴሞስቴን…ዴሞስቴን ብላ
ስሙን ደጋግማ በመጥራት እንድታስተካክል ለማድረግ ጥረዋል፤ነገርግን ተማሪዋ
ርማቱን አልወሰደችም፡፡ የማስተካከያው ግብረመልስ በሆሄያት ያጠራር ግድፈትን
ለማስተካከል የቀረበ ሲሆን ትክክለኛውን የቃላት ንበት ለማወቅና በሆሄያት ግድፈት
ምክንያት የሚከሰተውን የትርጉም መዛባት ለማስወገድ ይረዳል፡፡

41
ምሣሌ 11

64 መ/ርት፡ ሠራተኞች የእንስራውን ውሃ ደፉት እህ

65 ተ2፡ ሰራተኞቹ የእንስራውን ውሃ ደፉት፡፡ሰራተኞቹ

የሚለው ባለቤት ነው፡፡የእንስራውን ውሃ የሚለው

ተሳቢ ነው ደፉት የሚለው ባለቤት ነው፡፡

66 መ/ርት፡ ማሰሪያ አንቀፅ

(ም 1፣ ክ ሠ፣ ክ/ጊዜ 2፣አ 5)

በምሣሌ አስራአንድ እንደሚታየው በመቶ አስራ ስድስተኛው የመናገር ተራ ላይ


የተማሪ ሁለት የዓ.ነገር ክፍሎቹን ስትተነትን ደፉት የሚለውን ቃል ባለቤት ስትል
መምህርቷ ማሰሪያ አንቀፅ በማለት ተግባሩን ገልፀው የማስተካከያ ግብረመልስ
ሰጥተዋል፡፡የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለክተው አንዳንድ ጊዜ ደግሞ
መምህራንም ሆኑ ተማሪዎች ሲሳሳቱ የማስተካከያ ግብረመልስ አይሰጡም፡፡ይህም
በምልከታው ወቅት የፊደል ግድፈት ሲታይባቸው ተማሪዎች ርማት እንደማይሰጡ
ለማስተዋል ተችሏል፡

ምሣሌ 12

ተ8፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ የሚለው ስማዊ ሀረግ

ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጠቻት፡፡

(ም 3፣ ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 3)

በመፀሀፉ የተቀመጠው ዓ.ነገር የሚለው ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ


ገንዘብ ሠጣት ነው፡፡ነገርግን ተማሪ ስምንት ሰጠቻት ብሎ ሲያነብ የማስተካከያ
ርማት አልተሰጠውም፡፡

ምሣሌ 13

49 ተ19፡ ጓደኛችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ

የሚለው ስማዊ ሀረግ ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ቀልጣፎች

ናቸው፡፡

50 መ/ርት፡ እሺ…እ…ሺ ሌላስ?ትክክል አይደለም፡፡

42
(ም 3፣ ክ ሠ፣ ክ/ጊዜ3፣አ 6)

በምሳሌ አስራሶስት እንደሚታየው ተማሪ አስራ ዘጠኝ ጓደኞቻችን የሚለውን ቃል


ጓደኛችን ብላ አንብባ የማስተካከያ ግብረመልስ አልተሰጣትም፡፡መምህርቷ «ትክክል
አይደለም» በማለት ማስተካከያ የሰጠችው የዓ.ነገር ክፍሉን በመሳሳቷ እንጂ የቃሉን
ንበት በትክክል ባለመፈፀሟ አይደለም ከዚህ መረዳት የሚቻለው መምህራንም ሆነ
የክፍሉ ተማሪዎች የማስተካከያ ግብረመልስ የሚሰጡት ለሰዋሠው ግድፈቶች እንጂ
ለቃላት ንበት አይደለም፡፡ባጠቃላይ በምሳሌ አስራሁለትና አስራሶስት መረጃዎች
እንደሚያሳዩት ለሆሄያት ግድፈት የማስተካከያ ግብረመልስ ባለመሰጠቱ ዐ.ነገሩ
ውስጥ የባለቤት አለመስማማት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

4.1.4. ገምጋሚ ግብረመልስ


መረጃው እንደሚያመለክተው ይህ ግብረመልስ በውጤት ላይ የተመሰረተ ሲሆን
ተማሪዎች የሚሻሻሉበትን መንገድ ይጠቁማል፡፡መምህራን የባለፈውን ትምህርት
ተማሪዎች ማስታወሳቸውን ለመለየት ይጠቀሙበታል፡፡

ምሳሌ14

01 መ/ርት፡ በባለፈው ክ/ጊዜ ምን ተማርን?

ተ1፡ ሰዋሠው

02 መ/ርት፡ ሰዋሠው፣በሰዋሠው ዙሪያ ላይ ምን? ምን አየን?

03ተ2፡ ዐ/ነገር ከስማዊ ሀረግና ከግሳዊ ሀረግ ይመሰረታል ፡፡

04 መ/ርት፡ ዐ.ነገርን ወይም ስማዊ ሀረግና ቅጽላዊ ሀረግ

በመመስረት ዐ.ነገርን እንደመሰረትን አይተናል

ሌላስ?ሌላስ?ምን ሰርተን ነበር? ሌላ እህ ሌላስ

05 ተ3፡ ዐ.ነገርን ……እሺ …..ቅጽል ….እሺ…የአንድን ቃል

ስማዊ ሀረግ ቅጽላዊ ሀረጉን አወጣን ፤ ካወጣን በኋላ

ደግሞ በስማዊ ሀረግ እና ቅጽላዊ ሀረግ ዐ.ነገርን ሰራን

(ም 3፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

43
በምሳሌ አስራአራት እንደሚታየው መምህርቷ ቀደም ብለው ያስተማሩትን ይዘት
ተማሪዎች እንዲከልሱ አድርገዋል፡፡በአንደኛው፣ በሶስተኛው፣ በአራተኛውና
በአምስተኛው የመናገር ተራ ተማሪዎች የሚያስታውሱትን ተናግረዋል፡፡ተማሪ
አንድ፣ተማሪ ሁለትና ተማሪ ሶስት ባለፈው ክፍለጊዜ የተማሩትን በማስታወስ
ገምጋሚ ግብረመልስን ተግብረዋል፡፡

4.1.5. ገላጭ ግብረመልስ


ገላጭ ግብረመልስ ተማሪዎች ራሳቸውን ገምግመው ርማት እንዲወስዱ የሚያደርግ
ነው፡፡

ምሳሌ 15

73 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ነጭናጫ ልጅ…ቅፅላዊ

74 መ/ርት፡ እ?

75 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ቅፅላዊ ሀረግ ነጭናጫ ልጅ

76 መ/ርት፡ ነጭናጫ ቆይ አዳምጧት…ነጭናጫ ልጅ ሳይሆን

77 ተ18፡ አዋቂ ልጅ

78 መ/ርት፡ ወይም የልጅ አዋቂ…

79 ተ18፡ ልጅ ለሚለው የልጅ አዋቂ ወ/ሮ አበበች የልጅ አዋቂ

አላት፡፡

(ም2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ2)

በምሳሌ አስራአምስት እንደሚታየው ተማሪ አስራ ስምንት የመሰረተችው ሀረግ


ትክክል ስላልሆነ መምህርቷ«በይአስተካክይ» በማለት ስህተቷን እንድትረዳና
እንድታስተካክል ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ነገርግን ተማሪዋ ስህተቷን ለመረዳት
አልቻለችም፡፡ስለዚህ ገላጭ ግብረመልሱ ተማሪዋ የሀረግ አወቃቀሩን ባለመረዳቷ
የቀረበ ቢሆንም ተማሪዋ ሀረጉን አላስተካከለችም፤ በመሆኑም መምህርቷ ሌላ
ግብረመልስ በመስጠት መዋቅሩን ገልፀዋል፡፡መምህርቷም ቢሆኑ የሀረግ አወቃቀሩን
አላስረዱም፡፡

44
4.1.6. ውጫዊ ግብረመልስ

4.1.6.1. ከፊልና ሙሉ ግብረመልስ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለከተው ከፊል ግብረመልስ የተማሪውን ምላሽ
መሰረት በማድረግ በተወሰኑ ነገሮች ላይ ብቻ ግብረመልስ መስጠት ሲሆን ሙሉ
ግብረመልስ ደግሞ የተማሪው ምላሽ በምን በምን ትክክል ነው በምን በምን ደግሞ
ትክክል አይደለም በማለት ደረጃ በደረጃ ነጥሎ በማየት ግብረመልስ መስጠት
ነው፡፡

ምሳሌ16

161 መ/ርት፡ አንቺ ምድር ፍረጂኝ ምን አይነት ዘይቤ ነው?

162 ተ4፡ ፈሊጥ ነው

163 መ/ርት፡ ፈሊጥ ወይስ ዘይቤ

164 ተ2፡ ዘይቤ ነው

165 መ/ርት፡ ዘይቤ ምን ነው፡፡ምን አይነት ዘይቤ?ምን ዓይነት

ዘይቤ?

166 ተ32፡ ተምሳሌት ዘይቤ? አይደለም፡፡

167 ተ4፡ እንቶኔ ዘይቤ

168 መ/ርት፡ እንቶኔ ዘይቤ አንቺ ምድር ፍረጂኝ እያለ ነው እኮ

አንቺ ምድር ፍረጂኝ የሚለው ዘይቤ ነው ምን አይነት

ዘይቤ? እንቶኔ ዘይቤ

(ም 1፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 1፣አ 6)

በምሳሌ አስራስድስት እንደተቀመጠው መምህርቷ ሙሉ ግብረመልስ ባይሰጡም


ከፊል ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ይኸውም ተማሪ አራት በመቶ ሥልሳ ሁለተኛው
የመናገር ተራ ፈሊጥ ነው ብሎ ሲመልስ መምህርቷ ፈሊጥ ወይስ ዘይቤ ብለው
ጠይቀው በመቶ ስልሳኛው የመናገር ተራ ላይ ተማሪ ሁለት ዘይቤ ብሎ በመለሰው
መልስ ላይ ተንተርሰው ዘይቤ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በመቶ ስልሳ ሰባተኛው
የመናገር ተራ ላይ ዘይቤው እንቶኔ እንደሆነ ተማሪ አራት ስትናገር መምህርቷም

45
ዘይቤውን በመድገም አንቺ ምድር ፍረጂኝ እያለ ነው እኮ በማለት በመግለጽ
ከፊል ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ከፊል የተባለበትም ምክንያት እንቶኔ የተባለበትን
ምክንያት በግልጽ ስላላስቀመጡ ነው ፡፡

ምሳሌ 17

85 መ/ርት፡ እሺ…ሌላ ቅፅል…የሚመሰርትልኝ…እስቲ…ሌላ ቅፅል?

86 ተ10፡ ብልጥ

87 መ/ርት፡ ብልጥ እሺ…ይቺን ሀረግ የሚያደርግልኝ ብልጥና እህ…

88 ተ4፡ ብልጥ ልጅ

89 መ/ርት፡ እሺ ተመልከቱ አሁን ብልጥ ልጅ ብለን ስንፅፍ እኛ

መፀሀፋችን ላይ የታዘዝነው ምናዊ ሀረግ እንድንመሰርት

ነው?

90 ተጋ፡ ቅፅላዊ ሀረግ

91 መ/ርት፡ ቅፅላዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ቅፅላዊ ሀረግ

ስንመሰርት ደግሞ ቀኝ መሪው ምን መሆን አለበት?

ቅፅል አንተ ግን የነገርከን ብልጥ ልጅ ስንል ቀኝ

መሪያችን ማነው?ልጅ ነው፡፡ልጅ ደግሞ የቃል ክፍሉ

ምንድነው? ስም ነው፡፡

(ም1፣ክሀ፣ክ/ጊዜ1፣አ1)

በምሳሌ አስራሰባት እንደሚታየው መምህርቷ ሙሉ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡


ይኸውም ተማሪ አራት ቅፅላዊ ሀረግ ብሎ የመሰረተው ሀረግ ስህተትነቱን ለማሳየት
የመሰረተው ሀረግ ስማዊ እንደሆነና ስማዊ የሆነውም በመሪው ምክንያት እንደሆነ
ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

4.1.6.2. ይዘታዊና ቅርፃዊ ግብረመልስ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያሳየው ይዘታዊ ግብረመልስ ተማሪው መግለጽ
የፈለገውን ጉዳይ ትርጉም ባለው መልኩ መግለጽ አለመግለጹን ለማሳየት የሚሰጥ
ግብረመልስ ነው፡፡

46
ምሳሌ18

69 ተ7፡ የህፃን ቁምነገረኛ

70 መ/ርት፡ የህፃን ቁምነገረኛ ቅጽላዊ ሀረግ ነው::

71 ተ7፡ የህፃን ቁምነገረኛ …..ሀሳብ የለውም::

72 መ/ርት፡ የህፃን ቁምነገረኛ…..ሀሳብ ……የለውም፡፡እሺ

የህፃን ቁምነገረኛ ሀሳብ የለውም ነው እንዴ

የሚሆነው? የህፃን ቁምነገረኛ ቅጽላዊ ሀረግ

ነው ትክክል ነው፡፡ ሀረጉ…

(ም 2 ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ 5)

ምሳሌ አስራስምንት እንደሚያሳየው ተማሪ ሰባት በስልሳ ዘጠነኛው የመናገር ተራ


ላይ ተማሪ ሰባት ሀረጉን በትክክል ቢያቀናጅም በሁለት መቶ ሰባ አንደኛው
የመናገር ተራ ተማሪ ሰባት የመሰረተው ዐ.ነገር ትክክል አይደለም፡፡ዐ.ነገሩን
መስርቷል፡፡ ነገር ግን ዐ.ነገሩን በትርጉም ደረጃ ሲታይ ትክክል አይደለም፡፡ቁም
ነገረኛ የሚለው ቃልና ሀሳብ የለውም የሚለው ሀረግ ሊዛመዱ የሚችሉ አይደሉም
በመሆኑም መምህርቷ ሀረጉ ትክክል እንደሆነና ዐ.ነገሩ ግን ትክክል እንዳልሆነ
ለመጠቆም ሞክረዋል፡፡ መምህርቷ ተማሪው ዐ.ነገሩን ሲመሰርት ያቀናጃቸው
ሀረጋት ከትርጉም አንፃር ተስማሚነት የሌላቸው መሆናቸውን ማሳየታቸው ይዘታዊ
ግብረ መልስ አሰኝቶታል፡፡

ምሳሌ19

72 መ/ርት፡ እ… ልሙጥ ወረቀት እስኪ ዐ.ነገር የሚያደርግልኝ?

73 ተ1፡ አበበ ቤት ልሙጥ ወረቀት ይገኛል ፡፡

74 መ/ርት፡ እነ አበበ ቤት ልሙጥ ወረቀት አለ ፡፡

(ም1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ1፣አ 1)

በምሳሌ አስራዘጠኝ ደግሞ እንደሚታየው መምህርቷ ልሙጥ ወረቀት የሚለውን


ስማዊ ሀረግ በመጠቀም ሀረግ እንዲመሰርቱ አድርጋለች፡፡በሰባ ሶስተኛው የመናገር

47
ተራ ላይ ተማሪ አንድ ዐ/ነገር መስርቷል፡፡መምህርቷ እነ የሚለውን መስተዋድድና
አለ የሚለውን ማሰሪያአንቀጽ በማስገባት ሀሳቡ የተሟላ እንዲሆን አድርገዋል ፡፡

ምሳሌ 20

47 ተ15፡ «ህብረተሰቡ ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰሩ» ነው

የሚለው አሳሰሩ፡፡

48 መ/ርት፡ «እሺ ህብረተሰቡ ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰረ»

ነው የሚለው እህ አሳሰረ ….. ትክክል ነው ፡፡

49 ተ3፡ አሳሰሩ …. አሳሰሩ ……

50 መ/ርት፡ እ? ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰረ አሳሰሩ ሳይሆን

አሳሰረ ነው እንጂ አሳሰሩ አይሆንም፡፡

(ም 1 ፣ክ ሠ ፣ክ/ጊዜ1፣አ4)

በምሳሌ ሃያ እንደተመለከተው ተማሪ አስራአምስት በአርባ ሰባተኛው የመናገር ተራ


የማሰሪያ አንቀፁን ሲያስተካክል ህብረተሰብ ከሚለው ባለቤት ጋር የማይስማማ
ማሰሪያ አንቀጽ መርጧል፤ ይህም ሀሳቡ እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ መምህርቷም
ምክንያቱን ባይገልጹም አሳሰሩ የሚለው እንደማይሆን አሳሰረ የሚለው ቃል
ተስማሚ እንደሆነ በመግለጽ ይዞታዊ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ነገር ግን
ማሰሪያአንቀፁ ለምን እንደማይሆን (ተስማሚ እንዳልሆነ) ቢገልፁ የተሻለ ነበር ፡፡

ቅርጻዊ ግብረመልስ፡- ተማሪዎች የሚማሩትን ቋንቋ ሰዋሠዋዊ ስርአትን በትክክል


ማዋቀርና አለማዋቀራቸውን መሰረት በማድረግ የሚሰጥ ግብረመልስ ነው ፡፡

ምሳሌ 21

73 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ነጭናጫ ልጅ ቅጽላዊ

74 መ/ርት፡ እ?

75 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ቅጽላዊ ሀረግ ነጭናጫ ልጅ

76 መ/ርት፡ ነጭናጫ ልጅ ቅጽላዊ ሀረግ ነው እንዴ?ምን

ዓይነት ነው ?

48
77 ተ3፡ ስማዊ ሀረግ

78 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረግ ላይ ይህን አስተካክይ ነጭናጫ ልጅ

79 ተ18፡ አዋቂ ልጅ

80 መ/ርት፡ ወይም የልጅ አዋቂ….እህ

(ም 2 ፣ ክ ሠ ፣ክ/ጊዜ 2፣አ5)

በምሳሌ ሀያአንድ እንደሚታየው በሰባሶስተኛው የመናገር ተራ ተማሪ አስራ ስምንት


እንዲመሰርት የተጠየቀው ቅጽላዊ ሀረግ ቢሆንም በስተቀኝ ስም በማስቀመጥ ሀረጉን
በማዋቀሩ መምህርቷ ተማሪዎችን በጋራ ርማት እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡ተማሪዎቹም
ሀረጉ ስማዊ ሀረግ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡መምህርቷም መዋቅሩን እንድታስተካክል
እድል ሰጥተዋትም ባታስተካክልም መምህርቷ የልጅ አዋቂ በሚል መዋቅሩን
አስተካክለዋል ፡፡

ምሳሌ 22

124 መ/ርት፡ የስራ....አዋኪ...እሺ እስቲ ዐ.ነገር የሚያደርግልኝ...ይህን

ዐ.ነገር የሚያደርግልኝ እህ....

125 ተ25፡ አበበ ትምህርት አውኮታል ፡፡

126መ/ርት፡ አውኮታል... እሺ ይቺ እንዳለች ባንቀይራት ልክነሽ

ቅርጿን ባንቀይራት የስራ አዋኪ የምትለዋን ቅርጿን

ባንቀይራት

(ም 1፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ1፣አ1)

በምሳሌ ሀያሁለት እንደተገለፀው የልጅ አዋኪ በሚለው ቅጽላዊ ሀረግ ዐረፍተነገር


እንዲመሰርቱ ሲደረግ በመቶ ሃያአምስተኛው የመናገር ተራ ተማሪ ሀያ አንድ
ሀረጉን ቅርፁን አውኮታል በሚል ቀይራዋለች፡፡የስም ገላጭ መሆኑ ቀርቶ ማሰሪያ
አንቀጽ አድርጋዋለች፡፡መምህርቷም ገላጩን በትክክል አለማስገባቷን በትክክል
በመግለጽ ቅርፁን እንድትቀይር ነግረዋት ቅርፃዊ ርማት ሰጥተዋል ፡፡ቅርፃዊ
ርማቱም ሰዋሠዋዊ ህግን ለመረዳት የሚያስችል ፋይዳ አለው፡፡

49
4.2. የቃል ግብረመልስ የሚቀርቡባቸው ስልቶች ምንምን ናቸው?

የቃል ግብረመልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች እንደገና ማሰራት፣ ግልፅ ርማት


መስጠት፣ መድገምና ማነሳሳት ናቸው ፡፡

4.2.1. እንደገና ማሰራት


ይህ ስልት መምህራን እንደገና የሚያሰሯቸው በቋንቋው ውስጥ የተማሪዎችን
የቃላት አጠቃቀም ለማስተካከልና የሰሩትን ስህተት ለመቀነስ በሚል ነው፡፡

ምሳሌ 23

93 ተ19፡ የተማሪ

94 መ/ርት፡ እ?

95 ተ2፡ የተማሪ

96 መ/ርት፡ እሺ.....ተመልከቱ የተማሪ- አሁን ተማሪ ቅጽል ነው?

97 ተ3፡ ስም ነው ፡፡

98 መ/ርት፡ ስም ነው፡፡እጅ አሁን መጽሀፋችን ያዘዘን ምን

እንድናወጣ ነው?ቅጽል ነው የምትመርጡልኝ ፡፡ ቅጽል

ነው የምትመርጡልኝ..እህ..

99 ተ20፡ ብልህ

100 መ/ርት፡ ብልህ ...እሺ አሁን አንቺ ያሰብሺው ቅድም

ይመስለኛል፡፡ሀረግ አርጊው እስኪ ብልህን የቅድሟን

አቀናጂና ፡፡ ሀረግ አርጊው

101 ተ19፡ (ዝም አለች)

102 መ/ርት፡ የተማሪ ብለሻል አይደል?

103 ተ19፡ አዎ

104 መ/ርት፡ ቀኝ መሪው ብልህ ተሰጥቶናል፡፡ቅጽል አንድ ላይ

አቀናጂና ቅጽላዊ ሀረግ አርጊው

105 ተ19፡ የተማሪ ብልጥ

50
106 መ/ርት፡ ጎበዝ የተማሪ ብልህ ለማለት ነበር ያሰብሺው

መጀመሪያ የተማሪ ያልሺኝ መጀመሪያ ብልህ ወይም

ብልጥን ለማምጣት ነው የታዘዝነው ግን ቅጽል ስለሆነ

መጀመሪያ ምኑን መምረጥ አለብን? ቅጽሉን መምረጥ

አለብን፡፡

(ም1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ1፣አ1)

በምሳሌ ሀያሶስት እንደሚታየው ተማሪ አስራዘጠኝ የተማሪ የሚል ቃል ስትመርጥ


መምህርቷ መምረጥ ያለባት ቅጽል መሆኑን በመግለጽ ድጋሚ ሌላ ቃል
እንድትመርጥ አነሳስተዋታል፡፡ ተማሪ ሀያ በዘጠኛዘጠኛው የመናገር ተራ ብልህ
የሚል ቃል ስትመርጥ መምህርቷ ተማሪ አስራ ዘጠኝን ድጋሚ ሀረጉን
እንድትመሰርት አድርገው ድጋሚ አሰርተዋታል፡፡በዚህም ተማሪዋ «የተማሪ»
የሚለው ቃል ቅጽላዊ ሀረግ እንደማይሆን ተረድታ ትክክለኛ ሀረግ መመስረት
ችላለች፡፡ስለዚህ ይህ ስልት ተግባራዊ የሆነው የተማሪዋን ስህተት ለመቀነስ በመሆኑ
ተማሪዋ ድጋሚ ስትሰራ ስህተቷን እንድትረዳ ከማስቻሉም ባለፈ ትክክለኛውን
ምላሽ እንድታገኝ አድርጓል፡፡

ምሳሌ 24

27 ተ8፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ የሚለው ግሳዊ ሀረጉ

ደግሞ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጠቻት ፡፡

28 መ/ርት፡ እሺ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ የሚለው ስማዊ

ሀረግ ነው፡፡ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት የሚለው ግሳዊ

ሀረግ ነው፡፡እሺ ሌላስ? እስቲ ሌላ እህ?

29 ተ9፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት

ስማዊ ሀረግ ሁለት ሙሉ ልብስ ግሳዊ ሀረግ እንድታሰፋ

ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት፡፡

30 መ/ርት፡ እሺ ሌላስ? ሌላስ ? ይህን የሚሰራልኝ ? እህ

31 ተ2፡ ይህንኑ

51
32 መ/ርት፡ አዎ

33 ተ2፡ ሁለት ሙሉ ልብስ የሚለው ሁለት ሙሉ ልብስ

እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት ፡፡የሚለው ደግሞ

ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡ስማዊ ሀረጉን ሙሉ ልብስ ሁለት ሙሉ

ልብስ ሰጣት እዚህጋ ልብስ የሚለው ስም ስለሆነ ስማዊ ሀረግ

ይሆናል፡፡እዚህጋ ደግሞ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት

ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው ፡፡

34 መ/ርት፡ እሺ ሌላስ? ሌላስ

35 ተ3፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት

ነው የሚለው ዋና ዐ.ነገር ስማዊ ሀረጉ ሁለት ሙሉ

ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ እስከሚለው ስማዊ ሀረግ

ገንዘብ ሰጣት የሚለው ግሳዊ ሀረግ

36 መ/ርት፡ አዎ ጥሩ ነው፡፡ትክክል ናት ሁለት ሙሉልብስ

እድታሰፋ ጓደኛዋ ማነው ገንዘብ የሰጣት? ብንል ስማዊ

ሀረግ ውስጥ ምን ይገኛል ብለናል ?ባለቤቱ ይገኛል

ስለዚህ ማነው ገንዘብ የሰጣት ጓደኛዋ....ጓደኛዋ

እስከሚለው ድረስ ነው ስለዚህ ሁለት ሙሉልብስ

እንድታሰፋ ጓደኛዋ እስከሚለው ድረስ ደሞ

ምንድነው?ስማዊ ሀረግ ነው ገንዘብ ሰጣት የሚለው

ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

(ም 3፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 3፣አ6)

በምሳሌ ሀያአራት እንደሚታየው ተማሪዎች የታዘዙትን ከዐ.ነገር ውስጥ ባለቤቱን


የያዘ ስማዊ ሀረግና ማሰሪያ አንቀጹን የያዘ ግሳዊ ሀረግ ማሳየት ነው፡፡ከሃያሰባተኛው
የመናገር ተራ እስከ ሰላሳ ሶስተኛው የመናገር ተራ ድረስ ተማሪ ስምንት ተማሪ
ዘጠኝና ተማሪ ሁለት ደጋግመው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ደጋግመው እንዲሰሩ
የተደረጉትም በትክክል የባለቤቱን ክፍል መለየት ስላልቻሉ ነው፡፡ይህንኑ ዐ.ነገር

52
ለአራተኛ ጊዜ የሰራችው ተማሪ ሶስት መልሱን በትክክል ተናግራለች፡፡ መምህርቷ
የሰሩትን ስህተት ለማስተካከል ሲሉ አንዱን ዐ.ነገር አራት ጊዜ አሰርተው
በመጨረሻም ትክክለኛውን መልስ እንዲረዱ አድርገዋል፡፡የተሳሳተው ጥያቄ ደግሞ
የሚሰራው በአንድ ተማሪ ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡መምህርቷ በተደጋጋሚ እንደገና
ያሰሩት እድል የተሰጣቸው ተማሪዎች ስህተት በመስራታቸው ነው፡፡በተደጋጋሚ
ማሰራታቸው በመጨረሻ ትክክለኛውን መልስ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል፡፡

4.2.2. ግልጽ ርማት መስጠት


የመረጃ ትንተናው እንደሚጠቁመው በዚህ ስልት ተማሪዎች በቀጥታ ትክክል
እንዳልሆኑ ይነገራቸዋል ፡፡

ምሳሌ 25

የለመንኩሽ ብድር ስለጠፋብሽ

እሰይ ደስ ብሎኛል ባልተገኘልሽ የሚል አንድ ቅኔ ያለው ግጥም አለ ፡፡

ግጥማችን ህብረቃል ካገኘን በኋላ ሰሙን ለማግኘት የተለያዩ ስልቶች

እንጠቀማለን፡፡በዚህ ምሳሌ መሰረት ሌሎች ስለምሰጣችሁ ከኔ ጋር

ሁኑ፡፡እሺ እስቲ ህብረቃሉ የሚነግረኝ እህ

24 ተ9፡ ህብረቃል እሰይ...ደስ ማለት ነው ፡፡

25 መ/ርት፡ እሺ...እሱ...አይደለም...እህ

(ም 3፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 3፣አ3)

በምሳሌ ሀያአምስት እንደሚታየው የቅኔውን ህብረቃል ተማሪ ዘጠኝ ስለተሳሳተች


መምህርቷ እሱ አይደለም በማለት ግልጽ ርማት በመስጠት ግብረመልስ
ሰጥተዋታል፡፡

ምሳሌ 26

57 ተ13፡ ንጽህናውን ያልጠበቀ ምግብ የበላ ተማሪ ታመመ

ንጽህናውን ያልጠበቀ ምግብ የሚለው ስማዊ ሀረግ

የበላው የሚለው ግሳዊ ሀረግ

58 መ/ርት፡ እሺ..ትክክል ናት?

53
59 ተጋ፡ አይደለችም ፡፡

(ም2፣ክሠ፣ክ/ጊዜ2፣አ 5)

በምሳሌ ሀያ ስድስት ተማሪ አስራ ሶስት የዐ.ነገሩን ባለቤት የያዘውን ስማዊ ሀረግ
ስትለይ ትክክል ስላልነበረች መምህርቷ ተማሪዎችን ትክክል ናት? ብለው ሲጠይቁ
ተማሪዎች በጋራ አይደለችም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ከዚህ መረዳት የሚቻለው
ግልጽ ርማቱ የሚሰጠው በመምህራን ወይም በተማሪዎች ይሆናል ማለት ነው ፡፡

4.2.3. መድገም
የመረጃ ትንተናው እንደሚጠቁመው ይህ ስልት ስህተት የሆኑ ቃላቶችን ወይም
ዐ.ነገሮችን በመድገም ተማሪዎች ስህተታቸውን እንዲረዱ ማድረግ ነው ፡፡

ምሳሌ 27

122 መ/ርት፡ አዋኪ...አዋኪ እና አዋቂ እሺ ሌላ እስቲ....ይህን ሀረግ

የሚያደርግልኝ?

123 ተ7፡ የስራ አዋኪ

124 መ/ርት፡ የስራ አዋኪ እሺ....እስቲ ይህ ዐ.ነገር የሚያደርግልኝ

125 ተ21፡ አበበ ትምህርት አውኮታል፡፡

126 መ/ርት፡ አውኮታል፡፡እሺ ይቺ እንዳለች ባንቀይራት ልክ

ነው፡፡ቅርጿን ባንቀይራት የስራ አዋኪ የምትለውን

ቅርጿን ባንቀይራት

(ም 1፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ 1፣አ1)

በምሳሌ ሃያ ሰባት የቀረበው የሃሳብ ልውውጥ እንደሚያሳየው ተማሪ ሀያ አንድ ስራ


አዋኪ የሚለውን ሀረግ ተጠቅማ ዐ.ነገር እንድትመሰርት ቢፈለግም ተማሪዋ ግን
ሀረጉን አውኮታል በሚለው ተክታዋለች፡፡በመሆኑም መምህርቷ ሀረጉን
እንዳልተጠቀመች ለማሳየት አውኮታል የሚለውን ቃል ደግመውታል፡፡
በመቀጠልም ቅርጹን እንደቀየረችው በመግለጽ እንድታስተካክል አነሳስተዋታል፡፡
ይህን ስልት መምህሯ የተጠቀሙት የቅርፅ ለውጥ በመከሰቱ ምክንያት ቢሆንም
ተማሪዋ ግን ግብረመልሱን ተቀብላ አላስተካከለችም፡፡

54
ምሳሌ 28

28 መ/ርት፡ በጣሊያን ወረራ ዘመን ለሀገራችን ነፃነት ከተዋደቁት

በርካታ ወጣቶች ውስጥ አንዱ ዘርጋ ናጂ ነበር፡፡እህ?

29 ተ6፡ አራት ነጥብ

30 መ/ርት፡ አራት ነጥብ ዘርጋ ነጂ እህ...

31 ተ4፡ ነጠላ ሰረዝ

32 መ/ርት፡ ነጠላ ሰረዝ የምንጠቀመው ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው

የሚዘረዘሩ ነገሮች ለመለየት ነው፡፡አሁን ስለ ዘርጋ ናጂ

ልናወራ ነው ገና እ?

(ም 2፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ 2፣አ2)

በምሳሌ ሀያ ስምንት እንደሚታየው ተማሪዎች ስርዓተነጥብን በተገቢው ቦታ


እንዲያስቀምጡ ያዛል፡፡ነገርግን ተማሪ አራት በሠላሣ አንደኛው የመናገር ተራ ላይ
ነጠላ ሰረዝ የሚል ስርዓተ ነጥብ ቢናገርም መምህርቷ ነጠላ ሰረዝ የሚለውን
በመድገም ለምን እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡

ምሳሌ 29

41 መ/ርት፡ ያ ፀጉሩ በጀርባውና በትከሻው ላይ ተንዠርግጎ ወርዶ

ሲታይ ልዩ ግርማ ያጎናጽፋል ፡፡እ....

42 ተ11፡ ትዕምርተጥቅስ

43 መ/ርት፡ ትምህርተ ጥቅስ? (በጥርጣሬ ድምጽ) እህ ...

44 ተ12፡ አራት ነጥብ

45 መ/ርት፡ አራት ነጥብ? (በርግጠኝነት ድምጽ)

(ም 2 ፣ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 2፣አ2)

በምሳሌ ሀያዘጠኝ እንደሚታየው መምህርቷ አንድ የተሟላ ዐ.ነገር ካነበቡ በኋላ


ስርዓተ ነጥቡን እንዲናገሩ ሲያደርጉ በአርባ ሁለተኛው የመናገር ተራ ተማሪ አስራ
አንድ ትዕምርተጥቅስ ብሎ የሰጠውን መልስ መምህርቷ ትምህርተጥቅስ ብላ ደግማ
ለሌላ ተማሪ እድል ሰጥታለች፡፡ ተማሪውም አራት ነጥብ ብሎ ሲመልስ መምህርቷ

55
ተማሪው የተናገረውን መልስ ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ መልሱን አራት ነጥብ ብላ
ተናግራለች፡፡የመረጃ ትንተናው እንደሚያሳየው የመድገም ስልት ስህተት የሆኑ
ቃላቶችን መድገም ቢሆንም በዚህ ጥናት የምልከታ መረጃ እንደታየው ትክክል
የሆኑ መልሶችም ተደግመው ለተማሪዎች እርግጠኛ እንዲሆኑባቸው ይደረጋል ፡፡

ምሳሌ 30

09 መ/ርት፡ ፍካሬያዊ ፍቺ

10 ተ4፡ አስተዳዳደሪ (ድምፁን ለማስማትያስቸግር ነበር)

11 ተ4፡ አስተዳዳሪ

13 መ/ርት፡ አስተዳዳሪ፣ዋና ወይም ፊት ለፊት ማለት ነው ፡፡

(ም 3 ፣ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 3፣አ3)

በምሳሌ እንደተቀመጠው መምህርቷ ተማሪ አራት የሰጠውን ፍካሬያዊ ፍቺ


ለመስማት ስለተቸገሩ እንዲደግመው አድርገዋል፡፡በመሆኑም ስህተትን ለማሳየት
ብቻ ሳይሆን መግባባት ሳይቻልም ሊደገም ይችላል፡፡የሚደግሙት መምህራን ብቻ
ሳይሆኑ ተማሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡የመድገም ስልት ተግባራዊ ሲሆን የመግባባት
ችግርን ለማስወገድ ያስችላል፡፡

4.2.4. ማነሳሳት
የመረጃ ትንተናው እንዳመለከተው ተማሪዎች የውስጣቸውን እንዲገልፁ ማድረግ
ነው ፡፡

ምሳሌ 31

93 ተ19፡ የተማሪ

94 መ/ርት፡ እ?

95 ተ2፡ የተማሪ

96 መ/ርት፡ እሺ..ተመልከቱ...የተማሪ...አሁን..ተማሪቅጽል

ነው?

56
97 ተጋ፡ ስም ነው፡፡

98 መ/ርት፡ ስም ነው እኛ መጽሀፋችን እንድናወጣ ያዘዘን

ምንድነው?ቅጽል

99 ተ20፡ ብልህ

100 መ/ርት፡ ብልህ...እሺ...አሁን አንቺ ያሰብሺው ቅድም

ይመስለኛል፡፡ ሀረግ አርጊው እኪ ብልህ የቅድሟን

አቀናጂና ፡፡ሀረግ አርጊው፡፡አይዞሽ

101 ተ19፡ (ለአፍታ ዝም አለች)

102 መ/ርት፡ የተማሪ ብለሽ አይደለም?

103 ተ19፡ አዎ

104 መ/ርት፡ ቀኝ መሪው ብልህ ተሰጥተውናል፡፡ቅጽል አንድ

ላይ አቀናጂና ቅጽላዊ ሀረግ አርጊው ፡፡

105 ተ19፡ የተማሪ ብልጥ

106 መ/ርት፡ ጎበዝ…የተማሪ ብልጥ...

(ም 1፣ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 1፣አ1)

በምሳሌ ሰላሳ አንድ እንደሚታየው በዘጠናሦስተኛው የመናገር ተራ ለቅጽል የቃል


ክፍል የተማሪ የሚል ቃል ስለመረጠች መምህርቷ ቅጽል አለመሆኑን ተናግረው
ሌሎች ተማሪዎች ቅጽል እንዲመርጡ በማድረግ ተማሪ አስራዘጠኝ ድጋሚ ሁለቱን
አቀናጅታ ሀረግ እንድትመሰርት አነሳስተዋታል፡፡አይዞሽ የሚል የማበረታቻ ቃል
በመጠቀም በመቶ አምስተኛው የመናገር ተራ በመምህርቷ ጥረት የተማሪ ብልጥ
የሚል ሀረግ መስርታለች፡፡

ምሳሌ 32

36 መ/ርት፡ የፈተና ወረቀት ስማዊ ሀረግ ነው፡፡የፈተና ወረቀት

ተቀበለ የሚለው ዐ.ነገር ይሆናል እህ ሌላስ ብዙ

መመስረት እንችላለን ፡፡ መስርት እስኪ

37 ተ11፡ አልገባኝም

57
38 መ/ርት፡ አልገባኝም? እነዚህን ተጠቅመህ እኮ ስማዊ ሀረግ

መመስረት ነው ፡፡

(ም 2፣ ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ5)

በምሳሌ ሰላሳሁለት እንደሚታየው መምህርቷ ተማሪ አስራ አንድን ሀረግ


እንዲመሰርት በጥያቄ መልክ ቢያነሳሱትም ተማሪው አልገባኝም የሚል ምላሽ
ሰጥቶ ሀረጉን ሳይመሰርት ቀርቷል፡፡ መምህርቷ የማነሳሻ ግብረመልስ ቢያቀርቡም
ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡በተጨማሪም መምህራን ዲስኩር አመልካች ቃላት
በመጠቀም ተማሪዎችን ያነሳሳሉ፡፡

ምሳሌ 32

79 ተ2፡ አምስተኛውን የመጠንቀቅን አስፈላጊነት የሚመክሩ

ለሚለው

80 መ/ርት፡ እህ

81 ተ2፡ ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ

82 መ/ርት፡ እህ

83 ተ2፡ ያልጠረጠረ ተመነጠረ

84 መ/ርት፡ እሺ የመጠንቀቅን አስፈላጊነት የሚመክሩ ምሳሌያዊ

አነጋገሮች ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ

፣ያልጠረጠረ ተመነጠረ ....ሌላው ሳይቃጠል በቅጠል

ጥሩ...ሌላስ?...እህ

85 ተ4፡ ስድስተኛው ርህራሄና ይቅርታ ማድረግን የሚያመለክቱ

የሚለውን መተው ነገሬን ከተተው..... ደሞ ሰው ሆኖ

የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ

(ም1፣ክሠ፣ከ/ጊዜ1፣አ 4)

በምሳሌ ሰላሳሁለት እንደሚታየው መምህርቷ ተማሪዎችን እህ በማለት ለመልስ


ያነሳሷቸዋል፡፡ ይኸውም ተማሪ ሰባዘጠኝ በሁለተኛው የመናገር ተራ የመጠንቀቅን

58
አስፈላጊነት የሚመክሩ ለሚለው ስትል መምህርቷ «እህ» በማለት መልሱን
እንድትመልስ አድርገዋል፡፡በመቶ ሰማንያ ስድስተኛው የመናገር ተራም ተማሪ
ሁለት ምሳሌያዊ አነጋገሩን ስትናገር“እህ” በማለት ለሶስተኛው ምሳሌያዊ አነጋገር
አነሳስተዋታል፡፡መምህርቷ ሌሎችም እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥሩ...ሌላስ?....እህ
በማለት እንዲገልፁ ታነሳሳቸዋለች፡፡ዲስኩር አመልካች ቃላቱ በማነሳሻ
ግብረመልስነት መቅረባቸው ተግባቦቱ እንዲቀጥል ረድቷል፡፡

4.3. በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል ግብረመልስ


ምን አይነት ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ አለው?
በቋንቋ ትምህርት ውስጥ ለቋንቋ ለመዳ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት መካከል
ግብረመልስ ዋነኛው ነው፡፡ተማሪዎች የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ ትክክል
ወይም ስህተት መሆናቸውን የሚያውቁበት መንገድ ያስፈልጋል፡፡የመረጃ ትንተናው
እንደሚያመለክተው ይህም ከጓደኛቸውና ከመምህራን የሚያገኙት ግብረመልስ
ነው፡፡ግብረመልሶቹ ተማሪዎችን ማነሳሳት፣ስህተታቸውን ማስተካከል እና ማድነቅን
መሰረት አድርገው የሚቀርቡ ሲሆን እነዚህ ጥቅል ፋይዳዎች መረጃውን መሰረት
በማድረግ በንዑሳን ክፍሎች እንደሚከተለው ተተንትነው ቀርበዋል፡፡

4.3.1. የግብረመልስ ትምህርታዊ አስተዋጽኦ


መረጃው እንደሚያመለክተው ግብረመልስ የቃላት ክፍሎችን ፣የቃላት ምርጫ፣
ስነጽሁፋዊ ቃላትን ፣የዐ.ነገር ክፍሎችን ለይቶ ለማሳየት ይረዳል ፡፡

4.3.1.1. የቃል ክፍሎች


የመረጃ ትንተናው እንደሚያሳየው በተማሪዎች ዘንድ ቃላት ተሰጥቶ ትክክለኛ
ቃላትን በቃል ክፍሉ እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ በዚህም ስህተት ይሰራሉ፤
መምህራንም ግብረመልስ ይሰጣሉ ፡፡

ምሳሌ 33

130 ተ26፡ የተናደደ ሰው አደጋ ሊደርስበት ይችላል፡፡የተናደደ

የሚለው ቅጽል

131 መ/ርት፡ የተናደደ ሰው አደጋ ሊደርስበት ይችላል፡፡ነው የሚለው

59
ቅጽል ነው ብላለች ሌላ

132 ተ27፡ ግስ

133 መ/ርት፡ ግስ ነው፡፡

134 ተ28፡ መስተዋድድ

135 ተ3፡ ግስ ነው፡፡

136 መ/ርት፡ እህ…አዎ የተናደደ የሚለው በራሱ ግስ ነው ፡፡

(ም1፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 1፣አ 4)

በምሳሌ ሰላሳሶስት እንደሚታየው በዐ.ነገር ውስጥ የተሰመረበት ቃል የቃል ክፍል


መለየት በሚል የቀረበውን ተግባር ተማሪ ሀያስድስት የተናደደ የሚለውን ቃል
ቅጽል ስትል በመቶ ሰላሳ አምስተኛው የመናገር ተራ ተማሪዎች ግስ ነው፡፡ብለው
ግብረመልስ ሲሰጡ በመቶ ሰላሳ ስድስተኛው የመናገር ተራ ላይ መምህርቷ አዎ
ብለው በማረጋገጥ ግስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በመሆኑም ተማሪዎች የቃል ክፍሎች
ቢሳሳቱም ግብረመልስ ከተሰጣቸው ትክክለኛው የቃል ክፍል እንዲያውቁ
ይደረጋል፡፡ግብረመልሱ የቃል ክፍል በመሳሳታቸው ምክንያት የቀረበ ሲሆን
የተሰጣቸውን ቃል ትክክለኛውን የቃል ክፍል እንዲያውቁ ረድቷል፡፡

ምሳሌ 34

27 መ/ርት፡ አንድ ስም የሚመርጥልኝ ስም…ስም የሚመርጥልኝ?

28 ተ1፡ አዲስ

29 መ/ርት፡ አዲስ…ስም…አዲስ…ስም አይደለም፡፡ያው የሰው ስምን

በቅጽል፣በግስም፣በስም ስለሚጠሩ ነው፡፡አሁን አንተ

ያሰብከው ይመስለኛል አዲስ የሚባል ሰውዬውን ነው

ከሆነ ግን በዚህ ላይ ይህ ቅጽል ነው፡፡

(ም 1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 1)

ከላይ የቀረበው የጥየቄና መልስ ልውውጥ እንደሚያሳየው ተማሪ አንድ የመረጠው


ቃል ቅጽል እንጂ ስም አለመሆኑን ተማሪ አንድ ስህተቱን እንደፈፀመም
በማስረዳት የቃል ክፍሉን ትክክል እንዳልሆነ ግልጽ ግብረመልስ ሰጥተዋል ፡፡

60
ምሳሌ 35

55 መ/ርት፡ ስም የሚነግረኝ…እህ?

56 ተ3፡ ደግ

57 መ/ርት፡ ደግ እሺ…ደግ ስም ነው?

58 ተ3፡ አይደለም፡፡

59 መ/ርት፡ ቅጽል ነው ፡፡

(ም 1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 1)

በምሳሌ ሰላሳ አምስት እንደሚታየው መምህርቷ ስም የቃል ክፍል እንዲናገሩ


ስትጠይቅ ተማሪ ሶስት ቅጽል ሆነ ቃል በመምረጡ መምህርቷ ተማሪዎችን
በመጠየቅ ቃሉ ቅፅል እንደሆነ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡መምህርቷም በሀምሳ
ዘጠነኛው የመናገር ተራ ላይ ቅጽል ነው የሚል ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡

4.3.1.2. የሀረግ ምስረታ


ተማሪዎች ልክ እንደ ቃላት ሁሉ ሀረግ ሲመሰርቱ ስህተት ይፈጥራሉ፡፡ በዚህም
ሰዋሠዋዊ ህጉን ለመግለጽ መምህራንም ሆኑ ተማሪዎች ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡

ምሳሌ 36

81 ተ10፡ ብልጥ

82 መ/ርት፡ ብልጥ እሺ ይችን ሀረግ የሚያረግልኝ ብልጥ እህ

83 ተ4፡ ብልጥ ልጅ

84 መ/ርት፡ እሺ …ተመልከቱ አሁን ብልጥ...ልጅ ብለን

ስንጽፍ እኛ መጽሀፋችን ላይ የታዘዝነው ምናዊ

ሀረግ እንድንመሰርት ነው ፡፡

85 ተ3፡ ቅጽላዊ ሀረግ

86 መ/ርት፡ ቅጽላዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ቅጽላዊ ሀረግ

ስንመሰርት ደግሞ ቀኝ መሪው ምን መሆን

አለበት? ቅጽል አንተ ግን የነገርከን ብልጥ

61
ልጅ ስንል ቀኝ መሪያችን ማነው ? ልጅ

ነው፡፡ልጅ ደግሞ የቃል ክፍሉ ምንድነው?ስም

ነው ፡፡አሁን ይህ ስማዊ ሀረግ እንጂ ቅጽላዊ

ሀረግ አልሆነልንም ፡፡

(ም 1፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 1፣አ1)

በምሳሌ ሰላሳ ስድስት እንደሚታየው ተማሪ አስር ብልጥ የሚል ቃል


መርጣለች፡፡ተማሪ አራት ደግሞ ብልጥ ልጅ የሚል ሀረግ ቢመሰርትም
በሰማንያአራተኛው የመናገር ተራ ላይ መምህርቷ ተማሪዎችን መጽሀፋቸው ምን
አይነት ሀረግ እንዲመሰርቱ እንዳዘዛቸው በመጠየቅ ተማሪዎች በጋራ ቅጽላዊ ሀረግ
የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡መምህርቷም ተመልሳ ቅጽላዊ ሀረግ ሲመሰርቱ መሪው
ቅጽል መሆን እንዳለበት ተማሪው የመሰረተው ግን ስማዊ ሀረግ እንደሆነ
በመሰረቱት ግብረመልስ ሰጥተዋል ፡፡

ምሳሌ 37

43 ተ14፡ አዋቂ

44 መ/ርት፡ እህ

45 ተ14፡ አዋቂ ሰው

46 መ/ርት፡ አዋቂ ነው ያልሺው?

47 ተ14፡ አዎ

48 ተ14፡ አዋቂውን ተጠቅመሽ ቅፅል መስርቺ?

49 ተ14፡ አበበ አዋቂ ነው ፡፡

50 መ/ርት፡ ሀረግ ከዚሁ ላይ ማለት ነው፡፡

51 ተ14፡ (ምላሽ አልሰጠችም)

52 መ/ርት፡ እስቲ ሌላ የሚሰራልኝ ፡፡ ሌላ…

53 ተ8፡ የወጣት የሚለው የወጣት ፈጣን ቅጽላዊ ሀረግ ነው ፡፡

(ም 2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ5)

62
ከላይ በቀረበው የጥያቄና መልስ ልውውጥ እንደሚታየው ተማሪ አስራ አራት አዋቂ
የሚል ቅፅል ብትመርጥም የመሰረተችው ሀረግ ግን ስማዊ ሀረግ ነው፡፡መምህርቷ
በድጋሚ ሀረጉን እንድታስተካክል ቢያነሳሷትም መልስ አልሠጠችም፡፡ሀረጉ
የተሳሳተ ቢሆንም መምህርቷ ሌላ የሚሠራልኝ?የሚል ጥያቄ አቀረቡ እንጂ ሀረጉ
ትክክል መሆን አለመሆኑን የሚያሳይ ግብረመልስ አልሰጡም፡፡ቀጣዩ ተማሪም
አዋቂ የሚለውን ቅፅል በመተው ፈጣን የሚለውን ተጠቅሞ ነው ቅፅላዊ ሀረግ
መስርቷል፡፡ግብረመልሱ የመጀመሪያዋን ተማሪ ለመልስ ባያነሳሳትም በሌላ ተማሪ
የሀረጉን መዋቅር ለማስተካከል ረድቷል፡፡

ምሳሌ 38

09 ተ3፡ አዲስ ......ስማዊ ሀረጉ አዲስ ልብስ አበበ አዲስ

ልብስ ለብሷል፡፡

10 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ አዲስ...አዲስ ልብስ ሀረግ

ነው፡፡አበበ አዲስ ልብስ ለብሷል፡፡ይህ ዓ.ነገር

ነው፡፡

(ም 2፣ክ ሠ፣ከ/ጊዜ2፣አ5)

በምሳሌ ሰላሳስምንት የቀረበው መረጃ እንደሚያሳየው ተማሪ ሶስት የመረጠው አዲስ


የሚለውን ቃል ነው፡፡የመሰረተው ሀረግ ስማዊ ሀረግ ቢሆንም የመረጠው
የመጀመሪያ ቃል ግን ቅፅል ቢሆንም መምህርቷ ግን ለቃሉ ትኩረት አልሠጡም፡፡

ምሳሌ 39

73 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ነጭናጫ ልጅ...ቅፅላዊ

74 መ/ርት፡ እ?

75 ተ18፡ ልጅ ለሚለው ቅፅላዊ ሀረግ ነጭናጫ ልጅ

76 መ/ርት፡ ነጭናጫ ቆይ አዳምጧት?ነጭናጫ ልጅ ብላለች

ነጭናጫ ልጅ ቅፅላዊ ሀረግ ነው እንዴ?ምን ዓይነት

ነው?

77 ተጋ፡ ስማዊ ሀረግ

63
78 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረግ በይ ይህን አስተካክይ ነጭናጫ ልጅ

ሳይሆን

79 ተ18፡ አዋቂ ልጅ

80 መ/ርት፡ ወይም የልጅ አዋቂ

(ም 2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ5)

በሰባ ሶስተኛው የመናገር ተራ ተማሪ አስራ ስምንት የመሰረተችው ስማዊ ሀረግ


በመሆኑ መምህርቷ ተማሪዎችን እንዲያስተካክሉ ሲጠይቁ ተማሪዎችም በጋራ
ስማዊ ሀረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡መምህርቷ ተማሪዋን ድጋሚ አስተካከይ በማለት
ቢያነሳሷትም ተማሪዋ መልሳ የመሰረተችው አዋቂ ልጅ የሚል ስማዊ ሀረግ
ነው፡፡መምህርቷም ቀጥተኛ ባልሆነ ሁኔታ ቅፅላዊ ሀረጉን አስተካክለው ለመመስረት
ግብረመልስ በመስጠት ሰዋሠዋዊ ህጉን አሳይተዋል፡፡ከምሳሌ ሰላሳስድስት እስከ
ሰላሳ ዘጠኝ የቀረቡት ግብረመልሶች የሃረግ መዋቅርን ለማስተካከል የቀረቡ ሲሆኑ
ለመምህርቷም ሰዋሠዋዊ ህጉን ለማሳየት አግዟል፡፡

4.3.1.3. የቃላት ንበት የሚያስከትለውን የትርጉም ለውጥ


ተማሪዎች ቃላት ሲጠብቁና ሲላሉ የሚያሳዩትን የትርጉም ለውጥ ሳይረዱ ሲቀሩ
መምህራን ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡

ምሳሌ 40

103 ተ12፡ እንስራ ነው የሚለው ሀገራችንን ተባብረን እንስራ አሉ

ጠቅላይ ሚንስቴሩ እእእ...አለሚቱ እንሰራውን

ሠበረችው፡፡

104 መ/ርት፡ እሺ በመጀመሪያው ዓ.ነገር ማንኛው ነው

የጠበቀው?እ...ሆሄ(ፊደል)

105 ተ12፡ እንስራ

106 መ/ርት፡ እኮ ማንኛው?

107 ተ12፡ ራ...ስ

108 መ/ርት፡ ራ....ስ....እስቲ እሷ በሰራችው ዓ.ነገር ጠባቂው ድምፅ

64
የትኛው ነው? ዐ.ነገሩን ምን ነበር ያልሽው?

109 ተ12፡ አገራችንን ተባብረን እንስራ?

110 መ/ርት፡ በሀገራችን ተባብረን እንስራ የጠበቀው ሆሄ

ማነው?እዚህ ጋር ስ...ን ናት

(ም1፣ ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 1፣አ 4)

በምሳሌ አርባ እንደሚታየው ተማሪ አስራ ሁለት እንስራ በሚለው ቃል ውስጥ


የጠበቀውን ድምጽ እንድታሳዩ ስትጠየቅ ራ....ስ...ብላ በመመለሷ መምህርቷ በመቶ
አስረኛው የመናገር ተራ «ን» መሆኗን በመንገር ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡ይህም
ተማሪዎችን እርግጠኛ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡የተሰጠው ግብረመልስ የቃላቱን ንበት
እንዲያውቁ የቀረበ ሲሆን በጥርጣሬ የመለሱትን መልስ እርግጠኛ እንዲሆኑ
አድርጓል፡፡

4.3.1.4. የስርዓተ ነጥብ አገባብ

ስርዓተነጥብ በተገቢ ቦታቸው ላይ መጠቀም እንዳለባቸው ለማሳየት መምህራን


ግብረመልስ ይሰጣሉ ፡፡

ምሳሌ 41

41 መ/ርት፡ የፀጉሩ በጀርባውና በትከሻው ላይ ተዠርጎ ወርዶ ሲታይ

ልዩ ግርማ ያጎናፅፋል እህ....

42 ተ11፡ ትዕምርተጥቅስ

43 መ/ርት፡ ትምህርተ ጥቅስ (በጥርጣሬ ድምፅ) እህ

44 ተ12፡ አራት ነጥብ

45 መ/ርት፡ አራት ነጥብ (በእርግጠኝነት ድምፅ)

(ም 2፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 2፣አ 2)

በምሳሌ አርባአንድ እንደሚታየው መምህርቷ አንድ ሙሉ ዓ.ነገር ካነበበች በኋላ


መጠቀም ያለባቸውን ስርዓተ ነጥብ ስትጠይቅ ተማሪ አስራአንድ ትዕምርተጥቅስ
ብሎ ሲመልስ ከመምህርቷ ድምፅ ተማሪው ትክክል እንዳልሆነ መረዳት

65
ይቻላል፡፡ተማሪ አስራ ሁለት ግን አራት ነጥብ ብላ ስትናገር መምህርቷ መልሱን
ለመድገም ለትክክለኛነቷ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡

ምሳሌ 42

45 መ/ርት፡ ዘርጋ ጢም አልባ ሲሆን እህ.....

46 ተ3፡ ቅንፍ

47 መ/ርት፡ ቅንፍ ቅንፍን የምንጠቀመው ወይምን

ለማመልከት ነው፡፡አማራጭ ሲኖር ነው፡፡አሁንም እ....

48 ተ3፡ ሁለት ነጥብ ከሰረዝ ጠቅላላ ገፅታው የሰው በዓይን

የሚማርክ ሸበላ.... ሸበላ

49 ተ14፡ ቅንፍ

50 መ/ርት፡ ቅንፍ ምን ያደርጋል?ይከፈታል ቆንጆ ካልን በኋላ

ሁለተኛው ዘጠኝ ላይ ቅንፍ ምን ያደርጋል?ይዘጋል፡፡

(ም 2 ፣ክ ሀ ፣ክ/ጊዜ 2፣አ 2)

ምሳሌ አርባ ሁለት እንደሚያመለክተው ተማሪ ሶስት የሚዘረዘሩ ሃሳቦች


ከመጀመራቸው በፊት የተጠቀመው ሥርዓተ ነጥብ ቅንፍ የሚል ሲሆን
መምህርቷም ቅንፍን መጠቀም አማራጭ ሃሳብ ሲኖር መሆኑን በመንገር ስህተቱን
ጠቁመው እርማት ሰጥተዋል፡፡ተማሪ ሶስት ሁለት ከሰረዝ በማለት የስርዓተነጥቡን
ማስተካከያ ተናግሯል፡፡ቀጥሎ በሃምሳኛው የመናገር ተራ መምህርቷ ቀጣዩን ዐ.ነገር
በማንበብ የቅንፍን ተግባር እንዲረዱት ለማድረግ ችለዋል፡፡ይኸውም ሸበላና ቆንጆ
የሚለውን ቃል በመጠቀም ተማሪዎች ቅንፍ የሚለውን ስርዓተ ነጥብ እንዲጠቀሙ
አድርገዋል፡፡

4.4.1.5. ዓ.ነገር
የመረጃ ትንተናው እንደሚጠቁመው የዐ.ነገር ክፍሎችና ዓይነቶችን ለማስገንዘብ
መምህራን ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡

ምሳሌ 43

83 ተ15፡ እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ይህም

66
ውስብስብ ዓ.ነገር ነው ምክንያቱም እንግዳው ሰውዬ ዛሬ

እንግዳው ሰውዬ አንድ ዓ.ነገር ነው፡፡ ዛሬ ጠዋት ወደ

ሀገሩ ተመለሰ የሚለው፡፡

84 መ/ርት፡ እሺ እንግዳው ሰውዬ የሚለው ዓ.ነገር ነው እንዴ?

85 ተጋ፡ አይደለም፡፡

86 መ/ርት፡ ሀረግ ነው እስቲ የሚያስተካክል.....እህ

87 ተ16፡ እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ወደ ሀገሩ ተመለሰ የሚለው

ዓ.ነገር ተራ ዓ.ነገር ነው

(ም 3፣ክ ሠ፣ከ/ጊዜ 3፣አ 6)

ከላይ የቀረበው የሀሳብ ልውውጥ እንደሚታየው ዐረፍተነገሩን ከሰዋሠዋዊ አንጻር


እንደሚከፍሉ ሲደረጉ ተማሪ አስራ አምስት የተሰጠውን ዐረፍተነገር ውስብስብ
መሆኑን ሲገለጽ መምህርቷ ግን ተማሪ አስራአምስትን ስጠይቅ ተማሪዎች በጋራም
አለመሆኑ ገልፀዋል፡፡መምህርቷም ለሌላ ተማሪ እድል ሰጥተው ተማሪ አስራስድስት
ተራ ዐረፍተነገር ነው በማለት ግብረመልስ ሰጥታለች፡፡በመሆኑም መምህራንም ሆኑ
የክፍሉ ተማሪዎች ስህተት ሲሰሩ ግብረመልስ ይሰጣሉ ፡፡

ምሳሌ 44

40 መ/ርት፡ ሶስተኛው

41 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት

ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው፡፡፡ጓደኞቼ ጠዋት

ጠዋት ተነስተው ስማዊ ሀረግ ይሆናሉ፡፡ስፖርት

ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው እሱ ግሳዊ ሀረግ

ነው፡፡

42 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ እስከምን ድረስ ነው?ጠዋት ጠዋት እስከተለው?

43 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

44 መ/ርት፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እንደሚከተለው

ድረስ ነው?ትላለች እስቲ ሌላስ?

67
45 ተ4፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት

ስለሚሰሩ እዚህ ጋር ድረስ ስማዊ ሀረግ ነው

ቀልጣፎች ናቸው፡፡ይህ ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው ፡፡

46 መ/ርት፡ እሺ…ትክክል አይደለም ፡፡ እስቲ

47 ተ19፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት እስከሚለው

ስማዊ ሀረግ ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው ፡፡ ግሳዊ ሀረግ

48 መ/ርት፡ እ….ሺ ሌላስ ትክክል አይደለም ፡፡

49 ተ5፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት

ስለሚሰሩ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ግሳዊ ሀረጉ

ደግሞ ቀልጣፎች ናቸው ፡፡

50 መ/ርት፡ እ….ሺ ሌላስ ትክክል አይደለም ፡፡

51 ተ2፡ ጓደኞቻችን የሚለው ሰዋዊ ሀረግ ጠዋት ጠዋት

ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው

የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረጉ ነው ፡፡

52 መ/ርት፡ አ….ዎ ጓደኞቻችን እስከሚለው ነው ስማዊ ሀረጉ

ጓደኞቻችን ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ጠዋት ጠዋት

ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች

የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ፡፡ ጓደኞቻችን ስማዊ

ሀረግ ነው፡፡ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት

ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው ደሞ ምንድነው

ነው?ግሳዊ ሀረግ ነው ፡፡

(ም 2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ 5)

በምሳሌ አርባአራት እንደሚታየው ተማሪ አስራ አንድ፣ ተማሪ አራት፣ ተማሪ አስራ
ዘጠኝ፣ እና ተማሪ አምስት የዐረፍተነገሩን ባለቤት የያዘው ስማዊ ሀረግና
ማሰሪያአቀጽን የያዘው ግሳዊ ሀረግ ለመለየት ቢጥሩም አራቱም ተማሪዎች ስማዊ
ሀረጉን መለየት አልቻሉም፡ መምህርቷም ስህተት መሆናቸውን በቀጥታ በመጠቆም

68
ሌላስ በማለት ተማሪዎችን እንዲሞክሩ አነሳስተዋል፡፡ በመጨረሻም ተማሪ ሁለት
በሀምሳ አንደኛው የመናገር ተራ ላይ በትክክል ባለቤቱን የያዘው ስማዊ ሀረግ
ተናግራ ትክክለኛውን እዲያውቁ አድርጋለች፡፡ስለዚህ ግብረመልሱን በተደጋጋሚ
መለዋወጣቸው የዐ.ነገር ክፍሉን በትክክል እንዲያውቁ ያስቻለ ትምህርታዊ ፋይዳ
አለው፡፡

4.3.1.6. ስነ- ጽሁፋዊ ሃሳቦች


የመረጃ ትንተናው እንደሚገልፀው እንደ ዘይቤ ፣ፈሊጥ፣ ምሳሌያዊ አነጋገርና ቅኔ
ስነ-ጽሁፋዊ ሃሳቦች በክፍል ውስጥ በሚቀርቡበት ጊዜ ትንታኔ ሲሰጡ ሲሳሳቱ
ግብረመልስ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

ምሳሌ 45

173 መ/ርት፡ ይናገር ሀውልቱ… ሀውልቱ እ…

174 ተ31፡ ዘይቤ

175 መ/ርት፡ እ?

176 ተ31፡ ዘይቤ

177መ/ርት፡ ትክክል ናት፡፡ምን ዓይነት ዘይቤ? የዘይቤውን ዓይነት ንገሪኝ?

178 ተ31፡ ሠወኛ

179 መ/ርት፡ እ?

180 ተ31፡ ሠወኛ

181 መ/ርት፡ ሠወኛ … ዘይቤ ነው? …እህ

182 ተ36፡ ፈሊጣዊ

183 መ/ርት፡ ዘይቤ ነው፡፡ምን ዓይነት ዘይቤ ይላችኋል?

184 ተ36፡ ፈሊጣዊ

185 መ/ርት፡ እንዴ…ፈሊጣዊ የሚባል ዘይቤ አለ እንዴ?

186 ተ12፡ እንቶኔ ዘይቤ

187 መ/ርት፡ እንቶኔ ዘይቤ፡፡እንቶኔ ዘይቤ ነው፡፡

(ም 1፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 1፣አ 4)

69
በምሳሌ አርባአምስት እንደሚታየው ፈሊጥና ዘይቤን መለየት የሚል ጥያቄ ያለ
ሲሆን ይናገር ሀውልቱ የሚለውን ሀሳብ ተማሪ ሰላሳ አንድ ዘይቤብላ ብትመልስም
ምን ዓይነት ዘይቤ እንደሆነ ስትጠይቅ ግን የዘይቤው ዓይነት ሠወኛ ነው፡፡ በማለቷ
ለሌላ ተማሪ እድል ተሠጥቶ ተማሪ ሠላሳ ስድስት ፈሊጣዊ የሚል መልስ ሲሰጥ
መምህርቷ ዘይቤ ተብሎ እንደተመለሰና ዘይቤ መሆኑም ትክክል እንደሆነ
ለማስታወስ ሞክረዋል፡፡ጥያቄው ዘይቤው ምን እንደሆነ እንዲገልፁ እንደሆነ
ተናግረው ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ተማሪ ሠላሳ አንድም በድጋሚ ፈሊጣዊ ብሎ
የገለፀው በዓይነቱ ሲመደብ ሳይሆን የዘይቤውን ዓይነት መሆኑን በድጋሚ በመግለፅ
ግብረመልስ ሠጥቷል፡፡በመሆኑም መምህርቷም ፈሊጣዊ የሚባል ዘይቤ አለ
እንዴ?ብለው በመጠየቅ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ተማሪ አስራሁለትም እንቶኔ ዘይቤ
መሆኑን ተናግራለች፡፡ መምህርቷም ቃሉን በመድገም ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡

ምሳሌ 46

23 መ/ርት፡ የለመንኩሽ ብዕር ስለጠፋብሽ እሰይ ደስ ብሎኛል

ባልተገኘልሽ፡፡ የሚል አንድ ቅኔ ያለው ግጥም ነው፡፡

የግጥማችን ህብረ ቃል ካገኘን በኋላ ሠሙን ለማግኘት

የተለያዩ ስልቶችን እንጠቀማለን፡፡በዚህ ምሳሌ መሠረት

ሌሎች የሚሰሩ ስለምሰጣችሁ ከኔ ጋር ሁኑ፡፡እሺ እስቲ

ህብረ ቃሉን የሚነግረኝ? እህ…

24 ተ9፡ ህብረ ቃሉ እሰይ ደስ ማለት ነው፡፡

25 መ/ርት፡ እሺ … እሱ አይደለም … እህ

26 ተ10፡ ባልተገኘልሽ

27 መ/ርት፡ ህብረቃላችን ማነው? ባልተገኘልሽ፡፡

(ም 3፣ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 3)

70
በምሳሌ አርባስድስትም እንደሚታየው የቅኔውን ክፍል ለመለየት ምሳሌ
የሚሆናቸውን ግጥም ሰጥተዋል፡፡ተማሪ ዘጠኝም የቅኔውን ህብረ ቃል ከግጥም
ውስጥ አውጥታለች ነገር ግን ስህተት ስለሆነች መምህርቷም ትክክል አለመሆኑን
ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ለተማሪ አስርም እድል ሠጥተው ባልተገኘልሽ የሚል
መሆኑን ገልጿል፡፡ መምህርቷም ትክክል መሆኑን በመድገም አረጋግጠዋል፡፡
ነገርግን መምህርቷ የተናገሩት የቅኔውን ህብረቃል ሳይሆን ቃሉን ነጣጥላ በማንበቧ
ወርቁ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

4.3.1.7. የቃላት ንበት (የሆሄያት ግድፈት)


ተማሪዎች የተሠጣቸውን ጥያቄ ወይም ዐ.ነገር ሲያነቡ ስህተት ይፈፅማሉ በዚህ
ምልከታም ስህተቱ ተከስቶ ግብረመልስ የተሰጣቸውም ያልተሰጣቸውም የፊደል
ግድፈቶች አሉ፡፡

ምሳሌ 47

42 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋትጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ

ቀልጣፎች ናቸው (ጓደኞቻችን የሚለውን ጓደኞቼ ብላ

ስታነብ ግብረመልስ አልተሰጣትም) ጓደኞቼ ጠዋትጠዋት

ተነስተው ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ስፖርት ስለሚሰሩ

ቀልጣፎች ናቸው ግሳዊ ሀረግ፡፡

43 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ እስከ ምንድረስ ነው?ጠዋት ጠዋት

እስከሚለው?

44 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

45 መ/ርት፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እስከሚለው ትላለች

እስኪ ሌላስ?

46 ተ19፡ ጓደኛችን ጠዋትጠዋት ተነስተው ስፖርት እስከሚለው

ስማዊ ሀረግ ቀልጣፎች ናቸው ግሳዊ ሀረግ

(ጓደኞቻችን የሚለውን ጓደኛችን በማለት አንብባለች)

(ም 3፣ ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

71
በምሳሌ አርባሰባት እንደሚታየው ጥያቄው የዐ.ነገሩን ባለቤት የሚያሳይ ስማዊ
ሀረግና የዐ.ነገሩን ማሠሪያ አንቀፅ የያዘ ግሳዊ ሀረግ መለየት ሲሆን መምህርቷም
ትኩረት ሰጥተው ግብረመልስ የሚሰጡት ለዐ.ነገር ክፍሎቹ ነበር፡፡ ነገርግን
ተማሪዎቹ የተሳሳቱት የዐ.ነገሩ ክፍሎች ብቻ ሳይሆን የቃሉን ንበትም ነው፡፡
መምህርቷ ግን ትኩረት አልሰጡትም፡፡ ይኸውም የዐ.ነገሩ የመጀመሪያ ቃል
የሚለው ጓደኞቻችን ሲሆን ተማሪ አስራ አንድ ጓደኞቼ በማለት፣ ተማሪ አስራ
ዘጠኝ ደግሞ ጓደኛችን በማለት አንብበዋል፡፡ ተማሪ አስራ አንድ የመደብ
አለመስማማት፣ ተማሪ አስራ ዘጠኝ ደግሞ የቁጥር አለመስማማት እንዲፈጠር
ቢያደርጉም መምህርቷ ግን ግብረመልስ የሚሰጡት መፀሀፍ ባስቀመጠው ትዕዛዝ
መሠረት ሲሳሳቱ እንጂ ለሌሎች ስህተት ግብረመልስ አይሰጡም፡፡

4.3.2. የግብረመልስ ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለከተው በክፍል ውስጥ በሚከናወኑ የቋንቋ ተግባራት
ውስጥ የተግባቦት ችግር ሲከሠት ግብረመልስ ይሰጣል፡፡ ይህም ግብረመልስ
ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን ያጋጠማቸውን ችግር ለመፍታት ይረዳቸዋል፡፡
እነዚህም፡- ቃላት በትክክል እንዲጠሩ መፈለግ፣የተባለውን በትክክል አለማዳመጥ
ወይም ማረጋገጫ መሻት፣ ተጨማሪ ማብራሪያ መፈለግ የተፈጠሩ የተግባቦት
ችግሮች ሆነው ግብረመልስ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

4.3.2.1. ቃላት በትክክል እንዲጠሩ መፈለግ


መምህራን ተማሪዎች የጠሩትን ቃል ቢሰሟቸውም በትክክል እንዲጠሯቸው
ሲፈልጉ ቃሉን ደጋግመው በመጥራት በትክክል እዲያነቡ የሚረዳ ግብረመልስ
ይሰጧቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ግብረመልሱን ሊቀበሉም ላይቀበሉም ይችላሉ፡፡

ምሳሌ 48

126 ተ2፡ በዚህ ዘመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንደ ጥንታዊ

ግሪካዊያን ዴስሞን

127 መ/ርት፡ ዴሞሰቴን … ዴሞስቴን

(ም3፣ክ ሠ ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

72
በምሳሌ አርባስምንት እንደሚታየው ተማሪ ሁለት የግሪኩን የንግግር አባት
ሳትጠራው ዴስሞን ብላ የነበረ ሲሆን መምህርቷ ግን ዴሞስቴን ዴሞስቴን በማለት
በተደጋጋሚ ስሙን በመጥራት ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡ተማሪዋ ግን ስሙን
ለመጥራት ስለከበዳት ይሁን በሌላ ምክንያት ቃሉን ደግማ አልጠራችውም ፡፡

4.3.2.2. የተባለውን በትክክል አለማዳመጥ ወይም ማረጋገጫ መሻት


መምህራን ተማሪዎች የሰጡትን ምላሽ በትክክል ካላዳመጡ ወይም ይበልጥ
እርግጠኛ ለመሆን ሲሉ ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡ተማሪዎችም ምላሻቸውን በመድገም
ማረጋገጫ ይሰጣሉ፡፡

ምሳሌ 49

40 መ/ርት፡ ሶስተኛው (ጥያቄው የዐ.ነገሩን ስማዊና ግሳዊ ሀረግ

መለየት ነው)

41 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች

ናቸው፡፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስማዊ ሀረግ

ይሆናል፣ስፖርት ስለሚሰሩቀልጣፎች ናቸው እሱ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

42 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ እስከምን ድረስ ነው?ጠዋት ጠዋት

እስከሚለው?

43 ተ11፡ ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

44 መ/ርት፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እስከሚለው ድረስ ነው ትላለች

እስቲ ሌላስ?

45 ተ4፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ

እዚህ ድረስ ስማዊ ሀረግ ነው ቀልጣፎች ናቸው፡፡ይህ

ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

46 መ/ርት፡ እሺ ትክክል አይደለም፡፡ እስቲ?

47 ተ19፡ ጓደኛችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት እስከሚለው

ስማዊ ሀረግ፣ ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው፡፡

(ም 2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ2፣አ 5)

73
የተማሪዎቹን መልስ ለማረጋገጥ ራሳቸውን እስከምንድረስ? የሚል ጥያቄ በመጠየቅ
እንዲደግሙላቸው ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡ተናጋሪውም ቃሉን ወይም ሃሳቡን
መድገም ግብረመልስ ይሰጥና ያረጋግጣል፡፡

ምሳሌ 50

118 መ/ርት፡ አንድ አንድ ቅፅል የሚፈልግልኝ እህ?

119 ተ2፡ አዋኪ

120 መ/ርት፡ እ?

121 ተ2፡ አዋኪ … አዋኪ… አዋቂ እና አዋኪ

(ም1፣ክ ሀ፣ ክ/ጊዜ 1፣አ 1)

በምሳሌ ሀምሳ እንደሚታየው ተማሪ ሁለት የጠራው ቅፅል መምህርቷ


ስላልተሰማቸውና ከአዋቂ ጋር ስለተመሳሰለባቸው እ? በማለት እንዲደግመው
ሲያነሳሱት ተማሪው በድጋሚ ቃሉን ሁለት ጊዜ በመጥራት የመረጠው ቅፅል አዋኪ
በመሆኑ ለማረጋገጥ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ መምህርቷም ከሱ በመከተል ቃሉን
በመጥራት የተመሳሰለባቸውን ቃል በመጥራት ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡በመሆኑም
መምህራን ተማሪዎች የመረጡት ቃል ግራ ካጋባቸው ወደ ግብረመልስ ይገባሉ፡፡

ምሳሌ 51

09 መ/ርት፡ ዓይን ፍካሬያዊ ፍች

10 ተ4፡ አስተዳዳሪ (ድምፁን ለመስማት ያስቸግር ነበር)

11 መ/ርት፡ እ?

12 ተ4፡ አስተዳዳሪ

13 መ/ርት፡ አስተዳዳሪ

(ም 3፣ ክ ሀ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 3)

በምሳሌ ሀምሳ አንድ እንደሚታየው መምህርቷና ተማሪው የግብረመልስ ልውውጥ


ያካሄዱት የተማሪው ድምፅ በትክክል ባለመሰማቱ ምክንያት ነው፡፡ ተማሪ አራት
ዓይን ለሚለው ቃል የሰጠው የፍካሬ ትርጉም ስላልተሰማት እንዲደግምላቸው «እ»
የሚል አነሳሽ ግብረመልስ ሲሰጡት ተማሪውም ቃን በመድገም እንዲሠማ

74
አድርጓል፡፡ መምህርቷም በድጋሚው የመናገር ተራ የተሰማቸው መሆኑን ቃሉን
በመድገም አሳውቀዋል፡፡

ምሳሌ 52

42 መ/ርት፡ ቅፅላዊ…ሀረግ ነው በዚሁ መሠረት ደግሞ ሌሎቹን

ስሩ፡፡እስቲ የሚሰራልኝ እንዴ ተሳተፉ እንጂ …ምነው?

43 ተ14፡ አዋቂ

44 መ/ርት፡ እህ?

45 ተ14፡ አዋቂ ሰው

46 መ/ርት፡ አዋቂ ነው ያልሽው?

47 ተ14፡ አዎ

(ም 2፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 2፣አ 5)

በምሳሌ ሀምሳሁለትም እንደሚታየው መምህርቷ ቅፅላዊ ሀረግ ለመመስረት


የሚያስችል ቃል ስትጠይቃቸው ተማሪ አስራ አራት አዋቂ የሚል ቃል መርጣ
ስትመሰርት ግን ስማዊ ሀረግ በመመስረቷ መምህርቷም ቅፅል መምረጧን
ለማረጋገጥ ጥያቄያዊ ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ ተማሪ አስራ አራት «አዎ» የሚል
የማረጋገጫ ግብረመልስ ሠጥታለች፡፡ መምህርቷም በጥያቄ መልክ ግብረመልስ
የሰጡት ተማሪዋ ቅፅል መርጣ ስማዊ ሀረግ በመመስረቷ ምክንያት ነው፡፡

4.3.2.3. ተጨማሪ ማብራሪያ መፈለግ


የመረጃ ትንተናው እንደሚያመለክተው መምህራን ተማሪዎች መልስ ሲሰጧቸው
ለምን? የትኛው? እንዴት የሚሉ መጠይቃዊ ቃላትን በመጠቀም በተግባቦት ላይ
ችግር ካለ ግልጽነትን ለመፍጠር ያግዛል ፡፡

ምሳሌ 53

87 ተ16፡ እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ጠዋት ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡

75
የሚለው ዐ.ነገር ተራ ዐ.ነገር ነው፡፡

88 መ/ርት፡ ለምን?

89 ተ16፡ ምክንያቱም እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ጠዋት ወደ አገሩ

ተመለሰ፡፡ውስብስብ ዐ.ነገር ሁለትና ከዛ በላይ ሲሆን

90 መ/ርት፡ ከዛ በላይ ምን?

91 ተ16፡ ሁለትና ከዛ በላይ ዐ/.ነገር ይይዛል ፡፡

92 መ/ርት፡ ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግስ

(ም 2፣ክ ሠ፣ከ/ጊዜ2፣አ 5)

ከላይ በቀረበው የጥያቄና መልስ ልውውጥ እንደሚታየው ተማሪ አስራ ስድስት


ዐ.ነገሩን ተራ በማለት ስትመድብ መምህርቷ ለምን? የሚል ግብረመልስ ሰጥተው
ምክንያቷን እንድትገልጽ አነሳስተዋታል፡፡ተማሪ አስራስድስት ምክንያቱን ከዐ.ነገር
ብዛት ጋር አያይዛ ሁለትና ከዛ በላይ የያዘ ሲሆን የሚል ግብረመልስ ስትሰጥ
ሀሳቡ ግልጽ ስላልነበር መምህርቷ ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን ምን? የሚል
ግብረመልስ ሲሰጡ በድጋሚ ተማሪዋም ሁለትና ከዛ በላይ ዐ.ነገር ይይዛል የሚል
መልስ ሠጥታታለች፡፡ መምህርቷም በመጨረሻ ተማሪዋ ለሰጠችው ግብረመልስ
ይበልጥ ግልጽ የሚያደርግላቸው ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግስ የሚል ትክክለኛ ቃል
የያዘ ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡

ምሳሌ 54

103 ተ12፡ እንስራ ነው የሚለው ሀገራችንን ተባብረን እንስራ አሉ

ጠቅላይ ሚኒስቴራችን እእእ…አለሚቱ እንስራውን

ሰበረችው ፡፡

104 መ/ርት፡ እሺ በመጀመሪያ ዐ›ነገሩ ማንኛው ነው የጠበቀው?

እ…ሆሄ….ፊደል

105 ተ12፡ እንስራ

106 መ/ርት፡ እኮ ማንኛው?

107 ተ12፡ ራ…..ስ

76
108 መ/ርት፡ ራ…ስ እስቲ ሌላስ እስቲ እሷ በሰራችው ዐ.ነገር

ጠባቂው ድምጽ የትኛው ነው ?ዐ.ነገሩ ምን ነበር

ያልሺው?

109 ተ12፡ ሀገራችንን ተባብረን እንስራ

110 መ/ርት፡ ሀገራችንን ተባብረን እንስራ የጠበቀው ሆሄ ማነው?እዚህ

ጋር...ስ...ን ናት፡፡ ን ናት፡፡ ቀጣይ ዐ.ነገር

111 ተ3፡ አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው ፡፡

112 መ/ርት፡ አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው፡፡እዚህ ጋር ጠባቂዋ

ድምጽ “ስ” ሳትሆን “ን” ናት፡

(ም 1፣ክ ሠ፣ ክ/ጊዜ 1፣አ 4)

በምሳሌ ሀምሳአራት እንደሚታየው ተማሪ አስራ ሁለት በመሰረተችው ዐ.ነገር


ዐ.ነገሩን ስታነብ የጠበቀውን ድምጽ እንድትናገር መምህርቷ ሲጠየቋት ተማሪዋ
ቃሉን በመጥራት ግብረመልስ ሠጥታለች፡፡መምህርቷ እንደገና ዐ.ነገሩን
እንድትናገር በመጠየቅ የጠበቀው ሆሄን በድጋሚ እንድትገልጽ ጠይቀዋታል፡፡ተማሪ
አስራ ሁለትም ራ…ስ የሚሉ ሆሄያት በመጥራት ግብረመልስ ሠጥታለች፡፡
መምህርቷም ትክክል እንዳልሆነች በመጠቆም የጠበቀችው ሆሄ «ን» ናት የሚል
ግብረመልስ ሠጥተዋል፡፡ምሳሌ ሀምሳአራት እንደሚያሳየው በቃላት ንበት
የተግባቦት ችግር ሲያጋጥም ወደ ግልጽነት የሚወስድ ግብረመልስ ያስፈልጋል፡፡
መምህርቷ ደጋግመው መጠየቃቸው ተግባቦቱ እንዳይቋረጥ ያደረገ ሲሆን
የጠበቀውንም ድምፅ ለመረዳት አስችሏል፡፡

4.3.2.4. የጠፉ ሀሳቦችን የሚገልጹ ዲስኩር አመልካች ቃላት


ተማሪዎች ለጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ወይም ሀሳባቸውን ሲገልጹ የጠፋባቸውን
ቃላት እንትን….እእእ…የመሳሰሉትን ቃላት ይጠቀማሉ ፡፡

ምሳሌ 55

10 መ/ርት፡ ዐ.ነገር በውስጡ የሚይዛቸው የግስ ወይም

የማሰሪያ አንቀጽ መጠን በስንት ይከፈላል?

77
11 ተ3፡ በሁለት

12 መ/ርት፡ እጅ አውጥታችሁ መልሱ እህ…

13 ተ3፡ በሁለት

14 መ/ርት፡ በሁለት ነው ምንና ምን?

15 ተ14፡ ስማዊ ሀረግና እንትን … ቅጽላዊ ሀረግ

(ም 3፣ክ ሠ፣ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

በምሳሌ ሀምሳአምስት እንደሚታየው ተማሪ አራት ዐ.ነገሩን ዓይነት ሲከፋፍል


ስማዊ ሀረግ ቀጥሎ “እንትን” የሚል ግብረመልስ ሰጥቷል፡፡ይህም የጠፋበት ክፍል
ለመተካት እንደሆነ ለመረዳት ይቻላል፡፡ይህን ቃል መጠቀሙ የጠፋበትን ሀረግ
እስኪያስታውስ ሀረጉን ተክቶ ተግባቦቱ እንዲቀጥል ረድቷል፡፡

ምሳሌ 56

04 መ/ርት፡ ዐ.ነገርን ወይም ስማዊ ሀረግንና ቅጽላዊ ሀረግን በመመስረት

ዐ.ነገርን እንደመሰረትን አይተናል፡፡ሌላስ? ሌላስ ? ምን

ሰርተን ነበርን?ሌላ… እህ .ሌላስ

05 ተ3፡ ዐ.ነገርን…እእ….ቅጽል…እእ የአንድን ስም ቃል ስማዊ ሀረግና

ቅጽላዊ ሀረጉን አወጣን ካወጣን በኋላ ደግሞ በስማዊ ሀረግና

እና ቅጽላዊ ሀረግ ዐ.ነገርን ሰራን፡፡

(ም 3፣ክፍል ሠ፣ ክ/ጊዜ 3፣አ 6)

በምሳሌ ሀምሳስድስት እንደሚታየው ተማሪ ሶስት በባለፈው ክፍለጊዜ የተማሩትን


እንድታስታውስ ስትጠይቅ ዐ.ነገርን ካለች በኋላ እእ የሚል ቃል
ተጠቅማልች፡፡ቀጥሎ ያለውን ቃል ከመጥራቷ በፊት ሀሳቡ ስለጠፋባት ያንን
ግብረመልስ እንደፈታ መውሰጃ ተጠቅማበታለች፡፡ቅጽል ካለች በኋላም መልሳ “እእ”
የሚለውን ተጠቅማለች፡፡ቀጥሎ የምትናገረውን ሀሳብ እንድታሰላስል እድል
ሰጥቷታል፡፡በመሆኑም ሁለቱም ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት ተማሪዎች የሚገልጹት
ሀሳብ ሲጠፋባቸው «እንትን፣እእ» የሚሉ ግብረመልሶች ይሰጣሉ፤እነዚህ

78
ግብረመልሶች የጠፋባቸውን ሀሳቦች ለመተካት ወይም የማሰላሰያ እድል ለማግኘት
ያግዛቸዋል ፡፡

4.4. የጥናቱ ግኝት ማብራሪያ


በዚህ ክፍል በምልከታ ወቅት በመቅረፀምስል የተሰበሰበውን መረጃ መስረት በማድረግ
ትንተና ተከናውኖ በመሪ ጥያቄዎች መነሻነት ቀርቧል፡፡በመረጃ ትንተናው የተገኘው
ውጤት ከቀደምት ጥናቶች ጋር ያለውን አንድነትና ልዩነት ለማሳየት ተሞክሯል፡፡

4.4.1. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለ ጊዜያት በመምህራኑና በተማሪዎች


የሚቀርቡ የቃል ግብረ መልስ ዓይነቶች
በምዕራፍ ሁለት እንደገለፀው Cole & Lorna (1994) Richard & Lockert (1996)
Anne (2013) በክፍል ውስጥ አሉታዊና አዎንታዊ ግብረመልስ እንደሚሰጥ
ገልፀዋል፡፡በሌላ መልኩ የማስተካከያ፣ገምጋሚና ገላጭ የሚባሉ ግብረመልስ አይነቶች
እንደሚጠቀሙ Namara (1999) ፣ Jhon (2007) ይገልፃሉ፡፡Richard &
lockert(1996፣ Anne (2013)፣Cole & Lorna (1994) ገለፃ አዎንታዊ ግብረመልስ
ተማሪዎች ትክክለኛ ተግባር ለመፈፀማቸው ማረጋገጫ ነው፡፡በዚህም ጥናት
እንደታየው ተማሪዎች ትክክለኛ ሀረግ ሲመሰርቱ፣ትክክለኛ ገለፃ ሲጠቀሙ፣ትክክለኛ
ነው፣አዎ፣ጥሩ ነው የሚለው ቃላት ተጠቅመው መምህራን የተማሪዎች ትክክለኛነት
ይገልፃሉ፡፡

Richard & lockert(1996፣ Anne (2013)፣ Cole & Lorna (1994) እንደጠቆሙት
መምህራን ብዙ ጊዜ የሚጠቀሙት አሉታዊውን እንደሆነ እና አዎንታዊ ግብረመልስን
እንብዛም እንደማይጠቀሙ ጠቁመዋል፡፡ምክንያቱም ተማሪዎች የሚሻሻሉት
ስህተታቸው ሲነገራቸው ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጥናት ግኝት
እንደታየው መምህራን በቀጥታ አሉታዊቀውን ከመጠቀም ይልቅ ወደ አዎንታዊ
ግብረመልስ እንደሚያደሉ ነው፡፡አይዞሽ ፣እንደገና መስርቺ ፣ቀጥይ (ቀጥል) እያሉ
በማበረታታት ተማሪዎችን በቀጥታ ስህተት መሆናቸውን ከማሳየት ይልቅ እንዲነሳሱ
ያደርጋሉ፡፡በርግጥ በዚህ ጥናት ግኝትም ትክክል አይደለም፣አይደለም የሚሉ አሉታዊ
ግብረመልሶች ተስተውለዋል፡፡ነገርግን አብዛኛውን ጊዜ በክፍል ውስጥ የተገበሩት
ሁለቱም ናቸው፡፡

79
የማስተካከያ የቃል ግብረመልስ Namara (1999) እንደሚሉት ስህተታቸው በቀጥታ
ይጠቀሙበታል ነው፡፡በዚህ ጥናት ሀረግ እና ዐ.ነገር ሲመሰረቱ ስህተታቸው ሲጠቁም
ተስተውለዋል፡፡እንደ Namara (1999) ይህ ግብረመልስ በብዛት የሚያገለግለው
መመሪያዎችን ለማሳየት ነው ቢሉም በዚህ ጥናት ግኝት ግን ይበልጥ የተስተዋለው
በሀረግ ምስረታ ወቅት ነው ፡፡ገምጋሚ ግብረመልስ Namara (1999) ፣Jhon (2007)
እንደተጠቆሙት ለተማሪዎች መሻሻላቸውን የሚያሳዮ ጥቅል አስተያየት የሚሰጡበት
መሆኑን ገልጸዋል፡፡በዚህ ጥናት ውጤት ይበልጥ የታየው መምህራን ተማሪዎቻቸውን
የባለፈውን ክፍለጊዜ የትምህርት ይዘት ምንያህል እንደሚያስታውሱት ለመለካት ብቻ
የሚቀርብ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ሃይማኖት (2011)፣ዳዊት (2008)፣አስካል (2001) እና
እታለማሁ (2006) በጥናታቸው መምህራን ብዙ ጊዜ በክፍል ውስጥ የሚጠቀሙት
ግብረመልስ ገምጋሚ እንደሆነ ጠቁመዋል፤በዚህ ጥናት ግኝት ግን ይህ ግብረመልስ
እንብዛም ባለመስተዋሉ ከነሃይማኖት ጥናት ጋር ይቃረናል፡፡

Cole & Lorna (1994) ውስጣዊና ውጪዊ ግብረመልስ፣የሚቀርበው በዝርዝር


የተማሪዎችን ትክክለኛነትና ስህተት ነጣጥሎ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚያሳይ
ሲሆን በዚህ ጥናት እንደታየው አባዛኛውን ጊዜ የሚሰጧቸው ግብረመልስ ከፊል
የሚባለውን ነው፡፡ በዚህ ጥናት በብዛት «ትክክል አይደለም» ወይም «ትክክል ነው»
በማለት ይገልጻሉ እንጂ ስለ ትክክልነቱም ሆነ ስለ ስህተትነቱ ጥልቅ ማብራሪያ
ሲሰጡ አልታዩም፡፡ Cole & Lorna (1994) እንደሚሉት በተደጋጋሚ ባይሆንም
አንዳንድ ጊዜ ሙሉ ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡ Cole & Lorna (1994) ቅርፃዊ
ግብረመልስ ለሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች እንጂ ለአፈፈት ተማሪዎች አያስፈልግም፤
ምክንያቱም አፈፈቶች የቅርፅ ስህተት አይፈፅሙም የሚል ድምዳሜ ላይ
ደርሰዋል፤ይህም ከዚህ ጥናት ውጤት ጋር ፍጹም ይቃረናል፡፡ ፋንታዬ (1998) ም
በጥናታቸው ያመለከቱ ሲሆን በዚህም ጥናት ተማሪዎች ሀሳባቸውን በትክክል
እንዲገልጹና ሰዋሠዋዊ ስርዓትን የተመለከቱ ቅርፃዊ ግብረመልሶችን እንደሚሰጡ
ታይቷል፡፡ነገርግን Jenifer (2017) ሰዋሠው በሆኑ ጉዳዮች እንጂ በሌሎች ተግባራት
ላይ ግብረመልስ እንደማይሰጥ በጥናታቸው ከገለጹት ጋር ይቃረናል፡፡ Jenifer
(2017) ቅርፃዊ ግብረመልስ የሚያስፈልገው ለሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች ነው እንጂ
ለአፈፈቶች አይደለም በማለት ጠቁመዋል፡፡

80
4.4.2 የቃል ግብረ መልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች
በዚህ ጥናት ውጤት መሰረት የቃል ግብረመልስ የሚቀርብባቸው ስልቶች እንደገና
ማሰራት ፣ግልፅ እርማት መስጠት ፣መድገምና ማነሳሳት ናቸው፡፡ይህም John
(2007) ጋር ይመሳሰላል፡፡ተማሪዎች የሰሩትን ስህተት ለመቀነስ የሚል ሀሳብ
John (2007) ገልፀዋል፡፡በዚህ ጥናትም ተማሪዎች ስህተት ሲሰሩ መምህራን
እንደገና ሲያሰሩ ይታያል፡፡ John (2007) ግልፅ ርማት መስጠትም ምን ዓይነት
ስህተት እንደሰሩ የሚጠቆሙበትና ትክክል እንዳልሆኑ የሚነገርበት ነው፡፡ስለዚህ
ይህ ጥናት John (2007) ካቀረቡት ሀሳብ ጋር በመጠኑ ቢመሳሰልም በጥናቱ
ውጤት መምህራን በብዛት ስህተት እንደሆኑ ይነግሯቸዋል እንጂ ለምን ስህተት
እንደሆኑ አይነግሯቸውም፡፡መዋቀሩን በትክክል እንዲረዱ ለማድረግ በመጠኑ
በሀረግ ምስረታ ወቅት ለምን ስህተት እንደሆኑ ይጠቁሟቸዋል፡፡በሌላ ጉዳይ ግን
ትክክል አይደለም አይደለችም ይላሉ እንጂ ስህተትነቱ ለምን እንደሆነ ግልፅ የሆነ
ማብራሪያ አይሰጡም፡፡በመድገም ስልት John (2007) ጋር የዚህ ጥናት ውጤት
የሚመሳሰል ሲሆን ስህተት የሆኑ ቃላትና ዐ.ነገሮችን በመድገም
ይነግራቸዋል፡፡በዚህ ጥናትም መምህራን ቃሉን ደግመው በመጥራት ስህተትነቱን
ያመለክታሉ፡፡

John (2007) ፣ Jenifer (2017) የማነሳሳት ስልት አስፈላጊ እንደሆነና ተማሪዎች


የማነሳሻ ግብረመልስ ሲሰጣቸው ይበልጥ ይሞክራሉ የሚል ድምዳሜ
አስቀምጠዋል፡፡የዚህ ጥናት ውጤትም እንደሚያመለክተው የማነሳሻን ግብረመልስ
መምህራን ሲከናውኑት ድጋሚ የሚሞክሩ ተማሪዎች አሉ፡፡ቀጥል፣ ቀጥይ፣ ሞክር
ቢባሉም ዝም የሚሉም አሉ፡፡ ስለዚህ ማነሳሳቱ ሊሰራም ላይሰራም እንደሚችል
ይህ ጥናት ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም «እህ፣እ» የሚሉ ዲስኩር ቃላትም
መምህራን ለመልስ እንደሚያነሳሷቸው ያመለክታል፡፡ነገርግን ፋንታዬ(1998)
ግብረመልሶቹ የሚቀርቡት በተገቢው ጊዜ እንደማይቀርቡ በጥናታቸው ቢገልፁም
በዚህ ጥናት ግኝት ግን የቃል ግብረመልሶቹ ለተማሪዎቹ የሚሰጡት በትክክለኛው
ጊዜ ነው፡፡በመሆኑም የዚህ ጥናት ግኝት ከፋንታዬ ጥናት ጋር ይቀረናል፡፡

81
4.4.3. በአማርኛ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚቀርበው የቃል ግብረመልስ ያለው
ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋጽኦ
የቃል ግብረመልስ ጠቀሜታ እንዳለው Anne (2013) ፣ Cole & Lorna (1994)
Richards & Lockhart (1996) ፣ፋንታዬ (1998) በጥቅሉ ገልፃሉ፡፡ እንደምሁራኑ
ገለፃ ተማሪዎች መልሶችን እንዲያፈልቁ እንዲነሳሱ፣ትኩረት እንዲሰጡ…ወዘተ
በማለት የግብረመልስን አስተዋጽኦ ገልጸዋል፡፡በዚህ ጥናት ውጤት ግን ንዑሳን
ሀሳቦች ተዘጋጅቶላቸው ቀርበዋል፡፡አስተዋፅኦ መኖሩን ማመልከቻቸው ከዚህ ጥናት
ጋር ይመሳሰላሉ፡፡በዚህ ጥናትም የግብረ መልስን አስተዋጽኦ ትምህርታዊና
ተግባቦታዊ በሚል ተከፍለው ውጤቱን በትንተናው ለማሳየት ተሞክሯል፡፡የተገኘው
ውጤትም ትምህርታዊ አስተዋጾዎቹ የቃል ክፍሎችን እንዲለዩ ማድረግ፣ሀረጋትን
በትክክል እንዲመሰርቱ ማድረግ፣የቃላት ንበት የሚያስከትለውን የትርጉም ለውጥ
ማስገንዘብ ስርዓተ ነጥቦችን በትክክል እንዲጠቀሙ ማድረግ፣ ዐ.ነገርን በትክክል
እንዲያዋቅሩና በሰዋሰዋዊ ቅርፅ እንዲመደቡ እንዲለዩና ስያሜያቸውን የሚያደርጉ
የቃል ግብረ መልሶችን ተሠጥተዋል፡፡ይህ ግን በጥናቶችና በምሁራኑ ሀሳብ ላይ
አልተመለከቱም፡፡

ተግባቦታዊ አስተዋጽኦው ደግሞ በክፍል ውስጥ የተግባቦት ችግር ሊያጋጥሟቸው


እነዚያን ለመቅረፍ የሚሰጡት ግብረመልስ እንደሆነ የጥናቱ ውጤት
ያሳያል፡፡እነዚህም የተባለውን በትክክል ካላዳመጡት “እ” የሚል ግብረመልስ
በመስጠት እንዲደገምላቸው በማድረግ ያረጋግጣሉ፡፡እንዲህ ነው ያልከው፣ያልሽው
በማለትም ይጠይቁና ያረጋግጣሉ፡፡ቃላትን በትክክል ተማሪዎች ካልጠሩም
የተግባቦቱን ችግር ለመቅረፍ ሲሉ ተማሪዎቹ አሳስተው የጠሩትን ቃል አስተካክለው
በመጥራት ግብረመልስ ይሰጣሉ፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ለምን? ምን?
ማንኛው? ማነው? በማለት ግብረመልስ እየሰጡ ተማሪዎች ሀሳባቸውን
እንዲያሰፉ፣ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ያደርጋሉ፡፡ የሚል ውጤት ላይ
ደርሷል፡፡ «እንትን፣እእ»የሚሉ ዲስኩር ቃላትን በመጠቀም የጠፉላቸውን ሀሳቦች
ተክተው ግብረመልስ በመስጠት የተግባቦት ችግር እንዳይከሰት እንደሚያደርጉ
የመረጃ ትንተናው አመላክቷል፡፡

82
ምዕራፍ አምስት፣የጥናቱ ማጠቃለያና አስተያየት

5.1. ማጠቃለያ
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍለጊዜያት የሚሰጡትን የቃል
ግብረ መልሶች ዓይነት፣ የአቀራረብ ስልትና ትምህርታዊና ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ
መመርመር ነው፡፡ የትንተናውን ግኝት የጥናቱን ዝርዝር ዓላማዎች መሰረት
በማድረግ እንደሚከተለው ማጠቃለያ ላይ ደረሷል፡፡

የመጀመሪያው ዝርዝር ዓላማ መምህራንና ተማሪዎች በአማርኛ ትምህርት


ክፍለጊዜያት ምን ዓይነት ግብረመልስ እንደሚሰጡ መለየት ሲሆን የዚህ ጥናት
ውጤት እንዳመለከተው የሚቀርቡት የቃል ግብረመልሶች በዓይነታቸው አወንታዊ
አሉታዊ፣ የማስተካከያ፣ ገምጋሚ ይዘታዊና ቅርጻዊ ተብለው የሚመደቡ ናቸው፡፡
ከነዚህ ውስጥ መምህራን የሚጠቀሙት አወንታዊ፣ አሉታዊ፣ የማስተካከያና ቅርፃዊ
የሚባሉትን ሲሆን ለገምጋሚና ለይዘታዊ ግብረመልሶች ትኩረት እንደማይሰጡ
አሳይቷል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው አወንታዊ ግብረመልስን መምህራን
የተማሪዎቻቸውን ጠንካራ ጎን ለማሳየት የሚጠቀሙበት ሲሆን ጎበዝ፣ በጣምጥሩ
የሚሉ ግብረመልሶችን በመጠቀም ተማሪዎች ጥሩ ሙከራ ማድረጋቸውንና
ትክክለኛ መልስ መመለሳቸውን ያበረታቱበታል፡፡

አሉታዊ ግብረመልስን ደግሞ ተማሪዎች ስህተት መሆናቸውን ለማሳየት


የሚጠቀሙበት ሲሆን «ትክክል አይደለም» ወይም «አይደለም» የሚሉ ቃላትን
በመጠቀም የተማሪዎችን ስህተት በቀጥታ ይጠቁማሉ፡፡ በሀረግና በዐ.ነገር ምስረታ
ወቅት የተሳሳቱትን መዋቅር ለማሳየት የማስተካከያ ግብረመልስ የሚጠቀሙ ሲሆን፣
በባለፈው ክፍለጊዜ የተማሯቸውን ይዘቶች ተማሪዎቻቸው እንዲያስታውሱ
ለማድረግ መምህራን ገምጋሚ ግብረመልስን ይጠቀማሉ፡፡ ሌላው የሚጠቀሙት
የግብረመልስ ዓይነት ቅርፃዊ ግብረመልስን ሲሆን መምህራን የቋንቋውን ሰዋሠዋዊ
ስርዓት ለተማሪዎች ለማሳየት የሚጠቀሙት ግብረመልስ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ይዘታዊ ግብረመልስን የሚጠቀሙ ሲሆን ተማሪዎች ሀሳባቸው ትርጉም ባለው
መንገድ መግለፃቸውን ለማረጋገጥ ይጠቀሙበታል፡፡

83
ሁለተኛው ዝርዝር ዓላማ የቃል ግብረመልሶቹ የሚቀርቡባቸውን ስልቶች መለየት
ሲሆን የቃል ግብረመልሶቹ ሲቀረቡ እንደገና ማሰራት፣ ግልጽ ርማት መስጠት
፣መድገምና ማነሳሳት የሚሉ ስልቶችን ይጠቀማሉ፡፡ የጥናቱ ውጤት
እንዳመለከተው የተማሪዎችን ስህተት ለመቀነስ መምህራን እንደገና ማሰራትን
የሚጠቀሙ ሲሆን፣ተማሪዎቻቸው ስህተት መሆናቸውን በቀጥታ ለመንገርና
ስህተታቸውም ለማስተካከል ግልፅ ርማት መስጠት የሚለውን ስልት ይተገብራሉ፡፡
የመድገም ስልትን በመጠቀም ደግሞ ተማሪዎች የተናገሩትን ስህተት የሆነ ቃል
ወይም ዐ.ነገር መምህራን በመድገም የተማሪዎችን ስህተት እንደሚጠቁሙበት
ውጤቱ አመላክቷል፡፡ የማነሳሳት ስልትን ደግሞ መምህራን ተማሪዎቻቸውን
የውስጣቸውን እንዲገልፁ ወይም ሙከራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ሲጠቀሙበት
ተስተውሏል፡፡

ሶስተኛው ዝርዝር ዓላማ የቃል ግብረመልሱ ምን ዓይነት ምን ምን ትምህርታዊና


ተግባቦታዊ ፋይዳ እንዳለው መመርመር ሲሆን የቃል ግብረመልሶቹ ትምህርታዊና
ተግባቦታዊ አስተዋፅኦ ያላቸው ሲሆን የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው ትምህርታዊ
አስተዋፅኦ የቃል ክፍሎችን፣ሀረጋትና ዐ.ነገርን በትክክል እንዲለዩና እንዲያዋቅሩ
ማድረግ፣ የቃላት ንበት የሚያስከትለውን ለውጥ ማሳየትና ስነ-ፅሁፋዊ ስያሜዎችን
በትክክል መለየት የሚሉት ናቸው፡፡ ይህም የቋንቋው መዋቅር እና ስያሜዎችን
በትክክል እንዲረዱ ያስቻለ ትምህርታዊ ፋይዳ አስገኝቷል፡፡

በተግባቦታዊ ፋይዳው ደግሞ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን የመረዳት ችግር


ሲያጋጥማቸው ተግባቦቱ እንዳይደናቀፍ የሚያስቀጥሉበት ሲሆን የቃል
ግብረመልሱን የሚለዋወጡት የተባለውን በትክክል ባለማዳመጥ፣ቃላትን በትክክል
ባለመጥራት፣ ተጨማሪ ማብራሪያ መሻት የሚሉ ተግባቦቱ እንዲቀጥል የሚያደርጉ
የቃል ግብረመልሶችን ይለዋወጣሉ፡፡ ነገርግን መምህራን ለሆሄያት ግድፈት
ስህተቶች ትኩረት አይሰጡም፡፡ ግብረመልሶቹ ስህተቶችን ለማስተካከል፣
ተማሪዎችን ለማበረታታትና ለማነሳሳት እንዲሁም ግልፅነትን ለመፍጠር በሚሉት
ምክንያቶች የተነሳ ይቀርባሉ፡፡

84
5.2. አስተያየት
የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
ክፍለጊዜያት የተሰጠው የቃል ግብረመልስ ጠንካራና ደካማ ጎን እንዳለው
ጠቁሟል፡፡ይህን ውጤት መሰረት በማድረግ ለባለድርሻ አካላት አስተያየት
ለመጠቆም ተሞክሯል፡፡

ለአማርኛ ቋንቋ መምህራን፡- የጥናቱ ዉጤት እንዳመለከተው በክፍል ዉስጥ


የሚቀርቡ የቃል ግብረ መልሶች አወንታዊ፣ አሉታዊ፣ የማስተካከያ፣ ገምጋሚ፣
ይዘታዊና ቅርፃዊ መሆኑ ተመልክተዋል፡፡ እነዚህ ግብረመልሶች የቋንቋ ትምህርቱን
ለማሳካት አስተዋፅኦ አላቸው፡፡ ነገር ግን መምህራን የሚያተኩሩት ቅርፃዊ ለሆነው
ሲሆን ሌሎቹም የግብረመልስ ዓይነቶች በትክክል ቢሰጡ የተሻለ ይሆናል፡፡
ገምጋሚ ግብረመልሶችን የቀደመውን የትምህርት ይዘት ለመከለስ ብቻ ሳይሆን
በእለቱ የተማሩትንም መረዳታቸውን ለመፈተሽ ቢጠቀሙበት የተሻለ ይሆናል፡፡
ስልቶቹም በክፍል ውስጥ ሲተገበሩ የመማር ማስተማር ክንውኑን የተሳካ
ስለሚያደርጉ ሁልጊዜም ቢተገበሩ መልካም ይሆናል፡፡ መምህራን ግልፅ ርማት
በሚሰጡበት ጊዜም ለተማሪዎች ስህተት ማብራሪያ ቢሠጡ የተሻለ ነው፡፡
በተጨማሪ ለተማሪዎችም እድል በመስጠት ርስበርስ እንዲተራረሙ ቢደረግ
መርምረው ስህተቶችን ቢያወጡ የቋንቋ መዋቅሮችን እንዲረዱ ያደርጋል፡፡
የፊደል ስህተቶችም የተግባቦት እንከን ስለሚሆኑ መምህራን ትኩረት ሰጥተው
የማስተካከያ ግብረመልስ ቢሰጡባቸው የተሻለ ይሆናል፡፡

ለመማሪያ መሣሪያ አዘጋጆች፡- የክፍል ውስጥ የቃል ግብረመልስ የቋንቋ


ትምህርቱን የሚያሳካ መሣሪያ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ተማሪዎችና
መምህራን ሊግባቡ የሚችሉት በግብረመልስ ሳቢያ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም
የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መሳሪያ አዘጋጆች ማለትም መፅሀፍትን፣መረሀ
ትምህርትን፣ መምሪያዎችን ወ.ዘ.ተ. ሲያዘጋጁና ተግባራትን ሲቀርጹ ተማሪዎችና
መምህራን የሚሳተፉበት፣ ለግብረመልስ ምቹ የሆኑ ሆነው ማዘጋጀት አለባቸው፡፡
ከገለጻ ይልቅ ለአፍልቆት የሚያነሳሱ ተግባራት መካተት አለባቸው፡፡

85
ለመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት፡- በመማሪያ ክፍል ውስጥ የቃል ግብረመልስ
ልውውጥ የሚኖረው ተማሪዎችና መምህራን በእኩል ደረጃ ሊያሳትፉ የሚችል
የማስተማሪያ ዘዴ ሲኖር ነው፡፡ ይህም ተማሪዎቹ በቋንቋ ትምህርት የመነሳሳት
ፍላጎት እንዲኖራቸውና መምህራኑን የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ ለመረዳትና
ፍላጎታቸውን ለማሟላት ያስችላል፡፡ በመሆኑም መምህራንን የሚያሠለጥኑ ተቋማት
የግብረመልስን ትምህርታዊና ተግባቦታዊ ፋይዳ ለመረዳት ስልጠናውን ከዚህ
አንፃር ቢያዘጋጁ የተሻለ ይሆናሉ፡፡

ለጥናት አድራጊዎች፡- ይህ ጥናት የተደረገው ትምህርታዊና ተግባቦታዊ ፋይዳውን


አጣምሮ ነው፡፡ ነገርግን ሁለቱንም በየዘርፋቸው በስፋት በተናጠል ቢጠኑ፣
ከአማርኛ አፈፈት ተማሪዎች ውጪ አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ
ተማሪዎች ትኩረት በማድረግ የክፍል ውስጥ የቃል ግብረመልስ ያለውን ፋይዳ
ለማሳየት የሚያስችል ጥናት ቢደረግ፣ የአማርኛ አፈፈቶች ላይም ቢሆን የክፍል
ውስጥ የቃል ግብረመልስ ያለውን ፋይዳ ለማስረዳት የሚያስችሉ ተጨማሪ ጥናቶች
ቢሰሩ መልካም ይሆናል፡፡

86
ዋቢ ፅሁፎች

ሀይማኖት ንጉሴ፡፡ (2011) ፡፡ «የድርሰት መልመጃዎች ላይ የሚሰጡ የቃልና

የፅሁፍ ግብረመልሶች ትንተና ፡፡» የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ

ትምህርት ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት ፡፡ደ/ብርሃን

ዩንቨርስቲ፣ (ያልታተመ)፡፡

አስካል ማናዬ፡፡ (2001)፡፡«ተማሪዎች ለሚፅፏቸው ድርሰቶች በመምህራን የሚሰጡ

ምላሾች የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማሻሻል ረገድ ያላቸው

ተፅዕኖ»፡፡ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ፣አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (ያልታተመ)፡፡

እታለማሁ ታዬ፡፡ (2006)፡፡«የ9ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በተማሪዎች

የጽሁፍ መለማመጃ ላይ የሚሰጡትን ጽሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ፍተሻ»፡፡ ድህረ

ምረቃ ት/ቤት፣ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (ያልታተመ)፡፡

ከበደ ይመር፡፡ (2009) ፡፡«የመማሪያ ክፍል የድርድር ዲስኩር መንስኤ፣ብልሃትና

መፍትሄ ትንተና»፡፡ በተግባራዊ ስነ ልሳን የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን

ማስተማር የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት፡፡አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ

(ያልታተመ)፡፡

ፋንታዬ በየነ፡፡ (1998) ፡፡ «የደ/ብርሃን ሀይለማርያም ማሞ መሰናዶ ት/ቤት

የአማርኛ መምህራን ቃላዊ ምጋቤ ምላሽ አሰጣጥ ስልቶች ፍተሻ፡፡» ለአርትስ

ማስተርስ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ቴስስ፡፡ አዲስአበባ ዩንቨርስቲ (ያልታተመ) ፡፡

ያለው እንዳወቀ፡፡ (2009) ፡፡ የምርምርመሠረታዊ መርሆችና አተገባበር፡፡ ባህር

ዳር፣ ተፈሪ ስዩም ማተሚያ ድርጅት፡፡

ዳዊት ፍሬህይወት፡፡ (2008)፡፡« የመምህር ተማሪ ምክክርና የመምህር የጽሁፍ

ምጋቤምላሽ በተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ላይ ያላቸው ተጽዕኖ፡፡» በተግባራዊ

ስነልሳን የኢትዮጽያ ቋንቋዎች ማስተማር መርሃግብር ለዶክትሬት ዲግሪ

ማሟያ የተከናወነ ጥናት፡፡አዲስአበባ ዩንቨርስቲ (ያልታተመ)፡፡

87
Anne, D.(2013).Giving corrective oral feed back in biolingual contect.study

In second language acquistion.27,(4);79-103.

Barbara, M.(2002) .Feedback . washington; washington state university.

Cole, .P.G & Lorena, K.S.C (1994).Teaching principle & practice

.australia printce Hall Australia private Ltd.

Creswell, J. (2014). Research design qualitative quantitative e & mixed

methods. Unitedstate of America; sage publications.


Ellis, R.(2009).Corrective feedback & teacher development. University of

California.

Ferris, D. (1998).The uitimate giude to writing adissertation.https// research

Metdlogy net e- book.

Gurrero, M. & Villamil,.(2000). Activating the ZPD: mutual scaffolding in

L2 peer revision. Modern language journal 84(2) 51-68.


Jenifer, L.(2017) The effect of oral feed back in class room under

graduate student: London; Penguin.


John, H. & Helen, T.(2007). «The power of feedback». review of

educational Research.

John, H. & Helen,T.(2007).Visible learning & feedback. Washington.

American Phychoiogical Association.TESOL 20(6);72-89.

Keh, C.(1990). Feedback in writing precess model & methods for

impiementation.ELT;Jornal 44(4) 290.


Kathleen, M.(2017). «Summary & analysis of oral corrective feedback

Research».International Literacy Association.

Lorna, M. (2008).«Feedback review of educational research» .

Lyster, & saito,.(2010). Oral feed back in class room SLA. cambridge

university press.

88
Macdonald, R.(1991).« Developmental students processing of teacher

feedback in oral practice.» Review of research education.London;

Longman.

Michael, H.(2011). The role of implict negative feedback.California

university.

Namara, E.(1999).Positive pupil management & motivation. London;

David Fulton Publisher.

Nunan, .D (1996). The self direct teacher practice: Cambridge university

press.

Nsw government.(2015).Types of feedback .phase 3; vol 32. South africa

;published by Nsw public school.

Richard, J. & Lockart, C.(1996). Reflecting theory in second language

class rooms; Cambrige.


Rollinson, P. (2005). Using peers feedback in the ESL writing class

ELT; jornal 59(1); 174-183.

Susan, M.(2008). How to give effective feedback to your students .Virginia.

Ur, p. (1996).A Course in teacher practice & theory. Cambridge.

Wajnryb,.R. (1992).Classroom observation task a resource book for

language teachers & teaching. Cambridge: Cambridge


university press.

Wolf, p.(2010). Brain matters translating research into ciass room

practice. USA; Ascp published.

89
አባሪዎች

አባሪ አንድ

ምዝግብ መረጃ አንድ


ክፍል ሀ
የተማሪ ቁጥር 43
ጊዜ፡- 40፡ ደቂቃ
የት/ት ርዕስ ፡- የዓ.ነገር ክፍሎችና ዓይነቶች
መምህርቷ የትምህርት ዓይነቱንና የእለቱን ሁለት የትምህርት ርዕሶች በጥቁር ሰሌዳ ላይ
ፃፉ፡፡

01 መ/ርት፡ በ142 ላይ ያለውን ማስታወሻ ትንሽ ማብራሪያ ልስጥና የክፍልስራ


እሰጣችኋለሁ፡፡መፅሀፋችሁን 142 ላይ ታወጣላችሁ፡፡ ገጽ 142 ላይ ያለውን ማስታወሻ
በሁለት መልኩ ነው የምናየው፡፡ የዓ.ነገር ክፍሎችና የዓ.ነገር አይነቶች ብለን
እንከፍላቸዋለን፡፡ የዓ.ነገሮች ክፍሎች ስንል በአንድ ዓ.ነገር ውስጥ ያሉትን ክፍሎች ማለት
ነው፡፡ እነሱም ሁለት ናቸው፡፡ የስማዊ ሀረግ ክፍልና የግሳዊ ሀረግ ክፍል ብለን በስንት
እንከፍላቸዋለን? በሁለት የስማዊ ሀረግ ክፍል የምንለው ከዓ.ነገሩ መጀመሪያ እስከ ዓ.ነገሩ
ባለቤት ድረስ ያለውን ምን ብለን እንጠራዋለን? የዓ.ነገሩ የስማዊ ሀረግ ክፍል እንለዋለን፡፡
ለምሳሌ፡- የአበበ በሬ ትናንት ታረደ፡፡ የሚል አንድ ዓ.ነገር ብንመሰርት በዚህ ዓ.ነገር
ውስጥ የባለቤት ክፍልና ማሰሪያ አንቀጽ ክፍል ወይም ደግሞ የግሳዊ ሀረግ ክፍል ብለን
የምንለው ነገር አለ፡፡ መጀመሪያ የባለቤት ክፍል ወይም የስማዊ ሀረግ ክፍሉን ለማወቅ
ምኑን እንፈልጋለን? ባለቤቱን እንፈልጋለን፡፡ የዓ.ነገሩ ባለቤት ፡፡ የዓ.ነገሩን ባለቤት
ለመፈለግ ደግሞ ግሱን ይዘን ምን የሚል ጥያቄ እንጠይቃለን? “ማ” የሚል ጥያቄ
እንጠይቃለን፡፡ የዓ.ነገራችን ማሰሪያ አንቀጽ ማነው? ታረደ፡፡ ማነው የታረደው?

ተጋ ፡ በሬው

መ/ርት ፡ በሬው፡፡ ስለዚህ የዓ.ነገራችን ባለቤት ማነው?

ተጋ ፡ በሬው

መ/ርት ፡ ከዓ.ነገሩ መጀመሪያ እስከ ዓ.ነገሩ ባለቤት ድረስ ያለውን ምናዊ ሀረግ
እንለዋለን? ስማዊ ሀረግ እንለዋለን፡፡ ከዓ.ነገሩ ባለቤት ቀጥሎ እስከ ዓ.ነገሩ መጨረሻ
ያለውን ደግሞ ምን እንለዋለን? ግሳዊ ሀረግ ፡፡ ስለዚህ በአንድ ዓ.ነገር ውስጥ ሁለት
ክፍሎች አሉ፡፡ የስማዊ ሀረግ ክፍልና የግሳዊ ሀረግ ክፍል ብለን እንላለን ማለት
ነው፡፡የዓ.ነገር አይነቶች ስንል ደግሞ በስንት ነው የሚከፈሉት?

ተጋ ፡ በሁለት

መ/ርት ፡ በሁለት ተራ ዓ.ነገርና ውስብስብ ብለን በሁለት እንከፍላቸዋለን፡ዓ.ነገሮቹን ተራ


ነገር እና ውስብስብ ዓ.ነገር ለማለት የዓ.ነገሩ መርዘም ማጠር የቃላት ብዛት ከመስፈርት

90
ውስጥ አይገባም፡፡ተራና ውስብስብ ዓ.ነገር ለማለት ዋናው መስፈርታችን በዓ.ነገር ውስጥ
ያለው የግስ ብዛት ነው፡፡በዐ.ነገር ውስጥ ያለው የግስ ብዛት አንድ ብቻ ከሆነ የዓ.ነገር
አይነቱን ምን እንለዋለን? ተራ እንላለን? ነገር ግን በዓ.ነገራችን ውስጥ ያለው የግስ ብዛት
ሁለትና በላይ ከሆነ ደግሞ የዓ.ነገር አይነቱን ምን እንላለን?ውስብስብ ለምሳሌ፡-ወንድሜ
ከአዲስ አበባ በመኪና መጣ፡፡ የሚል አንድ ዓ.ነገር ብንመሰርትና ልጁ ወድቆ ተሰበረ፡፡
የሚል ሌላ ዓ.ነገር ብንመሰርት እነዚህ ሁለት ዓ.ነገሮች ስንመለከታቸው ረጅምና አጭር
ይመስሉናል፡፡ያ ማለት ረጅም ተራ አጭር ውስብሰብ ፣አጭሩ ተራ፣ረጅሙ ውስብሰብ ብለን
መወሰን አንችልም፡፡ተራና ውስብሰብ ስለመሆኑ እና ለመወሰን በዓ.ነገር ውስጥ ያለውን ምን
እንፈልጋለን? የግስ ብዛት እንፈልጋለን፡፡ ወንድሜ ምንድን ነው የቃል ክፍሉ ?

ተጋ ፡ ስም

03 መ/ርት ፡ ስም አዲስ አበባ

04 መተ ፡ ስም

05 መ/ርት ፡ በመኪና ምንድንነው?

06 መተ ፡ ስም

07 መ/ርት ፡መጣ ምንድን ነው?

08 መተ ፡ ግስ

09 መ/ርት ፡ስለዚህ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ ስንት የግስ ብዛት አለ?

10 መተ ፡ አንድ

11 መ/ርት ፡ አንድ የግስ ብዛት ካለ ደግሞ የዓ.ነገር አይነታችን ምን ይባላል?

12 መተ፡ ተራ ዓ.ነገር ይባላል፡፡

13 መ/ርት፡ ሁለተኛውን ስንመለከት ደግሞ ልጁ ምንድን ነው?

14 መተ ፡ ስም

15 መ/ርት ፡ ወድቆ ምንድነው

16 መተ፡ ተውሳከ ግስ

17 መ/ርት፡ ተሰበረ ምንድነው?

18 መተ፡ ግስ

19 መ/ርት ፡ ስንት ግስ አለ?

20 መተ ፡- ሁለት

21 መ/ርት ፡ በዐ.ነገራችን ውስጥ ያለው የግስ ብዛት ሁለትና ከዚያ በላይ ከሆነ ዓ.ነገሩ
አጭር ቢሆንም የዓ.ነገር አይነታችንን ምን እንላለን፡፡

22 መተ፡ ውስብስብ

91
23 መ/ርት፡ይኽ ውስብስብ ዓ.ነገር ስንት ተራ ዓ.ነገር ይወጠዋል?ሁለት ልጁ ወደቀ ልጁ
ደግሞ ምን ሆነ?

24 መተ ፡ ተሰበረ

25 መ/ርት፡የሚል ስንት ዓ.ነገር ይወጣዋል?ሁለት ይወጠዋል፡፡ ስለዚህ እናንተ ትኩረት


ልታደርጉ የሚገባው በዓ.ነገር ውስጥ ያለውን የግስ ብዛት ነው እንጂ የዓ.ነገሩ መርዘምና
ማጠር በዐ.ነገሩ ውስጥ ያለው የቃላት ብዛት ጥቂት መሆንና ብዙ መሆን ተራና ውስብስብ
ዓ.ነገር ለማለት እንደመስፈርትነት ሊቀመጥ አይችልም፡፡ተራና ውስብስብ ዓ.ነገር ለማለት
መስፈርቱ የምናረገው የምኑን ብዛት ነው? የግስ ብዛት ነው፡፡ በዓ.ነገሩ ውስጥ ያለው የግስ
ብዛት አንድ ብቻ ከሆነ ምን ይባላል?

26 ተጋ፡ ተራ

27 መ/ርት፡ ሁለትና ከዚያ በላይ ከሆነ ደግሞ

28 መተ፡ ውስብስብ ይባላል ማለት ነው፡፡

29 መ/ርት ፡ እስኪ በዚህ መሰረት መፅሀፋችሁን ገፅ መቶ አርባሶስት ላይ አውጡና


እየተከተላችሁኝ ነው?

30 ተጋ፡ አዎ

31 መ/ርት፡ ትዕዛዝ ሶስት ላይ ከአንድ እስከ አምስት የተዘረዘሩ ዓ.ነገሮች ተሰጥተዋል፡፡


ከነዚህ ዓ.ነገሮች ውስጥ ምኑን ታወጣላችሁ? ስማዊ ሀረግና ግሳዊ ሀረግ ታወጣላችሁ፡፡
ትዕዛዝ አራት ላይ ከአንድ እስከ አምስት ሌላ ዓ.ነገሮች ተሰጥተዋል፡፡ እነሱም ደግሞ
ከፃፋችሁ በኋላ ተራ ዓ.ነገር ውስብስብ ዓ.ነገር መሆናቸውን ትለያላችሁ ማለት ነው፡፡ እስኪ
በደብተር... ጀምሩ... እኔ እየዞርኩ አግዛችኋለሁ፡፡ (ተማሪዎች በደብተራችሁ ጥያቄዎችን
መስራት ጀምሩ) (መ/ርቷ የተማሪዎቻቸውን ደብተር ማረም ጀመሩ፡፡) (የተወሰኑ
ደብተሮችን ካረሙ በኋላ ወደ ጥያቄዎቹ ተመለሱ፡፡) መልሶቹ ቀድመው ከሰጧቸው የቤት
ስራ መልሶች ጀመሩ)

31 መ/ርት፡ ገጽ 141 አውጡ፡፡በባለፈው ክፍለጊዜ ስለ ስማዊ ሀረግና ቅጽላዊ ሀረግ


ተምረናል፤ስማዊ ሀረግ የምንላቸው ቀኝ መሪያቸው ወይም ከቀኝ በኩል ስም ሲሆን የሀረጉን
ዓይነት ምን እንለዋለን?ስማዊ ሀረግ የቤት ስራችን የተሰጠን .... ቃላት ተሰጥቷል፡፡
ከቃላቱ.....ውስጥ ቅፅሎችና ስሞች ተደበላልቀው ተሰጥተውናል፡፡መጀመሪያ አንድ ስም
እንመርጣለን፡፡ በዚያ ስም ስማዊ ሀረግ እንመርጣለን፡፡ስማዊ ሀረጉን ደግሞ ምን
እናደርጋለን ብለናል? ዓ.ነገር እናደርጋለን ብለናል፡፡ ስለዚህ አንድ ተማሪ እስኪ
የተሰጡትን ከመጀመሪያው ትዕዛዝ ትዕዛዝ አንድ ላይ ከተሰጡት ቃላት ውስጥ አንድ ስም
የሚመርጥልኝ ... ስም ...ስም የሚመርጥልኝ ፡- እሺ....

32 ተ1 ፡ አዲስ

33 መ/ርት፡ አዲስ... ስም.... አዲስ.... ስም አይደለም፡፡ ያው የሰው ስሞች በቅፅልም፣


በግስም፣ በስም ስለሚጠሩ ነው፡፡አሁን አንተ ያሰብክው ይመስለኛል፡፡ አዲስ የሚባል
ሰውዬውን ነው፡፡ ግን በዚህ ላይ ይህ ቅፅል ነው፡፡ ሌላ ስም

34 ተ2፡ ቤት

92
35 መ/ርት ፡ እሺ... አሁን ቤት የሚለው ቃል ስም ነው፡፡ ይህን ስም ተጠቅማችሁ ይህን
ስም ቀኝ መሪ አርጋችሁ ሀረግ አርጋችሁ....ሀረግ አርጉልኝ.... ስማዊ ሀረግ
የሚያደርግልን....እ

36 ተ3 ፡ ትልቅ ቤት

37 መ/ርት ፡ትልቅ ቤት....በጣም ጥሩ መሪያችን ማነው?

38 መተ ፡ ቤት

39 መ/ርት፡ ምን አይነት ሀረግ መሰረትን?

40 ተጋ ፡ ትልቅ ቤት

41 መ/ርት፡ ምን አይነት ሀረግ መሰረትን?...ምንአይነት ሀረግ መሰረትን?

42 ተመ ፡ ስማዊ ሀረግ መሰረትን፡፡ ይህንን ዐ.ነገር አርጎ የሚያሟላልኝ፡፡ ይህንኑ ነው


የምታሟሉት!

43 ተጋ፡ አየለ ትልቅ ቤት ሰራ፡፡

44 መ/ርት፡አየለ ትልቅ ቤት ሰራ (በጥቁር ሰሌዳ ላይ ጻፉ) እሺ አንድ ጨረስን፡፡አምስት


ነው የታዘዝነው፡፡ ሌላ አሁንም ከመፅሃፉ ላይ ሌላ ስም የሚመርጥልኝ.... እ...

45 ተ5፡ ሰው

46 መ/ርት፡ ሰው...ሰው..... ሰው... እሺ አሁን ስም አርገናል፡፡ይህንን ደግሞ ስማዊ


ሀረግ የሚያደርግኝ? ስማዊ ሀረግ ስናድርግ ስሙ ምን መሪ ይሆናል? ቀኝ .... መሪ
ይሆናል፡፡ እሺ

47 ተ6 ፡ ትልቅ ሰው

48 መ/ርት፡ ትልቅ ሰው.... አሁን ስማዊ ሀረጋችንን መሰረት ይህንን ስማዊ ሀረግ ደግሞ
ዓ.ነገር አረግን እናሟላው እስኪ፡፡ ትልቅ .... ሰው

49 ተ6 ፡ አየለ ትልቅ ሰው ነው፡፡

50 መ/ርት ፡ አየለ ... ትልቅ.... ሰው ....ነው፡፡ ሁለት አሁንም ከመፅሃፋችሁ ላይ ስም


የሚመርጥልን.... እህ

51 ተ7 ፡ ሹራብ

52 መ/ርት ፡ ሹራብ.... ሹራብ ይህንን ቀኝ መሪ አርጎ ስማዊ ሀረግ የሚመሰርትልኝ ፡፡


ስማዊ ሀረግ ...እህ.... አንቺ

53 ተ8፡ ትልቅ ሹራብ.....

54 መ/ርት፡ እሺ.... እስኪ ከትልቅ ሌላ.... ሌላ ... እስኪ ሌላ አርጋችሁ..... ትክክል ነሽ


አልተሳሳትሽም፡፡ እህ ....

55 ተ9፡ አዲስ ሹራብ

93
56 መ/ርት፡ አዲስ ሹራብ፡፡ አዲስ ሹራብ ፡፡ አሁን ስማዊ ሀረግ ሆኖልናል፡፡ ዓ.ነገር
አርጎ የሚያሟላልኝ፡፡ እህ...

57 ተ10፡ አበበ አዲስ ሹራብ ገዛ፡፡

58 መ/ርት፡አበበ .... አዲስ.... ሹራብ... ገዛ፡፡ ስንት ሆነልን፡፡

59 ተጋ፡ ሦስት

60 መ/ርት፡ ሁለት ይቀረናል፡፡ ስም የሚነግረኝ.... ስም የሚነግረኝ.... እኽ....

61 ተ3 ፡ ደግ

62 መ/ርት፡ ደግ... እሺ.... ደግ ስም ነው?

63 ተጋ፡ አይደለም

64 መ/ርት ፡ቅፅል ነው፡፡ ስም ነው የምትመርጡልኝ!

65 ተ12፡ ምጣድ

66 መ/ርት፡ ምጣድ...እሺ ስም ተገኝቷል ቀኝ መሪ አረጋችሁ ሀረግ አርጉልኝ፡፡ እህ...

67 ተ12 ፡ የቁም ምጣድ

68 መ/ርት፡ የቁም ምጣድ፡ ማለት ቆሞ በቁም የሚጋገርበት የተተከለ ማለት ነው


እሺ...ይህንኑ ዓ.ነገር አርጉት እስኪ... ጥግ

69 ተ13 ፡ አለሚቱ ትልቅ ምጣድ ገዛች፡፡

70 ተ14 ፡ አለሚቱ የቁም ምጣድ ገዛች፡፡ (የማስተካከያ ርማት ሠጥታለች)

71 መ/ርት ፡የቁም ምጣድ እንዳለ ይገዛል?እሺ... ሌላ ... እህ

72 ተ5፡ አልማዝ ትልቅ የቁም ምጣድ ተከለች፡፡

73 መ/ርት፡ እሺ እናስተካክለው፡፡አልማዝ...የቁም ምጣድ አላት፡፡ብለን ብናስተካክለው


የተሻለ ይሆናል፡፡ስንት ሆነልን? አራት፡፡ አንድ የመጨረሻ፡፡አንድ ስም የሚነግረኝ፡፡ እዛ
ኋላ

74 ተ15 ፡ ወረቀት

75 መ/ርት፡ እሺ... ወረቀት...ሀረግ የሚያረግልኝ....እሺ እስኪ አዲስ እጅ....እ...መሀል

76 ተ16፡ ልሙጥ ወረቀት

77 መ/ርት፡ እ... ልሙጥ ወረቀት እስኪ ዓ.ነገር የሚያረግልኝ

78 ተ1 ፡ አበበ ቤት ልሙጥ ወረቀት ይገኛል፡፡

79 መ/ርት፡ እነ አበበ ቤት ልሙጥ ወረቀት አለ፡፡ ስለዚህ አሁን ስንት ስማዊ ሀረግ
መሰረትን?አምስት ቀጣዩ ትዕዛዛችን ደግሞ የተሰጡ ቅፅሎች አሉ፡፡ አምስት ቅፅሎች

94
መጀመሪያ አምስት ቅፅላዊ ሀረግ ... ቀጥሎ ደግሞ ዓ.ነገር እናረጋቸዋልን፡፡ ማለት ነው እሺ
፡፡ ቅፅሎቹ መፅሃፋችን ላይ ተሰጥጠውናል፡፡ አሁንም ቅፅል እስኪ የሚነግረኝ ... እህ

80 ተ17 ፡ ደግ

81 መ/ርት ፡ደግ ... ደግ.... እሺ ቅፅል ነው ደግ ይህንን ቀኝ መሪ አድርጋችሁ ቅፅላዊ


ሀረግ የሚመሰርትልኝ፡፡ ደግ ... እህ

82 ተ7 ፡ የሰው ደግ

83 መ/ርት፡ የሰው...ደግ እሺ ይህንኑ ዓ.ነገር የሚያደርግልኝ፡፡ዓ.ነገር.... እህ

84 ተ3 ፡ አበበ የሰው ደግ ነው፡፡

85 መ/ርት፡ አበበ... የሰው ...ደግ... ነው፡፡እሺ ሌላ ቅፅል.... እስቲ ...ሌላ


ቅጽል...እንደመሰረትን

86 ተ10፡ ብልጥ

87 መ/ርት፡ ብልጥ.... እሺ.... ይችን ሀረግ የሚያደርግልኝ.... ብልጥና እህ

88 ተ4 ፡ ብልጥ ልጅ

89 መ/ርት ፡ እሺ ... ተመለከቱ አሁን ብልጥ... ልጅ ብለን ስንፅፍ እኛ መፅሃፋችን ላይ


የታዘዝነው ምናዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው?

90 ተጋ ፡- ቅፅላዊ ሀረግ

91 መ/ርት ፡ቅፅላዊ ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ ቅፅላዊ ሀረግ ስንመሰርት ደግሞ ቀኝ


መሪው ምን መሆን አለበት? ቅፅል አንተ ግን የነገርክን ብልጥ ልጅ ስንል ቀኝ መሪዎችን
ማነው? ልጅ ነው፡፡ ልጅ ደግሞ የቃል ክፍሉ ምንድን ነው? ስም ነው፡፡አሁን ይኽ ስማዊ
ሀረግ እንጅ ቅጽላዊ ሃረግ አልሆነልንም የመጻሃፋችን ትእዛዝ ግን ቅጽል መርጠን ምናዊ
ሀረግ እንድንመሰርት ነው? ቅጽላዊ ---ሀረግ እንድንመሰርት ነው፡፡ ሌላ እስኪ ይቺው
የሚያስተካክላት --ሌላ እስቲ---

92 ተ1 ፡ የሰው ብልጥ

93 መ/ርት፡ የሰው ብልጥ--አሁን--ልዩነቱ ገብቶሃል?ቅድም ቀኝ መሪያችን ስም ነበር


አሁን ደግሞ ቀኝ መሪያችን ምን ሆነ ? ቅጽል ቀኝ መሪያችን ቅጽል ሲሆን ሀረጉ ምን
ይሆናል ?ቅጽላዊ

94 ተመ፡ ሀረግ

95 መ/ርት፡ስም ሲሆን ግን ምናዊ ሀረግ ነበር የሚሆነው? ስማዊ ሀረግ ለዛ ነው


ያስቆምኩህ እሺ--እስኪ ዐ.ነገር የሚደርግልኝ ---ዐ.ነገር የሚያደርግልኝ ---ከኃላ

96 ተ18፡ አለሙ የሰው ብልጥ ነው፡፡

97 መ/ርት፡ አለሙ ---የሰው---ብልጥ ---ነው፡፡ስንት መሰረትን ሁለት ሌላ እስቲ


ቅጽል የሚመሰርትልኝ ---እህ

98 ተ19 ፡የተማሪ

95
99 መ/ርት፡ እ…

100 ተ2፡ የተማሪ

101 መ/ርት፡ እሺ---ተመልከቱ --የተማሪ --አሁን ተማሪ ቅጽል ነው?

102 ተጋ፡ ስም ነው፡፡

103 መ/ርት ፡ ስም ነው፡፡ እኔ አሁን መጸሀፋችን ያዘዘን ምን እንድናመጣ ነው?ቅጽል ---


ቅጽል ነው የምትመርጡልኝ ፡፡ቅጽል ነው የምትመርጡልኝ --እህ--

104 ተ20፡ብልህ

105 መ/ርት ብልህ---እሺ አሁን አንቺ ያሰብሽው ቅድም ይመስለኛል፡፡ሀረግ አርጊው እስኪ-
ብልህን የቅድሟን አቀናጂና ፡፡ሀረግ አርጊው ፡፡አይዞሽ

106 ተ19፡ (ለአፍታ ዝም ብላ ቆመች)

107 መ/ርት፡ የተማሪ ብለሻል አይደል?

108 ተ19፡ አዎ

109 መ/ርት፡ቀኝመሪው ብልህ ተሰጥቶናል፡፡ቅጽል አንድ ላይ አቀናጂና ቅጽላዊ ሀረግ


አርጊው፡፡

110 ተ19 ፡የተማሪ ብልጥ

111 መ/ርት፡ ጎበዝ የተማሪብልህ ለማለት ነበር ያሰብሺው መጀመሪያ የተማሪ ያልሽኝ
መጀመሪያ ብልህን ወይም ብልጥን ለማምጣት ነው፡፡የታዘዘነው ግን ቅጽል ስለሆነ
መጀመሪያ ምኑን መምረጥ አለብን?ቅጽሉን መምረጥ አለብን፡፡ሀረጋችን የተማሪ ብልህ---
ዐ.ነገር የሚያረግልኝ፡፡ እስኪ ዐ.ነገር የሚያደርገው --እሺ --እህ--

112 ተ20፡አየለች የተማሪ ብልህ ናት፡፡

113 መ/ርት፡አየለች---የተማሪ---ብልህ-ናት፡፡ስንት መሰረትን?ሶስት--እሺ--ሁለት


ይቀረናል፡፡እስቲ ሌላ ቅጽል የሚመሰርትልኝ ---ቅጽል --እህ--

114 ተ14 ፡ የልጅ

115 መ/ርት ፡ እሺ ---የልጅ --አሁንም ---ልጅ ምንድነው?

116 ተጋ ፡ስም

117 መ/ርት ፡ ስም ነው----መጀመሪያ የምትመርጡልኝ ምን መሆን አለበት?ቅጽል መሆን


ያለበት፡፡ ከዛ ከስሙ ጋር ተያይዙና ምን ትመሰርታላችሁ?ቅጽላዊሀረግ
ትመሰርታላችሁ፡፡ጥሩ --ሙከራሽ ጥሩ ነው፡፡

118 ተ21:አዋቂ

119 መ/ርት: አዋቂ የቃል ክፍሉ ምንድነው? ቅጽል ---አሁን እስቲ ይህንን ቀኝ መሪ
አድርገን ምን ማድረግ እንችላለን ?ቅጽላዊ ሀረግ --- እናረገዋለን ፡፡---እህ --

120 ተ5 : የልጅ አዋቂ

96
121 መ/ርት : የልጅ አዋቂ --ቅጽላዊ ሀረግ ሆነልን ፡፡ዐ.ሀረግ የሚያደርግልን ፡፡ዐ.ነገር
የሚያደርግልን፡፡እስኪ እህ---

122 ተ1: የሙስጦፋ ልጅ የልጅ አዋቂ ነው፡፡

123 መ/ርት : እሽ-- የሙስጠፋ ልጅ --የልጅ-- አዋቂ --ነው፡፡ በጣም ጥሩ እሺ--

አንድ ይቀረናል ፡፡አንድ--አንድ ቅጽል የሚፈልግልኝ ---እህ ---

124 ተ2፡ አዋኪ

125 መ/ርት፡ እ?

126 ተ2 ፡ አዋኪ --አዋኪ

127 መ/ርት ፡ አዋኪ--አዋኪ--አዋቂ እና አዋኪ እሺ--ሌላ እስቲ--ይህን ሀረግ የሚያረግልኝ

128 ተ7 ፡ የስራ አዋኪ

129 መ/ርት፡የስራ-- አዋኪ እሺ እስቲ ዐ.ነገር የሚያደርግኝ---ይህንን ዐ.ነገ የሚያደርግልኝ-


እህ

130 ተ21፡አበበ ትምህርት አውኮታል፡፡

131 መ/ርት ፡ አውኮታል … እሺ ይቺ እንዳለች ባንቀይራት ልክ ነሽ ፡፡ቅርጿን


ባንቀይራት የስራ አዋኪ የምትለዋን ቅርጿን ባንቀይራት

132 ተ13 ፡ አበበ የስራ አዋኪ ነው፡፡

133 መ/ርት ፡ እሺ… ይህን የስራ አዋኪን እንደ ባለቤት አድርጋችሁ


መስርቱልኝ፡፡ባለቤቱን የሚገልፅ አርጋችሁ እሺ .. እህ

134 ተ7 ፡ ቤት መስራት የስራ አዋኪ ነው

135 መ/ርት፡ ቤት መስራት …እስቲ ሌላ … እህ

136 ተ3፡ አበበየስራ አዋኪ መስራት ይወዳል፡፡

137 መ/ርት ፡ እ..ሺ… ለማት የፈለግሽው ስራ እንዳይሰራ ለማድረግ ይፈልጋል ነው


አይደል ለማለት የፈለግሽው?

138 ተ3 ፡ አዎ

139 መ/ርት፡ስለዚህ አየለ የስራ አዋኪ ነው፡፡ወይ አይስራ ወይ አይስራ ስንት ሞላልን
?አምስት

140 ተጋ፡ አምስት

142 መ/ርት ፡ በጣም ጥሩ … ሰለዚህ እነዚህን ሰማዊ ሀረግና ቅፅላዊ ሀረግ ካረጉት ቀጥሎ
የምንሄደው ወደ ክፍል ስራችን ነው፡፡ መፅሃፋችሁን መቶ አርባ ሶስት... መቶ… አርባ
ሶስት አወጣችሁ?

143 ተጋ ፡አዎ

97
144 መ/ርት ፡ እሺ ዐ.ነገሮችን ተሠጥተውናል ዐ.ነገሮችን የስማዊ ሀረግ ክፍልና የግሳዊ
ሀረግ ክፍል ነው የምናወጣው የመጀመሪያው ዐ.ነገር ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ
ጓደኛዋ ገንዘብ ሠጣት፡፤ ይላል፡፡ መጀመሪያ ባለቤቱን እናገኛለን፡፡ ማነው ገንዘብ የሰጣት?

145 መተ፡ ጓደኛዋ

146 መ/ርት ፡አሁን እስኪ ስማዊ ሀረጉን የሚነግረኝ

147 ተ1፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ…

148 መ/ርት ፡ ጓደኛዋ እስከሚለው ድረስ ምንድነው?ስማዊ ሀረግ… እሺ ግሳዊ ሀረጉስ


ከዚህ ላይ የሚነግረኝ… ግሳዊ ሀረጉን የሚነግረኝ

149 ተ7 ፡ ሰጣት … ገንዘብ ሰጣት

150 መ/ርት ፡ ገንዘብ … ሰጣት፡፡ እሺ እጅ እያወጣን እንመልስ ፡፡ ቁርሳቸውን


በልተው በጠዋት ወደ ት/ቤት የመጡት ተማሪዎች ቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ፡፡ እጅ
አውጥቶ የሚነግረኝ ነው የምፈልገው ባለቤቱን የሚነግረኝ እነማን ናቸው ቅርጫት ኳስ
የሚጫወቱት? ... እህ…

151 ተ6 ፡ ቁርሳቸውን በልተው በጠዋት የመጡት ተማሪዎች እስከሚለው የስማዊ ሀረግ


ነው፤ የቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ

152 መ/ርት ፡ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡ምክንያቱም የዐ.ነገራችን ባለቤት እነማ ሰለሆኑ


ተማሪዎች እሺ… ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች
ናቸው፡፡ ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው፡፡ እህ

153 ተ4፡ ጓደኞቻችን የሚለው ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ ከዛ ጠዋት ጠዋት ተነስተው
ስፖርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

154 መ/ርት ፡ ግሳዊ ሀረግ … ታናሽ እህቴ ከቤተሰቦቻችን ሁሉ የተለየች ባለሙያ ናት፡፡
የተለየች ባለሙያ ናት ፡፡ እህ….

155 ተ5፡ ታናሽ እህቴ የሚለው ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ከቤተሰቦቿ ሁሉ የተለየች


ባለሙያ ነች የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ

156 መ/ርት ፡ ግሳዊ ሀረግ … ንፅህናውን ያልጠበቀ ምግብ የበላው ተማሪ ታመመ፡፡ እህ

157 ተ1 ፡ ንፅህናውን ያልጠበቀ ምግብ የበላው ተማሪ እንደሚለው ድረስ ሰማዊ ሀረግ
ይሆናል፡፡ታመመ ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ማለት ነው፡፡

158 መ/ርት፡ የመጨረሻ ታዘዝነው ደግሞ ተራና ውስብስብ እያልን ነው የምንመልሰው


ቅድም እንዳየነው ተራ ዐ.ነገር የምንለው በዐ.ነገሩ ውስጥ ያለው የግስ ብዛት ስንት ሲሆን
ነው?...አንዱ … ውስብስብ ዐ.ነገር የምንለው ደግሞ በዐ.ነገር ውስጥ ያለው የግስ ብዛት
ሁለትና ከዚያ በላይ ሲሆን እሺ…ልጄ ዛሬ ጠዋት ብዙ ጥያቄዎችን አቀረበልኝ፡፡ እህ…

159 ተ21፡ ተራ

98
160 መ/ርት፡ ተራ ዐ.ነገር … ምክንያቱም ስንት የግስ ብዛት ነው ያለው አንድ ብቻ ነው
አቀረበልኝ፡፡ ስለዚህ ምን ዓይነት ዐ.ነገር እንላለን ተራ ዐ.ነገር እሺ ጨዋታውን ፊት ለፊት
በማየቴ ደስ አለኝ ፡፡ ሁለት ይወጣልናል እ… ምን ዓይነት ነው?

161 ተ22 ፡ ውስብስብ

162 መ/ርት ፡ ውስብስብ ጨዋታው ፊት ለፊት አየሁ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ሁለት … ስንት


ግስ አለው?ሁለት ሁለት ግስ ካው ደግሞ የዐ.ነገር ዓይነቱን ምን እንለዋለን? ውስብስብ
ግርማ ሆስፒታል ሄዶ ወንድሙን ጠየቀ፡፡ እህ

163 ተ4፡ ውስብስብ

164 መ/ርት፡ ውስብስብ ዐ.ነገር ፡፡ግርማ ሆስፒታል ሄዶ፡፡ግርማ ወንድሙን ጠየቀ፡፡ሁለት


ግስ ካለው የዐ.ነገር አይነቱ ምን ይሆናል? ውስብስብ መኪና እንዳይገጫት ስለፈራች
መንገዱን ተሻግራ ሄዳ ዶሮ ለመግዛት አልፈለገችም ፡፡ እህ

165 ተ8፡ ውስብስብ ዐ.ነገር

166 መ/ርት፡ ውስብሰብብ ዐ.ነገር እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ጠዋት ወደ ሀገሩ ተመለሰ ፡፡


እህ…

167 ተ2 ፡ ተራ

168 መ/ርት ፡ ተራ ዐ.ነገር እሺ ከዚህ ቀጥሎ መፀሀፋችሁን ገፅ መቶ አርባ ሰባት


ታወጣላችሁ፡፡ አዲስ ምዕራፍ ነው የምንጀምረው ገፅ መቶ አርባ ሰባት ላይ ምዕራፍ ዘጠኝ
ምርጥ ንግግር አዲስ ምዕራፍ በጀመርን ጊዜ ምዕራፉን ካጠናቀቅን በኋላ ከኛ የሚጠበቅ
ነገር አለ፡፡ ምን እናሳካለን፣ይህን ምዕራፍ የምናሳካቸው በመለየት ዓላማዎቹን አንብበው
የዕለቱን የት/ቤት ክ/ጊዜ ተጠናቀቀ፡፡

99
አባሪ ሁለት

ምዝግብ መረጃ ሁለት


ክፍል ሀ
የተማሪ ቁጥር 48
ጊዜ፡- 40 ደቂቃ
የትምህርቱ ርዕስ፡- ስርዓተ ነጥብ
01 መ/ርት፡ ሌሎች ስርዓተ ነጥቦች አሉ ግን ነጠላ ትዕምርተጥቅስና ትምዕርተ ጥቅስን
ሁለቱን ነገሮች ማየት ስላለብን ስለዚህ የሚያስፈልጉን ከኔ ጋ ቶሎ ቶሎ ፃፉ (በማለት
ማስታወሻውን በጥቁር ሰሌዳው ላይ መፃፍ ጀመሩ ተማሪዎች ማስታወሻውን መፃፍ
ቀጠሉ፡፡

መ/ርት ፡ ስርዓተ ነጥቦች አገልግሎታቸው ፅሁፍ ተገቢውን መልዕክት እንዲያስተላልፍ


ይረዱናል፤በአማርኛ ቋንቋ ውስጥ ያሉትን ስርዓተ ነጥቦች እነዚህም ከዚህ በፊት ያየናቸው
ቢኖሩንም አሁን ግን የሁለቱን እናያለን‹፡፡ትዕምርተጥቅስ በዋነኛነት የመጀመሪያ ተግባሩ
የሌላ ሰው ሀሳብን ከራሳችን አባባል ለመለየት ነው ይኸ ማለት አንድ ፅሁፍ በምንፅፍበት
ጊዜ የራሳችንን ሀሳብ ብቻ አመንጭተን ላንፅፍ እንችላለን የሰዎችን ሀሳብ ወስደን ልንፅፍ
እንችላለን ፡፡ነገር ግን የወሰድነውን ሀሳብ እንደራሳችን ሀሳብ አድርገን ራሳችን
እንዳመነጨነው ሃሳብ አድርገን ማቅረብ ያስቀጣል፡፡ እንደሌብነት ነው የሚቆጠረው ታዲያ
ይህ ሀሳብ የኔ አይደለም ከሌላ ሰው የወሰድኩት ሀሳብ ነው ብለን በምን ውስጥ
እናስቀምጣለን? በትምዕርተ ጥቅስ ውስጥ እናስቀምጣለን፡፡ ትምዕርተ ጥቅስን ስናስቀምጥ
በሁለት መልኩ መጥቀስ እንችላለን፡፡ ይህ የመፃፊያ ወረቀታችን ቢሆን ከሌሎች ሰዎች
የወሰድነው ሀሳብ ከአራት መስመር በታች ወይም ከአርባ ቃላት በታች ከሆነ ፅሁፉን
ከራሳችን ሀሳብ ጋር በማደባለቅ የሌላ ሰው ሀሳብን በትምዕርተ ጥቅስ ውስጥ
እናስቀምጣለን፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የራሳችንን ሀሳብ እናስቀምጣለን፡፡ ዝርው ፅሁፍን
በምንፅፍበት ጊዜ ከግራ ህዳግ በመጀመር እስከ ቀኝ ህዳግ ግጥም አድርገን እንፅፋለን
፡፡ነገር ግን የወሰድነው ሀሳብ ከአርባ ቃላት በላይና ከአራት መስመር በላይ ከሆነና ሰፊ
ሀሳብ ከሆነ ከቀኝና ከግራ ህዳግ ገባ በማለት ልክ እንደ ግጥም አፃፃፍ ከፃፍን በኋላ ምን
አንጠቀምም? ትምዕርተ ጥቅስን አንጠቀምም? ልዩነታቸው ከአራት መስመር በታችና
ከአርባ ቃላት በታች ከሆነ ከራሳችን ጋር አደባልቀን በምን እንቀነብበዋለን? በትምዕርተ
ጥቅስ … እናስቀምጠዋለን፡፡ ነገር ግን ሀሳቡ ሰፊ ከሆነ የግድ ትዕምርተጥቅስን መጠቀም
አይጠበቅብንም ፤ ከቀኝና ከግራ ገባ ብለን የሰውዬውን ሀሳብ መፃፋችን ራሱ ምን
እንደተጠቀምን? ትምዕርተጥቅስ እንደተጠቀምን ያመላክታል፡፡ ትዕምርተጥቅስን ስለዚህ
ትዕምርተጥቅስን የሰውን አባባል ከሌላ ሰው ለመለየት የምንጠቀምበት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ
ተውኔታዊ ፅሁፎችን በምንፅፍበት ጊዜ “ስክሪብት” በምንፅፍበት ጊዜ … ወይም ጭውውትን
ሁለት ሆናችሁ…ሶስት ሆናችሁ…አባትና ልጅ ሆናችሁ… ፃፉና አምጡ ትባላላችሁ ያንን
ጭውውት በምንፅፍበት ጊዜ .. የእያንዳንዱን ተጫዋቾች ሀሳብ በአዲስ መስመርና በምን
ውስጥ ይቀመጣል? በትዕምርተጥቅስ ውስጥ ይቀመጣል፡፡(ተማሪዎችን ጥያቄ በመጠየቅ
የማነሳሻ ግብረ መልስ ይሠጣሉ፡፡)

ለምሳሌ ፡- እዚህ መሀመድና አያሌው ንግግር እያደረጉ ነው፡፡ አጭር ናት ሶስት ነጥብ ወደ
ታች ያረኩት ይቀጥላል ለማለት ነው፡፡ ነገር ግን እያንዳንዳቸውን ስንመለከት - መሀመድ
ጋቢውን ለብሶ “ እትትት ……. አለ እነዚህን በትዕምርተጥቅስ ውስጥ ያላስቀመጥናቸው

100
ለምንድን ነው? ማን ያላቸው ስለሆነ ነው ?ፀሃፊው የተናገራቸው ስለሆነ ነው፡፡ መሀመድ
ምን ብቻ ነው ያለው? እትትት… አያሌው ምን አለው?“በረደህ” ብሎ ጠየቀው፡፡
እያንዳንዷን የእያንዳንዱን ተጫዋች ሀሳብ በምን ውስጥ እናስቀምጣለን?በትዕምርተ
ጥቅስና ባዲስ መስመር እናስቀምጣለን፡፡ሌላው ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስ ነው፡፡ “ልብ በሉ”
ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስ የምንጠቀመው በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ነው፡፡ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ
ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስ ሊወጣ አይችልም በአጭሩ ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስን የምንጠቀመው
እኛ ከሌላ ሰው ሀሳብ ስንወስድ ያ ሀሳብ የወሰድንበት ሰውዬ ሲጀመር ሀሳቡን የወሰደው
ከሌለ ሰው ከሆነና ሌላ ሶስተኛ ወገን ካለ የመጀመሪያው የምንጩን ሰውዬ ሀሳብ በነጠላ
ትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ እኛ ሀሳብ የወሰድንበትን ሀሳብ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ
የፀሀፊው ሀሳብ ደግሞ ከትዕምርተ ጥቅስ ውጭ እናስቀምጣለን፡፡ ይቺን ምሳሌ
እንመልከትና ሌላ ደግሞ እሰጣችኋለሁ፡፡ ምሳሌ፡- ወንድሜ እናትሽ ናፈቀችኝ
ብላለች ብሎ ሲነግረኝ ስቅስቅ ብዩ አለቀስኩ፡፡የሚል ቢኖር በዚህ ዐ.ነገር ውስጥ ሶስት
አካላት አሉ፡፡ ወንድሜ አለ፡፡እናቴ አለች እና ራሱ ማን አለ ?ፀሀፊው እስኪ እጅ አውጥቶ
የሚነግረኝ ነው የምፈልገው መጀመሪያ ከሶስቱ አካላት ውስጥ መልዕክት የላከው ማነው?
እጅ አውጥቶ የሚነግረኝ ዐ.ነገሩ የሚለው ወንድሜ “ እናትሽ ናፈቀችኝ ብላለች ብሎ
ሲነግረኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ማነው መጀመሪያ መልዕክት የላከው?መጀመሪያ ንግግር
ያረገው ማነው ከወንድሜ፣ ከእናቴና ከፀሀፊው ንግግር ያደረገው ማነው?

02 ተ1 ፡- እናትሽ

03 መ/ርት ፡-ማነው?

04 ተጋ ፡ እናትሽ

05 መ/ርት ፡ እሺ አሁን እናቴ ምንድነው ያለችው? ምን አለች?ወንድሜ እናትሽ


ናፈቀችኝ ብላለች ብሎ ሲነግረኝ ስቅስቅ ብዩ አለቀስኩ፡፡ እጅ አውጥቶ የሚነግረኝ …
እናቴ ምን ብላ ነው የላከችው?

06 መ/ርት፡ እ?

07 ተ2 ፡ ናፈቀችኝ

08 መ/ርት፡ ናፈቀችኝ... ስለዚህ ይቺን የመጀመሪያዋን ሀሳብ በምን ውስጥ እናስቀምጣለን?


በነጠላ ትዕምርተጥቅስ ውስጥ…እናቴ ቀጥታ ነው እንዴ ለኔ ናፈቀችኝ ያለችው?

09 ተጋ ፡ አይደለም

10 መ/ርት ፡ ለማነው?

11 ተጋ፡ ለወንድሜ

12 መ/ርት፡ ለወንድሜ ፣ወንድሜ ደግሞ ለኔ ነገረኝ፡፡ ምን አለ? እጅ ወጥቶ


የሚነግረኝ?እሱ ደግሞ ሁለተኛው ወገን ነው፡፡ ምን አለ?እ…

13 ተ3፡ ናፈቀችኝ ብላለች ፡፡ብላለች የሚለው ጋ

14 መ/ርት ፡ እሺ… ጥሩ…እሷን ብቻ ነው ያለው?ይቺን ብቻ ነው የተናገረው

15 ተ4፡ እናትሽ ናፈቀችኝ ብላች

101
16 መ/ርት፡ እናትሽ ናፈቀችን ብላለች፡፡ይችን ደግሞ ሁለተኛው ወገንን እኛ ሀሳብ
የወሰድንበት ሀሳብ በምን ውስጥ እናረጋለን? በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ፡፡ ወንድሜ የሚለውና
ስቅስቅ ብዩ አለቀስኩ የሚለውን በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያላስቀመጥነው ለምንድነው?

17 ተጋ፡ የፀሀፊው ንግግር ስለሆነ

18 መ/ርት፡ የፀሀፊው ንግግር ስለሆነ፡፡ እስኪ አንድ እንድገምና እንየው፡፡ አለቃው


መምህሩ እንዳትረብሹ ብሏል አለ፡፡ እስኪ እዚህ ላይ አስገብታችሁ ታሳዩኛላችሁ፡፡
(መምህርቷ እየተዘዋወሩ ተማሪዎችን ተመለከቱ፡፡)ስትጨርሱ መልሱን አሳዩ (ተማሪዎችም
ስራቸውን ለመምህርቷ በተናጠል አሳዩ)ጊዜያችንን ለመቆጠብ በጋራ እንስራ… ልክ
እንደላይኛው ሁሉ እዚህ ጋር የስንት ሰው ንግግር አለ፡፡የአለቃው፣ የመምህሩና የፀሀፊው
አለ፡፡ እሺ … መጀመሪያ ንግግር ያደረገው ማነው? …መጀመሪያ ንግግር ያደረገው
መነው? እጅ አውጥቶ የሚነግረኝ

19 ተ5፡ መምህሩ

20 መ/ርት፡ መምህሩ፡፡ ምን አሉ?

21 ተጋ ፡ እንዳትረብሹ ፡፡

22 መ/ርት፡ እንዳትረብሹ፡፡ ስለዚህ ይቺን ሀሳብ በምን ውስጥ እናስቀመምጣታለን?በነጠላ


ትምዕርተጥቅስ ውስጥ፡፡ ብለው ለማነው የነገሩት?ለአለቃው፡፡ አለቃው ደግሞ ምን አለ?

23 ተ3፡ “መ/ሩ እንዳትረብሹ ብሏል” ይቺን ደግሞ በምን እናደርጋለን?በድርብትምዕርተ


ጥቅስ፡፡አለቃውና አለ ያለው ሰውዬ ማነው?

24 ተጋ ፡ ፀሀፊው

25 መ/ርት ፡- ስለዚህ የፀሀፊው ሀሳብ ደግሞ ከምን ውጭ እናደርጋለን፡፡ እስኪ አሁን


ወደ የቤት ስራችን እንሂድና ያልተሟላውን አንቀፅ በትክክለኛ ስርዓተ ነጥቦች አሟልተን
አንቀፁ መልዕክቱን እንዲያስተላልፍ እናደርጋለን ፡፡ፅሁፋችሁን ገፅ 155፡፡ እኔ ሳነብላችሁ
እናንተ እጃችሁን እያወጣችሁ ስርዓተነጥቡን ትነግሩኛላችሁ፡፡ ከላይ የተሰጡት አራት
ስርዓተነጥቦች አሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሁለት ነጥብ ከሠረዝንም ደግሞ መምረጥ
ትችላላችሁ፡፡ እኔ አንቀፁን ሳነብላችሁ እናንተ የስርዓተ ነጥቡን ዓይነት እጃችሁን
እያወጣችሁ ትነግሩኛላችሁ፡፡

መ/ርት ፡ በጣሊያን ወረራ ዘመን ለሀገራቸው ነፃነት ከተዋደቁት በርካታ ወጣቶች ውስጥ
አንዱ ዘርጋ ናጂ ነበር እህ …

26 ተ6፡ አራት ነጥብ

27 መ/ርት ፡ አራት …ነጥብ ዘርጋ ናጂ እህ …

28 ተ4፡ ነጠላ ሰረዝ

29 መ/ርት ፡ ነጠላ ሰረዝ የምንጠቀመው ተመሳሳይነት ሙያ ያላቸው የሚዘረዘሩ ነገሮች


ለመለየት ነው፡፡ አሁን ስለዘርጋ ናጂ ልናወራ ነው ገና እ …

30 ተ1፡ ሁለት ነጥብ ከሠረዝ … እሺ ቁመቱ ለዥም...ቁመቱ ረዥም…እህ

31 ተ7፡ ነጠላ ሠረዝ

102
32 መ/ርት ፡ አጥንቶቹ ሰፋፊ … እህ

33 ተ8፡ ነጠላ ሰረዝ

34 መ/ርት ፡ ነጠላ ሰረዝ መልኩ ቀይ ... እህ…

31 ተ9 ፡ ነጠላ ሰረዝ

32 መ/ርት ፡ነጠላ ሰረዝ ፀጉሩ ከልክ በላይ አድጎ በሶስትዮሽ የተሸረበ ነበር... እ

33 ተ10 ፡ አራት ነጥብ

34 መ/ርት ፡ አራት … ነጥብ ... ያፅጉሩ በጀርባውና በትከሻው ላይ ተንዥርግጎ ወርዶ


ሲታይ ልዩ ግርማ ያጎናፅፈዋል እህ …

35 ተ11 ፡ ትምዕርተጥቅስ

36 መ/ርት ፡ ትምዕርተጥቅስ (በጥርጣሬ ድምፅ) እህ…

37 ተ12 ፡ አራት ነጥብ

38 መ/ርት ፡ አራትነጥብ (በእርግጠኝነት ድምፅ) ዘርጋ ጠም አልባ ሲሆን እህ…

39 ተ3 ፡ ቅንፍ

40 መ/ርት ፡ቅ…ንፍ ቅንፍን የምንጠቀመው ወይም ለመተካት ነው፡፡አማራጭ ሲኖር


ነው ፡ አሁንም እ …

41 ተ13፡ሁለት ነጥብ ከሠረዝ

42 መ/ርት ፡ሁለት ነጥብ ከሠረዝ ጠቅላላ ገፅታው የሠው ዓይን የሚማርክ ሸበላ …
ሸበላ

43 ተ14፡ቅንፍ

44 መ/ርት ፡ ቅንፍ ምን ይደረጋል?ይከፈታል ቆንጆ ካልን በኋላ ሁለተኛው ዘጠኝ ላይ


ቅንፍ ምን ይደረጋል? ይዘጋል… ነበር

45 ተ15፡ አራት ነጥብ

46 መ/ርት ፡ አራት … ነጥብ ዘርጋ ለአራት አመታት ያህል በዋሻና በጫካ ውስጥ ሲኖር
የሚለው ላይ ምንም ዓይነት ስርዓተ ነጥብ ባናስገባበት ጥሩ ነው ሹርባው በወገቡ ከታጠቀው
የቆዳ ዝናር በታች ወርዶ ይታይ ነበር

47 ተ16 ፡አራት ነጥብ

48 መ/ርት ፡ አራት … ነጥብ በጎታ ገበያም ሆነ በሌሎች ስፍራዎች አጋጥሟት ያየችው


ሴት ሁሉ

49 ተ3፡ ትምዕርተጥቅስ

50 መ/ርት ፡ትዕምርተጥቅስ ምን ይደረጋል? ይከፈታል፡፡ ዓይኔ ይፍሰስልህ እንልና ደግሞ

103
ትዕምርተጥቅስ ምን ያደርጋል ?ይዘጋል ሳትል አታልፍም.. ነበር አራት

51 ተጋ ፡ነጥብ

52 መ/ርት ፡ አሁን ደግሞ ባለን ሠዓት ቀጥሎ ያለውን ትዕዛዝ እንሠራለን፡፡ ትዕዛዙ
በሚከተሉት ዓ.ነገሮች ውስጥ ያሉትን የስምና የግስ ሙያዎች ለይታችሁ በመተንተን
ሙያቸውን አሳዩ ነው የሚለው፡፡ ለምሳሌ የተሰጠን አለ ሜላት የቤቱን ወለል አጠበች ፡፡
የሚል ዓ.ነገር ተሰጥቶን በሚለው ዐ.ነገር ውስጥ ሜላትና የቤት ወለል አለ፡፡ ሜላት
ምንድነው?ባለቤት ነው፡፡ በዚህ መሠረት እንድንሰራ ነው፡፡ የቤት ወለል ደግሞ ምንድነው?
ተሳቢ አጠበች ደግሞ ማሰሪያ አንቀፅ ነው፡፡ ባለፈው እንደተማርነው ክለሳ ለማድረግ ያክል
በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ባለቤት፣ ተሳቢና ማሰሪያአንቀፅ አሉ፡፡ማሰሪያ አንቀፅ የምንለው
የዐ.ነገሩን መጋቻ ወይም መቋጫ ነው፡፡ ባለቤት የምንለው ድርጊት ፈፃሚው አካል ነው፡፡
“ማ” የሚል ጥያቄ ስንጠይቅ ማሰሪያአንቀፅን ይዘን “ማ” የሚል ጥያቄ ስንጠይቅ የምናገኘው
መልስ ምንድነው ባለቤት ነው፡፡አሁን ማሰሪያ አንቀፁን ይዘን “ማንን” የሚል ጥያቄ
ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ምንድነው?ተሳቢ ነው፡፡ ተሳቢ ማለት ድርጊት የሚፈፀምበት
አካል ነው፡፡ ባለቤት ማለት ድርጊት ፈፃሚው አካል ነው፡፡ እሺ በዚህ መሠረት
በመፀሀፋችሁ አምስት ዐ.ነገሮች አሉ፡፡ የአምስቱን ዐ.ነገሮች ባለቤት፣ተሳቢና ማሠሪያ
አንቀፅ እንለያለን፡፡ እሰኪ በጠረጰዛ የምሰጣችሁ አምስት ደቂቃ ነው
ቀጥሎ፡፡(ውይይታቸውን ቀጠሉ) (የውይይቱ ሠዓት አበቃ)

መ/ርት ፡ እጅ እያወጣችሁ ነው እሺ የምትመልሱት፡፡ ልጅቷ ላሚቷን አለበች … እህ…

53 ተ16 ፡ ልጅቷ የሚለው ባለቤት ፣ ላሚቷን የሚለው ደግሞ ተሳቢ ሲሆን አለበች
የሚለው ደግሞ ማሰሪያ አንቀፅ

54 መ/ርት፡ ማሰሪያ አንቀፅ በጣም ጥሩ ህፃኗ ልጅ የመስኮቱን መጋረጃ ጎተተችው፡፡ እህ…

55 ተ15፡ ህፃኗ ልጅ የመስኮቱን መጋረጃ ጎተተችው ነው የሚለው ህፃኗ ልጅ ባለቤት ፣


የመስኮቱን መጋረጃ የሚለው ደግሞ ተሳቢ … ጎተተችው ማሰሪያ አንቀፅ

56 መ/ርት ፡ማሰሪያ … አንቀፅ ሠራተኞች የእንስራውን ውሃ ደፉት ፡፡ እህ

57 ተ2፡ ሠራተኞቹ የእንስራውን ውሃ ደፉት ፡፡ ሠራተኞቹ የሚለው ባለቤት ነው


የእንስራውን ውሃ የሚለው ተሳቢ ነው ደፉት የሚለው ባለቤት ነው

58 መ/ርት ፡ ማሰሪያ አንቀፅ (የማስተካከያ ግብር መልስ ሰጥተዋል)

ተ2 ፡ማሰሪያ አንቀፅ

59 መ/ርት ፡ ማሰሪያ … አንቀፅ ወታደሩ የታጠቀውን ሽጉጥ አወጣ እሰቲ…

60 ተ17 ፡ ወታደሩ የሚለው ባለቤት ይሆናል የታጠቀውን ሽጉጥ የሚለው ተሳቢ አወጣ
የሚለው ደግሞ ማሰሪያ አንቀፅ

61 መ/ርት ፡ ማሰሪያ አንቀፅ … ችግኞቹን ውሃ አጠጣች፡፡

62 ተ18፡ችግኞች የሚለው ተሳቢ ናቸው፡፡ እሷ ደግሞ የሚለው ባለቤት ይሆናል አጠጣች


የሚለው ማሠሪያ አንቀፅ

63 መ/ርት ፡ ማሰሪያ አንቀፅ እሺ በዚህ መሠረት ከጨረስን ችግኞቹን ውሃ አጠጣች


ሰንል ባለቤቱን ሁል ጊዜ በቀጥታ ላናገኝ እንችላለን፡፡ማነች ያጠጣችው? እሷ፡፡ በውስጠ

104
ታዋቂ ሴት የሆነች ሰው ፆታዋ ሴት የሆነ ሰው ምን አጠጣች? ውሃ አጠጣች፡፡ ስለዚህ
ባለቤቱ ማን ይሆናል ማለት ነው እሷ ይሆናል ማለት ነው፡፡ቀጥሎ ደግሞ የተዘረዘሩት
ቃላት አሉ፡፡ በቃላቱ ዐ.ነገር ከሠራን በኋላ ዐ.ነገር ውስጥ ቃላቱን እንደ ባለቤት፣እንደ
ተሳቢ ወይም እንደ ንብረት መጠቀማችንን እንገልፃለን፡፡እናንተ መጀመሪያ ዐ.ነገሩን
ትሰሩና ስታነቡት ሌሎቹጓደኞቻችሁ ደግሞ እንደ ባለቤት ነው የተጠቀማችሁት?ወይ እንደ
ተሳቢ እንደሆነ፣ወይ ደግሞ ንብረት አመልካች እንደሆኑ ይገልፁልናል ማለት
ነው፡፡በስድስቱ ትሰራላችሁ፣በሬ፣ልብስ፣ሴት፣ውሻ፣ ስጋና ፅሁፍ አንድ ዐ.ነገር ስሩ መጀመሪያ
አንዳንድ ዐ.ነገር ቶሎ በሉ፡፡ ወረቀት ላይ ስሩና (ተማሪዎች በጋራ እየተወያዩ መስራት
ቀጠሉ መ/ርቷ እየተዘዋወሩ መመልከት ጀመሩ) ሰዓቱ ስላለቀ የቤት ስራ ክፍል አራትና
ክፍል አምስትን ሰጥተው ክ/ጊዜ ተጠናቀቀ፡፡

105
አባሪ ሶስት

ምዝግብ መረጃ ሶስት


ክፍል ሀ
የተማሪ ቁጥር 40
ጊዜ 40 ደቂቃ
የት/ት ርዕስ የቃላት እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍቺ፣ቅኔ
መ/ርቷ ወደ ክፍል ገብተው ርዕሱን ፅፈው በሠንጠረዥ ውስጥ እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍቺ
የሚሰጡ ቃላትን ፃፉ፡፡ የፃፏቸው ቃላት ዶሮ፣አይን፣ልብና ጎጆ

01 መ/ርት ፡ከኔ ጋር ናችሁ፡፡

02 ተጋ ፡አዎ

03 መ/ርት ፡ ለዚህ ቃላት ምን እንሰጣለን? እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍቺ እንሰጣለን


ለመከለስ ያክል እማሬዊ ፍች የምንለው ፣ እማሬያዊ ፍች የምንለው የቃላቱ ቀጥተኛ
(መዝገበ ቃላዊ) ፍች ነው፡፡ ፍካሬያዊ ፍች የምንለው ደሞ የቃሉ ሚስጥራዊ ፍች፡፡ እነዚህ
ቃላት ዶሮ፣ዓይን፣ልብ፣ጎጆ የሚሉት አራት ቃላት ተሰጥተውናል፡፡ ለቃላቱ እማሬያዊና
ፍካሬያዊ እንሰጣለን ዶሮ ማለት እማሬያዊ ፍች እስቲ የሚነግረኝ… እህ…

04 ተ1 ፡ ሁለት እግር ያላት እንቁላል ጣይ ዶሮ

05 መ/ርት ፡ እንቁላል ጣይ የቤት እንስሳ ፍካሬያዊ ፍች ደግሞ አጭር ዓይን እስቲ


እማሬያዊ ፍች የሚነግረኝ?

06 ተ2 ፡ የሠው የአካል ክፍል

07 መ/ርት ፡ የሠው የአካል ክፍል … እሺ.. ፍካሬያዊ ፍችስ … እየሞላችሁ

08 ተ3 ፡ ለሰው ልጅ ለማየት የሚያገለግል

09 መ/ርት ፡ይኸው ለሰው ልጆች ለማየት የሚጠቅም ፣የሠው የአካል ክፍል፣ሁለት የሆነ
የሚሉት በሙሉ ምን ዓይነት ፍች ናቸው?እማሬያዊ ፍች ናቸው፡፡ ፍካሬያዊ ፍች

10. ተ4 ፡አስተዳዳሪ (ድምፁን ለመስማት ያስቸግር ነበር)

11. መ/ርት ፡እ?

12 ተ4 ፡ አስተዳዳሪ

13 መ/ርት ፡ አስተዳዳሪ፣ዋና ወይም ፊት ለፊት ማለት ነው፡፡ልብ … ልብ


እማሬያዊ ፍች
14 ተ5 ፡የሠው አካል

106
16 መ/ርት፡የሠውነት የአካል ክፍል፣ ደም ለመርጨት የሚያገለግል አጠቃላይ ለልብ
የምንሰጣቸው ቀጥተኛ ማብራሪያዎች እማሬያዊ ፍች ይባላሉ፡፡ ፍካሬያዊ ፍች

17 ተ6 ፡ ደፋር

18 መ/ርት፡ ደፋር … እሺ … ጎጆ እማሬያዊ ፍች… እህ

19 ተ7 ፡ መኖሪያ

20. መ/ርት ፡ መኖሪያ ምን?

21 ተ7 ፡ቤት

22 መ/ርት ፡ መኖሪያ… ቤት…እሺ…ፍካሬያዊ ፍች

23 ተ8 ፡ትዳር

24 መ/ርት፡ትዳር ወይም ኑሮ እንላለን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ስለ እማሬያዊና ፍካሬያዊ


ፍች ይህንን ያክል ካልን ቀጥለን የምንሄደው ምን ላይ ይሆናል፡፡ ቅኔ ላይ ይሆናል፡፡ ቅኔ
ከትርጓሜው ስንነሳ በፅሁፍ በቃል ወይም በፅሁፍ ደግሞ ዝርው ወይም በግጥም ሊቀርብ
የሚችል ነው፡፡ ነገር ግን በአማርኛ ውስጥ ተዘወትሮ የሚነገረው በግጥም ውስጥ
ነው፡፡በግጥም ውስጥ ቅኔ ለመባል ቢያንስ ስንት ትርጉም ያስፈልገዋል?ሁለት ትርጉም
ያስፈልገዋል፡፡ሁለት ትርጉም የሌለው ግጥም ከሆነ ያ ነገር ቅኔ ሳይሆን ዝም ብሎ
ምንድነው? ግጥም ነው፡፡ በቅኔ ውስጥ ህብረቃል ሰምና ወርቅ የሚባሉ ሶስት ነገሮች
አሉ፡፡ህብረቃል የሚለው እያንዳንዳቸው ትርጓሜ ለመስጠት ያክል ህብረት ማለት የጋራ
ማለት ነው፡፡ የጋራ ቃል ስንል የማና የማ የጋራ? የሰምና የወርቅ የወርቅ የጋራ ቃል
ወይም ሀረግ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ህብረ ቃል ማለት ሰሙንና ወርቁን አንድ ላይ ሸፍኖ
፣ጠቅሎ፣የጋራ አድርጎ የያዘ ቃል ወይም ደሞ ሀረግ ምን ተብሎ ይጠራል?ህብር ቃል
ይባላል ማለት ነው፡፡ ልክ ከስሙ እንደምንረዳው ህብረ ስንል የህብረት ማለት ነው፡፡ የማና
የማ የህብረት? የሰምን የወርቅ የህብረት ማለት ነው፡፡ ልክ አንድ ሻማን ብንመለከት
ሻማው ለመብራት ከላይ የሚቀልተው ነገርና ውስጡ ያለችው ምን ያስፈልጋሉ? ክር
ያስፈልጋሉ፡፤ ክሩንና የሚቀልጠውን ነገር አንድ ላ ምን እንለዋለን? ሻማ እንላለን፡፡ ልክ
ሰምና ወርቅን የያዘውን ቃል አንድ ላይ ምን እንደምንለው ሁሉ? ህብረ ቃል ፡፡ሰም
የምንለው ደሞ ከላኛው ስንኞች ዌም ከግጥሙ ስንኞች በቀጥታ ስናነብ የምናገኝው ቀጥተኛ
ፍች .. ቀጥተኛ ፍች ምን ተብሎ ይጠራል? ሠም ይባላል፡፡ ልክ ቅድም እንደነገርኳችሁ
ሻማው እንዲበራ ክሯን የሸፈናት ቀላጩ ነገር ልክ እንደምን ልንቆጥረው እንችላለን? እንደ
ሰም ልንቆጥረው እንችላለን ማለት ነው፡፡ ወርቅ የምንለው ደሞ የተለያዩ የቅኔ መፍቻ
ስልቶችን ተጠቅመን በነዛ ቅኔ መፍቻ ስልቶች አማካኝነት ተመራምረን ጥናት አድርገን
የምናገኝው ሚስጥራዊ ትርጉም ደሞ ምን ተብሎ ይጠራል?ወርቅ ተብሎ ይጠራል ማለት
ነው፡፡ እስቲ ለምሳሌ አንድ እንስራና እንይ፡፡

የለመንኩሽ ብዕር ስለጠፋብሽ

እሰይ ደስ ብሎኛል ባልተገኘልሽ

የሚል አንድ ቅኔ ያለው ግጥም አለ፡፡


ግጥማችን ህብር ቃል ካገኘን በኋላ ሠሙን ለማግኘት የተለያዩ ስልቶችን እንጠቀማለን፡፡
በዚህ ምሳሌ መሠረት ሌሎች የሚሰሩ ስለምሰታችሁ ከኔ ጋር ሁኑ፡፡ እሺ እስቲ ህብረ
ቃሉን የሚነግረኝ? (ግጥሙን ደግመው አነበቡ)… እህ…

107
25 ተ9 ፡ህብረ ቃል እሰይ ደስ…ማለት ነው

26 መ/ርት ፡ እሺ … እሱ … አይደለም ..እህ ..

27 ተ10 ፡ባልተገኘልሽ

28 መ/ርት ፡ህብረ ቃላችን ማነው? ባል .. ተገኘልሽ እሺ ትርጉም አንድ … አንደኛው


ትርጉም ለማግኘት ከላይኛው ስንኝ ተነስተን ቀጥታ ፍች እንሰጣለን፡፡ ( ግጥሙን ደግመው
አነበቡ) ብዕርሽ ምን በሆነብሽ ለማለት ፈልጎ ነው? እህ …

29 ተ6 ፡በጠፋብሽ

30 መ/ርት ፡ብዕርሽ … ሳይገኝልሽ በቀረ… የሚል አንድ ትርጉም አለው ፡፡ ሁለተኛው


ትርጉም ለማግኘት ከቅኔ መፍቻ ስልቶች ውስጥ አንዱ ህብረቃሉን በቀጥታ ለስንት
መክፈል ነው? ሁለት መክፈል ነው፡፡ ህብረ ቃሉን አንድ ቃል የነበረውን ህብረ ቃል
ለሁለት ከፍለን ሁለት የተለያዩ ፍች የሚሰጡ ቃላት ስናደርጋቸው ተመራምረን ምኑን
እናገኛለን? ወርቁን እንገኛለን ማለት ነው፡፡ እሁለት ስንከፍለው ባል እና ተገኘልሽ የሚል
ሁለት ፍች ያለው ቃል እንገኛለን ፡፡ ምን ማለት ነው ይኸስ? ይኸስ ምን ማለት ነው? እህ

31 ተ11 ፡ባል ተገኝቶልሻል፡፡

32 መ/ርት፡ሁለተኛው የሚያገባሽ ባል እ…አገኘሽ የሚል ትርጉም እንገኛለን ማለት


ነው፡፡ እስቲ የቱ ነው ሠም? የቱ ነው ወርቅ? እጅ አውጥቶ የሚነግረኝ …. እህ …

33 ተ11 ፡ሁለተኛው ባል ተገኘልሽ የሚለው ወርቅ …

34 መ/ርት ፡ባልተገኘልሽ የሚለው ምንድነው?ወርቅ … እህ..

35 ተ12 ፡ያኛው ደሞ … ሰም

36 መ/ርት ፡ የላይኛው ደሞ ምን ይሆናል ሠም ይሆናል፡፡ እስቲ በዚህ መሠረት


በጠረጴዛችሁ ትሆኑና የምፅፍላችሁን ቅኔዎች ህብረቃል፣ ሠምና ወርቅ
ታወጣላችሁ፡፡(ቅኔዎቹን በጥቁር ሠሌዳው ላይ ፃፉ) ሀኪም ቤት አልሄደች ያለችው ከቤት
እኔ ምን ላድርጋት ያችን ልጅ አሟት

1. ምነው አንድ ፋኖስ የላችሁ


ኩራዝ ብቻ ቤታችሁ
2. እኔ የልጇ ልጅ እሷ የናቴ እናት
አኳኋኗ ሁሉ እንዳያት እንዳያት
3. የልጃገረድ አውታታ
ከመንገድ ዳር ተኝታ
ተነሺ በሏት ምነው
ይኸ ሁሉ አለማፈር ነው፡፡

መ/ርት፡እነዚህን አራቱን ህብረ ቃል ፣ ሰምና ወርቅ ትሰራላችሁ? እየመጣሁ


አግዛችኋለሁ፡፡(ተማሪዎችም እጎናቸው ከተቀመጡት ተማሪዎች ጋር ውይይታቸውን
ለተወሰነ ደቂቃ ቀጠሉ) መምህርቷም እየተዘዋወሩ ያስረዳሉ፤ሥራቸውን ይመለከታሉ
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ መምህርቷ በቃ አሉ፡፡)

መ/ርት ፡እሺ በቃ .. በጋራ እንስራ እንግዲህ የተለዩ የቅኜ መፍቻ ስልቶችን ተጠቅመን
በነዚህ በአራት ግጥሞች ህብረ ቃል ሰምና ወርቅ እንዴት እንደምናወጣ ልምምድ

108
እናደርጋለን፡፡ ለመከለስ ያክል ህብረቃል የምንለው ሰሙንና ወርቁን አንድ ላይ አጠቃሎ
የያዘ ቃል ወይም ሀረግ ህብረቃል ይባላል፡፡ ሠም የምንለው ደሞ ግጥሙን ስናነብ ምንም
ምርምር ሳናደርግ በቀጥታ የምንሰጣቸው ቀጥተኛ ፍች ሠም ይባላል፡፡ ወርቅ የምንለው
ደሞ የተለያዩ የቅኔ መፍቻ ስልቶችን ተጠቅመን የምናገኘው ሚስጥራዊ ፍች ምን ይባላል?
ወርቅ ይባላል ማለት ነው ፡፡

1. ሀኪም ቤት አልሄደች ያለችው ከቤት


እኔ ምን ላድርጋት ያችን ልጅ አሟት

37 ተ13 ፡ህብረቃሉ አሟት ሲሆን ሠም ወርቁ ደሞ ቤት ውስጥ ሆና ወሬ አወሩባት፡፡

38 መ/ርት ፡እሺ… ወርቁ ደሞ በክፉ አነሷት የሚል ወርቅ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ ይህን
ግጥም ሠምና ወርቁን ለማግኘት የተጠቀምንበት ስልት ለህብረቃሉ ስንት ፍች በመስጠት
ነው? ሁለት ፍች በመስጠት ነው፡፡ ምንም ሳናደርግ ከላይ ተነስተን (ግጥሙን አነበቡ)
ምንም ምርምር ሳናደርግ ከላይኛው ስንኝ ተነስተን የምናገኘው ፍች ፡፡ ልጅቷ ምን
ሆናለች ማለት ነው? ታማለች፡፡ ይህን ሰም እንላለን፡፡ አሟት የሚለውን ህመም ከሚለው
ፍች ደግሞ ሌላ ፍች ሁለተኛ ፍች ስንሰጠው ደሞ … ልጅቷን በምን አነሷት በክፉ አነሷት
የሚል ወርቅ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡ምነው አንድ ፋኖስ የላችሁ ኩራዝ ብቻ ቤታችሁ

39 ተ14፡ህብረቃሉ ኩራዝ ብቻ

40 መ/ርት ፡ኩራዝ ህብረቃሉ ብቻ የሚለውን ብንጨምረውም ባንጨምረውም ለውጥ


ስለማያመጣ ህብረቃሉ ማነው ኩራዝ

41 ተ14፡ሰሙ ደሞ ቤታችሁ በኩራዝ ብቻ የተሞላ ነው

42 መ/ርት ፡ የምታበሩት ምንደነው?ኩራዝ … ነው

43 ተ14 ፡ወርቁ ደሞ አጭር ናችሁ ነው፡፡ እሺ ... ይኸንን ግጥም ይኸንን ቅኔ ለመፍታት
የተጠቀምንበት ስልት ደሞ ምን መስጠት ነው?ፈሊጣዊ ፍች መስጠት ነው፡፡ ከላይ ስንኝ
ተነስተን ምነው አንድ ፋኖስ የላችሁ ኩራዝ ብቻ ቤታችሁ ስንል እናንተ መብራት
የምታበሩት በፋኖስ ሳይሆን በምንድነው? በኩራዝ ነው የሚል ስለምናገኝ ይህን ሰም
እንለዋለን፡፡ ኩራዝ የሚለውን ቃል ደሞ ፈሊጣዊ ፍች ስንሰጠው ኩራዝ ማለት ምን ማለት
ነው? አጭር ማለት ነው፡፡

እኔ የልጇ ልጅ እሷ የናቴ እናት

አኳኋኗ ሁሉ እንዳያት እንዳያት…እህ..

44 ተ15 ፡ ህብረቃሉ የሚለው እንዳያት እንዳያት

45 መ/ርት ፡ህብረቃላችን እንዳያት እንዳያት

46 ተ15፡ሰሙ ደሞ አኳኋኗ ሁሉ እንዳያት ነው

47 መ/ርት፡እንዳያት ነው

48 ተ15 ፡አዎ...ወርቁ ደሞ ምንደነው?እንዳያት እንዳያት ትፈልጋለች ወይም


እንድመለከታት ትፈልጋለች ፡፤ ማለት ነው፡፡

109
49 መ/ርት፡ በጣም አሪፍ ፡፡ እሺ … ህብረቃላችን ማነው?እንዳያት እንዳያት ነው፡፡
ከላይኛው ስንኝ ተነስተን እኔ የልጇ ልጅ እሷ የናቴ እናት ሲል ሠማችን ምንድነው? አያቴ
ናት ነው፡፡ ወርቃችን ደሞ እንዳያት እንዳያት የሚለው ከግጥሙ ስንኞች ውጭ ሌላ
ትርጓሜ ስንሰጠው ልጅቷ እኔን እንድመለከታት ትፈልጋለች፡፡ የሚል ወርቅ እናገኝለታለን
ማለት ነው፡፡

የልጃገረድ አውታታ

ከመንገድ ዳር ተኝታ

ተነሺ በሏት ምነው

ይህ ሁሉ አለማፈር ነው፡፡ እህ.. እሺ

50 ተ1 ፡ህብረቃል አለማፈር

51 መ/ርት ፡አለማፈር

52 ተ1 ፡ሰሙ ደሞ እፍረት የሌላት

53 መ/ርት ፡ሠሙ እፍረት የላትም እህ…

54 ተ1 ፡ወርቁ ደሞ ሰው ሁሉ ሟች ነው

56 መ/ርት፡ ሰው ሁሉ

57 ተ16 ፡ሟች ነው
58 መ/ርት ፡እሺ...ይኸንን ወርቅ ለማግኘት በድብቅ ስርዓት ድምፃዊ አፃፃፍ ለሁለት
ከፍለን ወደ ፊደላዊ አፃፃፍ ስንቀረው ምኑን እናገኛለን? ወርቁን እንገኛለን፡፡ ስርዓተ
ድምፃዊ አፃፃፍን ለማግኘት ለ ለማለት ምን እንላለን? ልኧ ማ ለማለት ምኣፈ ለማለት
ፍኧ ከዛ ማን አለን? ር ይኸንን እስንት እንከፍላለን? እሁለትኣልኧም/ ኣፍኧር እንደገና
ይኸንን ስርዓት ድምፃዊ አፃፃፍ ወርቁን ለማግኘት ወደ ምናዊ አፃፃፍ እንቀይራለን? ወደ
ፊደላዊ አፃፃፍ እንቀይራለን፡፡ኣ… ይወርዳል ምክንያቱም አናባቢዎች በቃል መጀመሪያ
ከመጡ እንደምን ይቆጠራሉ?እንደተነባቢ ..ይቆጠራሉልኧ… ለ ል ወደለ ስትቀየር ማን
ይጠፋል? ኧ ማ ቀረን? ም፡፡ ምንም የሚል ቃል መሠረትን አለም ከዛ ኣ ይወርዳል
ምክንያቱም አናባቢ በቃል መጀመሪያ ከመጣ እንደምን ይቆጠራል? እንደተነባቢ
ይቆጠራል፡፡ፍኧ ስንል ፍ ማን ይሆናል? ፈ ማን ይጠፋል? ኧ ማቀረን? ር ምን የሚል
ቃል መሠረትን?አለም አፈር አለም አፈር ማለት ሁለተኛው ትርጓሜ ምን ማለት ነው?ሰው
ሁሉ ሟች ነው… ማለት ነው፡፡ስለዚህ ወርቃችን ሰው ሁሉ ሟች ነው፡፡ ሰማችን ደሞ
ከላይኛው ተነስተን (ግጥሙን ደግመው አነበቡ) ቀጥታ ስንተረጉመው ልጅቷ ምን የላትም?
እፍረት የላይኖረዋል ማለት ነው በዚህ መሠረት መፀሀፋችሁን መቶ ስልሳ ላይ ያለውን ከሀ
- ሸ የተሰጠውለሚቀጥለው ክ/ጊዜ የቤት ስራ ሠርታችሁ ትመጣላችሁ፡፡

(የእለቱ ክ/ጊዜ አበቃ)

110
አባሪ አራት

ምዝግብ መረጃ አራት


ክፍል ሠ
የተማሪ ቁጥር 52
የጊዜ መጠን 40 ደቂቃ

የእለቱ ትምህርት ርዕስ፡- ሰዋሠውና ስነ ፅሁፍ


መምህርቷ የባለፈው ክፍለ ጊዜ ይዘት ጠየቁ

01 መ/ርት፡ በባለፈው ክፍለ ጊዜ ምን ተማርን?ምን ተማርን?

02 ተ1 ፡በባለፈው ክ/ጊዜ የተማርነው የቃላት መጥበቅና መላላት ነው፡፡ በአማርኛ ቋንቋ


በአንዳንድ ቃላት ጠብቀውና ላልተው ሲነበቡ የተለያየ ፍቺ እንደሚሰጡ ተምረናል፡፡

03 መ/ርት ፡ እሺ ጥሩ… በባለፈው ክ/ጊዜ በቃላት ውስጥ ያሉ ሆሄዎች ሲጠብቁና ሲላሉ


የሚሰጡትን ፍች አይተናል አደል

04 ተጋ ፡ አዎ

05 መ/ርት ፡አብዛኛው ጠባቂ ድምፆች ሶስት ከሆነ የት ነው የሚገኘው ብለናል? በቃላት


መካከል ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በየት ይገኛሉ ብለናል? በቃላት መጨረሻ ይገኛል
ብለናል፡፡ አንድም ሆሄ ወይም ድምፅ በቃል መጀመሪያ ምን አይልም ብለን ነበር?
አይጠብቅም ብለናል፡፡ መልመጃ ሰጥቻችኋለሁ አደል?

06 ተጋ ፡ አዎ

07 መ/ርት ፡እስቲ አውጡ ደብተራችሁን አውጡ ገፅ ስንት ነው መቶ ሀያ ስምንት ሰዋሰው


ክፍሎችን ተጠቅማችሁ ምን እንድትሰሩ ነው? ዐ.ነገር እንድትሰሩ ነው ብለን ነበር፡፡ ስንት
ዓይነት የቃል ክፍሎችን አሉ ብለን ነበር እጅ አውጥታችሁ…

08 ተ2 ፡ አምስት የቃል ክፍሎች አሉ፡፡ ስም፣ ቅፅል፣ ግስ፣ ተውሳከ ግስና መስተዋድድ

09 መ/ርት ፡ እሺ… ጥሩ…. አዎ… አምስት አይነት የቃል ክፍሎች እንዳሉ


አይተናል፡፡ስም፣ ግስ፣ ቅፅል፣ ተውሳከ ግስ እና መስተዋድድ (በማለት በቁጥር ሰሌዳው ላይ
ፃፉ) እነዚህን አይተናል፡፡ እነኝህ የቃል ክፍሎች እነሱን ተጠቅማችሁ ምን መስራት ነው?
ዐ.ነገር… የተሰጣችሁ የቃል ክፍል አለ በዛ ተጠቅማችሁ ዐ.ነገር እንድትሰሩ
ነው፤የተሰጣችሁ እስኪ የሚሰራልኝ አንደኛ.. ቃሉ ማነው? በሬ ይላል.. እስቲ በዛ
የሚሰራልኝ?.. በሬ በሚለው ዐ.ነገር የሚሰራልኝ …

10 ተ3 ፡ በሬ በሚለው በሬው ክፉኛ ወደቀ

11 መ/ርት ፡ እ.. ቃሉ በሬ ነው፡፡ በሬው ክፉኛ ወደቀ፡፡ እሺ.. ጥሩ..ትክክል ናት፡፡


ሌላስ.. ሌላ.. ደግ.. እህ

12 ተ4 ፡ አበበ በጣም ደግ ነው፡፡

111
13 መ/ርት ፡ አበበ… በጣም… ደግ… ነው፡፡ደግ ምንድነው በዚህ ዐ.ነገር እ…ሌላ…
ሶስተኛው ማለት ነው፡፡ እስቲ..ቀጥል..

16 ተ5 ፡ አበበ በጣም ተጫዋች ነው፡፡

17 መ/ርት ፡እ?

18 ተ5 አበበ በጣም ተጫዋች ነው፡፡

19 መ/ርት፡ እ… እ…ትክክል ነው እንዴ

20 ተጋ ፡አደለም!

21 መ/ርት፡ እስቲ ይኸን የሚሰራልኝ ተጫወተ ነው የሚለው

ግሱ ተጫወተ ነው ግስ ነው፡፡ እህ…

22 ተ6 ፡ አየለ እግር ኳስ ተጫወተ፡፡

23 መ/ርት ፡ አየለ እግር ኳስ ተጫወተ፡፡ እሺ አራተኛ… አራተኛው

24 ተ7 ፡ እሺ … ደን የሚለው ነው፡፡ ደን ከጨፈጨፍን ንፁህ አየር አናገኝም፡፡

25 መ/ርት፡ ደን ከጨፈጨፍን ንፁህ አየር አናገኝም፡፡ ይቻላል፡፡ ጥሩ ነው፡፡ እሺ


አምስተኛው … አምስተኛው፡፡

26 ተ8 ፡ስለ ነው የሚለው ስለ አበበ ኑሮ ሰዎች ተገረሙ፡፡

27 መ/ርት ፡ እስኪ ድገመው?

28 ተ8 ፡ ስለ አበበ ኑሮ ሰዎች ተገረሙ፡፡

29 መ/ርት ፡ ስለ አበበ ኑሮ ሰዎች ምን አሉ?

30 ተ8 ፡ ተገረሙ

31 መ/ርት ፡ ተገረሙ? ተገረሙ ነው ያልከኝ? ተገረሙ፡፡እሺ… ሌላስ ስለ የሚለው .. ሌላ

32 ተ9 ፡ ፈጣን በቅሎ አለችኝ፡፡

33 መ/ርት ፡ እ? ፈጣን የሚለው ቅፅል ነው፡፡ እህ…

34 ተ9 ፡ ፈጣን በቅሎ አለችኝ፡፡

35 መ/ርት ፡ ፈጣን በቅሎ አለችኝ… እሺ.. ጥሩ.. እሺ.. ሰባተኛው.. ቶሎ..

ነው የሚለው፡፡

36 ተ10 ፡ አበበ ወደ ት/ቤት ቶሎ ቶሎ ይሄዳል

37 መ/ርት ፡ እእ… አበበ ወደ ት/ቤት ቶሎ ቶሎ ሄደ፡፡ ሌላስ-- ጥሩ.. እህ..

38 ተ11፡ አበበ ከት/ቤት ቶሎ መጣ፡፡

112
39 መ/ርት፡ አበበ ከት/ቤት ቶሎ መጣ፡፡ ጥሩ … ስምንተኛው እህ

40 ተ12 ፡አበበ ወደ ት/ቤት ሄደ ፡፡

41 መ/ርት ፡ እ? ወደ ነው መስተዋድድ ነው ፡፡

42 ተ12 ፡ ወደ ት/ቤት ሄደ

43 መ/ርት ፡አበበ ወደ ት/ቤት ሄደ፡፡ ይቻላል ወደ የሚለው መስተዋድድ ነው እሺ…

ዘጠነኛው… እህ?

44 ተ13 ፡ ደመቀ ፍየሉን አሰረ ፡፡ እህ

45 መ/ርት ፡ደመቀ ፍየሉን አሰረ ፡፡ አስረኛው

46 ተ14 ፡አስቴር ክፉኛ ታመመች ፡፡

47 መ/ርት ፡እሺ … አስቴር

48 ተጋ ፡ክፉኛ ታመመች፡፡ክፉኛ የሚለው ኧ? ተውሳከግስ፡፡ ይበቃናል ይህን ካየን


ሌላው ሁለተኛው ቅንፍ ውስጥ ያው ግሶች አሉ ፡፡ ግሶችን በምሳሌው መሠረት በክፍት
ቦታ በሚስማማው መልኩ በመቀየር ሌሎች ግሶች በመቀየር ዐ/ነገሩን አሟሉ ይላል፡፡ ምሳሌ
እዚህ ጋ ህፃኑ ልጅ ልብሱን በእናቱ አጠበ ይላል፡፡ ግሱ አጠበ ሳይሆን መሆን ያለበት
ምንድነው ?

49 መ ተ ፡ አሳጠበ

50 መ/ርት፡አሳጠበ ነው መሆን ያለበት እስቲ በዚህ መሰረት አንደኛውን የሚሰራልኝ…


አንደኛውን የሚሰራልኝ

51 ተ15 ፡ ህብረተሰቡ ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰሩ ነው የሚለው አሳሰሩ

52 መ/ርት፡እሺ ህብረተሰቡ ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰረ ነው የሚለው እህ


… አሳሰረ … ትክክል ነው

53 ተጋ ፡አሳሰሩ …አሳሰሩ

54 መ/ርት፡እ?ወንጀለኛውን ለፓሊስ በመጠቆም አሰረ አሳሰሩ ሳይሆን አሳሰረ ነው እንጂ


አሳሰሩ አይሆንም ፡፡ ሁለተኛው እህ

55 ተ16፡የስፖርት ልብሱን ለብሶ ሰዉነቱን አሞቀ ነው የሚለው አሟሟቀ

56 መ/ርት ፡የስፖርት ልብሱን ለብሶ ሰውነቱን አሞቀ ነው የሚለው አሟሟቀ ብላለች


ትክክል ናት አዎ የስፖርት ልብሱን ለብሶ ሰውነቱን ምን አረገ ? አሟሟቀ ሶስተኛ …

57 ተ17፡ ደረቅ እንጨት ሰበሰበና ክብሪት ተጠቅሞ እሳቱን አቃጠለ ነው የሚለው


አቀጣጠለ

58 መ/ርት ፡እሺ … አቀጣጠለ ትክክል ናት፡፡

59 ተጋ ፡ አዎ

113
60 መ/ርት፡ትክክል ናት ደረቅ እንጨት ሰበሰበና ክብሪት ተጠቅሞ እሳቱን ምን አለ?
አቃጠለ ሳይሆን አቀጣጠለ፡፡ አራተኛው

61 ተ1 ፡ሀገር ጎብኝው ያለፍቃድ አውሬ ገደልኩ ነው የሚለው አልገደልኩም ብሎ


ተከራከረ

62 መ/ርት ፡ ሀገር ጎብኚው ያለፍቃድ አውሬ አልገደልኩም ብላለች ትክክል ናት?

63 ተጋ ፡ አዎ

64 መ/ርት ፡ አዎ አልገደልኩም ብሎ ተከራከረ ፡፡ አልገደልኩም ፡፡ እሺ አምስተኛው


… አምስተኛ … እህ

65 ተ18 ፡ ቆሻሻ መጠያ ጉድጓድ በሰራተኛ ቆፈርኩ ነው የሚለው አስቆፈርኩ

66 መ/ርት ፡ እ? የቆሻሻ መጠያ ጉድጓድ በሰራተኛ ቆፈርኩ ነው አስቆፈርኩ፡፡ ሌላም


የቤት ስራ አለን አይደል ? ሌላው ክፍል አምስት ምሳሌያዊ አነጋገሩ ተሰጥቷችኋል፡፡ እ
ማለት ለአንዱ መነሻ በማድረግ ለምሳሌ የመተባበርን አስፈላጊነትን የሚያስተምሩ
ምሳሌያዊ አነጋገሮች አሉ፡፡ እነሱም ምንድናቸው? ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ፣ አንድ
አይነድ አንድ አይፈርድ ፣ በአንድ አይጨበጨብም ፡፡ ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ
ለሀምሳ ሰው ጌጡ የሚል አለ እነዚህ ምንድናቸው ? የመተባበር አስፈላጊነት የሚያስተምሩ
ናቸው እናንተ እስቲ ከዚህ ውስጥ መርጣችሁ ሰርታችሁ እንድትመጡ ብያችኋለሁ፡፡ እሺ
…ቆይ… እሺ

67 ተ7 ፡ ስድስተኛውን መርጫለሁ ፡፡ርህራሄና ይቅርታ ማድረግ የሚያበረታቱ ሲታጠቡ


እስከክንድ ሲታጠቁ ከሆድ

68 መ/ርት ፡ ርህራሄና ይቅርታ ማድረግን የሚያበረታቱ… እህ?

69 ተ7 ፡ ሲታጠቡ እስከክንድ ሲታረቁ እስከሆድ

70 መ/ርት ፡ እህ? ሲታጠቁ እህ

71 ተ7 ፡ ሲታጠቡ እስከክንድ ሲታረቁ ከሆድ

72 መ/ርት ፡ እሺ ሌላ

72 ተ3 ፡ የችኮላ ጎጂነትን የማስተዋል ጠቀሜታን የሚያመላክቱ የቸኮለች አፍሳ ለቀመች

74 መ/ርት ፡ ቆይ (በማለት ሀሳቡን በጥቁር ሰሌዳው ላይ ፃፉ)

75 ተ3 ፡ የጅብ ችኩል የበሬ ቀንድ ይነክሳል

76 መ/ርት ፡ የቸኮለች አፍሳ ለቀመች

77 ተ3 ፡ የጅብ ችኩል የበሬ ቀንድይ ነክሳል፣ የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳ ሰንበሌጥ፣

ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል፡፡

78 መ/ርት እሺ … ሌላስ … እስቲ … የችኮላ ጎጂነትን … እንትን የሚሉ

79 ተ19 ፡የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች

114
80 መ/ርት ፡ የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እሺ ሌላስ የችኮላ ጎጂነትን

81 ተ20 ፡ አተርፍ ባይ አጉዳይ

82 መ/ርት ፡ አተርፍ ባይ አጉዳይ … እሺ … ጥሩ ያው የችኮላ ጎጂነትን እንትን የሚሉ


ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል ፤ የነቶሎቶሎ ቤት ግርግዳው ሰንበሌጥ፤ የቸኮለች አፍሳ
ለቀመች ፤ ችኩል …ችኩል ቅቤ ያንቀዋል፡፡ እ ችኩል እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ይገባል፤
ችኩል አፍ ሞትን ይመርጣል፡፡ እነዚህ የችኮላ አላስፈላጊነትን የሚያስተምሩ ምሳሌያዊ
አነጋገሮች ናቸው፡፡ እስቲ የመረጣችሁትን ምሳሌያዊ አነጋገር … ሌላ እህ

83 ተ2 ፡ አምስተኛውን የመጠንቀቅን አስፈላጊነት የሚመክሩ ለሚለው

84 መ/ርት፡ እህ

85 ተ2 ፡ ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ

86 መ/ርት፡ እህ

87 ተ2 ፡ ያልጠረጠረ ተመነጠረ

88 መ/ርት፡ እሺ የመጠንቀቅን አስፈላጊነት የሚመክሩ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ታሞ


ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ፣ያልጠረጠረ ተመነጠረ… ሌላው ሳይቃጠል በቅጠል
…ጥሩ …ሌላስ… እህ

89 ተ4፡ስድስተኛው ርህራሄና ይቅርታ ማድረግን የሚያመላክቱ የሚለው መተው ነገሬን


ከተተው … ደሞ ሰው ሆኖ የማይበድል እንጨት ሆኖ የማይጨስ

90 መ/ርት ፡ እሺ … ሌላስ … ሌላ …ሌላ ደስ ያላችሁን ከዚህ ውስጥ አንዱን መርጣችሁ


የሰራችሁትን … እስቲ ሰነፍን … የሚወቅሱ … ሰነፍን የሚወቅሱ

91 ተ12 ፡ ሰነፍ እረኛ ከሩቅ ይመልሳል

92 መ/ርት ፡ ሰነፍ እረኛ ከሩቅ ይመልሳል ፡፡…. ሌላስ …ሌላ ሰነፍ ሰው እ ? ያሰንፋል
፣ ሰነፍ ውሃ ውስጥ ገብቶ ያልበዋል፣ ሰነፍ ውሃ ውስጥ ገብቶ ያልበዋል፣ ሰነፍ ገበሬ
በመስከረም

93 ተጋ ፡ ያርሳል

94 መ/ርት፡ ያርማል እእእ… ይበቃናል መልመጃ ሌላም አለን አደል?

95 ተጋ ፡ አዎ

96 መ/ርት ፡ የክለሳ ጥያቄዎች አሉ ገጽ 130 ፣131 ላይ የክለሳ ጥያቄዎች ከአንደኛው


እስከ አምስተኛው እስቲ … ያንደኛውን … አንደኛውን ተውት ብያችኋለሁ አደል? እስቲ
ሁለተኛውን … ሁለተኛው ከዚህ በታች የቀረቡት ቃላት ጠብቀውና ላልተው ሲነበቡ
የሚሰጡትን ፍቺ በዐረፍተነገር ውስጥ አሳዩ ነው የሚለው እስቲ … ቃሉ ማነው ?

97 ተ9 ፡ይመራል ጠብቆ ሲነበብ ይመራል (ራ ጠብቆ ይነበባል)

98 መ/ርት፡ ዐ/ነገር ሠርተህ ነው!

115
99 ተ9 ፡ የ… የ… የሀይስኩል ት/ቤታችን በርዕሰ መምህሩ ይመራል፤ ዛሬ የበላሁት ሙዝ
ይመራል፡፡

100 መ/ርት ፡በርዕሰ መምህሩ ይመራል፤ ዛሬ የበላሁት ሙዝ ይመራል ሌላ እህ ጥሩ

101 ተ21 ፡ ሲጠብቅ የኢትዮጵያ ህዝብ በአብይ ይመራል፡፡ሲላላ ደግሞ አለቃው


የክፍሉን ፀጥታ ይመራል፡፡

102 መ/ርት፡ በአብይ ይመራል፡፡ሁለተኛ ያልሽው ምንድነው?

103 ተ22 ፡ አለቃው የክፍሉን ፀጥታ ይመራል፡፡

104 መ/ርት፡ አለቃው የክፍሉን ፀጥታ ይመራል ማነው የጠበቀው ሆሄ እሺ የኢትዮጵያ


ህዝብ በአብይ ይመራል፡፡ ራ ነው እዚህ ጋ ከዛ ከዛ የክፈሉን ፀጥታ ይመራል ሌላስ …
ይህንኑ እህ …

105 ተ23 ፡ ልጁ ሰዎች ይመራል ፤ሬት ይመራል፡፡

106 መ/ርት ፡ ራ ጠብቃ ነው … ሌላ

107 ተ12 ፡ እንስራ ነው የሚለው ሀገራችንን ተባብረን እንስራ አሉ ጠቅላይ ሚኒስቴራችን


እእእ …. አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው

108 መ/ርት ፡ እሺ በመጀመሪያው ዐ/ነገር ማንኛው ነው የጠበቀው? እ … ሆሄ ፊደል

109 ተ12 ፡ እንስራ

110 መ/ርት ፡ እኮ ማንኛው?

111 ተ12 ፡ ራ… ስ

112 መ/ርት፡ ራ… ስ … እስቲ ሌላስ እስቲ እሷ በሰራችው ዐ/ነገር ጠባቂው ድምጽ

የትኛው ነው? ዐ/ነገሩን ምን ነበር ያልሽው?

113 ተ12 ፡ሀገራችን ተባብረን እንስራ

114 መ/ርት ፡ በሀገራችን ተባብረን እንስራ …የጠበቀው ሆሄ ማነው? እዚህ ጋር … ስ …


ን ናት ፡፡ ን ናት ፡፡ ቀጣይ ዐ/ነገር

115 ተጋ ፡ አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው

116 መ/ርት ፡ አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው እዚህ ጋር ጠባቂዋ ድምጽ ስ ሳትሆን ን


ናት፡፡ መጀመሪያ ማለት አገራችን …በአገራችን… ጠንክረን እንስራ ስንል ን ናት
የጠበቀችው አለሚቱ እንስራውን ሰበረችው ን ምን ሆና ነው? ላልታ ነው ፡፡ ጠባቂው
ድምጽ ስ ሳትሆን ን ናት እ ሐ … ሐ ቀና ይላል እህ

117 ተ2 ፡ ከበቤቴ ወጥቼ ቀና ስል ዳመናው አርግዟል ፡፡ በትምህርት ቤታችን ቀና


መሆን አለብን ፡፡

118 መ/ርት፡ ማንኛው ነው የጠበቀው ወይስ የላላው? በሁለቱም ዐ/ነገር ይህኛው ላልቶ
ነው ይኸኛው ጠብቆ ነው የምትለው?

116
119 ተ2፡ ቀና ስል ና ላልታለች ቀና ስል ደግሞ ና ጠብቃለች፡፡

120 መ/ርት ፡ እሺ …ሌላስ …ሌላስ … እህ እሺ መ … እህ

121 ተ13 ፡ ቃሉ የሚለው ገና ነው ላልቶ ሲነበብ ፀሀይዋ ገና አልወጣችም ጠብቆ ሲነበብ


ደሞ አመት በአል ገና ደርሷል የሚጠብቀው ና ነው፡፡

122 መ/ርት ፡ የገና በአል ደርሷል፡፡ጠባቂዋ ድምጽ ማናት?ና ናት እህ

123 ተ2 ፡ገና ነው ሁለቱም ጋር የሚጠብቀው ገና ና ገና ይሆናል፡፡ ገና ትናንትና

መጥታለች፡፡ ገና ሲሆን ደሞ ለገና በአል ቤተሰቦቼ ጋር እወርዳለሁ፡፡

124 መ/ርት ፡ለገና በአል ቤተሰቦቼ ጋር እሄዳለሁ እሺ ሌላስ እሺ፡፡ስናጠብቀው ማናት?


ገና የጌታችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል ነው፡፡ ብንል ጠባቂዋ
ድምጽ ማናት ? ና ናት እ ልጁ ገና ትምህርት ቤት አልመጣም ብንል እዚህ ጋር ና ምን
ሆና ነው ? ላልታ ነው ፡፡

125 ተ24 ፡መጋዝ ነው የሚለው ሰዉ ወደ ለቅሶ ቤት መጋዝ ጀመረ ፡፡ ይህ ጠብቆ ነው


ላልቶ ደሞ የከበደ መጋዝ አይቆርጥም፡፡

126 መ/ርት ፡ የከበደ መጋዝ … እ?

127 ተጋ ፡ አይቆርጥም፡፡

128 መ/ርት ፡ አይቆርጥም ሌላ… እህ …

129 ተ25፡ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መጋዝ ጀመሩ፡፡ ሲጠብቅ ነው ሲላላ ደሞ


ሰዎች እንጨት ለመቁረጥ መጋዝ ፈለጉ፡፡

130 መ/ርት፡ፈለጉ…ሌላስ …ጥሩ …ሌላ… እስቲ…እሺ መጋዝ የሚለው ቃል መጋዝ


ለእንጨት መቁረጫ የሚያገለግል መሳሪያ ነው፤መጋዝ ለእንጨት መቁረጫ የሚያገለግል
መሳሪያ ነው፡፡ ይኸ ጋ ምን ሆና ነው?ላልታ ማሳው ላይ የታጨደው ጤፍ ወደ አውድማው
መጋዝ አለበት መወሰድ ስለዚህ ጋ እዚህ ጋ ምን ሆና ነው? ጠብቃ ነው፡፡ ሌላው
ሶስተኛውን ደግሞ እንስራ … ሶስተኛውን እህ… ትዛዙን አንብበው?

131 ተ3 ፡ ዐ/ነገር በተሰመረባቸው ቃላት ከየትኛው በቃል ክፍል እንደተመደቡ ግለፁ፡፡


ሀ/አበበ ጎበዝ ተማሪ ነው ጎበዝ የሚለው ቅጽል ነው

132 መ/ርት፡ እሺ … አበበ ጎበዝ ተማሪ ነው የሚለውን የተሰመረበት ጎበዝ ነው ጎበዝ


ከየትኛው የቃል ክፍል ይመደባል? ከቅጽል ብላለች ትክክል ነች ?

133 ተጋ ፡ አዎ

134 መ/ርት ፡አዎ ጎበዝ የሚለው ቅጽል ነው ሁለተኛው …ሁለተኛው እህ?

135 ተ26 ፡ የተናደደ ሰው አደጋ ሊደርስበት ይችላል፡፡ የተናደደ የሚለው ቅጽል

136 መ/ርት፡ተናደደ ሰው አደጋ ሊደርስበት ይችላል፡፡ ነው የሚለው ቅጽል ነው ብላለች …


ሌላ

137 ተ27 ፡ ግስ

117
138 መ/ርት ፡ ግስ ነው፡፡

139 ተ28 ፡ መስተዋድድ

140 ተጋ ፡ ግስ ነው

141 መ/ርት፡ እህ … አዎ … የተናደደ የሚለው በራሱ ግስ ነው ሶስተኛው እህ …

142 ተ12፡ ለስራ ወደ ገጠር ሄደ ፡፡ ወደ የሚለው መስተዋድድ

143 መ/ርት፡ የተሰመረበት ለ እና ወደ ነው ወደ የሚለው መስተዋድድ ነው ለ ሳ?

144 ተ12 ፡ መስተዋድድ

145 መ/ርት፡ ለ እና ወደ የሚለው መስተዋድድ ነውትላለች ትክክል ናት? ለ እና ወደ


ምንድናቸው ? መስተዋድድ ናቸው፡፡ አራተኛ

146 ተ29 ፡ አውሮፕላኗ እበረረች ሄደች ፡፡ እየበረረች ተውሳከግስ

147 መ/ርት፡አውሮፕላኗ እበረረች ሄደች፡፡እየበረረች ተውሳከግስ ነው ብሏል ትክክልነው?

እህ ትክክል ነው፡፡ እሱ እ አውሮፕላኗ እበረረች ሄደች፡፡ እየበረረች የሚለው ምንድነው?

ተውሳከግስ …ተውሳከግስ እሺ ቀጥይ፡፡

148 ተ30 ፡ የችኮላ ስራ አያስተማምንም ስራ የሚለው ስም፡፡

149 መ/ርት ፡ስራ የሚለው የቃል ክፍሉ ስም ነው ትክክል ናት፡፡

150 ተጋ ፡አዎ

151 መ/ርት፡አዎ ስራ የሚለው የቃል ክፍሉ ምንድነው?ስም ነው የዘይቤ አይነቶች ስንትነ


ናቸው?

152 ተ20 ፡ አነፃፃሪ ዘይቤ …ስምንት ናቸው፡፡ የዘይቤ አይነቶች እነሱም አነፃፃሪ
ዘይቤ፣ተለዋጭ ዘይቤ ፣ሰወኛ ዘይቤ፣እንቶኔ ዘይቤ እንደገና ደግሞ ተምሳሌት
ዘይቤ፣አካባቢያዊ ዘይቤ፣ ምፀትና ኩሸት ወይም ግነት የምንላቸው ናቸው፡፡

153 መ/ርት ፡ኧ ዘይቤዎች ብዙ አይነት አሉ እኛ ግን ስምንቶቹን ነው የምናየው እነሱም


ምንድናቸው የመጀመሪያው አነፃፃሪ ዘይቤ ምንድነው ብለን ነበር?አነፃፃሪ ዘይቤ …አነፃፃሪ
ዘይቤ ማለት ምን ማለት ነው? እ

154 ተ1፡አነፃፃሪ ዘይቤ ማለት ኧኧኧ…. ሁለት ነገሮችን ፣ሀሳቦችን ፣ድርጊቶችን ወዘተ
በማነፃፀር ወይም በማወዳደር የሚፈጠር ዘይቤ ነው፡፡

155 መ/ርት ፡ እሺ አነፃፃሪ ዘይቤ የምንለው ጥሩ ነው ሁለትና ከዛ ባለይ የሆኑ


ድርጊቶችን ሀሳቦችን በማነፃፀርና በማወዳደር የሚፈጠር የዘይቤ አይነት ሲሆን ማነፃፀሪያ
ቃላትን ይጠቀማል፡፡ እነሱም ፡- እንደ ፣ያክል፣ ይፋካከር ፣ይመስል… የሚሉ ማነፃፀሪያ
ቃላትን ይጠቀማሉ ፡፡ ተነፃፃሪ ዘይቤ ጎልቶ እንዲወጣ የተፈለገው ነገር ምንድነው
ብያችሁ ነበር? እ?

118
156 ተ2 ፡ አነፃፀሪ ዘይቤ ሁለትና ከዛ በላ የሆኑ ነገሮችን በማነፃፀር የሚገለጽ ጎልቶ
የሚወጣው ነገር ተገላጭ ይባላል፡፡ ያንን ደግሞ ጎልቶ የሚያወጣው ነገር ገላጭ
በሁለታቸው መካከል የምንጠቀማቸው ቃላት ደግሞ ሰበበ ንጽጽር

157 መ/ርት ፡ እሺ …ጥሩ ነው ያው በአነፃፃሪ ዘይቤ ጎልቶ እንዲወጣ የተፈለገው ነገር


ተገላጭ ሲባል ተገላጩን ደግሞ አድምቆ ፣አጉልቶ ያሳየው ደግሞ ምን ይባላል? ገላጭ
ሲባል በተገላጩና በገላጩ ነገር መካከል ያለው ምን ይባላል? ሰበበ ንጽጽር እንደሚባል
አይተናል ሁለተኛው ደግሞ ምን ዘይቤ ነበር?

158 ተጋ ፡ ተለወጭ

159 መ/ርት ፡ እጅ አውጥታችሁ…እጅ አውጥታችሁ

160 ተ31 ፡ተለዋጭ ዘይቤ የአንድን ባህሪያት ወደሌላው በመስጠት የዘይቤ አይነት ነው፡፡
ለምሳሌ ልጅቱ ፀሀይ … ልጅቱ በፀሀይነት … ልጅቱ በጸሀይነት ልጅቱ ቆላ ተሰጠው …
ለሚለው አብነት ጅብ ነው

161 መ/ርት ፡ እሺ ጥሩ ያው ተለዋጭ ዘይቤ የምንለው የአንድን ነገር ድርጊት ፣ችሎታ


ለሌላ ነገር በመስጠት ምን የሚል ነው?የሚፈጠር የዘይቤ አይነት ነው ተለዋጭ ዘይቤ
እጄ በረዶ ሆነ ብንል ቀጥሎ ዘይቤና ፈሊጥ በማለት መልሱ አንቺ ምድር ፍረጂኝ ምን
አይነት ዘይቤ ነው?

162 ተ4 ፡ ፈሊጥ ነው፡፡

163 መ/ርት፡ ፈሊጥ ወይስ ዘይቤ

164 ተ2 ፡ ዘይቤ ነው፡፡

165 መ/ርት ፡ ዘይቤ ነው፡፡ምን አይነት ዘይቤ … ምን ዓይነት ዘይቤ

168 ተ32፡ ተምሳሌት ዘይቤ

169 መ/ርት ፡ ተምሳሌት ዘይቤ? አይደለም እህ?

170 ተ4፡ አነፃፃሪ ዘይቤ

171 መ/ርት ፡አነፃፃሪ ዘይቤ

172 ተ33፡ ሰወኛ ዘይቤ

173 መ/ርት ፡ሰወኛ ዘይቤ … ሰወኛ ዘይቤ እህ

174 ተ34 ፡ ግነት ዘይቤ

175 መ/ርት ፡ግነት ዘይቤ (እህህ የሚል የሳቅ ድምፅ አሰማች)

176 ተ4 ፡ እንቶኔ ዘይቤ

176 መ/ርት ፡ እንቶኔ ዘይቤ (በእርግጠኝነት ድምፅ) አንቺ ምድር ፍረጅኝ እያለ ነው
እኮ አንቺ ምድር ፍረጂኝ የሚለው ዘይቤ ነው፡፡ ምን ዓይነት ዘይቤ ነው?እንቶኔ ዘይቤ
ነው፡፡ ሐ ልብ ገዛ ይላል፡፡ የሚለው ምንድነው?

119
177 ተ35 ፡ፈሊጥ

178 መ/ርት፡ ፈሊጥ ነው፡፡ልብ ገዛ የሚለው ምንድነው?ፈሊጥ ነው፤ጥሩ … መ ይናገር


ሀውልቱ … ይናገር ሀውልቱ እ…

179 ተ31 ፡ዘይቤ

180 መ/ርት ፡ እ?

181 ተ31 ፡ዘይቤ

182 መ/ርት ፡ትክክል ናት፡፡ምን ዓይነት ዘይቤ?የዘይቤውን ዓይነት ንገሪኝ?

183 ተ31፡ ሰወኛ

184 መ/ርት፡ እ?

185 ተ31 ፡ሰወኛ

186 መ/ርት፡ሰወኛ… ዘይቤ ነው?...እህ

187 ተ3 ፡ፈሊጣዊ

188 መ/ርት ፡ዘይቤ ነው ምን ዓይነት ዘይቤ ይላችኋል?

189 ተ36፡ ፈሊጣዊ

190 መ/ርት፡እንዴ…ፈሊጣዊ የሚባል ዘይቤ አለ እንዴ?

191 ተ12 ፡እንቶኔ ዘይቤ

192 መ/ርት ፡እንቶኔ ዘይቤ ፡፡እንቶኔ ዘይቤ ነው፡፡እ…ሠ ራሷን ቻለች ይላል፡፡ ራሷን
ቻለች

193 ተ37 ፡ዘይቤ

194 መ/ርት ፡ ዘይቤ እህ …

195 ተ38 ፡ፈሊጥ

196 መ/ርት፡ፈሊጥ ነው ዘይቤ ሳይሆን ፈሊጥ ነው፡፡ረ ልጁ አንበሳ ነው፡፡ልጁ አንበሳ


ነው፡፡ እህ

197 ተ39 ፡ዘይቤ ነው፡፡

198 መ/ርት፡ ዘይቤ ነው፡፡

199 ተ39 ፡ተለዋጭ ዘይቤ

200. መ/ርት ፡ምን ዓይነት ዘይቤ? ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ሌላው ሰ በሬ ወለደ ይላል፡፡
በሬ ወለደ እስቲ እህ…

201 ተ40 ፡ተምሳሌት ዘይቤ

120
202 መ/ርት፡ተምሳሌት ዘይቤ ነው… ሌላስ ተምሳሌት ዘይቤ ነው… ሌላስ

203 ተ35 ፡ፈሊጥ ነው፡፡

204 መ/ርት፡ ፈሊጥ ነው፡፡ ፈሊጥ ነው፡፡ በሬ ወለደ የሚለው ፈሊጥ ነው እንጂ ዘይቤ
አይደለም፡ ሸ ሆድና ጀርባ ይላል፡፡

205 ተ12 ፡ፈሊጣዊ

206 መ/ርት፡ ፈሊጥ ነው፡፡እሺ ሌላ ጥያቄዎች አሉን፡፡ ገፅ 78 ላይ የክለሳ ጥያቄዎቹን


አሁን እንሰራለን፡፡ እስቲ አንደኛውን የሚሰራልኝ? የክለሳ ጥያቄ አንደኛ …እስቲ
ሌሎቻችሁሳ

207 ተ2፡ የመኝታ ክፍሉ በቂ ብርሀን ስላላገኘ ጨልሟል ነው የሚለው በሚለው ዐ.ነገር
ውስጥ ብርሀን የሚለው ቃል አገልግሎት ላይ የዋለው በእማሬያዊ ወይስ ፍካሬያዊ ነው
የሚለው ብርሀን የሚለው በቀጥታ ብርሀን የሚለውን ትርጉም ይዞ ስለሆነ የገባው ይህ
ዐ.ነገር ምንደነው? እማሬያዊ …እ እ …እማሬያዊ ትርጉም ይዞ ነው የገባው፡፡

208 መ/ርት፡ እሺ ትክክል ነው፡፡ የመኝታ ክፍሉ በቂ ብርሀን ስላላገኘ ጨልሟል በሚለው
ዐ.ነገር ብርሀን የሚለው ቃል የገባው እማሬያዊ ነው ወይስ በፍካሬያዊ ፍቺ ነው የሚለው
በምን ፍቺ ነው የገባው? ትክክል ነው እማሬያዊ ፍቺ ነው ወይም በቀጥታ ነው የገባው
የቃሉ እማሬያዊ ፍቺ ምንደነው ብለናል? የቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ ወይም መዝገበ ቃላዊ ፍቺ
ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዐ.ነገር ውስጥ የገባው ብርሀን የሚለው የገባው በእማሬያዊ ፍቺ ነው፡፡
ሌሎች ጥያቄዎች አሉ የተወሰኑ ደቂቃ ተወያዩባቸው፡፡ (ጥያቄውን ሳይሰሩ የዕለቱ ክ/ጊዜ
ተጠናቀቀ)

121
አባሪ አምስት

ምዝግብ መረጃ አምስት


ክፍል ሠ
የተማሪ ቁጥር 46
ጊዜ 40 ደቂቃ
የትምህርቱ ርዕስ፡-ቃላት እና ዐ.ነገር
በቃላቱ ሀረግና ዓረፍተነገር መስርቱ
01 ተ1፡ ትልቅ፣ ትልቅ በሬ አበበ ዛሬ ትልቅ በሬ ገዛ

02 መ/ርት፡ እሺ አበበ ዛሬ ትልቅ በሬ ገዛ፡፡ መጀመሪያ ስማዊ ሀረጉን መስርትልኝ!

03 ተ1፡እ…ስማዊ ሀረጉ ትልቅ በሬ ነው፡፡ ዐ/ነገሩ ደግሞ አበበ ዛሬ ትልቅ በሬ ገዛ

04 መ/ርት፡ትልቅ በሬ … አበበ ዛሬ ትልቅ በሬ ገዛ፡፡ እሺ … ጥሩ

05 ተ2፡ ቀይ መጀመሪያ ቅጽላዊ ሀረጉ ቀይ ቀለም

06 መተ ፡ ስማዊ ሀረግ… ስማዊ ሀረግ

07 ተ2፡ ስማዊ ሀረጉ ቀይ ቀለም አበበች ቀይ ቀለም ትወዳለች፡፡

08 መ/ርት፡ኧ … ቀይ ቀለም የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ ቀይ ቀለም የሚለው አበበች


ቀይ ቀለም ትወዳለች ዐ/ነገር ነው፡፡ እሺ… ጥሩ ሌላስ

09 ተ3፡አዲስ … ስማዊ ሀረጉ አዲስ ልብስ አበበ አዲስ ልብስ ለብሷል፡፡

10 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረጉ አዲስ … አዲስ ልብስ ሀረግ ነው፡፡ አበበ አዲስ ልብስ
ለብሷል፡፡ ይህ ዐ/ነገር ነው ሌላስ … እህ

11 ተ4 ፡ሰባራ ይላል… ሰባራ ፍየል ዐ/ነገር ሰባራ ፍየል ዐለችው

12 መ/ርት ፡ሰባራ?

13 ተ4 ፡ሰባራ ፍየል አለችው

14 መ/ርት፡ሰባራ ፍየል አረድኩ፡፡ እሺ… ሌላስ …

15 ተ5 ፡በዚሁነው በሌላ?

16መ/ርት ፡በነኝሁ መስራት ትችላላችሁ፡፡ለምሳሌ…ረጅም መንገድ ብሏል፡፡ረጅምም እዚሁ


ላይ አለ ቃሉ …. መንገድም እዚሁ አለ፡፡የእግር መንገድ ይላል፡፡የእግር የሚል አለ
መንገድም አለ አይደል ? በነዚሁ መስራት ትችላላችሁ እዚሁ ላይ ባሉት ማለት ነው፡፡

17 ተ6 ፡ሰው በሚለው?

122
18 መ/ርት፡ ደስ ባለሽ አንቺ ….

19 ተ6፡ረጅም ሰው አለ፡፡ ሰው የሚለው ቃሉ ሰው… ረጅም ሰው…

20 መ/ርት፡ሰው የሚል አለ እዚህ ጋ ? … እረጅም ሰው … ረጅም … ሰው … ስማዊ


ሀረግ ነው፡፡ ረጅም ሰው አለ … ወይም ረጅም ሰው አለ ሌላስ …

21 ተ7፡ቤት

22 መ/ርት፡እ?

23 ተ7፡ ቤት የሚለው ትልቅ ቤት ስማዊ ሀረግ ነው ደግሞ ዐ/ነገር ሲሰራ ትልቅ ቤት


ገዛሁ፡፡

24 መ/ርት ፡ትልቅ ቤት… ትልቅ ቤት … የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ ትልቅ ቤት ገዛሁ
የሚለው ደሞ ምንድ ነው?

25 ተጋ ፡ዐ/ነገር

26 መ/ርት፡ እ … ዐ/ነገር ነው፡፡ ጥሩ… ሌላስ … ሌላስ …. ተሳተፉ

27 ተ8፡ አዲስ ሹራብ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ፡፡ እንትን …. ዐ/ነገር ሲሰራ ደግሞ…
ዐ/ነገር ሲሰራ አዲስ ሹራብ ገዛሁ ፡፡

28 መ/ርት፡ አዲስ ሹራብ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ዐ/ነገር ሲባል ደሞ አዲስ ሹራብ ገዛሁ
አዲስ ሹራብ ገዛሁ… ሌላስ …

29 ተ9 ፡ ምጣድ የሚለው ዐ/ነገር ነው፡፡ እንትን…. ስማዊ ሀረግ ነው ትልቅ ምጣድ


ገዛሁ ዐ/ነገር

30 መ/ርት፡ እ እ…ምጣድ የሚለው እ… ትልቅ ምጣድ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው፡፡


ትልቅ ምጣድ ገዛሁ፡፡ የሚለው ደሞ ምንድነው? ዐ/ነገር ነው ፡፡ ሌላስ … እህ …

31 ተ10፡ ወረቀት የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ዐ/ነገር ሲሰራ የፈተና ወረቀት ተሰጠን፡፡

32 መ/ርት ፡ ወረቀት…መጀመሪያ ሀረጉን መስርቺ?

33 ተ10 ፡ወረቀት … የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው

34 መ/ርት፡ራሱ ወረቀት ቃል ነው እንጂ፡፡

35 ተ10፡ ቃል ነው፡፡ ኧ … የፈተና ወረቀት ተሰጠ፡፡ አበበ የፈተና ወረቀት ተሰጠው ፡

36 መ/ርት፡የፈተና ወረቀት… ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ የፈተና ወረቀት ተቀበለ የሚለው


ዐ/ነገር ይሆናል፡፡ እሺ ሌላስ? ብዙ መመስረት እንችላለን ፡፡ መስርት እስኪ

37 ተ11፡አልገባኝም

38 መ/ርት፡ አልገባኝም? እነዚህን ተጠቅመህ እኮ… ስማዊ ሀረግ መመስረት ነው፡፡

39 ተ12 ፡ትንሽ መጽሀፍ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ትንሽ መጽሀፍ አለኝ ዐ/ነገር

40 መ/ርት ፡ትንሽ መጽሀፍ አለኝ ዐ/ነገር ይሆናል፡፡

123
41 ተ13 ፡ጥቂት ብዕር ለሚለው ጥቂት ብዕር አለኝ

42 መ/ርት ፡ ጥቂት ብዕር … ቢሆን … ጥቂት ብዕር አለኝ ፡፡ዐ/ነገር ይሆናል፡፡ እሺ


ይበቃናል፡፡ አሁን ረጅም የሚለው ረጅም … ረጅም መንገድ ብንል እዚህ ጋር መንገድ
የሚለውን የቃል ክፍሉ ምንድነው? ስም ነው? የሀረጉ አይነት ምን ይባላል? ስማዊ ሀረግ፡፡
ረጅም መንገድ ሄድን ማለት እንችላለን፡፡ ትልቅ የሚለውን… ትልቅ ቤት… ትልቅ ቤት
ገዛሁ እንላለን፡፡ ሌላው ቀይ … ቀይ ሹራብ … ቀይ ሹራብ …ሹራብ ምንድናው የቃል
ክፍሉ? ስም ነው ስለዚህ የሀረጉ አይነት ምንድነው? ስማዊ ሀረግ … ቀይ ሹራብ አለኝ
ማለት እንችላለን፡፡ ሰባራ የሚል አለ ሰባራ ምጣድ …. ምጣድ የሚለው የቃል ክፍሉ
ምንድነው ? ስም ነው ፡፡ የሀረጉ አይነት ስማዊ ሀረግ ሰባራ ምጣድ እንጀራ ያበላሻል
ማለት እንችላለን፡፡ አዲስ ብእር … ብእር የሚለው የቃል ክፍሉ ስም ነው፡፡ አዲስ ብእር
አለኝ ወይም ገዛሁ ማለት እንችላለን፡፡ ብዙ መሪያቸውን ስም አድርገን ስማዊ ሀረግ
መመስረት እንችላለን፡፡ ከዛ በኋላ ስማዊ ሀረግ ከመሰረትን በኋላ ደሞ ምን ማረግ
እንችላለን? ዐ/ነገር መመስረት እንችላለን፡፡ ሌላው ሁለተኛው በሚከተሉት ቃላት ዉስጥ
አምስት ቅጽላዊ ሀረግ በመመስረት ዐ/ነገር ስሩባቸው መጀመሪያ ቅጽላዊ ሀረግ
ትመሰርታላችሁ ፡፡ የልጅ አዋቂ ይላል የህፃን ብልጥ ፣ የተማሪ ብልህ… አዋቂ ፣ብልጥ፣
ብልህ… የሚሉት የቃል ክፍላቸው ምንድነው ?መሪያቸው ቅጽል ነው አደል ? የሀረጉ
አይነት ምንድነው ? ቅጽላዊ … ቅጽላዊ ሀረግ ነው በዚህ መሰረት ደግሞ ሌሎቹን ስሩ ፡፡
እስቲ የሚሰራልኝ? እንዴ ተሳተፉ እንጂ… ምነው?

43 ተ14 ፡አዋቂ

44 መ/ርት፡ እህ

45 ተ14 ፡አዋቂ ሰው

46. መ/ርት፡ አዋቂ ነው ያልሽው?

47 ተ14 ፡ አዎ

48 መ/ርት፡አዋቂን ተጠቅመሽ ቅጽል መስርቺ

49 ተ14 ፡ አበበ አዋቂ ነው

50 መ/ርት፡ሀረግ ከዚሁ ላይ ማለት ነው

51 ተ14 ፡(ምላሽ አልሰጠችም)

52 መ/ርት፡እስቲ ሌላ የሚሰራልኝ ፡፡ ሌላ …

53 ተ8፡የወጣት የሚለው … የወጣት ፈጣን ቅጽላዊ ሀረግ ነው

54 መ/ርት፡ የወጣት …. ምን ?

55 ተ8 ፡ፈጣን

56 መ/ርት፡ የወጣት ፈጣን

57 ተ8 ፡ዐ/ነገር ሲሰራበት ደግሞ የወጣት ፈጣን በሰዎች ዘንድ ይወደዳል ፡፡

58. መ/ርት ፡የወጣት ፈጣን የሚለው ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡ የወጣት ፈጣን በሰዎች ዘንድ

124
ተወዳጅ ነው፡፡ ሌላስ?

59. ተ16፡ ብልህ በሚለው … የተማሪ … ብልህ የሚለው … ስም … ቅጽላዊ ሀረግ

ይሆናል፡፡ የተማሪ ብልህ በትምህርት ቤታችን ሞልቷል፡፡

60 መ/ርት፡ የተማሪ ብልህ … ብንል ስማዊ… ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡ የተማሪ ብልህ

በትምህርት ቤታችን አለ… ብንል ዐ/ነገር ይሆናል፡፡ ሌላስ

61 ተ17 ፡ብልጥ የሚለው ቅጽላዊ ሀረጉ ብልጥ ድመት …. ድመት … ብልጥ ድመት

62 መ/ርት፡ብልጥ ድመት… ቅጽላዊ ሀረግ ነው እንዴ? እ… ብልጥ ድመት ትላለች

ምንድነው?

63 ተጋ፡ስማዊ ሀረግ ነው፡፡

64 መ/ርት፡ ስማዊ ሀረግ ነው ፡፡ እስቲ …

65 ተ1፡ብልጥ በሚለው ስማዊ ሀረጉ … ቅጽላዊ ሀረጉ የገበሬ ብልጥ በሀገራችን የገበሬ

ብልጥ ሞልቷል፡፡

66 መ/ርት ፡ብልጥ የሚለው … የገበሬ …

67 ተ1፡ ይህ ዐ/ነገር ነው ፡፡

68 መ/ርት፡የገበሬ ብልጥ ብንል… ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡ብልጥ ቅጽል ነው የሀረጉ አይነት


ምን ሆነ? ቅጽላዊ ሀረግ በሀገራችን የገበሬ ብልጥ አለ ብንል ዐ/ነገር ሆነ ሌላስ ጥሩ …
ሌሎቻችሁም ተሳተፉ እንጂ?

69 ተ7 ፡ የህፃን ቁም ነገረኛ

70 መ/ርት፡ የህፃን ቁም ነገረኛ ቅጽላዊ ሀረግ ነው

71 ተ7 ፡የህፃን ቁም ነገረኛ …. ሀሳብ የለውም፡፡

72 መ/ርት፡የህፃን ቁምነገረኛ …. ሀሳብ … የለውም ፡፡ እሺ … የህፃን ቁም ነገረኛ ሀሳብ


የለውም ነው እንዴ የሚሆነው ? የህፃን ቁምነገረኛ ቅጽላዊ ሀረግ ነው ትክክል ነው ዐ/ነገሩ

73 ተ18 ፡ልጅ ለሚለው ነጭናጫ ልጅ…. ቅጽላዊ

74 መ/ርት፡ እ?

75 ተ18፡ልጅ ለሚለው ቅጽላዊ ሀገረግ ነጭናጫ ልጅ

76 መ/ርት፡ ነጭናጫ …ቆይ አዳምጧት …ነጭናጫ ልጅ ብላለች ነጭናጫ ልጅ ቅጽላዊ


ሀረግ ነው እንዴ? ምን አይነት ነው?

77 ተጋ፡ስማዊ ሀረግ

78 መ/ርት፡ስማዊ ሀረግ በይ ይህን አስተካክይ ነጭናጫ ልጅ ሳይሆን

125
79 ተ18፡አዋቂ ልጅ

80 መ/ርት ፡ወይም … የልጅ አዋቂ … እህ

81 ተ18 ፡ልጅ ለሚለው የልጅ አዋቂ ወ/ሮ አበበች የልጅ አዋቂ ወለደች

82 መ/ርት ፡የልጅ አዋቂ ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡ወ/ሮ አበበች የልጅ አዋቂ አላት፡፡ እህ…

83 ተ15 ፡የህፃን ደግ የሚለው ቅጽላዊ ሀረግ ነው የህፃን ደግ በሰዎች ዘንድ ይወደዳል፡፡

84 መ/ርት፡ ቅጽላዊ ሀረጉ የህፃን ደግ ነው፡፡ የህፃን ደግ ዐ/ነገር ስንመሰርትበት የህፃን


ደግ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት አለው ሌላስ?

85 ተ2 ፡ የተማሪ ጎበዝ አበበ የተማሪ ጎበዝ …ጎበዝ … ተማሪ …አበበ የጎበዝ ተማሪ
ነው፡፡

86 መ/ርት ፡ አበበ የተማሪ ጎበዝ ነው ፡፡ እሺ… የተማሪ ጎበዝ … ሌላስ …እህ

87 ተ17 ፡እናት ደግ … እናት ደግ ለልጅዋ ሩህሩህ ናት ፡፡

88 መ/ርት ፡የእናት

89 ተ17፡ ደግ

90 መ/ርት ፡ደግ … እህ

91 ተ17፡ለልጇ ሩህሩህ ነች፡፡

92 መ/ርት፡የናት ደግ የሚለው ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡የናት ደግ ለልጆችወሳኝነት አለው

(ጠቀሜታ አለው) ማለት እንችላለን፡፡ እህ … ቀጥል

93 ተ6 ፡አለሚቱ ቁም ነገረኛ ነች፡፡

94 መ/ርት፡ ምን? ሀረጉን መስርቺ…ሀረጉን መስርቺ?

95 ተ6 ፡አለሚቱ ሀረግ

96 መ/ርት፡ ቁምነገረኛ አለ ፡፡ እህ

97 ተ6 ፡ቁም ነገረኛ ደግሞ አለሚቱ ቁምነገረኛ ነች ፡፡ አለሚቱ ሀረግ

98 መ/ርት፡ እሺ ….ሌላስ?

99 ተ18 ፡ደግ በሚለው የተማሪ ደግ አለ፡፡

100 መ/ርት ፡ደግ የሚለው የተማሪ ደግ ቢሆን ቅጽላዊ ሀረግ ነው፡፡ ዐ/ነገሩ የተማሪ ደግ

አለ ሌላስ 101 ተ16 ፡ቁም ነገረኛ የሚለው የሰው ቁምነገረኛ ቅጽላዊ ሀረግ
ይሆናል፡፡የሰው ቁምነገረኛ የለም

126
አባሪ ስድስት

ምዝግብ መረጃ ስድስት


ክፍል ሀ
የተማሪ ቁጥር 43
ጊዜ 40 ደቂቃ
የትምህርቱ ርእስ
የዐ/ነገር ክፍሎችና ምርጥ ንግግር
01 መ/ርት፡ ወደ ክፍል እንደገቡ በባለፈው ክፍለጊዜ ምን ተማርን?ብለው ጠየቁ

02 ተ1 ፡ሰዋሠው

03 መ/ርት፡ ሰዋሠው፣በሰዋሠው ዙሪያ ላይ ምን? ምን አየን?

05 ተ2 ፡ ዐ/ነገር ከስማዊ ሀረግና ከግሳዊ ሀረግ ይመሰረታል

06 መ/ርት ፡ ዐ/ነገርን ወይም ስማዊ ሀረግንና ቅጽላዊ ሀረግን በመመስረት ዐ/ነገርን


እንደመሰረትን አይተናል፡፡ ሌላስ… ሌላስ …ምን ሰርተን ነበር? ሌላ… እህ … ሌላስ?

07 ተ3፡ ዐ/ነገርን … እ እ… ቅጽል እእ የአንድን ስም ቃል ስማዊ ሀረግና ቅጽላዊ ሀረጉን


አወጣን ካወጣን በኋላ ደግሞ በስማዊ ሀረግ እና ቅጽላዊ ሀረግ ዐ/ነገር ሰራር

08 መ/ርት፡ እሺ…ኧ …በባለፈው ክፍለጊዜ ዐ/ነገርን አይተናል፡፡ ዐ/ነገር ከስማዊ ሀረግና


ከግሳዊ ሀረግ ምን እንደሚል ነው? እንደሚመሰረት ነው፡፡ዐ/ነገር ከስማዊ ሀረግና ከግሳዊ
ሀረግ ይመሰረታል ብለናል ስማዊ ሀረግ ውስጥ ምን ይኖራል?ብለን ነበር፡፡

09 ተጋ ፡ ባለቤት

10 መ/ርት፡ ባለቤት ስማዊ ሀረግ ውስጥ ባለቤት እናገኛለን፡፡ግሳዊ ሀረግ ውስጥ ማን


እናገኛለን?

11 ተጋ ፡ማሰሪያ አንቀጽ

12 መ/ርት፡ ማሰሪያ አንቀጽን እንደሚገኝ አይተናል፡፡ሌላ ደግሞ ዐ/ነገር በውስጡ


በሚይዛቸው የግስ ወይም የማሰሪያ አንቀፅ መጠን በስንት ተከፈለ?

13 ተጋ ፡በሁለት

14 መ/ርት፡እጅ አውጥታችሁ መልሱ… እህ …

15 ተ3 ፡በሁለት

16 መ/ርት ፡ በሁለት ነው፡፡ምንና ምን?

127
17 ተ4 ፡ስማዊ ሀረግና እንትን … ቅጽላዊ ሀረግ

18 መ/ርት ፡ እሱ ዐ/ነገር ከምን ይመሰረታል?ከስማዊ ሀረግና ከግሳዊ ሀረግ ብለናል፡፡


ዐ/ነገር በውስጡ በሚይዛቸው የማሰሪያ አንቀጽ ብዛት ወይም የግስ ብዛት በስንት ይከፈላል?
ነው ያልነው

19 ተ5 ፡ በሁለት ተራና ውስብስብ

20 መ/ርት ፡ተራና ውስብስብ እንደሚባል አይተናል፡፡ተራና ዉስብስብ ዐ/ነገር… ተራ


የምንለው ምንድነው?ተራ ዐ/ነገር ማለት ምን ማለት ነው ብለን ነበር እስቲ ቀጥይ … ተራ
ዐ/ነገር ምንድነው

21 ተ6 ፡ ተራ ዐ/ነገር ማለት ከአንድ ማሰሪያ አንቀጽ ብቻ ሊመሰረት የሚችል ማለት


ነው፡፡

22 መ/ርት ፡ እሺ …ተራ ዐ/ነገር ማለት ከአንድ ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግስ የሚመሰረት


ነው አለች ትክክል ናት?

23 ተጋ ፡ አዎ

24 መ/ርት ፡አዎ ተራ ዐ/ነገር ከአንድ ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግስ የሚመሰረት ከሆነ


ምን ብለናል? ተራ ወይም ነጠላ ዐ/ነገር ብለናል፡፡ሁለተኛው ምንድነው ያልነው?

25 ተ7 ፡ ውስብስብ ዐ/ነገር የምንለው ከሁለትና … ሁለትና ከዛ በላይ ከሆኑ ግሶች ወይም


ቃሎች የሚመሰረት ነው

26 መ/ርት ፡ አዎ…ውስብስብ ዐ/ነገር የምንለው ሁለትና ከዛ በላይ በሆኑ ማሰሪያ


አንቀፆች ወይም ግሶች የሚመሰረት ከሆነ ምን ብለናል? ውስብስብ ዐ/ነገር እንደሚባል
አይተናል፡፡ በዚህ መሰረት የቤት ስራ ሰጥቼአለሁ አንደኛው ከተሰጠን ዐ/ነገር ውስጥ ስማዊ
ሀረጉን እና ግሳዊ ሀረጉን ማውጣት ነው መለየት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ዐ/ነገር ከተሰጠው
ዐ/ነገር ውስጥ ምን? ተራ ዐ/ነገር የሆኑትና ውስብስብ የሆኑ ዐ/ነገርችን መለየት ፣ለምን ተራ
እንዳላችሁ፣ ለምን ውስብስብ እንዳላችሁ እንድትለዩ ሰጠቻችኋለሁ አይደል ?

27 ተጋ ፡ አዎ

28 መ/ርት፡ እስቲ እንስራው፡፡ወደ መልመጃው ለምሳሌ፡-ትናንት የመጣችው ተማሪ


በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት አመጣች
፡፡የሚለው ዐ/ነገር ነው ይህ ዐ/ነገር ከምን ተመሰረተ? ከስማዊ ሀረግና ከግሳዊ ሀረግ ነው፡፡
ስማዊ ሀረጉን ስናወጣው ትናንት የመጣችው ተማሪ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው
ብለናል፡፡በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት አመጣች
የሚለው ደግሞ ምንድነው? ግሳዊ ሀረግና ከስማዊ ሀረግ ምን መሰረትን? ዐ/ነገር መሰረትን
ስማዊ ሀረግ ዉስጥ ባለቤቱን አገኘነው፤ግሳዊ ሀረግ ውስጥ ደግሞ ማሰሪያ አንቀጽ አገኘን፡፡
በዚህ መሰረት እስቲ አንደኛውን የሚሰራልኝ…አንደኛውን የሚሰራልኝ? እህ …

29 ተ8 ፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ የሚለው ስማዊ ሀረግ ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ጓደኛዋ
ገንዘብ ሰጠቻት (ሰጣት የሚለውን ሰጠቻት ብሎ አንብቦ ርማት አልተሰጠውም)

30 መ/ርት ፡እሺ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው … ጓደኛዋ


ገንዘብ ሰጣት የሚለው ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡ እሺ ሌላስ … እስቲ ሌላ እህ …

128
31 ተ9፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት፡፡ ስማዊ ሀረግ ሁለት
ሙሉ ልብስ …ግሳዊ ሀረግ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት ፡፡

32 መ/ርት ፡እሺ ሌላስ? ሌላስ ?ይህንን የሚሰራልኝ? እህ …

33 ተ2 ፡ይህንኑ?

34 መ/ርት ፡ አዎ

35 ተ2 ፡ሁለት ሙሉ ልብስ የሚለው ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ


ሰጣት፡፡ የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡ ስማዊ ሀረጉን ሙሉ ልብስ…ሁለት ሙሉ ልብስ
ሰጣት … እዚህ ጋ ልብስ የሚለው ስም ስለሆነ ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ እዚህ ጋ ደግሞ
እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት የሚለው ሰጣት ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

36 መ/ርት፡ እሺ ሌላስ? ሌላስ?

37 ተ3 ፡ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ ገንዘብ ሰጣት ነው የሚለው ዋናው


ዐ/ነገር ስማዊ ሀረጉ ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ እስተሚለው ስማዊ ሀረግ
ገንዘብ ሰጣት የሚለው ግሳዊ ሀረግ

38 መ/ርት ፡ አ…ዎ ጥሩ ነው፡፡ትክክል ናት ሁለት ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ


ማነው? ገንዘብ የሰጣት ብንል ስማዊ ሀረግ ውስጥ ምን ይገኛል ብለናል? ባለቤቱ ይገኛል
ስለዚህ ማነው ገንዘብ የሰጣት ጓደኛዋ …ጓደኛዋ እስከሚለው ድረስ ነው ስለዚህ ሁለት
ሙሉ ልብስ እንድታሰፋ ጓደኛዋ እስከሚለው ድረስ ደሞ ምንድነው? ስማዊ ሀረግ ነው ፡፡
ገንዘብ ሰጣት የሚለው ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው ፡፡ ግሳዊ … ሀረግ ነው፡፡ ሁለተኛው እ…

39 ተ10 ፡ ቁርሳቸውን በልተው በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪዎች


የቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ የሚለው ዐ/ነገር ነው፡፡ ስማዊ ሀረጉ ቁርሳቸውን በልተው
በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪዎች የሚለው ሲሆን ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ
የቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ ፡፡

40 መ/ርት ፡ ቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ ፡፡እሺ… ቁርሳቸውን በልተው በጠዋት ወደ


ትምህርት ቤት የመጡት ተማሪዎች እስከሚለው ድረስ ስማዊ ሀረግ ነው ብሎናል ፤
ቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ የሚለው ግሳዊ ሀረግ ነው ብሎናል ትክክል ነው?

40 ተጋ ፡ አዎ

41 መ/ርት ፡ እ …ትክክል ነው አዎ ቁርሳቸውን በልተው በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት


የመጡት ተማሪዎች እስከሚለው ድረስ ስማዊ ሀረግ ነው ቅርጫት ኳስ ይጫወታሉ ግሳዊ
ሀረግ ነው ትክክል ነው፡፡ ሶስተኛው

42 ተ11 ፡ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው


(ጓደኞቻችን የሚለውን ጓደኞቼ ብላ አንብባ ርማት አልተሰጣትም) ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት
ተነስተው ስማዊ ሀረግ ይሆናል፡፡ ስፓርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው እሱ ግሳዊ ሀረግ
ነው፡፡

43 መ/ርት ፡ስማዊ ሀረጉ እስከምን ድረስ ነው? ጠዋት ጠዋት እስከሚለው ?

44 ተ11፡ጓደኞቼ ጠዋት ጠዋት ተነስተው

45 መ/ርት ፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው እስከሚለው ድረስ ነው ትላለች እስቲ ሌላስ?

129
46 ተ4 ፡ ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት ስለሚሰሩ እዚህ ጋር ድረስ
ስማዊ ሀረግ ነው ቀልጣፎች ናቸው ፡፡ ይህ ደግሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡

47 መ/ርት ፡ እሺ …ትክክል አይደለም፡፡ እስቲ?

48 ተ19 ፡ ጓደኛችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት እስከሚለው ስማዊ ሀረግ፣


ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው፡፡ግሳዊ ሀረግ (ጓደኞቻችን የሚለውን ጓደኛችን ብላ አንብባ
ርማት አልተሰጣትም)

49 መ/ርት ፡እሺ ሌላስ ትክክል አደለችም እህ?

50 ተ5 ፡ጓደኞቻችን ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት ስለሚሰሩ የሚለው ስማዊ ሀረግ


ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ቀልጣፎች ናቸው

51 መ/ርት ፡ እ …ሺ ሌላስ? ትክክል አደለም፡፡

52 ተ2 ፡ጓደኞቻችን የሚለው ስማዊ ሀረግ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት ስለሚሰሩ


ቀልጣፎች ናቸው የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ

53 መ/ርት ፡አ…ዎ ጓደኞቻችን እስከሚለው ነው ስማዊ ሀረጉ ጓደኞቻችን ስማዊ ሀረግ


ነው፡፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓርት ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው የሚለው ስማዊ ሀረግ
ነው ፡፡ ጓደኞቻችን የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው፡፡ ጠዋት ጠዋት ተነስተው ስፓረት
ስለሚሰሩ ቀልጣፎች ናቸው ደሞ ምንድነው? ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡ አስተካክሉ… አራተኛው
… አራተኛው?

54 ተ12 ፡ ታናሽ እህቴ ከቤተሰቦቻችን ሁሉ የተለየች ባለሙያ ናት ፡፡ ታናሽ እህቴ


የሚለው ስማዊ ሀረግ ከቤተሰባችን ሁሉ ባለሙያ ነች የሚለው ደግሞ ግሳዊ ሀረግ፡፡

55 መ/ርት ፡ እሺ ታናሽ እህቴ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ብላለች ከቤተሰቦቻችን ሁሉ


የተለየች ባለሙያ ነች ግሳዊ ሀረግ ነው ትላለች ትክክል ናት፡፡

56 ተጋ ፡ አዎ

57 መ/ርት ፡ አዎ ትክክል ናት ታናሽ እህቴ የሚለው ስማዊ ሀረግ ነው ፡፡


ከቤተሰቦቻችን ሁሉ ተለየች ባለሙያ ነች የሚለው ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው፡፡አምስተኛው
እስቲ … እህ

58 ተ13 ፡ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ የበላው ተማሪ ታመመ ንጽህናው ያልተጠበቀ


ምግብ ሚለው ስማዊ ሀረግ የበላው ተማሪ የሚለው ግሳዊ ሀረግ፡፡

59 መ/ርት፡ እሺ…ትክክልናት?

60 ተጋ ፡አይደለችም፡፡

61 መ/ርት ፡ እሷ ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ የሚለውን ድረስ ያለውን ስማዊ ሀረግ


ነው ትላለች፡፡ እስቲ

62 ተ9 ፡ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ የበላው የሚለው ስማዊ ሀረግ ታመመ የሚለው


ግሳዊ

መ/ርት ፡ ታመመ የሚለው ግሳዊ ሀረግ ነው ፡፡ ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ የበላው


ተማሪ ስማዊ ሀረግ ታመመ የሚለው ደሞ ግሳዊ ሀረግ ነው ትክክል ናት ሌላው ደሞ

130
አራተኛው ጥያቄ እንሄዳለን ትእዛዝ ከሚከተሉት ዐ/ነገሮች ተራና ውስብስብ የሆኑትን
በመለየት ተራና ውስብስብ ያላችሁበትን ምክንያት ለይታችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ
ነው የሚለው፡፡ እስቲ አንደኛ የሚሰራልኝ … እስኪ አሁን ደሞ ያልተሳተፋችሁ

63 ተ14 ፡ ልጄ ዛሬ ጠዋት ብዙ ጥያቄዎችን አቀረበልኝ ነው የሚለው መጀመሪያ


ጥያቄው ተራና ውስብስብ ይሆነውን መለየት ነው ልጄ ዛሬ ጠዋት ብዙ ጥያቄዎችን
አቀረበልኝ የሚለው ተራ ነው፡፡

64 መ/ርት ፡ ልጄ ዛሬ ጠዋት ብዙ ጥያቄ አቀረበልኝ የሚለው ተራ ነው ለምንድነው ተራ


ነው ያልሽበት ምክንያት?

65 ተ15 ፡አንድ አንቀጽ ብቻ ነው የያዘ

66 መ/ርት ፡አንድ ማሰሪያ አንቀጽ ብቻ ስለያዘ ወይም ግስ ብቻ ማንኛው ነው ግሱ


ማነው?

67 ተጋ ፡ አቀረበልኝ

68 መ/ርት፡አቀረበልኝ ትክክል ናት አዎ ልጄ ዛሬ ጠዋት ብዙ ጥያቄ አቀረበልኝ ነው


የሚለው አቀረበልኝ የሚለው ብቻ ነው ግስ ያለው፡፡ማሰሪያአንቀጽ ያለው ዐ/ነገሩ
ምንድነው? ተራ ዐ/ነገር ነው፡፡ሁለተኛው … ሁለተኛው

69 ተ4 ፡ጨዋታውን ፊት ለፊት በማየቴ ደስ አለኝ ፡፡ ውስብስብ

70 መ/ርት ፡ ለምን?

71 ተ4 ፡ እንትን … የመጨረሻው ቃል ከሁለትና ሁለትና ከሁለት በላይ … እንትን


ስለተመሰረተ … ማሰሪያ አነንቀጽ

72 መ/ርት ፡ሁለትና ከዛ በላይ ማሰሪያአንቀጽ ወይም ግስ ተመስርቷል ፡፡ የትኛው

ነው ግሱ ምን ምን የሚል አለው?

73 ተ4 ፡ አለኝ ፡፡ ደስ አለኝ

74 መ/ርት ፡እህ ሌላስ … እህ … እስቲ

75 ተ3 ፡ ጨዋታውን ፊት ለፊት በማየቴ ደስ አለኝ ፡፡ይህ ዐ/ነገር ውስብስብ ዐ/ነገር ነው


፡፡ ምክንያቱም ሁለት ማሰሪያ አንቀጽ አለው ፡፡ እነሱም፡- ጨዋታውን ፊት ፊት በማየቴ
ይህንን አንድ ዐ/ነገር ማድረግ እንችላለን፡፡ ጨዋታዉን አየሁ፡- የሚል አንድ ጨዋታውን
ፊት ለፊት በማየቴ ደስ አለኝ ፡፡ ደስ አለኝ የሚለው ደግሞ ሁለተኛ ማሰሪያ አንቀጽ

76 መ/ርት ፡ እሺ…ጥሩ…ጨዋታውን ፊት ለፊት አየሁ ማለት እንችላለን፡፡ ከዚህ ዐ/ነገር


ጨዋታውን ፊት ለፊት አየሁ፤ ጨዋታውን በማየቴ ደስ አለኝ፡፡ ስለዚህ ስንት ግስ
አለው? ሁለት …ሁለት ግስ ስላለው ምንድነው ዐ/ነገሩ ?ውስብስብ ዐ/ነገር ነው፡፡ውስብስብ
ዐ/ነገር ነው ፡፡ ሶስተኛው … ሶስተኛ እህ

77 ተ14 ፡ ግርማ ሆስፒታል ሄዶ ወንድሙን ጠየቀ ፡፡ውስብስብ ዐ/ነገር ነው ምክንቱም


ግርማ ሆስፒታል ሄዶ አንድ ተራ ነው፤ ወንድሙን ጠየቀ ደግሞ ሁለት

78 መ/ርት ፡ ሌላ ዐ/ነገር ነው ፤ እሺ …ኧ ውስብስብ አረፍተነገር ነው ያለው ትክክል


ነው አይደል? ምክንያቱም ምንድነው ? ግርማ ሆስፒታል ሄደ አንድ ዐ/ነገር ማውጣት

131
እንችላለን፡፡ አንድ ማሰሪያ አንቀጽ ሄደ የሚለው ግርማ ሆስፒታል ሄዶ ወንድሙን ጠየቀ
የሚለው ደሞ ሌላ ዐ/ነገር ሌላ ማሰሪያ አንቀጽ ስለምንችል ምንድነው ? ዐ/ነገሩ ማለት
ነው? ውስብስብ ዐ/ነገር ነው፡፡ ሶስተኛው … አራተኛው … ማለት ነው… እስቲ እህ

79 ተ7 ፡ መኪና እንዳገጫት ስለፈራች መንገዱን ተሻግራ ዶሮ ለመግዛት


አልፈለገችም፡፡ይህ ውስብስብ ዐ/ነገር ነው፡፡ምክንያቱም መኪና እንዳይገጫት ስለፈራች
መንገዱን ተሻግራ ሄደች ፡፡ ይህን አንድ ዐ/ነገር እንለዋለን፡፡ እንደገና ደግሞ መኪና
እንዳገጫት ስለፈራች መንገዱን ተሻግራ ሄዳ ዶሮ ለመግዛት አልፈለገችም፡፡

80 መ/ርት ፡ስለዚህ…ከስንት በላይ ግሶች ይዟል?ወይም ማሰሪያአንቀጽ ይዟል?

81 ተጋ ፡ ሁለትና ከዛ በላይ

82 መ/ርት፡ከሁለት በላይ ስለሆነ ምንድነው? ውስብስብ ዐ/ነገር ነው፡፡ ውስብስብ ዐ/ነገር


ነው፡፡ የመጨረሻው አምስተኛውን የሚሰራልኝ …አምስተኛውን

83 ተ15 ፡እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡ ይህም ውስብስብ ዐ/ነገር ነው፡፡


ምክንያቱም እንግዳው ሰውዬ ዛሬ እንግዳው ሰውዬ አንድ ዐ/ነገር ነው፡፡ ዛሬ ጠዋት
ወዳገሩ ተመለሰ የሚለው

84 መ/ርት፡ እሺ… እንግዳው ሰውዬ የሚለው ዐ/ነገር ነው እንዴ?

85 ተጋ ፡ አይደለም ፡፡

86 መ/ርት ፡ሀረግ ነው እስቲ የሚያስተካክል … እህ

87 ተ16 ፡እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ጠዋት ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡የሚለው ዐ/ነገር ተራ ዐ/ነገር


ነው፡፡

88 መ/ርት፡ ለምን?

89 ተ16 ፡ ምክንያቱም እንግዳው ሰውዬ ዛሬ ጠዋት ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ውስብስብ


ዐ/ነገር ሁለትና ከዛ በላይ የያዘ ሲሆን

90 መ/ርት ፡ ከዛ በላይ ምን?

91 ተ16፡ ሁለትና ከዛ በላይ ዐ/ነገር ይይዛል፡፡

92 መ/ርት ፡ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግስ

93 ተ16 ፡አዎ ማሰሪያ አንቀጽ ተራ ደሞ አንድ ይሆናል ማለት ነው

94 መ/ርት ፡ ስለዚህ እዚያ ግሱ ስንት ነው?

95 ተጋ ፡አንድ ነው

96 መ/ርት ፡ አንድ ብቻ ምን የሚለው?

97 ተጋ፡ ተመለሰ

98 መ/ርት ፡ ተመለሰ ፡፡ የሚለው ስለዚህ እንግዳው ሰውዬ ወደ ሀገሩ ተመለሰ የሚል አለ


፡፡ ተመለሰ የሚለው ነው፡፡ አንዱ… አንዱ… ማሰሪያ አንቀጽ ወይም አንድ ግስ ስላለው

132
ምንድነው? ተራ ዐ/ነገር ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ጋር የምንረዳው ዐ/ነገር እስከተሰጠ ድረስ
ስማዊ ሀረግ ግሳዊ ሀረጎችን መለየት ነው፡፡ ያው ስማዊ ሀረግ የምንለው የዐ/ነገሩ ምን
የሚገኝበት ነው ብያችኋለሁ? ባለቤት የሚገኝበት ነው ግሳዊ ሀረጉ ደግሞ ያረፍተነገሩ
ማሰሪያ አንቀጽ የሚይዝ ነው ሌላው ደሞ ዐ/ነገር በሚይዘው የግስ ብዛት በሁለት
ተከፈለ፡፡ውስብስብና ተራ … ተራ የምንለው አንድ ግስ ወይም ማሰሪያ አንቀጽ ከያዘ ተራ
ነው በብለናል፡፡ሁለትና ከዛ በላይ ማሰሪያ አንቀጽ ወይም ግሶች ከያዘ ምን
ይባላል?ዉስብስብ ይባላል፡፡ ግልጽ ያልሆነ ነገር ወይም ጥያቄ ካለ ጠይቁ ! ከሌለ ወደ
ቀጣዩ እንሄዳለን፡፡ እዚህ ጋር ስለ ዐ/ነገር ስማዊ ሀረግና ግሳዊ ሀረግ አመሰራረት ከግሳዊ
ሀረግና ከስማዊ ሀረግ ተመስርቶልናል፡ ሌላው ደሞ ዐ/ነገር በሚይዘው የግስ ብዛት
ዉስብስብና ተራ ብለናል፡፡ግልጽ ያልሆነላችሁ ነገር ካለ ጥያቄ ጠይቁ ግልጽ ያልሆነላችሁ
ነገር ካለ ጥያቄ የለም? ከሌለ ወደ ቀጣዩ እንሄዳለን ገጽ 147 ላይ አውጡ! ምዕራፍ ዘጠኝን
ነው የምናየው ምርጥ ንግግር የሚል አለ፡፡ሌላው ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች አሉ፡፡ያንን ንባብ
ከማንበባችሁ በፊት የሚቀርቡ ጥያቆዎች አሉ እነሱን እንሰራለን፡፡(መምህርቷ በጥቁር
ሰሌዳው ላይ ርዕሱን ፃፉ) ቅድመ ንባብ ጥያቄዎችን እንመልሳለን አንደኛው ጥያቄ የምርጥ
ንግግር ጥበብ እንዴት ያለ ነው?የምታውቁትን… እስቲ ተወያዩባቸው ምንባቡን
እንዳታነቡ( መምህርቷ እየተዘዋወሩ ጥያቄውን ከፋፍለው ሰጡ) ሁለተኛው ስለጥንታዊ
ግሪክ ስልጣኔ አንብባችሁ ወይም ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ይላል ጥሩ ተናጋሪ መሆን
እንዴት ያሉ ጥቅሞች አሉት ? አራተኛው በአንድ ንግግር የአድማጭን ቀልብ ሊስብ
ወይም ላይስብ የሚችልባቸው ጉዳዮች ምንድናቸው?ይላል እስቲ ጎን ለጎን ተወያዩባቸውና
እሺ ይበቃናል… እስቲ አንደኛ ጥያቄ የሚሰራልኝ?

99 ተ17 ፡ የምርጥ ተናጋሪ ጥበብ እንዴት ያለ ነው?የሚለው የምርጥ ተናጋሪ ጥበብ


የምንለው ተደማጭነትና ተከታታይነት ሲገኝለት ነው፡፡ እና የሰራው ውጤት የተሻለ ሲሆን

100 መ/ርት ፡ እህ ሌላስ? አንደኛውን የሚሰራልኝ?

101 ተ16 ፡ የምርጥ ተናጋሪ ጥበብ እንዴት ያለ ነው የሚለው እጥር ምጥን ብሎ እና ማራኪ
ሲሆን ይህ የምርጥ ተናጋሪ ጥበብ ይባላል ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው … ሁለተኛው

102 ተ2 ፡ ስለጥንት ግሪክ ስልጣኔ ሰምታችሁ ወይም አንብባችሁ ታውቃላችሁ?አዎ ግሪክ


ሁለት ከተሞች አሏት፡፡ እነሱም፡- አቴንስና ስፓርታ ሲሆኑ ግሪክ … አቴንስ ቀጥተኛ
ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ትከተላለች፡፡ ስፓርታ ደግሞ በውክልና ነው… እንትን … የምትለው

103 መ/ርት ፡እሺ … ጥሩ …ሌላስ …ሌላስ ሶስተኛው … ሶስተኛው ማለት ነው፡፡ ጥሩ


ተናጋሪ መሆን እንዴት ያሉ ጥቅሞች አሉት? ይላል ፡፡ ጥሩ ተናጋሪ መሆን እንዴት
ጥቅሞች አሉት? ማለት ጥሩ ተናጋሪ መሆን እንዴት ያለ ጥቅም አለው? እህ … እስቲ
ይህን የሚሰራልኝ የመሰላችሁን ማለት ነው፡፡

104 ተ17 ፡ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ያለው ጥቅም ምንድነው? የሚናገረው ነገር ተደማጭነትና

ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

105 መ/ርት ፡ እሺ … የሚናገረው ነገር ተደመጭነት ተቀባይነት እንዲኖረው ይጠቅማል፡፡

ጥሩ ተናጋሪ መሆን … ሌላስ … እህ

106 ተ3 ፡ ጥሩ ተናጋሪ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትና ተቀባይነት እንዲኖረን ያደርገናል

133
107 መ/ርት ፡ ጥሩ ተናጋሪ መሆናችን በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትና ተቀባይነት እንዲኖረ
ያደርጋል፡፡ጥሩ…አራተኛው ጥያቄ አንድ ንግግር የአድማጭን ቃል ሊስብ ወይም ላስብ
የሚችልባቸው ጉዳዬች ምን ምን ናቸው? ይላችኋል፡፡ እህ …

108 ተ2 ፡ የምርጥ ንግግር ተናጋሪ ጥበብ ጥሩ መሆንና ጥሩ አለመሆን ናቸው

109 መ/ርት የምርጥ ንግግር ጥበቡ ጥሩ መሆኑና አለመሆኑ ሊስብ ላስብ ይችላል፡፡ ጥሩ

110 ተ18 ፡ ባለባበሱ … ባነጋገሩ ሊስበን ይችላል

111 መ/ርት ፡ እሺ ባለባበሱና ባነጋገሩ ሊስበን ላይስበን ይችላል ትላለች፡፡ ጥሩ እስቲ መልሳችሁ
ትክክል መሆን አለመሆኑን እ … ቀጣዩ ምንባብ አንብቡት ፡፡ እሱን ታነቡና ሌሎች
ጥያቄዎችን እሰጣቸዋለሁ፡፡ (ጥያቄዎቹን በመከፋፈል ሰጥተው ለተወሰነ ደቂቃ መልሱን
አንብበው እንዲፈልጉ አድርገዋል) አንደኛውን ጥያቄ …እህ

112 ተ4 ፡ በጥንታዊ የግሪክ ስልጣኔ ጥሩይ ተናጋሪ ለመሆን እንዴት ያሉ ዝግጅቶች ይጠይቃል
(ጥሩ የሚለውን ጥሩይ አንብቦ ርማት አልተሰጠውም) እሺ ...አንደኛ ወደ ሸንጎ ሲሄዱ
ዴሞስቴን ከነሱ ጋር ንግግሩን እንዲያዳምጥ እያስከተሉት ጊዜ … ደሞ … ዴሞስቴን
ከሰው ተለይቶ እንደባህታዊ ብቻውን እኖረ ንግግር የማሳመር ጥበብ ይማር እንደነበር ፣
ደሞ የሚንተባተበው ምላሱን ለማፍታታት ሲል አፉ ውስጥ ጠጠር እየጨመረ ነበር፤
ብቻውንም ሆኖ እንደእብድ ሰው ከፍ ባለ ድምጽ በመናገር አንደበቱን ገራ እንደዚሁም
ደሞ በጉባኤ ፊት በሚናገርበት ሠዓት ህዝቡ ንግግሩን በማቋረጥ የሚያደርግበት፣
የሚጠቀምበት … የተጠቃሚነት ሹክታ ለመልመድና ለማሸነፍ እንዲረዳው ሲል ነው፡፡

113 መ/ርት ፡ እሺ… ሌላስ … እህ …

114 ተ6፡ ስለጥንታዊ ግሪክ ስልጣኔ ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንዴት ያሉ ዝግጅቶች ይጠይቃል?
በጥንታዊ የግሪክ ስልጣኔ ተናጋሪ ያሉ ዝግጅቶች በፊት የራሱን ዝግጅት ያደርጋል
ማለትም ያለባበስ፣ ያነጋገር፣ ያኳኋን፣ ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ያሉትን ነገሮች ማድረግ
ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ፡- ጥሩ ተናጋሪ ስንል ባነጋገሩ የተባ በንግግሩ ጥሩ የሆነ ቃላቶችን
መምረጥ አለብን

115 መ/ርት ፡ እሺ … ሌላስ … በጥንታዊ የግሪክ ስልጣኔ ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንዴት ያሉ


ዝግጅቶች ይጠይቃል? ነው የሚላችሁ እስቲ አንደኛው የደረሳችሁ ፡፡ ዴሞስቴን
ብንወስደዉ ማለት ነው ምንድነው ያረገው? ጥሩ ተናጋሪ ከሆነው አስተማሪው ጋር ሸንጎ ሄዶ
አስተማሪው ክሊስትራ ሲናገር ለመስማት ወዴት ነው የሄደው? ወደ ሸንጎ በመሄድ ንግግሩን
ምን አርጓል? አዳምጧል፡፡ ስለዚህ ወደ ሸንጎ ተናጋሪ ንግግር በሚያቀርቡበት ጊዜ ሸንጎ
ሄዶ ንግግር ምን በማድረግ ነው ? አንደበቱን መናገር ያኮላተፈው ነበር አፉ ውስጥ ጠጠር
በመጨመር ምንድነው ያረገው ? እ… አንደበቱን ምን እንዳደረገው ነው ኮልታፋ ምላሱን
እንደገራው ነው የሚገልፀው፡፡ ሶስተኛ ደሞ ምንድነው? ከሰዎች ተገልሎ ዋሻ ውስጥ
ለስምንት አመታት ውስጥ በመሆን ከሰዎች ተለይቶ ንግግር ምን እንዳደረገ ነው? እንትን
የሚለው እንደተለማመደ ነው የሚገልፀው ስለዚህ ሸንጎ ሄዶ ምን በማድረግ ንግግርን
በማዳመጥ ሁለተኛው ደሞ ምንድነው? ኮልታፋ የነበረውን አፍ ጠጠር ዉስጥ በመጨመር
መግራት ወይም ማሰልጠን እንደቻለ ነው፡፡ ሌላዉ ደሞ ዋሻ ውስጥ ለስምንት አመታት
ውስጥ በመኖር የንግግር ልምምድ እንደቻለ እስከሚችል ድረስ ቆይቶ ንግግር ችሎ
እንደወጣ ነው የሚገልፀው ፡፡ ሁለተኛው … ሁለተኛዉ ጥያቄ … እጅ አውጡ የደረሳችሁ
፡፡ እህ …

134
116 ተ19 ፡ ባለንበት ዘመን አሳማኝ ምክንያት አቅርቦ በሰላና በጠነከረ አንደበት አድማጮችን
መሳብ ጠቀሜታ የሚኖረው እንዴት ነው? የሚለው … ምርጥ ንግግር ከፍተኛ ጥበብ
ነው፡፡ ሀሳብ የምቅረብ ጥበብ ፣የንግግር ጥበብ፣ሀሳብ በቋንቋና አቀራረብ ይሻል፡፡ የንግግር
ታዳሚዎች ስሜት አቀራረብ ፣ስሜት በአንደበት አገላለፅ ወዘተ አጥብቆ መያዝና ወደ
ሚፈለግበት አቅጣጫ መምራት ያስፈልጋል ፡

117 መ/ርት፡ እሺ … ሌላስ …እህ

118 ተ20 ፡ ባለንበት ዘመን አሳማኝ ምክንያት አቅርቦ በሰላና በጠነከረ አንደበት አድማጮችን
መሳብ ጠቀሜታው የሚኖረው እንዴት ነው? ጥሩ ተናጋሪ በመሆን አድማጮችን ለመሳብ

119 መ/ርት፡ እህ … ቀጥይ

120 ተ20 ፡ ጨርሻለሁ

121 መ/ርት፡ ሌላስ … ሌላ ሁለተኛ የደረሳችሁ ባለንበት ዘመን አስፈላጊ ምክንያቶቸች አቅርቦ
በጠነከረ አንደበት አድማጭን መሳብ ጠቃሚ የሚሆነው እንዴት ነው?ነው የሚላችሁ
እሺ…እህ
122 ተ17 ፡ ጠቃሚ የሚሆነው የተፈጥሮ እፍረታችንን እንድናስወግድ ይረዳናል፡፡ እ… ጠንካራ
መረጃ ሰብሳቢ ከመሆናችንም ተርፈን ለማስተማር እንበቃለን፡፡

123 መ/ርት ፡ እሺ …. ባለንበት ዘመን አስፈላጊ ምክንያቶችን አቅርቦ በጠነከረ አንደበት


አድማጭን መሳብ ጠቃሚ የሚሆነው እንዴት ነው? ለሚለው ያው … ንግግር አድርገን
ማለት ነው ባድማጮች ፊት ስንቆም ለምሳሌ ዶመሰቲን ሲናገር ኮልታፋ ነበር እንዲህ
በል እንዲህ አትበል እያሉት ነበር የተናገረው ስለዚህ ምን መሆን አለበት አድማጮችን
ፊት ከመቅረባችን በፊት የንግግር ልምምድ ምን ማድረግ አለብን ? ልምምድ አድርገን
ባድማጩ ዘንድ መቅረብ አለብን ነው የሚለው ሌላው የምናቀርበው ንግግሮች ላድማጩ
ወቅታዊ ሀሳቦችን ፣ሳቢና ማራኪ የሆኑ ሀሳቦችን ምን ማድረግ አለብን ? ማቅረብ
ይኖርብናል፡፡ አንደበተ ርቱዕ ካልሆንን ወይም ጥሩ ተናጋሪ ካልሆንን አድማጩ ምን
አይለንም? አይስበውም ወይም አያዳምጠንም ሶስተኛው ... ሶስተኛው …እህ

124 ተ21፡ ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንዴት ይቻላል? ጥሩ ተናጋሪ መሆን የሚቻለው በትምህርት ቤት
ውስጥ ልምድ በማድረግ ጥሩ ተጋሪ መሆን ይቻላል፡፡ በቤተ መጽሀፍ ውስጥ እጠናን
የተረዳነውን ለክፍል ጓደኞቻችን በማቅረብ በምናቀርብ ጊዜ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይቻላል፡፡
ስብሰባ በምንሰበሰብበት ሠዓት አስተያየት ስንሰጥ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይቻላል፡፡

125 መ/ርት ፡ እሺ … ጥሩ … ሌላ … ይህንኑ የደረሳችሁ ሶስተኛ … እህ … እሺ … አራተኛ ያዉ


ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንዴት ይቻላል? ነው የሚላችሁ ያው ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ሌላው
መጽሀፍን በማንበብ … መጽሀፍን በማንበብ ጥሩ ተናጋሪ መሆን አለብን፡፡ ንግግር
በሚደረግበት ጊዜ በማዳመጥም አዳምጠንም ለንግግሩ ምን በመስጠት ? በስብሰባ ላይ
በመገኘት ምላሽ በመስጠት ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይቻላል፡፡ ሌላው የንግግር ልምምድ
መድረክ ላይ ወጥተን በማድረግ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይቻላል ነው የሚላችሁ…. አራተኛው
… አራተኛው

126 ተ10 ፡ በሀገሪቱ ጥንታዊ ስልጣኔ ጋር በተያያዘ የዴሞስቴንን ታሪክ ማጥናት ለምን ይጠቅማል?
ነው የሚለው ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ነው ጥሩ ተናጋሪ ሆነን ደግሞ በሰዎች ዘንድ
ተቀባይነትን ለማትረፍ ነው

135
127 መ/ርት ፡ እሺ ሌላስ …. አራተኛ … አራተኛ የደረሳችሁ … እ ፈጠን በሏ ከግሪክ ጥንታዊ
ስልጣኔ ጋር በተያያዘ የዴሞስቴንን ታሪክ ማጥናት ለምን ይጠቅማል ነው የሚለው ታሪክ
ማጥናት የሚጠቅመው ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ነው፡፡ እሱ እንዴት ያለ መናገር የማይችል
ነበር መጨረሻ ጥሩ ተናጋሪ እንደሆነ የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ የሱነ ን ታሪክ ማጥናት የ
ሚጠቅመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ነው አምስተኛው … አምስተኛ… እህ

128 ተ22 ፡ በዚህ ዘመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንደጥንታዊ ግሪካዊያን ዴሞስቴን ከሰዎች ተገልግሎ
ለብቻ በመሆን ንግግር መለማመድ አስፈላጊ ይሆናል እንዴት? ( ተገልሎ የሚለውን
ተገልግሎ ብሎ ሲያነብ እርማት አልተሰጠውም) አስፈላጊ አይሆንም ምክንያቱም መጽሀፍ
በማንበብ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይቻላል ሰዎችን ሰብስቦ መላመድ (መለማመድ የሚለውን
መላመድ ብሎ ገልጿል)፡፡ ይቻላል ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲያቀርብ ይለማመዳል በዚሁ መሰረት
ጥሩ ተናጋሪ ይሆናል፡፡

129 መ/ርት፡ እሺ … ሌላስ

130 ተ2 ፡ በዚህ ዘመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንደ ጥንታዊ ግሪካዊያን ዴስሞን

131 መ/ርት ፡ ዴሞስቴን …. ዴሞስቴን

132 ተ2 ፡ ተገልሎ ለብቻ መለማመድ አስፈላጊ ይሆናል ምክንያቱም ብቻዉን ከተለማመደ የተለያዩ
መድረኮችና ሸንጎዎች ላይ ሲቀርብ ምንም የሚያቅተው ነገር የለም ስለዚህ … አዎ

133 መ/ርት ፡ እሺ …እኔ የሱ ተቃራኒ ነኝ በዚህ ዘመን ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን እንደጥንታዊ


ግሪካዊያን ዴሞስቴን ከሰዎች ተገልሎ ንግግር መለማመድ አስፈላጊ ይሆናል ወይ
አይሆንም እሱ ለስምንት ዓመት ዋሻ ውስጥ ገብቶ ጸጉሩን ግማሽ ተላጭቶ ግማሹን ሳይላጭ
እብድ መስሎ ስምንት አመት ኖሮ ንግግር ለመደ አደል እንዴ? ስምንት አመት ሙሉ
ላይፈጅብን ይችላል፡፡ ከሰዎች ፊት እየወጣን ንግግር እያቀረብን፣ ስብሰባ ላይ እየተገኘን
ከጓደኞቻችን ጋር እየሆንን ንግግር መለማመድ አንችልም እንዴ? ንግግር መለማመድ
እንደሚቻል ነው እንጂ ለስምንት ዓመታት ተገልሎ መኖር አስቸጋሪ ነው አይደል እንዴ?
ስለዚህ ከጓደኞቻችን ፊት ፣ስብሰባ ላይ በመገኘት ጥያቄዎች በመጠየቅ እኛ ተሳትፎ
በማድረግ ንግግር መለማመድ እንችላለን፡፡ እሺ ቀጥይ… እህ …

134 ተ23 ፡ ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን መሰልጠን ወይም መገራት ያለባቸው ያካል ክፍሎች የትኞቹ
ናቸው? ምላሳችን ሊሆን ይችላል፤ ጉሮሮችን … ድዳችን …መንጋችንም (መንጋጋችን
የሚለውን መንጋችን ብሎ ተናግሯል) ማንቀሳቀስ

135 መ/ርት ፡ ጥሩ ያው ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን መሰልጠን ወይም መገራት ያለባቸው የአካል ክፍሎች
የትኞቹ ናቸው? ካልን ለንግግር የሚውሉት የአንደበት አካላት ጥርስ ፣ምላስ ፣ ከናፍር
፣ድድ፣ማንቁርት እነዚህ ምን መሆን አለባቸው?መሰልጠን ወይም መገራት አለባቸው ፡፡
ይበቃናል የቀጣዩን መልመጃ ስሩና ኑ ( የእለቱ ከ/ጊዜ ተጠናቀቀ)

136

You might also like