You are on page 1of 28

አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ በፈቱ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች

አማርኛ ቋንቋ ለመማር ያላቸው ፍላጎትና


የፈተና ውጤታቸው ዝምድና
(በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ስር በሚገኙ ሁለት
ትምህርት ቤቶች ተተኳሪነት)

ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ትልመ ጥናት

ሰናይት ወ/ስላሴ (ID.NO……

አማካሪ

ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
የኅብረተሰብ ሣይንስና ቋንቋዎች ኮሌጅ
የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሁፍ - አማርኛ ትምህርት ክፍል
የድህረ ምረቃ

ታህሳስ 2015

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
ማውጫ

ይዘት ገጽ
ምስጋና……………………………………………………………………………
አጠቃሎ………………………………………………………………………………………ii
ምዕራፍ አንድ:መግቢያ
1.1.የጥናቱ ዳራ………………………………………………………………………………..
1.2 .የጥናቱ አነሳሽ ችግር…………………………….……………………………….
1.3.የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች
1.4. የጥናቱ ዓላማ…………………………………………………………………………..
1.5.የጥናቱ አስፈላጊነት…………………………………………………………………
1.6.የጥናቱ ወሰን…………………………………………………………………………
ምዕራፍ ሁለት፡- ክለሳ ድርሳ
2.1. ፍላጎት ምንድ ነው?.............................................................................................
2.2. የፍላጎት ጠቀሜታ………………………………………………………………………
2.3. ፍላጎትና የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት……………………………………
2.4.ፍላጎት በትምህርት ውስጥ ያለው ሚና………………………………………………….
2.5.ፍላጎትን ማጥናት ለምን አስፈለገ ?...........................................................................
2.6. የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ የሚሳድሩ ተላውጦዎች……………
2.6.1. ተማሪው ለሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ባለው አመለካከት ሳቢያ የሚከሰት
ተፅዕኖ…………………………………………………………………………………
2.6.2 ተማሪው ለሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ባለው ተነሳሽነት ምክንያት የሚከሰት
ተጽዕኖ……………………………………………………………………………….
2.6.3. በስነ ልቦና ችግር ምክንያት የሚከሰት ተጽዕኖ………………………………
2.6.4. በቤተሰብ በኩል የሚመጣ ተጽዕኖ…………………………………………….....
2.6.5. በተማሪው ጓደኞች በኩል የሚከሰት ተጽእኖ
2.6.6.ተማሪው ከሚኖርበት ህብረተሰብ በኩል የሚመጣ ተጽዕኖ
2.6.7. በቋንቋ መምህራን ስብእና እና በማስተማሪያ ዘዴ ምክንያት የሚከሰት
ተጽዕኖ
2.6.8. በመማሪያ መጽሀፉ ምክንያት የሚከሰት ተጽዕኖ
2.7. በፍላጎትና በተማሪው ውጤት ጋር ያለው ዝምድና
2.8.የቀደምት ስራዎች ቅኝት………………………………………………………

1
ምዕራፍ ሦስት………………………………………………………………………….
የአጠናን ዘዴ………………………………………………………………………….
3.1 የጥናቱ ንድፍ………………………………………………………………………
3.2. የናሙና አመራረጥ ዘዴ……………………………………………………………
3.2.1.የመስተዳድር አመራረጥ……………………………………………………………
3.2.3.የትምህርት ቤት አመራረጥ
3.2.4.የክፍልና የምድብ አመራረጥ
3.2.5.የተማሪዎች አመራረጥ………………………………………………………………
3.2.6.የመምህራን አመራረጥ……………………………………………………………
3.3. የመረጃ መሰብሰቢ መሳሪዎች…………………………………………………………
3.3.1. የጽሁፍ መጠይቅ
3.3.2. ቃለ መጠይቅ
3.3.3. ሰነድ ፍተሻ……………………………………………………………………………
3.4. የመረጃ አተናተን ዘዴ………………………………………………………
ዋቢ መፅሀፍት
ግምታዊ የጊዜ ሰሌዳ
ግምታዊ የበጀት ሰሌዳ

ምዕራፍ አንድ

መግቢያ

1.1 የጥናቱ ዳራ
ቋንቋ የሰው ልጅ ዋነኛ መግባቢያ ነው፡፡ በቋንቋ ላይ የሚደረጉ ጥናቶችና ምርምሮች የተሻለ የቋንቋ
አጠቃቀም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡ በጥናት ላይ የተደገፈ አሰራር
2
እንዲሁም የመማር ማስተማር ተግባር ደግሞ የተሳሳተውን አካሄድ ለማቃናት፣ መልካም ጎኑን ይበልጥ
ለማጠናከር እንዲቻል ይረዳል፡፡ስለዚህ የቋንቋ ትምህረት ለአፍ-ፈትም ሆነ ለኢ-አፍ-ፈት ተማሪዎች
ሲቀርብ በጥናት የተደገፈ መረጃን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡ይህን ተግባር ለማከናወንም የተማሪዎቹን
ፍላጎት፣ ባህላዊ ዳራን ፣የተነሳሽነት ሁኔታ፣ አካባቢያዊ ተጽዕኖን፣አመለካከትን፣ የእውቀት ደረጃን ማወቁ
ወሳኝ እንደሆነ Harmer(1991) እና Brown (2007) አስረድተዋል ፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩ ተላውጦዎች ውስጥ ፍላጎት በቋንቋ ትምህርትም ሆነ በሌላ ትምህርት ዙሪያ አብይና
መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡የፍላጎት መኖር ያለመኖር ለአንድ ተግባር ስኬታማ መሆን ያለመሆን ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ስለዚህ ለትምህርቱ አወንታዊ ፍላጎት ያለውቸው ተማሪዎች በክፍል ውስጥ እርስ በእርሳቸው ጥያቄ
ይጠያየቃሉ፣ መልስ ሲመልሱ፣ ከመምህራቸው ጋር በመወያየት ተገቢ የሆነ ግብረ መልስ ወዘተ…ሲያገኙ፣
በአንፃሩ ደግሞ ለትምህርቱ አሉታዊ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ጥያቄ ሲጠይቁም ሆነ መልስ ሲመልሱ
ወዘተ… አይታዩም በማለት ማስረሻ (2003) ያስረዳሉ፡፡

ከላይ ከቀረበው ሃሳብ በተጨማሪም ፍላጎት በተለይም ኢ-አፍ-ፈት ለሆኑ ተማሪዎች በትምህርቱ ሂደት ላይ
ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ በርካታ ተላውጣዎች መካከል አንዱ በቋንቋውና በትምህርቱ ያለው ፍላጎት ነው፡፡
ተማሪው ከክፍል ውጪም ሆነ ከክፍል ውስጥ የሚገጥሙት ችግሮች ከፍላጎት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ
ግንኙነት አላቸው፡፡ለትምህርቱ ቀረበ ቋንቋና የትምህርት ስርአቱ፣ የማስተማሪያ መሳሪያዎች፣ የመምህሩ
የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች፣ የተማሪዎች ባልንጀራ፣ ወላጆችና ማህበረሰቡ፣ ተማሪው ለትምህርቱ
አወነወታዊ ወይም አሉታዊ ፍላጎትእንዲኖራቸው ከሚያስችሉ ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው
(ስሚዝ 1971፣ 82፤ሀርመር 1990፣4)፡፡
ይህ ማለት ተማሪው ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ አወንታዊ ፍላጎት ካለውና ውስጣዊ ተነሳሽነት ካለው
በፍላጎቱና በውጤቱ መካከል የጠበቀ ግንኙነት ይኖረዋል፡፡ በአንፃሩ አሉታዊ ፍላጎት ካለውና ውስጣዊ ተነሳሽነት
ከሌለው በፍላጎቱና በውጤቱ መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንደማይኖረው በብዙ ምሁራን ጥናቶች ተረጋግጧል
(ታደለ 1990፣139)፡፡

ስለዚህ በተማሪዎች ተተኳሪው ትመህርት ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ተላውጣዎችን ፈትሾ
በማየት በተማሪዎች ዘንድ የሚፈጠረውን የአወንታዊ ፍላጎት ገፅታን ማጎልበትና በአንፃሩ ደግሞ አሉታዊ
ገፅታን በመቀየር የሚቻለው በጥናት መረጋገጥ ሲቻል ነው፡፡

እንግዲህ ከላይ በዝርዝር የተጠቀሰውን ሳይንሳዊ ዳራን መሰረት በማድረግ አጥኚዋ በድሬዳዋ ከተማ
መስተዳድር ውስጥ ትኩረት ሰጥታ ወደምታጠናው በናሙናነት በሚመረጡ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት

3
ቤቶች በ 2015 ዓ.ም የሚማሩ የ 9 ኛ ክፍል የኦሮሚኛ ቋንቋ አፍ-ፈት ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን
በማስተማር ሂደት ላይ ያላቸውን ፍላጎትና የፈተና ውጤታቸው ዝምድና የምታጠና ይሆናል፡፡

1.2 የጥናቱ አነሳሽ ችግር


በቋንቋ ትምህርት በተለይም በሁለተኛ ቋንቋ በመማር ማስተማር ሂደት ወቅት ተማሪውን የተለያዩ
ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ስነ ትምህርታዊና ስነ ልሳናዊ ችግሮች ይገጥሙታል፡፡ አንድን ትምህርት በመማር
ሂደት ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩት ነገሮች ውስጥ አንዱ ተማሪው ለቋንቋውና ለትምህርቱ የሚኖረው ፍላጎት
እንደሆነ የተለያዩ ምሁራን አስረድተዋል፡፡ በክፍልም ሆነ ከክፍል ውጪ ተማሪውን የሚያጋጥሙት ተፅዕኖዎች
ከተማሪው ፍላጎት ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው፡፡ እነዚህም፡- የማስተማሪያ
መሳሪያዎች፣ የተማሪዎቹ ባልንጀሮች፣ ወላጆች፣ ማህበረሰቡ፣ የመምህሩ ስብእና፣ መምህሩ የሚጠቀመው
የማስተማሪያ ዘዴ ወዘተ….ተማሪው ለትምህርቱ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ናቸው
በማለት Gardner (1968)፣Muller (1971) እና Harmer (1990) ይገልጻሉ፡፡

አማርኛ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ በኦሮምኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች ላይ የተለያዩ ጥናቶች
ተደርገዋል፡፡አበበ (1990) አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ
ያላቸው አመለካከት በአዋሽ መላካሳ አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚል ርዕስ ባቀረበው ጥናታዊ
ፅሁፉ፣ እንዳመለከተው በጥናቱ ውስጥ ከታቀፉት ሦስት አራተኛው እጅ አማርኛ ቋንቋን ለመማር ፍላጎት
እንደሌላቸው አረጋግጧል፡፡በተጨማሪም አሰፋ (1994) ሀዋስ ከፍተኛ 2 ኛደረጃ ት/ቤት አፋቸውን በኦሮምኛ
ቋንቋ የፈቱ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸው አተያይ በሚል ርዕስ ባቀረበው ጥናታዊ ጽሁፉ፣
በጥናቱ ውስጥ ከታቀፉት 52ተጠኚ ተማሪዎች አማርኛን መማር ምንም ጥቅም እንደማያስገኝላቸው
አስረድቷል፡፡
ከላይ ከቀረቡት ጥናቶች መገንዘብ የሚቻለው አማርኛ ቋንቋ ትምህርትን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ
አፋቸውን በኦሮምኛ የፈቱ ተማሪዎች ትምህርቱን ለመማር ያላቸው አመለካከትና አተያይ አናሳ እንደሆነ
ያመለክታል፡፡ ይህ ደግሞ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ስላለው ለአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ትኩረት እንዳይሰጡ ሊያደርግ ይችላል፡፡
የዚህ ጥናት መነሻ ችግርም በኦሮምኛ ቋንቋ አፍ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች የ 8 ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ በኋላ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲገቡ አማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው ፍላጎት በጣም አናሳ በመሆኑ
ምክንያት በመማር ማስተማር ሂደት ዙሪያ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የመወያያ ነጥብ ሆኖ በተደጋጋሚ
እየቀረበ እንደሚያከራክር አጥኚዋ ካላት የረጅም ጊዜ የማስተማር ልምድ ችግሩን ተመልክታለች፡፡ስለዚህ
አጥኝዋ ይህን ችግር መነሻ በማድረግ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር በናሙናነት በሚመረጡት ሁለት 2 ኛ
ደረጃ ት/ቤቶች የሚማሩ አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ የ 2015 ዓ.ም የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት ለመማር ያላቸውን ፍላጎትና የፈተና ውጤታቸው ዝምድናን ለመፈተሸ ተነሳስታለች፡፡

4
1.3.የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች
ይህ ጥናት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ጥያቄዎች ይመልሳል ተብሎ ይታሰባል፡፡
1. በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋን ትምህርት ያላቸው
ፍላጎት ምን ይመስላል?
2. በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ መማር ማስተማር
ግብአቶች (ለመማሪያ መፅሃፉና ለመምህራን) ያላቸው ፍላጎት እንዴት ይገመገማል?
3. በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ሲማሩ ወላጆች፣ ጓደኞችና
ማህበረሰቡ በተማሪዎች ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ አለን?
4. በተማሪዎች ፍላጎትና በውጤታቸው መካከል ምን አይነት ዝምድና ይኖራል?
1.4 የጥናቱ ዓላማ
የዚህ ጥናት አብይ አላማ፣ አፋቸውን በኦሮሚኛ ቋንቋ የፈቱ የ 9 ኛ ክፍል በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን
የፈቱ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ መማር ያላቸው ፍላጎትና የፈተና ውጤታቸውን ዝምድና መፈተሸ፡፡
1. በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ሲማሩ
ያላቸውን ፍላጎት ለይቶ ማመልከት፣
2. በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ መማር ማስተማር
ግብአቶች(ለመማሪያ መፅሃፉና ለመምህራን) ያላቸው ፍላጎት መፈተሸ፣
3.በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋ ትምህርትን ሲማሩ
ወላጆች፣ ጓደኞችና ማህበረሰቡ በተማሪዎች ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተፅዕኖ አለን፣
4. አሉታዊ ፍላጎት በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን በፈቱ ተማሪዎች ፈተና ውጤት
ላይ ሚኖረው አሉታዊ ተጽዕኖ ምን ያህል እንደሆነ በፍተሻ ማረጋገጥ የሚሉት ናቸው፡፡
1.5. የጥናቱ አስፈላጊነት
ጥናቱ የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች በማስገኘት ረገድ አስፈላጊ ነው ተብሎ ይታሰባል ፡፡
1. አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸውን
ፍላጎት ደረጃ ለማሳየት፡፡
2. አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን የመማር ፍጎት ላይ
አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ ለመምህራን፣ ለትምህርት
ባለሞያዎች እና ለሌሎችም ለሚመለከታቸው አካላት መረጃ ሊሰጥ ይችላል፡፡
3.ለመምህራን በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የመማር
ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች መፍትሄ ለይቶ ለማመልከት
ያስችላል፡፡
4.ወደፊት በዚህ ርዕስ ላይና ዙሪያ ጥናት ለሚያደርጉ ሰዎች መነሻ ሀሳብ ይሆናል

5
ተብሎ ይገመታል፡፡
1.6 የጥናቱ ወሰን
ይህ ጥናት የሚመለከተው በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ውስጥ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶችን ማዳረስ ስለማይችል በስሩ በሚገኙ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች በ 2015 ዓ.ም የሚማሩ አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ የ 9 ኛ
ክፍል ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡ በመስተዳድሩ ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ አፋቸውን
የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸውን ፍላጎትና የፈተና ውጤታቸው ላይ
ብቻ የሚፈትሽ ይሆናል፡፡

ምዕራፍ ሁለት
ክለሳ ድርሳናት

6
2.1. ፍላጎት ምንድ ነው?
የፍላጎትን ምንነት በሚመለከት የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ትንተናዎችን ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡ይሁን እንጂ
የሁሉም ምሁራን ሀሳብ ወደ አንድ ምድብ ሊካተት የሚችል መሆኑን Skinner (1985) አስረድቷል፡፡ በዚህ
ጉዳይ ላይ የተለያዩ ምሁራን የሰጡትን ብያኔ እንደሚከተለው ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡ Abraham (1954)
ፍላጎት የሚለውን ቃል ሲያብራራ፣ የሰው ልጅ ለህልውናው ወይም ለሞራሉ የሚያስፈልገውን እንዲያሟላ
የሚያስገድደው፣ የሚጎትተው፣ ለተግባሩ የሚያነሳሳውና የሚገፋፋው ውስጣዊ የመሻት ስሜቱ እንደሆነ
ይገልጻል፡፡
ከላይ ከተሰጠው ሃሳብ መረዳት እንደሚቻለው ፍላጎት ማንኛውንም ተግባር ለማከናወን የሚያስችልና
ውስጣዊ መነሳሳትን የሚፈጥር ሀይል እንደመሆኑ መጠን በመማር ማስተማሩ ሂደት ውስጥ ያለ ፍላጎት
የሚከናወን ማንኛውም እንቅስቃሴ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ያሻል፡፡ ፍላጎት የሰብዕና
መገለጫ አንዱ አካል ሲሆን እንደ አመለካከትና ተነሳሽነት ሁሉም በስነ-ልቦና ጥናት ከሚተኮርባቸው
ተላውጦዎች አንዱ እንደሆነ Hamlin (1996) ያስረዳል፡፡ከዚህም በተጨማሪ Torne (1997) እንደገለጸው፣
ፍላጎት የአንድ ግለሰብ ስሜትና ዝንባሌ የሚገለጽበት ወይም ደግሞ ግለሰቡ የአንድን ነገር ምንነት ለማወቅ
የሚገፋፋው ሃይል እንደሆነ አስረድቷል ፡፡ እንደ Lee (1976) አገላለጽ፣ ፍላጎት በአንድ ሁነት ውስጥ
ለመሳተፍ ወይም ድሪጊቱን ለመፈጸም የሚያስችል ውስጣዊ መሻት ነው በማለት አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም
Evans (1965) ፍላጎት ሰው የሚሰራውን ወይም የሚያደርገውን ነገር ሊወስን የሚችል ሀይል እንደሆነ
አመልክቷል፡፡ እንዲሁም Hurlock (1996) ፍላጎት ማለት ወደተወሰነ ግብና አላማ ሊመራ የሚችል ሃይል
እንደሆነ ያስረዳል፡፡ Skinner (1985) በበኩሉ ፍላጎት የታቀደን አላማ ከግብ ለማድረስ የሚከናወንን ተግባር
መውደድና አለመውደድን፣ ውስጣዊ ተነሳሽነትን፣ ለተፈለገው ነገር ትኩረት እንዲሰጥና በአንድ ነገር ለመሳብ
ወይም ላለመሳብ ምክንያት የሚሆን ውስጣዊ ተግባር እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ከላይ ከቀረበው የተለያዩ ምሁራን ሀሳብ መረዳት የሚቻለው ፍላጎት አንድ ነገር የመውደድና የመጥላት ሀይል
ሲሆን፣ በአንድ በተወሰነ ነገር ላይ የማትኮር ሁኔታና ወደ ማናቸውም ተግባርም የሚመራ አንድ ሃይል መሆኑን
መረዳት አያዳግትም፡፡ስለሆነም ፍላጎት አንድን ተግባር ለማከናወንና ለመፈፀም ፍቃደኛ የመሆን ወይም
ያለመሆን መልስ የሚሰጥበት ውስጣዊ ግፊት ወይም መሻት ነው ፡፡
2.2. የፍላጎት ጠቀሜታ
ፍላጎት በትምህርትም ሆነ በተለያዩ እንቅስቃሴና ተግባራት ውስጥ አንድን ድርጊት ለማከናወንና ውጤታማ
ለመሆን የበኩሉን አስተዋጾ ሊያደርግ እንደሚችል የተለያዩ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡Garry (1970) የፍላጎትን
ጠቀሜታ አስመልክ to እንደገለፀው፣ አላማ ጥንካሬ እንዲኖረው ፍላጎት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ይህም
በመሆኑ አንድን ተግባር የሚያከናውን ማንኛውም ሰው ለተግባሩ የጠና ፍላጎት ካለው ስራውን በትክክል
እንዲያከናውን ያደርገዋል፡፡ አላማን መሰረት አድርጎ የሚከናወን ተግባር ከፍላጎት ጋር ተያይዥነት ያለው
መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ሙሉ ሀይልን ለመጠቀምና ተግባራትን በአጥጋቢና በጥሩ ሁኔታ ለማከናወን
የሚረዳና ተነሳሽነትን በሰዎች ዘንድ የሚፈጥር ሀይል ነው፡፡Harmer (1991) እንዳስረተዋል፣ ሰዎች ለአንድ
7
ተግባር ወይም ጉዳይ ፍላጎት የሚኖራቸው ከሆነ ተግባሩን ለማከናወን ውስጣዊ የሆነ ተነሳሽነት ወይም ግፊት
እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ፍላጎት የመማር ማስተማሩን ተግባር ለማከናወን ብቻ የሚያስፈልግ ሳይሆን ማንኛውንም
በክፍልም ሆነ ከክፍል ውጪ የሚከናወኑ ተግባራትን ለመፈፀም ወይም ለማከናወን ወሳኝነት እንዳለው ከላይ
የቀረበው የተለያዩ ምሁራን ሀሳብ ያመለክታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለቀረበው ትምህርት ፍላጎት የሌለውን
ተማሪ ለማስተማር መጣር ወይም መሞከር ውጤቱ ከድካምና ልፋት ያለፈ ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ
ተገቢ ይሆናል፡፡
2.3. ፍላጎትና የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት
ፍላጎት የኢ-አፍ-ፈት ተማሪዎች ለትምህርት በቀረበላቸው ሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው ፍላጎት
በቋንቋው ስኬታማ መሆን አለመሆን ሊያመለክት እንደሚችል በተለያዩ ምሁራን ዘንድ ይነገራል፡፡ Sposky
(1989) ፍላጎት በሁለተኛ ቋንቋ ውስጥ ያለውን ሚና ሲገልጽ፣ የቋንቋው ተማሪ አዎንታዊ አመካከት
አዎንታዊ የመማር ፍላጎትን እንደሚያመጣ ሁሉ አሉታዊ አመካከት ደግሞ አሉታዊ የመማር ፍላጎትን
እንደሚያስከትል ወይም እንደሚያመጣ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም እንደ Gardner (2007) እይታ ደግሞ
በሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች አመለካከትና ፍላጎት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስፈላጊውን
መረጃ ማግኘት ከተቻለ፤ በዙሪያው የሚከሰቱ ችግሮችን አስቀድሞ ለመፍታትና የመማር ማስተማሩን ሂደት
የሰመረ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስረድቷል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተማሪው ቋንቋውን ለመማር
ፍላጎት ከሌለውና ሁለተኛ ቋንቋውን ለምን አላማ እንደሚማር ካላወቀ ለቋንቋው ትምህርት አሉታዊ
አመለካከት እንደሚኖረው በማለት ይገልፃል፡፡
በአጠቃላይ የተማሪዎችን ፍላጎት በማወቅ የመማር ማስተማሩን ተግባራት ለማከናወን መንቀሳቀስ
ተፈላጊውን ውጤት ለማግኘትና የመማር ማስተማሩ ሂደት የተቃናና የሰመረ እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ
ተማሪዎች በሁሉም የክፍል ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፉ ስለሚያስችል የተማሪዎቹ ፍላጎት ምን
እንደሆነአስቀድሞ ማወቅናለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ተገቢነው፡፡

2.4.ፍላጎት በትምህርት ውስጥ ያለው ሚና


ምሁራን ስለ ፍላጎትና ትምህርትን አስመልክተ ያላቸው አተያይ የተለያ ነው፡፡ እሸቱ (1997) Buglsk(1971)ን
ዋቢ አድርገው እንደገለፁት ተማሪው ለትምህርቱ አወንታዊ የሆነ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል፡፡ለመማር ፍላጎት
የሌለው ከሆነ ትምህርቱን ፈጽሞ ሊማር አይችልም፡፡ስለዚህ አንድን የትምህርት አይነት ለማስተማር
በምንነሳበት ጊዜ ተማሪው ለሚማረው ትምህርት የሚኖረው ፍላጎት አስቀድሞ ሊታወቅ ይገባል፡፡ፍላጎት
ካለው ትምህርቱም በተገቢው መንገድ መከታተል ይችላል፡፡የመማር ፍልጎት የሌለው ተማሪ ግን ትምህርቱን
በተገቢው መንገድ መከታተል አይችልም፡፡የመማር ፍላጎት የሌለው ተማሪ በክፍል ውስጥ ጥያቄ የመጠየቅ፣
ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ የመስጠት፣ የክፍል ስራና የቤት ስራ የመስራት ወዘተ የመሳሰሉ የክፍል ውስጥም ሆነ
የክፍል ውጪ ተግባራትን ለማከናወን ሲቸገሩ ይታያሉ በማለት ያብራራሉ፡፡

8
ከላይ ከረበው ሃሳብ በተጨማሪም Skinner(1985) ሲያብራሩ፣ ተማሪው የሚሰጠውን ትምህርት ከልብ
የማይከታተል ከሆነ፣ ትምህርቱ ሲሰጥ ከልብ የማያዳምጥ፣ የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባ የማይረዳ፣
በመማሪያ መፅሀፉ ውስጥ የቀረበውን ምንባብ የማያነብና በመፅሀሩ ውስጥ የተካተቱ ጥያቄዎችን ወዘተ
የማይሰራ ከሆነ ተማሪው የመምር ፍላጎት የሌለው መሆኑም ያመላክታል ይላሉ፡፡ስለዚህ ተማሪው ለሚሰጠው
ትምህርት ፍላጎት እንዲኖረው የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ከዚሁ በተጨማሪም ደግሞ ተማሪው
በትምህርቱ ፍላጎት እንዲኖረው መምሀራንም ሆኑ ማህበረሰቡ ተማሪዎች በትምህርታቸው ጥሩ አመለካከት
እንዲኖራቸው መቀስቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አለበለዚያ ግን ለትምህርቱ ፍላጎት የሌለው ተማሪ ማስተማሩ
በክፍል ውስጥ ለሌለ ተማሪ እንደ ማስተማር ይቆጠራል፡፡

በአጠቃላይ ከቀረበው የምሁራኑ ሃሳብ መረዳት የሚቻለው ፍላጎት ለትምህርት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው
ነው፡፡ተማሪው ትምህርቱን በአግባቡ እንዲከታተል በክፍል ውስጥ የሚከናወነው የመማር ማሰተማር ሂደት
በተማሪ ፍለጎትን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡በመሆኑም የተማሪውን የመማር ፍላጎት ለማሳደግ
የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተማሪው የመማር ፍላጎት ከፍ እንዲል አስተዋፅኦ ማድረግ አለባቸው፡፡

2.5.ፍላጎትን ማጥናት ለምን ያስፈልጋል?


መምህራን የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት አውቀው ትምህርቱን ከመጀመራቸው በፊት የተማሪዎችን ፍላጎት
መሰረት ያደረገ የትምህርት እቅድ ለማዘጋጀት ስለሚረዳ የተማሪዎች ፍላጎትን ማጥናት ያስፈልጋል፡፡
ምክንያቱም ፍላጎት ለትንህርቱ ተነሳሸነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ስለሚረዳ ነው በማለት
Harmer(1991)ን ዋቢ አድርገው ገልፀዋል፡፡ Skinner(1989) እንደሚሉትም ተማሪዎች ለሚቀርብላቸው
ትምህርት የየራሳቸው የሆነ ፍላጎት ስላላቸው፣ መምህሩ በሚያስተምርበት ወቅት የተማሪዎችን ፍላጎት
አስቀድሞ ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ትምህረቱም መቅረብ ያለበት የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት አድርጎ ሊሆን
ይገባል በማለት ይገልፃሉ፡፡

ከላይ ከቀረበው ሃሳብ በተጨማሪም Skinner (1959) እንደገለፁት የተማሪዎችን ፍላጎት ማጥናት
ስለተማሪው ማንነት ለማወቅ ይጠቅማል፡፡ ተማሪው ለትምህርቱ ያለው ፍላጎት አወንታዊ ከሆነ ያህንኑ በጥሩ
ሁኔታ ጠብቆ ለማቆየት የተማሪዎችን ፍላጎት አስቀድሞ ማወቁ ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ የተማሪው ፍላጎት
አስቀድሞ ማወቅ ለሚቀርበው ትምህርት እንደ መነሻ ሆኖ ያገለግላል፡፡

በአጠቃላይ ከመወሁራኑ አገላለፅ እንደምንረዳው ማንኛውም ሰው እራሱን ለትምህርት ካላዘጋጀ በቀር


ትምህርቱን በትክክል መማር አይችልም፡፡ስለዚህ ያለፍላጎት በአጋጥሚ የሚከናወን ትምህርት ግቡን
አይመታም፡፡በመሆኑም የተማሪውን ፍላጎት በማነሳሳት፣ አስፈላጊና ተገቢ የሆኑ የማስተማሪያ ዘዴዎችን
ለመጠቀም ተማሪዎቹ ጥሩ አመለካከት እንዲሆራቸው ወዘተ…ለማድረግ የተማሪዎቹን ፍላጎት ማጥናት
አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡

9
2.6. የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች
በአንድ ተማሪ የሁለተኛ ቋንቋ የመማር ሂደት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ተላውጦዎች በርካታ እንደሆኑ የመስኩ
ምሁራንያስረዳሉ፡፡ ምሁራኑ ካነሷቸው ውስጥ ፡- የመምህሩ ስብእና፣ ወላጆች፣ ማህበረሰቡ፣ የመምህሩ
የማስተማሪያ ዘዴ፣ጓደኞች ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ተማሪዎች ሁለተኛ ቋንቋ ሲማሩ እነዚህ የተጠቀሱት
ተላውጦዎች በትምህርታቸው ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ የበኩላቸውን
አስተዋጽኦ እንደሚያሳድሩ Gardner (1968)፣ እና Harmer (1990) ያስረዳሉ፡፡ ታደሰ (2004) አገላለጽ፣
የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች ታላሚውን ቋንቋ ሲማሩ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉትን
እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡፡
 የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች ቢያንስ አንድ ሌላ ቋንቋ፣የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ስለሚያውቁ ግፊቱ
የመጀመሪያ ቋንቋ ማወቁን ያህል ጠንካራ ያለመሆን፣
 የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች አንድ ሌላ ቋንቋ ቀደም ሲል በማወቃቸው ያ ቋንቋ ከሁለተኛው ቋንቋ ጋር
እየተጋጨ ስለሚያስቸግራቸው፣
 የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች ቋንቋውን የሚማሩት በሚያጋጥማቸውና በሚመቻቸው ሁኔታ ወይም
በሁኔታዎች አስገዳጅነትና ዝግጅት ባለው የመማርሂደት (FormalLearning) በመሆኑ፣
 የሁለተኛ ቋንቋን የሚማሩ ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንደሚለምዱ ህፃናት ያለመሰልቸት
ለረጅም ጊዜ መለማመድ(መማር) ያለመፈለጋቸው ነው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ ከቀረበው ሀሳብ መረዳት እንደሚቻለው በሁለተኛ ቋንቋ ተማሪ የመማር ፍላጎት ላይ
በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ተላውጦዎች እንዳሉ
ነው፡፡ ከዚህ በማስከተል ተጽዕኖ ያሳድራሉ ተብለው በተለያዩ ምሁራን ዘንድ የቀረቡትን ተላውጦዎች
ለማየት ይሞከራል፡

2.6.1.ተማሪው ለሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ባለው አመለካከት ሳቢያ


የሚከሰት ተጽዕኖ
ለአንድ የትምህርት አይነት ተማሪው አሉታዊ አመለካካት ካለው ትምህርቱን ለመማር አሉታዊ ተጽዕኖ
እንደሚያድርበት ሁሉ ተማሪው ለቀረበው ትምህርት አዎንታዊ አመለካከት ካለው ትምህርቱን ለመማር
አዎንታዊ ተጽእኖ ያድርበታል በማለት Hurlock (1996) ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ Dubin and Olshtain
(1986) እንዳስረዱት፣ ለትምህርት በቀረበው ቋንቋ ላይ አሉታዊ አተያይን ከሚፈጥሩት ምክንያቶች አንዱ
ከቋንቋው የሚገኘው ጥቅም ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪው ከቋንቋው ትምህርቱ ጥቅም አገኝበታለሁ ብሎ ካሰበ
ለቋንቋው አዎንታዊ አመለካከት በማዳበር ቋንቋውን ለመማር ያለው ፍላጎት ይጨምራል፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ
በ Spolsky (1989) አመለካከት አንድን የትምህርት አይነት ለመማር ባለው ፍላጎት ላይ ያለውን አዎንታዊና
አሉታዊ ተጽዕኖ ሲገልጹ፣ ተማሪዎች ለአንድ ትምህርት ጥሩ አመለካከት ካላቸው የቀረበውን ትምህርት
ለመማር ፍላጎት ሲኖራቸው፣ አሉታዊ አመለካከት ካላቸው ግን ለትምህርቱ ጥላቻ እንደሚያድርባቸው

10
አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ታደሰ (2004) ተማሪዎች አንድን ትምህርት ከባድ ነው የሚል አመለላከት
ካላቸው በትምህርቱ ላይ አሉታዊ አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚችል ሁሉ ትምህርቱ ጥቅም ይሰጣል
ብለው ካሰቡ ትምህርቱን ለመማር አዎንታዊ አመለካከት ይኖራቸዋል ሲል አስረድቷል፡፡
ከላይ እንደተገለጸው ተማሪው በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ አመለካከት ካለው የትምህርቱ ሂደት
የተቃና ይሆናል፤ ነገር ግን ተማሪው አሉታዊ አመለካከት ካለው በተቃራኒው በትምህርቱ ሂደት ላይ የራሱ
የሆነ አሉታዊ ጫና ይፈጥራል፡፡
በአጠቃላይ ከተሰጠው ብያኔ መረዳት የሚቻለው የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው ለትምህርት በቀረበው ሁለተኛ
ቋንቋ ላይ የሚኖረው አመለካካት ወይም አተያይ በተማሪው የትምህርት አቀባበል ላይ ስለሚንጸባረቅ
አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ምሁራኑ ከሰጡት አስተያየት
መረዳት ይቻላል፡፡

2.6.2. ተማሪው ለሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ባለው ተነሳሽነት ምክንያት የሚከሰት


ተጽዕኖ
ተነሳሽነት ለማንኛውም ውስብስብ ተግባር ስኬታማነት ወይም ስኬት አልባነት መገለጫ እንደሆነ Brown (2007) ያስረዳል፡፡
ተነሳሽነት የአእምሮና ስሜት መቀስቀስ ሁኔታ፣ አንድን ነገር ለመተግበር ወደ ውሳኔ የሚመራ፣ ዘላቂነት ወዳለው አእምሯዊና አካላዊ
ጥረት የሚያነሳሳ፣ ቀድሞ የታቀደ ግብን ለማሳካት የሚረዳ ብሎም ወደ ውጤታማነት እንደሚያደርስ William (1997)
asredtal፡፡ እንደ Harmer (1983) እና Brown (2007) አገላለጽ፣ሁለት አይነት የተማሪዎች ተነሳሽነት አሉ፡፡ እነርሱም፡-
ውስጣዊና ውጫዊ ተነሳሽነት ናቸው፡፡ በተጨማሪ Ltil wood (1981) እንደገለጸው፣ ተነሳሽነት መማርን በቀዳሚነት
የመቀስቀስ፣ ከትምህርት በኋላም የተገኘውን እውቀት ዘላቂ እንዲሆን የመርዳት በአጠቃላይ የማትጋት ሀይል አለው :: እንዲሁም
Spolsky (1989) እንዳስረዳው፣ መነሳሳት ያላቸው ተማሪዎች በሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ተግባር ውስጥ ተሳታፊ ይሆናሉ፤
በተቃራኒው ግን ተነሳሽነት የሌላቸው ተማሪዎች በቀረበላቸው የሁለተኘ ቋንቋ ትምህርት ውስጥ ተሳታፊ እንደማይሆኑ
አመልክቷል፡፡ ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ Gardner (2007) አንዳስረዱት አዎንታዊ ተጽእኖ ከጥሩ ውጤትና ከንቁ
የክፍል ውስጥ ተሳትፎ ጋር ሲጣመር፣ አሉታዊ ተጽዕኖ ያለባቸው ተማሪዎች ግን በትምህርታቸው አዝጋሚ፣
በቋንቋ ክሂል እድገት ደግሞ ደካሞች አንደሚሆኑ ይጠቁማሉ፡፡
ከላይ ከቀረበው የምሁራን ሃሳብ መገንዘብ የሚቻለው ተማሪዎች በሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ ያላቸው ተነሳሽነት
በታላሚው ቋንቋ ላይ አዎንታዊወይም አሉታዊ ጫና የሚያሳድር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ መምህራን ተማሪዎች
ለቀረበላቸው የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት አዎንታዊ ተነሳሽነት እንዲኖራቸው በመምክርና በማበረታ የበኩላቸውን
አስተዋጾኦ ቢያደርጉ የተሻለ ውጤት እንደሚገኝ የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡

2.6.3.በስነልቦና ችግር ምክንያት የሚከሰት ተጽዕኖ


Gardner (2007) አገላለጽ ስነልቦናዊ ጉዳይ ሲባል የሚያያዘው ከተማሪዎቹ የግል ጉዳይ ጋር ሲሆን፣ ተማሪዎቹ
ከክፍል ውጪ ስላለው ሁኔታ በአእምሯቸው ውስጥ ይዘውት የሚመጡት መጥፎ ነገር በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን
ትምህርት በደንብ እንዳይከታተሉ የሚደርጋቸው ነው፡፡በመሆኑም እንደ Harmer (1991) አነጋገር ተማሪዎች
በሚናገሩት ቋንቋ ስኬታማ ከሆኑ ሁልጊዜም በቋንቋው ላይ ጥሩ የአጠቃቀም ዝንባሌ ይኖራቸዋል፡፡በማያያዝም
11
ከበፊቱ ጀምሮ በቋንቋው አጠቃቀም ላይ ውድቀት ካለ አሁንም ይሄው ውድቀት ይከሰትብናል የሚል ፍራቻ
ያድርባቸዋል ሲል አስረድቷል፡፡ሌላው በሁለተኛ ቋንቋ ትምህረት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው ተማሪው ስህተት
ብፈጽም ምን እባላለሁ በሚል ፍርሀትና ጭንቀት ምክንያት የሚከሰት የስነልቦና ችግር እንደሆነ Torne(1997)
ይገልፃሉ፡፡

ከላይ ከቀረበው ሀሳብ መረዳት እንደሚቻለው ተማሪው በውስጡ ያለው የስነልቦና ሁኔታ በክፍል ውስጥ ያለውን
የመማር ማስተማር ውጤታማ ወይም ውጤት አልባ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው በማወቅ የመማር
ማስተማሩ ሂደት ውጤታማ እና የሰመረ እንዲሆን ተማሪዎቹን በማነቃቃታና በማደፋፈር በትምርቱ ላይ ተሳታፊ
እንዲሆኑ ሁኔታዎች ማመቻቸት ተገቢ ነው፡፡

2.6.4. በቤተሰብ በኩል የሚመጣ ተጽዕኖ


እንደ Gardner (2007) አገላለጽ፣ ልጆች በሁለተኛ ቋንቋ ትምህርታቸው የሚያገኙት ስኬትም ሆነ ውድቀት
ወላጆቻቸው ለትምህርት በቀረበው በሁለተኛ ቋንቋ ላይ ያላቸው አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ ለቋንቋው
አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ወላጆች ልጆቻቸው የቤትና የክፍል ስራዎችን ጠንክረው እንዲሰሩና ተግተው
እንዲያጠኑ በማበረታታት ለጥሩ ውጤት እንደሚያበቋቸው፤ በሌላ በኩል ደግሞ አሉታዊ አመለካከት ያላቸው
ወላጆች ደግሞ ለትምህርት የቀረበውን ሁለተኛ ቋንቋ ልጆቻቸው እንዲማሩ ካለማድረጋቸው የተነሳ
ልጆቻቸውን በማበረታታት የሚጫወቱት ሚና በጣም ደካማ እንደሆነ እነዚሁ ምሁራን አስረድተዋል፡፡
በዚህም የተነሳ በወላጆቻቸው የማይበረታቱት ተማሪዎች በወላጆቻቸው ከሚበረታቱት በተቃራኒው
የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ለመማር አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡ ወላጆች ለትምህርት በቀረበው ሁለተኛ
ቋንቋ ላይ ያላቸው አዎንታዊ አመለካከት የልጆቻቸውን የመማር ፍላጎት በማነቃቃትና በማነሳሳት
የሚጠበቀውን ብቃት ብሎም ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ይታመናል፡፡በ Gardner (1985) እይታ የወላጆች
ማበረታቻና የልጆች ሁለተኛ ቋንቋ ውጤት ጥምረት በሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ
በማሳደር ረገድ ከፍተኛውን ሚና እንደሚጫወት አስረድቷል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ ከቀረበው የምሁራን ሀሳብ መረዳት የሚቻለው የቋንቋው ተማሪ ቤተሰብ ተማሪው
በሚማረው የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ የሚያሳው አመለካከት ወይም አተያይ ተማሪውን በማነቃቃት
አለያም በማደከም በሚማረው ትምህርት ፍላጎት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ
የማይናቅ ድርሻ እንዳለው ነው፡፡ስለዚህ ወላጆ ከባለድርሻ አካላት ውስጥ አንዱ እንደመሆናቸው መጠን
ልጆቻቸውን ለታላሚው ትምህርት አነሳሽና ገንቢ የሆነ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ
እንዳለባቸው ይታመናል፡፡

2.6.5. በተማሪው ጓደኞች በኩል የሚከሰት ተጽእኖ


በአንድ ተማሪ የህይውት ጉዞ ላይ ተጽእኖ ከሚያሳድሩት ተላዎጦዎች መካክል አንዱ በተማሪው ጓደኞች
በኩል የሚመጣው ተጽዕኖ ነው፡፡ የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው የእድሜ እኩዮችና ጓደኞች በተማሪው ላይ
አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ ማሳደር እንደሚችሉ Harmer (1991) ይገልልፃል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ
12
Harmer (1983) እንደገለፀው የጓደኞች ወይም የእድሜ እኩዮች አመለካከት በሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው ላይ
አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ረገድ ከሌሎች ተጽእኖዎች ይልቅ ከፍተኛ ተጽእኖ የማድረስ
ሀይል እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡ በእድሜ እኩዮች የሚከሰተውን አሉታዊ ተጽዕኖ በተማሪው ወላጆችና
በቋንቋውመምህራን ለመቀነስ ጥረት ካልተደረገ ሁለተኛ ቋንቋን የመማር ፍላጎታቸው ሊቀንስ እንደሚችል
እነዚሁ ምሁራን አስረድተዋል፡፡ይሁን እንጂ በእድሜ እኩዮች በኩል በሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች ላይ
የሚመጣው ጫና ምንጊዜም ቢሆን በእድሜ እርከን ስለሚወሰን ልጆች በተፈጥሯቸው አዲስ ነገር የማወቅ
ጉጉ ባህሪ ስላላቸው በጓደኞቻቸው በኩል የሚመጣባቸው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንደየ
እድሜያቸው ሁኔታ እንደሚገደብ Gardner (1985) አስረድቷል ፡፡

ከላይ በተለያዩ ምሁራን የቀረበውን ሃሳብ መሰረት በማድረግ መረዳት የሚቻለው የተማሪው ጓደኞች
የማህበረሰቡ አባል እንደመሆናቸው መጠን ይዘውት ያመጡትን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ
በጓደኞቻቸው ላይ በማንጸባረቅ በመማር ማስተማሩም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ
በማሳደር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በማወቅ የማስተማሩን ሂደት ስኬታማ ለማድረግ ብጤዎች ላይ
ገንቢ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ መስራትእንደሚገባ ነው፡፡

2.6.6.ተማሪው ከሚኖርበት ህብረተሰብ በኩል የሚመጣ ተጽዕኖ


የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው የህብረተሰቡ አባል እንደመሆኑ መጠን በጥሩውም ይሁን በመጥፎው ነገር
ከህብረተሰቡ የሚጋራቸው ነገሮች አሉ፡፡ ምክንያቱም ተማሪው ከቤተሰቡ ጋር ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን
ቀስ በቀስ ለህብረተሰቡ ስርአት ተገዢ እንደሚሆንና እንዲሁም ተማሪው ባለበት ህብረተ-ሰብ መታቀፉ
በሚማረው የቋንቋ ትምህርት ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር Harmer (1991) አስረድቷል፡፡
እንዲሁም የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው ህብረተሰብ ለትምህርት በቀረበው ሁለተኛ ቋንቋ ላይ የሚያንጸባርቀው
አሉታዊ አመለካከት የተማሪውን የመማር ፍላጎት እንደሚያዳክመው የበርካታ ምሁራን የጥናት ውጤቶች
አሳይቷል፡፡ ለምሳሌም Gardner (2007) ተማሪዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ አመለካከት መዳበር ተማሪው
የሚኖርበት ህብረተሰብ ለአፍ-ፈቱ ህብረተሰብ ካለው አመለካከት የመነጨ እንደነበር አመልተዋል፡፡

በአጠቃላይ የኢ-አፍ-ፈቱ ህብረተሰብ ለትምህርት በቀረበው ሁለተኛ ቋንቋ ላይ የሚኖረው አዎንታዊም ሆነ


አሉታዊ አመለካከት በሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው ፍላጎት ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደሩ ረገድ
የማይናቅ ድርሻ ስለሚኖረው በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ጫና የሚሳድር መሆኑን በመረዳት ህብረተሰቡ
ለታላሚው ቋንቋ አዎንታዊ አተያይ እንዲኖረው ተገቢውን ጥረት ማድረግአስፈላጊ ነው ፡፡

2.6.7.በቋንቋ መምህራን ስብእና እና በማስተማሪያ ዘዴ ምክንያት


የሚከሰት ተጽዕኖ
በትምህርት ትግበራ ወቅት የመማር ማስተማሩን ተግባር ውጤታማና ፍሬያማ ለማድረግ የመምህሩ ስብዕና
እና ትምህርቱን የማስተማሪያው ዘዴ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ጎን በተማሪዎች ፍላጎት ላይ
13
የሚያሳድረው ተጽእኖ እንዳለው ይገመታል፡፡ ለሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት የቀረበውን ትምህርት በሙሉ
ፍላጎት፣ በንቃትና በተሳትፎ ተማሪው መማር እንዲችል ሁኔታዎችን ለማስተካከል ጥረት ከሚያደርጉ አካላት
ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው መምህሩ ስለሆነ የመማር ማስተማሩን ሁኔታ ለማመቻቸት ያላሰለሰ
ጥረት ማድረግ እንዳለበት Harmer (1990) እና Spolesky (1989) ያስረዳሉ፡፡

መምህሩ ተማሪዎች ለትምህርት የቀረበውን ሁለተኛ ቋንቋ ሲማሩ ምን ስሜት እንደሚሰማቸው፣


በትምህርቱ ክንዋኔ ወቅት በፍላጎትና በንቃት መሳተፍ አለመሳተፋቸውን፣ ለቋንቋው ተናጋሪ ባለቤትና
ለትምህርቱ ያላቸውን መልካምና መጥፎ አተያይ፣ ስለራሱ ስለመምህሩና ስለሚጠቀምበት የማስተማሪያ
ስልት ያላቸው እይታ ምን እንደሚመስል በማወቅ፣ ለተማሪዎቹ መልካም አመለካከት ኖሮት የትምህርቱን
ሂደት መምራት እንደሚገባው brown (2007) ያስገነዝባል፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚያስተምረው
ቋንቋና ለቋንቋው ተናጋሪ ማህበረሰብ እንዲሁም ለተማሪዎቹ ጥላቻ ካለው የትምህርቱ መማር ማስተማር
ሂደት አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል Harmer (1990) አስረድቷል፡፡ እንዲሁም torne (1997) እንዳስረዳው፣
የቋንቋ ትምህርቱን ለማስተማር የቀረበውመምህር ስብእና በተማሪው ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ
ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ ይሄው ምሁር እንደ ምክንያት የሚያቀርበው የአንድ መምህር ተግባር የአምባ ገነንነትና
የአመጸኝነት ስሜት በተማሪዎቹ ላይ የሚያንጸባርቅ ከሆነ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ አሉታዊ ጫና
ስለሚያሳድር በተማሪዎቹ ላይ ፍራቻና ጭንቀትን ያሳድራል፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎቹ ለትምህርት በቀረበው
ቋንቋ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችል Evanse (1965) ያስረዳል፡፡ በሌላበኩል ታደስ (2004)
እንዳብራራው፣ የሁለተኛ ቋንቋ መምህር ለተማሪዎቹ አዎንታዊ አመለካከት ኖሮት፣ የክፍል ተግባራትንና
የክፍሉን ሁኔታ ለተግባቦት ምቹበማድረግ፣ ተማሪዎቹ በተለያዩ ተግባራት ሲሰማሩማ በረታታት፣ መምራት፣
ድጋፍ መስጠት፣ ተማሪዎች ከሰህተታቸው እዲማሩ ማድረግና ማበረታታት አንዱ ሌላውን እንዲያርም
በማድረግ የበለጠ የቀረበላቸውን ትምህርት እንዲማሩ ሊያደርግ ይችላል፤ ከዚህ ውጭ ግን መምህሩ ፈላጭ
ቆራጭ ከሆነ ተማሪው በሚማረው የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርትላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

ስለዚህ የመምህሩ ስብእና በተማሪዎች የመማር ፍላጎት ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ
ሊያሳድር እንደሚችል ከላይ ከቀረበው የተለያዩ ምሁራን ሀሳብ መረዳት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ታደሰ (2004) ተማሪዎች ለቀረበላቸው ትምህርት ፍላጎት እንዲኖራቸው መምህራን በክፍል
ውስጥ በሚያስተምሩበት ወቅት የተማሪውን ጠንካራ ጎን ማጉላት፣ ከተማሪው ህይወት ጋር የተገናኘ ምሳሌ
መስጠት፣ ሁልጊዜ ድርቅ ያለ ዕውነታ ላይ ብቻ ባለማተኮር፣ የተማሪዎቹን ወቅታዊ ስሜት በመጠቀም እና
የማስተማሪያ ስልትን በመለዋወጥ የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ማነቃቀት እንደሚጠበቅባቸው ያስረዳል፡፡

ከላይ በተለያዩ ምሁራን እንደተገለጸው የቋንቋ መምህራን ስብእናም ሆነ የማስተማሪያው ዘዴ ለትምህርት


በቀረበው የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊሳድር ስለሚችል፣ የመማር
ማስተማሩ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን መምህራን በስነምግባር የታነጹ፣ የተማሪውን ስብዕና የሚጠብቁ ና
14
ጥሩ አተያይ ያላቸው እንዲሁም የተማሪውን የመማር ፍላጎት ሊያነሳሱ የሚችሉ፣ አሳታፊና ተገቢነት
ያላቸውን የማስተማሪያ ዘዴዎችን መጠቀም እንዳለባቸው መገንዘብ ያሻል፡፡

2.6.8.በመማሪያ መጽሀፉ ምክንያት የሚከሰት ተጽዕኖ


ለትምህርት የሚቀርብ የመማሪያ መጽሀፍ የተማሪዎችን ፍላጎት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ በማድረግ ረገድ
ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የተለያዩ አጥኚዎች ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ የቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ከመዘጋጀቱ
በፊት ትምህርቱን የሚማረው ተማሪ ቋንቋውን ለምን አላማ ሲል እንደሚማረው፣ፍላጎቱ ምን
እንደሆነ፣ለትምህርት ለቀረበው ቋንቋ ያለውን አመለካከት፣ የወጣበትን ማህበረሰብ ማንነትና
ፍላጎት፣ያለበትን የእወቀት ደረጃ፣ የቋንቋው ትምህርት የቀረበበትን ሁኔታ ማወቅ በሚያስችሉ የጥናት
መረጃዎች ላይ የተመሰረቱ መሆን እንደሚገባቸው Dubin(1986) አስረድተዋል ፡፡ እንዲሁም ታደሰ (2004)
የመማሪያ መጽሀፍት የሚዘጋጁበት አብይ ምክንያት በውስጣቸው በሚይዟቸው ደረጃቸውን በጠበቁ
የትምህርት ልምዶች አማካይነት የትምህርት አላማዎችን ከግብ የማድረስ አላማ እንዳለው በመግለጽ፣
ማንኛውም ትምህርት በመረሃ ግብር የሚመራ፣ በስርአት የተቀነባበረ አላማ ስለሚኖረው እነዚህን አላማዎች
ከግብ ለማድረስ ይቻል ዘንድ ለይዘት ምርጫና አደረጃጀት ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል በማለት
አብራርቷል፡፡ በ Dubin (1986) አስተያየት መማሪያ መጽሀፍት ከመዘጋጀታቸው በፊት የተማሪውን ማንነት
ማለትም ዜግነቱን፣ የትምህርት ዳራውን ወዘተ.. የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሀሳቦችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ
መሆን እንዳለባቸው የገለፀ ሲሆን ፣ በማከልም የመማሪያ መጽሀፍት ሲዘጋጅ ተማሪውን መሰረት በማድረግ
ለቋንቋ ትምህርቱ ጥሩ አመለካከትና የመማር ፍላጎት እንዲኖረው የሚያነሳሳ ሆኖ መዘጋጀት እንዳለበት
አስረድቷል፡፡

ስለዚህ የቋንቋው ትምህርት በተገቢውና በተቃና መንገድ የመማር ማስተማሩ ተግባር እንዲካሄድ የቋንቋ
መማሪያ መጽሀፍት የተማሪውን ፍላጎት እና ዳራዊ ችሎታ መሰረት አድርገው መዘጋጀት እንዳለባቸው
መረዳት ያሻል፡፡

እንዲሁም እንደ ወንድወሰን (1989) አገላለጽ፣ የመማሪያ መጽሀፍት በተማሪው ፍላጎት ላይ ተመስርተው
በጥንቃቄ ከተዘጋጁ የተማሪውን የመማር ፍላጎት አነቃቅተው ለቋንቋውና ለትምህርቱ የሚኖረውን
አመለካከት አዎንታዊ በማድረግ ለጥሩ ውጤት ያደርሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ Dubin (1986) እንዳስረዳው
የመማሪያ መጽሀፍት የተማሪዎችን የመማር ፍላጎትና ለትምህርቱ ያላቸውን አመለካከት ለማበረታታት፡-

 የትምህርት መሳሪያዎች ዝግጅት ልምድ ያላቸውን ባለሞያዎችንና መምህራን ባቀናጀ


መልኩ መዘጋጀት እንዳለባቸው፣
 በመጽሀፉ አማካይነት ለተማሪው እንዲቀርቡ የተፈለጉት የትምህርት ይዘቶችና
ስልቶች ከመርሀ ትምህርቱ ጋርግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚገባቸውና

15
 የመማሪያ መጽሀፍቱ መምህሩ እንዲያስተምር፣ ተማሪው እንዲማር የሚረዱ
ሆነው የተዘጋጁ እንጂ ጫና የሚፈጥሩባቸው ሆነው መዘጋጀት እንደሌለባቸው ነው፡፡

በአጠቃላይ የመማሪያ መጽሀፍት በሚዘጋጅበት ጊዜ የቋንቋ ተማሪውን መሰረት በማድረግ፣የመማር


ማስተማሩን ተግባር ግቡን እንዲመታ በተማሪው ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ተማሪውን የሚማርክ፣ የሚያነቃቃ፣
ልዩልዩ ተግባራትን ለማከናወን የሚያሳትፍና ችሎታውን መሰረት ያደረገ እንዲሁም ወደታለመው አላማ
የሚያደርስ መሆን እንዳለበት ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተማሪው ለቀረበለት የቋንቋ ትምህርት የሚኖረው ፍላጎት
አናሳ እንደሚሆን ብሎም የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት እንደማይቻል የሚያጠራጥር አይሆንም፡፡

2.7. ፍላጎት ከተማሪው ውጤት ጋር ያለው ዝምድና

የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪው ትምህርቱን ተፈትኖ የሚያገኘው ውጤት የተማሪውን የመማር ፍላጎት
በማነሳሳትም ሆነ በማዳከም የራሱ የሆነ ተጽዕኖ እንዳለው የተለያዩ ምሁራን የራሳቸውን አስተያየት
ሲሰነዝሩ ይስተዋላል፡፡ተዋበች (2003) Gardner (1985)ን፣ ዋቢ በማድረግ አዎንታዊ ተጽዕኖ ከከፍተኛ
ውጤት፣ አሉታዊ ተጽዕኖ ከዝቅተኛ ውጤትና ከደካማ የትምህርት ተሳትፎ ጋር ተዛማጅነት እንዳለው
በመግለጽ፣ ተማሪዎች ለሚማሩት ሁለተኛ ቋንቋ አዎንታዊ አመለካከት ካላቸው በትምህርቱ ንቁ ተሳታፊ
ከመሆናቸውም በላይ በራሳቸው የመተማመን ስሜት ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡ በራሳቸው የሚተማመኑ
ተማሪዎች ደግሞ የቋንቋውንም ትምህርት ፍላጎት እና ጥረት በተሟላ ሁኔታ ስለሚማሩ ውጤታቸው
የተሻለ ሆኗል ከሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል በማለት አስረድታለች፡፡

እንዲሁም Harmer (1991) ተማሪው ያለው ዳራዊ እውቀት በቋንቋው ትምህርት ፍላጎት ላይ ለውጥ
እንደሚያስከትል በመግለጽ፣ቀደም ሲል ውጤቱ ስኬታማ ካልሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ጥሩ ውጤት
አምጥቶ ማለፍ እንደማይችል ስለሚገምት በትምህርቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር በማመልከት፣
ተማሪዎች በሚማሩት የቋንቋ ትምህርት የሚያገኙትን ውጤት ምክንያት በማድረግ በትምህርቱ ላይ
አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያዳብሩ ይችላሉ በማለት አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም ወንድወሰን
(1989) ታደለ (1990)ን በመጥቀስ እንደገለፀው፣ በቋንቋ ትምህርት ሂደት ተማሪው የሚገጥመውና በውስጡ
የሚያልፍበት ሁኔታ፣ የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት፣ የቋንቋው መምህር፣ የማስተማሪያ መሳሪያዎች፣
በአጠቃላይ የትምህርቱ ስርአትና ሌሎች ማህበራዊ የሆኑ ጉዳዮች፣ በመማር ማስተማሩ ሂደት ተማሪው
ከነዚህ ጉዳዮች ጋር በሚያደርገው መስተጋብርና እንቅስቃሴ በሚመነጭ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ
ሊያድርበት ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪው በትምህርቱ ሂደት ከሚያደርገው የመማር ጥረትና ውጤት ጋር
ይገናኛል በማለት ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ከቀረበው ሀሳብ መገንዘብ እንደሚቻለው ተማሪው በላሚው ትምህርት የሚያገኘው
ውጤት ተማሪውን በማበረታታት ወይም በማዳከም ረገድ ተጽዕኖ ማሳደር እንደሚችል ነው፡፡ ውጤቱ

16
ስኬታማ ከሆነ ትምህርቱን የመማር ፍላጎት እንደሚኖረው ሁሉ ውጤቱ ዝቅተኛ ከሆነ ደግሞ የመማር
ፍላጎቱም አናሳ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ ተማሪው በትምህርቱ በሚያገኘው ውጤት የተነሳ
ታላሚውን ቋንቋ የመማር ፍላጎቱ ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው፡፡

2.7.የቀደምት ስራዎች ቅኝት


በዚህ ጥናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚመሳሰሉ ጥናታዊ ጽሁፎችን ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
በዳሰሳው ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም ወቅት በጥናቱ
የቀረቡ የትኩረት ነጥቦች፣ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች፣ የጥናቶቹ ውጤት እና የመፍትሄ ሀሳቦች
ተቃኝተዋል፡፡
ፀጋዬ (1996) ለ 2 ኛ ዲግሪ የቀረበ የሟሟያ ጽሁፍ ሲሆን የጥናታቸው ርዕስም ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት በሚኖራቸው አመለካከት ላይ ዝምድና ያላቸው ተላውጦዎች ፣በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
መንግስታዊ ባልሆኑ ትምህርት ቤቶች የሚል ነው፡፡ በጥናቱ ላይ የተተኮረባቸው አብይ ይዘቶች ተማሪዎች
ለታላሚ ቋንቋቸው ያላቸው አመለካከት አወንታዊ መሆኑም አስመልክቶ መንግስታዊ ባልሆኑ ትምህርት
ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸው አመለካከት አወንታዊና አሉታዊ መንስኤች ምንድን
ናቸው የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቷል፡፡ መረጃዎቹም ከወላጆች፣ ከተማሪዎችና ከመምህራን በፅሁፍ መጠይቅ፣
በቃለ መጠይቅና በምልከታ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡
በጥናታቸውም ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋና የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መካከል ልዩነት መሆሩን በመገንዘብ
አማርኛ ቋንቋችን በመሆኑ እንወደዋለን ሲሉ፣ ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግን በአብዛኛው ያላቸው
አመለካከት አወንታዊ ያለመሆኑን በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡ አልፎ አልፎ ግን ለቋንቋ ትምህርቱ በጎ
አመለካከት ያላቸው ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም ወንድወሰን (1989) የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሀድይኛ የሆነ የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና የውጤታቸው ዝምድና የሚል ሲሆን፣ ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ
የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ ነው፡፡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችም የጽሁፍ መጠይቅ ፣ የክፍል ምልከታ
በማድረግ እና የአንደኛ መንፈቀ- አመትና የመሰናዶ /model/ ፈተና ድምር አማካይ ውጤት በመውሰድ ነው፡፡
የጥናቱ ውጤት እንዳሳየው ተማሪዎቹ ለቋንቋውና ለትምህርቱ አዎንታዊ አመለካከት እንዳላቸው
ሲያመለክት፣ በአመለካከትና በፈተና ውጤት መካክል የጎላ ዝምድና እንደሌለ አስረድቷል፡፡ በአስተያየቱ
የሚመለከታቸው ክፍሎች ሁሉ የተማሪዎች አመለካከት ከመማር ማስተማር ጋር ግንኙነት እንዳለው
አውቀው፣ ለፍላጎታቸው ተስማሚና ለአመለካከታቸው ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉ የትምህርት መሳሪያዎችን
ሊያቀርቡላቸው ቢችሉ የተሻለ ውጤት ሊመዘገብ ይችላል በማለት አስረድቷል፡፡
ተዋበች (2003) ለ 2 ኛ ድግሪ ማሟያ ባቀረበችው ጽሁፏ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከፊኛ የሆነ የ 10 ኛ ክፍል
ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና የፈተና ውጤት ዝምድና የሚል ነው፡፡ ጥናቷም
ትኩረት ያደረገው በአመለካከትና በፈተና ውጤት ዝምድና ላይ ሲሆን፣ ለመረጃ መሰብሰቢያ የተጠቀመችው

17
የጽሁፍ መጠይቅ፣የክፍል ውስጥ ምልከታ፣ቃለ መጠይቅና የ 2003 ዓ.ም. ተከታታይ ምዘናና የአንደኛ መንፈቀ
አመት አማካይ ውጤት ነው፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው ብዙ ተማሪዎች ለቋንቋውና ለትምህርቱ
ያላቸው አመለካከት አናሳ እንደሆነ ከመጠቆሟም በላይ በተማሪዎቹ አመለካከትና በፈተናው ውጤታቸው
መካከል ዝቅተኛ አዎንታዊ አመለካከትና ከማለፊያ ውጤት ጋር ዝምድና እንዳለው አመልክታለች፡፡ እንደ
መፍትሄም ያስቀመጠችው ተማሪዎች ለአማርኛና ለሌሎች የትምህርት አይነቶች እኩል ፍላጎት
እንዲኖራቸው አንዱ ሌላውን በማይጫን መልኩ የተለያየ የስነጽሁፍ ክበባትና የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም
በመፍጠር ለታላሚው ቋንቋ ፍላጎታቸውን ማነሳሳት እንደሚቻል አስገንዝባለች፡፡
ይህን ጥናት ከቀረቡት ከወንደሰንና ከተዋበች ጥናቶች ጋር የሚያመሳስለው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን እንደ
ሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ ተማሪዎች ላይ መካሄዱ እምዲሁም የሰነድ ፍተሻ መጠቀሙ፡፡ ሌላው የጽሁፍ
መጠይቅን ለመረጃ መሰብሰቢያነት በመጠቀሙ ከሶስቱ የቀደምት ጥናቶች ጋር ያመሳስለዋል፡፡ እንዲሁም ቃለ-
መጠይቅን ለመረጃ መሰብሰቢነት በመጠቀሙና 10 ኛ ክፍል ላይ ጥናቱ መደረጉ ከፀጋዬና ተዋበች ጥናት ጋር
እንዲመሳሰል አድርጎታል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ በከተማ መስተዳድር ውስጥ መደረጉ ከፀጋዬ ጥናት ጋር
ያመሳስለዋል፡፡

ይህ ጥናት ከቀደምት ጥናቶች ጋር የሚያመሳስለው እንዳለ ሁሉ ልዩነትም አለው፡፡ ከቀደምት ስራዎች


የሚለየው አብይ ልዩነት በኦሮምኛ ቋንቋ አፍ ፈት የሆኑ ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋ ለመማር ያላቸው
ፍላጎትና የውጤት ተዛምዶ መፈተሸ ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ሌላው ልዩነት ከቋንቋ አንፃርም ኦሮምኛ ቋንቋ አፍ-
ፈት ተማሪዎች ላይ መደረጉ ከፀጋዬ፣ከተዋበችና ከወንድወስን ልዩ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ገላጭ
(Descriptive) የምርምር ንድፍ መከተሉ እንዲሁ ሌላው ልዩነት ነው፡፡ እንዲሁም ከጊዜና ከቦታም አንጻር
ሲታይ ከላይ ከተገለጹት ቀደምት ጥናቶች ልዩ ያደርገዋል፡፡

ምዕራፍ ሦስት

የአጠናን ዘዴ

3.1. የጥናቱ ንድፍ


ይህ ጥናት ቅይጥ(mixed) የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን የሚከተል ነው፡፡አይነታዊ የመረጃ መሰብሰቢያ
የተከተልበት ትምክንያት ከመምህራን በቃለ መጠይቅ የተገኘውን መረጃ በገለጻ የምታቀርብ ሲሆን፣ መጠናዊ
የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ የምትጠቀምበት ምክንያት ደግሞ ከተጠኚ ተማሪዎች በጽሁፍ መጠይቅ
የሚሰበሰበውን መረጃ በቁጥርና በፐርሰንት ለማቅረብ ነው፡፡

ጥናቱ ገላጭ (Descriptive) የምርምር ንድፍን መሰረት አድርጎ የሚቀርብ ነው፡፡ ቃሉ እንደሚያመለክተው
ተመራማሪዋ አንድ ጉዳይ አንስታ ሁኔታዎች ብሩህ እስኪሆኑ ድረስ ምንነታቸውን፣ እንዴትነታቸውን፣
ማናነታቸውን፣ የድርጊቶችን አኳኀንና ምን በመሆን ላይ እንዳለ በገለፃ መልክ የምታቀርብበት ነው፡፡

18
ጥናቱ የገለፃ ስልት የተከተልበት ምክንያት የጥናቱን ርዕሰ ጉዳይ ለመግለጽ የሚያስችል ዘዴ በመሆኑና ለጥናቱ
አጋዥ የሚሆኑ መረጃዎችን ማለትም በጽሁፍ መጠይቅና በቃለ መጠይቅ የሚሰበሰቡትን መረጃዎች
ለመተንተን ምቹ በመሆኑ ነው፡፡
3.2 የናሙና አመራረጥ ዘዴ
3.2.1.የከተማመስተዳድአመራረጥ
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ መስተዳድሮች ሁለት ሲሆኑ አጥኚዋ ለጥናቱ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት
ይረዳው ዘንድ አመቺ (convenience sampling) ንሞና በመጠቀም የድሬዳዋ መስተዳድርን ትመርጣለች፡፡
ይህ መስተዳድር የምትመርጥበት ምክንያት አጥኝዋ ከዚህ መስተዳድር በቂ መረጃ፣ በቂ ትብብርና የሰው
ሀይል ማግኘት እንደምትችል በማሰብ ነው፡፡

3.2.2. የትምህርት ቤት አመራረጥ


በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ውስጥ 8 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ ት/ቤቶች ውስጥ የእጣ
ንሞና (Lottery System)ን በመጠቀም ሁለት 2 ኛ ደረጃ ትምህት ቤቶች ትመርጣለች፡፡ የዕጣ ንሞና
የሚመረጥበት ምክንያት ለሁሉም ትምህርት ቤቶች እኩል ዕድል ለመስጠት ነው፡፡
3.2.3. የክፍልና የምድብ አመራረጥ
በድሬዳዋ ከተማ መሰተዳድር ከ 9-12 ኛ ክፍል ውስጥ 9 ኛ ክፍልን የምትመርጥ ሲሆን ይህን ክፍል
የመረጠችበት ምክንያት ተማሪዎቹ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርታቸውን ስለሚጀምሩ ነው፡፡ የምድብ አመራረጡን በመለከተ በናሙናነት ከሚመረጠው ትምህርት
ቤቶች ውስጥ ካሉ ምድቦች የእጣ ንሞና (Lottery System) በመጠቀም አራት በድምሩ ስምንት ምድብ
ይመረጣሉ፡፡
3.2.4.የተማሪዎች አመራረጥ
አጥኝዋ በናሙናነት ከሚመረጡ 8 ምድቦች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን ስብጥራዊ የንሞና ዘዴ (Stratified
Smpling) በመጠቀም ኦሮምኛ አፍ- ፈት የሆኑ ተማሪዎች ይመረጣሉ::
3.2.5. የመምህራን ናሙና አመራረጥ
ለዚህ ጥናት በናሙናነት በሚመረጡ በ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ
መምህራን ጠቅላይ ንሞና (Comprehensive Sampling) በመጠቀም ሁሉም በቃለ-መጠይቁ ውሰጥ
ይሳተፋሉ፡፡ ይህ የንሞና ዘዴ የተመረጠበት ምክንያት አማርኛ ቋንቋን የሚያስተምሩ መምህራን ቁጥር
አነስተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
3.3 የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች
ለዚህ ጥናት ዋናው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የጽሁፍ መጠይቅ ሲሆን ፣ ለተማሪዎች የሚቀርብ በጽሁፍ
መጠይቅ የሚገኘውን መረጃ ይበልጥ ለማጠናከር ቃለ መጠይቅና የሰነድ ፍተሻ ለመረጃ መሰብሰቢነት ተግባር
ላይ ይውላል፡፡ የመረጃ ምንጮቹም ተማሪዎችና መምህራን ይሆናሉ፡፡

19
3.3.1 የጽሁፍ መጠይቅ

በዚህ ጥናት ውስጥ በዋነኛነት የመረጃ መሰብሰቢያ ሆኖ የሚመረጠው የጽሁፍ መጠይቅ ነው፡፡ ያለው (2006)
እንደገለጸው፣ የጽሁፍ መጠይቅ በዋናነት የተመረጠበት ምክንያት፡-ቆጣቢ፣ የመላሾቹን ማንነት የማይገልጽ ና
ለሁሉም ተጠኚዎች አንድ አይነት ጥያቄ የሚያቀርብ ስለሆነ ነው፡፡

የጽሁፍ መጠይቆቹ የተዘጋጁት ክለሳ ድርሳኑን መሰረት በማድግ ሲሆን፣ በጽሁፍ መጠይቁ ተማሪዎች አማርኛ
ቋንቋን በማስተማር ሂደት ላይ ያላቸውን ፍላጎት መፈተሽ የሚመለከቱ ጥያቄዎች የሚካተቱ ሲሆኑ
ጥያቄዎቹም ሶስት ክፍሎች ያኖሩታል፡፡የመጀመሪያው ክፍል የተጠኚዎቹን ዳራ የሚመለከት ሲሆን፣
ሁለተኛው ክፍል ዝግ

ጥያቄዎችን እና ሶስተኛው ክፍል ደግሞ ክፍት ጥያቄዎችን ያካትታል፡፡ዝግ ጥያቄዎቹ የሊከርት ሞዴልን
መሰረት በማድረግ የተዘጋጁ ሲሆን፣ በጣም እስማማለሁ(5)፣ እስማማለሁ(4)፣ መወሰን ያቅተኛል(3)፣
አልስማማም(2)፣ ጭራሽ አልስማማም(1) የሚሉ አማራጮችን ተካተው በሰንጠረዥ የሚቀርብ ሲሆን
ክፍት (ልቅ) ጥያቄዎቹ ደግሞ የተጠኚዎችን ነጻ አስተያየት የሚሹ ይሆናሉ፡፡ መጠይቆቹ በአጥኝዋ ከተዘጋጁ
በኋላ በአማካሪው አስፈላጊው እርምትና ማስተካከያ ከተደረገባቸው በኋላ መጠይቆቹን ለተጠኚዎቹ
በማደል ሞልተው ሲጨርሱ አጥኝዋ መረጃውን ትሰበስባለች፡፡

የመጠይቆቹን አስተማማኝነት፣ ግልጽነትና ተነባቢነት ለማወቅ ፣ የጥናቱን አላማ ግብ ለማድረስ እንዲሁም


የጥናቱን መሰረታዊ ጥያቄ መመለሳቸውን ለማረጋገጥ በናሙናነት አሚመረጡ ትምህርት ቤት ውጪ አንድ 2 ኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት በ 2015 ዓ.ም በሚማሩና በጥናቱ ውስጥ ባልተካተቱ ሰላሳ ኦሮምኛ አፍ-ፈት የሆኑ .የዘጠኛ
ክፍል ተማሪዎች ላይ ሙከራ ይደረጋል፡፡በናሙናነት ውጪ ባለ አንድ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ካሉ የ 9 ኛ
ክፍል ምድቦች ውስጥ፣ አንድ ምድብ በእጣ ንሞና አመራረጥ ይመረጣል፡፡ በማስከተልም በናሙናነት
ከተመረጠው ምድብ ውስጥ በኦሮምኛ ቋንቋ አፍ-ፈት የሆኑ ተማሪዎች ሲመዘገቡ የሞሉትን ሰነድ በማየት
ስብጥራዊ የንሞና ዘዴ በመጠቀም ይለያሉ፡፡ የሚመረጡትን ተማሪዎች አንድ ክፍል ውስጥ በማስገባት የጽሁፍ
መጠይቁን ኣላማ ገለጻ ይሰጣቸዋል፣ በመመሪያው መሰረት መጠይቁን ሞልተው ይመልሳሉ፡፡ በዚህም መሰረት
የመጠይቁ አስተማማኝ መሆኑን Cronbach,s Alfa coafficiant reliability index of 0.70 እና በላይ
አስተማማኝ እንደሆነ ከተረጋገጠ በኃላ መጠይቁ ዋናውን መረጃ ለመሰብሰብ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
3.3.2 ቃለ መጠይቅ
በጽሁፍ መጠይቁ የሚገኘውን መረጃ ለማጠናከር በአጋዥነት ለመምህራን ቃለመጠይቅ ይቀርባል፡፡ በጥናቱ
ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግው የቃለ መጠይቅ አይነት (Semi Structured Interview) ይሆናል፡፡ይህ የቃለ
መጠይቅ አይነት የሚመረጥበ ምክንያት መላሹ የራሱን ሀሳብ ለመስጠት ነጻ የሚያደርገው ስለሚሆን ነው፡፡የቃለ
መጠይቅ ጥያቄዎች ብዛት እንደ ርእሰ ጉዳዩ የሚወሰን ሲሆን የቃል ጥያቄዎች የሚዘጋጁት በምዕራፍ ሁለት ስር
20
የቀረቡትን ክለሳድረሳናት መሰረት ባድረግ ነው::ቃለ-መጠይቆቹ በአጥኝዋ ከተዘጋጁ በኋላ በቀጥታ ለተጥኚዎቹ
ከመቅረባቸው በፊት ለአማካሪው ቀርበው ከተገመገሙና አስፈላጊው ማሻሻያ ከተደረገባቸው በኋላ ተገቢውን
መረጃ ማስገኘት እንደሚችሉ ሲታመንባቸው፣ ቃለ መጠይቆቹ ለመምህራን ቀርበው ለጥናቱ መረጃ ይሰበሰባል፡፡
መምህራን ቃለ-መጠይቅ በሚደረግላቸው ጊዜ ለቃለ መጠይቁ የሰጡትን መረጃ በወረቀት ላይ ለማስፈርና ተመሳሳይ
መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማቀናጀት ይመች ዘንድ የተጠኚዎችን ፍቃድ በመጠየቅ መቅረጸ ድምጽ ትጠቀማለች፡፡
3.3.3.ሰነድ ፍተሻ
ተማሪዎች በተከታታይ ምዘናና በአንደኛ መንፈቅ የሚያገኙትን ውጤትና ፍላጎት በተዛምዶ ቀመር ተሰልቶ በሁለቱ
መካከል የሚኖረውን ጥምረት የሚተነተኑ ይሆናል፡፡የሚገኘውንም ውጤት የበለጠ ለማጠናከር የተማሪውን የ 2015 ዓ.ም
የዘጠነኛ ክፍል ተከታታይ ምዘናና የአንደኛ መንፈቅ አመት ፈተና ውጤት ድምር አማካኝ ተወስዶ በቀመር ስልት
ተተንትኖ የሚገኘው ውጤት ይተረጎማል፡፡

3.5. የመረጃ አተናተን ዘዴ


በዚህ ጥናት ውስጥ መጠናዊና አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተግባር ላይ ይውላሉ ፡፡ከተማሪዎች በጽሁፍ መጠይቅ እና
ከመምህራን በቃለ መጠይቅ የተገኙ መረጃዎች ይተነተናሉ፡፡በተጠኚዎቹ የተሞላው የጽሁፍ መጠይቅ የሚሰበሰበው መረጃ
ተለይቶ ለእያንዳንዱ ጥያቄ የተሰጠውን መልስ በጥራት በመልቀም ተቆጥሮ በሰንጠረዥ ይቀርባል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ
መረጃዎችን በግልጽ ለማሳየት እንዲቻል አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ቦታ ሁሉ ሰንጠረዦችንና ስሌቶችን በቁጥር ፣ በመቶኛ
(percent) እንዲሁም በአማካኝ በማስላት በጥንቃቄ ይቀርባል፡፡በቃለ መጠይቅ የተገኘውም መረጃ ጣልቃ እየገባ በገለፃ
ሲተነተን፣የ 2015 ዓ.ም ተከታታይ ምዘናና የአንደኛ መንፈቅ አመት ፈተና ውጤት ድምር አማካኝ ተወስዶ በቀመር ስልት
ተተንትኖ ይቀርባል፡፡ በመጨረሻም በሶስቱ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የሚገኘው ውጤት መሰረት በማድረግ ከተለያዩ
ተዛማጅነት ካላቸው ክለሳ ድርሳናት ጋር በማገናዘብ በአጥኝዋ ማጠቃለያና መደምደሚያ ይሰጣል፡፡

ዋቢ መፅሃፍት

ማስረሻ ደባኖ ፡፡(2003)፡፡ አሳታፊ የማስተማር ዘዴ አተገባበር፡፡በሆሳህና መምህራም


ትምህርት ኮሌጅ
ታደሰ ሲባሞ።(2004)፡፡አማርኛን የማስተማር ስነዘዴ።አዲስ አበባ፤ትምህርት
ሚኒስቴር፡፡
ተዋበች ተክሌ፡፡(2003)፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ከፊኛ የሆነ የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች
21
ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና የፈተና ውጤት ዝምድና (ደቡብ
ክልል)::2 ኛ ድግሪማሟያ የቀረበ ጽሁፍ፡፡›› አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣(ያልታተመ)፡፡
አሰፋ አማየሁ፡፡ (1994)፡፡‹‹ በሆለታ ከፍተኛ 2 ኛደረጃ ት/ቤት አፋቸውን በኦሮምኛ
የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ያላቸው አተያይ፡፡››
ለባችለር ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ፡፡አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ፣(ያልታተመ)፡፡
አበበ ሽፈራው ፡፡(1990)፡፡‹‹ አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ
ት/ት ላይ ያላቸው አመለካከት በሰበተሰ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፡፡››
ኮ.መ.ት.ኮ.፣(ያልታተመ)
ወንድወሰን በየነ፡፡ (1989)፡፡ ‹‹የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሀድይኛ የሆነ የ 12 ኛ ክፍል
ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና የፈተና ውጤታቸው
ዝምድና፡፡››በቋንቋዎች ተቋም ለ2ኛ ድግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት፡፡አዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ (ያልታተመ) ፡፡

የለው እንዳወቅ ሙሉ፡፡ (2006) ፡፡ የምርምር መሰረታዊ መርሆዎችናአተገባበር፡፡


ባህርዳር ዩንቨርሲቲ ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡፡

ጸጋዬ አረጋይ፡፡(1996)፡፡“ ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሚኖራቸው አመለካከት


ላይ ዝምድና ያላቸው ተላውጦዎች በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መንግስታዊ
ባልሆኑ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ጥናት፡፡ አዲስ አበባ፣ በቋንቋዎች ተቋም
ለኤም.ኤ. ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት፡፡(ያልታተመ)
Brown.H.D.(2007). Principles of Lannguage Learning and Teaching.San
Francisco State of University: Pearson Longman.
Crombach,L.L. (1963). Educational Psychology.London: horcurt.Prac and Worled
Inc.

Dubin, F. and E. Olshtain.(1986).Course Design Developing Programs and


Materials for Language Learning.Cambridge.CU
Evans, K. M. (1965). Attiude and Interest in Education.London, Routeledge and
kegno paul Ltd.
Garry.R.(1970).The Neture and Conditions of Learning.3rdEd.NewJese,
prentice.Hall I
Gardner.R.C.(1985).Social psychology and Second Language Learning.The Role

22
of Attiude and Motivation.London,Edward.Amold.
----------.(2007).Motivation and Second Language Acquision.porta.Linguarum,8,9-
20.GarderR.andLambert.(1972).Attitude and Motivation Second Lnguage
Learning.Rowley,Mass:Newburg house.
Harmer,J.(1983). The practice of English Learning Teaching.New
York,longman.
Harmer,J .(1990). The practice of English Learning Teaching .New York,long
man.Group ltd.
------------.(1991). Hand Book of Language Teachers.The Practiceof
Englihs Language Teaching.(New Education).new York, Longman.
Krashen.S.(1985).TheImput Hypothesis Issues are Implication.Harlow,Consman.
Language in Ethiopia. London: Oxford University Press..
Little.Wood.W.(1981).Communicative Language Teaching.Cambridge,
Cambridge University press.
Skinner.E.C .(1985). Educational Psychology .New York, prentice Hall. Inc.
---------------.(1989).Educational Psychology. 4thed. New Delhi: Mentice, Hallofindia
privetlimited.
Smith, Alfred,N.(1971).“importance of Attitude in foregn language learning”. The
modern Language Journals Vol,55,No 2.
Stewart.W.A.(1968).National Developmen and Language Diversity.in Fresh
man.J.(ed). Reading in Sociology of Language paris:Moutons and
co.printers.(44-216)
Stern,H.N.(1983).Fundamental Concept of Languag Teaching.London,Oxford
Universitypress.Inc.
-------------.(1992).Issues and Options in Language Teaching.0xford University
press.

23
ss.
Spolsky,Bernard.(1989).Condition for Second Language Learning.Oxford.CUP.
Tsii.M.B.(2003). understanding Expertisein Teaching case Studies of ESL
Teachers.Hongkong :Cambridge Universty press.
Ur,Penny.(1996).Acourse in Language Teaching Practice and Theory.Cambridge,
Cambridge:University Press.
Walki, A. Googel (2000).contextual factors in second language Acqusition
Htt/cal,Orga.resources / digest/005 Contextual,htm/
Webb,V.and Kembo-sure.(2000).African Voices an Introducation to the Language
and Lingustics of Africa.Cape Towen:oxford University press
Southern Africa.
William.M.M.Burden.B.(1997).psychology for Language Teacher.Asocial
Constiructivist Approach. Cambridge:Oxford University press.

24
ግምታዊ የጊዜ ሰሌዳ

ተ.ቁ የክንውኑ ዓይነት የሚከናወንበት ጊዜ


1 በርዕሱ ወይም በችግሩ ዙሪያ ጥልቅ ዕውቀትን ለማግኘት የቀደምት ከመስከረም 1-30 /2015 ዓ.ም
ጥናቶችን ማንበብ
2 ለትልመ ጥናቱ ዝግጅት የሚሆኑየመረጃ ምንጭ የሆኑ መጻህፍትን ከጥቅምት 1 እስከ 30/2015 ዓ.ም
ማሰባሰብ፣ ማስታወሻ መያዝ
3 ምዕራፍ አንድን እስከ ምእራፍ ሶስት የተሰራውን ትልመ ጥናት ለአማካሪ ከህዳር 1-10/2015 ዓ.ም.
መምህሩ ማቅረብ
4 የአማካሪን አስተያየት መሰረት በማድረግ ከምዕራፍ አንድ እስከ ምእራፍ ከህዳር 15- 30 ቀን 2015 ዓ.ም.
ሶስት አስተያየት የተሰጠበትን ትልመ ጥናት አስተካክሎ እንደገና መስራት

5 መረጃውን መሰብሰብ ከታህሳስ 1- 30 ቀን 2015 ዓ.ም.እና


ጥር 1-15/2015 ዓ.ም
6 ማደራጀትና መተንተን
ጥር 15-30/2015 ዓ.ም እና የካቲት 1-
30/2015 ዓ.ም
7 ምእራፍ አራትን አዘጋጅቶ ለአማካሪ ማቅረብ፡፡ ከመጋቢት 1-30/2015 ዓ.ም

8 የምእራፍ አራትን ስራ በአማካሪ ማስገምገም እና በተሰጠ አስተያየትና ከሚያዝያ 1 እስከ 15/2015 ዓ.ም.
እርምት መሰረት ማስተካከል፡፡
9 ምእራፍ አምስትን አዘጋጅቶ ለአማካሪ ማቅረብ፡፡ ከሚያዚያ 15-30 ቀን 2015 ዓ.ም.
10 የምእራፍ አምስትን ስራ በአማካሪ ማስገምገም እና በተሰጠ አስተያየትና ከግንቦት 1-ግንቦት 15/2015 ዓ.ም
እርምት መሰረት ማስተካከል፡፡
11 አጠቃላይ የጥናቱን ምዕራፎች አቀናብሮ ለአማካሪ ማቅረብ ከግንቦት 15 እስከ 30/2015 ዓ.ም
12 መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ካሉ አስተካክሎ የመጨረሻውን ጥናት ከሰኔ 1 -20/2015 ዓ.ም
ማሳተም

ግምታዊ የወጪ ሰሌዳ

አስፈላጊ ነገሮች የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

25
ብር ሣን ብር ሣን
ብዛት
ለጽህፈት መሳሪያዎች
 ባለመስመር ወረቀት በደስጣ 2 100 00 200 00
 ልሙጥ ወረቀት በደስጣ 2 100 00 200 00
 ቢክ እስክሪብቶ 20 5 00 100 00
 እርሳስ 10 2 00 20 00
 ላፒስ 2 10 00 20 00
ለልዩ ልዩ አገልግሎት
ለትራንስፖርት 2500 00
 ፍለሽ ባለ GB8 2 300 00 600 00
 ማጻፊያ 500 5 00 2500 00
 ፎቶ ኮፒ 500 5 00 2500 00
 ማስጠረዣ 3 100 00 300 00
 ለረዳት መረጃሰብሳቢ መምህራን የአበል 3 100 00 300 00
ክፍያ ------ 3000 00
ፕሪንት ወይም ለህትመት 500 5 00 2500 00
መጠባበቂያ በጀት 2000 00
ጠቅላላ ድምር 16860 00

26
27

You might also like