You are on page 1of 13

ዲላ ዩኒቨርስቲ

የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብዕ ኮሌጅ

የአማርኛ ቋንቋ ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል

በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ


መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብ ፍተሻ

በኃይሉ ለማ
ማውጫ
ማውጫ........................................................................................................................................I

ምዕራፍ አንድ................................................................................................................................1

1. መግቢያ......................................................................................................................................1

1.1. የጥናቱ ዳራ........................................................................................................................1

1.2 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት.......................................................................................................3

1.3 የጥናቱ አላማ......................................................................................................................4

1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ.................................................................................................................4

1.5 የጥናቱ ወሰን.......................................................................................................................5

1.6 የአጠናን ዘዴ........................................................................................................................5

1.6.1 የጥናቱ ንድፍ..................................................................................................................5

1.6.2. የናሙና አመራረጥ.......................................................................................................6

1.6.3 የመረጃ ማስበሰቢያ ዘዴ.................................................................................................7

1.6.4 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ..................................................................................................8

2. የበጀት መከፋፈል እና የጊዜ መርሐግብር.......................................................................................9

2.1 የበጀት መከፋፈል.................................................................................................................9

2.2. የጊዜ መርሐግብር...............................................................................................................9

ዋቢዎች......................................................................................................................................11

I
ምዕራፍ አንድ

1. መግቢያ
1.1. የጥናቱ ዳራ
ስነ-ጽሁፍ በሰው ልጅ ታሪክ ለረጅም ዘመናት የቆየ ኪነጥበብ በመሆኑ ብዙ ሀሳቦች የተሰነዘሩበት፣ ብዙ
ክርክሮችና ምርምሮች የተደረጉበት መስክ ነው፡፡ ስለምንነቱ፣ ስለአፈጣጠር ሚስጥሩ፣ ስለሚያካትታቸው
ነገሮች፣ በሰዎች ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖና ስለሚሰጠው አገልግሎት ያልተባለ ነገር የለም፡፡ ስነ-ጽሁፍ
ከራሱ ባለሙያዎች በተጨማሪ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችና የተለያዩ ሙህራን ስለስነ ጽሁፍ ምንነት
የተለያዩ ብያኔዎች ይሰጣሉ።በዚህም የተነሳ ስነ ጽሁፍ አንድ ወጥ ብያኔ የለው።

በድሉ ዋቅጅራ (2007) ስነፅሁፍ በህይወት ዉስጥ የሚከሰቱ ስፍር ቁጥር የሌላቸዉ ድርጊቶችን እና
ሁኔታዎችን መሰረት አድርጎ የሚፃፍ የኪነጥበብ ዘርፍ ነዉ በማለት የስነፅሁፍን ምንነት ይገልፃል፡፡

ዘሪሁን (1996) ስነ ጽሁፍ የሰው ልጅ የሀሳብ መግለጫ ዘዴ ነው። ነገር ግን በሚገባ ተቀነባበሮ ቢጻፍም
በቃላት የተገለጸ ማንኛም ነገር ሁሉ ከስነ ጽሁፍ ይቆጠራል ማለት አይደለም፡፡ ዋነኛ አላማቸው ለምሳሌ
ቴክኒካዊ ፣ትምህርታዊ እና ጋዜጣዊ እውቀትን የመስጠት የሆነ ጽሁፎች በሁሉም ባይሆንም
በአብዘሀኛወቹ ሀያሲያን ከስነ ጽሁፍ ጎራ አይመደቡም። አንዳንድ የጽሁፍ መልኮች ግን በሁሉም ዘንድ ስነ
ጽሁፍ እናም ኪነጥበብ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡ ከነዚህ መካከል አንዳነዶቹ ሙከራዎች ኪነጥበባዊ ብቃት
የሚባለው ነገር ያላቸው የተዋጣላቸው ይሆናሉ፡፡ ከሌላቸው ደግሞ ውድቅ ስራዎች ይሆናሉ በማለት የስነ
ጽሁፍን ብያኔን ጠቅለል አድረጎ ገልጽዋል።

ባህርዳር ዩንቨርስቲ አማርኛ ትምህርት ክፍል (1998) ላይነስና ሌሎች (1974) ን በመጥቀስ የሰው ልጅ
ድርጊት ሌጣውን አይገለጽም፡፡ የሰዎች ድርጊት፣ ገጠመኝ፣ ባህልና ወግ ዋነኛ መከሰቻው ስነጽሁፍ ነው፡፡
ይህ ማለት ስነጽሁፍ ያለቋንቋ ምንም መከሰቻ የለውም ማለት ነው፡፡” በማለት ካብራራ በኋላ
ሲያጠቃልለው “ቋንቋና ተግባቦት ሁለት የመቆራኛ ወይም የመዛመቻ መንገዶች አሏቸው፡፡ እነሱም
ንግግርና ስነጽሁፍ ናቸው፡፡ ተመሳስሏቸውም ሁለቱም በቋንቋ ይከወናሉ፤ በቋንቋ የተነሳም ይኖራሉ፡፡
የስሜትና የሀሳብ መሸጋገሪያ ናቸው፡፡ የሁለት አካላትን (የመልዕክት አፍላቂና አቀባይ) ተሳትፎን ይሻሉ፡፡
የሰባዕዊ ፍጡራን ብቻ ፀጋ ናቸው፡፡ “ በማለት ቁርኝነታቸውን ይበልጥ ግልጽ አድርጎታል፡፡

በድሉ ዋቅጅራ (2007) ስነጽሁፍን በቋንቋ ማስተማሪያ መሳሪያነት መገልገል የተለያዩ የስነጽሁፍ ይዘቶች
ቅንጫቢዎችን በመጠቀም የቋንቋ አብይ ክሂሎችን የሰዋሰዉና የቃላት እዉቀታቸዉን እንዲያዳብሩ
ማድረግ ነዉ፡፡ ቋንቋ አራት ክሂሎች አሉት፡፡ መናገር ማዳመጥ መፃፍና ማንበብ ናቸው፡፡ የስነ ፅሁፍ በት/ት
ውስጥ መካተት ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የማንበብን፣ በመካከለኛ ደረጃ ደግሞ የማዳመጥ፣ የመናገርና፣
የመፃፍ ክሂሎችን እንዲያዳብሩ ያግዛል፡፡

በቋንቋ ማስተማሪያነት የሚውሉ ስነ-ጹሁፋዊ ስራዎች አመራረጥ ዙሪያ ብዙ ምሁራን አስተያየታቸውን


ሰጥተዋል። ከነዚህም መካከል፤ካሚላ (2009) እንደገለፀችው ለቋንቋ ማስተማሪያነት የሚያገለግሉ ስነ-

1
ጽሁፍ ስራዎችን ወደ ክፍል አምጥተን ከመተግበራችን በፊት ስነ-ጽሁፋዊ ስራው ምንምን ነገሮችን
ማሟላት እንዳለበት ተገንዝበን ከተለያዩ ጉዳዮች አንፃር መምረጥ ይኖርብናል በማለት ገልፃለች፡፡

ካሚላ (2009) በድሉ(1996፡16)ን ጠቅሳ እንደገለጸችው ተማሪዎችን የድርጊት ተሳታፊ ማድረግ


የሚቻለው በምንመርጠው ስነ-ጽሁፋዊ ስራ የተማሪዎችን ፍላጎትና የትምህርት ደረጃ እስከጠበቀ፣በክፍል
ውስጥ የሚቀርብበት መንገድ ሳቢ እስከሆነ፣ተማሪዎች በራሳቸው መንገድ እንዲያነቡና እንዲተገብሩ
እሰከተፈቀደላቸው ድረስ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የስነ-ጹሁፍ ስራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ Brumfit and carter(1986,189)ን ጠቅሳ እንደገለፀችው ስነ-ጽሁፋዊ ስራዎችን
ለቋንቋ ማስተማሪያነት ለመጠቀም ስንመርጥ እንደ መስፈርት የምንጠቀምባቸው ጉዳዮች የተማሪዎችን
ስነ-ልሳናዊ ደረጃ፣ የተማሪዎችን ባህላዊ ዳራ፣ የስነ-ጽሁፋዊ ስራው ርዝማኔ፣ የስነ-ትምህርታዊ
ጠቀሜታው መታየት እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡ ከነዚህ ሙህራን የምንረዳው ለቋንቋ ማስተማሪነት
የሚያገለግሉ ስነ-ጹሁፋዊ ስራዎችን ስንመርጥ የተማሪዎችን ዳራ፣ ደረጃ፣ ባህልና ሐይማኖት ላይ ትኩረት
በመስጠት መምረጥ እንዳለብን ያስረዳሉ፡፡ስለዚህ የስነ-ጹሁፍ ስራ አመራረጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ከሚላ (2009) Carter and long (1991) ን በመጥቀስ በስነ ጽሁፍ ቋንቋን የማስተማር ተግባር እ.ኤ.አ
በ 1970 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ልዩ ትኩረት እንዳልነበረዉና በ 1980 ዎቹ ዉስጥ ግን ሁኔታዎች እየተለወጡ
ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ መምጣቱን ታስረዳለች፡፡

በሁሉም አጥኚዎች የተደረሰበት የጥናት ውጤት የሚያመለክተው የመፅሐፍቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘት ለቋንቋ
ክሂል ማስተማሪያነት ብቃት እንደሌላቸውና የተማሪዎቹም የአንብቦ መረዳት ችሎታ አናሳ መሆኑ፤
እንዲሁም ለተዘጋጁበት የክፍል ደረጃ ምንባቦቹ የማይመጣጠኑ መሆናቸውን ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ ይህም
ጥናት ደግሞ በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት
በመፈተሽ ችግሮቹን መርምሮ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

1.2 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት


የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች የቋንቋ ክሂልን በማዳበር ረገድ መፅሐፍት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ ለመማሪያ በየክፍል
ደረጃው በሚዘጋጁት መፃሕፍት ውስጥ የተካተቱት ስነ-ጽሁፍ የቋንቋ ክሂል ዓቢይ አላማው አንብቦ
መረዳትን ማጎልበት በመሆኑ ከርዕሱ ጀምሮ ሳቢና ማራኪ ሊሆን ይገባል፡: አንብቦ የመረዳት ክሂል ሲጎለበት
ለመግባቢያነት አገልግሎት ከመዋል ባለፈ ሌሎች ትምህርቶችን ለመማር ስለሌሎች ለማወቅ የረቀቀ
አስተሳሰብን ለመስጠት ትልቁን ድርሻ የሚይዝ መሆኑን Millar (1962) ይገልፃሉ፡፡

አንብቦ መረዳት ስኬታማ ሊሆን የሚችለው በተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ ስነ-ጽሁፍ
እንደሚነበቡ ሣቢ ሆነው ሲቀርቡ ወይም ሲዘጋጁ ነው፡፡ አንድ ስነ-ጽሁፍ ተነባቢ ነው የሚባለው ተማሪዎቹ
በቀላሉ አንብበው የሚረዱት ሲሆን ነው፡፡ ይህም የሚወሰነው በአብዛኛው በአቀራረቡና በአደረጃጀቱ ነው፡፡

2
ከሚነበበው ፅሁፍ ለአብነት ያህል በስነ-ጽሁፍ ውስጥ ያለው አማካይ የዐረፍተ-ነገር ርዝመት፣ የአዳዲስ
ቃላት ቁጥርና የቋንቋው ሰዋስዋዊ አደረጃጀት መሆኑን Rechardes እና Schmilt (2002) ያስረዳሉ፡፡

በማስተማሪያ መጽሐፉ የቀረቡት የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች ችግር ሲከሰት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች
ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገብ፣ የክፍል መድገምና ከትምህርት ገበታ ማቋረጥን ያስከትላል፡፡ ይህንን ችግር
ለመከላከል በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች ሲዘጋጁ ሣቢና ማራኪ እንዲሆኑ
የክብደት ደረጃቸው ከብዙሃኑ ተማሪዎች ችሎታ ጋር የተመጣጠነ እንዲሆን Mattall (1988) እና Hedge
(1987) ይመክራሉ፡፡ ይህ እንግዲህ የሚያሳየዉ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ አጥኚዎች የደረሱበትን ፍተሻ
ውጤት የሚለያይና ግልፅነቱም አጠራጣሪና እንደሚገባ ያልተብራራ ስለሆነ አጥኚው ይህን ችግር
ለመቅረፍ በመነሳት ሙከራ ማድረጉ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከደረሱበት ጥናቶች መገንዘብ የሚቻለው በስነ-
ጽሁፍ ይዘቶች ላይ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ነዉ፤ ይህም በተለይ ለመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች የሚቀርቡ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች አንብቦ ለመረዳት የሚያዳግትና የተማሪዎቹም የማንበብ
አቅም የሚፈትሽ ይመስላል፡፡ ይህ ችግር ደግሞ የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት አዘገጃጀትና አቀራረብ ላይ
ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ አጥኚው ለዚህ ጥናት መነሻ የሆኑት ሁለት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
አንደኛው ምክንያት በ 2015 ዓ.ም በተዘጋጀውና አሁን እየተሰራበት ያለው የአማርኛ ቋንቋ የተማሪው
መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ በቀረቡት የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች ለቋንቋ ክሂል መዳበር የይዘት አቀራረቡ ላይ
የተደረጉ ጥናቶች በበቂ አለመኖሩ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት አጥኚው ለረጅም ዓመታት በሠራበትና
አሁንም በሚሠራበት በተፈሪ ኬላ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ የ 7 ኛ እና
8 ኛ ክፍል ተማሪዎች በመማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ያለውን (የተካተቱትን) የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች ተማሪዎቹ
አንብበውም ሆነ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን ሠርተው እንዲያመጡ ሲታዘዙ ተግባራቱን
አለማከናወናቸውና ለማከናወንም ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አጥኚው ማየቱ
ለጥናቱ መነሻ ሆኗል፡፡ በ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መጽሐፍ የቀረቡ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች
ለማንበብ ፍላጎታቸውን የሚያነሳሱ ወይም የማያነሳሱ ተማሪዎችን ምክንያት ብንመረምር ብናጠና
ከአሁን በፊት ቀድሞ በብዙሃን መገናኛ የቀረቡና ምንባቦቹም በውጫዊ ፈተናነት አይሠጡም የሚሉ
አስተሳሰቦች ስላሉ የማንበብ ተነሳሽነቱም ቀንሶ ይታያል፡፡ በዚህ መነሻነት በ 2015 ዓ.ም ለተዘጋጀው እና
እስከአሁን በሥራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት
የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ለታለመላቸው የክፍል ደረጃ ለቋንቋ ክሂሎች ያለውን
ተገቢነት በመመርመር (በመፈተሸ) የሚከተሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት ያደርጋል፡፡

1. የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት ስነ-ጽሁፍ የይዘት


አደረጃጀታቸው ምን ይመስላል?

2. የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች


አቀራረብ ምን ይመስላል?

3
1.3 የጥናቱ አላማ
የዚህ ጥናት ዓብይ አላማ በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች
የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና
አደረጃጀት ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው፡፡ይህን አጠቃላይ አላማ መነሻ በማድረግም ለሚከተሉት
ዝርዝር አላማዎች መልስ ለመስጠት ሞክሯል፡፡

 የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት ስነ-ጽሁፍ የይዘት


አደረጃጀታቸው ምን እንደሚመስሉ መመርመር፤

 የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የተካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች


አቀራረብ ምን እንደሚመስሉ መመርመር ናቸው፡፡

1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ


በአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍት ውስጥ ከሚቀርቡ የትምህርት ይዘቶች መካከል አንዱ የሥነ፟
ጽሁፍ ትምህርት ነው፡፡ በመሆኑም በታላሚው መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘት
አቀራረብና አደረጃጀት መገምገም የሚከተሉ ት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታመናል፡፡

 በሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት አቀራረብና አደረጃጀት ረገድ በተተኳሪው መጽሀፍ ውስጥ የታዩትን
ጠንካራና ደካማ ጎን በማሳየት ጠንካራ ጎኑ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን፣ ደካማ ጎኑ ደግሞ
የሚሻሻልበትን አቅጣጫ ለቋንቋ መማርያ መጽሀፍ አዘጋጆች ይጠቁማል፡፡

 በመማሪያ መጽሃፉ ውስጥ የቀረበውን የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት አቀራረብና አደረጃጀት በመፈተሸ
ምን አይነት ገፅታ እንዳለው በመጠቆም በመስኩ ለሚደረግ ቀጣይ ጥናት የበኩሉን አስተዋጾ
ያበረክታል፡፡

 የደረጃውን የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍ የሚያዘጋጁና የሚያሻሽሉ አካላት


በዝግጅታቸውም ሆነ በማሻሻል ሂደታቸው ሊገለገሉባቸው የሚችሉ ግብአቶችን በአቅሙ
ይጠቁማል፡፡

 የቋንቋ መምህራን ይህን ጥናት የማየት እድል ቢገጥማቸው የሚያስተምሩባቸው መፃህፍት የሥነ፟
ጽሁፍ ይዘታቸው ለመገምገም የሚያስችላቸውን መነሻ ሀሳብ ሊያገኙበት ይችላሉ፡፡

 በቀጣይ ከዚህ ርዕስ ጋር ተዛማጅ የሆነ ጥናት ማድረግ ለሚያደርጉ አካላት የመነሻ ሀሳብ
ይሰጣቸል፡፡

1.5 የጥናቱ ወሰን


በተተኳሪው መጻህፍ ውስጥ የተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች በርካታ ቢሆኑም ይህጥናት ትኩረት ያደረገው
በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ
መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ብቻ ለደረጃው
ከተዘጋጀ መርሃ ትምህርት ጋር አያይዞ የሚመለከት ነው።
4
1.6 የአጠናን ዘዴ
1.6.1 የጥናቱ ንድፍ

ይህ ጥናት በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ


ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀትን
ለመፈተሸ ገላጭ የምርምር ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ለተዘጋጀበት የክፍል ደረጃ
የቀረቡት ሥነ፟ ጽሁፎች የቋንቋ ክሂላቸውን ለማዳበር ያላቸውን ዓላማና ይዘት አጥኚው ሲያጠናው የሥነ፟
ጽሁፎቹንም የተነባቢነት ደረጃ በታየው የተለያዩ አጥኚዎች ጥናት እንዲሁም ተማሪዎቹ በሚያሳዩት
አናሳፍላጎትና ችሎታ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን ተጠቅሞ መፈተሹ ተመራጭ ሆኗል፡፡

1.6.2. የናሙና አመራረጥ


1.6.2.1 የትምህርት ቤት ናሙና አመራረጥ

ጥናቱ ለማከናወን የታቀደው በሲዳማ ክልል በአለታ ጩኮ ዞን በኦቲልቾ ወረዳ በሚገኘው በተፈሪ ኬላ
አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነዉ፡፡ ትምህርት ቤቱም የተመረጠው በአመቺ የናሙና
አወሳሰድ (Convenience Sampling) ስልት ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊ ስልትን የተከተለ በመሆኑ
የትኛውም ትምህርት ቤት ቢመረጥ መስራት ይቻላል፡፡ ሆኖም ለአጥኚዋ የስራ አካባቢ ቅርብ ቢሆን
ጥናቱን በቅርበት ለመከታተል፣ በጥናቱ የሚሳተፉ መምህራንንና ተማሪዎችን መረጃ የመስጠት ትብብር
ለማግኘት የተፈሪ ኬላ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥናቱ እንዲካሄድበት
ተመርጧል፡፡

1.6.2.2. የክፍል ደረጃ ናሙና አመራረጥ

ለጥናቱ የተመረጠው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ነው፡፡ ይህም የተመረጠበት
ምክንያት አጥኚው በተፈሪ ኬላ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል
የአማርኛ ቋንቋ መምህር በመሆን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉና አሁንም በማገልገል ላይ ያሉ ሲሆን
በመማር ማስተማሩ ሂደት ተማሪዎቹ በመማሪያ መጽሐፉ ተገልጋይ እንደመሆናቸው የቋንቋ ክሂላቸውን
ከማሳደግ አንጻር ሲማሩ የሚያሳዩትን ስህተቶች በመመልከትና በመመርመር ችግሩን ፈትሾ የመፍትሔ
ሀሳብ የሚሆን ጥቁምታ ለማድረግ በተጨማሪም ተማሪዎቹ በቀጣይ የ 8 ተኛ ክፍል ክልላዊ ማጠቃልያ
ፈተና የሚወስዱና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያቸው ስለሆነ የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል
የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ተመራጭ ሆኗል፡፡

በአመቺ ናሙና በተመረጠው በሲዳማ ክልል በአለታ ጩኮ ዞን በሚገኘው በተፈሪ ኬላ አንደኛና መለስተኛ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 2015 ዓ.ም ወሰነ ትምህርት በመማር ላይ ከነበሩት አራት የ 7 ኛ እና የ 8 ኛ
ክፍል (ሀ፤ ለ ፤ ሐ እና መ) የመማሪያ ክፍሎች መካከል በቀላል እጣ የናሙና አመራረጥ ዘዴ (Simple
Random Sampling) በመጠቀም ‹‹ለ›› ክፍል ተመርጧል።

5
1.6.2.3. የመምህራን የናሙና አመራረጥ

በአማርኛ ትምህርት ክፍል ከሰለጠኑ መምህራን መካከል የወሳኝ ናሙና አካል የሆነዉን አላማ ተኮር
የናሙና መረጣ ዘዴን በመጠቀም 4 የአማርኛ መምህራንን መርጫለሁ፡፡ ይህን ዘዴ በመጠቀም አራቱን
መምህራን የመረጥነዉ እነሱ የ 6 ኛ ክፍል መምህራን ስለሆኑ ነዉ፡፡

1.6.2.4. የተማሪዎች የናሙና አመራረጥ

በተመረጠዉ ክፍል ዉስጥ በ 7 ኛ እና 8 ኛ ‹‹ለ›› ክፍል 64 ሴትና 81 ወንድ በድምሩ 132 ተማሪዎች ሲገኙ
ከነዚህ ዉስጥም በእጣ ናሙና ስልት ክፍ 8 ሴትና 6 ወንድ በድምሩ 14 ተማሪዎችን ለዚህ ጥናት
ተመርጣዋል፡፡

1.6.3 የመረጃ ማስበሰቢያ ዘዴ


ይህን ጥናት ከግብ ለማድረስ ተለያ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች ጥቅም ላይ ዉለዋል፡፡ ከነዚህም ዋነኞቹ
ምልከታ መጠይቅ እና ቃለ መጠይቅ ናቸዉ፡፡

1.6.3.1. ምልከታ

በዚህ ጥናት ምልከታ ተገቢና ዋነኛ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳርያ ሆኖ አገልግሉዋል፡፡ ይህ ምልከታ
በተጠኚነት በተመረጡ የ 7 ኛ እና 8 ኛ ‹‹ለ›› ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህር በሚያስተምርበት ጊዜ
ተካሂዱዋል፡፡

1.6.3.2. የፅሁፍ መጠይቅ

ይህ መረጃ በስብሰቢያ ስልት መሰብሰቢያ ስልት ከእያንዳንዱ የጥናት ተሳታፈ ዝርዝር መረጃዎችን
ለማግኘት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በዚህ ጥናትም የ 7 ኛ እና 8 ኛ ‹‹ለ›› ክፍል የቋንቋ ክህሎት በሥነ፟ ጽሁፍ
ይዘቶች ላይ ያተከረ ዝግ ጥያቄዎችን የያዘ መጠይቆች እንዲቀርቡ ይደርጋል። አነዚህ የፅሁፍ መጠያቆችም
ከክፍሉ ለተመረጡ ተበትነዉ ከተማሉ በኃላ መጠያቁን እንደመልስ የወሰዳል ፡፡

1.6.3.3 ሰነድ ፍተሻ

ይህ ጥናት በሲዳማ ክልል በ 2015 ዓ.ም. ስራ ላይ በዋለው የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ


ቋንቋ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የተካተቱ የሥነ፟ ጽሁፍ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀትን
ላይ ያተኩራል፡፡ የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አጠቃላይ ዓላማዎች የተማሪዎቹን
የማዳመጥ፣የመናገር፣ የማንበብና የመጻፍ ክሂሎች ማዳበር፣ የስነ-ፅሑፍና የስነ-ልሳን ዕውቀቶቻቸውን
ማጎልበት ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብአቶች (ሥነ ፅሑፎች) በመጽሐፉ ውስጥ
እንዳሉ ቢታወቅም የነዚህን ስነ-ፅሑፎች የተነባቢነት ደረጃ መመርመር ደግሞ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ለዚህም
ሲባል የ 7 ኛ እና 8 ኛ ክፍል ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ አብይ የመረጃ ምንጭ በመሆን አገልግሏል፡፡
በመማሪያ መፅሐፉ ውስጥ በአጠቃላይ ያሉ ስነ-ፅሑፎች የተካተቱ ሲሆን ስነ-ፅሑፎቹ የተለያዩ ይዘቶችና

6
ጭብጦችን ለማስተላለፍ በልብወለድ፣ በኢልብወለድ፣ በግጥም በተውኔት ወዘተ….መልክ የቀረቡ ናቸው፡፡
በይዘት ረገድም ስለቋንቋ ፅንሰ-ሀሳባዊ ዕውቀት፣ ስለቅርሶች ምንነትና አጠባበቅ፣ ስለወግ ምንነት፣
ስለልብወለድ አላባውያን፣ ስለቋንቋ ለዛ ማስገኛ ስልቶች፣ ስለግጥም፣ ስለአርበኝነትና ተጋድሎ፣
ስለትውፊት፣ ስኬታማ እንዴት መሆን እንደሚቻልና ስለኪነ-ጥበብ ዕውቀት ይሠፍራል፡፡

1.6.4 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ


በተመረጡ የመረጃ መሰብሰቢያ መሰርያዎች የተገኘ-ትን ፤ጥናቱ የሚሆን መረጃ ምልከታ እና በጽሑፍ
መጠይቅ በመከፋፈል መረጃዎችን በአይነትና በመጠን የመተንተኛ ዘዴዎችን ተከናዉኗል፡፡ የተመረጡ
መረጃዎችን በመጠን በማደራጀት በቁጥር መግለጫዎች እንዲሁም በሠንጠርዥ በታሊ ሥራ መረጃዎችን
በማደራጀት ከተጫማሪ የትንተኛ ማዉሪያ መረጃዎች ጋር ለአየነትም ተደራጅቶ ቀርቡዋል፡፡

7
2. የበጀት መከፋፈል እና የጊዜ መርሐግብር
2.1 የበጀት መከፋፈል
S.N ንጥል ብዛት ክፍል አይነት ንጥል አመታዊ አስተያየት
ዋጋ(ብር) ዋጋ(ብር)

1 ወረቀት 500 pages - 150 150

2 ፍላሽ (8 ጂቢ) 1 ጂቢ 250 250

3 ብዕር 5 BIC 6 30

4 እርማት ፈሳሽ 1 - 25 25

5 ገዥ 1 - 7 7

6 ኮምፒውተር ይፃፉ Per page ኤ4 5 1000


እና ያትሙ

7 መጓጓዣ - - - 2000

ጠቅላላ 3462 ብር
ዋጋ

2.2. የጊዜ መርሐግብር


S. Activity Time Schedule
N

ነሃ መ ጥ ህዳ ታ ጥር የ መጋ ሚ ግ ሰኔ ሃም Remark
ስ ቅ ህ ካ ያ ን

1 የርዕስ ምርጫ x x
x

2 የመጀመሪያውን  x
ረቂቅ ሀሳብ መጻፍ xx

3 ሁለተኛውን ረቂቅ  x

8
መጻፍ

የመጨረሻውን  x
ረቂቅ ረቂቅ መጻፍ
4

የውሂብ ስብስብ  x

የመጀመሪያውን  x
የሪፖርት ረቂቅ
6
መጻፍ

7 ሁለተኛ የሪፖርት  x
ረቂቅ መጻፍ

የመጨረሻውን  x x
የሪፖርት ረቂቅ
8
መጻፍ

9 ከአማካሪ ጋር x x x x x x x x x x x x
ይገናኙ

9
ዋቢዎች
በድሉ ዋቅጅራ፡፡(2007)፡፡ በስነጽሁፍ ቋንቋን ማስተማር፡፡ አዲስ አበባ፣ ፋር ኢስት ኃላ/የተ/የግል ማህበር፡፡

ዘሪሁን አስፋው፡፡ (1996) ፡፡ የስነ ጽሁፍ መሰረታዊያን ፡፡ አድስ አብባ፣ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡፡

Lazar, G. (1993). Literature and Language Teaching. Cambridge: Cambridge University


Press.

Non fiction.https://en.wikipedia.org/wiki/Non-fiction

The features of non-literary translated language: a pilot study


http://www.lancaster.ac.uk/fass/projects/corpus/UCCTS2010Proceedings/papers

Simon Eliot and W.R.Owens . (1998 ) . A Handbook


toLiteraryResearchttps://books.google.com/books/about/A_Handbook_to_Literary_Researc
h.html

What are English Literary


Studies?http://www2.anglistik.uni-freiburg.de/intranet/englishbasics/Basic01.htm#Whatislit.

10
1

You might also like