You are on page 1of 12

በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር

የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል

በኃይሉ አማረ ID. PGW/17254/12

ለ ተሾመ (ዶ/ር)

2013 ዓ.ም
ማውጫ

ይዘት ገጽ

መግቢያ …………………………………………………….1

ዳራ …………………………………………………………1

የጥናቱ አላማ………………………………………………..3

ዘዴዎች ………………………………………………… ..3

ነባር ሥራ. ………………………………………………….4

ቃለመጠይቅ. ………………………………………………..5

ሥነ-ፅሁፍን የማንበብ ሰባት አፈታሪካዊ ትንተናዎች ………7

ማጠቃለያ……………………… ……………………………13

ስነ-ፅሁፍ በውጭ ቋንቋ ትምህርት ላይ ያለው ሚና


መግቢያ፡- ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው የስነ-ፅፍ ሚና በውጭ ቋንቋ መማር ትምህርት ሲሆን ይኸውም የስኬታማ
የውጭ ቋንቋ ተማሪዎችን በአፈታሪክ ብቃታዊ ምዘና በመጠቀም ነው፡፡

1 ኛ. በቋንቋው ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች በቅርብ ጊዜ የተደረገ ጥናትን በመመርመር ማሳኮናሱ፡ - ለመገምገም
የሞከረው የቀድሞ የጃፓን ባለሙያዎች እንዴት የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዳዳበሩ ለመገምም ሙከራ አድርጓል፡፡
ይኸውም የተወሰኑ በቋንቋው ብቃት ያላቸው ጃፓናውያኖች ተሞክሮ በመመርመር ሲሆን ለምሳሌ እንደ
ኢናዞኒቶች (1862-1933) ቴንሽን አካደራ (1862-1913) እና ሔዴሳብደ ሳይቶ (1866-1929) በዚህም ውስጥ
የእነዚህን ልሂቃን የሥነ-ፅሁፍ ንባብ ለእነሱ ስኬታማነት ያበረከተውን ውጣዊና ውጫዊ አስተዋፅዖ ለመመርመር
ይሞክራል፡፡

2 ኛ. በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ሥኬታማ ከሆኑ ተማሪዎች ጋር የተደረገውን መጠይቅ እየተነተነ የውጪ ቋንቋን
የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ስነ-ፅሁፍ ያለው ሚና ለመለየት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሱ የውጭ ቋንቋ ተማሪዎች
በተገኘ አፈታሪክ መረጃ ስነ-ፅሁፍ ለቋንቋ ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅዖና አበርክቶ እንዳለው ይናገራል፡፡ ነገር ግን አፈታሪካዊ
መረጃ ግን እንደ ዋና ማስረጃ ሆኖ አያገለግልም፡፡

ዳራ
በታካሺ በምዕራፍ 2 ላይ የተገለጸውና የተብራራው ሌላው በተጨማሪም በዚህ መጽሐፍ የቋንቋን ክህሎት በተፈጥሮ
ተግባራዊ ልምምድ የሚያደርጉበትን ታሳቢ ለማድረግ ቋንቋን እንደ ሁለተኛው ቋንቋ በተለይ እንግሊዝኛን እንደ
ሁለተኛ ቋንቋቸው የሚማሩትንና በተለያየ ሥራ ላይ በተጨማሪም ጥቂት የቋንቋ መምህራን፤ ተመራማሪዎችና
የትምህርት ባለሙያዎችን የተመለከተ ነው፡፡ ሥርዓተ ትምህርቱ የማስተማር ዘዴውና የመማሪያ መሣሪያዎችን ሁሉ
ወቅቱ በሚፈልገው መንገድ መቃኘት እንዳለበት ይገልፃል፡፡ የዚህን ዓለምአቀፋዊና ከብሔራዊ ልምድ ሺፉሚ ሳቶ
(2000 – 2003) የሚስማማበት ወይም ሚያነሳው የመከራከሪያ ነጥብ በጃፓን የሚሰጠው ተጨማሪ የእንግሊዝኛ
ትምህርት አጥጋቢ አይደለም፤ ለምሣሌነት የዘረዘራቸውና ያስቀመጣቸውን ነጥቦች እንመልከት፡-

በራሱ መሥፈርትና ካላቸው መረጃ በመነሳት 10 ጃፓን ዜጎችን (ጃፓናውያንን) በዓለም አቀፋዊ ድርጅት ውስጥ
የሚሠሩትን በሜጂ ኤራ (1868-1912) ፤ ቲሾ ኤራ (1912-1926)፤ እና ቅድመ ሸዋ ኤራ (1926-1989) እንደገና
በተናጥል በልዩነት የተቀመጠውን ኢዶ ኤራ (1603-1868) የሚያሳዩት በተለይ የእንግሊዝኛ ችሎታ ብቃት ቢያንስ ብዙ
ጃፓናውያንን ለማወዳደር EFL እንግሊዝኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ሚማሩትን የትምህርት ሂደታቸው ሲታይ እንኳን
በስፋት ለመጠቀም ይቅርና ለማስተማርም በቂ አይደለም፡፡

የሳቶ ጥናት ስኬት/ግኝት/ ብዙ ጃፓናውን ተማሪዎችንና መምህራንን ያስደነገጠ፤ የጃፓን ዜግነት ያላቸው (ጃፓናውያን)
እንግሊዝኛ ቋንቋ ላይ ደካማ እንደሆኑ አምኗል፡፡ እስቲ የሚከተለውን ምሣሌ እንመልከት ሦስት በእንግሊዝኛ የጠነከሩ
(እንግሊዝኛን) ያጠኑትን እንመልከት ሥማቸውም ኢናዞ፤አቶቢ፤ ቴንሽን አካይኩራና ሂድሳ ቡሮ፡፡

የሳቶ ስኬት/ግኝት/ ኢናዞኒቶቢ በተለያዩ ሃገራት እየተንቀሳቀሰ የእንግሊዝኛ ትምህርት ሥልጠና ይሰጣል፤ እንዲሁም
በተለያየ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሰዎች እንደ ሳቶ (2000 - 2003) ግኝት አገላለፅ በልምድ በጥሩ ሁኔታ መግባባት
እንደሚችል እና ኒቶቢ ንባቡንም ጥሩ እንደሚያነብ ገልጿል፡፡ በቶኪዮ የእንግሊዝኛ ትምህርት መማሪያ ትምህርት ቤት
የገባው በ 11 ዓመቱ እና የእንግሊዝኛ መፅሐፉን በአጭር ጊዜ ውስጥ ፅፎታል፡፡ በሳፓሮ የእንግሊዝኛ ኮሌጅ በ 15 ዓመቱና
በተከታታይ በቤተ መፅሐፍት ውስጥ የተለያዩ መፃሕፍትን ያነብ ነበር፡፡ በ 18 ዓመቱ ናቲብ ማንበብ እንደገና በቶማስ
ካርሌል ጀመረ፤ እሱም ለጃፓናውን ከበድ የሚል ፅሁፍና የእንግሊዝኛ ትምህርት ነው፡፡ ከዚያም በ 21 ዓመቱ በቲኪዮ
ዩኒቨርሲቴ ገባ፤ ከ 2 ዓመታት በኋላ ቡሽዶ የተሰኘ ጃፓን መንፈስ 1900 ቲንሽ አካኮሉ የቲ መጽሐፍ ፀሐፊ ነው፤ በፅሁፉ
በጥልቀት የጃፓንን የኪነ ጥበብ ታሪክና ጃፓንን ጨምሮ ሌሎች ምሥራቅ ባህልና አስተሳሰብ እንዲሁም የአሜሪካንን
ሥነ ጥበብ ዳስሷል፡፡
አካኮ በ 19 ዓመቱ የመጀመሪያ ልጁ ተወለደ፤ አካኮ የሚያጠቃልለው በእንግሊዝኛ የረጅም ልብ ወለድ ጽሑፉ
የጃፓኖችን የተለየ ንባብ እና እያንዳንዱ ለልጆቹ በእያንዳንዷ ሌሊት በመኝታ ሰዓት የሚናገሩትን ሙከራና ምሥክርነት
በፀሐፊው (በደራሲው) የተዳሰሰው እንግሊዝኛን ለማስተማር ምቹ እንደሆነ ነው፡፡

ሂድሳ ቡሮ ሳቶ ብዙ የእንግሊዝኛ መጽሐፍትን ያደተ ነው፤ ከእነዚህም የጃፓን መዝገበ ቃላት ይገኙበታል፡፡ ሂድሳቡሮ በ 8
ዓመቱ ማያጅ ባኮኮ የተባለ የእንግሊዝኛ ትምህርት ቤት ገባ፤ በትምህርት ቤቱ ውስጥ እንግሊዝኛን ለ 5 ሰዓታት ያህል
ያዳምጥ ነበር፡፡ በ 14 ዓመቱ በኢንጅነሪንግ ትምህርት ቤት ገባ፤ ጥሩ የሆኑ መፅሐፍትን ከቤተ መጽሐፍ እየወሰደ ለ 3
ዓመታት ያህል ያነብ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ሳቶ (2003) ያስረገጠው እንገሊዝኛን በደንብ ለማወቅ ወሣኝ መሆኑን ነው፡፡

እነዚህ ጃፓናውያን እንግሊዝኛውን ባልተጠበቀ መልኩ የብዙ ዘመናት የንባብ ውጤት እና ልምድ እንግሊዝኛን አንዳንዴና
የተወሰነ ቦታ ላይ በመማር ወይም ጊዜ በመውሰድ ወይም በሌላ መንገድ የንባብ ልምድ የእንግሊዝኛን ቋንቋ ካለበት
ደረጃ ያሳድጋል ብለዋል፡፡ (Saito; 2003; 88; translated from Japanese into English by Sato himself) እሱ
በተለይ ትኩረት የሚሰጠው ጃፓናውያንን እንደዚህ እንግሊዝኛውን የበለጠ የቻሉት ባለማቋረጥ ልብወለድ ፅሁፎችን
በማንበብ ነው፡፡ ከአፈ- ፈቶች አንጻር ሲታይ ተመራጭ እና ጥሩ አያያዝ ይመስላል፤ ይህም እሳቤ በአርካዌስ (2012)
ምርምር በፍተሻው 59 በእንግሊዝኛ የበቁ በሜጂና በቲሾ ኤራ መረጃ መሠረት ተከታታይነት ያለው ንባብ መለማመድ
ለመማር እጅግ ወሣኝ ነገር ነው፡፡

በተሰጠን ሁለት ትልልቅ ልዩነቶች ጃፓናውያን በማንበብ የሁለት ቋንቋ መግባቢያ ክህሎቶቻቸውን አሳድገዋል ይህ
የሚያመለክተን እውነታ እንግሊዝኛን ለማወቅ የግድ አፈ - ፈት መሆን አይጠበቅብንም ጃፓናውያን በመማር አውቀ
ውታል ብቁ ሆነዋል፡፡ ለማወቅ ለመረዳትና ብቁ ለመሆን የምንማርበትና የምንውልበት አካባቢ ይወስነዋል፡፡

1. The aim of the study (የጥናቱ ዓላማ)


የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የሳይቶን (2000, 2003) የቋንቋ ጥናት አተገባበር እንዴት እንደሚተገበር መመርመር ሲሆን
ትኩረቱም በቀድሞ የጃፓን የእንግሊዘኛ ልሂቃን (ቋንቋውን መሰረት አድርገው የተፃፉ ፅሁፎችን በጥልቀት በማንበብ
ቋንቋውን ለመማር እንደ አንድ ውጤታማ እንዳደረጋቸው ) ቋንቋውን እየተማሩ ላሉ ተማሪዎች ያለውን አስተዋፅኦ
መፈተሸ፡፡ ይኸውም ስኬታማ የውጪ ቋንቋ ተማሪዎችጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅን በመመርመር ሊውቋቸው
የፈለጉትን ቋንቋዎች ማለትም እንግሊዝኛ፣ ጃፓንኛ እና ቻይንኛ ስነ-ፅሁፍ የውጪ ቋንቋ ለቋንቋ ዕውቀታቸው መዳር
ያለውን አስተዋጽዖ ለማብራራት ሞክሯል፡፡

በተጨማሪም በቀድሞና በአሁኑ ያሉትን የመማር ስልቶችና ግብአቶች ማለትም እንግሊዝኛ ትምህርት ለማስፋፋት
በአኗኗር ዘዴ መለወጥ፣ በቴክኖሎጂ ዕድገት፣ በተማሪዎች አጠናን፣ ትምህርት አቀባበልና የስራ ተነሳሽነት ላይ ለውጥ
ያመጣል፡፡

የአንዳንድ ስኬታማ ተማሪዎችን የቋንቋ የመማር ሂደትን በጥንቃቄ መመርመር ለተማሪዎችና ለ ESL/ERL መምህራን
(አስተማሪዎች) እደግብአት ይሆናል ተብሎ ይታመናል፡፡

2. Methodology (ዘዴዎቹ)
የአፈታሪክ ማብራሪያ እና ለውጭ ቋንቋ ጥናትና ምርምር ያለው ጠቀሜታ (ፋይዳ)

በዚህ ጥናት በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ስኬታማ የሆኑ የውጪ ቋንቋ ተማሪዎች ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅን
በመመርመር ነው፡፡
ይህ ዓይነት የአጠናን ዘዴ አፈ-ታሪክ ሲባል ማለትም በማድመጥና በመጠየቅ (በቃለ ምልልስ) የሚከናወን ነው፡፡ ይህ
ብዙውን ጊዜ በታሪክ ትምህርት ላይ ይጠቀሙበታል፡፡ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ጥልቅና ውስብስብ መረጃዎችን
ለማግኘት ይጠቅማል፡፡ ከተግዳሮቱ ባሻገር ማለትም ከጥቂት ቁጥር ተሳታፊነትና የሰዎች መረጃዎች
በግልጽልማስታወስና የመረዳት ብቃት አፈታሪክ ዘዴ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡

ለምሳሌ፡- አጥኚዎች በሰነድ ደረጃ ያልተሰነዱ መረጃዎችን እንዲገነዘቡ ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ጠቃሚ ታሪካዊ
ኩነቶችን፣ ውሳኔዎችን አውዳዊ ለማድረግ ይረዳል፡፡

ታላላቅ ኩነቶች ስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የተራው ህዝብ አመለካከት ይዋጣል፡፡ የአፈ -ታሪክ
አስተዋጽዖ ከታሪክ ትምህርት ባለፈ ይህን ,አጠናን ዘዴ በቅርቡ በሌሎች የትምህርት መስኮች ማለትም በፖለቲካ፣
በህክምና ነርሲንግ፣ በትምህርት እየተተገበረ ይገኛል፡፡

አፈ - ታሪክን ለእንግሊዝኛ ትምህርት መተግበር ተማሪዎች የቋንቋ ዕውቀት ግባቸውን ለማሳካት ይረዳቸዋል፡፡ የፅሁፍ
መጠይቆችና እስታቲካዊ ትንተናዎች፣ የብዙ መረጃ ሰጭዎችን አጠቃላይ ስለቋንቋ ያላቸውን ግንዛቤ ለማግኘት
ይጠቅማሉ፡፡ ነገር ግን አፈ-ታሪክ አጥኝዎችን በተወሰነ ርዕስ ላይ በጥልቀት እንዲመረም ይረዳቸዋል፡፡

በተግባር ሲታይ ቋንቋውን በመማር ያገኙና፣ በቋንቋው አፋቸውን የፈቱ ሲነፃፀሩ ቁጥራቸው ቋንቋን በመማር ያገኙ
አናሳ ነው፡፡

3. የኋላ (ነባር) ሥራ /Seminal Works/


በአፈ ታሪክ በብዛት እንደሚባለው ዘዴ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጥናት በጃፓን ተማሪዎች የተሠሩ ብጥቅጣቂዎች ናቸው፡፡
እንደ ቃለ መጠይቅ በአምስት ጥቃቅን ከሥራ ልምድ ጋር በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለው የሕይወት ታሪክ በራሳቸው ብቃት
እንግሊዝኛውን አውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ብዙ ቁጥር ያላቸው ተሣታፊዎች ብቃታቸው ውስን በመሆኑ እና
የልምምዱም ወቅት በቂ ስላይደለ የመማር ማስተማሩም ትግበራ እንዲሁ በቂ ስለማይሆን ተማሪው የራሱን ጥረት
ካላከለበት ወደ ሚፈለገው ደረጃ መድረስ ይቸገራል፡፡ በአጠቃላይ በተሰበሰው መረጃ መሠረት ተርጉሞ መረዳት ወሳኝ
እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡

ታኪቱ (2007፤ 2010) 18 የእንግሊዝኛ ብቁ ተማሪዎችን ጠይቋል በዚህ መሠረት ለማመዛዘን የሁለቱን ውጤት
/ሥሌት/ በተጠየቁት ብዙ ቁጥር ባላቸው በተመዘገቡበት እንዲሁም መረጃ በሰጡት 18 ተጠኚዎች ዘዴው ብቁ ሊሆን
ይችላል ግን መረጃ ጊዜያዊ ነው፡፡በዋናነት የሥነ - ፅሑፍ ሚና በቋንቋ ትምህርት ውስጥ ይህ ነው ተብሎ የሚወሰን
የሚገለፅ ሳይሆን እጅግ በጣም ሰፊ እንደሆነ እናያለን፡፡

ከአጠቃላይ ምልከታ ደግሞ ስናይ ቤንሰንና ኑናንስ (2005) ዘጠኝ መነሻ ጥናቶች /ነባር ሥራዎችን/ በዚህ መነሻ ፈትሾ
ታሪኩን አስቀምጧል የእያንዳንዱን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ዘርዝሯል፡፡ በአጥኚው የተገለፀው ቋንቋን ለማጥናት
ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ነው፡፡ ይኸውም የተነሳሽነት ስሜትና ዕድሜ፤ የመማር ማስተማሩ ሂደት እና
እምነት እና ጥናት እንዲሁም የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ሁኔታ የተለያዩ የመማር ማስተማር ሂደትን ማየት እንችላለን
ከእነዚህም እያንዳንዱን እየመረጥን ከተለያዩ ሃገራት ደግሞ ተሞክሮዋቸውን በመውሰድ በደንብ በየምዕራፉ በማደራጀ፤
ውጤታማ የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም ጥሩ በሆነ መንገድ ተማሪዎቻችንን መሥመር ማስያዝ እንችላለን፡፡

4
4. ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠየቅ ጥሩ ውጤታማ የሆነ የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ ነው፡፡

4.1. የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ምንድን ነው?

ታካቺ (2007) በደረጃ ያስቀመጠው ጃፓናውያን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የተማሩበት ብቃት እሳቤ፡-

1. የትውልድ ቦታቸው እንግሊዝኛውን በየዕለቱ የሚጠቀሙበት መሠረታዊ ቦታ አለመሆኑ፡፡


2. መግባባትና መነጋገር የሚጀምሩት በ 12 ዓመት ዕድሜያቸው በመሆኑ፡፡
3. የመጀመሪ ትምህርታቸውን እና አካባቢያቸውን በጃፓንኛ ይማሩ እና በቀጣዩ የታለመውን ቋንቋ ይማራሉ፡፡
4. በየዕለቱ በልማድ እንግሊዝኛውን አይማሩትም፡፡
5. በአሁኑ ሰዓት ሠራተኞች ከቀጣሪዎቻቸው ፍላጎት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ይለምዳሉ፡፡
6. በታላሚው ቋንቋ ተወዳዳሪ ለመሆን፡፡

የታኩቺ ትኩረት የጃፓናውያን የቋንቋ የማወቅ ሂደት ስድስቱን ቅድመ ሁኔታ ይነካል በመሆኑም የዛሬ የእንግሊዝኛ ቋንቋ
ትምህርት ሁኔታም የወጣ ብቃት የለውም እንደ ሁኔታው ተለዋዋጭ ነው፤ ምክንያቱም የጃፓናውያን ቁጥር መብዛት
ልምድ አንድ ቦታ አይቆምም ወጣቶቹ ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው አፈ -ፈት የሆኑ የቋንቋው ተናጋሪዎችን ስለሚያገኙ
የተሳለ ብቃት ይኖራቸዋል፡፡

በታኩቺስ ምክንያት ደግሞ የሚለው ትኩረትን ሰብሳቢ ካደረጉ እንግሊዝኛ ሊለመድ የሚችል የመጀመሪያ ታላሚ ቋንቋ
ነው፤ስለዚህ እያንዳንዱ ጃፓናውያን ታሳቢ ማድረግ ያለበት ታላሚውን ቋንቋ ነው፡፡

ማንኛውም አጥኚ በቃለ መጠይቅ ቢመርጥና በእሱ በኩል ቢያጠና ሁለት ሊመሩት የሚችሉ መመሪያዎች አሉ፡፡

1. ጃፓንኛ አፈ ፈቶችን
2. ታላሚውን ቋንቋ በመማር ልምድ ብቁ ማድረጉን

በዚህ መመሪያ መሠረት ተቀጣሪው እንግሊዝኛውን ማወቅ እንዳለበት በደንብ ይረዳል፡፡

ልጆች(ወጣቶች) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ደረጃ በሚያድጉበት ጊዜ እንደ ዩኒቨርሲቲ ባሉት ተቋማት ውስጥ በሚገቡበት
ጊዜ ውጤታቸው በ TOEIC (1990) ወይም ወደ አንደኛ ክፍል በሚደርሱበት ጊዜ EIKEN TEST IN
PRACTICAL ENGLISH ተግባራዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሙከራ ይሰጣቸዋል፡፡ የበቃው በሌላ መንገድ የቅኝቱን
ልምድ ያስተካክላል ፡፡

በተመሳሳይ የዕድሜ ክልልና ፆታ እንዲሁም የዕድገት ደረጃ ላይ ያሉት ለአሁን ይጠቅማል፤ ምክንያቱም እንደነዚህ ያሉ
ተማሪዎች ከጎልማሶች ይልቅ አእምሮአቸውና የማስታወስ ብቃታቸው ከፍ ያለ ስለሆነ ወደፊት በደንብ ለመግፋትና
ለመረዳት ምቹ ናቸው፡፡ በስፋት የጃፓን ተማሪዎችንና በከፍተኛ ደረጃ ላያ ያሉ የቋንቋ ምሁሮች ጃፓንን ከቀረው ዓለም
ጋር ያገናኟታል ግን ሁሉም ቋንቋ ያጠና ውጤታማና ስኬታማ ነው ማለት ሳይሆን በጥቂት መማር ማስተማር የሚታይ
ነገር አለ፡፡

ይህ ጥናት የሚያጠቃልለው ማጠቃለያ የሚሰጠው ጃፓናውያን ባልሆኑ ተማሪዎች ጃፓንኛን የሚማሩት በእነሱ
መሠረትነት ከንድፈ ሃሳብ እኩል እንግሊዝኛውን እንደ ውጪ ቋንቋ ይማሩታል፡፡ በሌላ አገላለጽ ይህ ውጤት አፈ ፈት
ጃፓናውያንና አፈ-ፈት ያልሆኑ ወይም አፋቸውን በጃፓንኛ ቋንቋ የፈቱ አና አፋቸውን በጃፓንኛ ቋንቋ ያልፈቱ ሲማሩ
የመማር ማስተማር ሂደቱ ጠንከር ያለ እይታ ይፈልጋል፡፡
5.የትምህርቱ ዓነትና የቃለ መጠይቁ ዓይነት
በ መቢጋት 2011 እና ሚያዚያ – 2014 ዓመታት ውስጥ ጠንካራ የሆነ ቃለ መጠይቅ ተደርጎ ነበር በአጠቃላይ 35
ተማሪዎች ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሲሆን 31 ጃፓን የእንግሊዝኛን ቋንቋ አንዱ ግን ቻይንኛን የሚማር አንዱ
በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ የሚማር አንዱ አሜሪካዊና አንዱ ቻይንኛን የሚማር ጃፓናዊ ሁሉም
በጃፓን ለረጅም ዓመታት የኖሩ ሲሆን አንዱ ኮሪያዊ ደግሞ ጃፓንኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይማራል፡፡

31 ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ስምንቱ ወንዶችና ሴቶች 18 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አምስቱ የድህረ ምረቃ
ተማሪዎች፤ የከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ ዝቅተኛ ደረጃ ተማሪዎች ናቸው፡፡ 18 ከሃገራቸው ይልቅ እዚህ ብዙ የሰነበቱ
ናቸው፡፡

በአማካኝ ቃለ መጠይቁ የወሰደው ጊዜ ሁለት ሰዓት ነው፡፡ ቃለ መጠይቁ ያጠነጠነው በመነሻው በጃፓን ቃለ መጠይቅ
አፈ-ፈቶችን ነው፡፡ ሁሉም የተሳተፉት ሁለት ቋንቋ ተናጋሪዎች ወይም ሦስት እና ከዚያ በላይ ተናጋሪዎች ላይ ታላሚን
ቋንቋ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ቃለ መጠይቁ የተደረገው ከልጅነት እስከ ዕውቀት ባለው ልምድ ሂደት እንዲሁም ተዋረድ
ነው እነሱም ታላሚ ቋንቋውን ወይም የውጪ ቋንቋን ለረጅም ጊዜ የሚማሩትን ነው፡፡

ከዚህ በኋላ ተሳታፊዎች በሰጡት መረጃ መሠረት ዕውቀታቸውን ወይም ክሂሎቻቸውን አዳብረዋል፡፡ በጥያቄ እና
መልስ በማነቃቃት ታላሚውን የውጪ ቋንቋ በውድቀት ውስጥ ስኬትን ተምረዋል፡፡ እያንዳንዱ ተጠያቂ መቅረፀ ድምጽ
እና ተርጓሚ በፀሐፊው ተዘጋጅቶ ነበር፡፡

6 ሥነ - ፅሑፍን ማንበብ ሰባት አፈ -ታሪካዊ ትንተናዎች አሉ


በጣም ብዙ ተሳታፊዎች በቃለ መጠይቅ ከመሳተፍ ጥቂት ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ማሣተፍ ጥሩና ጠቃሚ ነው፡፡ ሰባት
ማጣቀሻ ለትምህርት ውጤታማነት ሥነ-ፅሁፍ ማንበብ ይጠቅማል፡፡

በሠንጠረዥ 15.1. የተሰጠው ማጠቃለያ ዳራ እና ስኬት /ውጤት/ ነው፡፡


በመሆኑም የቃል በቃል ትርጉም አልፎ አልፎ መጠቀምም በጃፓን የእንግሊዝና ክፍለ ጊዜ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰባት ቃለ
መጠይቅ ከተደረገላቸው መሀል በተሰጠው መልካም ምላሽ የቃልበቃል ትርጉም ብዙም አይደነቅም፡፡የባሰ ተሳታፊዎች
ትኩረት ያደረጉም የሥነ-ጽሁፍን ሚና በቋንቋ ትምህርት ውስጥ ነው፡፡ የሰባቱ የቃለመጠይቅ አምስቱ ታላሚውን ቋንቋ
በስራቸውም ምክንያት ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ በዝቅተኛው ክፍል ግን ወደ አንደኛ በሚያልፉት ብዙም አይጎላም፡፡ ይህ
እንግዲህ የሚያመለክተን ጥቂት ቁጥር ባላቸው ተማሪዎች ቋንቋን ለማስተማር እጅግ ወሳኝ እንደሆነ ያመለክታል፡፡
በከፍተኛ ደረጃ ተቋም ላይ ያሉ ተማሪዎች ሥነ-ጽሁፍ ቋንቋን ለመለማመድ ቢጠቀሙ ጥሩ እንደሆነ ይገልፃል፡፡

አፈ-ታሪክ -1 MITANI HARA MASAK

7. እንግሊዝኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ


የመጀመሪያው ምሣሌ ማሳኮ ነች እሱም በጃፓን የእንግሊዝኛ ምልልስ ወይም ንግግር ትምህርት ቤት አስተማሪ
ነው፡፡ የእሱ ምሥክርነት በከፍተኛ ደረጃ የእንግሊዝኛን ብቃት ትምህርት ቤት የአሜሪካ ቆይታዬ ምንም ተፅዕኖ
አላደረገብኝም፡፡
ምሥክርነት - ሀ

ማንበብ እወደለሁ ስለዚህ ሁለቱንም ጃፓንኛውንም እንገሊዝኛውንም ጎን ለጎን አድርጌ በደንብ አነባለሁ፡፡
በአሜሪካ መቆየት፤ ተመልሶ መምጣት ብዙ ነገሮችን፤ ብዙ መፅሀፍቶችንና ወረቀቶችን ማንበብ አስችሎኛል፤
በወር ውስጥ ጥቂት መፅሐፎችን ማንበብ ቋንቋውን እንድጠላው ደርገኛል፡፡ ስለዚህ የእንግሊዝኛ ቋንቋ
ለማዳበር ብዙ አንባቢ መሆን ይጠበቅብኛል፡፡ እንደገናም በጃፓን ኮሌጅ ውስጥ ያሉት ከተለያየ አካባቢ የመጡት
ሁሉ በማንበብ ብቁ ሆነው እንደ አፈ ፈት እንግሊዝኛ ተናጋሪ በደንብ መናገር ይችላሉ፡፡

አፈ ታሪክ - 2. HIRAI MARI

ሁለተኛ ምሣሌ ማሪ የመጀመሪያ ዓመት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪ እሷም የምታስረግጠው በትጋት
የተፃፉትን የሥነ - ጽሁፍ መፅሐፍትን ማንበብን ነው፡፡ የአሷ ስኬት ከ 1 ኛ ክፍል EIKEN ምዘና ተግባራዊ
ልምምድን እስከ 3 ኛ ደረጃ ተማሪ እስከሆነችበት ጊዜ ድረስ ዘልቃለች፤ ሆኖም የቆየችው በ USA በ 6 እና በ 11 ዓመቷ
መሃል ባለው ልምዷ

በአጠቃላይ አልጠቀማትም ወሳኙንና ከባዱን ብቃት ማረጋገጫ ሙከራ ከወሰደች በኋላ ምንባብ ላይ ትኩረት ማድረግ
እንዳለባት አረጋገጠች፡፡

ምሥክርነት - ለ

በዩናይትድ እስቴትስ ቆይታዬ በጣም በጥልቀት የተሳብኩት ሥዕላዊ መፅሐፍ ላይ ነው፤ ይኸውም በትምህርት ቤቴ ቤተ -
መፅሐፍ ውስጥ የማገኘው ማንበብ የምፈልገው እሱን ነው፡፡ ወደ ጃፓን ስመለስ እንግልዝኛውን ማንበብ የቀጠልኩት
የወረቀት ጀርባን ነው፤ ማለትም ፅሁፎችን እነሱም ሁሉንም የእንግሊዝናንና የአሜሪካንን ሥነ ፅሁፍ በዚ የእንግሊዝና
ችሎታዬ ሊዳብር ችሏል፡፡ በ 8 ዓመት ዕድሜዬ ለ 15 ደቂቃ በየቀኑ ትምህርት ቤት ውስጥ ብዙ ሳቢ መፅሐፍቶችን ታነብ
ነበር፡፡ በቃለ መጠይቁ ሰዓት የሁለት ከተሞች ተረትና ሮሚዮና ዡሊየት በግሏ አፈ ፈት ተናጋሪዎች ትማር ነበር ፡፡
በተጨማሪም ብዙ በቃለ መተይቅ አማካይነት ለአምስት ዓመታት ያህል እና ከዚ በላ ካሉት ብቸኛዋ ሜሪ ቋንቋውን
ለራሷ በሚገባ አሳድጋለች፡፡

አፈ-ታሪክ - 3 የጃፓን እንግሊዝኛ ምሁር

ሦስተኛው መጠይቅ የጃፓን የእንግሊዝኛ ምሁር ነው፡፡ እሱ ከ 1 ኛ ደረጃ ጀምሮ በ EIKEN TEST /ምዘና/ ትግበራ
ያለፈ የእንግሊዝና መፅሐፍትንና መጣጥፎችን ያሣተመ ነው፤ እሱ ጥናት የጀመረው በመለስተና ደረጃ ላይ ባሉ ብዙ
ጃፓናውያን ተማሪዎች ነው በመጀመሪያ ያናገረው አፈ-ፈት የሆኑትን ተናጋሪዎችን እንደ መጀመሪያ ዲግሪ በማሰብ
ነው፡፡ ያጠናውም በስፋት በሃያዎቹ ነው፤ግን በትኩረት ያደረገው የሱን ቅድሚያ መጠይቅ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጥናት
እገዛና አጠቃላይ ክሂሎችን ነው፡፡ ዋናው ትኩረት ግን ከጉዞ ቅድሚያ የተለያዩ መሣሪዎች ውስጣዊም ውጪያዊም
አንብቧል፡፡

ምሥክርነት - ሐ

እንደ ሦስተኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለጥናቴ ትኩረት እሰጣለሁ፤ እኔ እንግሊዝኛን እማር የነበረው በስጦታ ነው፤ የኔ
እንግሊዝና ንባብ በጋዜጣ ነው፤ ምክንያቱም ሥነ - ፅሁፍን ብዙም አልወደውም ነበር፡፡ ጃፓንኛ ሥነ-ፅሁፍንም እንዲሁ
በሰዋሰው ጎበዝ ነበርኩ ግን በጣም የሚመስጠኝ ትርጉም ነው፡፡ ማንኛውንም ጽሁፍ ሳነብ ከበድ ያለ ወይም ለየት ያለ
ጽሁፍ ሊገጥመኝ እንደሚችል ስለምረዳ መዝገበ ቃላትን አጠገቤ እይዛለሁ፤ ከዚያም የማላውቀውን ቃል እረዳለሁ፡፡
ከዚያ በኋላ የአሜሪካም ሆነ የእንግሊዙ እንግሊዝኛ ዘመን ተሻጋሪ ሆኑትን ልብ ወለድ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በጣም
የመሰጠኝ መፅሐፍ “በ A.5. Byatt’s possession,” የተሰኘው ነው፡፡ ያነበብኩትም የድኅረ ምረቃ ተማሪ ሆኜ ብሪትሽ
ዩኒቭርሲቲ ከመግባቴ በፊት ነው፡፡ በተጨማሪም እሱ መፅሐፍ እጅግ ከባድ መፅሐፍ ነበር የቃል ዕውቀት የሚጠይቅ ግን
አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ የእንግሊዝኛን ሥነ ጽሁፍ የማንበብ ስሜቴ በጣም ተጋጋለ፤ እኔ የእንግሊዝኛን ሥነ ፅሑፍ
የማንበብ ፍላጎት ያደረብኝ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡

ከምሥክርነቱ የምንረዳው ወይም ምሥክርነቱ የሚገልጽልን ውጤታማ አንባቢ ለመሆን ሁሉም ከመነሻው እንደ አፈ -
ፈት የቋንቋው ተናጋሪ አንባቢ እንዳልሆነ ነው፡፡ ሌላው ብቃቱን ያገኘው በቃለ መጠይቁ ወቅት በበቂ ሁኔታ መዝገበ
ቃላትን መጠቀሙ ነው፡፡ ጥሩ በሚባል ደረጃ መዝገበ ቃላት ጃፓናውያን የኤሌክትሪካል መሣሪያን ጫፍ እንደ ምሣሌ
በማንሳት እና አነጋገሩንም በአፈ- ፈት ሰዎች ስለተቀዳ በቀላሉ ያዋህዱታል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና
ምሁራን ያሳተሙትን መዝገበ ቃላት የመጠቀም ዕድሉ ስላላቸው ለተማሪዎች ትልቅ ድጋፍ ነው፡፡

አፈ-ታሪክ - 4 ጃፓናዊው ተርጔሚ


ሌላኛው ተጠያቂ ጃፓናዊው ተርጓሚ ነው እሱ ደግሞ በትኩረት የተጠቀመው መፅሐፍ የእንግሊዝኛ ፍልስፍና እና
የእንግሊዝኛ ሥነ ፅሁፍ የአስተሳሰብ አድማሱን ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው እንዳደረገው ይገልፃል፡፡ የአስተሳሰቡ
መለወጥ መፅሐፍ ማንበቡ እንደሆነ ይናገራል፡፡

ምሥክርነት - መ

የእንግሊዝኛ ፍልስፍና መፅሐፍና የሥነ - ፅሁፍና መፅሐፍ በጣም ሳቢ ሆነው ነው ያገኘኋቸው ምክንያቱም ከብስለቴና
ከዕውቀቴ ጋር በቀጥታ ስንቅ ስለሚመግቡና ስለሚገናኑ ነው፡፡ እነሱን ማንበብ እንግሊዝኛን ለመፃፍ ለሚፈልጉ ሁሉ
እጅግ ተቃሚ ናቸው የብዙ ሰዎችን መፅሓፍ ማንበብ እንግሊዝና ጽሁፎችን መረዳት ሰዋሰውንና ቃላትን ለመረዳት
ዕድል ይፈጥራል፤ ግን እኔ ማንበብ የምፈልገው በጣም ውስጤን የሚፈትሽና ማንነቴን የሚገልፅልኝን ነው፡፡ ያውም
በእንግሊዝኛ ፅሁፍ የተደራጀውን ነው፡፡ በተጨማሪም ፀሓፊዎች ዘመን ተሻጋሪ አጠቃላይ ተመራጭ የሆኑ ቃላትንና
አገላለፅን እንዲሁም በጥንቃቄ ሃሳባቸውን የሚያጋሩንን ነው፡፡ በዚያም ስሜት ስናነብ ቁልፍ ሠላምንና መረዳት ወይም
እንግሊዝኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋውን በጥሩ ሁኔታ እንዲለማመዱት ዕገዛና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡እሷም
ትኩረት ሰጥታ የምትለው ፍልስፍናውን እንቀስማለን እና ሃይማኖታዊ ዕውቀቶቻችንም ስናነብ በታላሚ ቋንቋ
የተፃፈውን ፈልገን ቢሆን ተግባቦትን ከፍ ደርግልናል፡፡ የተሻለ እሰቤና ባህልን እንዲሁም ዕሴትን የነባር ሃገር ቋንቋን
ማስወጣት ተገቢ አይደለም፡፡ ይህ አለመረዳት ነው፡፡

አፈ-ታሪክ - 5 ካቶ አያኖ

ይህ የሥራ ዕቅድ የታሳቢውን ቋንቋ ልምድና ክህሎታዊ ተግባቦት ያላቸውን ግን ውስን ስኬታማ ማሪዎች ያጠቃልላል፤
ተማሪዎቹ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው የ 1 ኛ ደረጃ ምንባብና ዋናውን ፅሁፍ አቅልሎ ማመር ነው፡፡ ብዙ ተማሪዎች
በከፍተኛ ደረጃ ላይ እና በዩኒቨርሲቲ ላይ ጥሩ አጋዥ ነገር ያገኛሉ፡፡ ቀጣዩ ምሥክርነት ከአያኖ የ 4 ዓመት የዩኒቨርሲቲ
ተማሪ ርቃ የማትኖር፡፡ እሷም የራሷን የዕውቀት ችሎታ ያዳበረችው ከ 615 ( L325 : R 290) በፀደይ ደግሞ 2010
ወደ 780 (L410 : R 3701) በግንቦት በቀጣዩ ዓመት የተጠቀመችው GRS እሱም ከፍተኛ ውጤት ተመዘገበበት
በጃፓን ወሳኝ ዩኒቨርሲቲ ለምንም ተጨማሪ ጊዜና ልምድ ነው፡፡ 9
ምሥክርነት - ሰ

እንደ እኔ ወጣ ያለና የተሸለ የማስተማር ዘዴ ቢኖረኝና ብጠቀምም በስፋት ማንኛውንም መፅሐፍ ማንበቤ
የእንግሊዝኛና የአሜሪካንን የሥነ-ፅሁፍ ውጤቶችን ግልጽና ቀላል አድርጎልኛል፡፡ እስከ መጋቢት 2011 በየቀኑ ለሦስት
ሰዓት ያህል ማንበብን ለአምስት ወራት ያህል በትክክል ተገወባራዊ አደረግሁት፡፡ በአጠቃላ ምርጫዬ ያደረግሁት 10000
ያህል ቃላት ያሉትን መጽሐፍ በየቀኑ መጨረስ፤ በማነብበትም ጊዜ ምንም ነገር ለመናገር ልምምድ አላደርግም (
አልሞክርም) ፡፡ ሆኖም የንባብ ችሎታዬን ተጨማሪ የማንበብና ፈጣን ግብረ መልስ ሆኖኛል እንደ ዕውነቱ ከሆነ
በአዕምሮዬ በቀላሉ መጠቀም የምችላቸውን ቃላትና ሃረጋትን እንዲሁም ዐረፍተ ነገሮችን በማንበብ አዳብሬያለሁ
በተጨማሪም ማንበብን በብቃትና ንግግርንም ከዚሁ ጎን ለጎን አዳብሬለሁ፡፡

የአያኖ ትኩረት የቃላት ትርጓሜ እና የቃላትን ዕውቀት መረዳት ላይ ነው፡፡ የእሷ ምሥክርነት የሚያስረዳን ሳናቋርጥ
ማንበባችን ቋንቋን በተቀላጠፈና ብቃት ባለው ሁኔታ ማንበብ እና መፃፍ እንደምንችል በጃፓን ተገልጧል ቀጣዩ ደግሞ
ተማሪዎች ወደ መብቃት ደረጃና የነጠረ የአነባብ ብቃት ማሳደግ የሚችሉት የንባብ መሣሪያዎቻቸውን ከሚማሩት ጋር
መዋሃድ ሲችል ነው፡፡

6.2. ሌላው የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎች


የአሁኑ ጥናት ትኩረት ደግሞ ታላሚ ተማሪዎችን በሁለተኛ ቋንቋ እንደ ጃፓንና ቻይና፤ ይሁንና ፍፁም የሆነውን ልዩነት
አፈ ፈት የሆኑ እና ታላሚ የሆኑ ቋንቋዎች በጃፓኖች ሁኔታ ማስኬድ፡፡ ይህ ክፍል ትኩረቱ ለተጠያቂዎች አሜሪካዊ
ተማሪ በጃፓን ውስጥና ጃፓናዊ ተማሪ በቻይና ውስጥ ነው፡፡

አፈ-ታሪክ - 6 ቶም ጋሊ

ይህ ክፍል ደግሞ የሚጀምረው ቶም ጋሊ ውጪ ቋንቋን የለመደበት ሁኔታን ያስቃኘናል፡፡ ፕሮፌሰር ጋሊ Eigo no Aya
(Fingurs of English) የተሰኘውን መፅሐፍ የደረሰ ነው፡፡ ከዚህ አፈ-ፈት ከሆነው ጃፓናዊ እንዴት ታላሚ ቋንቋን
እንደ አስፈላጊነቱ ብቁ እንሆናለን፡፡ በውይይታችን ትምህርት ልምድ ልውውጥ ነው፤ ግን ደግሞ አስፈላጊ ባህልን
በአቋራጭ መልመድ፤ እሱም የሚገልጸው ውስኗን ገለፃ፤ ውጤታማ በሆነ ገለፃ ቃል በቃል መረዳት ነው፡፡

እሱ የሚያስረግጠው ውጤታማ ንባባ የቃል በቃል ሥራ እና የእሱ የመጀመሪያ የውጪ ቋንቋው ራሺያኛ ነው፡፡
በመምህሩ ዕገዛና ምክር የውጪ ቋንቋን ለማድመጥ የጨኮለና የተዋጣለት አንባቢ እንዲሆን የራሺያን የሥነ ፅሁፍ ሥራ
እንዲያነብ አድርጎታል፡፡ በመጀመሪያ የራሺያን መፅሐፍ በመዝገበ ቃላት ዕገዛ አንብቦታል ግን ይህ ልምድ ከግማሽ
ሰዓታት በላይ በአንድ ገፅ ላይ መቆየት ሆነበት ስለዚህ የመምህሩን ምክር መጠየቅ ነበረበት፤ የመምህሩም ምላሽ
እያንዳንዱን ነገር በመዝገበ ቃላት መፈተሸ ሳይሆን ፍላሽ ካርድ በማዘጋጀት ከባድ ከባድ ቃላት ሲያጋጥሙት እና ዋናዋና
ቃላት ሲያጋጥሙ መዝገበ ቃላት መጠቀም እንዳለበት ነገረው

10

ሁለቱን ተግባራት እርስ በእርሳቸው ተመጋጋቢ ሆኑለት እናም ከዓመት በኋላ የእሱ ንባብ በጣም ብቃት ያለው ሆነ፡፡

በቶልሰቶየ የተፃፈው “wart and Peace” የተሰኘውን ዘመን ተሸጋሪ ፅሁፍና ሥራ አንብቧል፡፡ እንደ እሱ ልምድ እጅግ
በጣም የጠቀመው የጃፓንን አልፋቤት ማጥናት መጀመሩ ነው፡፡

ፕሮፌሰር ጋሊ ጃፓንኛን መማር ሲጀምር በጃፓን የ 26 ዓመት ሰው ሆኖ ነው፡፡ ከትቂት ዓመታት ጥናት በኋላ ዘመናዊ
ጃፓንናዘመን ተሸጋሪ ሆኑትን የጃፓንን ፅሁፎች በሜጂ ኤራ እንደ ሶሲኪናፂዩ ማነበብ ጀመረ ደግሞ እሱንም
የሚያስማማ ሃሳብ ማንበብ ሙሉ ሰው ማድረጉን ነው፡፡ ማንኛውንም ፅሁፍ ማንበብ ከቻልን አዳዲስ ቃላትን ማወቅ
እንችላለን፡፡ አዳዲስ ቃላትን ካወቅን ደግሞ ንግግርና ፅሁፍ አያቅተንም፡፡

ምሥክርነት - ሸ

ልብ-ወለድን የሚያነብ በክፍሉ የሚፈጥረው ምናባዊ ፍስሐ /ፈገግ/ በማለት ለመደሰት መንገድ ይጠርግለታል የቃላት
ሥራ ደግሞ ብዙ ቃላትን ከምናነበው ነገር ውስጥ እንድናውቅ ያደርገናል፡፡ በጋዜጣ ለምሣሌ ምንም እንግሊዝኛ ተናጋሪ
የለም እንበል ወይም ከዕለታዊ ንግግር ያለፈ ነገር የሚያውቅ የለም እንበል፡፡ ከእነዚህ ቃላት ተነሳ ያለ ገደብ ብዙ ቃላትንና
ትርጓሜዎችን ያውቃሉ ፡፡ እሱ በተጨማሪ ትኩረት ያደረገው ሥነ ፅሁፍ የሕዝብን ማንነትና የሕዝቡን ዕሴት በተለያዩ
ሀገራት ያሣውቃል፡፡ የሥነ ፅሁፍን ሥራዎች ማንበብ የባህልን ጥንት አመጣጥ እና ቋንቋን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም
የጃፓኖችን የዚህ ዕድገት ደረጃ እንረዳለን መጀመሪያ ቋንቋውን ለመረዳት እስከ አሁን እጅግ ይከብደኛል፡፡ እንዴትስ
ተማሩ? ቤተሰቦቻቸው ታማሚና እንክብካቤ የሚፈልጉ ናቸው ታዲያ እንዴት በዙ? እንደሁኔታው ለመተርጎም ብነሳም
የጃፓንን የሥነ-ፅሁፍ ሥራ ወይም ልብወለድ ወይም አጭር ልብወለድ የጃፓኖቹን አስተሳሰብ እና ችግራቸውን ልትረዳ
ትችለለህ፡፡ በፅሁፍ ውስጥ ልብወለድ ደራሲ የሞት ሃሳብ ሊያነሳ ይችላል፡፡ በገፀ ባህሪያት ሞት የዕለት ዕለት ህይወት
ተሞክሮ ነው ጤና እና እንክብካቤን ለሽማግሌዎች እንደ ግለሰባዊ ንግግር ነው፡፡ እንደዚህም መዕራፍ የቅርብ ጓደኛ ነው፡፡
በዚህም የጃፓን የሥነ ፅሁፍ ሥራ እንዳውም ዘመናዊና ከልብ ዕገዛ ያደረገልኝ እንዲሁም ስለ ጃፓናውያን በተሸለ መልኩ
ግንዛቤ እንዲኖረኝ፤ ሁኔታውን እንዳስብ ያደረገኝ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጋሊ በጃፓን የኖሩት ከ 30 ዓመት በላይ ነው እና ብዙ
የውጪ ሃገር ሰዎችንም ለረጅም ጊዜ አግኝተው ብዙ ሃሣብና ልምድ ተለዋውጠዋል፡፡ እንደ መጠይቁ አካሄድ ብርቅዬ
የጃፓንን ባህልና ዕድገት እንዲሁም ቋንቋውን የጃፓንን ሥነ ፅሁፍ ሥራ አሳድጓል፡፡

አፈ-ታሪክ - 7 ካዊ ቶም ሂሮ

ቶምሂሮ ውጤታማ ጃፓናዊ የቻይና እና እንግሊዝኛን በሥነ -ፅሁፍ ሥራ እና በቃለ መጠይቅ ራሱን ያበቃ ነው፡፡ እሱም
ብቸኛ በንግድ ዓለም ተሠማርረቶ የሚሠራ ልዩ የቋንቋ ተማሪ ነው፡፡

11

ሆኖም ጃፓንኛንና ቻይንኛን ቋንቋን በጠቂቱ ይሞክራል ሁሌም አይደለም፡፡ የቻይንኛን ቋንቋ በባህሪው ውስብስብና
ከባድ የእፀ መዋቅር እንዲሁም የአነባበቡ እና የስሜት አገላለፁ አስቸጋሪ ነው፡፡ በአብዛኛው ጃፓናውያን የቻይናን ቋንቋ
በመለስተኛ ደረጃና በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የማይማሩት ለዚህ ነው፡፡ ከእንግሊዝኛ ይልቅ ከበድ ይላል፡፡
ቶም ሂሮ ቻይንኛ ነበረ የተማረው በሮምናንት አውስትራሊያ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ እንደ እሱ አገላለጽ የቻይንኛ
ትምህርት ትኩረት የሚጠይቅና በባህሪ መተርጎም የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ቡድሃ ሥነ ፅሁፍ፤ ሥነ ቃል እና ዘመን ተሸጋሪ
የሆኑ ፅሁፎችን ብናነብ በጥቂቱ መረዳት እንደምንችል ይገልፃል፡፡

ምሥክርነት -ቀ
በትምህርት ደረጃ እና ማዕከላዊ የመንግሥት አገዛዝ ጋር በስብሰባም ሆነ በተለያዩ ጉዳዮች አወራለሁ የሚል እሳቤ
በአእምሮዬ መጥቶም አያውቅም፡፡ ብዙ ተገልጋዮች እና ቻይናውያን ለንግግራቸው ማጠቀሻ የሚጠቀሙት yoji –
jukugo በተለይ በሚማሩበት ወቅት፡፡ ከልጅነት ጀምሮ የፈሊጣዊ ንግግር እና እነዚህም ደግሞ በቀጥተኛ ይሁን ኢ-
ቀጥተኛ መንገድ እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው በአጠቃላይ በፈሊጥ ራሳቸውን ያለማምዳሉ፡፡ አንድ ሰው ራሱን ከቋንቋ
ጋር ለማዋሃድ ፈሊጥን በንግግሩ መሃል በተደጋጋሚ መጠቀም አለበት፡፡ ያም የቻይናውያን ብሂል ስለሆነ ቻይናውያን
በቀላሉ ቋንቋውን ያለማምዱታል፡፡ እንደ እኔ ምንም ዓይነት መመሪያ የለኝም ግን ቋንቋን ለመለማመድ ከአፈ - ፈቶች
ጋር መነጋገር የግድ ይላል፡፡ እኔ የሚሰማኝ እንደ መደበኛ ትምህርት ቻይና ደግሞ የእኔ ብቃት ካለው የንግድ ዘርፍ
ከተናጋሪዎች ጋር ለመቀላቀል ነው፡፡ ሁሉም ከባህሩ በላይ ደቡብ እስያ ላይ ትገናለች፡፡ ይሁንና በከፍተኛ ደረጃ ከዚህ
ማህበረሰብ ጋር ለመቀላቀል እነደ ፕሮፌሰር ወይም መንግሥታዊ ሠራተኛ (ቢሮክራሲ) ቻይንኛን መነጋገርና ባህላቸውን
መቀበል ዋና ነው፡፡ ያ ማኅበረሰብ ሰው ተቀባይ ነው፡፡በተለይ መንግሥታዊ ተቋም ላይ ያሉ ሰዎች ከዘመን ተሻጋሪ የቻና
ሥነ ፅሁፍና ፍልስፍና ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፡ እንደ ሱስ በዘመን ተሸጋሪ ቻይናን በመፈተሸ ተጠምደዋል፡፡ ቶመሂሮ
አስረግጦ የሚናገረው ቋንቋን በመማር ሂደት ቻይንኛን እንደ ውጪ ቋንቋ ስናጠና የሥነ ፅሁፍ ሥራዎችን እናሳድጋለን
ይህም እንደ ብረት የጠነከረ ማንነት ይኖረናል፡፡
12

8. Conclusion ማጠቃለያ (መደምደሚያ)


በዚህ ጥናት ላይ ለማየት እንደተሞከረው ከሳይቶና ከ ኤሪካዊ ግኝት በመነሳት ሲሆን ይኸውም ስነ -ፅሁፍን ማንበብ
ለአንድ ሰው በውጭ ቋንቋ ተምሮ ስኬታማ ለመሆን ያለውን ሚና ለማሳየት ነው፡፡

በዚህ ጥናት የጥቂት ከፍተኛ ደረጃ ተማሪዎች ልምድ እንደሚያሳየው የተለያዩ ፅሁፎችን ማንበብ በውጪ ቋንቋ
መበልጸግ ስኬታማ ለመሆን እንደ አንድ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

በተለይ ስነ-ፅሁፍን ማንበብ በቋንቋው ለመበልጸግ ብቻ ሳይሆን በሉአላዊ ማህበረሰብ ያለውን የባህል ልውውጥ
ለማሳደግና ለመገንዘብ ጠቀሜታ አለው፡፡

የአንዳንድ ስኬታማ የውጭ ቋንቋ ተማሪዎች ከበፊትና አሁን ካለው ልምድ ለመረዳት እደሚቻለው ስነ -ፅሁፋዊ
ስራዎችን በስፋትና በጥልቀት ማነበብ አለማቀፋዊ ሰው ለመሆን የራሱ የሆነ አስተዋፅዖ እንዳለው መረዳት ይቻላል፡፡

ለምሳሌ እነ ኒቶቢ ና አካከራና አንዳድ ቃለ-ምልልስ ከተደረገላቸው ሰዎች በተገኘ መረጃ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በባለፉት 150 ዓመታት የትምርት አሰጣጡ የጠለዋወጠ የመጣ ሲሆን የተለያዩ ተማሪዎች የተለያዩ የመማሪ ዘደዎችንና
ግብአቶችን ይጠቀማሉ ለምሳሌ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም ኢንተርኔት፣ ዲቪዲና የኤሌክትኒክስ ዲክሽነሪ
ይጠቀማሉ፡፡ለሌላ የውጭ ቋንቋ ተማሪዎች ምንም እንኳን እነዚህ ዕቃዎች ባይገኙም፡፡ አብዛኞቹ ስኬታማ ተማሪዎች
እነዚህን ግብዓቶች ለቋንቋ ክህሎታቸውን ለማሳደግ ተጠቅመውባቸዋል፡፡

13

You might also like