You are on page 1of 3

1.

የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን የማስተማር ዘዴ


ቋንቋን ለማስተማር ከሚረዱት ዘዴዎች መካከል ሰዋሰውን ማጥናት አንዱ ሲሆን ከቅርብ ጊዜያቶች ወዲህ

(recent times) ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩት ዘዴዎች መካከል ደግሞ ተግባቦት (communication) ላይ

ማተኮር የበለጠ ጠቃሚ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።

ተግባቦት ላይ መሠረት ያደረጉ የቋንቋ ማስተማር ዘዴዎች (Communicative language teaching

approach) በራሳቸው ሂደት ላይ ያተኮሩ እና ውጤት ላይ ያተኮሩ ተብለው በሁለት የሚከፈሉ ሲሆኑ የግእዝ

ትምህርትን ለማስተማር ውጤትን መሠረት ያደረገው ዘዴ በአንጻሩ የተሻለ ሲሆን በዚህም ዘርፍ የተመደቡትን

መጻሕፍትን መጠቀምንና አስቀድሞ የተቀረጹ ዓላማዎች (text-based instruction & competency-based

instruction) ላይ ተመሥርቶ ትምህርቱን መስጠት ጠቃሚ ይሆናል።

የቋንቋ ሕግጋትን ማወቅ ቋንቋን ለመቻል ጠቃሚ ቢሆንም ቋንቋን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተጠቅሞ

መግባባት መቻል ሊቀድም የሚገባው ተግባር ነው። ለዚህም የሚከተሉትን ሥነ ዘዴዎች መጠቀም

ያስፈልጋል፡፡

ለቋንቋ ተግባቦት መርሕን የተከተለ ሥርዓተ ትምህርት መንደፍ፣

መራሕያን እና የግስ እርባታን ተማሪዎች ከተማሩበት ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው ማስተማር፣


ተማሪዎች በተማሩበት ርእስ መሠረት ምሳሌ በመስጠት፣ መልመጃ በማሠራት እና የሚሠሩ ሥራዎች

በመጽሐፉ ውስጥ መካተት አለባቸው።

የግእዝ ቋንቋን ከተማሪዎች የዕለት ከዕለት ኩነቶች ጋር በማዋሓድ በግእዝ ቋንቋ እርስ በእርስ ለመግባባት

የሚቻልበትን ዓውድ መፍጠር፣

በክፍል ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት ከገሃዱ ዓለም (Real world situation) ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው

እንዲሆኑ ማድረግ፣

የግእዝ ቃላት ትርጉም በተማሪዎች የክፍል ደረጃ ተመጥኖ በቀላሉ ሊሰጥ የሚችል እንደ መዝገበ ቃላት

የሚያገለግል በሶፍት ኮፒ ተዘጋጅቶ ኮምፒውተር ክፍል ቢደረግ (Reference Books)፣

ተማሪዎች የመጻፍ ክህሎታቸው እንዲያድግ መልመጃ (Work book) እንዲያዘጋጁ በማድረግ ማሠራት፣

አጫጭር ትምህርቶችን በድምፅ እና በምስል መቅረፅና የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለተማሪዎች

እንዲደርስ ማስተማር ያስፈልጋል።


በአጠቃላይ የግእዝ ቋንቋ የትምህርት ሥርዓት የሚከተሉትን ጥቅሞች በሚያስገኙ መንገድ ሊቀረጽ ይገባል፦

1. የተለያዩ መጻሕፍትን ለማንበብ የሚረዱ ሆነው መቀረጽ አለባቸው፣


2. ሳይንሳዊ እና ሀገራዊ ዕሴቶችን የያዙ ፣
3. ተግባቦትን መሠረት ያደረጉ፣
4. የተማሪዎችን ስሜትና ፍላጎት ለመግለጽ የሚያመቹ መሆን አለባቸው፣
5. ለመማርና ለአዳዲስ ነገሮች አቅጣጫ ለማግኘት ፣
6. በቂና ጠቃሚ የአገሪቱን እምቅ ዕሴቶች በውስጣቸው ለማስረጽ፣
7. ታሪካዊ፣ ሳይንሳዊ እና መንፈሳዊ ሀብቶችን እንዲያስተላልፉና እንዲዘግቡ ሆነው መደራጀት አለባቸው።

2. በየክፍሉ ደረጃ የሚዘጋጁ የማስተማሪያ መጻሕፍት መያዝ ያለባቸው ዓበይት ተግባራት

3. የግእዝ መማሪያ መጽሓፍት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች

11 ኛ ክፍል
 ስመ ተጸውአ፣ ስመ ኊባሬ፣ ስመ ምዕላድ ምንም ሳይቀር ከ 10 ኛ ክፍል የተደገመ ነው፣
 9 ኛ ክፍል ላይ ያለው ስለ አገባብ ተደግሟል፣
 9 ኛ ክፍል ላይ ያለው ገሲሶተ ግስ ተደግሟል፣
 አርባእቱ ንባባት ከ 5 ኛ ክፍል የተደገመ መሆን፣
 ስለ ቅፅ ከጉባኤ ቃና ጀምሮ እስከ መወድስ የተፃፈው ስለ ቅኔ በደንብ ሳይማሩ ስለሆነ መክበዱ፣
 በአጠቃላይ ሲታይ አብዛኛው ርዕስ ከታች ክፍል ተወስዶ የተደገመ መሆኑ ነው፣
12 ኛ ክፍል
 በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ በሙሉ በኩሉ አገባባት ናቸው (አቢይ አገባብ፣ ደቂቅ አገባብ፣ ንዑስ አገባብ)፣
 ከአገባባት ጋር ሌሎች ጽሁፎች አለመካተታቸው፣
 የአገባቦች ጥቅም በደንብ አልተብራራም፣
 የአገባቦችን ጥቅም ለማወቅ መጀመሪያ አገባብ ምንድነው የሚለውን ማወቅ ይኖርባቸው ነበር፣
 ከአገባቦች ውስጥም የተዘበራረቀ ነገር ተጨምሮበታል (አርእስተ ግስ፣ ቀተለ፣ ቀደሰ…)፣
 ስርዓተ ንባብ ከ 5 ኛ ክፍል የተደገመ መሆኑ፣
 ሕብረ ንባብ የተደገመ ነው፣
 ቦዝ አንቀጽ ከ 7 ኛ ክፍል የተደገመ መሆኑ፣
 አዕማድ አርዕስት የተደገመ መሆኑ፣

5.12. ፲፩ኛ
፩. (ፊደላት/ቀለማት) ግስ ዘይትዌጠን ቦቶሙ

፪. (ፊደላት/ቀለማት) ግስ ዘኢይትዌጠን ቦቶሙ

፫. ፊደላት (ቀለማት) ዘይከውኑ ለፍጻሜ አናቅጽ

፬. በጊዜ ዝርዝር (ትንታኔ) ለዘንድ ወለትእዛዝ ዘያላሐልሁ ፊደላት (ልሕሉሀ ዘይገብሩ ፊደላት/ቀለማት

፭. ንባብ

፮. ምንት ውእቱ አገባብ

፯. መስተዋድድ ወመስተፃምር ዘምስለ ምሳሌ

፰. ትውፊት

፱. ተምሳሌት

፲. ዳዊት ዘቀዳሚት

5.13. ፲፪ኛ
፩. ዐቢይ አገባብ በዝርዝር

፪. ንኡስ አገባብ በዝርዝር

፫. ደቂቅ አገባብ በዝርዝር

፬. ቦዝ አንቀጽ

፭. መሠረተ እርባታ ዝርዝር

፮. ምንት ውእቱ ቅኔ

፯. ክፍላተ ቅኔ

፰. ፍኖተ ቅኔ

፱. ዜማ ልክ

፲. ምህጻረ ቃል

፲፩. ዳዊት ዘእሑድ

You might also like