Professional Documents
Culture Documents
ZX
ZX
በመጀመሪያ በምህረቱ እና በቸርነቱ ጠብቆ ለዚህ ላደረሰኝ ለድንግል ማርያም ልጅ ለልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይድረሰው በመቀጠልም ጥናታዊ ፅሁፉ እዚህ ደረጃ እስኪደርስ የጎደለውን አሟልቶ የተጣመመውን
አቃንቶ ዘወትር የሆነውን ምክሩን እየለገሰ ጥናቱ አሁን ካለበት ደረጃ እንዲደርስ ለረዳኝ አማካሪዬ ለኢሳያስ
ይልማ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በመቀጠልም እኔን ከፍ ለማድረግ እነሱ ዝቅ ብለው እዚህ ላደረሱኝ
ቤተሰቦቼ ምስጋናየ ከልብ ነው። በመጨረሻም በችግሬ ጊዜ ከፊቴ ሳይጠፉ መፍትሔ በመፈለግ አብረውኝ
የነበሩ ጓደኞቼን ከልብ አመሰግናለሁ።
አጠቃሎ
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ አገልግሎት ላይ የዋሉ የማስታወቂያ ፅሁፎች የቋንቋ
አጠቃቀምን ተንትኖ ማሳየት ነው። ጥናቱ አመቺ የናሙ ናአመራረጥ ዘዴን በመከተል ተካሂዷል። የመረጃ
መሰብሰቢያ ዘዴዎችም ሰነድ ፍተሻ እና ያልታቀደ ምልከታ ናቸው። በተገኘው መረጃ መሠረትም የቋንቋ
አጠቃቀም፣ የቃላት ምስል ከሳችነት እና ታዋሽነት ሁኔታ እንዲሁም ሰዋሰዋዊ የቃላት አጠቃቀም
ተተንትነዋል። በዚህ ጥናት ማወቅ የተቻለው በቃላት አጠቃቀም የዘዬ (ቀበልኛ) ቃላትን ማዘውተር፣ ድረታ
እና ተደጋጋሚ ቃላትን የመጠቀም ችግር፤ ከሰዋሰው አንፃር ደግሞ የቁጥር እና የመደብ አለመስማማት
እንዲሁም ስርአተ ነጥብን በአግባቡ ያለ መጠቀም ችግር ያለበት መሆኑን ነው። እነዚህ ችግሮች ደግሞ
በማስታወቂያ አማካይነት መልዕክት ለአንባቢ በሚቀርብበት ወቅት መልዕክቱን ለማንበብ እና ለመረዳት
አዳጋች እንዳደረጉት ተደርሶባቸዋል።
ምዕራፍ አንድ
1 መግቢያ
1.1 የጥናቱ ዳራ
የሠው ልጅ ሀሳቡን በፅሁፍ መግለፅ የጀመረው የዛሬ አምስት አመት ገደማ እንደነበር ይነገራል። ፅሁፍ
ከመጀመሩ ወይም ከመገኘቱ በፊትም ሠዎች ለብዙ ዘመናት ሀሳባቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ወዘተ. ሲገልፁ
የኖሩት በንግግር ነበር። ፅሁፍ የሚታዩ እና የሚዳሰሱ ልማዳዊ ወይም ስምምነታዊ ምልክቶች አማካኝነት
የሚቀርብ የንግግር ቋንቋን ቀርፆ የማቆያ ስልት ነው(አብነት፣277) ።
የመጀመሪያው ፅህፈት ተጀመረ ተብሎ የሚነገረው በሱሜሪያውያን ህዝቦች አማካኝነት ሜሶፓታሜያ ውስጥ
ሲሆን የፅሑፉ መጠሪያ ኩኒፎርም ወይም የሽብልቅ ፅሁፍ በመባል ይታወቃል። ሌሎች ደግሞ ጥንታዊ ፅሁፍ
በግብፃውያን የተፃፈው ሔሮግራፊክስ የተሠኘው ነው ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ የአሜሪካኖች ኮሎምቢያ
የዖልሜክ እና የማያን ህዝቦች እንደጀመሩት እና አየዳበረ እንደመጣ ይታመናል በማለት አብነት (2007፣277)
ገልፆታል።
ከዚሁ ጋር አያይዞ የስርዓተ ፅሕፈት አጀማመር እና እድገትን ያጠኑ ጠበብት እንደገለፁት ለዛሬዎቹ ልዩ ልዩ
የፅሁፍ የመሠረቶች ስዕላዊ ፅህፈት፣ ቀለማዊ ፅህፈት፣ ፊደላዊ ፅህፈት የተባሉት ደረጃ በጀረጃ እያደረጉ አሁን
ካለበት እንደደረሰ ያብራራሉ (አብነት 2007፣232) ።
ፅሁፍ ስርዓትን ተከትሎ መልዕክት ለአንባቢ የሚያደርሰው ቋንቋ የሚፈቅደውን የድምፆች፣ የቃላት፣
የሀረጋት፣ የዓአረፍተ ነገሮች፣ የአንቀፅ እና የድርሰት አገባብ ስርዓትን ማወቅ ሲቻል ነው። ይህ ካልሆነ ትርጉም
አልባ መሆን እና የትርጉም መለወጥን በማስከተል ትርጉም እንዲፋለስ ያደርጋል።
በፅሁፍ አማካኝነት ሀሳብን ለማስተላለፍ ደግሞ የፅሁፍ ስርዓቶችን ማወቅ እና መጠቀም ያስፈልጋል። ይሄንን
አስመልክቶ ሳሙኤል (1999) ባዩሬኒ (1988፣1)ን በመጥቀስ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍሯል።
ሰንፅፍ እና ስንናገር ከምናወጣቸው ድምፆች ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ማለትም
ፊደሎች (የፊደሎችን ቅንጅት) እንጠቀማለን። በአንድ በኩል ፅህፈት የንግግር ድምፆችን
የሚወክሉ ምልክቶችን የመቅዳት እና በወረቀት ላይ የማስፈር ተግባር ነው ሊባል ይችላል፤
ነገር ግን የንግግር ድምፆችን የሚወክሉ ምልክቶችን፣ ቃላትን፣ ዓረፍተ ነገሮችን
ለመመስረት በቋንቋው ስርዓት መሰረት ተቀናብረው መዋቀር (መሰደር) አለባቸው።
ከዚህም እንደምንረዳው ፅህፈት የራሱ ስርዓት ያለው ድምፆች ቃላትን፣ ቃላት ሀረጋትን፣ ሀረጋት ዓረፍተ
ነገሮችን መገንባት እና አረፍተ ነገሮችም ርስ በዕርሳቸው ተገናኝተው የቋንቋዉን ስርዓት መጠበቅ
እንዳለባቸው ነው። ዐረፍተ ነገሮች የተዛመዱ፣ የተከታተሉ እና የተቆራኙ ከሆነ የሀሳብ አንድነት እና ጥምረት
ያለው ፅሁፍ መፃፍ ይቻላል።
በአጠቃላይ ፅሁፍ በአካል መግለፅ ማለትም በንግግር መልዕክትን ማስተላለፍ በማንችልበት ሁኔታ መልዕክትን
ለማስተላለፍ፣ ሀሳብን ቀርፆ ለትውልድ ለማቆየት፣ ዘመን ተሻጋሪነትን ለማጎልበት፣ ወዘተ ያገለግላል።
ለምሳሌ ደብዳቤዎች፣ መልዕክቶች፣ የተለያዩ የደስታም ሆነ ሀዘን መግለጫዎች፣ ትምህርታዊ ሰነዶች፣
መፅሄቶች፣ ጋዜጦች፣ ማስታወቂያዎች እና የመሳሰሉት ሁሉ የሚቀርቡበት የሚቀርቡት በፅሁፍ ነው።
በመሆኑም የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት የሆነው በፅሁፍ ሀሳብ ከሚገለፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው
የማስታወቂያ የቋንቋ አጠቃቀም ነው። የቀደሙ አባቶች ወይም ነገስታት ማስታወቂያ የሚውሉ የክተት
ጥሪዎችን፣ የአዋጅ ነጋሪ ቃሎችን፣ የቤተክርስቲያን ደውሎችን፣ የከበሮና ፅናፅል ድምፆችን፣ ወዘተ. ሲሆን
በአሁኑ ጌዜ ደግሞ መስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች (ግለሰቦች) ለጨረታ፣ ለቅጥር፣ ለደንብ እና ለትዕዛዛት ገለፃ፣
ለመሸጥ፣ ለመግዛት፣ ለመለወጥ፣ የጠፋን ለመፈለግ፣ አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ ወዘተ.
የሚጠቀሙበት ፅሁፍ ነው። በመሆኑም ነገሮችን ለማስተላለፍ ግልፅ እና ለሰው እይታ በሚመች ቦታ ላይ
በመለጠፍ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት እና በመሳሰሉት ላይ በመፃፍ እንዲሁም በዜና ማሰራጫዎች በሬድዮ፣
ቴሌቪዥን፣ በኢንተርኔት፣ ወዘተ. የሚያደርጉበት የሀሳብ መግለጫ ነው (ባህሩ 2004፣122) ።
የማስታወቂያ መሰረተ ሀሳቦች ሲነሱ ብዙዎች የተለያዩ ትርጉም የሚሰጡ ተያያዥ ቃላት እና ሀሳባቸውን
ይሰነዝራሉ። ብዙውን (advertising) ሲነሳ የማሻሻጥ የእወቁልን እና የህዝብ ግንኙነት የሚሉትን ቃላት
በተለዋዋጭነት እንጠቀምባቸዋለን። ዳንኤል (200፣57) “እወቁልን የሚለው ሀሳብ ዕወቁ ብቻ ሳይሆን
የማግባባት እና የዕእመኑኝ ፍላጎትም አለበት። ዕወቁልኝ እነዚህ ባህሪያት ከማስታወቂያ ጋር እጅጉን ያቆራኙት
እንጂ የልዩነት ነጥቦችም አሉት፤ ዕወቁልኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል እጅጉን የቀረበ ነው።” በማለት
ይገልፁታል።
ማስታወቂያ የአንድን ምርት፣ አገልግሎት (ሀሳብ) ለማስተዋወቅ ሲሆን ምርቶችን ለማማሻሻጥ ወይም
አገልግሎትን ለሰዎች ለማሳወቅ እና ረጅም የሚቆይ አመኔታን ለማምጣት የሚጠቅም ነው። ስለሆነም
ማስታወቂያ በግል፣ በፓለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎች፣ በማህበራዊ ተቋማት፣በጎ ፈቃደኛ ቡድኖች እና
በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ ይውላል (ወርልድ ቡክስ ሳይክሎፒድያ 1994፣72) ።
1.6 የጥናቱ ዘዴ
የጥናቱ ዘዴ ሲባል ጥናቱ በምን መልክ እንደሚጓዝ የሚያሳይ እና የጥናቱን ጠቅላላ ሁኔታ የሚመለከት ነው።
በመሆኑም ጥናቱ በገላጭ የምርምር ስልት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በዚህ ክፍል ውስጥም የናሙና አመራረጥ
ዘዴ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ እና የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተብራርተዋል።