You are on page 1of 5

1 በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መርሀ ትምህርት ውስት የማዳመጥ ክሂል ለማዳበር የቀረቡ ይዘቶች ትንትናነና

ግምገማ

እቴነሽ ተገኘ

ደጀኔ/ዶ/

1986

በዚህ ጥናት በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መርሀ ትምህርት ውስጥ ማዳመጥን ክሃል ለማዳበር የቀረቡ ይዘቶችን
ለመተንተንና ለመገምገም፤ ከተማሪዎች ፍላጎት ችሎታና ዝንባሌ ጋር የሚጣጣሙ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ
ተሞክራል፡፡

ጥናቱም ይዘቶቹን ስልማዳመጥ ክሂል ከተለያዪ ምሁራን ከተገኙ ንድፈ ሀሳቦችና ከተማሪዎች ፍላጎት አበባ
ከተገኘ ውጤቶች ጋር በማገናዘብ ተጠንቷል ፡፡

-በመርሀ ትምህርቱ ውስጥ የማዳመጥን ክሂል ለማዳበር የቀረቡ ይዘቶች ከተማሪዎቹ ፍላጎት አንጻር ሲታዩ በጣም
አነስተኛና የተለያዩ የማዳመጥ አይነቶችን ያላካተቱ ናቸው Á ላካተቱ ናቸው፡፡

-ይዘቶቹ የትኛውን ክሂል ለማዳበር እንደተፈለገ በግል î ና በዝርዝር አያሳዩም፡፡ይዘቶቹም ሆኑ በይዘቶቹ አንጻር
የቀረቡት የክፍል ውስጥ ልምምዶች የተገለጹበት ቋንቋ ግልጽነጽት የጎደለው በመሆኑና ከዚህም ጋር የማዳመጥና
የመናገር ክሄሎችን የሚያዳብሩ ይዘቶች በአንድነት በመቅረባቸው በየትኛው ክሂል ለይ ሊተኮር እንደተፈለገ
አሻሚ ትርጉም ይሰጣሉ ፡፡

-ይዘቶቹ በመርሀ ትምህርቱ ውስጥ የቀረቡበት ቅደም ተከተል የክብደት ደረጃቸውን የጠበቀ አይደለም፡፡ በአንድ
ሴሚስተር በተከታታዪ በቀረቡበትም ሆነ በአንደኛውና በሁለተኛው ሴሚስተር በቀረቡበት ይዘቶች መካከል
የክብደት ደረጃቸው አለመጠበቁ በግልፅ ታይታል ፡፡

-ይዘቶቹ ግልጽነት በጎደልው ሁኔታ በቃላት ተደባብው ቢገለፁም አንዳንድ የማዳመጥ ዋናና ንኡሳን ክሂሎችን
ለመዳሰስ ሞክረዋል፤በዚህም በአፍ መፈቻ ቓንቓ የማዳመጥ ትምህርት ሊተኮርባቸው በሚገቡ የማዳመጥ
አይነቶች ለይ አትኩረዋል፡፡ ይህም በተማሪዎች የፍላጎት አበባ የተገኘው መረጃ ከሚያሳየው የተማሪዎቹ አፍ
መፍቻ ቋንቃቋ 92.6./. አማርኛ/ለትምህርት የቀረበው ቋንቋ/ከመሆኑ ጋር የሚጣጣምና በይዘቶቹ ላይ የታየ
ጠንካራ ጎን ንወ፡፡

በአጠቃላይ በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቐንቐ መርሀ ትምህርት ውስጥ የማዳመጥ ተገቢውን ትኩረት አላገኘም፡፡
የማዳመጥ ክሂል በአጠቃላይ አላማ፤ በዝርዝር በይዘት ምርጫ ደረጃ ከመናገር ክሂል ጋር ተደርቦ በመቀለብ

2 አሊጎሪ በአማርኛ ዘመናዊ አጫጭር ልቦለዶች

እንዳለጌታ ከበደ

2004

ቴዎድሮስ ገበሬ

አጠቃሎ
አሊጎሪ በአማርኛ ዘመናዊ አጫጭ ልቦለዶች በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ጥናት የአሊጎሪን ምንነትና
ጠቀሜታን፤የአሊጎሪ የሥነ ጽሑፍ ውስጥ ያለውን ቦታ ምን እንደሚመስል እና አሊጎሪ በአማረኛ ቋንቋ በተጸፉ
አጫጭር ልቦለዶች ውስጥ የተሰጠው ቦታ ማሳት አላማ አድርጎ የተነሳ፡፡

ጥናቱ አራት ምዕራፎች አሉት ፡፡ምዕራፍ አንድ መግቢያ የጥናቱ ዳራ የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት ፤የጥናቱ
አላማ ፤የትናቱ ጠቀሜታ፤የጥናቱ ውስን አና የጥናቱ ዘዴ የዛል በምዕራፍ ሁለት ላይ ክለሳ ድርሳን የቀርብ
ሲሆን ፤ይህም በንድፈ ሀሳባዊ ቅኝት ሥር የአሊጎሪን ምንነት ፤ጠቀሜታንና አሊጎ] በአማርኛ ሥነፅሁፍ ሥራ
ሥራዎች ውስጥ ተዳስሰዋል ፡፡ምዕራፍ ሦሰት አልጎሪ በአማርኛ ዘመናዊ አጫጭር ልቦለዶች የሚል ርዕስ
የሚከተል ሲሆን በረዕሱም ደራሲያን የተደረሱከስብሃት ገብረ እግዚአብሔር አምስት ስድስት ሰባት ከተሰው
መፅሐፍ ውስጥ ሁለት ልቦለዶች፤ከአዳም ረታ ማህሌት እና አለንጋና ምስር ከተሰኙ ሁለት መፅሕፍት ውስጥ
ሁለት ልቦለዶች፤ ከአሰአምንው ባረጋ የትሮይ ፈረስ መፅሐፍ ውስጥ አንድ ልቦለድ ፤ከአለማየሁ ገበየሁ የአበሻ
ፊት ውስጥ አንድ ልቦለድ እና ከሚካካኤል ሽፈራው የወፍ ማስፈራሪያ ውስጥ አንድ ልቦለድ በጠቃላጥ ሰባት
አጫጭር ልቦለዶች ከሊጎሪ የሥነ ጽሑፍ ብልሀት አንፃር ተተንትንው ቀርበዋል፡፡

በመሆኑም አጫጭር ልቦለዶቹ በሰውኛ አቀራረብ የተሳሉ ገፀ ባህሬትን በመጠቀም ሀይማኖታዊ ሞራላዊ ፤ሥነ
ምግባራዊአና ፖለቲካዊ መልዕክቶች በአሊጎሪ የሥነጽሑፍ ብልሀት አማካኝነት አቅርበዋል፡፡እንዲሁም በልቦለዶቹ
ውስጥ ትዕምርቶች ምልክቶችና ተነፃፃሪ ዘይቢዎች አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ደራስኑ አንደ አውራ ዶሮ ያሉ
እንስሳትን፤እንደ ወራት ያሉ ረቂቅ ነገሮችን እንደ ቢራቢሮ ያሉ ነፍሳት የሰውኛ ባህሪ ሰጥተው ቀርፀዋቸዋል፡፡ እንደ
ትዕምረት ደግሞ ‹‹ዘፍ›› ዘላለማዊ ህይወትንና ቤተሰብን ፡‹‹ቢራቢሮ››ነፍስን ፤ ‹‹አበባ››ውብ ልጃገረድን
፤‹‹ወንበር›› ዙፋንን እንዲወክሉ ሆነው መቅረፃቸው የጥናቱ ውጤት ያመለክታል፡፡

3 የ‹‹ቶፕዳውን››top-down)የንባብ ማስተማሪያ ሞዴል በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለመዳበር


ያለው ተግባዊነትና

ውጤታማነት ፤በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ የተካሄደ ጥናት

እንግዳ ዘውደዴ

አዲስ አበባ

1992 ዓ.ም

ዶ/ር አርጋ ሀ/ሚካኤል

የዚህ ጥናት ዋና አላማ የ‹‹ቶፕዳውን ››የንባብ ማስተማሪያ ሞዴልን በአማርኛ ቓንቓ እንደ አንድ
አንብቦ መረዳት ችሎታ ማዳበሪያ ዘዴ መጠቀም የሚኖረው ውጤታማነትና ተግባራዊነት መመርመር ነው፡፡
በመሆኑም በቅድሚያ በአሁኑ ወቅት በአማርኛ የንባብ ትምህርት ክፍል-ጊዜ አያገለገለ ያለው የማስተማሪያ ዘዴ
ምን እንደሚ እንደሚመስል የሚመለክት ዳራዊ መረጃ በቅድመ ሙከራ ጥናት ማግኘት፤ቀጥሎም የሙከራ
ምርምር experiemental research)ማካሄድና በሙከራ የተገኘውን ውጤት የሚያጠናክሩ አጋዥ መረጃዎችን ደግሞ
በግሞ በድሀረ ሙከራ ጥናት ማሰባሰብ የጥናት ማሰባሰብ ጥናቱ የአሰራር ዘዴ ነው፡፡

ለቅድመ ሙክራ ጥናት አስፍላጊ የሆኑ መረጃዎች የተጠናቀቁ በአራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች አራት ስድስት የመማሪያ ምድቦች በተካሄዱ ምልከታዎች ነው፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቀት የሚሰው የንባብ
ትምህረት ልምምድ ተማሪዎችን እንደማያሳትፍ ፤አብዛኛዎቹ ትምህርታዊ ተግባራት በመምህራኑ እንደሚከነወን
ተማሪዎች በቂ ልምምድ እንደማያደርጉ ለማርጋገጥ ተላል፡፡
የተጠቀሰው ዳራዊ መረጃ ከተገኝ በኀላ የጥናቱ ዋና አካል የሆነውን የሙከራ ምርምር ለማካሄድ 160 ተማሪዎች
የሚገኙባቸው ሁለት የመማሪያ ምድቦችን በእጣ በመምረጥ የቁጥጥርና የሙከራ ምድቦች (control and
experimental groups)አደራጅቶ የሙክራ ምድቡን የ‹‹ቶፕዳውን››የንባብ ትምህርት አቀራረብ መመሪያ በሚዘው
መሰረት የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ በተለመደው ዘዴ እንዲማሩ ተደረገ ፡፡ልምምዱ ከመጀመሩ በፊት ለሁለት
ቡድኖች ተመሳሳይ ቅድመ ትምህረት ፈተና (pre-test)ተሰጥቶ ውጤቱ በ(ቴስት)(t-ste) ከተሰላ በኀላ በ 0.05
የጉልሀነት ደረጃ (significance level) አና በ 158 የነጻነት ደረጃ (degree of fereedom)0.260 ከ t-ሰንጠረዥ ዋጋ 1.960
ያነሰ ሆኖ በመገኘቱ ፤ሁለቱ ቡድኖቹ የችሎታ መበላለጥ እንደማይታይባቸውና ተመጣጣኝ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡
ለሙከራ አላማ ስኬትም አጥኚው በድሀረ ልምምድ የፈተና ውጤት መሰረት በቁጥጥሩና በሙከራው ቡድን
መካከል የችሎታ መበላልጥ አንደማይታባቸውና ተመመጣጣኝ መሆናችወ ተረጋገጠ፡፡ ለሙከራው ቡድን መከላከል
የችሎታ መበላለጥ አይታይም የሚል ባዶ መላምት(ho)አና በድሀረ ልምምድ የፈተና ውጤት መሰረት መሰረት
በቁጥጥሩና በሙከራው ቡድን መካከል የችሎታ መበላለጥ ይኖራል የሚል አማራጭ መላምት (HI)ይዞ ተነሳ፡፡
ጥናቱ ለስድስት ሳምንታት የተካሔደ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በቅድመ ትምህርት ፈትና ውጤት ተመሳሰይ
ችሎታ ስለነበራችው ተመሳሳይ ያለውን ትምህርት የዘት ተከታትለዋል ፡፡የሙክራው ግዜ እንደተጠናቀቀም
ለሁለቱም ቡድኖች ተመሳሳይ ድህረ ልምምድ ፈተና(Poste –test) ተሰጥቶአቸው ውጤቱ ከፍ በሎ በተጠቀሰው
የአስታሰቲክ ስልት ‹two-tailed)ተሰጥአችወ ውጤቱ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው የእሰታትስቲክስ ስልት ‘’two-
tailed’’ ከተሰላ በኃላ በ 005 የጉልሀነት ደረጃ በ 158 የነጻነት የተገኘው ውጤት 3.173 ከ t-ሰንጠረዥ ዋጋ 1.960
የበለጠ በመሆኑ የሙከራው ቡድን የችሎታ ብልጫእንዳመጣ የሚያረጋግጥ በመሆኑ አጥኚው ይዞት የተነሳው ባዶ
መላ-ምት ተቀባይነት አላግኘም ፡፡አንደዚሁም የድህረ ሙከራ መረጃዎችን ለማግኘት
4 የ 11 ኛክፍል ተማሪዎ ሀሳባቸውን በጽሁፍ የመግለፅ ችሎታ
ክፍሌ ሐብተማርያም

ታደለ አዳሙ(ዶ/ር)
1986

የጥናቱ አበይ አላማ የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች ሐሳባቸውን በፅሑፍ አቀናብረው ለመግለፅ ያላቸውን ችሎታ
ማጥናት ነው፡፡ለዚህም የተመረጡት የመረጃ ምንጮች የጥሁፍ መጠይቅና የችሎታ መለኪያ ፍትና ሲሆኑ፤
ለሚመለከታቸው መምህራን መጠይቅ በማስሞላትና ለተጠኚዎቹ ፈተና በመስጠት መረጃዎች ተሰብስበዋል
የናሙና መምህራኑ ተመረጡት በጥናቱ ከታቀፉት ሃያ ት/ቤቶች በአስራ ሁለቱ 11 ኛ ክፍል አማረኛ
የሚያስተምሩት መምህራንና ተቀዳሚ መምህራን በሙሉ መጠይቁን እንዲሞሉ በማድረግ
ነው፡፡
5 ‹‹የበሪ ሀገረ-ሰባዊ እምነት በደቡብ እሪ ወረዳ በዎባመር አካባቢ.››
ኮማንደር መሐመድ
ጥቅምት 2005 ዓ.ም
ዘሪሁን አስፋው
ባይለየኝ ጣሰው

በደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ብሔረሰብ ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ ሀገረ-ሰባዊ እምነቶችን ይከተላል ፡፡የኦሪ
ብሔረሰብ ሀገርሰባዊ አምነቱ አድርጎ ከሚከተላቸው በርካታ አምነቶች ውስጥ የበሪ እምነት አጅግ ይዘወተራል
፡፡ ‹‹በሪ››ሴት አማልክት ስትሆን በወንድ አማልክትነት ከሚታመኑት ‹‹ሳቢ›› እና ‹‹ጸይሲ›› የበለጠ ዘወትር
አምልኮ ይደረግለታል ፡፡በየክስተቱና በየአጋጣሚው የበሪ ስም ይነሳል ፤ ለበሪ አምልኮ ይፈጸምለታል ፡፡ከ 1976 ዓ.ም
ወዲህ በሌሎች ርዕሶች ስር የበሪን አምነት በጥቂቱ ጠቅሰው ካለፉት አንዳንድ ጥናቶች በስተቀር በእምነቱ ላይ
አቢይ ትኩርት አድርጎ የተካሔደ ጥናት አላገጠመኝም፡፡

6 . ለኢትዮጵያ ስነፅሑፍና ፎክሎር ኤም.ኤ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ


ወርቅነሽ ቱፋ
ሚያዚያ 2004 ዓ.ም
ዘሪሁን ቱፋ
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተመረጡ ሶስት መፅሕፍት ውስጥ ማለትም በፀሐይ መላኩ ‹‹እመምኔት››
በየዝና ወርቁ ‹‹የደራሲዋ ፋይል ›› እንዲሁም በእነዬ ሺበሺ ‹‹የገቦ ፍሬ›› ረጅም ልቦለዶች ውስጥ ሴት እና
ወንድ ገፀባህሪያት የተሳሉበትን መንገድ መመርመር ፤ አካላዊ እና ህሊናዊ መልካቸው ምን እደሚመስል ማሳየት
እንዲሁም በሶስቱ ረጅም ልቦለዶች ውስጥ ያሉትን ተመሳስሎዎች እና ልዩነቶች መመርመርና ማሳት ነው፡፡

7. በማስተማሪያ ቋንቋ ፤ ቦኦሮሚያ ክልል ለአራተኛ ክፍል የተዘጋጀ ያማርኛ የንባብ ክሂል ትምህርት አቀራረብ
ተገቢነት
ወንድአጥ` ደነቀ
መኮንን ዲሳሳ
ሰኔ 1993
ይህ ጥናት በኦሮሚያ ክልል አማርኛ መማሪያ ቋንቋቸው ለሆኑ ያራተ የአራትኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጥ
የንባብ ክሂል ትምህርት አቀራረብ ፤ለዚያው ደረጃ የቀረበው የአካባቢ ሳይንስ ጥምህርት የሚጠየቀውን የንባብ
ከሂል ለማዳበር ምን ያህል በቃት አለው; ክሂሉን በተሻለ መልኩ ለማዳበር የንባብ ትምህርቱ እንዴት ቢቀርብ
ይሻላል ; የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ፤ ገላጭ (descriptive)እና ሙከራዊ (Experimental)የጥናት ዘዴን
በመጠቀም የትምህርቱን አቀራረብ የገመገመና አማረጭ የትምህረት አቀራረብ በማዘገጀት በሙከራ የፈተሸ
ጥናት ነው፡፡
ለአራተኛ ረፍል ተማሪዎች የቀረበው የአማርኛ የንባብ ጥምህርት አቀራርብ ክሂሉን ለማዳበር ያለው ብቃት

8. የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሀዲይኛ የሆነ የአስራ ሁለትኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማረኛ ቋንቋ ትምህርት የላቸውን
አመለካከትና የፈተና ውጤታቸው ዝምድና
ወንድወሰን በየነ
ግንቦት 15/1989 ዓ.ም
ደጀኔ ለታ
የዚህ ጥናት ዋና አላማ ተማሪዎች ለአመረኛ ቋንቋና ትምህርት ያላቸው አመለካከት ከፈተና ውጤታቸው
ጋር ያለውን ዝምድና መመርመር ነው ፡፡ ተጠንዎች በሀዲያ ዞን በሚገኙ አራት ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች /ዋቸሞ የካቲት ሞርሲጦ ጊምቢቹ/የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሀዲይኛ የሆነ የአስራ ሁለተኛ
ክፍል ተማሪዎች ናችወ፡፡

9 ’ከ 2001-2004 ዓ.ም የተሰጡ የ 10 ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ አገር አቀፍ እና ሞዴል ፈተናዎች የይዘትና
አቀራረብ ንጽጽር በጋምቤላ ክልል በሁለት የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መነሻነት
ወንድማገኝ አደም
ሰኔ/2005 ዓ.ም
አማኑኤል ገብሩ
ይህ ጥናት ከ 2001-2004 ዓ.ም በተሰጡ የጋምቤላ ክልል ሁለት የ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤቶች የ 10 ኛ ክፍል አማረኛ
ቋንቋ የክፍል ሞዴል ፈተናዎችን እና የአገር-አቀፍ ፈተናዎችን አቀራረቦቻቸውንና ይዘቶቻችዉን ማነፃፀር
ዓይነተኛ አላማው ነው ፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ እና መጠናዊ የምርምር ዘዴዎችን በመጠቀም መሰረታዊ ጥያቄዎችን
ተንተረሶ ከሰነድ ምርመራው የተገኙ መረጃዎችን በክለሳ ድርሳናት
ውስጥ በተጠቀሱ የምሁራን ሀሳቦች ጥንካሬ እንዲገኙ በማድረግ ለመተንተን ሞክሯል፡፡በሁለት የፈተና ዓይነቶች
መካክል ያሉ የተዛምዶ መጠኖችም በፒርሰን የተዛምዶ መጠን መወሰኛ ቀመር እየተሰሉ ተገልፀዋል ፡፡

10. የሽመናና የጥልፍ ትውፊት በአክሱም


ዋልተንጉስ መኮንን
ዘሪሁን አስፋው
ተክለሃይማኖት ኀ/ስላሴ
ጥር 2000 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በቁሳዊ ባህል ላይ ጥልቅ ምርምር ያደረጉ የፎክሎር ባለሙያዎች ፤ ቁሳዊ ባህል የሰው ልጅ ውስጣዊ መንፈስ
በቁሶች ቅርፅ ይዘትና
ጠባይ ግዝፈት የሚነሳ ጥበብ እንደሆነ ይኖራል ፡፡ቁሳዊ ባህል በተፈጥሮና በባህል ፤ ብሎም በሰው ልጅ
መካከል ያለን ዝምድና
¾ ምንረዳበት መንገድ ንወ፡፡ የቁሶቹች አመራረትም ሆነ አጠቃቀም ከታሪክ ከማህበረ ባህላዊና ከስነልቦና
ሁኔታዎች ጋር አብሮ የበቀለና ስር የሰደደ ሂደት በመሆኑ የሚመረቱት ቁሶች ሌሎችን የመረጃ ምንጮች
ለመተንተን እንደ ደጋፊ ማስረጃ በመሆንም ያገለግላሉ ፡፡ የአንድን ማህበራዊ ስርአት ሆነ አስተሳሰብ
በማንፀባረቅ ጥልቅ የሆነ ትርጉም ይሰጣሉ፡፡

11 የሀድያ ብሔረሰብ ባህላዊ ጋብቻና የሰርግ ስነስርአት


ዝናሽ ሰለሞን
2004 አዲስ አበባ
ዘሪሁን አስፋው
በሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዶዋቾ ወረዳ በሚፈጸው ባህላዊ ጋብቻ እና የሰርግ ስነስርአት ክዋኔ ላይ ከዚህ በፊት
እኔ እስከማውቀው ድረስ ጥናት አልተደረገም ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናት በወረደው የሚፈፀመውን ባህላዊ ጋብቻና
የሠርግ ስነስርአት ክዋኔን ማሳየትና በእያንዳንዱ ስርአት ውስጥ ያሉ ተግባራትን ምንነትና ፋይዳን መግለፅ ዋነኛ
አላማ ያደረገ ነው፡፡ የጥናቱን አላማ ከግብ ለማድረስም አውድን መሰረት ያደረገ ምልከታ ቃለ መጠይቅና ቡድን
ተኮር ውይይት በመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴነት ያገለገሉ ሲሆን በነዚያህ ዘዴ የተሰበሰቡ መረጃዎች ክዋኔን መሰረት
ባደረገ ዘዴ

12 u9— ክፍል የአማርኛ መማሪያ መፅሐፍ ውስጥ አንብቦ የመዳት ትምህርት አቀራረብ ግምገማ
የሺጥላ ምንይልሸዋ
ሰኔ 2000 ዓ.ም
ኑሩ መሐመድ (ደ/ር)
ይህ ጥናት የንባብ ትምህርት ዋነኛ አካል የሆነው አንብቦ የመረዳት ጥምህርት በዘጠነኛ ክፍል የአማረኛ ቋንቋ
መማረያ መፅሐፍ ውስጥ አንብቦ የመረዳትን ችሎታ ለማዳበር በሚያግዝ መንገድ መቅረቡን በመፈተሽ ላይ
የሚያተኩር ነው፡፡ምንባቦቹ የተማሪዎችን ፍላጎት ማሟላትና አለማሟላታችወን ፤የምንባቦች ይዘቶች
ለተማሪዎቹ ያላችወን ግልፅነትና ተስማሚነት አንብቦ የመረዳት መልመጃዎች ባህር ወዘተ ላይ ትኩረት
ተደርጓል፡፡

13 .በኦሮምኛ ቋንቋ አፋችውን የፈቱ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች በኣማርኛ ቋንቋ
አንብቦ የመረዳት ክሂላቸውን ለማዳበር ተራክቧዊ የንባንብ ክሂል ማስተማሪያ ሞዴልን በክፍል ውስጥ ተጠቅሞ
ማስተማር ያለው አስተዋጽኦ

የኔስው ደሴ
ተደለ አዳሙ(ዶ/ር)
ግንነቦት 1990 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ንባብን ለብዙ ተግባራት እናውለዋለን፡፡ ንባብ እውቀትን ለማግኘት አዲስ የተከናወኑ ክስተቶችን ለማወቅም ሆነ
ጊዜን ለማሳለፍ እንገለገልበታለን ፡፡ንባብ ካለው ጠቀሜታ አንጻር ክሂሉን በመደበኛ ሁኔታ በትምህርት ቤት
ማዳበር ያስፈልጋል ፡፡የዚህ ጥናት ዋና ዓላማም በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎችን በአማርኛ ቋንቋ
አንብቦ የመረዳት ክሂላቸውን ለማዳበር ከንባብ ክሂል ማስተማሪያ ሞዴል ውስጥ ተራክባዊ የንባብ ክሂል
ማስተማሪያ ሞዴል አስተዋፅኦ ይኖረዋልን የሚለውን ጥያቄ በፍትነታዊ የምርምር ዘዴ ለመፈተሽ ሲባል አልሞ
የተነሳ ነው፡፡

You might also like