You are on page 1of 170

አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አማርኛ እንደ መጀመሪያ ቋንቋ

የመምህር መምሪያመጽሐፍ

፲ኛክፍል

በአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶበኦሮሚያ


ብ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ የተስማማ

አስማምቶ አዘጋጆች፡-

ግሩም ጥበቡ (M.A)

ታምሩ ገለታ (M.Ed)

ገምጋሚዎች፡- በላይነሽ ደነቀ (Phd)

ታሪኩ ነገሰ (Phd)

ጥራትተቆጣጣሪ

ይልፋሸዋ ጥላሁን (BEd)

ግራፊክስ
ታደሰ ድንቁ

i
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ማውጫ
መግቢያ ................................................................................................................i

ምዕራፍ አንድ

ቋንቋና ማህበረሰብ .............................................................................................. 1

ምዕራፍ ሁለት

ባህላዊ ጋብቻ .................................................................................................... 18

ምዕራፍ ሶስት

ሴቶችና ልማት ................................................................................................. 32

ምዕራፍ አራት

በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት ........................................................................... 46

ምዕራፍአምስት

ቋንቋዊ ለዛ........................................................................................................ 60

ምዕራፍ ስድስት

የታላላቆች ሚና ................................................................................................ 82

ምዕራፍ ሰባት

ረጅም ልቦለድ .................................................................................................. 94

ምዕራፍ ስምንት

መገናኛ ብዙኀን .............................................................................................. 108

ምዕራፍ ዘጠኝ

ሥራ ፈጠራ .................................................................................................... 122

ii
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መግቢያ

ይህ ለዘጠነኛ ክፍል ማስተማሪያነት የተዘጋጀው የመምህር መምሪያ’ በኦሮሚያ


አማርኛን እንደመጀመሪያ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎችን የሚያስተምሩ መምህራን
አጠቃላይ የክፍል ውስጡን የመማር ማስተማር ሂደት እንዲመሩበት ታስቦ ነው።
መምሪያው መነሻ ያደረገው በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን አዲስ
መርሃትምህርት እና ለዚሁ ደረጃ ለተማሪዎች ተብሎ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
የተዘጋጀውን መማሪያ መፅሐፍ መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም መምሪያው
ተማሪዎች እንዲሟሯቸው የተቀረፁትን ይዘቶች፣ ይዘቶቹን መሰረት አድርገውም
የተሰናዱትን ተግባራትና መልመጃዎች አሳታፊ በሆነ መልኩ በመማሪያ ክፍል
ውስጥና ከመማሪያ ክፍል ውጪ እየተገበሩ የትምህርቱን ግብ ማሳካት
የሚቻልባቸውን ሁኔታዎችና አካሄዶችን በተመለከተ አጠቃላይነት ያለው ጥቆማ
ለመምህር አቅርቧል። ከዚህም ሌላ የክፍል አደረጃጀትና አስተዳደሩ ምን መምሰል
እንዳለበት፣ ምዘናው እንዴት ሊከናወን እንደሚችልና መሰረታዊ የቋንቋ ክህሎቱቹ
እንዴት መቀናጀት እንዳለባቸው መነሻ ሀሳብ ሰጥቷል። እነዚህን ጥቆማዎችና መነሻ
ሀሳቦችም መምህራን የሚያገኟቸውን ተሞክሮዎች እና አዳዲስ አሰራሮችን
እየቀመሩ በመጠቀም እያጎለበቷቸው የሚጠበቀውን ውጤት ተማሪዎቻቸው
እንዲያሳኩ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል። ለዚህም መምህራን
የየአካባቢያቸውን፣ የየክፍላቸውንና የየተማሪዎቻቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት
ውስጥ በማስገባት መምሪያውን ተግባራዊ ያደርጉታል ተብሎ ይጠበቃል።

የመምሪያው አደረጃጀትና ይዘት

ይህ የመምህር መምሪያ ከላይ እንደተገለፀው የተማሪ መፅሐፍን በመንተራስ


የተዘጋጀ በመሆኑ የይዘት አደረጃጀቱም ይህንኑ የተከተለ ነው። ስለሆነም በተማሪ
መፅሐፍ ውስጥ የተቀመጡት ምእራፎች በቅደም ተከተል ቀርበውበታል።
በየምዕራፉ ለሚከናወኑ የማዳመጥ ተግባራት የተዘጋጁት ግብአቶችም በመምህር
መምሪያው ተካትተዋል። አስፈላጊ ይሆናሉ ተብለው በታሰቡ ይዘቶች ላይም
ተጨማሪ ማስታወሻዎች የተሰጡ ሲሆን፣ በየደረጃው ለቀረቡ በናሙናነት ለተመረጡ
iii
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መልመጃ ጥያቄዎች ምላሾችና ለየተግባራቱ አፈጻጸም የሚረዱ አማራጭ ሀሳቦች


እንዲካተቱበት ሆኗል። እነዚህ ምላሾችና ሀሳቦች የቀረቡትም በቋንቋ ትምህርቱ
አሰጣጥ ወቅት ወጥነት ያለው አካሄድ እንዲኖር ታስቦ ሲሆን፣ መምህርና ተማሪዎቹ
እንደየ ሁኔታው (አውዱ) የሚያቀርቧቸው ተጨማሪ ምላሾችና አካሄዶችም ከግምት
የሚገቡ ናቸው።

ልዩ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦች

 የየትኛውም ክፍለ ጊዜ ትምህርት ሲቀርብ አራቱን የቋንቋ መሠረታዊ


ክሂሎች በተመጣጠነ (በተቀናጀ) መልኩ ያካተተ ይሆናል።
 የትምህርቱ አቀራረብ አሳታፊ፣ ተግባቦታዊና ትብብራዊ የማስተማር ዘዴን
መርህ የተከተለ መሆን ይገባዋል።
 የልስራ፣ እንስራ ስሩ የትምህርት አቀራረብ ሁልጊዜም እንዲተገበር
ይመከራል፤
 ሁሉም ተማሪዎች ከተመሳሳይ ዳራ ያልመጡ ወይም ተመሳሳይ ልምድ
የሌላቸው ስለሚሆን በመማር ወቅት የሚቸገሩ ተማሪዎችን ቀስ በቀስ
የማብቃት ስልትን (scaffolding) በመተግበር ማገዝ ይገባል።
 ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችና ላቅ ያለ አፈፃፀም የሚያሳዩ ተማሪዎች
ሲያጋጥሙንም ችሎታዎቻቸውን ለማዝለቅ ማበረታትና ተጨማሪ
ተግባራትን እያዘጋጀን በመምጣት ማትጋት ይገባል።
 በክፍል ተሳትፎ ወቅት ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድን መከተል ይገባናል
(የባህል፣ የሀይማኖት፣ የጾታ፣ የአካል ጉዳተኝነት ወዘተ ጉዳዮች
አካታችነትን ከግምት ማስገባት)
ተማሪዎቹ በሚማሩበት አካባቢ በሌላ መልኩ የሚተረጎም ቃል ወይም አገላለጽ
ወይም ምስል ሲያጋጥም (ታቡ የሆነ) በሌላ መተካት ያስፈልጋል።

iv
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
ቋንቋና ማህበረሰብ

(የክፍለጊዜ ብዛት 8)

የሚጠበቁ ውጤቶች፡-
ተማሪዎች ይህንን ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ፡-

መረጃዎችን በማዳመጥ ይለያሉ።

ውይይት በማድረግየተገኘውን ውጤት በቃል ያንጸባርቃሉ።

ሰፊ ርዕሰ-ጉዳይን የያዘ ጽሁፍ በማንበብ ተደራሲያንን ይለያሉ።

ገላጭ ቃላትን ለይተው ያመለክታሉ።

በጽሁፋችሁ ውስጥ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ይጠቀማሉ።

በደረጃቸው ድርሰት ይጽፋሉ።

ጥምር ቃላትን በመመስረት በዓረፍተነገር ውስጥ ይጠቀማሉ።

የማስተማሪያ ዘዴ

 የተለያዩ የማዳመጥ ትምህርት ክንውኖችን ተግባር ላይ በማዋል


ትምህርቱን ማቅረብ
 የአንብቦ መረዳት ማስተማሪያ ስልቶችን በመጠቀም የአንብቦ መረዳት
ጥያቄዎችን እንዲሰሩ ማበረታታት
 ቀስቃሽ ጥያቄዎችን በማቅረብ እንዲወያዩ ማድረግ
 ምሳሌ አቅርቦ ተዘውታሪ ቃላትን በአውድ ውስጥ እንዲጠቀሙ ማትጋት
 ተዘበራርቀው የቀረቡትን ዓረፍተነገሮችን ምሳሌ በመስጠት
ቅደምተከተላቸውን አስተካክለው አንቀጽ እንዲጽፉ ማገዝ

1
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

 የቋንቋውን ስርዓት ተከትለው ድርሰት እንዲጽፉ ማንቃት


 ስለድርሰት ምንነት ገለጻ ማቅረብና ምሳሌ መስጠት ያንንም መሰረት
አድርገው ድርሰት እንዲጽፉ ማገዝ
 ምሳሌ በማቅረብ የጥምር ቃላት አመሰራረትን እንዲለዩማድረግ
 ሰዋስዋዊ ትክክለኛነትን ጠብቀው መጻፋቸውን ማረጋገጥ
 ጠቃሚና ትርጉም ያለው ግብረ መልስ መስጠት

ማሳሰቢያ

1. ሁሉም ክፍለጊዜዎች የመግቢያ (ማስተዋወቂያ)፣ የአቅርቦት እና የመደምደሚያ


(ክለሳ) ክፍል ያላቸው መሆኑን፣

2. በሁሉም ክፍለጊዜዎች ጅማሮ ወቅት ያለፈውን ክፍለጊዜ ትምህርት ማስታወስና


የክለሳ ጥያቄዎች ወይም ነጥቦች ማቅረብ ሊታለፍ እንደማይገባ፣

3. የምንከተለው የትምህርት ሥርዓት የአካቶ ትምህርትን መርህ የሚከተል በመሆኑ


በክፍላችን ውስጥ የሚቀርበውን ትምህርት በተለያየ መንገድ ለመማር የሚሹ
ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ተማሪዎች ስለሚኖሩ፤ ትምህርቱ ሁሉንም
ተማሪዎቻችንን ያማከለ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ያለብን ስለመሆኑ፣

4. የትምህርት ይዘቶቻንን ተጨባጭ በሆነ መንገድ ለማቅረብ አጋዥ የትምህርት


መሳሪያዎችንና መርጃ መሳሪያዎችን እየመረጥንና እያዘጋጀን በአግባቡ
መጠቀም እንደሚኖርብን፣

5. ከማንኛውም አድልዎ የጸዳ ሀገር በቀል ዕውቀትን መሠረት ያደረገ ትምህርትና


የአቀራረብ መርህን መከተል እንዳለብን ወዘተ መገንዘብ ይኖርብናል።

2
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አንድ፡ማዳመጥ

ርዕስ፡ ቋንቋና ጽሕፈት

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 በጥሞናአዳምጠው ምላሽይሰጣሉ።
ቅድመ ማዳመጥ

በትምህርት አንድ ስር የተማሪዎችን የማዳመጥ ተነሳሽነት የሚጨምሩና የቀረበውን


ይዘት ከቀደመ ዕውቀታቸው ጋር እንዲያዛምዱ የሚረዱ የተለያዩ ጥያቄዎች
ቀርበዋል። እባክዎ መምህር ተማሪዎቹ እነዚህን ጥያቄዎች እንዲመልሱ
ያበረታቷቸው። በመቀጠልም ወደ ዋናው የማዳመጥ ተግባር ይሸጋገሩ። በመጀመሪያ
የቀረበውን ምንባብ ሁለት ጊዜ በተለያየ ፍጥነት ያንብቡላቸው። በመጀመሪያው
ንባብ አጠቃላይ ሀሳብ ላይ በሁለተኛው ንባብ ዝርዝር ሀሳቦች ላይ ትኩረት ሰጥተው
እንዲያዳምጡ ይንገሯቸው።

መምህርትምህርቱን ሲያቀርቡ(መስማት የተሳናቸውን እና ማየት የተሳናቸውን


እንዲሁም ሌሎችን ማካተትዎን አይዘንጉ።)የማዳመጡንፅሑፍ ከማንበብዎት
በፊት ተማሪዎችን የምዕራፉን ዓላማ እንዲረዱ ጊዜ ይስጧቸው፤

ቅድመማዳመጥ

በቅድመ ማዳመጥ ላይ የሰፈሩትን ጥያቄዎች (የቃላት ዓውድ) በመጠየቅ ስለ ቋንቋና


ጽህፈት የሚያውቁትን እንዲናገሩና የማያውቁትን እንዲገምቱ ያድርጓቸው።
 ቋንቋ ድምጻዊና አንደበታዊ የሰው ልጅ መግባቢያ መሆኑን
ይጠቁሟቸው።
 ስለቋንቋ አጀማመር ሊቃውንት የተለያዩ መላምቶችን መሰንዘራቸውንና
በዚህ ምንባብ ሁለቱ በዋነኛነት መጠቀሳቸውን ይጠቁሟቸው።
 ቋንቋና ጽሕፈት ስላላቸው ግንኙነት ግምታቸውን ለጓደኞቻቸው
እንዲያስረዱ ያድርጉ።
3
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

 ተማሪዎች ምላሽ በሚሰጡበት ጊዜ ያበረታቷቸው፤ ቀጥለውም የቋንቋ


ምንነትና አጀማመር እንዲሁም የጽህፈት የሽግግር ደረጃዎችን ለማንበብ
እንዲዘጋጁ ያበረታቷቸው። ይህንንም ያረጋግጡ።
 ቀጥለውም ቋንቋና ጽህፈት የሚለውን ምንባብ በተረጋጋ መልኩ ሁለት ጊዜ
ያንብቡላቸው።ሲነበብላቸውም በተረጋጋ መልኩ ማስታወሻ ለመያዝ
እንዲሞክሩ ይጠቁሟቸው።ከዚያ በፊት ግን በሶስት ደቂቃ የማዳመጥ ጊዜ
እና አዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን እንዲያነቧቸው ያድርጉ።በመጨረሻም
ለሁሉም በሚሰማ የድምፅ ምጣኔ ምንባቡን ማንበብ ይጀምሩ (በአማራጭነት
ቀድመው በሌላ ሰው በማስነበብ ድምጽ ቀርጸው ሊያቀርቡላቸውም ይችላሉ
(ለምሳሌ በሞባይል ስልክዎ)።

በማንበብ ሂደት ወቅት (በድጋሚ ሲያነቡላቸው) የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎቹን


እያሰሩ ይሂዱ በተቻለ መጠን ተማሪዎቹ በትኩረት እንዲከታቱሉና እንዲሳተፉ
ያበረታቷቸው።
የማዳመጥ ትምህርት ምንባብ

ቋንቋናጽሕፈት

ቋንቋ ድምፆች በስርዓት ተዋቅረው የሚመሰርቱት ድምጻዊና አንደበታዊ የሰው ልጅ


መግባቢያ ነው።ቋንቋ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ፣አንዱ ከሌላው ጋር ሀሳብ
የሚለዋወጥበት የመግባቢያ መሳሪያ ነው። ይህ ሰብአዊ መግባቢያ መቼና እንዴት
ተፈጥሮ አገልግሎት ላይ እንደዋለ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስረቶ ለማወቅ
ያዳግታል። ይሁን እንጂ በጥናት ላይ የተመሰረተው የምሁራን መላምት፣ ጊዜው
ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት እንደሆነ ያስረዳል። በመሆኑም የስነ-ሰብ ተመራማሪዎች
የቋንቋ ጥንተ አመጣጥ መላምትን ጠቅለል አድርገው በሁለት ይከፍሉታል። እነሱም
የሐሳባውያንና የቁስ አካላውያን የቋንቋ አጀማመር መላምት የተሰኙ ሲሆኑ
ሐሳባውያን ቋንቋ ከየት መጣ ተብለው ሲጠየቁ ‹‹ቋንቋ ከመለኮት ወይም ከፈጣሪ
ለሰው ልጅ የተሰጠ ፀጋ ነው›› ብለው ይመልሳሉ። ቁስ አካላውያን ደግሞ ‹‹ቋንቋ

4
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የሰው ልጆች ስራን ለመስራትና እርስ በርስ ለመግባባት ካላቸው ፅኑ ፍላጎት አንፃር
የተፈጠረ የአዝጋሚ ለውጥ ውጤት ነው›› ብለው ያምናሉ።

1. ሰብአዊ የሆነ ፍጡር ሁሉ ሊግባባበት የሚችል መሳሪያ _______ ነው።


2.የቋንቋ የትመጣነት መላምቶች__________ እና_____________ናቸው።

ጽህፈት የንግግር ወኪል ሲሆን ለሰው ልጅ የቀደሙ አባቶቹን ታሪክ፣ የራሱን ቅርስና
ባህል ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲሁም ለገዛ ህልውናው ልማት መሰረት
ለመጣል ብሎምበተፈጥሮ ላይ ለመሰልጠን ትልቅ ሚና ፈጥሮለታል። ይሁን እንጂ
ጽህፈት መቼ፣ የትናእንዴት እንደተፈጠረ የተሟላ ምላሽ ማግኘት ያስቸግራል።
ፅህፈት በትክክል የፈለቀበትቦታ እዚህ ነው ባይባልም ዛሬ ካለበት ደረጃ ለመድረስ
በየዘመናቱ አራት የተለያዩ ጉልህየዕድገት ደረጃዎችን ተሸጋግሯል። እነዚህም
ስዕላዊ፣ ቃላዊ፣ ቀለማዊና ፊደላዊ የአፃፃፍ ዘዴዎች ናቸው።

የመጀመሪያው የአፃፃፍ ዘዴ ስዕላዊ የአፃፃፍ ዘዴ ሲሆን በግምት ከዛሬ 5ሺህ ዓመት


በፊት ሳይጀመር እንዳልቀረ ለሚገመተውና እስከ ዛሬ ለዘለቀው ስርዓተ ጽህፈት
መነሻ መሰረት ነበር። በዚህ ዘዴ አንባቢው ከሰዓሊው ጋር አንድ ዓይነት ቋንቋ
ባይናገርም ስዕሉን ተመልክቶ መልዕክቱን ለመረዳት አያዳግተውም።

ሁለተኛው ደግሞ ቃላዊ የአፃፃፍ ዘዴ ነው። ዘዴው ለመጀመሪያ ጊዜ ቋንቋና ጽህፈት


ቀጥተኛ ግንኙነት ያሳዩበት ነው።አንድ ምልክት በቋንቋው ውስጥ የሚገኝ አንድ
ቃልን ወክሎ በአገልግሎት ላይ የዋለ ነው። የአረብኛ ቋንቋ ቁጥሮች ለዚህ ምሳሌ
ሲሆኑ የቋንቋውን ስርዓተ ጽህፈት ለመማር ከባድ፣በመጠቀም ወቅትም ውስብስብ
ነው።

ሶስተኛው ቀለማዊ የአፃፃፍ ዘዴ በአመዛኙ እያንዳንዱ ቀለም ባንድ ምልክት ሲገለፅ፣


ቃሉ ደግሞ በተወሰኑ ቀለማዊ ምልክቶች ይገለፃል። የሀገራችን የሴም ቋንቋዎች
የሚጠቀሙበት ስርዓት ለዚህ ዘዴ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።

5
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

3. ለመማር ከባድ፣ ለመጠቀም ውስብስብ የሆነ የአፃፃፍ ስርዓት ___ ነው።

አራተኛው ፊደላዊ የአፃፃፍ ዘዴ ሲሆን በጽህፈት ታሪክ ውስጥ የቅርብ የሚሰኝ


ግኝት ነው።በፊደላዊ አጻጻፍ እያንዳንዱ ምልክት የሚወክለው አንድ ነጠላ ድምጽን
ነው። ለዚህ ስልት ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው እንግሊዘኛ ቋንቋ የሚጠቀምበት የጽህፈት
ስርዓት ነው።

(ጌታቸው በለጠ፤ የጥበባት ጉባዔ፣ 2004 ዓ.ም ተሻሽሎየቀረበ)

መምህር ምንባቡን ደግመው ካነበቡላቸው በኋላ ተማሪዎችዎ ባዳመጡት ምንባብ


መሰረት የድህረ ምንባብ ጥያቄዎቹን እንዲመልሱ ያበረታቷቸው።

ምዘና

• በቋንቋና ጽሕፈት ምንነት እንዲሁም አጀማመር ላይ ተወያይተው


የተጠናከረ ሐሳብ ላይ መድረሳቸውን በጥያቄና መልስ መገምገም፣
• ካዳመጡትፅሁፍ ውስጥ ያገኙትን መረጃ ለሌሎች እንዲያካፍሉመጠየቅ፣

• ያዳመጡትን በትክክለኛ ቋንቋእና በልበሙሉነትመግለጻቸውን መመዘን፣

(ማሳሰቢያ፡-በማዳመጥ ክሂል ስር ለቀረቡት መልመጃዎች (ጥያቄዎች) መልሶቹ


በዚሁ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ተሰጥተዋል)

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

• ዝግጅት አድርገው ውይይት ማካሄድ ይችላሉ።

• ቃላዊ ዘገባ ያቀርባሉ።


በዚህ ክፍለ ጊዜ የቀረበው ትምህርት ተማሪዎች የውይይት አካሄድ መሰረታዊ
ነጥቦችን ተረድተው የውይይት ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጠበቃል። በመሆኑም መምህር

6
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በቅድሚያ ተማሪዎችዎ ስለውይይት ምንነትና አካሄድ የሚያውቁትን እንዲናገሩ


ይጋብዟቸው። አያይዘውም ውይይት የዘመናዊ አለም መገለጫ እንደሆነና ሰዎች
የመወያየት ባህልን እያጎለበቱ በሄዱ ቁጥር ከግጭት የራቀ ማህበረሰብን ለመገንባት
የሚችሉ መሆኑን በአጽንዖት ያንሱላቸው።

ቀጣዩ ተግባር በተማሪዎቹ መጽሐፍ ላይ ውይይትን አስመልክቶ የቀረበውን ጽሑፍ


በማስታወሻ መልክ በደብተራቸው ላይ እንዲጽፉ ማድረግ ነው።በማስከተልም
በእያንዳንዱ ነጥብ (የውይይት ምንነት፣ ዝግጀት፣ አቀራረብ) ዙሪያ ገለጻ በማቅረብ
ግንዛቤ ማስያዝ ይገባል።

በመጨረሻም ግንዛቤ የያዙባቸውን ነጥቦች ወደ ተግባር ለመቀየር


እንዲችሉናዝግጅት አድርገው በውይይት የመሳተፍ እድል እንዲያገኙበአነስተኛ
ቡድን በማደራጀት በተግባር አንድስር በቀረቡት ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት
እንዲያደርጉ መመሪያ ይስጧቸው። አፈጻጸማቸውንም እየተዘዋወሩ ይቃኙ።
(የክፍልዎን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባትም ውይይቱን የጋራ (የሙሉ ክፍል)
ሊያደርጉትም ይችላሉ)።

ይህ ተግባር ሲጠናቀቅ ቃላዊ ዘገባን በተመለከተ የቀረበው አጭር ማስታወሻ ላይ


በመነጋገር በቀጣዩ ክፍለጊዜ ተማሪዎች ስለሰሙት (ከመገናኛ ብዙኀን)፣
ስለተመለከቱት ወይም ስላከናወኑት ተግባር ቃላዊ ዘገባ አዘጋጅተው እንዲመጡ
መመሪያ ይስጧቸው (ተግባር ሁለት) (ጊዜ የሚበቃችሁ ከሆነም ከውይይቱ በኋላ
ልታከናውኑት ትችላላችሁ)።

ምዘና

 ውይይት በማድረግ የተገኘውን ውጤት በቃል ማቅረባቸውን መመዘን፣


 በቃላዊ ዘገባ አቅርቦት ወቅት ተገቢ ዝግጅት ስለመደረጉ ግምገማ ማካሄድ፣

7
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

ተማሪዎች በዚህን ንዑስ ትምህርት ክፍል፡-

 የጽሁፍን አጠቃላይ ሀሳብ ለማግኘት ያነባሉ።


 አንብበው መረዳታቸውን የሚያመላክቱ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።

ቅድመ ንባብ

በመጀመሪያ ተማሪዎች ስለ ቋንቋና ሰው የቀረበላቸውን ቅድመ ምንባብ ጥያቄዎች


እየጠየቁ በርዕሱ ዙሪያ ያላቸውን እውቀት እንዲናገሩ ይጋብዟቸው። በዚሁ መሠረት
ቋንቋ እና ሰው ስላላቸው ግንኙነት፣ ቋንቋ ባይኖር የሰው ልጅ እንዴት ሊኖር ይችል
እንደ ነበር ወዘተ ነጥቦች ላይ ከተወያዩባቸው በኋላ በምንባቡ ውስጥ የሚነሱ ፍሬ
ነገሮች ምን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ከርዕሱ ተነስተው እንዲተነብዩ ይንገሯቸው።
በቅድመ ማንበብ ጊዜ የቀረቡትን ቃላት ፍቺ ገምተው ምላሻቸውን ለጓደኞቻቸው
ያጋሩ ዘንድም ያበረታቷቸው። ሌሎች አዳዲስ ቃላትና ሀረጋት ሲያጋጥሟቸውም
ከምንባቡ አውድ አንጻር ፍቻቸውን እየገመቱ ማንበብ እንዳለባቸው ያሳስቧቸው።

የንባብ ጊዜ

መምህር ይህ ክፍል ለቅድመ ንባብ ተግባር ከ5-6 ደቂቃዎችን ከተገለገሉ በኋላ


ተማሪዎችዎ ሙሉ ትኩረታቸውን ምንባቡ ላይ በማድረግ ወደ ማንበብ ተግባሩ
እንዲገቡ የሚያደርጉበት ነው። ሁሉም ተሳታፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥም
እየተዘዋወሩ ቅኝት እንዲያደርጉ ይመከራል።

ተማሪዎችዎ የምንባቡን የተወሰኑ ክፍሎች አንብበው ካጠናቀቁ በኋላም የተነበቡትን


አንቀጾች መሰረት በማድረግ የተዘጋጁትን ጥያቄዎች ይመልሳሉ። ስለሆነም እባክዎ
መምህር ተማሪዎችዎ ንባባቸውንገታ እንዲያደርጉ በመጠየቅ የቀረቡትን የንብብ
ጊዜ ጥያቄዎች እንዲሰሩ ያበረታቷቸው። ጥያቄዎቹን ከመለሱና

8
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ከተነጋገራችሁባቸው በኋላም ቀሪውን የንባብ ክፍል አንብበው እንዲያጠናቅቁ


ይንገሯቸው።

በመጀመሪያው ዙር ሁሉም አንቀጾች ተነብበው ከተጠናቀቁ በኋላ ተማሪዎች


ምንባቡን አንዴ ፈጠን ባለ መልኩ ደግመው እንዲያነቡት ይንገሯቸው (በዚህ ጊዜ
የንባብ ጊዜ ጥያቄዎቹ ይታለፋሉ)። አንብበው ሲጨርሱም ሙሉውን ምንባብ
መሰረት በማድረግ የድህረ ማንበብ ጥያቄዎቹን እንዲሰሩ ይጋብዟቸው። ክሂሎችን
እያቀናጁ ለመጠቀም ያመች ዘንድም ጥያቄዎቹ በተማሪዎቹ መለማመጃ ደብተር
ላይ ተጽፈው የሚመለሱ ናቸው። እባክዎ መምህር በዚሁ መሰረት እየተከታተሉ
ያስፈጽሙ። እገዛ (ተጨማሪ ጊዜ ለሚያስፈልጋቸው)፣ ማበልጸጊያ (ፈጥነው
ለሚጨርሱ ተጨማሪ ስራ መስጠት) እና ምጋቤ ምላሽም እንደ የሁኔታው እያስማሙ
ይስጧቸው።

(የጥያቄዎቹ ምላሾች በምዕራፉ መጨረሻ ላይ በማመሳከሪያነት ቀርበዋል)

ክፍል አራት፡ መጻፍ

ተማሪዎች ይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-


 ምሳሌያዊ አነጋገሮችን በጽሑፍ ውስጥ ይጠቀማሉ።
 አንቀጽ ይጽፋሉ።
 ለደረጃው የሚመጥን ድርሰት ይጽፋሉ።

አንቀጽ መፃፍ

በዚህ ንዑስ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች አንቀጽ እንዲጽፉ የሚጠበቅ ሲሆን


በትዕዛዝ(ሀ) ስር በተገለጸው መሰረት ቀደም ሲል አንብበውት የነበረውን ምንባብ
መሰረት በማድረግ ስለቋንቋና ሰው ግንኙነት የተረዱትን በራሳቸው ቃላት ያትታሉ።

በመቀጠልም በትዕዛዝ (ለ)ስር የተዛቡ አረፍተነገሮችን አስተካክለው አንቀጽ


እንዲጽፉ የሚያስችል ተግባር ቀርቧል። በመሆኑም መምህር እባክዎ ተማሪዎችዎ

9
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መጀመሪያ በግላቸው ቀጥሎ ደግሞ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ እንዲሰሩ ይጋብዟቸው።


በመጨረሻም በጥንድ የተስማሙበትን ለክፍሉ ያቅርቡ፤ አጠቃላይ እንደክፍል
ስምምነት ሲደረስበትም አንቀጹን ደብተራቸው ላይ እንዲጽፉት ያድርጓቸው።

ተግባር ሦስት ተማሪዎችዎ አጭር ድርሰት (ከአንድ በላይ አንቀጽ ያለው) እንዲጽፉ
እድል የሚያገኙበት ነው።መምህር አስቀድመው ግን ስለድርሰት ምንነት አጠር ያለ
ገለጻ ያቅርቡላቸው (ለዚህም ዋቢ መጽሐፍትን ይጠቀሙ)፡-

 ድርሰት ከአንቀጽ ቀጥሎ ያለ የጽህፈት ክፍል ስለመሆኑ፣


 ድርሰት ስለአንድ ጉዳይ ወይም ታሪክ ተጠየቃዊ በሆነ ቅደም ተከተል ገለጻ፣
ሀተታ ወይም ትንታኔ ማቅረብ የሚያስችል መሆኑን፣
 እንዲሁም ድርሰት ሲጻፍ በአንቀፆቹ መካከል አንድነት (የሀሳብ
ተመሳሳይነት)፣ ተለጣጣቂነት (ተያያዥነት ያላቸው መሆን)፣ አጽንዖት
(ትኩረት የተሰጠው ነገር በተለያየ መንገድ መደጋገም)
 ድርሰት የመግቢያ አንቀጽ፣ የሀተታ አንቀጾች(ዋና ክፍል) እና የመደምደሚያ
አንቀጽ (ማሳረጊያ) ክፍሎች ያሉት መሆኑን ወዘተ

መምህር የኮረና ወረርሽኝ በቅርብ ጊዜ የተከሰተና ሀገራችንን ጨምሮ አለማቀፉ


ማህበረሰብ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲያስተናግድ እንደነበረና
አሁንም ድረስ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ እንዳላገገመ ግልጽ ነው። ይህንን የቅርብ ጊዜ
ክስተት መነሻ በማድረግም ተማሪዎችዎ የግል ገጠመኞቻቸውን፣ በአካባቢያቸው
የሚገኙ ሰዎችን ልምዶች ወይም ከመገናኛ ብዙኀን የሰሙትን፣ ያዩትንና ያነበቡትን
መነሻ በማድረግ አንድ ድርሰት እንዲጽፉ ይጠበቃል። በመሆኑም እርስዎ ተገቢ
ገለጻዎችን በመስጠት ተማሪዎቹ አስቀድመው ስለሚያካትቷቸው ሀሳቦች ንድፍ
እንዲያዘጋጁና ያንን ንድፍ መሰረት አድርገውም ድርሰቱን እንዲጽፉ ማድረግ
ይጠበቅበዎታል።ይህንን ተግባር በሁለት ከፍለው እንዲያካሂዱ ማድረግ የሚቻል
ሲሆን ለምሳሌ ንድፉንና የመጀመሪያውን ሙከራ በክፍል ውስጥ አድርገው
የመጨረሻውን ስራ በየቤታቸው ሰርተው እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል።

10
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና፡-

 ተማሪዎች የጻፏቸውን አንቀጾች ተለዋውጠው እንዲተራረሙ ማድረግ


 በምልከታ የየግል ተሳትፏቸውን መቃኘት
 ድርሰታቸውን ሰብስቦ ከሀሳብ ፍሰትና ከተገቢነት አንጻር መመዘንና ተገቢ
ምጋቤ ምላሽ በጽሑፍ በመስጠት

ክፍል አምስት፡ ቃላት

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-


 ለቃላት መዝገበ ቃላዊ ፍች ይሰጣሉ።
 ጥምር ቃላትን ይመሰርታሉ።

መምህር ወደ ዋናው ትምህርት ከመግባታችሁ በፊት ተማሪዎችዎ የተወሰኑ ቃላትን


ደብተራቸው ላይ እንዲጽፉ ያድርጉ (ቢያንስ አስር)። ጽፈው ሲጨርሱ ወደ ዋናው
ትምህርት ግቡ።

ጥምር ቃላት

በዚህ ክፍል ከቃላት ትምህርት ክፍል ጋር ተያያዥነት ያለው ይዘት (ጥምር ቃላት)
ቀርቧል። ይህንን ጽንሰ ሀሳብ በተመለከተም በተማሪ መጽሐፍ ላይ ገለጻና
ምሳሌዎች ተሰጥተዋል። እባክዎ መምህር ያንን መነሻ በማድረግ ማብራሪያ
ይስጧቸው፤ ማብራሪያውን በማስከተልም የቀረቡትን መልመጃዎች በትዕዛዛቱ
መሰረት ደብተራቸው ላይ ጽፈው አስቀድመው በግላቸው፣ በማስከተልም ከጎናቸው
ካሉ ጓደኞቻቸው ጋር እንዲያመሳክሩ ያድርጉ፤ እርስዎም ደብተራቸውን ሰብስበው
እርማት ሊሰጡበት ይችላሉ።

መልመጃ አምስት ለጥምር ቃላት/ፈሊጦች/ መዝገበ ቃላዊ ፍች መስጠትን


የተመለከተ ነው። በትዕዛዙ መሰረት ይሰራ፤ ደብተራቸውን ሰብስበው እርማት
ሊሰጡበትም ይችላሉ።

11
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

 ከቃላት ሚና አንጻር ገላጭ ቃላትን ለይተው ያመለክታሉ።


 ገላጭ ቃላትን ይጠቀማሉ።

በዚህ ክፍል የቃላትን ሚና በተመለከተ ማስታወሻ በተማሪ መጽሐፍ ላይ የቀረበ


ሲሆን ያንኑ መነሻ በማድረግ ገለጻ ያድርጉላቸው፤ ማስታወሻውንም ደብተራቸው
ላይ እንዲጽፉ ይንገሯቸው። እባክዎ በገለጻ ወቅት ተጨማሪ ምሳሌዎችን
ይስጧቸው።

ትዕዛዝ 2- ቀደም ሲል ከጻፏቸው ቃላት መካከል ገለጭ የሆኑትነ (ለምሳሌ ቅጽሎች)


የሆኑትን እንዲለዩና እንዲናገሩ ይጠበቃል።

ትዕዛዝ 3- ከቀረበው አንቀጽ ገላጭ የሆኑ ቃላትን መለየት በዚህ ክፍል የሚጠበቅ
ነው፤ በዚሁ መሰረት ያሰሯቸው። በአማራጭነት የራስዎን አንቀጽ መርጠው
በተጨማሪነት ሊያቀርቡላቸውም ይችላሉ።

መልሶች
ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ
ቅድመማዳመጥ
1. ሀ. አንደበታዊ - አፋዊ (በአንደበት አካላት አማካኝነት በሚፈጠሩ ድምጾች
የምንግባባበት)
ለ.መላምት - ግምታዊ አስተያየት፣አተያይ፣ አመለካከት፣ እሳቤ…
ሐ.አዝጋሚ - በቀስታ፣ ሂደቱን ጠብቆ፣ በድንገት ያልሆነ
መ. ጉልህ - አብይ፣ በደንብ የሚታይ፣ ዋነኛ
የማዳመጥ ጊዜ
1. ቋንቋ 3.ቃላዊ አጻጻፍ
2. ሐሳባዊያን እና ቁስ አካላዊያንስዕላዊ አጻጻፍ

12
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች


ሀ. 1. ቋንቋ በአንደበት አካላት አማካኝነት በዘፈቀደ የተፈጠሩ ድምጻዊ ትዕምርቶች
ስርዓት ባለው መልኩ ተቀናጅተው የሚፈጥሩት ሰዎች ሀሳባቸውን
ለመለዋወጥ የሚጠቀሙበት የመግባቢያ መሳሪያ ነው ማለት ይቻላል።
2. ስዕላዊ፣ ቃላዊ፣ ቀለማዊ እና ፊደላዊ
3. ቀለማዊ
4. ስዕላዊ አጻጻፍ አንድ ስዕል (ምልክት) አንድ ነገርን (ሀሳብን) ሲወክል፤ ፊደላዊ
አጻጻፍአንድ ምልክት አንድ ነጠላ ድምጽን ሲወክል
5. ቁስ አካላውያን ቋንቋ የሰው ልጆች ስራን ለመስራትና እርስ በርስ
ለመግባባት ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የፈጠሩት የአዝጋሚ ለውጥ
ውጤት ነው ብለው ያምናሉ።
ለ. 1ኛ. ስዕላዊ 2ኛ.ቃላዊ 3ኛ.ቀለማዊ 4ኛ.ፊደላዊ

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተግባር አንድ
ሀ.የተለያዩ መልሶች
ለ.የተለያዩ መልሶች
ተግባር ሁለት
ተማሪዎቹ በቃል የሚያቀርቡት ዘገባ
ክፍል ሦስት፡ ማንበብ
ቅድመማንበብ ጥያቄዎች
1. የተለያዩ መልሶች (ለምሳሌ ሰው ያለ ቋንቋ፤ ቋንቋም ያለ ሰው ሊኖሩ አይችሉም፤
ቋንቋ የሰው ልጅ ብቻ ነው ሊጠቀምበት የሚችለው…)
2. የተለያዩ መልሶች (ለምሳሌ፡ ሌላ መግባቢያ ይፈጥር ይሆናል፤ እንደእንስሳት
በማይለዋወጥ ድምጽ ብቻ ይግባባ ይሆናል፤ በምድር ላይ መኖር አይቻለውም
ነበር፤ ማህበራዊ ህይወት መመስረት አይቻለውም…)

13
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

3. ሀ. ቋንቋ የሰው ልጅ ሀሳቡን ለመሰሎቹ ለማስተላለፍ ወይም ከመሰሎቹ ለመቀበል


የሚገለገልበት የመግባቢያ መሳሪያ ነው
ለ. ምርምር - ጥናት፣ በመረጃ ተደግፎ አንዳች ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ማሰስ
ሐ. ቃል አልባ ተግባቦት- የአካል እንቅስቃሴን (የፊት ገጽታ፣ አይን፣ ዕጅ፣ እግር፣
ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን በመጠቀም መግባባት )
የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎች
ሀ. የተለያዩ መልሶች (ለምሳሌ ስለቋንቋና ሰው የማይነጣጠል ግንኙነት፤
ስለየቋንቋ አጀማመር መላምት፣ ስለዳግማዊ ፍሬዴሪክ ያልተሳካ ሙከራ…)
ለ. ንጉስ ዳግማዊ ፍሬዴሪክ፤ ቋንቋ በፈጣሪ ለአዳምና ሄዋን የተሰጠ ነው
የሚለውን ለማረጋገጥ
የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች
መልመጃ ሁለት
ሀ. በምንባቡ መሰረት በቃል መመለስ
1. ቋንቋ በፈጣሪ የተሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ
2. የሰው ልጆች ተፈጥሯዊ ስሪት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ማንነትም ያስፈልጋቸዋል፤
ተግባቦታዊ መስተጋብር ለዘለቄታዊ ህይወት ወሳኝ በመሆኑ
3. የሰው ልጅ የቀደመ (ተፈጥሯዊ) ቋንቋ ምን እንደነበር ለማወቅ ፍላጎት፣
(1)አምስት አፍ ያልፈቱ ህጻናትን ለይቶ ወሰደ፣ (2) በአሳዳጊ እናቶችና ነርሶች
ክትትል ስር እንዲውሉ ተደረጉ፣ (3) ንክኪና ተግባቦት፣ ስሜት አንጸባራቂ
ተግባራት ፈጽሞ ተከለከለ፣ (4) ሂደቱ ለሦስት አመታት ያህል እንዲዘልቅ
ተደረገ፤ (5) ውጤት (ያልተገመተ፤ ሁሉም ህጻናት ለሞት ተዳረጉ)
4. አንድነት፡- ሁለቱም ሙከራዊ ጥናት ይመስላሉ፣ ሁለቱም ቋንቋን የተመለከቱ
ናቸው፤ ሁለቱም የሰው ልጆችን ለጥናቱ ተጠኝነት ተጠቅመዋል።
ልዩነት፡- ታሪክ አንድ ረዘም ያለ ጊዜ ፈጅቷል፤ ታረክ ሁለት አጭርጊዜ ወስዷል፤
ታሪክ አንድ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግቧል፤ ታሪክ ሁለት ከተያዙት ሁለት
መላምቷች (ሰው ያለ ቋንቋ መቆየት ይችላል፤ ሰው ያለ ቋንቋ መቆየት

14
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አይችልም) አንዱን በውጤቱ አግኝቷል (ያለ ቋንቋዊ ተግባቦት ለረዥም ጊዜ


መቆየት አለመቻሉ)
5. ሰውና ቋንቋ የማይነጣጠሉ መሆኑን…
ለ. ሀ. ስልጣኔ - ለውጥ (አዲስ አሰራር፤ ዘመናዊነት)
ለ. ግኝት - የፍለጋ ውጤት ()
ሐ. አፍ ያልፈቱ-መናገር ያልጀመሩ፤ ቋንቋ ያልቻሉ
መ. የተቸረ - የተሰጠ፤ የተበረከተ
ሠ. ተገድቧል- ተከልክሏል፣ ታቅቧል(ጥቅም ላይ እንዳይውል ታግዷል)
ረ. ተስፋ ሰንቆ - እምነት ይዞ፣ ገምቶ፣ ይሆናል ብሎ ተመኝቶ
ሰ. ፍንትው - ግልጽ (ʻጽʻ ጠብቆ)፣ ፍክት (ʻክʼ ጠብቆ ይነበባል)
ሸ. ተጠቃሽ - ምሳሌ የሚሆን፤ ማሳያ፣ አብነት
ክፍል አራት (ትምህርት አራት)፡ መጻፍ
መልመጃ ሦስት
ሀ. የተለያዩ ምላሾች (ተማሪዎች ከምንባቡ የተረዱትን ጨመቅ አድርገው በአንድ
አንቀጽ እንዲጽፉት ይጠበቃል)
ለ. ትክክለኛው ቅደም ተከተል (4፣ 2፣ 3፣ 1 ወይም 4፣ 2፣ 1፣ 3)
ተግባር ሦስት
1. ማንኛውም የቋንቋውን ስርዓት የተከተለና የሀሳብ ፍሰቱ ተቀባይነት ያለው
ድርሰት ምላሽ ይሆናል (መምህር የተማሪዎቹን ምላሾች ሰብስበው እርማት
እንዲሰጡበትም ይጠበቃል)
2. ማንኛውም ተገቢ ምላሽ (መምህር የተማሪዎቹን ምላሾች ሰብስበው እርማት
እንዲሰጡበትም ይጠበቃል)

15
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አምስት፡ ቃላት


የቃላት ሚና
መልመጃ አራት

1. ወፍ ዘራሽዓለምአቀፍ አየር ወለድ ገመና ከታች


ዓመተምህረት ወዶ ገብ ሥነሥርዓት

ራስ ገዝ ላብ አደር መል ክዓ ምድር
2.ተማሪዎቹ የሚጽፏቸው ተቀባይነት ያላቸው ዓረፍተ ነገሮች
መልመጃ አምስት

ሀ.ነገረፈጅ - ጠበቃ፣ ተሟጋች፣ አቡካቶ

ለ.እግረ ሙቅ - እግር ብረት

ሐ.ፈር ቀዳጅ - የመጀመሪያ፣ መሰረት የጣለ

መ.ውሃ ገብ - ውሃ ያለበትና ለመስኖ የሚያመች መሬት

ሠ.ኩታ ገጠም - ድንበርተኛ፣ ወሰንተኛ


ረ.ግንባር ቀደም - የመጀመሪያ፣ ቀዳሚ
ሰ.ግብረ ሀይል - አንድ ስራ ሊሰራ የተቋቋመ ቡድን
ሸ. ው ሃ ወ ለድ - መ ነሻው ው ሃ የሆነ (ለበሽታ )

ቀ. ዓይነ ቆሎ - አይነ ትላልቅ

በ. ወርቅ ቅብ - ውስጡ ሌላ ሆኖ ላዩ ወርቅ


ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው
1.የተለያዩ መልሶች (ተማሪዎቹ በአዕምሯቸው የከሰቷቸው ቃላት)
2.የተለያዩ መልሶች (ገላጭ የሆኑ ቃላት)

16
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የክለሳ ጥያቄዎች መልስ


1. ቀጥ ብሎ የተሰደረ፣ ጎላ ጎላ ያሉ፣ ቀይ ዳማ፣ ግርማ፣ ረዘም ያለ፣ ደልዳላ፣
የፈረጠሙ፣ ከደረቱ ወጣ ያለ፣ ሆዱ ከጀርባው ሊጣበቅ..
2. በምልክት፣ በድምጽ (የንግግር ድምጽ የሆኑም ያልሆኑም፤ ዋ፣ ኣ፣ ሆ ሆ፣ ዝ፣ ኡ
ኡ፣)፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ (በእጅ፣ ጭንቅላት፣ ትከሻ)፣ የፊት ገጽታ በመለዋወጥ
3. (የተለያዩ መልሶች)
4. የተለያዩ መልሶች (ጥምር ቃላቱን በመጠቀም የሚመሰረቱ አረፍተ ነገሮች)

17
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሁለት
ባህላዊ ጋብቻ
(የክፍለጊዜ ብዛት 8)

የሚጠበቁት ውጤቶች

ተማሪዎች ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ፡-


የሌሎችን ንግግር በማዳመጥ ግብረ መልስ ይሰጣሉ።
ክርክር ያደርጋሉ።
የጽሁፍን ሀሳብ እያገናዘቡ ያነባሉ።
የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ሀሳባቸውን በፅሁፍ ይገልጻሉ።
ትምህርታዊ እና ቴክኒካዊ ቃላትን በጽሁፍ እና በንግግር ውስጥ
ይጠቀማሉ።
አስረጅ፣መጠይቃዊ እና ትዕዛዛዊ አረፍተነገሮችን በጽሁፋቸው ውስጥ
ይገለገላሉ።

የማስተማሪያ ዘዴ

 የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን እንዲሰሩ መጠየቅ


 አዎንታዊ ምላሽ መስጠት
 ያዳመጡትን መሰረት አድርገው የተወያዩበትን እንዲናገሩ ማበረታታት
 ያዳመጡትን መሰረት አድርገው ጥያቄዎች ላይ በቡድን በመሆን ከተወያዩ
በኋላ የደረሱበትን ድምዳሜ ለክፍል ጓደኞቻቸው በቃል እንዲያቀርቡ
ማነሳሳት
 ችግርን የማቃለል ተግባራትን ሰጥቶ መፍትሄ እንዲያመነጩ ዕድል መስጠት

18
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

 ተዘበራርቀው የተቀመጡትን ተግባራት ቅደም ተከተል በማስያዝ ለክፍል


ጓደኞቻቸው እንዲተርኩ ማበረታታት ።
 ከክፍል ውጪ የሚሰሯቸው መስተጋብርን የሚፈጥሩ ተግባራትን መስጠት
 ስለባላዊ ጋብቻ የሚያውቁትን እንዲናገሩ ማነሳሳት
 የአንብቦ መረዳት ስልቶችን ተግባራዊ አድርገው ‹‹የቦረና ባህላዊ ጋብቻ››
የሚለውን ምንባብ እንዲያነቡ ማድረግ
 ምንባቡን መሰረት አድርገው የወጡ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ማበረታታት
 አላስፈላጊ ቃላትን የመጠቀም ልምድን እንዲያስወግዱ አቅጣጫ ማሳየት
 የድርሰት አካላትን ከግንዛቤ በማስገባት ምሳሌ አቅርቦ ጥቂት አንቀጾችያሉት
ድርሰት እንዲጽፉ ማገዝ
 የተለያዩየ አረፍተነገር አይነቶችን ደጋግመው እንዲጽፉ ፣እርስበርስ
እንዲገማገሙና ምጋቤ ምላሽ እንዲሰጣጡ ማትጋት

ክፍል አንድ ማዳመጥ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 በጥሞና አዳምጠው ስላዳመጡት ነገር ምላሽ ይሰጣሉ።

ቅድመ ማዳመጥ
በትምህርት አንድ ስር ተማሪዎች ወደ ማዳመጥ ተግባሩ ከመሄዳቸው በፊት ስለርዕሰ
ጉዳዩ ያላቸውን የቀደመ ዕውቀት እንዲፈትሹ የሚያስችሉ ጥያቄዎች
ቀርበውላቸዋል።መምህር እባክዎን የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎቹን በመጠየቅ ወደ
ማዳመጡ ተግባር በንቃት እንዲገቡ ያበረታቷቸው።

1. ጋብቻ ማለት ምን ማለት ነው? ስለጋብቻ ወይም ትዳር የምታውቁትን


ተናገሩ።
2. በሀገራችን ያለፍላጎት በጠለፋ የሚፈጸም ጋብቻ ወንጀል ነው። በዚህ መንገድ
የሚፈጸም ጋብቻ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ተወያዩና ሃሳቦቻችሁን ለሌሎች
19
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አጋሩ።
3. የሚከተሉት ቃላት በምታዳምጡት ምንባብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ፍቻቸውን ገምቱ።
ሀ. መረዳዳት ለ. ውህደት ሐ. አጋር መ. ቃል ኪዳን
ከዚህ በታች ‹‹ጋብቻ›› የተሰኘውን ምንባብን ከማንበብዎ በፊት የቅድመ ማዳመጥ
ጥያቄዎችን ለማሰራት ተማሪዎችዎን በቡድን ያደራጇቸው። የቀረበውን ምንባብ
ሁለት ጊዜ ያንብቡላቸው። በመጀመሪያው ንባብ አጠቃላይ፣ በሁለተኛው ንባብ
ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡም ይንገሯቸው። በማዳመጥ
ሂደትና በአዳምጦ መረዳት ጊዜ የሚሰራቸውን ጥያቄዎች በተመለከተም ግልጽ
መመሪያ ይስጧቸው። ከዚህ በኋላ የተቋረጠው ጋብቻ የሚለውን ምንባብ ተሰሚነት
ባለው ድምፅ ያንቡቡላቸው።(ከተቻለም ቀድመው በሌላ ሰው ምንባቡን አስነብበውና
ቀርጸው በማቅረብ ሊያስደምጧቸው ይችላሉ፤ ሌላ መምህርም በተጋባዥ አንባቢነት
ሊያካትቱ ይችላሉ።)

በመጨረሻም የአዳምጦ መረዳት ጥያቄችን በትዕዛዛቱ መሰረት በግል፣


በጥንድና/ወይም በቡድን ሆነው እንዲሰሩ ያድርጓቸው።ተሳትፏቸውንም እየተዘዋወሩ
ይቃኙ።

ጋብቻ
ጋብቻ በየትኛውም ማህበረሰብ እጅግ መሰረታዊ የሆነና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ
ለመኖር ዋስትና የሚሰጥ ውህደት የሚጀመርበት መንገድ ነው። ይህ አስተማማኝ
ግንኙነት ለቤተሰብ ኑሮ የሚሆን ምግብን፣ ልብስን፣ መጠለያን የመሳሰሉ ነገሮችን
በማቀራረብና ልጆችን ወልዶ ማሳደግ፣ በችግርና በመከራ ጊዜ መረዳዳት፣ በዕድሜ
የገፉ ወይም ችግረኛ ቤተሰብን መርዳትን ወዘተ ይይዛል። የሚጋቡት ሁለት ሰዎች
በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ተጣምረው ለመኖር በወሰኑ ተቃራኒ ጾታዎች መሃል
የሚደረግ ስምምነት ቢሆንም በመንግስት፣ በአካባቢው ባህልና ልማድ ተቀባይነት
ባለው መንገድ የሚፈጸም ውህደት ነው። ይህ ውህደት በሚኖሩበት አከባቢ ባልና
ሚስት መሆናቸውን እውቂያ በሚሰጥ መንገድ በሰርግ ስነስርዓት ወይም መጠነኛ
20
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የእወቁልን ድግስ ይፈጸማል። እውቂያው ተስማምተው ለመጋባታቸው ምስክሮች


ወይም እማኞች የሚሆኑ ሰዎች ባሉበት ወይም ለመጋባት ስልጣን ካለው ክፍል
የምስክር ወረቀት በማግኘት ሊደረግ ይችላል።

በጣም ቀላሉ የጋብቻ ትርጉም በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል የሚፈጸም የእድሜ
ልክ ውህደት ነው። ይህ ቀላል የሚመስል መግለጫ በውስጡ የሚጋቡ ወጣቶችን
ቤተሰብ፣ ዘመድና ወዳጅ፣ የሚኖሩበትን ማህበረሰብ ባህልና ልማድ፣ የመንግስትን
ህግ፣ እንዲሁም ወደፊት አብረው በመኖር የሚያፈሯቸውን ልጆችና ንብረት ወዘተ
የሚመለከት ሰፊ ጉዳዮችን የሚያጠቃልል እሳቤ ነው። በዚህ መልኩ ጋብቻ ያለፈ፣
ያሁንና የወደፊት ዘመናትን የምናያይዝበትና እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ
አብሮ በመኖር ለመጪው ዘመናችን ሳይቀር የምንቀይስበትን ዘዴ ይጠይቃል። ይህ
ዘዴ ገና ከጅምሩ የጋብቻን ምንነትና የራስን ማንነት ከማወቅ ተነስቶ ለማግባት
የሚወስኑትን ሰው ማፈላለግን፣ የመጠናናትና የመተዋወቅ ጊዜን ማሳለፍን እና
ሕጋዊና ተቀባይነት ባለው መልክ ጋብቻ መፈጸምን ያጠቃልላል።

የማደመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

ሀ.ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለመኖር ዋስትና የሚሰጥ ውህደት የሚጀመርበት


________ ነው።
ለ.ጋብቻ የሚያስተሳስረው የትኞቹን ዘመናት ነው?
ሐ. ቀጣዩ የምንባቡ ክፍል ምን ምን ጉዳዮችን የሚያነሳ ይመስላችኋል?

በቀደመው ዘመን ጋብቻ በአብዛኛው ወላጆች ለልጆቻቸው የትዳር አጋር


የሚሆኗቸውን በመምረጥና በማጨት የሚያዘጋጁት የትዳር ምስረታ ነበር። ይህ
ዓይነቱ ጋብቻ በዘመድና በየአከባቢው ባህል ወይም ልማድ የታቀፈና ከሰርጉ እስከ
እለተ ሞት ድረስ ባልና ሚስቱ ባላቸው የአንድነት ሕይወት በምን መልክ
ተቀናጅተው እንደሚኖሩ በአካባቢው ልማድና ባህል በመደንገጉ በብዙ መንገድ
አጀማመሩ ግልጽና ቀላል ነበር። በነገራችን ላይ ይህ አካሄድ በከፍተኛ መጠን ቁጥሩ
21
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እየቀነሰ ቢሆንም አሁንም ድረስ በበርካታ የሀገራችን አካባቢዎች ሲፈጸም ይታያል።


ይሁን እንጂ ከቀደመው ጋር ሲመዛዘን በዘመናችን በተለይም በከተሞች አከባቢ
የሚታየው የጋብቻ ሁኔታ ሁለት ወጣቶች ተፈላልገው በመገናኘት፣ የትዳር
ጅማሬያቸውን ሕጋዊነት ባለው መንገድ በቃል ኪዳን ለማሰር የሚያደርጉት ጉዞ
ልክ ተራራን ከሁለት ተቃራኒ አቅጣጫ ወጥቶ ከጫፉ ላይ እንደመገናኘት ያህል
ነው። ሆኖም ተራራውን የሚወጡበት ፍጥነት፣ የሚወስድባቸው ጊዜና የሚጨርሱት
ጉልበት የተለያየ ሊሆን ይችላል። ለአንዳንዱ የቤተሰብ፣ የዘመድና ወዳጅ
የማያቋርጥ ድጋፍና ማበረታቻ ስለሚደረግለት አወጣጡ ቀላል ሊሆን ይችላል።
ሌላው ከራሱም ሆነ ከሌላው ቤተሰብ ጋር እልህ አስጨራሽ መሰናክል አልፎ ከጫፉ
ላይ የሚደርስ ሊሆን ይችላል። ትልቁ ነገር በደረሰባቸው ችግር ተስፋ ሳይቆርጡ
ከጫፉ መገናኘታቸው ነው።

ወጣቶች የሚጋቡበትን የመምረጥ መብትም ሆነ ሃላፊነት ባላቸው አካባቢ ጋብቻ


ከመፈለግ፣ ከመተዋወቅና ከመፈቃቀድ ጀምሮ በትጭጭት በኩል ወደ ሰርግ
ይደርሳሉ። ከዚህ የተነሳ ወጣቶች የሚሆኗቸውን የትዳር ጓደኛ ፈልገው ለማግኘት
ካሉት እጅግ ብዙ አማራጮች ውስጥ ከባህሪያቸው፣ ከራዕያቸውና ፍላጎታቸው ጋር
የሚሄዱትን ለማግኘት ሰፊ አሰሳ ያደርጋሉ። አሰሳው ብዙ ጊዜ ሊፈጅ ወይም
አቋራጭ መንገድ ተገኝቶ በቀላሉ ሊቀናቸው ይችላልሉ። በተለምዶ ወንዶች ‘እንጋባ’
ብለው የመጠየቁ ድፍረት የሚታይባቸው ቢሆንም፣ ሴቷም ከወንዱ ባላነሰ መንገድ
‘እህል ውሃ አጣጬ ይሆናል’ ብላ አውጥታና አውርዳ የወሰነችበትን የትዳሯ አጋር
እንዲሆን የምትጠይቅበት አጋጣሚ ቀላል የሚባል አይደለም።

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በጥናት ላይ የተመሰረተና በጥንቃቄ ተጠናንቶ


የሚጀመር የትዳር ህይወት ሰላማዊ፣ ከጠንካራ ግጭት የጸዳና ረዥም ጊዜ
የመዝለቅም እድል ያለው ነው። በአንጻሩ በችኮላ፣ በደንብ ሳይተዋወቁና ምራቅ
በደንብ ሳይዋጥ ወይም እድሜ ሳይጠና የሚፈጸም ጋብቻ ከጭቅጭቅ የጸዳና ዘላቂ
ሆኖ የመቀጠል እድሉ አናሳ ይመስላል።

22
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

(የሺጥላ መንግስቱ፣ 1998። መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበ)

ምዘና

• የተማሪዎቹን እንቅስቃሴ እና ተሳትፎ በእያንዳንዱ መልመጃ ላይ


በምልከታ መከታተል።

• ተማሪዎቹን ስለይዘቱ ጥያቄ በመጠየቅ መረዳታቸውን መመዘን።

• በገቡበት አውድ መሰረት ለቀረቡላቸው ቃላት ፍች መስጠታቸውን


ደብተሮቻቸውን ሰብስቦ በማረመም ምጋቤ ምላሽ መስጠት

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

• ክርክር ለማድረግ የሚያስችሉ መርሆችን ይረዳሉ።

• የክርክር ማካሄጃ መርሆችን ተከትለው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ


ክርክር ያደርጋሉ።
መምህር በዚህ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ የክርክርን ምንነትንና ክርክር እንዴት
መካሄድ እንዳለበት ከተረዱ በኋላ በተግባር የክርክር ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ
ይጠበቃል። ስለሆነም እርስዎ በተማሪዎቹ መጽሐፍ ላይ የቀረበውን ማስታወሻ
መነሻ በማድረግ ገለጸ እንዲያቀርቡላቸው ይጠበቃል። ገለጻዎትንም ተማሪዎችዎ
ቀደም ሲል በመደበኛ ክርክር ተሳትፎ ያላቸው ስለመሆኑ ወይም ክርክር ሲካሄድ
ተከታትለው ያውቁ እንደሆን በመጠየቅ ቢሆን ትምህርቱን ከቀደመ ልምዳቸው ጋር
እንዲያስተሳስሩት እድል ይፈጥርላቸዋል።

ተግባር አንድ

ማስታወሻውን መሰረት ያደረገ ገለጻ ካቀረቡ በኋላ በመማሪያ መጽሐፉ ላይ


የቀረበውን መከራከሪያ ርዕስ ወይም የራሳቸውን ርዕስ መርጠው ዝግጅት ያለው
ክርክር እንዲያካሂዱ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው።ይህንንም በየቤት ስራ መልክ
23
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሊሰጧቸው ይችላሉ። (በዕለቱ በቂ ጊዜ ከተገኘ በፈቃደኞች ለማሳያ የሚሆን ክርክር


በተለመዱ ጉዳዮች ላይ ማካሄድ ይቻላል። ለምሳሌ ‘በገጠር መኖር በከተማ ከመኖር
ይሻላል’)

ተማሪዎችዎ በቡድን ተከፋፍለው እንዲከራከሩ እድሉን ሲያመቻቹላቸው፣


ተከራካሪዎች፣ ዳኞች እና ሰዓት ተቆጣጣሪዎች እንዳሉ ልብ ይሏል።

መምህር ክርክሩ ሲካሄድ ምዘና እንደሚያካሂዱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በቂ ዝግጅት


ስለመደረጉና የክርክር መርሆቹ በአግባቡ ስራ ላይ ስለመዋላቸው ትኩረት ሊሰጡበት
ይችላሉ።(ክርክሩ የሚካሄድበት ደረጃን ከፍ ለማድረግም አንዱን ክፍል ከሌላኛው
ጋር በማገናኘት ሊያከራክሯቸው ይችላሉ።)

 ስለባህላዊ ጋብቻ ሰዎችን ጠይቀው በመምጣት ቃላዊ ዘገባም ያቀርባሉ።

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ (የቦረና ባህላዊ ጋብቻ)

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

• በአካባቢያቸው ስለሚካሄዱ ባህላዊ ጋብቻዎች ይናገራሉ።

• የባህላዊ ጋብቻ እሴቶችን ይዘረዝራሉ።


መምህር በዚህ ክፍለጊዜ ተማሪዎችዎ ማንበብን በክፍል ውስጥ በተግባር
ይለማመዱታል። ይህ ልምምድም በወደፊቱ የእውኑ አለም ህይወታቸው አንባቢዎች
እንዲሆኑና በተሰማሩበት መስክም ስኬታማ እንዲሆኑ ፈር ቀዳጅ ይሆንላቸዋል።
በክፍል ሦስት የማንበብ ተግባሩን በሶስት ደረጃዎች ከፍለው ማቅረብ የሚጠበቅብዎ
ሲሆን ቀጥለን አንድ በአንድ እንያቸው።

ቅድመ ንባብ

በዚህ ቀዳሚ ክፍል ተማሪዎች የሚያነቡትን ይዘት በተመለከተ የቀደመ


እውቀታቸውን በመቀስቀስና ተነሳሽነታቸውን በመጨመር ለማንበብ ዝግጁ

24
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እንዲሆኑ የሚደረግበት ነው። በመሆኑም መምህር የተወሰነ ደቂቃ ወስደው


የቀረቡትን የቅድመ ምንባብ ጥያቄዎች ተማሪዎችዎ በቃል እንዲመልሱ ያድርጉ፤
ተማሪዎችዎ ዳራዊ እውቀታቸውን መነሻ በማድረግም ይከብዷቸዋል ተብለው
ከምንባቡ ተወስደው የቀረቡትን ቃላት ፍች እንዲገምቱ ያድርጉ። ይህንን
ሲጨርሱም ተማሪዎችዎ ወደ ማንበብ ተግባሩ በትኩረት እንዲገቡ ያበረታቷቸው።

የንባብ ጊዜ

በምንባብ ጊዜ ተማሪዎች ‘የቦረና ባህላዊ ጋብቻ’ የተሰኘውን ምንባብ በለሆሳስ


የሚያነቡት ይሆናል። ምንባቡን ባጠቃላይ ሁለት ጊዜ ደግመው እንዲያነቡት
የሚጠበቅ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ማንበብ አፍታ ጊዜ ወስደው በምንባቡ ውስጥ
የቀረቡትን የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ። የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎቹ ሦስት
ሲሆኑ እባክዎ መምህር የተነበበውን የምንባብ ክፍል መሰረት አድርገው እንዲመልሱ
ያበረታቷቸው፤ ጊዜም ሰጥተው በተያዙት ደቂቃዎች እንዲያጠናቅቋቸው ያድርጉ።
ያንን ሲጨርሱ ቀጣዩን ክፍል ወደ ማንበቡ እንዲመለሱ ያድርጓቸው። ሲጨርሱ
ምንባቡን አንዴ መለስ ብለው በቀለጠፈ መንገድ እንዲያነቡት ያድርጓቸው።

የአንብቦመረዳት ጥያቄዎች/ድህረ ማንበብ/

ምንባቡ ተነቦ ሲጠናቀቅ በጽሑፍ የሚመለሱ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች


ቀርበዋል። መምህር እባክዎ በዚህ ክፍለጊዜ ምንባቡን አንድ ጊዜ እንዲነበብ
ያድርጉና (በአማራጭነት እርስዎም ድምጽ አሰምተው ሊያነቡላቸው ይችላሉ)
በመልመጃ ሁለት ስር ያሉ ጥያቄዎችን ሁሉም ተማሪዎች በደብተራቸው ላይ ጽፈው
መልስ እንዲሰጡባቸው ይጠይቋቸው። በመቀጠልም ከጎናቸው ካሉ የክፍል ጓደኞች
ጋር ጥንድ ጥንድ እየሆኑ የጻፉትን እንዲያነጻጽሩ ያበረታቷቸው፤ አፈጻጸሙንም
እየተዘዋወሩ ይመልከቱ።(ጊዜዎትን አብቃቅተው ለመጠቀምም የተወሰኑትን ድህረ
ምንባብ ጥያቄዎች ተማሪዎችዎ በየቤት ስራ መልክ እንዲሰሯቸው ሊያደርጉ
ይችላሉ፤ ጥያቄዎቹን በመስራትና በማቅረብ ወቅትም የተማሪዎችዎን አደረጃጀትም
በግል፣ በጥንድ፣ በቡድን ወይም በጋራ እንዲሆን ሊያደርጉ ይችላሉ።)
25
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አራት፡ መጻፍ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

• የድርሰት ክፍሎችን ይለያሉ።

• የተማሯቸውን የድርሰት ክፍሎች የሚያሳዩ ድርሰቶችን ይጽፋሉ።


የዕለቱ ትምህርት ድርሰት መጻፍን የተመለከተ እንደሆነ በመግለጽ በተማሪው
መጽሀፍ ላይ የቀረበውን አጭር ማስታወሻ መነሻ በማድረግ ስለድርሰት ክፍሎች
ማብራሪያ ያቅርቡላቸው። ማብራሪያዎችን ተጨባጭ ለማድረግም አንድ ማሳያ
የሚሆን ድርሰት (ቢያንስ አምስት አንቀጾች ያሉት) በጽሑፍ ወይም በንባብ
ያቅርቡላቸው።

በመቀጠል በተማሪ መጽሐፍ ውስጥ የቀረበውን መልመጃ/ተግባር እንዲሰሩት


ማበረታታት ይጠበቅቦታል። ተግባሩ ተማሪዎች የድርሰት ክፍሎችን ለይተው
እንዲያውቋቸው ከማስቻሉም ባሻገር ድርሰት መጻፍን በተግባር እንዲለማመዱ
የሚያስልነው። ስለሆነም መምህር እባክዎ ተማሪዎች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩት
ያበረታቷቸው፤ ሰርተው ሲጨርሱም ተገቢውን ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።ልምምዱ
ቀጣይነት ያለው እንዲሆንም ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲሰሩ ሊያቀርቡላቸው
ይችላሉ።

ክፍል አምስት፡ ቃላት

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

• ተዘውታሪና ሙያዊ ቃላትን ይለያሉ።

• አላስፈላጊ የቃላት አጠቃቀምን ያስወግዳሉ።

• የተጓደለ አንቀጽን ማሟላት ይችላሉ።

መምህር በዚህ ይዘት ውስጥ የቃላት አጠቃቀምን በተመለከተ የተሰጠውን ማብራሪያ

26
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ገለጻ በመስጠት ተግባር ተኮር በማድረግ ተማሪዎች ዘወትራዊና ሙያዊ የሚባሉትን


ቃላት እንዲለዩ ያድርጓቸው። የቀረበውን ማስታወሻ እያነበቡ ማስታወሻ እንዲወስዱ
ይንገሯቸው። በመቀጠል የቃላት ድግግሞሽ፣ ድረታ እንዲሁም የተሰለቹ ቃላት
ያሉባቸውን ዓረፍተ ነገሮች በማቅረብ አስተካከልው እንዲጽፉ መለማመጃዎችን
በተናጠል ያሰሯቸው። በመጨረሻ የሰሯቸውን ዓረፍተ ነገሮች በጋራ ለማረም
የጥያቄና መልስ ስልትን ተግባር ላይ ያውሉ። እንደተማሪዎችዎ ብዛትና የክፍል
አቀማመጥ ምላሾቹን በግል፣ በጥንድ ወይም በቡድን እንዲታዩ ማድረግ ይችላሉ፤
በአማራጭነትም እርስዎ ደብተራቸውን ሰብስበው እርማት ሊሰጡበት ይችላሉ።

በመቀጠል በዓፍተነገር ውስጥ የሚገኙ ሙያዊና ተዘውታሪ ቃላትን ለይተው


እንዲያወጡ በተናጠል ይስሩ። ሌላው የተሟላ ሃሳብ ማስተላፍ የማይችል አንቀጽ
ቀርቧል።ይህን ያልተሟላ አንቀጽ ቃላቶቹን እየመረጡ ክፍት ቦታዎችን በተገቢ
ቃላት እንዲያሟሉ ያድርጓቸው። ተማሪዎች ቃላቱ ለሚገቡበት ቦታ ተስማሚ ቅርጽ
እንዲይዙ ማድረጋቸውን በተመለከተም ማሳሰቢያ ይስጧቸው። በመጨረሻ
የተስተካከለውን ወጥ አንቀጽ የተወሰኑ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንባብ
እንዲያቀርቡ ያድርጉ፤ ሌሎቹም አስተያየት እንዲሰጡበት ይጋብዟቸው።
ምዘና
• የቢጤ እርማት ሲሰጥ መከታተል፣
• ተማሪዎች ሙያዊና ዘወትራዊ ቃላት በጽሁፋቸው ውስጥ
መጠቀማቸውን ማረጋገጥ፣
• የተሰለቹ፣ የተደረቱ እናድግግሞሽ ያለባቸው ቃላትን የያዙ ዓረፍተ
ነገሮች በማቅረብና እንዲያስተካክሉ በማድረግ መገምገም፣

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-
• የአረፍተነገር ስልቶችን ለይተው ያውቃሉ።
• የተለያዩ የአረፍተነገር አይነቶችን ይመሰርታሉ።
• አወንታዊና አሉታዊ አረፍተነገሮችን ይጽፋሉ።

27
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መምህር በዚህ ክፍል ስለዓረፍተ ነገር ስልቶች ከተማሪዎችዎ ጋር ከመነጋገርዎ


በፊት ስለ ዓረፍተ ነገር ምንነትና ዓይነቶች የሚያውቁትን እንዲናገሩ በመጠየቅ
ይጀምሩ።አንዳቸው የሰጡት ምላሽ ላይም ሌሎቹ አስተያየት እንዲሰጡ ይጋብዙ፤
ይህም እርስበርስ ሀሳብ ለመለዋወጥ ያስችላቸዋል።በመቀጠል የተማሪዎቹን መጽሐፍ
መሰረት በማድረግ ስለ ስልቶች አጭር ማብራሪያ በመስጠት ማስታወሻ
ያስይዟቸው። ስለ ዓረፍተነ ገ ር ስ ል ቶ ቹ ም ተ ጨ ማ ሪ ም ሳ ሌ ዎ ች ን በ ማ ቅ ረ ብ
ሁሉም ተማሪዎች ግንዛቤ መፍጠራቸውን እርግጠኛ ይሁኑ። ከዚህ
ቀ ጥ ሎ ይህንን ለማዳበር የቀረቡ መለማጃዎችን ሐተታዊ (አዎንታዊ፣ አሉታዊ)፣
ትእዛዛዊ፣ መጠይቃዊና አጋናኝ እያሉ በተናጠልያ ሰሯቸው።እንዲሁም አዎንታዊ
ዓረፍተነገሮችን በመመስረት ወደ አሉታዊዓረፍተ ነገሮች እንዲለውጧቸው ያድርጉና
በደብተራቸው ላይ እርማት በማድረግ ገንቢ ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው። በአጠቃላይ
የተለያዩ ተማሪ ተኮር የማስተማሪ ስልቶችን እየተገበሩ ተማሪዎች የተለያዩ ዓረፍተ
ነገሮችን እንዲለዩና እንዲመሰርቱ ተገቢውን ድጋፍ ያድርጉላቸው።

ምዘና
• መጠይቃዊ፣ ሐተታዊ፣ ትዕዛዛዊ አጋናኝ ዓረፍተ ነገሮችን መለየታቸውን
ማረጋገጥ፣
• አዎንታዊ ዓረፍተ ነገሮችን ወደ አሉታዊ ዓረፍተነገሮችመለወጥ
መቻላቸውን መቃኘት፣
• የተማሯቸውን ስልቶች በመንተራስ የየራሳቸውን አረፍተነገሮች
መመስረታቸውን ማረጋገጥ

በምዕራፉ የተካተቱ ጥያቄዎች መልስ

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ


ቅድመማዳመጥ
1. ልምዳቸውን መሠረት ያደረጉ ማናቸውም ተቀባይነት ያላቸው ምላሾች

28
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

2. አካላዊ (በወሊድ ጊዜ መቸገር)፣ አእምሯዊና ስነልቦናዊ ጉዳት (ከጓደኞች


መለየት፣ ትዳርን እንደአልባሌ ነገረ መቁጠር…)
3. ሀ. መረዳዳት - መተጋገዝ ለ. ውህደት - ጥምረት ሐ. አጋር - አቻ
መ. ቃል ኪዳን - ውል
አዳምጦ መረዳት
1. ትዳር በሰው ልጆች ህይወት ውስጥ መሰረታዊ ነገር መሆኑን፤ጉዳዩ ተጋቢዎችን
ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የሚመለከት መሆኑን…
2. ከባህሪያቸው፣ ከራዕያቸውና ፍላጎታቸው ጋር የሚሄዱትን ለማግኘት
3. የትዳር አጋሬ፤ አኗኗሪዬ
4. በችኮላ፣ በደንብ ሳይተዋወቁና ምራቅ በደንብ ሳይዋጥ ወይም እድሜ ሳይጠና
የሚፈጸም ጋብቻ፤ ምክንያቱም ተጋብተው ሲተዋወቁ እንደማይጣጠሙ ይረዱና
ወደ ፍቺ ያመራሉ (ሳይተዋወቁ ተጋብተው ሲተዋወቁ ተፋቱ እንደሚባለው)
እውቂያ - መተዋወቅ፣ ግንኙነት ተቀናጅተው - ተጣምረው፣
እማኞች- ምስክሮች፣ ታዛቢዎች የምስክር ወረቀት- ማረጋገጫ፣ ማስረጃ
እልህ አስጨራሽ - አልፊ፣ ተስፋ አስቆራጭ
ክፍል ሁለት፡ መናገር
ተግባር አንድ
 ዝግጅት ተደርጎ የሚቀርብ ክርክር፡
 ቤተሰብ ወይም የአካቢ ሰው ተጠይቆ የሚቀርብ ቃላዊ ዘገባ
ክፍል ሦስት፡ ማንበብ
ቅድመ ንባብ
ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ጥያቄዎች ተማሪዎች ልምዶቻቸውን መሰረት አድርገው
የተለያዩ መልሶች ሊሰጡ ይችላሉ።

ቃላት
ሀ. መተጫጨት - ቃል መገባባት ሐ. ሰይመው - ወክለው/ሾመው
ለ. እልፍኝ - ጎጆ/መኖሪያ መ. ቀን ተቆረጠ - ተወሰነ
29
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የንባብ ጊዜ
ሀ. ቀን መቁረጥ
ለ. ከጓደኞቿ
ሐ. ለጋብቻ ስለታሰበችው ልጅ ከተለያዩ ምንጮች የሚሰበሰበው
የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች
መልመጃ ሁለት
1. ሐሰት 2. እውነት 3.እውነት 4.ሐሰት 5. ሐሰት
መልመጃ ሦስት
1. ሐ 2. ሀ. 3. ለ 4. መ 5.ሀ
መልመጃ አራት
1. መ 2. ረ 3.ለ 4.ሠ 5.ሀ 6. ሐ
ክፍል አራት፡ መጻፍ
መልመጃ አምስት
(ተማሪዎች የሚጽፏቸው ተቀባይነት ያላቸውና ከስህተት የጸዱ አንቀጾች)
ተግባር ሦስት
(ተማሪዎች የሚጽፏቸው ተቀባይነት ያላቸውና ከስህተት የጸዱ አንቀጾች)
ክፍል አምስት፡ ቃላት
መልመጃ ስድስት
ሀ. 1. በርዕሰ ከተማችን የመኖሪያ ቤት ችግር አለ።
2. አርኣያ መሆን ሲገባቸው አልሆኑም።
3. በሀቅ ላይ የተመሰረተ አባባል ነው። ወይም እውነተኛ አባባል ነው።
4. ስቃዬ በርትቶብኝ ለጎረቤቴ ልገልጽ ፈልጌ በስንት ጥረት ደረስኩ።ወይም
ስቃዬን ለጎረቤቴ ልገልጽ በስንት መከራ ደረስኩ።
5. የአባቴ እህት መጣች። ወይም አክስቴ መጣች።
6. ታላቁ ደራሲ ግብዓተ መሬቱ ትናንትና ተፈጸመ።
7. የማስበውን ያወቀብኝ መስሎኝ ድንግጥ አልኩ።
ለ.1. ምህንድስና 2. የውሃ ልክ 3. – 4. –
30
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መልመጃ ሰባት
እያንዳንዱ የቀለም ጠብታ ልዩ_ሚስጥራትን_የያዘ ሆኖ እናገኘዋለን።
የምንጠቀማቸው ቀለማት እራሳቸውን ችለው እንደ__ፊደላት_የሚነበቡ ናቸውና፣
ቀለማቱን በተገቢው ካላሰባጠርናቸው ፊደላቱ የተዘበራረቀ መጽሃፍ ጽፎ
እንደማሳተም__ይሆኑብናልበተመሳሳይ_በፋሽኖች_ውስጥም ጊዜና ሁኔታንያላገናዘ
በቀለማትን የምንጠቀም ከሆነ የምናቀርብለት ማህበረሰብ ይህንን የመቀበል
ፍላጎትአይኖረውም።ጊዜና ሁኔታዎችን ማገናዘብ በእጅጉ_ወሳኝነትአላቸው።
በአብዛኛው የምንከተላቸው የፋሽን ፈጠራዎች ውድቀት የሚጀምረው ከእነዚህ
_አንጻርነው የፈጠራዎቹ እድሜም በጣም አጭርና እንደመብረቅ ብልጭታ ገና
ሳይታዩ የሚከስሙይሆናሉ።

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


መልመጃ ስምንት
ሀ. ሀ.ሐተታዊ /አሉታዊ/ ለ. ጥያቄያዊሐ. ሐተታዊ /አወንታዊ/
መ. ትዕዛዛዊ ሠ. ሀተታዊ /አወንታዊ/ ረ. ሐተታዊ /አሉታዊ/
ሰ. አጋናኝ ሸ. ሐተታዊ /አወንታዊ/
ለ. (ተማሪዎች የሚመሰርቷቸው የተለያዩ ተቀባይነት ያላቸው አረፍተ ነገሮች)
ሐ. (ተማሪዎች የሚመሰርቷቸውየተለያዩ ተቀባይነት ያላቸው አረፍተ ነገሮች)
የክለሳ ጥያቄዎች
(ተማሪዎች የሚጽፏቸው የተለያዩ ተቀባይነት ያላቸው መልሶች)

31
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሶስት
ሴቶችና ልማት
(የክፍለጊዜ ብዛት 8)

የሚጠበቁ ውጤቶች

ተማሪዎች ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ፡-

 ከተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ሴቶችና ልማትን በተመለከተ አዳምጠው


የተናጋሪዎችን ሀሳብ ይገመግማሉ፤

 አንድን ምንባብ አንብበው ተፈላጊውን ሀሳብ ያወጣሉ፤

 በሴቶችና ልማት ዙሪያ ቃለመጠይቅ በማድረግ ያገኙትን ሀሳብ በቃል


ያንጸባርቃሉ፤

 በአንድ አንቀፅ ማጠቃለያ ይጽፋሉ፤

 አረፍተነገሮችን ከሰዋስዋዊ ቅርጻቸው አንጻር ይለያሉ።

የማስተማሪያ ዘዴ

 የቀደመ እውቀታቸውን ተጠቅመው ምንባቡ ስለምን እንደሚያወሳ እንዲናገሩ


መቀስቀስ፣
 ተማሪን ማዕከል ያደረጉ የማስተማር ዘዴዎችን መተግበር፣
 ከዝርዝር ወደአጠቃላይ ወይም ከአጠቃላይ ወደዝርዝር የማስተማሪያ
ብልሐቶችን መጠቀም፣
 የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቦ እንዲመልሱ ማድረግ፣
 የቋንቋ ክሂሎችን በተግባር ማለማመድ

32
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

 የመገመት ችሎታቸውእንዲጠናከር መስራት


 ምንባቡን መሰረት አድርገው የወጡ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ማበረታታት
 በክፍል ውስጥ የሚማሩትን ከውጫዊው አለም ጋር ማዛመድ
 አዳዲስ ቃላትን ከአውዳቸው እንዲረዱ ፍንጭ መስጠት
 ሞዴል ሆኖ ማሳየትና ቀስ በቀስ ራን የማስቻል ስልትን መጠቀም
 አበበች ጎበናን ከሚዘክረው ምንባብ ያገኙትን አዳዲስ ሀሳብ በአስተዋጽኦ
መልክ ካደራጁ በኋላ አንቀጽ እንዲጽፉ ማበረታታት
 ድርሰት እንዲጽፉ ማነሳሳት
 ተራ እና ውስብስብ አረፍተነገሮችን በተመለከተ በጥንድና በቡድን ሆነው
እንዲወያዩ ማድረግ

ግምገማ

 ያዳመጡትን መረዳታቸውን መጠየቅ


 ሴቶች ከልማት ጋር ያላቸውን ትስስር በተመለከተ ግንዛቤ ማዳበራቸውን
ማጤን
 አዳምጠው ተገቢ ምላሽ መስጠት መቻላቸውን መፈተሽ
 ያነበቡትን መረዳታቸውን መመዘን
 በተለያዩ አውዶች ውስጥ ያሉ አዳዲስ ቃላትን ለይተው በማውጣት አውዳዊ
ፍቺ መስጠታቸውን ማረጋገጥ
 ለቃላት ተመሳሳይ ትርጉም መስጠታቸውን መከታተል
 ለቃላት መዝገበ ቃላዊና አውዳዊ ፍች መስጠታቸውንማረጋገጥ
 አንቀጽና ድርሰት መጻፋቸውን ያረጋግጡ
 ተራ እና ውስብስብ አረፍተነገሮች መለየት መቻላቸውን መፈተሽ
 ተራ እና ውስብስብ አረፍተነገሮችን ጽፈው እንዲያቀርቡ ማድረግ

33
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ትምህርት አንድ፡ ማዳመጥ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 የተነበበውን ምንባብ አዳምጠው መልዕክቱን ይመዝናሉ።


 ዋናና ዝርዝር መረጃዎችን ይለያሉ።
 የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።

መምህር በዚህ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ እርስዎ የሚያነቡላቸውን ምንባብ


በጥሞና በማዳመጥ ዝርዝር መረጃዎችን አስታውሶ ጥያቄዎች መመለስን
የሚለማመዱበት ነው። በመሆኑም አስቀድመው የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎችን
ካሰሯቸውና ለማዳመጥ ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ምንባቡን ቢያንስ ሁለት
ጊዜ ያንብቡላቸው።በመጀመሪያው ማንበብም ወቅትም የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎችን
በመጠየቅ ምላሽ ይቀበሏቸው (ድጋሚ በማንበብ ወቅት ጥያቄዎቹ ይዘለላሉ)።

የሴቶች ሚና

ሴቶች በማህበረሰባቸው ውስጥ እጅግ ወሳኝና አይተኬ ሚናዎች አሏቸው። ለአንድ


ማህበረሰብ ውጤታማነትና ስኬት ሴቶች የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ እንዲሁ በቀላሉ
ተጠቅሶ የሚልፍ አይደለም።

አንድ ማህበረሰብ ተመስርቶ ሊቆም የሚችለው ሴቶች በሚያከናውኗቸው ተግባራት


ነው። ሴቶች ሚና የሚለካው ልጆችን ወልደው እየተንከባከቡ በማሳደጋቸው ብቻ
ሳይሆን አጠቃላይ ለማህበረሰባቸው ልማትና እድገት ከሚያበረክቱት አስተዋጽዖም
አንጻር ነው። የተወሰኑትን ሚናዎች ቀጥለን እንመለከታለን።

ሴቶች በሀገር ግንባታ የላቀ ሚና አላቸው። የአንድ ሀገር እድገት ያለ ሴቶች ንቁ


ተሳትፎ የትም ሊደርስ አይችልም። በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ሴቶች በርካታ
አበርክቶዎችን አከናውነዋል። ለመብቶቻቸውና ለነጻነቶቻቸው በመፋለም አሁን
ያለው ማህበረሰብ እንደማህበረሰብ እንዲቆም አድርገዋል። ለማህበረሰብ ሁሉ አቀፍ

34
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አድገት የላቀ አስተዋጽዖ አድርገዋል አሁንም እያደረጉ ነው፤ ይህ ተግባራቸውም


ወደፊትም ይቀጥላል።

ሴቶች ለማህበረሰቡ ህልውና የሚያደርጉት አስተዋጽዖ ከውልደታቸው ጀምሮ እስከ


እለተ ሞታቸው ዘለቄታ ያለው ነው። ተግባራቸው የሚጀምረው ህጻናትን
በመንከባከብና በትክክለኛው መስመር እንዲጓዙ ትክክለኛውን ምሪት በመስጠት
ነው። ለህጻናት የህይውትን ትርጉም በማስተማር ሀላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ሆነው
እንዲዘልቁ ያስችላሉ። ይህንን ባያደርጉ ኖሮ ዛሬ ያለው ማህበረሰብ እንደማህበረሰብ
ቆሞ ለመሄድ አይቻለውም ነበር።

የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

1. የአንድ ሀገር እድገት ያለ ሴቶች ________________ የትም ሊደርስ


አይችልም።

2. የሴቶች ተግባር የሚጀምረው ________________ በመንከባከብና ትክክለኛ


ምሪት በመስጠት ነው።

3. አንድ ማህበረሰብ ተመስርቶ ሊቆም የሚችለው እንዴት ነው?

4. ቀጣዩ የምንባቡ ክፍል ምን ምን ጉዳዮችን ሊያነሳ ይችላል ብላችሁ


ትገምታላችሁ?
በሌላ በኩል ሴቶች በማህበረሰብ የምጣኔ ሀብት እድገት ከፍተኛውን ሚና
ይጫወታሉ። አንድ ቤተሰብ ለሚያመነጨው ገቢ ሴቶች ዋነኛ የጀርባ አጥንት
ናቸው። ምንም እንኳ ተገቢው እውቅና ባይቸራቸውም ከወንዶች ባልተናነሰ
ለሚገኘው ገቢ ጉልህ አስተዋጽዖአቸው የሚካድ አይደለም።

አድሏዊነትን በመዋጋትና ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን በማድረጉ ረገድም ሴቶች


ወሳኝ ሚናዎችን ይጫወታሉ። ከዚህም ባሻገር ሰላማዊና ተቻችሎ በጋራ ለመኖር
የሚችል ማህበረሰብ በመፍጠሩም ረገድ ሴቶች ከወንዶች የላቀ ድርሻ አላቸው።

35
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሴቶች በአንድ ማህበረሰብ የፖለቲካ ለውጥ ውስጥም ያላቸው አበርክቶ እንዲሁ


በቀላሉ የሚገመት አይደለም። የሁሉም የማህበረሰብ አካላት ድምጾች እንዲሰሙና
እንዲከበሩ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል፤ እያደረጉም ይገኛል። ለራሳቸው ለሴቶች
መብቶች ቀዳሚ ጋሻ በመሆን ፍትሐዊ ማህበረሰብ እንዲመሰረት ለሚደረገው ጥረት
ዋነኛ ተዋናዮቹ ሴቶች ናቸው።

በአጠቃላይ ሴቶች በሁሏቀፍ የማህበረሰብ እድገት እጅግ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ


ብሎ በልበ ሙሉነት መናገር ይቻላል። ስለሆነም ይህንን ሚናቸውን እውቅና
በመስጠትና የጥረታቸው አጋሮች በመሆን የሀገርን ዘላቂ ልማትና ሰላም ማረጋገጥ
ከሁሉም ወገን የሚጠበቅ ይሆናል።

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-


 ከጓደኞቻቸው ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
ተግባር አንድ እና ሁለት
ውድ መምህር ይህ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ትውውቅ
በማድረግ የሚያገኟቸውን መረጃዎች መልሰው እንዲያጋሩ የሚያስችላቸው እድል
የሚያገኙበት ነው።ስለሆነም ተማሪዎችዎ ስለሴቶችና ሴቶች ለልማት ያላቸውን
አስተዋጽዖ በተመለከተ በአካባቢያቸው ተደራሽ የሆኑ የመገናኛ ብዙኀን
የሚያቀርቧቸውን መርሃግብሮች በመከታተልና ዝግጅት በማድረግ ያገኙትን መረጃ
በጽብረቃ መልክ ለክፍላቸው እንዲያቀርቡ በየቤት ስራ መልክ ይስጧቸው፤ በክፍል
አቅርቦት ወቅትም ክትትል በማድረግ ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።
በማስከተል ቃለመጠይቅ ማድረግን ተማሪዎችዎ እንዲለማመዱ ሁኔታዎችን
ያመቻቹላቸው። ለዚህም ይረዳዎ ዘንድ በተማሪዎቹ መጽሐፍ ላይ የቃለመጠይቅ
አቀራረብን በተመለከተ የቀረበውን ማስታወሻ ይመልከቱ። ማስታወሻውን መሰረት
አድርገውም ገለጻ ከሰጧቸው በኋላ ተማሪዎችዎ ዝግጅት አድርገው በአቅራቢያቸው

36
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ወደሚገኝ መንግስታዊ ተቋም በመሄድ ቃለመጠይቅ እንዲያደርጉና ዘገባ


እንዲያቀርቡ ምሪት ይስጧቸው።
በአቅርቦትና ልምምድ ወቅትም የንግግር ክሂሎቻቸውን የመሻሻል ደረጃ በየግላቸው
ይመዝኗቸው።
ምዘና
 በአይን ቅኝት በማድረግ ሁሉም በማዳመጥ ተግባሩ ወቅት እየተሳተፉ
መሆኑን ማረጋገጥ
 በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ዘፈቀዳዊ በሆነ መንገድ ተማሪዎችን እየጠቆሙ
ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-


 የጽሁፍን ፍሬ ሀሳብ አንብበው ከራስ ጋር ያዋህዳሉ።
መምህር እባክዎ ተማሪዎችዎ ማንበብን በተግባር ይለማመዱት ዘንድ ዝግጅት
አድርገው በንቃት ወደ ማንበብ ተግባሩ እንዲገቡ ያበረታቷቸው። የማንበብ
ትምህርቱ በደረጃ ተከፋፍሎ የሚቀርብ ሲሆን በመግቢያው ክፍል የቅድመማንበብ
ጥያቄዎችን፣ በማቅረቢያ ግዜ ደግሞ ማንበብንና የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎችን እና
በማጠቃለያው ክፍል የድህረ ማንበብ ጥያቄዎችን ያሰሯቸው።
ቅድመ ንባብ
ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ንባብ ከመግባታቸው በፊት ለማንበብ የተነሳሱ እንዲሆኑና
የማንበብ አላማ እንዲይዙ የሚከተሉትን ተግባራት እንዲከናውኑ ያድረጉ።
 ከቀደመ እውቀታቸውን በመጠቀም ለማንበብ ዝግጁ እንዲሆኑ፣
 ስለአበበች ጎበና የሚያውቁትን እንዲናገሩ፣
 አዳዲስ ቃላትን ከአውዳቸው ለመረዳት እንዲሞክሩ

37
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የንባብ ጊዜ
መምህር በዚህኛው የንባብ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ
ወደሚያነቡት የጽሑፍ አሃድ ላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ስለሆነም ተማሪዎች
ምንባቡን በጥሞና እንዲያነቡ የማንበቢያ ደቂቃ ወስኖ በመስጠትና በንባቡ ሂደት
ወቅትም እየተዘዋወሩ በመመልከት የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን መቃኘት
ያስፈልጋል። በንባብ ወቅት አዳዲስ ቃላት ሊያጋጥሟቸው እንደሚችሉም
በማስታወስ እየመዘገቧቸው እንዲሄዱ ወይም ከገቡበት አውድ ፍቻቸውን እንዲገምቱ
ማድረግ ይገባል።ከዚህም በተጨማሪ በንባብ ጊዜ እንዲመለሱ ተብለው የቀረቡ
ጥያቄዎችም ስላሉ የጽሑፉን የተወሰነ ክፍል አንብበው የሚመልሷቸው ይሆናል።
ድህረ ንባብ
የድህረ ንባብ ጊዜ አንድ ጽሑፍ ተነቦ ሲያበቃ ከጹሁፉ ጋር በተያያዘ ተረድኦት
ላይ መደረስ አለመደረሱን ለማረጋገጥ፣ ዋናና ዝርዝር ሀሳቦች ለመለየት፣ የጽሑፉን
ጭብጥ ለመረዳት፣ የጸሐፊን ሀሳብ ለመጠየቅ፣ የራስ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ፣
ማጠቃለያ ለመስጠት ወዘተ ያስችላል።ስለሆነም መምህር የቀረበውን ምንባብና
ምንባቡን ከማንበብ በኋላ ከተማሪዎች የሚጠበቀውን የትምህርት ውጤት ከግምት
በማስገባት ይህንን ክፍል የተማሪዎችን አጠቃላይ ተረድኦት ለመመዘን
ሊጠቀሙበት ይገባል። በድህረ ንባብ ክፍል የቀረቡትን ጥያቄዎችም አሳታፊ በሆነ
መንገድ እንዲመለሱና ገንቢ የሆነ ግብረመልስ እንዲሰጥባቸው ማድረግ ይጠበቃል።
ለዚህም ተማሪዎች በግል፣ በጥንድ፣ በቡድንና በጋራ እንዲሰሯቸው ሁኔታዎችን
ማመቻቸት ተገቢ ይሆናል።

ክፍል አራት፡ መጻፍ


ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-
 የሴቶችን የልማት ተሳትፎ በተመለከተ አንቀጽ ይጽፋሉ።
 ያነበቡትን ጽሑፍ በተመለከተ የማጠቃለያ አንቀጽ ይጽፋሉ።
 ጅምር ድርሰትን ያጠናቅቃሉ።

38
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መልመጃ አራት

መጻፍን በተግባር እንዲለማመዱ በሚጠበቅባቸው በዚህ ክፍል ተማሪዎች


የኢትዮጵያ ሴቶች ልማትን በማቀለጣጠፉ ዙሪያ ያላቸውን አስተዋጽዖ በተመለከተ
አንቀጾች ይጽፋሉ።ለዚህም በአካባቢያቸው ያለውን የሴቶች ተሳትፎ ከግምት
ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ ስለሚያውቁት ነገር መጻፉ የሀሳብ ፍሰቱ ቀለል እንዲል
ያደርግላቸዋል። ስለሆነም እባክዎ መምህር ተማሪዎቹ አካባቢያቸውን በንቃት
በማሰስ ሴቶች (እህቶች፣ አክስቶች፣ እናቶች) ያላቸውን ሚና በጽሑፍ እንዲያሰፍሩ
ያበረታቷቸው፤ ማሳያ የሚሆንም አንቀጽ ያቅርቡላቸው።

በሌላ በኩል ያነበቡትን ምንባብ አጠቃላይ ሀሳብ (ጭምቅ ሀሳብ) በራሳቸው አገላለጽ
ወይም ቃላት መልሰው እንዲጽፉትም በዚህ ክፍል አላማ ተይዞበታል።ስለዚህ አበበች
ጎበናን የተመለከተውን ጽሑፍ በአንድ አንቀጽ አጠቃልለው እንዲጽፉ መመሪያ
ይስጧቸው፤ አፈጻጸማቸውንም በመገምገም ገንቢ የሆነ ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።
ይህ ተግባር በክፍል ውስጥ ወይም በየቤት ስራ መልክ ከክፍል ውጪ ሊሰራ
ይችላል።

የቀረበውን ቻርት መነሻ በማድረግም ሴቶች በአካባቢያቸው ያላቸውን ማህበራዊ፣


ባህላዊ፣ ፖለቲካዊ… ወዘተ ሚናዎች በምሳሌ አስደግፈው አንድ አንቀጽ እንዲጽፉ
ያበረታቷቸው። ጽፈው ሲያመጡም እርማት በማድረግ ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።

ምዘና

 ለተሰጣቸው ጽሁፍ በአንድ አንቀጽ ማጠቃለያ መፃፋቸውን ማረጋገጥ፣


 ማሪዎች በቃለ መጠይቅ ያገኙትን ሀሳብ /መረጃ/ ያቀናጁበትን መንገድና
የፃፉትን ፅሁፍ መመዘን፣

39
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አምስት፡ ቃላት

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 ለቃላት መዝገበቃላዊና አውዳዊ ፍች ይሰጣሉ።


 አንድን ቃል በተለያየ አውድ ውስጥ እያስገቡ የተለያየ ፍች እንደሚሰጥ
ያሳያሉ።
 የቀረበ ገለጻን ከተገቢው ቃላት ጋር ያዛምዳሉ።
 የአዳዲስ ቃላትን ፍች በተመለከተ ከጓደኞቻቸው ጋር ይወያያሉ።

ውድ መምህር በዚህ ንዑስ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ ከተወሰኑ አዳዲስ ቃላት


ጋር ይተዋወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ይሁን እንጂ ከሚተዋወቋቸው ቃላት ባሻገር
ወሳኝ ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደው አዳዲስ ቃላትን ፍቺ የማወቂያ መንገዶችን ወይም
ስልቶችን በተግባር የመጠቀም ክህሎትን ማዳበራቸው ነው።ይህም ወደፊት በእውኑ
አለም ለሚገጥማቸው ከማንበብ ጋር የተያያዘ ተግዳሮት መፍትሄ የሚሆን ስንቅ
የሚያጎናጽፋቸው ነው። ስለሆነም ለቃላት ፍች መዝገበ ቃላትን፣ የገቡበት አውድን፣
የቃላት ዝምድናዊ ግንኙነትን፣ እርባታን፣ ገለጻን ወዘተ ከግምት በማስገባት
እንዲያገኙ ማለማመዱ ተገቢ ይሆናል ማለት ነው።

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 ተራና ውስብስብ አረፍተነገሮችን ይለያሉ።


 ተራና ውስብስብ አረፍተነገሮችን ይመሰርታሉ።
 ከውስብስብ አረፍተነገሮች ተራ አረፍተነገሮችን አውጥተው ይጽፋሉ።
 የጻፏቸውን አረፍተነገሮች ይዘው እርስበርስ ይገማገማሉ።

በሰዋስው ንዑስ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች በዋነኛነት ተራ እና ውስብስብ ስለተሰኙ


አረፍተነገሮች ግንዛቤ እንዲያገኙና ይህንንም ግንዛቤ ወደተግባር ቀይረው
40
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አረፍተነገሮችን በቀላሉ መመስረት እንዲችሉ ትኩረት ተሰጥቶታል። በመሆኑም


መምህር ተማሪዎች ይህንን የሚጠበቅ ውጤት ያሳኩ ዘንድ አጠር ያለ መንደርደሪያ
ገለጻ ስለአረፍተነገር አይነቶቹ በመስጠት ተግባራዊ ልምምድ እንዲያደርጉ
ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው (በግል፣ በጥንድ፣ በቡድን ወይም በጋራ እንዲሰሩ)።
እርስበርስ ከሚያደርጉት መገማገም በተጓዳኝም የተወሰኑትን መልመጃዎች ከሰሩ
በኋላ ደብተሮቻቸውን ሰብስበው በማረም ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።

የመልመጃ መልሶች

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ

የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

1. ንቁ ተሳትፎ 2. ልጆችን

3. ሴቶች በሚያከናውኗቸው ተግባራት ነው 4. የተለያዩ ግምታዊ መልሶች

አዳምጦ መረዳት

1. ማህበረሰብ መመስረት፣ ልጆችን ወልዶ መንከባከብ፣ ሀገር ግንባታ፣ ለመብትና


ለነጻነት በመፋለም፣ ምጣኔ ሀብት እድገት፣ አድሏዊነትን በመዋጋትና
ማህበራዊ ፍትህ በማስፈን እና የፖለቲካ ለውጥ በማምጣት ወዘተ

2. በሁሏቀፍ የማህበረሰብ እድገት እጅግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ

3. የሁሉም የማህበረሰብ አካላት ድምጾች እንዲሰሙና እንዲከበሩ ከፍተኛ


ተጋድሎ በማድረጋቸው። ለራሳቸው ለሴቶች መብቶች ቀዳሚ ጋሻ በመሆን
ፍትሐዊ ማህበረሰብ እንዲመሰረት ለሚደረገው ጥረት ዋነኛ ተዋናዮቹ
በመሆናቸው

4. ከውልደታቸው ጀምሮ እስከ እለተ ሞታቸው

5. ዛሬ ያለው ማህበረሰብ እንደማህበረሰብ ቆሞ ለመሄድ አይቻለውም ነበር


41
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

የቅድመማንበብ ጥያቄዎች

1. (የተለያዩ መልሶች ሊሰጡ ይችላሉ)


2. (ጣይቱ ብጡል፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ አበበች ጎበና፣ ጌጤ ዋሚ፣ ብርቱካን
ሚደቅሳ፣ ደራርቱ ቱሉ…)
3. (የተለያዩ መልሶች ሊሰጡ ይችላሉ)

የንባብ ጊዜ ጥያቄዎች

1. የኢጣሊያ ኢትዮጵያን መውረር


2. አስራ አንድ
3. እናታቸው ቤት
የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች

ሀ. 1. እውነት 2. ሐሰት3. ሐሰት 4. እውነት 5. እውነት 6. ሐሰት

ለ. 1. እንዴት ታዋርጂናለሽ ተብለው ወደ ባላቸው እንዲመለሱ ተደረጉ

2. የምስጋናና የእውቅና ሽልማቶች፤ (በምንባቡ ባይጠቀስም የክብር ዶክትሬት


ከጅማ ዩኒቨርሲቲ?)

3. የተጎሳቆሉ ሃያ ህጻናትን ለማሳደግ ወደ ራሳቸው በመውሰዳቸው

42
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

4.

ተግዳሮቶች ስኬቶች
 ትዳራቸውን ትተዋል  ለርካታ የተቸገሩ ህጻናት ደርሰዋል
 በዘመዶቻቸው ዘንድ  ብዙዎች እራሳቸውን እንዲችሉ
እንደእብድ አስተምረው አብቅተዋል
ተቆጥረዋል  በሀገር ውስጥና በአለምአቀፍ
 ያላቸውን ንብረት ተቋማት እውቅናን አግኝተዋል
(ጌጣጌጦች)  የሚያልሙትን የበጎ አድራጎት
እስከመሸጥ ደርሰዋል ተቋም በስማቸው ማቋቋም ችለዋል
 ቆሎ በመሸጥ  ከሁሉ በላይ የልጆችንና ህጻናትን
ያስጠጓቸውን ልጆች ፈገግታ ማየት ችለዋል
በህይወት ለማቆየት
ጥረዋል

መልመጃ ሦስት

ሀ. አላዘለቃቸውም (አላስቀጠላቸውም፤አላሻገራቸውም) ረ. ልቀቱ (ጫፍ፣ ከፍታ)

ለ. አዋጭ (አትራፊ) ሰ. ነፍስ ያላወቁ (ጨቅላ)

ሐ. ተሻገሩት (አለፉት) ሸ. የወረረችበት (የያዘችበት)

መ. መርህ (ሥርዓት፣ አካሄድ፣ ህግ) ቀ. ቀናነት (በጎነት)

ሠ. ተበርክተውላቸዋል (ተሰጥተዋቸዋል) በ. የሚያተጋቸው (የሚያበረታቸው)

43
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አራት፡ መጻፍ

መልመጃ አራት

ከ1-4(በጽሑፍ የሚመለሱ ተቀባይነት ያላቸውና ሰዋስዋዊ ስርዓትን የተከተሉ


የፅሑፍ መልሶች)

ክፍል አምስት፡ ቃላት

መልመጃ አምስት

ሀ.

1. ቁንጮ (ስ)1.ዙሪያውን ከተላጨ በኋላ መሃል ኣናት ላይ የሚቀር የልጅ ጸጉር

/የሳርቤት ክዳን ኣናት/ (ዘይቤ) ዋነኛ፣ የበላይ፣ ታዋቂ

2. አምበልጋ (ቅ) ፈሪ፣ ቡክን

3. መልቲ (ቅ) አታላይ፣ አጭበርባሪ፣ ቀጣፊ


4. ተቆራመደ (ግ) ተኮማተረ፣ ተኮራመተ፣ ተጨበጠ፣ ቆረፈደ

/ በችግር፣ በድህነት ተጎሳቆለ፣ ተሰቃየ

5. ዳረጎት (ስ) ድርጎ / ስጦታ፣ ጉርሻ

6. ቀልጣፋ (ቅ) አንድን ነገር በፍጥነት መስራት የሚችል፤ፈጣን

7. ደለዘ (ግ) ሰረዘ፣ አጠፋ፣ ደመሰሰ(ጽሑፍን በቀለም)

8. ሲራክ (ቅ) ብልህ፣ አዋቂ

9. ረጃ (ስ) ሁለተኛ፤ ተመልሶ የተፈላ ቡና

10. ሐጫ (ቅ) ነጭ፤ በረዶ የሚመስል (ሃጫ በረዶ - ደቃቅ በረዶ)

ለ.

1. ሐ 2. ሀ 3.ለ 4.ሀ 5.ሐ 6. መ

44
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


ሀ. በአራት (ነጠላ፣ ድርብ፣ ድብልቅ፣ ድርብ ድብልቅ)
ለ. 1. ተራ 2. ውስብስብ 3.ተራ 4.ተራ
5. ውስብስብ 6. ውስብስብ 7.ተራ 8.ውስብስብ
ሐ. 1. ሀ. ዛፎችና ቅጠሎች ዳንኪራ ረገጡ።
ለ. ዛፎችና ቅጠሎች ተወዛወዙ።
2. ሀ. ካፊያው መሬቱን ማራስ ጀመረ።
ለ. ትኩስ የአፈር ሽታ አፍንጫውን ወጋው።
3.ሀ. በምድር ላይ እርግቦች አሉ (ይኖራሉ)።
ለ. በምድር ላይ እባቦች በርካታ ናቸው።
4. ሀ. እንደ ውሃ ዝም ብሎ ፈሰሰ።
ለ. (እሱ) የህይወት እንቅፋት ነው።
ሐ. ታላላቆቻችን መክረውናል።
5. ሀ. ምድር አረንጓዴ ቀሚሷን እንደገና ለበሰች።
ለ. ምድርን እንንከባከባት
6. ሀ. ወላጆቼ ወደ ገበያ ሄዱ። ሐ. ወላጆቼ ከገበያ መጡ።
ለ. ወላጆቼ አትክልትና ፍራፍሬ ገዙ።
7. ሀ. ግዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም።
ለ. የወደፊት ህልማችንን እናሳካ።
8. ሀ. እህቴና እኔ ወላጆቻችንን በአቅማችን የቤት ስራ እናግዛቸዋለን።
ለ. እህቴ ቤት አጸዳች።
ሐ. እኔ ምግብ አበስላለሁ።
መ. (የተለያዩ መልሶች)

45
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ አራት
በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት

(የክፍለጊዜ ብዛት8)

የሚጠበቁ ውጤቶች

ተማሪዎች ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ፡-

 የተለያዩ ተናጋሪዎችን ሃሳብ በማዳመጥ ትንተና ይሰጣሉ።


 የቀረበ ጽሑፍን አንብበው ይረዳሉ።
 ፈሊጣዊ አገላለጾችን በንግግራቸው እና በጽሁፋቸው ውስጥ ይጠቀማሉ።
 ለቃላት ተመሳሳይ እና ተቃራኒ ፍቺዎችን ይሰጣሉ።
 ፈሊጣዊ አነጋገሮችን ትጠቀማላችሁ፤
 ድርሰት ይጽፋሉ።
 የቃል ክፍሎችን ለይተውያመለክታሉ።

የማስተማሪያ ዘዴ

 የጥንድና የቡድን ስራ መስጠት


 የውይይት ዘዴን መተግበር
 አሳታፊ ገለጻ ብልሃትን መገልገል
 የጥያቄና መልስ ስልት
 ድጋፍና ማበልጸጊያን እንደአስፈላጊነቱ መጠቀም

46
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 አዳምጠው ተመሳሳይ አጠቃላይና ዝርዝር መረጃዎችን ይለያሉ።


 ያዳመጡትን በራሳቸው ቃል መልሰው ይናገራሉ።

በዚህ ንዑስ ትምህርት ክፍል መቻቻልን በተመለከተ በመምህር የሚቀርብን ምንባብ


ተማሪዎች ያዳምጣሉ። በዚህም አጠቃላይ እና ዝርዝር መረጃን ለይቶ የማመልከት
አቅምን ያጎለብታሉ ተብሎ ይጠበቃል።መቻቻልን በተመለከተ የተለያዩ ታዋቂ
ሰዎች የሰጧቸውን አስተያየቶች በማዳመጥም ምን ለማለት እንደተፈለገ መልሰው
ትንታኔም ይሰጣሉ። ይህም የሌላን ሰው ሀሳብ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የመመልከት
እድል ይፈጥርላቸዋል። ስለሆነም እባክዎ መምህር ለዚህ የሚሆን አውድ በመፍጠር
ተማሪዎችዎን በንቃት እንዲሳተፉ ያበረታቷቸው።

ቅድመ ማዳመጥ

መምህር ወደ ዋናው የማዳመጥ ተግባር ከመግባትዎ በፊት ተማሪዎችዎ መቻቻልን


በተመለከተ ያላቸውን የቀደመ እውቀት እየፈተሹ እንዲጠቀሙ የቅድመ ማዳመጥ
ጥያቄዎቹን አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲመለሱ ያድርጉ። የቀረቡት ጥያቄዎች
ሦስት ሲሆኑ መጀመሪያ በግል ተሰርተውና ቀጥሎ ደግሞ በቡድን ውይይት ዳብረው
ለክፍሉ ምላሾቻቸው እንዲቀርቡ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው። ለቅድመ ማዳመጥ
የሚያዘው ጊዜ ግን የተለጠጠ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባል (ቢበዛ እስከ 7 ደቂቃ)

የመቻቻልጀግኖች

የተለያዩ ሃይማኖት፣ እምነት፣ አመለካከት፣ አስተሳሰብ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ ብሔር፣ ሕዝብ፣


ወዘተ ባለበት ኅብረተሰብ ውስጥ ለመቻቻል ሲባል የሚከፈል የመስዋዕትነት ዓይነቱ
እጅግ በጣም ብዙ ነው።መከፈሉ ግን ዋጋ አለው።በመቻቻል ሰላም ይሰፍናል።
አብሮ መኖር ይፈጠራል። የሰው ሕይወት፣ንብረት፣የሥራጊዜ፣ወዘተ የበለጠ

47
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እንዳይጠፋ ያደርጋል። ያለምንም ጥርጥር ይህችን አገር ወደ ተሻለ የታሪክ አድማስ


ልናሸጋግራት የምንችለው መቻቻልን በመካከላችን ስናሰፍን ብቻ ነው።

ለመሆኑ ስለመቻቻል በዓለም የታወቁ የመቻቻል ጀግኖች (ሊቃውንት) ምንብለዋል?


ነገሩ በጣም ሰፊ ቢሆንም በጥቂቱ እንመልከተው።

ዓለም በግንባርቀደምነት ከሚጠራቸው የመቻቻል ጀግኖች መካከል ደቡብ


አፍሪካዊው ኔልሰንማንዴላ አንዱ ናቸው።እ.ኤ.አ ጁላይ 18 ቀን 1918 የተወለዱት
ኔልሰንማንዴላ፤የመረረ ጥላቻን፣ የቀለምና የዘርልዩነትን፣ ኢ-ፍትሐዊ አስተዳደርን
ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል።

እኚህም ታላቅ ሰው ከድል በኋላ ሕዝብን የበደሉ ሰዎችን ሁሉ ይቅር በማለት


በአገራቸው የተቻቻለ ኅብረተሰብ ይኖር ዘንድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ
ታግለዋል።እኚህ የኖቤልሽልማት ባለቤት፤ «የሰውልጅ ታላቅ ክብር ከመውደቁ ላይ
ሳይሆን በወደቀ ቁጥር ለመነሳት ከመቻሉ ላይነው» በማለት ተቻችሎ ለመኖር ሲባል
የሚከፈል መስዋዕትነት ቢኖርም ተስፋ ሳይቆርጡ መቀጠል
አስፈላጊመሆኑንያስታውሱናል።

እንደኔልሰንማንዴላ ሁሉ አገራቸውን ከእንግሊዝ ቅኝአገዛዝ ያወጡት


ማሐንዳስካራማቻድጋንዲ (1869-1948) በሕይወታቸው ከፍተኛ ፈተና ያሳለፉ
የመቻቻል ጀግና ሲሆኑ፣ እሳቸውም «የተለወጠች ዓለምን ለመመልከት የምትሻ ከሆነ
ራስህ ተለወጥ» ይላሉ።

ቻይናዊው የቡድሃ ሃይማኖት አባትዳላይላማ 14ኛ (ላሞዞንደሩብበ1935 ተወለዱ)


በሕይወት ዘመናቸው ስለሰላም፣ ስለመቻቻል፣ ስለፍቅር፣ስለአብሮመኖር በሰበኩ
ከፍተኛ መንገላታት፣ስቃይና ስደት ደርሶባቸዋል። ይሁን እንጂ እሳቸው «በሚቻለው
ሁሉ ሩሁሩሆች ሁኑ፣ ያምምንጊዜምይቻላል፤ ደስታ ተዘጋጅቶ የሚገኝ ሳይሆን
ከራስህ ድርጊት የሚገኝነው፤» በማለት ሰዎች ተቻችለው ለመኖር ተግተው
መሥራት እንዳለባቸው አበክረው ያስገነዝባሉ።በእኚህ ታላቅ ሰው አባባል መቻቻልን

48
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ተግባራዊ ስናደርግ ጠላታችን ብለን የፈረጅነው አስተማሪያችን ሆኖ ልናገኘው


እንችላለን።

ዕውቁ ሊባኖሳዊ ደራሲ ኸሊልጂብራን (1883-1931) ብዙ መጻሕፍት በመጻፍ


የታወቀና ለዓረብ ሥነጽሑፍ በዘመናዊ መንገድ መዳበር አስተዋጽኦያደረገነው።
«አንተወንድሜነህ፤እኔምእወድሃለሁ።በቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ውስጥ
ተንበርክከህ ስታመልክ አፈቅርሃለሁ።አንተም ወንድሜ በመስጊድ ውስጥ ፀሎት
የምታደርሰው እንደዚያው።የገናናው ፈጣሪያችን የፍቅር ጣቶች የተዘረጉት ለሁሉም
ስለሆነ፣ለሁሉም ምሉዕነት መንፈስ እየሰጡ ስለሆነና ሁላችንንም ለመቀበል በጉጉት
የሚጠብቅ ስለሆነ እኔና አንተ ሁላችንም የአንድ ሃይማኖት ልጆችነን፤›› ማለቱ
ይታወቃል።

ታዋቂው ሩሲያዊው ድንቅ የሥነጽሑፍ ሰው ቶልስቶይ፤ «ሁሉም ሰው ለመለወጥ


የሚፈልገው ሁሉንም ሰዎች ነው፤አንድም ሰው ግን ራሱን ለመለወጥ ጥረት ሲያደርግ
አይታይም፤» በማለት ለመቻቻል ከሁሉ አስቀድሞ ራስን መለወጥ እንደሚያስፈልግ
በነዚህ እምቅቃላት ያስተምረናል።

እንደ ብልህ ውድ የአሜሪካ ልጅ የሚቆጠሩት ፕሬዚዳንት ጆንኤፍኬኔዲ (1917-


1963) በበኩላቸው፤ «ልባችንና ዕውቀታችንን አስተባብረን ከልብ ብንሠራ፣
የዘረኛነትንና የአለመቻቻል አመለካከትን ለመቀየር ብንችል፣በሕይወት ዘመናችን
ያሉ ሕፃናት የኅብረብሔራትን ውበት ሊያደንቁ እንደሚችሉ በሀቅአምናለሁ።ይህም
ሳይሆን ቀርቶ ልዩነታችንን ልናቆም ካልቻልን ቢያንስ ዓለማችንን ለልዩነት ምቹ
ልናደርጋት ይገባል» በማለት ለሰዎች ተቻችሎ መኖር ጥረት መደረግ እንዳለበት
አሳስበዋል።

በአጠቃላይ ሁሉም ሰው ሰላም፣መቻቻልና አብሮ መኖርያስፈልገዋል እናም፣ለሁሉም


ዕድሜና ለሁሉም ሕዝብ እንዲሁም ለእናትአገራችን ሰላም፣መቻቻልና አብሮ መኖር
ያስፈልጋቸዋል።ሁሉም ሰዎች ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ፣ቀን ከሰዎች ጋር
ሲገናኙና ሌሊት ለመተኛት ጋደም ሲሉ የሰላም ቀንእና ሌት እንዲሆንላቸው
49
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ይመኛሉ።ሰላም የሰፈነበት ቀንእና ሌሊት ከሁሉም ስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ


ነውና።በሰላምና በፍቅር አብሮ መኖርና መቻቻል ዛሬም ወደፊትም አስፈላጊ
ናቸው።በመሆናቸውም በየዘመኑይደገማሉ።ይደጋገማሉ።

(የመቻቻልጀግኖች፤በተሾመብርሃኑከማል (https://www.addisadmassnews.com))

የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች (ድህረ ማዳመጥ)


በአዳምጦ መረዳት ክፍል የተደመጠውን ምንባብ መሰረት ያደረጉ የተለያዩ
ጥያቄዎች ቀርበዋል። እነዚህን ጥያቄዎችም በግል፣ በጥንድ እና መጨረሻ ላይም
በቡድን በመሆን እየተወያዩ ምላሽ የሚሰጡባቸው ይሆናል።

ከድህረ ማዳመጥ ጥያቄዎቹ በተጓዳኝ የቃላት ፍች ተረድኦታቸውን ለመፈተሽ ይረዳ


ዘንድ ከተደመጠው ምንባብ የወጡ ቃላትን ከአውዳቸው ለመረዳት እንዲሞክሩ
የሚያስችል ተግባር ቀርቦላቸዋል። ተግባሩንም መጀመሪያ በግላቸው በመሞከር
ቀጥሎ እንደክፍል በጋራ እየተወያዩ ምላሽ እንዲሰጡባቸው ያድርጉ። የተማሪዎቹን
አፈጻጸም ምዘናም ከዚሁ ጋር በማያያዝ ሊያካሂዱት ይችላሉ። በመጨረሻም እርስዎ
የማረጋገጫ ሀሳብ በማቅረብ ትምህርቱን ይቋጩላቸው።

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 የተከባብሮ መኖርን ጠቀሜታ በተመለከተ መረጃ አሰባስበው በቃል


ያቀርባሉ፤
 ዝግጅት አድርገው ቃለመጠይቅ ያካሂዳሉ፤
 የገጸባህሪያትን ምልልስ አጥንተው በቃል ይተውናሉ፤
 የጠያቂና የተጠያቂነትን ሚና ይጫወታሉ (ቃለ ምልልስ ያደርጋሉ)።

መምህር በመናገር ትምህርት ክፍል ተማሪዎች መረጃ አሰባስበው በልዩነት ውስጥ


ስላለ አንድነት ጠቀሜታ ቃላዊ ጽብረቃ ያቀርባሉ። እንዲሁም

50
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ቃለመጠይቅማድረግን በተግባር ይለማመዳሉ።ስለሆነም አስቀድመው ዝግጅት


በማድረግ አቅርቦቱን በተሳካ መልኩ እንዲያካሂዱ በቂ የመዘጋጃ ጊዜ እንዲሰጧቸው
ይጠበቃል። ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ሲቀርቡም ሁሉንም ተማሪዎች ባሳተፈ
ሁኔታና የመናገር እድሉንበሚያስገኝ መልኩእንዲከናወን ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በአማራጭነት ከቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል መርጠው ወይም


የራሳቸውን የመናገሪያ ጉዳይ ላይ ዝግጅት ያለው መደበኛ ንግግር በየግላቸው
እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባርም ቀርቧል። ይህም የተማሪዎችን በሰዎች ፊት
የመናገር እድልን ከመስጠቱም ባሻገር በራስ የመተማመን አቅምን እንዲያጎለብቱ
ያስችላቸዋል።

ተማሪዎች የገጸባህሪያትን ምልልስ አጥንተው በሚና ጨዋታ መልኩ ለክፍል


ጓደኞቻቸው እንዲያቀርቡ የሚጋብዘው መልመጃም ሌላኛው የመናገር ክሂልን
ለማለማመጃነት የቀረበነው። (በአበዳሪና ተበዳሪ መካከል ያለውን ስነልቦናዊ
ልዩነት(ክፍተት) አንስተው የበላይነትና የበታችነትን የሚያመላክቱት አገላለጾች
የትኞቹ እንደሆኑ እየተወያዩ እንዲያስረዱ እድልም መስጠት ይችላሉ።)

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት በሚከናወኑበት ወቅት ጊዜው ተብቃቅቶ


ካልተሸፈነ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ ከሌሎች ጋር ተዳብሎ ሊቀርብ ይችላል፤ የመዘጋጃ፣
የማቅረቢያ እና የመገማገሚያ ደቂቃዎችም ሊመደቡለት ይገባል።

በአጠቃላይ የንግግር መለማመጃዎቹ የየተግባራቱ ትዕዛዞች በሚያመለክቱት


መሰረት የሚተገበሩ እንዲሆኑ እባክዎ መምህር ቅድመ ዝግጅት አድርገው በአግባቡ
እንዲፈጸሙ የበኩልዎን አስተዋጽዖ ይወጡ፤ ምዘናዎንም በዝግጅትና አቅርቦት
ወቅት ያከናውኑ። ሁሉንም ክሂሎች በተናጠል ማየቱና መመዘኑ የተማሪዎቻችንን
ሁሏቀፍ የቋንቋ ችሎታ ለማወቅ የሚያስችል መሆኑን መረዳትም ይገባል።

51
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 ስለብዝኀነት መገለጫዎች ለይተው ይናገራሉ።


 በልዩነት ውስጥ ስላለ አንድነት ጠቀሜታ ያስረዳሉ።
 ንባብን በተግባር እየተለማመዱ አንብቦ የመረዳት ጥያቄዎችን ይመልሳሉ።

መምህር የማንበብን ክሂል በዋነኝነት ትኩረቱ ያደረገው ትምህርት በዚህ ክፍል


ይቀርባል። የማንበብ ክሂል ደግሞ ሊጎለብት የሚችለው በማንበብ ነው። የክፍል
ውስጥ ማንበብ እንደመነሻ የሚያገለግል እንጂ በራሱ ምሉዕ አይደለም፤ ስለሆነም
ተማሪዎችዎ ይህንን አጠቃላይ ህይወታቸውን የሚመሩበትን ክሂል ሌሎች
የትምህርት አይነቶችንም ለመካን እጅግ ወሳኝ ነው መሆኑን በመረዳት በምሉዕነት
ክሂሉን እንዲያጎለብቱ ከክፍል ውጪ ባለው አለምም ማንበብን ሆነኝ ብለው
ደጋግመው እንዲከውኑት በአጽንዎት ይምከሯቸው።

እባክዎ መምህር ተማሪዎችዎ የቅድመማንበብ ጥያቄዎችን ከሰሩ በኋላ


የቀረበላቸውን ‘የብዝኀነት ህብር' የተሰኘ ምንባብ እንዲያነቡ ሁኔታዎችን
ያመቻቹላቸው፤ ሁሉም የተግባሩ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋጡ። በማንበብ
ወቅትም የቀረቡትን የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎች እየመለሱ እንዲሄዱ ያሳስቧቸው።
ሙሉውን ምንባብ አንብበው ሲጨርሱም ምንባቡን መልሰው እያዩ የድህረማንበብ
ጥያቄዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ ያበረታቷቸው። አፈጻጸሙንም እየተዘዋወሩ
ይመልከቱ። በእለቱ ጥያቄዎቹን መልሰው ካልጨረሱም በአማራጭነት በየቤት ስራ
መልክ ሰርተው እንዲመጡና ሲመጡም እርስዎ ደብተሮቻቸውን ሰብስበው
በማረምና ምጋቤ ምላሽ በመስጠት ማስኬድ ይችላሉ፤ በጥያቄዎቹ ላይ የጋራ
ውይይት ማድረግም ሌላው አማራጭ ነው።

52
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አራት፡ መጻፍ (ድርሰት)

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 የድርሰትን ምንነት በትክክል ይገልጻሉ፤


 ድርሰት ለመጻፍ የሚያስችል ቢጋር ይነድፋሉ፤
 ድርሰት ይጽፋሉ።

በትምህርት ክፍል አራት ተማሪዎች ስለድርሰት ምንነትና ድርሰት የመጻፍ ሂደት


ከማወቃቸውም ባሻገር ድርሰት መጻፍን በተግባር ይለማዳሉ። በመሆኑም መምህር
የተማሪዎች መጽሐፍ ላይ የተሰጠውን ማስታወሻ መነሻ በማድረግ ስለድርሰት
ምንነት የተማሪዎቹን የቀደመ ዕውቀት መፈተሽ በሚያስችል መልኩ ጀምረው ገለጻ
እንዲያቀርቡላቸው ይጠበቃል። ይህም አጠር ባለ ማስታዎሻ እንዲታገዝ ይሁን።

ገለጻውና ማስታወሻ መስጠቱ ከተጠናቀቀ በኋላም በክፍል ውስጥ በመረጡት ርዕስ


ቢጋር አዘጋጅተው የየራሳቸውን ድርሰት እንዲጽፉ ያበረታቷቸው። አስቀድመው
ለቢጋር ዝግጅት የሚሆን ጊዜ (እስከ 10 ደቂቃ) ይስጧቸው፤ ሲጨርሱም
ከብጤዎቻቸው ጋር ቢጋሮቻቸውን ተቀያይረው እንዲተራረሙ ያድርጉ። ከዚያም
ወደ ዋናው ጽሑፍ እንዲገቡ መመሪያ ይስጧቸው (15-20 ደቂቃ)፤ እየተዘዋወሩም
ሂደቱን ይቃኙ። ሲጨርሱም የተወሰኑ ተማሪዎች በንባብ ድርሰቶቻቸውን
እንዲያቀርቡ እድል መስጠት ይችላሉ ወይም ስራዎቻቸውን ሰብስበው እርማት
ይስጡባቸው (10-15 ደቂቃ)።

በቀጣዩ የትምህርት ክፍለጊዜ በተመሳሳይ መልኩ የድርሰት መጻፉን ልምምድ


ይገፉበት ዘንድ‘መርካቶ' በሚል ርዕስ የተነደፈውን ቢጋር መነሻ በማድረግ ሦስት
አንቀጽ ያለው ድርሰት እንዲጽፉ እገዛ ያድርጉላቸው። ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ
መሆናቸውን እየተከታተሉም አፈጻጸማቸውን ይገምግሙ። በመጨረሻም እንደክፍል
ተማሪዎችዎ ብዛት ስራዎቻቸውን ሰብስቦ በማረም ወይም በጥንድ ወይም በቡድን
እንዲተራረሙ በማድረግ ተገቢውን ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።

53
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በተግባር አራት ስርም ፈሊጣዊ አነጋገሮች ቀርበው ፍች እንዲሰጣቸውና ፍች


ከተሰጣቸው በኋላ አንቀጽ እንዲጻፍባቸው ተጠይቋል። በመሆኑም ተማሪዎችዎ
ትዕዛዙን ተከትለው በየቤት ስራ መልክ እንዲሩት ያድርጓቸው።

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ተጨማሪ ድርሰት የመጻፍ ተግባሮችን በግል ስራ መልክ


ሊሰጧቸውና ልምምዳቸውን ከክፍል ውጭም እንዲያጠናክሩ ሊያደርጓቸው
ይችላሉ።

ክፍል አምስት፡ ቃላት

ተማሪዎች የቃላት ትምህርት ክፍልን ከተከታተሉ በኋላ፡-

 የፈሊጣዊ አነጋሮችን ምንነት ይናገራሉ፤


 ለፈሊጣዊ አነጋገሮች ፍች ይሰጣሉ፤
 ለቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ ይሰጣሉ።

በዚህ ክፍል ፈሊጣዊ አነጋገሮችን ከፍቺያቸው ጋር ማዛመድን የሚጠይቅ መልመጃ


ቀርቧል፡፡ ይህም በግል የሚሰራ ሲሆን፣ በመቀጠል በጥንድ ወይም በቡድን መልሶቹ
ላይ ውይይት ሊደረግባቸው ይችላል።

በፈሊጣዊ አነጋሮች ትምህርት ስር ሌላው ተግባር ተማሪዎች ለቃላት ተመሳሳይ


እና ተቃራኒ ፍቺ እንዲሰጡ እድል የሚፈጥር መልመጃ መስራት ነው። ስለሆነም
መምህር በሁለት ተከፍለው የቀረቡትን ቃላት ተማሪዎች ትዕዛዛቱን ተከትለው
ምላሽ እንዲሰጡባቸው ያድርጉ። የምላሾቻቸውን ትክክለኛነት ያጢኑ።

ለየክፍለ ጊዜዎቹም ክለሳና ማጠቃለያ መስጠት እንዲሁም የየክፍለጊዜው


ከትምህርቱ የሚጠበቁት ውጤቶች መሳካት ያለመሳካታቸውን ማረጋገጡ
የመምህራን ዋነኛ ተግባር መሆኑን አይርሱ።

54
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 የአማርኛ ቃላትን በየቃል ክፍላቸው ለይተው ያውቃሉ።


 ቃላትን በየቃል ክፍላቸው ይመድባሉ።

መምህር በተማሪ መጽሐፍ ውስጥ የተገለጹት የአማርኛ የቃል ክፍሎች አምስት


ናቸው (ስም፣ ቅጽል፣ ግስ፣ ተውሳከ ግስ እና መስተዋድድ)።የቀረበውን ማስታወሻ
መነሻ በማድረግም ገለጻ ያቅርቡላቸው፤ ተጨማሪ ምሳሌዎችም ይስጧቸው። አጠር
ያለ የጽሑፍ ማስታወሻም መያዛቸውን ያረጋግጡ። የአማርኛ ቃላትን በየክፍላቸው
መመደብ የሚያስችላቸው አቅም እስኪጎለብትም መለማመጃዎን በማቅረብ እገዛ
ያድርጉላቸው (ለምሳሌ የተለያዩ ቃላትን በማቅረብ በየቃል ክፍላቸው
እንዲመድቧቸው ማድረግ)።

በመጨረሻም ተማሪዎችዎ በመመሪያ መጽሐፋቸው ላይ የቀረቡላቸውን


መልመጃዎች በመጻፍ እንዲሰሩ ያድርጓቸው፤ አወንታዊ ምጋቤ ምላሽም
ይስጧቸው።

ውድ መምህር የአማርኛ ቃላት በተለያየ ጊዜ በተለያየ አከፋፈል እንዲቀርቡ ሲደረግ


ይስተዋላል፤ ገበያ ላይ የሚገኙ የተለያዩ መጽሐፍትም በቃል ክፍሎቹ ምደባ ዙሪያ
ግልጽ የሆነ ስምምነት እንደሌለ አመላካች ናቸው።ስለሆነም እርስዎ እነዚህን
እውነታዎች ለተማሪዎችዎ በመጠቆም ቃላቱን በየክፍላቸው የመከፋፈሉ ሁኔታ
መለያየት ብዙም ሊያስጨንቃቸው እንደማይገባና ጸሐፊዎች በገባቸውና ሌሎች
ቋንቋዎችን (በተለይ እንግሊዝኛን) መሰረት እያደረጉ ሊከፋፍሉ እንደሚችሉ
መረዳት እንዳለባቸው ብቻ ያሳስቧቸው። በእነሱ ክፍል ደረጃም የቀረበላቸውን
አከፋፈል ብቻ ልብ እንዲሉ ይደረግ።

55
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በምዕራፉ የቀረቡ መልመጃዎችና ተግባራት መልሶች


ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ
ቅድመ ማዳመጥ
1. መቻቻል ሰዎች ልዩነቶቻቸውን አቻችለው (ሳይጋጩ) በሰላም አብሮ
የመኖራቸውን ጉዳይ የሚመለከት ነው
2. የተለያዩ መልሶች (ልምዶቻቸውን መሰረት ያደረጉ)
3. ህብረታችን ይጠነክራል፣ በችግርና በደስታ ወቅት አብረን እንሆናለን፣ ጠጠላት
መጠቀሚያ አንሆንም፣ ልጆቻችን በሰላም ወጥተው ይገባሉ፣ ደስተኛ ማህበረሰብ
ይፈጠራል…
መልመጃ አንድ
ሀ. ምርጫ
1. መ 2. ሐ 3. ሀ 4. ለ 5.ሀ

ለ. አዛምድ
1. ሠ 2. ረ 3. ሐ 4. መ 5. ለ 6. ሀ

ሐ.

1. መስዋዕትነት - ራስን አሳልፎ መስጠት 5. አበክረው - አጽንዖት ሰጥተው

2. መንገላታት - ውጣውረድ ማሳለፍ 6. የተዘረጉት - የተማጸኑት

3. ይደጋገማሉ - መላልሰው ይከሰታሉ 7. የሰፈነበት - የረበበበት/ያለበት

4. መቻቻል - መተሳሰብ/አለመጣላት 8. ጉጉት- ተነሳስዖት/ምኞት/መሻት

9. ተግተው - ጠንክረው

መ. የተለያዩ መልሶች (የተደመጡ ነጥቦች ይዘረዘራሉ)

56
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

ቅድመ ማንበብ

1. የተለያዩ መልሶች (ሰዎች የተለያየ ፍላጎት፣ አመለካከት፣ ሀይማኖት፣ ጾታ፣


ማህበራዊ ደረጃ፣ እድሜ… ልዩነቶች ቢኖራቸውም እነዚህ ልዩነቶች
ሳያለያዩአቸው አብረው ይኖራሉ)

2. የተለያዩ መልሶች

3. ብዝሃነት - መልከ ብዙነት (ተመሳሳይ) ወግ - ልማድ (ተመሳሳይ)

- አንድ አይነትነት(ተቃራኒ) - ያልተለመደ (ተቃራኒ)

ቀንበር - ሸክም፣ ጫና (ተመሳሳይ) ማቀላጠፍ - ማፋጠን (ተመሳሳይ)

ነጻነት (ተቃራኒ) ማሰናከል (ተቃራኒ)

የማንበብ ጊዜ

1. የተለያዩ መልሶች (የተረዱትን መናገር)

2. ኢትዮጵያ 3. የልዩነት ህብር

የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች

ምርጫ፡- ሀ. 1. መ 2. ሀ 3.መ 4.ሐ 5. ለ

ለ. የቃል መልስ

1. (ተማሪዎች የሚሰጧቸው ተወባይነት ያለው ማንኛው መልስ)

2. ሀይማኖትንና ዘርን ከግምት ያላስገባው የጋብቻና መዋለድ

3. የውጭ ጠላቶች (ወራሪዎች) በመጡ ጊዜ

57
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

4. ትልቅ መነቃቃትን በመፍጠር ትግላቸውን በተደራጀ መልኩ


እንዲያቀለጣጥፉና ሀገሮቻቸውን ነጻ እንዲያወጡ በማድረጉ

5. (የተለያዩ መልሶች)

መልመጃ ሁለት

ሀ. መቻቻል - መተሳሰብ/አለመጋጨት መ. ዘብ - ጠባቂ/በረኛ

ለ. ስብጥር - የተውጣጣ/ከዚህም ከዚያምሠ. አስተናግዳ - ተቀብላ

ሐ. የሚያጎናጽፍ - የሚያቀዳጅረ. መቃቃር - መጣላት/መኳረፍ

ክፍል አራት፡- መጻፍ

መልመጃ ሦስት እና 4 (ተቀባይነት ያላቸው የተለያዩ መልሶች)


ተግባር አራት
ጸጉር ስንጠቃ - ነገር ፍለጋ ዓይነ አፋር (ፊት ለፊት የማያይ፣ የማይናገር)
እግረ እርጥብ - ገደኛ (ገድ ያለው) እጅ በእጅ - ወዲያው (በካሽ)
እጅ አጠረው - ተቸገረ (አቅም አነሰው) ዓይነ ልም - ተንኮለኛ
ሆደ ሰፊ - ቻይ፣ ታጋሽ የግንባር ስጋ - ሚስጢር የማይቋጥር
እግረ ደረቅ - ገደ ቢስ አፍ ለአፍ - በጣም ተጠጋግተው
አይኑን ገለጠ- (ፊደል ቆጠረ) እግረ ጣለው - ድንገት መጣ

መልመጃ አምስት
አዛምድ (ፈሊጦች)
1. ሐ 2. መ 3.ሠ 4.ለ 5. ሀ

58
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መልመጃ ስድስት
1. ተመሳሳይ ፍቺ
ሀ. መቋደሻ- የዶሮ ጨጓራ ሰ. ወሸከሬ - የማይረባ፣ ተልካሻ
ለ. መናጆ - አካሂያጅ ሠ. ወርች - የከብት ፊት እግር ስጋ
ሐ. ህላዌ - መኖር ረ. ቅምጫና - መጠጫ/ከቅል የተሰራ
መ. ሸፍጥ - ተንኮል ሸ. ድርሰት - ጽሑፍ
2.ተቃራኒ ፍቺ
ሀ. ህልም - እውንሠ. አደባባይ - ማጀት/ጓዳ
ለ. ተባረከ - ተረገመ ረ. ብርቅ - ስልቹ/አሮጌ
ሐ. ባላንጣ - ወዳጅሰ. ማክሰም - ማለምለም
መ. የምስራች - መርዶሸ. ንቁ - ፈዛዛ
መልመጃ ሰባት
ሀ. 1. ተውሳከ ግስ 2. መስተዋድድ 3.ስም 4. ግስ 5. ስም
6. ቅጽል 7. ተውሳከ ግስ 8. መስተዋድድ 9. ቅፅል 10.ግስ
ለ. 1. ተውሳከ ግስ 2. ስም 3.መስተዋድድ 4. ግስ
5. ቅጽል 6. ቅጽል 7.ስም 8. ተውሳከ ግስ/ስም
ሐ. የተለያዩ መልሶች

59
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ አምስት
ቋንቋዊ ለዛ
(የክፍለጊዜ ብዛት 8)

የሚጠበቁ ውጤቶች

ተማሪዎች ከዚህ ምዕራፍ ትምህርት በኋላ፡-

 የቀረበ ታሪክ አዳምጠው ጥያቄዎች ይመልሳሉ።


 የቋንቋ ለዛን ፅንሰ ሀሳብ ይገልጻሉ።
 የቋንቋ ለዛ ማስገኛ ዘውጎችን ይዘረዝራሉ።
 ምሳሌያዊ ንግግሮችን፣ እንቆቅልሾችን፣ አፈታሪኮችን ይለያሉ።
 የተለያዩ የቋንቋ ለዛ ማስገኛ ስልቶች ጭብጦችን ይተነትናሉ።
 ለዛ ያለው ቋንቋ እየተጠቀሙ ሀሳባቸውን ይገልጻሉ።

የማስተማሪያ ዘዴ

 ከዝርዝር ወደ አጠቃላይ ወይም ከአጠቃላይ ወደዝርዝር የማስተማሪያ


ስልቶችን ተጠቅሞ ማስተማር።
 ተማሪን ማዕከል ያደረጉ የማስተማር ዘዴዎችንና ብልሃቶችን መጠቀም።
 ትምህርቱን የእለት ከእለት ህይወታቸው ጋር እያያዙ ማቅረብ
 ከክፍል ውጪ የሚሰሩ መስተጋብርን የሚፈጥሩ ተግባራትን እንዲሰሩ
ማድረግ
 የቋንቋ ክሂሎቹን እያቀናጁ ማቅረብ
 የክፍል አደረጃጀቱን በግል፣ በጥንድ፣ በቡድንና በጋራ ለመስራት የሚያስችል
ለማድረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
 አረፍተነገር ጽፈው እንዲያነቡ ማድረግ
60
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አንድ፡ማዳመጥ

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 ተረት በንቃት አዳምጠው ጥያቄዎች ይመልሳሉ።

ቅድመ ማዳመጥ

በክፍል አንድ ስር የተማሪዎችን የማዳመጥ ፍላጎት የሚያነሳሱ ጥያቄዎች


ቀርበዋል። እባክዎ መምህር የቅድመማዳመጥ ጥያቄዎቹን መልሶች ተቀብለዋቸው
ወደ ዋናው ትምህርት ይግቡ። በሚያዳምጡበት ጊዜም አጫጭር ማስታወሻ የመያዝ
ልምድ እንዲያዳብሩ ምክር ይለግሷቸው።

ሀ. ስነቃል በቃል የሚፈጠር፣ በቃል የሚኖርና በቃል ከትውልድ ትውልድ


የሚተላለፍ ውበት ያለው የሰው ልጅ የፈጠራ ስራ ነው፤ አንዱ የስነጽሑፍ ዘርፍ
ነው ብለው የተማሪዎችዎን ምላሽ (ስለስነቃል የሰጡትን) ሊያጠቃልሉላቸው
ይችላሉ። አይነቶቹም በዝርው የሚቀርቡና በግጥምና ዜማ የሚባሉ ናቸው።(ተረት፣
አፈታሪክ፣ ሀተታ ተፈጥሮ…፤ የልጆች ጨዋታ፣ ባህላዊ ዘፈኖች፣ ሙሾ…)

ለ. ተረት ሙሉ በሙሉ ፈጠራ ሲሆን፣ አፈታሪክ ግን አንድ እውነተኛ ክስተትን


መነሻ በማድረግና ፈጠራ በመጨመር የሚነገር ትረካ ነው።

የቅድመ ማዳመጥ ተግባሩን ካጠናቀቃችሁ በኋላ የማዳመጥ ዝግጁነታቸውን


በማረጋገጥ በቀጥታ ወደ ማንበቡ (የሚደመጠውን ጽሁፍ ወደ ማቅረቡ) ይሂዱ።
አንብበው ሲጨርሱም የድህረ ማዳመጥ ጥያቀዎቹን በጽሑፍ እንዲመልሱ
ያሳስቧቸው፤ ተፈጻሚነቱንም ይከታተሉ። በመጨረሻም ምላሾቻቸውንለክፍሉ በቃል
እንዲያጋሩ ይጋብዟቸው።

61
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ቃል አፍራሹ ተኩላ

ድሮ ድሮ በጣም የተራበ ተኩላ ነበረ። ረሃቡን ለማስታገስም አንዲት አይጠ መጎጥ


አይቶ ለመያዝ ሞከረ፤ ይሁን እንጂ አይጠ መጎጧ ሩጣ አመለጠችው።ጦጣም አይቶ
ለመያዝ ሲሞክር አምልጣው ዛፍ ላይ ወጣች። ጥቂት ቆይቶ የሰባ አነስተኛ አይጥ
ተመለከተ። “ይህንን ይዤ ብበላው ጥሩ ሳይሆን አይቀርም፣” ብሎም በውስጡ አሰበ።

አይጡም ቀድሞ አይቶት ኖሮ ወደ አንድ ትልቅ አለት ስር ሮጠና ዘሎ ወደ ጉድጓዱ


ገባ። ተኩላውም “ይህለኔ ቀላል ነው ቆፍሬ አወጣዋለሁ” ሲል አሰበ። ወደ ትልቁ
አለት ስርም በፍጥነት ገባና መቆፈር ጀመረ። ቶሎ ቶሎ እየቆፈረም ጉድጓዱን
አራቀውና ሳያስበው አለቱ ተንከባሎ ወደቀበት። የእጅ መዳፉም በአለቱ ተያዘበት።
መንቀሳቀስም አልቻለም።

“እባካችሁ ድረሱልኝ! እርዱኝ! እርዱኝ!” እያለም መጮህ ጀመረ። ጥንቸልም ይህንን


የጩኸት ድምጽ ስትሰማ እየሮጠች መጣች።

“ምን ነክቶህ ነው እንደዚህ የምትጮኸው ወንድም ተኩላ?” ስትልም ጠየቀችው።


እሱም፣ “አንድ የሰባ አይጥ አግኝቼ አድኜው ልበላ አስቤ ነበር፤ ግን ይሄው
እንደምታይኝ አለት መዳፌ ላይ ወደቀብኝ። እባክሽ እርጂኝ” በማለት ተማጽኖውን
አቀረበ።

“ምን ይሻላል? ባግዝህ ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን እንደምታየኝ ትንሽና አቅም የሌለኝ


ነኝ፤ አለቱ ደግሞ ትልቅ ነው። ይህ የሚቻለኝ አይመስለኝም። ግን ይበለውና
ባነሳልህ ምን ታደርግልኛለህ?” ስትል በትህትና ጠየቀችው።

“ኧረ ለዚህ ምንም አታስቢ፤ አንቺ ብቻ ከዚህ አደጋ ገላግይኝ እንጂ አይተሽው
የማታውቂውን አይነት ምርጥ እራት ሰርቼ አበላሻለሁ።” ሲል ቃል ገባላት።

“በጣም ጥሩ፤ እንዲህ ከሆነ ላግዝህ እሞክራለሁ፣” አለች ጥንቸል። ጠጋ ብላም አለቱን
ገፋ አደረገችው። አለቱ ፈጽሞ አይንቀሳቀስም። ሀይሏን አሰባስባ በተደጋጋሚ

62
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሞከረችው። በመጨረሻም ተሳካላትና ድንጋዩን ከተኩላው መዳፍ ላይ ማንሸራተት


ቻለች።

በዚህ በጎ ስራዋም ጥንቸል ፈገግ አለች። “አሁን ቃል የገባህልኝን እራት ለመጋበዝ


ዝግጁ ነኝ!” ስትልም ደስ በሚል ስሜት ውስጥ ሁና ተናገረች።

“የምን እራት ነው የምትይው?” ሲል መለሰ ተኩላ። “ቀልድሽን አቁሚ፤ ባይሆን እኔ


በጣም ርቦኛል፤ አንቺ ደግሞ ትንሽና ጣፋጭ ትመስያለሽ። ስለዚህ ልበላሽ
ወስኛለሁ።”

“ምን?! እኔ ከአደጋ አትርፌህ! መልሰህ እኔን ልትበላ? እራት እሰራልሻለሁ ብለህ


ቃል ገብተህልኝስ አልነበር?” ስትል ጥንቸል ፍርሃት ውስጥ ሆና ተናገረች።

“እኔ ተኩላ ነኝ፤ አንቺ ደግሞ ጥንቸል፣” መለሰ ተኩላ፣ “ተኩላዎች ደግሞ ሁልጊዜም
ቢሆን ጥንቸሎችን ይመገባሉ። ከኔ ጋር ክርክር ውስጥ ባትገቢ ይሻልሻል፣”
አፈጠጠባት።

“ይህ በጣም ፍትሐዊ አይደለም፤ ሽማግሌዎችን ፈልገን ምክራቸውን መስማት


ይኖርብናል፣” በማለት ጥንቸል አማራጭ ሀሳብ አቀረበች።

በዚህም ተኩላና ጥንቸል ተያይዘው ሽማግሌዎች ፍለጋ መሄድ ጀመሩ።


በመጨረሻም ተሳክቶላቸው አንድ አዛውንት ሰው አገኙ።

“እንደምን አሉ?” ብላ ሰላምታ ካቀረበች በኋላ፣ “እባክዎትን ይርዱኝ፤ ይህ ተኩላ


ካልበላሁሽ እያለኝ ነው። ይሁን እንጂ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ህይወቱን ከአደጋ
ታድጌለታለሁ። በትልቅ አለት ተይዞ ሲጮህ ደርሼ ነው ያላቀቅኩት። ምርጥ እራት
እጋብዝሻለሁ ብሉም ቃል ገብቶልኝ ነበር። ይህን ቃሉንም አጥፎ ይኸው ይዤ
ካልበላሁሽ እያለኝ ነው” በማለት የሆነውን ሁሉ ዘረዘረች።

63
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

“ይህማ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፤ ተኩላ አንተ ጥንቸልን ልትበላት አይገባም።


የዋለችልህን ውለታ መዘንጋት የለብህም። በል አሁን ተዋት ትሂድበት።” በማለት
አዛውንቱ ተኩላን ገሰጹት።

“ኦው፣ በፍጹም አይሆንም፤ እኔ አልለቃትም። ማንም ሊያስቆመኝ አይችልም!


እሞክራለሁ ካልክ አንተንም ዘነጣጥዬ ነው የምበላህ” ሲል በቁጣ ተናገረ።

በዚህን ጊዜ አዛውንቱም ፍርሃት አደረባቸው።

“እባክህን እኔንማ አትንካኝ፤ እኔ’ኮ ላስታርቃችሁ ብዬ ነው። ፍርዱ ላይ ምናልባት


ተሳስቼ ሊሆን ይችላል፤ ግን የመጨረሻ ውሳኔ አይደለም፤ ትንሽ ሳልቸኩል
አልቀረሁም።አንተም ልክ ልትሆን ትችላለህ። የመጨረሻውን ውሳኔ ለመስጠት
እንዲመቸኝ ሁኔታውን በደንብ ማጤን አለብኝ። እስቲ አለቱ የታል አሳዩኝ?”
በማለት ተናገሩ።

ቀጥሎ ምን የሚሆን ይመስላችኋል?

“ይህማ ቀላል ነው፤ ምንም ችግር የለውም ኑ ሂደን እንየው፤ ተከተሉኝ፣” በማለት
ተኩላ ፈጥኖ መለሰ።

በዚህም አዛውንቱ ከተኩላውና ጥንቸሏ ጋር ሆነው አለቱ ወዳለበት ስፍራ መጓዝ


ጀመሩ።

ሲደርሱም “አንተ ምን ስታደርግ ነበር?” ጠየቁ አዛውንቱ።

“አይጥ እያደንኩ ነበር፣” መለሰ ተኩላ፣ “አይጧ ዘላ እዚህ ጉድጓድ ውስጥ ገባች፤
ስለሆነም ልያዛት ብዬ ወደ ታች አርቄ ቆፈርኩት። ነገር ግን ይህ አለቱ የእጄ
መዳፍ ላይ ወደቀብኝና አደናቀፈኝ።”

“የትኛው አለት ነው?” በማለት አዛውንቱ ጠየቁ።

“ይኸኛው ነው፣” ሲል ተኩላው አመለከተ።

64
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

“ጥንቸል እንዴት ሆነህ፣ የቱ ጋ ነበር ያገኘችህ?“

“ይኸው እዚህ ጋ፣” ብሎ ተኩላው በርከክ ብሎ የነበረበትን ሁኔታ አሳየ።

አዛውንቱም ወደ ጥንቸሏ እየተመለከቱ፣ “አንቺ ጥንቸል ዋሽተሽኛል፤ አንቺ ትንሽና


ደካማ ስትሆኝ እንዴት ይህንን አለት ልታንቀሳቅሺ ቻልሽ? እኔ አላምንሽም፣”
አሏት።

“ኸረ እውነት አንቀሳቅሼዋለሁ፣ አልዋሸሁም!” ስትል ጮክ ብላ መለሰች።

“እንደዚያ ከሆነ እስቲ እንዴት እንዴት እንዳንቀሳቀስሽው አሳይን፤” በማለት


ጠየቋት።

ጥንቸልም እንደቀድሞው ሁሉ አቅሟን አስተባብራ አለቱን ብትገፋው ተንከባሎ


የተኩላው መዳፍ ላይ ቀድሞ እንደነበረው ሆኖ አረፈ።

“ልክ እንደዚህ ሆኖ ነበር ተኩላውን ያገኘሽው?” ጠየቁ አዛውንቱ።

ጥንቸል ራሷን ፊትና ኋላ በማነቃነቅ አወንታዋን ገለጸች።

“ጥንቸሏ እንደዚህ ሁነህ ነበር ያገኘችህ?” በመቀጠል ቀበሮን ጠየቁት።

“አዎ፣” በማለት እሱም ራሱን በማወዛወዝ መለሰ።

“በጣም ጥሩ፤ አሁን ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት ምቹ ነው፣” አሉ አዛውንቱ


ጉሮሯቸውን እየሳሉ። “አሁን ከዚህ ሩጠሸ ሂጂ ጥንቸል። እኔም ወደ ቤቴ ላዝግም!”

በመጨረሻም ጥንቸልና አዛውንቱ ቃሉን ማክበር የተሳነውን ተኩላ በአለት


እንደተያዘ ጥለውት በሰላም ጉዟቸውን ቀጠሉ ይባላል።

(ከባሌ አካባቢ የተገኘ ተረት፤ ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ፤ Elizabeth Laird, The


Story Project, 1996 in collaboration with MOE)

65
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ተማሪዎችይህንን ንዑስ ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ፡-

 በተወሰኑ የስነቃል አይነቶች ዙሪያ ይወያያሉ።


 ስነቃልን እየተጠቀሙ ሀሳባቸውን ይገልጻሉ።

(ይህ የመናገር ትምህርት ከአንድ በላይ ክፍለጊዜ እንደሚፈጅ ይገመታል)

መምህር በዚህ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ አስደሳች ጊዜን እንደሚያሳልፉ


ይታመናል። ምክንያቱም የስነጽሑፍ አካል የሆነውን ስነቃልን በተመለከተ
ስለሚወያዩና ስነቃሉንም መልሰው የመጠቀም አድልም ስለሚያገኙ ነው።

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ጥያቄዎች (ተግባር 1) ስለስነቃል ዘርፎቹ (ምሳሌያዊ


አነጋገር፣ ተረት፣ አፈታሪክና እንቆቅልሽ…) ያላቸውን ግንዛቤ አንዱ ለሌላው
በማጋራት ውይይት እንዲያደርጉ የሚጋብዙ ናቸው።ስለሆነም ስለምንነታቸው፣
ስለሚሰጧቸው ጠቀሜታዎችና በንግግር ውስጥ እንዴት እንደምንገለገልባቸው
እንዲወያዩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ተፈጻሚነቱንም ይከታተሉ።

በመቀጠል የቀረበውን አጭር ማስታወሻ እንዲጽፉ በማድረግ ስለስነቃል ዘርፎቹ


በውይይት የተደረሰበትን ጭብጥ እንዲያጠናክሩ ያድርጓቸው።

ሌላኛው ክፍል ለስነቃል ዘርፎቹ የሚሆኑ ምሳሌዎች የቀረቡበትና ተማሪዎችዎም


እነዚህን መሰረት አድርገው ጥንድ ጥንድ በመሆን እንዲወያዩ እድል የሚያገኙበት
ነው። በመሆኑም መምህር ሁሉም ተማሪዎች አጋር አግኝተው ምሳሌዎቹ ስለምን
እንደሚናገሩና እንዴት በእውኑ አለም እንደምንጠቀምባቸው በተመለከተ
እንዲነጋገሩ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው። እየተዘዋወሩም ተሳትፏቸውን ይቃኙ።
ውይይታቸውን ሲያገባድዱም ሀሳቦቻቸውን ለሌሎቹ እንዲያጋሩ የተወሰኑትን
ይጋብዟቸው።

66
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በመጨረሻም የየራሳቸውን አራት አራት እንቆቅልሾች በማዘጋጀት (ወይም ሰው


ጠይቀውና አንብበው በማምጣት) ክፍል ውስጥ እንዲጠያየቁ ያበረታቷቸው።ሁሉም
ተማሪ የመናገር እድል ማግኘቱ ላይም ትኩረት እንዲሰጡም ይጠበቃል።

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ

ቅድመ ምንባብ ጥያቄዎች

መምህር የቋንቋ ለዛ ማስገኛ የሚለውን ምንባብ ከማስነበብዎ በፊት በተማሪ


መጽሐፍላይ የቀረቡትን የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች በቡድን በማሰራት
ተማሪዎችዎ ወደእለቱ ትምህርት በተነሳስዖት እንዲገቡ ያድርጓቸው።
የክፍልዎን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ጥያቄዎቹ በጋራ እንዲሰሩ
ማድረግም ይችላሉ።

(መምህር ለቅድመ ማንበብ ተግባራቱ የሚጠቀሙት ጊዜ ከአምስት ደቂቃ


ያልበለጠ እንዲሆን ይመከራል።)

የማንበብሂደት

ከቅድመ ንባብ ተግባራቱ ፍጻሜ በኋላ በቀጥታ ወደ ምንባቡ በመሄድ ምንባቡን


በየግላቸው በለሆሳስ እንዲያነቡ ያሳስቧቸው፤ አፈጻጸሙንም እየተዘዋወሩ
በመመልከት ንቁ ተሳታፊነታቸውን ይመዝኑ።
የማንበብ ጊዜጥያቄ

መምህርተማሪዎች እያነበቡ በመካከል ያነበቡትንና ቀጥሎ የሚመጣውን የምንባብ


ታሪክ ለመገመት የሚያስችሉ ሁለት ጥያቄዎች ቀርበዋል፤ ተማሪዎችዎ
ማንበባቸውን ገታ አድርገው ጥያቄዎቹን እንዲመልሷቸው ጥቆማ ይስጧቸው።

አንብቦመረዳት

ምንባቡን አንብበው ሲያጠናቅቁ የአንብቦመረዳት ጥያቄዎችን ያሰሯቸው።


የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎቹ በሦስት ክፍሎች የተከፈሉ ናቸው (እውነት/ሐሰት፣
67
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ቃላዊ ምላሽ ስጡ እና ለቃላትና ሀረጋት አውዳዊ ፍች መስጠት)። ሁሉንም


በትዕዛዛቱ መሰረት ያሰሯቸው። ምላሾቻቸውንም መሰረት በማድረግ አወንታዊ
ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።

በመጨረሻም ተመሳሳይ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ደብተራቸው ላይ ጽፈው


እንዲያዛምዷቸው ይንገሯቸው።

ምዘና
 ተማሪዎች የቋንቋ ለዛን ፅንሰ ሃሳብ እንዲያብራሩ መጠየቅ።
 ማንባብን በተግባር መለማመዳቸውን በምልከታ ማረጋገጥ
 በማጣመር ወይም በማቧደን ለዛ ያለው ቋንቋ እየተጠቀሙ ሀሳብ ማንሸራሸር
መቻላቸውን መመዘን
 በቋንቋ ለዛ ማስገኛ ስልቶች የተገለጹ ሀሳቦችን መረዳት መቻላቸውን
መፈተሸ

ክፍልአራት፡ ጽሕፈት

ተማሪዎች አንቀጽ የመጻፍ ልምምድ የሚያደርጉበት ስለሆነ ርዕሶች በሃሳብ


የሚስማሙ ከአራት በላይ ምሳሌያዊ ንግግሮችን በመሰብሰብ እንዲጽፉ
ያድርጓቸው መልሶቻቸውንም እርስበርስ እንዲጋሩይንገሯቸው።

ከጻፏቸው ምሳሌያዊ ንግግሮች የተወሰኑትን በመጠቀምም አንቀጽ በመጻፍ


ሀሳባቸውን ይገልጹ ዘንድ ያበረታቷቸው። የጻፉትንም ሰብስበው እርማት
ይስጡበት።

በመቀጠል የቅኔ ጥያቄዎች ህብረ ቃላቸውን በመለየት ሰምና ወርቅ ፍቺ


ምሳሌዎችን በመስጠት አስረዷቸው።በተጫማሪም ቅኔን ለመፍታት የሚያስችሉ
ዘዴዎች ተማሪዎች በቡድን እንዲረዱት ያድርጉና ምሳሌ በመስጠት
ትምህርቱን ተጨባጭ ያድርላቸው።

68
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ቅኔን ከተመለከተው ተግባር በመቀጠል የዘይቤያዊ ግጥሞች ቀርበዋል። እዚህ


ላይምተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት በግጥሞች ውስጥ ያሉትን ዘይቤዎች
በገባቸው ልክ ለመለየት እንዲሞክሩ ያትጓቸው። ስለዘይቤዎቹ ማብራሪያ
እንዲሰጡ ከማድረግ ባሻገርም ሀሳብ በመግለጽ ወቅት እንዲገለገሉባቸው
ያበረታቷቸው።

በጨረሻምከዚህ በታች የቀረቡልዎትን ነጥቦች መነሻ በማድረግ የዘይቤ


አይነቶችና ምሳሌዎቻቸውን አስመልክቶ አጫጭር ማስታወሻዎችን
ያቅርቡላቸው፤ ሁሉንም ነጥቦች ግን በዝርዝር ማቅረብ አይጠበቅብዎትም።
ከተማሪዎችዎ የቋንቋ ደረጃ ጋር ተገቢ ናቸው ለሚሏቸው ብቻ ትኩረት ይስጡ።

የዘይቤአይነቶች

ሰውኛ ዘይቤ

የሰውን ልዩ ልዩ ባህሪያት ፣ ድርጊት፣ መልክ፣ ችሎታና ወዘተ ሰው ላልሆኑ


ማንኛውም ህይወት ያላቸውና የሌላቸው ነገሮች በመስጠትና ልክ እንደሰው
እንደተናገሩና እንዳደረጉ በመቁጠርና የሰው ባህሪና ቋንቋ በማላበስ እንዲሁም
አንደበታዊ በማድረግ የሚፈጠር ዘይቤ ነው።

ምሳሌ ሀ. እህል ዱር አደረ ብቻውንም ዋለ፣

ጠላትእንደሌለውሰውእንዳልገደለ።

ለ. ብዕሩ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

እንቶኔ ዘይቤ

ከሰውኛ ዘይቤ ጋር ተቀራራቢ ሲሆን በአጠገባችንና በቅርብ የሌለን ረቂቅና


ግዑዝ ነገር በህይወት የሌለ እንዲሁም የማይናገሩ ማንኛውንም እጽዋትና
እንሰሳት በቅርብ እንዳሉና መልስ እንደሚሰጡ በመቁጠር የሚመሰረት ዘይቤ
ነው።
ምሳሌ፡- አዕዋፍ በጠዋቱ ተነሳ እምትሉኝ ለምን ይሆን ከተቶ፣

69
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ባማረ ድምጻችሁ መስኮቴ ተንኳኩቶ።


በሉ እኔስ ተነሳሁ ነቃሁኝ ታግየ፣
አዎ! በእርግጥ ነግቷል የሰው እግር ታየ።
ግን ልጠይቃችሁ አዕዋፍ በያይነቱ፣
ነጋ ጠባ ባዮች ሰርክ በየጠዋቱ።
ያነጋችሁት ቀን ባማረ ዜማችሁ፣

ለማን እንደጠባ ግን ታውቅታላችሁ?

ለዋጭ ዘይቤ

በነገሮች መካከል የባህሪ ምስስል በመፍጠር የአንዱን ባህሪና መልክ ለሌላው


በመስጠት የሚፈጠር ነው።

ምሳሌ፡- ገንዘብ ሰርገኛ ነው ሰው ሲያቀርብ ሰብስቦ፣

ድህነት ግን ሲያርቅ ይመስላል ተስቦ።

አነጻጻሪ ዘይቤ

በማይመሳሰሉና ከተለያየ ጎራ በመጡ ሁለት ነገሮች፣ ባህሪዎች፣ ድርጊቶችና


ሃሳቦች መካከል አንድ ተመሳሳይ ገጽታና የጋራ ባህሪ በመውሰድ እያነጻጸረ
የሚያቀርብ ዘይቤ ሲሆን የማነጻጸሪያ ቃላት (እንደ፣ ያክል፣ ይመስል…)
የሚጠቀም ነው።

ምሳሌ፡- ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ፤ ተንከባለለ እንደሙቀጫ

አያዎ ዘይቤ

በሁለት ተቃራኒ ቃላት፣ ሀረጋት፣ አረፍተ ነገሮች ወይም ሃሳቦች የሚመሰረት


ነው። ከላይ ሲያዩት እውነት የማይመስልና ከእውነታው ጋር የሚጋጭ
የሚመስል፣ ጠለቅ ብለን ስንመረምረው ግን ረቀቅ ያለ እውነትነት ያለው
መሆኑን የሚያሳይ ዘይቤ ነው።
ምሳሌ፡- እየሳቁ ማልቀስ፣ የጠገበ ረሀብተኛ፣ ለሞት አንሙትለት፣

70
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ግነት ዘይቤ

ነገሮችንና ሁኔታዎችን ካላቸው ነባራዊ ሁነታ በላይ ሆን ብሎ በማግዘፍና


በማጋነን የማቅረብ ሁኔታ ነው።

ምሳሌ፡- የሰማይ ስባሪ ያክላል

ምጸት ዘይቤ

ሁለት ተቃራኒ መልኮች የሚታዩበት ሲሆን አንደኛው ከላይ የሚደግፍ፣


ሁለተኛው ደግሞ የሚነቅፍና የሚያጥላላ ዘይቤ ነው። ምጸትን ለመረዳት
የተናጋሪውን አጠቃላይ ድምጸት፣ የአካል እንቅስቃሴና የፊት መለዋወጥ
ማስተዋል ያስፈልጋል።

ፐ ፐ፣ አንተማ ንጉሰ ነግስት አይደለህ፣ መች አርሰህ ትበላለህ!?

ተምሳሌት ዘይቤ (symbol)

ተምሳሌታዊ ዘይቤ የአንድን ነገር ወይም ሃሳብ ወይም ደርጊት ለወከል የቆመ
ነው። ትምሳሌታዊ ዘይቤ ዋነኛ ባህሪው ውክልና ነው። አንድ ነግር የሌላ ነገር
ተምሳሌት ነው ሲባል የሚወከለው ነግር በዋናው ምትክ ገብቷል ማለት ነው።

ምሳሌ፡- እርግብ - የሰላም ተምሳሌት

አካባቢያዊ ተምሳሌት

በአንድ አካባቢ የሚገኙ ሰዎች አንድ አይነት ሃሳብን ለማስተላለፍ


የሚጠቀሙበት ዘይቤ ነው። እናትን በሃገር፣ ሚዛንን የፍትህ፣ ሦስት ጉልቻን
ትዳር፣ ቤትን የቤተሰብ፣ ረመጥ፡ን የተስፋና የሃላፊ ጊዜ፣ አገልግልን የእህል
ውሀ፣ ወንዝን ሃሳብ፣ ጥቁር ልብስን ለኢትዩጵያውያን የሀዘን ተምሳሌት ለህንዶች
የደስታ መግለጫ ማድረግ የተለመደ ነው።

አለም አቀፋዊ (ሁለንተናዊ ተምሳሌት)

በተለያዩ ሀገሮች መካከል የሚደረግ የባህል ውርርስ በብዙዎች ተመሳሳይ የሆነ


ሲሆን አበባን ለፍቅር (ተስፋ)፣ መስቀልን ስቃይ፣ መከራን ለትዕግስት፣ ሠዓትን

71
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ለጊዜ፣ የጧት ፀሀይን ለየተስፋ፣ የማታ ፀሀይን ለየእርጅና፣ ልሙጥ ክብ ቀለበት


የትዳር መገለጫዎች ማድረግየተለመደ ነው።

ግላዊ ተምሳሌት

ደራሲው በሌሎች ሠዎች ያልተሞከረ ግን ፍች ያለው ለአንድ አይነት ጠቃሚ


አገልግሎት ሊውል የሚችል ተምሳሌት ሊመርጥ ይችላል። ይህ ተምሳሌት
አገልግሎቱ የሃሳብ ጥልቀትን ለማስገኘት ነው።

ምስያ ዘይቤ
አንድን ሀሳብ፣ ድርጊት፣ሁኔታ፣ባህሪ(ተፈጥሮ) በባህሪም ሆነ በቅርፅ ተመሳሳይ
ይሆናሉ ተብሎ የተገመተን ነገር አብሮ በማምጣት የፊተኛው የኋለኛውን
ይበልጥ እንዲያጎላውና እንዲያደምቀው ለማድረግ የሚገባ ነው።
ምሳሌ፡- ጠዋት ብትታይም ፀሐይ ከፍ ብላ
የማታ የማታ እርሷም ዝቅ ብላ
አይቀርም መጥለቋ አይቀርም መውረዷ
ሰውንም ስናየው ሳለ በህወቱ
እሸት ነው ለጋ ነው በወጣትነቱ
በጠዋቱ ጉዞ ምንም ቢበረታ
አይቀርም መድከሙ ሲመሽ ወደ ማታ

ንቡር ጠቃሽ ዘይቤ

ያለፈ ታዋቂ ክስተትን፣ ታዋቂ ባለክስተትን ከታሪክ ድርሳናት፣ከታላላቅ የፈጠራ


ስራዎች፣ከቅዱሳን መጽሀፍት ወዘተ በመውሰድ ያሁኑን ታሪክና ባለታሪክ
ለማድመቅ የሚያገለግል ዘይቤ ነው።

ምሳሌ፡-እንደ ሎጥ ሚስት ተገትሬ ቀረሁ ፣

ተንኮለኛውን - ኢያጎ

የእዮብ ትዕግስት ይስጥህ

72
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በስመ ሀዳሪ ዘይቤ

መኖሪያውን ጠርቶ ነዋሪውን፣ ነዋሪውን ጠርቶ መኖሪውን ለመግለፅ የሚቻልበት


ዘይቤ ነው።

ምሳሌ፡- አንዲት ቆንጆ ልጅ አየሁ ለማለት አንድ ውብ አፍንጫ አየሁ

ዳኛው አደላብኝ ለማለት ወንበሩ አደላብኝ ማለት

አሊጎሪ ዘይቤ

ለረቂቅ ሀሳብ፣ባህሪ ወይም ድርጊት ተጨባጭነትን ወይም ሰውነትን በመስጠት


የሚመሰረት ነው። ጥበብ፣ድንቁርና፣ትህትና፣ቅንነት የመሳሰሉትን የሰው ባህሪያት
አግዝፎና ተጨባጭ አድርጎ ሰዋዊ ባህሪ አላብሶ ማቅረብ

ምሳሌ፡- በጎል ጥበብ የረቀቀው የቅንነት በረኛ ይሉኝታን ገነደሰው።

ድንቁርናን ትምህርት ካገኛት ከምድረ ገጽ ያጠፋታል።

ወይዘሮ ርህራሄ አቶ ጭካኔን እዝነት አስተማረው።

ሌላው ተማሪዎች የማሰላሰል አቅማቸውን ለማሳደግ የቀረቡ ጅምር ስንኞች


ቅኔያዊ አነጋገር በማድረግ የመጨረሻቸውን ስንኝ እንዲያሟሉ ያድርጉ። በዚህ
ጊዜ ተማሪዎች በሚመሰርቷቸው ቅኔዎች ማስተካከያ በመስጠት
ያበረታቷቸውን። ስለ የቅኔ መፍቻ መንገዶች የሚከተለውን ማስታወሻ
ይጠቀሙ።
ቅኔን ለመፍታት የሚያስችሉ ዘዴዎች

1.ቃልን ከቃል ጋር በማገናኘት

ምሣሌ፡- ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ

በሬ ሣላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ።

ህብረቃል፡- በሬሣላይ
ሰም፡-የሚያርስበሬሳልመለከትመጣሁ።

ወርቅ፡- በሬሣ ላይ ሬሣን ሙትን በድንን እየረገጥኩ መጣሁ።


73
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምሳሌ፡-አዳራሹ ሰፊበሩአልጠበባችሁ
በተራ በተራ ምነው መግባታችሁ
ኅብረቃሉ፡- በተራበተራ
ሰሙ፡- ተራችሁን ጠብቃችሁ መግባትወርቁ፡
-በተራበሰውተራመግባት
2.ቃሉን በማጥበቅና በማላላት፡-
ምሣሌ፡- በባላገር ገበያ ከመንከራተት
ከተማይሻላል ልብስ ለመግዛት።
ህብረቃል፡- ልብስ
ሠም፡- ጨርቅ የሚለበስ (ሲላላ)
ወርቅ፡-አሣቢአእምሮ(ሲጠብቅ፤ ልብብ)
3.ቃልን በመሰንጠቅ

ዘርፋፋ፡-ዘርወጣልን

ምሣሌ፡-ሠብሰቤይዤ ልብሳቸውን
ምነው ውንድሞቼ እራቁታቸውን።
ህብረቃል፡- እራቁታቸውን
ሠም፡- ተራቆቱ እርቃነ ስጋቸውን ሆኑ
ወርቁ፡-እህታቸውንራቁበሞትተለዩ።
4.ታሪክን በማወቅ(በመከታተል)
ምሣሌ፡- ሰልከኛው ሲያሣልፍ ቃል አሣስቶ ነው
መኮንን አይደለም የሞተው ድሃ ነው።
ህብረቃል፡- መኮንን
ሠሙ፡- ድህ ይሆናል እንጅ መኮንን (ሀብታም) አልሞተም
ወርቁ፡-የተጎዳው ድሀው ነው፤የሚያስበሉት፣ ችግሩን የሚረዱለት ልዑል ራስ
መኮንን ሞቱ

74
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና
 ምሳሌያዊ አነጋገሮችን፣ዘይቤዎችና ቅኔዎችን መለየትና አለመለየታቸውን
ጥያቄ በመጠየቅ መመዘን
 የጻፏቸውንዘይቤያዊግጥሞችበክፍልውስጥሲያቀርቡመከታተል
 የተማሪዎችን የአፈጻጸም ሁኔታ መሰረት በማድረግ አንዳንዶቹን ተግባራት
ከክፍልውጪ ጊዜ ወስደው በየቤት ሥራ መልክ ሰርተው እንዲያመጡ
በማድረግ እርማት መስጠት
ክፍልአምስት፡ቃላት
በቃላት ይዘት ስርተማሪዎች ለየቃላት መዝገበ ቃላዊ፣ ተመሳሳይና ተቃራኒ
ፍቺዎችን እንዲሰጡ የሚጠይቁ ተግባራት ቀርበዋል።ይህንኑ አላማ ያሳኩ ዘንድም
እርስዎ ክትትል በማድረግ እገዛ ያድርጉላቸው።

ተማሪዎች ስራዎቻቸውን እየተጋሩ እንዲገማገሙና የተለየ ድጋፍ የሚሹ ካሉም


እገዛ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቹ። እንዲሁም ጥንድ ጥንድ ሆነው በተማሪ
መጽሐፍ ላይ የተሰጡትን ቃላት መሰረት በማድረግ በመካከላቸው ያለውን
አንድነትና ልዩነት በሚያሳይ መልኩ ዓረፍተነገር እንዲመሰርቱ በማድረግ
ያስቀርቧቸው። የተሳሳቱትንም በማቃናትና እርማት በመስጠት ያበረታቷቸው።
የተወሰኑ ተማሪዎችን በመጋበዝም አረፍተነገሮቻቸውን በጥቁር ሰሌዳው ላይ
እንዲጽፉ ያድርጉ።

ምዘና
 የተለያዩ ቃላትን ፍቺ መስጠታቸውን ጥያቄ መመዘን
 የጥንድ ቃላትን ዓረፍተ ነገር በመስጠት ያላቸውን አንድነትና ልዩነት
የሚያሳይ ዓረፍተ ነገር ሲመሰርቱ መመልከት

ክፍል ስድስት፡ሰዋስው
ውድ መምህር በሰዋስው ትምህርት ክፍል ተማሪዎች በሌሎች ምዕራፎች
የተማሯቸውን ሰዋስዋዊ ይዘቶች በክለሳ መልክ እንዲሰሯቸው ታስቧል። በመሆኑም
ስምና ግስ የቃል ክፍሎችን እንዲለዩ እና አረፍነገሮችን መስርተው እንዲያቀርቡ
የሚጋብዙ ተግባራት ቀርበዋል። እባክዎትን መምህር በተማሪ መጽሐፍ ውስጥ
75
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ከተሰጡት በተጨማሪ ሌሎች መልመጃዎችን አስቀድመው በማዘጋጀት


ያቅርቡላቸው። ተግባራቱንም አሳታፊ በሆነ መንገድ (በግል፣ በጥንድ፣ በቡድን፣
በጋራ) ያሰሯቸው። ተገቢውን ምጋቤ ምላሽም ይስጧቸው።

ምዘና
 ተማሪዎችስምንና ግስን በትክክል መለየትና አለመለየታቸውን በጥያቄና
መልስ መመዘን
 ተገቢ አረግተነገሮች መመስረታቸውን በክትትል ማረጋገጥ

መርጃመሳሪያዎች
 መቅረጸ ድምጽ
 ለየይዘቱ አመቺ የሆኑ መሳሪያዎች (በተማሪና መምህር የሚዘጋጁ፣
ከትምህርት ማዕከል በውሰት የሚገኙ

በናሙናነት የተመረጡ ጥያቄዎች መልስ

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ


ቅድመ ማዳመጥ

1. የተለያዩ መልሶች (ስነቃል በቃል አማካኝነት የሚፈጠር፣ በቃል የሚኖር፣


በቃል የሚተላለፍ ውበት ያለው የሰው ልጆች ገጠመኝ ማንጸባረቂያ የፈጠራ
ስራ ነው)

2. የተለያዩ መልሶች (እውነታን፣ ባህልን፣ ሞራላዊ አስተምህሮን፣ ልማድን…)

3. የተለያዩ ልምዳቸውን መሰረት ያደረጉ መልሶች

አዳምጦ መረዳት

1. ተኩላ፣ ጥንቸል እና አዛውንት (ሽማግሌ)


2. አይጠ ሞገጥ
3. አይተሽው የማታውቂውን አይነት ምርጥ እራት ሰርቼ አበላሻለሁ ስላላት
76
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

4. እሷ ጥንቸል እሱ ደግሞ ተኩላ የመሆኑን፤ “እኔ ተኩላ ነኝ፤ አንቺ ደግሞ


ጥንቸል፣ ተኩላዎች ደግሞ ሁልጊዜም ቢሆን ጥንቸሎችን ይመገባሉ”
5. ውሳኔ 1፡ “ይህማ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም፤ ተኩላ አንተ ጥንቸልን
ልትበላት አይገባም። የዋለችልህን ውለታ መዘንጋት የለብህም። በል አሁን
ተዋት ትሂድበት።” ምክንያት፡ ውሳኔያቸውን የቀየሩት ተኩላው
ስላስፈራራው
6. ደግ ለዋለላችሁ ክፉ አትመልሱ፤ ቃላችሁን ጠብቁ፤ (ክፉ የሚሰራ ሳይቀጣ
አይቀርም)

ክፍል ሁለት፡ መናገር


ተግባር አንድ

1 እና 2 (የተለያዩ መልሶች ይጠበቃሉ)

ተግባር ሁለት

(ከጥንድ ጥንድ ውይይት በኋላ የተለያዩ መልሶች)

ሐ.እንቆቅልሽ

ሀ. ጥላ ለ. ስም ሐ. መቃብር
የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች

መልመጃ ሁለት

ሀ. 1. ሀሰት 2. እውነት 3.እውነት 4.እውነት 5.ሐሰት 6. ሀሰት

ለ 1-5 ማስታወሻውን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ መልሶች

ሐ.

1.በአደባባይ - በግልጽ/በሚታይ ሥፍራ 7.ወትሯዊ - ተለምዷዊ


2. ተግሳጽ - ምክር 8. ማፈንገጥ - መለየት

77
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

3. አንደበተ ርቱዕ - ተናግሮ አሳማኝ9. ፍስሃ - ደስታ

4. ጨምቀው - አጠቃልለው10. አጽንኦት - ትኩረት

5. ምስል ከሳች - ስዕል ፈጣሪ11. ለዛ - ውበት (ጣዕም)

6. አግዝፎ - አተልቆ12. ስውር - ድብቅ

ክፍልአራት፡መጻፍ
መልመጃ ሦስት
የተለያዩ መልሶች (ምሳሌያዊ ንግግሮችን በመሰብሰብ የሚመለስ)
መልመጃ አራት
1. የተለያዩ መልሶች
2. በተለያዩ ዘይቤዎች የተጻፉ ግጥሞች
ክፍል አምስት፡ ቃላት
መልመጃ አምስት

1. ሀ.አጉረጠረጠ - አፈጠጠ መ.መረቅ - ፈሳሽ ወጥ

ለ.በለዘ - ጠቆረ/ተበላሸ ሠ.ተቀናጀ - ተጣመረ

ሐ.ቦረቦረ - ቆፋፈረረ.ዘመዘመ - ቀመቀመ፣ በክር ጠለፈ (ለልብስ)

2. ሀ.መልካም - መጥፎ/ክፉ መ.ወዳጅ - ጠላት/ባላንጣ


ለ.እድገት - ክስረት ሠ.ማርጀት - ወጣት መሆን

ሐ.ሆነ - አልሆነም/ሳይሆን ቀረ ረ.ወጠነ - ተወ/ ማቀድ አቆመ


3. የተለያዩ አረፍተነገሮች (የቃላቱን ተቃርኖ የሚሳዩ)
መልመጃ ስድስት
አዛምድ
1.ሰ 2.ሀ 3.ረ 4.መ 5.ለ

78
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


መልመጃ ሰባት
ሀ.1.ውሀክፍቱንአድሮእንዳናጣጤና፣
ከዳድኜእንደሆንልየውእንደገና።

ህብረቃል ከዳድኜ
ሰም ክፍቱን እንዳይሆንልክደነው
ወርቅ ከእዳ ድኜ(ተላቅቄ) እንደሆን
ቅኔውየተፈታበትዘዴቃል በመከፋፈል

2. አስራ ሁለት ውሻ ታስሮ ከደጅሽ፣


አስፈትቼገባሁእኔወዳጅሽ።
ህብረቃል አስፈትቼ
ሰም ውሻዎቹን አስለቅቄ/ዞር አስደርጌ
ወርቅ ፍትሃት አስብዬ/ጸሎት አስደርጌ
ቅኔውየተፈታበትዘዴየቃሉን የተለያየ ትርጉም በማወቅ

3.ሚስቴ በየዓይነቱ ቁርሴን ስትሰጠኝ፣


ቅንጨዋ ናት በጣም የምትጣፍጠኝ።
ህብረቃል ቅንጨዋ ናት
ሰም ቅንጬ ከሌሎች ምግቦች በተለየ ትጣፍጠኛለች
ወርቅ ቅን፣ ጨዋ ናት (እሷ)
ቅኔውየተፈታበትዘዴቃላት በመከፋፈል

4.አዳራሹሰፊበሩ አልጠበባችሁ፣
በተራበተራምነውመግባታችሁ።
ህብረቃል በተራ በተራ
ሰም በመደዳ/በሰልፍ

79
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ወርቅ በተራበ ሰው ተራ ለምን ገባችሁ


ቅኔውየተፈታበትዘዴቃላትን/ሀረጋትን በማገናኘት
ለ.1. በጣም አደነቅሁ ተመልክቼ፣
የሰውን ስራ አይቼ።
ህብረቃል፡ የሰውን ስራ
ሰም፡ ሰው የሰራውን ስራ አይቼ
ወርቅ፡የሰው እንስራ/ ከሸክላ የተሰራ ማሰሮ/
ቅኔውየተፈታበት፡ቃላትን በማገናኘት
2. ድጓ ጾመ ድጓ ተሰቅሎ ከቤቴ፣
እኔን የሚቆጨኝ ሳልማር መቅረቴ።
ህብረቃል፡ ሳልማር
ሰም፡ ትምህርት ሳልማር መቅረቴ
ወርቅ፡ ከፈጣሪ ምህረት ሳላገኝ መቅረቴ
ቅኔውየተፈታበት፡ ቃላትን በማገናኘት
3. ወተት በጨለማ ታበላሻላችሁ፣
ቀን እንዲህ ይገፋል እኔ ላሳያችሁ።
ህብረቃል፡ ቀን እንዲህ ይገፋል
ሰም፡ ቀን ቀን ወተት የሚገፋው እንደዚህ ነው፤ እዩት
ወርቅ፡ ቀን እንደዚህ ይሄዳል/ ችግር ያልፋል
ቅኔውየተፈታበት፡ የቃሉን የተለያየ ፍቺ/አውድ/ በማወቅ
4. እሬት በመታቀፍ አለቀ ሸማዬ፣
በቃ አድርገህ ስጠኝ እባክህ ጌታየ።
ህብረቃል፡ በቃ አድርገህ ስጠኝ
ሰም፡ ሸማዬ እየተበላሸ ስለሆነ አንተው ልበሰው/አድርገው
ወርቅ፡ የሚበቃኝን ያህል አንተው ስጠኝ/ በቃ አድርገህ
ቅኔውየተፈታበት፡ቃሉን በማጥበቅና በማላላት (በቃ/ብኧቅኣ/፣
/ብኧቅቅኣ/)
80
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መልመጃ ስምንት

የተለያዩ መልሶች

የክለሳ ጥያቄዎች

2. የሚከተሉትን ጅምር (የተጓደሉ) ምሳሌያዊ አነጋገሮች አሟሉ።


ሀ. ከአፍ የወጣ ቃል ከእጅ የወደቀ እንቁላል።
ለ. ክርና መርፌ፤ሰንደዶና ወስፌ
ሐ.ከመምህሩደቀመዝሙሩ
መ.ያለፍቅርሰላምያለደመናዝናብ
ሠ.ከፎከረይሻላልየጠረጠረ

ረ.ያለአቻ ጋብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ

81
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ስድስት
የታላላቆች ሚና
(የክፍለጊዜ ብዛት 8)

የሚጠበቁ ውጤቶች
ተማሪዎችይህንን ትምህርትተከታትለው ካጠናቀቁ በኋላ፡-

• በማዳመጥየፅሁፍንዋናሀሳብይተነትናሉ።

• በክርክርበመሳተፍምክንያታዊዳኝነትይሰጣሉ።

• በማንበብእንደገናጨምቀውይፅፋሉ።

• የስራማመልከቻደብዳቤ ያዘጋጃሉ።
• አብሮ ሂያጅ ቃላትን ማጣመር ይችላሉ።

• ተሸጋሪና ኢተሻጋሪግሶችንበመለየትይጠቀማሉ።

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ


ቅድመማዳመጥ

በዚህ ትምህርት ክፍል ውስጥ የቅድመ ማዳመጥ ተግባራት በማሰራት


ስለሚደመጠው ምንባብ የቀደመእውቀታቸውን በመስቀስ እንዲያሰላስሉ
ያድርጓቸው።

በተማሪ መጽሐፍ ላይ ተማሪዎች በአካባቢያቸው የሚገኙ ‹‹ታላላቅ ሰዎችሚና››


ምን እንደሆነ ከክፍል ጓደኞቻችሁ ጋር ተወያተው እንዲያቀርቡ የሚጋብዝ ጥያቄ
ቀርቧል።ስለሆነም ተማሪዎችዎን በአነስተኛ ቡድን (4/5) በማቧደን በጉዳዩ ላይ
እንዲወያዩና የደረሱበትን ለክፍሉ እንዲያጋሩ ያድርጉ።

82
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ወደ የማዳመጥ ተግባሩ ከመግባታቸው በፊትም በቅድመ ማዳመጥ የተሰጡትን


ቃላት ፍቺ እንዲገምቱ እድል ይስጧቸው።

ሀ. ረቂቅ - የማይጨበጥ/ውስብስብ ሐ. ተወጠነ - ታቀደ/ታሰበ

ለ. ፍንትው - ግልጥ ብሎ/ፈክቶ/ መ. ታድጎ - ተከላክሎ/ጠብቆ

የማዳመጥ ሂደት

በመቀጠል ትኩረታቸውን አሰባስበው ወደ ማዳመጡ ተግባር እንዲገቡ ይንገሯቸው።

ይህ ምንባብ በግጥም መልኩ የቀረበ በመሆኑ እርስዎ አስቀድመው ተደጋግመው


በማንበብ ፍሰቱን ጠብቆ እንዲቀርብ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብዎታል።
በአማራጭነትም ሌላ ሰው በማስነበብ ወይም አስቀድሞ የተዘጋጀ ካለ በሞባይልዎ
ቀርጸው/አሰናድተው ያቅርቡላቸው።

”ሀገር ማለት የኔ ልጅ“ ግጥም ቢያንስ ሁለት ጊዜ እንዲነበብላቸው/ እንዲያዳምጡት


የሚጠበቅ ሲሆን፣ በሂደቱም ተማሪዎች የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄውን እንዲመልሱት
ያድርጉ።
ሀገርማለትየኔልጅ

ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገርማለት፣

እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ፣የተወለድሽበት አፈር፤

እትብትሽ የተቀበረበት፣ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤


ብቻ እንዳይመስልሽ።
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።
ሀገር ማለት ልጄ፣

ሀገር ማለት ምስል ነው፣በህሊና የምታኖሪው፤

ከማማ ማህፀን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ፤

በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ፣


83
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤


በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
በተሻገርሽውዥረት፤
በተሳልሽበት ታቦት ፣ ወይ በተማፀንሽው ከራማ፤
በእውቀትሽናበህይወትሽ፣
በእውነትሽናበስሜትሽ፣

የምትቀቢው ምስል ነው፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤

ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፣


ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።

የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

መምህር ግጥሙን ማንበብዎን ገታ በማድረግ የሚከተሉትን የማዳመጥ ጊዜ


ጥያቄዎች ይጠይቁ።
1. እትብትሽ _____________፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር ብቻ
እዳይመስልሽ።
2. ሀገር ______________ ነው ቃሉ።

3. ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፣ ______________ የማትቀይሪው።

4. የግጥሙ ደራሲ መልዕክቱን ለማን እንደሚናገር አድርጎ ነው


ያቀረበው?

ሀገርማለት የኔ ልጅ፣
ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ባንደበት አይናገሩት፤
በጆሮአያደመጡት፣
አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አፋርኛ፣ ቅማንትኛ፣
ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት።
የኔልጅ
አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞውና ሲዳማው፣ ጉራግኛሽንባይሰማ፤
84
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ያልገባሽው እንዳይመስልሽ፣ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።


የየልቦናችንንሀቅ፣ፍንትው አድርጎ እያሳየ፣
ህዝቦችንከሰንደቃቸው፣አስተሳስሮያቆየ።
ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስተዋት፤
ሲከፋሽትሸሸጊበት፣ሲደላሽትኳኳይበት።
የኔልጅ፣

አያት ቅም አያትሽ፣ ሰላም ሲሆን ከውልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ

ሲያቀናወረቱን፣

ለእኔናላንቺመኖሪያ፣ሲያቀናቀዬናቤቱን፤

ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤

ከኦሮሞው ከትገሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣…ከሁሉም የጦቢያልጆች፣

አጥንቱን እያማገረ፤

ሀገር ይሉት መግባቢያ፣ ሰንደቅ ይሉት መለያ፣ ሲያቆይልሽ፣

በጉራግኛ ማትገልጪው፣ በጎጥ ማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!


እና የኔልጅ፣
ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺየሚያስፈልግሽ፣
ከወልቄጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፣
ከወልቄጤ አድማስ ማዶ፣ ለተወጠነው እድገትሽ።
እና ልብ በይ ልጄ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበትአይናገሩት፤
በጆሮ አያደምጡት።
ከሁሉምበላይየኔልጅ፣
ተፈጥሮ ከቸረችው በረከት፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፣
ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የኔ የምትይው ከለላ።
ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
የሰብእናሽግማሽ ውል፣ ወገነውማሕተምሽ።
85
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ዜጋነው ልጄ ሀገርሽ።
መሬትማየኔልጅ፣
በእምነትሽና በእውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፣ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ፣
ለተስፋሽ ካልተመገብሽው፣
መሬትማባዳነው፣ ላለማውየሚለማ፣
ለተስማማውየሚስማማ።

ዥረቱም ግድ የለውም፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል፣


ተራራውምደንቆሮነው፣ለቦረቦረውይበሳል፣መሬቱ
አይደልም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሀገርሽ፣
ስተቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አሰታሞ፣ ስትሞቺ
አፈርሚያለብስሽ።
በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ።
ወገንነው ልጄሀገርሽ።
እናየኔልጅ፣

ሀገርረቂቅ ነውቃሉ፣

ሀገርውስብስብ ነውውሉ።

(በድሉዋቅጅራ2007፡81-84)

ውድ መምህር ቀጥሎ ተማሪዎችም የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎቹን እንዲሰሯቸው


እድል ይስጧቸው።ቀደም ሲል በማዳመጥ ጊዜ በግል የመለሷቸውን ጥያቄዎች
በቡድን እንዲወያዩባቸው ካደረጉ በኋላ፣ የተማሪ መጽሐፍ ላይ የሚገኙት ሁለት
መልመጃዎች ቃላትንና አጠቃላይ የግጥሙን ጭብጥ የተመለከቱ ናቸው።
ተግባራቱን በማከናወን ወቅትም አራቱም መሰረታዊ የቋንቋ ክሂሎች እየተቀናጁ
ጥቅም ላይ ይውላሉ (ያዳምጣሉ፣ ስለመልሶቻቸው ይነጋገራሉ፣ ይጽፋሉ፣ የጻፉትን
መልሰው ያነባሉ፤ ይወያያሉ)

86
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና

• ተማሪዎችከሰሙትፅሁፍውስጥዋናውንሀሳብነቅሰውማውጣት
መቻላቸውን መመዘን።

• ተገቢውን ቃላት በመጠቀም፣ የሌሎችን ሀሳብ በማክበር እና በልበ


ሙሉነት ሀሳባቸውን መግለፃቸውን መገምገም።

ክፍል ሁለት፡መናገር
መምህር በዚህ ንግግርን ለመለማመድ እድል በሚሰጠው ክፍል
የክርክርስልትንበመተግበርተማሪዎችዎ በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታትና
ተፈጻሚነቱንም መከታተል ይጠበቅብዎታል። ተግባሩም አስቀድሞ መዘጋጀትን
ስለሚጠይቅ ተግባሩን ከእለቱ ክፍለጊዜ ቀደም ብለው ይስጧቸው።ለዚህም ያመች
ዘንድ አስቀድመው ተማሪዎችዎንበቡድንያደራጇቸው።

ከቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ወይም ሌላ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ እርስዎ


በተጨማሪነት በማቅረብ አንዱን መርጠው ምክንያታዊ የሆነ ውይይት (ወይን
መደበኛ ክርክር) እንዲያካሂዱ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው።

ተሳታፊ ተማሪዎቹ የየራሳቸው ሚና የሚኖራቸው ሲሆን ሚናዎቹም ተከራካሪ፣ ዳኛ


እና ታዳሚ(አድማጭ) መሆን ናቸው። በዚሁ መሰረት አምስት አምስት ተከራካሪ
ያለው ሁለት ቡድን (ተጻራሪ፣) አራት ዳኞች (ሦስት ዳኞች፤ አንድ ሰዓት
ተቆጣጣሪ)፣ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ታዳሚ ሆነው ይሰናዳሉ።

ምዘና

• የክርክር ዝግጅትና አቀራረብን በተመለከተ የተደረገውን ተሳትፎና


የመጣውን ለውጥ ማጤን

• ምክንያታዊ ሃሳብ አመንጭተው የማቅረብና የማሳመን ብቃታቸውን


መመዘን፤

87
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሶስት፡ ንባብ

ቅድመ ንባብ

መምህር በዚህ ትምህርት ክፍል “የሰፈሩአድባር” የሚለውን ምንባብ ከማስነበብዎ


በፊት በተማሪ መጽሐፍ ላይ የቀረቡትን የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች በቡድን
በማሰራት የተማሪዎችን ዳራዊ እውቀትይቀስቅሱ።

በቅድመ ንባብ ክፍል ሦስት ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱ በተናጠል ቀሪው
ሦስተኛ ጥያቄ ደግሞ ከቡድን ውይይት በኋላ የሚመለስ ነው።

የማንበብ ጊዜ

ውድ መምህር ምንባቡን ተማሪዎችዎ በግል በለሆሳስ እንዲያነቡት የሚጠበቅ ሲሆን፣


በተጨማሪነት የገጸባህሪያቱን ሚና ተከፋፍለው በትረካ
(ምልልስ)መልክእንዲያቀርቡትምማድረግ ይችላሉ።

በማንበብ ሂደት ወቅት ተማሪዎች እያነበቡ በመካከል ያነበቡትንና ቀጥሎ


የሚመጣውን የምንባብ ታሪክ ለመገመት የሚያስችሉ ሁለት ጥያቄዎች ቀርበዋል
እነዚህን ጥያቄዎች ማንበባቸውን ገታ አድርገው እንዲመልሷቸው ጥቆማይስጧቸው፤
ምላሾቻቸውንምይቀበሉ።
አንብቦመረዳት

ይህ ክፍል ተማሪዎቻችን ከማንበብ ተግባሩ በኋላ በምንባቡ የተነሱትን ዝርዝርና


ዋና ዋና ሀሳቦች ምን ያህል መለየት እንደቻሉና አጠቃላይ የምንባቡን ይዘትም
ምን ያህል እንደተረዱት ለመፈተሸ የቀረቡ ናቸው።ስለሆነም ትዕዛዛቱን እየተከተሉ
ጥያቄዎቹን በአግባቡ እንዲመልሷቸው ያሳስቧቸው።

የምርጫ ጥያቄዎች በደብተራቸው እንዲሰሩ ያድርጉ።እንዲሁም በቃል የሚመለሱና


የሚብራሩትን ጥያቄዎችን በትእዛዛቱ መሰረት በቡድን ተወያይተው በቡድን
ተወካያቸው አማካኝነት እንዲያቀርቡያድርጉ፤ተገቢውን ምጋቤምላሽ

88
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በመስጠትምያበረታቷቸው።
ምዘና

• አንብበው መረዳታቸውንቃላዊና ጽሑፋዊ ጽብረቃ (በግል፣ በጥንድና


በቡድን) እንዲሰጡ በማድረግ ማረጋገጥ

• በርዕሱዙሪያጠቃሚናገንቢአስተያየቶችንመስጠታቸውንመከታተል

ክፍል አራት፡መጻፍ

መምህር ተማሪዎች በዚህ ክፍል ስለደብዳቤ ምንነት እና አይቶች ተረድተው


በተግባር ደግሞ ደብዳቤእንዲጽፉ ይጠበቃል።

ስለሆነም አስቀድመው ደብዳቤ ጽፈው ያውቁ እንደሆነና ደብዳቤ ለምን ለምን


ጉዳዮች (በግል ለሰላምታ እና ለመስሪያቤት በማመልከቻነት) ሊጽፉ እንደሚችሉ
በመጠየቅና ምላሻቸውን በቃል በመቀበልጀምረው ወደ ማስታወሻው ይሂዱ።
ማስታወሻውንም እንዲያነቡና ጠቃሚ ነጥቦችን እንዲወስዱ ያድርጉ።

ለማሳያነት የቀረቡትን ደብዳቤዎች በተመለከተም በቡድን ሆነው ዋናዋና ክፍሎቹን


በማንሳት እንዲወያዩ ያድርጓቸው።በመጨረሻም የራሳቸውን ማመልከቻ (የመስሪያ
ቤት ደብዳቤ) እንዲጽፉ ያድርጉ።እየተዘዋወሩም ምልከታ በማድረግ
መጻፍየሚቸገሩ ተማሪዎች ካጋጠሙዎት ተጨማሪ እገዛ ያድርጉላቸው። ተማሪዎቹ
የየግላቸውን ጽፈው ሲያጠናቅቁም ስራዎቻቸውን በመቀያየር እርስበእርስእርማት
እንዲሰጣጡ እድል ይስጧቸው።በመጨረሻም አንድ ወይም ሁለት ናሙና ስራዎችን
በማሳያነት ለክፍሉ እንዲያቀርቡ ይጋብዟቸው፤ ሁሉንም የደብዳቤ ክፍሎች
ስለማካተታቸው በማየት አጠቃላይ ምጋቤ ምላሽም ይስጧቸው (እዚህ ላይ
ማመልከቻ ደብዳቤ መጻፉ በዕለቱ ክፍለ ጊዜ ካልተጠናቀቀ በየቤት ስራ መልክ
ሰርተው እንዲመጡም ማድረግ ይቻላል)።

89
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና

• የቢጤእርማት እንዲካሄድ ማስቻል፤

• ተማሪዎች የፃፉትን ደብዳቤ በትክክል መልዕክቱን


ማስተላለፍንየሰዋስው አጠቃቀም እና በትክክል የተደራጀ አፃፃፍ
መከተላቸውንመገምገም፤
• ከመግቢያ እስከ መደምደሚያ እንዴት ሂደቱን እንደጠበቁና
እንዳገናኙት፣ የቋንቋ አጠቃቀማቸውን፣ በራሳቸው መልሰው ሲፅፉ
ሰዋስውን በትክክለኛ መንገድ መጠቀማቸውን መገምገም።

ክፍልአምስት፡ ቃላት (አብሮሂያጅ ቃላት)

በቃላት ትምህርት ክፍል በዋነኛነት አብሮሂያጅ ቃላትን በተመለከተ የቀረበ


ምሳሌናተማሪዎች ልምምድ እንዲያደርጉ የተሰናዱ መልመጃ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

እባክዎ መምህር ምሳሌውን ሰሌዳ ላይ በመጻፍ ለተማሪዎችዎ ገለጻ ይስጧቸውና


እሱን መሰረት አድርገውም ቀጥለው የቀረቡትን ጥያቄዎች እንዲሰሩ ይጋብዟቸው።

ትምሀርቱን ይበልጥ ተጨባጭ ለማድረግ ቻርቶች(ገበታዎች) ጥቅም ላይ እንዲውሉ


የሚጠበቅ ሲሆን፣‘ቤት’ ለሚለው ቃል በተማሪ መጽሐፍ ላይ የቀረበው ምሳሌ ጥሩ
ማሳያ ነው። እረስዎም ተማሪዎቹ ያንን መሰረት አድርገው ለተሰጧቸው ቃላት
አብሮሂያጅ ቃላትን በቻርት ታግዘው እንዲያመለክቱ ያሳስቧቸው።

በአዛምድ መልክ የቀረበውንም ተግባር ደብተራቸው ላይ በመጻፍ ጥንድ ጥንድ


ሆነው እንዲተራረሙ መመሪያ ይስጧቸው።አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ደብተሮቻቸውን
ሰብስበው እርማት ሊሰጡበት ይችላሉ።

ምዘና

• የቃል ጥያቄመጠየቅ

• የአብሮሂያጅ ቃላት ተዛምዶን በገበታ (ቻርት) መልኩ መግለጽ


መቻላቸውን በምልከታ ማረጋገጥ
90
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

• በጥንድ ወይም በቡድን ሆነው ሃሳብ ሲያንሸራሽሩ ተሳትፏቸውን


መገምገም

• አብሮሂያጅ ቃላትን አመንጭተው በንግግርና ጽሑፍ መግለጽ


መቻላቸውን መፈተሽ

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

መምህር በዚህ ይዘት ውስጥ የድርጊት ግሶች (ሳቢናኢሳቢግሶች) የሚባሉት


ቀርበዋል።ተማሪዎች ስለ የድርጊት ግሶች የቀረበውን ማስታወሻ በማንበብ ግንዛቤ
እንዲይዙና አበይት ነጥቦችንም በማስታወሻ መልክ እንዲወስዱ ያድርጓቸው።
መጽሐፉ ላይ ከቀረቡት በተጨማሪ የተለያዩ ምሳሌዎችን በማቅረብም
ማስታወሻውን ያጠናክሩላቸው።

ውድ መምህር በማስከተልም ተሻጋሪና ኢ-ተሻጋሪ ግሶችን ይበልጥ ለይተው


ለመጠቀም እንዲችሉም በመለማመጃነት የቀረቡትን ጥያቄዎች ደብተሮቻቸው ላይ
ጽፈው እንዲሰሯቸው ያበረታቷቸው።በመልሶቻቸው ላይም የጋራ ውይይት አድርጉ፤
አስፈላጊ ሲሆንም ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።

ተማሪዎችዎ ተጨማሪ የመለማመጃ ተግባራት የሚያስፈልጋቸው ከሆነም


አሰናድተው ይስጧቸው፤ ሳቢ እና ኢ-ሳቢ ግሶችን በተመለከተም ተጨማሪ ገለጻ
ያቅርቡላቸው።
ምዘና

• የድርጊት ግሶችን ከሌሎች ግሶች (የመሆን) መለየት


ያለመለየታቸውን ይፈትሹ

• ተሻጋሪና ኢ-ተሻጋሪ ግሶችን የያዙ ዓረፍተ ነገሮችን


አንብበው ስለግሶቹ እንዲገልጹ ማድረግ

• ደብተሮቻቸውን ሰብስቦ ማረምና ምጋቤ ምላሽ መስጠት

91
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መርጃመሳሪያዎች

• መቅረጸድምጽ/ሞባይል

በናሙናነት የተመረጡ የጥያቄዎች መልስ


ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ

የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

1. የተቀበረበት 2. ረቂቅ 3.ባንደበት 4. ለሴት ልጁ

ድህረ ማዳመጥ

መልመጃ አንድ(የቃላቱ ፍቺ የተሰጠ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ አረፍተነገሮችን


ይመሰርቱባቸዋል)
ሀ.ሀገር - መኖሪያ/ዜግነት ማግኛ ረ.ፍንትው - ግልጥ
ለ.ዥረት - ወራጅ ወንዝ ሰ.የላቡን - የወዙን/የለፋበትን
ሐ.ባዳ - ዘመድ ያልሆነ ሸ.ከራማ - አድባር
መ.ጥሪት - ሀብት ቀ.የሚለማ - የሚያፈራ
ሠ.ሸቅጦ- ነግዶ በ. ደጃፍ - በቀዬ/በበር
መልመጃ ሁለት

(ምንባቡን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ መልሶች ከተማሪዎች ይጠበቃሉ)

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ


አንብቦ የመረዳት ጥያቄዎች
መልመጃ ሦስት
ሀ. 1. ሀ 2. ለ 3. ሐ 4. ሀ 5.መ 6. ለ
ለ. ከ 1-5 (ሁሉም መልሶች ምንባቡን መሰረት በማድረግ ይመለሳሉ)

92
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል አምስት፡ ቃላት

መንገድ (አየር መንገድ፣ አቋራጭ መንገድ፣ አማራጭ መንገድ፣ መሄጃ መንገድ…)


ምግብ (የተመጣጠነ ምግብ፣ የተበላሸ ምግብ፣ ምግብ ቤት፣ የልጆች ምግብ፣
የምግብ እጥረት፣ የምግብ አዳራሽ…)
መስጠት (እጅ መስጠት፣ ገንዘብ መስጠት፣ አንገት መስጠት፣ ደም መስጠት፣
ህይወት መስጠት…)
ወለድ (ውሃ ወለድ፣ አየር ወለድ፣ ልብ ወለድ…)

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


መልመጃ ሰባት

ሀ. 1. ተቀበለ - ሳቢ 2. አጣላት - ሳቢ 3.አለቀሰች - ኢሳቢ


4. ሰጠች - ሳቢ 5. ወደቀ - ኢሳቢ 6. ይደሰታሉ - ኢሳቢ

1. ተኛ - ኢተሻጋሪ 7. ፃፈ - ተሻጋሪ

2. ፈነጨ - ኢተሻጋሪ 8. ሞተ - ኢተሻጋሪ

3. ነቃች - ኢተሻጋሪ 9. ላከ - ተሻጋሪ

4. ደበደበ - ተሻጋሪ 10. ወደደ - ተሻጋሪ

5. ዘመረች - ኢተሻጋሪ 11. ተቀበለ - ተሻጋሪ

6. ነቀፈች - ተሻጋሪ 12. አረሰ - ተሻጋሪ

93
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ሰባት
ረጅም ልቦለድ

(ስምንት ክፍለጊዜ 8)

የሚጠበቁ ውጤቶች
ተማሪዎችከዚህትምህርትመጠናቀቅበኋላ፡-

የረጅም ልቦለድ ቅንጫቢ ታሪክ አዳምጣችሁ ጥያቄዎች


ትመልሳላችሁ

የረዥም ልቦለድን ምንነትን ያብራራሉ።

የልቦለድክፍሎችንይገልጻሉ።

የቀረበ ጽሑፍን አንብበው ጥያቄዎች ይመልሳሉ።

በተገቢው መንገድ ማስታወሻ ይይዛሉ።

ሙያዊ ቃላትን ለይተው ይጠቀማሉ።

የገቢር እና የተገብሮ ግሶችን ይገለገላሉ።

ትምህርት አንድ፡ ማዳመጥ


ርዕስ፡-ቆንጆዎቹ (ቅንጫቢ)

ቅድመማዳመጥ

ወድ መምህር ተማሪዎችዎ ወደማዳመጡ ተግባር ከመግባታቸው በፊት ለማዳመጡ


ዝግጁነት እንዲኖራቸውና ይዘቱን ከቀደመ እውቀታቸው ጋር እንዲያዛምዱት
የቀረቡትን የቅድመ ማዳመጥ ጥያቄዎች እንዲመልሱ ይጠይቋቸው። (ከ3 – 5

94
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ደቂቃ)

ለማዳመጥ ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ምንባቦቹን ድምፅዎን ከፍአድርገው


ያንብቡላቸው፤ ወይም አስቀድመው በመቅረጸ ድምፅ ቀድተው አዘጋጅተው ከሆነ
እሱን ያስደምጧቸው። በመጀመሪያው ንባብ አጋማሽ ላይ ማንበብዎን ገታ
አድርገው የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎቹን እንዲመልሱ ይጋብዟቸው፤ የተመለሰው መልስ
ልክ ወይም ልክ ላይሆን ይችላል። ማንበብዎን (ማስደመጥዎን) ይቀጥሉ።

መምህር ተማሪዎችዎ ታሪኩን ለሁለተኛ ጊዜ ካደመጡ በኋላ የድህረ ማዳመጥ


ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ይጠበቃል። በመሆኑም ትዕዛዛቱን መሰረት አድርገው
ጥያቄዎቹን እንዲመልሱ ያበረታቷቸው፤ አፈጻጸማቸውንም እየተዘዋወሩ
ይመልከቱ። ሲጨርሱም ስራዎቻቸውን እረስበርስ እንዲተራረሙ ያድርጉ፤ በእለቱ
ካልተጠናቀቀ በየቤት ስራ መልክ ሊያሰሯቸውም ይችላሉ።አሻሚ የሆኑ መልሶች
ያላቸው ጉዳዮች ካጋጠሟቸው፣ አጣርተው ይመልሱ ዘንድ ምንባቡን ለመጨረሻ
ጊዜ ፈጠን ባለ አነባበብ አንዴ ያነቡላቸዋል።

ቆንጆዎቹ(ቅንጫቢ)
… … …

“ናትዬ…ና…” ድምጿ እንደ ወፍ ትንፋሽ ሳሳ።

“ምንድን ነው ንገሪኝ ርብቃ?” ጉንጮቿን እንደያዘ ደግሞ ጠየቃት።

“ናትዬ…”

“ኪርርር…ር!”

ናትናኤል ቀልጠፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳና ነጠላ ጫማውን አጥልቆ


የመኝታቤቱን በር ከፍቶ ወጣ።

“ሃሎ… ” አለ እንግዳ ድምጽ መቀበያ ክፍል ውስጥ ያለውን ስልክ አንስቶ።

“ሃሎ … ናትናኤል?” አለ የታፈነ የሚመስል ጎርነን ያለ ድምጽ።


95
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

“ነኝ … ማን ልበል?”

”አብርሃም ነኝ። እንድንገናኝ እፈልጋለሁ። አሁን በአስር ደቂቃ ውስጥ


እንድትደርስ። ሆቴል ዲ-አፍሪክ ነው ያለሁት… ትሰማኛለህ? የመኪናህን ትንሹን
መብራት ሳታጠፋ በሩ ላይ መኪናህን አቁም። እጠብቅሃለሁ…“

”ሃሎ … ሃሎ“ ናትናኤል ተጣራ። ስልኩ ግን ተዘግቶ ነበር።

ለጥቂት ሰከንዶች የስልኩን መነጋገሪያ እንዳንጠለጠለ አመነታ።


ሰዓቱን ተመለከተ። ለሦስት ሩብ ጉዳይ። አብርሃም ውጪ የማምሸት ጸባይ
የለውም። እስከሚያውቀው ድረስ። ደግሞስ ቀን ያልተነጋገሩት አሁን የሚነግረው
ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ? ስልኩንስ ለምን ቸኩሎ ዘጋ? አነጋገሩም ጥድፊያና
ችኮላ የተቀላቀለው ነበር። 'ምን ሆኖ ይሆን?' ናትናኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ክፉ
ታሰበው። አደጋ ደርሶበት ይሆን? ድምጹም ትክክል አይደለም - ጎረነነ።

“ማነው? ምን ሆንክ?” አለች ሲቻኮል ስታየው ርብቃ ከተኛችበት


ተነስታ አልጋው መሃል ቁጭ እያለች።

“ደህና ነኝ። አብርሃም ነው።” ቀልጠፍ ብሎ ልብሱን ይለባብስ ጀመር።

“እና የት ልትሄድ ነው በሌሊት?” ከላይዋ ላይ ብርድ ልብሱን ገፋ ተነሳች።

“ሆቴል ዲ. አፍሪክ ነው ያለኝ። ትንሽ ችግር ሳይገጥመው


አይቀርም። እንጃ ነገሩ ትክክል አይደለም።” ናትናኤል ፈጠን ብሎ ሱሪውን
አጠለቀ። ሸሚዙን እስኪለብስ መቆየት አልፈለገም። ድፍን አንገት ያለውን
ወፍራም ሹራቡን አጠለቀና ፀጉራም ካፖርቱን ከቁም ሳጥን ውስጥ ጎትቶ
አወጣው።

“ምን ሆንኩ አለ?” አለች ርብቃ ግራ ተጋብታ።

“ዛሬ ጠዋት አግኝቼው ነበር ለአንድ ጉዳይ። ለምን እንደፈለገኝ ግን


አልነገረኝም። ዝም ብሎ 'ና’ ነው ያለኝ።” ናትናኤል የሚለው ሲጠፋው ትከሻውን
96
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሰበቀና ተወው። ከራስጌ የመኪናውን ቁልፍ አነሳና አልጋውን ዞሮ አቀፍ አድርጎ


ግንባሯ ላይ ሳማት። “ተኚ። አልቆይም። እሺ … በሩን ከውጭ ቆልፌ በስር
እወረውረዋለሁ።” እየተቻኮለ ወጣ። ዘግቶት የሄደው በር ላይ አፍጥጣ ቀረች።

አሳንሰሩ እስኪመጣ መጠበቅ አልፈለገም። አስር ደቂቃ ነው ያለው


አብርሃም። ሁለት ሁለቱን ሁለት ሁለቱን እየዘለለ በፎቁ ቁልቅል ተንደረደረ።

“ምነው ደህና?” አሉት የማታው ዘበኛ ወፍራም የሌሊት ካፖርታቸውን


እንደደረቡከተኮፈሱበት አጥር ላይ እየተነሱ።

“ሠላም ነው።” ፈጠን ብሎ መኪናው ውስጥ ገባ።

መኪናውን አስነስቶ ከግቢው ወጣ። መንገዱ ጭር ብሏል። ብን ብን የሚለው


ካፊያ የመኪናውን የፊት መስታወት በጥቃቅን ነጠብጣቦች ሸፈነው። የዝናብ
መጥረጊያውን ተጫነና ፍጥነቱን ጨመረ። ብሔራዊ ቲያትር አጠገብ ሲደርስ ዝናቡ
ሃይል ጨምሮ የመኪናውን ጣሪያ ያቀልጠው ጀመር። ያለ እረፍት ውልብ ውልብ
የሚለው የዝናብ መጥረጊያ ትንፋሽ ያጠረው መሰለ። ሰዓቱን ተመለከተ። አራት
ሊሞላ ጥቂት ደቂቃዎች ቀርተዋል። ዘግይቷል። ፍጥነቱን ጨመረ። ሠንጋ ተራ
ያለው መንገድ መብራት ቦግ ብሏል። ቀዩ የትራፊክ መብራት ከመሬቱ ላይ ሲያርፍ
በዝናቡ የተዘፈቀው አስፋልት የእሳት ጎርፍ የፈሰሰበት ይመስል ደም ይመስላል።
ናትናኤል ከጎንና ከጎን የሚመጣ መኪና እንዳለ ተመለከተ። መስቀልያው መንገድ
ንጸፁህ ነው… አማን ነው። ቤንዚን መስጫው ላይ ቆመበት። መኪናው ቀዩን
የትራፊክ መብራት አልፋ ተሽቀነጠረች። ሜክሲኮ አደባባይ እንደደረሰ ወደ ቀኝ
ታጠፈና ጎኑን ሰጥቶ ወደቆመው ሆቴል ተጣደፈ።

የማዳመጥ ጊዜ ጥያቄዎች

1. ናትናኤል በምሽት ከቤቱ ወጥቶ የሄደበት ምክንያት ምን ነበር?


2. ናትናኤል ጓደኛው አብርሃምን ሊያገኘው የሚሄደው ወዴት ነው?
መንገድ ላይ ከተገተረው ሆቴል አፋፍ ሲደርስ ጥግ ይዞ ቆመ። ሞተሩን አጠፋና

97
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

መብራቱን ቀንሶ ትንሹን መብራት እንዳበራ ተጠባበቀ።


እልሁ ቢወጣለትም ዝናቡ አሁንም ሳግ ይተናነቀዋል። የዝናብ መጥረጊያው
በዝግታ እላይ ታች ይላል። የፊት መስታወቱ በገዛ ትንፋሹ በጉም ተሸፍኗል።
እጁን ሰድዶ ወለወለው። ዙሪያውን ተመለከተ። የሆቴሉ ደንበኞች ያቆሟቸው
ጥቂት መኪናዎች ከፎቁ ስር በተርታ ተኮልኩለዋል። መንገዱ ጭር ብሏል።
ከመንገዱ ባሻገር ጥጉን ይዛ አንድ ሲትሮይን መኪና ቆማለች። አብርሃም የለም…

“አሌ - ቀጥል።” አለ የአረብ ገጽታ ያለው ከሲትሮይኗ መሪ ኋላ


የተቀመጠው ሰው በፈረንሳይኛ። “አስታውስ፤ ጊዜ አትውሰድ፤ መስኮቱን አንኳኳ።
ዝቅ እንዳደረገ አንድ ብቻ ክተትለት። መኪናውን አዙሬ እጠብቅሃለው።”

አጠገቡ የተቀመጠው ጥቁር ሰው ጭንቅላቱን በስምምነት ነቀነቀ።


ከደረበው ካፖርት የጎን ኪስ ውስጥ ሽጉጥ አወጣና በግራ እጁ ይዞት የነበረውን
ቱቦ የመሰለ የድምጽ ማፈኛ ገጠመለት። በአውራ ጣቱ የሽጉጡን መዶሻ ወደኋላ
መልሶ የሲትሮይኗን በር ከፍቶ ወጣ።

ዝናቡ ይሁን ወይ አለቅጥ የረዘመው ቁመቱ ሰውየው ከትከሻው ጎበጥ ያለ


ነው። በቀኙ የያዘውን ሽጉጥ በካፖርቱ የጎን ኪስ ውስጥ ሸጉጦ መንገዱን ተሻግሮ
አነስተኛ መብራቷን እንዳበራች ወደቆመችው 131 ፊያት አመራ።

ዝናቡ ይወርዳል። የዝናብ መጥረጊያው ሳይሰለች ከወዲያ ወዲህ


ይንቀዠቀዣል። ናትናኤል የመኪናውን ትንሽ መብራት ሳያጠፋ አይኖቹን
በሰፊው ከፍቶ የሆቴሉን በር ይመለከታል። ዝናቡ ብን ብን ይላል። አብርሃም
የለም።

ድንገት የመኪናው መስኮት ሲንኳኳ ተሰማው። ናትናኤል ፊቱን መለስ


አድርጎ ተመለከተ። በዝናቡ ነጠብጣብ በተሸፈነው መስኮት ውስጥ የታየው ግን
የተሰባበረና የተወለጋገደ ምስል ነበር። ቢሆንም የሰው ቅርጽ መሆኑ ይለያል።
'አብርሃም?’ ናትናኤል እጁን ሰድዶ መስኮቱን ዝቅ አደረገ።

98
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የዝናብ ካፖርት ደርቦ ብን ብን በሚለው ዝናብ የቆመው ሰው አብርሃም


አለመሆኑን ወዲያው ተረዳ። ደነገጠ። ስህተቱ ትዝ አለው፤ ያጠፋው ጥፋት ፊቱ
ላይ ድቅን አለበት።

“አቤት …?” አለ የሚከተለው እየታወቀው።

“መንጃ ፈቃድ።” አለው ትራፊክ ፖሊሱ ሠላምታ ከሰጠው በኋላ። የሠንጋ


ተራን የትራፊክ መብራት ጥሶ ሲያልፍ ነበር ጥግ ይዞ የነበረ ሞተረኛ ትራፊክ
ፖሊስ ሞተር ብስኪሌቱን አስነስቶ በዝናብ ውስጥ የተከታተለው።

ናትናኤል ደረቱን ዳበሰ። ሹራብ ድፍን ሹራብ። መንጃ ፈቃዱስ? ኮቱ ኪስ


ውስጥ? እቤት! የሚከተለው ጭቅጭቅ ሲታሰበው ጭንቅላቱን ይፈልጠው ጀመር።
“ይቅርታ ወንድም ችግር ገጥሞኝ…” የሚለው ጠፋው ናትናኤል።
“መንጃ ፈቃድ ጌታዬ።” ፈርጠም አለ ትራፊክ ፖሊሱ።
ናትናኤል መኪናው ውስጥ ተኮፍሶ መደራደሩ እንደማያዛልቀው ሲረዳ ቀልጠፍ
ብሎ በሩን ከፈተና ከመኪናው ወረደ። ትራፊክ ፖሊሱ ወደኋላው አፈግፍጎ
በዝምታ ይመለከተው ጀመር።
“ወንድም… ችግር አጋጥሞኝ ድንገት ከቤት ቸኩዬ ነው የወጣሁት …
መብራቱንም የጣስኩት ለዚህ ነው። ይቅርታ አድርግልኝ።” ወደጎን ሸፈፍ ሸፈፍ
እያለ የሚዘንበው ዝናብ ፊት ፊቱን አለው።
“መጀመሪያ መንጃ ፈቃድዎን ጌታዬ።”
“እሱን ነውኮ የምልህ። አየህ ቸኩዬ ስወጣ…”
“መንጃ ፈቃድ የሎትም?“ በጨለማው ውስጥ ትራፊክ ፖሊሱ ፈገግ ያለ መሰለው።
“አለኝ - አለኝ። እቤት እረስቼው ስለወጣሁ ነው።” ናትናኤል በራሱ ተናደደ።
”እሺ ጌታዬ … ወደ ጣቢያ ሄደን ብንነጋገር ይሻላል።“

(ቆንጆዎቹ፤ ሰርቅ ዳ. 1989፣ ገጽ 58 - 62)

99
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና

• በታሪኩ ውስጥ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮች መረዳታቸውን


ማረጋገጥ

• በተደመጠው ታሪክ ውስጥ የተፈጸሙ ድርጊቶችን


አስታውሰው በቃል መናገር መቻላቸውን መመዘን

ክፍልሁለት፡ መናገር
ወድ መምህር የማዳመጥ ክሂል ማዳመጥን በተግባር በመለማመድ ሊዳብር
እንደሚችለው ሁሉ የተማሪዎቻችን የመናገር ክሂል ችሎታ ሊጎለብት የሚችለውም
ንግግርን በተጨባጭ መከወን እንዲችሉ ስናደርግ ነው። በመሆኑም በክፍል ውስጥ
በመነሻነት ተማሪዎች የሚያደርጉት ንግግር በዋነኝነት በወደፊቱ እውናዊ
ህይወታቸው ጥሩ የተግባቦት አቅም እንዲኖራቸው መንገድ ይጠርግላቸዋል።
ስለሆነም በመናገር ትምህርት ክፍለጊዜ ወቅት ተገቢ ማበረታቻዎችን በማድረግ
ሁሉም ተማሪዎችዎ በንቃት እንዲሳተፉ እገዛ ያድርጉላቸው፤ ተከታታይ
ምልከታዎች በማድረግም የንግግር ክሂል ችሎታዎቻቸውን ይመዝኑ።

በምዕራፍ 7 በመናገር ትምህርት ክፍል ሁለት ተግባራት የቀረቡ ሲሆን፣


በመጀመሪያው ተግባር 'ከቆንጆዎቹ’ ረዥም ልቦለድ የተቀነጨበውና በማዳመጥ
ትምህርት ክፍል ስር የቀረበውን ታሪክ መነሻ በማድረግ ቀጣዩን ክፍል በየራሳቸው
እየተነበዩ እንዲናገሩ የሚጋብዘው ተግባር ይቀርባል።ተማሪዎች በቡድን በቡድን
እየሆኑ ሀሳብ እንዲለዋወጡ ይጠበቃል። ሲጠናቀቅም አምስት ወይም ስድስት ያህል
ተሳታፊዎችን በመጋበዝ ሀሳባቸውን እንዲያጋሩ ያድርጉ። (ከ10 -15 ደቂቃ) እዚህ
ላይ ሁሉም ተማሪ የመናገር እድል እንዲያገኝ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በየቡድኑ ይበልጥ
ሳቢ በሆነ መልኩ የታሪኩን ክፍል ያዋቀረ ተመርጦ ሀሳቡን ለክፍሉእንዲያጋራ
የሚደረግ ይሆናል።

ሁለተኛው ተግባር ከዚህ ቀደም ስላነበቧቸው ዘመን ተሻጋሪ ልቦለዶች ታሪክ


የሚያስታውሱትን በንግግር መልክ (በቃል) ለክፍል እንዲያቀርቡ የሚጋዝ ነው።
100
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እዚህም ላይ የተማሪዎች የነቃ ተሳትፎ ያስፈልጋል።

እባክዎ መምህር ተማሪዎችዎን እያበረታቱ ሁሉም ተሳታፊ የሚሆኑበትን እድል


ያመቻቹ፤ ምዘናውንም በተግባር የንግግር ተሳትፏቸውን እያዩ ያከናውኑ።

ምዘና

• ጥያቄበመጠየቅመረዳትናአለመረዳታቸውንመመዘን፣

• ተማሪዎችተወያይተውሲያቀርቡምልከታማድረግ፣

ክፍል ሶስት፡ ንባብ

ቅድመምንባብ ጥያቄዎች

መምህር ልቦለድን አስመልክቶ የቀረበውን ምንባብ ከማስነበብዎ በፊት በተማሪ


መጽሐፍ ላይ የቀረቡትን የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች ተማሪዎችዎ በቡድን በቡድን
እየሆኑ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንዲሰሯቸው ያድርጉ። ይህም ቀደም ሲል ልቦለድን
አስመልክቶ የነበራቸውን እሳቤ እንዲያጋሩና ራሳቸውም ከሌሎች እንዲጋሩ
እድልይፈጥርላቸዋል።
የማንበብ ሂደት

መምህር ተማሪዎችዎ ምንባቡን በየግላቸው በለሆሳስ እያነበቡአጫጭር ነጥቦችን


በማስታወሻ መልክ እንዲይዙያድርጉ።
የማንበብ ጊዜ ጥያቄዎች

በዚህ ንዑስ ክፍል ተማሪዎች ቀደም ሲል ካነበቡት የጽሑፍ ክፍል ምን እንደተረዱ


እንዲናገሩ የሚጠይቅና ቀሪው የምንባብ ክፍል ስለልቦለድ ጽሑፍ ምን ምን
ተጨማሪ ነጥቦችን ሊነግረን እንደሚችል እንዲገምቱ (እንዲተነብዩ) የሚጋብዝ ጥያቄ
ቀርቧል። እርስዎም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተማሪዎችዎ ንባባቸውን ገታ
አድርገው ጥያቄዎቹን በቃል እንዲመልሱ ያበረታቷቸው።

101
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አንብቦመረዳት

ውድ መምህር ተማሪዎችዎ ምንባቡን አንብበው ማጠናቀቃቸውን ሲያረጋግጡ


የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን ወደ መስራቱ እንዲሸጋገሩ ይጋብዟቸው።
በመጀመሪያም ምንባቡንመሰረት በማድረግ የቀረቡትን የእውነት/ሀሰትእና የምርጫ
ጥያቄዎች ደብተራቸው ላይ ጽፈው እንዲሰሯቸው ያድርጓቸው። እንዲሁም በቃል
እያብራሩ እንዲመልሷቸው የተሰጡትን ጥያቄዎችንም በትእዛዛቸው መሰረት
እንዲሰሩ ያድርጉ፤ማስተካከያ በመስጠትምያበረታቷቸው።በጋራ በሚሰሩበት
ወቅትም የሁሉንም ተማሪዎች ተሳትፎ ባማከለና በጥያቄና መልስ ስልት ይሁን።
በመጨረሻም ስለልቦለድ ምንነት እና የልቦለድ አላባውያን አጠርያለ የማሳረጊያ
ገለጻ በማቅረብ ትምህርቱን ያጠናቁ።

ምዘና

• በልቦለድ ውስጥ የሚካተቱ አላባውያን ምንምን እንደሆኑ እንዲዘረዝሩ


እና እንዲያብራሩ መጠየቅ፣
• በቡድን ውይይት ወቅት የተሳትፏቸውን መጠን በምልከታ
በመከታተል መመዘን
• በጽሑፍ የተሰጡ ምላሾችን ደብተራቸውን በመሰብሰብ እርማት
መስጠት

ክፍል አራት፡መጻፍ

የልቦለድ ድርሰት የሚጽፉ ደራሲያን በሚስሏቸው ገጸባህሪያት አማካኝነት


የሚያቀርቡልንን ታሪክ የሚጽፉት የተለያዩ የአጻጻፍ ቴክኒኮችን በመጠቀም
ነው።ቴክኒኮቹንም በተናጠል ወይም አንዱን ከሌላው ጋር እያቀናጁ ሊጠቀሙ
የሚችሉ ሲሆን፣ የፈጠራ አቅማቸውንም የሚገልጡባቸው ናቸው።

በዚህ ክፍል የልቦለድ ዘዴዎችን አስመልክቶ አጭር ማስታወሻ ቀርቧል።


መምህር ተማሪዎችዎ ይህንን ማስታወሻ እንዲያነቡ ካደረጉበኋላበቅርባቸው
102
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የሚያገኙትን አንድ የልቦለድ ስራ (መጽሐፍ) በማንበብ ልቦለዱ የተጻፈበትን


ዘዴ በምሳሌ አስደግፈው በገለጻ መልክ በጽሑፍ እንዲያዘጋጁና ለክፍሉ አቅርበው
እንዲያነቡ ያበረታቷቸው።በጽሑፋቸው ውስጥም የልቦለዱን ጭብጥ፣
ገጸባህሪያት፣ ዋና ዋና ግጭቶችና ሌሎች አላባዊያንን እንዲጠቅሱ ያሳስቧቸው።
አፈጻጸማቸውንም ይከታተሉ፤ ያዘጋጁትን ጽሑፍም ከክፍል አቅርቦት በኋላ
ሰብስበው እርማት ይስጡበት።
ምዘና

• የልቦለድ አላባዊያንን መለየት መቻላቸውን በቃልና በጽሑፍ


ተግባራት ወቅት ማረጋገጥ

• ልቦለድ አንብበው
የልቦለድዘዴዎችንበትክክልመለየትናአለመለየታቸውንመገምገም።

ክፍል አምስት፡ ቃላት

በዚህ የቃላት ትምህርት ክፍል የተወሰኑ ቃላትበመጥበቅና በመላላት እንዴት


የፍች ልዩነት እንደሚያስከትሉ የሚታይበት ነው።በዚህም ተማሪዎች
የሚቀርብላቸውን ገለጻና የሚሰጧቸውን ምሳሌዎች መሰረት አድርገው
ጥብቀትንና መላላትን አረፍተነገሮችን በመመስረት በተግባር እንዲያሳዩ
ይጠበቃል።

ውድ መምህር እርስዎም የዚህን ተግባር ተፈጻሚነት አስቀድመው ዝግጅት


በማድረግና ተጨማሪ ምሳሌዎችን በማቅረብና ምጋቤ ምላሾችን በመስጠት
የተለመደ እገዛዎን ለተማሪዎችዎ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በትምህርት ክፍሉ የተለያዩ ተግባራት የቀረቡ ሲሆን፣ ትዕዛዛቱን ተከትለው


እንዲሰሯቸው ይጠበቃል።እንደአስፈላጊነቱም ተማሪዎች ሌሎች ቃላትን
በራሳቸው ፈልገው ቃላቱን በማጥበቅና በማላላት አረፍተነገሮችን
መስርተውፍቻቸውን እንዲያሳዩ ሊታዘዙ ይችላሉ።
103
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና
• ተማሪዎች በቡድን የቃላት መጠበቅና መላላት የክፍል ስራ መስጠትና
መገምገም።
• የራሳቸውን ቃላት መርጠው ቃላቱን በማጥበቅና በማላላት
አረፍተነገሮች መመስረት መቻላቸውን ማረጋገጥ።

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

በዚህ የሰዋስው ትምህርት ክፍል በዓረፍተ ነገር መዋቅር ውስጥ በተደጋጋሚ


የሚከሰቱ የተለያዩ ሰውስዋዊ ስህተቶችን የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት
ይደረግባቸውል። በዚህም ተማሪዎች ከስህተት የጸዱ አረፍተነገሮችን
እንዲመሰርቱ ወይም ተቀባይነት ያላቸውን የአረፍተነገር መዋቅሮች እየተጠቀሙ
ሀሳባቸውን እንዲገልጹ የሚያስችሏቸውን ልምዶች ይቀስሙበታል።

አረፍተነገሮችን በመመስረት ወቅት በተደጋጋሚ ከሚያጋጥሙት ስህተቶች


መካከል የቁጥር፤ የጾታ፣ የመደብአለመስማማት፣የተሳቢ አመልካች ካለቦታው
መግባት ወይም መቅረት፣የእምርአመልካች መቅረት ወይም ያለቦታው መግባት፣
እንዲሁም የሀረግ አለመጣጣም ወዘተ…የሚጠቀሱ ናቸው።ስለሆነም መምህር
እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የተማሪ መጽሐፍንና ሌሎች ማጣቀሻዎችን
(ዋቢዎችን) መነሻ አድርገው በማስታወሻ የተደገፈ ገለጻና ማሳያ የሚሆኑ
ምሳሌዎችን ያቅርቡላቸው።

መመህር በመጨረሻም የቀረቡትን መልመጃ ጥያቄዎች በየግላቸው ሰርተው


እንዲያሳርሙ በማድረግ አወንታዊ ምጋቤ ምላሽ ይስጧቸው።ድጋፍ (ተጨማሪ
ጊዜ ለሚፈልጉ) ወይም ማበልጸጊያ (ፈጥነው ተግባራቱን ለሚከውኑ) ለሚሹ
ተማሪዎችም ተጨማሪ መለማመጃ ጥያቄዎችን አዘጋጅቶ በመስጠትና
ለውጣቸውን በመከታተል እገዛ እንዲያደርጉላቸው ይጠበቃል።

104
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና
• ሰዋስዋዊ ስህተት የሌለባቸው ዓረፍተነገር መመስረታቸውን እና
አለመመስረታቸውን ማረጋገጥ።
• ሰዋስዋዊ ስህተት ያለባቸውን ዓረፍተነገሮችን አስተካለው መጻፍና
አለመጻፋቸውንመመዘን።

የተመረጡ የጥያቄዎችመልስ
ትምህርት አንድ፡ ማዳመጥ
የማዳመጥ ጊዜ
1. ጓደኛው አብርሃምን ለመገናኘት 2. ወደ ዲ አፍሪክ ሆቴል
የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች
መልመጃ አንድ
1. ርብቃ
2. ትከሻውን ሰበቀና ተወው (ከርብቃ ጋር ሲያወራ)/ መኪናውን ከፍቶ ወረደ
(ከትራፊኩ ጋ ሲያወራ)
3. ቀዩ የጥራፊክ መብራት ከመሬቱ ላይ ሲያርፍ
4. ትራፊክ መብራት ጥሶ አልፎ ስለነበር ገዳዩ ሳይመጣ አስቀድሞ በሞተር
ሳይክል ሲከታተለው የነበረው ትራፊክ ፖሊስ ጣልቃ በመግባቱና ይዞት ወደ
ፖሊስ ጣቢያ በመሄዱ
5. ናትናኤልና ርብቃ ተኝተው ሲያወሩ ነበር፣ ስልክ ተደወለ፣ ስልኩን አነሳ፣
ጓደኛውን ሊያገኝ ከቤት ወጣ፣ ዲ. አፍሪክ ሆቴል ደረሰ፣ ሊገድሉት የፈለጉት
ሲብቁት ነበር፣ ገዳዩ ሽጉጥ አቀባብሎ ወረደ፣ ናትናዔል መብራት ጥሶ ስለነበር
ትራፊኩ ተከታትሎት መጣ፣ መንጃ ፈቃድ ጠየቀው…ስላልያዘ ወደ ፖሊስ
ጣቢያ ይዞት ሄደ…

105
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ


መልመጃ ሁለት
ሀ. 1. ሀሰት 2. እውነት 3.ሀሰት 4.እውነት 5.እውነት 6. ሀሰት

ለ. 1. ሐ 2. ሀ 3. ሐ 4.መ 5.ለ

ሐ. 1. ታሪኩ የእውኑን አለም ይመስላል እንጂ በትክክል ተፈጽሞ የተገኘ


አይደለም (የእውኑን አለም ገጠመኝ መነሻ አድር በምናብ የተፈጠረ ነው)
2. ረጅም ልቦለድ በርካታ ገጸባህሪያት አሉት፣ ታሪኩ ይጠማዘዛል(በርካታ
ቅርንጫፎች አሉት)፣ አንብቦ ለመጨረስ ረጅም ጊዜ ይፈጃል፣ ከህይወት እስከ
ሞት ይተርካል፣ ዝግ ብሎ ይጓዛል፣ ከአንድ በላይ ጭብጥ ይኖረዋል…
3. ሙሉ ታሪኩን በማንበብ (የተደጋገሙ ሀሳቦችን በመንተራስ)፣ ከገጸባህሪያቱ
ንግግርና ድርጊት፣ ከተራኪው ጥቆማ…
4. ልቦለድ ስለሰው ልጆች ገጠመኝ የሚጻፍ ጽብረቃ ነው (ህይወት)፣ ነገሩ ሊሆን
ወይም ሊፈጸም የሚችል ነው (እውነት)፣ ደራሲው ቃላትን እየመረጠ
ባማረ(ሳቢ በሆነ) መልኩ ያቀርብልናል (ውበት)
5. ግጭት በተፈጥሮው መድረሻ ስላለው ቀጥሎ ምን ይሆን፣ ምን ሊከሰት ይችላል
እያልን ስለምንከታተለው ልብ ይሰቅላል ስለሆነም በጉጉት እስከፍጻሜው
እንድናነበው ይገፋፋናል…
ክፍል አምስት፡ ቃላት
መልመጃ ሦስት
1. ሀ. የሚያርሰው (ላልቶ- የሚያረጥበው፤ ጠብቆ- ሰውነት
የሚገነባው/የወለደች)
ለ. በራ (ላልቶ- ራሰ መላጣ፤ ጠብቆ - ብርሃን ሰጠ
ሐ. ሽፍታ (ላልቶ - ዘራፊ፣ ቀማኛ፤ ጠብቆ- ፊት ወይም ቆዳ ላይ የሚታይ
ብጉር)
መ. ከዳኝ (ላልቶ - ክዳን የሚከድን/ሸፋኝ፤ ጠብቆ - ቃሉን
አፈረሰ/አልሰጥም አለ)
106
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሠ. ይጣላል (ላልቶ - ይወገዳል፤ ጠብቆ - ይጋጫል፣ አታካሮ ያስነሳል)


ረ. አማች (ላልቶ - የጋብቻ ዘመድ ፤ ጠብቆ - ስም አነሳች/ሀሜት/)
ሰ. ሰባ (ላልቶ - ቁጥር፤ ጠብቆ - ወፈረ/ጮማ ሆነ)
ሸ. ቀላ (ላልቶ - ቀይ ሆነ (ቀላ አለ)፤ ጠብቆ - አረደ/ አንገት ቆረጠ)
2. 1. በመላላት 2.በመጥበቅ 3.በመላላት 4.በመጥበቅ 5. በመላላት
ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው
መልመጃ አራት

ሀ. 1. ገበሬው በሬውን ሸጠ።

2. ሰነፍ ተማሪዎች ዘወትር ይጨነቃሉ። /ሰነፍ ተማሪ ዘወትር


ይጨነቃል።/

3. ኢትዮጵያ የተለያዩ የአትክልት አይነቶችን ታመርታለች።

4. አካባቢን ማጽዳት ተላላፊ በሽታን ለመከላከል ይረዳል።

5. ሯጩ ልጅ በፍጥነት እየሮጠ መጣ።


ለ.

መረን ለቀቅ የቋንቋ አጠቃቀመም ከማህበራዊ ገጽታ አንጻር ሲታይ አሉታዊ


መልኩጎልቶይታያል።ይህም ምንም እንኳ ተግባቦትን ባያደናቅፍም ማሻከሩ
ግንአይቀርም።ስለዚህ የቋንቋ አጠቃቀማችን ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይነው።
ለምሳሌ ታላላቅን አንቱ እያሉ በአክብሮት ማናገር፣ የሚቀርቡንና ወጣት
የሆኑትን ደግሞ አንተ/አንቺ እያሉ በትህትና ማዋራት ይገባል።ይህንንም ፊት
ለፊት ሆነን በምንነጋገርበት ወቅትም ሆነ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሀሳብ
በምንለዋወጥበት ወቅት ልንተገብረው ይገባል።

107
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ስምንት
መገናኛ ብዙኀን

ርዕስ፡-የመገናኛብዙኀን (8ክፍለ ጊዜ)

የሚጠበቁ ውጤቶች
ተማሪዎችየዚህን ምዕራፉንትምህርትካጠናቀቁበኋላ፡-

• በቃልየተላለፍን መልዕክት በጥሞና በማዳመጥ የማጠቃለያ ሀሳብ


ይሰጣሉ፡
• የተሰጣቸውን ንግግርአዳምጠው ምክረ ሀሳብ(አስተያየት)ያቀርባሉ።

• የፅሁፉን ዋናፍሬ ሃሳብ በማንበብ ይለያሉ።

• ምክንያታዊ ቅደም ተከተልን በጠበቀ መልኩ አከራካሪ ድርሰትይጽፋሉ።

• የፅሁፍን ዓውድ በመጠበቅተመሳሳይና ተቃራኒትርጉሞችንይጠቀማሉ።

• ሰዋስዋዊ ጊዜንበ ትክክል ይጠቀማሉ።

ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ

ውድ መምህር ይህ ክፍል ስምንተኛውን ምዕራፍ የምንጀምርበት ነው። በመሆኑም


ተማሪዎች ቀድሞ ሲያደርጉት እንደነበረው ርዕሱን ከተዋወቁ በኋላ የሚጠበቁ
ውጤቶችን እንዲያነቡ በማድረግ ወደ ማዳመጥ ትምህርቱ እንዲሸጋገሩ ሁኔታዎችን
ያመቻቹላቸው።

ቅድመማዳመጥ
መምህር በቅድመ ማዳመጥ ተግባር ስር ተማሪዎች የቀደመ ልምዳቸውን መሰረት
108
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አድርገው የሚመልሷቸው ጥያቄዎች ቀርበዋል። ጥያቄዎቹን ተራ በተራ በማስነበብ


በጋራ መልሷቸው። የቀረቡት ቃላት ያላቸውን ፍቺም ተማሪዎቹ ገምተው ወደ
ማዳመጡ ተግባር እንዲገቡ ያበረታቷቸው።ማዳመጥ ከመጀመራቸው በፊትም
ከርዕሱ በመነሳት ምንምን ነጥቦች ሊነሱ እንደሚችሉ እንዲተነብዩም ሊያደርጉ
ይችላሉ።

ለማዳመጥ መዘጋጀታቸውን ካረጋገጡ በኋላ ጽሁፉን ቢያንስ ሁለት ጊዜ


ያንብቡላቸው። በመጨረሻም የቀረቡትን የድህረ ማዳመጥ ጥያቄዎች፣
የተደመጠውን ምንባብ መነሻ አድርገው እንዲመልሷቸው ሁኔታዎችን
በማመቻቸት የአዳምጦ መረዳት ንኡስ ክሂላቸው ያለበትን ደረጃ ይመዝኑ።

ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን

ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመልካም ነገር ስንጠቀማቸው የሚሰጡንን ጠቀሜታ ያህል


ለክፉ ነገር ስንጠቀማቸው መርዝ የሚረጩ፣ ሰዎችን እርስ በርስ የሚያጋጩ፣
የሌሎችን ስብዕና የሚጎዱ በዋናነት ግን ተቻችሎ በአብሮነት መኖርን በእጅጉ
የሚያመናምኑ ሊሆኑ ይችላሉ።

በቀደሙት ሚዲያዎች ማለትም በቴሌቭዥን፣ ሬዲዮ፣ በጋዜጦችና መጽሄቶች ላይ


ያለው በቡድን መረጃዎችን የማጣራት፣ ሚዛናዊነትና ትክክለኛነትን የማስጠበቅ
ተግባር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቦታ የለውም። ለምሳሌ በቀደሙት መገናኛ
ብዙሃን ሪፖርተሮች የሚያመጡትን መረጃ አርታኢዎች ትክክለኛነቱን ያጣራሉ፣
ሚዛናዊነቱን ይመዝናሉ፣ የተገኘው መረጃ በህብረተሰቡ ላይ ሊያመጣ የሚችላቸውን
ጉዳቶችና ጠቀሜታዎች መዝነው በማጥራት ዘገባው እንዲተላለፍ ያደርጋሉ።
በማህበራዊ ድረ-ገፆች ግን ይሄ ዕድል እጅግ የቀነሰ ነው። አንድ ሰው በተሰማው
ስሜት ወይም ባገኘው መረጃ ላይ ተመርኩዞ መረጃን ያለከልካይ ማሰራጨት
ይችላል። በመልካምም ሆነ በጥላቻ መንፈስ ተነሳስቶ እውነታውን ደብቆ ሀሰተኛ
መረጃ በመፍጠር ሊያሰራጭና ጥፋት ሊያደርስ ይችላል።

109
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ማህበራዊ ድረ-ገፆች ዜጎችን በአገራቸው ማንኛውም ጉዳዮች ላይ “ያገባኛል” በሚል


ስሜት በነጻነት ሀሳባቸውን በመግለጽ እንዲሳተፉ በማስቻላቸውና በአብሮነት
ተከባብረውእንዲኖሩ ጥርጊያውን በማመቻቸታቸው ተቀባይነታቸው ከፍተኛ ነው።
ይሁን እንጂ በተቃራኒው በማህበራዊ ድረ-ገጾችም ሆነ በዋናዎቹ መገናኛ ብዙሃን
ላይ ያለውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በጥንቃቄና በሃላፊነት ስሜት
ካልተጠቀምንበት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዘነ ይሆናል። አለም አንድ በሆነችበት
በዚህ ወቅት የመረጃን ፍጥነትና ተደራሽነት ማንም ሊቆጣጠረው አይቻለውም።
ዴሞክራሲ ጎልብቶባቸዋል የሚባሉ አገሮች ጭምር በማህበራዊ ሚዲያዎች
በሚተላለፉ የተዛቡ መልዕክቶች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እየገቡ ስለመሆናቸው
በተደጋጋሚ ከሚታዩ ሁነቶች መረዳት አያዳግትም። በተለያዩ ድረ-ገፆች የሚተላለፉ
የሀሰት ወሬዎችና የጥላቻ ንግግሮች ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ
ቀውስ አስከትለውባቸዋል።

በተቀራኒው ማህበራዊ መገናኛዎችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው በርካታ መልካም


የሆኑ ተግባራትን እናስፈጽምባቸዋለን። ለምሳሌ በአገራችንም ሆነ በሌሎች
አካባቢዎች እንደ ፌስቡክ፣ ትዊተርና ቴሌግራም የመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችን
በመጠቀም በፋይናንስና በሌሎችም ድጋፎች እጥረት ምክንያት በሰው ህይወት ላይ
ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ ተችሏል፤ እየተደረገም ነው። የመታከሚያ ገንዘብ
አጥሯቸው በበሽታ የሚሰቃዩ ህሙማን በእነዚህ መገናኛዎች አማካኝነት በሚለቀቁ
መረጃዎች ብዙ ድጋፎችን ማግኘት ችለዋል። ለረጅም ዓመታት ተጠፋፍተው የነበሩ
ቤተሰቦች ተገናኝተዋል። በእነዚሁ ሚዲያዎች አማካኝነት ብዙዎች ወዳጅነት
መስርተው በትዳር በመጣመር ልጆች ወልደው ስመዋል።

በተለይ እኛ ኢትዮጵያን በሀዘንና ደስታ አንዳችን ለአንዳችን ቀድመን የምንደርስ


በአንድነታችን ውስጥ ልዩነታችን በውበት የሚገለጽ፣ የወገናችን ጉዳት የሚጎዳን፣
ህመሙ የሚጠዘጥዘን፣ ሞቱ እንቅልፍ የሚነሳን ነን። ይህን ለዘመናት ተከባብሮ፣
ተቻችሎና ተፋቅሮ የመኖር እሴት የቀድሞውም ይሁን ያሁኑ ትውልድ ጠንቅቆ
ያውቀዋል። ይሁን እንጂ ይህንን መልካም እሴት ጠብቆና ተንከባክቦ ማቆየት
110
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ካልተቻለ፣ በሀሰት የሚነዙ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች ጉዳት ሊያደርሱበትና ዘላቂ


የመሆኑን ጉዳይ ሊሸረሽሩት ይችላሉ። በተለያዩ ጊዜያት እየየናቸው የመጣናቸው
የተጋነኑና በሀሰት ተቀነባብረው በማህበራዊ ሚዲያ የሚወጡ ከፋፋይ መረጃዎች
የፈጠሯቸው ቀውሶችም የቅርብ ጊዜ ትዝታዎቻችን ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎችና ድረ ገጾች የሚለቀቁ የበሬ ወለደ መረጃዎች በተለይ


ወጣቱን ትውልድ ስሜታዊ በማድረግ አላስፈላጊ ተግባራት ውስጥ እንዲገባ የሚገፋፉ
በመሆናቸው፣ በልዩ ጥንቃቄ ሊታዩ ይገባል። ሀገራችንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት
የዜጎቻቸውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሳይጋፉ፣ በማህበራዊ መገናኛዎች
የሚነዙ የሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር ጠንከር ያሉ ህጎችን በማውጣት
እየተገበሩ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ህጎቹ መውጣታቸው ብቻውን የመጨረሻ መፍትሔ
ሊሆን ስለማይችል፣ ዜጎች መረጃዎችን እያጠሩ በመውሰድና ሀሰተኛ ወሬዎችን
በመጠየፍ ብሎም ለስርጭታቸው ተባባሪ ባለመሆን የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል።
ይህንን ካደረግንና የማህበራዊ መገናኛዎችን አወንታዊ ጎኖች በአግባቡ ከተጠቀምን
በርካታ በረከቶችን እንቋደሳለን።

(ከኢዜአ ድረገጽ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎበት የተወሰደ)

ምዘና

• የተለያዩ መልዕክቶችን በጥሞና በማዳመጥ የማጠቃለያ ሀሳብ መስጠት


መቻላቸውን ማረጋገጥ፣
• ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች የመጡንግግሮች ላይ ጠቃሚ የሆኑ
ሂሶች መስጠታቸውንመመዘን፣
• ማንኛውንም ንግግር አዳምጠው ግብረ መልስ መስጠታቸውን መመዘን፣

ክፍል ሁለት፡ መናገር

ውድ መምህር፣ በዚህ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችዎ ንግግርን በተግባር


ለመለማመድ የሚረዳቸው የንግግር የማድረጊያ ተግባርቀርቦላቸዋል። ይህንንም

111
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እድል እንዲጠቀሙበት ለማድረግም ሁሉም ተማሪዎችዎ በንቃት እንዲሳተፉ


ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው።

ተግባሩ ከቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች መርጠው ክርክር እንዲደረጉ የሚጋብዝ ነው።


የክርክር ርዕሶቹም የሚከተሉትናቸው፡-

ሀ.የማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ጥቅማቸው ወይስ ጉዳታቸው ያመዝናል? ለምን?

ለ. ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሰዎችን ማህበራዊ ግንኙነት አጠናክረዋል ወይስ


አላጠናከሩም?

ምዘና

• የተወሳሰቡና ረጅም ከሆኑንግግሮችዋናውንሀሳብ


ማውጣታቸውንመመዘን፤
• በሚወያዩበት ወቅት ሀሳብ ማንጸባረቃቸውን መገምገም፤
• ልምዶቻቸውን ቀምረው ማጋራት መቻላቸውን ማጤን

ክፈል ሶስት፡ ንባብ


ቅድመ ምንባብ

የቅድመ ምንባብ ጥያቄዎች አላማ የተማሪዎችን ዳራ (የቀደመ ዕውቀት)


ወደሚነበበው ምንባብ እንዲሸጋገር ማስቻል ነው። በዚሁ መሰረት በዚህ ክፍል
ተማሪዎች እንዲመልሷቸውና ተነሳስኦት ኑሯቸው ወደ ማንበቡ ተግባር እንዲገቡ
የሚያስችሉ ሦስት ጥያቄዎች በተማሪ መጽሐፍ ላይ ቀርበዋል። እባክዎትን
መምህር ጥያቄዎቹ ከአጭር ጊዜ ውይይት በኋላ በቃል እንዲመለሱ ያድርጓቸው።

የምንባብሂደት

ዳራዊ እውቀታቸውን ካንጸባረቁ በኋላ ስለ ርዕሱ ገለጻ በመስጠት ምንባቡን


በተናጠል ድምጻቸውን ሳያሰሙ በዓይን እንቅስቃሴ ወይም በየተራ በማስነሳት አንድ

112
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ተማሪ ሲያነብ ሌሎቹ ከመጽሐፋቸው እየተከታተሉ እንዲያነቡ ያድርጓቸው።


ምንባቡን እያነበቡ እያለ የሚገጥሟቸውን አዳዲስ ቃላትና ሀረጋት በማስታወሻ
ደብተራቸው ላይ እየጻፉ እንዲሄዱምይንገሯቸው። ሁሉም በማንበብ ተግባሩ
እየተሳተፉ መሆናቸውን ለማረጋጥም ክፍል ውስጥ በመዘዋወር ቅኝት ያድርጉ።

የምንባብ ጊዜ

በምንባብ ጊዜ ደግሞ ንባባቸውን ገታ አድርገው ካነበቧቸው አንቀጾች


ምንእንደተረዱ ጥያቄዎቹን በመጠየቅ ይመዝኗቸው። የተወሰኑ ተማሪዎችን
መልስምበየተራ ይቀበሉ። በቀሩትአንቀፆችምምን ምንነጥቦች ሊነሱእንደሚችሉ
ግምታቸውንእንዲያስቀምጡ ይጠይቋቸው።

አንብቦ መረዳት

በማስከተል ወደምንባባቸው ተምልሰው የቀረውን ክፍል እንዲያነቡያድርጉ።


ምንባቡን እንደጨረሱ በቅድመ እና በጊዜ ምንባብ ጥያቄዎች ላይ የገመቷቸውን
መልሶች ትክክልመሆንናአለመሆናቸው እንዲያረጋግጡ እድል ይስጧቸው።

ተማሪዎች ምንባባቸውን እንደጨረሱ በትእዛዝ አንድ የቀረቡትን የ‹‹እውነት ሀሰት››


ጥያቄዎች በእርስዎ መሪነት ከነምክንያታቸው በጽሁፍ እንዲመልሱ ያድርጉ።
በሁለተኛው ትእዛዝ የቀረቡትን የምርጫ ጥያቄዎችም በተናጠል በደብታራቸው ላይ
እንዲሰሩ ያድርጉ። በደብተራቸው ላይ የሰሯቸውን ጥያቄዎች ተወያይተው
መልሶቻቸውን የጋራ ካደረጉ በኋላ እርማት ይስጧቸው። እርማት በሚሰጡበት ጊዜ
ሁሉንም ተማሪዎች እያሳተፉ ቢሆን ተመራጭ ነው።

የ‹‹እውነት/ሀሰት››እና‹‹የምርጫ›› ጥያቄዎችን ሲመልሱ ማብራሪያ


እንደሚያስፈልጋቸው ያሳውቋቸው። በዚህም የመገናኛ ብዙኀንን ምንነት፣ የመገናኛ
ብዙኀንና ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን አንድነትና ልዩነት፣ የማህበራዊ መገናኛ
ብዙኀን አይነቶች እንዲሁም ጥቅምና ጉዳት በሰፊው እንዲያውቁ ያድርጓቸው።
በተለይ ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ትልቅ ኪሳራ
113
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እንደሚያስከትል ማሳያ በመጥቀስ ያሳውቋቸው።

በሶስተኛው ትዕዛዝ ተማሪዎቹን በጥንድ እንዲወያዩ ሁኔታዎችን ካመቻቹ በኋላ


‹‹መገናኛ ብዙኀን›› በሚለው ምንባብ ውስጥ ስለ መገናኛ ብዙኀን ጠቀሜታ የቀረቡ
ይዘቶችን በማንበብ ተወያይተው ለክፍል ጓደኞቻቸው በጽሁፍ እንዲያቀርቡ
ያድርጉ።

ማህበራዊ መገናኛ ብዙኀንን በሚመለከት በምንባቡ ውስጥ ያገኙትን ቁም ነገር


መጀመሪያ ከነበራቸው እውቀት ጋር በማነጻጸር በጽሁፍ አስተያየት /ሂስ/
እንዲያደርጉና በቀጣዩ ክፍለጊዜ ‹‹ጽሕፈት›› በሚለው ክፍል እንዲያቀርቡ የቤት
ስራ ይስጧቸው።

ምዘና

• የመገናኛ ብዙኀን ምንነትና አይነቶችን መረዳታቸውን መመዘን፣

• የማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን አይነቶች፣ ጥቅምና ጉዳት


መለየታቸውን መመዘን፣
• የተለያዩ የማንበብ ስልቶችን መተግበራቸውን መመዘን፣

ክፍል አራት፡ መፃፍ

በዚህ ክፍል የመጻፍ ክሂልን የሚያዳብሩ ይዘቶች ቀርበዋል።በመጀመሪያው


ጥያቄድርሰት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተወያይተው ለጓደኞቻቸው በቃል
እንዲያቀርቡያበረታቷቸው። በሁለተኛው ደግሞ የድርሰት አይነቶችን በመዘርዘር
አንድነታቸውንና ልዩነታቸውን በጽሁፍ እንዲያስረዱያድርጉ።

መልሶቻቸውን ከተቀበሉ በኋላ ስለአመዛዛኝና ገላጭ ድርሰት የቀረበውን ማስታዎሻ


እያነበቡ እንዲወያዩ ጥቂት ደቂቃይስጧቸው።

ድርሰት በስርዓት የተዋቀሩ ዓረፍተ ነገሮች ወይም አንቀጾች እንደሚመሰርቱትና


114
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የተለመዱ የድርሰት አይነቶች ያሉ ስለመሆናቸውም ያስረዷቸው። በመማሪያ


መጽሐፋቸው ላይየቀረቡትን አመዛዛኝ ድርሰት እና ገላጭ ድርሰት በምሳሌ
ያስረዷቸው።ማስታወሻውንም በደብተራቸውላይ እንዲጽፉ ያድርጉ።

ተራኪና ስዕላዊ ድርሰትን የሚመለከት ማስታዎሻና ምሳሌዎች ከዚህ በታች


ቀርበውልዎታል። በመሆኑም በመማሪያ መጽሐፋቸው ላይ የቀረቡትን አመዛዛኝና
ገላጭድርሰቶች ከተማሩ በኋላ ስለተራኪና ስዕላዊ ድርሰት የሚያውቅትን
ይጠጥቋቸው።ቀጥለውም ከማብራሪያዎቹ ስር የቀረቡትን ምሳሌዎች ያንብቡላቸውና
በየትኞቹ የድርሰት አይነቶች እንደቀረቡ ይጠይቋቸው።በመጨረሻም ማስታወሻውን
ይስጧቸው።ስለስዕላዊ ድርሰት ሲያስረዷቸው ከገላጭ ድርሰት ጋር ተቀራራቢ
እንደሆነና ብዙ ባለሙያዎች ስዕላዊ ድርሰትን በገላጭ ድርሰት ስር እንደሚመድቡት
ያስረዷቸው። ነገር ግን ስዕላዊ ድርሰት የሚጠቀማቸው ቃላት በአዕምሯችን ምስል
የሚፈጥሩ እንደሆኑ ያስረዷቸው።በዘወትራዊና በተለመደው የቃላት አጠቃቀም
የምንጽፍ ከሆነ ድርሰቱ ስዕላዊ ሳይሆንገላጭእንደሆነም ያሳውቋቸው።

ለአብነትም ገላጭ ድርሰት አንድን አካል በቃላት አማካኝነት ስሎየሚያቀርብ ወይም


የሚያሳይ ነው።ሊገለጽ የሚፈለገው ነገር ቁመና፣መልክ፣ቅርፅ፣ መጠን፣ ጠባይ ሁኔታ፣
አጠቃላይ ማንነት እንደ ስዕል ያቀርባል። ከዚህም የተነሳ የገላጭድርሰት ሌላው
ስያሜው ስእላዊ ድርሰት ነው። ስእላዊና ገላጭ ድርሰትን አንድ አድርገው
የሚያቀርቡ ጸሀፊዎች አሉ ነገር ግን ልዩነታቸው ገለጻው በአዕምሮ ምስል መከሰት
ከቻለ ስዕላዊ ድርሰት ይባላል በአንጻሩ ደግሞ ገለጻው በአእምሮ ስዕልመሳልካልቻ
ለገላጭድርሰትይባላል።

ማስታወሻ
ተራኪ ድርሰት፡- ስላለፈ አንድ ድርጊት የሚተርክ ወይም የሚያትት የድርሰት
አይነትነው። ሁኔታዎችን፣ ክስተቶችን፣ ድርጊቶችንና ሰንሰለታዊ እውነቶችንየጊዜ
ቅደም ተከተላቸውን ጠብቆ እንዲህ እንዲህ ሆነ፣እንዲህ እንዲህ ተደረገ እያለ
የሚያቀርብ ጽሁፍ ነው።በተራኪ ድርሰት አብዛኛውን ጊዜ እንደ የህይወትታሪክ፣

115
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በጊዜና በቦታ ቅደም ተከተል እየተደራጁ የሚቀርቡ ሃሳቦች ወዘተ…ይቀርቡበታል።


ምሳሌ፡-
አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በመዓበልተመታና መርከቡ
ተሰባብራ በባህሩ ሰመጠች ሰውዬው እንደ ምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ
ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይይኖራል…ምግቡን ዓሳ
አያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።

አንድ ቀን ዓሳ ሊያድን ወደ ባህሩ እየሄደ በማሃል እዛች ባህር ላይ ጭስ ሸቶት


ዞርብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው… እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት
አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል
አለቀሰ ፈጠሪውን ወቀሰ እንዴትእዚህ ባህርላይብቻዬንጥለሀኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለሀኝ
ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለህ ብሎ አለቀሰ አማረረ…

ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ


መርከብ አየተደሰተ… የመርከቡ ሰዎች መጥተውጭነው ወሰዱት። ከዚያም
የመርከቡን ሰዎች ጠየቃቸው! እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ
እናንተ እንዴት አገኛቹኝ? አላቸው… መርከበኞቹም እኛማ በዛኛው በኩል ዞረን
እየሄድን ነበር ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለንመጣን አንተን
አገኘን አሉት።

ስዕላዊድርሰት፡-አንድን ነገር በቃላት አማካኝነት ስሎ በአዕምሮ ውስጥ ምስል


እንዲከሰት ወይም እንዲፈጠር የሚያደርግ የድርሰት ዓይነትነው።ከዚህ ባሻገር
የአንድን ነገር ሁኔታ በአይን እንዳዩት በእጅ እንደዳሰሱት በጀሮ በቅርብ ሆኖ
እንደሰሙት በጠቅላላው ግዙፍአድርጎ የሚያቀርብ ጽሁፍ ነው።

ምሳሌ፡-
እግሮቿ በጠረጴዛው ስር ይታያሉ፤ቀይቀለም የተቀቡት አውራጣቶቿ
የሚያሾፉበት መሰለው፣ እንደገና አይን ለአይን ተጋጩ ረጃጅም እጆቹን
የሚያገባበት ጠፋው ከት ብላ ሳቀችበት ምን እንዳሳቃት አልገባውም። ጠይም
116
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ፊቱ አሸቦመሰለ።ወዲያውኑ ቀጠሮ የሰጠው ባለስልጣን መጣ ቁመናው አጭር


ሆኖ ቦርጫም ነበር።
ከድርሰት አይነቶቹ ገለጻ በኋላ የቀረቡት አራት አንቀጾች ከየትኛው የድርሰት
አይነት እንደሚመደቡ በአነስተኛ ቡድን ሆነው ተወያይተው እንዲመልሱ
ተማሪዎችዎን ይዘዟቸው።ምላሻቸውንም በጋራ ተነጋገሩበት። በመቀጠልም
ከቀረቡት ርዕሶች መካከል መርጠው ከተማሯቸው የድርሰት አይነቶች መካከል
አመዛዛኝና ገላጭ ድርሰትን በመጠቀም አንቀጽ ጽፈው ለክፍል ጓደኞቻቸው
እንዲያነቡላቸው ያበረታቷቸው።የፃፏቸው አንቀጾች ትክክል ስለመሆናቸውም
እርማትይስጧቸው።
በመጨረሻም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ከገጠመኞቻቸው
በመነሳት አከራካሪ ድርሰት ጽፈው እንዲመጡ በየቤት ስራ መልክ ይስጧቸው።
ምዘና

• የድርሰትምንነትናአይነቶችንመለየታቸውንመመዘን፣

• እርስ በርስ እንዲገማገሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት

• ምክንያታዊቅደምተከተልንበጠበቀመልኩአከራካሪናገላጭድርሰትመፃፋ
ቸውንማረጋገጥ፣
• የጻፉትፅሁፍምንያህልየተደራጀእንደሆነመመዘን።

ክፍል አምስት፡ቃላት

በዚህ ክፍል የቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍችን የሚመለከተውን ማስታወሻ


በምሳሌካስረዷቸው በኋላ ከስሩ የቀረቡትን ጥያቄዎች በየግላቸው የክፍል ወይም
የቤት ስራይስጧቸው። መስራታቸውን ካረጋገጡላቸው በኋላም እርማት
ያድርጉላቸው።

ከዚህም በተጨማሪ ለቀረቡ ቃላት ተመሳሳይና ተጠቃራኒ ፍች መስጠትን


የተመለከቱትን ጥያቄዎች በየግላቸው ሰርተው እንዲያሳዩ ካደረጉ በኋላ በጋራ
117
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

እንዲወያዩባቸውያድረጓቸው።

ምዘና

• አውድን መሰረት አድርገው ለቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ


ይሰጣሉ፤

• ለተለተያዩ ቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ትርጉሞችን መስጠታቸውን


መመዘን፣

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

ውድ መምህር! ሰዋስውን ለማስተማር የግስ ጊዜየሚለውን ማስታወሻ ተማሪዎችዎ


በየግላቸው እንዲያነቡ ካደረጉ በኋላ በቡድን እንዲወያዩበት ጥቂት ደቂቃዎች
ይስጧቸው።ቀጥለውም ጊዜ አንድ ድርጊት መቼ እንደተፈጸመ ወይምመቼ
እንደሚፈፀም የሚገልፅ የግስ ባህሪ እንደሆነና ጊዜ በሶስት እንደሚከፈልምሳሌ
በመስጠትያስረዷቸው።

ማስታወሻውን ከተረዱ በኋላ በቡድን ተከፋፍለው ግሶችን የኃላፊ፣ የአሁን


እናየትንቢት ጊዜ ግሶች በማለት እንዲለዩ የክፍል ወይም የቤት ስራ ይስጧቸው።
ከዚህምበተጨማሪ በሰንጠረዡ ውስጥ ለቀረቡት ቃላት በቡድን በመሆን ምሳሌውን
መሰረትአድርገው ቅጥያዎችን በመጨመር የኃላፊ፣የአሁን እና የትንቢት
ግሶችንእንዲያሟሉያድረጓቸው፤የክፍል ተሳትፏቸውንማበረታታትዎንም አይዘንጉ።

ምዘና

• በንግግር እና በጽሁፍ ውስጥ ሁሉንም የግዜ ግሶችን በትክክል


በመጠቀም ለፈለጉት ውጤት መጠቀም መቻላቸውን መመዘን፣
• የግሶችን የጊዜ ሁኔታ እንዴት በንግግራቸውና በፅሁፋቸው በትክክል
እንደተጠቀሙመገምገም።

118
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የተመረጡ ጥያቄዎችመልስ
ክፍል አንድ፡ ማዳመጥ
ሀ. 1. እውነት 2. ሐሰት 3.እውነት 4.ሐሰት 5. እውነት

ክፍል ሦስት፡ ማንበብ


የድህረ ማንበብ ጥያቄዎች
መልመጃ ሁለት

ሀ. 1. እውነት 2. እውነት 3.ሐሰት 4.ሐሰት 5. እውነት


ለ.1. ለ 2. መ 3.መ 4.ሐ 5. ሀ

ክፍል አራት፡መጻፍ
መልመጃ አራት

ሀ. ስዕላዊ ድርሰትሐ.ስዕላዊድርሰት
ለ. ተራኪ ድርሰትመ.አመዛዛኝ ድርሰት
ክፍልአምስት፡ቃላት
መልመጃ አምስት
ሀ. ተመሳሳይና ተቃራኒ
(በቅንፍ ውስጥ የመጀመሪያው ለቃሉ ተመሳሳይ ሁለተኛው ተቃራኒ ነው)

- መግታት (ማስቆም፤ ማስኬድ)- እሴቶች (ቅርሶች፤ ዋጋ አልባዎች)


- እንዲያሳልጡ (እንዲያቀላጥፉ፤ እንዲያሰናክሉ) - እምቅ (የካበተ፤የመነመነ)
- ዘርፈ ብዙ (በያቅጣጫው፤ ውስን) - ተግዳሮቶች (እንቅፋቶች፤ እድሎች)
- ህልሞቻቸውን (ትልሞቻቸውን፤ቅዠቶቻቸውን)- እንዳይሸረሽሩ (እንዳይቦረቦሩ፤
እንዲሸረሸሩ)

119
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ለ. ተመሳሳይናተቃራኒ

(በቅንፉ ውስጥ የመጀመሪያው ቃል ለቃሉ ተመሳሳይ ሁለተኛው ደግሞ


ተቃራኒ ነው።)

1. በመጣመር (በመቀናጀት፤በመነጣጠል)
2. የሚያመናምኑ (የሚያጭጩ፤ የሚያልቡ) የሚያስማሙ)
3. ያገባኛል (ይመለከተኛል፤ አያገባኝም)ኮስምኖባቸዋል)
4. ተከባብሮ (ተቻችሎ፤ ተናንቆ)
5.መፍትሔ (ቁልፍ፤ ተግዳሮት)

6.ሚዛናዊነት (ፍትሐዊነት፤ አድሏዊነት)

7. የሚያጋጩ (የሚያጣሉ፤

8. ጎልብቶባቸዋል (ዳብሮባቸዋል፤

9. በሬ ወለደ (ውሸት፤ ሀቅ)

10.አወንታዊ (በጎ፤ አሉታዊ)

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው


መልመጃ ስድስት
1.ሀ.ትመጣለች (የትንቢት ጊዜ) ሠ.ደረሰች (ሀላፊ ጊዜ)
ለ. ፈራ (ሀላፊ ጊዜ) ረ. አለፈ (ሀላፊ ጊዜ)
ሐ. ይሰበሰባል (የትንቢት ጊዜ) ሰ. ይሸፍን(የትንቢት ጊዜ)
መ. ነበር (ሀላፊ ጊዜ) ሸ. እየጸዳ ነው (የአሁን ጊዜ)

120
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

2. 1. ሀላፊ 2. የትንቢት 3.ሀላፊ 4. ሀላፊ 5.የአሁን

ተ.ቁ የኃላፊጊዜ የአሁንጊዜ የትንቢትጊዜ


አመሰገነ እያመሰገነነው ያመስግናል
1. ተኛ እየተኛነው ይተኛል
2. ጻፈች እየጻፈች ነው ትጽፋለች
3. ዘፈነ እየዘፈነ ነው ይዘፍናል
4. ሰበረ እየሰበረነው ይሰብራል
5. ገሰጸ እየገሰጸ ነው ይገስጻል
6. ተገኘ እየተገኘ ነው ይገኛል

የክለሳ ጥያቄዎች

3 በሚከተለው ሰንጠረዥ ውስጥ ለሚገኙ ቃላት በምሳሌው


መሰረትተመሳሳይናተቃራኒፍቻቸውን አሟሉ።

ተ.ቁ ቃል ተመሳሳይፍቺ ተቃራኒፍቺ


በደምሳሳው በጥቅሉ በነጠላው
መናድ ማፍረስ መደርደር
1. ቆንቋና ስስታም ቸር/ለጋስ
2. ገሀድ ይፋ ድብቅ፣ምስጢር
3. ጨቀነ፣ አመረረ ራራ
4. ምርቃት ምስጋና እርግማን
5. አዋቀረ ገነበ አፈረሰ
6. አውሸለሸለ አውተፈተፈ በስርዓትሰራ

121
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዕራፍ ዘጠኝ
ሥራ ፈጠራ
(ስምንትክፍለጊዜ)

የሚጠበቁ ውጤቶች

ተማሪዎች የምዕራፉን ትምህርት ካጠናቀቁ በኋላ፡-


• በቃል የተለያየን መልዕክት በጥሞና በማዳመጥ መስማማታቸውንና
ለመስማማታቸውን ያሳያሉ።
• ተማሪዎች ሀሳባቸውን በምክንያት በማስደገፍ በቃልይገልፃሉ።

• ጽሁፉን በማንበብ ለማን እንደ ተፃፈ ይለያሉ።

• የአዳዲስ ቃላትን ፍች ከፅሁፍ አውድ በመነሳትያወጣሉ።

• በዓረፍተነገር ውስጥ ተሸጋሪና ኢተሸጋሪ ግሶችን ይጠቀማሉ።

ክፍል አንድ፡ማዳመጥ
የሥራ ፈጠራሃሳብመገኛምንጮች

አዲስ የንግድ ሥራ ድርጅት ወይም ኢንተርፕራይዝ ለመመስረት በመጀመሪያ


በምን የንግድ ዘርፍ መሰማራት እንደምንፈልግ መምረጥ ያስፈልጋል።
የምንመርጠው የንግድዓይነት ነባር ወይም አዲስ የሚለውን ለመወሰን የራሳችን
የፈጠራ ችሎታና ቀደምሲል በዚህ መንገድ የተዘጋጀንበትን አዲስሃሳብ ሊኖር
ይገባል። አዲስም ሆነ ነባር የንግድ አይነት ለመመስረት መምረጥ ይኖርብናል።
አዳዲስ የንግድ ሃሳቦችን ለማግኘት የተለያዩ ዘዴዎችን ልንጠቀም እንችላለን።

122
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

በብዛት የተለመዱት የአዳዲስ የንግድ ሃሳብ ምንጮች ኢንተርኔት፣ደንበኞች፣


ነባር የንግድ ድርጅቶች፣አከፋፋዮችና የመንግስት የጥናትና ምርምር ተቋማት
ወዘተ ናቸው። እልመከታቸው፡-

ኢንተርኔት፡- ኢንተርኔት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዋነኛ የአዳዲስ ሃሳቦችና


መረጃዎች ምንጭ በመሆን እያገለገለ ያለ ቴክኖሎጂ ነው።በተለይ በአሁኑ ዘመን
እጅግ የበዙ መረጃዎችን ከኢንተርኔት መስኮት በቀላሉማግኝትይቻለል።ብዙ
በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ወጣቶች በተለይ በእንጨትና
ብረት ስራ ላይ የተሰማሩት ብዙ የምርት ዲዛይኖቻቸውን የሚያገኙት
ከኢንተርኔት ነው።በተለያዩ ሀገሮች የተለያዩ ባህሎችናልማዶች እንዳሉ ሁሉ
የምርት አይነቶችም እንዲሁ የበዙና የተለያዩ ናቸው።እነዚያን ምርቶች ከእኛ
አካባቢ ጋር ሊስማማ በሚችል መልኩ ዲዛይን አድርጎና አሻሽሎ በሀገር ውስጥ
ጥሬ እቃዎች በማምረት ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ገበያ ማቅረብይቻላል።

ደንበኞች፡- የደንበኞችን ፍላጎትና እርካታ ማረጋገጥ የሥራ ፈጣሪ ግለሰብ ዋነኛ


ተግባር ነው። ስለሆነም የደንበኞች ፍላጎት ምን እንደሆነ አሁን በሚቀርቡ
ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ያላቸው እርካታ እስከምን ድረስ እንደሆነ፣ ልንሰራ
ባሰብነው ምርት ወይም አገልግሎት የደንበኞቻችንን ፍላጎትለማርካት የምንችል
መሆን አለመሆናችንን ማጤን ይጠበቅብናል።

ነባርየንግድድርጅቶች፡-በገበያው ውስጥ የቆዩ የንግድ ድርጅቶች ወይም


ኢንተርፕራይዞች ከሚሰጡት አገልግሎትና ከሚያቀርቧቸው ምርቶች በመነሳት
ምንመሻሻሎች ብናደርግ ብቁ ተወዳዳሪ ሆነን ልንቀርብ እንችላለን? የሚሉና
ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎችን በአእምሮአችን በማምጣት በራሳችን በርካታ
አዳዲስ የንግድ አማራጮችን ማመንጨት እንችላለን። በእኛ አካባቢ የሌሎና
በሌሎች አካባቢዎች የተለመዱ የምርትና የአገልግሎት አይነቶችን በመለየት
ልናስተዋውቅም እንችላለን።
123
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

አከፋፋዮች፡-አከፋፋዮች ተመራጭ የንግድ ሃሳብ ምንጮች ናቸዉ።ምክንያቱም


እነዚህ ተቋማት የህብረተሰቡን ፍላጎት በስፋት የማወቅ እድሉ ስላላቸዉ ነው።
ብዙ ጊዜ ከተለያዩ ድርጅቶች ተቀብለው ለሚያከፋፍሏቸዉ ምርቶች የበርካታ
ደንበኞችን አስተያየት ስለሚቀበሉ ከደንበኞች ምርጫ ጋር የተያያዙ በርካታ
ሀሳቦች ይኖራቸዋል።ከዚህም በላይ አዲስ የንግድሥራ ከጀመርን በኋላም
ምርቶቻችንን ወደገበያ በማቅረብ ሊረዱንምይችላሉ።

የመንግስትተቋማት፡-መንግስታዊ ተቋማት በብዙ መንገድ የአዳዲስ የንግድ


ሃሳቦች ምንጭ ሊሆን ይችላሉ።

o ከፈጠራ መብት ጋር ግንኙነት ያላቸው የመንግስት ተቋማት መረጃ


አላቸው።
o የጥናትና ምርምር ተቋማት የሚያሳትሟቸው የጥናት ምርምር ሥራዎች
እዚህ ይገኛሉ።
o የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ተቋማት ፍላጎቱ ላላቸዉ
ወጣቶች እንዲጠቀሙባቸው በየደረጃው ባለው የመንግስት መዋቅር
ተደራጅተው ስላሉ እነዚህን በቀጥታ መጠቀምና ከእነዚህ ሃሳቦች በመነሳትም
የራሳችንን አዳዲስ የንግድ ሃሳቦች ማፍለቅ እንችላለን።
o የመንግስት ፖሊሲዎችና ህጎችም ለአዳዲስ የንግድ ሃሳቦች መነሻ
ሊሆኑይችላሉ።

እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው አማራጮች በዋናነት የቀረቡ እንጂ እነዚህ ብቻ


አለመሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል። ሌሎች በሥራ ፈጣሪው አስተሳሰብ ልክ
በመረጃ ምንጭነት ሊያገለግሉ የሚችሉ በርካታ አማራጮችም ይኖራሉ። ስለዚህ
ሌሎችንም መንገዶች መቃኘትና መጠቀም ተገቢ ይሆናል።

https://yerasbusiness.com/የሥራ−ሃሳቦች-business-idea/

124
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ቅድመማዳመጥ

የቅድመ ማዳመጥ ተግባራት በማሰራት ስለሚደመጠው ምንባብ የቀደመ


እውቀታቸውን በመቀስቀስ እንዲያሰላስሉ ያድርጓቸው። በመማሪያ መጽሐፋቸው
ላይ ሁለት ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል። እነዚህን ጥያቄዎች በቡድንወይም
በጥንድ በጥያቄና መልስ (እርስዎ እየጠየቋቸው በየተራ እንዲመልሱ
በማድረግ)ያሰሯቸው።በሚያዳምጡበት ጊዜ የሚሰሩትን ተግባርም በግልፅ
ይንገሯቸው።

የማዳመጥ ትምህርቱ ትኩረት“የሥራ ፈጠራሃሳብመገኛምንጮች” በተሰኘው ርዕስ


ስር ስራ ለመፍጠር የሚነሱ ሰዎች፣ አላማቸው እንዲሳካ ስራ ለመፍጠር
የሚያስችላቸውን መነሻ ሀሳብ ከየት ሊያገኙት እንደሚችሉ የተጠቆመበት ነው።
በመሆኑም ተማሪዎቹ የማዳመጥ ንዑስ ክሂሎችን ከማጎልበት ባሻገር ለነገ
ህይወታቸው የሚጠቅማቸው ክህሎት ይቀስሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመቀጠል የተዘጋጀውን የማዳመጥ ንባብ ሲያነቡላቸው በትኩረት በማዳመጥ


ጥያቄዎችን ለመስራት መዘጋጀት እንዳለባቸው ይንገሯቸው። ምንባቡን
ድምፅዎን ከፍ አድርገው ያንብቡላቸው፤ወይም በመቅረጸ ድምፅ ቀድተው
ያስደምጧቸው።አንድ ጊዜ ከተነበበላቸው በኋላም ጥያቄዎቹን
እንዲያስተውሏቸው ያድረጉ፤ የቀራቸው መልስ ካለም ለሁለተኛጊዜ ረጋብለው
ያንብቡላቸው።

ቀጥሎ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተማሪዎች የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን


እንዲሰሩና ሲነበብላቸው ያላስተካከሉት ካለ አጠናቅቀው እንዲፅፉ እድል
ይስጧቸው። በድህረ ማዳመጥ ተራ ቁጥር አንድ ላይየቀረቡትን ቃላትም
አውዱን መሰረት አድረገው ፍች እንዲሰጧቸውና ከጓደኞቻቸው ምላሽ ጋር
እንዲያነጻጽሩት ይሁን።እንዲሁም በማዳመጥ ሂደት ወቅት ማስታወሻ

125
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የያዙባቸውን ነጥቦች ለሌሎች በማጋራት ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ


ያበረታቷቸው።በመጨረሻም የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎች በየግላቸው ከሰሩ
በኋላ በጥያቄና መልስ በጋራ ውይይት እንዲያጠናክሩት ሁኔታዎችን
ያመቻቹላቸው።በውይይት ወቅት ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጥያቄዎች ካሉ
ተፈላጊውን የምንባቡን ክፍል ደግመው በማንበብ እገዛ ያድርጉላቸው።

ምዘና

• ተማሪዎች በማዳመጥ ወቅት ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን መከታተል፣

• የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምን ያህል አዳምጠው


እንደተረዱ መመዘን፣
• ያዳመጡትን በማስረጃ በማስደገፍ ማቅረባቸውንመከታተል፣

ክፍል ሁለት፡ መናገር


የመናገር ክሂልን ለማስተማር ስራፈጠራ ምን እንደሆነእና በስራ አስፈላጊነት
ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ሁኔታዎችን ያመቻቹ። በዚህም ግላዊ
አመለካከታቸውን በማንሳት በየተራ እንዲናገሩ ያድርጉ።ሲናገሩም
ምክንያታዊና በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ለክፍል ጓደኞቻቸው እንዲያቀርቡ
ያበረታቷቸው። የስራ ፈጠራ ለማህበረሰቡ በተለይም ለወጣቶች
የሚሰጠውንጥቅም እንዲገልጹ ካደረጉ በኋላ በሀገር ዕድገት ላይ ያለውን
አዎንታዊ አስተዋጽኦ በቡድን ተወያይተው ሃሳባቸውን እንዲያንጸባርቁ
ያድርጓቸው። በተለይ ወጣቱ ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት መሸጋገር
እንደሚገባውና ይህም ለራስ፣ ለቤተሰብ፣ ለአካባቢ ማህበረሰብ፣ ለክልልና
በአጠቃላይም ለሀገር እድገት የሚኖረውን ወሳኝ ሚና አጽንኦት ሰጥተው የመነሻ
ሀሳብ ያቅርቡላቸው።

በመማሪያመጽሐፋቸውላይየቀረቡትን ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በክፍል

126
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ውስጥ ንግግር ካደረጉና በተግባር ልምምዱን ካካሄዱ በኋላ ተጨማሪ ሀሳቦች


ካላቸው አንስተው አንዲወያዩ ሁኔታዎችን ያመቻቹላቸው።

ምዘና

• ተማሪዎች አቋማቸውን አሳማኝ በሆነ ማስረጃ አስደግፈው


ማቅረባቸውን መገምገም፣
• ውይይትለማድረግየሚያስችሏቸውንሃሳቦችያደራጁበትንመንገድማጤን

• አጠቃላይ ተሳትፏቸውንና የሀሳብ ብስለታቸውን በማጤን ነጥብ
መስጠት

ክፍል ሶስት ፡ ንባብ

ቅድመምንባብጥያቄዎች

መምህር ‘ስራ ወዳዱ የጥበብ ባለሙያ’ በሚል ርዕስ ስለሰዓሊ ለማ ጉያ ታታሪነት


የሚያወሳውን ምንባብ ከማስነበብዎ በፊት በተማሪ መጽሐፍ ላይ የቀረቡትን
የቅድመ ንባብ ጥያቄዎች በየግላቸው በማሰራት የተማሪዎችን ዳራዊ እውቀት
ይቀስቅሱ፤የስራ ፈጠራጠቀሜታ ምን እንደሆነ፣ታዋቂ ከሆኑ ሰዓሊያን መካከል
እነማንን እንደሚያውቁ፣ ስለአርቲስት ለማ ጉያ የሚያውቁት ካለምሀሳብእንዲሰጡ
ይጋብዟቸው።

በተጨማሪም የምንባቡን ርዕስ መሰረት በማድረግ ከምንባቡ የሚጠብቁትን


በማስታወሻ ደብታራቸው እዲያሰፍሩ ያደርጉ።

የማንበብሂደት

ምንባቡን በየግላቸው በለሆሳስ እንዲያነቡ ወይም በየተራ እየተነሱ እንዲያነቡና


ሌሎችሲያነቡ እየተከታተሉ ማስታወሻ እንዲይዙ ያድርጓቸው።

127
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የምንባብ ጊዜ

ተማሪዎቹ ንባባቸውን ገታ አድርገው ከላይ ስላነበቡት የተረዱትን


እንዲያስታውሱ ይጠይቋቸው፤ መልሳቸውን ከተቀበሉ በኋላም በቀረው ምንባብ
ውስጥ ምን ሊያነቡእንደሚችሉ እንዲገምቱ እድል ይስጡ፤ በመቀጠልም ቀሪውን
ምንባብ ከላይ በጀመሩት መልኩአንብበውእንዲጨርሱ ያበረታቷቸው።
አንብቦመረዳት

ምንባቡን አንብበው ሲያጠናቅቁ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን በትዕዛዛቸው


መሰረትያሰሯቸው።ምንባቡንመሰረትበማድረግየቀረቡትንጥያቄዎች(መልመጃ
ሁለት) ያነበቡትን በማስታወስና ምንባቡን ተመልሰው በማየት እንዲመልሷቸው
ይጠበቃል፤ ተገቢውን ምጋቤ ምላሽም ይስጧቸው።

በሁለተኛው ትዕዛዝ የቀረበውበምንባቡ ውስጥ ያሉ የትኩረት ማጠንጠኛ


ነጥቦችን ከሚመለከታቸው አንቀጾች ጋር እንዲያዛምዱ ማስቻል ነው። ስለሆነም
ተማሪዎች በቅድሚያ በግል ቀጥሎ ደግሞ በጥንድ ሆነው እየተነጋገሩ የማዛመዱን
ተግባር እንዲከውኑ መመሪያ ይስጧቸው። አፈጻጸሙንም እየተዘዋወሩ ይቃኙ።
ምዘና
• ተማሪዎች የንባብ ክሂላቸው መዳበሩንመመዘን።
• የተማሪዎቹን ተግባርናተሳትፎ መከታተል፣
• አንብበው መረዳታቸውን ምላሻቸውን በመቀበል መፈተሽ፣
9.5 ትምህርት አራት፡ ጽሕፈት

በዚህ ክፍል የተማሪዎች የጽሕፈት ክሂል እንዲዳብር ማስታወሻ እንዴት


መውሰድ እንዳለባቸው የሚያመለክት ጽሑፍ ቀርቧል። ጽሑፉን ከማንበባቸው
በፊት‹‹በቃል ያለ ይረሳል በጽሁፍ ያለ ይወረሳል።››ማለት ምን ማለት እንደሆነ
እንዲመልሱ ይጠይቋቸው።ከጠየቃችኋቸው በኋላ መልሶቻቸውን በመቀበል ቀጥታ
ከስሩ የቀረበውን ማስታወሻ እንዲያነቡት ይፍቀዱላቸው።ከተወያዩበት በኋላ

128
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

የተረዱትንእንዲያንጸባርቁያድረጉ፤ማስታወሻውንምያስረዷቸው። በመሆኑም
ማስታወሻ ስለሚፈልገው ርዕሰ ጉዳይ መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች በጽሁፍ
መዝግቦ የሚያዝበት መንገድ እንደሆነ ማወቃቸውን የሚመዝኑ
ጥያቄዎችያቅርቡላቸው።

በተማሩት የማስታወሻ አያያዝ መሰረት በአካባቢያቸው በሥራ ፈጠራ ላይ


ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን አነጋግረው ማስታወሻ እንዲይዙ ያድርጉ። እያዳመጡ
የይዘቱን ማስታወሻም በክፍል ውስጥ እንዲያቀርቡ ያድረጉ። የማስታወሻ አያያዝ
መመሪያን የተከተለ መሆኑን አረጋግጠውም እርማት ይስጧቸው።

አዳምጠው ከሚይዙት ማስታወሻ በተጨማሪ ወደቤተመጻሕፍት ሄደው


አጭርልቦለድ እንዲያነቡና የማስታወሻ አያያዝ ስልትን በመጠቀም ማስታወሻ
እንዲይዙ ያድርጉ።በሚይዙት ማስታወሻም የሚያካትቷቸውን ነጥቦች
በተመለከተ ፍንጭ ይስጧቸው።(ለምሳሌገጸባህሪያት፣ጭብጥ፣
መቼት…እንዲያወጡ ማድረግ ይችላሉ።)ከዚህም በተጨማሪ የማስታወሻቸውን
የገጽ ብዛት ያሳውቋቸው።(ለምሳሌከአንድገጽያልበለጠማስታወሻይያዙ…)።
የያዙትን ማስታወሻ በክፍል ውስጥ በቃል ያስቀርቧቸው።የጽሕፈት ክሂላቸውን
እንዲያዳብሩ ሌሎች ተያያዥተግባራትን እንዲያከናውኑ በማድረግ እርማት
እየሰጡ ያበረታቷቸው።

ምዘና

• የጽሁፍ ክለሂላቸውንመመዘን

• በተገቢው መንገድ ማስታወሻ መያዝ መቻላቸውንማረጋገጥ፣

• ያቀረቡትን ጽሁፍ እና ዘገባ ጥራት መመዘን፣

129
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍልአምስት፡ቃላት

ውድ መምህር በቃላት ትምህርት ክፍል ሞያዊ ቃላት መጠቀምንና የቃላት ፍቺን


ከአውድ መረዳት የሚያስችሉ መለማመጃ ጥያቄዎች ቀርበዋል።እንዲሁም ‹ስራ
ወዳዱ የጥበብ ባለሙያ› ከሚለው ምንባብ የተወሰዱና ተማሪዎች ፍቻቸውን
ተረድተው አረፍተነገሮች እንዲመሰርቱባቸው የሚጋብዝ መልመጃም ተሰጥቷል።
ሁሉንም ጥያቄዎች አስቀድመው በግላቸው እንዲሰሩ በማበረታታትና የሰሩትን
ከጓደኞቻቻው ጋር እንዲጋሩ በማድረግ ትምህርቱን ማስኬድ ይችላሉ።አስፈላጊ
ሆኖ ሲገኝም የተሳሳቱትን በማቃናት እርማት እየሰጡ ያበረታቷቸው።ጥሩ
ዓረፍተነገር የጻፉ ተማሪዎችንም በሰሌዳ ላይ በመጻፍ በማስደረግ ለጋራ ውይይት
ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይችላሉ።
ምዘና

• ሙያዊ ቃላትን ከሌሎች ቃላት መለየት መቻላቸውን ማረጋገጥ፣

• ቃላትን በዓረፍተነገር ውስጥ በትክክለኛ አውዳቸው መጠቀማቸውን


መመዘን፣

• የቃላትን ፍቺ ከአውድ አንጻር መለየታቸውን ማጤን

ክፍል ስድስት፡ ሰዋስው

በሰዋስው ስር ገቢርና ተገቢሮ ግስምን እንደሆኑ በቡድንተወያይተው በመለየት


ምሳሌ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፤ ይህንንም እንዲያሳኩ ማበረታታት ተገቢ ነው።
በማስከተልም የግስ ጠባይ በሚል የቀረበውን ማስታወሻ ወደ ደብተራቸው
እንዲገለብጡና ትኩረት ሰጥተው እንዲያነቡት ይደረጋል። እንዲሁም
ተሳታፊነታቸውንም እየተዘዋወሩ መመልከትና አስፈላጊ ሲሆንም በአግባቡ
ማንበባቸውን ቃላዊ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ፍተሻ ማድረግ እንደሚገባ መገንዘብ
መልካም ነው።
130
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ምዘና

• ገቢርና የተገብሮ ግሶችን ለይተው ማወቃቸውን መፈተሽ

• ገቢር ግሶችን ወደ ተገብሮ ግሶች መለወጥ መቻላቸውን ማየት

• የገቢርና የተገብሮ ግሶችን ተጠቅመው የየራሳቸውን ዓረፍተነገሮች


መመስረታቸውን ማጤን፤ ደብተሮቻቸውን ሰብስቦ ማረም
መርጃ መሳሪያ
 ገቢርና ተገብሮ ግሶችን ለመለየት የሚያስችል ቻርት
 መቅረጸ ድምጽ
 የተለያዩ የስዕል ስራዎች (ከተገኘ የሰዓሊ ለማ ጉያን)

በናሙናነት የተመረጡ ጥያቄዎች መልስ


አዳምጦ መረዳት

መልመጃ አንድ

1. እርካታ - ደስታምርምር - ጥናት/ፍተሻ

ደንበኞች - ገዢዎችአማራጮች - መተኪያዎች

ማመንጨት - ማፍለቅ ዘርፍ - መስክ/ሞያ

ተቋማት - ድርጅቶች መቃኘት - መመልከት

2. ኢንተርኔት፣ ደንበኞች፣ ነባር የንግድ ድርጅቶች፣ አከፋፋዮችና የመንግስት


የጥናትና ምርምር ተቋማት ወዘተ

3. (የተለያየ መልስ ይጠበቃል)

4. (የተለያየ መልስ)

131
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ክፍል ሁለት፡ ማንበብ

መልመጃ ሁለት

ሀ. 1. (መረዳታቸውን የሚያመላክት መልስ)

2. እናታቸው

3. በአውሮፕላን ቴክኒሽያንነት፣ በመምህርነት፣ በሰዓሊነት፣ ሀገር በማስተዋወቅ፣


አዲ የአሳሳል ጥበብ በመፍጠር፣ ትምህርት ቤት በመክፈትና ተከታዮችን
በማፍራት፣ መጽሐፍ በመጻፍ፣ አርዓያ በመሆን…

4. (የተለያዩ መልሶች)

5. ጸጉሩ ባልተነሳለት የፍየል ቆዳ ላይ በቀለም ስዕል መሳል መቻላቸው፤


አዲስ ያሳሳል ዘይቤ በመከተላቸው

ለ. አዛምድ- 1.ረ 2. ሀ 3. ቀ 4. ሐ 5.ሠ 6. መ 7. ቀ 8.ሰ 9.ለ

ክፍል አምስት፡ ቃላት

መልመጃ ሦስት

ለ.1. ጎዳና - መንገድ 2. ተገላገለች - ወለደች 3. የስራ መስክ - ሞያ

4. እንተልም - እናቅድ/እናልም 5. አስደምመዋል - አስደንቀዋል/አስገርመዋል

ክፍልስድስት፡ ሰዋስው

2. በሚከተሉት ዓረፍነገሮች ውስጥ የሚገኙ ግሶችን ገቢር/አድረጊ/ ወይም


ተገብሮ/ተደራጊ/ በማለትጻፉ።
ሀ.ገቢር / አድራጊ/ መ.ተገብሮ/ተደራጊ/

ለ.ተገብሮ/ተደራጊ/ ሠ. ገቢር /አድራጊ

132
አማርኛ የመምህር መምሪያ 10ኛ ክፍል

ሐ.ገቢር /አድራጊ/
3.የሚከተሉትንገቢርግሶችወደተገብሮተገብሮዎችንደግሞወደገቢርግስለውጣችሁዓ
ረፍተ ነገር ስሩባቸው።
ሀ.ሰራ - ተሰራ መ.ታደሰች - አደሰች
ለ.መረቀ - ተመረቀ ሠ.ተቀማ - ቀማ
ሐ.ተጠናቀቀ - አጠናቀቀ ረ.ተሸለመች - ሸለመች
አጋዥመጽሐፍት

ማንኩሳ አታሚናአሳታሚ።(2009)።የጳውሎስ ኞኞ ስብስብ ስራዎች።


አዲስአበባ፣መላማተሚያ ድርጅት።
ባዬይማም። (2002)።አጭርናቀላልየአማርኛሰዋስው።አዲስአበባ፣
አልፋአታሚዎች።
ከበደሚካኤል። (1999)።ታሪክናምሳሌ1ኛመጽሐፍ።አዲሰአበባ፣
ሜጋአሳታሚናአከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር።(1999)።
ታሪክናምሳሌ2ኛመጽሐፍ።አዲሰአበባ፣ሜጋአሳታሚናአከፋፋይ
ኃ/የተ/የግ/ማህበር።
ወረታው በዛብህ (ዶ/ር) ። (2008) ። ለራስ ማን እንደራስ የስኬታማነት የግል
መርህ መውጫ ቁጥር አንድ። አዲሰ አበባ፣ አልፋ አታሚዎች ኃ.የተ.
የግ.ማህበር።
ጌታሁን አማረ። (1989) ። ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀለላል አቀራረብ።
አዲሰ አበባ፣ አልፋ አሳታሚዎች።

133
ምዕራፍ አንድ ቋንቋና ማህበረሰብ (8ክ/)
የሚጠበቅውጤት
ተማሪዎችይህንንትምህርትካጠናቀቁበኋላ
 መረጃዎችንበማዳመጥይወያያሉ።
 ውይይትበማድረግየተገኘውንውጤትበቃልያንፀባርቃሉ።
 ሰፊርዕሰ-ጉዳይንየያዘጽሁፍበማንበብተደራሲያንንይለያሉ።
 በፅሁፋቸውውስጥምሳሌያዊአነጋገሮችንይጠቀማሉ።
 ድርሰትይጽፋሉ።
 ድርብቃላትበመመስረትይጠቀማሉ።

ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና


ተማሪዎች 1.1ማዳመጥ የማዳመጥክህሎትንለማስተማርየሚሆኑየተለያዩደረጃዎችንመጠቀ ተማሪዎችካዳመ
ከዚህትምህር 1.2ንግግር ም። ጡትፅሁፍ
ትበኋላ 1.3ምንባብ ቅድመማዳመጥ ውስጥያገኙትን
• ከተለያየ 1.4ቃላት • ተማሪዎችስለሚያዳምጡትፅሁፍይዘትከርዕሱበመነሳትእንዲ መረጃእንዲያካ
ቦታ 1.5ሰዋስው ገምቱማድረግ። ፍሉመጠየቅ።
የተነገሩ ምንያህሉተ

134
መልእክቶችንአ • ተማሪዎችበጣምራበመሆንፅሁፍውስጥያሉትንአዳዲስቃላትአ ማሪዎች
ዳምጠውውይይ ውዳዊፍቺእንዲሰጡማድረግ። የሰሙትን
ትያደርጋሉ። በማዳመጥጊዜ በትክክለኛቋንቋ

• ግልፅየሆነመመሪያመስጠት(ለምሳሌበማዳመጥጊዜምንመስ እናበልበሙሉነ

ራትእንዳለባቸው?ምንያህልጊዜማዳመጥእንዳለባቸው? ት

ወ.ዘ.ተ
በተሰጣቸው
• ተማሪዎችሙሉትኩረታቸውንፅሁፍላይእንዲያደረጉማመቻቸት
ርዕስ ዙሪያ
• ፅሁፍንድምፅንከፍአድርጎማንበብወይምበመቅረፀድምፅየተዘ
በመወያየት
ጋጁፅሁፎቸንመጠቀም።
በቃል

ሃሳባቸውን

135
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ያቀርባሉ። ፅሁፉን እንዲያዳመጡ እና በፅሁፉ መሰረት የተለያዩ መግለፃቸውንመመዘ
ፅሁፎችን ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ማድረግ። ለምሳሌ፦ አጭር ን።
አንብበው4አ መልስ ስጥ፣ባዶ ቦታ ሙላ ድህረማዳመጥ፡-ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪዎች
ድማጩን በቡድን ከተወያዩ በኋላ አርፍተነገሮችን እንደገና የፅሁፉንማጠቃለያ
ይገምታሉ። እንዲያስተካክሉ ማድረግ። በትክክልሂደቱን
ገላጭ ድርሰትእንዲፅፉ የሚረዱ መለማመጃዎችንመስጠት። ጠብቀው
ቃላትንለተለያ ለምሳሌ ርዕስ መስጠት ለክፍሉ ደረጃ የሚመጥን ተማሪዎች መፃፋቸውንመመዘን።
ዩተግባራትይ በቡድን እንዲወያዩበት ወቅቱን የጠበቀ ስሜት ቀስቃሽ ለቃላትትርጉም
ጠቀማሉ። ጉዳይ በመስጠት ለክፍሉ ሃሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ ለመስጠት ምንያህል
ሂደቶችን ማድረግ ለምሳሌ ኮሮና የመዝገበ ቃላት
ጠብቀውድርሰት ቅድመ ምንባብ፡- ተማሪዎቹ ከፅሁፉ ምን እደሚጠብቁ ትርጉምመጠቀማቸውን
ይፅፋሉ። ውይይትእንዲያደርጉማመቻቸት። መገምገም።
የቃላትንአ በአውዱመሰረትየቃላትንፍቺመስጠት። ለተማሪዎቹገንቢ
ውዳዊ ተማሪዎች በጥንድ በመሆን ፅሁፍ ውስጥ ያሉትን የሆነግብረ
ፍቺ አዳዲስ ቃላትአውዳዊ ፍቺ እንዲሰጡት ማድረግ። ምልስመስጠት።
በመጠቀም በማንበብ ጊዜ፡-ተማሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን
አርፍተ ነገር ማንበብ ላይ እንዲያደርጉ እና ከፅሁፉ የወጡ

136
ይመሰርሉ። ጥያቄዎችን መመለስ።
ጥምርቃላትንፈ ለምሳሌ ከአንቀፅ ውስጥ መዘርዝራዊ አርፍተነገሮችን
ጥረው እንዲለዩ፣አያያዥቃላትን፣አሳታፊቃላትን፣የሰርአተ ነጥብን
ይጠቀማሉ። መጠቀም…ወ.ዘ.ተ
ድህረማንበብ፡-ተማሪዎች በግላቸው የፅሁፉን ማጠቃለያ
እንዲፅፉ ከሁሉም በመሰብሰብና በመውሰድ ጠንካራ የሆነ
አንድ ማጠቃለያመስጠት።
• የመዝገበ ቃላት ትርጉም ለቃላት መስጠት የሚያስችሉ
መልመጃዎችን መስጠት
• ተማሪዎችልምምድእንዲያደርጉባቸውጥምርቃላትንመፍጠ
ርእናመጠቀምንማሳየት።

137
ምዕራፍ ሁለት ባህላዊ ጋብቻ (8ክ/ዜ)
የሚጠበቅውጤት

ተማሪዎችይህንትምህርትካጠናቀቁበኋላ

• የሌሎችንንግግርማዳመጥግብረመልስይሰጣሉ።
• ክርክርያደርጋሉ።
• የፅሁፍንሀሳብአገናዝበውያነባሉ።
• የተለያዩስልቶችንበመጠቀምሀሳባቸውንበፅሁፍይገልፃሉ።
• ትምህርታዊእናቴክኒካዊቃላትንበጽሁፍእናበንግግርውስጥይጠቀማሉ።
• አስረጅመጠይቃዊእናትዕዛዛዊዓ.ነገሮችንይጠቀማሉ።
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች 2.1ማዳመጥ ተማሪዎች ስለ ባህላዊ ጋብቻ ከቤተሰቦቻቸው የተማሪዎቹንእንቅስቃሴ
ከዚህ 2.2መናገር ጠይቀውእንዲመጡበማድረግ ያገኙትን ግብረ መልስ እና ተሳትፎ
ትምህርት 2.3ማንበብ ለክፍል ተማሪዎች እንዲያቀርቡማድረግ። በእያንዳንዱመልመጃ
በኋላ 2.4ፅህፈት ተማሪዎች የቡድን ክርክር የሚያደርጉበት መልመጃዎች ላይ መከታተል።
የሌሎችን 2.5ሰዋሰው መስጠት።ለምሳሌ፦የባህላዊጋብቻና ዘመናዊ ጋብቻን ተማሪዎች
ሀሳብበማዳመጥ ማነጻጸር በክርክርወቅትየሚያቀር
ጠለቅያለ የማንበብ ክህሎትን ለማስተማር የሚረዱ የተለያዩ ቧቸውን

138
ግብረ መልስ ስልቶችንና ደረጃዎችንመጠቀም። የማሳመኛ መንገዶች
በንግግር ቅድመንባብ መመዘን።
ይሰጣሉ። • ተማሪዎች ስለሚያነቡት ፅሁፍ ከቀድመ እውቀታቸው ተማሪዎች
ክፍል ውስጥ ተጠቅመው የሚሰጡትን ሃሳቦች ከተማሪዎች ማሰባሰብ። የፅሁፉንዋና ሃሳብ
በሚደረግ • ተማሪዎቹን በቡድን በማድረግ ስለባህላዊጋብቻ ዘገባ
ክርክርተሳትፎ የሚያውቁትን እንዲወያዩበት ለክፍልተማሪዎች
ሃሳባቸውን በቃልእንዲያቀርቡ
መጠየቅ።

በልበ ማድረግ። መጠይቃዊ፣አስረጅእና


ሙሉነት • በቡድን የተወያዩበትን ሀሳብ ለክፍሉ እንዲያንፃባርቁ ትዕዛዛዊ
ይገልፃሉ። ማድረግ። አርፍተነገሮችን
• ስለሚቀርብላቸው ፅሁፍ እንዲገምቱ/እንዲነጋሩ እድል
የአንድን መጠየቅ።
መስጠት።
ፅሁፍይዘት • በፅሁፍ ውስጥ ለተማሪዎች አዲስ የሆኑ ቃላት ካሉ
በማንበብ አውዳዊ ፍቺ በመስጠት በቡድን እንዲወያዩበትማድረግ።
ያገናዝባሉ። በንባብጊዜ
የተለያዩ • ሁሉምተማሪዎች በንባቡ ላይ እንዲሳተፉ/ፅሁፉን
ስልቶችን እንዲያነቡ ማድረግ።
በመጠቀም ፅሁፉን በሚያነቡ ጊዜ የሚሰሯቸውን መልመጃዎች

139
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች • እንዲጨርሱ እና በፀጥታ እንዲያነቡ ትዕዛዝ/ መመሪያ
የራሳቸውን ገንቢ
መስጠት ለምሳሌ በአጭሩ መልሱ፣ባዶ ቦታ ሙሉ፣የተለየውን
ሀሳብእና
ስም አውጡ…ወ.ዘ.ተ የሆነግብረ
አስተያየትበፅሁፍ
ይገልፃሉ። ድህረንባብ መልስ በርዕሱ
ተማሪዎች • ተማሪዎች ለጥያቄዎቹ በሰጡት ምላሽ ላይ በቡድን እንዲወያዩ ዙሪያ
ተዘውታሪ
ማድረግ። መሰጠት።
ውስብስብ ቃላትን
የተለመዱመንደርኛ • ተማሪዎችያላቸውን ሀሳብ በቃላቸው ለክፍልተማሪዎች
ቃላትየትምህርት እንዲያንፀባርቁ ማመቻቸት።
እና
• መግቢያ፣ሀተታ እና ማጠቃለያ ያለው ሙሉ ፅሁፍ
ቴክኒካዊቃላትን
ጨምሮበትክክል አዘጋጅተውእንዲያመጡማድረግ።
በሰፊው • ተማሪዎች በቡድን የተለያዩ አይነትጥያቄያዊ፤አስረጅና
አስረጅመጠይቃዊ፣
ትዕዛዛዊ ዐ.ነገሮችን መመስረት እንዲለማመዱ ማድረግ።
ትዕዛዛዊ እና
አጋናኝዓ.ነገሮችንይ
መሰርታሉ።
ጠቀማሉ።

140
ምዕራፍ ሶስት ሴቶች እና
እድገት(8ክ/ጊዜ)ከትምህርቱ

የሚጠበቅ ውጤት

ተማሪዎችይህትምህርትካጠናቀቁበኋላ

• ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሴቶች እድገትዙሪያ የቀረቡ ሀሳቦችን አዳምጠው ተናጋሪውን ሀሳብ ይገመግማሉ።
• ምንባቡን አንብበው ተፈላጊውን ሀሳብ ያወጣሉ።
• በሴቶች እድገት ዙሪያ ቃለመጠይቅ በማድረግ ያገኙትን ሀሳብ በቃልያንፀባርቃሉ።
• በአንድ አንቀፅ የተሰጣቸውን ፅሁፍ ማጠቃለያ ይፅፋሉ።
• ከውስብስብ አርፍተነገሮች ተራ (ነጠላ)ዓረፍተነገሮችን ያወጣሉ።

141
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች ማዳመጥ • አጀንዳቸውን በሴቶች እድገት ላይ ያደረጉ የተማሪዎችን
ከዚህ ንግግር የተለያዩመገናኛብዙሃን ቲቪ፣ሬዲዮ፣ዩቲዩብ ወ.ዘ.ተ) እንቅስቃሴና
ትምህርት ምንባብ ተማሪዎች እንዲያዳምጡ በማድረግ ተሳትፎ
በኋላ ፅህፈት የተናጋሪዎቹን አመለካከት በመመዘንለክፍል መከታተል።
ቃላት ተማሪዎች በቃል እንዲያንፀባርቁ ማድረግ። ተማሪዎች
የተናጋሪዎችን ሀሳብ ሰዋሰው • በእድገት ላይ ሴቶችን ማሳተፍ ያለው ጠቀሜታ በሚል ያቀረቡትን
በማዳመጥ ርዕስ ቃለ ምልልስ አድርገው እንዲመጡ በማድረግ ፣ ዘገባ መመዘን።
ይገመግማሉ። ያገኙትን ሀሳብ ለክፍል ተማሪዎች እንዲፀባረቁ ማድረግ። ተማሪዎች
• የማንበብ ክሂሎችን ለማስተማር የሚረዱ የተለያዩ በቃለመጠይቅ
ካነበቡ በኋላ ደረጃዎችን /ክፍሎችንመጠቀም። ያገኙትንሀሳብ/
ዋናውን ሀሳብ ቅድመንባብ መረጃ
ያወጣሉ። • ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት ፣ ከራሳቸው እውቀትና ያቀናጁበትን
ልምድ በመነሳት የሴቶች ተሳትፎ በሀገር እድገትላይ መንገድ
የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ እንዲወያዩበት ማድረግ።
°በተሰጣቸውርዕስ መመዘን
• በቡድን ውይይት የተገኘውን ሀሳብ ክፍል ውስጥ
ዙሪያቃለ መጠይቅ እንዲያንፀባርቁማድረግ።
በማድረግያገኙትን • ከመዝገበቃላትየቃላትንትርጉምእንዲሰጡማድረግ።

142
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ውጤት በንባብጊዜ ተማሪዎች በቃል
በቃል • ተማሪዎች በፀጥታ እንዲያነቡና የፅሁፉን ዋና ሀሳብ ያቀረቡትን
ያንፀባርሉ። እንዲያወጡ ማድረግየተለያዩ የመልመጃ ዘገባእና የፃፉትን
የአንድን ጥያቄዎችንእንዲመልሱማድረግ። ፅሁፍ
ፅሁፍማጠቃለያ ለምሳሌ አጭር መልስ ስጥ፣ ባዶ ቦታ መመዘን፡
በአንድአንቀፅ ሙሉ…ወ.ዘ.ተድህረንባብ ተማሪዎች
ይፅፋሉ። • ተማሪዎች ካነበቡት ፅሁፍ አንድ አንቀፅ ማጠቃለያ እንዲፅፉ ቀላልእና
ሁሉንም ማድረግ። ውስብስብ
የአርፍተ ነገር • የተለያዩ አርፍተ ነገር አይነቶችንና የመጀመሪያ ቋንቋ አረፍተ ነገሮችን
አይነቶች በመጻፍ ስምምነቶችን በመጠቀም የኢትዮጵያ የሴቶች ተሳትፎ በሀገር እንዲመሰርቱ
ይለማመዳሉ። እድገት ላይ በሚል ርዕስ ሙሉ ፅሁፍ እንዲያዘጋጁ ማድረግ። መጠየቅ።
• ተማሪዎች መዘርዝራዊ አቀራረብን በመጠቀም እንዲችሉ
ማድረግ እናተራ/ነጠላ/፣ ጥምርና ውስብስብ አርፍተ ነገሮች
መመስረት እንዲለማመዱማድረግ።
• በርዕሱ ዙሪያ ማስታወሻ መስጠት እና ትምህርቱን ማጠቃላል።

143
ምዕራፍ አራት፦ በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነት
(8ክ/ጊዜ)

ከትምህርቱ የሚጠበቅ ውጤት

ከዚህትምህርትመጠናቀቅበኋላ፡-

• የተለያዩ ተናጋሪዎችን ሀሳብ በማዳመጥ ትንተና ይሰጣሉ።


• በማንበብ የቃላት ትርጉምን ይለያሉ።
• ፈሊጣዊ አገላለጾችን በንግግራቸውእናበፅሁፋቸውውስጥይጠቀማሉ።
• የቃላትን ተመሳሳይእና ተቃራኒ ፍቺዎችንይሰጣሉ።
• አንቀፆችን ያብራራሉ።

144
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች • ክፍል ውስጥ ተማሪዎች በብዛት ሆነው ውይይት ተማሪዎችየሚያደ
ከዚህ ማዳመጥ እንዲያደርጉበማመቻቸትየተለያዩ ርጉትንእንቅስቃ
ትምህርት ንግግር ተናጋሪዎችንረጅም ንግግር እንዲያዳምጡ ሴናተሳትፎ
በኋላ ምንባብ በማድርግ እንዲተነትኑ፣እንዲያወዳድሩ፣ነጥቦችን ምልከታ
°ረዘምያሉ መፃፍ ማውጣት፣ለተለያዩ ነጥቦችምላሽ እንዲሰጡ ማድረግ።
ንግግሮችን ቃላት ማድረግ። የተማሪዎችንፅ
በማዳመጥ፣ ሰዋሰው • የተለያዩ የንባብ ክህሎትን የሚያሰድጉ ደረጃዎችን ሁፍ ትንተና
ነጥቦችን መጠቀም። መገምገም።
በማውጣት የአንድን ፅሁፍ
ቅድመምንባብ
ምላሽይሰጣሉ ዋና ሃሳቡን
• ተማሪዎች በቡድን በማደራጀት ከልምዳቸው
የተዘጋጀውን እንዲያዋህዱት
በመነሳት መቻቻል የሚያመጣውን ውጤት
ወይምሌላ መጠየቅ።
እንዲወያዩበት ማድረግ።
ለንባብ የሚሆን የተማሪዎችንበ
• የተወያዩበትን ለክፍል ተማሪዎች እንዲያንፀባርቁ
ጽሁፍን ፅሁፍና
ማድረግ።
በለሆሳስ
• ተማሪዎች ለመረዳት የሚያስቸግራቸውን ቃላት
በማንበብ
በማውጣትና
የማንበብ

145
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና

ስልቶች ተመሳሳይናተቃራኒትርጉማቸውንመስጠት። በንግግርወቅት


ተገንዝበው በማንበብወቅት ያላቸውን

ብቃታቸውን • ተማሪዎች በለሆሳስ እንዲያነቡ ከፅሁፍ ውስጥ የቃላት

ያሻሽላሉ፡ ዋናዋና ሀሳቦችን እንዲያወጡማድረግ። አጠቃቀም

ፈሊጣዊ • አጭር መልስ እንዲሰጡባቸው የተዘጋጁ መገምገም።

ንግግሮችን መልመጃዎችን እያነበቡእንዲመልሱማድረግ። ተማሪዎች

በፅሁፋቸው ድህረምንባብ የንግግር

ውስጥ በአግባቡ • ተማሪዎች በቀጥታ የሚተላልፉ የበይነመረብ መረጃዋችን ክፍሎችን፣

ይጠቀማሉ። እና የመገናኛብዙሃኖችን በማዳመጥ በልዩነት ውስጥ ያለ ጥቅማቸውንናአ

በተሰጣቸውርዕስላ አንድነት ስለሚሰጠው ጠቀሜታ ለክፍል ተማሪዎች በቃል ይነታቸውንእን

ይየተሟላፅሁፍ/መ ዲናገሩ
እንዲያቀርቡ ማድረግ።
ጣጥፍ/ መጠየቅ።
• ከቀረቡላቸው ርዕሶች መርጠው አጭር
ድርሰትይፅፋሉ ፅሁፍ/መጣጥፍ ተማሪዎች አዘጋጅተው እንዲመጡ
የቃላትን
ማድረግ።
ተመሳሳይ
• ተማሪዎች የቃላትን ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ እንዲሰጡ
/ተቃራኒ
ማድረግ፡
ፍችይሰጣሉ

146
ሁሉንም የንግግር • ተማሪዎችበቡድንበመሆንየንግግርክፍሎችንአይነትናጥቅ
ክፍሎችን ምምንእንደሆነእንዲወያዩማድረግ።
በመለየት
በአግባቡ
እናበትክክል
ይጠቀማሉ

147
ምዕራፍ አምስት የቋንቋ ለዛ (8ክ/ጊዜ)

ከትምህርቱ የሚጠበቅ ውጤት

ተማሪዎችይህንትምህርትካጠናቀቁበኋላ

• ተረት አዳምጠው የአዳምጦ መረዳት ጥያቄዎችን ይሰራሉ


• ስለምሰሌያዊ አነጋገር፣ ተረት እና አፈ ታሪክ የሚያውቁትን ይናገራሉ
• የቋንቋ ለዛን ፅንሰ ሀሳብይገልጻሉ።
• የቋንቋ ለዛን ዘውጎችይዘረዝራሉ።

• ምሳሌያዊንግገሮችን፣እንቆቅልሾችን፣አፈታሪኮችንይለያሉ።
• የተለያዩአይነትጭብጦችንይተነትናሉ።
• ዘይቤዎችን ተጠቅመው ግጥም ይጽፋሉ።
• ለቃላትተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ ይሰጣሉ።
• ለዛ ያለው ቋንቋ እየተጠቀሙ ሀሳባቸውን ይገልጻሉ።
• የቅኔ መፍቻ ብልሃቶችን ተረድተው ጥቅም ላይ ያውላሉ።
• ስሞችና ግሶችን ለይተው በአረፍተነገር ምስረታ ውስጥ ይጠቀማሉ።

148
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች ማዳመጥ • ተረት አዳምጣው ጥያቄዎችን እንዲመልሱ ተማሪዎች
ከዚህ መናገር ይደረጋል የሚያደርጉትንእን
ትምህርት ማንበብ • ተረት፣ አፈታሪከ፣ ምሳሌያዊ ንግግሮችንና ቅስቃሴናተሳትፎ
በኋላ መጻፍ እንቆቅልሾችን በቡድን በመሆን እንዲያወያዩበት መከታተል።
የቋንቋ ለዛ ፅነሰ ቃላት በማድረግና የተወያዩበትን ሃሳብ ለክፍልተማሪዎች ተማሪዎች
ሃሳብንይገልፃሉ ሰዋስው በቃል እንዲያቀርቡ ማድረግ። የቋንቋለዛን ፅንሰ
• የቋንቋ ለዛ ማስገኛ ስልቶችን የተመለከተ ሃሳብ
የቋንቋለዛን ምንባብ እንዲያነቡና መልመጃዎችን እንዲሰሩ እንዲያብራሩመጠ
ዘውጎች በመለየት ሁኔታዎችን ማመቻቸት የቅ።
ያብራራሉ። • የተለያዩ የቋንቋ ለዛ ማስገኛ ስልቶችን • ተማሪዎች
ለቃላት በጽሑፋቸው ውስጥ ማስጠቀም ። በምሳሌያዊ
ተመሳሳይና • የቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ የተመለከቱ አነጋገር
ተቃራኒ ፍቺ መልመጃዎችን ማሰራት፡ ፣ በእንቆቅልሽ
ይሰጣሉ • ያገኙትንሀሳብለክፍልተማሪዎችያንፃባርቁናበም እናበአፈታሪክመካ
ዘይቤዎችን ሳሌያዊአነጋገር፣ ከልያለውን
ለይተው በእንቆቅልሽእናበአፈታሪክመካከልስላለውልዩነት ልዩነትበትክክል
ይጠቀማሉ ውይይትእንዲያደርጉማመቻቸት። መለየትና

149
ምሳሌያዊ • ተማሪዎች የተለያዩ የቋንቋ ለዛ ጭብጦችን አለመለየታቸውን
አነጋገሮችን፤ እንዲተነትኑ ማድረግ። መመዘን።
እንቆቅልሾችንና • ስሞችንና ግሶችን ለይተው እንዲጠቀሙት ማድረግ
ቅኔዎችን ለተማሪዎች
ለይተው በርእሱ ዚሪያ
ይጠቀማሉ ጠቃሚና ገንቢ
ስምና ግሶችን የሆኑ ግብረ መልስ
ይለያሉ መስጠት
የምላስ ማፍታቻ
አይነቶች
በየአይነታቸው
ለይተው
ያስቀመጣሉ
የቃላዊ ስነ-
ጽሁፍይዘትን
ይተነትናሉ።

150
ምዕራፍ ስድስት፦የታላላቆች ሚና (8ክ/ጊዜ)

የሚጠበቅውጤት

ከዚህ ትምህርት መጠናቀቅ በኋላ ተማሪዎች

• በማድመጥ የፅሁፉን ዋናሀሳብ ይተነትናሉ።


• በክርክር በመሳተፍ ምክንያታዊ ዳኝነትይሰጣሉ።
• በማንበብ እንደገና ጨምቀውይፅፋሉ።
• የስራ ማመልከቻ ደብዳቤ ይጽፋሉ።
• አብሮ ሂያጅ ቃላትን ማጣመር ይችላሉ።
• ተሸጋሪ እና ኢ-ተሻጋሪግሶችን በመለየትይጠቀማሉ።

151
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች ማዳመጥ • የማዳመጥን ክህሎት መጨመር የሚያስችሉ • ተማሪዎች
ከዚህ መናገር ሶስቱን ደረጃዎች መጠቀም። ከሰሙትፅሁፍ ውስጥ
ትምህርት ማንበብ ቅድመማዳመጥ ዋናውን ሀሳብ እንዴት
በኋላ፦ መፃፍ • ተማሪዎች የቀደመ ዕውቀትና ልምዳቸውን ነቅሰው
ፅሁፍን አዳምጠው ቃላት በመጠቀም ስለ ታላላቆች ሚና ውይይት ሲያወጡእንደሚችሉመ
ዋናውን ሀሳብ ሰዋስው እንዲያደርጉ ማመቻቸት። መዘን።
በመቀመር • ተማሪዎች ከሚያዳምጡት ፅሁፍ ውስጥ • ተማሪዎች
ምክንያታዊ ለመረዳት አስቸጋሪ የሚሆንባቸውን ቃላት ተገቢውን ቃላት
የሆነምላሽ ማውጣትና አውዳዊ ፍቺ መስጠት፡፤በማዳመጥጊዜ በመጠቀም፣የሌሎችን
ይሰጣሉ። ፅሁፉን አዳምጠው የሚመልሷቸው መልመጃዎችን ሀሳብ በማክበርእና
• ተማሪዎን መስጠት ለምሳሌ ባዶ ቦታ ሙሉ፣አጭር መልስ በልበ
በሀገር/ ስጡ…ወ.ዘ.ተ ሙሉነትሀሳባቸውንመ
በአለም ግለፃቸውን
መገምገም።
• ከመግቢያ
እስከ
መደምደሚያ

152
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
አቀፍ ደረጃ ድህረማዳመጥ እንዴት ሂደቱን
ውስብስብበሆኑ • ተማሪዎች በማዳመጥ ጊዜ የመለሷቸው እንደ ጠበቁ እና
ጉዳዮች ላይ በቡድን ውይይት እንዲያደርጉ ማመቻቸት። እንዳገናኙት ፣ የቋንቋ
በክርክር በማካሄድ • ተማሪዎች የተለያዩ መልመጃዎችን እንዲለማመዱ አጠቃቀማቸውን ፣
ተገንዝበው ማድረግ ለምሳሌ ዋናሀሳብ ነቅሶ ማውጣት እና በራሳቸው መልሰው
አስተያት ለፅሁፍ ሀሳብ ምክንያታዊ ሲፅፉ ሰዋሰውን
ይሰጣሉ። የሆነ ምላሽ ማመንጨት/መስጠት በትክክለኛ መንገድ

• ተማሪዎች በሁለት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ክርክር መጠቀማቸውን


• በደረጃቸውየሚ እንዲያደርጉ ማመቻቸት መገምገም።
መጥኑ ለምሳሌ ዕርስበዕርስ የመከባበር ጉዳይበ ሚልርዕስ • ተማሪዎች
ፅሁፎችንአንብበ • ተማሪዎች የተሰጣቸውን ፅሁፍ በፀጥታ የፃፉትን ደብዳቤ
ውበመፃፍይተገብ እንዲያነቡና በራሳቸው ቃላት እንደገና እንዲፅፉት በትክክል
ራሉ። ማድረግ። መልዕክቱን
• ደብዳቤይፅፈሉ። • ለተማሪዎች የታተመ የደብዳቤ ፅሁፍ ማስተላለፉን
• የቃላትን እንዲመለከቱ በማድረግ ይዘቱን እንዲለዩ ማድረግ። የሰዋሰው አጠቃቀም
ትርጉሞችንይሰጣ • ተማሪዎች በቡድን በመሆን የአንድን ደብዳቤ እና በትክክል

ሉ። ዋናዋና ነገሮች ላይ እንዲወያዩ እና ሀሳባቸውን የተደራጀ አፃፃፍ

153
• ተሻጋሪእናኢተሻ እንዲገልፁ ማድረግ። መጠቀማቸውንመ
ጋሪግሶችንበንግግ • ተማሪዎችያነሱትንሀሳብመውሰድናማጠቃለያመስጠት። ገምገም።
ር • ተማሪዎችየስራማመልከቻደብዳቤእንዲፅፉማድረግ። • ተማሪዎች
እናበፅሁፍውስ • አብሮሂያጅ ቃልትን በማጣመር የቃላት ችሎታቸውን በትክክል
ጥይጠቀማሉ። እንዲያሳድጉ ማድረግ የምሳሌያዊ ንግግር

• ቃላትንበመገጣጠም (ምስረታ ምዕላዶችን አይነቶችን

በመጠቀም) ለቃላት ተጨማሪ መለየታቸውን

ትርጉምመስጠትእንዲለማመዱበቡድንማደራጀት። ወይም
አለመለየታቸውንመ

• ተሸጋሪ የሆኑና ተሸጋሪ ያልሆኑ ግሶችን መዘን።

እንዲለማመዱ በቡድን ማደራጀት እና በፅሁፍ • በርዕሱ ዙሪያ

ውስጥ እንዲጠቀሙበትማለማመድ። በጣም ጠቃሚና


ገንቢ
አስተያየቶችን
ለተማሪዎች
መስጠት።

154
ምዕራፍ ሰባት ልቦለድ (8 ክ/ጊዜ)

የሚጠበቅ ውጤት

ተማሪዎች ከዚህ ትምህርት በኋላ መሰረታዊ የቋንቋ ክሂሎች ችሎታን


ለማሻሻል በሚያስችል መልኩ፡-

• የልቦለድዋናሀሳብንዘርዘርአድርገውያብራራሉ።
• የልቦለድክፍሎችንያብራራሉ።
• የልቦለድባህሪያትንይለያሉ።
• ከልብወለድ ጽሑፍ ጋር የተገናኙ የሙያ ቃላትን ይለያሉ።
• በልቦለድውስጥየሚገኝአንድየተወሰነክፍልንለይተውእንደገናይፅፋሉ።

155
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች ከዚህ ማዳመጥ • ከተለያዩ ምንጮች ስለ ልቦለድ ፅንሰ ሀሳብ • የተማሪዎቹን
ትምህርት በኋላ፦ መናገር ተማሪዎች እንዲያነቡማድረግ። • እያንዳንዱን
• የልቦለዱን .ማንበብ ለምሳሌ የታተሙፅሁፎችን መፀሀፍትን…ወ.ዘ.ተ • እንቅስቃሴእናተ
ፍሬሀሳብ መጻፍ • ስለልቦለድ ፅንሰሀሳብ ያነበቡትን ተማሪዎች ሳትፎ
ይገልፃሉ። ቃላት በቡድን ሆነው እንዲወያዩበት በማድረግ ለክፍል • መከታተል።
• አጭር ሰዋስው ተማሪዎች ሀሳባቸውንእንዲያንፃባርቁማድረግ። • ተማሪዎችን
ልቦለድን • ለተማሪዎች የታተመ ልቦለድ በማሳየት ስለመፅሀፉ • የልቦለድንፅንሰሀ
ለመፃፍ የሚያውቁትን ሀሳብ መጠየቅ። ሳብ መጠየቅ።
የሚያስችሉ • የተመለከቱትን ልቦለድ በመኖሪያቤታቸው • በልብወለድ
ክፍሎችን እንዲያነቡት ማድረግ። ውስጥ የሚካተቱ
በመለየት • ተማሪዎች ካነሱሰት ሀሳቦች በመውሰድና ክፍሎችን
ይጠቀማሉ። ያነበቡትን መፀሀፍ መሰረት በማድረግ የልቦለድን • ምን እንደሆኑ
• የልቦለድንዋናገፀባህ ዋናዋና ክፍሎች ማሳየት። እንዲዘረዝሩ
ርይለይተውያወጣሉ። • ከታተመ ልቦለድ ውስጥ ሁሉንም እናእንዲያብራሩ
• የተለያዩ መካተትያለባቸውን ሁሉንም የልቦለድ አላባዊያንን መጠየቅ
የልብወለድአወቃቀሮ በራሳቸው አውጥተው እንዲያሳዩ ማድረግ። በርዕሱ • የልቦለድን
ችላይመወያየትእናይ ዙሪያ ማጠቃለያ እና ማስታወሻ ለተማሪዎቹ ባህሪያትበትክክል
ህየልቦለድአወቃቀርም መስጠት። መለየትናአለመለ
ን ያህል ትልሙ • ቃላትን በማጥበቅና በማላላት ፍች መስጠትን የታቸውንመገምገ
ላይተፅዕኖ እንዲለማመዱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ም።
እንደሚያደርስሀሳባቸ • ስህተት ያለባቸውን አረፍተ ነገሮች አስተካክለው
ውንይገልፃሉ። ይጽፋሉ

156
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች
ከልቦለድ ውስጥ • ተማሪዎች ካነበቡት ፅሁፍ በመነሳት የልቦለድ
አንድን ባህሪያትን ምን እንደሆኑ በቡድን ማወያየት እና
ሁኔታ/ድርጊት ለክፍል ተማሪዎች እንዲያንፃባርቁ ማድረግ።
ወይም ክፍል • ተማሪዎች ልቦለድ ማንበብ እንዲለማመዱ ማድረግ
በመምረጥ ለትወና እና ካነበቡት ውስጥ አንድ ክፍልን በመውሰድ
እንዲሆን በማድረግ ለትወና እንዲመች አድርገውእንዲፅፉትማድረግ።
እንደገናይፅፋሉ።

157
ምዕራፍ ስምንት፡-ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን (8ክ/ጊዜ)

የሚጠበቅውጤት

ተማሪዎችትምህርትካጠናቀቁበኋላ

• በቃል የተላለፈን መልዕክትን በጥሞና በማዳመጥ ማጠቃለያ ሀሳብ ይሰጣሉ።


• የተሰጠው ንንግግር አዳምጠው ምክረሀሳብ(አስተያየት)ይሰጣሉ።
• የፅሁፉን ዋና ጥቅም በማንበብ ይለያሉ
• ምክንያታዊ ቅደምተከተልን በጠበቀመልኩ አከራካሪ ድረሰትይፅፋሉ።

• ለቃላት ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ ይሰጣሉ።


• ሁሉንም ጊዜገላጭ ግሶችን በትክክል ይጠቀማሉ።

158
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
ተማሪዎች ከዚህ ማዳመጥ • ተማሪዎች ከማህበራዊ መገናኛ የተሰጠውን አንድ • ለተማሪዎች
ትምህርትበኋላ መናገር ንግግር እንዲያመጡና ያቀረቡትን
• በቃል የተላለፈን ማንበብ መደምደሚያ/ማጠቃለያእንዲሰሩለትበማድረግ በቃል የቃልዘገባ
መልዕክት በጥሞና መፃፍ እንያቀርቡ ማድረግ። ትክክለኛ
በማዳመጥ ቃላት • ተማሪዎች ማህበራዊ መገናኛ ብዙሀንን እንዲያዳምጡ ቅደምተከተሉን
ማጠቃለያ ሀሳብ ሰዋሰው በማድረግና በቡድን እንዲወያዩና አስተያየታቸውን የጠበቀና
ይሰጣሉ። እንዲሰጡማድረግ። ትርጉም
• በተለያዩ • ተማሪዎች በሁለት የተለያዩነርዕሶች ላይ ክርክር የሚሰጥመሆኑን
የመገናኛ እንዲያደርጉ ማመቻቸት መገምገም።
ብዙሃን ለምሳሌ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ጥቅምና ጉዳት • ተማሪዎች ምን
ምንጮች በሚል ርዕስ ያህል ሀሳባቸውን
• የማንበብ ክህሎትን ለማስተማር የሚረዱ የተለያዩ በትክክለኛ ቃላትን
ደረጃዎችንመጠቀም። በመጠቀም
ቅድመምንባብ በራስመተማመን

• የቀደመ ልምዳቸውን /እውቀታቸውን በመጠቀም


ስለማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በቡድን ሆነው
እንዲወያዩማድረግ።

159
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
እየጨመሩ የመጡ • የተወያዩበትንሀሳብለክፍልተማሪዎችእንዲያንፃባርቁማ እንዳቀረቡ
አወዛጋቢ ንግግሮች ድረግ። መመዘን።
ላይ ጠቃሚ የሆኑ • ተማሪዎችለመረዳትያስቸግራቸዋልብሎመምህሩያሰባ • የተማሪዎች
ሂሶች ይሰጣሉ። ቸውንአዳዲስ ቃላት ከፅሁፍ በማውጣት አውዱን የዳኝነትውሳኔ
• ለክፍሉ የጠበቀ ትርጉምእንዲሰጡማድረግ። ከመጸሀፉአንጸርም
የሚመጥኑ የተለያዩ በንባብጊዜ ን እንደሚመስል
ፅሁፎች ላይ • ተማሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን ፅሁፍ ላይ መመዘን።
የሚገኙትን እንዲያደርጉ እና በለሆሳስና ፍጥነት በጠበቀ መልኩ • ተማሪዎች
የተለያዩ የማንበብ በማንበብ የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲመልሱ የጻፉትፅሁፍ
ስልቶችን ማድረግ። ምን ያህል
በመተግበር እና ለምሳሌ ባዶቦታሙላ፣ዋናሀሳቦችን ዘርዝር፣አጭር መልስ በተደራጀ መልኩ
በጣም ለተወሳሰቡና ስጥ…ወ.ዘ፣ተ እንደተፃፉ
ረጅም ለሆኑ ድህረንባብ መመዘን።
ንግግሮች ዋናውን • ተማሪዎች በጥንድ በመሆን በፅሁፉን በጥቅም • ከአውዱ
ሀሳብ ነጥሎ አላማ ላይ እንዲወያዩ ማድረግ በመነሳትእንዴት
የማውጣት ስልት (ፅሁፉንለማንእንደተፃፈ) ተማሪዎች
ይተግብራሉ • ተማሪዎች የፅሁፉን ዋና መልዕክት ከእውነተኛ ተመሳሳይ

160
ምክንያታዊ ቅደም ህይወታቸውጋርእንዲያዛምዱትማድረግ። እናተቃራኒፍቺ
ተከተሉን በጠበቀ • ተማሪዎችን በጥንድ በጥንድ በማድረግ የፅሁፉን እንደተጠቀሙመ
መልኩ ዋና ይዘት እንዲመዝኑነ እና ሃሳባቸውን ገምገም።
ሙሉ በሙሉ እንዲያንፀባርቁ ማድረግ። • ተማሪዎች
ወይም አከራካሪ • ተማሪዎች በሚሰጣቸው ርዕሰ ላይ ምክንያታዊ ቅደም የግሶችን የጊዜ
አወያይ ወይም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ የተሟላ አከራከሪ ወይም ሁኔታ እንዴት
ገላጭ ፅሁፍ ገላጭድርሰትእንዲፅፉማድረግ። በንግግራቸውና
ይፅፋሉ፡፡ ለምሳሌ ከማህበራዊመገናኛንጋርየተገናኙርዕሶች በፅሁፋቸው
የተለያዩ አውዳዊ • አውዱን መሰረት በማድረግ ለቃላት ተመሳሳይና በትክክል
ተመሳሳይና ተቃራኒ ፍቺ መስጠት እንደተጠሙ
ተቃራኒ • ተማሪዎች የጊዜ ግሶችን እንዴት በንግግር እና መገምገም።
ትርጊሞችን በፅህፈት ውስጥ
ወስደው የተሻለውን እንደሚጠቀሙበቡድንበማድረግእንዲለማመዱና
በመምረጥ እንዲተገብሩማድረግ።
ይጠቀማሉ፡፡
በንግግርና በፅሁፍ
ውስጥ ሁሉንም
የጊዜ ግሶች
በትክክል በመጠቀም
በፈለጉት ውጤት
161
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና
መጠቀም
ይጀምራሉ። •
ለምሳሌየአሁን
ጊዜ ግስንለድራማ
ጽሁፍመጠቀም።

162
ምዕራፍ ዘጠኝ፡-ስራ ፈጠራ (8ክ/ጊዜ)
የሚጠበቅውጤት

ተማሪዎችይህንንትምህርትካጠናቀቁበኋላ

• አዳምጠው በማስረጃ መስማማታቸውንና አለማስማማታቸውንያሳያሉ።


• ተማሪዎች ሀሳባቸውን በምክንያት በማስደገፍ በቃል ይገልፃሉ።
• ፅሁፍ በማንበብ ለማን እንደተፃፈይለያሉ።
• በድምፀመቅረፅከሰሙትውስጥማስታወሻይይዛሉ።

• የአዳዲስቃላቶችንትርጉምከፅሁፍአውድበመነሳትያወጣሉ።
• በአርፍተነገርውስጥተሸጋሪእናኢተሸጋሪግሶችንይጠቀማሉ።

163
ብቃት ይዘት
ተማሪዎች ከዚህ ማዳመጥ • ተማሪዎች አንድን ጽሁፍ በማድመጥ በቀረበው • የተማሪዎችን
ትምህርት በኋላ፦ መናገር ሃሳብ መስማማታቸውንና አለመስማማታቸውን ተግባርና
• ተማሪዎች ማንበብ በማስረጃ በማስደገፍ እንዲያቀርቡ ማድረግ። ተሳትፎ
የተሰጣቸውን ጽሁፍ መፃፍ • የስራ ፈጠራ ጥቅሞች/አስፈላጊነት ዙሪያ ተማሪዋች መከታተል
በሚያዳምጡበት ቃላት ውይይት እንዲያደርጉና እይታቸውን ተቀባይነት ባለው • ምንያህል ተማሪዎች
ሰዓት የሚያስማሙና ሰዋሰው ምክንያት በማስደገፍ እንዲያቀርቡ ማድረግ። አቋማቸውን አሳማኝ
የማያስማሙ ነጥቦችን የማንበብ ክህሎትን የሚያጎለብቱ በሆነ ማስረጃ
ፈልገው በማውጣት የማስተማርትግበራዎችንመጠቀም። አስደግፈው
በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ቅድመ-ንባብ ማቅረባቸውን
መረዳት ያገኛሉ። • ተማሪዎችየቀደመእውቀታቸውንናልምዳቸውንበመጠ መገምገም
• ተማሪዎች ቀምየስራ ፈጠራ ጥቅሞች/አስፈላጊነት ዙሪያ • ተማሪዎች
በተሰጣቸው ጽሁፍ በቡድን ውይይት እንዲያደርጉማ መቻቸት። ውይይት ለማድረግ
ላይ ያላቸውን • ተማሪዎችን በጥንድመበማወያየት የሚያስችላቸውን
እይታ(በጽሁፍም ለአዳዲስቃላትየመዝገበቃላትፍቺእንዲሰጡማድረግ ሃሳባቸውን
ጭምር)መግለጽእናተ ያደራጁበትን
ቀባይነት መንገድ
ያለው ምክንያት
ያቀርባሉ።

164
ብቃት ይዘት የመማርስልቶችናየመርጃመሳሪያዎች ምዘና

• የተዘጋጀውን በንባብጊዜ መመዘን


ወይም ሌላ ለንባብ • ተማሪዎች በለሆሳስ በማንበብ የምንባቡን • ተማሪዎች
የሚሆን ጽሁፍ ጠቅላላ ሃሳብ እንዲይዙ ማድረግ ቃለምልልስ
በለሆሳስ በማንበብ • ተማሪዎች ጽሁፉ ለማን እንደተጻፈ እንዲለዩ ለማዘጋጀት ሀሳቦችን
አንብቦ የመረዳት እና ማድረግ(ተደራሲያን)። ያቀናበሩበትን
በለሆሳስ የማንበብ • ተማሪዎች የተሰጣቸው ስልትመገምገም።
ስልቶች ማለትም ጽሁፍምንለመግለጽ/ለማለትእንደተፈለገእንዲያሳዩማድረ • ተማሪዎች
በአሰሳ ማንበብን እና ግ ያቀረቡትንጽሁፍ
በጥልቅ የማንበብ • ተማሪዎች በጣም ውስብስብ የሆኑ እና ያልተለመዱ እናዘገባመመዘን
ስልትንያዳብራሉ። ቃላትንእንዲሁምትምህርታዊቃላትንየጽሁፉንአውድመሰ • ተማሪዎች
• ሰፋ ባለ መልኩ ረትበማድረግትርጉምመስጠትእንዲለማመዱማድረግ። ለቃላትአውዳዊ
የተለያዩአይነት • ተማሪዎችንበቡድንበርቱዕእናበኢርቱዕግሶችላይእን ፍቺእንዲሰጡ
የማስታወሻ ዲወያዩበማድረግበዓ.ነገርውስጥእንዲጠቀሙማድረግ። መጠየቅ
አያያዝስልቶችን • ተማሪዎች
መጠቀምማለትም አንጻራዊሀረጎችን ፤
እንደደወረደመጻፍ፤ አወዳዳሪእናአነጻጻሪ

165
ቅድመማስታወሻ ሀረጎችንየሚገልጹ
ዋናሀሳብንእናየተብራ የተለያምሳሌዎች
ራሀሳብንበመቅዳት እንዲሰጡማድረግ
አስተሳሰብንያነባሉ።
• የበለጠ ውስብስብ
እና ያልተለመዱ
ቃላትንበአውዳቸው
ቀይረው
ይጠቀማሉ።
• ርቱዕ እና
ኢርቱዕ ቃላትን
በትክክል እና
በአግባቡ በመለየት

ይጠቀማሉ ።ለምሳሌ፤
ሂደታዊ
ድርጊትንይገልፃሉ።

166

You might also like