You are on page 1of 105

የአማርኛ ሥነድምፀ ልሳንና

ሥነምዕላድ
Amharic Phonology and Morphology

1
የንግግር ድምፅ
ቁዋንቁዋ በዋናነት ሁለት የተለያዩ አገልግሎቶች አሉት
- ስነ ልሳናዊ => ሀሳብን ማስተላለፍ
- ማህበራዊ => ማንነትን መግለፅ
አንድ ሰው ሲናገር አንድም ሀሳቡን ያስተላልፋል አንድም ማንነቱን ይገልፃል፡፡
የማንኛውም ቁዋንቁዋ መሰረቱ ድምፅ ነው፡፡
የንግግር ድምፅ በአንደበት አካላት የሚፈጠር ነው፡፡
ድምፅ ለመፍጠር - የአንደበት አካላት
- አየር (ወደሳንባ የሚገባ ወይም ከሳንባ የሚወጣ)
- እንቅስቃሴ አስፈላጊ ናቸው፡፡
ከሳንባ የሚወጣው ወይም ወደሳንባ የሚገባው አየር በተለያዩ የአንደበት አካላት የተለያዩ
ቦታዎች ላይ እክል ይገጥመዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ የተፈጠሩትን ተናጠላዊ ድምፆች በማቀናጀት ትርጉም ያለው ነገር መፍጠርና
ሀሳብን በቁዋንቁዋ መግለፅ ይቻላል፡፡
በቁዋንቁዋ ውስጥ ላሉ የተለያዩ ድምፆች መፈጠር ምክንያቱ በአየሩ ላይ በተለያዩ የአንደበት
አካላት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚደርሰው እገዳ ነው፡፡

2

ድምፆቹ የሚፈጠሩበት ቦታና የአየሩ አወጣጥ ሁኔታ የተለያዩ ድምፆች እንዲፈጠሩ
ምክንያት ይሆናል፡፡
የአንደበት አካላት ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታዩ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ -
የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ፡፡
ተንቀሳቃሽ የአንደበት አካላት የሚባሉት
- ከንፈር
- ምላስ
- እንጥል
- የታችኛው መንገጭላ
የማይንቀሳቀሱ የአንደበት አካላት የሚባሉት ደግሞ
- ጥርስ
- ድድ
- ላንቃ
- ትናጋ

3

በቁዋንቁዋ ውስጥ የሚገኙትን ድምፆች አፈጣጠርና የአቀነጃጀት ሁኔታ የምናጠናበት
የስነልሳን ዘርፍ ስነድምፅ/ስነ ድምፀ ልሳን ይባላል፡፡
ስነ ድምፅ የድምፆችን ረቂቅ/ አዕምሮአዊ የሆነውን ውስጣዊ ባህርይ ይመረምራል፡፡
የስነ ድምፅ አላማ ፡- የአንድን ቁዋንቁዋ ንጥረ ድምፆች
መለየት
- የአንድን ቁዋንቁዋ የቀለም መዋቅር
መወሰን
- የተለያዩ ዘረ ድምፆችን መከሰቻ ቦታዎች መለየት
- የተለያዩ ድምፀ ልሳናዊ ሂደቶችን መለየት
- በአጠቃላይ የድምፆችን አፈጣጠርና ባህርይ መመርመር
ነው፡፡
በቁዋንቁዋ ውስጥ የሚገኙ ድምፆች በአጠቃላይ አናባቢና ተናባቢ ተብለው በሁለት ዋና
ዋና ክፍሎች ይመደባሉ፡፡

4
የአማርኛ ተናባቢ ድምፆች አፈጣጠርና ባህሪያት
 የአማርኛ ተናባቢ ድምፆች ከሳንባ የሚወጣው አየር በተለያዩ ቦታዎች ላይ
በተለያዩ የአንደበት አካላት ሲታገድና ሲለቀቅ የሚፈጠሩ ድምፆች ናቸው፡፡
 ተናባቢ ድምፆች የሚለዩት በመካነ ፍጥረታቸው፣ በባህርየ ፍጥረታቸውና
በንዝረታቸው ነው፡፡
 ድምፆቹ ከነዚህ በአንዱ ወይም በሁለቱ አለበለዚያም በሶስቱም ይለያያሉ፡፡
 መካነ ፍጥረት ፡- የድምፆች መፈጠሪያ ቦታ ሲሆን በላይኛው የአፋችን ክፍል ላይ
ከከንፈር እስከ ማንቁርት ያሉትን የአንደበት አካላት የሚያካትት ነው፡፡
 ከናፍራዊ ድምፆች ፡-
 ከንፈር ወስናዊ ድምፆች ፡-
 የድድ ድምፆች ፡-
 የላንቃ ድምፆች ፡-
 የትናጋ ድምፆች ፡-
 የማንቁርት ድምፆች ፡-

5

 ባህርየ ፍጥረት ፡- ድምፆቹ በሚፈጠሩበት ጊዜ የአየሩን አወጣጥ ሁኔታ የሚያሳይ ባህርይ ነው፡፡
 እግድ ድምፆች ፡- ከሳንባ የሚወጣው አየር በተለያዩ የአንደበት አካላት ሙሉ በሙሉ ሲታገድ
የሚፈጠሩ ድምፆች ናቸው፡፡
 ሙሉ በሙሉ የተነካኩት የአንደበት አካላት ሲላቀቁ የታገደው አየር በአንድ ጊዜ ይወጣል፡፡
 ታግዶ የተለቀቀው አየር የሚወጣው በአፍ በኩል ነው፡፡
 ድምፆቹም - ብ፣ ፕ፣ ጵ => ከናፍራዊ
- ት፣ ድ፣ ጥ => የድድ
- ክ፣ ክው፣ ግ፣ ግው፣ ቅ፣ ቅው => የትናጋ
- ዕ => የማንቁርት
 ፍትግ/ሹልክልክ ድምፆች ፡- ከሳንባ የሚወጣው አየር በተንቀሳቃሽ የአንደበት አካላት አማካኝነት
መውጫው ሲጠብበትና ባገኘው ክፍት ቦታ እየተሹለከለከ ሲወጣ የሚፈጠሩ ናቸው፡፡
 እነዚህ ድምፆች- ፍ => ከንፈር ወስናዊ
- ስ፣ ዝ፣ ፅ => የድድ
- ሽ፣ ዥ => የላንቃ/ድላንቃ
- ህ => የማንቁርት

6

 ፍግድ/ፍትግ ፡- የእግድና የፍትግ/ሹልክልክ ድምፆችን ባህሪያት አጣምረው የያዙ ድምፆች ናቸው፡፡
 የታገደው አየር ግን የሚወጣው በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስበቀስ ነው፡፡ በመሆኑም አየሩ ሙሉ በሙሉ
በመታገዱ የእግድ ድምፆችን በህሪያት ሲጋሩ የታገደው አየር በተለቀቀው ክፍት ቦታ ቀስ በቀስ
በመውጣቱ ደግሞ የፍትግ/ሹልክልክ ድምፆችን ባህሪያት ይጋራሉ፡፡
 እነዚህ ድምፆችም /ች፣ ጅ፣ ጭ/ ናቸው፡፡
 ሰርናዊ ድምፆች ፡- አየር በሰርን ዋሻ በኩል ሲወጣ የሚፈጠሩ ድምፆች ናቸው፡፡
 እንጥል ወደታች ዝቅ ብላ የአፍ ዋሻን ስትዘጋው አየር በሰርን ዋሻ በኩል እንዲወጣ ይገደዳል፡፡
በተቃራኒው ወደላይ ከፍ ብላ የሰርን ዋሻን ስትዘጋው ደግሞ አየሩ በአፍ በኩል ይወጣል፡፡ ድምፆቹም
በቅደም ተከተል ሰርናዊና አፋዊ ድምፆች ይባላሉ፡፡
 ሰርናዊ ድምፆች የሚባሉት /ም፣ን፣ ኝ/ ናቸው፡፡
 እነዚህ ድምፆች ነዛሪዎች ናቸው፡፡
 ጎናዊ ድምፆች ፡- አየር በምላስ ጎንና ጎን ሲወጣ የሚፈጠሩ ድምፆች ናቸው፡፡
 እነዚህ ድምፆች /ል፣ ር/ ሲሆኑ ሁለቱም ነዛሪ ናቸው፡፡
 ከፍናቢ ድምፆች ፡- የአናባቢነትንና ተናባቢነትን ባህሪያት አጣምረው የያዙ ድምፆች ናቸው፡፡
 እነዚህ ድምፆች ስርጭታቸው ከተናባቢ ድምፆች ጋር ሲመሳሰል አፈጣጠራቸው ግን ከአናባቢ
ድምፆች ጋር ይመሳሰላል፡፡
 ድምፆቹ / ው ና ይ/ ናቸው፡፡

7

 ንዝረት ፡- ድምፆቹ በሚፈጠሩበት ጊዜ ህብለ ድምፆች
(ርግብግቢት) የሚያሳዩትን የመርገብገብ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡
 የአማርኛ ተናባቢዎች ከንዝረታቸው አንፃር ነዛሪና ኢ-ነዛሪ
ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡
 ነዛሪ ድምፆች፡- ድምፆቹ በሚፈጠሩበት ወቅት ህብለ
ድምፆች/ርግብግቢት ተጠጋግተው ስለሚገኙ አየሩ ሲወጣ
ገፍትሮአቸው ይወጣል በዚህ ጊዜ ይርገበገበሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ
የሚፈጠሩት ድምፆች ነዛሪ ይባላሉ፡፡
 ኢ-ነዛሪ ድምፆች፡- ድምፆቹ በሚፈተሩበት ጊዜ ህብለ
ድምፆች/ርግብግቢት ተራርቀው ሲለሚገኙ የሚወጣው አየር
አይገፈትራቸውም ስለዚህም አይርገበገቡም፡፡ በዚህ ሁኔታ
የሚፈጠሩት ድምፆችም ኢ-ነዛሪ ይባላሉ፡፡
8
የአማርኛ አናባቢ ድምፆች አፈጣጠር
አናባቢ ድምፆች ከሳንባ የሚወጣው አየር ሳይታገድ እንደልቡ በሚወጣበት ጊዜ የሚፈጠሩ ድምፆች ናቸው፡፡
አናባቢ ድምፆች ልቅ ድምፆች ናቸው፡፡
የማስተጋባት ደረጃቸው ከተናባቢ ድምፆች ይልቅ የአናባቢ ድምፆች ከፍተኛ ነው፡፡
አናባቢ ድምፆች በሙሉ ነዛሪዎች ናቸው፡፡
አናባቢ ድምፆች የሚለዩት በምላስ የወደፊትና የወደሁዋላ እንቅስቃሴ፣ የወደላይና የወደታች እንቅስቃሴ
እና በከንፈር ቅርፅ ሁኔታ ነው፡፡
ለአናባቢ ድምፆች መፈጠር ከፍተኛ ድርሻ ያለው ምላስ ነው፡፡
ከምላስ የወደፊትና የወደሁዋላ እንቅስቃሴ አንፃር፡-
- /ኢ፣ ኤ/ => የፊት
- /A፣ እ፣ ኣ/ => የመሀል
- /ኡ፣ ኦ/ => የሁዋላ
ከምላስ የወደላይና የወደታች እንቅስቃሴ አንፃር፡-
- /ኡ፣ ኢ፣ እ/ => የላይ
- /A፣ ኦ፣ ኤ/ => የመሀል/ልከኛ
- /ኣ/ => የታች
ከከንፈር ቅርፅ አንፃር ፡- / ኡ ና ኦ/ ክብ ሲሆኑ ሌሎቹ በሙሉ ዝርግ ይባላሉ፡፡

9
የአማርኛ ንጥረ ድምፆችና ዘረ ድምፆች
 ቃላት በመካከላቸው የሚኖረው የቅርፅም ይሁን የፍች ልዩነት መነሻው በውስጣቸው
የያዙዋቸው ድምፆች ልዩነት ነው፡፡
 በቃላቱ ውስጥ የሚገኙት ድምፆች በሙሉ ወይም በከፊል ሊለያዩ ይችላሉ፡፡
 ቃላት የትለያዩ ትርጉሞች እንዲኖራቸው የሚያደርጉት ድምፆች ንጥረ ድምፆች ይባላሉ፡፡
 ንጥረ ድምፅ፡- አንዱ ድምፅ በገባበት ቦታ ሌላው ገብቶ የትርጉም ልዩነት የሚያመጣ ነው፡፡
 ዘረ ድምፅ፡- አንዱ ድምፅ በገባበት ቦታ ሌላው ገብቶ የትርጉም ለውጥ የማያመጣ ነው፡፡
 ድምፆች ንጥረ ድምፅ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ የምንጠቀምበት ዘዴ ንዑስ
ጥንድ ይባላል፡፡
 በንዑስ ጥንድ አማካኝነት ንጥረ ድምፅ መሆን አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ የምንፈልጋቸው
ድምፆች በንዑስ ጥንዱ ውስጥ የሚኖራቸው ቦታ ትይዩ መሆን አለበት፡፡
 ንጥረ ድምፆች በወራጅ መስመር ወይም በእዝባር የሚፃፉ ሲሆን ዘረ ድምፆች ግን በማዕዘን
ቅንፍ ይፃፋሉ፡፡
 ምሳሌ፡- አንገት/አንድ/አንበሳ/ገንፎ => ዘረ ድምፆች
- በረት/ወረት፣ ደረሰ/ፈረሰ፣ ቢሮ/ቢራ፣ ወር/ወፍ => ንጥረ ድምፆች

10
ንጥረ ድምፃዊና ዘረ ድምፃዊ አፃፃፍ
መደበኛው የአማርኛ የአፃፃፍ ስረዓት ቀለማዊ ነው፡፡ ማለትም በቃሉ ውስጥ የሚገኙት ተናባቢዎችና
አናባቢዎች በአንድ ላይ ተጣምረው ነው የሚፃፉት፡፡
በንጥረ ድምፃዊ ወይም በዘረ ድምፃዊ አፃፃፍ ስረዓት ግን አናባቢዎችና ተናባቢዎች ተነጣጥለው
ለየብቻቸው ነው የሚፃፉት፡፡
በቃላት ውስጥ ያሉ ትርጉም ለይ የሆኑ ድምፆች ንጥረ ድምፅ ተብለው ይጠራሉ፡፡
ሁለት ቃላት በሁለት የተለያዩ ድምፆች ምክንያት የተለያየ ትርጉም የሚይዙ ከሆነ እነዚያ ተፃራሪ
ድምፆች ንጥረ ድምፆች ናቸው፡፡
ንጥረ ድምፆቹ መገኛ ቦታ በቃል መጀመሪያ፣ በቃል መካከል ወይም በቃል መጨረሻ ሊሆን ይችላል፡፡
ንጥረ ድምፆች በቃል መጀመሪያ ላይ ሲገኙ፡-
ምሳሌ፡- /ስእር/
/ድእር/
ንጥረ ድምፆች በቃል መካከል ሲገኙ
ምሳሌ፡- /ቅኣል/
/ቅእል/
ንጥረ ድምፆች በቃል መጨረሻ ሲገኙ
ምሳሌ፡- /ቅኡም/
/ቅኡር/

11

የድምፆች ስርጭትና ቅንጅት
ቅንጅት ድምፆች አንዱ ከሌላው ጋር ሲቀናጅ ማን ከማን ጋር ይቀናጃል የሚለውን የሚመለከት ነው፡፡
• ተናጠላዊ ስርጭት፡- በቁዋንቁዋው ውስጥ ያሉ ተናጠላዊ ድምፆችን ስርጭት የሚመለከት ነው፡፡
• ሁሉም ንጥረ ድምፆች በቃል መጀመሪያ፣ መካከልና መጨረሻ የመሰለፍ እድል አላቸው፡፡
• በአማርኛ ሁሉም ተናባቢዎች ከ/ኝ/ በስተቀር በቃል መጀመሪያ ላይ ይሰለፋሉ፡፡
• ከአናባቢዎች ደግሞ /እ/ ና /ኣ/ በስፋት ይሰለፋሉ፡፡
• ቅንጅታዊ ስርጭት፡- በአንድ ቃል ውስጥ ያሉ ድምፆች ተቀናጅተው የሚሰለፉበትን ስረዓት ይመለከታል፡፡
• ከ/ኝ/ና ከዳረኞቹ አናባቢዎች በስተቀር ሌሎቹ ድምፆች በቃል መነሻ ላይ ከተገኙ ቀጥሎ የሚመጣው
ማነው?
• የመጀመሪያው ተናባቢ ከሆነ ቀጣዩ አናባቢ ነው፡፡
• የመጀመሪያው አናባቢ ከሆነ ደግሞ ቀጥሎ የሚመጣው አንድ ወይም ሁለት ተናባቢዎች ናቸው፡፡
• ድምፆች በቃላት ውስጥ ሲሰለፉ ወይም ሲሰደሩ ተናባቢ ከአናባቢ ወይም ከተናባቢ ጋር ሊሆን ይችላል፡፡
• በቃላት ውስጥ ተከታትለው የሚመጡት ተናባቢዎች በቃል መጀመሪያ ላይ አንድ ሲሆን በቃል መካከልና
መጨረሻ ላይ ግን ሁለት ተናባቢዎች ተከታትለው ሊመጡ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ - ሰንበት /ስኧንብኧት/ [ስኧምብኧት]
- አንገት /ኣንግኧት/ [ ኣ°ንግኧት ]
- ብቡ /ብእብኡ/ [ብውኡብውኡ ]
- አንድ /ኣንድ/ [ ኣንድ ]

12

አ › እ-ብኣብ
ተአ › /ንኣ/
አተ › /ኣፍ/
አተ ተ › /እጅጅ/
1 1

አተ ተ › /ኣንድ/ የመጀመሪያው ቀጣይ ከሆነ ብቻ


1 2

አለዚያ /እ/ ትገባለች /ፍእቅእር/


ተአተ › /ብኤት/ /ብኣት/
ተአተ ተ › /ልእብብ/ /ድኧግግ/
1 1

ተአተ ተ › /ምኧርዝ/ /ብኧልግ/


1 2

13
ጥያቄዎች
1. የስነ ድምፅን ምንነት አስረዱ፡፡
2. የድምፆችን አፈጣጠር በተመለከተ አጭር ማብራሪያ
ስጡ፡፡
3. የአማርኛ ተናባቢና አናባቢ ድምፆችን አፈጣጠር
አስረዱ፡፡
4. የዘረ ድምፅንና ንጥረ ድምፅን ምንነት አስረዱ፡፡
5. የሚከተሉትን ድምፆች ንጥረ ድምፅ መሆን
አለመሆናቸውን አሳዩ /ኤ፣ኣ/፣ /ን፣ም/፣ /ኧ፣ኣ/፣
/ር፣ል/፣ /ግ፣ክ/
6. ከላይ በተራ ቁጥር 5 የተሰጡትን ድምፆች ግለፅዋቸው፡፡
14

ቀለም
በድምፆች ቅንጅት የሚፈጠር አካል ነው፡፡
• ትርጉም ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል፡፡
• አንድ አናባቢ ብቻውን ወይም ከሌሎች ተናባቢዎች ጋር በመሆን ቀለሙን ሊመሰርት ይችላል፡፡
• ቃላት በሚይዙት ቀለም መሰረት ባለአንድ፣ ባለሁለት፣ ባለሶስት፣ ወዘተ ቀለም ይባላሉ፡፡
ምሳሌ፡- ስኧው › ባለአንድ
ግኧንንኣ › ባለሁለት
ድኧርርኧስኧ › ባለሶስት
• ባለአንድ ቀለም ቃል/ምዕላድ ተራ ቀለም ይባላል፡፡
• ከአንድ በላይ ቀለም ያላቸው ምዕላዶች ውስብስብ ይባላሉ፡፡
• በቀለም ውስጥ ያሉት ድምፆች ተናጠላዊ ቅደምተከተላዊ አሰላለፍ አላቸው ፡፡
• ተዋረዳዊ መዋቅርም አላቸው፡፡
• በቀለሙ ውስጥ አናባቢው ድምፅ ምሰሶ ወይም ቁንጩ ይባላል፡፡ ያለሱ መዋቅሩ ሊቆም
አይችልም፡፡ ምሰሶው ብቻውን መዋቅሩን ሊመሰርተው ይችላል፡፡ ምሰሶው አይቀሬ ነው፡፡
• አናባቢው ከሌሎች ተናባቢዎች ጋር በመሆን የቀለሙን አንድ ርከን መዋቅር ይመሰርታል፡፡ ይህ
ርከን ብቻውን ወይም ከሌላ ተናባቢ ጋር በመሆን የቀለሙን ሌላ ርከን ያዋቅራል፡፡

15
የቀለም እፀ መዋቅር

ከ ማ (ምት)

ም(ማ) ጨ

ል ኣ ም
- አናባቢ ማዕከልን፣ ማዕከልና ጨራሽ ምትን፣ ምትና ከፋች
ቀለምን ይመሰርታሉ፡፡
- ተናባቢዎቹ (ከፋችና ጨራሹ ድምፅ) ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ
ጊዜ ቀለሙ የሚዋቀረው ከምሰሶው ብቻ ይሆናል፡፡
16
ባለሁለት ቀለም
ኣስኣ

ቀ 1 ቀ 2

ከ ምት ከ ምት

ማ ጨ ማ ጨ

- ኣ - ስ ኣ -
17
በባለብዙ ቀለም ምዕላድ ውስጥ የቀለም መዋቅሩን
ለመወሰን የሚከተሉትን የአወቃቀር ስረዓት መከተል ይገባል

• መጀመሪያ ቃሉን/ምዕላዱን በንጥረ ድምፃዊ አፃፃፍ መፃፍ


• ከምዕላዱ ውስጥ አናባቢዎቹን መለየት
• አናባቢውን በስተግራ ከሚገኝ አንድ ተናባቢጋር ማቀናጀት
• አናባቢውን በቀኝ በኩል ከሚገኝ አንድ ሌላ ተናባቢ ጋር
ማቀናጀት
• በመጨረሻ የሚተርፈውን ተናባቢ ከጨራሹ ጋር ማቀናጀት
ምሳሌ፡- አላነጋገርናቸውም

ኣልኣንንኧግኣግግኧርንኣችችኧውም
18

• የቀለም አወቃቀር ስረዓቱ የሁሉም ቁዋንቁዋዎች ስረዓት ነው፡፡
• ጨራሽ ያለው ቀለም ዝግ ቀለም ሲባል
• ጨራሽ የሌለው ቀለም ግን ክፍት ቀለም ይባላል፡፡
• በአማርኛ ውስጥ ጨራሽ ያለው ቀለም ወይም ዝግ ቀለም የሚኖረው
የጨራሽ ድምፅ ብዛት አንድ ወይም ሁለት ሊሆን ይችላል፡፡
• ከአንድ ቀለም በላይ በያዘ ቃል ወይም ምዕላድ ውስጥ ሁለት ጨራሽ ድምፅ
ያለው ዝግ ቀለም ሁል ጊዜ የሚገኘው በመጨረሻው ቀለም ውስጥ ነው፡፡
• ባለአንድ ቀለም ቃል ወይም ምዕላድ ከሆነ ጨራሹ ድምፅ አንድ ወይም
ሁለት ሊሆን ይችላል፡፡

19
መልመጃ
• የሚከተሉትን ምዕላዶች በቀለም እፀ መዋቅር አሳዩ
ቤት ሰውነት
አይን ድንገት
እጅ በላ
አባት መንግስት
አካል አደፈረሰው

20
ድምፀ ልሳናዊ ሂደቶች
• ድምፆች ሲቀናጁ አንዱ በሌላው ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ያሳድራል፡፡ ይህ ተፅዕኖም
የተለያዩ የባህሪ ውርርሶችን ያስከትላል፡፡ ሂደቱም ድምፀ ልሳናዊ ሂደት ይባላል፡፡ ይህ
ሂደት የመመሳሰል፣ ከቦታ የመጥፋት፣ ቦታ የመቀያየር፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡
• ምስለት፡- ሁለት የተለያዩ ድምፆች በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት በከፊል ወይም
ሙሉ በሙሉ ሲያጠፉ የሚከሰት ድምፀ ልሳናዊ ሂደት ነው፡፡
• አንድ ድምፅ ጎረቤቱ ያለውን ድምፅ ባህርይ በከፊል/በሙሉ ሊወርስ ይችላል፡፡
• ይህ ሂደት ምስስሎሽ ሲባል ውጤቱ ደግሞ ምስለት ይባላል፡፡
• ሂደቱ የሚከሰትባቸው ድምፆች መሳይና አስመሳይ ይባላሉ፡፡
• ባህሪ ሰጪው አስመሳይ ሲባል ባህሪ ተቀባዩ ደግሞ መሳይ ይባላል፡፡
• መሳዩ ድምፅ ሁለት አይነት ቅርፅ አለው - ከምስለት በፊትና ከምስለት በሁዋላ፡፡
• ከምስለቱ በፊት ያለው ቅርፅ ታህታይ ቅርፅ ሲባል ከምስለቱ በሁዋላ ያለው ባህሪ ደግሞ
ላዕላይ ቅርፅ ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- በርቺ /ብኧርትኢ/ › ታህታይ ቅርፅ
[ብኧርችኢ] › ላዕላይ ቅርፅ

21

ድምጸ ልሳናዊ ሂደት የምንለው ድምፆች ተቀናጅተው በሚሰለፉበት ጊዜ
በቅርርባቸው ወይም በንክኪያቸው ምክንያት በራሳቸው ወይም
በጎረቤታቸው ላይ የሚከተለውን ለውጥ የምንመረምርበት ሂደት ነው፡፡
አንድ ድምፅ በቅንጅት ምክንያት የተላያዩ ድምፀ ልሳናዊ ሂደቶች
ከተከሰቱበት ያ ድምፅ ሁለት አይነት ቅርፅ ይኖረዋል ማለት ነው -
ከመለወጡ በፊትና ከተለወጠ በሁዋላ፡፡
ከመለወጡ በፊት ያለውን ቅርፅ ታህታይ ቅርፅ ስነለው ከተለወጠ በሁዋላ
ያለውን ቅርፅ ደግሞ ላዕላይ ቅርፅ እንለዋለን፡፡
ታህታይ ቅርፅ፡- አዕምሮአዊ ወይም ረቂቅ ቅርፅ ነው፡፡ በአዕምሮአችን ያለ
ነገር ግን በአንደበታችን የማናወጣው ቅርፅ ነው፡፡
ላዕላይ ቅርፅ፡- አንደበታዊ ወይም ተጨባጭ ቅርፅ ነው፡፡ ተጨባጭ ነው
የምንልበት ምክንያት በሚዳሰሱት የአንደበት ክፍሎች አማካኝነት
የሚነገርና በጆሮ የሚሰማ በመሆኑ ነው፡፡

22

• ምስስሎሹ ከሚካሄድበት አቅጣጫ አንፃር ገስጋሽ ወይም መላሻ ሊባል ይችላል፡፡
• ለዋጩ ድምፅ ከተለዋጩ በስተግራ የሚገኝ ከሆነና ወደፊት ሄዶ ባህሪውን የሚያወርስ
ከሆነ ገስጋሽ (የፊትዮሽ) ምስስሎሽ ሲባል ለዋጩ ድምፅ ከተለዋጩ በስተቀኝ የሚገኝ
ከሆነና ወደሁዋላ ተመልሶ ባህሪውን የሚያወርስ ከሆነ ምስስሎሹ መላሽ (የሁዋልዮሽ)
ይባላል፡፡ በአማርኛ ውስጥ በስፋት የምናገኘው መላሽ ምስስሎሽን ነው፡፡
• ከናፍራዊነት፡- መካነ ፍጥረቱ የከንፈር ያለነበረ ድምፅ ከከንፈር ድምፅ ጋር ሲቀናጅ
የሚፈጠር ሂደት ነው፡፡
ምሳሌ፡- /ኣንብኧስስኣ/ [ኣምብኧስስኣ ]
/ን/ [ ም ] -/ብ/
ታህታይ ለዋጭ ህግ [ ላዕላይ ] / ተፅዕኖ
/ግኧንፍኦ/ [ግኧምፍኦ]
/ን/ [ ም ] -/ፍ/
ታህታይ ለዋጭ ህግ [ ላዕላይ ] / ተፅዕኖ

23
ተጨማሪ ምሳሌዎች
/ግእንብኣር/ [ግእምብኣር]
/ኣንብኧጥጥኣ/ [ኣምብኧጥጥኣ]
/ዝእንብ/ [ዝእምብ]
/ክኧንፍኧር/ [ክኧምፍኧር]
/ክእንፍ/ [ክእምፍ]

24

• ላንቃዊነት፡- የላንቃ ያልሆነ ድምፅ በጎረቤቱ ድምፅ ምክንያት ወደላንቃ
ድምፅነት ሲለወጥ የሚከሰት ሂደት ነው፡፡
• ምስስሎሹ ከፊል ወይም ሙሉ ሊሆን ይችላል፡፡
• ከፊል ላንቃዊነት፡- ማንኛውም ተናባቢ ድምፅ ከፊት አናባቢዎች
(ኢናኤ) በፊት ሲገባ በከፊል ወደላንቃ ድምፅነት የሚቀየርበት ሂደት
ነው፡፡
ምሳሌ፡- /ክኢስ/ [ ክይኢስ ]
- /ብኤት/ [ብይኤት]
- /ክኧይስኢ/ [ክኧይስይኢ]
- /ቅኤስ/ [ቅይኤስ]
- /ቅኢም/ [ቅይኢም]
- /ግኤትኣ/ [ግይኤትኣ]
25

• ሙሉ ላንቃዊነት፡- የድድ ድምፆች ከፊት አናባቢዎች ወይም
ከላንቃ ድምፆች ቀደመው ሲገቡ ሙሉ በሙሉ ወደላንቃ ድምፅነት
የሚቀየሩበት ተደት ነው፡፡
ምሳሌ፡- /ግኧድኣል-ኢ/ [ግኧድኣይ]
/ዝኧንንኣጥ-ኢ/ [ዝኧንንኣጭ]
/ውኧስእድድ-ኤ/ [ውኧስእጅጅኤ]
/ልኧምእንን-ኤ/ [ልኧምእኝኝኤ]
/ግኧምት-ኢ/ [ግኧምችኢ]
/ቅኡርኧጥ-ኢ/ [ቅኡርኧጭኢ]
/ንኧቅእልል-ኤ/ [ንኧቅእይይኤ]

26

• ትናጋዊነት፡- የትናጋ ያልሆኑ ድምፆች ከትናጋ ድምፅ
ጋር ሲሰለፉ የሚፈጠር ሂደት ነው፡፡
• የትናጋ ድምፆች ሁዋለኛና ላይኛ ናቸው፡፡
ምሳሌ፡- /ኣንግኧት/ [ኣ ንግኧት]
/እንቅእርት/ [እ ንቅእርት]
/ድእንክ/ [ድእ ንክ]
/ምኧንግእስት/ [ምኧ ንግእስት]
/እንቅኡ/ [እ ንቅኡ]
/እንክእትት/ [እ ንክእትት]
27

• ማንቁርታዊነት፡- ከፈንጂ ድምፆች ጋር የሚሰለፍ
ድምፅ የማንቁርታዊነት ባህሪን ይወርሳል፡፡
• ፈንጂ ድምፆች ሁለት ቦታ አየር የሚታገድባቸው
ድምፆች ናቸው፡፡
ምሳሌ፡- /ኣስፅኣፍኧው/ [ኣፅፅኣፍኧው]
/ኣት-ጥኧይይእቅ/ [ኣጥጥኧይይእቅ]
/ኣት-ቅኧቅል/ [ኣቅቅኧቅል]

28

• ክበት፡- በተፈጥሮው ዝርግ የነበረ ድምፅ ወደክብነት ይቀየራል፡፡
• ከሁዋላ አናባቢዎች (ኡናኦ) ጋር ሲሰለፉ የሚከሰት ነው፡፡
ምሳሌ፡- /ስኡቅ/ [ስውኡቅ]
/ጥኦር/ [ጥውኦር]
/ስኡፍ/ [ስውኡፍ]
/ቅኦቅ/ [ቅውኦቅ]
/ቅኦምኧ/ [ቅውኦምኧ]
/ጥኦርኧ/ [ጥውኦርኧ]
/ክእፍኡ/ [ክእፍውኡ]
/ክኡርኣት/ [ክውኡርኣት]
29

• ድምፀት፡- በተፈጥሮው ኢነዛሪ የነበረ ድምፅ ወደነዛሪ
ድምፅ የሚቀየርበት ሂደት ነው፡፡
ምሳሌ፡- /አስ-ዝኧፍፍኧንኧ/ [ ኣዝዝኧፍፍኧንኧ]
/አስ-ዝኧርርኣህኡ/ [ኣዝዝኧርርኣህኡ]
• ኢድምፀት፡- አንድ ነዛሪ የነበረ ድምፅ በጎረቤቱ ኢ-ነዛሪ
ድምፅ ምክንያት ኢነዛሪ ድምፅ ይሆናል፡፡
ምሳሌ፡- ፍኧልልኧግ-ክ ፍኧልልኧክክ
- ድኧንንኧዝኧዝ-ክ ድኧንንኧዝኧስክ
- አል-ት-ውእጥኣ አትት-ውእጥኣ ትእዛዛ
- ፍኧዝኧዝ-ክኡ ፍኧዝኧስክኡ
30

• ግድፈት፡- አንድ ድምፅ በቅንጅት ምክንያት ከቦታው ሊጠፋ ይችላል፡፡
• በአንድ ቃል ውስጥ ድምፅ መገደፍ አለመገደፉን የምንለይባቸው የተለያዩ
ምልክቶች አሉ፡፡
• የአማርኛ ግሶች ባብዛኛው ባለሶስት እግር ናቸው፡፡ ስለዚህ ብዞዎቹ ባለሁለት
እግር ግሶች አንድ እግራቸውን የገደፉ ናቸው፡፡
• የሁሉም ግሶች ቅርፅ ተአተተአተአ ሲሆን ከዚህ ውጭ ያለው ቅርፅ የተገደፈ
ድምፅ መኖር አለመኖሩን ያሳየናል፡፡
• በግሶቹ ውስጥ የምናገኘው አናባቢ /ኧ/ ሲሆን ሌሎቹ አናባቢዎች የተገደፈ ድምፅ
መኖሩን የሚጠቁሙ ናቸው፡፡
• የተገደፈውን ድምፅ ለማወቅ የግሶቹን አቻ ሰሞች ሰንመለከት እናገኛዋለን፡፡
• በአቻ ስሞቹ ላይ የምናገኛት /ት/ በግሱ ውስጥ የተገደፈ ድምፅ ስለመኖሩ
የምትጠቁም ድምፅ ናት፡፡
• ግደፈቱ የሚካሄደው ባብዛኛው በግሶች ላይ ሲሆን በስሞች ላይም አልፎ አልፎ
ይታያል፡፡

31


ለምሳሌ አየለ በሚለው ግስ ውስጥ የተገደፈ ድምፅ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ
የሚከተለውን እንመልከት፡፡
• ግሱ በአናባቢ መጀመሩ የተገደፈ ድምፅ መኖሩን ይጠቁማል፡፡ ምክንያቱም ግሶች የሚጀምሩት
በተናባቢ እንጂ በአናባቢ አይደለም፡፡
• ግሱ በአናባቢ መጀመሩ የተጎረደው ድምፅ የመጀመሪያው ተናባቢ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
• በግሱ ውስጥ ያለው አናባቢ /ኣ/ መሆኑም ሌላው የተገደፈ ድምፅ ስለመኖሩ የሚጠቁም ነው፡፡
ምክንያቱም ባልገደፉ ግሶች ውስጥ የምናገኘው አናባቢ /ኧ/ ነው፡፡
• የተገደፈውን ድምፅ ማንነት ለማወቅ የግሱን አቻ ስም ማየት ተገቢ ነው፡፡ አቻ ስሙ ደግሞ
ሀይል ነው፡፡ ስለዚህ የተጎረደው ድምፅ /ህ/ ነው ማለት ይቻላል፡፡
• የግሱ ታህታይ ቅርፅ ህኧይይኧልኧ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
• አንድ ድምፅ ሲገደፍ ወይም ከቦታው ሲጠፋ ዝም ብሎ ሳይሆን ባህሪውን አጠገቡ ላለው ድምፅ
አውርሶ ነው፡፡
• በዚህ ግስ ውስጥ የተገደፈችው /ህ/ ስትሆን የታችነት ባህሪዋን አጠገቡዋ ላለው አናባቢ
አውርሳ ነው የጠፋችው፡፡
• ከ/ህ/ አጠገብ ያለው አናባቢ /ኧ/ ሲሆን የታችነት ባህሪን ከ/ህ/ ወርሶ የታች አናባቢ /ኣ/
ለመሆን ችሎአል፡፡

32

• በመሆኑም የግሱ ላዕላይ ቅርፅ /ኣይይኧልኧ/ ለመሆን ችሎአል ማለት ነው፡፡
• በአንድ ቃል ውስጥ የሚገደፈው /ህ/ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ድምፆችም ሊገደፉ ይችላሉ፡፡
• በአማርኛ ውስጥ በስፋት ሲገደፉ የሚታዩት ድምፆች /ህ፣ ዕ፣ ው ና ይ/ ናቸው፡፡ እነዚህ
ድምፆች ሲገደፉ አጠገባቸው ያለውን አናባቢ አንደሚከተላው አድርገው በመለወጥ
ነው፡፡
• /ህናዕ/ ሲገደፉ አጠገባቸው ያለው የመካከል አናባቢ ወደታች አናባቢነት ይለወጣል፡፡
/ው/ ስትገደፍ ደግሞ ይኼው አናባቢ ወደክብ አናባቢነት ሲቀየር /ይ/ ከተገደፈች
አናባቢው ወደፊት አናባቢነት ይለወጣል፡፡
ምሳሌ፡- በላ
- ሞተ
- መሼ
- ፃፈ - ሄደ
- ፈራ - ቆመ
- ሳለ -

33

• ጥበቀት፡- አንድ በተፈጥሮው ጥብቅ ያልሆነ ድምፅ በአነባበብ ምክንያት ጥብቅ ይሆናል፡፡
• ሂደቱ በሶስት ምክንያቶች ይከሰታል - በምስስሎሽ፣ በክትትሎሽና በተፈጥሮ፡፡
• በመስስሎሽና ክትትሎሽ የሚከሰተው ጥብቀት በስነ ምዕላዳዊ አውድ ላይ የሚታይ ሂደት
ነው፡፡
ምሳሌ፡- ስኤት- ትሁን፣ ብኤት- ስኧርርኣ፣ ልእቅቅኣምኢ
ጥኧርኣግኢ አድራጊ ስሞች
ስኧብኣርኢ
ስእብብኣርኢ የውጤት ስሞች
ጥእርርኣግኢ
በአንድ ቃል ውስጥ ከአንድ በላይ የጠበቀ ድምፅ ሊኖር ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- /ውኧትትኣድድኧር/
/ቅኧምምኣኝኝኣ/
/ምኧጥጥኣብብእኝኝ/
/ይኧምምኢፍፍኧልልኧግእብብእኝኝ/
ጥብቀት በአማርኛ ውስጥ ንጥረ ድምፃዊ ወይም ትርጉም ለይ ነው፡፡

34

• ልለት፡- የጥብቀት ተቃራኒ ነው፡፡
• እግድ ድምፆች ወደፍትግነት/ሹልክልክነት
የሚቀየሩበት ሂደት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ልኣብ፣ ክኣብ፣ ስእብ፣ ዝእንኣብ፣
ጥእግኣብ፣
ፅኧብኧል፣ ውኧብኧቅ
ጥእጅጅኣ-ኡ ጥጃው
ልኤልኣ-ኡ ሌላው
ጅኧብኧንኣ-ኢትኡ ጀበናይቱ
35
የአናባቢ ምስለት
• የአናባቢዎች ምስስሎሽ ከተናባቢዎቹ የተለየ ነው፡፡
• በተናባቢዎች ጊዜ ምስስሎሹ የሚከናወነው ጎን ለጎን በሆኑ
ድምፆች መካከል ሲሆን፣ በአናባቢዎች ጊዜ ግን ምስስሎሹ ርቀት
ያለው ነው፡፡
• በሚመሳሰሉት ድምፆች መካከል ተናባቢ ድምፅ አለ ምክንያቱም
አናባቢዎች ተከታትለው መምጣት አይየችሉም፡፡
ምሳሌ፡- ስኒ /ስእንኢ/ [ስኢንኢ]
እ-----›ኢ/-ኢ
ሽሮ /ሽእርኦ/ [ሽኡርኦ]
እ--------› ሮ/-ኦ
36

• ኢምስለት፡- ድምፆች በመካከላቸው ያለውን ተመሳስሎ ሲያሰፉ የሚያሳይ ክስተት
ነው፡፡
ምሳሌ፡- ኣቅጥኣጭጭኣ አግጥኣጭጭኣ
- ግእድግእድድኣ ግእርግእድድኣ
- ግኦድግውኣድድኣ ግኦርግውኣድድኣ
• ስርገት፡- የተናባቢ ክትትሎሽን ለመስበር ያገለግላል፡፡
• ቁዋነቁዋው ከሚፈቅደው የተናባቢ ድምፆች ክትትል በላይ ተከታትለው ሲመጡ
ስረዓቱን ለማስጠበቅ ፈልቃቂ የሆነችው /እ/ በተገቢው ቦታ ገብታ ታገለግላለች፡፡
ምሳሌ፡-ቅኧልድእህ፣ ስኣቅቅእህ፣ ልእብስ፣ ጥእብስ፣
ውእርስ፣ ቅእርስ
/እ/ በቃል መጀመሪያ ላይም ልትገባ ትችላለች፡፡
ምሳሌ፡- ር-ግምኣን እርግእምኣን
ር-ጥብኣን እርጥእብኣን
ስ-ፕኦርት እስፕኦርት

37

• ቦታ ቅየራ፡- ድምፆች ያለምንም የትርጉም ልዩነት
ቦታ የሚቀያየሩበት ሂደት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ምኧጥርኧብኢይኣ - ምኧርጥኧብኢይኣ
- ምኣክስኧኝኝኦ - ምኣስክኧኝኝኦ
- ክኧርኧብኦ - ክኧብኧርኦ

38
መልመጃ
• የተለያዩ ምሳሌዎችን በማንሳት የተካሄደባቸውን
ድምፀ ልሳናዊ ሂደቶች አብራሩ፡፡
• ማክሰኞ በጉራጌ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ማቅሰኞ
ይባላል፡፡ ይህ ቃል ለየትኛው ድምፀ ልሳናዊ ሂደት
ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ማብራሪያ ስጡ፡፡

39
መልመጃ
1. የሚከተሉትን ቃላት በንጥረ ድምፃዊና ዘረ ድምፃዊ አፃፃፍ ከፃፋችሁ
በሁዋላ የተካሄደባቸውን ድምፀ ልሳናዊ ሂደት አብራሩ፡፡
ሀ. ሞተ
ለ. መንጋ
ሐ. ጥንብ
መ. ወሳጅ
2. በሚከተሉት ቃላት ውስጥ የተጎረደውን ድምፅ ለይታችሁ አመልክቱ፡፡
ሀ. ቆመ
ለ. በራ
ሐ. አደገ
መ. ሄደ

40
..
3. ለሚከተሉት ቅንጅቶች መሳሌዎችን ስጡ፡፡
ሀ. አተ1ተ1
ለ. ተአተ1ተ1
ሐ. ተአተ1ተ2
መ. ተአተ
4. የሚከተሉትን ቃላት በቀለም እፀመዋቅር አሳዩ፡፡
ሀ.መንገድ
ለ. ብርቅርቅ
ሐ. አመል
መ. እንቁላል
5. የሚከተሉትን ድምፆች ንጥረ ድምፅ መሆን አለመሆናቸውን በንዑስ ጥንድ አሳዩ፡፡
(ድ፣ ጥ) (ን፣ ም) (ል፣ ር) (ኢ፣ ኤ)

41
..
• 5. የመስተዓምርን ምንነትና አይነቶች አብራርታችሁ
ለያነዳንዳቸው የተለያዩ ምሳሌዎችን ስጡ፡፡

42
ስነ ምዕላድ
• የቃላትን ውስጣዊ መዋቅር የሚያጠና የስነ ልሳን ዘርፍ ነው፡፡
• ምዕላድ በቁዋነቁዋ ውስጥ ትንሹ ትርጉም አዘል የሆነ አሀድ ነው፡፡
• አነስተኛ ወደሆኑ ትርጉም አዘል ክፍሎች ሊሸነሸን የማይችል የመጨረሻ
አሀድ ነው፡፡
• ቢሸነሸን የምናገኘው ትርጉም አልባ ክፍሎችን ነው፡፡
• ትርጉም አዘል ወደሆኑ ክፍልፋዮች የሚከፈል ከሆነ ምዕላድ አይደለም፡፡
• ከተከፋፈለ ከምዕላድ በላይ ስለሚሆን ቃል ተብሎ ይጠራል፡፡
• አንድ ቃል ከተለያዩ ምዕላዶች የተወቀረ ሊሆን ይችላል፡፡
• ከተላያዩ ምዕላዶች የተዋቀረ ቃል ከሆነ ምዕላዶቹ የያዙት ቦታ
የማይቀየር ነው፡፡
• የምዕላዶቹ ቦታ የሚቀየር ከሆነ የቃሉ ትርጉም ይቀየራል ወይም ቃሉ
ትርጉም አልባ ሊሆን ይችላል፡፡

43

• ምዕላድ ራሱን ችሎ ከማቆምና ካለመቆም አንፃር በሁለት ይከፈላል - ነፃ ምዕላድና ጥገኛ ምዕላድ
በመባል፡፡
• ነፃ ምዕላድ:- ራሱን ችሎ የሚቆም
- የራሱ የሆነ ትርጉም ያለው
- ሌሎች ምዕላዶችን ሊያስጠጋ የሚችል
• ጥገኛ ምዕላድ፡- ራሱን ችሎ የማይቆም
- የራሱ የሆነ ትርጉም የሌለው
- ትርጉሙ ይገለጥ ዘንድ ሌላ የሚጠጋበት አካል የሚፈልግ
• አንድ ምዕላድ የተለያዩ መገለጫዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡ እነዚህ የአንድ ምዕላድ የተለያዩ
መገለጫዎች ተመሳሳይ አገልግሎት ስላላቸው ዘረ ምዕላድ ይባላል፡፡
• ዘረምዕላዶች የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ነገር ግን አገልግሎታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ምዕላዶች ናቸው፡፡
ምሳሌ - በግ-ኤ፣ በሬ-ዬ
- ሰው-ኦች፣ ተማሪ-ዎች
• ምዕላዳዊ ትንተና ልክ እንደዐረፍተ ነገር ትንተና ሁሉ በአንድ ቃል ውስጥ ያሉ ምዕላዶችን
የምንተነትንበት ሂደት ነው፡፡
ምሳሌ- ቤት-ኦች፣ ስለ-ቤት-ኦች-ኣችን

44
የቃልና የምዕላድ
• አድነት፡- ሁለቱም የራሳቸው ትርጉም አላቸው
አንድነትና ልዩነት
- ቃል እንደነፃ ምዕላድ ሁሉ ራሱን ችሎ ይቆማል
- ቃል እንደነፃ ምዕላድ ሁሉ ከቃላት ክፍሎች ውስጥ
በአንዱ ሊመደብ ይችላል
• ልዩነት፡- ቃል ወደተለያዩ ትርጉም አዘል ክፍሎች ሊሸነሸን
ይችላል ምዕላድ ግን አይችልም
- ጥገኛ ምዕላድ ራሱን ችሎ አይቆምም ቃል ግን መቆም
ይችላል
- ጥገኛ ምዕላድ ከቃል ክፍሎች ውስጥ በአንዱ ሊመደብ
አይችልም
• በመሆኑም ነፃ ምዕላዶች ሁል ጊዜ ቃልም ምዕላድም ናቸው፡፡
• ከተለያዩ ምዕላዶች የተገኙ ቃላት ምዕላዳዊ ሊባሉ ይችላሉ
ምሳሌ፡- ሆዳም
ቤቶች
• ማንኛውም ቁዋንቁዋ የነፃና ጥገኛ ምዕላዶች ክምችት ነው
• ስነ ምዕለድ (ስነቃላት) የቃላትን ክፍፍልና ውስጣዊ ስርዓት እንዲሁም መዝገበ ቃላትን ያጠቃልላል

45
የአማርኛ ቃል ክፍሎች
• ቃላትን በክፍል በክፍላቸው ለመመደብ በዋናነት የሚያገለግሉት መስፈርቶች ቅርፅና አገባብ ናቸው ትርጉም እንደረዳት
መስፈርትነት ሊያገለግል ይችላል
• ቃላት በዋናነት በሁለት ይከፈላሉ - ዋና ዋና (የይዘት) ቃላትና ንዑሳን (የተግባር ቃላት) በመባል
• ዋና ዋና (የይዘት) ቃላት የሚባሉት ሲጠሩ የራሳቸው ትርጉም ያላቸው፣ ሌሎች ቃላትን ለመመስረት የሚያገለግሉ፣
ከሌሎች ቃላት ሊመሰረቱ የሚችሉ ናቸው፡፡
• ዋና ዋና ቃላት በቃል ደረጃ ትርጉም፣ በመዋቅር ደረጃ ደግሞ ሰዋሰዋዊ ተግባር አላቸው፡፡
- ነገሮችን የሚጠቁሙት - ስሞች
- የነገሮችን ባህሪያት የሚጠቁሙት - ቅፅሎች
- ድርጊቶችን የሚጠቁሙት - ግሶች
- አደራረጎችን የሚጠቁሙት - ተውሳከ ግሶች ይባላሉ፡፡
• ዋና ዋና ቃላት የገላጭነትና የተገላጭነት ባህርይ አላቸው፡፡
- ቅፅልና ተውሳከ ግስ ገላጮች ሲሆኑ
- ስምና ግስ ደግሞ ተገላጮች ናቸው
• ንዑሳን (የተግባር) ቃላት የሚባሉት ደግሞ ሌሎች ቃላትን ለመመስረት የማያገለግሉና እነሱም ከሌሎች ቃላት
የማይመሰረቱ ናቸው፡፡
• ንዑሳን የቃል ክፍሎች የራሳቸው ቃላዊ ትርጉም ሳይሆን መዋቅራዊ ተግባር ብቻ አላቸው፡፡
• የራሳቸው የሆነ ቁጥርን፣ ፆታን፣ ጊዜን አመልካች ቅጥያ የላቸውም፡፡
• ቁጥራቸው አይጨምርም አይቀንስም፡፡
• በዚህ ክፍል የሚመደቡት የቃል ክፍሎች መስተዋድድና መስተዓምር ናቸው፡፡

46

• ስም፡- አንድ ቃል በስም የቃል ክፍል ውስጥ ለመመደብ የሚቀጥሉትን መስፈርቶች ማሙዋላት
አለበት፡፡
 በቅርፁ -ኦች የሚለውን ምዕላድ የሚያስከትል
 በአገባቡ የአረፍተ ነገር ባለቤት በመሆን የሚያገለግል
 የአረፍተ ነገር ተሳቢ ሆኖ ሊገባ የሚችል
 የተለያዩ መስተዓምሮችን ሊወስድ የሚችል
 የተለያዩ ገላጮችን ሊወስድ የሚችል ከሆነ በስም የቃልክፍል ውስጥ ይመደባል፡፡
ምሳሌ፡- ልጅ
- ልጆች ሰው አክባሪ ናቸው
- ልጅ የፈጣሪ ስጦታ ነው
- እኔ ልጅ እወዳለሁ
- ያ ልጅ ጎበዝ ነው
- ትልቅ ልጅ አላት
• ተውላጠ ስሞች በቅርፅም በአገባብም ከስሞችጋር ይለያያሉ
- እሱ ጎበዝ ነው
- እኔ እሱን እወደዋለሁ
- እነሱ እኛን ይፈሩናል

47

• ግስ፡- በአገባቡ በአረፍተ ነገር መጨረሻ ላይ በመግባት የአረፍተ ነገሩ ማሰረያ አነቀፅ በመሆን የሚያገለግል፣
በቅርፁ መደብ አመልካች ምዕላዶችን (የባለቤትና የተሳቢ አፀፋ) መውሰድ የሚችል ቃል ሁሉ የቃል ክፍሉ ግስ
ይባላል፡፡
ምሳሌ፡- እኔ ዳቦ በላ-ሁ
- አንተ ወተት ጠጣ-ህ
- አንቺ ዶሮ ገዛ-ሽ
- አንተ እሱዋን መታ-ህ-ኣት
- እሱ እኔን ሰደብ-ኧ-ኝ
• ስምና ግስ በቁዋንቁዋው ውሰጥ የሚገኙ አብዘኛዎቹን ቃላት ይይዛሉ::
• በማንኛውም ቁዋንቁዋ ውስጥ የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቃለት የድርጊትና የነገር ስሞች ናቸው::
• አብዛኛዎቹ አረፍተ ነገሮችም የድርጊቶች መገለጫ የሆኑት የስሞችና የግሶች ቅንጅት ናቸው፡፡
• ሌሎቹ ቃላት የነዚህ አጃቢዎች ናቸው፡፡
• ቅፅል፡- ከስም በፊት እየገባ ስምን የሚገልፅ የቃልክፍል ነው፡፡
• ከስም በፊት የገባ ቃል ሁሉ ግን በቅፅል የቃል ክፍል ውስጥ ላይመደብ ይችላል፡፡
• ከስም በፊት የገባው ቃል ቅፅል መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ በጣም የሚለውን መስተዓምር መውሰድ አለበት፡፡
አለበለዚያ በቅፅል የቃል ክፍል ውስጥ አይመደብም፡፡
ምሳሌ፡- ጎበዝ ተማሪ
- በጣም ጎበዝ

48

• አንድ ቃል ሊመደብ የሚችለው በአንድ የቃል ክፍል ውስጥ
ብቻ ነው፡፡
• ቅፅሎች ከስሞችና ግሶች የሚለዩት በቅርፃቸው ብዛትን
ለማሳየት ቅድመመድረሻ እግራቸውን በመድገማቸው ነው፡፡
ምሳሌ፡- ረዥም ረዣዥም
አጭር አጫጭር
• ስሞች ግን ሙሉ ቃሉን ይደግማሉ
- ቀጠል ቅጥላቅጠል
- ጥብስ ጥብሳጥብስ

49
• ተውሳከ ግስ፡- የግስ ጭማሪ ማለት ነው፡፡

• ከግስ በፊት እየገባ ግሱ ስለሚገልፀው ነገር ተጨማሪ ማብራሪያ የሚሰጥ ነው፡፡
• የሚያጎላምሰውን ግስ ከቦታ፣ ከሁኔታ፣ ከጊዜና ከተለያዩ ነገሮች አንፃር ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
ምሳሌ፡- አስቴር ትናንት ምሳ አልበላችም፡፡
- አየለ ቶሎ መጣ፡፡
- ልጁ ምሳውን ገና አልበላም፡፡
- ካሳ ዛሬ ትምህርት ቤት አልመጣም፡፡
• ተውሳከ ግስ ብዙ ቃላት የሉትም፡፡
• ቃላት በቃል ክፍላቸው አንድ አይነት ሆነው በግብራቸው ግን የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ምሳሌ፡- ትናንት - ጊዜን ሲያመለክት
- ክፉኛ - ሁኔታን ያመለክታል
ካሳ ጥሩ ነጭ ላም አለችው
• ተውሳከ ግሳዊ ተግባር በብዛት የሚገለፀው በስማዊ ሀረጎች፣ በመስተዋድዳዊ ሀረጎች ወይም በጥገኛ አረፍተ
ነገሮች ነው፡፡
ምሳሌ፡- ልጁ በፍጥነት ተመለሰ፡፡
አልማዝ ባልዋ ከአዲስ አበባ ስለመጣ ተደስታለች፡፡

50

• መስተዋድድ፡- ከስም ጋር አየተዋቀረ መስተዋድዳዊ ሀረግን በመመስረት ተውሳከ ግሳዊ ተግባርን የሚፈፀም የቃል
ክፍል ነው፡፡
• ጊዜን፣ ቦታን፣ ምክንያትን፣ አላማን ያመለክታል፡፡
• ምንም አይነት ቅጣይ ምዕላድ አያስከትልም፡፡
• ለአዳዲስ ቃላት ምስረታ በመሰረትነት አያገለግልም፡፡
• መስተዋድዶች የራሳቸው የሆነ ትርጉም የላቸውም ተግባር ግን አላቸው፡፡
• ተግባራቸው ከስም ጋር አየተዋቀሩ መስተዋድዳዊ ሀረግን በመመስረት ተውሳከ ግሳዊ ተግባርን መፈፀም ነው፡፡
ምሳሌ፡- ስለትምህርት ብዙ ሰው ይቆረቆራል - ምክንያትን
- እንደእርግብ የዋህ ሁኑ - ንፅፅርን
- ወደጎንደር እሄዳለሁ - አቅጣጫን
- በሶስት ሰዓት ይመጣል - ጊዜን
- ለሰርግ የተጠመቀ ጠላ - አላማን ይገልፃል፡፡
• መስተዋድድ ከስም ጋር ሲገባ መስተፃምር ግን ከግስ ጋር ይገባል፡፡
- ካሳ ስለታመመ አስቴር አዘነች
- ካሳ እንደመጣ አስቴር ሄደች
- ካሳ ከሰከረ አስቴር ትናደዳለች
- ካሳ ስ-ይ-ሄድ አስቴር ትደሰታለች
• የመስተፃምሮች ተግባር የገቡበት አረፍተ ነገር ጥገኛ መሆኑን ማመልከት ነው፡፡
• ከስም ጋር የሚዋቀሩት ተራ መስተዋድድ ሲባሉ ከግስ ጋር የሚዋቀሩት ግን ሞይ ይባላሉ፡፡

51

• መስተዓምር፡- አንድ ነገር፣ ድርጊት፣ ባህርይ ከሌላው የተለየና የሚታወቀ መሆን አለመሆኑን
ያመለክታል፡፡
• ትርጉሙ የሚያሳውቅ፣ የሚለይ ማለት ነው፡፡
• ጥቆማው ከጊዜ ወይም ከቦታ አንፃር፣ ነገሩ የማን እንደሆነ ከማገናዘብ አንፃርና በመጠን ከመግለፅ አንፃር
ነው፡፡
• በአማርኛ ውስጥ የምናገኘው ስሶት አይነት መስተዓምሮችን ነው፡፡
• ጠቁዋሚ መስተዓምር፡- ከስማዊ ሀረግ ጋር እየገባ ስሙን ወይም ነገሩን ከጊዜና ከቦታ አንፃር ለይቶ
የሚጠቁም ሲሆን የራሱ የሆነ ትርጉም የለውም፡፡
- ተራ ጠቁዋሚ - ይህ፣ ያ፣ እኔ፣ አንተ
- ለይ ጠቁዋሚ - አንዱን ወይም የተወሰኑትን የሚለይ
(ይኼኛው፣ ያኛው፣ ላይኛው፣ ታችኛው)
• አገናዛቢ መስተዓምር፡- ባለንብረትነትን ወይም ባለገንዘብነትን የሚጠቁም ነው፡፡ የተፀውዖ ስሞችና
ተውላጠ ስሞች በዚህ ክፍል ይመደባሉ፣ ስሙን ቀድመው ይገባሉ፣ /የ/ የምትል ምዕላድ ያስቀድማሉ
(የኔ መፅሃፍ፣ የሱ ልብስ)
• መጣኝ መስተዓምር፡- አህዛዊ መጠንን ወይም አካላዊ መጠንን ይጠቁማሉ፡፡
- አንድ ልጅ፣ አንዳንድ ልጆች፣ ብዙ/ጥቂት ልጆች

52
የቃላት ርባት ስረዓት
• የርባታ ስረዓት ማለት ምን ማለት ነው? የተለያዩ
የቃላት ክፍሎችን በምሳሌነት በማንሳት አብራሩ፡፡
• የስም ርባታ
• የቅፅል ርባታ
• የግስ ርባታ

53

• ቃላት ለተለያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት ሲባል ቅርፃቸውን በከፊል ይቀያይራሉ፡፡
• ሰዋወዋዊው ተግባር ቃላቱ በአረፍተ ነገር ውስጥ እንዳላቸው ቦታና ተግባር የተለያየ ነው፡፡
• የስም ርባታ፡- ስሞች ለተለያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት (ለቁጥር፣ ለፆታ፣ ለሙያና ለእምርነት) ቅርፃቸውን በከፊል
ይለዋውጣሉ፡፡
ስሞች ለቁጥር ሲረቡ/ቅርፃቸውን ሲለዋውጡ
• ቁጥር፡- በአንድ ስም የሚጠቀስ ነገርን ስንትነት የሚገልፅ ሰዋሰዋዊ ተግባር ነው፡፡ ጠቅለል ባለ አገላለፅ ቁጥር ሁለት
አይነት ሲሆን ነጠላ ቁጥርና ብዙ ቁጥር በመባል ይታወቃል፡፡ አንድ ብቻ የሆነ ነገር/ ስም ነጠላ ሲባል ከአንድ በላይ
የሆነ ነገር/ስም ግን ብዙ ይባላል፡፡
• በአማርኛ ነጠላ ስም ለነጠላነቱ የሚሆን የተለየ ምልክት የለውም፡፡ ብዙ ቁጥር ግን ብዙነቱን የሚያመለክት ምዕላድ
አለው፡፡ የብዙ ቁጥር አመልካች ምዕላድዋ /-ኦች/ ናት፡፡
• አንዳንድ ነጠላ ስሞች ግን ንጥልነትን ወይም የተለየ መሆንን የሚያመለክቱበት ስረዓት አላቸው፡፡ እነዚህ ስሞች
ማንኛውም አይነት ስሞች ሳይሆኑ ዝምድናን የሚያሳዩና ሰዋዊ ስሞች ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ስሞች
ሁልጊዜም የሚገኙት ከመስተዓምር ጋር በመጣመር ነው፡፡
ምሳሌ፡- ባል-እየ-ው ማለት ሲቻል ቤት-እየ-ው ማለት ግን አይቻልም፡፡
• በሌላ በኩል አንዳንድ ሰሞች ራሳቸውን በመድገምና አጣማሪ ድምፅ በማስገባት ስብስብን የሚያመለክቱ ስሞች
አሉ፡፡
ምሳሌ፡- ቅጠል ቅጠል-ኣ-ቅጠል
ጌጥ ጌጥ-ኣ-ጌጥ
ቅመም ቅመም-ኣ-ቅመም

54

• ስሞች ለጾታ ሲረቡ፡- ስሞች ለጾታ ቅርፃቸውን በከፊል
ይለዋውጣሉ፡፡ ጾታ ተፈጥሮአዊ ወይም ሰዋሰዋዊ ሊሆን
ይችላል፡፡ በተፈጥሮ የወንድነትና የሴትነት ምልክት
ያለባቸው ወንድና ሴት ተብለው የሚከፈሉ ሲሆን
ሰዋሰዋዊውን ጾታ አንስታይና ተባዕታይ ብለን እንጠራዋለን፡፡
ሰዋሰዋዊው ጾታ ከተፈጥሮአዊው ጾታ ጋር ሊያያዝም
ላይያያዝም ይችላል፡፡
• ተባዕታይ ስሞች ለተባዕታይነታቸው የተለየ ምልክት
የላቸውም፡፡ አንስተይ ስሞች ግን ለአንስታይነታቸው /-
ኢት/-ኣ የሚል ምዕላድ ያስከትላሉ፡፡ ይህ ምዕላድ የሚገኘው
ወይ በስሞቹ ላይ አልያም በግሶቹ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡
55

• ስሞች ለሙያ ሲረቡ፡- ስሞች ለሙያ ቅርፃቸውን በከፊል ይለዋውጣሉ፡፡ ሙያ አንድ ስም በገባበት
አረፍተ ነግር ውስጥ የሚኖረውን ሰዋሰዋዊ ተግባር የሚያመለክት ነው፡፡
• አንድ ስም በገባበት አረፍተ ነገር ውስጥ የባለቤትነት፣ በግሳዊ ሀረግ ውስጥ የተሳቢነት፣ በስማዊ ሀረግ
ውስጥ ደግሞ የዘርፍነት አገልግሎት/ተግባር አለው፡፡
• ስሞች ባለቤት ሆነው በሚገቡበት ጊዜ የአረፍተ ነገሩ ባለቤት መሆናቸውን የሚያሳይ የተለየ ምልክት
የላቸውም፡፡ ስለዚህም ለባለቤትነት ቅርፃቸውን አይቀይሩም ወይም አይረቡም ማለት ነው፡፡
• በግሳዊ ሀረግ ውስጥ በተሳቢነት የሚያገለግል ስም ተሳቢነቱን የሚያመለክት ምዕላድ (-ን)ን
ያስከትላል፡፡
• በዘርፍነት የሚያገለግል ስም የተለያዩ ምዕላዶችን ያስከትላል፡፡ ዘርፍነት ባለገንዘብነትን የሚያሳይ
ሰዋሰዋዊ ተግባር ነው፡፡ ዘርፍነት በሁለት መንገድ ሊገለፅ ይችላል - በአገናዛቢ አፀፋና በአገናዛቢ
መስተዓምር ወይም ሁለት ስሞችን በያዘ ሀረግ ውስጥ በመጀመሪያው ስም ላይ /የ-/ን በመጨመር፡፡
ምሳሌ፡- የአንተ ቤት ቤትህ
የእኔ ቤት ቤቴ
የእንቺ ቤት ቤትሽ
የተማሪዎቹ ልብስ ልብሳቸው
የልጁ ደብተር ደብተሩ

56

• ስሞች ለእምርነት ሲረቡ፡- አንድ ስም እምር ነው ሲባል
ከሌላው ተለይቶ በተናጋሪውና በአድማጩ ዘንድ የታወቀ ነው
ማለት ነው፡፡ ስሞችም ለዚህ ሰዋሰዋዊ ተግባር ቅርፃቸውን
በከፊል ይለዋውጣሉ፡፡ አንድ ስም እምር ሲሆን ካልታመረው
ስም የሚለይበት ምልክት (-ኡ) አለው፡፡
• የእምርነት አመልካች የሆነችው ምዕላድ (-ኡ)ና የጾታ አመልካች
የሆኑት (-ኢት እና -ኣ) በአንድነት በአንድ ስም ላይ ይገኛሉ፡፡
ምሳሌ፡- ተባዕታይ አንስታይ
በግ-ኡ በግ-ኢት-ኡ/በግ-ኡ-ኣ
እስ-ኡ እስ-ኡ-ኣ
ድመት-ኡ ድመት-ኢት-ኡ/ድመት-ኡ-ኣ
57
የቅፅል ርባታ
• ልክ እንደስሞች ሁሉ ቅፅሎችም ለተላያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት (ለቁጥር፣
ለጾታ፣ ለሙያ፣ ለእምርነት) ቅርፃቸውን በከፊል ይቀያይራሉ፡፡
• ቅፅሎች ለተለያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት ቅርፃቸውን ሲለዋውጡ የሚመሰረቱት
በሚገልፁአቸው ስሞች ላይ ነው፡፡ ቅርፃቸውም የሚወሰነው በሚገልፁት ስም
መሰረት ነው፡፡
• ቅፅሎች ቁጥር ሲረቡ፡- ልክ እንደስሞች ሁሉ ቅፅሎችም ለነጠላ ቁጥር የተለየ
ምልክት የላቸውም፡፡ ለብዙ ቁጥር ግን በተለያየ መንገድ ቅርፃቸውን
ይለዋውጣሉ፡፡ አንደኛው ልክ እንደስሞች ሁሉ የብዙ ቁጥር አመልካች የሆነውን
ምዕላድ (-ኦች) በማስከተል ሲሆን ሌላው ደግሞ የቃሉን ቅድመ መድረሻ እግር
በመድግም ነው፡፡ በሁለቱም መንገድ ቅርፃቸውን በሚለውጡ ጊዜ ከሚገልፁት
ስም ጋር በቁጥር ስምሙ መሆን አለባቸው፡፡ አለበለዚያ አረፍተ ነገሩ ተቀባይነት
ያጣል፡፡
ምሳሌ፡- ጥቁር ጥቁሮች/ጥቋቁር
ረዥም ረዥሞች/ረዣዥም

58

• ቅፅሎች ለሙያ ሲረቡ፡- ሰሞች ቅርፃቸውን የሚለውጡት ለተሳቢነትና ለዘርፍ ሙያ
ነው፡፡ ቅፅሎች ግን ቅርፃቸውን የሚቀይሩት ለተሳቢነት ሙያ ብቻ ነው፡፡
ምሳሌ፡- ጥቁሩን በግ ሸጠው፡፡
ትልቁን ልጅ ጠራው፡፡
• ቅፅሎች ለእምርነት ሲረቡ፡- ቅፅሎች ለእምርነት ቅርጻቸውን በከፊል ይቀይራሉ፡፡
የእምርነት ምልክቱ (-ኡ) በቅፅሉ ላይ የሚጨመር ከሆነ በስም ላይ ሊገባ አይችልም፡፡
ምሳሌ፡- ትልቁ ልጅ ማለት ሲቻል ትልቁ ልጁ ማለት ግን
አይቻልም፡፡
• ቅፅሎች ለጾታ ሲረቡ፡- ቅፅሎች ለፆታም ቅርፃቸውን በከፊል ይቀያይራሉ፡፡
ለተባዕታይ ጾታ የተለየ ምልክት አይመስዱም፡፡ ለአንስታይ ጾታ ግን (-ኢት/-ኣ)
የምትለውን አመልካች ምዕላድ ይወስዳሉ፡፡
ምሳሌ፡- ጎበዟ ልጅ ማለት ሲቻል ጎበዟ ልጅቷ ማለት ግን
አይቻልም፡፡

59
የግስ ርባታ
• ግሶች ለመደብ፣ ለፆታ፣ ለቁጥር፣ ለአንቀፅ፣ ለጊዜና፣ ለስልት የተለያዩ ቅጥያዎችን
በማስከተል ወይም በማስቀደም፣ የመካከል ወይም ቅደም መድረሻ እግራቸውን
በማጥበቅና ባለማጥበቅ አልያም ከተላያዩ ረዳት ግሶች ጋር በመጣመር ለተለያዩ
ሰዋሰዋዊ ተግባራት ቅርፃቸውን ይለዋውጣሉ (ይረባሉ)፡፡
• ግሶች ለመደብ ሲረቡ፡- መደብ በንግግር ወቅት የሰዎችን (የንግግሩን ተሳታፊዎች)
ሚና ያሳያል፡፡ አንደኛ መደብ ተናጋሪን፣ ሁለተኛ መደብ አድማጭን፣ ሶስተኛ
መደብ ደግሞ ታዛቢን ያመለክታሉ፡፡
ምሳሌ፡- እኔ/እኛ - ተናጋሪ
አንተ/አንቺ/እናንተ - አድማጭ
እሱ/እሱዋ/እነሱ - ታዛቢ
• መደብ በሁለት መልኩ ይከሰታል - በነፃ ምዕላድ (መደበኛ ተውላጠ ስሞች) እና
- በጥገኛ ምዕላድ (አፀፋ ተውላጠ ስሞች)
በሌላ በኩል ተጨማሪ ተውላጠ ስሞችም አሉ - እንትን - ተውላጠ ነገር
- እንትና - ለሰው

60

• አፀፋ ተውላጠ ስሞች የመደበኛ ተውላጠ ስሞች እጣፊ
(አምሳል) ናቸው፡፡ የሚከሰቱትም በስሞችና በግሶች ላይ ነው፡፡
በግሶች ላይ ሲከሰቱ በሁለት መልኩ ነው - በቀዳማይና በቦዝ
አንቀፅ ጊዜ ግሱን ተከትለው፣ በካልዓይ ግስ ጊዜ ግን ግሱን
ቀድመው ይገባሉ፡፡
ግስ (ሰበረ) ስም (ስብራት)
ካልዓይ ቀዳማይ ስብራት-የ
እ-ሰብር ሰበር-ኩ ስብራት-ህ
ት-ሰብር ሰበር-ክ ስብራት-ሽ
ይ-ሰብር ሰበር-ኧ ስብራት-ኣችሁ
እን-ሰብር ሰበር-ኡ ስብራት-ኣችን

61

• የመደብ፣ የፆታና የቁጥር ምዕላዶች ተለያይተው ሳይሆን ተዋህደው ገብተዋል፡፡
በአንድነትም የባለቤት አፀፋ ይባላሉ፡፡ ስሙ በገሃድ ባይከሰትም አፀፋዎቹ ይጠቁሙታል፡፡
- በግስ ላይ የሚገኙት የባለቤት አፀፋ ሲባሉ
- በስም ላይ የሚገኙት ደግሞ አገናዛቢ አፀፋ ይባላሉ
- የተሳቢ አፀፋዎቹ ከባለቤት አፀፋዎቹ ቀጥለው ይገባሉ
- ሁሉም አፀፋዎች የመደብ፣ የቁጥርና የፆታ አመልካች ቅጥያዎች ውሁድ ናቸው፡፡
• መስተዋድዳዊ (የመስተዋድድ) አፀፋ በግሱ ለሚገለፀው ተግባር ተጎጅነት ወይም
ተጠቃሚነትን ያሳያል፡፡
ተጎጂ - በ
ተጠቃሚ - ለ
ምሳሌ፡- በአዲሱ ቢላዋ በግ አረድ-ኧ-በት
የመስተዋድዳዊ ሀረጉ አፀፋ -ት ናት
- ለገነት ገንዘብ ወሰድ-ኧ-ላት
የመስተዋድዳዊ ሀረጉ አፀፋ -ኣት ናት

62

• ግሶች ለአነቀፅ ሲረቡ፡- በአንድ ግስ የሚገለፀው ድርጊት ማለቅ አላማለቁን (መፈፀም
አለመፈፀሙን) የሚያሳይ ሰዋሰዋዊ ተግባር አንቀፅ ይባላል፡፡
- የተፈፀመ ድርጊትን የሚያሳይ - የቀዳማይ አንቀፅ ግስ ሲባል
- ያለተፈፀመ ድርጊትን የሚያሳይ - የካልዓይ አንቀፅ ግስ ይባላል፡፡
• በአማርኛ ውስጥ የተለያዩ የአንቀፅ አይነቶች አሉ፡፡
• አቃጅ አንቀፅ፡- አንድ ድርጊት መታቀዱን ያሳያል
- /ል/ የሚል ምዕላድ አለው
- የሚመሰረተው በካልዓይ ግስ ነው
ምሳሌ፡- ካሳ እንጨት ል-ይ-ፈልጥ ነው
• ወጣኝ አንቀፅ፡- ከድርጊቱ ገላጭ አምድ ቀጥሎ ጀመር የሚልምዕላድ ያስገባል፡፡
- ጀመር የገላጭ አምዱ ረዳት ነው
- ግሱ የሚመሰረተው በካልዓይ ግስ ነው
- ድርጊቱ መጀመሩን ብቻ ያሳያል
ምሳሌ፡- ካሳ እንጨት ይ-ፈልጥ ጀመር

63

• ቀጣይ አንቀፅ፡- አንድ የተጀመረ ድርጊት ሳይቁዋረጥ መቀጠሉን ያሳያል፡፡
- እየ የሚል ምዕላድ ያስቀድማል
- የሚመሰረተው በቀዳማይ አንቀፅ ግስ ነው
- “ነው” የሚለው ረዳት ግስ ሲሆን አንቀፁ አየፈለጠ የሚለው
ነው፡፡
ምሳሌ፡- ካሳ እንጨት እየ-ፈለጠ ነው
• ጨራሽ አንቀፅ፡- ድርጊቱ ተፈፅሞ ማለቁን ያሳያል፡፡
- የሚገለፀው በቦዝ አንቀፅ ነው
- ቦዝ አንቀፅ ቀዳማይ ወይም ካልዓይ አንቀፅ ካልተከተለው በራሱ
አይቆምም (ጊዜን ብቻውን አይገልፅም)
- የጨራሽ አንቀፅ መሰረቱ ካልዓይ አንቀፅ ነው
ምሳሌ - ካሳ እንጨት ፈልጦ ሄደ

64
ግሶች ለጊዜ ሲረቡ
• አንድ ድርጊት የተፈፀምበትን (የሚፈፀምበትን) ጊዜ የሚያሳይ
ሰዋሰዋዊ ባህርይ ነው፡፡
• ስለድርጊቱ ንግግር ከሚደረግበት ጊዜ ተነስተን የሀላፊ፣ የአሁን፣
የትንቢት ልንል እንችላለን፡፡ ጊዜው የሚገለፀው በአንቀፆች
መሰረትነትና በረዳት ግሶች ወይም በጊዜ አመልካች ተውሳከ ግሶች
ነው፡፡
• ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ጊዜ ሁለት አይነት ነው- ሀላፊና ኢሀላፊ ፡፡
• ሀላፊ ጊዜ፡- ባለፈ ጊዜ የተፈፀመ ድርጊትን ያሳያል፡፡
- የዋህ፣ የቅርብና የሩቅ ተብሎ በሶስት ይከፈላል
- የዋህ ሀላፊ በቀዳማይ አንቀፅ ሲገለፅ
- የቅርብና የሩቅ ሀላፊዎች በካለዓይ አንቀፅና በረዳት ግሶች
ይገለፃሉ፡፡
65

• የዋህ ሀላፊ፡- ድርጊቱ ባለፈ ጊዜ ተፈፅሞ ማለቁን ብቻ ይጠቁማል እንጂ
ትክክለኛውን ጊዜ አያመለክትም፡፡
ምሳሌ፡- ሰበረ፣ ገደለች…
- ጊዜውን ለማሳየት የጊዜ ተውሳከ ግሶች ያስፈልጋሉ፡፡
ምሳሌ፡- ትናንት ሰበረ፣ ዛሬ ገደለች፣ አሁን ሰማች…
• የቅርብ ሀላፊ፡- ድርጊቱ ከተፈፀመ ብዙ ያልቆየ መሆኑን ያሳያል፡፡
- የሚገለፀው በጨራሽ አንቀፅ አምድና /-አል/ በሚል
ረዳት ነው፡፡
ምሳሌ፡- ገድል-ኦ-አል፣ በልት-ኣ-ኣለች
• የሩቅ ሀላፊ፡- አንድ ድርጊት ከተፈፀመ መቆየቱን ያሳያል፡፡
- ነበር ከሚላው ረዳት ግስ ጋር ይጣመራል፡፡
ምሳሌ፡- ሰብር-ኦ ነበር፣ ሰምት-ኣ ነበር

66

• ኢሀላፊ ጊዜ፡- ገና ያልተፈፀመ ድርጊትን ያሳያል፡፡
- የሚመሰረተው በካልዓይ አንቀፅ ላይ /-ኣል/
የሚል ረዳት ግስ በመቀጠል ነው፡፡
ምሳሌ፡- ይ-ሰብር-ኣል
ይ-መጥ-ኣል
ይ-ሰር-ኣል
• የማይቁዋረጥጊዜ፡- ድርጊቱ ተጀምሮ በመከናወን ላይ ያለና ገና ያልተፈፀመ
መሆኑን ያመለክታል፡፡
• እየ- የሚል ምዕላድ በግሱ ላይ በማስቀደምና ከተለያዩ ግሶችና ረዳት ግሶች ጋር
በመጣመር ጊዜውን ያመለክታል፡፡
ምሳሌ፡- እየ-አነበበ -ነው - (የአሁን ጊዜ)
- ነበር - (የሀላፊ ጊዜ)
-ይጠብቅሀል - (የትንቢት ጊዜ)

67
ግሶች ለስልት ሲረቡ
• ከአረፍተ ነገር ወይም ከቁዋንቁዋ አጠቃቀም ጋር የተገናዘበ
ሰዋሰዋዊ ባህርይ ነው፡፡
• አረፍተ ነገሩ ለመጠየቅ፣ ለትዕዛዝ፣ ለመቃወም፣ ወዘተ
ሊሆን ይችላል፡፡
• እነዚህን ለመግለፅ የተለያዩ መዋቅሮች ያስፈልጋሉ፡፡
• የምንገልፅበት ስረዓትም ስልት ይባላል፡፡
• አረፍተ ነገሮች ከአገልግሎታቸው አንፃር ሀተታዊ፣
ትዕዛዛዊ፣ መጠይቃዊ፣ አሉታዊ፣ ወዘተ ተብለው ይጠራሉ፡፡
• ልዩነቱን የሚፈጥረው ግሱ ነው፡፡
• ልዩነቱም የአምድ፣ የቅጣይ፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡
68
የቡድን ስራ
1.ስሞችና ቅፅሎች ለተለያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት ሲረቡ በመካከላቸው ያለውን አንድነትና
ልዩነት በምሳሌ አብራሩ፡፡ (ሁሉም ሰዋሰዋዊ ተግባራት ትኩረት ይሰጣቸው፡፡)
2.የመደብ መከሰቻ መንገዶችን አብራርታችሁ ለያንዳንዳቸው የተለያዩ ምሳሌዎችን ስጡ፡፡
3.አፀፋዎች በየትኛው የቃል ክፍል ላይ ሊታዩ ይችላሉ፣ ስያሜዎቻቸው ምን ምን
እንደሚባሉ አብራርታችሁ ለያንዳንዳቸው ምሳሌዎችን ስጡ፡፡
4.ካሳ ወደጎንደር ሊሄድ ነው፡፡
ካሳ በነገሩ ይስቅ ጀመር፡፡
ካሳ ከአዲስ አበባ እየመጣ ነው፡፡
ካሳ አዋሳ ደርሶ መጣ፡፡
በነዚህ አረፍተ ነገሮች ውስጥ ያሉትን አንቀፆች በመጥቀስ ማብራሪያዎችን ስጡ፡፡
5.ገደለ፣መጣ እነዚህን ግሶች ለሁሉም የጊዜ አይነቶች ሲረቡ በሁሉም መደብ፣ፆታና ቁጥር
አሳዩ፡፡

69
የክፍል ስራ
1. እንደታመምሽ ነገረኝ፡፡ በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ ያሉትን
አፀፋዎች ለይታችሁ አመልክቱ፡፡
2. ልጁ ለአስቴር አንድ ትልቅ መፅሀፍ ቶሎ ሰጣት፡፡ በዚህ አረፍተ
ነገር ውስጥ ያሉትን ቃላት በየቃል ክፍላቸው መድቡ፡፡
3. በሚከተሉት ቃላት ውስጥ ያሉትን የርባታና የምስረታ
ምዕላዶች ለይታችሁ አሳዩ ልጅነታችን፣ ተራራማው፣
ኢትዮጵያዊው፣ ልባሞች፡፡
4. ግ-ድ-ል ከሚለው ስር ላይ የተለያዩ አምዶችን መስርቱ፡፡
5. በውልድ ስምና በውልድ ቅፅል ውስጥ የሚካተቱ ሁለት ሁለት
ምሳሌዎችን ስጡ፡፡

70
ቤት ወሰድ የቡድን ስራ
1. የስም ምስረታ ቡድን 2፣ 6፣ 7
2. የቅፅል ምስረታ ቡድን 3፣ 4፣ 5
3. የግስ ምስረታ ቡድን 1፣ 8

71
የቃላት ምስረታ ስረዓት
• በርባታ ጊዜ ሶስቱ የቁዋነቁዋው ዋና ዋና የቃል ክፍሎች ማለትም ስም፣ ግስና ቅፅል ለተለያዩ ሰዋሰዋዊ ተግባራት
የተለያዩ ቅጥያዎችን በማስቀደም ወይም በማስከተል፣ ራሳቸውን በሙሉ ወይም በከፊል በመድገም ቅርፃቸውን
ሲለዋውጡ (ሲረቡ) ተመልክተናል፡፡
• በዚህ ክፍል ደግሞ በዋና ዋና ቃላት ውስጥ የሚመደቡ የቃላት ክፍሎች እንዴት አዳዲስ ቃላትን እንደሚመሰርቱና
የአመሰራረት ስረዓታቸው ምን እንደሚመስል የምንመለከትበት ነው፡፡
• በቁዋንቁዋው ውስጥ ያሉ ቃላት በአጠቃላይ ውልድና ነባር ይባላሉ፡፡
• ነባሮቹ ቃላት ስነድምፀ ልሳናዊ ምዕላድ ሲባሉ ውልዶቹ ስነምዕላዳዊ ቃላት ይባላሉ፡፡
• በቁዋንቁዋው ውስጥ ያሉ የይዘትቃላት የተለያዩ የአመሰራረት ስረዓትን በመከተል አዳዲስ ቃላት ይመሰረታሉ፡፡

የስም ምሰረታ
• ስሞች ነባርና ውልድ በመባል በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ፡፡
• ውልድ ስሞች፡- ከስም፣ ከቅፅልና ከግስ ሊመሰረቱ ይችላሉ፡፡
- ነባር ስሞች /-ነት/ የሚል መስራች ቅጥያ በማስከተል ረቂቅ ስሞችን
ይመሰርታሉ፡፡
ምሳሌ፡- ልጅነት፣ ሴትነት፣ ሰውነት
- ከቅፅል የሚመሰረቱ ረቂቅ ውልድ ስሞች
ቅፅሎች ልክ እንደስሞች ሁሉ /-ነት/ የሚለውን መስራች ቅጥያ በማስከተል ረቂቅ ስሞችን
ይመሰርታሉ፡፡
ምሳሌ፡- ደግነት፣ ጥሩነት፣ ብልህነት፣ ቸርነት

72

• ረቂቅ ስሞች ከስምና ከቅፅል /-ነት/ን በምጨምር ይመሰረታሉ፡፡
• ረቂቅ ስሞች ከውልድ ስሞች፣ ከነፃ ወይም እስር ቅፅላዊ አምድ ላይ /-ኧት/ በመጨመር
የመሰረታሉ፡፡
ስም ውልድ ስም እስር አምድ ውልድ ስም
ክብር ክብረት ድረስ- ድርሰት
ሹም ሹመት ቅብጥ- ቅብጠት
ቅፅል ክስር- ክስረት
ብስል ብስለት ፍጥር- ፍጥረት
ቅርብ ቅርበት ውፍር- ውፍረት
ብልጥ ብልጠት ውርድ- ውርደት
እውቅ እውቀት ግድፍ- ግድፈት

73

• ስምና ቅፅል አንድ አይነት የአምድ አመሰራረት ስለሚከተሉ አንዱን ከሌላው በቀላሉ ለመለየት ያዳግታል፡፡
ቅርፅ › ቅእርፅ ስም የአምድ
ብልጥ › ብእልጥ ቅፅል አመሰራረታቸው
ተመሳሳይ ነው
• ረቂቅ ስሞች ባህሪን ስለሚያመለክቱ የብዛት ምልክት የላቸውም ስለዚህ ከተቆጣሪ ስሞች ይለያሉ፡፡
ልጅ - ኦች ልጆች › ትክክል ሲሁሀን
ብልጠት- ኦች ብልጠቶች › ግን ስህተት ነው
• በወል ስሞችና የባህሪ ቅፅሎች ላይ /-ኦ/ን በመጨመር መጠሪያ ስሞች ይመሰረታሉ፡፡
ስም ውልድ ስም (መጠሪያ) የባህሪ ስሞች ናቸው
ውሻ ውሾ
ሌባ ሌቦ
ንፍጥ ንፍጦ
ቅፅል
ቂል ቂሎ
ሞኝ ሞኞ
ብልጥ ብልጦ

74

• የቁጥር አመልካች ምዕላድ የሆነውን /-ኦች/ አይወስዱም ይልቁንም /እነ-/ን ይወስዳሉ፡፡
• የባህሪ ስሞች በሰዋሰዋዊ ባህሪያቸው እንደሌሎቹ ስሞች ባለቤት ወይም ተሳቢ በመሆን ያገለግላሉ፡፡
ምሳሌ - ሌቦ መጣ፡፡
- ሌቦን አየሁት፡፡
• በአማርኛ የግሶች እንዲሁም የተወሰኑ ቅፅሎችና ስሞች መሰረት ተናባቢ ድምፆች ናቸው፡፡ ተናባቢዎቹ ከአንድ እስከ ስድስት
ሊደርሱ ይችላሉ፡፡
• ተናባቢዎቹ በአንድነት ስር ሲባሉ በተናጠል ደግሞ እግር ይባላሉ፡፡
• ስሩ ብቻውን አጠቃላይ የሆነ ትርጉምና ቅርፅ አለው፡፡
• ስር አምድ ነው
ብ-ል-ጥ ከመብለጥ ጋር የተያያዘ ትርጉም አለው፡፡
• ውልድ ስሞች ከግስ ስር ወይም ከአምድ ሊመሰረቱ ይችላሉ
- ከስር የሚመሰረቱት በተናባቢዎቹ መካከል አናባቢዎችን በማስገባት ሲሆን
- ከአምድ የሚመሰረቱት ደግሞ የተለያዩ ቅጥያዎችን በመቀጠል (በማስቀደም/ በማስከተል) ወይም
የስሩን ተናባቢ በመድገም ነው፡፡
ስር ውልድ ስም
ል-ብ-ስ ልእብስ
ጥ-ቅ-ም ጥእቅም
ም-ር-ት ምእርት
ው-ር-ስ ውእርስ

75

• በአምድ ላይ /-ኦሽ/ን ወይም /-ንንኣ/ን በመጨመር
የሚመሰረቱ ውልድ ስሞች
አምድ ውልድ ስም
ቅልም- ቅልሞሽ
ስርቅ- ስርቆሽ
ግርድ- ግርዶሽ
ጥብቅ- ጥብቅና
ድርቅ- ድርቅና
ግብር- ግብርና
ትህት- ትህትና
76

• -ኦሽ በነፃ ምዕላድ ላይም ሊጨመር ይችላል፡፡
ቅብብል › ቅብብሎሽ
ድብብቅ › ድብብቆሽ
ድግግም › ድግግሞሽ
• በ/-ንንኣ/ የሚመሰረቱት ስሞች ሙያን/ሁኔታን ያሳያሉ፡፡
• በአምድ ላይ /-ኣት/ በመጨመር የሚመሰረቱ ውልድ ስሞች
አምድ ውልድ ስም
ስብር- ስብራት
ሽልም- ሽልማት
ዕርም- ዕርማት
77

• በእስር አምድ ላይ /-ኦት/ ወይም /-ኦታ/ በመጨመር የሚገኙ ውልድ ስሞች
አምድ ውልድ ስም
ፍጅ ፍጆታ
ችል ችሎታ
ስም ስሞታ
ብስ- ብሶት
ቅንጥ- ቅንጦት
ስርቅ- ስርቆት
• በተጨማሪም /-ኣ/ን በቅድመ መድረሻ /-ኤ/ን በመድረሻ እግር ላይ በመቀጠል የሚመሰረቱ ውልድ ስሞች
አሉ፡፡
ስር ውልድ ስም
ድ-ክ-ም ድካም
ጥ-ግ-ብ ጥጋብ
ዝ-ን-ብ ዝናብ የውጤት ስሞች ናቸው
ቅ-ድድ-ስ ቅዳሴ
ው-ድድ-ስ ውዳሴ
ት-ክክ-ዝ ትካዜ

78

• በእስር አምድ ላይ /-ኤት/ በመጨመር የሚመሰረቱ
ውጥ- ውጤት
ስል- ስሌት
ቅል- ቅሌት
• /-ኢት/ የሚለውን ምዕላድ በመጨመር የሚመሰረቱ
ድርግ- ድርጊት
ግፍ- ግፊት
ዕልቅ- እልቂት
• /-ኢያ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
ግፍ- ግፊያ
ዝርፍ- ዝርፊያ
ሽም- ሽሚያ
ፍልም- ፍልሚያ
ልፍ- ልፊያ

79

• /-ኣ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
ሽፍት- ሽፍታ
ጭፍር- ጭፍራ
ብስን- ብስና
• /-ኧ/ን በመተሻ እግር ላይ በመጨመር የሚመሰረቱ
ስ-ር-ግ ሰርግ
ም-ል-ስ መልስ
ብ-ል-ግ በልግ

80

• /-ኧኛ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
ሰርግ ሰርገኛ
ሰልፍ ሰልፈኛ የሙያተኛ ስሞች
ፈረስ ፈረሰኛ
ጥበብ ጥበበኛ
• /ኧ/ን በመነሻና በቅድመ መድረሻ እግሮች ላይ በመጨመር የሚመሰረቱ
ቅ-ል-ም ቀለም
ቅ-ር-ጥ ቀረጥ
ም-ድ-ብ መደብ
ን-ግ-ር ነገር
• ይህ አናባቢ የሚመሰርተው ነፃ ምዕላዶችን ብቻ ሳይሆን እስር
አምዶችንም ይመሰርታል፡፡

81

• በ/ኧ/ አማካኝነት በተመሰረተ እስር አምድ ላይ /-ኣ/ን በመጨመር የሚመሰረቱ
ውልድ ስሞች
ሰበር- ሰበራ
ፈተን- ፈተና
ዘረፍ- ዘረፋ
• በአምድ ላይ /ኢ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
ሰባክ- ሰባኪ
ጠራግ- ጠራጊ አድራጊ ስሞች
ወላድ- ወላጅ
ጥራግ- ጥራጊ
ውዳቅ- ውዳቂ ተደራጊ ስሞች
ልቃም- ልቃሚ

82

• /መ-/ን በመጨመር የሚመሰረቱ
-ስደብ መስደብ
-ስበር መስበር አርዕሰት (የድርጊት ስሞች)
-ጥረግ መጥረግ
• አርዕስታዊ ስሞች ላይ /-ኢያ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
መጥረግ- መጥረጊያ
መስበር- መስበሪያ
መፍለጥ- መፍለጫ
• በአምድ መነሻ ላይ /-ኣ/ን በመጨመርና ቅድመ መድረሻ እግሩን በመድገም
የሚመሰረቱ
-ሰበር አሰባበር
-ነገር አነጋገር ሳቢ ዘር (አደራረግን ያሳያሉ)
-ለበስ አለባበስ

83

የቅፅል ምስረታ
ቅፅሎችም እንደሰሞች ሁሉ ነባርና ውልድ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡
• ነባር የሚባሉት ፎኒማዊ የሆኑት እንደ ብልህ፣ ትሁት፣ ደግ፣ የዋህ፣ ያሉት ሲሆኑ
• ውልድ የሚባሉት ደግሞ ምዕላዳዊ የሆኑት ሀይለኛ፣ ክፉ፣ ቂመኛ፣ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
• ነባሮቹ ቅፅሎች በቁጥር በጣም አነስተኛ ናቸው፡፡
• በቁዋንቁዋው ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ቅፅሎች ውልድ ናቸው፡፡
• የሚወለዱትም ከስም፣ ከስር፣ ወይም ከአምድ ነው፡፡
• ከስም የሚመሰረቱ ቅፅሎች
ስም ውልድ ቅፅሎች
ሀይል ሀይለኛ
ቂም ቂመኛ
ወረት ወረተኛ
• መስራች ምዕላዱ /-ኧኛ/ ነው፡፡
• በስም ላይ /-ኣም/ የሚለውን ምዕላድ በመጨመር የሚመሰረቱ
ስም ውልድ ቅፅል
ሆድ ሆዳም
ሀብት ሀብታም የብዛት/የክምችት ቅፅሎች
ጥፍር ጥፍራም

84

• /-ኣማ/ የሚለውን መስራች ምዕላድ በመጨመር የሚመሰረቱ
ስም ውልድ ቅፅል
ተራራ ተራራማ
አሸዋ አሸዋማ
እሾህ እሾሀማ
ድንጋይ ድንጋያማ
አይን አይናማ
ወርቅ ወርቃማ
• /-ኣዊ/ የሚለውን መስራች ምዕላድ በመጨመር የሚመሰረቱ
ስም ውልድ ቅፅል
ወገን ወገናዊ - የወገን ቅፅል ሊባሉ ይችላሉ
ዘመን ዘመናዊ - በአገባባቸው ከስም ጋር ስለሚመሳሰሉ
ሀገር ሀገራዊ በስም ውስጥ ሊመደቡ ይችላሉ
ምሳሌ፡- ሰዎቹ ጀግኖች ናቸው
ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች ናቸው
ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያዊያን ያሉ ቃላት ቅፅልን አስቀድመው ሊገቡ ይችላሉ
ምሳሌ፡- ጅግኖች ኢትዮጵያዊያን
አንድ ቅፅል ቅፅል ሊባል የሚችለው በጣምን ሲወስድ ነው ነገር ግን
- በጣም መንፈሳዊ ተማሪ ማለት ሲቻል
- በጣም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ማለት ግን አይቻልም

85

• /-ኣዊ/ ስምንም ቅፅልንም ይመሰርታል
ውልድ ስም ውልድ ቅፅል
ኢትዮጵያዊ ወገናዊ
ዘመናዊ
ሀገራዊ
መንፈሳዊ
ፍትሀዊ
ወቅታዊ
• እስር አምድ ላይ /-ኣ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
አምድ ውልድ ቅፅል
ጠማም- ጠማማ
መላጥ- መላጣ የአይነት ቅፅሎች
ቀርፋፍ- ቀርፋፋ

86

• እስር አምድ ላይ /-ኢታ/ በመጨመር የሚመሰረቱ
አምድ ውልድ ቅፅል
ከስ- ከሲታ
ሳቅ- ሳቂታ
አስጠል- አስጠሊታ
• ከስር የሚመሰረቱ ውልድ ቅፅሎች መስራች ቅጥያ /-ኧ/
ስር ቅፅል
ስ-ን-ፍ ሰነፍ
ድ-ን-ዝ ደነዝ
ድ-ር-ቅ ደረቅ የባህርይ ቅፅሎች
ው-ድ-ል ወደል

87

• በስሮች ውስጥ /ኧ/ንና /ኢ/ን በመጨመርና ቅድመ
መድረሻ እግርን በመድገም የሚመሰረቱ ውልድ
ቅፅሎች
ስር ውልድ ቅፅል
ር-ዝዝ-ም ረዥም
ቅ-ጥጥ-ን ቀጭን
ጥ-ይይ-ም ጠይም የአይነት ቅፅል
ህ-ጥጥ-ር አጭር

88

• በስር ቅድመ መድረሻ እግር ላይ /-ኡ/ን በመጨመር
ስር ውልድ ቅፅል
ክ-ብ-ር ክቡር
ን-ፅ-ህ ንፁህ
ጥ-ቅ-ር ጥቁር
ክ-ፍ ክፉ
ብ-ር-ት ብርቱ
• በስሮቹ መካከል /ኧ/ንና /ኣ/ን በቅደም ተከተል በማስገባትና ቅድመ መድረሻ እግሩን በማጥበቅ
የሚመሰረቱ
ስር ውልድ ቅፅል
ክ-ብብ-ድ ከባድ
ቅ-ልል-ል ቀላል
ድ-ቅቅ-ቅ ደቃቅ
ድ-ምም-ቅ ደማቅ
ው-ልል-ድ ወላድ
ድ-ፍፍ-ር ደፋር

89
በጥመራ የሚመሰረቱ ቅፅሎች
• በአጣማሪ የሚመሰረቱ
ስም ቅፅል ውልድ ቅፅል
አይን ደረቅ አይነ ደረቅ
ልብ ቅን ልበ ቅን
ሆድ ሰፊ ሆደ ሰፊ
እግር ቀላል እግረ ቀላል
• ያለ አጣማሪ የሚመሰረቱ
ሹል አፍ ሹል አፍ
አጉራ ዘለል አጉራ ዘለል
90
የግስ ምስረታ
• ስምና ቅፅል የመሳሰሉት የቃል ክፍሎች ከሌሎች የቃል ክፍሎች ሊመሰረቱ ይችላሉ ግስ ግን የሚመሰረተው ከራሱ የቃል ክፍል ብቻ እንጂ
እንደሌሎቹ የቃል ክፍሎች ከሌሎች ሊመሰረት አይችልም፡፡
• ግስ በአብዛኛው የሚመሰረተው ከስር ላይ በአናባቢዎች ከሚመሰረቱ አሃዶች ነው፡፡
• አሃዶቹም አዕማድ በመባል ይታወቃሉ፡፡
• ከየስሩ ሊመሰረቱ የሚችሉት አዕማድ ሰባት ናቸው፡፡፡
አድራጊ ተደራጊ
አዳራጊ ተዳራጊ
አደራራጊ ተደራራጊ
አስደራጊ
• የድርጊትን መደጋገም/መዘውተር የሚያሳይ አምድ ደራራጊ አምድ ይባላል፡፡
• መዳረግን የሚያሳየው ደግሞ ደራጊ ይባላል፡፡
ደራጊ
አድራጊ ተደራጊ
አስደራጊ
ዳራጊ
አዳራጊ (ሀ) ተዳራጊ
አዳራጊ (ለ)
ደራራጊ
አደራራጊ (ሀ) ተደራራጊ
አደራራጊ (ለ)

91

• ደራጊ አምድ፡- ያለምንም መስራች ምዕላድ ቅጥያ ይመሰረታል፡፡
- በስሩ ላይ በቀጥታ /ኧ/ን በመጨመር ይመሰረታል፡፡
- የአናባቢው ቁጥር አንደተናባቢው ቁጥር ይለያያል (ባለሶስት ተናባቢው ሁለት አናባቢ
ሲኖረው ባለአራት ተናባቢው ደግሞ ሶስት አናባቢ ይናነረዋል…)፡፡
ስር ቀዳማይ አምድ
ስ-ብ-ር ሰበር-
ል-ም-ን ለመን-
ፍ-ል-ግ ፈለግ-
ድ-ም-ር ደመር-
• አድራጊ አምድ፡- አንድ ሰው አንድን ድርጊት ራሱ በሌላ ነገር ላይ መፈፀሙን ያሳያል፡፡
- አመሰራረቱ በደራጊ አምድ ላይ /አ-/ን በመጨመር ነው፡፡
ደራጊ አድራጊ
ቀመስ- አቀመስ-
በል- አበል-
ለበስ- አለበስ-
ወረድ- አወረድ-
ወጥ- አወጥ-

92

• አስደራጊ አምድ፡- አንድ ሰው አንድን ድርጊት በሌላው
ማስፈፀሙን ያሳያል፡፡
- የሚመሰረተው በደራጊ/አድራጊ አምድ
ላይ /አስ-/ በመጨመር ነው
ደራጊ አስደራጊ
ዘረፍ- አስዘረፍ-
ገረፍ- አስገረፍ-
ቆረጥ- አስቆረጥ-
ገዝ- አስገዝ-
ለክ- አስለክ-
93

• ተደራጊ አምድ፡- አንድ ድርጊት በአንድ ነገር ላይ መፈፀሙን
ያሳያል፡፡
- በደራጊ አምድ መነሻ ላይ /ተ-/ን
በመጨመር ይመሰረታል፡፡
ደራጊ ተደራጊ
ገደል- ተገደል-
በል- ተበል-
ጠጥ- ተጠጥ-
ጀመር- ተጀመር-
ፈረም- ተፈረም-
ቀመስ- ተቀመስ-
94

• ዳራጊ አምድ፡- ለሌሎች አዕማድ ምስረታ መሰረት የሚሆን እስር
አምድ ነው፡፡
ስር አምድ
ስ-ብ-ር -ሳበር
ፍ-ል-ግ -ፋለግ
ግ-ድ-ል -ጋደል
ፍ-ል-ም -ፋለም
• በስሩ ውስጥ /ኣ/ንና /ኧ/ን በቅደምተከተል በማስገባትና ቅድመ
መድረሻ እግሩን በመድገም ይመሰረታል፡፡
• ትርጉማቸውም ሆነ የቃል ክፍላቸው ግልፅ የሚሆነው በመነሻው
ላይ አዳራጊ አምድ ሲገባ ነው፡፡
95

• አዳራጊ አምድ (ሀ)፡- በአንድ ድርጊት ላይ መሳተፍን ወይም አድራጊውን ማገዝን ያመለክታል፡፡
የሚመሰረተው ከዳራጊ አምድ ነው፡፡
ዳራጊ አዳራጊ
-ሳበር- አሳበር-
-ፋለግ- አፋለግ-
-ዳረስ- አዳረስ-
-ላቀስ- አላቀስ-
-ጋደል- አጋደል-
• ተዳራጊ አምድ፡- አንድ ነገር/ሰው ከሌላ ነገር/ሰው ጋር የሆነ ነገር መዳረግን ያሳያል፡፡ የሚመሰረተው
በዳራጊ አምድ ላይ /ተ/ን በመጨመር ነው፡፡
ዳራጊ ተዳራጊ
-ጋደል- ተጋደል-
-ቃለድ- ተቃለድ-
-ካፈል- ተካፈል-
-ቃረን- ተቃረን-
-ፋለም- ተፋለም-
-ዋግ- ተዋግ-

96

• አዳራጊ አምድ (ለ)፡- ሁለት ሰዎች የሆነ ነገር እንዲደራረጉ ምክንያት የሚሆን ነው፡፡
ተዳራጊ አዳራጊ
ተጋደል- አጋደል-
ተፋለም- አፋለም-
ተጣል- አጣል-
በዚህ አምድ ላይ /ኧ/ ትጠፋለች ሁለት ተናባቢ ስለሚፈቀድ /ት/ ደግሞ ከመጀመሪያው ድምፅ ጋር
ትመሳሰላለች፡፡
• ደራራጊ አምድ፡-አንድ ተደጋግሞ የሚፈፀም ድርጊትን ያሳያል፡፡
ስር ደራራጊ
ስ-ብ-ር ሰባበር-
ቅ-ል-ድ ቀላለድ-
ስ-ድ-ብ ሰዳደብ-
• አደራራጊ አምድ (ሀ)፡- ደጋግሞ ተባባሪ መሆንን ያሳያል፡፡ /አ/ የሚለውን ምዕላድ በደራራጊ አምድ ላይ
በማስገባት ይመሰረታል፡፡
ደራራጊ አደራራጊ
ገዳደል- አገዳደል-
ሰባበር- አሰባበር-
ፈላለጥ- አፈላለጥ-

97

• ተደራራጊ አምድ፡- በደራራጊ አምድ ላይ /ተ-/ን በመጨመር ይመሰረታል፡፡
ሰዎች ርስበርስ የሆነ ነገር መደራረጋቸውን ያሳያል፡፡
ደራራጊ ተደራራጊ
ገዳደል- ተገዳደል-
ፈራረም- ተፈራረም-
ሰዳደብ- ተሰዳደብ-
ፈላለግ- ተፈላለግ-
• አደራራጊ አምድ (ለ)፡- በደራራጊ አመድ ላይ /አ-/ን በመጨመር ይመሰረታል፡፡
ከሁለት የበለጡ ሰዎች አንድ ነገር እንዲደራረጉ ማድረግን ያሳያል፡፡
ደራራጊ ተደራራጊ አደራራጊ
ገዳደል- ተገዳደል- አገዳደል-
ደባደብ- ተደባደብ- አደባበደብ-
ቀዳደም- ተቀዳደም- አቀዳደም-

98
የባህርይ አምድ
• ሆነ ተብሎ ወይም የተለመደ ባህሪ በመሆኑ
የሚፈፀም ድርጊትን የሚያሳይ አምድ ነው፡፡
• በአመሰራረቱ ወይም በቅርፁ ከተዳራጊ አምድ ጋር
ተመሳሳይ ሲሆኑ በትርጉም ግን የተለያዩ ናቸው፡፡
• የሚመሰረቱት በዳራጊ አምድ ላይ ነው፡፡
ዳራጊ የባህርይ አምድ
-ሳደብ- ተሳደብ-
-ናገር- ተናገር-
-ተናከስ- ተናከስ-
99
አፀፋዊ አምድ
• ድርጊትን ሳይሆን ሁኔታን ያሳያል፡፡
• በነፃ ወይም በእስር አምድ ላይ /ተ-/ የምትል ምዕላድ
በመጨመር ይመሰረታሉ፡፡
ቀየም- ተቀየም-
ደሰት- ተደሰት-
ጨነቅ- ተጨነቅ-

100
የአደራረግ አምድ
• አንድ ድርጊት እንዴት እንደተፈፀመ ያሳያል፡፡
• ድርጊቱ በሀይል/በቀስታ ወይም በጥንቃቄ /በዘፈቀደ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል፡፡
• አጠንካሪ አዕማድ፡- በሀይል/በድንገት የተፈፀመ ድርጊትን ያሳያሉ፡፡
ስር አጠንካሪ
ስ-ብ-ር ስብር-
ክ-ፍ-ት ክፍት-
ም-ል-ስ ምልስ-
ው-ር-ድ ውርድ-
ዝ-ግ ዝግት-
ብ-ል ብልት-
ግ-ፍ ግፍት-
ው-ጥ ውጥት-
• እንደግስ የሚቆጠሩት ከ “አለ” ወይም “አደረገ” ጋር ሲቀናጁ ነው፡፡

101

• አለሳላሽ አዕማድ፡- ረጋና ቀስ ብሎ የተፈፀመ ድርጊትን ያሳያሉ፡፡
ስር አለሳላሽ
ስ-ብ-ር ሰብር-
ክ-ፍ-ት ከፍት-
ው-ር-ድ ወረድ-
ም-ል-ስ መለስ-
• ግስ የሚሆነው ጥምሩ ነው፡፡
ሰበር አደረገ
ከፈት አደረገ
• የአደራረግ አዕማድ በተግባራቸው ግስም ተውሳከ ግስም ናቸው፡፡
• በግስነታቸው ድርጊትን በተውሳከ ግስነታቸው ደግሞ አደራረግን ያሳያሉ፡፡

102
የጥምር ግሶች አመሰራረት
• ጥምር ግሶች የሚመሰረቱት አለ ወይም አደረገ ከሚሉት ግሶች ጋር በመጣመር ነው፡፡
• አደራረግን የሚያሳዩት ግሶች በዚህ ውስጥ የሚመደቡ ውልድ ግሶች ናቸው፡፡
• ግሶቹ ከስሞች ጋርም አየተጣመሩ ጥምር ግስን ይመሰርታሉ፡፡
ፀጥ አለ ፀጥ አደረገ
ከፍ አለ ከፍ አደረገ
ቀና አለ ቀና አደረገ
• አምዱ በከፊል በመደጋገም የነገሩን መደጋገም የሚያለክቱ ጥምር ግሶችም ይመሰረታሉ፡፡
• ተቃራኒ ቃላትንም በማጣመር የሚመሰረቱ አሉ፡፡
• እነዚህ ጥምር ግሶች ከአለና አደረገ ጋር ሲጣመሩ የሚመሰረቱት ጥምር ግሶች ውስብስብ ጥምር ግሶች ይባላሉ፡፡
ብቅ ጥልቅ አለ ያዝ ለቀቅ አደረ
ሳብ ረገብ አለ ወጣ ገባ አደረ
ፈራ ተባ አለ
• ደጋጋሚ የሆኑ ጥምር ግሶች ከአለና አደረገ ጋር ሲጣመሩ የሚመሰረቱትም ጥምር ግስ እንዲሁ ውስብስብ ጥምር
ግስ ይባላል፡፡
ያዝ ያዝ አደረገ
ሰበር ሰበር አደረገ
ስብር ስብር አለ

103
ውልድ ተውሳከ ግሶች
• በቁዋንቁዋው ውስጥ ያሉት ተውሳከ ግሶች ቁጥራቸው ብዙ አይደለም፡፡
• ተግባሩ የሚገለጸው በመስተዋድዳዊ ሀረጎች፣ በጥገኛ አረፍተ ነገሮች
ወይም በአደራረግ አዕምድ ነው፡፡
• ነባር ተውሳከ ግሶች ገና፣ ቶሎ፣ መቼ…ነባር የጊዜ ተውሳከ ግሶች ይባላሉ፡፡
• ውልድ ተውሳከ ግሶች የሚባሉት ደግሞ
ቅፅል ተውሳከ ግስ
ክፉ ክፉኛ
ጅል ጅልኛ
ግም ግምኛ
ምን ምንኛ
• በተጨማሪ እንደ የሁዋሊት፣ የምብርክክ፣ የጎድን፣ የጎሪጥ፣ የመሳሰሉት
በስሞች ላይ /የ-/ን በመጨመር ይመሰረታሉ፡፡

104
በጥመራ የሚመሰረቱ ተውሳከ ግሶች
• በቁዋንቁዋው ውስጥ ያሉ ተውሳከ ግሶች በቁጥር አነስተኛ
ቢሆኑም የተወሰኑ በጥመራ የሚመሰረቱ ተውሳከ ግሶችም አሉ፡፡
• ጥምር ተውሳከ ግሶቹ የሚመሰረቱት ቃሎችን በመደጋገምና
አጣማሪ በመጠቀም ነው፡፡
• በመደጋገም የሚመሰረቱ
ትንሽ ትንሽ
ጥቂት ጥቂት
ቶሎ ቶሎ
• በጥመራ የሚመሰረቱ
ቀስበቀስ
እጅበእጅ
105

You might also like