You are on page 1of 8

ክሩዝ ትምህርት ቤት አዲስአበባ

CRUISE S CHOOL, ADDIS ABABA

የ 5 ኛ ክፍል የሙዚቃ ትምህርት


ምዕራፍ አንድ
መሠረታዊ የሙዚቃ ትርጉምና ጠቀሜታ
1. ሙዚቃ ምንድነው?
ሙዚቃ የሰው ልጅ የማድመጥ ስሜትን መማረክ የሚችል የድምፅ
ቅንብር ነው። የሙዚቃ ድምፆች ማራኪ እንዲሆኑ በሥርዓት የመደርደርና
የማቀናጀት ጥበብ ውጤት ነው ማለትም ይቻላል።
ከዚህ ትርጉም በመነሳት ለሙዚቃ መሠረቱ ድምፅ እንደሆነ በቀላሉ
መረዳት ይቻላል። ያለድምፅ ሙዚቃ ሊታሰብ አይችልም። ይህ ቢባልም
ሁሉም ድምፆች ሙዚቃ ሊያስገኙ አይችሉም።
በዚህ ምክንያት የምንሰማቸው ድምፆች በሁለት ይከፈላሉ።
እነርሱም፦ 1. ሁካታ ( Noise )
2. ሙዚቃዊ ድምፅ ( Musical sound )
1. ሁካታ ( Noise ) ካልተስተካከሉ የአየር ርክርኮች ( Vibration ) የሚፈጠሩ
ለጆሮ ተስማሚ ያልሆኑ ድምፆች ሁሉ ሁካታ በመባል ይጠራሉ።
ለምሳሌ፦ የመኪናዎች ጡሩምባ ሲንጫጫ
- መስታወት፣ ብርጭቆ፣ ብረት ወ.ዘ.ተ ሲወድቅ የሚፈጠሩ ድምፆች
- መስኮት፣ በር በኃይል ሲዘጋ የሚፈጠሩ ድምፆች ወ.ዘ.ተ. ስሜትን
የሚረብሹ በመሆናቸው ሁካታ ውስጥ ይመ ደባሉ።
2. ሙዚቃዊ ድምፅ (Musical Sound) ከተስተካከለና ቅደም ተከተልን ከጠበቀ
የአየር ርክርክ (Vibration ) የሚፈጠሩ ለጆሮ ተስማሚ የሆኑ ስሜትን የማይረብሹ
ድምፆች ሁሉ ሙዚቃዊ ድምፅ በመባል ይጠራሉ።
ምሳሌ፡- በማንጎራጎር ከንግግር የሚሰሙ ድምፆች
- የዋሽንት ድምፅ፣የከበሮ ድምፅ ወ.ዘ.ተ.የሚፈጠሩ ድምፆች ስሜትን
የማይረብሹ ተስማሚ ድምፆች በመሆናቸው ሙዚቃዊ ድምፅ
ውስጥ ይመደባሉ ።
የሰው ልጅ ሙያና ችሎታውን ተጠቅሞ ሙዚቃዊ ድምፅን በማቀነባበር ሙዚቃን
ይደርሳል። ተቀነባብሮ የሚቀርብ ሙዚቃ የደስታ፣ የሀዘን፣ የፍቅር፣ የጥላቻ፣
የትዝታ፣ የትካዜ ወ.ዘ.ተ. ስሜትን ይቀሰቅሳል፣ ይማርካል፣ ያዝናናል፣ ያስተክዛል፣
ያስጨፍራል፣ ያስለቅሳል ባጠቃላይ ሙዚቃ በሰው ስሜት ውሰጥ የሚያሳድራቸው
ተፅእኖዎች ለመግለፅ ̋ ሙዚቃ የህይወት ቅመም ነች ̋ የተሰኘውን አባባል በዓለም
ዙሪያ የሚገኙ ህዝቦች ይስማሙበታል።
2. የሙዚቃ ድምፅ ባህሪያት
ባለፈው ጊዜ እንደተማራችሁት ሙዚቃዊ ድምፅ ከሁካታ የሚለይባቸው አራት
መሰረታዊ ባህሪያት አሉት።
እነሱም፦ 1. የድምፅ ቃና ( Pitch )
2. የድምፅ ቆይታ (Duration)

3. የድምፅ ኃይል (Intensit )

4. የድምፅ ዓይነት (Tone quality)

1. የድምፅ ቃና ( Pitch )፦ የሙዚቃ ድምፅ ከፍተኛ የመሆን (ቀጭን የመሆን ) ወይም


ዝቅተኛ የመሆን (ወፍራም የመሆን) ተለዋጭ የሆነ ባህርይ መገለጫ ነው።
ምሳሌ ፦ አንድን መዝሙር ሴቶች በቀጭን ድምፃቸው ሲዘምሩት በተመሳሳይ
ያንኑ መዝሙር
ወንዶች በወፍራም ድምፃቸው ሊዘምሩት ይችላሉ።
- በአብዛኛው የሴቶች የድምፅ ቃና ቀጭን ሲሆን በአንፃሩ የወንዶች
የድምፅ ቃና
ወፍራም ነው።
- ዋሽንት አንፃራዊ የሆኑ ቀጭንና ወፍራም ድምፆች አሉት።
2. የድምፅ ቆይታ (Duration)፦ የሙዚቃዊ ድምፅ የመርዘም ወይም የማጠር
ተለዋዋጭ
ባሕርይ መግለጫ ነው።
ምሳሌ ፦ የውሻ ጩኸት ዉ ዉ ዉ አጫጭር ቆይታ ያላቸው ሦስት ድምፆች
ቆይታቸው
አጭር አጭር ነው።
- የጅብ ጩኸት እዉዉዉ….. አንድ ጊዜ የሚወጣ ሆኖ ቆይታውም
ከውሻ ድምፅ ሲነፃፀር ረጅም ነው።
- ሙዚቃዊ ድምፅም ቆይታው መርዘም ማጠር ይችላል።
3. የድምፅ ኃይል (Intensity)፦ የሙዚቃ ድምፅ የመለስለስ ወይም የመጉላት
(Softness or Loudness) ባህርይ መግለጫ ነው።

ምሳሌ ፦ በክፍል ውስጥ አጠገባችሁ የተቀመጠን ጓደኛችሁን ስታነጋግሩ


የምትጠቀሙት ድምፅ
ጮክ ያለ ሳይሆን ቀስ ያለ ለስላሳ ነው። በሌላ በኩል ሜዳ ውስጥ በርቀት
የሚገኝን ልጅ
ስትጠሩ የምታወጡት ድምፅ ጮክ ያለ የጎላ ነው።
- የሙዚቃ ድምፅ የመለስለስ እና የመጉላት ባህርይ አለው።
4. የድምፅ አይነት ( Tone quality)፦ አንድን ድምፅ ከሌላው የሚለይበት ልዩ ለዛ
የሚገለፅበት
ባህርይ ነው።
ምሳሌ ፦ የዋሽንት ድምፅ ከማሲንቆ ድምፅ
- የበገና ድምፅ ከክራር ድምፅ ያለችግር እንለያለን። ድምፆቹን
ለመለየት የቻልነው እያንዳንዱ ድምፅ የግል የሆነ ከሌሎች
የሚለይበት ለዛ በተፈጥሮ ባህርይ ስላለ ነው።

3.ሙዚቃ በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ያለው ጠቀሜታ


የሰው ልጅ ለብቻው ሊኖር አይችልም ህልውናው ከሌሎች መሰል ሰዎች
ህልውና ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው። ሰው በኑሮ ሂደቱ ውስጥ በሥራ፣ በደስታ፣
በሀዘን፣ በኃይማኖታዊ አምነቱ የሚያደርጋቸው የዕለት ተዕለት የማያቋርጥ
ግንኙነት ማህበራዊ ህይወት አንለዋለን።
ሰው በማህበራዊ ህይወት ውስጥ በሚያከናውናቸው ተግባራት ሙዚቃን
መገለጫው በማድረግ ይጠቀማል።
- ገበሬው ሲያርስ በሬዎቹን እያሞገሰ ያንጎራጉራል ድካሙን ይረሳል።
- በህብረት ሥራዎች፣ በደቦ ፣ በእጅ ሥራን አቀላጥፎ ለመከወን
የሥራ ዘፈኖችን ይዘፍናል።
- አናት ህፃን ልጇን አንቅልፍ ለማስተኛት በለስላሳ ዜማ እሹሩሩን
ታዜማለች።
- በልደት በሰርግ የሚዜሙ የህዝብ ሙዚቃዎች አሉ።
- በሞት የሀዘን እንጉርጉሮ ይደመጣል።
- በኃይማኖታዊ እምነት ሰው ፈጣሪዬ ነው የሚለውን በዜማ
ያመሰግናል።
- ልጆች በበዓላት ቀናት ተሰባስበው የሚያዜሙት የሚጨፍሩት
የራሳቸው የሆነና ከትውልድ የወረሱት ሙዚቃዊ ጨዋታዎች
አሏቸው። እነዚህ ሁሉ ሙዚቃ በማህበራዊ ህይወት ውስጥ የለውን
አስተዋፅዎ የሚገልፁ ናቸው።
በአጠቃላይ
- በሙዚቃ የህዝቦችን ወግና ባህል ማወቅ ይቻላል።
- ሙዚቃ ያለድካም ስሜት ሥራን ለማከናወን ይጠቅማል።
- በሙዚቃ ትምህርታዊ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።
- በሙዚቃ በመደነስ በመጨፈር ሰውነት ይዝናናል።
- በሙዚቃ ግንኙነት ይጠናከራል፣ ያግባባል ያፋቅራል።
- ሙዚቃን በመፃፍ በማንበብ ዕውቀት ይገኛል ክህሎት ይዳብራል፡፡
- ሙዚቃ የገቢ ምንጭ ያስገኛል።
መልመጃ
ከሚከተሉት ድርጊቶች የሚፈጠር ድምፅ ከየትኛው ምድብ የሚመደብ እንደሆነ
ለይታችሁ ፃፉ
ምሳሌ፦ የዋሽንነት ድምፅ ምድብ ሙዚቃዊ ድምፅ ነው።
- ጠርሙስ ሲወድቅ የሚሰማ ድምፅ ሁካታ ነው።

1. የበረዶ ዝናብ የቤት ጣሪያ ሲመታ የሚሰማ ድምፅ ________________________________________

2. በአዳራሽ የሚገኙ ሰዎች የእርስበርስ ወሬ ________________________________________

3. የፒያኖ ቁልፎችን በየተራ በጣት በመጫወት የሚሰሙ ድምፆች


________________________________________

4. በመድረክ ላይ የሚሰማ የግጥም ንባብ ድምፅ ________________________________________

5. የፒያኖ ቁልፎችን በጡጫ በመምታት የሚፈጠር ድምፅ ________________________________________

በ ̋ ሀ ̋ ሥር የተዘረዘሩትን ድርጊቶች በ ̋ ለ ̋ ሥር ከሚገኙት ስያሜዎች ጋር አዛምዱ


̋ሀ ̋ ̋ለ”
---------- 1. ሰው ሀዘንና ትካዜ የሚገለፅበት ሙዚቃ ሀ. ሽለላ፣ፉከራ
----------- 2. የጋብቻ ሥነ ሥርዓት ዘፈን ለ. እንጉርጉሮ
----------- 3. የጦር ሜዳ የጀግንነት ዜማ ሐ . ዝየራ
----------- 4. የህፃናት እንቅልፍ ማስተኛ ዜማ መ. እሹሩሩ
------------5. የቤተክርስቲያን ዝማሬ ሠ. ቅዳሴ
ረ. ሀይሎጋ፣ ሙሽራዬ

ከዚህ በታች ለቀረቡት ጥያቄዎች ቀጥሎ በሳጥን ውስጥ ከተጠቀሱት መካከል ትክክለኛ
መልሳቸውን በመምረጥ ክፍት ቦታዎችን ሙሉ፡፡

ከፍተኛ ድምፅ ቃና ሀይል


ቆይታ ዝቅተኛ ድምፅ የድምፅ ቀለም

1. ________________________________________ የሙዚቃ ድምፅ የመቅጠንና የመወፈር ባህርይ ነው።

2. ቀጭን ድምፅ ማለት ________________________________________ ማለት ነው።

3. ________________________________________ የሙዚቃ ድምፅ የመለስለስና የመጉላት ባህርይ ነው።

4. አንድን ድምፅ ከሌላው የሚለየው ልዩ ባህርይ ________________________________________

5. ________________________________________ ወፍራም ድምፅ ማለት ነው።

6. ________________________________________ የሙዚቃ ድምፅ ማለት ነው።

ምዕራፍ ሁለት
የሙዚቃ ቲዮሪ ትምህርት
ሙዚቃ እንዴት እንደሚፃፍና እንደሚነበብ ትምህርት የምናገኝበት የሙዚቃ ዘርፍ
የሙዚቃ ቲዮሪ ትምህርት ነው።
በዚህ ክፍል የምንማረው
 የሙዚቃ ድምፅ ምልክቶች
 የሙዚቃ ፊደሎች ያላቸውን ዋጋ እና
 ሙዚቃ ለማንበብ የሚረዱ ምልክቶችን ይሆናል።

1. የሙዚቃ ድምፅ ምልክቶች፦ የሙዚቃ ድምፅ የሚፃፍበት ምልክት ኖታ በመባል


ይጠራል።
- ኖታ ሁለት ዓይነቶች አሉት

1. የድምፅ ኖታ

2. የዕረፍት ኖታ

1.የድምፅ ኖታ ፦ የሙዚቃ ድምፅ በሥራ ላይ የሚቆይበትን የጊዜ ቆይታ


የሚያመለክት ነው።
2. የዕረፍት ኖታ፦ የሙዚቃ ድምፅ በሥራ ላይ የማይውልበትን የጊዜ ቆይታ
የሚያመለክት የድምፅ አንፃራዊ ኖታ ነው።
ከድምፅ ኖታዎች እና ከዕረፍት ኖታዎች መካከል ከዚህ በታች የተመለከቱት
ይገኛሉ።

የድምፅ ኖታዎች ዓይነት የዕረፍት ኖታዎች ዓይነት

የድምፅ ኖታዎችም ሆኑ የዕረፍት ኖታዎች የጊዜ ቆይታ መጠን የሚለካው በምት


( beat ) ነው።

- ምት (beat) ምንድነው? እኩልና ተከታታይነት ያላቸው የሰውነት


ክፍል ወይም የነገሮች እንቅስቃሴ ነው።

ምሳሌ፦ የልባችን ምት እኩል የሆኑ ተከታታይ ንዝረቶች አሉት ይህ ንዝረት የልብ ምት ብለን እንጠራዋለን።

2. የኖታ ዓይነቶች ያላቸው ምትና መጠሪያ ስም

የድምፅ የዕረፍት
ኖታ ምልክት የምት መጠን መጠሪያ ስም

4 ሙሉ ኖታ፣ ሙሉ ዕረፍት
2 ግማሽ ኖታ፣ ግማሽ ዕረፍት

1 ሩብ ኖታ፣ ሩብ ዕረፍት

½ ⅛ ኖታ፣ ⅛ ዕረፍት

¼ 1/16 ኖታ፣ 1/16 ዕረፍት

You might also like