You are on page 1of 2

ሰው ለሰው

…………………………………………………………………….
ሰው ለሰው (2)
ቢፋቀር ምነው 2
…………………………………………………………………….
ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ
ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም(2) ሳያይ
ሀብትን ያከማቻል ቀኑን ሳያውቀው
በድንገት ሲጠራ(2) ላይከተለው
አዝ………..
…………………………………………………………………….
የሰው ልጅ በተራው መጠራቱ ላይቀር
ምነው አንዱ ላንዱ መቃብር(2) ባይቆፍር
አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት
ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም (2) ከመሬት
አዝ ...
…………………………………………………………………….
ዋ ! ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ
አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨልም(2) ሲመሽ
ድሃ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ
በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን(2) መሄዱ
አዝ….
…………………………………………………………………….
ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊያውን ቢሰራ
በህንጻ ላይ ህንጻ ቢያስመስል ተራራ
አይቀርም መሄዱ ሁሉም(2) በየተራ
አዝ ………….

You might also like