You are on page 1of 3

እምዬ ማርያም በሕብረት የሚባል የፍልሠታ

መዝሙር

እምዬ ማርያም ምን ሆናለች


አንገቷን ደፍታ ታለቅሳለች
ስታለቅስ የወልድ ቀሚስ እስኪርስ
ስታነባ አብቅሎ አደረ ጽጌ አበባ
ያን አበባ አስረው ገረፉት እንደ ሌባ
እኔን እናትክን ይግረፉኝ ሀሰት በቃልህ ላይገኝ (2)
ዐርብ ሊሰቀል ሐሙስን ተሰናበታት እናቱን
እናትዬ ቆይ ታዪኛለሽ ተሰቅዬ
ይስቀሉኝ ሀሰት በቃልህ ላይገኝ
ከሁሉ ሁሉ ጤፍ ታንሳለች
አፈር ላይ ወድቃ ትነሣለች
ከዚያች ጤፍ ያዳም ልጅ ሁሉ አትስነፍ (2)
ያዳም ልጅ ሁሉ ሰነፈና
የሰማይ ቤቱን እረሳና
ተው አትርሣ ተሠርቶልሀል የእሣት አልጋ
ያን የእሣት አልጋ የእሣት ባሕር
እንደምን ብዬ ልሻገር
ተሻገሩት አሉ የሠሩት ምግባር
አንቺ አማልጂኝ እግዚእተ ኩሉ ሰላም ለኪ (2)
ውኃ ቢጠማው ቢለምን ሐሞት አጠጡት የዝሆን
እኒህ ስሡ ለዝናብ ጌታ ወኃ ነሡ (2)
ኪዳነ ምሕረት ሩኅሩህ
ተይ አታቁሚኝ ከበሩ
የሲዖል አለንጋ መራራ ነው አሉ
አንቺ አማልጂኝ እግዚእተ ኩሉ ሰላም ለኪ (2)
መልዐከ ሚካኤል ያ ክንፋማ
ሶዖል ወረደ ነፍስ ሊቃማ
ሚካኤል አንተ የሁሉ ባለሟል (2)
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሉህ
ዘንዶ ሰገደ ከእግርህ
ዕፁብ ድንቅ ይባላል የሰማይ ደብርህ
አንተ አማልደኝ በረደዔትህ ሰጊድ ሰላም (2)
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
መጥቼብኋለሁ ከሩቅ
አጋምና ቀጋ እየበላሁ ስንቅ
አንቱ አማልዱኝ መንፈሰ ጽድቅ ሰጊድ ሰላም (2)
ጻድቅ ያሉ እንደሁ ተክለ ሃይማኖት
በአንድ እግራቸው ቆመው ሰባት ዓመት
ለተአምኖ ሰባት ባቄላ ምግብ ሆኖ
ከዚያውም እየሰጡለት ለማንም (2)
ንሽቴ ንሽቴ አጫውቺኝ በሞቴ
እያልጉብሽ ላይ ላይ እያልኩብሽ ላይ ላይ አንቺ ትሆኛለሽ
የበላይ
ንሽቴ ንሽቴ አጫውቺኝ በሞቴ
እያልጉብሽ ሲሲ እያልኩብሽ ሲሲ አንቺ ትሆኛለሽ ለነፍሴ

You might also like