You are on page 1of 12

Unedited version. There may be word errors.

በጌቴ ሴማኒ አባታችን ሆይ


ቅኝት አባታችን ሆይ በሰማያት ላይ ያለህ
በጌቴ ሰማኒ በአትክልቱ ቦታ (2) ተለይቶ ይመስገን ክብር ስምህ
ለኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ (2) መንግሥትህን የምንፈልጋት ከጥንቱ
አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት (2) በልጅነት ትምጣ ትስጠን አቤቱ
በእኛም ነበረብን የዘላለም ሞት (2) ፈቃድህም ይህ እንዲደረግ ይሁን
መስቀል ተሸከሞ ሲወጣ ተራራ (2) በሰማይ ሞተን ተነስተን ከደይን
ይገርፋት ነበረ ሁሉም በየተራ (2) እንድንኖር ምሥጋናህ ምግብ ሆኖን
ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ (2) ዛሬም በምድር በሥጋ ሕይወት ሳለን
እያየች በመስቀል ልጇ ስንገላታ (2) ምግባችን በየእለቱ አውቀህ ስጠን
በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው (2) ይቅር በለን የበደልንህን ነገር
እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ማራቸው (2) ወንድማችን የበደለንም ቢኖር
በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ (2) እንደአቅማችን እኛም እንድንል ይቅር
በሲዊች ተፈርፎ ሞተ ተቀበረ (2) ከገነሀማ ከክፋ ሁሉ መዓት
ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ (2) አትጣለን አድነን እንጂ ከሞት
ኢየሱስ ጌታ ነው አልፋና ኦሜጋ (2) ይህች መንግሥት የማያገኛት ኃልፈት
ጌትነትም ከሀሊነትም ክብርም
ናቸውና የአንተ ገንዘቦች ሁሉም
በመስቀል ተሰቅሎ ለዓለም ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡
የተላከው ቅዱስ ገብርኤል ከጌታ
በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ ሰላም ለኪ ብሎ ከሰጠሸ ከጌታ
አለምን ለማዳን የማይሞተው ሞተ (2) እኔ ባሪያሽ ልብሴን ስታጠቅ ስፈታ
ከሞተ ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ (2) ሰላም ልልሽ ይገባኛል ጠዋት ማታ
መስቀል አሸከሙት ውለታው ይህ ሆኖ (2) ማርያም ሆይ እመቤቴ ሆይ ድንግል
መከራውን ሳስብ ሳስታውሰው ቀኑን እንዳለሽ ቅዱስ ገብርኤል ሰላም
ይቆስላል ይደማል ልቤ በሀዘብ (2) የአሸናፊ የእግዚአብሄር እናት ድንግል
መች ለራሱ ነበር ይህ ሁሉ መከራ (2) በሥጋሽም በሕሊናሽም ድንግል
መስቀል ተሸክሞ የወጣው ተራራ (2) ሰላም ለኪ እንደርሱ ሁሉ እኔም
ሲያጎርሱት የሚነክስ ሰው ክፉ ነውና እውሩን ቢያበራ የሌለብሽ የነፍስ የሥጋ መርገም
ጎባጣን ቢያቀና ብሩክ ነው የማህጸንሽ ፍሬም
ጌታዬን ሰቀሉት አይሁድ ጨከኑና (2) ምነው አያሳዝን እንደቀድሞው ብሩክ አምላክ ነው ዛሬም
የአይሁድ ክፋት (2) እግዚአብሄር ወልድ በመጣ ጊዜ ለካሳ
የዝናቡን ጌታ ውሃ ሲነፍጉት (2) እንበለ ዘር እንደ ንብና እንደ ዓሳ
በተንኮል በሀጥያት ቀሩ እንደሰከሩ (2) ከነፍስሽ ነፍስ ከሥጋሽ ሥጋ ቢነሳ
ሙታን ከመቃብር ተነስተው ሲያስተምሩ ((2) ደስ ያለሽ ወይ ጸጋን አግኝተሸ ከጌታ
እናታችን ሔዋን ወዩ ባይ አልቅሺ ደስ ይበልሽ የማቀርብልሽ ሰላምታ
የንቺን ህመም ታሞ ከሞተ ሊያድንሽ ለምኝልኝ ሳትሰለቺ ጧት ማታ
የህያዋን ጌታ ተሰቀለልሽ (2) ውድ ልጅሽ እንዲያደርግልኝ ይቅርታ
አየጉድ አየጉድ ዓለም የኋላሽ ይቅር ብሎ ኃጢአታችንን ሁሉን
መድኃኒት ክርስቶስ በግፍ ሞተብሽ (2) እንዲያድነን በአንቺ ተማጽነን አለን
በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ሲቆርስ (2) ለዓለም ወለዓለም አሜን፡፡
በችንካር ተወግቶ ደሙንም ሲያፈስ
ዋለች በመከራ ድንግል ስታለቅስ /2/
ሰውነትሽ ራዳ ሀዘን ከበበሽ
ሥቃይ መከራውም ዳግም ፀናብሽ
ተሰቅሎ ሥራይ አንድዬ ልጅሽ /2/
ቢፈስም እንባዬ ሆኖ መንታ መንታ
መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታ
ላለቀሻው ለቅሶ ድንግል የዛን ለታ እናት የዛን ለታ
ባለቀሽው ለቅሶ በልጅሽ ህመም (2)
ከሀጢአት ነጻሁኝ ዳንኩኝ ከገሀነም (2)

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ስነ ሥነ ፍጥረት ስለ ልደት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ድንግልም በምትወልድበት ወራት
አሐዱ አምላከ ብዬ ሰላምታ ሳደርስ በሮም ንጉስ በአውግስጦስ ቁሳር መንግስት
ለፈጠርከኝ ለሰማይ ንጉሥ ሰው ሁሉ ግብር ሊቆጠር ታዘዘ
እንዴት አለህ መጥቼ እስካይ ድረስ ከገሊላ ከነበረበት መንደር
ያስደንቃል ያኗኗራቸው የጥንቱ ቤተልሄም ወደምትባል ሀገር
የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የሦስቱ ከኤፍራታ ይወጣል ንጉስ
ሦስት ናቸው በአካል በገጽ በስም ሚኪያስ የተናገረው ሊደርስ
አንድ ናቸው በትእዛዝ በክብር ፍፁም ሳታፋልስ የወላዶችን ስርኣት
ሰላሶችእም ቅደመ ዓለም ሲኖሩ በታህሳስ በሀያ ዘጠኝ እለት
ዓለም መፍጠር እሁድ ቅድመ ዓለም ሲኖሩ ከዛው ሳሉ የምትወልደት ቢደርስ
ዓለም መፍጠር እሁድ በሰርክ ጀመሩ ተወለደ ድንግልናዋን ሳይጥስ
ያን ጊዜውን ሰባት ፈጠሩ በቅጽበት ቤት ባይኖራት መጥታለችና ከሩቅ
አስቀድመው ሰማይና ምድርን በፊት ከበረት ጠቀለለችው በጨርቅ
አራተኛ መላእክትና ጽልመት ሊፈጸም የኢሳያስ ነገሩ
ሰባተኛ ማይና ነፋስ እሳት እንስሳትም ትንፋሻቸውን ገበሩ
በአርምሞ ይህን ሁሉ ፈጥረው ከዚያ ቦታ ከብት ጠባቂዎች ነበሩ
ተናገሩ ለይኩን ብርሃን ብለው ያይ ነበር ካሉበት ቦታ ድረስ
ሰኞ ጠዋት ውኃን ከፈሉት ከሶስት የብርሃን ጎርፍ ከቤተልሄን ሲፈስ
አንደኛውን አዘቅት አረጉት ከምድር እረኞችም የብርሃንን ጎርፍ አይተው
ሁለቱን ሰማይ አረጉት ጠፈር እጅጉን ፈሩ ምን ነገር ነው ብለው
ማክሰኞም አብቅይ አሏት ምድርን መላዕኩም ፍርሀታቸውን አርቆ
አበቀለች ሳር ቅጠሉን እህሉን ነገራቸው ተድላ ደስታውን አድንቆ
ረብዕም ረቂቅ ሥራን ሲሰሩ ልዑል አምላክ ላዳም ብሎ ተዋረደ
ከዋክብትን ፀሐይ ጨረቃን ፈጠሩ ከድንግል በዳዊት ባህሪ ተወልዶ
ሐሙስም አልተውምና መፍጠር ጨርቅ ለብሶ ከበረት መሀል ተጥሎ
የሚበሩ ክንፍ ያላቸውን ነገር አለላችሁ የሄዳችሁ እዮት በቶሎ
የማይበሩ ክንፍ ያላቸውን ነገር እንዲህ ብሎ ሲነግራቸው በዜና
የማይበሩ የሚሄዱትን በእግር ከእሱ ጋር ብዙ መላእከት መጡና
በባህርም ዓሳ ጉማሬ ሳይቀር አቀረቡ ከእረኞች ጋር ምስጋና
ዓርብ ጠዋት አዳምን የኛን አባት ስብአት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ንግበር ብለው በነሱ አምሳል ሠሩት ለአለም እስከ ዘለአለም ድረስ፡፡
በሳልስት ሄዋንን ፈጥረው ሰጡት
ትርዳህ ብለው ብቻውን ሆኖ በኒያዩት
የሥላሲዎች የፍጥረታቸው ፍጻሜ
በሰባት ቀን ዳርቻ ሆነች ቅዳሜ
ስብሀት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ፡፡

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ስለ ዳግም ምጽአት ስለ ሚሥጢረ ሆሳዕና
አርገንስራውን ሁሉ አምነን በስመ አብ ብለን እስኪ ሰላምታ እናድርስ
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
ነገር ግን ዳግም ይመጣል ስላልን እስኪ እናስታውሰው የሆሳዕናን ትዕይንት
ከጻድቃን ከመላእከት ቦሆንም የሆነውን የነበረው ያን ዕለት
የሚያውቅ የለም የሚመጣበትን ቀኑን ከፋሲካ በሚቀድመው ሰሞን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓቱን ዘካሪያስ የሚባል ነብይ ካህን
ግሩም ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት ደስ ይበልሽ ኢየሩሳሌም ጽዮን
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ ንጉስሽ ይመጣልና አሁን
ከያለበት ይሰባሰባል ከአንድ አፍታ በአህያ ላይ እንደ አንድ ድሀ ምስኪን
ከአጥንታችን ትቢያ የሆነ አፈር እንዲህ ብሎ የተናገረው ቃሉን
ጅብ የበላው የተበታተበው ከዱር ለመፈፀም በአህያ ላይ ሆኖ መድህን
የራስ ፀጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር ሲመጣ አይታ እሱ መሆኑን ለይታ
ተሳስቶ ያንዱ ወደ አንዱ ሳይዞር ሀገሪቱ ተቀበለችው በእልልታ
በየራሱ ይሰባሰባል ሁሉም በመንገዱም ቅጠሉን ቆርጠው በእርጥቡ
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም ልብሳቸውን ያነጠፉ አሉ ከሕዝብ
ነፍሱ የሌለው በድን ይሆናል ፍጹም ሁለተኛም ዳዊት ልበ አምላክ ነውና
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ ሲዘምር እያስማማ በበገና
ይነሳሉ መልካም የሰሩ በእልልታ አስቀድሞ ይህችን ዕለትን ዜና
የብርሃን ልብስ የብርሃን ቀሚስ ለብሰው አዘጋጀህ ከህጻናት አፍ ምስጋና
እንደ ፀሐይ እንደ ቨረቃ ደምቀው ላለው ትንቢት መፈጸሚያ ቀን ናትና
እግዚአብሄርን ፈጣሪያቸውን መስለው እንዲህ ሆኖ ከቤተ መቅደስ ሲገባ
ይሰሙ በቀሙ ቆመው ፍርዱን ሕጻናት እየወረዱ ከጀርባ
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር በጣታቸው እያጨበጨቡ ዘንባባ
ጠግበው ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር በእግዚአብሄር ስም የምትመጣው አምላክ
ገብቶ መውጣት ብሩክ ነህ ለዘለዓል ብሩክ
አግኝቶ ማጣት የዳዊት ልክ መድሀኒት የሆንክ ለሁሉ
ችጋር የሌለበት ድንጋይቱን አገር ሆሣዕና መባል ተገባህ እያሉ
ይወርሳሉ መልካም የሰሩ በምድር በደስታ በፊት በፊቱ ዘለሉ፡፡
ሀጣአንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው ይህን ሰምተው ፈሪሳውያን ጸሐፍት
መልካቸውን እጅግ ከቁራ ጠቁረው ቢናደዱ ቢመላባቸው ቅንዓት
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው ሕጻናቱን ተው በላቸው አሉት
ዲያቢሎስ አለቃቸውን መስለው እንዲህ አለ ሲመልስላቸው ጌታ
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው ከጠላችሁ የህጻናቱን እልልታ
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው ድንጋዮቹ የሚገባቸው ዝምታ
ከለቅሶና ጥርስ ማፋጨት በቀር ያመስግኑ በእናንተ በስዎች ፈንታ
ተድላ ደስታ የሌለበት አገር በዚህ ጊዜ አምላክነቱን ሲገልጡ
ይወርሳሉ ክፉ የሰሩ በምድር ድንጋዮቹ በፊት በፊቱ እየሮጡ
እንዲ አርገው መጽሀፍት ሁሉ እንዳሉ እንደ ሰዎች የምስጋና ድምጽ ሰጡ
በየስራ ይከፋፍለዋል ለሁሉ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ፡፡
ስብአት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ለአለም እስከ ዘለአለም ድረስ፡፡

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
አባ ግራኝ ሞተ
/ስለ አፄ ቴዎድሮስ/ አስቀድሞ
አስቀድሞ ነፍሱ ሳትወጣ በፊት
አባ ግራኝ ሞተ የሆድ ወዳጅ /2/ እናቱን ቆማ ስታለቅስ ቢያያት
ለዮሐንስ አደራ ብሎ ሰጣት
የሚበላኝ ጮማ የሚያጠጣኝ ጠጅ ይርዳሽ ያጽናሽ ይህ ልጅሽ ነው አላት
እርሱንም ቆሞ ሲያለቅስ ቢያየው
ታጠቅ ብሎ ፈረስ ካሳ ብሎ ስም ቢወደው ለእናቱ አደራ ሰጠው
ዐርብ ዐርብ ይሸበራል እየሩሳሌም ዮሐንስም እያለቀሰ በሞቱ
እናቱን አኖራት ወስዶ ከቤቱ
ሺህ ገመር ሺህ ጎራች የሸዋ ፈረስ ሊፈጸም የተናገረው ዳዊት
አይሁድ ጌታን ውሃ ጠማኝ ሲል ሰሙት
አንድ ጥርኝ ሆነ ቢዘልቅ ቴዎድሮስ መጣጣውን ውሃ ቀላቅለው ሰጡት
ፈረሱ አባ ታጠቅ ስሙ ቴዎድሮስ ቀመሰና ያን የሰጡትን ሀሞት
ተፈጸመ ትንቢቱ ሁሉ አሁን
ጠላት የሚበትን እንደዐውሎ ነፋስ ይህን ብሎ ዘለፍ አድርጎ ራሱን
በሥልጣኑ ከሥጋው ለያት ነፍሱን
መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ በነፍስ ወርዶ ነፍሳት ካሉበት አዘቅት
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ ነፍሳትን የወረዱትን ከጥንት
ከዚያ አውጥቶ ወስዶ አገባቸው ገነት
መቅደላ መቅደላ አንች ክፉ ጎራ ተጠራጥሮ አንዱ ሐራዊ ሞቱን
ሴቱን ሁሉ ንቆ ሲኮራ ሲኮራ ሞተ ብሎ በጦር ቢወጋው ጎኑን
አፈሰሰ ከውሃ ጋር ደሙን
ወንዱ አንቺን ወደደ ተኛ ካንቺ ጋራ አይሁድም እርግጥ መሞቱን አውቀው
ሳያዝኑለት ነገ ሰንበት ነው ብለው
አያችሁት ወይ ያኝበሳውን ሞት አይደር አሉ ከመስቀል ይውረድ ሥጋው
በሰው እጅ መሞትን ነውር አድርጎት ኒቆዲሞስ ቀድመ በሌሎት ያየው
ዮሴፍም በአርማትያስ ያለው
እርሳሱን እንደ ጠጅ ጎርሶ ሲጠጣት ሞተ ሳይፈሩ ከጲላጦስ ፊት ቆመው
ተካሰሱ በድኑን እናውርድ ብለው
አውሮፓም ያውቁሀል አፍሪካም ያውቁሀል ጲላጦስ ጠዋት ስላየው ታግሶ
እስያም ያውቁሀል ትዕግስቱን ጻድቅነቱን አስታውሶ
እንዴት ሞተ ብሎ ጠየቀ መላልሶ
እንኳን የሰው ንጉስ ውሃ እንኳ ፈርቶሀል ሞተ ቢሉት እጅግ አዘነ ተከዘ
በድኑን ስጡ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዘ
አባትና እናቱ ያለ አንድ አልወለዱ ከመስቀሉ አወረዱና ሁለቱ
የትግሬንም ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ ገነዙን በድርብ በፍታ በሽቱ
ከተክል ውስጥ ከአዲስ መቃብር ቀብረውት
ወንድ ያለ ራስዎ ገድለውም አያውቁ መቃብሩን በታላቅ ድንጋይ ገጠሙት
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኙዋቸው ወልድ ጌታ በተናገረው መሰረት
ተነሳና ህቱም መቃብር ሳይከፍት
ማረከን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው ለማርያም ወዶ ተገልጦ ታያት
ረቢ ብትል አይዞሽ ጠንክሪ አላት
ምን አሉ እንጊሎዞች ሲገቡ አገራቸው እንዲህ ሆኖ ሞቶ ተነስቶ በፍጥነት
ለወሬ አይመቹም ተንኮነኞች ናቸው አዳምን አንባው ከተድላ ገነት
የአዳም ልጆች ያሁን ያላቸሁ
እንደ አፄ ቴዎድሮስ አላየሁም ኩሩ በመሬት አመስግኑት
ስላወጣኋሁ ከእሳት
ቢመጡ እንጊዚዞች ምክር ሊማከሩ ስብሀት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
በአርምሞ ሸኙዋቸው ሳያኘጋግሩ ለዘላለም ምስጋናህ ይብዛ ክርስቶስ
ለዓለም ወለዓለም አሜን

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
እመቤቴ
መቤቴ አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና
የፍጥረት ሁሉ አለኝታ አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና (2)
ክብርን ስለምንሽ ይግባልኝ ላንች ሰላምታ ከምድርም ፍቅር ጠፍቷልና (2)
እንደ ቸርነትህ አድነን (2)
እናታችን አማላጃችን ድንግል ክርስቲያን ነንና እንዋደድ (2)
ተስፋችን ነሽ የጽድቅ ብርሃን አክሊል እባክህ አንውጣ ካንተ መንገድ (2)
አቤቱ ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ (2)
ማርያም ሆን አንች የገን መውራሳ ሰውን የሚያስወድድ ያለ እንከን (2)
እንኳን ለሰው የምትራሪ ነሽ ለውሻ አንደበታችን እንዲናገር (2)
ለቃለ ወንጌሉ የደከመ (2)
ባንች አምነው በቃል ኪዳንሸ ተማጽነው ምግብርና እውነት ሰተሰጠው (2)
ገነት ገቡ ኃጥአን ስርየት አግኝተው እባክህ አድለን ሁነኛ ሰው (2)
አንተን የሚመስል በሕይወት (2)
ባንች ምልጅ ባንች ልመና ያመኑ ፍቅርና ትህትና የግል ሀብቱ (2)
በቃል ኪዳንሽ በኪዳንሽ በልጅሽ አምነው የፀኑ የማስመሰል ፍቅር እየበዛ (2)
ሰው ረክሏልና እንደዋዛ (2)
ለክብር ብቁ ከዳግመኛ ሞትም የዳኑ ፍፁም መዋደድን ስጠንና (2)
ኑሮ ከፍቶት ደኃ ሲጨነቅ በቤቱ አዲስ ሰው አንሁን እንደገና (2)
ደገኛ ሰው ማግኘት አስቸግሯል (2)
አይዞሽ ብለሽ የምታጽናኝው እናቱ እስከ መጨረሻ ማን ይፀናል (2)
ሲራብ ጉርሱ ሲዝል ሲደክም ብርታቱ ምግባሩ ትክክል እውነተኛ (2)
ልቡ የሚያፀየፍ ክዳተኛ (2)
አንች እኮ ነሽ ለችግረኛ ህይወቱ
ምጽዋት ሲሰጥ ስለ ቅዱሱ ስምሽ
ሲደሰቱ መዕመናን በውል ምልጃሽ ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ
ተለይቼ እንዳልቀር ምስኪን ልጅሽ ኢትዮጵያ ሆይ ተነሽ ክብርንም ልበሽ
በአዲስ ምሥጋና ይመላ ልብሽ
ከጌታዬ አማልጅኝ ድንግል እባክሽ
የተወደደ ነው በእግዚአብሄር ሕዝብሽ (2)
ታውኮብኝ የዓለም ጣጣ በህይወቴ ንብረቴ ጠፊ ነው ከንቱ የማይረባ
በግፍና ቅሚያ በአመጽ ሲገነባ
ስፍገመገም እጅግ ጠንቶብኝ ጉዳቴ
ሲሳይሽ ብዙ ነው ከአምላክ የተሰጠሸ
ታድኝን ዘንድ ከሥጋ ወጥመድ ጭንቀቴ በረከት ለማግኘት መሥራት ነው ጠንክረሽ
የአሕዛብ ብልፅግና አያስቀናሽ ፍጹም
ድረሽልኝ ድንግል ማርያም እናቴ
ኃላፊ ጠፊ ነው ምኞቱም ዓለሙት
ኃይማኖቴ ቢታይ ቢመዘን ምግባሬ ደመና ነውና ይበናል በቅጽበት
በግፍ የተገኘ የተከማቸ ሀብት
ስለሚበልጥ ከክብሬ ይልቅ ነውሬ
ይልቅ በቅንነት በሰላም ለሥራ
በሰንሰለት እጅና እግሬን ታስሬ ሲሳዩ ብዙ ነው ክብሩም አያባራ
ጉቦና ፍትሕን ማጣመም እንዳንለምድ
በገሃነም ይበዛልና አሳሬ
ከወንጌሉ ጋራ አለብን መዛመድ
በምልጃሽ አሁን አድኝን ዛሬ፡፡ እግዚአብሄር ያለው ሰው በእርሱ የታመነ
ከግፍ ሥራ ህመም አካላቱ ዳነ
ክርስቲያን ነኝ ብሎ ጉቦ የሚበላ
የሚያቃጥል እሳት ያገኛዋል ኋላ
በመታመን ፀጋ ይጠራ ስማችን
እውነተኛ እንሁን ለውድ ሀገራችን
የራሱን ሳይሻ ለሀገር የሚያስብ ሰው
በእግዚአብሄር ዘንድ የተወደደ ነው

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
አልፈርድም እኔ ስለ ቸርነትህ
ቅኝት -
ቅኝት
አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢአት ስለ ቸርነትህ ጌታ ተመስገን
በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በስልጣን ስለ ፍፁም ፍቅርህ አምላክ ተመስገን
የቸርነቱ አምላክ ባይተወው በደሌን ሁሉ ማነው የገመተ ከዛሬ መድረስን
ውስጤ ቢፈተሸ በተሰጠኝ ህግ በቅዱስ ቃሉ ልብሱ ሳሰሴሰነካ በእሳቱ ወላፈን
በምን ምግባሬ በምን እፈርዳለሁ ዐይኔን አቅንቼ ባህሩን አሻግሮ ማዕበል አቁሞ
በደሌ በዝቶ ለራሴ ሳላውቅ በኃጢአት ሞቼ እርሱ ያውቅልናል ለመጪው ቀን ደግሞ
ይልቅ የአንዱን ሸክም ሌላው ሰው አዝሎ መጓዝ ይሻላል ሃሌ ሃሌ ሉያ መስዋዕት እናቅርብ
መፍረድ ከመጣ አንድም ሰው አይድን ሁሉም በድሏል ጌታ ይፈልጋል የተሰበረ ልብ
ወንድም ወንድሙን እየከሰሰ ለፍርድ አቁሞ ክርስቶስ ከሌለው ፍቅር ላይኖረው
ክርስቲያን ሆኖ ከወንድሙ ጋር እየተጣላ ሰላም ሰላም ይላል ፍጥረታዊው ሰው
ዓለም ዳኘችን በፀብ ፍርድ ቤት ታረቁ ብላ ሰላም ሰላም ይላል የዘመኑ ሰው
ክርስቲያን ሆነን በህዝብ መሀል እየተካሰስን የኢየሱስ ነገር ለሚጠፉት ሁሉ
አምላክ አዘነ የመስቀሉን ዓላም ስተን የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሁሉ
መቼ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን ሞኝነት መስሏቸው ክህደት ተሞሉ
አይተናል ሲምር ለጠላቶቹ ምህረት ሲለምን የስንፍና አመል እያናወዛቸው
ለጽድቅ ሥራ ለእውነት ብለን መጥተና እንጂ መጾም መጸለዩ ይጎዳናል ብለው
ማነው የሾመን በወንድሞች ላይ አድርጎ ፈራጅ አምላክን ቢክዱ ፍቅርን ነፈጋቸው

የኛ ጌታ
የአብርሃም አምላክ ቅኝት-
ቅኝት-

የኛ ጌታ የኛ መድኀን
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ቤዛ በቸርነትህ ታደገን
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ እኛ እንደሆነ ኃይል የለን
የሐሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት
በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት ጠዋት ለምልማ ማታ ጠፋች
ጲላጦስ ከሰሰው በሰንሰለት አስሮ የሰው ህሊና እያባባች
ከሮማዊው መንግስት እንዲኖር ተባብሮ ዓለም ምኗ ነው የጣፈጠን
ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ እያሳሳቀ የወሰደን
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ ዛሬ አለች ሲሏት ትጠፋለች
ከነተንኮሏ ዓለም ሟች ነች
በብርሃን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ እሾህ በቅሎባት እሾኅ ሆና
በችንካር ላይ ሆነው ምንም ሳይሰለቹ በመተላለፍ ሰው ሊያልቅ ነው
የብርሃን አክሊል ለሰማዕት ያደለ ከእኛ ጋራ ያለው ሃያል ነው
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ በሥጋዊ ዓይን ባናየው
የጦሯ ብዛት መች አድኗት
በህይወቴ ዓለምን ትምክህት ተዋህዷት

እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኛ


እንደሰው ንብረት ወደረኛ
በህይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ ለእኔ በወንጌል ማመኔ (2) እንደ ዓለም ጉልበት ጉልበተኛ
በአምላክ ፊት ሲታይ ሕመምተኛ
ህይወቴ ሲመራ ጌታ በቃልህ
ጣፋጭ ይሆን ነበር ሲያድሰኝ ፍቅርህ
ያንተ ፀጋ ቤታ ስለበዛልኝ ሰላም እስኪ
ጨለማህ ተገፎ ብርሃንህ መራኝ ቅኝት-
ወዴት እሄዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ › ሰላም እለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ
ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ ማርያም እምና ናስተበቁአኪ
ምን አይነት መውደድ ነው ለኔ አንተ ያለህ እምአርዌ ነአዊ ተማህፀነ ብኪ
በእንተ ሀና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ
ምን ይከፈለዋል ለፍፁም ፍቅርህ ማኀበረነ ዮም ድንግል ባርኪ
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለእኔ ያለህ
ምን ያከፈለዋል ለፍጹም ፍቅርህ
ደጅህ ላይ ተጥዬ ደጅህ ላይ ልሙት
ቃልህን ልጠብቅ በፍጹም ፍርሀት

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ለእኔስ ልዩ ነች ማን ይመራመር
ለእኔስ ልዩ ደንግል ማርያም ቅኝት-
ለእኔስ ልዩ ነች እመብርሃን ማን ይመራመር
ፈልጌ (2) ላንቺ ምሥጋና አላገኘሁም (2) ያንተን ሥራ ያንተን ክብር
ልቤ ሲያበቅል የኃጢአት አረም ማን ይመራመር
ውስጤ ሲሸፍት አልተወችኝም አዳምና ሔዋን ጠፍቷቸው መንገዱ (2)
ከቤተ መቅደስ እጇን ዘርግታ ለሰው ልጅ መከራ ትተውለት ሄዱ
ትጠራኛለች የኔ መከታ እስከዚያው ድረስ ነው ሲሶ ማረሳችን (2)
የሆዴን ሀዘን የልቤን ምሥጢር እንገባው የለም ወይ በየመሬታችን
እነግርሻለሁ አንድም ሳይቀር እግዚአብሔር ምን ይበል እኛ ቅጥ ብናጠሠ (2)
የምትሽሽጊ የሕዝብን ኃጢአት በስምንተኛው ሺ በቀጠሮ መጣ
ለእኔስ ልዩ ነሽ ድንግል አዛኝት አዳም በበደለው ጌታ ለዓለም ክሶ (2)
ጣዕሙ ልዩለ ነው ከእርሷ ጋር መኖር ቆሟል ቀራኒዮ ከለሜዳ ለብሶ
ድንግልን ይዤ መቼም አላፍር አልህም እንዳልል እንዲህ ይደረገል (2)
ወደ ጽድቅ ሕይወት ትወስደኛለች የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
ድንግል ማርያም ለኔ እናቴኮ ነች እባክህ አምላኬ አትመራመረኝ (2)
በሀዘን ስሰበር ማንና እጠራለሁ እንደ በላኤ ሰብ በጥቂት ነገር ማረኝ
ውስጤ ሲደማ ለማን እንገራለሁ
ከኃጢአት እድፍ ንፁህ መሆኛዬ አንተነህ ይላሉ የዓለም ሁሉ ጌታ
አንቺ ነሽ ድንግል የኔስ መጽናኛዬ ሰማይና ምድርን ያቆምክ ያለዋልታ
የኃጢአት ቁስል ያለአንቺ አይጠርግም ወዴት እንዴት ይሆን ያለህበት ቦታ
ልጅሽ ሳይፈቅድ በህይወት አልኖርም እነግርህ ነበር እኔ በቆይታ
ከልጅሽ ሌላ መድህን የለኝም የሰራችልኝን የእናትህን ወሮታ
ከፀሎት በቀር ፍፁም አልድንም
ሁልጊዜ አትለይም እሷ ከእኔ እርዳታ
ድንግል ስልሽ ምግብና መጠጤን በውል አዘጋጅታ
እግሬን አሳጥባ ዙፋን አዘርግታ
ድንግል ስልሽ ማርያም ስልሽ ትከተለኛለች እርሷ በልእልና
እንደ በላኤ ሰብ ይጋርደኝ ጥላሽ ድንግል ስልሽ ለእርሷ ልእልና የለውም ቅሬታ
በጭንቅ ውስጥ ሆኜ ከቦኝ መከራ ልጇ ፍፁም ንጉሥ የለው ባለአታ
የአምላክ እናት ስምሽን ስጠራ እኔስ ይገርመኛል ከጠዋት እስከ ማታ
ታማልጅኝ ዘንድ ልቦናሽ ይራራ /2/ ካለሁበት ሀገር አለመለየቷ
ጭንቄ በረታ ሀዘን ከበበኝ
ኃጢአቴ በዛ ተስፋ ቢስ ሆንኩኝ ለሁሉ ነው እርሷ ይህ ሩህሩህነቷ
ድንግል እመቼቴ ምልጃሽ አይለየኝ /2/ አይበዛም እንደኔ ይህ መልካምነቷ
ልጅሽ በሰጠሸ ቃል ኪዳንሽ
ተግተሸ ዘወትር እያማለድሽ አንቺ አማልጂን እንዲ መድኃኒት ለዓለሙ
የሰውን ልጅ ሁሉ ታስሰምሪዋለሽ /2/ ወልደ አብ ሲለምን አባ ስረይሎሙ
ስምሽ እንደ ማር እየጣፈጠኝ እመቤት እመቤት የዓለም መድኃኒት
ደግነትሽም እየመሰጠኝ እንድታማልጂኝ በዕለተ ምጽአት
ሁሌ እዘምራለሁ ልቤን ደስ እያለኝ /2/ ምንም ክፉ ብንሆን አውቀን ብናጠፋ
እምነቴ ሳስቶ ጽድቅም ባልሠራ አዛኝቷ አስምሪን እናት አትገፋ
እመቤቴ ሆይ ነፍሴን አደራ ንኡ ና ሑሩ ሲል ሲያደራጅ ልጅሽ
አስታርቀሽ አኑሪያት ከቅዱሳን ጋራ /2/ እንደ በላኤሰብ ያድነን ጥላሽ
ድንግል በሃና በእናትሽ
በኢያቄምም በአባትሽ እባክህ አምላኬ አትመራመረኝ (2)
ተማጽኜሻለሁ ልቁም በፊትሽ /2/ እንደ በላኤ ስ በጥቂት ነገር ማረኝ
አንቺን ስጠራ ልቤ ይረካል
ሀዘን ርቆ ሰላም ይተካል ያንተን ሥራ ያንተን ግብር ማን ይመራመር
ለሀዘንተኞች ተስፋ ከቶ እንዳንቺ የታል /2/

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ስቀለው መጾሙን ይጾማል
ቅኝት ቅኝት-
ቅኝት-
ስቀለው ስቀለው እያሉ
አይሁድ በአንተ ላይ ተማማሉ መጾሙን ይጾማል ሁሉም የአዳም ልጅ /2/
እውነተኛ ዳኛ አንተ ሆነህ ሳለ የጊዜውን መድረስ የሚያውቅ የለም እንጂ /3/
የጲላጦስን ፍርድ ፍቅርህ ተቀበለ ይደርሳል ሰዓቱ ሳስብ ሌላ ሌላ /2/
የተሰቀለውን ሥጋውን ሣልበላ /3/
ጌታ ይቅር በለን /2/ ድጓ ጾመ ድጓ ተሰቅሎ ከቤቴ /2/
ምንም ብንበድልህ የእጆችህ ሥራ ነን /2/ አውይ አለማወቅ ሳልማር መቅረቴ /3/
ተጠማሁ ተጠማሁ እያለ ደግሞ ድግሜ ቀረኝ አሌፋቱ /2/
በቀራንዮ ላይ መስቀል ላይ ሆነልን አድኀነኒ ሣልል አትጥራኝ በከንቱ /3/
የአፍላጋት ጌታ አንተ ሆነህ ሳለህ እኔስ እሄዳለሁ አጣቢ ፍለጋ /2/
ሆምጣጤ አጠጡህ ሳለህ ተቸንክረህ በጣም አድፎብኛል የለበስኩት ሥጋ /3/
ማን መታህ ንገረን እያሉ ዳዊት እንዴት ይሙት ሳንተዋወቀው /2/
ፊቱን እየጸፉት ሲሳደቡ ዋሉ የሚመጣውን ሁሉ በገና የሚያውቀው /3/
ምንም አልመለስ ምነውም አላለ ዐርብ ረቡዕን ገደብኩ በሥጋ በአዋዜ /2/
ህማሙን በትዕግስት አውቆ ተቀበለ እንዲህ ለሚደርሰው ለማይቆየው ጊዜ /3/
ምራቅ እየተፋ ፊትህ ላይ ከሥጋው ሳልበላ ተጠይፌ ደሙን /2/
ሲገርፉህ ሲሰድቡህ ስተሰቃይ ማን ይችለው ይሆን የላይ ቤት ረሃቡን /3/
ምንም ሳትመልስ በፍቅር አየሀቸው ከንብረቱ ሁሉ አልጋዬ ነው ሀብቴ /2/
በመስቀል ሰቀሉህ አንተም ሞትክላቸው አድርሶኝ ይመጣል ከዘላለም ቤቴ /3/
ይቅርባይ ነህና መሀሪ ብልህ ነው ስትሉኝ እዩት ሞኝነቱን /2/
ትህትና ፍቅርን አስተማሪ በራሴ ላይ ሆኖ አላውቀውም ሞቴን /3/
ገርፈው ለሰቀሉት ለፈፉ በፊቱ መማሩንስ ዳዊት ተምሬ ነበረ /2/
ምህረትን ጠየቀ ከአብ ከአባቱ ከአምላኪየ ሳልደርሰ ልቤ ሰንፎ ቀረ /3/
መከራህን ሳስብ ስቃይህን እንኳን ነአኩተከ በስመ አብም ቸገረኝ /2/
መስቀል ላይ እንደዋልክ እርቃንህን ዳዊት እንዴት ተማርክ እባክህ ንገረኝ /3/
ነፍሴ ተጨነቀች እጅጉን አዘነች
ፍዳና በደሏን እያሰላሰለች እኔስ በምግባሬ
ቅኝት -
እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ/2/
ያ ድሀ ተጣራ እዘኚልኝ ድንግል እለምንሻለሁ
ያ ድሀ ተጣራ እግዚአብሔርም ለማው ደርሶ ስላንኳኳ ከፀባኦት ያንን የእሳት ባህር እንዳላይ አደራ
እንባው ድረሺልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ /2/
አምላክ በቸርነት በምህረት ጎበኘው የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና
የናሆም መድኃኒት ንኢ በደመና /2/
ባለቀሰ ጊዜ ግራ የገባው ሰው
መሻትህ ብቻ ነው የሚፈለግብህ አንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ
እግዚአብሔርን ጥራ እመን ትድናለህ የልቤ መጽናኛ እረዳት ምርኩዜ /2/
ንገረው ችግርክን የውስጥህን ብሶት
ይሽረዋልና አስፈሪውን ህይወት አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ
ግራ የተጋባው የተከፋው ገጽህ እማጸንሻለሁ በደሌን አውቄ /2/
ይበራል በፀሎት አምላክህን ጠይቅ
ለወገን ለዘመድ ያስቸገረው መላ
ሲቀል ታየዋለህ ካነባህ በኋላ
ሳግና ንዴትህ ይቀራል ይሻራል
በርሱ ፈንታ ሰላም ፍቅር ይከብሀል
በከንቱ መጨነቅ እራስን መጥላቱ
ነውና የአጋንንት መግቢያ ምልክቱ
ሀዘን በህሊናህ በፈሰሰ ጊዜ
ንገረው ለአምላክህ የልብህን ትካዜ

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ወላዲት አምላክ ምድረ ቀራንዮ
ቅኝት-
ቅኝት- ቅኝት-
ቅኝት-
ወላዲት አምላክ የሁሉ እመቤት
ለምኝልን ለኛ ከልጅሽ ምህረት ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጎልጎታ
በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት መድኃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ
እንዲያወጣን ነጻ ከፍርድ ቅጣት መስክሪ አንቺ ምድር ግእዚቷ ሥፍራ
ድንግል ሆይ ለምኝልን (2) መድኃኒጽ ክርስቶስ ያየብሽ መከራ
ደሙ እንደውሃ ሲፈስ ከመስቀል ላይ
በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን በቀራንዮ መዳን መከራውን ሲያይ
በምድራዊ ምኞች ናውዞ ልቦናችን ፀሀይ ከለከለች ለመስጠት ብርሃን
ፍቅርና ትህትና ጠፍቶ ከፊታችን ለመሸፈን ብላ የአምላክን እርቃን
ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ስራችን ሁሉንም ለማድረግ ሥልጣን ቢኖረው
ድንግል ሆይ ለምኝልን (2) በእንጨት ተሰቅሉ ፍቅሩን ገለፀው
የምስኪኖች ተስፋ የደካሞችም ኃይል በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ
ጠውልገናል እኛ ጥላ ሁኚን ድንግል የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀራንዮ ዋለ
እምነት ጨምሪልን የመዳንን ፋና እጆቹና እግሮቹ በችንካር ተመተው
ድንግል ሆይ ለምኝልን (2) ይቅርታ አደረገ ለዚህ ኃጢአታቸው
ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ ቸሩ መድኃኔዓለም እባክህ ማረን
ተነቅለን እንዳንቀር ከዘላለም ተድላ ደካሞች ነንና እንዳንቀር ጠፍተን
በፍቅርሽ መልሺን ከሲኦል ጎዳና በቆረስከው ሥጋህ ባፈሰስከው ደም
ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና አቤቱ ተራዳን ለዘለዓለም
ድንግል ሆይ ለምኝልን (2)
ኑ እንቅረብ
ቅኝት- ወላዲተ ቃል
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ /2/ ቅኝት-
ሥጋውን እንብላ ደሙንም እንጠጣ
ድንግል /2/ ወላዲተ ቃል /2/
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ድንግል
ተሰውቶልናል እንመገበው ያንቺስ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር ››
እድፉን ኃጢአታችንን በንስሓ አንፅተን ሥጋሽ በምድር ላይ የት አለ እንደፍጡር ››
እንቀበል አምነን በልጅነታችን ዐርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር ››
መቅረብ ወደ ጌታ በእምነት የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው ሥጋሽን ሲያሳርጉ መላእክተ ሰማይ ድንግል
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ ››
ከዋክብት ከሰማይ የተነጠፉለት መግነዝ ተረከበ ለሐዋርያት ሊያሳይ ››
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን ትንሣኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው ድንግል
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን ሐዋርያት ፆመው ተገለጽሽላቸው ››
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ ተቀብራ አልቀረችመ በምድር ከደጇ ››
ከግዝዣው ተጠራን አዋጁም ታወጀ ወደ ላይ ዐረገች እሷም እንደልጇ ››
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሳኤ ድንግል
ይህችን ዕድል ፈጥረን እንጠቀምባት እርገቷን አውቁ በንጹህ ሱባኤ ››
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት እኛም አንፀልይ ደጃችን እንዝጋ ››
ካሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ ››
የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
የአዋጅ ነጋሪ ቃል ኑ እናመሰግን
ቅኝት-
ቅኝት- ኑ እናመስግን ከልባችን የሰማዩን አባታችን
የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሃ አየለ ከዚህ ዕለተ ከዚህ ዓመቴ ያደረሰን ሁላችንን
የእግዚአብሔርን መንግስት አስተካክሉ እያለ የዕለት የዓመት የዘመናትም ጌታ
ምሥክርነቱን ዮሐንስ ሲየስረዳን ለዚህ ላደረስከኝ ዘመኔን ሳትገታ
ልባችሁ ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን አቀርብልሀለሁ የክብር ሰላምታ /2/
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም የሰው ልጆች ዕድሜ ጥንቱንም ቢቆጠር
አውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና አንድ ቀን አይሞላ እንደአንተ አቆጣጠር /2/
ካለተስተካከለ መንገድ የለምና ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
የእግዚአብሔርን መንገድ እንመስርት ሁላችን ወዳንተ አንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ማለፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሀብታችን ደካማ ነውና ሰው እድሜ ከራበው /2/
ክፉትና ተንኮል ከልባችን ይጥፉ እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ጽድቅና ርኀራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ ምድርን በአበባ ሰማይን በኮከብ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል እንዳሸበረቅካት አስተውዬ ሳስሰብሰ /2/
ሕይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል በከንቱ ጊዜያችንን ፈፅሞ እንዳይጠፋ
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን በርትተን ከሰራን ያላንዳች ነቀፋ
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን አምላክ የሚሰጠን አለን ሙሉ ተስፋ /2/
ከበደላችንም አንጻን አደራህን ከንቱ ካሣለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
በክፉ አንዳንጠፋ እኛ ልጆችህ ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላ ዓለምን ብገዛ /2/
ጊዜዬ እስኪደርስ እንደቸርነትህ
ቅኝት-
ቅኝት-
ቅኝት
ጊዜዬ እስኪደርስ ወዳንተ መምጫዬ እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን (2)
ለንስሓ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ እንደምህረትህም ይቅርታን ስጠን (2)
ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ ከኃጢአቴም አንፃኝ ከክፉ በደሌ (2)
ከፍቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ (2)
ተስፋዬ ረዳቴ አንተ አትጣለኝ አንተን ብቻ በደልሁ ክፉም አደረግሁ (2)
አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ (2)
መሃሪ ይቅር ባይ ምህረትህ ይጎብኘኝ ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን (2)
ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ መውደቄን ተመለከተ አምላከ ብርሀን (2)
አዳኜ መድኃኒቴ ሰላም ላክልኝ አሁን ትባርክ ዘንድ ማህበራችንን ጸሎታችንን
የድኀነት ደጆች በፍቅር ክፈትልኝ ጌታ ሆይ ላክልን ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤልን
አቤቱ ምህረትህ በእኔ ላይ ይሁን አሁን ትጠብቅ ዘንድ ሀገራችንን ኢትዮጵያን
ተጨነኩኝ ጌታዬ ስጠኝ ሰላምን ጌታ ሆይ ላክልን ጰራቅሊጦስን መንፈስ ቅዱስን
ከክፉ እንድሸሽ አርቀኝ እኔን
በጎ እንድሰራ ምራኝ መንገዱን
ሕይወት ሞት ድኀነት መኖራቸውን ባምንም
ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጉኝም
ሥርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም
ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም
የበደሌ ብዛቱ የሚያስከፋ ቢሆን
በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን
ወደ አንተ እመጣለሁ አደራ ነፍሴን
በስማያዊ ቤት አኑር ህይወቴን

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
አቤቱ አንተን እጠራለሁ ሰአሊለነ ማርያም
ቅኝት
አቤቱ አንተን እጠራለሁ ቅኝት
ነፍሴን ወዳንተ አነሳለሁ ሰአሊለን ማርያም (2)
ዝም አትበለኝ እጮሃለሁ (2) ሀበ ወልድኪ ሔር መድኃኔዓለም
የኃጢአት ሽክም ከብዶኛል ለምኝልን ማርያም (2)
የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል ከቸሩ ከልጅሽ ከመድኃኔዓለም
የሰይጣን ፋላፃ አጥቅቶኛል (2)
ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ ለመኑ እነግር ሀዘነ ልብየ
ምሥኪን ተስፋ ቢስ አነስተኛ እንበሌኪ ማርያም ትግዝዕትየ
ከመንጋህ የራቅሁኝ ብቸኛ (2) ወፍጡነ ስምእኒ ጸሎትየ
ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ብለኸኝ
የንስሀን በር ክፈትልኝ ማርያም------
ለምኝልን ማርያም------
መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ (2) ለማን እነግራለሁ የልቤን ሀዘን
የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ የጌታዬ እናት ከአንቺ በቀር
የቃለህ በረከት ራበኝ
እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ
ፈጥነሽ ስሚኝ ጸሎቴን
ካንተ ኮብልዬ ተንከራተትኩኝ ስዓሊለነ ማርያም …..
ምንም ላይረባ ካንተ ባከንኩኝ ድንግል ሆይ አሳስቢ ሀዘን መከራሽን
ለበስባሽ ሥጋዬ የተገዛሁኝ
በሄርድስ ዘመን የደረስብሽን (2)
ድንግል ሆይ አሳስቢ እረሀብ ጥምሽን
አቤቱ ፈጣሪያችን በግብፅ በረሀ የደረሰብሽን (2)
ቅኝት
አቤቱ ፈጣሪያችን መድኃኒታችን አምላካችን አባታችን ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ
በአንተ ላይ ነው ዘላለም ተስፋችን ሰ ለንጹሀን አይደል ላደፉት አሳስቢ (2)
ቀንና ሌሊቱን የምታፈራርቅ ለምኚልን ማርያም ……..
አምላክ አንተ ብቻ ሥራህ የሚያስደንቅ
መዓትህ የራቀ ምህረትህ የበዛ ክብሬ ተስፋዬነሽ እናቴ እልሻለሁ
በረቂቅ ሥልጣንህ ሁሉን የምትገዛ ስምሽን ስጠራ ከጭንቀቴ አርፋለሁ (2)
በበደልነው በደል በስራነው ሥራ ውዷ ስጦታዬ ድንግል ሆይ ነይልኝ
በትህትና ፈፀምክ ያን ሁሉ መከራ ባዶነቴን አይተሸ ጉድለቴን ሙይልኝ (2)
ሰይጣን በተንኮሉ አንዳያጠምደን ሰዓሊለነ ማርያም ------
በሕይወት ጎዳና ወዳንተ ምራን
ያንተ ምሕረትና ያንተ ቸርነት በእንተ ፍቅረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ተነግሮ አያልቅም በሰው አንደበት ምስለኪ ማርያም በሀሌ ሉያ
የዘላለም አምላክ የፍቅር የሠላም ሀዘና ስምኢ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ
አቤቱ ተመስገን እስከ ዘለዓለም ሰዓሊለነ ማርያም --------

Unedited version. There may be word errors.


Unedited version. There may be word errors.
ሰላም ተዋህዶ
ቅኝት -
ሰላም ተዋህዶ ሰላም ኦርቶዶክስ
በደሙ ያጸናሽ መድኀን ኢየሱስ (2)
የአዳም መመኪያ የሄዋን ሀገር
አንቺ አይደለሽም ወይ የቅዱሳን ክብር (2)
በከንቱ የሞተው የአቤል መስዋዕት
የሄኖክ ሀይማኖት ያዳንሽው ከሞት
አንቺ የኖህ መርከብ የሴም በረከት (2)
በአብርሃም ድንኳን ተወልደሽ ያደግሽ
የይስሀቅ መአዛ ወደር የሌለሽ
ያዕቆብ በህልሙ በቤቴል ያየሽ
የዩሴፍ አጽናኙ ተዋህዶ ነሽ (2)
ሰላም ተዋህዶ ……..
የሙሴ ጽላት ነሽ የአሮን በትር
የኢያሱ ሀውልት የጌዲዮን ጸምር
የሳሙኤል ሙዳይ የእሴይ ትውልድ
የዳዊት በገና የሰሎሞን ዘውድ
የታተመች ገነት የምስጢር ጉድጓ (2)
ቡአዴና ህድረት የኬልቄዶን ዘር
ቱሳሄና ሚጠት ውላጤም ጭምር
ያልተቀላቀለሽ ንጽህቲቱ ምድር
ኢሳይያስም አይቶ በሩቅ መነጽር
ስለቅድሰስናሽ ሆነ ምስክር (2)
ሰላም ተዋህዶ …..
በነኤልያስ ቤት የወርቅ መሶብ
ውስጥሽ የተሞላ በምሥጢር ምግብ
የኤልሳ ማስሮ የህይወት መዝገብ
ፋራን የምትባይ የእንባቆም ተራራ
ሁሉን የምታሳይ ከቀኝ ከግራ
የህዝቅኤል እልፍኝ ባለአንድ በራፍ
የማትከፈቺው በኬልቄዶን ቁልፍ (2)
የህግ መፋለቂያ የነፃነጽ ቦታ
የሚኪያስ ሀገር አንቺ ነሽ ኤፍራታ
እፀ ህይወታችን የኤፌሶን ቅርስ
የተፈወሱብሽ እነ ኡቡን ቄርሎስ
ለተፈወስንሰብሽ ከኬልቄዶን ቁስል
ተዋህዶ ላንቺ እልል አንበል (2)
ሰላም ተዋህዶ ……
አንቺን በማየቱ በብርሃን ተቋም
ደስ አለው ከልቡ ዘካርያስም
በውስጥም በውጪም የሌለሽ እንከን
የህይወት ምግብ ነሽ ተዋህዳችን (2)
ሐዋርያት ይምጡ ያውሩ ያንቺን ዜና
የሚያውቅ ሲናገር ደስ ያሰኛልና
ሰማዕታት ልጆችሽ የፃፉሽ በደም
የህይወት መጽሐፍ ነሽ የፅድቅ የሰላም (2)
አንቺን ለመጠበቅ እስከ አለም ፍፃሜ
ቃል እንገባለን ባለንበት ዕድሜ (2)
እናምናለንና በፈጣሪያችን
እናምናለንና በአምላካችን
ካንቺ እንደማንለይ ምን ጊዜም ቢሆን (2)
ሰላም ተዋህዶ ……

Unedited version. There may be word errors.

You might also like