You are on page 1of 10

አዱስ አሇበት ዩኒቨርሲቲው

ሂዩማኒቲስ፣ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጆርናሉዝምና ኮሚዩኒኬሽን ኮላጅ


የአማርኛ ቋንቋ፣ ስነ ጽሁፍና ፎክልር ትምህርት ክፍሌ
የዴህረ ምረቃ መርሃ ግብር

"ስነ- ቃሌን መሰረት አዴርገው የተሰሩ ጥናታዊ ፁሁፎች ግምገማ” በሚሌ ሇ “Field work

in folklore ኮርስ ማሟያነት የቀረበ

መኩሪያ አያላው መ.ቁ GSR/5826/13

መሰረት አሇሙ መ.ቁ GSR/ 1255/15

ያረጋሌ ጫኔ መ.ቁ GSR/5714/15

ሇ የኔዓሇም አረድ (ድ/ር)


አዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮጵያ

02/08/2015 ዓ.ም
ይዘት ማውጫ
1. መጣጥፍ አንዴ ........................................................................................................... 3

2. መጣጥፍ -ሁሇት ......................................................................................................... 7

3. መጣጥፍ - ሶስት ........................................................................................................ 9


1. መጣጥፍ አንዴ

የአገው ብሄረሰብ የማንነት ቃሊዊ ዝርው ተረኮች ፊይዲ በሚሌ 2004 ዓ.ም ሇፎክልር
የማስተርስ ዱግሪ የተሰራ ጥናታዊ ፁሁፍ ሊይ ከቅርፅና ይዘት አንፃር የተዯረገ ግምገማ

የጥናታዊ ወረቀቱ አጥኝ፦ ትዕግስት አሇማየሁ

ገምጋሚዎች፦ መኩሪያ አያላው፣መሰረት አሇሙና ያረጋሌ

የገፅ ብዛት፦ ዘጠና ስምንት

ይህ የአገው ብሄረሰብ የማንነት ቃሊዊ ዝርው ተረኮች ፊይዲ በሚሌ በትዕግስት አሇማየሁ በ
2004 ዓ.ም ሇፎክልር የማስተርስ ዱግሪ የተሰራ ጥናታዊ ፁሁፍን ከቅርፅና ይዘት አንፃር
ሇማየት የተዘጋጀ ግምገማ ሆኖ ጥናታዊ ፁሁፈ በአራት ክፍሌ የተዋቀረ ሲሆን ግምገማው
መጀመሪያ ከቅርፅ አንፃር ከጥል ዯግሞ ይዘቱን ሇመዲሰስ የሚሞክር ነው፡፡

1. ከቅርፅ አንፃር

አንዴን አካዲሚያዊ ጥናታዊ ፁሁፍን ሳይንሳዊ ከሚያሰኘው አንደ የቅርፅ ጉዲይ ነው፡፡ቅርፅ
በምርምር ሂዯት ውስጥ እንዯ ጥናታዊ ርዕሰ-ጉዲይ ባህሪ፣አይነትና በተመራማሪው ፍሊጎት
ይወሰናሌ፡፡ የተመራማሪው ፍሊጎት ዯግሞ የሚወሰነው ይዞት ከሚነሳው የምርምር ባህሪ
የሚመነጭ ነው፡፡ ጥናታዊ ፁሁፍ-በዯሳሇኝና በመሰሇኝ የሚሰራ እንዲሌሆነ በመስኩ የሚኖሩ
ሙያተኞችና ፍሊጎት ያሊቸው ሁለ ሌብ የሚለት ጉዲይ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የትዕግስት
አሇማየሁ ጥናታዊ ፁሁፍ ከቅርፅ አንፃር እንዯሚከተሇው ቀርቧሌ፦

 ልጎና፣ወር፣ ሁሇተኛ ሽፊን የሇውም… አማካሪው ማን እንዯሆነ የሚገሌፅ ገፅ የሇውም፡፡


 ከማውጫ ቀዴመው የሚመጡ መሰረታዊ ጉዲዮች አሌተካተቱም ማሇትም ማረጋገጫ፣
የፇታኝ ቦርዴ አባሊት ማረጋገጫ የሚያሳይ፣ሙዲዬ ቃሊት ወዘተ
 ማውጫው ምዕራፍ የሇውም…. ነገር ግን በመግቢያ በአራት ክፍልች የተዋቀረ መሆኑን
ይገሌፃሌ፡፡
 የጥናቱ ጥያቄዎች በማውጫው አሌተካተተም እንዱሁም የጥናቱ ወሰንና ጠቀሜታ
ቦታቸውን የጠበቁ አይዯሇም፡፡
 የጥናቱ ዋና አሊማ እና ንዑስ አሊማዎች ከማሇት ይሌቅ ከዝርዝር አሊማዎች መጀመሩ
ያሌተሇመዯ ቅርፅ ሆኖ አግኝተነዋሌ፡፡ ዝርዝር አሊማዎችን ተከትል የጥናቱ ጥያቄዎች
ተቀሊቅሇው መቀመጣቸው ያሌተሇመዯ ነው፡፡
 የሚገርመው በምርምር ሂዯት ውስጥ የጥናት አይነት፣ዕይታና ዱዛይን ምርምርን
ሳይንሳዊ የሚያዯርገው ጉዲይ ሲሆን በዚህ ጥናታዊ ፁሁፍ ተዘሎሌ፡፡ በጥናቱ ዘዳ ስር
የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዳ ተቀምጧሌ፡፡ጥናቱ የጥናት ስነ-ዘዳን አዯረጃጀት ሂዯት
የተከተሇ አይዯሇም፡፡
 ክሇሳ ዴርሳናት በባህሪው ሶስት ክፍልችን የያዘ ነው፡፡ ፅንሰ-ሀሳባዊ ቅኝት፣ንዴፇ-ሀሳባዊ
ቅኝትና የተዛማጅ ፁሁፍ ቅኝት ሲሆን በዚህ ጥናት ፅንሰ-ሀሳባዊ ቅኝት በንዴፇ-ሃሳባዊ
ቅኝት ተተክቶ መጀመሪያ መቀመጡ የክሇሳ ዴርሳናት ቅርፅን የተከተሇ አይዯሇም፡፡
የፅንሰ-ሀሳባዊ ቅኝት ይዘቶች በንዴፇ ሀሳብ ርዕስ ስር መቀመጡ ስህተት ነው፡፡
 ከቅርፅ አንፃር የጥናቱ አንደ ጥንካሬ የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት በግሌፅ ተቀምጧሌ፡፡
 የትንተና ምዕራፍ ሂዯቱ ቅርፅ ከቃሊት ግዴፇቶች ውጭ የጥናቱ ጥንካሬ ነው፡፡
 ጥናቱ አስተያየት የሇውም፡፡
 ዋቢ-መፅሃፍት በተመሇከተ የጥናታዊ ፁሁፈ ጥንካሬ ነው፡፡ ነገር ግን አሌፎ አሌፎ
ወጥነት ይጎሇዋሌ፡፡
 የአባሪ በተገቢ ሁኔታ የተቀመጠ ቢሆንም የፎቶ ግራፍ አባሪዎች ውስንነት
ይታይበታሌ፡፡
 ማረጋገጫ መጨረሻ በጥናቱ የመጨረሻ ገፅ መቀመጡ ያሌተሇመዯ ነው፡፡
 አባሪ ሊይ የቃሇ-መጠይቅ ጥያቄዎችና የፍቃዴ ፎርም አሌተያያዘም፡፡
 በአጠቃሊይ የትግዕስት አሇማየሁ ጥናታዊ ፁሁፍ ከቅርፅ አንፃር በብዙ ክፍተቶች
የተሞሊ ነው፡፡
2. ጥናታዊ-ፁሁፈ ከይዘት አንፃር

አጠቃል የጥናት ዋና ጭምቅ ማሳያ ሲሆን ጥናታዊ ጹሁፈ ከእዚህ አንፃር አንዴ አጠቃል
ማሟሊት ያሇበትን በመጠኑ ያሟሊ ሲሆን በጥናት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዳነት ቃሇ-መጠይቅ፣
ምሌከታና የቡዴን ውይይት የተጠቀመ መሆኑን ገሌፃ በተጨማሪም የተሇያዩ ፁፎች ሇመረጃ
ምንጭነት እንዯተጠቀመች ትገሌፃሇች፡፡ የመዛግብት ዲሰሳ የጥናቱ አካሌ መሆን ሲኖርበት
አሌተካተተም፡፡የጥናቱ ግኝት ተረኮች ሇማህበረሰቡ ምን ፊይዲ እንዯሰጡት አጥኝዋ ስታስቀምጥ
የበታችነት በላሊ ማህበረሰብ ግፉት ይዯርስበት ስሇነበር የበታችነት ስሜት ማህበረሰቡ
ስሇሚሰማው ከታሊሊቅ ሰዎች በተረኮቹ ራሱን ያስጠጋ ነበር ትሊሊች…. ነገር ግን የተረኮቹ
ፊይዲ በጥቅሌና በተናጠሌ በውሌ የታየ ስሇመሆኑ ያጠራጥራሌ፡፡
በምዕራፍ አንዴ ውስጥ የጥናቱ ዲራ አፃፃፍና ይዘት ማሟሊት ያሇበትን ዋና የዲራ ባህሪያት
ይዟሌ፡፡ ከአጥኝው ርዕሰ ጉዲይ ወዯ ፅንሰ ሀሳባዊ ቅኝት dedactive approch የጠከተሇ
በመሆኑ የጥናታዊ ፁሁፈን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው፡፡ ነገር ግን ዲራው የጥናቱን
ውስንነት…ችግር የሚያሳይ አይዯሇም፡፡የጥናቱ ዋና አሊማ፣ዝርዝር አሊማዎችና የጥናቱ
ጥያቄዎች ጥናቱ ሇተነሳበት ርዕሰ-ጉዲይን ተከትሇው የተዋቀሩ/የተሰናሰለ መሆናቸው የጥናቱ
በጎ ጎኖች ናቸው፡፡ ነገር ግን ተረኮቹ ሇመፇጠራቸውና ሇመቆየታቸው የሚሇው ዝርዝር አሊማና
ጥያቄ የሚቶልጅ ወይም creation methology ፅንሰ-ሀሳብ ውስጥ የሚታይ ጉዲይ ሲሆን
የሚቶልጅ አንጻር ዯግሞ የጥናቱ ትኩረት አይዯሇም፡፡ የጥናቱ ወሰን ከቦታ ወሰን አንፃር
በዚገም ወረዲ የትኞቹን ቀበላዎች እንዲካተተና እንዲሊካተተ በግሌፅ አሊስቀመጠም፡፡ በፎክልር
ጥናት ውስጥ ትሌቅ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ የርዕሰ ጉዲይ ወሰኑ ተጨባጭና ግሌፅ
አይዯሌም፡፡

በምዕራፍ አንዴ የጥናቱ ዘዳ ተብል የተገሇፀው ከሚባሌ ይሌቅ ስነ-ዘዳ ሆኖ በዝርዝር የጥናቱ
አይነቱ፣እይታ፣ፍሌስፍናና ዱዛይን ተሰናስሇው በግሌፅና አጥኝዋ እንዳት ጥናቷን ሌሰራ
እንዲሰበች፣ሇምን እነዚህን መጠቀም እንዯፇሇገች በምክኒያት ማስቀመጥ ሲኖርባት ተዘሇዋሌ፡፡
አጥኝው በቀጥታ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያዎችን በመጀመሪያ ያስቀመጠ ሲሆን የመረጃ
መሰብሰቢያዎቹን ቃሇ-መጠይቅ፣ ምሌከታ የቡዴን ውይይት ሇምንና በምን መስፇርት
እንዯመረጠች፣ እንዳት እንዯተጠቀመችባቸውና ቁጥራቸውን በምክኒያት አሊስቀመጠችም፡፡
በየትኛው ቀበላ ምን ያህሌ ናሙናዎችንና ቃሇ መጠይቅ ሰዎችንና የቡዴን ተተኳሪዎችን
ሇናሙናነት እንዯወሰዯች አይገሌፅም፡፡ መዛግብት ነክ ፁሁፎችን መጠቀሟን በፁሁፏ ውስጥ
ትገሌፃሇች ነገር ግን የመዛግብት ዲሰሳ እንዯ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዳ አሌተቀመጠም፡፡
በአጠቃሊይ የጥናቱ ስነ-ዘዳ እጅግ በክፍተቶች የተሞሊ ነው፡፡ ሳይንሳዊነት የሇውም፡፡

የመረጃ አተናተን ዘዳ functional ንዴፇ-ሀሳብ ሇመተንተኛነት መጠቀሟን አጥኝዋ ትገሌፃሇች


ነገር ግን ጠቀሜታዊነት ንዴፇ ሀሳብ እንጅ መተንተኛ አይዯሇም፡፡ ጥናቱ መተንተኛ የሇውም
ማሇት ይቻሊሌ፡፡የአተናተን ቅዯም ተከተሊዊ ሂዯት በግሌፅ አያሳይም፡፡

ሁሇተኛው ወሳኝ ምዕራፍ ክሇሳ ዴርሳናት ሲሆን መያዝ ያሇበት ፅንሰ-ሀሳባዊ ቅኝት፣ንዴፇ-
ሀሳባዊ ቅኝትና ተግባራዊ ስራዎች ሲሆን በዚህ ጥናት በፅንሰ-ሀሳባዊ ቅኝት ቦታ ንዴፇ-ሀሳብ
ቅኝት በተሳሳተ መንገዴ ተቀሊቅል ቀርቧሌ፡፡ በንዴፇ-ሀሳብ ስር የፎክልርና የተረክ ጉዲዮች
የተዲሰሱ ሲሆን በይዘት ዯረጃ የተብራራ አይዯሇም፡፡ ተረክ የተመራማሪዋ ዋና ጉዲይ በመሆኑ
በጥሌቀት መዘርዘር፣መከፊፇሌና conceptualized መዯረግ ሲገባው ቁንፅሌ ነው፡፡ የፎክልር
ጉዲይ የቀረበበት ሁኔታ ግሌብ ነው፡፡ በተሇይ አጥኝዋ የተጠቀመችው ንዴፇ-ሀሳብ አንዴ ብቻ
ሲሆን ቁንፅሌ አቀራረብ ያሇው ነው፡፡ አንዴ ንዴፇ-ሀሳብ መሆኑ ጥናቱን ዯካማ ያዯረገው
ይመስሇናሌ፡፡ በተግባራዊ ንዴፇ-ሀሳብ መጠቀስ የነበራባቸው ዋና ዋና ሀሳባውያን ሇምንጭነት
አሌጠቀመችም፡፡በአጠቃሊይ ክሇሳ ዴርሳናቱ ቁንፅሌ ብቻ ሳይሆን የምርምር ሙግት/discourse
በእጅጉ ይቀረዋሌ፡፡ ዯካማ ነው፡፡ ነገር ግን የጠዛማጅ ጥናቶች ቅኝት በዝርዝርና በተገቢ ሁኔታ
መሰራቱ የጥናታዊ ፁሁፈ ጥንካሬ ነው፡፡

የመጨረሻው ምዕራፍ የጥናቱ የመረጃ ትንት ሲሆን በፅንሰ-ሀሳብና በጥረ-መረጃው ተሰናስል


መቅረቡ ሳይንሳዊ ነው፡፡ የመረጃ ትንተናው በስፊት የመዛግብት ዲሰሳ የተጠቀመ ሲሆን አጥኝዋ
በጥናቷ መዛግብት ዲሰሳን አሇመጠቀሟ ተቃርኖ ነው፡፡ የሚገርመው አንዲንድቹ ተረኮችም
በቃሇ-መጠይቅ የተገኙ ሳይሆን በመዛግብት ተፃፇው አጥኝዋ የተጠቀመችባቸው እንጅ
ከማህበረሰቡ primary ምንጭ የጠገኙ አይዯሇም፡፡ አጥኝዋ በመረጃ መሰብሰቢያነት ምሌከታን
እንዯተጠቀመች የገሇፀች ቢሆንም በመረጃ ትንተና ወቅት ውስን ሆኖ ታይቷሌ፡፡ በመጨረሻም
የአንዴ ጥናት ዋና መነሻና መዴረሻ ግኝትና መፍትሄ ነው፡፡ አጥኝዋ ተረኮቹ ከትውሌዴ ወዯ
ትውሌዴ እንዱተሊሇፈም ሆነ ተጨማሪ ጥናት እንዱዯረግ ያስቀመጠችው
አስተያየት/recommendations አሇመኖሩ ጥናቱን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋሌ፡፡

በአጠቃሊይ የትግዕስት አሇማየሁ ጥናታዊ ፁሁፍ በቅርፅም ሆነ በይዘት በስፊት ክፍተቶች


የተስተዋለበት ነው፡፡ አጠቃል፣የዲራ አፃፃፍ፣የተግባራዊ ስራዎች ቅኝት፣የመረጃ ትንተናና
የዋቢ-መፅሀፍት አዯራዯር የጥናቱ ጥንካሬዎች ናቸው፡፡
2. መጣጥፍ -ሁሇት

ይህ አጭር መጣጥፍ በዓዴቃኔ ማርያም መካነ ቅደሳን አንዴነት ገዲም የሚነገሩ ተረኮች
በሚሌ በ2007 ዓ.ም ሇፎክልር የሚስተርስ ዱግሪ የተሰራ ጥናታዊ ፅሁፍን ከቅርፅና ይዘት
አንፃር ሇመገምገም የተሞከረበት ነዉ፡፡

የጥናት ወረቀቱ አቅራቢ፦ ወንዯሰን ሞሊ

የገፅ ብዛት፦ ሰማኒያ

1. ከቅርፅ አንፃር

 አጥኚዉ በምስጋና ጀምሮ አጠቃል አስከትል በአምስት ክፍልች ያቀረበ ቢሆንም ከዚህ
በፉት መካተት የነበረባቸው የፇተኝ ቦርዴ አባሊት ስም፣ የአማካሪ ማረጋገጫ
አሌተካተተም
 ማዉጫ ሇይ ምዕራፍ አሌተቀመጠም ነገር ግን በአምስት ክፍልች እንዯቀረበ
በመግቢያው ሊይ ይገሌፃሌ
 በመጀመሪያው መግቢያ ክፍሌ ከቅርፅ አንፃር መካተት ያሇባቸው በአግባቡ
የተካቱና ተሰናስነው የቀረቡ ናቸው፡፡ ነገር ግን የጥናቱ ወሰን ሊይ ይበጁኛሌ ያሌኳቸው
ሊይ ብቻ ተወስኛሇሁ በሚሌ ግሌፅ በሆነ መንገዴ ሳይወሰን ታሌፏሌ ፡፡ይህንን እንዯ
ዴክመት አይተነዋሌ፡፡
 ጥናቱ ጠቀሜታ በሚሇው ክፍሌ ጠቀሜታዎቹ ተነጣጥሇው በዝርዝር አሌተቀመጡም
ይህም እንዯ ክፍተት የሚታይ ነው፡፡
 የጥናቱ ዘዳ ከመረጃ አሰባሰብ እና አተናተን አንፃር በሚገባ ተገሌጿሌ፡፡
 ክሇሳ ዴርሳን በሚሇው ክፍሌ የንዴፇ ሀሳብና የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት በሰፉው
ማዴረጉ ጠንካራ ጎኑ ነው፡፡
 አካባቢያዊ ዲራ በቀረበበት ሦስተኛው ክፍሌ አሊማዬ ብል ከተነሳበት ሀሳብ አንፃር
በዝርዝር መቅረቡ አግባብነት አሇው ያስብሇዋሌ፡፡
 በትንተና ምዕራፍ ሂዯቱ ከይዘታቸዉ አንፃር በንዑሳን ክፍልች ከፊፊል ግሌፅና
ተጠየቃዊ አካሄዴ ተከትሎሌ፡፡
 በማጠቃሇያ ክፍሌ ከምዕራፈ እንዲሚጠበቀዉ የጥናቱ አጠቃሊይ ግኝትና አሰተያየት
አስቀምጧሌ፤ይህም ጠንካራ ጎን ነዉ፡፡
 ዋቢ መፃህፍት በተገቢ ሁኔታ መቀመጡ የጥናቱ ጠንካራ ጎን ነው፡፡
 አባሪ አሇማያያዙ ዯካማ ጎኑ ነው፡፡

በአጠቃሊይ የወንዯሰን ሞሊ ጥናታዊ ፁሁፍ በርካታ ጠንካራ ጎኖች ቢኖሩትም መጠነኛ ዯካማ
ጎኖች ታይተዉ በታሌ፡፡ ከፎክልር የመስክ ሂዯት አንጻር መግቢያ የክሇስ ዴርሳንና አካባቢ
ዲራ(በከፉሌ) በቅዴመ መስክ ሂዯት ማጠቃሇያ የተከናወኑ ሲሆን አካባቢያዊ ዯግሞ
ዲራ(በከፉሌ) እና የተረኮቹ አሰባሰብ በመስክ ወቅት የተከናወኑ ተግባራት ናቸው ማጠቃሇያ
ክፍለ ሊይ ዯግሞ በዴህረ መስክ ስር ይካተታሌ፡፡

2.ከይዘት አንጸር

አጠቃል የየምዕራፍቹ ጭምቅ ማሳያ እንዯሆነ ይታወቃሌ በሆኑም አጠቃል ማሟሊት ያሇበትን
ያሟሊ ሲሆን በጥናቱ ወሰን በሚሇው ዋና ክፍሌ ያሌተጠቀሰ የተረኮች ብዛት አጠቃል ሊይ
በቁጥር ተወስኖ ይገኛሌ ፡፡ ይህም የራሱ ክፍሌ ሊይ ሳይቀመጥ አጠቃለ ሊይ እንዳት መጣ
የሚሌ ጥያቄ ፇጥሮብናሌ፡፡

በመግቢያው አጠቃሊይ የምዕራፍን ጨመቅ የቀረበበት ክፍሌ ሲሆን የጥናቱ ዲራ አቀራረብ


ከጠቅሊሊ ወዯ ዉስን የሄዯና የዲራ አንፃፃፍ ባህሪያትን ተከትል የቀረበ በመሆኑ ጠንካራ ጎኑ
ነዉ፡፡ በዲራ ክፍሌ ዉስጥ የተካተቱትየጥናቱ ዓሇማ ፤ የጥናቱ ጥያቄዎችና ጠቀሜታ እርስ
በእርስ ተመጋቢ የሆኑና በአግባቡ የተዋቀሩ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን በጥናቱ ወሰን ከናመና
አመራረጥ አንፃር ተወስኖ በግሌፅ አሌተቀመጠም፡፡ አሊማና ዝርዝር አሊማ የተገሇፀበት ቃሌ
ተመሳሳይነት ይታይበታሌ፡፡ የጥናት የመረጃ ትሊትና ከዓሊማዉ አንፃር በንዑስ ክፍሌ ከፊፊል
በንዴፇሀሳብና በመስክ ወቅት በምሌከታና ቃሇመጠየቅ ተሰበሰበትዉን መረጃ መሰረት በማዴረግ
ሳይንሳዊና ግሌጽ በሆነ መንገዴ ተተንትኗሌ፡፡የአንዴ ጥናት መዴረሻዉ የሆነዉን ግኝት
አንኚዉ በሚገባ ገሌፆ የራሱን አስተያየት አክል ማጠናቀቁ ማጠቃሇያውን የተሳካ
አዴርጎታሌ።

በአጠቃሊይ የወንዯሰን ሞሊ ጥናት በቅርፅም ሆነ በይዘት የታዩት ክፍተቶች እንዲለ ሆነዉ


ከጥናቱ ዘዳ ፣ ተዘማጅ ፁሁፍች ቅኝት ዯሰሳ ፡ በትንተና ስሌት ፣ ዋቢ መፃህፍት አጠቃቀምና
ማጠቃሇያ ጠንካራ ጎኖች ናቸዉ፡፡
3. መጣጥፍ - ሶስት
ይህ አጭር መጣጥፍ በዯሊንታ ወረዲ የአቡሸቴ እና የ አ ኧይ ቦላ ቃሌ ግጥሞች ይዘት ጥናት
በሚሌ መኮንን አስማማዉ 2007 ዓ.ም ሇፎክልር የማስተርስ ዴግሪ የማማያነት የቀረበ
ጥናታዊ ፁሂፍን ሇመገምገም የሞከረ ነዉ፡፡

1. ከቅርፅ አንፃር

 የመጀመሪያና ሁሇተኛ ሽፊን የአማካሪና ፇታኝ ማንነት የተገሇፀ ቢሆንም አማካሪና


ፇታኝ ቦርዴ አባሊት ማረጋገጫ የላሇዉ መሆኑ ክፍተት ነዉ
 ፅሁፍ በአጠቃል ጅምሮ ምስጋናን አስከትል ሙዲየ ቃሊትን ጨምሮ አካባቢያዊ ካርታ
አስቀምጦ ወዯ ማዉጫ ይመራናሌ፡ ከምስጋና ከጠቃልን ማስቀዯሙ ከቅርፅ አንጻር
የጠየቃዊ ነዉ ብሇን አናምንም ።ጥናቱ ከአዯረጃጀትአንፃር በስዴስት ምዕራፎች ተቀምጦ
ሳሇ በአጠቃል ሊይ አምስት ክፍልች አለት በማሇት ይገሌፃሌ በመሆኑም
ሇማጠቃሇያው ምዕራፍ ሳይሰጠው አሌፏሌ ይህ የጥናቱ ክፍተት ነው።
 ሙዲየ ቃሊትና አካባቢዊ ገሇፃ ካርታ ማቅረቡ በይዘቱ ዉስጥ ሇሚያጋጥሙ የቃሊትና
የቦታ እንግዴነትን የሚቀንስ በመሆኑጠንካራ ጎኑ ነዉ፡፡ በመግቢያዉ የትናቱን
አዯረጃጀት በመግሇፅ ይጀምራሌ ይህም በዚህ አካሄደ ግሌፅ ስሇሚያዯርግ ጥሩ
መንዯርዯሪያ ሆኖ አግኝቸነዋሌ መተካት ያሇባቸዉ የጥናቱ ዲራ፣ አሊማ፣ ጥያቄ
ጠቀሜታ ወሰንና የጥናቱ ዘዳ እጅግ በተዯራጀና ግሌጽ በሆነ ሁኔታ ተቀምጠው
መገኘታቸ ው ጠንካራ ጎን ነዉ፡፡ክሊስ ዴርካን ክፍሌ ከንዴፇ ሃሳባዊ ቅኝት የተዛማች
ጽሁፎች ቅኝት ቀዴሞ መምጣቱ ቦታው አይዯሇም፡፡
 በማጠቃሇያው የሚጠበቀዉን አጠቃሊይ ግኝትና አስተያየቱን አስቀምጧሌ፡፡
 ዋቢ መፃህፍት የቁሌፍ አቀባዮች ስም ዝርዝርና አባሪዎች በሚገባ ተዯራጀተዉ
ተገሌፀዋሌ ይህም ጠንካራ ጎኑ ነው፡፡

በአጠቃሊይ የመኮንን አስማማዉ ጥናታዊ ጽሁፍ ከቅርፅ አንፃር በአመዛኙ ጠንካራ ጎኞች
ቢሆኑም የተጠቀሱት ዯካማ ጎኖች ታይተውበታሌ፡፡ ከፍክልር የመስክ ሂዯት አንፃር ከክፍሌ
አንዴ በትሌመ ጥናት የሚከናወኑ መሆናቸዉ፡፡ የመግቢያዉና ክሇስ ዴርሳን በቅዴመ መስክ
የተከናዉና ሲሆን አካባቢዊ ዲራና የመረጃው አሰባሰብ በቦታው በመገኘት በምሌከታና ቃሇ
መጠይቅ የተገኙ መረጃዎች በመሆናቸው በመስክ ወቅት ክንውን ሲሆኑ የመረጃ
ትንተናና የማጠቃሇያ ክፍለ ዯግሞ የዴህረ መስክ ሂዯት ነዉ፡፡
2. ከይዘት አንፃር

 ከቅርፅ አንጻር አጠቃል ምስጋናን ቀዴሞ መምጣቱ እንጂ ከይዘት አንጻር የአጠቃልን
ባህሪ በሚገባ የያዘና ሇሁለም ጥያቄዎች መሌስ የሚሰጥ ነዉ፡፡
 ክሇሳ ዴርሳን ክፍሌ ያሇ ቦታው ቢቀመጥም የንዴፇ ሀሳብ ዲሰሳው ከምንነትና ፊይዲ
አንፃር የተሇያዩ ምሁራንና መፃህፍትን በመጥቀስ አብራርቷሌ ። የተዛማጅ ፅሁፎች
ቅኝት ክፍሌ የተዲሰሱት ጥናቶች በቂ ሆነው አሊገኘናቸውም፡፡
 አካባቢያዊ ዲራ በመግቢያው ሊይ በካርታ ማስቀመጡና በዚህ ክፍሌ ገሇፃ ማዴረጉ
መሌካም ቢሆንም ሰፉ ሆኖ አግኝተነዋሌ።
 በክፍሌ አራት የቃሌ ግጥሞቹ አዯራረስ እና አከዋወን በሚሇው ርዕሰ ጉዲይ አጥኚው
ቦታው ሊይ በመገኘት ኢ_ተሳትፏዊ_ ምሌከታና ቃሇ መጠይቅ በማዴረግ መረጃውን
እንዯሰበሰበ ይገሌፃሌ። ነገር ግን በመሰክ ቅዴመ ዝግጅት ወቅት ከዘረዘራቸው አስፇሊጊ፥
ቁሶች መሀሌ መቅረፀ ዴምፅ አሊካተተም በመሆኑም ቃሇ መጠይቁን በመቅረፀ ዴምፅና
አሌያዘም ? የሚሌ ጥያቄ ፇጥሮብናሌ ። በክፍሌ አምስት ትንተና ክፍሌ በቅዴመ መስክ
እና በመስክ ወቅት የሰበሰባቸውን መረጃዎች መሠረት በማዴረግ መረጃውን በቅዴመ
ተከተሌ ፣ በአይነት እና ባስቀመጠው አሊማ መሰረት በሚገባ ተተንትኗሌ።
 በማጠቃለያውም ከማጠቃለያ በሚጠበቀው ልክ የተገኘው ግኝት፣ ፋይዳና የአጥኚው አስተያየት በስጋት ድምፀት
ተገልጿል። ይህም መደምደምያው አግባብነት ያለው ነው ያስብለዋል።

በአጠቃሊይ የመኮንን አስማማው ጥናት በቅርፅም ሆነ በይዘት የታዩ ጥቂት ክፍተቶች እንዲለ
ሆነው ሙዲየ ቃሊትን መጠቀሙ፣ አካባቢያዊ ዲራ በካርታ ማስዯገፈ፣ የጥናት ዲራውን
በተዯራጀ መንገዴ ማቅረቡና በማጠቃሇያ የሚጠበቀውን ግኝትና አስተያየት ማስቀመጡ
ጠንካራ ጎኑ ናቸው።

You might also like