You are on page 1of 16

የፎክሎር የመስክ ምርምር

ELFo 622

የንባብ ጽሑፍ ስድስት


19/02/2013
የፎክሎር የመስክ ምርምር ሂደቶች
• ባለፈው ንባብ በአጠቃላይ የምርምር ሂደቶች የሚባሉትን አይታችሁዋል፡፡ እነዚሁ ሂደቶች
በፎክሎር የጥናት መስክ ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉበትን ሁኔታ ስንቃኝ በዋናነት ሶስት
ሂደቶችን እናገኛለን፡፡የሂደቶቹ መከፋፈያም መሰረት የሚያደርገው መስክን ይሆናል፡፡
እነርሱም፡- ቅድመ መስክ ሂደት፤የመስክ ወቅት(ጊዜ መስክ) እና ድህረ መስክ ሂደት
ናቸው፡፡ ቅድመ መስክ ሂደት የሚባሉት ለምርምሩ አላማ የሚሆኑ መረጃዎችን የሚገኙበት
ቦታ ተሄዶ ከባህሉ ባለቤቶች ከመሰብሰብ በፊት ያሉትን ተግባራት የሚመለከት ነው፡፡
እነዚህም በአንድ በኩል ባለፈው ንባባችሁ የተገለጹት ስድስት ጉዳዮች ሲሆኑ፣ በሌላ በኩል
ደግሞ መረጃ ለመሰብሰብ ወደ መስክ ከመኬዱ በፊት የሚከናወኑ ተግባራት የሚከተሉት
ናቸው፡፡
ርዕሰ ጉዳይን መለየት
• በምርምር ሂደት ተቀዳሚው ጉዳይ ርዕሰ ጉዳይን (ችግርን) መለየት ነው፡፡ አንድ
አጥኚ ምርምር ለማድረግ ሲነሳ ምንን ጉዳይ ማጥናት እንዳለበት መለየት እና
መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ሀሳቡም የሚመጣው ከግል ልምድ፣ በየጊዜው ከሚነበቡ
ድርሳናት እንዲሁም በተለያዩ ኮርሶች ከሚነሱ መሰረታዊ ነጥቦች ሊሆን ይችላል፡፡
የርዕሰ ጉዳይ መረጣው ከተከናወነ በሁዋላ ቀጣዩ ጉዳይ የሚሆነው ሀሳቡን ወደ
ጽሑፍ ቀይሮ ርዕስ ማድረግ ነው፡፡ ርዕሱም ጉዳዩ (ችግሩ) የሚገለጽበት መንገድ
ነው፡፡
• ተመራማሪው የምርምር ርዕስ ለመምረጥ ሲነሳ “ይህ ጉዳይ መረጃ የሚሻና መረጃስ
ሊገኝለት የሚችል ነው?” የሚለውን ጥያቄ ቀድሞ ማሰብ በጉዳዩ ላይም መዘጋጀት
ይኖርበታል፡፡
ርዕሰ ጉዳይን መለየት
• ለዚህም ምክንያቱ ሳይንሳዊ ሂደቶችን ማለፍን የማይጠይቁ ጉዳዮች በምርምር ርዕስነት
ሊመረጡ ስለማይገባ ነው፤ ሳይንስ ተጠየቃዊ ሂደት በመሆኑም ጭምር ነው፡፡
• ለምሳሌ፡- መንገድ ላይ አየሄድን አንድ በእድሜ የጠና የመኪና መንገድ ለመሻገር
ተቸግሮ ብናይ ያን ሰው ለመርዳት ብንፈልግ ለችግሩ መፍትሄ የምንሰጠው መንገዱን
ለማሻገር መሞከር አልያም ሊያሻግረው የሚችል ሰውን በመጥራት ነው፡፡
• ይህም ለምን መሻገር አቃተው እንዴት መሻገር አቃተው የሚሉትን ጠይቀን ለዚያ
መልስ ካገኘን በሁዋላ የምንተገብረው አይደለም፡፡ ምሳሌ ሁለት በአንድ አካባቢ
የተከሰተን የደን መጨፍጨፍ በሚመለከት (ችግሩ የደን መጨፍጨፍ ነው) ጉዳዩን
ማጣራት ወዲያው መፍትሄ ሊሰጠው አይችልም፤ ምክንያቱም የደን መጨፍጨፉም
በጊዜ ሂደት የመጣ በመሆኑ ምክንያቶቹን በተለያዩ አማራጮች ማጣራትን
ይጠይቃል፡፡
የቀጠለ
• በመሆኑም ከቀረቡት ምሳሌዎች ሂደታዊ ምርመራን የሚጠይቀው ሁለተኛው
ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ የምርምር ችግር (problem) የምንለው
የተመራማሪውን ትኩረት የሳበ ተመራማሪው ወደ አንድ ግብ ለመድረስና መፍትሄ
ሊሻለት የሚፈልግ፣ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ እውቀትና ጉልበት ተቀናጅተው መረጃ ላይ
በመደገፍ ግላዊ ስሜትንና ሀሳብን ሳያስገባ ነባራዊውን አለም በሚያንፀባርቅ
መልኩ ትንተናና ማብራሪያ ሊሰጥበት ያሰበና የተነሳበት አንዳች ጉዳይ ነው
(ያለው፣2009 ዓ.ም.) ሊባል ይችላል፡፡
• ችግር ተመራማሪው በመረጃ ላይ ተደግፎ የራሱን ግለ ሃሳባዊነትና ስሜት ሳያስገባ
ነባራዊውን ዓለም በሚያሳይ መልክ ትንትና ለማድረግ የሚነሳበት ጉዳይ ነው
ማለት ይቻላል፡፡
የርዕስ መረጣ ምንጮች
በተለያዩ ደረጃዎች ለሚሰሩ የምርምር ስራዎች ርዕስ መምረጥ ሲታሰብ ለርዕስ መረጣው
አቅጣጫ/ፍንጭ/ ከሚከተሉት ማግኘት ይቻላል፡፡
• በመስኩ ያሉ መጣጥፎች፣ መጽሐፎች እና የመመረቂያ የጥናት ወረቀቶች
• ኮንፍረንሶች ወርክሾፖች እና አቅርቦቶች(presentations)
• በተለያዩ የጥናት ስራዎች ውስጥ የሚቀርቡ አስተያየቶች ይሁንታዎች እና የመፍትሔ
ሀሳቦች
• የተለያዩ ኮርሶች
• የስራ ቦታዎች
• በመስኩ ካሉ ምሁራን ጋር በመወያየት
• በቤተመጻህፍት ከሚገኙ የኢንተርኔት ምንጮች ወዘተ.
በርዕስ መረጣ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች
• አንድ ተመራማሪ ለምርምር የሚሆንን ርዕስ በሚመርጥበት(በምትመርጥበት) ጊዜ
የሚከተሉት ጉዳዮች ከግምት የሚገቡ ናቸው፡፡
• የተመራማሪው ፍላጎት፡- የምርምር ስራ በተለይ እንደፎክሎር ባሉ ዘርፎች
የሚከናወን ጥናት የተመራማሪውን እውቀት፣ ጉልበት እና ጊዜ የሚፈልግ ነው፡፡
በመሆኑም የሚጠናውን ጉዳይ ውጤታማ እንዲሆን በተመራማሪው ፍላጎት ላይ
የተመሰረተ ቢሆን ይመረጣል፡፡
• የምርምር ስነምግባራዊ ተቀባይነት፡-የምርምር ስራ ሲካሄድ እንደ አጠቃላይና
እንደየዘርፉ ሊሟሉ የሚገባቸው ስነምግባራዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ ስለዚህ በየትኛውም
መስክ በሚካሄድ ጥናት ርዕሰጉዳዩ ከመመረጡ በፊት በተመረጠው ዘርፍ
ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን ተመራማሪው/ዋ/ ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ስነምግባራዊ ጉዳዩ ከተመራማሪው፣ከሚጠናው ርዕሰ ጉዳይ እንዲሁም ከተጠኚው
ቡድን አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡
የቀጠለ
• •ተቋማዊ እገዛ/እርዳታ፡- ይህ አንድ ርዕሰ ጉዳይ የሚጠናበትን አቅጣጫ እና
ስፋት/ጥበት ከሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ምርምሩ በተቋማት ገንዘብ
ድጋፍ የሚሰራ ከሆነ በተቋሙ ህግና ደንብ መገዛት የግድ ይሆናል፡፡ የጉዳዩ
የአጠናን አቅጣጫም ሆነ ወሰንም እንዲሁ፡፡
• •የጥናቱ አስፈላጊነት፡- ይህ ርዕሰ ጉዳዩ መጠናቱ ምን ጠቀሜታ አለው?
ባይጠናስ ምን ይሆናል? ለሚሉና መሰል ጥያቄዎች መልስ መስጠትን
ይመለከታል፡፡
• •ለመስኩ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ፡- ጉዳዩ ከዚህ በፊት በመስኩ ከተጠኑ
ጉዳዮች የተለየ ምን አዲስ ነገር ይዞ ይመጣል? የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ
መሆን አለበት፤
• •የጊዜ ተግዳሮቶች፡- ልክ እንደ ተቋማዊ እገዛ ሁሉ የጊዜ መስፋትና ማነስ
በሚጠናው ጉዳይ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ይኖራል፡፡ በመሆኑም
ተመራማሪው አንድን ችግር ሊመርጥ ሲነሳ (ስትነሳ) ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ
የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይገባዋል (ይገባታል)፡፡
የቀጠለ
• ጥልቀት/ወሰን፡- ይህም እንደቀደመው ሁሉ ተመራማሪው ባለበት ደረጃ ምን ላይ
መወሰን አለበት፣ በምን ያክል ጥልቀትስ ጉዳዩን ሊያጠናው ይገባል የሚለውን
ይመለከታል፡፡ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የሚሰራ የምርምር ስራ በኤምኤ ደረጃ
ከሚሰራው ስራ በስፋትም በጥልቀትም የተለየ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ
ተመራማሪው በክፍል ውስጥ ከሚማረው ትምህርት በተጨማሪ ባለበት ደረጃ
በመስኩ የተሰሩ ቀደምት ጥናቶችን ማንበብ ይኖርበታል፡፡
• •ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፡- አንድን የምርምር ጉዳይ ለመምረጥ በምናስብበት ጊዜ
ከግምት ልናስገባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ምርምሩ የሚሰራበትን
የገንዘብ አቅም ይመለከታል፡፡ ተመራማሪዋ(ው) የገንዘብ፣ የጊዜ ሁኔታን ከግምት
ማስገባት ይኖርባ(በ)ታል፡፡
የርዕስ አቀራረብ

• የምርምር ርእስ በምናሰፍርበት • የማያስፈልጉ ቃላትን ማስወገድ


ጊዜ ልናተኩርባቸው የሚገባንን ይቻል ዘንድ እያንዳንዱ ቃል
ነጥቦች በተመለከተ ከዚህ በታች በትክክል ተፈላጊውን መልእክት
በሰፈሩት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ማስተላለፍ መቻሉን ማረጋገጥ፤
ማተኮር ያስፈልጋል፡፡ • ቃላትና ሀረጎች ሰዋስዋዊ በሆነ
• በተቻለ መጠን የርእሱን ሀሳብ መንገድ ተስተካክለው
ሳያንዛዙ በጥቂት ቃላት መግለፅ መቀመጣቸውን ማረጋገጥ፡፡
መቻል፤
• የቀረበው ርዕስ ከሞላጎደል
• ርእሱ የሚገለፅበትን ሀረግ በተቻለ
ጉዳያችንን ጨምቆ የሚገልጽልን
መጠን አጭር ለማድረግ
መሆን አለበት፡፡
መሞከር፤
የምርምር ጥያቄዎችን ማዘጋጀት
• በምርምር ሂደት አቀራረብ የተለያዩ ቅደም ተከተሎችን ከተለያዩ ምንጮች ልናገኝ
እንችላለን፡፡ ባለፈው ባያችሁት የምርምር ሂደት ቅደም ተከተል መሰረት ከርዕስ ቀጥሎ
የሚመጣው የምርምር ጥያቄዎችን ማዘጋጀት ነው፡፡ ቀጥለን እንመልከት፡-
• የምርምር ጥያቄዎች የምርምሩን ችግር ለመፍታት መነሻም ሆነ መድረሻ የሆኑ ሀሳቦች
የሚንጸባረቁበት ነው፡፡ ይህም ተመራማሪው ሊፈታው ያሰበው ችግር ምንጩን፣ሂደቱን እና
ይዞታውን በመመርመር መልስ ሊያስገኙ የሚችሉ ቁልፍ ጉዳዮች የሚንጸባረቁበት ነው፡፡
ጥያቄዎቹም የመረጃውን አይነት፣ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን፣ መረጃ ሊገኝ
የሚችልባቸውን አካላት ሁሉ ይወስናሉ፡፡ በተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች
መተግበሪያነት ከሚቀርቡ ጥያቄዎች የሚለዩትም ሰፊና ጥልቅ ሀሳብን የሚይዙ
በመሆናቸው ነው፡፡
የምርምር ዲዛይን(ንድፍ)(Design)
የምርምር ንድፍ (ዲዛይን)
• የምርምር ዲዛይን የሚባለው የምርምር ስራው አጠቃላይ ቢጋርን
የሚያሳይ ሲሆን ተመራማሪው ከመጀመሪያው የምርምር ሂደት ጀምሮ
የምርምር ስራው እስከሚጠናቀቅበት ድረስ የሚያከናውናቸውን
ተግባራት የሚመለከት ነው፡፡ በመሆኑም የምርምር ንድፍ
በሚዘጋጅበት ጊዜ የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ በማስገባት
ሊሆን ይገባል፡፡
በምርምር ንድፍ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች
• (i) ጥናቱ ስለምንድነው/ የሚጠናው ምንድነው?(What is the study
about?)
• (ii) ምርምሩን ማድረግ ለምን አስፈለገ (Why is the study being made? )
• (iii) ጥናቱ የት ይካሄዳል ? (Where will the study be carried out? )
• (iv) ምን አይነት መረጃ ያስፈልገዋል ? (What type of data is required? )
• (v) አስፈላጊው መረጃ ከየት ይገኛል ? (Where can the required data be
found?)
• (vi) ምን ያክል ጊዜ ይፈልጋል ? (What periods of time will the study
include?
የምርምር ንድፍ/ዲዛይን
• (vii) የትኛው የናሙና አይነት ተግባራዊ ይደረጋል (What
will be the sample design?)
• (viii) የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎቹስ ምን ምንድናቸው
(What techniques of data collection will be
used? )
• (ix) መረጃው እንዴት ይተነተናል (How will the data be
analysed? )
• (x) የመረጃው ዘገባ በምን መንገድ ይቀርባል (In what style
will the report be prepared? )
በአጠቃላይ
• አንድ የምርምር ንድፍ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያሙዋላ ይገባል፡፡
• (a) ግልጽ አነሳሽ ምክንያት;
• (b) መረጃ ለመሰብሰብ የታቀዱ ዘዴዎችና የጥናቱ አካሄድ;
• (c) ሊጠና የታሰበው አካላይ(population);
• and (d) መረጃውን ለማደራጀትና ለመተንተን ተግባራዊ ሊደረጉ የታሰቡ
ዘዴዎች ናቸው፡፡(Khotari,2004,32)
• በምርምር ሂደት መሰረት ከምርምር ንድፍ ቀጥሎ የሚመጣው መረጃ መሰብሰብ
ነው፡፡ ነገር ግን በአካዳሚያዊ የምርምር ስራ አንድ ተመራማሪ ወደመስክ
ለመሰማራት የምርምሩ ርዕስ በሚመለከተው አካል ይሁንታ ያገኘ ሊሆን ይገባል፡፡

You might also like