Professional Documents
Culture Documents
March 8
March 8
ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን
አጋሩ
አስተያየቶችን ይዩ
Print
በሴቶች ጉዳዮች በኩል የታዩ መሻሻሎች የሚንጸባረቁበት፣ አስፋላጊ ለውጦች እንዲደረጉ ጥሪ የሚቀርብበት፣
በዓለም ደረጃ ለጾታ እኩልነት ለሚሰሩ ሴቶች ብርታትና ቁርጠኝነት እውቅና የሚሰጥበት እለት ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ዛሬ እ.አ.አ. አቆጣጠር ማርች ስምንት ማለት መጋቢት ስምንት በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚከበር የሴቶች ቀን
ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ. በ 1975 ዓ.ም. ዕለቱን የሴቶች መብትና የዓለምአቀፍ ሰላም
የሚታሰብበት እንዲሆን ሰየመው። በ 1977 ዓ.ም. ደግሞ በመንግስታቱ ድርጅት በውሳኔነት ጸደቀ።
በሴቶች ጉዳዮች በኩል የታዩ መሻሻሎች የሚንጸባረቁበት፣ አስፋላጊ ለውጦች እንዲደረጉ ጥሪ የሚቀርብበት፣
በዓለም ደረጃ ለጾታ እኩልነት ለሚሰሩ ሴቶች ብርታትና ቁርጠኝነት እውቅና የሚሰጥበት እለት ነው።
ሴቶችና ልጃገረዶች በዓለም ደረጃ የትምህርት እድል ለማግኘት፣ እኩልነታቸው በህግ ፊት እንዲከበር፣ ሴቶች
በባንክ ገንዘብ የማስቀመጥንና የማውጣትን፣ ስልጠናን የጎልማሶች ትምህርትን ለመሳሰሉት ወንዶች
ለሚያገኙት መሰረታዊ አገልግሎትም ተደራሽነት እንዲኖራቸው ስለሚያደርጉት ትግል እንዲታወቅ
የሚያስችልበት እለትም ነው። ሴቶች መሰረታዊ የሆነው ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበርና የማንም ንብረት
ሳይሆኑ ነጻ ስዎች ተደርገው እንዲታዩ ሲታገሉ ኖረዋል።
ሴቶችና ልጃገረዶች ካለፉት 41 ዓመታት ወዲህ በተሻለ ሁኔታ ይገኛሉ። ግን አሁንም ቢሆን ብዙ የሚቀር ነገር
አለ። በዓለም ደረጃ በድህነት ከሚፈረጁት ሰዎች አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። በማንኛውም የዓለም ክፍል
የወንዶችን ያህል መብትና እድል አለን ሊሉ የሚችሉ ሴቶች የሉም። ስራቸው ተገቢ ዋጋ አያገኝም።
ከወንዶች ጋር በአንድ አይነት ስራ ላይ ተሰማርተው ወንዶች ከሚያገኙት ክፍያ በ 30 እና በ 40 ከመቶ ያነሰ
ነው የሚከፈላቸው። በኢኮኖሚ ራሳቸውን አለመቻላቸው ራሱ በሌላውም ህይወታቸው ሃይል
እንዳይኖራቸው ያደርጋል። በጾታ ላይ ለተመሰረተ ጥቃት ይጋለጣሉ።
EMBED SHARE
ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በዓለም ዙርያ
EMBED SHARE
The code has been copied to your clipboard.
640 360
width px height px
Share on Facebook
Share on Twitter
0:533:332:51
እ.አ.አ. እስከ 2030 ዓ.ም. በሚኖረው ጊዜ ውስጥ (በ 15 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ማለት ነው) የሴቶች እኩልነት
የሚረጋገጥበት ጊዜ እንዲሆን፣ በያዝነው ዓመት ትኩረት ተሰጥቶበታል።
ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ 15 ዓመታት ውስጥ ዘላቂ የልማት አጀንዳ እንዲኖር ያወጣው እቅድ
አካል ነው። ድርጅቱ የጾታ እኩልነትና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንዲሁም ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ
ለማደረግ ካለው ቁርጠኛነት ጋር የተያያዘ ነው።
ይህም በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውም አይነት አድልዎና ማንኛውም አይነት በሴቶች ላይ የሚፈጸም
ጥቃት እንዲቆም፣ ከእድሜ በታች የሆኑ ልጃገረዶችን በግዴታ መዳርና ግርዘት ማቆም የመሳሰሉትን
ያካትታል። ልጃገረዶችና ወንዶች ጥራቱ የተጠበቀ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ማድረግም በድረጅቱ ግብ
ውስጥ ተካቷል።
ማንኛውም እድገት የሚፈልግ ማህበረሰብ ሴቶች ራሳቸው እንዲችሉ ከወንዶች ጋር እኩል መብት
እንዲኖራቸው ለማድረግ መጀመር ይኖርበታል።
ዛሬ ተከብሮ በዋለው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶችና ልጃገረዶች ክብር በመስጠት ዓለም ሴቶችና
ልጃገረዶች የሚጨቆኑበት ሳይሆን መላ የብቃት መሰረታቸውን የሚተገበሩበት እንዲሆን ቆርጠን የምንነሳበት
እለት ነው ሲል የዛሬው ርእሰ-አነቀጽ ሀተታውን አብቅቷል።
በጋዜጣዉ ሪፓርተር
የዓለም ሴቶች ቀን በየዓመቱ በውጮቹ አቆጣጠር ማርች 8፣ በኢትዮጵያ የካቲት 29 እየተከበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከ 1967
ዓ.ም. ወዲህ በየዓመቱ እያከበረችው ሲሆን፣ እንደወቅቱ ርዕዮተ ዓለም ፖስተሮች ሲዘጋጁለት ኖሯል፡፡ ከ 36 ዓመት በፊት
(1971 ዓ.ም.) በኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ዘመን፣ በአዲስ አበባ የዓለም ሴቶች ቀንን
ለማክበር የተሠራጨውን (በግራ) እና ዘንድሮ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት በፖስተርና በፖስት ካርድ መልክ
ያሳተመውንና ያሠራጨው እዚህ ላይ ይመለከቷል፡፡ (ሔኖክ መደብር)
ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ?
18 የካቲት 2019
ወጣቶች
የዓለም የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያው ውስጥ በሚመጣው እሁድ ማለትም የካቲት 29 ቀን የዓለም የሴቶች ቀን ይከበራል። የኢትዮጵያ ሴቶች
ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር የዘንድሮው መሪ ቃል ደግሞ «የሴቶች ደህንነትና መብት መከበር ለሰላማችንና
ለህልውናችን መሠረት ነው » የሚል ነው።
Volume 90%
አውዲዮውን ያዳምጡ።10:14
የዓለም የሴቶች ቀን
በየዓመቱ በጎርጎሪዮሳዊው መጋቢት 8 ቀን የዓለም የሴቶች ቀን ይከበራል። ከዚህ የሴቶች ቀን ጋር በተያያዘ የመብት እና የእኩልነት
ጥያቄዎች አብረው ይነሳሉ። አንድ የዓለም ባንክ ጥናት እንደሚያመላክተው በዓለም ላይ 143 ሃገራት የሴቶች እና ወንዶች እኩልነትን
በሕገ መንግሥታቸው ላይ ያሰፈሩ ቢሆንም ስምንት ሃገራት ማለትም ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ሲውዲን፣ አይስላንድ፣
ሉክስንበርግ፤ ፈረንሳይ እና ሊትዌኒያ ብቻ ናቸው የሴቶች እና የወንዶች እኩልነት መብትን የሚያረጋግጡት። ጥናቱ ትኩረቱን
ያደረገውም ሥራን፣ የቤተሰብ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ የጡረታን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ላይ ተመርኩዞ ነው። የሚያሳዝነው ነገር
ግን እስካሁን በየትኛውም ሀገር የወንድ እና የሴቶች እኩልነት ሙሉ በሙሉ አለመረጋገጡን ነው የግሎባል ጀንደር ጋፕ መዘርዝር
የሚጠቁመው።
የዘንድሮው የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሴቶች ቀን መሪ ቃል "I am Generation Equality" ወይም «የእኩልነት ትውልድ ነኝ»
የሚል ነው። በርግጥ አዲሱ ወይም የአሁኑ የኢትዮጵያ ትውልድ እኩልነቱ ተረጋግጧል ብሎ ያምናል? DW ያነጋገራቸው ወጣቶች
እንደሚሉት በፊት ከነበረው ሁኔታ አሁን ላይ የተሻለ ነገር ነው ያለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከግንዛቤ ሁኔታ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው
የሚለው አንድ ወጣት ወደ ተግባር ሲመጣ ብዙ ተግዳሮቾች አሉ ይላል። « በተለይ ባለሁበት ባህር ዳር አካባቢ ገጠር የሚገኙ ሴቶች
ላይ የወንዶች ተፅዕኖ ከፍ ያለ ነው።» ይላል። ወንዶ ገነት የምትኖረው ወጣትም ይህን ትጋራለች « አንዳንድ አካባቢ ሴት ወጣቶች
ሰርተው እንዲለወጡ አያደርጓቸውም የቤት እመቤት ብቻ ሆነው እንዲቀሩ ነው የሚፈልጉት»
ወይዘሮ ስመኝ ውቤ በኢትዮጵያ ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ናቸው። የሚሰሩበት መሥሪያ ቤት
የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ቀንን ያከበረው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚከበርበት ዕለት አራት ቀን ቀደም ብሎ ነበር። « በዓሉን
በሁለት መልክ ነው ያከበርነው አንዱ ጥቃት ደርሶባቸው በተለያዩ ማዕከል ውስጥ ላሉ ሁለት ተቋማት ድጋፍ እንዲሰጡ በማድረግ
ሲሆን ሌላው ደግሞ የመድረክ ውይይት በማካሄድ ነበር። » ይላሉ የአለም የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 109 ኛ ጊዜ
በኢትዮጵያ ደግሞ ለ 44 ኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሆነ የሚናገሩት ሚኒስትር ዴታ። የተለያዩ የሃገሪቱ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት
ይኸው ውይይት ላይ አሁንም ለሴቶች ፈተና ናቸው ተብለው የተነሱት ጉዳዮች ወይዘሮ ስመኝ እንደሚሉት ሴቶች ላይ
የሚፈፀመውት የተለያዩ ጥቃቶች ናቸው።
የዘንድሮው የሴቶች ቀን መሪ ቃል «የሴቶች ደህንነትና መብት መከበር ለሰላማችንና ለህልውናችን መሠረት ነው» የሚል ነው።
ሚኒስቴሩ ይህንን ርዕስ የመረጠበትንም ምክንያት በሀገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ነው ። « በሀገራችን በተለያዩ ምክንያት ግጭቶች
አሉ። በዚህ ደግሞ ዋንኛ ተጠቂ እየሆኑ ያሉት ሴቶች እና ህፃናት ናቸው» ይላሉ ወይዘሮ ስመኝ። መሥሪያ ቤታቸው ጥቃት
ከሚለው አንዱም የታገቱት ሴት ተማሪዎችን ጉዳይ ነው። « በሴቶች ላይ እንደዚህ አይነት ጥቃቶች የሚደርሱ ከሆነ የሚጎዳው
አጠቃላይ ማህበረሰቡ ነው። »
ሌላው የዘንድሮውን የዓለም የሴቶች ቀንን በሚመለከት የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ትኩረት እንዲሰጥበት ያለው ጉዳይ
የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎን በሚመለከት ነው።
« የሴቶች የፖለቲካ ለውጥን በሚመለከት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ለውጥ ነው ያለው» የሚሉት ወይዘሮ ስመኝ
«በመጪው ምርጫ ምን ያህሉ ፓርቲ ሴቶችን ወደ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማምጣት ጥረት ያደርጋል» የሚለው እንደሚያሳስባቸው
ተናግረዋል።