You are on page 1of 20

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የመማር ማስተማር ዕቅድ(Educational lesson plan)


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የመማር ማስተማር ዕቅድ(Educational lesson plan)
ማንኛውም ስራ ስኬታማ እና ውጤታማ የሚሆነው ታቅዶ ሲሰራ ነው፡፡
የመማር ማስተማር ስራን ውጤታማ ለማድረግ ሂደቱን በጥንቃቄና በሚገባ ማቀድ እጅግ አስፈላጊ ነው
የትምህርት ዕቅድ ከመሰራቱ በፊት ዓላማ ሊለይለት የሥራው ቅደም ተከተል ሊወሰን
አስፈላጊ ግብአቶች ሊዘጋጁለት ይገባል ይህን ስራ የሚያቀናጅልን ነገር እቅድ ልንለው እንችላለን፡፡
የመማር ማስተማር እቅድ አካላት(elements of lesson plan)
የመማር ማስተማር የሚይዛቸው ዋናዋና አካላት የሚከተሉት ናቸው
1.የመማር ማስተማር ዓላማዎች Objectives
ዓላማ የአንድ ነገር መዳረሻ ጫፍ ሲሆን በማማር ማስተማር ስራ በተማሪዎች ዘንድ የአእምሮ፣የአመለካከት
እና የትግበራ ለውጥን ያሳየናል፡፡
1.የአእምሮ እድገት (ለውጥ)፡ Cognitive በእእምሮ ላይ ብቻ የሚመጣን መዳበር ወይም ለውጥ
የሚያመለክት ሲሆን ስድስት ደረጃዎች አሉት፡፡
1.1.እውቀት Knowledge አእምሮ አንድን ሐሳብ (ቃል) በቃል በመሸምደድየሚይዝበት ደረጃ ሲሆን
በአእምሮ እድገትም የመጀመሪያው ነው
1.2.ግንዛቤ፤ comprehension ይህ በአእምሮ እድገት ሂደት ውስጥ የተማሩትን ሀሳብ በራስ አባባል መግለጽን
ያመለክታል ይህም መረዳትን ያመለክታል ለምሳሌ የተማሩትን ከራስ ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር መግለጽ
1.3.ትግበራ ፤application አንድን ሐሳብ የተረዳ ሰው ያንን ሐሳብ በሌላ ቦታ ከሌላ ሁኔታ እና ሐሳብ ጋር
በማገናኘት ለአእምሮ ጥያቄ መልስ መስጠትን የሚያመለክት ደረጃ ነው ለምሳሌ የእግዚአብሔር ቸርነቱ
እንዴት እንደሚታይ ( እንደሚገለጽ)የተማረ ሰው በህይወቱ (በኑሮው)፣እግዚአብሔር አምላክ የቸርነት
ስራውን ሲሠራ ሲያይ ያንን መቀበል የቸርነቱ ውጤት መሆኑን መገንዘብ ትግበራ ይሆናል
1.4.ትንተና፤ analysis በነገሮች መካከል ያለን ልዩነት አእምሮ ማየት የሚችልበት ደረጃ ነው በዚህ ደረጃ
በነገሮች እና ሐሳች መካከል ያለውን ልዩነት ብቻ ሳይሆን አንድነትንም ማየት እና መረዳት ይጠበቃል፡፡
1.5.ማቀናበር፤ synthesis በሐሳቦች ፣በነገሮች፣ወዘተ መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት መመልከት የቻለ
አእምሮ ባለው ላይ አንድ አዲስ ሐሳብ ወይም ነገር (አዲስነቱ ለዓለም ላይሆን ይችላል)፣ይመሰርታል፣ይህም
ማቀናበር ይባላል፡፡
1.6.ግምገማ፤evaluation ይህ ደረጃ አእምሮ ጠቃሚውን ከጎጂው በመለየት ( አንድነት እና ልዩነትን መሰረት
አድርጎ)ውስጣዊ (የራስ የሆነ)፣እና ውጫዊ (የባለሙያዎች) መስፈርትን ተንተርሶ የሚበጀውን የሚመርጥበት
፣የሚወሰንበት እና የሚመዘንበት ደረጃ ነው፡፡
2.የአመለካከት ዕድገት (ለውጥ)፤ Affective domain በሚማረው ሰው ሰብእና ውስጥ የስሜት ለውጥ ወይም
እድገትን የሚያመለክተው ይህ ምድብ አምስት ደረጃዎች እነሱም
2.1.መቀበል፤ receiving በዚህ ደረጃ ተማሪው አንድን የትምህርት ሐሳብ ያስፈልገኛል ወይም ይጠቅመኛል
በሚል እምነት በትኩረት መከታተል ይጠበቅበታል ይህ እውን የሚሆነው ትምህርቱ ከሚማረው ሰው ሐሳብ
ፍላጎት፣ችሎታ፣ልምድ፣ወዘተ ጋር ተጣጥሞ ሲቀርብ ነው፡፡
2.2.መመለስ፤ responding በዚህ ደረጃ የሚማረው ሰው የሚማረውን የትምህርት ሐሳብ ያገባኛል
ይመለከተኛል በሚል እምነት ከራሱ የሚጠበቅበትን ተግባር ለማከናወን ፈቃደኛ ሆኖ መነሳትን ብሎም
ተግባራዊ ምላሽ መስጠትን ያመለክታል፡፡
2.3.ዋጋ መስጠት ወይም እሴት ማበጀት፣ valuing ለሚማረው ትምህርት እምነት ማዳበርን ወይም
ለእቃዎች ለክስተቶች ወዘተ እሴት ማበጀት የሚጠበቅበት የአመለካከት ደረጃ ነው፡፡
2.4.ማደራጀት፤ organizing በዚህ ደረጃ የሚማረው ሰው ለተለያዩ ነገሮች ሁኔታዎች ወዘተ እሴት
ከማዳበሩም ባሻገር ያዳበሩትን እሴቶች እንዲጣጣሙ( እንዳይቃረኑ) አድርጎ ማስተሳሰር ይገባዋል ለዚህም
የሚጠቅመውን ከጎጂው በሚገባ ለመለየት ደጋግሞ መማር ማስታወስ ያስፈልገዋል፡፡
2.5.ጽኑነት፤ Characterization በዚህ ደረጃ የሚማረው ሰው የማይለወጥ ወጥ የሆነ ጽናት
የሚንጸባረቅበት፣በጊዜና በቦታ የማይለዋወጥ፣ አቋም ያዳብርበታል፡፡
3. የችሎታ ወይም የክህሎት እድገት(ለውጥ) psychomotor domain በሚማረው ላይ የሚከሰትን የችሎታ
ወይም የክህሎት መዳበር የሚያመለክት ሲሆን በዚህ ምድብ ውስጥ አምስት ደረጃዎችን ይዟል እነርሱም
3.1. ኩረጃ፤ Imitation ይህ ደረጃ የክህሎት እድገት ደረጃ መጀመሪያ ሲሆን ሰዎች ሲሰሩ ያዩትን ተግባር
ለማከናወን ባዩት መሰረት መስራትን ያመለክታል የዚህ ደረጃ መነሻው አንድን ተግባር ለማከናወን የሚያስችል
ውስጣዊ የሆነ ግፊት ሲሆን መገለጫው ደግሞ በውስጣዊ ግፊት ተነሳስቶ ተግባሩን ባዩት (በሰሙት)፣መሰረት
እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆነ የልምድ ገጽታ ማከናወንን ያመለክታል፡፡
3.2. መተግር፤ Manipulation ይህም መመሪያን፣በመቀበል፣የተሸለውን የአሰራር መንገድ በመምረጥ ተግባሩን
በዚያው መሰረት የማከናወን ደረጃ ነው ልምምድ በስፋትም የሚታይበት ደረጃ ነው፡፡
3.3.በትክክል ማከናወን precision ይህ ደረጃ ተግባርን በፍጥነት እና በጥራት ( በጥንቃቄ)ማከናወንን
ያመለክታልበዚህ ደረጃ ተማሪው ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት የተለያዩ ሂደቶችን የመቆጣጠር አቅሙ ከፍ
ያለ ሲሆን ነገሮችንም አንደአመጣጣቸው መመለስ ይችላል፡፡
3.4.በቅልጥፍና ማከናወን Articulation ይህ ደረጃ ተማሪው ቅደም ተከተል ያላቸውን የተለያዩ
ተግባራትየሚያከናውንበት ደረጃ ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ተግባራቱን በቅደም ተከተል የአገባብ (የአተገባበር)
ፍጥነትን እና ጥራትን ጠብቆ በቅደም ተከተላቸው ማከናወን ከተማሪው ይጠበቃል፡፡
3.5.ተፈጥሮአዊ ማድረግ Naturalization ይህ ደረጃ በክህሎት እድገት ደረጃ የመጨረሻው ሲሆን
በዝቅተኛ ኃይልና ጊዜ ተግባርን ማከናወን የሚቻልበት ደረጃ ነው ደረጃው ተግባሩን የህይወት አካል( የራስ
ተፈጥሮ አካል) የሚያደርግበት ደረጃ ነው፡፡
የትምህርቱ ይዘት፤ content
የሚማረው ሰው የሚማረው ትምህርት ሐሳብ ሲሆን መሰረቱ የመማር ማስተማር ዓላማ ነው፡፡ የመማር
ማስተማር ዓላማን መሰረትነት ላይ የሚመነጨው ይዘት ምንግዜም ዓላማውን ዳር ማድረስ የመያስችል
የትምህርት ሐሳብ ነው፡፡ይህን ሐሳብ የምናስተምረው ትምህርት ነው ሊሰኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የመሰረተ
ሃይማኖት ይዘት የቅዱሳት መጻህፍት ይዘት እና ትምህርት
የመማር ማስተማር መርጃ መሳሪያ teaching aid
ለተማሪዎች የሚቀርበው ትምህርት ግልጽ፣ ተጨባጭእና ከህይወት ጋር የተቆራኘ ለማድረግ መምህራን
የሚጠቁሟቸው ነጥቦችን እና ሁኔታዎችን ያጠቃልላሉ፡፡ሚዲያ የሚለው ቃል ሲፈታ መረጃ ያለውን
ማንኛውንም ነገር ወይም ሁኔታ ያካትታል፡፡ በዚህ መሰረት የመማር ማስተማር ሚዲያዎች የመማር
ማስተማረት ሂደቱ አካላት እንጂ ረዳት ተደርገው ሊገመቱ አይገባም ስለሆነም የትምህርቱን አካል መተው
ትምህርቱን ምውት ሊያደርገው ስለሚችል መምህራን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባቸዋል፡፡
የመማር ማስተማር ዘዴ methods of teaching
መምህራን ትምህርቱን የሚያቀርቡበት መንገድ ሲሆን መሰረቱ የትምህርቱ ዓላማ፣የትምህርቱ
ይዘት፣የተማሪው ፍላጎት፣ችሎታ ወዘተ ነው የመማር ማስተማር ዘዴ ዓላማውን ግብ ማድረስ ይጠበቅበታል
ለዚህም ስኬታማነት መምህራን የሚበጀውን ዘዴ መምረጥ እና አጠቃቀሙን አተገባበሩን በዕቅዱ ውስጥ
በሚገባ ማስፈር ወይም መተንተን ይገባቸዋል፡፡
የጊዜ ምደባ እና አጠቃቀም time allotment
አንድን ተግባር ማናወን የሚያስችል ዕቅድ በሚዘጋጅበት ጊዜ የተለያዩ ሂደቶችያላቸውን
ቅደም ተከተል (የቱ ከየቱ ቀጥሎ)እና መጠናቀቅ የሚገባቸውን ወቅት በማልት ረገድ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ አለው ፡፡ ስለሆነም በእቅድ ተግባራት የሚፈጁትን የጊዜ መጠን እና የተግባራቱ
ቅደም ተከተል ማሳየት ተገቢ ነው፡፡
የምዘና እና ግምገማ ዘዴ measurement and evaluation
በመማር ማስተማሩ ሂደት ዓላማው ስኬታማ መሆኑን በየጊዜው ለማረጋገጥ የሚያስችሉ
የምዘና እና ግምገማ ዘዴዎችን በየደረጃው መለየት በእቅዱ ውስጥም መካተታቸውን
ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡
የመማር ማስተማር እቅድ አዘገጃጀት lesson plan preparation
የመማር ማስተዘማር እቅድ በተለያየ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን ዋና ዋናዎቹም ዓመታዊ እቅድ(የኮርስ እቅድ)፣
ሳምንታዊ ዕቅድ፣እና ዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ ናቸው፡፡በዚህ ክፍል ትኩረት የምንሰጠው ለዓመታዊ
የትምህርት ዕቅድ እና ለዕለት ትምህርት እቅድ ነው፡፡
ዓመታዊ የትምህርት ዕቅድ Annual lesson plan
ዓመታዊ የትምህርት ዕቅድ መምህሩ ለአንድ የትምህርት ዓይነት የክፍል ደረጃ በዓመቱ ውስጥ
የሚያከናውናቸውን ዋናዋና ተግባራት በማካተት የሚያዘጋጀው እቅድ ነው፡፡ በመሆኑም በዚዘህ የትምህርት
እቅድ ውስጥ የትምህርቱ ዓላማ፣ የትምህርቱ ይዘት፣የመማር ማስተማር ዘዴዎች፣ መርጃ መሳሪያዎች
እንዲሁም የግምገማ ስልቶች ጠቅለል ባለ መልኩ ይገለጻሉ(ይታቀዳሉ)
ዓመታዊ የማስተማሪያ ዕቅድ ቅጽ
1. የሰንበት ትምህርት ቤቱ ስም ___________________________
2. የትምህርት ዘመን____________________________________
3.የመምህሩ ስም______________________________________
4.የትምህርቱ ዓይነት___________________________________
5.የማስተማሪያ ክፍል___________________________________
6.በዓመቱ ለትምህርቱ የተሰጠው ሰዓት__________________________
7.በዓመት ለትምህርቱ የተሰጠው የክፍለ ጊዜው ብዛት_______________________________
8. ለክፍለ ጊዜው የተመደበ ደቂቃ
9. የትምህርቱ ዋና ዓላማ
መንፈቀ ወር ሳምንት ዐቢይ እና ንዑስ ዝርዝር የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያ ምዘና እና ግምገማ ምርመራ
ዓመት ርእስ ዓላማዎች ዘዴ (ዋቢ ዘዴ
መጻሕፍት)
ዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ
ዕለታዊ የማስተማሪያ ዕቅድ የሚባለው በአንድ ክፍለ ጊዜ የሚተላለፈውን የትምህርት ዕቅድ ለማመልከት
ሲሆን በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች በዝርዝር ያሳያል
1.ዝርዝር ዓላማዎች
2.ዝርዝር የትምህርት ይዘቶች
3.የመምህሩ እና የተማሪው ተግባራት በዝርዝር
4.የመማር ማስተማር መሳሪያ(ሚዲያ)እና አጠቃቀሙ
5.የመማር ማስተማር ዘዴ እና አተገባበሩ
6.ምዘና እና ግምገማ ዘዴ እና አጠቃቀሙ
7. የጊዜ ድልድል እና ስርጭት በየተግባራቱ ያካትታል
ሁለት ዓይነት የዕለታዊ የማስተማሪያ ዕቅድ ቅጾች አሉየአግድም እና ቀጥተኛ ወይም ቁልቁል ዕቅዶች ሲሆኑ
ቀጥተኛው በዘብዛኛው ተማሪ እና ተግባርን ማእከል ያደረገ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመቅረጽ አመቺ
በመሆኑ ብዙዎች ይመርጡታል መምህራን ከሁለቱ የተመቻቸውን እና የመረጡትን መጠቀም ይችላሉ
ቀጥተኛ ዕለታዊ የማስተማሪያ ዕቅድ
1. የመምህሩ ስም
2. የትምህርቱ ዓይነት
3. የትምህርቱ ርዕስ ወይም ርዕሶች
4.ትምህርቱ የሚሰጥበት ዕለት እና ቀን
5.የክፍለ ጊዜ ርዝማኔ
6.የትምህርቱ ዝርዝር ዓላማዎች
የትምህርቱ ዓላማዎች በገላጭ ቃላት የተቀመጡ እና SMART
1. ውሱን (Specific)
2.ሊለኩ የሚችሉ (measurable)
3.ትክክለኛ የሆኑ (accuracy)
4.አስተማማኝ የሆኑ (reliable)
5. በጊዜ የተለኩ (Time frame) መሆን ይገባቸዋል እንዲሁም በተቻለ መጠን ከፍተኛ የባህርይ
ዕድገት ደረጃዎችን ቢያመለክቱ ይመረጣል፡፡
የመማር ማስተማር ሂደት

በዚህ ክፍል የመምህሩ እና የተማሪዎች ተግባራት በዝርዝር ይገለጻሉ እኚህ ተግባራት በአራት ንዑሳን ክፍሎች የተከፈሉ
ናቸው እነሱም

1. መግቢያ፤

-ያለፈውን ትምርት የሚያስታውስ

-የዕለቱን ትምህርት ከዓላማው ጋር አያይዞ የማስተዋወቅ ክፍል ነው

2.አቀራረብ

የዕለቱ ትምህርት የሚቀርብበት ዋናው ክፍል ሲሆን በዚህ ክፍል ውስጥ መምህራን የሚጠቀሟቸው መርጃ መሳሪያዎች
(ሚዲያዎች) ከመማር ማስተማር ዘዴዎች ጋር በተያያዘ መል የሚተገበሩ ረግባራት (የመምህር እና የተማሪዎች)
በዝርዝር በቅደም ተከተል የሚገለጽበት ይሆናል፡፡

3. ማጠናከሪያ

በዚህ ክፍል ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ይበልጥ በአእምሮዋቸው ውስጥ ሰርጾ እንዲቀር የሚያስችሉ ተግባራት
ይከናወናሉ እነዚህም ተግባራት በዕቅዱ ውስጥ በዝርዝር ይቀመጣሉ የዕለቱ ትምህርት በአጭሩ እንዴት
እንደሚከለስላቸው ይታቀድበታል

4. ግምገማ ይህ ክፍል ተማሪዎች የተማሩትን ትምርት እንዴት አድርገው እንደተቀበሉት በሚፈለገው መጠን
ትምህርቱን እንደተረዱት እና እንዴት እንደተገበሩት እና እንደሚተገብሩት የሚመዘንበት ክፍል ሲሆን ይህ ክፍ
በስተመጨረሻ ብቻ ሳይሆን መጀመሪያ መሃልም ላይ ሊሆን እና በአጠቃላይ ትምህርቱ እንዲያመጣ የሚፈለገውን
ውጤት ማምጣት አለማምጣቱን የምንለካበት ክፍል ነው፡፡
ዕለታዊ የትምህርት እቅድ አግድም ቅጽ
1. የመምህሩ ስም
2. የትምህርቱ ዓይነት
3.ትምህርቱ የሚሰጥበት ዕለት እና ቀን
4.የዕለቱ ትምህርት ርዕስ
5.ክፍለጊዜው
6.ለክፍለ ጊዜው የተሰጠው ደቂቃ
7.የትምህርቱ ዝርዝር ዓላማ
የጊዜ የትምህርቱ ዋና ዋና የመማር ማስተማር ሂደት መርጃ መሳሪያ ምዘና እና ምርመራ
ድልድል(ደቂቃ) ይዘቶች ግምገማ

የተማሪው ተግባር የመምህሩ ተግባር

መግቢያ መግቢያ

አቀራረብ አቀራረብ

ማጠናከሪያ ማጠናከሪያ

ግምገማ ግምገማ
የመማር ማስተማር እቅድ ለትላንቱም ለዛሬውም እንዲሁም ለነገውም የሚጠቅም ለመማር ማስተማር
ሂደት ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም መምህራን ይህንን ተገንዝበው ማስተማሪያ እቅድ አዘጋጅተው
ለእያንዳንዱ የሚመለከተው ክፍል እሱን አቅርበው እንዲያስተምሩ ይመከራል ምክንያቱም
የማስተማሪያ እቅድ የሚከተሉት ወሳኝ ጥቅሞችን ይሰጣል እና
ለሰንበት ትምህርት ቤቱ
1. መምህሩ ምን እንደሚያስተምር
2. ማንን እንደሚያስተምር
3. ለምን እንደሚያስተምር
4. በምን እንደሚያስተምር
5.ምን እንዳስተማረ እና ምን እንደቀረው
6. የቱ ጋር እንዳለ
7. መፍጠን መዘግየቱን ለመከታተል
8. ከዓላማው አንጻር አዛምዶ ትምህርቶቹን እያስተማረ እንደሆነ እንዲያውቅ ይረዳዋል
9. ለቁጥጥር እና ለክትትል ለግምገማም ያግዘዋል
10. መርሐግብሩን እንዲሁም ለትምህርቱ የተሰጠውን ሰዓት እንዲገመግም እና ማሻሻያ እንዲያደርግ
ለመምህሩ
1. ትምህርቱን መቼ ጀምሮ መቼ እንደሚጨርስ ያሳውቀዋል
2. በየጊዜው ምን ላይ ነበር ያቆምነው ከማለት ያድነዋል
3. ምን ለምን እንደሚያስተምር ያሳውቀዋል
4. ከዓላማ አንጻር ትምህርቱን እንዲያስተምር ያግዘዋል
5.የትምህርት መቆራረጥ እና መደጋገም እንዳይኖር ይረዳዋል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

You might also like