Professional Documents
Culture Documents
MUKURAB
MUKURAB
ምኩራብ» ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያኸል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቦታው ይገኝ እንደነበር ወንጌል “በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ”
(ማር 1፡21) ይላል፡፡
ተጠቅሷል፡፡)
ከዚህ ምእመናን ወደ ቤተ ለጸሎት ዘወትር ስለመገኘት እንድናውቅና እንድናስብ ይገባ ዘንድ ከጾሙ ሳምንታት ውስጥ
አንዱን ምኵራብ በሚል ስያሜ ተሰይሞ እንድናስበው ተደረገ (ማቴ.21፥13)፡፡ ስለዚህ ምዕመናን በዚህ የጸሎት ስፍራ
በቤተ ክርስቲያናችን ዘወትር እየተገኘን እንድንጸልይ፣ እንድንማርና ሕይወታችንን በዚያ እንድንመሠረት የእግዚአብሔር
ቃል “በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ” (ነህምያ 6፡10) ይለናል፡፡
ምኩራብ - ሦስተኛው ቤተ መቅደስ
ጌታ ኢየሱስ ግን “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ” ብሎ፣ “ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ”
ተናገረ። ለአይሁድ ይህ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር አልተዋጠላቸውም፤ አልተቀበሉትምም። እነርሱ የሚያወሩለት
መቅደስና ጌታ ኢየሱስ የሚያወራው መቅደስ ፈጽመው አይገናኙም ነበር። እነርሱ ስለሚፈርሰውና ከድንጋይ ስለ
ተሠራው ቤተ መቅደስ ሲያወሩ፣ እርሱ ግን ስለ ሕያውና ፈጽሞ ስለማይሞተው ሕያው ቤተ መቅደስነቱ ተናገራቸው።
ይህን ለማስተዋል የቤተ መቅደሶቹን ይዘት ማየቱ በጥቂቱ ይጠቅመናል።
ፊተኛው መቅደስ
ፊተኛው መቅደስ የተሰጠው ከእግዚአብሔር በሰሎሞን አማካይነት ነው። ያ መቅደስ ግርማውና ክብሩ እጅግ
የሚያስደንቅ ነበር፤ ሰሎሞን አባቱ ዳዊት ባከማቸው ሃብት፣ መቅደሱን የሠራው እጅግ አንቆጥቁጦ፤ አስውቦ ነበር።
እግዚአብሔር ራሱ በዚህ መቅደስ ተገኝቶ ሰሎሞንን በተደጋጋሚ በጨለማ ውስጥ ኾኖ ተናግሮት ነበር። ይህ መቅደስ
ለአይሁድ ብቻ ያይደለ፣ ከአይሁድ ውጭና የኪዳኑ አካል ያልኾነም ሰው መጥቶ በዚያ ቢጸልይ እግዚአብሔር
እንደሚሰማው ቃል የገባበት መቅደስ ነበር።
የመሰጠቱ ዋነኛ ዓላማም፣ እግዚአብሔር አምላክ ክብሩን በዚያ መቅደስ ውስጥ በመግለጥ፣ በሕዝቡ መካከል ለመኖር
ነበር። ሥፍራው የያህዌ ዋነኛ መታወቂያ፤ የአምልኮ ማዕከል፤ የእግዚአብሔር መገለጥ የሚታይበትም ቅዱስ ስፍራ
ነበር። በእርግጥ መቅደሱ የአይሁድ ብቸኛ ተስፋና የአምልኮአቸው ማዕከል ነበር፤ ነገር ግን ኀጢአትን ስለ ሠሩ እጅግ
ውብና ማራኪው ቤተ መቅደስ በናቡከደነጾር ፈርሶ ፍጹም ምድረ በዳ ኾነ።
ኹለተኛው ቤተ መቅደስ
ፊተኛው ቤተ መቅደስ ከፈረሰና እስራኤል ለሰባ ዓመታት ያህል በባቢሎን ምርኮ ከተገዙ በኋላ፣ በእነ ዘሩባቤል መሪነት
ኹለተኛው ቤተ መቅደስ ተገነባ። ምንም እንኳ ግንባታው እጅግ የተለያየ ቢሆንም፣ የኹለተኛው ቤተ መቅደስ ዓላማም
ከፊተኛው ቤተ መቅደስ የተለየ አይደለም። ከዚህም ባለፈ ታላቁ ሄሮድስ በአይሁድ ዘንድ ድጋፍና ተወዳጅነት ለማግኘት
ሲል፣ መቅደሱን ለአርባ ስድስት ዓመታት ያህል በሚማርክ መልኩ አድሶትና አስፋፍቶት ነበር። ነገር ግን ይህም መቅደስ
በ 70 ዓ.ም እስከ ዛሬ ድረስ ዳግም መሠራት እስከማይችል ድረስ ፈጽሞ ፈረሰ፤ ፈራረሰ፤ ወደመ።
እግዚአብሔር አንድን መቅደስ ለእስራኤል የሰጣቸው፣ ክብሩንና ራሱን ለእነርሱ ሊገልጥና ለዘወትርም በዚያ
እንደሚገኝ ኪዳን በመግባት ነበር።
ሦስተኛው ቤተ መቅደስ