You are on page 1of 4

ሰሙነ ሕማማት

በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እጅግ ከሚወደዱ እና ከሚናፈቁወቅቶች አንዱ ሰሙነ ሕማማት ነው፡
፡ በዕለተ ሆሳዕና ጀምሮ በዕለተትንሣኤ የሚጠናቀቀው እጅግ ላቅ ያለ መንፈሳዊ ሕይወት የሚታይበትጊዜ ነው፡
፡ በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς, Hagia
kai Megale Hebdomas ታላቁ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞሰሙነ ሕማማት፡፡
የሕማማትን ወቅት ከመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮክርስቲያኖች ያከብሩት እንደነበር የሚያሳዩ ጥንታውያን መዛግ
ብትአሉ፡
፡ በሕግ ደረጃ ክርስቲያኖች በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም ሥራነጻ ሆነው፣ ፍርድ ቤቶችም ተዘግተው እንዲከበሩ የወሰነ
ው ደግሞታላቁ ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡
እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዳዲስ ክርስቲያኖች ለመጠመቅይመርጡት የነበረው ጊዜ የትንሣኤን ቀን ነበር፡
፡ ለዚህም ሁለት ዓይነትምክንያቶች ነበሯቸው፡
፡ የመጀመርያው ሰሙነ ሕማማትን በልዩ ሁኔታጾመው በትንሣኤው ቀን መጠመቁ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ኃይልስለሚሰጥ ሲ
ሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስትምህርት መጠመቅ ከክርስቶስ ጋር ሞቶ ከክርስቶስ ጋር መነሳትነ
ውና ጥምቀቱን ከትንሣኤው ጋር አያይዘውት ነበር፡፡
የሕማማት ሰሞን የኦሪት ጊዜን የሚያስታውስ ሰሞን ነው፡
፡ አዳዲስክርስቲያኖቸም ይህንን ሰሞን ያለፈ ሕይወታቸውን ለማስታወስ እናለማልቀስ ብሎም ራሳቸውን ወደ ሐዲስ ዘመ
ን ለመለወጥይጠቀሙበት ነበር፡፡
በመጀመርያው መቶ ክፍለ ዘመን ከዓርብ ጀምሮ ሰሙነ ሕማማትንማክበር የተዘወተረ ነበር፡
፡ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግንስድስቱንም ቀን ማክበር የክርስቲያኖች ሥርዓት እየሆነ መጣ፡፡
ለዚሀም መነሻ የሆነው የአባቶቻችን ቀኖና የተሰኘው ከሐዋርያት ዘመንጀምሮ የተደነገጉ ቀኖናት መዝገብ በቦታው መዳረስ
ነው፡
፡ በዚህመዝገብ ዐንቀጽ 5 ቁጥር 19 ላይ «በሰሞነ ሕማማት ከሳምንቱሁለተኛ ቀን (ሰኞ) እስከ ቅዳሜ የሰንበት መዘጋጃ ቀ
ን ድረስ ጹሙ፡፡በእነዚህም ጊዜያት ከእንጀራ እና ከጨው፣ ከማባያም በቀር ሌላ ነገርአትብሉ፡
፡ ለመጠጥም ውኃ ብቻ ይሁንላችሁ» ይላል፡፡
የኛም ግብረ ሕማማት ይህንኑ የሐዋርያት ቀኖና በመጥቀስ በክፍልአንድ ሠላሳ አንደኛ ትእዛዝ በሚለው ርእስ ሥር «በሕ
ማማት ሰሞንከእንጀራ፣ ከጨው እና ከውኃ በቀር ምንም ምንም አትብሉ» ይላል፡፡
በ260 ዓም ለባሲሊደስ በጻፈው ደብዳቤ እያንዳንዷን የሰሞነሕማማት ቀን እና ሰዓት ከክርስቶስ መከራ ጋር በማያያዝ ገል
ጾ ነበር፡፡
በ2ኛው ወይንም በ3ኛው መክዘ ተሰባስቦ መጠረዙ የሚነገርለትየሶርያው ዲድስቅልያም ሰሙነ ሕማማት እንዴት መጾም
እንዳለበትይደነግጋል፡
፡ አቡሊዲስ ዘሮም በጻፈው የሐዋርያት ትውፊት (215 ዓም) ስለ ሰሙነ ሕማማት ሥርዓት ይደነግጋል፡
፡ እያንዳንዷንም ሰዓትከክርስቶስ መከራ ጋር ያገናኛታል፡፡
ሰሙነ ሕማማት አሁን ያለውን መልክ የያዘው በ4ኛው መክዘበኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ በቄርሎስ ዘመን ነው፡
፡ ፓትርያርክ ቄርሎስበመጨረሻዎቹ ዓመታት በኢየሩሳሌም ከሚከበረው የጌታችን ትንሣኤበፊት ያለውን ሰሙነ ሕማማት
እያንዳንዱን ቀን በማሰብ የሚከበርበትንሥርዓት ሠርቶ ነበር፡
፡ ከ381 እስከ 385 ወደ ኢየሩሳሌም ለመሳለምየሄደችው ኤገርያ የተባለች ስፔናዊ በኢየሩሳሌም እንዴት ሰሙነሕማማት
ይከበር እንደነበር የታሪክ መዝገብ ትታልናለች፡፡
ኤገርያ በጉዞ ማስታወሻዋ እንዲህ ትተርክልናለች
«በዓሉ የሚጀምረው በዕለተ እሑድ ነው፡
፡ በዚህ ዕለት ስለዓልዓዛር ትንሣኤ የሚገልጠው የወንጌል ክፍል ጠዋትይነበባል፡
፡ በሆሳዕና ዕለት ከሰዓት በኋላ ሁሉም ሰው ወደደብረ ዘይት ይወጣል፡
፡ ከዚያም በጸጥታ የዘንባባ ዛፍተሸክሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል፡
፡ ይህንንምበመጀመርያዎቹ ሦስት ቀናት ይፈጽማሉ፡
፡ ይህም ጌታችንማታ ማታ ከከተማዋ ወጥቶ በደብረ ዘይት ያደረገውንጸሎት ለማስታወስ ነው፡፡
በጸሎተ ኀሙስ ጠዋት ቅዳሴ ይቀደሳል፡
፡ (ይህም በዓመቱውስጥ በመስቀሉ መቅደስ ላይ የሚደረግ ቅዳሴ ነው)፡፡
ከሰዓት በኋላ ሌላ ቅዳሴ ተቀድሶ በደብረ ዘይት ተራራ ላይቆስጠንጢኖስ ባሠራው በኤሊዎና ቤተ ክርስቲያ
ን ሁሉምአብያተ ክርስቲያናት መብራት ያበራሉ፡፡ ከእኩለ ሌሊት በኋላደግሞ ወደ ጌቴ ሴማኒ ይጓዛሉ፡
፡ በዚያም እስከ ንጋትቆይተው የዓርብ ማለዳውን ወንጌል ለማንበብ ወደ ጎልጎታይመለሳሉ፡፡
ዓርብ ማለዳ ሁሉም መስቀሉን (በኢየሩሳሌም የነበረውንየጌታን መስቀል ነው) ቤተ ክርስቲያን አልባሳትያስ
ጌጡታል፡
፡ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጌታችንበጎልጎታ በተሰቀለበት ላይ ሁሉም ተሰብስቦ ጸሎትያደርሳል፣ ያለቅሳል
፣ ያዝናል፡
፡ በሠርክ ሁሉም አብያተክርስቲያናት ወደ ስቅለቱ ቦታ በመጓዝ በዚያ ስለ ስቅለቱ እናመቃብሩ የሚገልጠው
ወንጌል ይነበባል፡፡ ቅዳሜ ዕለትበየቤተ ክርስቲያኑ መብራት ይበራል፡፡»
ሰሙነ ሕማማትን ልዩ በሆነ ሁኔታ የማክበሩ ሥርዓት ከኢየሩሳሌምበተሳላሚዎች አማካይነት ወደ ልዩ ልዩ ሀገሮች መግባ
ቱ ይታመናል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበው ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ዘመንአንሥቶ ወደ ኢየሩሳሌም የመጓዝ ሥርዓት ነበራቸውና
ይህንን ሥርዓትቀድመው ሳይወስዱት አይቀሩም፡
፡ ቅዱስ ያሬድ ለዚህ ሰሙን የሚሆንሥርዓት መሥራቱን ስናይም ይበልጥ ያጠናክርልናል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ አሁን በምናየው መልኩ የሰሙነ ሕማማትምንባባትን ያዘጋጁት የገዳመ መቃርስ መነኮሳት መሆናቸውን
ግብረሕማማት ይገልጥልናል፡
፡ በእነዚህ የገዳመ መቃርስ አባቶች በመታገዝየእስክንድርያው ፓትርያርክ አቡነ ገብርኤል 2ኛ (1131-
1145) (የኛግብረ ሕማማት "ጸሐፊ የነበረው የታሪክ ልጅ አባታችን አባ ቅብርያል"ይለዋል፡
፡ ኢብን ቱርያክ የሚለውን ተርጉሞ ሳይሆን አይቀርም፡፡
) በእርሱ አስተባባሪነት ሊቃውንቱ ለየቀኑ እና ለየሰዓቱ የሚሆኑትንምንባባት ከብሉይ እና ከሐዲስ እያውጣጡ አዘጋጇቸ
ው፡፡
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ደግሞ የብሕንሳው ጳጳስ አቡነ ቡትሮስምንባባቱን ለየሰዓታቱ በተመጣጣኝ ሁኔታ በማካፈል ሁሉ
ም ቀናትተመጣኝ የሆኑ ሁሉም ዓይነት ምንባባት እንዲኖሯቸው አድርገዋል፡፡
ግብረ ሕማማታችንም «ከኦሪት እና ከነቢያት፣ ከነዌ ልጅ ከኢያሱ፣
ከንጉሥ ሰሎሞን መጽሐፍ ወስዶ ሁላቸው ትክክል እስከሆኑ ድረስበየሰዓቱ ሁሉ የሚገባውን አደረገ፡
፡ አባቶች ከተናገሩት ሁለት ሁለትተግሣፅ እና ምክር አንዱ በነግህ አንዱም በማታ እንዲነበብ አደረገ»ይላል፡፡
ግብረ ሕማማት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ የተተረጎመበትን ራሱ ግብረሕማማት ይነግረናል፡
፡ በመጽሐፉ መጨረሻ በሰላማ መተርጉም ጊዜ(1340 ( 1380) ገብቶ መተርጎሙን ያሳያል፡
፡ በግብረ ሕማማቱያለው ምንባብ አንዳንድ ጊዜ ከግብፁ ግብረ ሕማማት ይበልጣል፡፡
በግብፁ ግብረ ሕማማት የሌሉት ተአምረ ማርያም እና ተአምረኢየሱስም ተካተተዋል፡
፡ ይህም የኢትዮጵያ ሊቃውንት እጅ በትርጉሙእና በዝግጅቱ ሥራ ላይ መኖሩን ያመለክተናል፡፡
በግብረ ሕማማት ውስጥየሚገኙ ባዕድ ቃላት
በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃ
ላትይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡
ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡
፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለትነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ
ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡
ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ»በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡
ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡
እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው
ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡
ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው
ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው
አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-ki-riey enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተመንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡
አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-a-geh-e enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
Em-nees the-tee mo-zess-pota enti vasilia so
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተመንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስ
በን»ማለት ነው፡፡
ሥርዓተ ሕማማት
በሐዋርያት ቀኖና እንዲህ ይላል «ይልቁንም በእነዚህ በስድስቱ ቀኖችመጾም የሚችል ቢኖር ሁለት ሁለት ቀን ይጹም፡
፡ የማይችል ግን አንድአንድ ቀን ይጹም፡፡ ሌሎችን ቀኖች እስከ ዘጠኝ ሰዓት ይጹሙ፤
እችላለሁ የሚል ግን ፀሐይ እስኪገባ ይጹም፡
፡ በቤተ ክርስቲያንውስጥ ተሰብስባችሁ መጻሕፍተ ኦሪትን እና መጻሕፍተ ነቢያትን፣
የዳዊትንም መዝሙር እያነበባችሁ በምስጋና በጸሎት ዶሮእስከሚጮኽ ድረስ የሌሊቱን ሰዓት ጠብቁ፡፡
አንድ ምእመን የታመመ ቢሆን ወይም ክርስቲያን በሌለበት አገር ሆኖሳያውቅ የሕማማት ሰሞን ቢያልፍበት ወይንም በደዌ
ውስጥ ሆኖቢቀርበት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሰውነቱን በማድከምም ደስታን ያድርግ፡፡
ባለመፍራት እንዳይጠፋ ውስጣዊ ሰውነቱን ይመርምር፡፡
ጾምን ከመፍታታቸው በፊት ገላቸውን ይታጠቡ፤ ሁሉም መብራትየሚያበሩ ይሁኑ፡፡
የቻለ ዓርብ እና ቅዳሜ ሁለት ቀን ይጹም፤ ሁለት ቀን መጾም የማይችልበሽተኛ ቢሆን ግን ቀዳም ሥዑርን ይጹም፡
፡ የኀዘን ቀን ስለሆነች፡፡እንጀራ እና ጨውም አይቅመስ፡፡»

ዲ. ዳንኤል ክብረት

You might also like