You are on page 1of 2

ትንቢተ ሚክያስ

ሚክያስ ማለት በዕብራይስጥ ሚክያህ ወይም ሚካህ (ኤር 26፡18) ይባላል። ሚክያስ የስሙ

ትርጉም ''መኑ ከመ አምላክ ማን እንደ እግዚአብሄር ''ወይም እግዚአብሄርን የሚመስል ማን

ነው (ሚክ 7፡18፤መሳ 17፡1፤ኤር 36፡11)። ሞሬሽት ወይም ሞሬታዊው እየተባለም ይጠራ

ነበር። እንደ ነብዩ አሞጽ የገጠር ነዋሪ የነበረ ሰው ነው። ነብዩ ሚክያስ የተወለደው የፍልስጤም

ከተማ በሆነችው በጌት አጠገብ ከኢየሩሳሌም ደቡባዊ ምዕራብ 25 ኪሎሜትር ርቃ የምትገግኝ

''ሞሬት'' በተባለችዋ የይሁዳ ከተማ ናት (ሚክ 1፡1)። ስም የተሰየመውም የነብዩን ስም

ተከትሎ ነው፡፡
የትንቢተ ሚክያስ ይዘት

➢ ሰማሪያና ኢየሩሳሌም እንደሚፈርሱ1-3

➢ የተሰደዱት የአይሁድ ሕዝቦች እንደሚመለሱ፤ 2:12-13፣ 5:5-9፣ 7:7-20

➢ የእግዚአብሄር መንግስት መመስረትና ንግስና 4፡1-13 ፣ 2፡12-13

➢ የእግዚአብሄር ከቤተልሄም መወለድ። 5፡1-15

➢ የእግዚአብሄርና የህዝቡ ክርክር። 6፡1-16

➢ የእግዜብሀር ተግሳጽ ለ ለእስራኤል 7፡1-13

➢ ለእስራኤል ተስፋ 7፡4-20

በሀዲስ ኪዳን የተፈጸመው ትንቢት


እየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ይወለዳል

➢ ትንቢት አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትኾኚ

ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ዠምሮ ከዘለዓለም የኾነ፥በእስራኤልም

ላይ ገዢ የሚኾን ይወጣልኛል። 5፡2

የትንቢቱ ፍጻሜ ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ

ጊዜ፥እንሆ ሰብአ ሰገል የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴትነው።ኮከቡን በምሥራቅ

አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ማቴ 2፡1

እነርሱም፦አንቺ ቤተ ልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም፤ሕዝቤን

እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና


በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት። ማቴ 2፡5-6

You might also like