You are on page 1of 12

ደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን

የክረምት ቀዳማይ ትምህርት

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

ቡድን 4 ምደባ
ማውጫ
ትንቢተ ዳንኤል ................................................................................................................................................ 1
የትንቢቱ ይዘቶች.......................................................................................................................................... 1
ትንቢቱ ፍጻሜዉ ......................................................................................................................................... 2
ትንቢተ ዓሞጽ ................................................................................................................................................. 3
የትንቢቱ ይዘቶች.......................................................................................................................................... 3
ትንቢቱና ፍጻሜው ...................................................................................................................................... 3
ትንቢተ ሚልክያስ ............................................................................................................................................ 4
የትንቢቱ ይዘቶች.......................................................................................................................................... 4
ትንቢቱና ፍጻሜው ...................................................................................................................................... 4
ትንቢተ ሚክያስ............................................................................................................................................... 5
ትንቢተ ዮናስ ................................................................................................................................................... 6
የትንቢቱ ይዘቶች.......................................................................................................................................... 6
ትንቢቱና ፍጻሜው....................................................................................................................................... 6
ትንቢተ ናሆም ................................................................................................................................................. 7
ትንቢቱ ይዘቶች............................................................................................................................................ 7
ትንቢተ ዘካሪያስ .............................................................................................................................................. 8
ትንቢቱ ይዘቶች ........................................................................................................................................... 8
ትንቢቱና ፍጻሜ........................................................................................................................................... 9

i
ትንቢተ ዳንኤል

ዳንኤል ከ አበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሄር ፈራጅ ነው ማለት ነው።

የትንቢቱ ይዘቶች

ትንቢተ ዳንኤል ሁለት ክፍል አለው።

እነሱም

➢ የ ታሪክ ክፍል ዳን 1-6

1. የኢየሩሳሌም መከበብ፣ ጥበበኛና መልከ መልካም ልጆቿ ማለትም ዳንኤልና ሰለስቱ ደቂቅ(አናንያ ፣

ሚሳኤልና አዛርያ) ወደ ባቢሎን መማረክና ስማቸው መቀየሩ። ዳን 1፡1-7

2. ዳንኤልና ሰለስቱ ደቂቅ ጥራጥሬና ዉሃ ብቻ እንደሚመገቡና እግዚአብሄር ጥበብና ማስተዋልን

እንደሰጣቸው። ዳን 1፡7-21

3. ናቡከደነጾር ህልም አልሞ እንደረሳው፣ ህልሙን የሚፈታ ጠቢብ እንደጠፋና ጠቢባን እንዲጠፉ

ትዛዝ እንዳስተላለፍ። ዳን 2፡1-13

4. ዳንኤልና ባለንጀሮቹ እንዳይጠፉ ምህረትን ከ ፈጣሪ እንደለመኑና የናቡከደነጾር የህልሙ ሚስጢር

ለ ዳንኤል ራእይ እንደተገለጸለት፡ ዳን 2፡14-23

5. ሚስጥር ገላጭ የሰማይ አምላክ መሆኑን በማሳወቅ ህልሙን ከነ ሚስጥሩ ለናቡከደነጾር

እንደተናገር።ዳን 2፡24-35

6. ናቡከደነጾር ለ ደንኤል እንደሰገደና ደንኤልና ሰለስቱ ደቂቅ እንደተሾሙ። ዳን 2፡36-39

7. ናቡከደነጾር የወርቅ ምስል ማሰራቱና ለምስሉ ስገዱ ብሎ አህዛብን እንዳሰገዳቸው። ዳን 3፡1-7

8. አይሁድ ለ ምስሉ አንሰግድም ስላሉ መከሰሳቸውና ሰለስቱ ደቂቅ በ እቶን እሳት ዉስጥ

መጣላቸውና እንዲሁም እንደጸለዩና የ እግዚአብሄር መልአክ የሳቱን ነበልባል እንዳቀዘቀዘው። ዳን

3፡8-23

9. ናቡከደነጾር ከ ሰለስቱ ደቂቅ ጋር አራተኛ አካል እንዳየ እና በሰለስቱ ደቂቅ ፊት ለ እግዚአብሄር

እንደሰገደ እንደሾማቸው።ዳን 3፡24-30

10. ናቡከደነጾር ሁለተኛ ህልም አልሞ ዳንኤል እንደተረጎመለትና እንደመከረው። ዳን 4፡1-27

11. የናቡከደነጾር ህልም መድረስ እና ለእግዚአብሄር ምስጋና እንዳቀረበ። ዳን 4፡28-37

1
12. የናቡከደነጾር ልጅ ብልጣሶር መኳንቶችን እንደጋበዘ፣ለጣኦት አየሰገዱ ሳለ በንጉሱ ግንብ ላይ የሰው

ልጅ ጣት የጻፈችውን ቃል ዳንኤል መተርጎሙና የብልጣሶር ሞትና የ አርዮስ መንገስ። ዳን 5፡1-30

13. ዳንኤል ዳርዮስን እያገለገለ እያለ በ ሴራ ምክንያት ወደ አንበሳ ጉድጓድ መጣሉና መዳኑ እንዲሁም

በዳንኤል ላይ ያሴሩ መኳንቶች ከነ ቤተሰቦቻቸው በ አንበሶች መበላት። ዳን 6፡1-28

➢ የ ራዕይ ክፍል ዳን 7-12

1. ዳንኤል ያያቸው አራቱ ራእይና የህልሙ ፍች። ዳን 7፡1-28

2. ዳንኤል በ ራእይ አዉራ በግና ፍየል ማየቱና ህልሙን መላኩ ገብርኤል እንደተረጎመለት። ዳን 8፡1-27

3. ዳንኤል እየጸለየ እያለ መልአኩ ገብርኤል ስለ ሰባ ሱባዔዎች ራእይ እንደነገረው። ዳን 9፡1-27

4. በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው በራዕይ እንዳየና

እንዲሁምበሰሜንና በደቡብ ነገስታት መካከል ስለተደረጉ ነገስታት ይናገራል። ዳን 10-12

ትንቢቱ ፍጻሜዉ

1. ትንቢት በሌሊት ራእይ አየኹ፤እንሆም፥የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋራ መጣ በዘመናት

ወደሸመገለውም ደረሰ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ዳን 7፡13

የትንቢቱ ፍጻሜው በሌሊት ራእይ አየኹ እንሆም የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋራ መጣ በዘመናት

ወደሸመገለውም ደረሰ፤ወደ ፊቱም አቀረቡት። ራእይ 13 እስከ መጨረሻው

2
ትንቢተ ዓሞጽ

ዓሞጽ ማለት ጽኑዕ በእግዚአብሄር ማለት ነው። መፅሐፉ ስሙን ያገኘው ከነብዩ ነው፡፡ ደቂቅ ነቢያት ክፍል

የሚመደብ ነው፡፡ በቴቁሔ ሀገር ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነበረ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አልነበረም።

የትንቢቱ ይዘቶች

1. በእስራኤል ጎረቢት ሀገሮች ላይ(በደማስቆ፣በጋዛ፣ በኤዶም፣ በአሞንና በሞአብ) ላይ ስለሚመጣ ፍርድ።

ዓሞጽ1፡1-2፡5

2. በእስራኤል ላይ ስለሚመጣ ፍርድ 2፡6-16

3. በእስራኤል ላይ በኅጢያታቸው ምክንያት ስለሚመጣ ፍርድ 3፡1-6፡14

4. የአሚስያስና የአሞጽ ታሪክ7፡10-17

5. 5ቱ የፍርድ ራዕይ 7፡1-9፡ 10 1.

➢ የአንበጣ መንጋ 7፡1-3

➢ እሳት 7፡4-6

➢ ተጣሚ መስመር 7፡7-17

➢ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት እንቅብሬ 8፡1-14

➢ የተቀደሰን ቦታ ማቆርቆዝ 9፡1-10

6. በፍጻሜ ዘመን ስላለው ተስፋ 9፡11-15

ትንቢቱና ፍጻሜው

➢ በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለኹ፥የተናደውንም ቅጥሯን እጠግናለኹ፤

የፈረሰውንም ዐድሳለኹ፥እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለኹ፤ 9፡11

➢ የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለኹ፥የፈረሱትንም ከተማዎች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤

ወይንንም ይተክላሉ፥የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤አታክልትንም ያበጃሉ፥ፍሬውንም ይበላሉ። 9፡14

3
ትንቢተ ሚልክያስ

ሚልክያስ ከ ደቂቅ ነብያት መካከል አንዱ ሲሆን ትርጓሜውም መልእክተኛየ ማለት ነው።

ከነገደ ይሳኮር ማለትም ከ አባቱ ከ ፋሄልና ከ እናቱ ጽግኒ ተወልዷል።

የትንቢቱ ይዘቶች

1. እግዚአብሄር ህዝቡን እንደሚወድ ይናገራል። 1፡1-5

2. የካህናትና የህዝብ ኃጢያት 1፡6-2፡17

3. እግዚአብሄር መልዕክተኛውን እንደሚልክና እንደሚፈርድ። 3፡1-6

4. የንሰሀ ጥሪ እና አስራት በኩራት መክፈል እንዳለብንና በ ሀሴት መኖር እንደምንችል ይናገራል። 3፡7-12

5. እግዚአብሄር ከሚፈሩት፣ ከሚነቅፉትና ከማያከብሩት መካከል እንደሚለይ ይናገራል። 3፡13-4፡3

6. የሰው ልጅ ተዘጋጅቶ መኖር እንዳለበት ይናገራል። 4፡4-6

ትንቢቱና ፍጻሜው

➢ ትንቢት እንሆ መልእክተኛዬን እልካለኹ፥መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤እናንተም የምትፈልጉት ጌታ

በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ እንሆ ይመጣል፥ይላል የሰራዊት

ጌታ እግዚአብሔር።

የትንቢቱ ፍጻሜ እንሆ መንገድኽን በፊትኽ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትኽ እልካለኹ ተብሎ የተጻፈለት፡

ይህ ነውና። ማቴ 11፡10

4
ትንቢተ ሚክያስ

ሚክያስ ማለት በዕብራይስጥ ሚክያህ ወይም ሚካህ (ኤር 26፡18) ይባላል። ሚክያስ የስሙ ትርጉም ''መኑ ከመ

አምላክ ማን እንደ እግዚአብሄር ''ወይም እግዚአብሄርን የሚመስል ማን ነው (ሚክ 7፡18፤መሳ 17፡1፤ኤር 36፡11)።

ሞሬሽት ወይም ሞሬታዊው እየተባለም ይጠራ ነበር። እንደ ነብዩ አሞጽ የገጠር ነዋሪ የነበረ ሰው ነው። ነብዩ ሚክያስ

የተወለደው የፍልስጤም ከተማ በሆነችው በጌት አጠገብ ከኢየሩሳሌም ደቡባዊ ምዕራብ 25 ኪሎሜትር ርቃ

የምትገግኝ ''ሞሬት'' በተባለችዋ የይሁዳ ከተማ ናት (ሚክ 1፡1)። ስም የተሰየመውም የነብዩን ስም ተከትሎ ነው፡፡

የትንቢቱ ይዘቶች

➢ ሰማሪያና ኢየሩሳሌም እንደሚፈርሱ1-3

➢ የተሰደዱት የአይሁድ ሕዝቦች እንደሚመለሱ፤ 2:12-13፣ 5:5-9፣ 7:7-20

➢ የእግዚአብሄር መንግስት መመስረትና ንግስና 4፡1-13 ፣ 2፡12-13

➢ የእግዚአብሄር ከቤተልሄም መወለድ። 5፡1-15

➢ የእግዚአብሄርና የህዝቡ ክርክር። 6፡1-16

➢ የእግዜብሀር ተግሳጽ ለ ለእስራኤል 7፡1-13

➢ ለእስራኤል ተስፋ 7፡4-20

ትንቢቱና ፍጻሜው

እየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ይወለዳል

➢ ትንቢት አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትኾኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ከአንቺ

ግን አወጣጡ ከቀድሞ ዠምሮ ከዘለዓለም የኾነ፥በእስራኤልም ላይ ገዢ የሚኾን ይወጣልኛል። 5፡2

የትንቢቱ ፍጻሜ ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥እንሆ ሰብአ ሰገል

የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴትነው።ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ

ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ማቴ 2፡1

እነርሱም፦አንቺ ቤተ ልሔም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም፤ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ

መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት። ማቴ 2፡5-6

5
ትንቢተ ዮናስ

ዮናስ ትርጉሙ ርግብ ማለት ነው።አባቱም አማቴ ይባል ነበር። ዮናስ 1፡1 እና 2ኛ ነገስት 14፡25

keአስራ ሁለቱ የደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው።

የትንቢቱ ይዘቶች

1. ዮናስ ለእግዜአብሄር አልታዘዚም ብሎ በመርከብ ከሚጓዙ ሰዎች ጋር እንደኮበለለና ወደ ባህር

እንደተወረወረ። ዮናስ 1፡1-16

2. ዮናስን አሳ አንበሪ እንደበላው፣ አሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሁኖ እንደጸለየና ከ አሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ወደ

የብስ እንደወጣ። ዮናስ 2፡1-11

3. ዮናስ ወደ ነነዌ ሄዶ የነነዌ ሰዎች ንስሀ አንዲገቡ ጮኸ፣ንስሃ ከልገቡ ግን በ 3 ቀን ዉስጥ እንደምትጠፋ ፣

ዮናስ 3፡1-4

4. የነነዌ ሰዎች ንስሀ እንደገቡና ሳይጠፉ እንደቀሩ። ዮናስ 3፡5-10

5. ዮናስ እንዳዘነ፣ እንደተበሳጨ እና እግዜኣብሄር እንደገሰጸው። ዮናስ 4፡1-11

ትንቢቱና ፍጻሜው

1) ትንቢት፡ ዮናስ ወደ ነነዌ መሄድ ለ ነነዌ መዳን ምልክት ነበር። ዮናስ 3፡3
የትንቢቱ ፍጻሜ፡
➢ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆናቸው የሰው ልጅም ለዚች ትውልድ እንዲሁ

ምልክት ይሆናታል። ሉቃ 11፡30

➢ ክፍና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ትሻለች።ምልክት ግን ከነብዩ ከዮናስ

ምልክት በቀር አይሰጣትም። ማቴ 16፡4

2) ትንቢት፡ ዮናስ በ አሳ አንበሪ ሆድ ኡስጥ ሶስት ቀን ሶስት ሌሊት ቆይቶ እንደዋጣ። ዮናስ

2፡2

የትንቢቱ ፍጻሜ፡ ዮናስ ሦስት መአልትና ሦስት ሌሊት በአሳ አንበሪ ሆድ እንደነበረ

እንዲሁ የሰው ልጅ ሦስት መአልትና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይኖራል። ማቴ 12፡
40

6
ትንቢተ ናሆም

ናሆም ማለት መጽናናት ማለት ነው። ስለ ነነዌ ውድቀት ራእይ ያየ ነው ።ለ ይሁዳም ምስራችን የተናገረ ነብይም

ነው። ናሆም 1፡15

ትንቢቱ ይዘቶች

1. እግዜአብሄር ትግስተኛና ሀይሉም ታላቅ እንደሆነ፣ የፍርድና የበቀል አምላክ እንደሆነ ይገልጻል። ታሆም 1፡1-
14
2. የነነዌ ውድቀት፣መወረርና መበዝበዝ፣ የነነዌ ሀጢያት ዝርዝሮችና ሚን ያህል ታላቅ ከተማ ብትሆንም እንኳ

ሁሉ ነገሯ እንደሚወድም ይናገራል ናሆም 2፣3

7
ትንቢተ ዘካሪያስ

ዘካሪያስ ማለት ዝኩር ዝክረ እግዚአብሔር ማለርት ነው። ወይም ደግሞ እግዚአብሔር አስታወሰ፣አሰበ ማለት ነው።

የዘካሪያስ አያቱ አዶ አባቱ ደግሞ በራክዩ፡ ሲሆን ነገዱም፡ ከነገደ ሌዋውያን ነው።ዳርዮስ በነገሰ በሁለተኛው አመት በ

ስምንተኛው ወር ጀምሮ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጥቷል።

ትንቢቱ ይዘቶች

1. እግዚአብሔር ህዝቡን ከ መጥፎ ስራቹህ ተመለሱ ንስሃ ግቡ እያለ ይጣራል።ዘካ 1:3-6

2. ዘካሪያስ ስምንት ራእዮችን እንዳየ። ዘካ 1፡7 እስከ 6:1-15

እነሱም

✓ በዛፎች መካከል የተቀመጠ ፈረሰኛና ከበስተኋላውም ፈረሶች እንደነበርሩ ዘካርያስ 1፡7-17

✓ አራቱ ቀንዶችና አራት ጠራቢዎችን እንዳየ ዘካርያስ 1፡18-21

✓ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን እንዳየ ዘካርያስ 2

✓ ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ እንዳየ ዘካርያስ 3

✓ ዅለንተናው ወርቅ የኾነውን መቅረዝ በራሱም ላይ የዘይት ማሰሮ ያለው ሰባትም መብራቶችን

እንዳየ ይናገራል ዘካርያስ 4

✓ ጥቅል በራሪ መጽሀፍ እንዳየ ዘካርያስ 5፡1-4

✓ የኢፍ መስፈሪያ እንዳየ ዘካርያስ 5፡5-11

✓ አራት ሠረገላዎች ከኹለት የናስ ተራራ መካከል ሲወጡ እንዳየ ዘካርያስ 6፡1-8

3. እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነውን ጾም እንደማይከበል። ዘካ 7፡1-7

4. እውነተኛ ፍርድ፣ምጽዋትና ምህረት ማድረግ እንዳለባቸው ፣ ካላደረጉ ጊን ቁጣ እንደሚመጣባቸው

ይናገራል። ዘካ 7:8-17

5. እግዚአብሔር እየሩሳሌምን አንደሚያድናቸው፣ በጽድቅም አንደሚመራችምና እረፍት አንደሚያገኙ ተስፋ

ይሰጣቸዋል። ዘካ 8፡1-መጨረሻው

6. በእስራኤል ጠላቶች ላይ ስለሚመጣ ፍርድና ስለሚመጣው የጽዮን ንጉስ 9፡1-17

7. እግዚአብሔር ይሁዳንና እስራኤልን እንደሚጎበኛቸው፣አንድሚያበዛቸውና እንደገና አንደሚቋቁማቸው

አንዲሁም ትቢተኞችና የግብጽ መንግስት አንደሚወገድ ። 10፡1-11

8. ስለ እንቢተኞች አወዳደቅና ቅጣታቸው ዘካ 11፡1-17

9. እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚቀጣና እስራኤል እንደሚድኑ ተስፋም አንዲያደርጉ ይናገራል ዘካ 12፡፣ 13 14

10. ስ

8
ትንቢቱና ፍጻሜ

1. ትንቢቱ እነሆ ስሙ ቁጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል እርሱም የእግዚአብሔርን ቤት ይሰራል

ክብሩንም ይወስዳል በዙፋኑም ተቅምጦ ይገዛል። ዘካ 6፡12-13


የትንቢቱ ፍጻሜ
➢ የበኩር ልጇንም ወለደች አውራ ጣቱንም አሰረችው ሉቃ 2፡7

2. እኔም በፊታቹህ ደስ ብሏቹህ እንደሆነ ዋጋየን ስጡኝ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ እነሱም ለዋጋየ ሰላሳ ብር

መዘኑልኝ እግዚአብሔርም በከውር ጨምረው እነርሱ እንደፈተኑት የጠራ መሆኑን ፈትነው አለኝ

እኔምሰላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው ከውር ጨመርሁት። ዘካ 11፡12-13


የትንቢቱ ፍጻሜ
➢ ምን ትሰጡኛላቹህ? እኔም አሳልፌ እሰጣቹሀለው አላቸው እነርሱም ሰላሳ ብር መዘኑለት።

ማቴ 26፡15

➢ ያንጊዜ የነብዩ የ ኤርሚያስ ቃል የ እስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ

ሰላሳውን ብር ወሰዱ። ማቴ 27፡9

3. በዳዊትም ቤት ላይ በእየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ የደስታንና የሀሴትን መንፈስ አፈስሳለሁ የወጉትን ያዩት

ዘንድ አላቸው ወደ ልቅሶም ይመለሳሉሰውም ለወዳጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፣ ሰዉም ለበኩር ልጅ

እንደሚያዝን በመራራ ሀዘን ያዝኑለታል። ዘካ 12፡10

ማኒም ሰው ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ አንተ በእግዚአብሔር ስም ሀሰትን ተናግረሃልና

አትኖርም ይሉታል። ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባቱና እናቱ ይወጉታል። ዘካ 13-3

ሰውም ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድን ነው? ይለዋል እርሱም በወዳጆቼ ቤት የቆሰልሁት ቁስል ነው

ይላቸዋል። ዘካ 13፡6
የትንቢቱ ፍጻሜ
➢ ከዚህ በኋላ ገታችን እየሱስ እንደዚህ አላቸው በዚች ሌሊት ሁላቹህም ትከዱኛላቹህ

መጽሀፉ እረኛውን እገድለዋለሁ በጎቹም ይበተናሉ ብሎአልና ማቴ 26፡31

➢ ሌላውም መጽሀፍ ደግሞ የወጉትን ያዩታል ይላል። የዩሀንስ ወንጌል 19፡37

4. አንቺ የጽዮን ልጅን ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉስሽ ጻድቅና አዛኝ

ነው ትሁትምሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል። ዘካ 9፡


9
የትንቢቱ ፍጻሜ

9
➢ ጌታችን ወደ እየሩሳሌም ቀርቦ ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ በደረሰ ጊዜ ከደቀ

መዛሙርቱ ሁለቱን ላከ እንዲህም አላቸው በፊታቹህ ወዳለችው መንደር ሂዱ የንጊዜም

የታሰረች አህያ ከውርንጫዋ ጋር ታገኛላቹህ ፍቱና አምጡልኝ። ምን ታደርጋላቹህ?

የሚላቹህ ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ የንጊዜ የዱአችኋል።ይህ ሁሉ የሆነው በነብዩ

እንዲህ ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው ለጽዮን ልጅ እነሆ የውህ ንጉስሽ በአህያይቱና

በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሏት። ማቴ 21፡1-5

5. ብዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሀን አይሆንም ፣ አንዲት ቀንም ትሆናለች፣እርሷም በ

እግዚአብሔር ዘንድ የታወቀች ትሆናለች ቀንም አትሆንም፡ሌሊትም አትሆንም ሲመሽም ብርሀን ይሆናል።

አያለ ከ ዘካ 14፡6-19
የትንቢቱ ፍጻሜ
➢ ከተማይቱም ያበሩላት ዘንድ ጸሓይን ወይም ጨረቅን አትሻም ፣የ እግዚአብሔር ብርሀን

ያበራላታልና በጉም መብራቷ ነው፣ አህዛቢም በ ብርሀኑዋ ይመላለሳሉ፣የምድር

ነገስታትም ክብራቸውን ወደርሷ ያመጣሉ። እያለ ከ ዩሀንስ ራእይ 21፡23-27

10

You might also like