You are on page 1of 7

ስድስተኛ ሳምንት

የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት አንድምታ


- ጠቅላላ 25 ቁጥሮች እና 4 ንዑሳን ክፍሎች አሉት እነሱም፡-
o 1-11 ስለ ኢየሱስ መፈተን
o 12-17 ጌታ ኢየሱስ በቅፍርናሆም እንደተቀመጠ
o 18-22 ስለመጀመሪያዎች ሐዋርያት
o 23-25 ጌታ በገሊላ እየተዘዋወረ እንዳስተማረና ሕሙማንን ሁሉ እንደፈወሰ
1. ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፡፡
ሀ.1. ከዚያ ወዲያ ሲል ከምን በኋላ ማለቱ ነው?
- ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ማለቱ ነው፡፡
ሀ.2. መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው ሲል ምን ማለቱ ነው?
- ፈቃዱ አነሳስቶት ማለት ነው፡፡
- መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ማለት ነው፡፡ (ፈቃደ ወልድ - ፈቃደ መንፈስ ቅዱስ)
ሀ.3. ተጠምቆ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳም የሄደበት ምክንያት ምንድን ነው?
- እናንተም ተጠምቃችሁ አትዋሉ አትዳሩ እለቱን ወደ ገዳም ሂዱ ለማለት ነው፡፡
(አብነት ለመሆን)
ሀ.4. ለምን ወደ ገዳም ሄደ?
- አዳም ከዚህ ዓለም አፍአ (ውጭ) በምትሆን በገነት ድል ተነስቶ ነበርና እሱም ከዚህ
አለም አፍአ በምትሆን በገዳም በ3ቱ አርእስተ ኃጣውስ ድል ለመንሳት
- በገዳም ጾር ይቀላልና ለወጣንያን አብነት ለመሆን
- በገዳም ጾር ይጸናልና ለፍጹማን አብነት ለመሆን
o ክርስቶስ ዲያቢሎስን ድል የመታው (የነሳው) የሰውነቱ እንጂ በአምላክነቱ
አይደለም፡፡
2. አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ
ሀ.5. ለምን መጀመሪያ ጾምን አደረገ?
- ሰራዔ ሕግ ነውና፡፡
- የሥራ መጀመሪያ ጾም ነውና፡፡
- መብል ለኃጣውእ መሠረት እንደሆነ ጾምም ለምግባር ለትሩፋት መሠረት ናትና፡፡
ሀ.6.ለምን 40 ሌሊት ጾመ?
- ቀድሞ ነቢያት 40 አርባ ጾመው ስለነበረ ከነሱ ትንቢትና ሥርዓት ውጪ አለመሆኑ
ለማጠየቅ
o ሙሴ 40 ዓመቱ ለዕብራዊ ረድቶ ግብጻውያን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ቀብሮት ነበር፡
፡ ኦ.ዘጸ. 2፡11-12
o ሙሴ 40 የወልደ እግዚአብሔር፣ ዕብራዊ የአዳም፣ ግብጻዊ የዲያብሎስ አሸዋ
የመስቀል አንድም የ3ቱ አርአስተ ኃጣውእ ምሳሌ ነው፡፡
o እስራኤል ገዳም 40 ዓመታት ኑረው ምድር ርስት እንደገቡ እናንተን 40 ዕለታት
ብትጾሙ ገነበት መንግስተ ሰማያት ትገባላችሁ ሲል ነው፡፡
o ኤልያስ 40 ዕለታት ጾሞ ገነት እንደገና እናንተም 40 ዕለታት ጾማችሁ ገነት
መንግስተ ሰማያት ትገባላችሁ ለማለት ነው፡፡
o ሕዝቅኤል በግራ ጎኑ 40 ቀናት ተኝቶ 600 ሙታን አስነስቷል እናንተም 40
ዕለታት ብትጾሙ ምስጢር ይገለጥላችኋል ሲል ነው፡፡
o ዕባብ አካሉ የወፈረበት እንደሆነ 40 ቀናት ከምግብ ተከልክሎ ይታደሳል እናንተም
40 እለታት ብትጾሙ ተሐድሶተ ነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡
o አዳም በ40 ቀናት ያገኘው ልጅነት አስወግዶ ነበርና ለሱ እንደካሳ ለማጠየቅ
o በ40 ዕለታት ተስዕሎተ መልክእ ለተፈጸመለት ሰው ሁሉ ሊክስ እንደመጣ
ለማጠየቅ
o ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ተራበ ነገር ግን አልሳሳም ተዋጋ ድል አልተነሳም፡፡
ሀ.7. ጌታችን በጾሙ ጊዜ ሰርቶ ሥራ ያለን ምን ምን ግብራት ናቸው
- ጥምቀት
- ተአምኖ ኃጢአት
- ከዊነ ሰማዕት
- ተባሕታዊ
- ምንኩስና
3. ፈታኝም ቀርቦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው፡፡
ሀ.8. ዲያቢሎስ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ማለቱ ከየት ባገኘው መረጃ ነው?
- በዮርዳኖስ አባቱ ይህ የምወደው ልጄ ነው ሲል ሰምቶ ስለነበረ ነው፡፡
4. እርሱም መልሶ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ
አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡
ሀ.9. ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር የተጻፈው የትኛው መጽሐፍ ላይ ነው?
- ኦ.ዘጸ. 8፡3
ሀ.10. ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ማለቱ ምን ማለት ነው?
- እግዚአብሔር ዳን ያለው ይድናል ሙት ያለው ይሞታል ማለቱ ነው፡፡
- እግዚአብሔር ምግብ ይሁን ያለው ይሆናል ማለቱ ነው፡፡
- ሕግን መጠበቅና ቃለ እግዚአብሔር በመማር ማለት ነው፡፡
ሀ.11. ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ሲል ምን ማለቱ ነው?
- ባሕርይ እንስሳዊ ምግብ ሲያጣ ይጎዳል ባሕርይ መልአካዊ ትምህርት ሲያጣ ይጎዳል
ማለቱ ነው፡፡
ሀ.12. ዲያቢሎስን ጌታ አፉን ከፍቶ ፊቱን ጸፍቶ ያናገረው ምስጢር ምንድነው?
- ወልደ እግዚአብሔር ከሆንህ ይህ እንደ ደንጊያ ፈዞ ያለ ሰውነትህ ህብስተ ህይወት
ህብሰተ መድኃኒት ይሁን ብለህ እዘዝ ሲያሰኘው ነው፡፡
- ጌታም ሰው የሚድነው በእሩቅ ብእሲ ሥጋ እንዳይደለ ነገር ግን አካላዊ ቃል
በተዋሐደው ሥጋ እንጂ አለው፡፡
5. ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ
6. ጫፍ ላይ አቁሞ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ
እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሱሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ወደ
ታች ራስህን ወርቅር አለው፡፡
ሀ.13. ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደው ሲል እንዴት ነበር የወሰደው?
- ፈቃዱን አውቆ ስለሄደለት ነው እንጂ ጎትቶ ወይም አስገድዶ አልወሰደውም፡፡
- ካህናትን ድል በምነሳበት በቤተ መቅደስ መቼ ድል ይነሳኝ ነበር የሚል ጥያቄ
በዲያብሎስ ልቡና ይመላለስ ስለነበር ይህንን አውቆ ሄዶለታል፡፡
ሀ.14. ከዚህ ዘለህ ወደታች ውረድ ያለው ለምንድን ነው?
- ቢሰበር አርፈዋለሁ ባይሰበር ምትሐት አሰኘዋለሁ ብሎ ነው፡፡
- ቢያደርገው ደካማ አሰኘዋለሁ ቢያደርገው ሌላ ጾር እሻለታለሁ ብሎ ነው፡፡
- ቢያደርገው የሰይጣን ታዣዥ ብዬ ዕዳ እልበታለሁ ባያደርገው ድካሙን አይቼ
እቀርበዋለሁ ብሎ ነው፡፡
ሀ.15. መላእክቱን ስላንተ ያዝልሃል ተብሎ የተጠቀሰው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ላይ ነው?
- መዝ 90፡11-12
7. ኢየሱስም ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው፡፡
ሀ.16. ጌታን አትፈታተነው የሚለው ጥቅስ የት ይገኛል?
- ኦ.ዘዳ 10፡16
8. ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረዥም ወደሆነ ተራራ ወሰደው የዓለምንም መንግስታት ሁሉ
ክብራቸውን አሳይቶ ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሀለሁ አለው፡፡
ሀ.17. ወደ ረዥም ተራራ እንዴት ይሄዳል?
- ነገሥታት ድል በማልነሳበት በቤተ መቅደስ ቢሆን ድል ነሳኝ እንጂ ነገሥታትን ድል
በምነሳበት ተራራ ቢሆን መቼ ድል ይነሳኝ ነበር ብሎ ፈቃዱን ሲያሰላስል አውቆ
ሄዶለታል፡፡
9. ያን ጊዜ ኢየሱስ ሂድ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ
ተብሎ ተጽፎአልና አለው፡፡
ሀ.18. እርሱን ብቻ አምልክ የሚለው ጥቅስ የት ይገኛል?
- ኦ.ዘጸ 7፡13
ሀ.19. በ3ኛ ጊዜ ለምን ከዚህ ሂድ ብሎ አባረረው?
- በ3ተኛው ድል ንሱ ብሎ አብነት መሆኑን ለማሳወቅ
- ንጉሥ በመንግሥቱ ጎልማሳ በሚስቱ ጌታም በአምልኮቱ ቀናኢ ነውና፡፡
10. ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው እንሆም መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር፡፡
ሀ.20. ዲያብሎስ ትቶት የሄደው እስከመቼ ነው?
- ለጊዜው ነው ሉቃ. 4፡13 በዕለተ አርብ በአይሁድ ሥግው ሁኖ እስኪያስቅለው ድረስ
አይመለስበትም፡፡
ሀ.21. 3ቱ እርእስተ ኃጣውዕ ምን ምን ናቸው?
ሀ. ስስት፡- ያልሰጡትን መሻት- የመነኮሳት ጾር- በገዳም - በትዕግስት
ለ. ትዕቢት፡- አምላክ እሆናለሁ ማለት - የካህናት ጾር - በቤተ መቅስ- በትህትና
ሐ. ፍቅረ ንዋይ፡- በቃኝ አለማለት - የነገሥታት ጾር- በቤተ መቅደሱ- በትህትና
ሀ. 22. መላእክት ለምን ዲያቢሎስ ከሄደ በኋላ መጡ? (ድል ከተነሳ በኋላ)
- አስቀድመው መጥተው ቢሆን መላእክትን ይዞ ድል ነሳኝ እንጂ ብቻውንም ቢሆን
መች ድል ይነሳኝ ነበር እንዳይል፡፡
- እናንተም ድል ብትነሱ ይገድላችኋል ለማለት ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስ በቅፍርናሆን እንደተቀመጠ
11. ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ፡፡
ለ.1. ዮሐንስን እንዳጋዙት በሰማ ገዜ ለምን ሸሸ?
- መከራ በመጣባችሁ ጊዜ ሸሹ በማለት አብነት ለመሆን
12. ናዝሬትንም ትቶ በዘብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ
ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ፡፡
ለ.2. በቅፍርናሆም ምን እያደረገ ኖረ?
- እያስተማረ ኖረ፡፡
13. በነቢዩም በኢሳይያስ የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር የባሕር
14. መንገር በዮርዳኖስ ማዶ የአሕዛብ ገሊላ በጨለማ የተቀመጠው
15. ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፡፡ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው
የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፡፡ ት.ኢሳ.9፡1
ለ.3. በጨለማ ላሉ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው
- በሞት ጥላ ለሚኖሩ ብርሃን ወጣላቸው ማለቱ ነው፡፡
- በድንቁርና በቀቢጸ ተስፋ ለነበሩ ሰዎች ዕውቀት ተሰጣቸው ማለቱ ነው፡፡
- ሞት ባመጣው ምስል ለሚኖሩ ሰዎች ክርስቶስ ተወለደላቸው ማለት ነው፡፡
- በሞተ ሥጋ በሞተ ነፍስ ለነበሩ ልጅነት ተሰጣቸው ማለቱ ነው፡፡
- በኃጢአት በክህደት ለነበሩ ሃይማኖት ተገለጸላቸው ማለቱ ነው፡፡
- ኃጢአት ጨለማ ክህደት ደግሞ የሞት ጥላ የተባለው በጨለማ ላይ የዛፍ (የገደል)
ጥላ ሲጨመር ጨለማው እንደሚጸና በኃጢአትም ላይ ክህደት የተጨመረ እንደሆነ
ፍዳው ይጸናል ማለቱ ነው፡፡
16. ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ
ጀመር፡፡
ለ.4. ዮሐንስ ከተጋዘ በኋላ ማስተማሩ ስለምንድን ነው?
- መምህር ባለ በመምህር ላይ እናተምራለን አትበሉ ለማለት ነው፡፡
- መምህራችን ዮሐንስ ነበር ትምህርቱንም አለወጠውም የስንቱን እንስማ እንዳይሉና
ሕዝቡ ግራ እንዳይጋቡ ነው፡፡
- ዮሐንስ መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ያላችሁ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡
ስለ መጀመሪያዎች ሐዋርያት
17. በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም 2 ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን
ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ ዓሳ አጥማጆች ነበሩና፡፡
18. እርሱም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡
ሐ.1. በኋላዩ ኑና ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ ያለበት ምስጢር ፍቺ (ትርጉም) ምንድን
ነው?
- ለጊዜው በእግር ተከተሉኝ ፍጻሜው በግብር ምሰሉኝ ማለቱና ሰውን እንደ ዓሳ
ወንጌልን እንደ መረብ ይህን ዓለም እንደ ባሕር አድርጋችሁ እንድታስተምሩ
አድርጋችኋለሁ ሰላቸው ነው፡፡
19. ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከሉት፡፡
20. ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን 2 ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም
ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ
21. ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ ጠራቸውም፡፡ እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና
አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
ሐ.2. አባትህንና እናትህን አክብር የሚለውን ቃል እንዴት አባታቸውን ትተው ሲሄዱ
እንዳከበሩት ይቆጠራል?
- ከአባትህና ከእናትህ ክብር የእግዚአብሔር ማክበር ይበልጣል ብለው ነው፡፡
ጌታ የገሊላ እየተዘዋወረ እንዳስተማረና ሕሙማንን ሁሉ እንደፈወሰ
22. ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግስትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝቡም
ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር፡፡
መ.1. የመንግሥት ወንጌል ሲል ምን ማለቱ ነው?
- ጌትነቱን የምትናገር የምሥራች ቃል ማመን ነው፡፡
- ወልደ እግዚአብሔር እንደነገሠ ዲያቢሎስ እንደተሻረ ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ እንደጠፋ
ትናገራለችና ወንጌልን መንግስት ይላታል፡፡
23. ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ
አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሳባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ
ፈወሳቸውም፡፡
24. ከገሊላም ከአስሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ
ተከተሉት
መ.2. አሥሩ ከተማ የሚላቸው የትኞቹን ነው?
- ጲላጦስ ለቀረጥ ይመቸኛል ብሎ አንዱን ከተማ ለ10 ከፍሎት ስለነበር እነዚያን ነው፡

መ.3. የ5ቱ ገበያ ሕዝብ ለምን ለምን ይከተሉት ነበር?
ሀ. መልኩን እናያለን ብለው፡- ትንቢቱ መዝ 45፡2
ለ. ኅብስት አበርክቶ ያበላናል ብለው፡- ትንቢተ መዝ.78፡30
ሐ. ትምህርቱን እንሰማለን ብለው፡- ትንቢተ መዝ. 119፡103
መ. ከደዌያችን ይፈውሰናል ብለው፡- ትንቢቱ ኢሳ. 53፡4
ሠ. የኦሪትን መፍረሻ የወንጌልን መታነጫ እናያለን ብለው
መ.4. እኒህን በምን በምን ይፈውሳቸዋል?
- በሐልዩ፣ በነቢብ፣ በነቢብ፣ በዘፈረ ልብስ በወሪቀ ምራቅ

You might also like