You are on page 1of 41

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ዓላማ ያለው ሰው
ጉዞ
1
“እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ
ተናገረው፡-ለእስራኤል ልጆች
የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ
ዘንድ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ
እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ
አንድ ሰው ትልካላችሁ።”
ዘኁ. 13፡1-2 2
 “ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥
አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ
ተራሮችም ሂዱ፡፡ ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥
በእርሷዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥
ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥ የሚኖሩባትም
ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም
ከተሞች ሰፈሮች ወይም አምቦች እንደ ሆኑ፥ ምድሪቱም
ወፍራም ወይም ስስ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ
ሆነች እዩ፣ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፣ አይዟችሁ።

3
 “ወጡም፣ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር
እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። በደቡብም
በኩል ውጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ
ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ።
 “ወደኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ
ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ሁለቱም ሰዎች
በመሎጊያ ተሸከሙት፡፡ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም
አመጡ። የእስራኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረጡት ዘለላ
የዚያን ስፍራ ስም የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት።
4
 “ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። በፋራን
ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ
እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፡፡ ወሬውንም
ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ
አሳዩአቸው።

 “እንዲህምብለው ነገሩት፡- ወደ ላክኸን ምድር ደረስን፥


እርሷም ወተትና ማር ታፈስሳለች፥ ፍሬዋም ይህ ነው። ነገር
ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም
የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው፣ ደግሞም በዚያ የዔናቅን
ልጆች አየን።
5
 “በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጧል፣ በተራሮቹም ኬጢያዊና
ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፣ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ
አጠገብ ተቀምጧል።
 “ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና ‘ማሸነፍ
እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው’ አለ።
 ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ ‘በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ
ላይ መውጣት አንችልም’ አሉ። ስለ ሰለሏትም ምድር ክፉ ወሬ
ለእስራኤል ልጆች እያወሩ እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን
ሰዎች የምትበላ ምድር ናት፣ . . . እኛም በዓይናችን ግምት እንደ
አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን
አሉ።”
ዘኁ. 13፡17-33

6
 ከነዓንንሰልለው እንዲመጡ ሰው መርጠህ ላክ ያላቸው ራሱ
እግዚአብሔር ነበር፡፡ ሆኖም በመጣው መረጃ ሕዝቡ ሁሉ
ተሸበረ፡፡ ከግብጽ ያወጣቸውን እግዚአብሔርን አላመኑትም፤
ወደ ግብጽ ለመመለስ ፈለጉ እንጂ፡፡
 በመንፈሳዊ ሕይወት ወደፊት ያለው ጎዳና (መንገድ) ተራራ

እንደ መውጣት ያለ ነው፡፡ አንዳንዴ ከመንገዱ ሻካራነትና


አስቸጋሪነት የተነሣ ምነው ባልጀመርነው የሚያሰኝ ስሜት ሁሉ
ሊፈጠር ይችላል፡፡
 ሆኖም ወደ ኋላ መመለስም ደግሞ ቀላል አይደለም፡፡
 በማዶ የወይኑ አንድ ዘለላ አረግ ለሁለት ሰዎች በመሎጊያ

የሚሸከሙት የሚያስጎመዥ ፍሬ አለ፤ ሆኖም ለሕይወት አስጊ


የሆኑ አደገኛ ኃያላን ደግሞ በዚያው አለ፡፡ 7
 በግል ሕይወትም ሆነ በማኅበር አገልግሎት እንዲህ
ዓይነት ነገሮች ናቸው ብዙ ጊዜ የሚገጥሙት፡፡
 ሰው ስጋት ካለው ነገር ጋር ሳይጋፈጥ ማደግና ውጤት

ላይ መድረስ አይቻለውም፡፡
 ሆኖም ጉዞው በጣም ሻካራና ከፊታችን ያለው አስፈሪ

ሲሆን ብዙ ጊዜ ቀላል የሆነውን መንገድ ለመከተል


እንፈልጋለን፡፡ እርሱም ወደ ኋላ መመለስ ነው፡፡
 ሆኖም መንፈሳዊ ሞት ያለው በዚያ መንገድ ላይ ነው፡፡

8
“ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኳቸው
የተመለሱት ሰዎች ክፉ ወሬም ስለ ምድሪቱ
እያወሩ በእርሱ ላይ ማኅበሩ ሁሉ
እንዲያጕረመርሙ ያደረጉ፥ ክፉ ወሬ ያወሩ
እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት
ሞቱ። ነገር ግን ምድሪቱን ሊሰልሉ ከሄዱ
ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ
በሕይወት ተቀመጡ።”
ዘኁ. 14፡36-38 9
 ያመጡት መረጃና የደረሱበት ድምዳሜ በአካላዊ
ግዝፈትና በቁጥር ብዛት ላይ የተመሠረተ ነበር፡፡
 ከእግዚአብሔር ጋር ለሆነ ምንም ኃያል ነኝ ባይ
ሊያቆመው አይችልም፡፡ ለትእዛዛቱ ታዛዦች ሆነን
በመንገዱ ከተጓዝን ተስፋ አድርጎ ከሰጠን አገር
እንደርሳለን፡፡
 ይህ
ማለት ግን ኃያላኑ ዔናቃውያን ዝም ብለው ከነዓንን
ይለቃሉ ማለት ግን አይደለም፤ ፍልሚያ ይጠይቃሉ፤
ከሞት ጋር መጋፈጥን ይጠይቃል፡፡ መሞት ሊመጣም
ይችላል፡፡ 10
 ሆኖም በመጨረሻ ግን ድል እናደርጋቸዋለን፤
እግዚአብሔር ስለ እኛ ይዋጋቸዋልና፡፡ እርሱ ሞትን
እንኳ አሸንፎታልና፡፡
 “ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፡-

ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ።”


“ከእርሱጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ
ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት
አንችልም አሉ።”
11
 “ለማኅበሩም ውኃ አልነበረም፣ በሙሴና በአሮንም ላይ
ተሰበሰቡ።
 “ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ እንዲህም ብለው ተናገሩት፡-

ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው


በሞትን ኖሮ! እኛ ከብቶቻችንም በዚያ እንሞት ዘንድ
የእግዚአብሔርን ጉባኤ ወደዚህ ምድረ በዳ ለምን አመጣችሁ?
 “ወደዚህ ክፉ ስፍራ ታመጡን ዘንድ ከግብፅ ለምን

አወጣችሁን? ዘርና በለስ፣ ወይንም ሮማንም የሌለበት ስፍራ


ነው፣ የሚጠጣም ውኃ የለበትም።

12
 “ሙሴና አሮንም ከጉባኤው ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን
ደጃፍ ሂደው በግምባራቸው ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም
ክብር ተገለጠላቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ
ብሎ ተናገረው፡-
 “በትርህንውሰድ፣ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን
ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ
ተናገሩት፣ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ፡፡ እንዲሁም
ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ። ሙሴም
እንደ ታዘዘ በትሩን ከእግዚአብሔር ፊት ወሰደ።
13
 “ሙሴና አሮንም ጉባኤውን በድንጋዩ ፊት ሰብስበው፡-
እናንተ ዓመፀኞች፣ እንግዲህ ስሙ፣ በውኑ ከዚህ ድንጋይ
ውኃን እናወጣላችኋለን? አላቸው። ሙሴም እጁን
ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፡፡ ብዙም
ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ።
 “እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች

ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ


ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም
አላቸው።”
ዘኁ. 20፡2-13
14

ኢያሪኮ
“ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን
ነፉ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ
ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፣
ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ
ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ወሰዱ።”
ኢያ. 6
15
 አካን
 “እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፡- ለምን በግምባርህ
ተደፍተሃል? ቁም፣ እስራኤል በድሎአል፣ ያዘዝኋቸውንም
ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል፣ እርም የሆነውንም ነገር ወሰዱ፥
ሰረቁም፥ ዋሹም፥ በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።
ስለዚህም የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ፊት መቆም
አይችሉም፣ የተረገሙ ስለ ሆኑ በጠላቶቻቸው ፊት
ይሸሻሉ፡፡ እርም የሆነውንም ነገር ከመካከላችሁ
ካላጠፋችሁ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።

16
 “ተነሣና ሕዝቡን ቀድስ፥ እንዲህም በላቸው፡-
እስራኤል ሆይ፥ እርም የሆነ ነገር በመካከልህ አለ፣
እርምም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ
በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም ብሎ የእስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና እስከ ነገ ተቀደሱ።
“ . . . እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው
የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሷልና፥ በእስራኤልም
ዘንድ በደል አድርጓልና እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት
ይቃጠላሉ።” ኢያ. 7

17
 “በዘረፋመካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት
መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ
አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም እነሆም፥
በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ
በታች ነው አለው።
“ኢያሱም መልክተኞች ሰደደ ወደ ድንኳኑም ሮጡ
እነሆም፥ በድንኳኑ ውስጥ ተሸሽጎ ነበር፥ ብሩም
በበታቹ ነበረ።”
ኢያ. 7፡21-22
18
19
20
 almost 250 million visitors regardless of age or origin
have come from all over the planet to see it since its
opening in 1889.
 As France’s symbol in the world, and the showcase

of Paris, today it welcomes almost 7 million visitors


a year (around 75% of whom are foreigners), making it
the most visited monument that you have to pay for in
the world.
 In 2011, the Eiffel tower had more than 7
million visitors. That represents about a visitor
every four seconds, all year round, day and
night.
21
22
“ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ
አይቀርምና” ማቴ. 18፡7
1. ከአጉል አዛኞች
 “. . . ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፡- አይሁንብህ፣ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ
አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ
ጴጥሮስን፡- ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ
የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” ማቴ.
16፡21-24
 ሰማዕታትን ለወጣትነትህ እዘንለት፣ለውበትሽ እዘኚለት . . .

 አንተን ብቻ ምን አታገለህ ? ዝም ብለህ አታይም? . . .


23
2. ነገረ ክርስቶስ ካልገባቸው የክርስቶስ
“ተከታዮች”
 “ለደቀ መዛሙርቱ፡- የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ
አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሯችሁ አኑሩ አለ።
 “እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፥ እንዳይገባቸውም

ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገርም እንዳይጠይቁት ፈሩ።


 “ከእነርሱም ማን እንዲበልጥ ክርክር ተነሣባቸው።”
ሉቃ. 9፡44-46
 ሐዋርያትሕፃናትን ወደ ጌታችን ያመጡትን ወላጆች
እንደ ገሠጹአቸው 24
 “ወደኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ
ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ
በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ። የዳዊት ልጅ
ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።
 “ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፦ የዳዊት
ልጅ ሆይ፥ ማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ። ኢየሱስም
ቆመና ጥሩት አለ። ዕውሩንም አይዞህ፥ ተነሣ፥
ይጠራሃል ብለው ጠሩት።” ማር. 10፡46-49
25
3. በአሠራር ካለመግባባት
 “ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፡-
ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ
ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም
እንወቅ አለው።
 “በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ

ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን


ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ
ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር
አልመጣም ነበርና።
26
 “ስለዚህምእርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ
መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ
ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥
ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት
በኋላ ወጣ”
የሐዋ. 15፡36-40
አሮንና ሙሴ - ሙሴ ከተራራው ጽላቱን ይዞ ሲወርድ
አሮን ጣዖት ሠርቶ ጠበቀው፡፡ ዘጸ. 32

27
4. በዓላማ ከሚሠሩ ክፉዎች
“. . . ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ
እኛ ጸልዩ።” 2 ተሰ. 3፡1
 “ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ

በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።” 2 ጢሞ. 3፡13


“ሁኔታዎችንእንደ ፍላጎታችን
እንዲሆኑ መመኘት ሞኝነት ነው፡፡”
ዜኖ

28
 “ቤተ ክርስቲያንን እኛ አንጠብቃትም፣ ራሱ ይጠብቃታል”
 “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን

ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ


ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ከሄድሁ
በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች
እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ
ዘንድ ጠማማ

29
 ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ
አውቃለሁ። ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ
እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ
ትጉ።” የሐዋ. 20፡28-31
 “እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን

እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤ . . . ከእርሱ ጋር አብረን


የምንሠራ ነንና።” 1 ቆሮ. 3፡6-9
 “በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ

ጠብቁ” 1 ጴጥ. 5፡2

30
 “የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፡- የሰው ልጅ
ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥
እረኞችንም እንዲህ በላቸው፡- ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች
በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን?
 “.
. . የደከመውን አላጸናችሁትም፣ የታመመውንም
አላከማችሁትም፣ የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም፣ የባዘነውንም
አልመለሳችሁትም፣ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፣ በኃይልና
በጭቈናም ገዛችኋቸው። እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም
አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም።” ሕዝ. 34

31
 “ትንቢቱ መፈጸሙ ላይቀር አንድከም”
 “ሁን ያለው ላይቀር”

ትንቢት - ምክንያት ወይስ ውጤት? (Cause or


Consequence?)
 “የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን

የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው


ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው።” ማር. 14፡21

32
 “ስለሕዝብ ስለ መንግሥትም እነቅል አፈርስም
አጠፋም ዘንድ በተናገርሁ ጊዜ፥ ይህ ስለ እርሱ
የተናገርሁበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፥ እኔ አደርግበት
ዘንድ ካሰብሁት ክፉ ነገር እጸጸታለሁ። ስለ ሕዝቡም
ስለ መንግሥትም እሠራውና እተክለው ዘንድ
በተናገርሁ ጊዜ፥ በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ ቃሌንም
ባይሰማ፥ እኔ አደርግለት ዘንድ ስለ ተናገርሁት
መልካም ነገር እጸጸታለሁ።”
ኤር. 18፡7-10

33
 ብዙ ለውጥ ያመጡ ግለሰቦች አሉ፡፡

34
1. መንፈሳዊነት
 ክርስትና ሕይወት ነው፤ በውስጥ በአፍኣ የሚቆጣጠር፣ ሁለንተናን የሚለውጥ
ነው፡፡
 ከሁሉ በፊት የክርስትናን ምንነት በአግባቡ መረዳት ይገባል፡፡
ክርስትናን በአግባቡ የተረዱ ክርስቲያኖች ሁለንተናቸው በሙሉ
ይለወጣል፡፡
 “ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤
ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን
እርሻ ገዛ።” ማቴ. 13፡44

35
2. እውቀት
 በሐዋርያት ዘመን - መሔድና ማስተማር፣ መመስከር
 በጠበቆች (Apologists) ዘመን -
 በዘመነ ሰማዕታት -
 በዘመነ ሊቃውንት -
. . .

36
3. ዓላማ (ርእይ) ተኮር እንጂ ክስተት (ግለሰብ)
ተኮር አይደለም፡፡
(Being objective, not subjective)
አባቶቻችን ጉዳይ ተኮር እንጂ ግለሰብ ተኮር አልነበሩም፡፡
ሰዎችን ከስህተት ማውጣትና ከእውነት ጋር ማሰለፍ የቻሉት
ለዚህ ነበር፡፡
“Cyril send greetings in the Lord to the most beloved and
religious and beloved of God the reverend fellow
minister Nestorius”
እንደ ወንድም፣ ያውም እንደ ተወደደ ወንድም ነበር የሚጠራው፡፡

37
ለእምነት ጥብቅና መቆም እብሪተኛነት አይደለም፣ ከዚህም
ጋር አይገናኝም፡፡
 አቅጣጫ ማስቀየሪያ ጉዳዮች - እውነተኛ ጉዳዮች
 ክስተት - ከክስተቶቹ ጀርባ ያለው ዋና ጉዳይ
 “ነገር ግን ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አሳልፎ ሊሰጠው

ያለው የስምዖን ልጅ የአስቆሮቱ ይሁዳ ይህ ሽቱ ለሦስት


መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ያልተሰጠ ስለ ምን ነው?
አለ። ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች
ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ
ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።”
ዮሐ. 12፡4-6 38
4. ከራሱ በላይ ለዓላማው ያስባል፡፡
ሙሴ - ኢያሱ
5. ዓላማን በማሳካት እንጂ ለችግሮች ምክንያት
በማቅረብ አያምንም
6. ለዓላማው ቆራጥ ነው፡፡
ብዙ ጊዜ በአገልግሎት የምንመኛው ብዙ ነገር አለ ነገር ግን የሚገባንን ያክል ሰርተን
ለማምጣት የሚገባንን ድርሻ አንወጣም ከዚህ ጋር የአንዲት ደሮና የአንድ በግ
ታሪክ እንመልከት
ሁለቱ በወቅቱ ድርቅ ነበረና ርሃባቸውን ለማስተገስ በጋራ ተስማሙ ከዘማ ወደ ተግባር
ሲገቡ ደሮ እንቁላል ጣለችና ይዛ መጣች በግ ደግሞ ከምትመገበው ፍራፍሬ ይዛ
መጣች ከዛም መስማማት አልቻሉም ባቀረቡት ነገር ለምን ይመስሰችሃል
ሀሳባችሁን ግለፁ

39
እንግዲህ ያልተስማሙት የጋራ መሀብር ፍጥረን ልንኖር ነው …. ተብሎ
ግን እኔ ከሰውነቴ እንቁላልን ሳቀርብ አንቺ ከዱርና ከጉሮ አመጣሽ እንዴት
ድርሻችን እኩል ይሆናል ስትል
በግ የዋህ ስለሆነች ታድያ ምን ይሻላል ስትል ከአንድ ጭንሽ ስጋ አውጭና
እንመገብ
ስተውሉ ደሮ እንቁላል ማቅረባ ተፈጥሮአዊ ባሕሪዎ ስለሆነ ነው ነገር ግን
በግ ስጋው ሲቆረጥ መቁስል መድማት መታመም መሞትም ይመጣል በዚህ
ጊዜ ደርሻቸውን ስንመለከት
ደሮ ካላት ኮንትረቢውት/አስተዋፅኦ
በግ ደግሞ በሂወተዋ ኢንቮልመንት/መስዋትነት
ከዚህ የምንረደው ብዙ ጊዜ በአገልግሎት ውስጥ ሰዎች እንድ አለማዊነት
በብልጠት አጭብርበሮ እኩል መሆን ይፈልጋል
ከዚህ ጋር የደሮዋና የበጉን ድርሻ ስንመለከት

40
ስብሐት
ለእግዚአብሔር
41

You might also like