You are on page 1of 3

የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የጥር ወር 2015 የሴል የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት

ይህ የጥር ወር እግዚአብሔር በቃሉ እንደተናገረህ በድል የምትሻገርበት ወር ነው። ከፊትህ ያንተ የሆነ ነገር ግን ያላየከው፣
ያልረገጥከው፣ ያልጨበጥከው ርስት ጋር እንዳትደርስ ከሚጎትትህ እና ወደ ፊት እንዳትራመድ መንገድህን ከሚዘጋ ሃይል

በድል የምትሻገርበት ወር ነው። መዝሙረ ዳዊት 139 ፡ 15-16 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች
በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ
ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።

መወያያ 1 ፡ አንተ የፍጻሜ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ?


ፍጻሜህ በመጽሃፍ ተጽፎ አለ። እግዚአብሔር ለሕይወትህ በስራ ላይ ነው፣ አስቦ እና አቅዶ አንተን ወደ ምድር

አምጥቶሃል።ሁኔታዎች ባይመስሉ እንኳን ከእግዚአብሔር ጋር በትክክለኛ አቋም (Right standing)እስካለክ ድረስ


መጨረሻክ አሁን ያለህበት ሁኔታ አይደለም። ያንተ ፍጻሜ በእግዚአብሔር የተያዘ ነው። የአንተ ጥረት እና ግረት
በእግዚአብሔር ከተያዘልክ ፍጻሜ ጋር የሚወዳደር አይደለም።

ፍጻሜ ወደ ፊት እንድትሄድ የሚረዳህ ሃይል ነው። ሕይወት ሁል ጊዜ ወደ ፊት ነው። እግዚአ ሔር የያዘልህ ነገር ሁሉ ወደ

ፊት ነው። ከኋላ ያለውን ከተመለከትክ ለጉብኝት ወይም ለትምህርት ይሁንህ! አንተ እራስህን ካልገደብክ በስተቀር
ምንም ገደብ የለብህም። እግዚአብሔር የያዘልክ ፍጻሜ ‘እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ’ እንድትደርስ ነው።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3፡18 – 19 ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን
ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም
ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።

የፍጻሜህ አድራሻ ልብህ ነው። ልብህን አዳምጥ! ምንም ነገር ከፍጻሜ አያቆምህም። እግዚአብሔር ከጨለማው አለም
ያወጣህ ወደ መልካም ፍጻሜህ ሊያስገባህ ነው እንጂ በመንገድ ሊያስቀርህ አይደለም። አንተ ባላስተዋልከው መንገድም
ቢሆን ወደ መልካም ፍጻሜ ያደርስሃል። የእግዚአብሔር ቀኝ ይደግፍሃል።

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ
ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

ዮሴፍን ከፍጻሜው ሊያስቀረው ከፊቱ የመጣበትን ታላቅ መከራ አስብ። (ኦሪት ዘፍጥረት 37)በእያንዳንዱ የሕይወትህ
መንገድ፣በየደረጃው ከፊትህ የሚቆም ፈተና አለ።

የሕይወት ጉዞህን የሚወስነው የአንተ እውቀት፣ እምነት እና ተሻግሮ መግባት ነው።

የእምነት አዋጅ፡- አውቃለሁ፣ አምናለሁ፣በድል እሻገራለሁ!

መወያያ 2፡ እስኪ ሕይወትህን ዞር ብለህ ተመልከት፤ ተሻግረህ እንዳትገባ እንቅፋት ገጥሞኛል ብለህ ያሰብክበት ምዕራፍ
ካለህ አጋራን።

በሕይወት ወደ ፍጻሜህ እንዳትደርስ የሚገዳደሩ ሃይሎች አሉ፡-

1. ከኋላ ሆኖ የሚጎትት ኃይል

1
የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የጥር ወር 2015 የሴል የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት

ይህ ኃይል ባላንጣ እና ባላጋራ ነው። ያለፈ የቤተሰብህን ታሪክ፣ የራስህን የድካም ታሪክ፣ የደም ሃረግህን ተከትሎ ወደ
ፊት እንዳትሄድ ይከለክልሃል።የመጣህበትን የዘር ሃረግ እየቆጠረ፣ በማዋረድ፣ የማትረባ ነህ እያለ ያንኳስስሃል። ፈርኦን
የእስራኤልን ህዝብ ላለመልቀቅ የውሸት ይደራደር ነበር። እስራኤል ከእርሱ በእጁ ርቀት ላይ እንዲሆኑ ያቆያቸው ነበር።
ኢየሱስ ድንቅ ባደረገ ጊዜ ‘እናውቅሃለን’፣ ‘የጠራቢው ልጅ’ የሚሉት ነበሩ። እግዚአብሔር በሚያውቅህ ከማያውቅህ

ተለይ!!

የሉቃስ ወንጌል 4፡22

ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ፦ ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን ? ይሉ
ነበር።እርሱም፦ ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ፦ ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግኸው
የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ አላቸው።እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ
በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም።

ጎታች መንፈስ ወደ ፊት እንዳትሄድ የሚጎትትህ ኃይል ነው። ይህ ኃይል ያሳንስሃል፤በድሮ ስምህ የሚጠራ፣ቤተሰባዊ
መንፈስ ነው። አብሮ ያደገ፣ የኋላ ታሪክህን የሚያውቅ መንፈስ ነው። 1 ሳሙኤል 16፡11 ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ

ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል፤ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ
እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው።

2. ከፊት በመንገድህ ላይ ሆኖ አታልፍም፣አትገባም የሚል ኃይል


ዳዊት ወደ ታላቂቱ ጺዮን እንዳይገባ ኢያቡስ የተባለው ወደ ከተማዋ አትገባም ብሎት ነበር።

አማሌቅ እስራኤል ወደተስፋ ምድሩ በሚገሰግስበት ጊዜ በራፍዲም አላሳልፍህም ብሎ ተዋጋው።

1 ሳሙ 14፡2 ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ
እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ።

አማሌቅ የእስራኤል ወንድም የልጅ ልጅ ነው። (ዘፍጥረት 36፡9 – 12፣ መጽሃፈ አስቴር 7፡3- 9) አማሌቅ እና ሃማ
የእስራኤል ባላንጣዎች/ ባላጋራ ነበሩ። ባላጋራ የሆነ ጠላት ሲሸነፍ ፈጽሞ አይርቅም፣ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ እጅህ

የሚደክምበትን/ የሚወርድበትን፣(ዘጸአት 17፡ ከጌታ ጋር ያለህ ግንኙነት የሚበላሽበትን አጋጣሚ ይጠብቃል።

ኦሪት ዘጸአት 17፡ 8 – 14 ሙሴም ኢያሱን፦ ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔ ነገ
የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው። ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥
ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ
እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም
ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤
ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ። ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ።

መወያያ 3፡ ባላጋራን እንዴት ታሸንፈዋለክ?


2
የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የጥር ወር 2015 የሴል የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት

1. ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ባላጋራህን ተቃወም

የያዕቆብ መልዕክት 4፡ 7 – 8 እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤ወደ


እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።

2. ዝክሩን ፈጽመህ አጥፋ


ከአማሌቅ ጋር ያለህን ትስስር ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ። ጎረቤት አድርገህ አታስቀምጠው። የድሮ የሃጢያት ልምምድ፣
ውድቀት እንደገና በዙሪያህ ካንዣበበ አትታገሰው። በህልምህም በእውንህም እንዳይታሰብ አድርገው።

ኦሪት ዘጸአት 17 ፡ 14 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን
ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ ተናገር አለው።

ዘዳግም 25፡19 ፤ ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ
አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የአማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንን አትርሳ።

3. የቃሉን ሰይፍ አንሳ

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6 ፡17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።

እግዚአብሔር የነገረህን የበረከት ቃል አሰላስለው። በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ሃሳብህን እና ህልምህን በሙሉ


ተቆጣጠረው። ለአንተ የተነገረውን የእግዚአብሔርን ቃል ለግልህ ተቀበል። የእግዚአብሔር ቃል የጠላትን ፍላጻ
ያፈርሳል።

(ወደ እብራውያን 4፡12 ፣ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፡14 – 15፣ 2 ኛ ቆሮንቶስ 10 ፡5 ፣ መጽሃፈ ምሳሌ 4፡23)

መወያያ 4፡ ከትምህርቱ የተረዳከውን በአጭሩ አስረዳን።

You might also like