You are on page 1of 5

፩፦ የእግዚአብሔር መገለጥ ።

ፈጣርያችን ነው ብለን የምናምነው እግዚአብሔር ስሙን እንዴት አወቅን ? በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናጋሪዎች እኔ
"ኤሎሄ" "ያህዌ" እና "አዶናይ" ያለው ማነው። በመጽሐፍ ቅዱስ
ዘጸአት 3 (Exodus)
11፤ ሙሴም እግዚአብሔርን፡— ወደ ፈርዖን የምሄድ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ? አለው።
12፤ እርሱም፡— በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ
ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ፡ አለ።
13፤ ሙሴም እግዚአብሔርን፡— እነሆ፥ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፡— የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ
ላከኝ፡ ባልሁም ጊዜ፡— ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው።
14፤ እግዚአብሔርም ሙሴን፡— «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፡— «ያለና የሚኖር» ወደ
እናንተ ላከኝ ትላለህ፡ አለው።

በዝህ ክፍል እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ለሙሴ ትዕዛዝ ይሰጠዋል። ከላይ በምዕራፍ እንደምንመለከተው ሙሴ
ከግብፅ ሸሽቶ በምድያም ነበር። በዝህያም እግዚአብሔር በሚንበለበለው ቁጥቋጦ መካከል ሆኖ አናገሬው። ቁ ፲፬ ላይ
ነው እንግዲህ እግዚአብሔር ለሙሴ ስሙን የተናገረው ስሙም "ያለና የሚኖር ነው"። የእግዚአብሔርን ስም ራሱ
እግዚአብሔር ካልነገረን በስተቀር ማወቅ አይቻልም ።
ከላይ ለማየት እንዴተሞከረው እግዚአብሔር ራሱን ካልገለጠ በስተቀር ማንም ልያውቀው አይችልም ።
እግዚአብሔር ራሱን የገለጠ አምላክ ነው ።በተለያየ መንገድ እግዚአብሔር ስለማንነቱ ተናግሯል ። ከዝህም ውጭ
በራሳችን ጥረትና ምርምር ፤ በአጉል መንፈሳዊነትም እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም ። በመጽሐፍ ኢዮብ 11
(Job)
7፤ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር
ትችላለህን?
በዝህም ምዕራፍ እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ጥልቅ ምስጢር ማወቅ አንችልም ። ሰለ ታላቅነቱ በራሳችን
ጉልበት ማወቅ አንችልም ።እግዚአብሔር ከዕውቀታችን ፤ከመረዳታችን በላይ ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ራሱን
ለእኛ በምገባን መንገድ ገልጧል ።ይህንንም "አስተርእዮ" እንለዋለን ።ይህም እግዚአብሔር ራሱን ገልጧል ፤አሳቡን
አስታውቋል ማለት ነው። በዘመናት መካከል እግዚአብሔር የራሱን ማንነት በተለያየ መንገድ ስገልጥልን በተለያዩ
ሰወችም አማካኝነት ስናገረን ቆይቷል። ሆኖ በአጠቃላይ እግዚአብሔር በሁለት መንገድ ራሱን ለሰው ገልጧል ።
፩፦ General revelation/በአጠቃላይ መገለጥ።
መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ መንገድ እግዚአብሔር በተፈጥሮ ራሱን እንደገለጠ ይናገራል። ከነዝህም ሦስቱን እንመልከት።
1) መዝሙር 19 (Psalms)
፤ ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
፤ ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
፤ ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
፤ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
፤ በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ
ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
፤ አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።

መዝሙረኛው በዝህ ክፍል እንደምነግን ከሆነ የእግዚአብሔር ክብር በተፈጥሮ ተገልጦ እንመለከታለን ። ቁጥር 1 ፦
እንደ ማጠቃለያ ዐረፍት ነገር ነው ለምዕራፉ። የእግዚአብሔር ክብር ማንም ምንም ባያወራ በተፈጥሮ በኩል ግልጥ
ነው። ምንም ሳንል ምንም ሳንቀባጥር ከዘመናት በፍት እግዚአብሔር የከበሬ አምላክ ነው። የእጁ ሥራም ልደበቅም
አይቻልም ።
፦ቀናት ባለፉ ቁጥር ፣ሌልትም በሌልት በተቀያዬረ ግዜ ሁሉ ተፈጥሮ የፈጣሪውን መገኘት ያወራሉ ፤ ይናገራሉ ።
ቁጥር 1፦4
"The heaven continually display the fact that there is a creator . Even though creation doesn't
speaks audibly in words its message(voice) goes out to the endes if the earth. The message from
nature about glory of God reaches all nations and is equally intelligible to them all"
ቁጥር 4፦6
"Dominant in tye heaven is the sun. Like a bridge groom who is excitedly leaves his house on his
house on his wedding day, the sun rises and like the champion runner racing on his course , the
sun makes its circuit . These verses do more than speak of nature as as witness of Gods glory ;
They also undermine pagan beliefs , for the same way imagery was used of the sun god in ancient
near eastern literature " Bible knowledge commentary.

2) Acts 14 vs8-20 specially 17.


"Yet he didnot leave himself without witness ,for he did good by giving you rains from heaven and
fruitful season ,satisfying your hearts with food and gladness "
እግዚአብሔር ተፈጥሮ በምትሰጠው በረከት የራሱን ማንነት ምስክርነት ስሰጥ ነበር ።

3) Rome 1 vs 18-25

ከላይ ባሉ ክፍሎች እንደምንረዳው ከሆነ በአጠቃላይ መገለጥ የምንረዳው ነገር ቢኖር የእግዚአብሔር ማንነት ነው።
በአፅንኦትም የምያሳዬን ነገር ብኖር የእግዚአብሔር ጥበብና ኃይል ፣ መልካምነት ፣ግርማውነት ነው። ነገር ግን ይህ
መገለጥ የተገደበ ነው። በሙላትም የእግዚአብሔርን ማንነት አያሳየንም። ለዝህም ምክንያቱ የሚያዬው ሰው
በኃጥያት እስራት ውስጥ ሰለምገኝ። የ General revelation/የአጠቃላይ መገለጥ ፍይዳው ሰወች እግዚአብሔር
የለም የሚሉበትን ምክንያት ያሳጣል። ሆኖም ግን ይህ መገለጥ ወደ ድነት አያደሪሰንም። ስለዝህም ነው
እግዚአብሔር ራሱን በልዩ መገለጥ/Special revelation የገለጠው ።
ይህም ፋይዳው የወደቀው ሰው
፦የእርሱን ሙላት እንድያውቅ።
፦እንዴት እግዚአብሔር ኃጥያተኞች ላይ ከሚመጣው ቁጣ እንደምያድናቸው እንድያውቁ።
፦እንዴት መኖር እና እግዚአብሔር ማክበር እንዳለባቸው ማወቅ ሰለምያስፈልግ።

Mans chief and highest end is to glorify God, and fully to enjoy him forever .

፪፦ Specific revelation/ልዩ መገለጥ።

መገለጥ ማለት መከሰት ፤መታወቅ ፤መታየት ፤በዚህም መገኘት ማለት ነው። Revelation is Making plain or an
unfolding of that which is hidden .
Identity means who a person is, or the qualities of a person or group which make them different
from others. አንድ ሰው ራሱን ገለጠልን የምንሌው ብያንስ ሁለት ነገሮችን ስናውቅ ነው።
፦ማንነቱን/Identity
፦አሰተሳሰቡን/Will
እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ገለጠልን ስንልም ክብሩን ፣ጥበቡን ፣ባህሪውን ፣ፈቃዱን አሳውቋል ማለት ነው። ከላይ
ለማየት እንደሞከርነው አጠቃላይ የእግዚአብሔር መገለጥ በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ድነት ልወስደን አይችልም ።
ስለዝህ እግዚአብሔር በልዪ መገለጥ "በቃሉ" ተገለጠ ። በቃል ሰባል በሁለት መንገድ እንረዳዋለን ።
1 ፦የእግዚአብሔር አካላዊ ቃሉ ፦ኢየሱስ ክርስቶስ።
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አካላዊ መገለጥ ነው። ኢየሱስን ማወቅ ማለት እግዚአብሔርን ማወቅ ማለት ነው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክርነት ሰለ ኢየሱስ ማንነት እንመለከት።
፩) በኢየሱስ አገልግሎት ትልቅ ቦታ ከነበራቸው አገልጋዮች /ሐዋርያት መካከል አንዱና ዋንኛው የሆነው ሐዋርያው
ዮሐንስ ሰለ ማንነቱ በምገባ ጽፏል።
ዮሐንስ 1 (John)
"1፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። "
በዝህ ክፍል የምንመለከተው ሦስት መሰረታዊ ነገሮች ሰለ ኢየሱስ።
፦በመጀመሪያ ነበር ።
፦ከእግዚአብሔር ነበር።
፦እግዚአብሔር ነበር ።

ዮሐንስ 1 (John)
"14፤ ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው
ክብሩን አየን።" ከላይ ቁጥር አንድ ለይ ያለው ቃል ነው እንግድህ ሰው የሆነው ። ይህንን Incranation/ትስጉት
እንለዋለን ።

ዮሐንስ 1 (John)
18፤ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። በአ .መ.ት
ገለጠው በምል ተረከውን ይገልጻል። ከዝህ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ማንነቱን
ገልጧል ። በብሉይ ክዳን ብዙ ሰወች እግዚአብሔርን ተመልክቷል ይላል ቃሉ።ዘጸአት 24 (Exodus)
9፤ ሙሴም አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ፤
10፤ የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ
የሚመስል ወለል ነበረ።
11፤ እጁንም በእስራኤል አዛውንቶች ላይ አልዘረጋም፤ እነርሱም እግዚአብሔርን አዩ፥ በሉም ጠጡም።
ዘጸአት 33 (Exodus)
20፤ ደግሞም፡— ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም፡ አለ።

ስለዝህ ከነዝህ ጥቅሶች እንደምንረዳው ማንም እግዚአብሔርን በመለኮታዊ ባሕርይ ያዬ ሰው የለም ።ነገር ግን
ክርስቶስ ገለጠው።

፪) ቆላስያስ 1 ፥15
"እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው።"

፫) 2 ቆሮንቶስ 4 (2 Corinthians)
4፤ ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ
የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።
5፤ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች
እናደርጋለን።
፬) ዕብራውያን 1 (Hebrews)
3፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ
በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤

ከነዚህ ሦስት ጥቅሶች የምንረዳው ሁለት ጭብጦችን ነው።


፦ እግዚአብሔር የማይታይ አምለክ መሆኑን ።
፦የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ የሆነውና የሰው ሥጋ የለበሰው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ባህሪ መግለጽ ነው።
ስለዝህ በጥቅቱ በነዚህ ክፍሎች ተመሥርተን ኢየሱስ የእግዚአብሔር መገለጥ መሆኑን እናያለን ።
ሌሎች ጥቅሶች ፦(ዘፍ 1 እሰከ ራእይ 22)

2 ፦የእግዚአብሔር ሥነ ጽሑፍዊ ቃል ፦

መጽሐፍ ቅዱስ ፦የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሆኑ የእግዚአብሔር ምስክር ነው። ሰለ እግዚአብሔር ማንነትና ምንነት
እንድህም መልካም ሐሳቡንና ምክሩን ያወቅነው በቃሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰወች ሰለ እግዚአብሔር የሚያዉቁትን
የተናገሩበት ሳይሆን እግዚአብሔር ስለ ራሱ መናገር የሚፈልገውን የገለጠበት ነው። ቋንቋው እና ጻሐፍዮቹ ሰወች
ይሁኑ እንጅ ምንጩ እግዚአብሔር ነው።

እውነት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው?? THE ANSWER IS BOLDY YES.

፩፦ ሰለ ራሱ የምሰጠው ምስክርነት።
በመጽሐፍ ቅድስ ውስጥ
OT/

You might also like