Professional Documents
Culture Documents
Atse
Atse
፲፥፲፬”
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ሚያዚያ 2014
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 1 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ምስጋና
‹‹ምስጋና በሰማይ ለእግዚአብሔር ይሁን በምድርም ላይ ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው›› (አንቀጸ ብርሃን)
‹‹ቅድስት ሆይ ብፅዕት ነሸ የተመሰገንሽና የተባረክሽ ነሽ……. አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ከተለዩ የተለየሽ የመለኮት ማደሪያ ነሽ …. ቅድስት ሆይ
ልጅሽን ይቅርታ ያድለን ዘንድ ለምኝልን፡፡›› አሜን (አንቀጸ ብርሃን)
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 2 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ክፍል ፩
የኦሪት ዘጸአት መጽሐፍ መግቢያ
1. ኦሪት ዘጸአት
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 3 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
- እግዚአብሔር በሲና ሕግን ሰጥቶ ከእስራኤል ጋር ላደረገው ቃል ኪዳን ሙሴ መካከለኛ ነበር (ዘጸ 19, 7 ፣ ገላ 3, 19)፡፡
- እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳን መቅደስ አሠራ (ዘጸ 25-31 እና ከ 35-40)፡፡
- በእጁም አሮንና ልጆቹን ለክህነት የለየ ለሕዝቡም የጸለየ ካህን ነበር (መዝ 99, 6 ፣ ዘሌ 8 እና 9 ዘጸ 32, 30-32)፡፡
- እግዚአብሔር “አፍ ለአፍ በግልጥ” ያናገረው እግዚአብሔርንም “ፊት ለፊት” ያወቀ ነቢይ ነበር (ዘኁ 12, 6-8 ፣ ዘዳ 34, 10-12)፡፡
- አብዛኛዎቹ በእጅ ስለ ተጻፉ አምስቱ የኦሪት መጻሕፍት “የሙሴ” ተብለው ይጠራሉ (ሉቃ 24, 27)፡፡
ሙሴ ታቦት የተባለውን ቅዱስ ነገር እንደሠራ ይታወቃል ፤ ለመሆኑ የዚህ ታቦት አሠራሩ እንዴትና ከምን ነበር? ዋና አገልግሎቱስ ምን ነበር?
ሙሴ በእርግጥ ከግራር እንጨት ታቦትን እንዲሠራ ታዘዘ ፡፡ አሠራሩም ሣጥን ዓይነት ነበረ ፡፡ ርዝመቱ 125 ፣ ወርዱ 75 ፣ ቁመቱ 75 ሳንቲ ሜትር ያህል ነበረ ፡፡
ታቦቱ በወርቅ የተለበጠ መክደኛውም ከወርቅ የተሠራ ነበር ፤ በላዩም ሁለት ኪሩቤል ተቀርጸዋል ፡፡
1.4.1.2. ታቦት
የታቦቱ አገልግሎት የነበረው ፦
1. ዐሠርቱ ቃላት የተጻፉባቸው የሁለቱ ጽላት ማኖርያ
2. ከእስራኤል መሪዎች ጋር የእግዚአብሔር መገናኛ ነበር ፡፡ ስለዚህ ታቦቱ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የመኖሩ ምልክት ነበር (ዘጸ 25, 1-22 ፤ 40, 20) ፡፡
ሙሴ ታቦቱን አሠርቶ ሲያበቃ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አኖረው ፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ ይዘውት ይጓዙ ነበር ፡፡ በተለይም ዮርዳኖስን ሲሻገሩና ኢያሪኮን ሲዞሩ ካህናት
ተሸክመውት ፊት ፊት ይሄዱ ነበር (ኢያ 3, 16)፤ የእስራኤል ሕዝብ ከኃጢአታቸው ሳይመለሱ በጦርነት እንደ መከላከያ መሣርያ ሲሸከሙት ታቦቱ በመሳፍንት ዘመን
በፍልስጤማውያን ተማረከ ፡፡ ታቦቱ በእግዚአብሔር ስም የተጠራ ስለነበር እግዚአብሔር በፍልስጤማውያን ላይ ብዙ ተአምር አደረገ ፤ ፍልስጤማውያንም መለሱት (1
ሳሙ 4-6) ፡፡ በኋላም ዳዊት ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው ፡፡ ሲያመጣውም ዖዛ የተባለው ሰው በድፍረት ስለነካው ተቀሠፈ (2 ሳሙ 6) ፤ ሰሎሞንም ራሱ በሠራው ቤተ
መቅደስ አኖረው (1 ነገ 8) ፡፡ ታቦቱ በኢዮስያስ ዘመን በቤተ መቅደስ ነበረ (2 ዜና መ. 35, 3)፡፡ በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ወደፊት የእስራኤል ሕዝብ ስለ ታቦቱ ምንም
እንደማያስብ ትንቢት ተናገረ (ኤር 3, 16)፡፡
ነቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ሲያፈርስ ታቦቱ የጠፋ ይመስላል ፡፡ ምክንያቱም ዘሩባቤል በሠራው ቤተ መቅደስ ታቦት አልነበረምና ፡፡ በአዲስ ኪዳን የቃል ኪዳኑ ታቦት
በእግዚአብሔር ሰማያዊ መቅደስ እንደታየ ተጠቅሷል (ራእ 11, 19)፡፡
ሙሴ ከሲና ተራራና ከኮሬብ ጋር በተያያዘ መልኩ ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል ፤ ሙሴና ሲና ተራራ ግኑኝነታቸው ምንድን ነው?
ሲና ብዙ ጊዜ ተራራ እንደሆነ ሲጠቀስ ይደመጣል ፤ ነገር ግን ሲና ተራራ ሳይሆን ብዙ ተራሮች በውስጡ የያዘ ወይም ያካተተ ከግብጽ አገር በስተምሥራቅና
ከእስራኤል በስተደቡብ የሚገኝ አገር ነው ፡፡ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት 40 ዓመት እንደ ተጓዙ ይታወቃል (ዘጸ 19, 1) ፡፡ ሌላው ደብረ ሲና
የሚባለው ሲና ውስጥ ከሚገኙት ተራሮች አንዱ ሲሆን ዐሠርቱ ቃላት የተሰጡበት ተራራ ነው (ዘጸ 19, 20) ፡፡ ይህ ደብረ ሲና ኮሬብም ተብሎ ይጠራል (ዘጸ 3, 1 ፣ ዘዳ 4,
9-10) ፡፡ ሙሴም ዐሠርቱ ቃላት በዚህ ተራራ ላይ ሆኖ ስለተቀበለ ስሙ በተደጋጋሚ ከዚህ ተራራ ጋር በተያያዘ መልኩ ይጠራል ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 5 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 6 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
10. የሌላውን ሰው ቤቱን ፣ ርስቱን ፣ አገልጋዮቹን ፣ ከብቱን ፣ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ
ሰንበትን አክብር ፤ ቀድሰውም ሲል የትኛውን ቀን ያመለክታል? ለምንስ መከበር ያስፈልገዋል? አለማክበርስ ምን ሊያስከትል ይችላል?
ሰንበት በዕብራይስጥ “ማቆም” “መተው” ማለት ነው ፡፡ እስራኤላውያን ሰባተኛውን ቀን ለእግዚአብሔር እንዲቀድሱት ከላይ በተዘረዘሩት ዐሠርቱ ትእዛዛት
ተነግረዋል (ዘጸ 20, 8-11) ፡፡ ከዚህም በላይ ሰንበት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ነው (ዘጸ 31, 17) ፡፡ በዚህም ምክንያት ሰንበትን አለማክበር
ከባድ ቅጣትን ያስከትል ነበር (ዘኁ 15, 32-36) ፡፡
ሰንበት የእግዚአብሔር ሥራ እንዲታወስ ያደርጋል ፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ስድስት ቀን ሠርቶ እንዳረፈ ሁሉ ሰውም በዚህ ዓለም ሠርቶ ወደ ዘለዓለም ዕረፍት
አገራቸው ሲደርሱ ዐሠርቱ ቃላት በድጋሚ ተነገራቸው ፡፡ ከዚህም ላይ ሰንበት እግዚአብሔር እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እንዳወጣቸው ያመለክታል (ዘዳ 5, 12-16) ፡፡
እስራኤል ቀኑን በሚገባ ባለማክበራቸው በነቢያት ተወቅሰዋል (ሕዝ 20, 12-16 ፣ አሞ 8, 6) ፤ እንዲያከብሩትም ተስፋ ተሰጥቷቸዋል (ኢሳ 56, 2-4 ፣ 58, 13-14) ፡፡
ነህምያ ሰንበትን አስከብሯል (ነሀ 10, 31 ፣ 13, 15-22) ፡፡ ኢየሱስ ሰንበትን አክብሯል (ሉቃ 4, 16 ) ፤ የፈሪሳውያንን የሰንበት አከባበር ግን ተቃውሟል ፡፡ እነርሱ ቀኑ
እንዲከብር ብቻ እሸት ከመቅጠፍ ፣ ድውይ ከመፈወስ እስኪከለክሉ ድረስ ብዙ ሕግና ወግ ደንግገው ነበር ፡፡ ክርስቶስ ግን ከሰው ወግና ሥርዓት ምህረት እንደሚበልጥ
አስተማረ (ማቴ 12, 1-14)፡፡
እግዚአብሔርን ሳያስቈጣው አልቀረም (ዘጸ 32) ፡፡ አሮን ለተለየ አገልግሎት በእግዚአብሔር የተመረጠ ለመሆኑ በበትሩ ማቈጥቈጥ ታወቀለት (ዘኁ 17) ፡፡ ቢሆንም መሪባ
በተባለው ስፍራ ከሙሴ ጋር ሆኖ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባለማክበሩ ኃጢአት ሠራ (ዘኁ 20, 12) ፡፡
አሮን ከክህነት ሕይወት ጋር ለምን ተያይዞ ይጠቀሳል? ክህነት ማለት ምን ማለት ነው? ከብሉይ ኪዳን አኳያ ሲታይ አመሠራረቱስ እንዴት ነው?
በእርግጥ አሮን ሊቀ ካህናት እንዲሆን በመመረጡ ከሌዊ ወገን ካህናት የመጀመሪያው ሆነ (ዘጸ 28, 1) ፡፡ ልጆቹም ካህናት እንዲሆኑ ተቀደሱ (ዘሌ 8, 12- 13, 30) ፡፡ በ 123
ዓመቱ ሲሞት ሊቀ ካህናትነቱ ለልጁ ለአልዓዛር ተሰጠ (ዘኁ 20, 22-29 ፣ 33, 38 ፣ ዘዳ 10, 6) ፡፡ ከዚህም በላይ በአዲስ ኪዳን አሮን የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ተቈጥሯል
(ዕብ 5, 4-5) ፡፡
ክህነት (ካህን) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ነው ፡፡ ካህን ማለት አገልጋይ እንደማለት ነው ፡፡ ከብሉይ ኪዳን አኳያ ስናይ
አገልግሎቱ መሥዋዕትን በመሠዋትና ጸሎት በመጸለይ ይፈጸማል ፡፡ ካህን በማንኛውም ሃይማኖት አለ (ዘፍ 41, 45 ፣ 1 ሳሙ 6, 2 ሐዋ 14, 13) ፤ በመጀመሪያ እንደ አቤልና
ቃየል ሰው ለራሱ የራሱን መሥዋዕት አቅራቢና ሠዊ ነበር (ዘፍ 4, 3-4) ፤ በኋላም አንደ ኖኅና እንደ አብርሃም አባት ለቤተሰቡ ይሠዋ ነበር (ዘፍ 8, 20 ፣ 12, 7 ፣ 13, 18)
፡፡ ሕግ ሲሰጥ ግን አሮንና ልጆቹ ለእስራኤል ካህናት እንዲሆኑ ተመረጡ (ዘጸ 28, 1) ፡፡ ከአሮን ቤተሰብ ውጭ የሌዊ ዘሮች በመቅደስ ያገለግሉ ነበር እንጂ መሥዋዕትን
አልሠዉም (ዘኁ 3, 5-10)፡፡
ሆኖም ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው ቢሆንም እግዚአብሔር ራሱን ከገለጠለት እንደ ጌዴዎን መሥዋዕት ይሠዋ ነበር (መሳፍ 6, 18-26 ፣ 13, 16) ፤ እንደዚሁም
የእግዚአብሔር ካህናት ሲጠፉ ኤልያስ መሥዋዕት ሠዋ (1 ነገ 18, 30) ፡፡ ከአሮን ልጆችም ነውር ያለበት ከተገኘ አይሾምም ነበር (ዘሌ 21, 16-24) ፡፡
አሮንና ልጆቹ ሲሾሙ ልዩ ልብስ ለብሰው በዘይት ይቀቡ ነበር (ዘጸ 28, 40 ዘሌ 8) ፡፡ አገልግሎታቸውንም በብዙ ጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ታዘዙ (ዘጸ 30, 17-21) ፡፡ በዚያን
ጊዜ የካህናት ሥራ በመቅደስ ማገልገል (ዘኁ 16, 40 ፣ 18, 5) ሕግን ለአሕዛብ ማስተማር (2 ዜና መ. 15, 3 ሕዝ 7, 26) ፣ በኡሪምና ቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ
መጠየቅ (ዘጸ 28, 30 ዕዝ 2, 63) ፣ ተላላፊ በሽታ ያለባቸውን መለየት ነበር (ዘሌ 13, 1-3) ፡፡
በአጠቃላይ ካህናት በቤተ መቅደስ የሚፈጽሙትን አገልግሎት በሦስት (3) ይከፋላል ፦
1) ዕለታዊ አገልግሎት ፦ ይህ ጠዋትና ማታ የሚቃጠል መሥዋዕትን የመሠዋት ፣ በቅድስት መብራቶችን የማብራት ፣ ዕጣን የማጠን ፣ ሰው የሚያመጣውን መሥዋዕትም
በያይነቱ የማቅረብ አገልግሎት ነበር (ዘጸ 29, 38-39 ፣ 30, 1-8) ፡፡
2) ሳምንታዊ አገልግሎት ፦ በየሰንበቱ ዐሥራ ሁለት የመገኘቱን ኅብስት በገበታው ላይ የማኖር አገልግሎት ነው (ዘሌ 24, 5-9) ፡፡
3) ዓመታዊ አገልግሎት ፦ በማስተሥረያ ቀን ልዩ ሥርዓትን የመፈጸም አገልግሎት ነው (ዘሌ 16) ፡፡
ሊቀ ካህናት የሚባለውስ አመጣጡ ከየት ነው? የአገልግሎት ተግባሩስ ምንድን ነው? ከአሮን ጋር ለምን ታያይዞ ይጠቀሳል?
ሊቀ ካህናት ማለት ካህናትን የሚቆጣጠር የካህናት አለቃ ማለት ነው ፡፡ ይህ ማዕረግ በመጀመርያ ለአሮን በኋላም ከአሮን ቤተሰብ ለዋናው ስለተሰጠ ከአሮን ጋር በተያያዘ
መልኩ ብዙ ጊዜ ሲጠቀስ ይሰማል ፡፡ በመጀመርያ ጊዜ እልቅናው እስከ ሞት ድረስ ነበር ፤ በኋላ ግን ነገሥታት እንደፈለጉ ሊቃነ ካህናትን ይሾሙና ይሽሩ ነበር ፡፡
በክርስቶስ ጊዜም እንደነ ሐና ያሉ በሮም መንግሥት የተሾሙ ሊቃነ ካህናት ነበሩ (1 ነገ 2, 26 ሉቃ 3, 2) ፡፡ የሊቃነ ካህናቱ ልብሶች በዕውቅ (በልዩ ዓይነት) የተሠሩ ነበሩ
፡፡ እነርሱም ኡሪምና ቱሚም የተቀመጡበት የደረት ኪስ ፣ ኤፉድ ፣ ቀሚስ ፣ ዝንጉርጉር ሸሚዝ ፣ መጠምጠሚያ “ቅድስና ለእግዚአብሔር” የሚል የተቀረጸበት የወርቅ
አክሊልና መታጠቂያ ናቸው (ዘጸ 28, 1-39) ፡፡
አሮን ሲሾም ሙሴ እንዲያለብሰው በዘይትም እንዲቀባው ታዘዘ (ዘጸ 29, 1-9) ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 8 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
መልከ ጼዴቅ ከሙሴና ከአሮን በፊት እንደነበረና ከክህነታዊም አገልግሎት ጋር በተደጋጋሚ ይጠቀሳል ፤ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ከአሮን ክህነት ይበልጣል ወይስ
ያንሳል?
መልከ ጼዴቅ ማለት የጽድቅ ንጉሥ ማለት ነው፡፡ የሳሌም ንጉሥ ነበር ፡፡ ይህም የሰላም ንጉሥ ማለት ነው ፡፡ ምናልባትም “ሳሌም” ኢየሩሳሌም ይሆናል ፡፡
የእግዚአብሔርም ካህን ነበር (ዕብ 7, 1-3) ፡፡ አብርሃም ከጦርነት በተመለሰ ጊዜ መልከ ጼዴቅ ባረከው ፤ አብርሃምም ከሀብቱ ሁሉ ዐሥራትን ሰጠው (ዘፍ 14, 18-20) ፡፡
ክህነቱ በእርግጥም ከአሮን ክህነት እንደሚበልጥ ተጽፎለታል ፡፡ ይህም አንደኛ በሥጋዊ ትውልድ ሳይሆን በእግዚአብሔር መሐላ በመሾሙ (ዕብ 5, 5-6 ፣ 7, 13-17) ፡፡
ሁለተኛ በሞት ሳይወሰን ለዘለዓለም በማገልገሉ ነው (ዕብ 6, 20 ፣ 7, 3 እና ከ 23-25 ፡፡ ክርስቶስ እንደ መልከ ጼዴቅ በእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት በመባሉ የአሮንን
ክህነት አስቀርቷል (ዕብ 5, 7-10 ፣ 7, 11-19) ፡፡
የክርስቶስ ክህነት ከመልከ ጼዴቅና ከአሮን ክህነት(ሊቃነ ክህነት) ጋር በተያያዘ መልኩ እንዴት ሊገለጽ ይችላል?
ክርስቶስ እንደ መልከ ጼዴቅ ካህን ሆኖ ለኃጢአት ሁሉ የሚበቃውን መሥዋዕት አቅርቧልና የአሮን ክህነት አስቀርቷል (ዕብ 7, 11-28) ፡፡ የክህነቱን ሥራ የፈጸመው
በምድራዊ መቅደስ ሳይሆን በሰማያዊ መቅደስ ፣ በእንስሳት ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው (ዕብ 9, 11-12) ፡፡ አሁን ለኃጢአት ሌላ የደም መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልግም ፤
ሆኖም ምእመናን ሁሉ በክርስቶስ ሥራ መሠረት መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ስለሚያቀርቡ የሚሰጡትን ምስክርነትም ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር ስለሚያደርሱ
ካህናት ተብለዋል (ሮሜ 12, 1 ፣ ዕብ 10, 19-25 ፣ 13, 15 ፣ 1 ጴጥ 2, 5-9 ራዕ 1, 5-6) ፡፡
ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት በመሆን ራሱን አንድ ጊዜ ሠውቶ ወደ ሰማያዊ መቅደስ ገብቷልና የሊቀ ካህናት ሥራ በአዲስ ኪዳን ቀርቷል (ዕብ 9, 1-28 ፣
10, 12-21) ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 9 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
የተመረጡት የአብርሃም ዘሮች በግብፅ ለም በነበረው ምድር ሰፈሩ። በዚያም በሚቀጥሉት አራት ምዕተ አመታት ወደ ሰሜን ተንቀሳቅሰው ከነዓንን እስከሚይዙበት
ጊዜ ድረስ በዙ፤ በለጸጉም (ዘፍ፥ 15:13፤ ዘጸ፥12:41)።
ከዚያም ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉስ ወደ ስልጣን እንደመጣ ይነግረናል። የግብፅ ንጉስ ፈርዖንም የእስራኤልን ማደግና መብዛት ሲያዩ እጅግ በመፍራት
ዕድገታቸውን የሚያስቆምበት ዘዴ ፈልጎ "ባሮች" አደረጋቸው።
ፈርዖንም በእስራኤል ሕዝብ ላይ ግብር አስገባሪዎችን በመሾም አስጨነቃቸው፤ እጅግም አሰቃያቸው፤ "በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎች
ሾመባቸው"(ዘጸ፥1:11)። ነገር ግን ባስጨነቋቸው መጠን የእስራኤል ሕዝብ ቁጥር መብዛቱን ቀጠለ።
የዕብራዊያን ሴቶች ሲያዋልዱ ሕፃኑ ወንድ ከሆነ እንዲገደል የሚል ሌላ ትዕዛዝ ለአዋላጆች ተሰጠ። አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን ስለፈሩ ይህም አልተሳካም።
ንጉሱ ፈርዖን ሌላ ትዕዛዝ ሰጠ፤ "የሚወለደውንወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ሁሉ ግን በህይወት አድኑአት"(ዘጸ፥1:22)። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሁሉ
እግዚአብሔር ሕዝቡን ከቀድሞ ይልቅ እጅግ ማብዛቱን ቀጠለ።
እስራኤላውያንም ከበዛባቸው ጭቆና እና መከራ የተነሳ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እግዚአብሔርም የሕዝቡን ጩኸት ሰማ፤ ከአባቶቻቸው ጋር የገባውንም ኪዳን አሰበ። ሕዝቡን ነፃ ያወጣ ዘንድ ሙሴን ሰጣቸው።
ዘጸአት 1-4
የእግዚአብሔር ሕዝብ በባርነት ቀንበር ሥር መሆን እና እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት ለማውጣት ሙሴን ስለ መጥራቱ :: ዘጸ. 1-12፡36 እስራኤላውያን በግብፅ ምድር
ዘጸአት 25-40
1. እግዚአብሔርን የማምለኪያ ስፍራ የሆነው የመገናኛው ድንኳን እንዴት መሠራት እንዳለበት የሚናገረው መመሪያ ሰፊውን ክፍል ይዟል። ቀጥሎም የእስራኤል ሕዝብ
የተሰጣቸውን ትእዛዝ ተቀብለው እግዚአብሔር የሚኖርበትን የመገናኛ ድንኳን እንዴት እንደሠሩ ይናገራል።
2. በሁለተኛ ደረጃ የካህናትና የሊቀ ካህኑ አልባሳት እንዴት እንደተሠሩ የሚናገር ክፍል እናገኛለን።
3. ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ የጥጃን ምስል ሠርተው እንዴት እንዳመለኩ የሚናገር ክፍል እናገኛለን።
በአጠቃላይ የኦሪት ዘጸአት ታሪክ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡:
1. እስራኤላውያን በግብፅ ምድር (ዘጸ. 1-12፡36)
2. ከግብፅ ወደ ሲና ተራራ የተደረገ ጉዞ (ዘጸ. 12፡37- ምዕ. 18)
3. በሲና ተራራ የቃል ኪዳኑ መሰጠት (ዘጸ. 19-40)
በሲና ተራራ የተደረጉ አራት ዋና ዋና ድርጊቶች በኦሪት ዘጸአት ውስጥ ተገልጸዋል።
አንደኛ፡- እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በጽላት ላይ የጻፋቸውን ዓሠርቱን ትእዛዛት ሰጣቸው።
ሁለተኛ፥ የተቀደሱ ሕዝቦች ይሆኑ ዘንድ መጠበቅ ያለባቸውን የቃል ኪዳን መመዘኛዎች እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሰጣቸው።
ሦስተኛ፥ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን የሚያመልኩበትን የመገናኛ ድንኳን አሠራር የሚያመላክት ትእዛዝ ተቀበሉ። በተጨማሪ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ካህናትን
ለአገልግሎት የመመደብንም ትእዛዝ ሰጣቸው። በሲና ተራራ ላይ እያሉ እነዚህን ትእዛዛት ፈጸሙ።
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 10 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
አራተኛ፥ እስራኤላውያን የጥጃ ምስል ሠርተው በማምለክ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት አደረጉ፤ የማመንዘር ኃጢአትንም ፈጸሙ፤ እግዚአብሔርም በብርቱ ቀጣቸው።
ከዚህ በታች የኦሪት ዘጸአትን ታሪክ በሚገባ ለማስታወስ የሚረዳ ዝርዝር አስተዋጽኦ ቀርቦአል፡-
1. እግዚአብሔር ሕዝቡን – እስራኤልን ከግብፅ አዳነ (ዘጸ. 1-18)
ሀ. እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበዛ የገባውን ቃል ኪዳን ፈጸመ (ዘጸ. 1)
ለ. እግዚአብሔር ሙሴን ለመሪነት መርጦ አዘጋጀው (ዘጸ. 2-6)፣
ሐ. እግዚአብሔር ግብፅን በአሥር መቅሠፍቶች መታ (ዘጸ. 7-11)፤
መ. እግዚአብሔር የፋሲካን በዓል ለእስራኤል ሕዝብ ሰጠ (ዘጸ. 12፡1-28)፤
ሠ. እስራኤላውያን ከግብፅ ወጡ (ዘጸ. 12፡29-51)፤
ረ. በግብፅ የተወለዱት የእስራኤላውያን በኩራት በሙሉ ተቀደሱ (ዘጸ. 13፡ 1-16)፤
ሰ. እስራኤላውያን ቀይ ባሕርን ተሻገሩ (ዘጸ. 13፡17-15፡21)፤
ሸ. እስራኤላውያን ወደ ሲና ተራራ ተጓዙ (ዘጸ. 15፡22-18፡27)።
2. እግዚአብሔር በሲና ተራራ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ (ዘጸ. 19-24)
ሀ. አይሁድ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘትና ቃል ኪዳን ለመቀበል ተዘጋጁ (ዘጸ. 19)፤
ለ. እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ዓሠርቱን ትእዛዛት ሰጣቸው (ዘጸ. 20፡1-17)፤
ሐ. እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተቀደሰ አንዋንዋር መመሪያ ሰጣቸው (ዘጸ. 20፡18-23፤ 33)፤
መ. እስራኤላውያን በቃል ኪዳኑ ተስማሙ፤ ቃል ኪዳኑም ተረጋገጠ (ዘጸ. 24፡1-8)።
3. እግዚአብሔር የሚመለክበትን የመገናኛ ድንኳን አሠራር የሚመለከት ትእዛዝ ሰጠ (ዘጸ. 25-40)
ሀ. የመገናኛውን ድንኳን ለመሥራት ዝግጅት ተደረገ (ዘጸ. 24፡9-31፡18)፤
ለ. እስራኤላውያን ጣዖትን በማምለክ ኃጢአት ላይ ወደቁ፤ ተፈረደባቸውም (ዘጸ. 32-34)፤
ሐ. የማደሪያው ድንኳን ተሠራና እግዚአብሔር አደረበት (ሕልውናውን ገለጠበት) (ዘጸ. 35-40)።
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 11 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
• በበለጠ ደግሞ በየቤታችሁ መጽሐፍ ቅዱሶቻችሁን በማንበብ የተሻለ መረዳት እግዚአብሔር ይሰጣችኃል።
ዋና ዓላማ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን የእግዚአብሔር ባሕርይና ሥራ መግለጥ ነው፤ ስለዚህ በዘጸአት በርካታ እውነቶች:
1.እስራኤላውያንን ጌታ ከታደጋቸው በኋላ በስፍራው መድረሳቸውና በሲና መስፈራቸው (ዘፀ. 19፡1-2)
2.እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የቃል ኪዳን ውል መግባቱ (ዘፀ. 19፡7-8)
3.እስራኤል ቃል ኪዳኑን በመቀበል የሰጠው ምላሽ (ዘፀ. 19፡7-8)
4.ቃል ኪዳኑን በመደበኛ የመቀበል ዝግጅት (ዘፀ. 19፡9-25)
5.የዐሥርቱ ትእዛዛት መታወጅ (ዘፀ. 20፡1-17)
6.ሙሴ እንደ ቃል ኪዳኑ አማላጅ (ዘፀ. 20፡18-21)
7.የቃል ኪዳኑ መርኅዎች መቅረባቸው (ዘፀ. 20፡22-23፡22)
8.የቃል ኪዳኑ መጽናት (ዘፀ. 24፡1-18)
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 12 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ክፍል ፪
ትርጓሜ
2. የኦሪት የህግ መጽሐፍት ትርጓሜ
ይህንን የትርጓሜ መጻሕፍት ስታነብ የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል::
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 13 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ከሕገ ልቦናም በኋላ በሕገ ኦሪት ማለትም ከሙሴ ጀምሮ እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ ብዙ መሥዋእቶች ቀርበዋል በተለይም ይህ የመሥዋእት አቀራረብ ከሕገ ልቦና መሥዋእት
አቀራረብ ለየት የሚደርገው ብዙ የመሥዋእት አይነቶች ስላሉት እና መሥዋእቱም የሚቀርበው በተወሰኑ አካላት/ካህናት/ መሆኑ ነው፡፡( ዘጸ 29፡38፤ ዘሌ 24፡5-9 ፤ ዘጸ 23፡14 ፤
ዘጸ 34፡18 ፤ ዘሌ 23፡23-44 ፤ ፤ዘጸ 23፡16 ፤ዘሌ 23፡9-21 )፡፡
በተለይም እነዚህ መሥዋእቶች በተለያየ ምክንያት የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ ከነዚህም መካከል፡- ሰዎች ክህነት ሲቀበሉ ሲነግሱ እና ንዋያተ ቅድሳት ሲከብሩ ሰዎች ለመንጻት ከኃጢአታቸው
ለመላቀቅ ለመቀደስ ከበደል ከርኩሰት ለመንጻት……..( ዘሌ 12፡1፤ ዘሌ 14 ፤ ዘሌ 15፡16 ፤ ዘሌ 4፡1-35 ዘሌ 5፡1-19 ፤ ዘሌ 22፡23 ፤ ዘሌ 22፡23 ፤ዘሌ 11፡18 ፤ ዘሌ 6፡1)
ነበር፡፡
እነዚህ ለተለያዩ አላማ የሚቀርቡት መሥዋእትም በማቃጠል ደም በመርጨት በማጤስ በመጋገር .....ይቀርቡ ነበር፡፡( ዘሌ 7፡37 ፤ ዘሌ 6፡8 ፤ ዘሌ 6፡14 ፤ ዘሌ 6፡24 ፤ ዘሌ 7፡1 ፤
ዘሌ 7፡11-18 ፤ዘሌ 7፡28 ፤ ዘሌ 8፡22 )፡፡
እነዚህ መሥዋእቶች አፍአዊ የኃጢአት ስርየትን ቢያሰጡ እንጂ ዘለአለማዊ ህይወትን የነፍስ አርነትን ማሰጠት አልተቻላቸውም ነበር ምክንያቱ ደግሞ የሚቀርበው መሥዋእት
ፈርሰው በስብሰው ከሚቀሩ እንስሳት እና ከእህል ወገን በመሆኑ ፤ ሞትን ድል መንሳት የሚቻላቸው መሥዋእት ባለመሆናቸው ፤ መሥዋእቶቹም ተደጋጋሚ እና አስልቺ/ሸክም/
ስለሆኑ ነው ::
ዘሌ 17፡11 ፤ ዘሌ 17፡11 ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 14 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
የጥጃ ምስል አቁመው ጣኦት በማምለካቸው(ዘጸ 32፡4-35) ምክንያት ከነገድ ሌዋውያንን ለክህነት ማለትም የእለቱ መሥዋእት እንዲያቀርቡ ከቤተሰብ ደግሞ የአሮንን ቤተሰብ
ለሊቀ ካህንነት መርጦ በየአመቱ በማስተስረያ ቀን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲገቡ መሥዋእትን እንዲያቀርቡ የመረጠ ቢሆንም፡፡
ይህ የብሉይ ኪዳኑ የክህነት አገልግሎት በመሐላ የተሾመ ፤ በነገድ የተወሰነ ፤ ፍጹም ያልነበረ ፤ጊዜያዊ የነበረ ፤ አፍአዊ እንጂ ውሳጣዊ ዘለአለማዊ የሆነ የኃጢአት ሥርየትን የማያሰጥ
ነበር ፡፡ካህኑም /ሊቀ ካህኑም /አስቀድሞ ስለ እራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ህዝቡ ኃጢአት መሥዋእት የሚያቀርብ ድካም የበዛበት ህጸጽ ያለበት በሞት የሚወሰድ ነበር፡፡( ዘጸ 4፡10-
17 ፤ ዘጸ 30፡30 ፤ ዘሌ 10፡5 ፤ ዘጸ 28፡1)፡፡
► በብሉይ ኪዳን ሊቀ ክህናትና መሥዋዕት በተያያዘ መልኩ ሲገለጹ ይሰማል ፤ ለመሆኑ መሥዋዕት ማለት ምን ማለት ነው? አመጣጡና አደራረጉስ በምን ዓይነት መልኩ
ይከናወን ነበር?
እንደ ብሉይ አገላለጽ (የኦሪት መጻሕፍቶች) ሰው ለአምላኩ አንዳች ነገር ቢሰጥ ወይም ቢያቃጥል ያ ነገር መሥዋዕት ወይም ቁርባን ይባላል ፡፡ መሥዋዕቱም እንደ
ሥርዓቱ ዓይነት ሲሠዋ መሠዋቱ ልዩ ልዩ አሳብ ሊገልጥ ይችላል ፡፡ ለምሳሌ በአምላክ ፊት ተቀባይነትን ለማግኘት ወይም ለማጠንከር ይሆናል ፤ እንዲሁም የሰጪውም
እምነት ወይም ንስሓ ምስጋና ወይም ፍቅር ያሳያል ፡፡ መሥዋዕትን ያቀርቡ የነበሩ ሰዎች አንድ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ አረማውያንም
ደግሞ ለጣዖቶቻቸው ያቀርቡ ነበር ፡፡
በብሉይ ኪዳን ቃሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዘፍ 4, 4 ላይ ይገኛል ፡፡ እንዲሁም መሠረተ አሳቡ በዘፍ 3, 21 ላይ ተገልጿል ፡፡ ከሙሴ በፊት የጥንት አባቶች
ለእግዚአብሔር ይሠዉ ነበር (ዘፍ 4, 4፣ 8, 20 ፣ 12, 7) ፡፡ በኦሪት ሕግ ግን የካህናት ወገኖች ብቻ እንዲሠዉ ተፈቅዶላቸዋል (ዘኁ 3, 10) ፡፡ የኦሪትም መሥዋእቶች
ከሥጋ ከእህልና ከመጠጥ ነበሩ ፡፡ ከሥጋም ሲሆን ነውር ከሌላቸው ንጹሓን ከተባሉ እንስሶችና ወፎች መሆን ነበረበት (ዘፍ 8, 20 ፣ ዘሌ 22, 17-25) ፡፡
እግዚአብሔር ከእስራኤል ያዘዛቸው መሥዋዕቶች አምስት ዓይነት ናቸው ፤ እነዚህም የሚቃጠል መሥዋዕት ፣ የእህል ቁርባን ፣ የደኅንነት መሥዋዕት ፣ የኃጢአት
መሥዋዕትና የበደል መሥዋዕት ናቸው (ዘሌ 1-5) ፡፡
የመሥዋዕት አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በእንስሳት ሲፈጸም ፦
1) እንስሳው ንጹሕ የሆነና እንከን የሌለበት ነበር (ዘጸ 12, 5 ፣ ዘሌ 22, 24-25 1 ጴጥ 1, 18-19) ፡፡
2) አቅራቢው እጁን በእንስሳው ራስ ላይ ይጭናል (ዘሌ 1, 4) ፡፡ ይህን በማድረጉ በምሳሌነት ራሱን ከእንስሳው ጋር አንድ ያደርጋል ፤ ኃጢአቱንም ያሸክመዋል (ዘሌ 16,
21፣ ኢሳ 53, 6 ፣ 1 ጴጥ 2, 24) ፡፡
3) አቅራቢው ያርደዋል ፤ የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና (ሮሜ 6, 23 ዕብ 9, 28) ፡፡
4) ካህን የመሥዋዕቱን ደም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል (ዘሌ 1, 5 ፣ 17, 11 ፣ ዕብ 9, 12) ፡፡
5) ካህን ከእንስሳው እንደ መሥዋዕቱ ዓይነት ልዩ ልዩ ክፍልና ብልት ያቃጥላል ፡፡ ይህ በምሳሌነት አቅራቢው ራሱን ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንደሚያቀርብ ይገልጣል
(ዘፍ 8, 21 ፣ ሮሜ 12, 1 ፣ 2 ቆሮ 2, 14-16 ፣ ኤፌ 5, 2) ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 15 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
6) ካህን አንዳንድ ጊዜም አቅራቢው ከእንስሳ ያልተቃጠለውን በመሠዊያ አጠገብ ይበላል (ዘሌ 6, 26) ፡፡ ይህም በመሥዋዕቱ መሠረት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት
እንዳለው ያሳያል (1 ቆሮ 10, 14-22 የይሁዳ መልእክት ቁ.12) ፡፡
እነዚህ በብሉይ ኪዳን ይቀርቡ የነበሩ የተለያዩ መሥዋእቶች ፍጹም ድኅነትን ያላስገኙ ቢሆንም በጊዜው የሚያስገኙት ጥቅም እንዳለ ሆኖ ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌ እና ጥላ ነበሩ ቅዱስ
ጳውሎስ ይህንን አስመልክቶ‹‹ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 16 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
2.3.1.3. መና (ዘጸ፩፮፥፫፫)
ከእስራኤላውያን የግብጽ የባርነት ኑሮ አልፎ ወደ ተስፋይቱ ምድር ካረጉት ጉዞ (ከምድረ በዳው ጉዞ ጋር) በተያያዘ መልኩ “መና” ስለተባለው ምግብ ይነገራል ፡፡ ለመሆኑ
መና ማለት ምን ማለት ነው? ከሰማይ የወረደ ነው ሲባል ምን ያመለክታል?
በዕብራይስጥ ቋንቋ መና ማለት “ይህ ምንድን ነው?” ማለት ነው (ዘጸ 16, 15) ፡፡ እስራኤላውያን በተራቡ ጊዜ በምሽት ብዙ ድርጭቶች አየበረሩ መጥተው ሰፈሩን
ሸፈኑት ፤ በማለዳ ደግሞ በሰፈሩ ዙርያ ጤዛ ነበር ፤ ጤዛውም ከተነነ በኋላ ደቃቃና ስስ የሆነ ነገር በበረሓማው ምድር ላይ ታየ ፤ እርሱም በምድር ላይ ያረፈ ዐመዳይ
ይመስል ነበር ፡፡ እስራኤላውያን ባዩት ጊዜ ምን እንደሆነ ባለማወቃቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ (ዘጸ 16, 13-16) ፡፡ ከዚህ በመነሣት
ነው “መና” የሚለው ስም የተገኘው ፡፡ ስለዚህ መና ማለት “ይህ ነገር ምንድን ነው” ማለት ነው ፡፡
ስለዚህ መና ጠዋት ጠዋት ጠል ካለፍ በኋላ እንደ ደቃቅ ውርጭ ያለ በምድር ላይ ይታይ ነበር ፤ የእስራኤል ሕዝብም ለ 40 ዓመታት በምድረ በዳ ተመገቡት (ዘጸ 16, 35)
፡፡ እስራኤላውያን ጠዋት ጠዋት ያንን እየለቀሙ ይመገቡ ነበር ፡፡ ለማሳደር በሞከሩ ጊዜ ገማ ፤ በስድስተኛው ቀን ግን የተረፈው መና አልገማምና ለሰባተኛው ቀን ምግብ
ሆነ ፡፡ ለተተኪ ትውልድ ምስክር እንዲሆን አሮን ከመናው በጎሞር ውስጥ ከትቶ በቅድስተ ቅዱሳን አኖረው (ዘጸ 16, 13-36 ዕብ 9, 4) ፡፡ ከ 40 ዓመት በኋላ እስራኤል
በኢያሪኮ ምሥራቅ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ ሌላ ምግብ ስላገኙ መናው ቀረ (ኢያ 50, 10-12) ፡፡ እግዚአብሔር መናን ሲሰጥ እንዴት ወይም ምን እንደሆነ አይታወቅም ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 17 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
እግዚአብሔር መናን በመስጠቱ ሰው በዚህ ብቻ እንደማይኖር በእግዚአብሔር ቃልም እንደሚኖር (ዘዳ 8, 3-16) ፤ ሰባተኛው ቀን እንዲያከብር አስተማረ (ዘጸ 16, 19-30
ዘጸ 20, 8-10) ፡፡ ክርስቶስ የእስራኤል መና ከጠቀሰ በኋላ የሥጋው ሕይወትነት ከዚያ ይልቅ እጅግ የበለጠ መሆኑን አሳየ (ዮሐ 6, 26-71) ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 18 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ምሳሌ
እሥራኤል የአዳም ፣ መና የጌታ ምሳሌ ። ዘፀ ፩፮ ፥ ፩፫ ። እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ። ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥
ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው::
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 19 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
መላእክት ይመራመራሉ፤ ‹ለምን እኔ ፈጠርኳችሁ ብዬ ፈጣሪነትን በእጄ አላስገባም› ብሎ አሰበ፤ ከዚያም ‹እኔ ፈጣሪያችሁ ነኝ› በማለት ተናገረ፡፡ (ዘፍ። ፩፥፩፡፴፩፣ መጽሐፈ
አክሲማሮስ ዘእሑድ ከገጽ ፳፬፡፴፫)
የእስራኤል የኤርትራ ባህርን (ቀይ ባህርን) መሻገርም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ዘፀ 14፡21) ።
ሙሴ የክርስቶስ ፤ ባህሩን የከፈለባት በትር የመስቀል፤ ባህረ ኤርትራ የፍርድና የሲኦል ፤ በተከፈለው ባህር የተሻገሩት እስራኤል በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ በጥምቀት
ከእግዚአ ብሔር ተወልደው ባህረ ኃጢአትን የሚሻገሩ ምዕመናን ምሳሌ ነው ።
ዘሌ ፩፪÷፫ በዘመነ ሀዲስ ግን በጥምቀት ቢተካም ጌታ ሰው ቢሆንም ኦሪትን ሊሽር አልመጣምና በተወለደ በ፰ ቀኑ ስርዓተ ግዝረት ፈጽሟል፡፡
(ዘሌ 12፡1-10)፡፡ አዳም በተፈጠረ በ 40 ቀኑ፣ ሔዋንም በተፈጠረች በ 80 ቀኗ ወደ ርስታቸው ገነት እንደገቡ ሕጻናትም በ 40 እና በ 80 ቀናቸው ተጠምቀው
የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ወደሆነችው ወደ ቤተክርስቲያን ይገባሉ፡፡
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 20 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ዘጽ 30፡-18-20 ‹‹የመታጠቢያ ሰንና መቀመጫውን ከናስ ሥራ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል እርሱን አድርገህ ውኃን ትጨምርበታለህ። አሮንና
ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡበታል። ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት መስዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው
ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ፥ እንዳይሞቱ ይታጠቡበታል።››
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 21 ከ 14
የካልዓይ ትምህርት “መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው” ሮሜ. ፲፥፲፬”
ዘጸአት 30 ÷ 1-10
የዕጣን መሠዊያውን ሥራ፤ ከግራር እንጨት አድርገው። ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታውም ሁለት ክንድ ይሆናል፤ ቀንዶቹም
ከእርሱ ጋር በአንድነትየተሠሩ ይሁኑ። ላይኛውንና የግድግዳውንም ዙሪያ ቀንዶቹንም በጥሩ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ ታደርግለታለህ።
ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ። መሎጊያዎቹንም ከግራር
እንጨት አድርግ፥ በወርቅም ለብጣቸው። በምስክሩ ታቦት አጠገብም ካለው መጋረጃ በፊት ታኖረዋለህ ይህንም አንተን በምገናኝበት ከምስክሩ በላይ ባለው በስርየት
መክደኛ ፊት ታኖረዋለህ።
ኦሪት ዘጸአት 33:7
ሙሴም ድንኳኑን እየወሰደ ከሰፈር ውጭ ይተክለው ነበር፤ ከሰፈሩም ራቅ ያደርገው ነበር፤ የመገናኛውም ድንኳን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርንም የፈለገ ሁሉ ከሰፈር
ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይወጣ ነበር።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን
| የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰ/ት/ቤት ትምህርትና ሥልጠና ክፍል ገጽ 22 ከ 14