Professional Documents
Culture Documents
21
21
2. ሀልዎተ እግዚአብሔር
ሀልዎት፤ ሀለወ ኖረ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን፤ የእግዚአብሔርን መኖር የምንረዳበት ትምሕርት ነው። በዚህ
ትምሕርት፤ ስለ እግዚአብሔር ስሞች።
ስለ እግዚአብሔር ባህርይ።
እግዚአብሔርን ስለ ማየትና አለማየት፤ የሚሉትን እናያለን።
የእግዚአብሔር ስሞች እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች የገለጠው በስሙ ነው። ዘፍ 12፥1። ዘፀ. 3፥14። እኛ ሰዎችም
እግዚአብሔርን የምናውቀው በስሙ ነው። በስሙ እናምናለን፤ ለስሙ እንሰግዳለን፤ ስሙን ጠርተን እንድናለን። በስሙ
ለከበሩና፡ ስሙ ለተጠራባቸው፡ (ቅዱሳን መላእክት። ዘፍ 19፥1። ኢያ. 5፥13። ቅዱሳን ሰዎች፤ 1 ነገ 18፥7። ሮሜ 8፥30።
የቤተ መቅደስ ንዋያት። ዳን 5፥1። ቅዱሳት መካናት። 25፥17።) ተገቢውን ክብር እንሰጣለን።
በምድራዊ አስተዳደር በአገር መሪነት ደረጃ ያሉ ሰዎች፤ ስማቸው፣ ቢሯቸው፣ ያላቸው ነገር ሁሉ የተከበረ ነው። ጊዜያ ዊዉና
የሚያልፈው በሌሎች ሰዎች የሚተካው ሥልጣን ይህን ያህል ከተከበረ፡ በዘመን የማይለካ፣ በሌላ የማይተካ አምላክ፤
ያከበራቸው፣ የማያልፍና ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳኑን የሰጣቸው፣ በስሙ የተጠሩ ቅዱሳንማ በብዙ ሊከበሩ ይገባቸዋል። እኛ
ቅዱሳንን ስናከብር የባህርይ አማልክት ናቸው ብለን ሳይሆን እግዚአብሔር በስሙ ስላከበራቸው እነሱን ማክበር አምላካቸውን
ማክበር መሆኑን ስለምናውቅ ነው። እኛ ሰዎች እንኳን የምንወደውን ሌላው እንዲወድልን እንፈጋለን፡ የማይሳሳተውና ፍጹም
የሆነው አምላክ የወደዳቸውንና ያከበራቸውን ብናከብር ያከብረናል።
እግዚአብሔር ግን እንደ ስሙ ይሠራል ፡ነገር ግን ሁሉንም ባህርዩን የሚገልጽ አንድ ብቻ ስም የለውም። ሁሉም ስሞቹ
በየራሳቸው አንድን ሁኔታ ይገልጻሉ።
ለምሳሌ፤ እግዚአብሔር።
1. ሀ. እግዚእ – ጌታ ብሔር – ዓለም = የዓለም ጌታ። ጌትነቱን ይገልጻል።
ለ. እግዚእ – ጌታ ወልድ
አብ – አባት አብ
ሔር – ቸር መንፈስ ቅዱስ
ቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ሰዎች፤ ስማቸውን፤ «ኤል» ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር እያጣመሩ በመጠራት የአምላክ
አገልጋዮችና ስጦታዎች እንዲሁም የኃይሉ መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸውበታል። ከነዚህም መካከል፤ የሚከተሉትን
እናያለን።
ስም
ሚካኤል፤ (መኑ ከማከ) ማን እንደ አምላክ ማለት ሲሆን። ሰያሜውም የአምላክ፡ ባለሟልነቱን ይገልፃል ገብርኤል፤ ገብር
አገልጋይ = የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲሆን የሁሉም መላእክት ስማቸው ኤል ከሚለው የእግዚአብሔር ስም ጋር
የተጣመረና ትርጉሙም ተግባራቸውን የሚገልጽ ነው።
2. የእግዚአብሔር ባህርይ
የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ በሰው አእምሮ የማይመረመርና የማይወሰን ረቂቅ ነው። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር
መመራመርም ሆነ ለሌላውም ማስረዳት ይቻላል።
የመለኮትን ባህርይ ግን ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ የሚያውቅም ሆነ የሚያስረዳ ማንም የለም። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት
በገለጹልን መሠረት እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን።
እግዚአብሔር የፈጠረው ነፋስን እንኳን ከረቂቅነቱ የተነሳ በዓይናችን ማየት እንደማንችል ሁሉ። ዮሐ. 3፥8። ረቂቃን
ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩ ሊመረመርና ሊገመት የማይችል ረቂቅ ነው።
የመላእክትና የሰዎች ቅድስና ግን ፡ በሥራ የሚገኝ ፣ በሃይማኖት የተፈተነ ፣ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የፀጋ ቅድስና ነው።
የፍጡራን ቅድስና ፡ደረጃ አለው ከአንዱ የሌላው ይበልጣል። 1 ቆሮ. 15፥41። የእግዚአብሔር ቅድስና በመጠን አይወሰንም፤
እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለምና። ኢሳ 6፥3። ዕንባ 1፥13።
2.7 እግዚአብሔር ቸር ነው
የሰው ልጅ ቸርነቱ (ልግስናው) በኪሱ ያለው ሳንቲም እስኪያልቅ፤ እሱንም ቢሆን የሚሰጠው ተለምኖ ነው። እግዚአብ ሔር
ሁሉ ያለው ፣ ያለ ንፍገትና ያለ መሰሰት ለጋስ ፣ ስጦታው የማያልቅበት ፣ ኃጥዕ ጻድቅ ሳይል በቸርነቱ ለሁሉ ያለ አድልዎ
የሚያድል ማቴ 5፥41። ሳንለምነው የሚያስፈልገንን አውቆ የሚሰጠን ፣ ቸር አምላክ ነው። ማቴ 6፣32። ሰው የሚሰጠው
ከሌላው ያገኘውን ነው፤ ወደዚህ ዓለም የመጣው ራቁቱን ነው፤ ወደ ምድር ሲመለስም የሚያስከትለው ነገር የለውም። ኢዮ
1፥21። 1 ጢሞ 6፥7። እኛ ለሌሌሎች የምንሰጠው ከተረፈን ብቻ ነው አምላካችን ግን ለእኛ የሰጠን ራሱን ነው። ከዚህ
የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐ 15፥13። ሰው የሚሰጠው ለወዳጁ ፣ ለወገኑ ፣ ለሚመስለው… ነው እግዚአብሔር
ግን ጠላቶቹ ሳለን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ከራሱ ጋር አስታረቀን፤ ከዘለዓለም ሞትም አዳነን። ሮሜ 5፥10።
3.2 ሥነ ፍጥረት
“ራሱን ያለ ምስክር አልተወም”። የሐ ሥ 14፥17። በአንድ ባለሙያ (በፋብሪካ) የተሰሩ ነገሮች ሰሪያቸውን
እንደሚያስተዋውቁና እንደሚያስመሰግኑ ሁሉ ፍጠረታትም በእርሱ እንደተፈጠሩና እንደሚመሩ ስለ እግዚአብሔር መኖር
ምስክሮች በመሆን ፈጣሪያቸውን ያስተዋውቃሉ፡፡
ለምሳሌ እስራኤል በግብፅ አገር ለ 430 ዓመታት መኖራቸው በታሪክ ተመዝግቧል። ይህ ታሪካዊ ድርጊትም የተፈጸመው በእ
ግዚአበሔር ጥበብ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ዮሴፍ በመጀመሪያ ወደ ግብፅ ወርዶ ባለስልጣን በመሆን ለወገኖቹ
ከሀገራቸው መፍለስና ለጊዜውም ቢሆን የተሻለ ሕይወት ይኖሩ ዘንድ ምክንያት እንዲሆን ያደረገና ዘፍ 41፥39።
ሙሴ በአስቸጋሪ ወቅት በአስደናቂ ሁኔታ ተወልዶ በቤተ መንግስት እንዲያድግና በኋላም እስራኤልን እየመራ ከግብፅ ወደ
ከነዓን እንዲያወጣ ያደረገ እግዚአብሔር ነው። ዘፀ 3፥1። ሌሎችም በዓለም ታላላቅ የተባሉ ታሪኮችን በማስተዋል ከተረዳና
ቸው የእግዚአብሔር ኃያልነትና ሁሉን አድራጊነት እንደተገለፀባቸው ማወቅ እንችላለን።
በሌላም በኩል በዓለም ታሪከ ትልቅ ቦታ ያለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ስለ እግዚአብሔር መኖርና ስለ ድንቅ ስራዎቹ
እንዲሁም በወዳጆቹ ላይ አድሮ ያደረጋቸው ተአምራትና መለኮታዊ ኃይሉን ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔር ስም
የተጠራባቸው “ፀበሉ፤ እምነቱ፤ መስቀሉ….ተአምራት ሲያደርጉ፤ ህሙማን የእግዚአብሐርን ስም ጠርተው፤ መዳናቸው
እውነተኛና ህያው ምስክር ናቸው። በማስተዋል ለሚ ገነዘበው በዓለም ላይ የእግዚአብሔር ኃይል ያልተገለጠበት የታሪክ
ክፍል የለም።
እስራኤል የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ከመፍራታቸው የተነሳ፤ ሙሴን “እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን አንተ
ተናገረን” ይሉት ነበር። ዘፀ 20፥19። በሌላም በኩል አይሑድ ጌታን ሊይዙ በመጡበት ሰዓት “የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ”
ባላቸው ጊዜ ቁመው መስማት ስላልቻሉ መሬት ላይ ወደቁ። ዮሐ 18፥4። አምላክ በሥጋ በተገለጠበትም ሆነ በሌላ ጊዜ
ሰዎችን የሚያነጋግራቸው መስማት በሚችሉት መጠን እንጅ መለኮታዊ ድምፁን ሰምቶ በህይወት መኖር የሚችል ማንም
ፍጡር የለም።
ከላይ የገለጽናቸው ሁሉ የእግዚአብሔር ባህርይ በሰው አእምሮ የማይወሰንና በምርምር የማይደረስበት መሆኑን ለማስረዳት
ያህል እንጅ አምላክነቱን በሙሉ ያስረዳሉ ማለት አይደለም:: የእግዚአብሔርን ይቅርና የሰውን ባህርይ እንኳን ማወቅ ይከብ
ዳል ይሁን እንጅ የእኛን ታናሸነትና ውሱንነት፤ የእግዚአብሔርን ኃያልነት ለመረዳትና ለማወቅ ይረዳ ዘንድ ይህ ተጻፈ።