You are on page 1of 2

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በስሌታችሁ የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ስጦታውን ፈላጊ አይደለሁም። ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል ፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት
የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቼአለሁ . . . .. 417-19።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ስጦታ በተቀበለ ጊዜ ከልብ የቀረበውን ስጦታ በመጠኑ
(ብዛት) ሳይሆን ከቀረበበት የደስተኛነት ልብ የተነሣ ተሞልቻለሁ በማለት ሲባርካቸው እንመለከታለን፡፡ እነዚህ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች
ከሌሎች ክርስቲያኖች በተለየ ሁኔታ ለጳውሎስ ስጦታን ለመስጠት እንደ ተጉ ገልጾታል፡፡ (ቁ. 15-17) የሚበዛውን ፍሬ እንጂ ሲል የእርሱ
ፍላጎት እነርሱ የሚሰጡትን ገንዘብ ሳይሆን በክርስቶስ ፍቅር ለእርሱ በሰጡት ስጦታ እግዚአብሔር የሚያፈስላቸውን በረከት ብዛት
እንዲያገኙ እንደሚናፍቅ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅር የሚሰጠውን ስጦታ ተመልክቶ በበዛ በረከቱ የሚመልስ አምላክ አለን፡፡ ስጡ
ይሰጣችሁማል ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና ፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም . . . . ሉቃ. 6138።

ሰው ስለ ስለ መስጠት በእውነት ሊማር የሚችለው ከክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና ፤
ሀብታም ሲሆን ፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ 2ቆሮ. 819። እርሱ ከሁሉ አስቀድሞ የሰጠን ራሱን
እስከ ሞት ድረስ እኛን በመውደዱ ሕይወቱን ነውና አስቀድመን ሁለተናችንን ለእርሱ ልንሰጥ ይገባል፡፡ (ሮሜ 121-2) ለእግዚአብሔር
ቀድሞ ካልተሰጠ ማንነት የሚቀርበው ማንኛውም ስጦታ በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፡፡ (ሚል. 212-9) መጽሐፍ በዋጋ ተገዝታችኋልና
ለራሳችሁ አይደላችሁም ይላልና ራሳችንን ለእግዚአብሔር ስንሰጥ ከአንተ የተቀበልኩትን ለአንተ ሰጥቼአለሁ ማለታችን ነው፡፡
(1ቆሮ. 619-20) ክርስቲያን ከራሱ ቀጥሎ ለአምላኩ ሊሰጥ የሚገባው ጊዜውን ነው ፤ የምንሠራበት  የምንዝናናበት  . . . . ጊዜ
የሰጠን እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ከእርሱ ጋር ቃሉን ለማንበብ  በጸሎት ለመነጋገር  ከክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ለመሆን እንዲሁም
ለማገልገል ጊዜን አለመስጠት ታላቅ በደል ነው፡፡ #ጊዜን ለሰጠን አምላክ ጊዜን አንከልክለው$ በሦስተኛ ደረጃ ለእግዚአብሔር ሊሰጥ
የሚገባው እርሱ በሰጠን አካል (እጅ  እግር  ዓይን  አእምሮ  እውቀት  . . . .) ሠርተን ካገኘነው በረከት የምንሰጠው የተወደደ
ስጦታ ነው፡፡ . . . . አሁንም እንግዲህ ፥ አምላካችን ሆይ ፥ እንገዛልሃለን ፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን። ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ፥
ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና . . . . አቤቱ አምላካችን ሆይ ፥ ለቅዱስ ስምህ ቤት እንሠራ ዘንድ ይህ ያዘጋጀነው ባለጠግነት ሁሉ ከእጅህ
የመጣ ነው ፥ ሁሉም የአንተ ነው 1ዜና. 29112-16። አሁንም መታወስ ያለበት የእውነተኛና በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ስጦታ ቅደም
ተከተል ራስን መስጠት ፣ ቀጥሎም ጊዜን በመጨረሻም የእጃችንን ሥራ መሆኑ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ቤት ለአገልግሎቱ የምንሰጠው ስጦታ ዓይነቶች ፡-


1. አሥራት ፡- ከአሥር አንድ ማለት ሲሆን ይህ አንድ ግዴታና ሸክም ቆጥረን የምንሰጠው መሆን የለበትም፡፡ አሥራት አምላክነቱን 
ክብሩን የማመናችን መገለጫ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው?
ብላችኋል። በአሥራትና በበኩራት ነው። እናንተ ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ። በቤቴ ውስጥ መብል
እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ ፥ ይላል
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር . . . . ሚል. 318-11። አብርሃም አራቱን ነገሥታት ደል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ከምርኮው አንዳችም ለራሱ
ባይወስድም ለክርስቶስ ኢየሱስ ዘላለማዊ ክህነት ምሳሌ ለሆነው ለመልከ ጻዴቅ ከሁሉ አሥራትን ሰጥቷል፡፡ (ዘፍ. 14120) በጥንቆላ ቤት
ካገለገሉ ሰዎች ምስክርነት ስንሰማ ካገኛችሁት ምንም ሳትቆነጥሩ አሥራቴን አምጡ በማለት ሰይጣን አጥብቆ እንደሚያዝዝ ነው፡፡
ምክንያቱም አሥራት የአምላክነት ክብሩር ነውና ራሱን አምላክ ነኝ ለማለት ነው፡፡

2. በኩራት ፡- እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር ፥ ከፍሬህም ሁሉ በኩራት . . . . ምሳ. 319-10 ። በኩር የመጀመሪያ የሚለውን ትርጉም
የያዘ ሲሆን ሰው በመጀመሪያ ያገኘውን ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚሰጥበት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በስጦታ ስሌት ከአምላካችን ጋር
የምንከራከረው ይህን ያህል ብሰጥ ለእኔ ምን ይቀረኛል; የእግዚአብሔር መሆኑ ሳይዘነጋ ይህን ጥያቄ አንጠይቅ እግዚአብሔር ስንት ልጅ
ነበረው; እኛን ኃጢአተኞቹን ለማዳንስ ስንት ልጁን ሰጠ; ከሰጠ በኋላስ የቀረው ነገር ነበርን; መልሱን ለልባችን፡፡

3. የፈቃድ ስጦታ ፡- አምላኬ ሆይ ፥ ልብን እንድትመረምር ፥ ቅንነትንም እንድትወድድ አውቃለሁ ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ
አቅርቤአለሁ ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ 1ዜና 29117። (ዘሌ. 22118-21 ፣ ዘሌ. 7116 ፣
ዘዳ. 16110 ፣ ሕዝ. 46112) በሥራችን ላይ የተለያዩ ነገር ስናገኝ ወይም በልባችን ደስ በሚለን ጊዜ ለምንወዳቸው ፤ ለባል  ለሚስት
 ለልጅ  ለቤተሰብ  ለጓደኛ  . . . . አስበን በስጦታ ለማስደሰት የምንነሣበት ብዙ ጊዜ አለ፡፡ ነገር ግን የዚህ ሁሉ ምንጭ ለሆነው
እግዚአብሔር ከአሥራት በኩራት ሌላ ደስ ባሰኘን መጠን ባይሆን እንኳን በትንሹ በደስታ ለስጦታ እጃችንን እንዘረጋለታለንን; ማወቅ
የሚገባን የምንሰጠው እርሱን በማክበር የበለጠ እንዲባርከንና  አንተ ብቻ አምላኬ ነህ ለማለት እንጂ ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ (1ዜና. 29111
፣ 1ነገ. 2114 ፣ መዝ. 4917-12)
1
ብዙ ጊዜ ለእግዚአብሔር በሚሆነው ስጦታ ላይ እጃችን ለመዘርጋት ይቸገራል ወይም በልባችን ውስጥ ሙግት እንገባለን፡፡ አንድ ሰው
በሚኖርበት አገር ውስጥ ሲሠራ ሰራተኛ የሥራ ግብር ፣ ነጋዴም የንግድ ግብር ፣ . . . . ይከፍላል፡፡ ምክንያቱም በሰላም ሠርቶ ለማግኘት
የሕግ ጥበቃ ያገኘበት  መብቱን የሚያስከብርበት የሕግ ከለላ የሚያገኝበት  . . . . ነውና መክፈል ይገባዋል፡፡ በተለይ ክርስቲያን
ለመንግሥት መክፈል በሚገባው ግዴታ እንደ እግዚአብሔር ሰው በፍጹም ደስታና ታማኝነት መክፈል እንዳለበት ለማስገንዘብ እንወድዳለን፡፡
(ማቴ. 2217-21) ከዚህ አሳብ ስንነሣ ሠርን ላገኘነው ነገር ሁሉ የእኛ የሆነው የቱ ነው; ስለዚህ በደስታ እንስጥ፡፡ ይህንም እላለሁ። በጥቂት
የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል ፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል። እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ
እንዳሰበ ይስጥ ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም 2ቆሮ. 916-7። አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ ፤ #ለእግዚአብሔር የሚሆነውን አንድ
አሥረኛውን (አሥራት) ወይም ሌላውን ስጦታ መስጠት ስንሰስት የሚውጠው (ሰይጣንን ማለቱ ነው) መጥቶ ያለንን በሙሉና የኪራይ
ሰብሳቢነቴን በተጨማሪ ብሎ ነጥቆ ይሄዳል፡፡ $ የተሻለውና የበለጠው ለእግዚአብሔር ይሰጣል ለራስ ማድረግ ግን ሞት ነው፡፡ (ዘሌ. 712)

እግዚአብሔር በሰጠን ገንዘብ ባለቤቶችን ሳንሆን ባለ አደራዎች ነንና በፊቱ በቅርብ ጊዜ በተሰጠን ኃላፊነት ምን ያህል እንደታመንን መጠየቁ
አይቀርምና ይህንን እናስተውል፡፡ ስጦታን ለእግዚአብሔር ቤት ወይም ለበጎ ሥራ ለተቸገሩ ወገኖች ስንነሣ አስቀድመን በቀራንዮ ላይ ጌታ
ኢየሱስ ስለ እኛ በፈቃዱና በደስታ የከፈለውን መሥዋዕትነት ውድ የሆነ የቤዛነት ስጦታውን (ራሱን አሳልፎ እስኪሰጥ መወደዱን) በጸሎት
መንፈስ እናሰላስል ፤ ከዚያ በኋላ በሁሉ ነገር ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጸጋውን ያበዛልናል፡፡ (2ቆሮ. 819) ዘወትር በስጦታችን
ውስጥ ማስተዋል ያለብን እግዚአብሔር የሚመለከተው መጠኑን ሳይሆን አስቀድሞ ልባችንን ነው፡፡ በደስታ ወይስ በኀዘን ነው የምንሰጠው;
የመስጠት ኃላፊነት (አደራ) አለብኝ ብለን ነው ወይስ በግዴታ መንፈስ; የምንሰጠው መስጠት እንደሚገባኝ መጠን ነው ወይስ ይህ ይበቃል
ብዬ በራሴ አሳብ በመወሰን; . . . . (2ቆሮ. 8110-13) ጌታ በማር. 12141-44 ላይ ትንሿን የመበለቲቱን ስጦታ ያደነቀበት ምክንያት
መጠንን ሳይሆን የመስጠት ፈቃድን ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ የሚውል ስጦታ እንዲያመጡ ጌታ ሕዝብ እስራኤልን ባዘዘ ጊዜ
ስጦታቸው በደስታ ነበርና በዝቷል  ተርፏልና ከዚህ በላይ አታምጡ ተብሎ በአዋጅ እስኪከለከሉ ደርሷል፡፡ (ዘጸ. 363-7) እግዚአብሔርን
ደስ የሚያሰኘው ስጦታ እጃችን ከልባችን ጋር በአንድነት ሲዘረጋ ብቻ ነው፡፡ (ሰ.ኤር. 3141) እግዚአብሔር በባረከን መጠን በበጎ ሥራም 
መልካምን በማድረግ ልንበዛ ያስፈልገናል፡፡ (ቆላ. 1110-12 ፣ ሮሜ 217 ፣ 2ተሰ. 2116-17 ፣ 1ጢሞ. 6118-19) እግዚአብሔር
ከእኛ የሚጠብቅብን ባለን መጠን ነው፡፡ ለምሳሌ ካለው 10 ብር አንዲቷን በመስጠት ያልተዘጋጀ ሰው . . . . ያህል ቢኖረኝ ኖሮ . . . .
እሰጥ ነበር ቢል መልሱ ባለህ አልታመንክም ነው፡፡ (ሉቃ. 16111-12)

ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ከምንሰጠው ስጦታ ሌላ የተቸገሩትን ወገኖች እንድናስብ ይጠበቅብናል፡፡ እኛ ርኅሩኅህ የሆነውን የክርስቶስ
ልብ ያለን ስለ ሆንን በተለያየ ጉድለት ውስጥ ላሉትም ጌታ ከሰጠን በረከት ማካፈል ይጠበቅብናል፡፡ በተነ ፥ ለምስኪኖች ሰጠ ፥ ጽድቁ
ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ ፥ እግዚአብሔር ፥ ሁል ጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ፥ ጸጋን
ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል። ለዘሪ ዘርን ለመብላትም እንጀራን በብዙ የሚሰጥ እርሱም የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል ያበረክትላችሁማል ፥
የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል 2ቆሮ. 918-10፡፡ የተቸገሩ  እርዳታ የሚፈልጉ እጅግ ብዙ ናቸው ታዲያ እኔ ምንም ያህሉን ችግር
ልቀርፍ እችላለሁ? እንበል፡፡ በዮሐ. 619 ላይ የምናገኘው ብላቴና መልካም ምሳሌአችን ነው ፤ እርዳታ (ምግብ) በሚያስፈልጋቸው ብዙ
ሺህ ሰዎች መካከል ጥቂት ይዞ የቀረበ፡፡ ከልጅ (ብላቴና) በማይጠበቅ  ስስት በሌለበት ልብ ሰጥቷልና ጌታ ኢየሱስ በባረከው ጊዜ ሁሉም
ጠግበው 12 መሶብ ቁርስራሽ ተረፈ፡፡ ያለንበት ዘመን እጅግ ብዙ ሰዎች ከዕለት የምግብ ሰዓት አንዲቷን ጊዜ መጥገብ አይደለም ማግኘት
የሚቸገሩበት ነውና ዙሪያችንን በመመልክት በችግር የሚማቅቁትን እናስብ፡፡ ጠግበን ተርፎን ስናድር ጦማቸውን የሚያድሩ ፣ የተሻለ
ምግብ ስንበላ በሕይወት ለመኖር ምግብ ፈተና የሆነባቸው ፣ ልብስ ስንቀያይር ከራቁትነት ባልተለየ የሚሄዱ ፣ ለልጆቻችን የተሻለ ነገር
ስናስብ አሳዳጊ አጥተው በሜዳ ላይ እንደ ውሻ ቡችላ ተደራርበው ተኝተው ያሉ ፣ አባት እናታችን ስናስብ ጧሪ ቀባሪ አጥተው በቤት የቀሩ
አረጋዊያን መኖራቸውን ፣ የታመሙ ወገኖቻችንን ስንጠይቅ አስታማሚ አጥተው የ10 ብር መድኃኒት መግዛት አቅቷቸው ሕመማቸው
ወደ ሞት የሚወስዳቸው ፣ . . . . እንዳሉ በማሰብ የበኩላችንን ለማድረግ እንንቀሳቀስ፡፡ አንድ ምሳሌ እናንሣና እንጠቅልል ፤ እቴጌ ጣይቱ
የቆሎ ተማሪ ጥበበኛ ነውና በምንም አይሸነፍም የሚባለውን አሳብ ለማፍረስ በቤታቸው ብዙ ተማሪዎችን ይጋብዛሉ፡፡ ግብዣው ገንፎ ሲሆን
ለመብያ የተሰጣቸው ማንኪያ በጣም ረጃጅም ነበርና ለመብላት የማይቻል መሆኑን የተረዱት ዘዴኛ ተማሪዎች #ዚአከ ለዚአየ ፣ ዚአየ
ለዚአከ ፤ ትርጉም እኔ ለአንተ አንተ ለእኔ$ በማለት እየተጎራረሱ በልተው  ጠግበው ተነሡ ይባላል፡፡ #ኑሮ ለራስ ሲሉት ያጥራል
(ያንሳል) ለሌላው ሲሉት ግን ይረዝማል (ይበዛል) ይባላልና በፍቅር ሌሎችን በማሰብ #ለእኔ ብቻ; በሚለው ሰው መካከል የክርስቶስ
ኢየሱስን ፍቅር እንግለጽ፡፡ (ማቴ. 5114-16)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር የትምህርት ክፍል
ጥር 2003 ዓ.ም የመ.ሣ.ቁ . 121024 አዲስ አበባ
www.lidetalemariam.com
e-mail info@lidetalemariam.com 2

You might also like