You are on page 1of 2

ለዚህ ርዕስ መነሻ ያደረግነው አሳብ የሚገኘው በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 2 ላይ ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ያለመው ሕልም

ከእንቅልፍ በነቃ ጊዜ ከእርሱ ስለራቀ በዙሪያው እናውቅልሃለን ብለው የተሰበሰቡትን አስማተኞችና መተተኞች ሰብስቦ እርሱ
የጠፋበትን ሕልም ከነፍቺው እንዲገልጹለት አዘዘ፡፡ ቢያውቁ ብዙ ዋጋና ክብር የሚቀበሉ ሲሆን ባያገኙ ደግሞ ከነቤተሰቦቻቸው
እንደሚገደሉ ብዙ ጊዜም እንደማይሰጣቸው ገለጸላቸው፡፡ እነርሱም ንጉሡ የጠየቀው ነገር በጣም የቸገረና ምድራዊ የሆነ ሰው
ሊፈታው እንደማይችል በመግለጻቸው ንጉሡ ጠቢብ ነኝ ያለ ሁሉ እንዲገደል ትዕዛዝ ስላወጣ ወታደሮቹ መግደል ጀመሩ፡፡
በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር የቋጠረውን ቋጠሮ ማን ይፈታል? እርሱ የዘጋውንስ በር ማን ይከፍታል? የከፈተውንስ ማን ይዘጋል?
ጌታ እንቆቅልሽ አድርጐ የሰጠውንስ ማን ሊፈታ ይችላል? ከእርሱ ከራሱ በቀር ዛሬ ሰው ከፈቃደ እግዚአብሔር በመራቁ
የተከሰተበትን አለመታዘዝ ያስከተለበትን የፈተናና የመከራ ብዛት ይፈቱለት ዘንድ የራሳቸው እንቆቅልሽ ወዳለባቸው ሰዎች
ይሄዳል፤ ጠንቋይ ለራሱ አያውቅ እንዲሉ . . . በራሱ ችግር የተተበተበ ሰው ለሌላው ምን መፍትሔ ይኖረዋል? የሁሉ ነገር
መፍትሔ ያለው ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ?

የግድያው ትዕዛዝ ወጥቶ በሚፈጸምበት ጊዜ ነቢዩ ዳንኤል ቀርቦ ሕልሙንና ፍቺውን ማሳወቅ ይችል ዘንድ ጊዜ እንዲሰጠው ጠየቀ
ሰዎች በራሳቸው እንቆቅልሽ ውስጥ ገብተው በጭንቀት በሌላው ላይ መከራ ባበዙበት ወቅት ይህን የሚያስወግድ የእግዚአብሔር
ሰው ሲገኝ መከራ ያልፋል ጭንቀትም ይወገዳል፡፡ ዳንኤል ሁሉን በሚያውቅ አምላኩ ታምኗልና በፆምና በፀሎት በጠየቀው ጊዜ
የንጉሡን ሕልም ከነፍቺው አስታወቀው፡፡ የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት ዳንኤልም የሰማይን
አምላክ አመሰገነ፡፡ ዳንኤልም ተናገረ እንዲህም አለ ፡- ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም
ይባረክ . . . ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል፡፡ የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፡፡ ዳን. 219-22
በማለት አምላኩ እግዚአብሔርን አክብሯል፡፡ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሰዎች ..ሕዝብ.. በመከራ ውስጥ በሚሆኑ ጊዜ ማንም
ይጠፋ ዘንድ አይወድምና በመከራ ቀን ተፈላጊና ታማኝ ሰዎችን ካገኘ የምህረት እጁን ይዘረጋል፤ እውነተኛ ወዳጅነት
የሚፈተነውም በመከራ በክፉ ወቅት ነውና ዛሬም እግዚአብሔር ዘመኑን ..ሁኔታዎችን.. አስተውለን በምንፈልግበት ጊዜ
እንድንነሳሳ ይፈልጋል፡፡ /ሕዝ. 2230-31/ ጌታ እግዚአብሔር ስለሚጠፉ ሰዎች ግድ የሚለው ሰው መፈለጉ ከቅድስና ባህርይው
የተነሳ ኃጢአትን ስለማይታገስ በቁጣው በተነሳሳ ጊዜ ዘላለማዊ ምህረቱን እያሳሰበ በፍቅር የሚቆምለትን ሰው በጣም ይፈልጋል፡፡

በክፉ ቀን ተፈልገው ከተገኙ ቅዱሳን የምንማረው

1. ዳንአል ፡- ይህ ሰው እግዚአብሔርን የሚፈራ ቅን ሰው ቢሆንም እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው ከተማረኩ ዓመፀኞች ጋር


አብሮ ተማርኳል፤ ያለ በደላችን ከክፉዎች ጋር አብረን በመከራ ውስጥ መታሸት ቢያጋጥመን ከፊት የሚጠብቀንን ሰማያዊ ክብርና
በሥራው የማይሳሳተውን አምላካችንን እያሰብን ለፈቃዱ መገዛት እንጂ እኔም . . . ለምን? ማለት አይገባንም፡፡ ዳንኤል ራሱን
በጌታ ፊት ለመከራ ቀን ተፈላጊ ለመሆን ያዘጋጀው፡-

ሀ. ከረከሰ ነገር ራሱን በመጠበቅ ነው፡- እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና በፊቱ የሚቆሙ ሁሉ ከኃጢአት ተጠብቀውና ነጽተው
ሊታዘዙት ይወዳል፡፡ ዳን. 18-9 ፣ዕብ. 1214 ፣ 1ጴጥ. 115-17
ለ. ለእግዚአብሔርና ለሰው ታማኝ ነበር፡- ክርስቲያን ቅጣትን በመፍራት ሳይሆን ለአምላኩ ክብር ሲል ለሕገ እግዚአብሔርና
ለሰዎች ፤ ለግለሰብ ፣ ለመንግስት ፣ ለቤተሰብ ፣ ለጓደኛ . . ... ታማኝ መሆን ይገባዋል፡፡ ዳንኤል ላይ ሰበብ ይፈልጉ ነበር ነገር
ግን የታመነ ነበርና ስህተትና በደልም አልተገኘበትምና በእርሱ ላይ ሰበብና በደል ያገኙበት ዘንድ አለቻሉም፡፡ ዳን. 64-22

ሐ. ብርቱ የፆምና የጸሎት ሕይወት ነበረው፡- የሁሉም ነገር መፍትሔ ያለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያውቅ ስለነበር በነገር
ሁሉ ወደ አምላኩ ይቀርብ ነበር፡፡ ጠላቶቹ እንኳን እርሱን ለመወንጀል ያቀዱት ሲፀልይ ይገኛል የሚል ነበር ዳን. 611፡፡ ዛሬ
እኛስ በማንኛውም ጊዜ ብንፈልግስ ምን ስናደርግ እንገኝ ይሆን? ጽድቅ ወይም ኃጢአትን? ንጉሡ በጣም ይወደው የነበረ ቢሆንም
ከአንበሳ አፍ ..ከፍርድ.. ሊያድነው አልቻለም፡፡ ዳንኤልን ግን ሁል ጊዜ የሚያመልከው አምላኩ አዳነው፡፡ ዘወትር በትጋት
የምንጸልይ ከሆነ በእኛ ላይ የሚከፈተውን የዲያቢሎስ አፍ እንዘጋለን ..እናሸንፋለን.. የጸሎት ሕይወታችን ደካማ ከሆነ ደግሞ
በተከፈተው የሰይጣን ወጥመድ ገብተን እንጠፋለን፡፡ 1ጴጥ. 56-8

2. ነህምያ፡- ይህም ሰው ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ቢሆንም በምርኮ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ከዓመፀኞች ጋር ቢጋዙም
ጌታ አምላካቸው መሸሸጊያ ያዘጋጅላቸው ነበር፡፡ ከላይ ያየነው ዳንኤል የንጉሥ አማካሪ የነበረ ሲሆን ነህምያ ደግሞ የንጉሥ ጠጅ
አሳላፊ ነበር፡፡ ይህ ሰው፡-

ሀ. የእግዚአብሔር ክብርና የሕዝቡ ነገር ይከብደው ነበር፡- ዘወትር ስለ ቅድስቲቷ ከተማ በባርነት ስለሉ ወገኖቹ ይጠይቅ ነበር፡፡
የእግዚአብሔር ሰዎች የዘወትር የልባቸው ጭንቀት መንፈሳዊ ነገር ነውና፡፡ 2ቆሮ. 1122-28

ለ. የራሱን ምቾት አያስቀድምም ነበር ፡- በማራኪው አገር ንጉሥ ፊት ስለ አገሩና ሕዝቡ መጠየቅ የሞት ፍርድ ሊያስከትል
የሚችል ነበር፤ ቢሆንም ዝም አላለም፡፡ ነህ. 22 ፣ አስ. 416
ሐ. በጸሎት የበረታና የተጋ ሰው ነበር፡- በወቅቱ ስለ አገሩና ሕዝቡ ስለሰማው ነገር መፍትሔ ብሎ ያለው በአምላኩ ፊት አያሌ
ቀን ማዘን ፣ ማልቀስ፣ መፆምና መፀለይ ነበርና ጌታ በንጉሡ ፊት የፈረሰችውን ከተማ ይሰራ ዘንድ ፈቃድ ያገኝ ዘንድ ሞገስ
ሰጥቶታል፡፡ ነህ. 14
መ. ራሱንና ሕዝቡን ከኃጢአት በማራቅ በቅድስና ይመላለስ ነበር፡፡ ነህ. 133- 23

3. ሙሴ፡- ሙሴ የፈርፆን አልጋ ወራሽ የነበረ ቢሆንም የጓጓለት ነገር ቀጣይ ንጉሥ መሆንን ሳይሆን የወገኖቹ ሥቃይና መከራ
የሚወገድበትን መንገድ መፈለግ ነበር፡፡ ለሕዝብ፣ ለወገን ሲባል ከፍተኛ የሚባል ነገርም ሊተው ይችላል፡፡ ዘጸ. 211 ራሱን
ሲያዘጋጅም፡-

ሀ. ምርጫውን በማስተካከል ነበር፡- በፊቱ ንጉሥ ሆኖ ለጥቂት ጊዜ ..ተከብሮ.. ማለፍ አልያም በምድር መከራ ተቀብሎና ተንቆ
ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ለታላቅ ሰማያዊ ክብር መቆጠር የሚሉ አማራጮች ሲቀርቡ ለሰው ሞኝነት የሚመስለውን ግን ክቡር
የሆነውን ነገር መረጠ ዕብ 1124-28፡፡ ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመከራ ቀን እንዳይመርጠን እንዳይቀባን
ምርጫችንን ማስተካከል አቅቶን ተቸግረናል፤ ማገልገሉም በግብፅ መሆኑም ሁሉም እንዳይቀርብን የሞኝነት ነገር እናስባለን፡፡
ለ. ራሱን በቅድስና የሚጠብቅና ሕዝቡንም ወደ ቅድስና የሚጠራ ነበር፡- ቅድስና ወሳኝ የመጀመሪያ መለኪያ መሆኑን የተረዳ
ሰው ነበር፡፡ ዘጸ. 1914-15 ፣ ቁ. 23
ሐ. ከዚያም ሁሉ ጋር ጠንካራ የፆምና የፀሎት ሕይወት የነበረው፡- ዘጸ. 3428 ፣ የእግዚአብሔር ነገር ግድ የሚለውና ጌታ
በእርሱ ላይ ያለውን ዓላማ የተረዳ የሐዋ 725 ፣ የፍቅር ሰውና ትሑት የነበረ ሰው ነበር፡፡ ዘኁ. 133 ፣ ቁ. 11
ስናጠቃልለው በመከራ ቀን የተገኙና አምላካቸውን ደስ ባሰኙ ሰዎች ውስጥ ከሚታዩ ዋና ዋና ነገሮች፡-

1. ቅድስና፡- ቅድስና የእግዚአብሔር ባህርይ ነው፡፡ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና፡፡ ዕብ
1214 ለዚህ ምሳሌ ይሆን ዘንድ ለመከራ ቀን ተጠርቶ በቅድስና የጸናውን ዮሴፍን ዘፍ. 397-23፣ዘፍ. 457፣ ዘፍ. 5020-21
እንዲሁም ብዙዎችን ከመከራ እንዲያድን ተጠርቶ ቅድስናውን ባለመጠበቅ በዝሙት ጠንቅ በጠላቶቹ እጅ ወድቆ ስለ ተዋረደው
ሶምሶን ታሪክ ማየት ይቻላል፡፡ መሳ. 133-5 ፣ መሳ. 141-3 ቁ.8 ፣ መሳ. 161-21

2. ብርቱ የፆምና የፀሎት ሕይወት ፡- ዘወትር የእግዚአብሔርን ፊት በትጋት መፈለግ፣ በፆም ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ
ማስገዛት ይገባል፡፡ ኤር. 333 ፣ ኢዮ. 4210
3. እግዚአብሔር ለሰጣቸው አደራ መታመን፡- ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎች ብድራታቸውን ያወቁና የተረዱ ስለሆኑ በጊዚያዊ
አላፊና ጠፊ ነገር ሳይሳቡ ጸንተው በመታመን ይቆሙ ነበር፡፡ 2ጢሞ. 4 6-9
በመከራ ቀን ብትላላ ጉልበትህ ጥቂት ነው ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን እነሆ ይህን አላውቀውም
ብትል ልባችን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ነፍስህንም የሚመለከት እርሱ አያውቅምን? ለሰውስ እንደ ሥራው
አይመልስለትምን? ምሳ. 2410-12

You might also like