Professional Documents
Culture Documents
06.
06.
6
www.tlcfan.org 0
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
የእግዚአብሔር የምሕረት ሕግ
www.tlcfan.org 1
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ይህን ጥቅስ ጳውሎስ የጠቀሰው ከኢሳያስ 45፥23, ላይ ነው። ሙሉ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦
“እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ
ትድኑማላችሁ። ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም፦ ጕልበት ሁሉ ለእኔ
ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ። ስለ እኔም፦ በእግዚአብሔር ዘንድ
ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።
የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይባላል።”
እግዚአብሔር በራሱ ስም ማለ። ዘሁ. 14፥21, “ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና (AS I LIVE)
በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።" ብዙዎች ዛሬ ዙሪያቸው የሚሆነውን እያዮ
እግዚአብሔር በራሱ ምሎ የገባውን ቃል ይፈጽመዋል ብሎ ለማመን ይከብዳቸዋል። የሰው ልጆችን ሁሉ
እንደሚያንበረክክና ወደ ንስሃና ምሕረቱ እንደሚያመጣቸው ለማመን ይከብዳቸዋል። ጳውሎስ
እግዚአብሔር በራሱ እንደማለን የእስራኤል ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር እንደሚጸድቁ ሁሉን አልጻፈልንም።
ነገር ግን በሮሜ 11፥31 ላይ “እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ
እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም።” እኛ በተማርንበት አይነት ምሕረት ደግሞ እስራኤል ሁሉ ምሕረትን
እንደሚቀበሉ ይነግረናል። እንግዲህ የእስራኤል ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር የሚጸድቁ ከሆነ አሕዛብም ሁሉ
በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ። ጉልበት ሁሉ ይንበረከካል የሚለው ትክክለኛ ሃሳቡን ከኢሳያስ ተነስተን
ስንመለከተው እውነቱን በግልጽ እንረዳለን።
www.tlcfan.org 2
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
አንዳንድ ሰዎች በዕብራውያን. 9፥27 ”ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ
እንደ ተመደበባቸው፥” የሚለውን ቃል በተሳሳተ መልኩ በመረዳታቸው የተነሳ ሞት የመለወጥ ወይም
ምሕረትን የመቀበል ማብቂያ እድርገው ያዮታል። ይህም የእግዚአብሔር ቃልና ሕግጋት በትክክል
ካለመረዳት ወይም ካለማወቅ የሚመጣ ነው። እውነት ነው የነጩ ዙፋን ፍርድ የሚመጣው ከሞት
በኋላ ነው። ነገር ግን የትም ቦታ ላይ ቃሉ ሞት ለሰው የምሕረት መቀበያ ዘመን ወም ጊዜ ማብቂያው
እንደሆነ አይነግረንም። ይህ አይነት አስተሳሰብ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከወግና ስርዓት ከሃይማኖት
የመጣ ነው።
ከላይ እንዳየነው ንስሃ የምሕረት ማግኛ ብቸኛ ቁልፍ ነው። በንጉስ ዳዊት ሕይወት ውስጥ
በቃሉ እንደምናየው ምሕረት ፍርድን አይሰርዝም። በፍርድ ቅጣቱን ለሰው በመግለጥ ወደ ቀደመው
ስፍራው ሰውን በምሕረት ይመልሰዋል። በራእይ. 20፥14 " ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ።
ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።”
www.tlcfan.org 3
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
www.tlcfan.org 4
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
“የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤ ያላወቀ ግን
መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ
ይፈለግበታል፥ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል። በምድር ላይ እሳት ልጥል
መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ? “(ሉቃ.12፥47,48)
በመጨረሻው ፍርድ ዘመን ቀድመው የማያምኑ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ጽድቅን ይማራሉ።
“ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥
መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።”(ኢሳ. 26፥9) ይህም ወደ እግዚአብሔር ልጅነት ክብር
በፍጥረት ኢዮቤልዮ እስከሚገቡ ድረስ የሚቀጥል ነው። በዚያም ቀን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆናል።
(1.ቆሮ.15፥28).
ሰው በሰው ልጆች ሕግና ስርዓት መሰረት ሲቀጣ ወይም ብዙ ይቀጣል ወይም ጥቂት ይቀጣል
እንጂ ትክክለኛ ቅጣት ማስተላለፍ ሰው ፈጽሞ አይችልም። እግዚአብሔር ግን ማንንም አሳንሶም ሆነ
አስበልጦ አይፈርድም። ሁሉ እንደሚገባው ቅጣቱን ይቀጣል ወይም ይፈረድበታል። የእግዚአብሔር
ፍርድ የተሰራውን ሃጢያት ልክ ያህል ብቻ የሚቀጣ ነው። እግዚአብሔር ቅጣቱን አያንስም ወይም
አይጨምርም። ሰው 1000 ብር ቢሰርቅ በሰረቀው ፋንታ ሁለት እጥፍ እንዲከፍል እግዚአብሔር በሕጉ
ያዛል። ይህ ሰው ከፍርድ ቅጣት ውስጥ ላለመውደቅ አስር ሳንቲም ሳያጎድል ሊከፍል ይገባዋል። ሃጢያቱ
በልኩ ቅጣቱን ያገኛል። ከዚህ በላይ ለዘላለም ሲከፍል እንዲኖር እግዚአብሔር አያዝም። ይህ ሰው
እዳውን ሲጨርስ ነጻ ይመጣል። ለዚህ ነው ኢየሱስ ወደ ውጭ ጣሉት የመጨረሻውን ሳንቲም እስኪከፍል
ድረስ የሚለው። ይህ ሰው ከፍሎ ሲጨርስስ? እንደ እግዚአብሔር ሕግ ነጻ ይወጣል ወይም በጸጋው ስር
ይሆናል።
www.tlcfan.org 5
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ከሃጢያተኞች ዋንኛ የሆነው ሳኦልን በደማስቆ አግኝቶ ያበረከከው አይነት ብርሃን ነው።
ጳውሎስ ይህን የመጣውን ጌታ ወዶ ሳይሆን በግዱ ተቀበለ። ጌታ ለዚህ ጥላ እንዲሆን በክብሩ ተገልጦ
አንበረከከው። (ሐዋ.9) ይህም የኢዮቤልዮ ሕግ አሰራር የገለጥበት ዘንድ ነው። ይህ ሕግ ስለ ጌታ ምንም
ሳያዉቁ የሞቱትንና እያወቁም በራሳቸው ምርጫ በእርሷ ላይ እንደ ሳኦል አምጸው በሃጢያት ባርነት
ሊኖሩ የወደዱትን ሁሉ መጨረሻቸውን የሚያሳይ ሕግ ነው። ይህ አይነት ሰው ከእግዚአብሔር ነጻነትን
በመቀበል ወደ እርስቱ መመለሰን የግድ ይሰጠዋል። በኢዮቤልዮ ሕግ መዳን ወይም ወደ እርስታችን
መመለስ ተፈቅዶልናል መጥፋትና መሰቃየት በባርነትም ለዘላለም ለመኖር ብትፈልግም የለም። ሰውን
ለማሰቃየትና መሰቃየሁን የምትሰብኩ ካላችሁ እኔና እኔ የማመልከው እግዚአብሔር እንዲ አይነት ሰውን
ስለ ሃጢያቱ ማሰቃየት የለንም። ሰው ስለ ሃጢያቱ ቅጣትን ይቀበላል። ቅጣቱም የሃጢያቱን ልክ ያህል
ይሆናል። ቅጣቱ ሲፈጸም ከእስራቱ ወይም ከተጣለበት ቅጣት ይፈታል። ይህ የእግዚአብሔር የምሕረት
ሕግና አሰራር ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ፈለግን በሃጢያት እንጨማለቅ ወይም እንኑር ማለት
አይደለም። ምክንያቱም ሁሉ ሃጢያት ቅጣትና ፍርድ አለው። ይህ ባይሁን ኢየሱስ በመስቀል ላይ
መሞት አያስፈልገውም ነበርና ይህን አርነታችንን ለስጋችን ምክንያት አንስጥበት።
www.tlcfan.org 6
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ኢየሱስ በሉቃስ 12 እንደ ተናግረው ይህ የነጩ ዙፋን የፍርድ እሳት ለማያምኑ ብቻ እንዳል
ሆነ የእርሱ የሆኑ ባሪያዎቹም የሚፈረዱት በዚሁ እሳት እንደ ሆነ ያስረዳናል። ኢየሱስ ይህ እሳት በእርሱ
ዘመን ቢነድ ኖሮ ፍርድን ወዲያው ከትንሳኤው በኃላ ያደርግ ነበር። ኢየሱስ እሳትን ሊጥል መጥቷል ይህ
እሳት የእግዚአብሔር ሕግ ነው። ይህ እሳት ግን ያን ጊዜ በሁሉ ላይ አልነደደም ነበር። ምክንያቱም ፍርድ
ለሁሉ የሚሰጥበት ዘመኑ አልነበረምና ነው። ኢየሱስ ይህ እሳት ቢነድ ኖሮ ኢየሱስ ሌላ ምንም ማድረግ
አያስፈልገውም ነበር። የተናገረውም ይህንን ነው። ነገር ግን እሳቱ ለፍርድ ከእግዚአብሔር ዙፋን
የሚወጣበትን ቀንን ይቀጥራል። ደግሞ ይህ እሳት በፍርድ የሚወጣበት ዘመን ገና እንደ ሆነ መንፈስ
ቅዱስ ያስረዳል። ይህም ፍርድ ለእኛ እንዲሆን ኢየሱስ ቀድሞን በፍርድ ማለፍ በእሳቱ ውስጥ እራሱ
መጠመቅ ነበረበት። ስለዚህም ኢየሱስ እንደ ሕጉ በመስቀል ላይ ፍርድን በመቀበል እንደ ሕጉ በእሳት
መስዋዕት ሆነ። የእሳትን ጥምቀት ሰለ ሁሉ ተቀበለ በዚያም የእግዚአብሔርን ፍርድ አፈጻጸሙን አሳየ።
www.tlcfan.org 7
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ስለዚህ ሕግ ስንልን ኢየሱስ የሕጉ መካከለኛና ሰጪና ፈጻሚ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
የሚያምኑ ድል ያልነሱ ክርስቲያኖችና የማያምኑ ሁለቱም የሚፈረዱት በሕጉ ስለ ሆነ የክርስቲያኖችም
ፍርድ ሆነ የማይምኑ ፍርድ በእሳት ነው። ለማያምኑ ግን የእሳት ባሕር የሆነበት ምክንያት ብዙ ቁጣን
የሚቀበሉ ሰለሆነ ሳይሆን እነርሱም የሚቀበሉት ቅጣትና ፍርድ እንደየሥራቸውን መጠን ብቻ ነው።
የሚቀበሉት ነገር ግን እሳቱ ወይም በእነርሱ ላይ የወጣው የሕግ ፍርድ ባሕር መሆኑ የማያምኑት በፍርድ
ፊት እንደሚበዙ ብዛታቸውን በራእይ ለዮሐንስ እና ለእኛ የሚያመለክት ነው። ምክንያቱም በአመጸኞች
የሚደረገው ፍርድ በክርስቲያኖቹ ከሚደረገው ፍርድ ይልቅ ጊዜ የሚወስድ መሆኑን ብዙ መሆኑን
ለማመልከትም ጭምር ነው።
www.tlcfan.org 8
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ልጆችን የወለዱ ሰዎች ይህን ቅጣት መመልከት አያቅታቸውም። ቅጣት ለልጅ መልካሙንና
ክፉውን ለይቶ ልጅ ያድግ ይበስል ዘንድ ወሳኝና አስፈላጊ ነው። ዕብ.12፥5-11 ሕግ ልክ እንደ ሞግዚት
(schoolmaster) ወደ ክርስቶስ መልክና ባሕሪ የሚቀርጸንና የሚጠርበን ጥሩ ምዶሻና መሮ ነው።
በእያንዳንዱ ቅጣት መጨረሻ ይቅርታ ከአባት ዘንድ አለው። ከቅጣት በኃላ ያለ ምሕረት ልጅ አባቱን
እዲያከብር ያደርገዋል። ይህ እውነተኛ የሆነ የእግዚአብሔር ፍርሃትን በልጁ ላይ ያመጣል። ያልተገባ
ቅጣት ወይም መጠን ያለፈ ቅጣት ተቀጪውን መራራ ከማድረጉ በላይ ተቀጪው ትክክለኛ ያልሆነ
ፍርሃት ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል። ይህ አይነት ቅጣት የሚያደርጉ አባቶች ልጆችን ከማጣታቸው
ባሻገር መከበርን ያጣሉ።
“5-6 እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ
አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን
ምክር ረስታችኋል። 7 ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ
የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? 8 ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች
እንጂ ልጆች አይደላችሁም። 9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤
እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? 10 እነርሱ
መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል
ለጥቅማችን ይቀጣናል። 11 ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ
ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።”
www.tlcfan.org 9
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
ከዚህም የተነሳ ስንጸልይ እንኳን ወደ እርሱ በቀጥታ ከመሄድ ይልቅ በጻድቃን በኩል
አስቀድሞ መቅረብ ፍርድ ያቀላል በእነርሱ ስም መጸለይና ምጽዋት መቅረብ ይገባናል ይህም ምሕረትን
ፍትሃትን ያመጣልናል ይላሉ። ይህም እነሱን ስለ እኛ እንዲለምኑልን እንደሆነ ሕዝብን ያስተምራሉ።
ሰዎች ከክርስቶስ በፍርሃት መራቃቸውን ከተመለከትኩበት ቀን ጀምሮ አርነት በሚያወጣው
በእግዚአብሔር እውነት ቃሉ ሕዝቡ ነጻ ይወጣ ዘንድ ጸሎቴም ፍልጎቴም ነው። እባካችሁ የምትማኑት
እውነት እንደሆነ በእግዚአብሔር ቃል ፈትኑ መርምሩ። የሰውን ስብከት ወይም ትምህርት በአንድ
ሃይማኖት ዶክትሪን ወይም እምነት መፈተን ሞኝነትና ስሕተት ነው። ትክክለኛ የሆነ መፈተን
በእግዚአብሔር ቃል ብቻ የሆነ ምንም አይነት ሃይማኖተዊ ወገንተኝነት ካለው ማንነት ነጻ ወጥቶ
መፈተሽ ነው።
እንደ ኢያሱ ዛሬም እኔ በዚህ ምድር በሕይወት እስካለሁ ድረስ ይህ ሕዝብ የፈራውን
ታላቁን የእግዚአብሔር እረፍት ያለበትን እውነት ለመስለል እንደ እግዚአብሔር እይታ ነገሮችን ለማየት
ከዮርዳኖስ ባሕር ማዶ ርቆ ያለውን ለሕዝቡ የተገባውን የምድሪቱን ፍሬ ለሕዝቡ ይዤ ለመምጣት
ማንኛውንም ዮርዳኖስ ለማቋረጥ ቆርጫለሁ። ካሌብና ኢያሱ ነኝ ያለ አብሮኝ ይህን እውነት ይዞ
ይሰለፍ። ይህ እውነት በኢያሱና ካሌብ ላይ ድንጋይ እንዳስነሳ ድንጋይ እደሚነሳብን አውቀን ዋጋችንን
ተምነን ከእግዚአብሔርና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ብቻ እንወግን። የፈራና የደነገጠ ደግሞ ይመለስ።
እውነት ግን አንድ ነው። እውነት ደግሞ አይበሰብስም። የእውነት እውቀት ደግሞ አርነት ያወጣል።
እስቲ ልጆች ያላችሁ አባትና እናቶች ሁሉ ፍረዱኝ ልጆቻችሁ አባታቸውና እናታቸው እንዲ
ክፉ የሆነ አባትና እናት ናቸው ተብለው ቢማሩ ምን ይሰማችኃል? እውነትስ እንደ አባትስ ልጆቻችሁን
በማይጠፋ እሳት እያቃጠላችሁ ማየት ይሆንላችኃልን? እናንተ በዳቦ ፋንታ እባብ ካልሰጣችሁ የሰማይ
አባታችሁስ? ይህን ሊያደርግ አይችልምን? እኔም ዛሬ ሁላቹን ጳውሎስ እንዳለ እንደ ባለ አዕምሮ አስቡ
ብዮ ከሕሊናችሁና የእግዚአብሔር ቃል በዚች መጣጥፍ ትቼላችሁ አልፋለሁ።
www.tlcfan.org 10
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
www.tlcfan.org 11
የእግዚአብሔር መንግስት ሕጎች #6
www.tlcfan.org 12