You are on page 1of 2

የፍዳ ዓመት የሚጀምርበት ቀን ጌታ ተናገረኝ

ይህ ቀን የቁጣ ቀን ነው ፍዳ ማለት ፍርድ ማለት ነው የፍዳ ዓመት ማለት የፍርድ ዓመት ማለት ነው፡፡ በፍዳ ዓመት የሚሆነው ዋናው ነገር
ሐሰተኛ ክርስቶስ ይነሳል፣ይዋጋል፣ይገዛል፡፡ የፍዳ ዓመት የሚጀምርበት ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ ከተፃፈው ቀን ጋር የሚገናኝ ቀን ነው፡፡
ከትንቢተ ሕዝቀል መጽሐፍ ጋር ይገናኛል ፤ይኸውም ነቢይ ሕዝቀል በባብሎን ምርኮ ላይ እያለ ብዙ የፍርድ ራዕይዎችን አይቷል፡፡
እግዚአብሔር እሱን ያሳየውን ራዕይ ለሕዝቡ ተናግሯል ፤ ከተናገረውም ራዕይዎች ብዙዎቹ ለእስራኤል ሕ ዝብ ከባብሎን ከምርኮ መመለስ
ጋር ተያይዘው ተፈፅሟል፤በአህዛቦችም ላይ የተናገረው በዝያን ዘመን ተፈፅሟል፡፡ ቢሆንም አንዳንዶች ግን ከፍዳ ዓመት ጋር የሚመሳሰል ነው፤
በፊዳ ዘመን ይፈፀማል ትምንቢተ ሕዝ 14 12 -20 ያለው ሶስቱን ጻድቅ ሰዎችን ኖኅ፣ ዳንኤልን እና እዮብን ይጠቅሳል እነዝህ ሶስቱ ጻድቅ
ሰዎች እግዚአብሔር በከተማ እና በሀገር ፍርድ ባስተላለፈበት ቦታ ቢገኙ እንኳን እራሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ለሎችን ሕዝቦች በተሰቦች
ልጆቻቸውን ጭምር ማዳን እንደማይችሉ ይናገራል ይህም ከፊዳ ዓመት ጋር ይመሳሰላል የፍዳ ዓመት የትንቢት ኤርምያስ መጽሐፍም ጋር
ይገነኛል ነቢይ ኤርምያስ በእስራኤልና በአህዛቦች ለይ ጌታ እግዚአብሔር ለእሱ የተናገረውን የፍርድ

ትንቢት ተናግሯል የተናገረውም ለእስራኤል ከሰባ ዓመት ከምርኮ መመለስ ጋር ተያይዘው ተፈፅሟል በአህዛቦችም ላይ የተናገረው ተፈጽሟል
አንዳንዶቹ ግን ከፊዳ ዘመን ጋር ይመሳሰላል ትንቢተ ኤርምያስ 15 -1 ያለው ክፍል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትንና ከዝያ በፊት
በዘመናቸው እግዚአብሔር ፀሎታቸውን የሰማቸውን ሁለት ሰዎችን ሙሴን እና ሳሙኤልን ይጠቅሳል እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት
ቢቆሙ ና ቢፀልዩ እንኳ ለሐጢአተኛ ሕዝቦች ምህረት እንደማይደረግላቸው ይናገራል የፊዳ አመት ከዝህም ጋር ይመሳሰላል ሐሰተኛ ክርስቶስ
ከሐስተኛ ሐይማኖት ይነሳል ያሐሰተኛ ሐይማኖት ሐሰተኛ ዶክትሪን ይከተላል ሐሰተኛ ክርስቶስ እንዲነሳ የሚቀሰቅሰውና ኃይልን የሚሰጠው
ሰይጣን ወይም ዘንዶ የቀድሞ እባብ ነው፣ ከሰይጣን በተቀበለው ኃይል ብዙ ምልክቶችን ያደርጋል ሐሰተኛ ክርስቶስ አውሬ ይባላል አውሬ
የተባለበት ምክንያት ከሰይጣን ኃይልን ተቀብሎ በሰይጣን ኃይል ሰለሚሠራ ነው ያሰው ሐሰተኛ ክርስቶስ የተባለበት ምክንያት እኔ ክርስቶስ
ነኝ ብሎ ሰለሚመጣ እና እራሱን ሰለሚ ጠራ ነው ሐሰተኛ ክርስቶስ ወይም አውሬው በዘር እስራኤላዊ አይደለም አውሬው ብዙ ነገር
ይዋሻል እድሜንም ጭምር ይዋሻል እድሜው ከሰላሳ አምስት አመት በታች ይሆናል ነገር ግን በእድሜ የበሰለ ሰው በመምሰል በእድሜው ላይ
የተወሰኑ አመታትን ጨምሮ ይናገራል መጀመርያ ከእስራኤል ጋር ይስማማል ሶስት አ መት ከተኩል ይሠራል በሶስት አመት ተኩል ጦርነት
ይጀምራል የፍዳ ዓመት በዝያን ቀን ይጀምራል፡፡ ቀደም ብሎ የአውሬን ሃሳብ የሚከተሉትና የሚያደርጉት ሰዎች በምድር ስላሉት እነርሱን
ተጠቅሞ ራሱን ያደራጃል የራሱን ትምህርት ያስተምራል ትምህርቱን ወደ ሕዝብ ትምህርት ቤት ያስገባል ትምህርቱም እራሱን እንዲቀበሉት
እና ሐጢአትን እንዲሠሩ ያደርጋል፡፡ አሁን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት በምድር አለ ዋና አውረው ገና ይመጣል፡፡ ሰይጣን ሐሰተኛ ክርስቶስ
ወይም አውሬው እና ሐሰተኛ ነቢይ ሶስቱ በአንድ መንፈስ ይዋጋሉ ሐሰተኛ ነቢይ በዘር እስራኤላዊ አይደለም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ
እስራኤላዊ ነኝ ብሎ ያታልላል የአውረው ምልክት ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ነው ምልክቱን በቀኝ እጅ ወይም በግንባር

በተክኖሎጅ አማካይኝነት ይሰጣል በተ ክርስትያን በዚያን ዘመን ትኖራለች ከምድር አትጠፋም ነገር ግን ትሰደዳለች ታላቅ ስደት አላት
ማሸነፍ የምትችለው በታላቅ ፀሎት እና ጩኸት ጌታ ይጠብቃታል በድብቅ ታመልካለች ቃሉን ሰለጠበቀች በመከራ ዘመን በፈተና ጊዘ ጌታ
ይጠብቃታል ይህም የአውሬውን ምልክት በቀኝ እጇ ወይም በግንባሯ እንዳትቀበል ለአውረው እና ለምስሉ እንደዳትሰግድ በዚህ ምክንያት
ተሰድዳ እንዳትጠፋ ታላቅ ጩኸትና ፀሎት ወደ ጌታ ማድረስ አለባት ጌታም ይጠብቃታል በተክርስቲያን ማለት ጌታ ያለባት፣ ጌታ
የመሠረታት፣ ሙሉ በሙሉ ጌታ ኢየሱስ የሚገኝባት፣ የጌታ ደም ያለባት፣ የጌታ መንፈስ ያለባት ይህም ጌታ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን የላከባት

በምድርያለች፣በምድርያለች ሰማያዊ ሕዝብናት ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ በፍዳ ዘመን ላለች በቴ ክርስቲያን ወደ ጌታ መጮኽ አለባችሁ በመከራ
ዘመን የሚኖሩት ክርስትያኖች ዘሮቻችን ናቸው በተክርስትያን በመከራ ታልፋለች የአውረውን ምልክት የተቀበሉት ለአውሬው እና ለምስሉ
የሰገዱት ከአውረው ጋር የተባበሩት ሁሉ ከአውሬው ጋር ወደ ገሃነም እሳት ይጣላሉ የአውረውን ምልክት ያልተቀበሉት ለአውሬ ው እና
ለምስሉ ያልሰገዱት ጌታ ኢየሱስን ያመኑት ወደ ዘለአለም ሕይወት ይገባሉ፡፡ የአውረውን ምልክት ያልተቀበሉት ለአውሬና ለምስሉ ያልሰገዱት
ነገር ግን ጌታ ኢየሱስን ያላመኑት ከማንኛውም ከፍርድ ሊድኑት አይችሉም፡፡ የአውሬው ምልክት መድሃኒት ተብሎ በቀኝ እጅ ይሰጣል
ደግሞ በቀኝ እጅ በሚታሰር ጌጥ በሚመስሉ ጨርቆች ጌጥ በሚመስሉ ሌሎች ነገሮች ይሰጣል አሁንም እየተሰጠ ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ ይህን
ማወቅ አለባቸው ቁጥሩ በቀጥታ ሊሰጥ ወይም የቁጥሩ ድምር ተባዝቶ የቁጥሩ ሚስጥር ይሰጣል አሁንም እየተሰጠ ነው አውረውን
የተቀበሉት ከአውረው ጋር ይተባበራሉ አውሬ ውን የተቃወሙት እስራኤላዊያን ከአውሬው ጋር ይዋጋሉ ጌታ ኢየሱስ እስራኤላዊያንን ያግዛል
አውሬውን ያልተቀበሉት ክርስቲያኖች ከእስራኤል ጋር ይተባበራሉ አውሬው በአይሁዶች መቅደስ ይቀመጣል ተከታዮቹ ይሰግዳሉ
የአውሬው ተከታዮች anti-Christ ናቸው ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ለእስራኤል መፀለይ አለባችሁ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ቤተክርስቲያን የፍዳ
ዘመን ትምህርት ማስተማር አለባት ትምህርቱም ወደ ፊት እየሰፋ ይሄዳል አውረው ዋናው ሰይጣን ነው፡ ለሎቹ ሐሰተኛ ክርስቶስ እና
ሐሰተኛ ነቢይ ናቸው ባቢሎን በፊዳ ዘመን ያለች የነገስታት ንጉስ ከተማ ናት ሁሉን የሚያሳስት ነገር ከእሷ ወጣ በዝሙት ርኩሰት ሁሉን
ታረክሳለች ሰባ ዓመት ትገዛለች በአውረው ተሸንፋ ትወድቃለች ባቢሎን ወደቀች፡፡ የአውሬው ምስል ይበራል ውስጡ ግን ጨለማ ነው
ምስሉ በየቦታው ይቆማል ምልክቱን የተቀበለ ለአውረውና ለምስሉ የሰገደ በድን ወደ ሚቃጠል ወደ እሳት ባህር ይጣላል ማህተም ይፈታል
የፍዳ አመት ይጀምራል፡፡ መቅስፍቶችም ይጀምራሉ ከዛ በፊት በዓለም ሁሉ ወንገል ይሰበካል ከአሁኑ ዘመን ጀምሮ በኃይል ይሰበካል
በዚያን ዘመን በሁለቱ ምስክሮች ይሰበካ በዚያን ዘመን አንድ መቶ አርባ አራት ሽህ ሰዎች ከእስራኤል ለጌታ ይለያሉ እነርሱ በበጉ ደም
ታጥበው የነፁና ከሐጢአት የራቁ ጠንቃቃ ሰዎች ናቸው አነርሱ ከአውረው ጋር ይዋጋሉ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሆናል እነርሱም ከጌታ ጋር
ይሆናሉ በዝያን ዘመን በእስራኤልም በሌሎች ሀገሮችም ብዙ የተቀደሱ ሰዎች ይኖራሉ ደግሞ ብዙ ርኩሶችም ይኖራሉ የሁሉም ዋጋ በጌታ
ዘንድ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆንበት ምክንያት ሰይጣን ከጥልቁ እስር ሰለሚፈታ ነው ከዛ በፊት ግን ሰይጣን በመላእክቱና በጭፍሮቹ በኩል
ይሠራ ነበር ይህ ቀን የተገለጠበት ምክንያት እግዚአብሔር ሰውን ሁሉ ሰለሚወድ ሁሉም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ እንዲድንና ፡
የአውረውን ምልክት በቀኝ እጅ ወይም በግንባር እንዳይቀበል ለአውረውና ለምስሉ እንዳይ ሰግድ ነው መንፈስ ቅዱስ ይህን ቀን ተናግሯል
በዚያን ቀን ይፈፅማል ጌታ ይህን ቀን ለብዙዎች ይገልጣል፡፡ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር July 24፣ 20400 የፍዳ ዓመት ይጀምራል ጌታ
ኢየሱስ ወደ ምድር የሚመጣበት ቀን ማንም አያውቅም አለኝ ጌታ ይህ ጌታ ከገለጠው ጋር የሚገነኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ ራእይ 3-
10 ምዕራፍ ፡ 6 እስከ ምዕ 20 ምዕ 22 -11 ማቴ 16 -,፡15-19 ኤፌ 5፡25-27 ማቴ 24፡ 3-24 ማር 13 ፡32-37 ማቴ 24 ፡36-
44 ,ትንቢ ዳን 9-23-27 ,ዳን ምዕ 12 ፡2 ኛ ቆሮ 11 ፡14-15 2 ኛ ተሰ 2፡1-12 ትቶ 2 ፡11-15 ማቴ 7 ፡15

ጌታ ኢየሱስ የዘለአለም አምላክ ነው፡

You might also like