Professional Documents
Culture Documents
Kale Awadi Am
Kale Awadi Am
አንቀጽ
ስለ ሰበካው ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ገቢ
አንቀጽ
ስለ ሰበካው ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ወጪ .
አንቀጽ
የንብረትና ታሪካዊ ቅርሶች አመዘጋገብና አያያዝ
አንቀጽ
ስለሚሾሙ፣ስለሚቀጠሩና በበጎ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያንን
ስለሚያገለግሉ
አንቀጽ ፷
የሰበካው ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ልዩ ልዩ
ሠራተኞች መብትና ግዴታ
፩. መብት
፪. ግዴታ
አንቀጽ
የሰበካው ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መብትና ግዴታ
፩. መብት
፪. ግዴታ
አንቀጽ
የአገልጋይ ካህናትን ብዛት ስለመወሰን
አንቀጽ
ይህን ቃለ ዐዋዲ እና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በሚተላለፍ
ላይ የሚሰጥ ውሳኔ
አንቀጽ
የአፈጻጸም ሥነ ሥርዓት
አንቀጽ
የተፈጻሚነት ወሰን
አንቀጽ
የቃለ ዐዋዲው መሻሻል
አንቀጽ
ቃለ ዐዋዲው የሚጸናበት ጊዜ
ቃለ ዐዋዲ
አንቀጽ
የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
(ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ) አባላት
፩. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ------------------------
የጉባኤው ሰብሳቢ
፪. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ የጉባኤው------------------
ቃለ ዐዋዲ
አንደኛ ም/ሰብሳቢ
፫. በዚህ አንቀጽ በተራ ቍጥር ፬ እና ፭ ከተመለከቱት የካህናትና የምእ
መናን ተወካዮች መካከል ዕድሜው ከ፴ ዓመት ያላነሰ ከ፷ ዓመት
ያልበለጠ ብቁ ችሎታ ያለው በዚህ ጉባኤ የተመረጠ ካህን ወይም
ምእመን-------------------------------የጉባኤው ሁለተኛ ም/ሰብሳቢ
፬. ቍጥራቸው ከሁለት ያላነሱ ከአራት ያልበለጡ በአጠቃላይ ጉባኤው
ተመርጠው የተወከሉ ካህናት ----------------------------የጉባኤው
አባላት
፭. ከአንድ የወጣት ተወካይ ጋር ቍጥራቸው ከሁለት ያላነሱ ከአራት
ያልበለጡ በአጠቃላይ ጉባኤው ተመርጠው የተወከሉ ምእመናን ---
--------------------------------- የጉባኤው አባላት
፮. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኀላፊ --
----------------------የጉባኤው አባል
፯. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና
ጸሓፊ ------------------------ የጉባኤው ጸሐፊ
አንቀጽ ፶
የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
(ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ) ሥልጣንና ተግባር
በቃለ ዐዋዲው በአንቀጽ ፭ እና ፮ የተዘረዘሩትን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
ዐላማና ተግባር እየፈጸመና በሥራ መተርጐሙን እየተቈጣጠረ በተጨ
ማሪ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡፡
፺
ቃለ ዐዋዲ
፩. በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጣውን ደንብ፣ መመሪያና በመንበረ ፓትርያርክ
አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚተላለፈውን ውሳኔና መግለጫ
ለየአህጉረ ስብከቱና ለሚመለከታቸው ሁሉ በወቅቱ እንዲደርሳቸው
ያደርጋል፡፡
፪. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሠሩት ከፍተኛ ዕቅዶችና ለልዩ ልዩ መንፈሳዊና
ማኅበራዊ አገልግሎት የተወሰነውን ገንዘብ በደንቡ መሠረት በትክክል
መያዙንና መጠበቁን ይከታተላል፡፡
፫. ከየአጥቢያው አብያተ ክርስቲያናት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ አስተዳደርና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚከፈ
ለውን ገንዘብ ተቈጣጥሮ በየጊዜው ገቢ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
፬. የአጠቃላዩ ሰበካ አስተዳደር ገንዘብ አያያዝና የንብረት አጠባበቅ በቃለ
ዐዋዲው ከአንቀጽ እስከ በተደነገገው መሠረት መከናወኑን
ይከታተላል በሒሳብ አጣሪም ያስመረምራል፡፡
፭. የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የመተዳደሪያ ደንብና የሥራ መመሪያ እንደ
ዚሁም ሊሻሻል የሚገባውን የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት ሕግጋትና
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች እያጠና ለአጠቃላዩ ጉባኤ ያቀርባል፡፡
፮. በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወኑት የቤተ ክርስቲያን ዓይነተኛ ተግባራት
ማለት ለስብከተ ወንጌል፣ ለመንፈሳዊ ትምህርት፣ ለልማት፣ ለበጎ አድ
ራጎት፣ ለሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት ሀብትና አገልግሎት መስፋፋት
ዕቅድ እያወጣና መርሐ ግብር እያዘጋጀ ለአጠቃላዩ ጉባኤ አቅርቦ ሲፈቀ
ድለት በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
ቃለ ዐዋዲ
፯. ለመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ስብሰባ አጠቃላይ
ሪፖርት፣ የመነጋገሪያ አርእስት (አጀንዳ) እና መርሐ ግብር ያዘጋጃል፡፡
፰. የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ወይም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያርኩ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
ይሆናል፡፡
፱. በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈ
ሳዊ ጉባኤ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡
አንቀጽ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፩ መሠረት፡-
፩. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና አህጉረ ስብከት ፣ለገዳማትና አድባራት
እንዲሁም በየደረጃው ለተቋቋሙት ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት
ሁሉ የአስተዳደር ማእከልና ርእስ፣ ለቤተ ክህነት ሥራ አመራርና ለመን
ፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ የበላይ ኀላፊና ባለሙሉ ሥልጣን መሥሪያ
ቤት ነው፡፡
፪. የቅዱስ ሲኖዶስ ሕግና ደንብ፣ የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔና መመሪያ እንዲ
ሁም የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው በጽ/ቤቱና
በሥሩ በሚገኙት መምሪያዎችና ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች አማካይነት
ነው፡፡
፫. ከየአህጉረ ስብከቱ የሚቀርቡትን የአስተዳደርና የፍትሕ መንፈሳዊ
ጉዳዮችን እየተቀበለ የሚወስን የአስተዳደር ጉባኤ አለው፡፡
ቃለ ዐዋዲ
አንቀጽ
የፓትርያርኩ ሥልጣንና ተግባር
ፓትርያርኩ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ የተደነገገውና የሚከ
ተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡
፩. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገር ውስጥና በውጭ
ሀገር ለምትገኘዋ መላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንፈሳዊ አባትና የበላይ ጠባቂ፣ ለአንድነትዋና ለአስተዳደርዋ ከፍተኛ
ኀላፊና ባለሙሉ ሥልጣን በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትር
ያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን በርእሰ መንበርነት ይመራል፡፡
፪. ፓትርያርኩ የሁሉም መንፈሳዊ አባትና መሪ እንደመሆኑ መጠን በየደ
ረጃው ለሚገኙት የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት መሪዎች፣ ለካህ
ናትና ለምእመናን መመሪያ፣ ትምህርትና ቡራኬ ይሰጣል፡፡
፫. በመጀመሪያ ደረጃም ሆነ በይግባኝ የሚቀርቡት ጉዳዮች በጠቅላይ
ቤተ ክህነት ወይም በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ
እንዲታዩና ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
፬. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን የሚያፋልሱና ሌሎችም
የቤተ ክርስቲያን ዐበይት ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለመላው የቅዱስ ሲኖዶስ
አባላት (ሊቃነ ጳጳሳት)፤ አስፈላጊም ከሆነ ለመንበረ ፓትርያርክ አጠ
ቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት አስቸኳይ ጥሪ የማድረግ መብትና
ኀላፊነት አለው፡፡
ቃለ ዐዋዲ
፭. ከጥንት ጀምሮ ያለው የአኃት ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት
መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግንኙነት በበለጠ እንዲስፋፋና እንዲጠናከር
ያደርጋል፡፡
አንቀጽ
የጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር
ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ንኡስ
ቍጥር ፯ እና አንቀጽ የተደነገገውና የሚከተሉትሥልጣንና ተግባር
ይኖሩታል፡፡
፩. ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለቅዱስ ፓትር
ያርክ ሆኖ ለመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሥራ አመራር የገንዘብና ንብረት አስተዳደር የበላይ ኀላፊ በጠቅ
ላላው የቤተ ክህነት ዋና ባለሥልጣን ነው፡፡
፪. ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መን
ፈሳዊ ጉባኤን በም/ሰብሳቢነት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር
ጉባኤን በዋና ሰብሳቢነት ይመራል፡፡
፫. የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የቆመለትን ዐላማና ተግባር ለመፈጸምና ልዩ
ልዩ የክፍል ሥራዎችንም ለማሟላት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያ
ዎችና ድርጅቶች የሥራ መመሪያ ይሰጣል፤ እያንዳንዱ የሥራ ዘርፍ
ኀላፊም የተመደበበትን የሥራ ድርሻ በትክክል እያከናወነ መሆኑን
ይከታተላል ይቈጣጠራል፡፡
፬. በመጀመሪያ ደረጃም ሆነ በይግባኝ የሚቀርቡትን ጉዳዮች በመንበረ
ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ እንዲታዩና እንዲ
ቃለ ዐዋዲ
ወሰኑ ያደርጋል፡፡ ከዚህ ጉባኤ ሥልጣን በላይ የሆነውን ጉዳይ ለቋሚ
ሲኖዶስ ወይም ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርባል፡፡
፭. በየጊዜው ከየሰበካው ቤተ ክርስቲያን ለጠቅላላው አገልግሎት ጉዳይ
ተብሎ የሚከፈለው ገንዘብ ተጠቃልሎ መሰብሰቡንና በትክክለኛው
ቦታ በወቅቱ ገቢ መሆኑን ይከታተላል፡፡
፮. ማንኛውም ዓይነት ወጪ በሚደረግበት ጊዜ ለመንበረ ፓትርያርኩ
አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በተፈቀደው በጀት መሠረት መሆኑ
ንና የሒሳቡ አያያዝና የንብረቱ አጠባበቅ በቃለ ዐዋዲ አንቀጽ ፣
፣ እና በተዘረዘረው መሠረት መፈጸሙን ይቈጣጠራል፡፡
፯. በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ቍጥር ፲ በተደነገገው መሠረት
በበጀት የተመደበውን ማንኛውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብና
ንብረት ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር በጣምራ ፊርማ ያንቀሳቅሳል፡፡
በየዓመቱና አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜም በሕጋዊ ኦዲተር እንዲ
መረመር ያደርጋል፡፡
፰. የየአህጉረ ስብከቱን የባንክ ሒሳብ ለሚያንቀሳቅሱ ተወካዮች የውክልና
ደብዳቤ ለሚመለከተው ባንክ ይጽፋል፡፡
፱. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ አህጉረ ስብከትና አብያተ
ክርስቲያናት የሥራ ሂደታቸውን ይከታተላል፤ ይቈጣጠራል፡፡
፲. የየዓመቱን የሥራ ፍሬና የወደፊቱንም ዕቅድ የሚያስረዳ ሪፖርት በየዓ
መቱ በጥቅምት ወር ለሚደረገው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
ያቀርባል፤ አጠቃላይ ጉባኤው የመከረበትና ያሳለፈው የውሳኔ ሐሳብ
ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ሲጸድቅ በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
ቃለ ዐዋዲ
. የየመምሪያዎቹ፣የድርጅቶችና የልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች የሥራ ኀላፊ
ዎችን የሥራ ዝውውር እድገት በተመለከተ በጠቅላይ ቤተ ክህነት
ሥራ አስኪያጅ አቅራቢነት ተጠንቶና ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲስማሙበት
በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
. አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩን እያማከረ ይፈጽማል፤
ያስፈጽማል፡፡
አንቀጽ
ስለ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ
ም/ሥራ አስኪያጅ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ የተደነገገውና
የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡
፩. ም/ሥራ አስኪያጁ
ሀ/ ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ተለይተው በመመሪያ የሚሰጡትን
ተግባራት ያከናውናል
ለ/ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በማይኖርበት ጊዜ ተክቶት ይሠራል፡፡
፪. ም/ሥራ አስኪያጁ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ይሆናል፡፡
ምዕራፍ ፰
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ
የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት የአመራር ሥነ ሥርዓትና ተጨማሪ
የስብሰባ ጊዜ
፩. የሰበካ መንፈሳዊያን ጉባኤያት የአመራር ሥነ ሥርዓት
ቃለ ዐዋዲ
በየደረጃው የሚገኙት የሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት የአመራር ሥነ
ሥርዓት ቀጥሎ እንደተመለከተው ይሆናል፡፡
ሀ/ በማናቸውም ደረጃ የሚገኝ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከአባሎቹ ሁለት
ሦስተኛው ከተገኙ ጉባኤው እንደተሟላ ተቈጥሮ ሥራውን ሊቀጥል
ይችላል፡፡
ለ/ ለጉባኤው የቀረቡት ጉዳዮች የሚወሰኑት በዕለቱ በተገኙት አባሎች
ድምፅ ብልጫ ሲሆን ድምፁ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ ሰብሳ
ቢው ያለበት ወገን ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል፡፡
ሐ/ በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ የተወሰነው ጉዳይ በቃለ ጉባኤ ተዘጋጅቶ
በዕለቱ ስብሰባ ላይ የተገኙ አባላት ብቻ በሙሉ ይፈርሙበታል፡፡
መ/ የሰበካውን መንፈሳዊ ጉባኤ ውሳኔ የመፈጸምና የማስፈጸም ኀላፊነት
የጉባኤው ሰብሳቢ ነው፡፡
፪. ተጨማሪ የስብሰባ ጊዜ
በቃለ ዐዋዲ በምዕራፍ ፫ በአንቀጽ ፯ በተራ ቍጥር ፩ በፊደል (ለ)
እና (ሐ)፣ በምዕራፍ ፭ አንቀጽ በተራ ቍጥር ፩፣ በአንቀጽ
ተራ ቍጥር ፪ ከተገለጸው መደበኛ የስብሰባ ጊዜ በተጨማሪ
በየደረጃው የሚገኙት ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት አስቸኳይ ጉዳይ
ሲገጥማቸውና አስፈላጊ የሆነ ምክንያት ሲኖራቸው ወይም ከጉባኤው
አባላት መካከል ከግማሽ በላይ የሆኑት ስብሰባ እንዲደረግ ሲጠይቁ
በየሰብሳቢዎቻቸው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ስብሰባ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ቃለ ዐዋዲ
አንቀጽ
ስለ ሰበካው ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ገቢ
በቅዱሳት መጻሕፍት (በኦሪት ዘሌ ÷፴- ፤ በኦሪት ዘዳ ÷ -
፤ በኦሪት ዘኍ ÷፳- ፤ ነህ ፲÷ - ፤ትን.ሚል ፫÷፯- ፤
ማቴ ÷ ፤ የሐዋ ሥራ ፬÷ - ፤ ፩ኛ ቆሮ ÷፩-፯) በሕገ ቤተ
ክርስቲያን አንቀጽ ተራ ቍጥር እንደተደነገገው ማንኛውም ምእ
መን ከሚያገኘው ከማናቸውም ሀብቱና ንብረቱ ለእግዚአብሔር ቤተ
መቅደስ አገልግሎትና ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ካህናት በጠቅላላው
ለመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚውል ዐሥራት፣ በኵራት፣ ቀዳ
ምያት መክፈል ክርስቲያናዊ ግዴታው ነው፡፡
ከሰበካው ካህናትና ምእመናንም ሆነ ከሌሎች ልዩ ልዩ ቦታዎች የሚ
ገኘው የቤተ ክርስቲያን የገቢ ዓይነት ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
፩. የወርና የዓመት ክፍያ፣
ሀ/ ማንኛውም ክርስቲያን ከሚያገኘው ገቢ ላይ አስቦ ዐሥራት (ከዐሥር
አንድ) መክፈል በቅዱስ መጽሐፍ የታዘዘ ግዴታ ነው፡፡
ለ/ ገቢ ያለው ካህንም ሆነ ምእመን ለሚገለገልበት አጥቢያ ቤተ ክርስ
ቲያን የሰበካ ጉባኤ የአባልነት ክፍያ በየወሩ ብር ፳ (ሃያ) ይከፍላል፡፡
ሆኖም ግን የአከባቢውን ሁኔታ መሠረት በማድረግ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ
ጳጳስ በአስተዳደር ጉባኤ እየወሰነ ከ፳ (ከሃያ) ብር በላይ ሊያስከፍል
ይችላል፡፡
ሐ/ በጎ ፈቃድ ያለው ከላይ ከተጠቀሰው የበለጠ ክፍያ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ቃለ ዐዋዲ
መ/ ጥሬ ገንዘብ መክፈል ያልቻለ በዓይነት ከምርቱና ከሀብቱ የመክፈል
ክርስቲያናዊ ግዴታ አለበት፡፡
ሠ/ በዚሁ ተራ ቍጥር ከፊደል ሀ እስከ መ የተመለከተውን ክፍያ መክፈል
የማይችል ቢኖር ሁኔታው በሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
(ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ) ተጠንቶ ሊከፍል በሚችለው መጠን ይወሰ
ንለታል፡፡ ፈጽሞ ለመክፈል የማይችል ከሆነም በነጻ መንፈሳዊ አገል
ግሎት ይፈጸምለታል፡፡
ረ/ በጒልበትና በዕውቀት ሥራ መርዳት የሚችል ሆኖ ሲገኝ እንደች
ሎታው ለቤተ ከርስቲያን ተገቢውን አገልግሎት ማበርከት ይችላል፡፡
፪. ከሰበካውና ከሌሎች ምእመናን የሚገኘው የገንዘብ ገቢ፣
ሀ/ ስእለት
ለ/ ሙዳየ ምጽዋት
ሐ/ ስጦታ /መባእ/
መ/ የወርና የዓመት በዓል ገቢ
ሠ/ የቅርጻ ቅርጽና የተግባረ እድ ሽያጭ
ረ/ በጠበል አገልግሎት በሙዳየ ምጽዋት የሚገኝ ገቢና ከቤተ ክርስ
ቲያን ጐብኝዎች
ሰ/ ከሰንበት ት/ቤት፣ ከስብከተ ወንጌል እና ከልዩ ልዩ ክፍሎች መንፈ
ሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች
ሸ/ ከልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች
ቃለ ዐዋዲ
ቀ/ በዚህ የገቢ አርእስት ውስጥ ያልተጠቀሰ ማናቸውም ዓይነት ገቢና
ሌላም ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮችን በመፍጠር የሚገኝ ገንዘብና ንብረት
ይሆናል፡፡
፫. በዚህ አንቀጽ በተራ ቍጥር ፩ እና ፪ በዝርዝር የተገለጸው ገንዘብና
ንብረት ተጠቃልሎ በቤተ ክርስቲያኑ ገንዘብ ቤት የገንዘብ ወጪ
የሚደረገው በተፈቀደው ዓመታዊ የገንዘብ ድልድል /በጀት/ መሠረት
የሰበካው ሰብሳቢ በጽሑፍ ሲያዝ ብቻ ነው፡፡
፬. ማናቸውም ዓይነት የሰበካው ገንዘብና ንብረት ገቢ ለቍጥጥር እንዲ
ያመች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትር
ያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የበላይ ተቈጣጣሪነትና በመንበረ ጵጵስና ሀገረ
ስብከት ጽ/ቤት ኀላፊነት ታትሞ በሚወጣው በአንድ ዓይነት ሕጋዊ
ደረሰኝ /ካርኒ/ ብቻ ይሰበሰባል፡፡
፭. ይህን ቃለ ዐዋዲ በመተላለፍ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
ሳያውቀውና ሳይፈቅድ በሰበካው ቤተ ክርስቲያን ስም ሌላ የገቢ ካርኒ
አሳትሞ የሚሠራ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ወይም ግለሰብ በሕግ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡ ሲሠራባቸው የተገኙ ካርኒዎችም ዋጋ እንደሌላቸው ተቈጥሮ
እንዳይሠራባቸው ይታሸጋሉ፡፡ በተያዙት ካርኒዎች የተሰበሰበው ገንዘ
ብም በሕጋዊ ደረሰኝ ለቤተ ክርስቲያኑ ገቢ ይሆናል፡፡
፮. በየአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚገኘው ገንዘብ
በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ስም፣ ከወረዳ እስከ መንበረ ፓትርያርክ
አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚገኘው ገንዘብ፣ በየደረጃው በተቋ
፻
ቃለ ዐዋዲ
ቋመው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስም የባንክ ሒሳብ ተከፍቶለት ይቀ
መጣል፤ እንደየ አስፈላጊነቱ በውሳኔም በበጀት ዓመቱ በተያዘው ዕቅድ
መሠረት በሥራ ላይ ይውላል፡፡
አንቀጽ
ስለ ሰበካው ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ወጪ
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የገንዘብ ወጪ ከዚህ ቀጥሎ እንደተመለከተው
ይሆናል፡፡
፩. አጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ከካህናትና ምእመናን ክፍያ፣ ከስእለት፣
ከሙዳየ ምጽዋት፣ ከልማት ሥራዎችና ከማንኛውም ገቢ ላይ ፳%
(ሃያ ከመቶ) ለሀገረ ስብከት ይከፍላል፡፡ ሀገረ ስብከቱም በዚህ ቃለ
ዐዋዲ አንቀጽ ተራ ቍጥር ፭ መሠረት ክፍያውን ይፈጽማል
፪. ከበላይ አካል በተፈቀደ በጀት ድልድል መሠረት፡-
ሀ/ ለደመወዝ
ለ/ ለሥራ ማስኬጃ
ሐ/ በዕቅድ ለተያዙ ልዩ ልዩ ሥራዎች ወጪ ያደርጋል፡፡
፫. ከቤተ ክርስቲያኒቱ ወይም በየደረጃው ከሚገኘው የሰበካ መንፈሳዊ
ጉባኤ ገንዘብ ቤት የገንዘብ ወጪ የሚደረገው በተፈቀደው ዓመታዊ
የገንዘብ ድልድል /በጀት/ መሠረት የአጥቢያ ሰበካው አስተዳደሪ /ሰብ
ሳቢ/ በጽሑፍ ሲያዝ ብቻ ነው፡፡
፬. በማንኛውም ደረጃ የሚገኘው የሰበካ አስተዳደር የበጀት ዓመት ሐምሌ
፩ ቀን ተጀምሮ ሰኔ ፴ ቀን ይዘጋል፡፡
ቃለ ዐዋዲ
፭. በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በየደረጃው የተጠናቀረው የንብረት አያያዝና
አጠባበቅ የገንዘብ ገቢና ወጪ ሒሳብና የሥራ ክንውን ሪፖርት እስከ
ሐምሌ ፴ ቀን ድረስ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መድረስ
አለበት፡፡ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትም የበኩሉን አጥንቶና አጣርቶ ዓመታዊ
ሪፖርት እስከ ነሐሴ ፴ ቀን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
፮. በየደረጃው የተቋቋሙት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት ከተፈቀደላቸው
በጀት ውጭ የገንዘብ ወጪ ማድረግ አይችሉም
፯. የእያንዳንዱ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ገቢ የአንዱ ዓመት ከፍ፣ የአንዱ
ዓመት ገቢ ዝቅ ሊል ስለሚችል ለደመወዝ፣ ለሥራ ማስኬጃና ለቤተ
ክርስቲያን ማደሻ ታጥቶ ችግር እንዳይደርስ አስቀድሞ ጥንቃቄ በማ
ድረግ ማንኛውም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጽ/ቤት አዲስ የበጀት ድል
ድል በሚያደርግበት ወቅት በበጀት ከሚደለደለው ሒሳብ ላይ ለመጠ
ባበቂያ በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ ላይ % /ሃያ አምስት
ከመቶ/ በባንክ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ይህም ሒሳብ የሚንቀሳቀሰው
ተጠንቶ ሲቀርብ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ይሆናል፡፡
አንቀጽ
የንብረትና ታሪካዊ ቅርሶች አመዘጋገብና አያያዝ
፩. በቤተ ክርስቲያን ስም የሚገኙት ንዋያተ ቅድሳትና ጥንታውያን ቅርሶች
አመዘጋገብ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቋንቋ የግእዝ ፊደልና አኃዝ እንዲ
ሁም የተለመደው የመለያ ቍጥር (ኮድ) እየተሰጣቸው በቋሚ ባሕር
መዝገብ ተመዝግበው በጥንቃቄ ይቀመጣሉ፡፡
ቃለ ዐዋዲ
፪. በገዳማት፣ አድባራትና ገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙት ጥንታ
ውያን ቅርሶች በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ችግር ምክንያት ጒዳት የሚደ
ርስባቸው መሆኑ ሲታመንበትና ለጥንቃቄ ሲባል ከቦታ ወደ ቦታ
ለማዛወር ቢያስፈልግ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት በሀገረ
ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ሲወሰን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
ትእዛዝ እንዲንቀሳቀሱ ካልተደረገ በስተቀር ካሉበት ታሪካዊ ቦታ
በምንም ዓይነት መንቀሳቀስ የለባቸውም ፡፡
፫. የአንዱን ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ወይም ንብረት ካለበት ቦታ ወደ ሌላ
ያዛወረ ወይም የሰወረ ወይም የሰረቀና ያሰረቀ ወይም የሸጠና የለወጠ
ግለሰብ ወይም ድርጅት በፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ አድራጎቱን
የፈጸመው ሰው ካህን ከሆነ ከሥልጣነ ክህነቱና ከማንኛውም የቤተ
ክርስቲያን አገልግሎትና ከጥቅሙ ሁሉ ታግዶ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ
ወይም በሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አማካይነት ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ አስፈ
ላጊው ቅጣት ይወሰንበታል፡፡
፬. ለቅርሶች ደኅንነት ሲባል በበላይ አካል ታውቆና ተፈቅዶ ካልሆነ በቀር
ቅርሶችን በካሜራ፣ በማይክሮ ፊልም እና በሌሎች ኤሌክትሮኒክስ
መሣሪያዎች ማንሣት የተከለከለ ነው፡፡
አንቀጽ
ስለሚሾሙ፣ ስለሚቀጠሩና በበጎ ፈቃድ
ቤተ ክርስቲያንን ስለሚያገለግሉ
፩. የደብር አስተዳዳሪ መመዘኛ
አንድ ካህን የደብር አስተዳዳሪ ሆኖ ለመሾም የሚከተሉትን መመዘኛዎች
ማሟላት አለበት
ቃለ ዐዋዲ
፩. ክህነት ያለው እና ዕድሜው ከ፴ ዓመት በላይ የሆነው
፪. ቀድሶ ማስተማር የሚችል ቢቻል የሐዲሳት፣ የብሉያትና የሊቃውንት
መጻሕፍት የትርጓሜ ትምህርት ከሦስቱ አንዱን የተማረ ወይም ከመን
ፈሳዊ ኮሌጆች በዲፕሎማ ወይም ከዚያ በላይ የተመረቀ
፫. በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ቅን አገልግሎት የሰጠ
አንቀጽ
ቃለ ዐዋዲው የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ቃለ ዐዋዲ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጸድቆ
ከወጣበት ከሐምሌ ፳ ፻ ፱ ዓ.ም.
ጀምሮ የጸና ይሆናል ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ ሐምሌ ፳ ፻ ፱ ዓ.ም.
ቃለ ዐዋዲ
ስለካህናት ተልእኮና ስለሢመተ ክህነት፣
የካህናት ተልእኮ ደግሞ ሁለተኛ ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው፡፡ ሦስ
ተኛ ጊዜ በጎቼን አሰማራ አለው (ዮሐንስ
እነሆ እኔ እንደበጎች በተኲላዎች መካከል
. - )፡፡
እልካችኋለሁ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች
አንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ (ማቴ. ፲. )፡፡ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔር
መንጋ ጠብቁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ
ወደዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት
እንጂ በግድ ሳይሆን በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥ
ሁሉ ስበኩ፡፡ ያመነ የተጠመቀም ይድናል ያላመነ
ፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት ለመ
ግን ይፈረድበታል (ማርቆስ. . - )፡፡
ንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ አትግዙ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ
በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃች የማያልፈውን የክብርን አከሊል ትቀበላላችሁ
ኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተ (፩ኛ ጴጥ. ፭.፪-፬)፡፡
ማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እነ
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ
ሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ
ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ
ከእናንተ ጋር ነኝ (ማቴዎስ. . -፳)፡፡
እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው
አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ (ግብረ ሐዋርያት
ጠርተው እንዲህ አሉአቸው የአግዚአብሔርን ፳ . )፡፡
ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ
ነገር አይደለም፡፡ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ሢመተ ክህነት
ለማገልገል እንተጋለን (የሐዋርያት ሥራ. ፮.፪- ፩/ ‹‹እሙን ነገር›› ፡፡ ነገሩ ደግ ነው፡፡
፬)፡፡ ዘይፈቅድ ይሠየም ጳጳስ ሠናየ ግብረ ፈተወ /
ግብ.ሐዋ. ፳. /፡፡ ቅስና ሊሾም የወደደ በጎ
እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው
ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ አደረገ ቢወድ አይደለም በቅቶ ቢገኝ ነው፡፡
ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? መልካሙን የምሥ ፪/ ወባሕቱ ርቱዕ ይሠየም ጳጳስ ዘኢያደሉ
ራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ለገጽ (ዘሌዋ. . ቲቶ. ፩.፮.፯)፡፡
ናቸው ተብሎ እንደተጻፈ ካልተላኩ እንዴት
ነገር ግን በፍርድ በብያኔ በጸሎት በትምህርት
ይሰብካሉ? ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታ
በምጽዋት ፊት አይቶ የማያደላ ሊሾም ይገባል፡፡
ዘዙም፡፡ ኢሳይያስ ጌታ ሆይ ምስክርነታችንን
ዘአልቦ ምክንያት፡፡ ምክንያት ኃጢአት የሌለ
ማን አመነ? ብሎአልና፡፡ እንግዲያስ እምነት
በት፡፡ ዘአሐተ ብእሲተ አውሰበ፡፡ ያልደጋገመ
ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል
(ድንግል አይሾም አላለም)፡፡ ብእሲ ንቁህ ከንዋመ
ነው (ሮሜ. ፲. - )፡፡
ሐኬት የነቃ፡፡ ወጠቢብ ብልህ አስተዋይ፡፡ ወመ
ኢየሱስ ስምኦን ጴጥሮስን ትወደኛለህን? ፍቀሬ ነግድ፡፡ እንግዳ ተቀባይ፡፡ ዘአንጽሐ ርእሶ
አለው፡፡ አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታው ሰውነቱን ከኃጢአት የለየ፡፡ መመህር ወመገሥጽ
ቃለህ አለው፡፡ ግልገሎቼን አሰማራ አለው፡፡ የሚመክር የሚያስተምር፡፡
ሸ
ቃለ ዐዋዲ
፫/ ዘኢያበዝኅ ሰትየ ወይን /ዘሌዋ. .፱ ርኩባን፡፡ በአንድ ቦታ የተወሰኑ፡፡ አንድም ሕዋሳ
ቲቶ. ፩.፯/ መጠጥ የማያበዛ፡፡ ዘኢያፈጥን እዴሁ ታቸውን የሰበሰቡ ይኹኑ፡፡ እለ ኢያበዝኁ
ለዘቢጥ፡፡ ፈጥኖ የማይማታ፡፡ አንድም ፈጥኖ ሰትየ ወይን፡፡ መጠጥ የማያበዙ ይኹኑ አለ
የማይገዝት፡፡ ባቁዕ፡፡ መክሮ አስተምሮ የሚረባ ኢያፈቅሩ ረብሐ ከንቶ (ፊልጵ. ፩.፩፤ ግብ.ሐዋ.
የሚጠቅም፡፡ ዘኢይትገዓዝ በማይረባ በማይ ፮.፫)፡፡ ኃላፊውን ገንዘብ የማይወዱ ይኹኑ፡፡
ጠቅም ነገር የማይከራከር፡፡ ዘኢያፈቅር ንዋየ ፱/ እለ የዐቅቡ ምክረ ሃይማኖቶሙ በልብ
ኃላፊውን ከብት የማይወድ፡፡ ንጹሕ፡፡ ከክህደት ከኑፋቄ ንጹሕ በሆነ ልቡና
፬/ ዘሠናይ ሥርዓተ ቤቱ፡፡ የቤቱ ሥርዓት የሃይማኖታቸውን ትምህርት አጽንተው የያዙ
የተከናወነለት፡፡ ዘቦ ውሉድ ዘይትኤዘዙ በኲሉ ይኹኑ፡፡
ንጽሕ (፩ሳሙ. ፪. )፡፡ በንጽሕና ሆነው የተሠሩ ፲/ ወሎሙኒ ይቅድሙ አመክሮቶሙ፡፡
የተቀጡ ልጆች ያሉት፡፡ እሊያን ቅሉ አስቀድመው ይፍተኗቸው፡፡
፭/ ወዘሰ ኢይክል ሠሪዐ ቤቱ እፎኑ ያስተ ወእምዝ ይትለአኩ እምከመ ኅሩያን እሙንቱ፡፡
ሐምም ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ሰብኡን ሠርቶ ከዚህ በኋላ በቅተው ቢገኙ ይሾሙ፡፡
ቀጥቶ ማሳደር የማይቻለው ከሆነ በዓራቱ መዓ ስለዲያቆናውያት ሴቶች
ዝን ያሉ ምእመናንን ሠርቶ ቀጥቶ ያሳድራል
/ ወአንስትኒ ከማሁ እለ አንጽሐ ርእሶን
ብለው እንደ ምን ይሾሙታል?
(ቲቶ. ፪.፫)፡፡ አሁን ወንዶችን ዲያቆናት ንጹሐን
፮/ ወኢይኩን ዘእምሐዲስ ተክል፡፡ ከሐዲስ ይኹኑ እንዳልሁ ዲያቆናውያት ሴቶችም ሰውነታ
አማኒ ወገን አይሾም፡፡ ከመ ኢይትዓበይ እንዳ ቸውን ከኃጢአት የለዩ ይኹኑ እለ ተምህራ
ይታበይ ከኔ በላይ ቢያጡ እንጂ ሾሙኝ ብሎ፡፡ ሥርዓተ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተማሩ እለ
ወኢይጸለል፡፡ በድንቁርና እንዳይያዝ፡፡ ወኢይደቅ ኢያስተዳጉጻ፡፡ ነገር ሠርተው አንዱን ከአንዱ
ውስተ መሥገርተ ሰይጣን፡፡ ሰይጣን በተያዘበት የማያጣሉ ይኹኑ፡፡ ጠባባት ብልሆች ራትዓት፡፡
አሸክላ እንዳይያዝ /አለ/ ትዕቢት ነው፡፡
ቅኖች ይኹኑ፡፡ ወምእመናት በኲሉ በውሥጥ
፯/ ወዓዲ ርቱዕ ዘሰብእ አፍአ ይንዕድዎ / በአፍአ በሥራው ኹሉ የታመኑ ይኹኑ ወይት
ም. ፭.፲/፡፡ ዳግመኛም ከምግባር ከሃይማኖት ለአካ፡፡ (ይትለአካ) እንዲህ እንዲህ ያሉት ይሾሙ፡፡
በአፍአ ያሉ ሰዎች ያመሰገኑት ሊሆን ይገባል፡፡ በመልካም ላገለገሉ ዲያቆናት የበለጠ
ከመ ኢይደቅ ውስተ ጽእለት (፩ኛ. ቆሮ. ፭. . ያድርጉላቸው
)፡፡ በስድብ እንዳይወድቅ ማለት ተነቅፎ
/ ውብእሲኒ ዘአሐተ ብእሲተ አውሰበ
ምእመናንን እንዳያስነቅፍ ወመሥርገተ ሰይጣን
የቄሱን ተናግሮ የዲያቆኑን አልተናገረውም ነበርና
ሰይጣን ሰውን በሚይዝበት አሸክላ እንዳይያዝ፡፡
ዲያቆንም ያልደጋገመ ይሾም (ድንግል አይሾም
ስለ ዲያቆናት አላለም)፡፡ ዘቦ ወሉድ የተሠሩ የተቀጡ ልጆች
፰/ ወዲያቆናትኒ ከማሁ ንጹሓን፡፡ ዲያቆ ያሉት ዘሠናይ ግዕዘ ቤቱ ቊ. ፪ የቤቱ ሥርዓት
ናቱም ከማሁ እንደቄሱ ንጹሐን ይኹኑ፡፡ ወእስት የተከናወነለት፡፡
ቀ
ቃለ ዐዋዲ
/ ወእለሰ ሠናየ ይትለአኩ እንተ ተዐቢ የሚሾሙት ብዙ መዓርገ ሀብት አለና እንተ ተዐቢ
ሢመተ ይግበሩ ሎሙ (ማቴ. . )፡፡ (ሎሙ ሢመተ ይግበሩ ሎሙ፡፡ አንድም በኢየሱስ ክርስ
ለእለ ይትለአኩ በጎ ማገልገልን ላገለገሉ)ዲያቆ ቶስ አምኖ የሚሠሩት ብዙ ምግባር ትሩፋት አለና
ናት የበለጠ ያድርጉላቸው (አለ) ከዲቁና ወደ ይቅድሙ አመክሮቶሙ እምከመ ኅሩያን እሙ
ቅስና፡፡ ከቅስና ወደ ኤጲስ ቆጶስነት ያውጧቸው ንቱ፡፡ /የግዕዙ ንባብ ከነትርጓሜው ፩ኛ. ጢሞ.
በብዙኀ ሞገስ በሃይማኖተ ኢየሱስ ክርስቶስ ፫.፩- /፡፡
(፩ኛ ዮሐ. ፫. )፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ
ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መልእክትና መመሪያ
፩/ እለ ሠናየ ተልእኩ ቀሲሳን ምክዕቢተ በትምህርት በምጽዋት ፊት አይተህ ሳታደላ
ይደልዎሙ (ሮሜ. .፰ና . )፡፡ በጎ ማገል ይህን ትጠብቅ ዘንድ አዳኝብሃለሁ፡፡ ወኢታ
ገልን ላገለገሉ ቀሳውስት እጽፍ ድርብ ዋጋ ጽድቆ ለሰብእ ቅድመ ፍትሕ፡፡ ሳይመሰከርበት
ክብር ይገባቸዋል፡፡ ወፈድፋደሰ ለእለ ይሰርሑ እንዲያደርግ አውቃለሁ አትበል፡፡ ወኢትግበር
በቃል ወበምህሮ ይልቁንም በቃል ቃል ለቃል ምንተሂ በዘትትሔመይ፡፡ በምትነቀፍ ገንዘብ
የሰሙትን ወበምህሮ ከመጽሐፍ ያገኙትን የምትነቀፍበት ሥራ አትሥራ፡፡ ነገር ሠሪ እንጂ
በማስተማር ለሚደክሙ መምህራን እጽፍ ሰምቶ ቃል ለቃል ተጨዋውቶ ይሉታልና፡፡
ድርብ ክብር ይገባቸዋል፡፡ ወኢታጽድቆ ለሰብእ ቅድመ ፍትሕ፡፡ /አንድም/
፪/ወይብል መጽሐፍ ኢትፍጽሞ አፋሁ ሳይመሰከርለት እንዳያደርግ አውቃለሁ አትበል፡፡
ለላህም ሶበ ታከይድ እክለከ (ዘዳግ. .፬፣ ፩ኛ ወኢትግበር ምንተሂ በዘትትሔመይ፡፡ በምት
ነቀፍ ገንዘብ የምትነቀፍበትን ሥራ አትሥራ
ቆሮ. ፱.፱)፡፡ እህልህን በምታሄድበት ጊዜ
መማለጃ በልቶ ተዘምዶ ሥጋ ኑሮት አድልቶ
የላምህን አፉን አትሠረው ብሏልና፡፡ ወይደልዎ
ይሉታልና፡፡
አስቡ ለዘይትቀነይ ሉቃ. (፲፥፯)፡፡ ለሠራተኛ
ደመወዙ ይገባዋልና፡፡ ፮/ ወኢትሢም ፍጡነ ወኢመነሂ /ግብ
፫/ ላዕለ ልሂቅ ኢትስማዕ ውዴተ፡፡ በቄሱ ሐዋ. ፮-፯/ ማንንም ማን ሳትመረምር ፈጥነህ
ነገረ ሠሪ አትስማበት፡፡ ዘእንበለ ይዝልፍዎ አትሹም፡፡ ወኢትሳተፍ በዝ ውስተ ኃጢአተ
ክልኤቱ ወሠለስቱ ሰማዕት (ዮሐ. ፰. )፡፡ ባዕድ፡፡ በዚህ ሌላው በሠራው ኃጢአት አንተ
ሁለት ሶስት ሰዎች ሳይመሰክሩበት፡፡ በፍዳ እንዳትያዝ አኮ ዘገብረ ባሕቲቶ ዘይት
ኳነን አላ ዘሂ ሠምረ በኃጢአተ ዝኩ እንዲል፡፡
፬/ ወለእለሂ ስሕቱ በቅድመ ኲሉ ገሥ ወአንጽሕ እንከ ርእሰከ፡፡ ሰውነትህን ከኃጢአት
ጾሙ /ኤፌ. ፭. . /፡፡ ስሕቱ በቅድመ ኲሉ
ለይ፡፡ /፩ኛ. ጢሞ. ፭. - / የግዕዙ ንባብ
ገሥጾሙ በቅድመ ኲሉ በጉባኤ የበደሉትንም
ከነትርጓሜው፡፡
በጉባኤ ገሥፃቸው፡፡ ከመ ባዕድኒ ይፍራህ፡፡
ሌላው ፈርቶ ይገሠጽ ዘንድ ዝሉፍ እንዘ ይት ስለ ምእመናን የገንዘብ አስተዋጽኦ ማብራሪያ
ጌሠጽ አብድ ይከውን ማእምረ፤፤ እስመ ፈቀድክሙ ወአቅደምክሙ ትመጥው
፭/ አሰምዕ ለከ በቅድመ እግዚአብሔር፡፡ ነፍሰክሙ እምቀዳሚ ዓም፡፡ ካምና ጀምሮ
በእግዚአብሔር ፊት አዳኝብሃለሁ፡፡ ከመ ትዕቀብ ከጥንተ ስብከት ጀምሮ ከብታችሁን /ሀብታችሁን/
ዘንተ እንዘ ኢታደሉ፡፡ በፍርድ በብያኔ በጸሎት ታወጣጡ ዘንድ አስቀድማችሁ ወዳችኋልና፡፡
በ
ቃለ ዐዋዲ
፩/ ይእዜሰ አሁንስ እንዲያው በምኞት በዋልና ዘቦ ውኁድ አምስት ጎሞር ያገባ ነው
ትቀሩ? ግበሩሂ፡፡ አስተዋጽኦውን አወጣጡ፡፡ አላነሰውም አለ አምስት ሆኖ ይመገበዋልና፡፡
እስመ ፈቂድሂ እምፈቲው፡፡ ቁርጽ ሐልዮ፤ ከነቅዕ (አንድም) በአዲሱ /ዘቦ ብዙኀ/ ብዙ ብዕለ ሥጋ
ሐልዮ የተነሣ ነውና፡፡ ወገቢርሂ እምረኪብ፡፡ ያላቸው ምእመናን አሉ እንደመጠኑ ተክል
መስጠትም ከማግኘት የተነሣ ነውና ግበሩሂ ተክለው ተገብሮ ይዘው ይኖራሉ፡ አላነሳቸውም
ወፈጽሙሂ፡፡ አለ አሕዛብ ይጨምሩላቸዋልና፡፡ አንድም /ዘቦ
፪/ ወእምከመሰ ፈቂድ ሀሎ ይትመዘገብ ብዙኀ/ ብዙ ብዕለ ነፍስ ያላቸው ምእመናን አሉ
በዘይትከሀሎ፡፡ መስጠቱንስ መውደዱ ካለ፡፡ አልተረፋቸውም አለ ለአሕዛብ ይጸልያሉና፡፡ /
ዘቦ ውኁድ/ ጥቂት ብዕለ ነፍስ ያላቸው አሕዛብ
ወአኮ በአምጣነ ዘኢይትከሀሎ፡፡ /ምሳ. ፫.
አሉ አላነሳቸውም አለ ምእመናን ይጸልዩላቸ
ማር. . /:: የሌለውን ገንዘብ ሰጥቶ ያይደለ
ዋልና፡፡ /የግዕዙ ንባብ ከነትርጓሜው ፪ኛ.ቆሮ.
መስጠቱን በመውደዱ ብቻ ይመሰገናል፡፡ ዘሰ
፰ .፲- /፡፡
ይፈቅድ ይግበር ወኢይክል ይትዔረዮ ለዘይገብር
ወይክል እንዲል /አፈወርቅ/ አንድም የሌለውን ፮/ ወበእንተ አስተጋብኦሰ ለቅዱሳን /ግብ
ብዙውን ለጥቶ ያይደለ ያለውን ጥቂቱን ሰጥቶ ሐዋ. . .፪ ቆሮ. ም. ፰ና ፱/፡፡ ለቅዱሳን ስለ
ይመሰገናል፡፡ ሚሆን ስለአስተዋጽኦው ነገር፡፡ በከመ ሠራዕ
ክዎሙ ለቤተ ክርስቲያን ዘገላትያ /ገላት. ፪.፬/፡፡
፫/ ወዘአኮ ከመ ባዕድ ያዕርፍ ኪያክሙ
ለገላትያ ሰዎች እንደጻፍኩላቸው፡፡ እንዳዘዝኋቸው
ናጠውቅ፡፡ ነገር ግን በእናንተ ከብት ሌላው
ከማሁ አንትሙሂ ግበሩ፡፡ እናንተም አወጣጡ፡፡
ተድላ ደስታ ሊያደርግበት እናንተን የምናስቸግር
አይደለንም፡፡ ዳዕሙ ተሀልው ፅሩየ በዝ መዋ ፯/ በበእሑድ /ግብ. ሐዋ. ፳፥፯/ :: በበእሑድ/
ዕል፡፡ በዚህ ወራት አነዋራችሁ አንድ ወገን እሑድ እሑድ /በበውኁድ/ ጥቂት ጥቂት/
ይሆን ዘንድ ነው እንጂ እስመ ተረፈ ዚአክሙ በበአሐዱ/ ባያንዳንዱ፡፡ ኲሉ ብእሲ እምኔክሙ
ውስተ ንትጋ እልክቱ ይከውን፡፡ የናንተ ተረፍ ይዝግብ ሎቱ ዘተሰርሐ፡፡ ከናንተ ወገን ሰው
የነዚያን ጉድለት ይመላልና፡፡ ሁሉ የደከመበትን፡፡ አንድም የቀናውን ያወ
ጣጣ፡፡ ወዘረከበ በቤቱ ይዕቀብ፡፡ ያወጣጣ
፬/ ወተረፈ ዚአሆሙ ውስተ ንትጋ ዚአ ውንም በቤቱ አኑሮ ይጠብቅ፡፡ ከመ ኢይኩን
ክሙ ይከውን፡፡ የነዚያም ተረፍ የናንተን ጉድ ቅስት አመ መጻእኩ፡፡ በመጣሁ ጊዜ ጸብ
ለት ይመላልና፡፡ ከመ ይኩን ሀልዎትክሙ ዕሩየ ክርክር እንዳይሆን ይህ የኔ ይህ የኔ በማለት፡፡
በኲሉ፡፡ /ም. ፱. / አነዋራችሁ በሥራው ሁሉ
፰/ ወአመ በጻሕኩ እፌኑ ዘኀረይክሙ ቦቱ
አንድ ወገን ይሆን ዘንድ፡፡
ምስለ መልእክትየ፡፡ በመጣሁም ጊዜ ለመረ
፭ / እስመ ከመዝ ይቤ መጽሐፍ ዘቦ ብዙኀ ጣችሁት ሰው አስይዤ ከክታቤ ጋራ እሰድላ
ኢያትረፈ ብዙ ያለው አልተረፈውም፡፡ ወዘቦ ችኋለሁ፡፡ ከመ ይትረከብ ሀብትክሙ በኢየሩ
ውኁድ ኢያሕፀፀ /ዘፀአ. . /፡፡ ጥቂትም ሳሌም፡፡ ስጦታችሁ በኢየሩሳሌም ይገኝ ዘንድ
ያለው አላነሰውም ብሎ መጽሐፍ እንደ ከዚያ ቤተ ማኅበር አለና፡፡ አንድም በኢየሩ
ተናገረ /ሐተታ/ ዘቦ ብዙኀ በኦሪቱ አምሳ ጎሞር ሳሌም ሰማያዊት ዋጋ በማሰጠት ይታወቅ ዘንድ፡፡ /
ያገባ ነው አልተረፈውም አለ አምሳ ሆኖ ይመገ ፩ኛ. ቆሮ. .፩-፫/፡፡ የግዕዙ ንባብ ከነትርጓሜው፡
ተ
ቃለ ዐዋዲ
፱/ ወእምዝ አስተዋጽኡ አርድእት መጠነ ሕፃናት ወደጌታ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው
ይክሉ ወፈነው ለቢጾሙ እለ ይነብሩ ብሔረ ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው
ይሁዳ ምስለ በርናባስ ወሳውል ኀበ ኲሎሙ አትከልክሉአቸው፡፡ የአግዚአብሔር መንግሥት
ቀሲሳን፡፡ እንደነዚህ ላሉት ናትና፡፡ እውነት እላችኋለሁ
ከዚህም በኋላ ምእመናን የሚቻላቸውን የእግዚአበሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይ
ያህል ገንዘብ አወጣጥተው በብሔረ ይሁዳ ቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው፡፡ አቀፋ
ላሉ ምእመናን ለበርናባስና ለሳውል አስይዘው ቸውም እጁንም ጭኖ ባረካቸው፡፡ /ማር.
ከቀሳውስት ዘንድ ላኩ፡፡ /ግብረ ሐዋርያት ፲. - /፡፡
. / የግዕዙ ንባብ ከነትርጓሜው፡፡ ሊሠራ የማይወድ አይብላ
የድሀዋ መበለት አስተዋጽኦ ወንድሞች ሆይ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ
ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ
ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ
ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
በመዝገቡ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ
እናዛችኋለን፡፡ እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደ
ያይ ነበር ብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር
አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም ሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና በእናንተ
የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች፡፡ ደቀ መዛሙርቱንም ዘንድ ያለሥርዓት አልሄድንምና፡፡ ከእናንተ
ጠርቶ እውነት እላችኋለሁ በመዝገብ ውስጥ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና
ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሃ መበለት አብ ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር
ልጣ ጣለች ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና ይህች እንጂ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም፡፡
ግን ከጉድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ
ጣለች አላቸው /ማር. . - /፡፡ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ ያለ ሥልጣን ስለ
ሆንን አይደለም፡፡ ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን
እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳ
ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ
ልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ በኀዘን
ነበርና፡፡ ሥራ ከቶ ሳይሠሩ በሰው ነገር እየገቡ
ወይም በግድ አይደለም /፪ኛ. ቆሮ. ፱.፯/፡፡
ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ
ለታመመው በጌታ ስም ይጸልዩለት፡፡ አንዳንዶች ሰምተናልና፡፡ እንደነዚህ ያሉትንም
ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ
ክርስቲያንን ሽማግሌዎች /ቀሳውስት/ ወደ እርሱ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን
ይጥራ፡፡ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው እንመክራቸውማለን፡፡ እናንተ ግን ወንድሞች
ይጸልዩለት፡፡ የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ሆይ መልካም ሥራን ለመሥራ አትታክቱ፡፡
ጌታም ያስነሣዋል ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ
ሆነ ይሰረይለታል፡፡ እርስ በርሳችሁ በኃጢ ማንም ቢኖር ይህን ተመልከቱት ያፍርም ዘንድ
አታችሁ ተናዘዙ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ፡፡ ነገር ግን እንደ ወንድም
ስለ ሌላው ይጸልይ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቁጠሩት /፪ኛ.
እጅግ ኃይል ታደርጋለች /ያዕ. ፭. - /፡፡ ተሰ. ፫.፮- /፡፡
ቸ
ቃለ ዐዋዲ
ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሊፈት በሥጋ ወደሙ መወሰን
ኑት፡- ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ከምእመናን መካከል ለሰበካ መንፈሳዊ አስተ
ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? አሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ዳደር ጉባኤ የሚመረጡት አባላት በሕገ ቤተ
መልሶ እንዲህ አለ፡ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ክርስቲያን የጸኑ እንዲሆኑ በቃለ ዐዋዲው ምዕ
ሴት አደረጋቸው፣ ዓለም፡- ስለዚህ ሰው አባቱንና ራፍ ሦስት አንቀጽ ፲ ንኡስ አንቀጽ ፪ ፊደል
እናቱን ይተዋል፣ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፤ (ለ) ቁጥር ፩ የተደነገገው የቅዱስ ወንጌልን
ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል ቃል መሠረት በማድረግ ነው፡፡
አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፡፡ እውነት
እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም፡፡ እግዚብሔር እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው
ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየውም፡፡ እነ ክርስቶስን ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠ
ርሱም፡- እንኪያስ ሙሴ የፍችዋን ጽሕፈት ሰጥ ጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም፡፡ ሥጋዬን
ተው እንዲፈቱአት ስለምን አዘዘ? አሉት፡፡ እር የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት
ሱም፡- ሙሴ ስለልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡
ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ ከጥንት ግን እንዲህ ሥጋዬ እውነተኛ መብል፣ ደሜም እውነተኛ
አልነበረም፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፣ያለ ዝሙት መጠጥ ነውና፡፡ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚ
ምክንያት ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡
ሁሉ ያመነዝራል፣ የተፈታችውንም የሚያገባ ሕያው አብ እንደላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ
ያመነዝራል አላቸው፡፡ ሕያው እንደምሆን እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ
ደቀ መዛሙርቱም፡- የባልና የሚስት ሥር ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡
ዓት እንዲህ ከሆነ መጋባት አይጠቅምም አሉት፡፡ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው አባቶ
እርሱ ግን፡- ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ቻችሁ መና በልተው እንደሞቱ አይደለም ይህን
ለሁሉ አይደለም፣ በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል (ዮሐ.
ሆነው የተወለዱ አሉ፣ ሰውም የሰለባቸው ጃንደ ፮፥ - )፡፡
ረቦች አሉ፣ ስለመንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ
የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ፡፡ ሊቀበለው የሚችል ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፡- እንካችሁ ብሉ
ይቀበለው አላቸው (ማቴ. ፥፫— )፡፡ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋንም አንሥቶ አመስ
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፡- ሁላችሁ ከእርሱ
ንጹሕ ይሁን፣ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን ጠጡ፤ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ
እግዚብሔር ይፈርድባቸዋል (ዕብ. ፥፬)፡፡ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው (ማቴ፡ ፥ - )፡፡
ኘ
ቃለ ዐዋዲ
ወንድሞች ሆይ የሃይማኖታ
ክ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚ
ችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ብ ውን ኢየሱስን ተመልክተን
ኢየሱስ ክርስቶስን ር በፊታችን ያለውን ሩጫ
ትምህርተ መስቀሉን በትዕግሥት እንሩጥ፡፡
ተመልከቱ (ዕብራ. ፫፥፩)፡፡
አርዌ ብርቱን ተመልከት (ዕብራ. ፥፮-፱)
ነ
ቃለ ዐዋዲ
መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርሰቲያናት ምን ይላል?
በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን አለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል
መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡- በቀኝ እጁ ሰባቱን ስለሆንህ፤ ጎስቋላና ምስኪንም ድሀም እውርም
ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፤ ባለጠጋ
መካከል የሚሄደው እንዲህ ይላል፡- እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፤ ተጎናጽ
ፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ
ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አው
ልብስን፤ እንድታይም ዓይኖችህም የምትኳለውን
ቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል
ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ፡፡ እኔ የምወ
እንዲሁም ሳይሆኑ፡- ሐዋርያት ነን የሚሉትን
ዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤
መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው
እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ፡፡ እነሆ በደጅ ቆሜ
አውቃለሁ፤ ታግሠህማል፤ ስለስሜም ብለህ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም
ጸንተህ አልደከምህም፡፡ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ቢከፍትልኝ፤ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም
ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና፡፡ ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፡፡
እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም እኔ ደግሞ ድል እንደነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ
ግባ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና፡፡ እንግዲህ ላይ እንደተቀመጥሁ ፤ድል ለነሣው ከእኔ ጋር
ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደ በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡ መን
መውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣ ፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው
ብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከሥፍራው ይስማ (ራእ.፫፥ — )፡፡
እወስዳለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔ ደግሞ
የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃልና፡፡
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ
ያለው ይስማ፡፡ ድል ለነሣው በእግዚአብሔር
ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ
(ራእ. ፪፥፩—፯)፡፡……………..