Professional Documents
Culture Documents
01.
01.
www.tlcfan.org 0
መለከት #1
የእግዚአብሔር ሕጎች ሕይወት ያለባቸው ቃሎች ናቸው። ሐዋ.7፥38 ይህን ትምህርት መማር
ያስፈለገው ትውልዱን ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር ቃልና የመንግስቱ ሕግ ወደ ሆነው “ቶራ” ሚስጥር ዞር
ለማድረግ፣ ወደ መንግስቱ ሕግና ስርዓት ለመመለስ፣ ድል ነሺ የሆኑ አማኞችን ለመንግስቱ እንዲበቁ እንደ ቃሉ
ለማዘጋጀት ታስቦ ነው። ይህም በእግዚአብሔር መንፈስ ቃሉን በቃሉ ብቻ በመፍታት የሚፈጸም ነው።
የእግዚአብሔር ሕጎችን ኢየሱስ እንዳስተማረውና እንደተረጎመው ማየት ተገቢ ነው። ሉቃ.24፥44-45 “በዚያን
ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤” እንግዲህ ይህ ሳምንታዊ በእግዚአብሔር ሕጎች
ዙሩያ የሚያጠነጥነው የመንግስቱን ሕጎች ትምህርት በመግቢያዬ ነው። ጌታ አእምሮአችንን እንዲከፍት ጸሎቴ
ነው።
ኢየሱስ “እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ
የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም
ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።እላችኋለሁና፦ ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥
ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።” ማቴ.5
“ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤”
ሮሜ.8፥7፣ ዳንኤል.7፥25
ኢየሱስም “እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር
ላድርግ? አለው። እርሱም (ኢየሱስ)፦ ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት
መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው። እርሱም፦ የትኞችን? አለው። ኢየሱስም(ኢየሱስ)፦ አትግደል፥
አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።”
ማቴ 19፣ ገላ.5፥21
“ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች
የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።” 1.ቆሮ.6፥10
“ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ
ይሰጣችኋል፤” ዮሐ.14፥15
www.tlcfan.org 1
መለከት #1
“እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ
ትኖራላችሁ።…እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።” ዮሐ.15
“በነጻነት ሕግ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ እንዳላቸው ሰዎች እንዲህ ተናገሩ፥ እንዲህም አድርጉ።ምሕረትን
ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።. . . ከነፍስ የተለየ
ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” ያቆብ 2
ቀደም ብዬ ያነሳሁት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚፈልግ አንድ አማኝ በሚገባ ስለ ሶስቱ የሕይወቱ
መንፈሳዊ እድገት ደረጃዎች ትክክለኛ የሆነ እውቀት ሊኖረው ይገባል። አማኝ መንፈሳዊ እድገቱ ከየት ጀምሮ
እስከ የት ድረስ እንደሆነ በደንብ ጠንቅቆ ማወቅ ይጠበቅበታል። 2.ጴጥሮስ.3፥18 “ነገር ግን በጌታችንና
በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን“
እያንዳንዱ አማኝ በቃሉ ውስጥ ለማደግ በተለያየ ስፍራ ላይ በእግዚአብሔር ተጠርተናል። እድገታችን ግን ከየት
ተነስቶ የት ጋር የሚያበቃ እንደሆነ ስንቶቻችን እንናውቅ ይሆን? ሶስቱን የመንፈሳዊ የእድገታችን መነሻና
መድረሻዎችን በቃሉ ውስጥ በተለያየ ምሳሌዎች ተመስለው የተቀመጡልንን አስቀድመን እንመልከት፦
አማኝ እነዚህን የእድረት ደረጃዎች ወይም ሩጫዎች እንዲሮጥ ተጠርቷል። ከግልገልነት እስከ በግነት፣
ከአንደኛ ቀን እስከ ሶስተኛ ቀን፣ ከአደባባይ እስከ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከስጋ እስከ መንፈስ ፣ ከእምነት እስከ ፍቅር፣
ከ30 ፍሬ እስከ 100 ፍሬ፣ ከፋሲካ እስከ ዳስ በዓል፣ ከግብጽ እስከ ከነዓን ፣ ከመንገድ እስከ ሕይወት፣ ከአንደኛ
ሰማይ እስከ ሶስተኛ ሰማይ፣ ከውሃ ጥምቀት እስከ እሳት ጥምቀት. . .ወዘተ። ሁሉ አማኝ በቃሉ ውስጥ ለእድገት
ደረጃዎች በተቀመጡት ደረጃዎች ውስጥ የግድ ያልፍ ዘንድ የእግዚአብሔር ፍቃድና የመንግስቱ ሕግ ነው። ሰው
ዘሎ ከአንደኛው ወደ ሶስተኛው መግባት አይችልም። ግልገል ጠቦት ሳይሆን በግ አይሆንም። ደግሞም በግ እንጂ
ግልገል ድምጽ አይሰማም። ሰው ከግብጽ ዘሎ ከንዓን አይገባም። የግድ ምድረበዳውን ማለፍ አለበት።
ከአደባባይ ተዘሎ ቅድስተ ቅዱሳን አይገባም። ዛሬ ግን ብዙዎቻችን የተማርነው የተገላቢጦሽ ነው። ሰው እነዚህን
መንፈሳዊ እድገቶች ምን እንደሆኑ በትክክል ሲገባው የእግዚአብሔር መንግስት ሕግን ጥቅምንና አስፈላጊነት
በትክክለኛ መልኩ መረዳት ይችላል። (1) Justification (2) Santification (3) Glorification
www.tlcfan.org 2
መለከት #1
3) ትንሽ ያወቁ ነገር ግን በደንብ ያልገባቸው፦ የእግዚአብሔር ሕግ እንዳለ ያምናሉ። ሕጉን መታዘዝም
እንደሚገባም ያምናሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ ምን እደሆነና እንዴት መጠበቅ ወይም
ለምን መታዘዝ እንዳለባቸው የማያውቁ ነገር ግን በጣም ቅን ልብ ያላቸው አስተዋዬች ናቸው። ”
ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎ፦ ከሁሉ
ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት? ብሎ ጠየቀው።ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ
ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው። አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም
ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ
ይህች ናት።. . .(የጠየቀው ሰውም) በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም
እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት
ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው። ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ፦ አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት
የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።” ማር.12:፥26-35
www.tlcfan.org 3
መለከት #1
እንግዲህ ከዚህ ከላይ ከዘረዘርኩት ውስጥ በአንዱ ላይ ራስዎን ካገኙ በዚህ ትውልዶችን ለማንቃትና
ለማዘጋጀት በሚነፋው መለከት ትምህርት ክፍል ላይ የሚሰጡት ተከታታይ ትምህርቶች ለእርሶ ያስፈልጎታል
ብዬ አምናለሁ። ደግሞም ለዚህ ትምህርት ዝግጅት የሚረዳዎትን ሕይወት ያላቸው ቃሎች የሚለውንና
የእግዚአብሔር መንግስት የሚለውን መጽሐፎቼን ያንብቡ።
ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት የሙሴን ሕግጋት በሙሉ ጠብቋል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር
ሕግጋት የማይጠብቁትንና ጉልበት አልባ ያደረጉትን ጻፎችና ፈሪሳዊያንን ወቅሷል፣ ገስጿል። ኢየሱስም
የመጀመሪያውን የምድር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ አባቱ ሄደ። ኢየሱስ ከሄደ በኋላ የእርሱ ተከታዬች አማኝ
የሙሴን ሕግ መጠብቅ እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ለመነጋገር በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ነበር። ከስብስባው
በኋላም ውሳኔያቸውን አስተላልፈዋል። ዛሬ እንደዚያ አይነት ስብሰባ ማድረግ ባንችልም። ዛሬ ስለ እግዚአብሔር
ሕግ ወይም ስለ ሙሴ ሕግ በአማኞችና በማያምኑ ዘንድ የሚነሱትን ጥያቄዎች በቃሉ ለመመለስ እውነቱንም
ለማስተማር ቃሉን የምናስተምር ሰዎች ሁሉ ሃላፊነት ነው። በዚህ መለከት ጹሁፍ ላይ በፌስ ቡክ ሕብረት
አባሎችና ተከታታዬቼ የተጠየቁትን ጥያቄዎች እንደ እግዚአብሔር ቃል እመልሳለሁ። ደግሞም በሌላ ጊዜ
ተመሳሳይ የሆነ ጥያቄ ለሚያነሱ ሰዎች ይጠቅም ዘንድ በማሰብ በትምህርት መልኩ መቀመጥ እንዲችን
የተለያዮ ሕጎችን ፍቺዎችንም እንደቃሉ በመለከት ላይ አስተምራለሁ። በሚቀጥለው መለከት ቁጥር ሁለት ላይ
የእግዚአብሔር ሕግ ለምን፣ ለማንና በማን እንደተሰጠ የሚለውንና የእግዚአብሔር ሕግና የሙሴ ሕግጋት አንድ
እንደሆኑ እንመለከታለን። እከዚያው ድረስ እነዚህን ጥቅሶች እናሰላስል፦ መዝሙረ ዳዊት 119 በሙሉ
“የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን
ጠቢባን ያደርጋል።” መዝሙር.19፥7
“ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው
አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።”
ዕብ.8፥10
“መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ
ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥”
ዕብ.10፥15-16
“ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን
ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤” ራእይ.12፥17
www.tlcfan.org 4
መለከት #1
www.tlcfan.org 5