You are on page 1of 22

ከጥቅምት 20- 26

6ኛ ትምህርት
የውይይት መምሪያ
Oct 30-Nov 5

ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?

ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሣምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉትን
ጥቅሶች ያንብቡ፡ ዘዳ. 4:1–9፣ ማቴ. 15:1–9፣ ዘኁ.
25:1–15፣ 1ቆሮ. 10:13፣ ዘዳ. 4:32–35፣ ማቴ.
5:13–16።
የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ “ ‘ዛሬ እኔ በፊታችሁ
እንዳስቀመጥሁት ሕግ ያለ ጽድቅ የሆነ ሥርዓትና ሕግ
ያሉት ሌላ ታላቅ ሕዝብስ ማነው?’ ” (ዘዳ. 4፡8)።

የ ዘዳግም መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕራፎች


ሕዝቡ ከታሰበው ነጥብ እስኪደርስ ያለፈባቸውን
መንገዶች ቁልጭ አድርገው ከማስቀመጣቸው አኳያ
እንደ ታሪክ መማሪያ ድርሳን መቆጠር ይችላሉ። ምዕራፍ
አራት ስንገባ፣ የታሪኩ ትምህርት በአብዛኛው የስብከት
ቅርጽ እንደ ያዘ እንመለከታለን። እነዚያን ያለፉ ክስተቶች
መንገር ያስፈለገው በታሪክ ላይ ትኩረት ለማድረግ ብቻ
ሳይሆን፣ ይልቁንም በሕዝቡ መካከል የሚሠራውን
የእግዚአብሔር ኃይል እና ጸጋ ለማሳየት ጭምር ነው።
ምንም እንኳ እነዚህ ሕዝቦች ከአምላካዊው ፈቃድ
ቢያፈነግጡም፤ ጌታ ግን ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን
እያከበረ ነበር።

ምዕራፍ አራት የሚጀምረው “አሁንም” በሚል ቃል ነው።


እነዚህ ሕዝቦች የቅርብ ጊዜ ታሪካቸውን ገምግመው
ነበር፣ “አሁንም” እግዚአብሔር እነርሱን ወደዚህ ደረጃ
ለማምጣት ያደረጋቸውን በማስታወስ አድርጉ የሚላቸውን
ለማድረግ (ዘዳ. 10፡12) እየተጠባበቁ ነበር። “አሁንም”
ከሚለው ቃል ቀጥሎ የሚመጣው የመጀመሪያው ግሥ
የዕብራውያኑ “ሽማ” ወይም ስማ ሲሆን፤ ጥቅም ላይ
የዋለበት ቅርጽ በመላው የዘዳግም መጽሐፍ በተደጋጋሚ
ከቀረበው “ሽማ” (ስማ ወይም ታዘዝ) ጸሎት ጋር
ተመሳሳይ ነው። በመሆኑም ምዕራፉ እንዲህ ሲል
ይጀምራል፡ አሁንም እስራኤል፣ እኔ ላንተ ካደረኩልህ
የተነሣ እነዚህን መታዘዝ ይኖርብሃል…

እሁድ ጥቅምት 2 Oct 2

አትጨምርበት፣ አትቀንስለትም

ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡1-2። ጌታ “ሥርዓትና ሕጉን”


አስመልክቶ የሰጣቸው ግልጽ ማስጠንቀቂያዎች ምንድን
ናቸው? ማስጠንቀቂያዎቹ ተከታትለው የተሰጧቸው ለምን
ነበር? (ዘዳ. 12፡32)።

ጌታ “ሥርዓትና ሕጉን” እንዲታዘዙ--እንዳይጨምሩበት፣


እንዳይቀንሱለት ይነግራቸዋል። ለምን እንዲህ አለ?
ለመሆኑ ማንም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሕግ ለመለወጥ
ለምን ይፈልጋል? በእርግጥ መልሱን እናውቃለን።
“ሰይጣን የእግዚአብሔርን ሕግ ለመለወጥ በሰማይ
የጀመረውን ሥራ በጽናት ገፍቶበታል። የእግዚአብሔር ሕግ
የተሳሳተና መከለስ የሚያስፈልገው ነው ሲል ከውድቀቱ
አስቀድሞ በሰማይ ይዞት ብቅ ያለውን ንድፈ ሀሳብ
ዓለምን ለማሳመን ተሳክቶለታል። ራሳቸውን ክርስቲያን
ብለው የሚጠሩ ብዛት ያላቸው አብያተ ክርስቲያኖች
በቃላቸውም ባይሆን ባመለካከታቸው ተመሳሳይ ስህተት
መቀበላቸውን እያሳዩ ይገኛሉ”—Ellen G. White,
Selected Messages, Book 2, p. 107. ስለ
ጥንታዊቷ እስራኤል ስናስብ ሕዝቡ በተደጋጋሚ ችግር
ውስጥ ሲወድቅ እንመለከታለን። ይህ የሆነው የሕጉን
ድንጋጌዎች ችላ በማለታቸው ብቻ ሳይሆን ከሕጉ ሸርተት
እያሉ አተገባበር ላይ ያልተጠቀሱ ነገሮችን
በመጨማመራቸውና ውሎ አድሮ በመተላለፋቸው ነበር።

ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 15፡1-9። ምንም እንኳ በሌላ


ዐውድ ቢቀርብም፣ ሙሴ የእስራኤል ልጆችን አስመልክቶ
ማስጠንቀቂያ የሰጠበትን መርኅ ምሳሌ እንዴት
እንመለከተዋለን?

ዕብራውያኑ በስተ መጨረሻ ቃል የተገባላቸውን ምድር


ሲወርሱ፣ እንደ ጣኦት አምልኮ በመሳሰሉ ዙሪያ
የተሰጣቸውን ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያዎች በተደጋጋሚ
ችላ ይሉ ነበር። ይህን ተከትሎ እንዲያውም አንዳንዴ
ያሕዌን ያመለኩ ያህል ብዛት ያላቸውን መደበኛ የባዕድ
አምልኮ ሥርዓቶች ይተገብሩ ነበር። የሱስ ወደዚህ ምድር
በመጣበት ወቅት ሁሉንም ዓይነት ሰብዓዊ ወግ
በአምላካዊው አስተምህሮ ላይ ጨምረው ስለነበር የሱስ
ራሱ “የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ” ብሏቸዋል። ያም
ሆነ ይህ፣ በሕጉ ላይ በመጨመራቸው ወይም
በመቀነሳቸው አምላካዊው ድንጋጌ ተቀየረ፤ ይህን ተከትሎ
የሚመጣውን መመዘዝ መቀበላቸው ደግሞ የግድ ነበር።
እግዚአብሔር አድርጉ ካለው ውጪ እንዳንጨምር
እንዳንቀንስ እንዴት ልንጠነቀቅ እንችላለን?

ሰኞ ወይም ጥቅምት 2 Oct 2

ብዔል ፌጎር

በዘዳ. 4፡3-4--የእስራኤል ልጆች ስላለፈው ጊዜ


እንዲሁም ከዚህ ታሪክ ሊማሯቸው የሚገቡ ትንቢታዊና
ተግባራዊ እውነቶችን ለማስታወስ የሚያስችል ተጨማሪ
የታሪክ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡
ዘኁ. 25፡1-15። ምን ተከሰተ? ሕዝቡ ከዚህ ውድቀት
ምን ዓይነት መንፈሳዊ እና ተግባራዊ እውነቶችን መውሰድ
ነበረበት?

ምንም እንኳ እስራኤላውያን አንዳንድ አጎራባቾቻቸው


የነበሩ አረማዊ ብሔራትን ጠራርገው እንዲያጠፉ
የተሰጧቸው ትእዛዞች ብዙም ምቾት ባይሰጡንም፣ ነገር
ግን ይህ ክስተት ከትእዛዙ በስተጀርባ ያለውን አመክንዮ
ለመግለጽ እንደሚረዳ ጥርጥር የለውም። እስራኤል
ዙሪያዋን ለከበቧት አረማዊ ሕዝቦች--የእውነተኛውና
ብቸኛው አምላክ ምስክር መሆን ነበረባት። የእውነተኛውን
አምላክ አምልኮ ገጽታ በማሳየቱ ረገድ ምሳሌ መሆን
ነበረባቸው። እነርሱ ግን ከዚህ ይልቅ በዙሪያቸው ከነበሩ
አረማውያን “አማልክት” ጋር በመጣበቅ በዚህ ዓለም
ከሚወክሉት ብቸኛው አምላክ ላይ አመጻ በማድረጋቸው
ተደጋጋሚ ውድቀት ደረሰባቸው።

ምንም እንኳ “ማመንዘር” የተሰኘው ቃል ብዙውን ጊዜ


መንፈሳዊ ትርጉም ቢኖረውም፣ እስራኤል አረማዊ
አማልክትንና ልማዶችን ተከትላ ሄዳለች (ሆሴ 4፡12-
14)፣ ይህን ሁኔታ አስመልክቶ ቋንቋው (እና የተቀረው
ታሪክ) እንደሚጠቁመው ቢያንስ በመጀመሪያ ላይ
የዝሙት ኃጢአት ተሠርቶ ነበር። እዚህ ላይ እንደገና፣
ሰይጣን በኃጢአት የወደቀውን ሰብዓዊ ተፈጥሮ
ተጠቅሞ፣ ራሳቸውን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የፈቀዱ
ጣኦት አምላኪ ሴቶች-ወንዶቹን እንዲያማልሉ ማድረጉ
ግልጽ ነው። አካላዊ ምንዝር ወደ መንፈሳዊ ምንዝር
ሊያመራ መቻሉ እሙን ነው። በዚህ ጉዳይ ተሳታፊ የነበሩ
ሰዎች ከጊዜ በኋላ በጣኦት አምልኮ ወጥመድ ውስጥ
በመውደቃቸው “እስራኤል ብዔል ፌጎርን በማምለክ
ተባበረ”። ከዚህ ሐሰተኛ አማልክት ጋር በመጣበቅ
አልፈው ተርፈው መሥዋእት እስከ ማቅረብ ደረሱ።
ምንም እንኳ ብዙ ነገሮች የተማሩና የተነገራቸው
ቢሆንም፣ በስሜት እና ፍትዎት ሙቀት ተነድተው እንደ
አልባሌ የትም ሊጥሉት ፈቀዱ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ልቦናቸውን በመጀመሪያው አካላዊ ኃጢአት ስላደነደኑት
በሁለተኛው ማለትም የሰይጣን የመጨረሻ ግብ በሆነው
በመንፈሳዊው ለመውደቅ ጊዜ አልወሰደባቸውም።
አብልጠው ከመርከሳቸው የተነሣ፣ በጥቅሱ እንደ
ቀረበው የእስራኤል ማኅበር ከሙሴ ጋር በመገናኛ
ድንኳን ደጃፍ ስለ በደላቸው እያለቀሰ እያለ አንድ
እስራኤላዊ እነርሱ እያዩት ምድያማዊት ሴት ይዞ መጣ።
አእምሮአችን እና አካላችን በጥብቅ የተሳሰረ ነው። አንዱን
የሚነካው ነገር ሌላኛውንም ይነካዋል። የሥጋን ፈቃድ
መከተል ምን ያህል መንፈሳዊውን ማንነት
እንደሚያቃውስና አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ከዚህ ታሪክ
ምን እንማራለን?
ማክሰኞ ጥቅምት 2 Oct 2

ከጌታ አምላክ ጋር መጣበቅ

ከብዔል ፌጎር ጋር ኃጢአት የሠሩ በሺህ የሚቆጠሩ


ሰዎች ሞቱ። “ብዔል ፌጎርን የተከተሉትን ሁሉ
አጥፍቷቸዋል።” ሆኖም ብዙዎች ክህደቱን አልተከተሉም
ነበር። ለመሆኑ ያልተከተሉት እነማን ናቸው?
“አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁት እናንተ
ሁላችሁ ግን ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት አላችሁ።”
(ዘዳ. 4፡4)። ጥቅሱ በኃጢአት በወደቁ እና ባልወደቁ
መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት ያብራራል? ስለ ኃጢአት፣
ስለ ፈተና እና እግዚአብሔር በሕይወታችን ስላለው ኃይል
የቀረበልን አስፈላጊ መልእክት ምንድን ነው?
በዚህ ጥቅስ “ሁላችሁ” በሚል የቀረበውን ቃል፣ “ሁሉ”
በሚል ከቀረበው ቁ. 3 ጋር ያስተያዩ። ብዔል ፌጎርን
የተከተሉትን “ሁሉ” አጥፍቷቸዋል። ከእግዚአብሔር ጋር
የተጣበቃችሁ እናንተ “ሁላችሁ” ግን ይኸው እስከ ዛሬ
በሕይወት አላችሁ። በዚያን ወቅት መሃል ሰፋሪ
እንዳልነበረ ሁሉ እነሆ ዛሬም አይኖርም። የየሱስ ከመሆን
ወይም ካለመሆን ውጪ ሌላ አማራጭ የለም (ማቴ.
12፡30)። “ድብቅ” (dbq) በሚል የቀረበው
የዕብራይስጡ ቃል ጥብቅ ማለት፣ መጣበቅ የሚል ፍቺ
ያለው ሲሆን ብዙውን ጊዜ ከግል ማንነት ውጪ የሆነ
ነገርን በጥብቅ መከተልን እንዲሁም ጠንካራ
ቁርጠኝነትን ያመለክታል።

በዘፍ. 2፡ 24 የቀረበው ይኸው የዕብራይስጥ ቃል ሰው


እናትና አባቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣበቃል በሚል
ጥቅም ላይ ውሏል (በተጨማሪ፡ ሩት 1፡14)። ቃሉ
በተመሳሳይ ዐውድ በኦሪት ዘዳግም አራት ጊዜ ቀርቧል
(ዘዳ. 10፡20፣ ዘዳ. 11፡ 22፣ ዘዳ. 13፡4፣ ዘዳ.
30፡20)። እነዚህ ሕዝቦች ከእግዚአብሔር ጋር በመጣበቅ
ራሳቸውን ለእርሱ ሰጥተው ኃይልና ብርታት መቀበል
ነበረባቸው። እዚህ ላይ ማስታወስ የሚያስፈልገው ነጥብ
ሕዝቡ ራሱ የቃሉ ርዕሰ ጉዳይ መሆኑን ነው። ከእርሱ
በሚያገኙት ኃይል እና ብርታት ኃጢአትን መቋቋም ይችሉ
ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር “ለመጣበቅ” መምረጥ
ይኖርባቸዋል። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ መሳፍ. 24 እና 1ቆሮ.
10፡13። በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ እየተባለ ያለው ነገር
ምንድን ነው? መልእክቱ በዘዳ. 13፡4 መኖሩንም ልብ
ይሏል።

እግዚአብሔር የታመነ አምላክ እንደመሆኑ ከመውደቅ


ሊጠብቀን ይችላል። ይሁን እንጂ ታማኞች ብዔል ፌጎርን
ትተው ከእግዚአብሔር ጋር እንደተጣበቁ ሁሉ እኛም ንቁ
ምርጫ ልናደርግ ይገባል። ይህ ከሆነ ምንም ዓይነት ፈተና
ቢገጥመንም እንኳ በታማኝነት መጽናት እንችላለን። እንደ
ጸሎት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ አምልኮ እና ሕብረት ያሉ
ቁልፍ ነገሮች ከጌታ ጋር እንድንጣበቅ እንዴት ይረዱናል?

ረቡዕ ጥቅምት 2 Oct 2

ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?

በዘዳ. 4:4 የቀረበውን መልእክት ተከትለው የሚመጡት


ጥቂት ቁጥሮች በቅዱሳት መጻሕፍት ከምናገኛቸው ሁሉ
በእጅጉ ጥልቀት ያላቸውና ውበት የተላበሱ ናቸው። አንድ
ሰው--የዘዳግም መጽሐፍ አንኳር መልእክት የሚገኘው
በዚህ ስፍራ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሌላው ሁሉ ሐተታ ነው
ብሎ ሊሞግት ይችላል። እነዚህን ጥቅሶች ሲያነቡ፤ በዚህ
ስፍራ የቀረበው መርኅ ለእኛም ተግባራዊ ሊሆን
ስለሚችልባቸው የተለያዩ መንገዶች ያስቡ። ጥቅሶቹን
ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡5-9። ጌታ ለእስራኤል ያደረገውን በዚያ
መልኩ በሙሴ በኩል የተናገረው ለምንድን ነው?

ጌታ ሕዝቡ መጠራቱንና ለተለየ ምክንያት መመረጡን


እንዲገነዘብ ይፈልጋል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ
አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር ሲጠራው “ ‘ታላቅ ሕዝብ
አደርግሃለሁ’ ” (ዘፍ. 12፡2፣ ዘፍ. 18፡18) ብሎ ነግሮት
ነበር። እነርሱን ታላቅ ሕዝብ የማድረጉ ዓላማ “በምድር
የሚኖሩ ሕዝቦች” በእነርሱ አማካይነት “እንዲባረኩ” (ዘፍ.
12፡3) ነው። ምንም እንኳ የመጨረሻው በረከት መሲሑ
የሱስ በእነርሱ የትውልድ ሀረግ መምጣቱ ቢሆንም፤
እስከዚያው ግን ለዓለም ብርሃን መሆን ነበረባቸው። “ ‘
“ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ
ብርሃን አደርግሃለሁ” ’ ” (ኢሳ. 49፡6)።
ደኅንነት በእነርሱ መገኘት ስለነበረበት ሳይሆን፣ ነገር ግን
ብቻውን ሊያድን የሚችለው እውነተኛው አምላክ በእነርሱ
አማካይነት መገለጥ ስለነበረበት ነው። እስራኤል
ሰማያትንና ምድርን የፈጠረውን አምላክ እያመለከና
እያገለገለ ነበር። በአንጻሩ አረማውያን ለዐለት፣ ለድንጋይ፣
ለእንጨት እና አጋንንት ይሰግዱ ነበር (ዘዳ. 32፡17፣
መዝ. 106፡37)።

እንዴት ያለ ልዩነት ነው! በእነዚህ ቁጥሮች ሙሴ


እስራኤልን ልዩ የሚያደርገውን ሁለት ነገሮች ጠቁሟል።
አንደኛው፡ ጌታ በዓይነቱ እጅግ ልዩ በሆነ መንገድ
በመቅደሱ አማካይነት አጠገባቸው በመሆኑ--ሁለተኛው
ደግሞ “ጻድቅ የሆነ ሥርዓትና ሕግ” በፊታቸው
በማስቀመጡ ነበር። ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡32-
35። ሕዝቡ የተለየ ጥሪ እንደቀረበለት ይገነዘብ ዘንድ ጌታ
ምን ተጨማሪ ነገር እየነገራቸው ነበር?
እስራኤል እጅግ ብዙ የተቸረው ሕዝብ መሆኑ ምንም
አያጠያይቅም። ጥያቄው፡ አሁን ምላሻቸው ምን
ይሆናል?--የሚል ይሆናል።

ሐሙስ ጥቅምት 2 Oct 2

ጥበበኛነታችሁ እና አስተዋይነታችሁ

ቀደም ብለን በዘዳ. 4፡1-9 የተመለከትነው መግለጫ


የሕዝቡን የተለየ ማንነት ብቻ ሳይሆን ለሌላው ሁሉ ብርሃን
እንዲሆን መጠራቱን ጭምር አስነብቦናል። መታዘዝ፣
መከተል እና ጌታ ያዘዛቸውን ማድረግ--በእነዚህ ጥቅሶች
ሁሉ ድርና ማግ ሆነው የተሸመኑ ጽንሰ ሀሳቦች ናቸው።
ጥቅሱን በድጋሚ ያንብቡ፡ ዘዳ. 4፡6። ጌታ ይህ
“ጥበባችሁንና ማስተዋላችሁን” ለሌሎች ሕዝቦች
ይገልጣል ሲል በተለይ ምን ማለቱ ነው?
በመጀመሪያ ሲታይ ሥርዓትና ሕጎቹ ራሳቸው ጥበብ እና
አስተዋይነት የያዙ ይመስላል። ነገር ግን ጥቅሱ እንደዚያ
አይልም። እርግጥ ነው፤ ጌታ ሥርዓትና ሕግ
አስተምሯቸዋል። ነገር ግን ጥበበኝነታቸው እና
አስተዋይነታቸው የመጣው እነርሱን ከመጠበቃቸው እና
ከመታዘዛቸው ነው። መታዘዛቸው-ጥበባቸው እና
አስተዋይነታቸው ነበር። እስራኤል ዓለም አይቶት
የማያውቅ እጅግ ድንቅ የሕግ ሥርዓት፣ ደንብ እና
መመሪያ ሊኖረው ይችል ነበር (በእርግጥ ኖሮታል)፤ ነገር
ግን እስራኤል ካልተከተለው ምን ይረባዋል? ይልቁንም
ጥበበኛነታቸው እና አስተዋይነታቸው የመጣው
የእግዚአብሔር ሕጎች በተጨባጭ በሕይወታቸው
መገለጣቸውን ተከትሎ ነው። ጌታ በሰጣቸው እውነቶች
ሊኖሩ የተገባ የነበረ ሲሆን፤ ያን ማድረግ የሚችሉት
ደግሞ እነርሱኑ በመታዘዝ ብቻ ነበር። እስራኤል በዚያ
እውነት መሠረት ባይመላለስ ኖሮ፣ ያ ሁሉ ብርሃንም ሆነ
እውነት ለእነርሱም ሆነ በዙሪያቸው ለነበሩ አረማውያን
አንዳችም ጠቀሜታ ባልኖረው ነበር።

በመሆም ለሥርዓትና ሕጎቹ የመታዘዛቸው ቁም ነገር፣


ለዓለም ምስክር መሆናቸው ላይ ስለ ነበር ሥርዓትና
ሕጎቹን እንዲታዘዙ ተደጋጋሚ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
“የእግዚአብሔርን ሕግ መታዘዛቸው በዓለም
መንግሥታትና ሕዝቦች ፊት አስደናቂ ብልጽግና
ያጎናጽፋቸዋል። በሁሉም ዘርፍ በብልሃት የተሞላ ጥበብና
ችሎታ ሊሰጣቸው የሚችለው እርሱ መምህራቸው ሆኖ
ይቀጥላል። ሕጉን በመታዘዛቸው የተከበሩና ከሁሉ ልቀው
የሚታዩ ያደርጋቸዋል። የሚታዘዙ ከሆነ ሌሎች ብሔራትን
ከሚያጠቁ በሽታዎች ይጠበቃሉ፣ የብሩህና አስተዋይ
አእምሮ ባለቤት በመሆንም ይባረካሉ። የእግዚአብሔር
ክብር፣ ግርማ እና ኃይል በብልጽግናቸው ሁሉ መገለጥ
ነበረበት። የካህናት እና ልዑላን ግዛት ባለቤት መሆን
ነበረባቸው። በምድር ላይ ታላቅ ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ
እግዚአብሔር የእያንዳንዱ ክህሎት ባለቤት አድርጎ
ቸራቸው።”—Ellen G. White, Christ’s Object
Lessons, p. 288.

ጥቅሶቹን ያንብቡ፡ ማቴ. 5፡13-16። የሱስ ለጥንት


እስራኤላውያን የነገራቸውን በሚያንጸባርቅ መልኩ ዛሬ
በተመሳሳይ ለእኛ ምን እያለን ነው? እንደ ሰባተኛ ቀን
የዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂነታችን በተለይ ለእኛ እንዴት
በሥራ ላይ መዋል ይችላል?

አርብ ጥቅምት 2 Oct 2

ተጨማሪ ሀሳብ

“በሰማይ ታላቁ ተቃርኖ ከተነሣበት ከመጀመሪያ ጊዜ


አንስቶ የሰይጣን ዓላማ የእግዚአብሔርን ሕግ መሻር
ነበር። ይህን ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በፈጣሪ ላይ
አመጸ። ምንም እንኳ ከሰማይ ቢጣልም ተመሳሳይ ውጊያ
በምድር ማድረጉን ቀጠለ። ሰዎችን አስቶ አምላካዊውን
ሕግ እንዲጥሱ መምራት በጽናት የገፋበት ዓላማው ነበር።
ሕጉን ሙሉ በሙሉ ወደ ጎን ገሸሽ ማድረግም ይሁን ከሕጉ
አንዱን መቃወም ዞሮ ዞሮ ውጤቱ ተመሳሳይ ነው። ‘ሕግን
ሁሉ የሚፈጽም፣ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ቢኖር፣
ሁሉን እንደ ተላለፈ ይቆጠራል።’ (ያዕ. 2፡10)” —Ellen
G. White, The Great Controversy, p. 582.

ኤለን ኋይት ብዔል ፌጎርን አስመልክታ የሚከተለውን


ጽፋለች፡ “እስራኤላውያን በተከለከው ምድር ላይ አንድነት
በመፍጠር በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ወደቁ።
በሙዚቃውና በዳንሱ ተማልለውና በባዕድ ህዝቦች ጣኦት
ውበት ተስበው ለእግዚአብሔር ያላቸውን ታማኝነት
አጎደሉ። ግብዣውንና ፈንጠዝያውን ሲቀላቀሉ የወይን
ጠጁ አእምሮአቸውን ጋረደውና ራሳቸውን መቆጣጠር
ተሳናቸው። ከዚህ በኋላ የሥጋ ስሜታቸው ሙሉ ለሙሉ
ተቆጣጠራቸው። ሕሊናቸው በእርክስና ስለጎደፈ
ለጣኦቶቻቸው አጎንብሰው ሰገዱ። በአረማውያኑ
መሠዊያዎች ላይ መሥዋዕት በማቅረብ እጅግ በረከሰው
የባዕድ አምልኮ ሥርዓት ተሳታፊ ሆኑ።” (የኃይማኖት
አባቶች እና ነቢያት ቅጽ 2፤ ገጽ፡ 93።)

የመወያያ ጥያቄዎች:

1.እኛን የሰባተኛ ቀን ዳግም ምጽአቱ ተጠባባቂዎች


በጥንቷ እስራኤል ቦታ አድርገው ያስቡ። በዙሪያችን
ካለው ዓለም ብሎም ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት
በተቃራኒ ስለተሰጡን ነገሮች ያስቡ። ለእኛ የሚቀርበው
ጥያቄ፡ ለተሰጡን ነገሮች ምን ዓይነት ምላሽ እየሰጠን
ነው? “ጥበበኝነታችንንና አስተዋይነታችንን” ምን ያህል
በዓለም ፊት እያሳየን ነው?--የሚል ይሆናል።

2.“አምላካችሁን እግዚአብሔርን የተከተላችሁት እናንተ


ሁላችሁ ግን ይኸው እስከ ዛሬ በሕይወት አላችሁ።”
እግዚአብሔርን የተከተላችሁ ወይም ከእርሱ ጋር
የተጣበቃችሁ በሚል የቀረበው የጉዳዩ ባለቤት ሕዝቡ
ነው። ጌታ በኃይል ከራሱ ጋር እንድንጣበቅ
አያስገድደንም። ይልቁንም በሰጠን ቅዱስ የመምረጥ
ነጻነት አማካይነት ከእርሱ ጋር ለመጣበቅ ምርጫ
እናደርጋለን። አንዴ ያንን ምርጫ ካደረግን በኋላ እርሱን
የምንከተለውና ከእርሱ ጋር የምንጣበቀው እንዴት ነው?

3.በእሁድ ጥናት መጨረሻ በቀረበው ጥያቄ ላይ ትኩረት


ያድርጉ። በእግዚአብሔር ትእዛዛት ላይ መጨመር ወይም
መቀነስ ማለት ምን ማለት ነው? በገሃድ ከቀረበው ውጪ
ለምሳሌ ሰንበትን ለመለወጥ መሞከር--ብዙም ልብ
ሳንለው በረቀቀ አኳኋን ተግባራዊ መሆን የሚችለው
እንዴት ነው?

You might also like