You are on page 1of 16

Longing for GOD

የመጀመሪያ ዓመት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት


ጥያቄዎች
ጥናት አንድ፡-ህብረት
መዝ 133፤1-3 1 ኛ ጴጥ 4፤7-11 ዕብ 10፤25
1. መዝ 133፤1-3 የወንድሞችን ህብረት ከሁለት
ክስተቶች ጋር ያመሳስለዋል፡፡እነዚህ በምሳሌነት
የተጠቀሱ ክስተቶች ምንና ምን ናቸው?
2. ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ ማለት ምን
ማለት ነው?የክህነት ሽቶ እና የአርሞንኤም ጠል
ከወገኖች ህብረት ጋር በምን መልኩ አመሳሰለው?
3. በ 1 ኛ ጴጥ 4፤10 ላይ ደጋግ መጋቢዎች የተባሉት
እነማን ናቸው?ከምን የተነሳ መጋቢ ተባሉ?
4. ፍቅር የሐጢያትን ብዛት(1 ኛጴጥ 4፤8) እንዴት
መሸፈን እንደሚችል አብራራ፤
5. በዕብ 10፤25 መሰረት ከወገኖች ጋር ህብረት
ስለማድረግ ምን ወሰንክ?
ጥናት ሁለት ፡-በአንዳች አትጨነቁ
ፊል 4፤4-9
1. ጳውሎስ ለፊልጲስዮስ ሰዎች በምን አይነት
ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ነው ይህንን መልዕክት
የፃፈላቸው?በዚህ ጥቅስ መሰረት እነዚህ ሰዎች
ምን እንዲሆኑ ይመክራቸዋል?
2. በጌታ ደስ መሰኘት(ፊል 3፤1) እና በአንዳች
አለመጨነቅ ያላቸውን ዝምድና አብራራ፤
3. የጭንቀት መንስኤው የእምነት መጉደል መሆኑን
መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡የእምነት መጉደል ደግሞ
በሮሜ 14፤23 መሰረት ሐጢያት ነው፡፡አንተስ ምን
ታስባለህ?
4. በሚያስጨንቅ ነገር ውስጥ የኛና የእግዚአብሔር
ድርሻ ምንድነው?አዕምሮንም ሁሉ የሚያልፍ
ሰላም ሲል ምን ማለቱ ነው?ፊል 4፤7
5. በቁ.8 ላይ እንድናስባቸው የተዘረዘሩ ነገሮች ካለ
መጨነቅ ጋር ያላቸው ዝምድና ምንድን ነው?
አንተስ ስላለመጨነቅ ምን ወሰንክ?

ጥናት ሶስት፡-ህልውናውን መናፈቅ


መዝ 63፤1-11
1. ዳዊት ያለበትን ሁኔታ፡እየደረሰበት ያለውን
ችግርና የሚፀልየውን ፀሎት እያነፃፀርክ አብራራ፤
2. ህልውናውን መናፈቅ/የእግዚአብሔርን መገኘት
መናፈቅ/ ማለት ምን ማለት ነው?ያ ናፈቆትስ
በምን መልክ ሊገለፅ ይችላል?
3. ዳዊት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ስለ ህልውና
መፀለዩ ስለ ህይወት ተለምዶአዊ ያልሆነ ትርጉም
እንዳለው ያሳያል፡፡አሁን ባለህ አቋም በዳዊት ቦታ
ብትሆን ምን ምታደርግ ይመስለሃል?
4. ከእግዚአብሔር ፊት ረጅም ጊዜ ስትርቅ ምን
አይነት የስሜት ለውጥ ያመጣብሃል?
5. ህልውናውን የመናፈቅ ተግዳሮቶች ምን ምን
ናቸው?ከእነዚህ ተግዳሮቶች አልፈህ የመናፈቅ
ሂወትን እንዴት ልታስቀጥል ወሰንክ?

ጥናት አራት፡-ፀሎት
ዳን 6፤3-23 1 ኛ ተሰ 5፤17
1. የፀሎት ትርጉም በአንተ እንዴት ይታያል?
2. በዳንኤል ላይ የተገኘ ሰበብ ፀሎት ብቻ እንደነበር
ሁሉ በምንም ሁኔታ ውስጥ መፀለይ እንደሚቻል
ያስተምረናል፡፡በ 1 ኛ ተሰ 5፤17 ላይ ጳውሎስ
ሳታቋርጡ ፀልዩ ሲል ምን ለማለት ፈልጎ
ይመስልሃል?
3. ስለሚያሳድዱን እና ስለሚጠሉን ሰዎች መፀለይ
በአንተ እይታ ምን ይመስላል/ማቴ 5፤44-45/?
ጳውሎስ በብዙ ቦታ ፀልዩልን፣ስለእናንተ
እፀልያለሁ፣ይፀልዩልን ዘንድ ሲል ምን
ሊያሰተምረን ወዶ ነው?
4. የፀሎት መሰናክሎች ምን ምን ናቸው?
5. ከላይ የተዘረዘሩት መሳናክሎች ተቋቁሞ የግል
የፀሎት ጊዜን በቋሚነት መያዝ ይቻላል?በዳንኤል
ህይወት ካየኸው ምን ትወስናለህ?
ጥናት አምስት፡-በእግዚአብሔር መታመን
ኢሳ 40፤27-31 ኢሳ 30፤18 መዝ 37፤9
1. እግዚአብሔርን እንዳናስብ የሚያደርጉ ብዙ
ነገሮች ገጥመውን እግዚአብሔር ያላየ ወይም
የተወን ሲመስለን የሚሰማ ስሜት ምን አይነት
ነው?
2. ነብዩ የእስራኤል ሰዎች ላነሱት ቅሬታ የሰጠው
መልስ ያሉበትን ሁኔታ እንዴት ሊያስረሳቸው
ይችላል/ኢሳ 40፤28-29/?
3. ስለ መተማመን ከመነሳቱ በፊት በቁ.28 ላይ
የተገለፁትን የእግዚአብሔር ማንነት መገለጫዎች
በቁ.29 ከተገለፀው አሰራሩ ጋር እንዴት
እንደሚያያዝ አብራራ፤
4. እግዚአብሔርን በመተማመን ሲል እንዲሁ
ከመጠበቅ ጋር ምድነው
ሚለየው፤”እግዚአብሔርን በመተማመን
የሚጠባበቁ” ተብለው የተጠቀሱ ሰዎች
“ብላቴኖች እና ጎበዛዝት” ተብለው ከተገለፁት
ጋር በምን መልኩ ነው የተነፃፀሩት?
5. በራሳቸው ብርቱ ወይም ጎበዝ ከሚባሉ ሰዎች
አንተን የሚለይህ ነገር ምንድነው?በእግዚአብሄር
ስለመታመንስ በመጪው ዘመን ምን ልታደርግ
ወስነሃል?

ጥናት ስድስት፡-እግዚአብሔር በህይወታችን


ላይ ያለው አላማ
ኤፌ 3፤14-21 1 ኛ ጢሞ 2፤3-4
1. የምትኖርለት አላማ ያለህ ይመስልሃል?ካለህ
የመኖርህ አላማ ምንድነው?የእግዚአብሔርስ
አላማ/ፍላጎት በሰው ልጆች ላይ ምንድነው?
2. ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች የሚፀልይላቸው
ምን እንዲሆኑ ነው/ኤፌ 3፤16-18/?የዚህስ
የመጨረሻ ግቡ ምንድነው ቁ 19፤?
3. ስለፍቅርና ስለሀይል ምን እንማራለን?
4. ወደ እግዚአብሔር ፍፁም ሙላት መድረስ
ወይንም በክርስቶስ ሙላት መሞላት ማለት ምን
ማለት ነው/ቆላ 2፤9-15/?
5. እንደ አማኝ እግዚአብሔር ለህይወትህ ስላለው
አላማ ምን ተረዳህ?አሁን ካለህበት የደቀ
መዝሙርነት ህይወት ደረጃ ጋር ይህንን
ስታነፃፅረው ምን ማድረግ እንዳለብህ ትገነዘባለህ?

ጥናት ሰባት፡- ጓደኝነት እና የፍቅር


ህይወት
2 ኛ ቆሮ 6፤14 2 ኛ ቆሮ 7፤1 መሐ 8፤6
መክ 3፤1
1. ለአንድ አማኝ ከአህዛብ ጋር ያለ ጓደኝነት በምን
መልኩ መሆን እዳለበት ታስባለህ?
2. የማይመች አካሄድ ሲል ምን ማለቱ ነው?
3. ስለ ፍቅር ግንኙነት ምን ታስባለህ ?ለፍቅር
አመቺ ነው ሚባል ወቅት እና ዕድሜ ይኖራል
ብለህ ታስባለህ?አሁን ባለህበት ሁኔታ ፍቅር
ውስጥ ብትገባ ምን አይነት ጥቅም እና ጉዳት
አለው?
4. ለሁሉ ጊዜ አለው ሲል ምን ማለቱ ነው?ለአማኝ
ከማያምን ጋር የሚኖርን የፍቅር ግንኙነት
ገምግመህ ሚሰማህን ግለፅ፤
5. በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍፁም
እያደረግን ሲል ምን ማለቱ ነው?ከማይመች
አካሄድ በመለየት ለእግዚአብሔር ለመኖር ምን
ወሰንክ?
ጥናት ስምንት፡-የእግዚአብሔርን ቃል በግል
ማወቅ
ኢያሱ 1፤7-9
1. የእግዚአብሔር ቃል ላንተ ምንድነው?
2. በ 2 ኛ ጢሞ 3፤16-17 መሰረት የእግዚአብሔርን
ቃል ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
3. ከአፍህ አይለይ እና በቀንም በለሊትም አስበው
የሚሉት ሀሳቦች ምን ማለት ናቸው?
4. ስለ እግዚአብሔር ቃል ከመስማት ባለፈ በግል
የማወቅ ሂደቶች ምን ይመስሉሃል?
5. በግሌ የእግዚአብሔርን ቃል አውቃለው ብለህ
ታስባለህ፤ካልሆነስ ምን ወስነሃል?
ጥናት ዘጠኝ፡-ተፅዕኖ ፈጣሪነት
ማቴ 5፤13-16
1. ከሌላ ሰው ተፈጥሮብኝ ያዝኩት የምትለው
ተፅዕኖ በህይወትህ ላይ ይኖር ይሆን?ካለ
አዎንታዊና አሉታዊ ብለህ አስቀምጥ፤
2. በዚህ መፅሐፍ ማንነታችንን ከምን ነገሮች ጋር
ነው ያነፃፀረው?ተፅዕኖ ከመፍጠርስ ጋር ያለው
ግንኙነት ምንድነው?
3. በዙሪያህ ባሉ ሰዎች ላይ እንደ ብርሃን እና ጨው
ያለ ለማበላሸት ያልሆነ መልካም ተጽዕኖ በምን
መልኩ መፍጠር ይቻላል ብለህ ታስባለህ፤
4. ወደ ውጪ ተጥሎ መረገጥ ማለት ምን ማለት
ነው?የአማኝን ጨውነት የሚያጠፉት ነገሮች
ምንድን ናቸው?
5. ራስን ማግለል እና በሌሎች ተጽዕኖ ስር መሆን
ለአንድ አማኝ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ
አብራራ፤የራስህንም ውሳኔ ተናገር፤

ጥናት አስር፡-ወንጌልን መመስከር


1 ኛ ቆሮ 9፤19-23 ማር 16፤15 2 ኛ ጢሞ 4፤5
1. ይህን ታላቅ ተልዕኮ ማስፈጸም የማን ሃላፊነት
ይመስልሃል?
2. የወንጌል ሰባኪነትን ስራህ አድርግ ሲል ምን
ማለቱ ይመስልሃል/2 ኛ ጢሞ 4፤5/?
3. በዚህ ክፍል ሌሎችን ይጠቅም ዘንድ እንደ
አይሁድ፣ከህግ በታች እንዳለ፣ህግ እንደሌለው፣እንደ
ደካማ እንደሆነ ያሳየናል፡፡እንደ የሚለው
መስተፃምር ምንን ይገልጻል?
4. የጳውሎስ አይሁድን ለመጥቀም እንደ
አይሁድ፣ህግ የሌላቸውን ለመጥቀም ህግ
እንደሌለው ሆኗል፡፡አንተስ በዙሪያህ ያሉትን
ለመጥቀም ምን አይነት ዋጋ እንደሚያስከፍልህ
ታስባለህ?
5. “በወንጌል ማህበርተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል
ሁሉን አደርጋለሁ” ሲል እንመለከተዋለን፡፡አንተስ
ስለ ወንጌል ምን ለታደርግ ወስነሃል?

ጥናት አስራ አንድ፡-ዘመናዊነት


ዳን 1፤1-17
1. የዘመናዊነት ትርጉም ምንድነው ብለህ ታስባለህ
?
2. እነዳንኤል አሁን ባሉበት አገር እንደ ምርኮ
ካሉባቸው ግዴታዎች አኳያ የተሰጣቸውን ሁሉ
እየበሉና እየጠጡ ለመኖር ሰበብ ነበራቸው፡፡
ዘመናዊነት ላለመቀደስ ምክኒያት ሊሆንባቸው
የሚችሉ መንገዶችን ዘርዝር?
3. መጪውን ዘመን እና ክርስቲያናዊ የአኗኗር
ዘይቤን እንዴት ማስታረቅ ይቻላል ብለህ
ታስባለህ?
4. ባለመገለል ውስጥ ያለ ማህበራዊነትን ዘመን
ከሚያመጣቸው እንግዳ ነገሮች ጋር አስታርቆ
ክርስትናን ለማስቀጠል ከአንድ አማኝ ምን
ይጠበቃል?
5. እንዳትረክስ ልትወስድ ስለሚገባህ እርምጃ ከዚህ
ክፍል ምን ትማራለህ?
ጥናት አስራ ሁለት፡-ቤተ ክርስቲያን
ኤፌ 2፤11-22
1. በዚህ ክፍል መሰረት ቀድሞ የነበርንበት ህይወት
ምን አይነት ነበር?ርቀን የነበረውስ ከምንድነው?
2. ጌታ ኢየሱስ በሞቱ ያፈርሰው የጥል ግድግዳ
የነበረው በማንና ማን መካከል ነው?
3. ከእንግዲህ ወዲህ እንግዶችና መፃተኞች
አይደላችሁም ሲል ምን ማለቱ ነው?አዲስ
የሆነልንስ ነገር ምንድነው?
4. የቤተ ክርስቲያን ባለቤት ማን ነው?የእከሌ እና
የእከሊት ብለን መሰየማችንን እንዴት ታየዋለህ?
በየትኛውም ቦታ የቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም
ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን አካል መሆናችንን
ለማረጋገጥ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?
5. በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አንተ ያለህ ድርሻ
ምንድነው?

You might also like