You are on page 1of 2

የሚከተሉትን ጥያቄዎች እዉነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ

1.የፆታ ትርጉም በሰብዓዊ የተፈጥሮ አካል በሚለይበት ጊዜ ነው?

2.ከማህተበ ድንግልና ስያሜዎች ውስጥ አንዱ ህግ ይባላል?

3.ድንግል የሚለው ስያሜ ለሰው ብቻ የሚሰጥ ስም ነው ?

4.የምንኩስና ህይወት ከታዘዙት በላይ መስራት ነው ?

5.የጋብቻ ስርዓት የሚፈፀምበት መንገድ ምስጢረ ተክሊል ይባላል ?

ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ


1. ከጌታችን አበይት በዓላት ውስጥ የማይካተተው የቱ ነው

ሀ. ጥምቀት ለ. ግዝረት ሐ.ብስራት/ትስብዕት መ. ሆሳዕና

2. በዓለ ጥንተ ስቅለት መቼ ይከበራል

ሀ. ጥቅምት 27 ለ. መጋቢት 27 ሐ.መጋቢት 29 መ. ታህሳት 29

3. የመስከረም አንድ የመታሰቢያ በዓል ያልሆነው የቱ ነው

ሀ. የቅዱስ ዮሀንስ ለ. የፃድቁ ኢዮብ ሐ.የሀዋርያው ጴጥሮስ መ. ሊቀ መላዕክት ራጉኤል

4. ወርሃ ፅጌ የሚባለው ዘመን ከመቼ እስከ መቼ ነው

ሀ. ህዳር 6- ህዳር 30 ለ. መስከረም 26- ህዳር 6 ሐ. መስከረም 1- ጥቅምት 5 መ. መልሱ የለም

5. አሁን የምንጠቀምበትን የዘመን አቆጣጠር ያዘጋጀው ማን ነው

ሀ. ዲሜጥሮስ ለ.ጳውሎስ ሐ. ገማልያል መ. አትናቴዎስ

ለሚከተሉትን ጥያቄዎች በተማራችሁት መሰረት አብራርታለችሁ ፃፉ


6.ቤተክርስቲያን ስለ ፆታ ለምን ታስተምራለች ?

7.ድንግልና እና ማህተበ ድንግልና ያለውን ልዩነት አብራሩ?

8.ምንኩስናን ማለት ምን ማለት ነዉ ?

9.የጋብቻ ትርጉም እና ዓላማ ምንድን ነዉ?

10.ድንግልናቸውን ያልጠበቁ ጥንዶች የሚፈፀምላቸዉ የጋብቻ አይነት ምን ይባላል ?

11.በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የቅዱሳን አሰያየም እንዴት ነው ?4 ቱን ጥቀሱ?

12.ከተማራችሁት የቅዱሳን ትርጉም ዉስጥ 4 ቱን ጥቀሱ ?


13.ዓለምን ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነዉ ?በተመራችሁት መሰረት መልሱ?

14.እራስን ከማሸነፊያ ጥበቦች ዉስጥ 3 ቱን ጥቀሱ ?

15.ሰው እግዚአብሔርን እንዴት መምሰል ይችላል ?

16.ከተማራችሁት የቅዱሳን ሰዎች ምደባ ዉስጥ 4 ቱን አብራርታችሁ ፃፉ ?

17.ስለመላእክት አፈጣጠር የተማራችሁትን ፃፉ ?

18.የቅዱሳን መላእክትን ከተሞቻቸውን ፃፉ?

19.ንዋየ ቅድሳት ማለት ምን ማለት ነዉ ?

20.ቅዱሳት መፃህፍት ለምን ቅዱስ ተባሉ ?

21.መጋቢት 29 ከሚታሰቡ ነገሮች ውስጥ 2 ጥቀስ ?

22. የእመቤታችንን 5 ቱን አበይት በአላት ጥቀስ ?

23. የጌታችን ልደት ለምን ዘንድሮ ታህሳስ 28 ይከበራል?

You might also like