Professional Documents
Culture Documents
12 (Week 1)
12 (Week 1)
ከቡስካ በስተጀርባ
ምእራፍ አንድ
እስከ ገፅ አስራ አንድ ያለውን ገለጣ በወጉ ተረዱት፤ ከዚያም ተከትለው የመጡትን
የማስተዋወቂያ ጥያቄዎች መካከል የፈላጋችሁትን ሦስቱን በመምረጥ ምላሽ ስጡበት
1.እስከ ገፅ አስራ አንድ ባነበባችሁት ገለፃ የደራሲው ሰብእናን እና ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልዕክት
ለመጠቆም ሞክሩ ከሁሉ አስቀድሞ የደራሲውን ሙሉ ስም መፃፍ ይገባል፡፡
2፣ደራሲው በገጽ5 ላይ በመጀመሪያው አንቀጽ ውስጥ የባኞ ቤቱን አጠቃለይ ሁኔታ እንዴት ገለፀው?
ይታዩ ከነበሩትን ውጫዊ ገፅታዎች መካከል አምስቱን ግለፁ
ምእራፍ ሁለት
3.ከሎ ሆራ በልብ ወለዱ ውስጥ የተከሰተ ሁነኛ ገፀ ባህሪይ ነው፤የዚህን የገፀባህሪው ውጫዊና ውስጣዊ
ማንነት መረጃ እየጠቀሳችሁ ገልፁት(ገፅ 14-18)
4.የከሎ ዝምታ እና የስቲቭ ቅብጥብጥነት ለምን ለከርለት አልስማማሽ አላት የሁለቱ ወንዶች ሰብዕና
እንደ ‹‹አራማባና ቆቦ ተመሳሰለ? (ገፅ 18
5.‹‹መማሬን እርሳው››ካርለት ለስቲቭ የሰጠችው ያልተጠበቀ ምላሽ ነው፤ ይህን ያስባለትን መሰረታዊ
ምክንያት ከገፀባህሪያት አደረጃጀት አኳያ በማት ማብራሪያ ስጡ፡፡
6.ከትመህርት ዘርፍ ለከሎ ሰብዕና ቀረፃ ‹‹ከሶሲዮሎጂ ይልቅ የሳይኮሎጂ ተመህርትን ከሎ በእጅግ
ይጎዳል ›› ይህ የሆነበትን መሰረታዊ ምክንያት ምዕራፍ ሁለት በየገፁ አብራርቱዋል፡፡ ለዚህ አባባል
መልሳችሁን መረጃ በመስጠት ለማብራራት ሞክሩ፡፡
ምዕራፍ ሦስት
1. ‹‹አዎ! የከሎ ባህርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው፡፡ እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ
ማዘጋጀት አለብኘ፤›› አለች ካርለት፡፡ (ገጽ 22) ካርለት ይህን ለማለት የበቃችው ለምን ነበር? ይህን
ስትልስ ምን ለማለት ፈልጋ ነው?
2.‹‹ካርለት፡- ከሎን ‹‹ይህች አገር ልምላሜ፣ ውበትና ጥሬ ሀብት ሳያንሳት ቀድማ ነቅታ ምነው ተመልሳ
ተኛች?የእንቅልፍ መድሀኒት ማን አዋጣት? የውስጥ ይሆን የውጭ ሐኪም?››ላለችው የሰጠው መልስ
ምን ነበር? መልሱን በበቂ ሁኔታ አብራሩ(ገፀ26)
ምእራፍ አራት
2.የሐመር ሴት ልጅን አጠቃላይ ሕይወት አብራሩ ከጋብቻ በፊት እና ከጋብቻ በሁዋላ፡፡(ገፅ 32-35)
3.እናቱ በንቲ ሀይሎ አባቱ ሆራ ሸላ የተባሉት የከሎ ወላጆች በልጃቸው ሕይወት ውስጥ ምን አይነት
ትዝታ ትተው ኖሩ(ገፅ 35-36)
ምእራፍ አምስት
ሁለቱን መርጣችሁ ሥሩ
1.ከሐመር አውራጃዎች መካከል የሁለቱን የዲመካና የቱርሚን መልክአ ምድራዊ ገለፃ በመዘርዘር
ፃፉ(ገፅ 39)
2.ሽማግሌዎች በካርለት የተበሳጩት ከምን የተነሳ ነው? በሐመርስ ‹ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል
የተፈጠረች የእርሱ ፀጋ መሆኑዋ እንደት ይረጋገጥ ነበር?›› (ገፅ 42-44)
3.ካርለት ባል ያላገባች እና እጮኛ የሌላት መሆኑዋን ማሳወቅ ለምን ፈለገች? የዚህስ ገለፃ ምን ጠቃሚ
ወይም ጎጆ ውጤት አመጣ? (ገፅ 42-44)
ምዕራፍ ስድስት
1..ከምዕራፍ 1-6 የተዘረዘረውን የትረካ ሂደት በማስታወስ(ከዘጠኝ እስከ አስራ አንድ የተማራችሁትን
የልብ ወለድ አላባውያነን ከግመት በማስገባት) በታሪኩ ውስጥ ያሉትን፡-
ሀ.ገፀባህሪያት፣
ለ.ጭብጥ፣
ሐ.ግጭቶች
1.ምዕራፉ ‹‹ሦስት ወራት አለፈ…››በማለት ይጀምራል በሀመር የካርሎ ቆይታ ላይ እነዚህ ሦስት ወራት
ያመጡት ለውጦች በሰብእናዋ (በማንነቱዋላይ) ላይ ምን ምን ነበሩ ትላላችሁ ምላሻችሁን በምዕራፍ
ስድስት ላይ ብቻ ሳትወሰኑ እስከ ገፅ አርባ ዘጠኝ ያለውን በመሸፈን መልሱ፡፡
2.ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅና የሚጠጣ ተወዳጅም የሆነ መጠጥ ነው፡ በሀመሮች ዘንድ የቡና
ስነ ስርአትን ከተቀሩት የኢትጵያ ሕብረተሰቦች አኩዋያ ስታዩ ምን የተለየ የአዘገጃጀት ልዩነት አለው፡፡ (ገፅ
27)
3.‹‹አየህ ስቲቪ ከርቀት ጠቦ የሚታይህ ደልድይ ስትደርስበት ግን ሰፊ ነው›› ይህን ካርለት መጠቀም
የፈለገችበትን መሰረታዊ ምክንያት በማብራራት መልሱ (ገፅ 49)