You are on page 1of 15

See discussions, stats, and author profiles for this publication at: https://www.researchgate.

net/publication/337135699

Proverbs in Amharic

Book · October 2019

CITATIONS READS
0 63,764

1 author:

Daniel Aberra
Independent Scholar
15 PUBLICATIONS 18 CITATIONS

SEE PROFILE

All content following this page was uploaded by Daniel Aberra on 09 November 2019.

The user has requested enhancement of the downloaded file.


የዏማርኛ ምሳላያዊ አባባልች Proverbs in Amharic
ዲንኤሌ አበራ Daniel Aberra
20,000 ምሳላያዊ አባባልች
638 pages
https://www.amazon.com/dp/1697860079
Product details
$30.00
Paperback: 638 pages
October 11, 2019
ISBN-10: 1697860079
ISBN-13: 978-1697860078
Product Dimensions: 6 x 1.4 x 9 inches
Shipping Weight: 2.3 pounds

Introductory note
"አነሳስቶ ሊስጀመረኝ አስጀምሮ ሊስጨረሰኝ እግዚአብሓር አምሊክ ምስጋና ይግባው።" ይህ ጥቅስ ነባር መጻሔፍትን
ስናገሊብጥ የምናነበው፤ የምናገኘው ነው። የቃለን ክብዯት የምናውቀው ገብተን ስንዲክርበት ነው። ዲከራው ከአዯናቃፊ፣
እስከ አሰናካይ፣ ከአቃፊ እስከ ዯጋፊ ክስተቶች፣ ኹነቶች፣ ግሇሰቦች የሚናኙበት ዓሇም ነው። ከኹለም በሊይ ግን ዕፁብ
ዴንቅ ኹነው የምናገኛቸው ዯጋፊዎች የጸሏፊነት ጉዞውን ውብ ያዯርጉታሌ። ኑሩሌን፣ ክበሩሌን ከማሇት ውጪ ምስክርነቱን
እጃችኹ በገባው መጽሐፍ ማየት ነው። ኹላም ከአንዴ መጽሐፍ ጀርባ የአዕሊፋት እጅ አሇ፤ ይዘከሩ።

እነዚህን ከ20 ሺ በሊይ ምሳላያዊ አባባልች ሲጀመር የሰበስብኳቸው ሇማንነት እና ሇአገር-በቀሌ ዕውቀት ጥናት ነው።
ምሳላያዊ አባባልቹን አንዳ ከተየብኳቸው በኋሊ፣ ሇላልችም የሚጠቅም ከኾነ ሌካፈሇው በሚሌ መንፈስ
አቅርቤያቸዋሇሁ። የከርሞ ሰው ይበሇንና እነዚህን ምሳላያዊ አባባልች አበጃጅተን ታሪካችንን ባሔሊችንን አስተሳሰባችን፤
ላሊው ላሊውንም ወግ በላሊ ዕትም እናወጋሇን። በዚህ መግቢያ ኹሇት ሥያሜዎችን፣ ምሳላያዊ አባባልች እና ምሳላያዊ
አነጋገሮችን እያፈራረቅኹ ተጠቅሜያሇሁ።

የማንነትን ፍሇጋ ጉዞ ፦ ዕውቁ የቲያትር ባሇሙያ እና ስንኝ ቋጣሪ ጌትነት እንየው፤ እውነትን ፍሇጋ፣ ፍቅርን ፍሇጋ፣
ዕውቀትን ፍሇጋ እንዯሚሇው፤ ማንነትን ፍሇጋ በሚዯረግ ጉዞ፤ ይህ የምሳላያዊ አባባልች ስብስብ በአግባቡ ተሰናዴቶ
ሇአንባቢ፣ ሇተዯራሲ እንዱዯርስ በብርቱ ተዯክሞበታሌ፤ የብዙ ወገኖቻችን እጅም አሇበት። እንዯ የዏማርኛ ምሳላያዊ
አባባልች መጽሏፍ አሰናጅ ሌነግራችኹ የምችሇው ስሇ ራሳችን፣ ስሇ ማንነታችን፣ ሥር ስሇ ሰዯዯው ችግራችን፤ ውሇ ስሇ
ጠፋበት ኑሯችን፤ ስሇ አብሮ መኖራችን በይበሌጥ ሇማወቅ ‚የዏማርኛ ምሳላያዊ አባባልች‛ ዏይነተኛ የመረጃ ሰነዴ መኾኑን
ነው። ማሳሰቢያ ሇመጽሏፉ ተጠቃሚዎች፦ ምሳላያዊ አባባልቹም ኾነ ከእነሱ ጋራ ተያያዥ የኾኑ ጉዲዮችና ቁጥሮች በአንዴ
ወቅት የነበሩ፤ በዏማርኛ የተነገሩ መኾናቸውን ማሳያ እንጂ፤ የዛሬውን እኛነታችን ወይም ዘሇቄታዊ ነው ተብል መዯምዯም፤
ግንዛቤ ማሳዯር እና ተስፋ መቇረጥ የሇበትም - እንዯ አንዴ መረጃ፣ እንዯ አንዴ ግብአት ብቻ ነው መታየት ያሇበት።

1
ይህ ከ20 ሺ በሊይ ምሳላያዊ አባባልች ስብስብ መጽሏፍ ከሶሻሌ ሚዱያ ከተሇያዩ ግሇሰቦችና ምንጮች የተጠናቀረ ሲኾን፤
ከዚህ በፊት በምሳላያዊ አባባልች ሊይ የተሠሩ ሥራዎችን፤ በተሇይ የታተሙትን ሇማየትና እንዯ ምንጭ ሇመጠቀም
ሞክሬያሇሁ። ላልች መኖራቸውን የማውቀው ግን ያሊገኘኋቸው ሥራዎችም አለ፤ ወዯፊት መጻሔፍቱ ሲገኙ እና እዚህ
ከተሰናደት የተሇየ ምሳላያዊ አባባልች ካሎቸው ሇማካተት እጥራሇሁ።

ይህን መጽሐፍ ከላልቹ ሌዩ የሚያዯርገው፤ ምሳላያዊ አባባልቹ በተሇይ በመግቢያው ሇምን ሇምን መጠቀም እንዯምንችሌ
ማመሊከቱ፤ የስብስቡ መነሻም የባሔሌን የማንነትን ፍሇጋ እና ግንኙነት-ተኮር መኾኑ ነው። በተጨማሪም ይህንን ሥራ
ከቀዴሞዎቹ ሇየት የሚያዯርገው፤ በቀዯምቱ ጸሏፍት እና ሰብሳቢዎች ሌፋትና ውጤት መመሥረቱ የመጀመሪያው ሲኾን፤
በመጠን መግዘፉ ኹሇተኛው ነው። እስካኹን ያሇን፣ የምሳላያዊ አባባልች መጻሔፍት ያካተቱት ምሳላያዊ አባባልች ከ6
ሺሔ የዘሇሇ አይዯሇም የአቶ ክብረ አብ አዴማሱ ያሌታተመ ሥራ ሳይቇጠር። ይህ የአሁኑ መጽሏፍ በቁጥር የቀዴሞዎቹ
እጥፍ ነው ከ20,000 በሊይ ምሳላያዊ አባባልች ተካተውበታሌ። ይህ ማሇት ግን የቀዴሞዎቹ መጻሔፍት ዋጋ የሊቸውም
ማሇት አይዯሇም። ብዙ የተሇያዩ የምሳላያዊ አባባልች ባሔርያትን ያካተቱ፣ ዏውዴም የተመሇከቱ፤ የተሇያዩ ቋንቋዎችን
ያነጻጸሩም ግሩም ሥራዎች አሇባቸው።

በዚህ መጽሏፍ ከተካተቱት 20,000 ምሳላያዊ አባባልች 40 ከመቶው ከአራት ቃሊት የተመሠረቱት፣ 20 ከመቶው
ከዏምስት ቃሊት የተመሠረቱ፣ 15 ከመቶው ከስዴስት ቃሊት የተመሠረቱ እና 10 ከመቶው ከሦስት ቃሊት የተመሠረቱ
ናቸው። በዚህ ስላት መሠረት 85 ከመቶው ምሳላያዊ አባባልች ከሦስት እስከ ስዴስት ቃሊት አሊቸው ማሇት ነው። ግማሽ
ያኽለም ምሳላያዊ አባባልች ባሇአራት ቃሊት ናቸው። እነዚህ ቤት ሇመምታትም፣ ተወዲዲሪ፣ ተነጻጻሪ ነገሮችን
ሇመግሇጽም፣ ሇማስታወስም፣ ሌከኛ መስፈርት ናቸው። የቃሊቱ ቁጥር ማነስ ምሳላያዊ አባባልቹን ሇመታወስ ቀሊሌ
ያዯርጋቸዋሌ፤ ሲነገሩም ጊዜ አይፈጁም፤ መሌዕክታቸውንም በሚገባና በፍጥነት ያስተሊሌፋለ። መመጠናቸው የትርጉም
አሻሚነት ባሔርይ እንዲይኖራቸውም ያዯርጋሌ። ርግጥ ነው፤ ምሳላያዊ አባባልቻችን ከኹሇት እስከ ዏሥራ ኹሇት እና
ከዚያም በሊይ ቃሊትን ሉያካትቱ ይችሊለ። እነዚህ (ባሇ 2፣ 7-12 ቃሊት ምሳላያዊ አባባልች) ግን ከተጠቀሱት አራቱ
(ከሦስት እስከ ስዴስት ቃሊት) ምሳላያዊ አባባልች በመቶኛ ሲሰሊ ከአጠቃሊዩ 15 በመቶ ብቻ ናቸው።

ስሇ መጽሏፉ አሰነዲዴ
ምሳላያዊ አባባልች በተሇያየ መሌክ ሉሰናደ፣ ሉዯራጁ ይችሊለ - በፊዯሌ ተራ፣ በርዕሰ-ጉዲይ፣ በቃሌ ተመሳሳይነት ጥቂቶቹ
ናቸው። በዚህ መጽሐፍ ምሳላያዊ አባባልቹ የተዯራጁት በፊዯሌ ተራ ነው። ቅዯም ተከተሊዊ አጻጻፉም መዯበኛ የፊዯሌ
ተራን የጠበቀ ነው። ኾኖም (ሀ፣ሏ፣ ኀ፣ ኸ) አንዴ ዘር በመኾናቸው እንዱሁም (ሰ፣ ሠ) ፤ (አ፣ ዏ)፤ እና (ጸ፣ፀ) ተመሳሳይ
ዴምፀት ስሊሊቸው፤ ከተመሳሳዮቻቸው ጋራ በአንዴ ምዕራፍ ተካትተዋሌ።

1) ምዕራፍ 1 ሀ፣ ሏ፣ ኀ፣ ኸ
ሀ ባሇ፣ ዯሞዝ በለ።
ሏምላና ሙሽራ ሳይገሇጡ ነው።
ኀዘንና ዯስታ በአንዴ ገበታ።
ኹሇት የተመኘ፣ አንዴም አሊገኘ።

2
2) ምዕራፍ 4 ሰ፣ ሠ
ስም ከመቃብር በሊይ ይቆማሌ።
ሥራ ያጣ ሙቅ ያኝካሌ።

3) ምዕራፍ 12 አ፣ ዏ
ዏባይ ቢሸፍት፣ ተከዜን በፍሌጥ።
አባይ ጠንቋይ ቤት ያስፈታሌ።

4) ምዕራፍ 23 ጸ፣ፀ
ፀሑይና ጣውንት መሌክ ያጠፋሌ።
ጽዋውን የገሇበጡ፤ ጋኑን የጨሇጡ።

ሇፊዯሌ ተራ ሥር አሰነዲዴ መርህ የኾነው በምሳላያዊ አባባለ የተገኘ የመጀመሪያው ቃሌ ሲኾን፤ የመጀመሪያው ቃሌ
በኹሇት ምሳላያዊ አባባልች ተመሳሳይ ከኾነ፣ አባባሌ በኹሇተኛው ቃሌ ወይንም በሦስተኛው ወይንም በአራተኛው ቃሌ
ፊዯሌ ተራ ይሰዯራሌ።

ሏሰተኛ ምስክር ፥ ጉሌበት ይሰብር።


ሏሰተኛ ሲናገር ይታወቃሌ ፤ ሥሡ ሲበሊ ይታነቃሌ።
ሏሰተኛ ሲናገር ይታወቃሌ ፤ በሶ ሲበለት ያንቃሌ።
ሏሰተኛ በቃለ ፤ ስዯተኛ በቅለ ይታወቃለ።
ሏሰተኛ በቃለ ፤ ስዯተኛ በቅለ ይታወቃሌ።

ከእነዚህ 20 ሺ ምሳላያዊ አባባልች፣ ምሳላያዊ አነጋገሮች፣ ተረትና ምሳላዎች አንዲንዴ ጊዜ ተዯጋጋሚ የሚመስለ ይገኛለ።
ምሳላያዊ አባባልቹ የተሇየ ፍቺ ወይም የተወሰነ የፊዯሌ ቅርጽ መሇያየት የፍቺ ሌዩነት ያመጣሌ ብዬ ሳስብ ነው፤ እነዚህ
ተዯግመው እንዲካተቱ የተዯረጉት።

ምሳላያዊ አባባልቹን፤ እንዳት ተመዯቡ? የሚሌ ጥያቄ ቢነሣም በሥርወ-ቃሊት ነው። የትርጉም ሌዩነት ሲያመጡ እንዯ
ኹሇት ይጻፋለ (ምሳላ 5.1)። አንዴ ቀጣይ ቃሌ ሇምሳላ ‚ሀብታም” እና ‚ሀብታምና” የሚሇ ካሇ በ‛ሀብታምና” ቃሌ
የሚጀምረው ምሳላያዊ ንግግር እንዯ ዏዱስ ገብቷሌ (ምሳላ 2)። የሰዋስው ሌዩነት ከኾነ (ምሳላ 3)፤ የቀበሌኛ/ የንግግር
ጽሐፍ ሌዩነት ከኾነ (ምሳላ 4)፤ ወይም ተጨማሪ ቃሌ ከኾነም (ምሳላ 5) እንዱኹ በቅንፍ ይቀመጣሌ። ይህ በቅንፍ
መቀመጥ ቅንፍ ውስጥ ያለት ቃሊት በምሳላያዊ አባባሌ ውስጥ በተሇዋዋጭነት ይገኛሌ፤ ይነበባሌ፤ ይባሊሌ ሇማሇት ነው።

(1) የትርጉም ሌዩነት ሲያመጡ


ቀን ቢረዝም፣ ሌብ ይዯክም።
ቀን ቢረዝም፣ ሌብ ያዯክም።

(2) አንዴ ቀጣይ ቃሌ ሇምሳላ ‚ሀብታም” እና ‚ሀብታምና” ወዘተርፈ


ሀብታም ገንዘቡን ያስባሌ ፤ ዴኻ ቀኑን ይቇጥራሌ።
ሀብታምና ሀብታም ፥ አንተ ሇእኔ ፥ አንተ ሇእኔ ይባባሊሌ ምን ነው?
ሀብታችኹ ባሇበት ሌባችኹም ይገኛሌ።
ሀብታችን በውርስ ፥ ክብራችን በዏዋጅ።

(3) የሰዋስው ሌዩነት

3
በሬና በሬ መከሩ ፥ ቀንበር ሉሰብሩ።
በሬና በሬ መከሩ ፥ ቀንበር ሰበሩ።

(4) የቀበሌኛ/ የንግግር ጽሐፍ ሌዩነት


ተሰብሮ ቢጠገን ፥ እንዯ ቀዴሞው አይኾን።
ተሰብሮ ቢጠገን ፥ እንዯ ነበረ አይኾን።
ተሰብሮ ቢጠገን ፥ እንዯ ዴሮው አይኾን።

(5) ተጨማሪ ቃሌ
ተስፋ መስጠት ፥ ዕዲ መግባት።
ተስፋ መስጠት ፥ እያዩ ዕዲ መግባት።

አንዲንዴ ሔብረተሰቡ የሚያነውራቸው፤ እንዱሁም በተሇያዩ ሔብረተሰባዊ ዝምዴናዎች፤ ግንኙነቶች፣ መስተጋብሮች፣


እንዱሁም አብሮ ሇመኖር ሲባሌ፤ ሇተሇያዩ ጉዲዮች እና ሇሃይማኖቶች ክብር ሲባሌ የተወሰኑ ምሳላያዊ አባባልች፤ ቢኖሩም
በዚህ ዕትመት አሌተካተቱም።

ስሇ ምሳላያዊ አባባልች፦ እንዯ ቋንቋ አንዴ ዘርፍ ምሳላያዊ አባባልችን በሥነ ጽሐፍ እና በሥነ ቋንቋ ዓይን ማየት
ይቻሊሌ፡፡ ምሳላያዊ አባባሌ የትውፊት (የሥነ ቃሌ) ዘርፍ እንዯመኾኑም መጠን ባሔርያቱን በሚመሇከት ከሥነ ጽሐፍ
አንጻርም መታየት ይኖርበታሌ፤ የምሳላያዊ አባባልች ባሔርያትን አስመሌከቶም አንዲንዴ አጥኚዎች የበኩሊቸውን ቅቡሌ
ሏሳብ ጽፈዋሌ፤ ይህ መግቢያ ከሥነ ጽሐፍ አንጻር በአመዛኙ የዓሇም እሸቱን (1995፣ 1999)፣ የመስፍን መሰሇን (1999)
እንዱሁም የዘሪሁን አስፋውን (2002) የምሳላያዊ አባባልች ጥናት መሠረት አዴርጓሌ።

ስሇ ምሳላያዊ አባባልች ሥያሜ፣ ብይንና ባሔርያት፤ መስፍን (1999፡40) ባካኼዯው ጥናት፤ ምሳላያዊ አባባልች
የተሰኘውን የትውፊት ዘርፍ፣ ግሇሰቦች በተሇያየ ጊዜ የተሇያየ ሥያሜ ሰጥተውት አግኝቷሌ። ‚ምሳላ፣ ተረት፣ ዘይቤ፣
ንግግር፣ አባባሌ፣ ተረት/ምሳላ፣ ምሳላ/ተረት፣ ምሳላና ተረት፣ የምሳላ ንግግር፣ የቃሌ ትውፊት፣ ኪነ-ቃሌ፣ ምሳላያዊ
አባባሌ፣ ተረታዊ አነጋገር፣ ታሪክና ምሳላ፣ ጥንታዊ ምሳላ፣ ተረትና ምሳላ፣ ፈሉጣዊ አነጋገር፣ ምሳላያዊ ተረት፣ አፈ ታሪክ፣
ሌማዲዊ አባባሌ፣ ጥንታዊ የአነጋገር ብሑልች፣ አጫጭር ተረትና ምሳላዎች፣ ብሑሌ” ጥቂቶቹ ናቸው።

መስፍን ምሳላያዊ ንግግር ‚እየተሇመዯ የመጣ፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ማዕከሌም በአመዛኙ የሚጠቀምበት ሥያሜ
ቢኾንም፤ ሥያሜው (ምሳላያዊ ንግግር) ችግር ያሇበት፤ ይሄ በይሻሊሌ የተሰጠው ሥያሜም ተጨማሪ ውይይት
እንዯሚያስፈሌገው ገሌጿሌ” (ገጽ 61)። ኾኖም መስፍን (1999:61) ‘ምሳላያዊ ንግግር’ን proverb ሇምንሇው ትውፊት
ተገቢ ሥያሜ ነው ይሊሌ፤ ያቀረበው አመክንዮም አስማሚነት አሇው። በአጭሩ ሲገሇጽ ንግግርና ምሳላያዊ የሚለትን ቃሊት
አንዴ ሊይ አጣምሮ መሠየሚያ ማዴረጉ የትውፊቱ ዓይነት (proverb) የምሳላ ወገን መኾኑን፤ ከትውሌዴ ወዯ ትውሌዴ
በቃሌ ሲተሊሇፍ መኖሩንና ዛሬም የሚተሊሇፍ መኾኑን ያስገነዝባሌ። ስሇኾነም ኹሇቱ ቃሊት ተጣምረው ‚ምሳላያዊ ንግግር”
በሚሌ የሥነ-ቃሌ/ትውፊትን ዓይነት እንዱሠይሙ መዯረጋቸው ሥነ-ቃሊዊነቱንና ዓይነቱንም በትክክሌ መግሇጽ ብቻ ሳይኾን
የሥያሜ ችግሩን ሉቀርፍ ይችሊሌ። እንዯ እኔ ሀሳብ ምሳላያዊ የሚሇው ቃሌ አስማሚ ቢኾንም አፋዊ እና ከትውሌዴ ወዯ
ትውሌዴ የሚተሊሇፍን እሴት ‚ንግግር” ከማሇት አባባሌ ወይም ብሑሌ ብንሇው የበሇጠ ይገሌጸዋሌ። ‚ንግግር” በተሰኘው

4
ቃሌ ውስጥ አፋዊነት እንጂ ከትውሌዴ ወዯ ትውሌዴ መተሊሇፍን አመሌካች ነገር የሇምና። Proverb ሇሚባሇው የትውፊት
ዘርፍ- የእኔ ምርጫ ምሳላያዊ ብሑሌ ወይም ምሳላያዊ አባባሌ ነው። ወዯፊት የብሑሌ እና የአባባሌ ሥርወ-ቃሌ ‚አሇ፣
ማሇት፣ መባባላ፣ አባባሌ፣ ባሔላ፣ እንዱሁም ብሑሌ” አንዴ መኾኑን በማሳየት በአሁኑ ሰዓት ቅቡለን ሥያሜ፣ ምሳላያዊ
ንግግርን በምሳላያዊ ብሑሌ ወይም በምሳላያዊ አባባሌ እንተካዋሇን። እንዱሇመዴም እንጥራሇን። ይህ ዯግሞ የኔ ዏዱስ
ፈጠራ ሳይኾን መስፍን (1999:61) እንዯጠቀሰው ምሳላያዊ ንግግርን እና ተቀራራቢውን ሥያሜ መስፍን ሀብተማርያም
(አባባሌ)፤ ታዯሰ እሸቴ (አባባሌ)፣ ሁሴን በዲሶ (አባባሌ)፤ ውዴነህ ዓሇሙ (አባባሌ)፣ እንዱኹም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች
አካዲሚ (1973) (የቃሌ ትውፊት)፤ አስመሮም ገ/ሥ (ኪነ-ቃሌ) ከበዯ ሆሮድፋ (የቃሌ ትውፊት) መጠቀማቸውን አትቷሌ።
የተሻሇውን ሥያሜ ሇማስሇመዴ፤ ሇመጠቀም፤ ሇመከራከርም፣ መነሻ አሇን ማሇት ነው።

ምሳላያዊ ንግግር (አባባሌ) የትውፊት (ሥነ ቃሌ) አንዴ ዘርፍ ነው። እንዯ አንዴ የትውፊት ዘርፍነቱም በሔዝብ ሇሔዝብ
የተፈጠረ የባሔሌ መገሇጫ ተዯርጏ ይወሰዲሌ። ምሳላያዊ አባባሌ የሔዝብ ሀብት ስሇኾነም ዯራሲው እከላ ነው ተብል
ሉነገርሇት አይችሌም። ሲወርዴ ሲወራረዴ እዚህ ያሇንበት ዘመን የዯረሰ የአያት የቅዴም-አያቶቻችን ቅርስ ነው። ምሳላያዊ
አባባልች ዕምቅና የማሔበረሰቡ ነጸብራቅ ናቸው (ዓሇም 1999)። ‚ምሳላያዊ አነጋገሮቹ በውስጣቸው ዏምቀው የያዟቸው
ሏሳቦች ከማሔበረሰባዊ የዕሇት ከዕሇት ኑሮ ገጠመኝና ምሌከታ የተገኙ ሲኾኑ ማሔበረሰቡ የሚያምንባቸውና ሏቅነታቸውን
ያረጋገጠሊቸው የሏሳብ መግሇጫዎች ናቸው” (ዘሪሁን፤ 2002፣35)። በተያያዘ ዘሪሁን ምሳላያዊ አባባልች ዕምቅ ሏሳብ
መያዝ ብቻ ሳይኾን ራሳቸውም ቁጥብ፤ ዕምቅ ናቸው ይሊሌ። ‚ምሳላያዊ አነጋገር በማሔበረሰቡ ሌማዲዊ ስምምነት መሠረት
የሚፈጠር በቁጥብና በምርጥ ቃሊት በአጭር የሚነገር የተጨመቀ ጥሌቅ ሏሳብን የያዘ ነው” (ዘሪሁን፤ 2002፣35)። ዘሪሁን
ምሳላያዊ አባባልች ማሔበረሰባዊ መሠረት ብቻ ሳይኾን አጠቃሊይ ሰዋዊ ባሔርያትን ይገሌጻለ ይሊሌ። ተከታዩ የዘሪሁን
ሀሳብ ይህን አመሊካች ነው።
ምሳላያዊ አነጋገር የማሔበረሰቡን ዏሻራ ይዞ ስሇሚነሣ በማሔበረሰቡ ውስጥ የሚዯረጉትን ኑሯዊ እንቅስቃሴዎች
በመከተሌ ይመሠረታሌ…ሲቀጥሌም (ምሳላያዊ አባባልች) ኑሮን ሇማሟሊት ሰዎች ከሚፈጽሟቸው ሌዩ ሌዩ
ሥራዎች የተያያዘ ነው። የሰውን መሠረታዊ ባሔርያትና የተሇያዩ ጠባዮችንና ስሜቶችን በመመርኮዝ
ይፈጠራሌ…[እንዯ ማሳረጊያም:DA] ምሳላያዊ አነጋገሮች የማሔበረሰቡን ወግና ሌማዴ እንዱሁም አጠቃሊይ
የባሔሌ ገጽታ በመንተራስ የሚፈጠሩ ናቸው።(ዘሪሁን፤ 2002፣36)

ምሳላያዊ አባባሌ የትውፊት አንዴ ዘርፍ እንዯመኾኑ በዚህ ሳቢያ ከላልች ትውፊት ዓይነቶች ጋራ የሚጋራቸው በርካታ
ባሔርያት አለት። ከነዚህም ባሔርያት ዋና ዋና የሚሰኙት አፋዊነቱና ተሇዋዋጭነቱ ናቸው። አፋዊ ስሇኾነም ከአንዴ
ትውሌዴ ወዯ ላሊ ትውሌዴ የሚተሊሇፈው በቃሌ ነው። በቃሌ የሚተሊሇፍ ስሇኾነም በትውሌዴ ቅብብልሽ ውስጥ የቀዴሞ
ቅርጹን እንዯያዘ መቇየት አይችሌም። በዚህም ሳቢያ ከጊዜ ወዯ ጊዜ ከቦታ ወዯ ቦታ የመቀያየር ባሔርይ አሇው።
የተሇዋዋጭነት ባሔርይ አሇው የሚባሇውም ሇዚህ ነው (ዓሇም 1999)። ምሳላያዊ አባባሌ የተሇያዩ ጠቀሜታዎች አለት።
ከጠቀሜታዎቹም አንደና ዋነኛው ሇንግግር፤ ሇዛና ወዝን መሇገስ ነው። ‚ነገር በምሳላ፣ ጠጅ በብርላ፣ ዜማ በሃላ።”
እንዯሚባሇውም ሰዎች ንግግራቸውን ሇማሳመር ይገሇገለበታሌ። በምሳላያዊ አባባሌ የታጀበ ንግግር በቀሊለ የአዴማጭን
ቀሌብ መግዛት ይችሊሌ። ሇዚህም ነው ምሳላያዊ አባባሌ የንግግር ወይም የወግ ማጣፈጫ ቅመም ነው የሚባሇው (ዓሇም
1999)።

5
ምሳላያዊ አባባሌ ከንግግር ማሳመሪያነቱ በተጨማሪ በጽሐፍም ኾነ በንግግር ሏሳብን ሳያንዛዙ በአጭሩ ክሽን አዴርጏ
ሇማስቀመጥም ይረዲሌ። በባሔርይው ዕምቅነት ያሇው በመኾኑ የተንዛዛን ሏሳብ በአጭሩ ቅሌብጭ አዴርጏ ማስተሊሇፍ
የሚችሌ አቋራጭ የሏሳብ መግሇጫ ነው። በዚህም አንዴ ተናጋሪ ወይም ጸሏፊ ሀተታ ሳያበዛ ሀሳቡን በአጭሩ ማስፈር
እንዱችሌ ያግዛሌ። ከዚህም በተጨማሪ ምሳላያዊ አባባሌ መሌካም ምግባርን፣ ማስተዋሌን፣ ሥራ ማፍቀርን፣ መተባበርን፣
መረጋጋትን፣ ጀግንነትን፣ ወዘተ... በሔብረተሰቡ ውስጥ በማስረፅ ረገዴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አሇው (ዓሇም 1999)። ዘሪሁን
የምሳላያዊ አባባልችን አጠቃቀም በማያሻማ ቋንቋ እንዱህ ገሌጾታሌ።

ምሳላያዊ አነጋገር ሇሏሳብ መቋጫ፣ ማጠናከሪያ፣ ማጉሉያና ግሌጽ ማዴረጊያ ይኾናሌ። ሰዎች በንግግራቸው
ጣሌቃ እያስገቡ ምሬታቸውን፣ ምኞታቸውን፣ ኀዘን ዯስታቸውን፣ ስሇ ሔይወት ያሊቸውን አመሇካከት
ያንጸባርቁበታሌ። እምነታቸውን ይገሌጹበታሌ። በተጨማሪ ቅሬታቸውን የሚያሳውቁበት፣ አስነዋሪ ተግባርን
የሚነቅፉበት፣ እኩይ ዴርጊትን የሚያንቋሽሹበት፣ ሠናዩን የሚያሞግሱበት፣ ባጠቃሊይ በማሔበረሰባዊ ሔይወት
ውስጥ በሚዯረጉ ክንዋኔዎች ሊይ ሂስ የሚሰጡበት እጥር ምጥን ያሇ የሏሳብ መግሇጫ ነው (2002፣36)።

ምሳላያዊ አባባሌ በየትኛውም ማሔበራዊ ዏውዴ ውስጥ ትሌቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው። ይህ በመኾኑም ከዕሇት ተዕሇት ተራ
ተግባቦት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የውይይት መዴረኮች ዴረስ ያሇ ገዯብ ያገሇግሊሌ። በመኾኑም በፍርዴ ቤቶች፣ በአምሌኮ
ቦታዎች፣ በመገናኛ ብዙኃን፣ በሌዩ ሌዩ የሔትመት ውጤቶች፣ በከፍተኛ መንግሥታዊ ውይይቶችና ክርክሮች ውስጥ ሳይቀር
ትሌቅ አገሌግሌት ሊይ ይውሊሌ። በተሇይም ባሔሊዊ የሽምግሌና ሥርዓት በምሳላያዊ አባባሌ ታጅቦ ማየት የተሇመዯ ነው
(ዓሇም 1999)።

ምሳላያዊ አባባሌ አንዴ ወጥ የኾነ ቅርጽ ይዞ የሚገኝም አይዯሇም። እንዯ ኹኔታው በሏረግ፣ በዏረፍተ ነገር፣ በግጥምና
በጥያቄና መሌስ የተሇያየ ቅርጽ ይዞ ሉከሰት ይችሊሌ (ዓሇም 1999)። ሇአብነት ያህሌ ከዚህ የሚከተለትን ምሳላያዊ
አባባልች እንመሌከት (ወንዴወሰን እና ዓሇም 1995)።

1.1 በሏረግ መሌክ የሚቀርቡ ምሳላያዊ አባባልች


ከሇማበት የተጋባበት።
ሲመትሩሇት ይነጭ።
ሇማያውቅሽ ታጠኝ።

1.2 በዓረፍተ ነገር የሚቀርቡ ምሳላያዊ አባባልች


ሇተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው።
ላባ ተይዞ ደሊ አይጠየቅም።
ሌፋ ያሇው በህሌሙ ዲውሊ ይሸከማሌ።

1.3 በሰውኛ ዘይቤ የሚቀርቡ (በዕንስሳት የተነገሩ) ምሳላያዊ አባባልች


ሰውን ማመን ቀብሮ ነው አሇች ቀበሮ።
እምም አሇ አያ ጅቦ።

6
ዋ ትሊሇች አሞራ።
ዕቃቸውን አይከዴኑ ሰውን ላባ ይሊለ አሇች ዴመት።

1.4 በጥያቄና መሌስ መሌክ ያለ ምሳላያዊ አባባልች


አንበሳ ምን ይባሊሌ? ተበዴሮ። ምን ይከፍሊሌ? ማን ተናግሮ።
ማን ያርዲ? የቀበረ። ማን ይናገር? የነበረ።
ወጥን ማን ያውቃሌ? ቀሊዋጭ።

1.5 በግጥም መሌክ የሚቀርቡ ምሳላያዊ አባባልች


እኔስ እኼዲሇኹ ነገር አሊበዛም፤
እንጀራ ነው እንጂ ሰውን ሰው አይገዛም።
መሇመን የሇመዯ ምሊስ፤
በህሌሙ አቁማዲ ይዋስ።
ሇሰው ብሌ ሲያማ፤
ሇእኔ ብሇህ ስማ።
እበሊሇኹ ብሇህ መሬት አታዛጋ፤
ጠርጥሮ ጠርጥሮ ጨርሶታሌ ዏሌጋ።

1.6 ዘመነኛ ምሳላያዊ አባባልች


ማትሪክና ቀበላ የሚሠሩሇትን አያውቅም።
ፍየሌ ቦላ፣ ቅዝምዝም ጉላ።
ወይ በባላ ወይ በቦላ።
አይሱዙና የጋሪ ፈረስ አንዳ ከወዯቀ አይነሣም።
ወጣና ወጣና እንዯ ሸንበቇ ተንከባሇሇ እንዯ ሙቀጫ።
ሸርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትኾናሇች።

1.7 የአራዲ ወይም ቧሌታዊ ምሳላያዊ አባባልች


የቃመ ተጠቀመ፡፡ ያሌቃመ ተሇቀመ።
ምን እያሌኳት ታንቀሊፋሇች።
የቇጡን አወርዴ ብሊ ራሷ ወዯቀች።

ቀዯም ብዬ እንዲሌኩት ምሳላያዊ አባባልች ከሥነ ጽሐፍ አንጻር ብቻ ሳይኾን ከሥነ ቋንቋም አንጻርም ማየት ተገቢ ነው።
በዚህ መጽሐፍ የተሰናደት ምሳላያዊ አባባልች ከ98 ሺሔ በሊይ ቃሊት መዋቀራቸውን ከነዚህም ወዯ 26 ሺው ቃሊት ሌዩ
ሲኾኑ 72 ሺሔ ያህለ የተዯገሙ፣ የተዯጋገሙ ናቸው። እነዚህ የቃሊት ዴግግሞሾች፣ አዙረን ካየነው፣ ካሰሊሰሌነው ቃሊቱ

7
በመዯጋገማቸው ቃሊቱ የቆሙሇት ጉዲይ ወይም ነገር በምሳላያዊ አባባልች ውስጥ ተዯጋግመው እንዯ ዋና ጉዲይ ኾነው
የቀረቡ ነገረ-ጉዲዮችን አመሌካች ናቸው ማሇት ነው። ብዙ በተዯገሙ ቁጥር፣ ቃሊቱ ስሇሚገሌጹት፤ ስሇቆሙሇት ጉዲይ ብዙ
ይታሰባሌ፤ ብዙ ይተረካሌ፤ ብዙ ይባሊሌ ማሇት ነው። በቅዯም ተከተሌም ካየናቸው በ20ሺሔ ምሳላያዊ አባባልች ውስጥ
ነገረ-ጉዲዮቹ ወይም ዴግግሞሾቹ በቅዯም ተከተሌ ሰው፣ ሌጅ፣ ቤት፣ ሴት፣ ነገር፣ ውሃ፣ ሞኝ፣ ዴኻ እንዱሁም ሌብ ናቸው።
ስሇ እነዚህ ርዕሰ ጉዲዮች ብዙ ይባሊሌ። ብዙ ሌብ ውስጥ የሚገባ ነገርም አሇ ማሇት ነው። ሇነገሩስ ቢኾን ከሰው፣ ከሰውነት
በሊይ ምን ርዕሰ-ነገር ሉኖር ይችሊሌ? አንዲንዴ ግሶችም እንዯ "ነው" አይነቶቹ በከፍተኛ ዴግግሞሽ አገሌግሌት ሊይ
ውሇዋሌ። የ"ነው" አጠቃቀማችን ከላልች ግሶች ይሌቅ መብዛቱ የእኛን ባህሪ ፍንትው አዴርጎ ያሳያሌ።

ስሇ ምሳላያዊ አባባልቹ አሰነዲዴ፣ ሥያሜ እንዱሁም ስሇ ምሳላያዊ አባባልች ሥነ ጽሏፋዊ ይዘት አውግተናሌ። እንዱሁ
ዯረቅ ባሇው መረጃ ወዯ ዋናው ስብስብ ከማዘሌቃችኹ ዘና የሚያዯርጉ፣ ስሜትን፣ ማንነትን ቀስቃሽ የኾኑ አንዲንዴ
ምሳላያዊ አባባልችን ከሥነ ቋንቋ ይዘታቸው በተሇይ ከፍቺያቸው፣ ከዏውዲቸው፣ ከታሪካቸው አንጻር አይተን ወዯ ዋናው
ስብስቡ እንዘሌቃሇን። እናንተ አንባቢዎችም ተመሳሳዩን ፈሇግ መከተሌ ነው። በዚኹ አጋጣሚ ግርማ ሊቀውንና ዓሇም
እሸቱን ይቺን መንዯርዯሪያ በቅዴመ-ዕትመት ወቅት ስሊዩሌኝ ተገቢም አስተያየት ስሇሇገሱኝ በዴጋሚ ሊመስግን፤ ኾኖም
እዚህ ሇሚገኙ ስሏተቶችና መፋሇሶች ተጠያቂው እኔና እኔ ብቻ ነን።

የምሳላያዊ አባባልች ቅርጻዊ፣ ፍቺያዊና፣ ዏውዲዊ ባሔርያትን አስመሌክቶም፦ ቋንቋን፣ ባሔሌን ማንነትን ሇማጥናት
ሳይንሳዊ ዘዳ፣ ሳይንሳዊ መርሔዎች መከተሌ ግዴ ነው፤ ይህን ማዴረጉ ከአንዲንዴ አሊስፈሊጊ እንከኖች ይገሊግሊሌ። ሳይንስ፦
መረጃውንም (ዲታውንም)፣ ትንተናውንም ተጨባጭ፣ ተዯንጋጊ በማዴረግ ያምናሌ፣ ሳይንስ ይሰፍራሌ፣ ሳይንስ ይመዝናሌ።
ግሇሰቦችን ጠይቀን የምናገኘው መረጃ ምንም ጥንቃቄ ቢዯረግ እንኳን የግሌ አመሇካከት፣ እምነት እና ተፅዕኖ በሥራው
ውስጥ ይገባና ሥራውን እንዯ ስንዳና እንክርዲዴ ዴብሌቅ ያዯርገዋሌ። ምሳላያዊ አባባልች የዘመናት የሔብረተሰብ፣
የዕውቀት፣ የታሪክ፣ የፍሌስፍና፣ የኑሮ መርሔ፣ የቋንቋ የባሔሌ የጋራ ውጤት ስሇኾኑ በራሳቸው የሚኖራቸው ግሇሰባዊ
ወይም የተናጋሪውን ራስን የማግነን ተፅዕኖ እጅግ በጣም አናሳ ነው። ይህ የምሳላያዊ አባባልች ሔብረተሰባዊ ባሔሪ ግሊዊ-
ባሇቤት አሌባነቱ እውነተኛነት፣ ተጨባጭነት፣ ተዯንጋጊነት እንዱኖረው ያስችሇዋሌ። ሇምሳላ ቀኃሥ ብዙ ጊዜ ይለት
የነበረው ‚መከራን የቻሇ አሸናፊ ነው።” በእሳቸው ይነገር እንጂ ፈጣሪው እሳቸው ሇመኾናቸው ምንም ማረጋገጫ
አያስፈሌግም። የሇምም፤ ማግኘትም አይቻሌም፤ መሌዕክቱ ግን እውነት ነው፤ ተጨባጭ ነው፤ ተዯንጋጊ ነው። ጽናትን፣
አሌሞት ባይነትን፣ መከራን ተቋቁሞ የዘሇቀ ዴሌ ያዯርጋሌ ነው።

አንዲንዴ ምሳላያዊ ብሑሌ የታሪካችንን የማንነታችን አንዴ ገጽታ በአስዯማሚ መሌኩ ቀርጾ ማስቀረት ይችሊሌ። ‚ሴት
(ሌጅ) በማጀት፤ ወንዴ (ሌጅ) በችልት”፤ ሇዚህ አንዴ ማስረጃ ነው። ይህ ምሳላያዊ አባባሌ በተሇያየ ዏውዴ ሉገኝ ቢችሌም
መነሻው የቋንቋው ተናጋሪ ባሔሌ ነው። ጥሬ ፍቺው ‚የሴት ሌጅ በማጀት” ማሇት ሴት ሌጅ መሥራት ያሇባት፣
የምትሠራው፣ የምትከውነው ሙያዋ፣ መገኛዋ ማጀት- ማዕዴ ቤት- ጓዲ ነው ማሇት ሲኾን፣ ባሔሊዊ (ሌማዲዊ) መሠረተ
ሏሳቡ ግን ሇየት ይሊሌ። በገጠሩና ገጠር-ቀመስ የሀገራችን ክፍሌ ቤቶች ተራርቀው ነው የሚሠሩት፤ በመኻሌ በመኻሌ
ዕርሻው ይኖራሌ። የቤቶቹ ተራርቆ መሠራት ባሌና ሚስት ሲጣለ በተሇይ ምሽትና ላሉት ከኾነ ሚስት ከቤት ወጥታ ወዯ
ጏረቤት፣ ወዯ ዘመዴ፣ ወይም ወዯ ሔግ ሇመዴረስ አያስችሊትም። ከጨሇማው መግዘፍ፤ ከቤቱ መራቅ፤ ከአውሬው

8
መሰማራት፤ አዯጋውና ዕንቅፋቱ የሚስትየዋን ሔይወት አዯጋ ሊይ ይጥሇዋሌ፤ በግንኙነት መኻሌ ግጭት አይቀሬ ስሇኾነ።
ግጭቱ ዯግሞ እኩሌ አፍ፤ እኩሌ ጉሌበት እኩሌ ጡንቻ በላሊቸው መኻሌም ስሇኾነ፤ ግንኙነቱ ቀጣይ እንዱኾንና የአካሌ
ጉዲት ወይም ሞት ዯካማው ሊይ እንዲይዯርስ ተጠቂው ሇመሸሽ መቻሌ አሇበት። ውጪ መሸሽ ካሌተቻሇ ቀሪው ሽሽት ቤት
ውስጥ ነው። ቤት ውስጥ መፍትሓ መገኘት አሇበት። ዘዳኛዎቹ አባቶቻችን እና እናቶቻችን መሊ ፈጠሩ ማሇት ነው፤ ሽሽት
ወዯ ወንዴ አይዯፍሬው አባወራ አይዯፍሬው ማዕዴ ቤት- ጓዲ ምንም እንኳን ዛሬ መሥራቱን ባናውቅም። ሚስት፣ ሴት
ሌጅ ወዯ ውጭ ከመሮጥ ወዯ ማጀት እንዴትሮጥ፣ እንዴትገባ አቅጣጫውን ቀየሩት።

ማጀት ማሇት፦ ከጓዲነት ውጪ የሚስት፣ የሴት የማይዯፈር የማይገሰስ ግዛት፣ ክሌሌ ነው። ማጀት በር ኖረው አሌኖረው፤
ተከሇሇ አሌተከሇሇ፤ ተሸጎረ አሌተሸጎረ ወንዴ ዝር የማይሌበት ስፍራ ነው። ጸብ በተነሣ ጊዜ የሚስት / የእማወራ ዴርሻ
ሮጣ፤ ዘሊ ወዯ ማጀት መግባት ነው። ማጀት ከገባች አሇቀ ማሇት ነው። እዚያ ኾና መናገር የምትፈሌገውን መናገር፣ መርገም
የምትፈሌገውን መርገም ነው። ማን ከሌካይ ማን ሃይ ባይ አሇባት? ባሇ ሙሇ መብት፣ ባሇ ሙሇ ግዛት ነች። በሌማዴም
ወንዴ ሌጅ ማጀት መግባት አይዯሇም የአይዯፈሬውን ግዛት ዯፍ ከረገጠ ወንዴነቱ ያበቃሇታሌ። ትዲሩም ይበተናሌ፤
ማሔበረሰባዊ ቦታውንም ያጣሌ። አብዛኞቻችን የዚህ መጽሐፍ አንባቢዎች እዚህ ታሪካዊ ባሔሊዊ ዲራ ሊይ የዯረስን
አይመስሇኝም። በዛሬ በእኛ ዘመን በተወሰነ መሌኩ ጓዲ የሴት ግዛት እንዯኾነ እሰማሇኹ ግን ስፋት ያሇው የኑሮ መርሔ
አይመስሇኝም። ይህ ነበር የምሳላያዊ አባባሌ ‚ሴት በማጀት፤ ወንዴ በችልት።” መነሻ። ይህ ጥበብ ዏጀብ፤ ዏጃኢብ
አያሰኝም? የምሳላያዊ አባባልቻችን ዕምቅ ዕውቀት ገሊጭ አይመስሊችሁም? ይህንን ገሊሌጦ ሇማየት ሇማጤን (ሇማጥናት)
የሚጠይቀው የእኛን ትጋት ብቻ ነው። በዚህ አጋጣሚ ታሪኩን የዛሬ ኹሇት ዏሥርት ዓመታት በፊት ሊጫወተኝ ሇአያላው
ምትኩ ምስጋናዬ የሊቀ ነው።

ምሳላያዊ አባባልች ከሥነ ቋንቋ መዋቅር አንጻር በተሇያየ መንገዴም ሉጤኑ ይችሊለ። አንደ ቅርጻቸውን አስመሌክቶ
ከስንት ቃሊት ተዋቅረዋሌ ነው። የምሳላያዊ አባባልች ባብዛኛው ከአራት ቃሊትና ሏረጋት የሚዋቀሩ ሲኾን፤ በመዯበኛነት
የምሳላያዊ አባባልች ቃሊት ብዛት ከ3 እስከ 6 ሉዯርስ ይችሊሌ። ሇማስረጃም የሚከተለትን ይመሌከቱ።

ኹሇት ቃሊት / ሏረጋት :- ከፍትፍቱ ፊቱ።


ሦስት ቃሊት / ሏረጋት:- ጸጸት እያዯር ይመሠረት።
አራት ቃሊት/ ሏረጋት:- ፀሒይ የጠዋት አደኛ የሽበት።
ዏምስት ቃሊት/ ሏረጋት:- ጸጉራም ውሻ አሇ ሲለት ይሞታሌ።
ስዴስት ቃሊት/ ሏረጋት:- ጾም ገዲፊና ሰው ጠባቂ ሇጥቂት ይሳሳታሌ።
ሰባት ቃሊት/ ሏረጋት:- ጻዴቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛለ ኀጥአን ግን በተቃጠሩበት
ይተጣጣለ።
ስምንት ቃሊት/ ሏረጋት:-
ፀሒይ ካሌወጣ ከሰፈረበት አይነሣ አንበጣ፣ ሴት ምክንያት አታጣ።

9
ይህ ምሳላያዊ አባባልችን ከቅርጻቸው አንጻር ማጥናት ቀሊሌና ቀጥተኛው ሲኾን፤ ላሊው የጥናት ዘይቤ ዯግሞ የፍቺያቸው፤
የምስጢራቸው ይዘት ሊይ በማተኮር ይኾናሌ። ይሄ ዋነኛው ይመስሇኛሌ። ይህ የጥናት ዘዳ ምሳላያዊ አባባልችን ከሥነ-
ጽሐፍ፤ ከቋንቋ ሀብትነታቸው ውጪ ሇሔብረተሰባዊ ፋይዲቸው ተፈሊጊ እንዱኾኑ ያዯርጋቸዋሌ። ወዯ ይዘት ናሙናዊ
ምሌከታ ሇመንዯርዯር፤ የዕትመት ብርሃን ካዩት ምሳላያዊ አባባልች የተወሰኑትን እንይ።

(1) ምሳላያዊ አባባልች በተሇያዩ ዘመናት ተረትና ምሳላዎች አፋአዊ፤ በቃሌ የሚነገሩ፤ በቃሌ የሚተሊሇፉ ቢኾኑም
በዏማርኛ ሔትመት ከተጀመረ ጀምሮ ተጽፈው ያለ ተረትና ምሳላዎች ይህንን ይመስሊለ። ኢግናዚዮ ጉዊዱ በ1884 ዓ.ም.
ካሳተመው ብንጀመር፦ ሥጋ ኾነብኝ። ሻኛ ሇዢግና፤ ሻኛ ሇጅግና። የሰዲጅ ሇወዲጅ። ፋትልቪች በ1908 ዓ.ም. ካሳተመው:-
ከፍትፍቱ ፊቱ፤ ከፊቱ ፍትፍቱ። ያዋጁን በጆሮ። ለዊጂ ፉሴሊ በ1942 ዓ.ም. ካሳተመው ዯግሞ:- ሇማይችሇው አይሰጥ፤
ሊይችሌ አይሰጠውም / ሊይችሌ አይሰጥ። ሇቀባሪው አረደት። ማርሴ ግራውሌ እና ጆሴፍ ቱቢያና በ1972 ዓ.ም. በሔብረት
ካሳተሙት:- የበሊን ያብሊሊዋሌ / የበሊው አብሊሊው። ጉዴ እስከ እሐዴ። የተማረ የተሟረ፤ መማር መሟር /የተማረ ተሟረ።
ማርሴ ግራውሌ በ1978 ዓ.ም. ካሳተመው :- ቀስ በመቀስ /ቀስ እንዲይዯፈርስ / ቀስ እንዲይፈስ።

አንዲንዴ ምሳላያዊ አባባልቻችን በአቻ ቃሊት ሌዩነትም ከአንዴ ጊዜ በሊይ ይከሰታለ እንዯ መታፈር በከንፈር / መከበር
በከንፈር፤ በስተርጅና ሙሽርና /በስተርጅና ዴቁና፤ ከተዛመዯ የተዋዯዯ / ከተዛመዯ የተዋሇዯ፤ እየቇለ ጥሬ / እየፈጩ ጥሬ
ያሇት ዓይነቶቹ።

(2) ፍቺያዊ/ ፍካሬያዊ/ እማሬአዊ እይታ ምሳላያዊ አባባልች ብንወዴም ባንወዴም የጠፋውን (የተረሳውን) ዘሌማዴ
ማዘከሪያ ኾነው ይገኛለ። አንዲንዴቹን ብንመረምር ይህንን ኹነት እናይባቸዋሇን። አሁን ዘመን ተቀይሮ፤ ሰው ኹሇ እኩሌ
ኾኖ፤ ሌዩነቱ ሀብት ብቻ ኾኖ ነው እንጂ፤ ባዘመነው ታሪካችን፣ ሰው አቅሙ ኖረው አሌኖረው፤ እንኳን ጠጅ መጣሌ፣ በግሌ
በሬ አርድ መብሊት፣ ጥሇት ያሇው ነጠሊ መሌበስ ሇተወሰኑ የሔብረተሰብ ክፍልች የተዯነገገ መብት ነበር። ይህንን ዴንጋጌ
የተሊሇፈ ይከሰሳሌ፤ ይወቀሳሌ፤ ከንብረቱም እስከ መነቀሌ ይዯርሳሌ። በአዯባባይም፤ ባሇ ጥሇት ነጠሊ ሇብሶ የወጣ ጥሇቱ
ተቇርጦ ይሊካሌ። ከገጠር ወዯ ከተማ የዘሇቀ ግሇሰብ ‚የዏዱስ አባ ሰው ጏዲ የላሇው ነጠሊ አሌብሶ ሰዯዯኝ” ብሎሌ አለ
በአንዴ ወቅት። ሌብስ ብቻ ሳይኾን፤ ጠጅ ጥል መጠጣት፤ ማጠጣት፤ የሻኛ ሥጋ መብሊትም ሇመዯበኛው ሔዝብ የተፈቀዯ
አሌነበረም። ኢግናዚዮ ጉዊዲ በ1884 ዓ.ም.ዯብተራ ክፍሇ ጊዮርጊስን ዋቢ አዴርጏ ካሳተመው የምሳላያዊ ንግግር ጥንቅር
ይህንን የኢግናዚዮን ‚ሻኛ ሇዢግና፤ ሻኛ ሇጅግና” በኛ በዘመነኛው ‚ሻኛ ሇጀግና”ን ጥቅስ (ገጽ 33) እንይ፤ ኢግናዚዮ እንዱህ
ብሎሌ። ‚Il shagna è dovuto al valoroso Il shagna è la gobba che hanno i buoi di abissinia, e la cui
carne è assai buona e delicate; il proverbio risponde in certa guise al “à tout seigneur tout
honneur” Cf. D’Abbadie p.231. In luogo di ጅግና, nello Sciioa si dice ጃግና” "The shagna is the
bump that the oxen of Abyssinia have, and whose meat is much good and delicate; the proverb
answers in certain manners to the "honor to whom honor is due “the shagna” has to be the
courageous one." Cf. D' Abbadie p. 231.[Google translate]

10
ተጨማሪ ምሳላያዊ አባባልችን እና ፍቺያቸውን ሇአብነት ያህሌ ቀጥል እናያሇን። የሥራን ክቡርነት ሇማሳየት ‚መቀመጥ
መቆመጥ” ፤ ‚ሳይሇፉ አያተርፉ” ይሇዋሌ ዏማርኛ። ይቅር ባይነትን በዯግ ጏኑ ሇማሳየት ዯግሞ ‚ሲምሩ ያስተምሩ / ሲምር
ያስተምር” ይባሊሌ።

በግብረ-ገባዊ እሴቶቻችን ዘንዴ ፋይዲ ያሊቸው ምሳላያዊ አባባልቻችን በመንሥኤና ውጤት ተከታታይነት ያሊቸውም
ይገኛለ። የመጀመሪያው ምሳላያዊ ንግግር ውጤት ሇኹሇተኛው መንሥኤ እየኾነ ማሇት ነው። እንዯ ‚ያወቀ ናቀ” ወይም
‚የናቀ ወዯቀ” ያሇት። ‚ሌጅ በሌጅነት” / ‚ሌጅ በጅሌነት” ሌጅ በሌጅነት ሌጅነት ዯግሞ ከጅሌነት ካሊዋቂነት፣ ካሇመብሰሌ
ጋራ መተሳሰሩን ያጤኗሌ። ሌጅ መውሇዴ እና ማሳዯግ ዴካም፤ ጣመን ስሊሇው የጅሌ ሥራ ነው እንዯማሇት። በተጨማሪም
መጸሇይ ምንም ጉዲት እንዯላሇው ሲጸሌዩ መታየትም ዯረጃን ውበትን እንዯማያኮስስ ምሳላያዊ አባባልቻችን ያሳያለ።
‚አትሩጥ አንጋጥ” እና ‚ስሊንጋጠጡ አይገጡ” አንደ ነው። የባሇጋራን የባሊንጣን ዏቅም ማወቅን ጥቅም ሇማሳየት ‚ብመታው
ሰዯበኝ”፤ ‚ብጥሇው ገሇበጠኝ”ም የምትሌ ምሳላያዊ አባባሌም አሇችን።

የሰው ሌጆች ባሔርይ ኾኖ በሔብረተሰባዊ መስተጋብር የሥሌጣን ዯረጃን እንዲሇ በንጽጽር እንመሇከተዋሇን። ‚ሲወርዴ
ይዋረዴ”፤ ‚ሲያሌቅ አያምር”፤ ‚ሲያሌፍ ዋዛ”፤ ‚ታረጁ አይበጁ” የወጣ ይወርዲሌ፤ የወረዯ ዯግሞ ይዋረዲሌ፤ ማዕረጉ ዝቅ
ይሊሌ ነው። ሇሁሇም ጊዜ አሇው ሇማሇትም ‛በስተርጅና ሙሽርና”፤ ‚በስተርጅና ዴቁና” አይኾኑም ነው። ‚ሲያረጁ
አይበጁ”ምም የጡረተኛነት (የዕርጅና) ዕዴሜን አስከፊነት አመሊካች ነው። ሰው ምንም ትሌቅ፤ ምንም ሀብታም ቢኾንም
ሇመቆም፤ ሇመግዘፍ ኹሌ ጊዜ የትንሹን የአቅመ-ቢሱን ዴጋፍ ይፈሌጋሌ። ‚ጋን በጠጠር ይዯገፋሌ።” መጠንን ጋን ከጠጠር
አወዲዴራ ይቺን እሳቤ ቅሌብጭ ባሇ ቋንቋ ታሳያሇች።

ታሪካዊ፣ ዏውዲዊ ዲራቸው የሚታወቅ ተጨማሪ ምሳላያዊ አባባልችን ብናይ ዯግሞ ‚ሰው ቢማር ቄስ እንጂ ሰው መሊክ
አይኾንም።” ታሪካዊ ዲራው እንዱህ በቀዴሞው ዘመን፤ ሴተኛ ዏዲሪነት ዘመነኛ/ሌማዴ/ ወይም ባሔሌ ባሌኾነበት ጊዜ፤
አንዴ ወንዴ ሴቷን ሇወዲጅነት ጥያቄ ቄስ ይሌክባታሌ። የቄሱ መንፈሳዊ ተግባርና የተሊኩበት ጉዲይ የተጋጨባት ሴት
የሰጠችው መሌስ አካሌ ነው ምሳላያዊ አባባለ። ሙለ ግጥሙ ይህንን ይመስሊሌ።

ቢኾንም ይኾናሌ፤ ባይኾንም አይኾንም።


ሰው ቢማር ቄስ እንጂ፤ ሰው መሊክ አይኾንም።
ከእንግዲህ በኋሊ አትመሊሇስብኝ።
ሦስት ራብዕ ፊዯሌ ቇጥረኽ ዴረስብኝ።

ይህ ሰው መሌስ ተሰጥቶታሌ። ሦስቱ ራብዕ ፊዯሊት እነማን ናቸው? መሌሱ፦ ይህ ከወዲጅነት ጥያቄ ውጪ የኾነ የሰውን
የትምህርት ዯረጃ የፊዯሊችንን ቀመርና ሰዯር ከግምት ያስገባ መሌስ ነው። ወዲጅ ፈሊጊው መሌሱ ከገባው፤ ካወቀ
በተቀጠረበት ሰዓት ይኼዲሌ ማሇት ነው። ራብዕ (አራተኛ) ፊዯሊቱ ማ ታ ና ናቸው። ማታ ና፣ ና ማታ ይኾናሌ ማሇት
ነው። ማንነታችንን፤ ኑሮአችንን፣ ባሔሊችንን ገሊጭ ምሳላያዊ አባባልች በተሇይ የተወሰኑት አስዯማሚ ናቸው። እንዯ
እምነታችንም ዏጀብም፤ ዏጃ ኢብም ያሰኛለ።

11
1) ሽምግሌና በሀገራችን የተከበረ ግጭት ማብረጃ፤ ማስወገጃ፤ መፍትሓ መፈሇጊያ አይነተኛ መንገዴ ነው። ይህ ዯግሞ የበጏ
ፈቃዴ ሥራና ላሊም መስፈርት ያሇው ነው። ሇሽምግሌና የሚመረጥ ሰው የሚከበር፣ የሚዯመጥ፣ የሚታፈር መኾን
እንዲሇበት ምሳላያዊ ንግግሩ ‚ሳይታፈሩ መገሊገሌ ዕብዴ ያሰኛሌ።” አመሊካች ነው።

2) ‚ሦስት ጉሌቻ ይስጥህ። ሦስት ጉሌቻ ይቅጣህ።” ፦ ከሰው ሌጅ ግንኙነቶች አብሮ መኖር፣ ትዲር አንዴና ፈታኙ ነው።
ይህንን አስመሌክቶም የቻሊቸው አሸናፊን የዘፈን ግጥም አንዴ አንጓ እነኾ

ስሌቻው ቀዲዲ፣
መጫኛው ቁጥርጥር፣ በሬው መቀናጆ፣
ብርቱ ሰው አዴካሚ፣ እንዯምን ነሽ ጏጆ?

ሦስት ጉሌቻ ይስጥህ፤ የበሰሇ፣ የሞቀ ብሊ፣ ጭቅጭቅ ከቤትህ ይራቅ፤ ቤትህን በረከት ይሙሊው፤ የሞቀ ቤት ይኑርህ ነው።
ሦስት ጉሌጫ ይቅጣህ በአጭሩ ትዲር ‚ቅጣት ነው” ሀሊፊነት ነው። የተሳካ ትዲር (ስመ-ትዲር ሳይኾን) ጠንካራ ግብረ-ገባዊ
ኢኮኖሚያዊ እና አካሊዊ አቅም ይፈሌጋሌ። ከቻሊቸው ግጥም እንዲየነው ሞሌቶ አይሞሊም፤ አንደን ሲሇት አንደ ይጏዴሊሌ፤
እንዱሁ ባተላ እንዯተኾነ መሽቶ ይነጋሌ፤ ቀናትም ወራትም ዓመታት ያሌፋለ። ‚ወሊዴ ትጮኻሇች፤ መኻን ትተኛሇች።”
የሚባሇውም ሇዚሁ ሇጏጆ ነው። ሌጅ የወሇዯች ሴት የእርሷን መኖር ታቆምና ሇሌጇ መኖር ትጀምራሇች ነው። የእማወራ
ሚና ከሚስትነት ወዯ እናትነት ይሸጋገራሌ። ጏጆ ዯግሞ ጏጆ፣ ትዲርም ትዲር የሚኾነው ሌጅ ሲኖርበት ነው። ቀጣዩዋ
የሔዝብ ግጥም ይህንን አሳብ በዯንብ ታሳያሇች።

ኧረ ሌጅ ማሠሪያው ኧረ ሌጅ ገመደ፣
ጏጆማ ምን አሊት? ጥሇዋት ቢኼደ።

በተያያዘም ሌጅ ማሳዯግ ሥርዏት አሇው። ‚ግረፍ (ግን) ከባት አትሇፍ።” ሌጅ አቀጣጥ፤ እጅ እንዯፈቀዯ ሳይኾን ወግ
እንዲሇው አመሊካችም ነው። አገኘሁ፣ አቅም አሇኝ ተብል ዝም ብል አይመታም ነው የምሳላያዊ አባባሌ መሌዕክት።

ይህንን የምሳላያዊ አባባልች ስብስብ ሥራዬን ከሚያውቁት አንዶ እንዲሇችኝ ምሳላያዊ አባባልች የ‛ባሌቴቶች ወሬ” የሥራ
ፈቶች፣ የኋሊ ቀሮች ቧሌት አይዯሇም። ምሳላያዊ አባባልቻችን እንዱያውም ሀገር- በቀሌ ዕውቀትን፤ ሳይንሳዊ ዕውቀትን
አካቷሌ። የእኛ ተግባር መፈተሽ ብቻ ነው። ‚ጅብ ሉሰር ኺድ ተሰሮ ገባ። ፍየሌ በግርግር እናቱን ይሰርራሌ።” የጅብን
ፍናፍንት መኾን የፍየሌ ወጠጤ ሇተራክቦ ሴቲቱ ፍየሌ ሊይ ሲዯርስ እናቱ መኾኗን እንኳን አያስተውሌም ነው። ከዚህ
የበሇጠ ማስረጃ ምን ያስፈሌጋሌ? የቋንቋችንን ሀብት ቧሌት አሇመኾኑን ሇማሳየት። ማሔበረሰባዊ ግንኙነታችን ውስጥ
ሰሊምታ አንደ ነው። ምሳላያዊ አባባለ እንዯሚሇው ‚ሦስት ጊዜ እንዳት ዏዯራችኹ አንደ ሇነገር ነው።” ይህንን ያሌተጻፈ
ዯንብ ጥሶ ሰሊምታ ሇዯገመ ችግር አሇ፤ ነገር አሇ ማሇት ነው። ሦስት ጊዜ እንዳት ዏዯራችኹ አንደ ሇነገር ነው። ምሳላያዊ

12
አባባለ የነገር ጫሪውን መፍራት፤ ፈራ ተባ ማሇትንም ያሳያሌ። በምሳላያዊ አባባልቻችን የገበያ፣ የንግዴ ዕውቀትም ቢኾን
አይቀርብንም። ‚ቅቤ ነጋዳ ዘወትር ስሇ አቧራ ያወራሌ።” ‚ቅቤ ነጋዳ ዴርቅ ያወራሌ።” ቅቤ ቅባት ስሇኾነ ያወዛሌ ቅቤ
እርጥብ ነው። ስሇዚህ ሇመሸጥ ዋጋ ሇማስወዯዴ ዴርቅ ያወራሌ፤ የንግዴ ባሔሪው ስሇኾነ ማሇት ነው። ከዚኹ ከገበያና
ከንግዴ ግንኙነት ሳንወጣ ‚በሬ ግዙ ግዙ አንዴ ጨው ሊያግዙ።” የተሰኘው ምሳላያዊ አባባሌ ሰው መክሮ፤ ጏትጉቶ ዲፋ
ውስጥ ከትቶ በአራድቹ አባባሌ ማኖ አስነክቶ፤ ዕዲ ውስጥ ዘፍቆ ዞር እንዯማሇት ነው። (ጨው ብር ሇማሇት ነው። ጨው
(አሞላ ጨው) በዘመኑ መገበያያ ገንዘብ እንዯነበረም ያስተውሎሌ)። የሀብትን ነገር ካነሣን ‚ጮማ የበሊችኹ ጏመን የበሊነ
አብረን (ዘመን) ወጣን።” የተሰኘ ምሳላያዊ አባባሌም አሇን። አብሮ መኖር ይበሌጣሌ እንጂ ኹሊችንም ካሰብነው መዴረስ
አይቀርም ሇማሇት ነው መሌዕክቱ። ጮማ/ ሥጋ በዘመነኛው እሳቤ የበሽታ ምንጭ ቢኾንም የሀብታም ምግብ ነው። ጏመን
ዯግሞ የዴኻ ምግብ ነበር። ጮማም ብንበሊ፤ ጏመንም ብንበሊ፤ ኹሊችንም ዘመን እንሻገራሇን፤ ይቺን ቀን እናሌፋሇን፤
ሇሚያሌፍ ቀን አንተዛዘብ ነው መሌዕክቱ። በመጠጥም በኩሌ ቢኾን ምሳላያዊ አባባሊችን አይሰንፍም። ውሃ የዴኻ መጠጥ
ሲኾን፣ ሀብታም ቤት ሲኾን ጠጅ፣ ሲጠፋ ጠሊ ነው የሚጠጣው። የዴኻውን የጏመን እና የውሃ ጤና መስጠትን ሇማሳየት
‚ውሃን ማን ሰጠው ሇዴኻ” ትሊሇች ምሳላያዊ አባባሊችን።

የባሔሌ ምንነትን ብየናውን ቅሌብጭ ባሇች አገሊሇጽ ምሳላያዊ ንግግራችን ‚ጽዲት ሇምኔ ቁናስ ባሔላ።” ትሇናሇች።
የተዯጋገመ ነገር ሲጀመር ሌማዴ ሲዯገምም ሲሠሌስም አሌፎም ባሔሌ ይኾናሌ ማሇት ነው። ምሳላያዊ ንግግር ሇዏዱሱ
ትውሌዴ ባሔሌንም የነበረን ማሔበረሰባዊ መስተጋብርንም ማሳያ ነው እንዯ ‚ውቤ በረሒ (በ3 ቀን) አዯረግሸኝ ዴኻ” ዓይነቱ
ምሳላያዊ አባባሌ። ይቺን አባባሌ ሉሊት የሚችሇው በወር ዯመወዝ የሚያዴር ነው። ዯመወዙን ተቀብል ውቤ በረሒ ኼድ
(መጠጥ ቤቶች፣ ሴተኛ ዏዲሪዎች ሰፈር (ታሪክ ፦ ውቤ በረሒ ዏዱስ አበባ ከቅደስ ጊዮርጊስ በሊይ ያሇ ሰፈር በዯጃች ውቤ
የተቇረቇረ) ገብቶ የ30 ቀን ምንዲውን፤ የወር ዯመወዙን በኹሇትና በሦስት ቀን ጨርሶ አጨብጭቦ ገባ። የገንዘቡ ማሇቅ
ቢቇጨው ውቤ በረሒ በ 3 ቀን አዯረግሽኝ ዴኻ አሇኣ። ‚ጸጉር ሳይሸብት፣ እግር ሳይሸት አይቀርም።” ፦ ይህ የተፈጥሮ ሔግ
ነው። ጥቁሩ ጸጉር ነጭ፣ የታጀሇ እግርም፤ በጫማ የተሸፈነም በአመዛኙ ይሸታሌ ነው። እርግጥ ነው ራሰ-በራ መኾን አሇ።
እርግጥ ነው በባዴ እግር መኼዴ አሇ። እርግጥ ነው ባንዲንዴ ምክንያት እግራቸው ፈሳሽ የማያመነጭም አሇ - ይህ ግን
ያሌተሇመዯ ነው።

እንዯ መዯምዯሚያ፦ ምንም እንኳን በዚህ ‚ምሳላያዊ አባባልች በዏማርኛ” መጽሐፍ ውስጥ ባይካተቱም በነበሩት ሊይ
ተሻሽሇው የወጡ ምሳላያዊ አባባልች አለ። ይህ የተናጋሪዎቹን ፈጠራ የሚያሳዩ፤ ዘመንን የሚያመሊክቱ፤ የኑሮ ውዴነትን
የሚጠቁሙ ኾነው አግኝቻቸዋሇሁ።

ኹሇት ጉዴጓዴ ያሊት አይጥ፣ አንደን አከራየችው።


ቁንጮን ሲያታሌሎት፣ ፓንክ ብሇው ጠሯት።
ብሌጥ እስኪያስብ ሞኝ ይወሌዲሌ።
እንቁሊሌ ቀስ በቀስ በብር አንዴ ይኾናሌ።
ከባሌሽ ባላ ይበሌጣሌ፤ ማይክሮ ዌቭ አበዴሪኝ።

13
ወሬ ቢቇሇሌ፣ በአህያ አይጫንም።
የቇጡን አወርዴ ብሊ ሇትንሽ ወዴቃ ነበር።
የቇጡን አወርዴ ብሊ መሬት ሊይ ወዯቀች።
የቇጡን አወርዴ ብሊ ወንበር ሊይ ወጣች።
የቸኮሇች፣ እየሮጠች ኼዯች።
የነቶል ቶል ቤት ግርግዲው ኖራ ነው።
የአህያ ባሌ ሲስም ያሳምማሌ።
ፈሰስም ተጋቢኖም፣ ያው ሽሮ ነው።

በመጨረሻም ከ20 ሺሔ ምሳላያዊ አባባልች በሊይ ያካተተውን የዏማርኛ ምሳላያዊ አባባልች ስብስብን መጽሏፍ
እንዴታነቡ፤ እንዱኖራችኹ እየጋበዝኩ፤ ይቺን መንዯርዯሪያዬን (መቇስቇሻዬን) ተጨሌፎ ከማያሌቀው የዕውቀት የታሪክ፤
የባሔሌ የአኗኗር ማኅዯራችን ማሳያ ምሳላያዊ አባባልች በአንደ በቀዲማዊ ኃይሇ ሥሊሴ (ቀኃሥ) ተዘውታሪ ምሳላያዊ
ንግግር ሊሳርግ። ቀኃሥ በምሳላያዊ ንግግራቸው ከሚታወሱ የኢትዮጵያ መሪዎች አንደ ናቸው። ከትምህርት፤ ከኑሮ ራስን፤
በዕውቀት ከማዘመን ጋራ በተያያዘ በአንዴም በላሊም ዏውዴ እነዚህን ‚መከራን የቻሇ አሸናፊ ነው።”፣ ‚ያሊነበበ ያሌተማረ
ቤቱን በዴቡሽት (በዯቃቅ አሸዋ) ሊይ እንዯሠራ ሰው ይቇጠራሌ።” የተሰኙትን ምሳላያዊ አባባልችን ቀኃሥ መጠቀም
ያዘወትሩ ነበር።

መሌካም የምሳላያዊ አባባልች ማሰሊሰያ ጊዜ።

የጥቅስ ምንጮች
መስፍን መሰሇ። 1999 ዓ.ም.። የሥያሜ ችግር በሥነ-ቃሌ ናሙናዊ ጥናት። ዜና ሌሳን፤ አቋጥማ። 7.2:37-67።
ዓሇም እሸቱ። 1999 ዓ.ም.። ተግባራዊ የዏማርኛ ትምህርት ማጠናከሪያ (ከ7ኛ- 10ኛ ክፍሌ)። ዏዱስ አበባ፤ ብራና ማተሚያ ዴርጅት።
ወንዴወሰን አዲነና ዓሇም እሸቱ። 1995 ዓ.ም.። ዏማርኛ የተማሪው መጽሐፍ ዏሥራ አንዴኛ ክፍሌ። ዏዱስ አበባ፣ት.መ.ማ.ማ.ዴ.።
ዘሪሁን አስፋው። 2002 ዓ.ም.። የሥነ-ጽሐፍ መሠረታውያን። ዏዱስ አበባ፤ ንግዴ ማተሚያ ዴርጅት።
Faitlovitch, Jacques. 1907. የሏበሻ ተረት Abyssins: traduits, expliques et ennotes. Paris:Paul Geuthner.
Faitlovitch, Jacques. 1908-09. “Nouveaux proverbs Abyssina”, Rivesta di studi orientali. 2:757-766.
Fusela, Luigi. 1942. “Proverbi amarici” Rassegna di studi etiopici.anno. 2.3:283-311.
Griaule Marcel & Tubiana Joseph. 1972. Proverbes abyssins. Journal de la Société des Africanistes. Tome 42
fascicule 1. pp.55-88. Doi: 10.3406/jafr.1972.1698
Griaule, Marcel.1975. “Proverbes Abyssins, recueillis et traduits”. Journal de la Societe des Africanistes. 45:149-
180.
Guidi, Ignazio. 1892. “Nuovi proverbi strofe e racconti abissini”, Giornalle della Societa Asiatica Italiana. 6:3-36.
Guidi, Ignazio. 1894. “Proverbi, strofe e racconti abissini” tradotti a publicati da Ignazio Guidi. Roma: Tipografia
della Reale Academia dei Lincei.

ዲንኤሌ አበራ
ጥቅምት 2019

14

View publication stats

You might also like