You are on page 1of 7

ሥነጽሑፍ ምንድነው?

ሥነጽሑፍ ማለት ህልውናው በቃልና በፅሑፍ የሆነ በሰው ተዘጋጅቶ፣ ስለሰው አትቶና መልሶ ለሰው የሚቀርብ
አብይ የኪጥበብ ዘርፍ ነው፡፡

ስነጽሁፍ የሰውን ልጅ ጉዳዩ ያደረገ ስሜታዊ ፣መንፈሳዊና አዕምሯዊ ነገሮችን ለማግባባት የሚያገለግል
የምናብ እና የፈጠራ ስራ ነው፡፡ ልቦለዳዊነቱ፣ ምናባዊነቱ፣ ትርጉማዊነቱ፣ የአገላለጽ ስልቱና ስሜት ሰጭነቱ
መለያው ናቸው፡፡እንደ ታሪክ ጸሀፍት ተመራማሪዎች እና ጋዜጠኞች የስነ ጽሁፍ ጸሀፊ በትክክል የተደረገውን
ምክንያት የማቅረብ ግዴታ የለበትም፡፡ በትክክል የሆኑ ነገሮችን የመቅረጽ እና የማደራጀት ነጻነት አለው፡፡

ስነጽኁፍ የምንለው በቋንቋ አማካይነት በተለያዩ የአቀራረብ ስልቶች ተቀናጅቶ የሚቀርብ የሰው ልጆች
ገጠመኝ ነው፡፡ይህ ገጠመኝ እውነትንና ህይወትን ባንድ አጣጥሞ በቃልም ሆነ በጽሁፍ የሚቀርብ የፈጠራ ስራ
ነው፡፡ይህ የፈጠራ ስራ ስነግጥምን፣ አጭርና ረጅም ልብወለድን ተውኔትን /ድራማን/፣ስነቃልን የሚያጠቃልል
ሰፊ ክፍል ነው፡፡እነዚህ የስነጽኁፍ ክፍሎ የየራሳቸው የሆነ ባህርያት ያላቸው ያህል የሚያመሳስላቸው የጋራ
ባህርያትም አሏቸው፡፡

የሥነጽሑፍ ዘርፎች የሚባሉት አራት ናቸው፤ እነዚህም፡-

 ልቦለድ
 ግጥም
 ስነ-ቃልና
 ተውኔት ናቸው፡፡

ልቦለድ፡- ማለት አንድ ደራሲ ምናባዊ ችሎታውን ተጠቅሞ የገሃዱ አለምን ህይወት በስፋት ወይም አንዷን
ነጠላ ገጠመኝ መነሻ በማድረግ በምናቡ የፈጠራቸውን ገፀባህሪያት በመጠቀም እውን አስመስሎ
የሚያቀርብበት የስነፅሁፍ ዘርፍ ነው፡፡

ልብወለድ የምንለው በእውነተኛው አለም የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን የሚያሳዩአቸውን ሰዋዊ ባህርያትና


ክንዋኔዎች እውነት አስመስሎ የሚቀርብ የስነጽኁፍ ቅርፅ ነው፡፡በልብወለድ ውስጥ የህይወት እውነት
የሚንፀባረቅበት ይሁንእንጂ በቁሙ ግን እውነት አይደለም፡፡ማለትም በልብወለድ ውስጥ የተፈፀመው
ክንውንና ድርጊቱን የፈፀሙት ገፀባህርያት በእውነት አለም የነበሩና ድርጊታቸውም እውነት የሆነ አይደለም፡፡
ይሁንእንጂ ልብወለድ ከማህበራዊ ገጠመኝና ሊደርስ ይችላል ብሎ ደራሲው በምናብ ከሳለው የህይወት
እውነት የሚመሰረት በመሆኑ የማህበረሰቡን ህይወት የሚንፀባርቅ ነው፡፡
ልብወለድ የህይወትን እውነት የማንፀባረቅ ባህሪው ከሌሎች የስነጽሁፍ ዘሮች ጋር የሚጋራው ሲሆን
የራሱ የሆነም ባህርይ አለው፡፡
ልብወለድ
- በምናብ ከተፈጠረ አለም አንባቢን ይዞ የሚያስገባ ነው፡፡
- በደራሲው የተፈጠረ በመሆኑ አዲስ የሚባል ነው፡፡
- በዝርው የሚፃፍ ነው፡፡
- ረጅም የትረካ ስልትን ያስተናግዳል፡፡
- ረጅም በመሆኑ የገፀባህርያትን ህይወት ይተርካል፡፡
- በርካታ የህይወት ገፅታዎችን እንዲተነትን ቅርፁ ይፈቅድለታል፡፡

ልብወለድ የምንለው የገሃዱ አለምን እንደመስታወት ገልብጦ የሚያሳይ ኪነጥበባዊ ዋጋ ያለው የስነጽሁፍ ዘር
ነው፡፡የገሃዱ አለም ነፀብራቅ በመሆኑም የህይወት ስእል ነው ይባላል፡፡ይህም ማለት ህይወትን በቃላት ቀለም
አስውቦ የሚቀርብ ስለሆነ ነው፡፡

የልቦለድ አላባውያን
የልቦለድ አላባውያን ማለት ልቦለዱን የሚመሰርቱት መሰረታዊ ፍሬነገሮች ናቸው፤እነዚህም ሰባት ሲሆኑ
የሚከተሉት ናቸው፡፡ አንድ ደራሲም ልብወለድ ለመፃፍ ሲነሳ ትኩረት የሚደርገው በእነዚህ ፍሬነገሮች ላይ
ነው፡፡ እነዚህም የልብወለድ አላባውያን የሚባሉት ታሪክ፣ ትልም፣ ገፀባህርይ፣ ግጭት፣ መቼት፣ ጭብጥ፣ አንፃር
ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ታሪክና ገፀ-ባህርያትን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

፩.ታሪክ
ከልብወለድ ፍሬነገሮች መካከል አንዱታሪክ ነው፡፡ታሪክ የአንድ ልብወለድ ቀዳሚነገር ነው፡፡ማለትም
ልብወለዱ የሚነግረን ሃሳብም ሆነ መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞከረው በታሪኩ ነው፡፡ለዚህም ነው
አንድ ሰው ስለልብወለዱ መጽሀፍ ሲጠየቅ መጀመሪያ የሚያስታውሰው ታሪኩን ሲሆን ለመግለጽም
ሲነሳ እንደዚህ እንደዚህ አይነት ታሪክ ያለው መጽሀፍ ነው በሚል ነው፡፡
የገፀባህሪያት ድርጊት በጊዜ ቅደም ተከተል የተደረደሩበት ሁነቶች ትረካ ነው፡፡
 ለልቦለድ ቀዳሚ ነገር ነው፡፡
 የልቦለዱ አፅም ነው፡፡
 ታሪክ የድርጊቶችን ቅደም ተከተል ቁልጭ አድርጎ የማሳየት ባህርይ አለው፡፡
 ታሪክ የማጓጓት ባህርያ ያለው መሆን አለበት፡፡
 የታሪክ ሌላው ባህርይ ተአማኒ መሆን መቻል ነው፡፡
 ታሪክ በሰው ልጆች ገጠመኝ መነሻነት የድርጊትን ቅደም ተከተል በጊዜ እያከታተለ ተአማኒና
የሚያጓጓ ሆኖ የሚቀርብ የልብወለድ ፍሬነገር አንዱ ክፍል ነው፡፡

፪. ገፀባህሪ

 ገፀባህርያት ፡ የልብወለዱ ታሪክ ባለቤቶች ናቸው፡፡ገፀባህርያት የነበሩበትን ጊዜና ቦታ መሰረት


አድርገው መቀረጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ገፀባህርያት ስብእናቸው ተአማኒነት እንዲኖረው ወጥነትና
ኢፍፁምነት ያላቸው ሆነው መቀረፅ ይኖርባቸዋል፡፡ገፀባህርያት የገሃዱ አለም ሰዎች
የሚያከናውኑትን ሁሉ የሚያደርጉ የልብወለድ አለምሰዎች ናቸው፡፡

በልቦለድ ፅሁፍ ደራሲው ከምናቡ አመንጭቶ የሚፈጥራቸው የገሐዱ አለም ሰዎችን የሚወክሉ ፍጡራን
ናቸው፡፡

 የገፀባህሪያት አመላመል፡- ታማኝና ስብዕናን የተሞሉ መሆን አለባቸው፡፡


o የባህሪ ዘላቂነት ሊታይባቸው ይገባል፡፡
o ኢ-ፍፁምነት
o የእርሰ በእርስ ግንኙነት
 የገጸባህሪያት አቀራረብ ዘዴዎች፡-
ሀ.ቀጥተኛ/ርቱዕ/ አቀራረብ- ገፀባህሪያቱ በቀጥታ በመግለፅ የሚያቀርቡ ሲሆን ገፀባህሪያቱ ምን
እንደሚመስሉ ተራኪው ቆሞ የሚታዘብ ገፀባህሪ ይነግረናል፡፡
ለ. ኢ-ቀጥተኛ/ኢ-ርቱዕ/ አቀራረብ- ገፀባህሪያትን በድርጊት ያሳያል
-ተውኔታዊ አቀራረብ ይባላል

የገፀባህሪያት አይነቶች

ሀ. ፈርጀ ብዙ፡ - ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተሳሉ በመሆናቸው በቀላሉ የማይታወቁ ናቸው፡፡

 ምኞታቸውን፣ አመለካከታቸውንና ሙሉ ስብዕናቸውን በቀለቀሉ ለመረዳት ያዳግታል፡፡


 በልቦለድ ውስጥ ከምዕራፍ ምዕራፍ የሚሸጋገሩ እንጅ ወዲያው የሚከስሙ አይደሉም፡፡
 አብዛኛው የልቦለዱ ታሪክ የሚያጠነጥነው በእነሱ ህይወት ዙሪያ ነው፡፡

ለ. ፈርጀ አንድ፡ - በተደጋጋሚ የሚታዩ አንድ የተወሰነ ባህሪ ወይም ልምድ አላቸው፡፡

 ብቅ ባሉ ቁጥር ወዲው ሊለዩ ይችላሉ፡፡


 በብዙ አቅጣጫ ያልተቀረፁና ውስብስብነት የሌላቸው ናቸው፡፡
፫. መቼት፡-የልቦለዱ ታሪክ የተፈፀመበት ጊዜና ቦታ ማለት ነው፡፡
 መቼት ጓዘ ብዙ ነው፡፡ ለምሳሌ መልክዓምዳራዊ አቀማመጥ፣ ቤቶች፣ ህንፃዎች፣ ጎዳናዎች፣
የገበያ ቦታዎች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች ፣ ባህላዊ አለባበሶች፣ ባህላዊ አመጋገቦች ወ.ዘ.ተ.
የመቼቱ አካል ናቸው፡፡
፬. ግጭት፡ አንዱ ገፀባህሪ ከሌላወ ገፀባህሪ ገሰር የሚፈጥረው ንትርክ ፣ ገፀባህሪያቱ ይህን ልፈፅም
ወይስ አልፈፅም ብለው ከራሳቸው ሀሳብ ጋር ሚፈጥሩት ቅራኔ ነው፡፡
 የታሪኩ የጀርባ አጥንት ነው፡፡
 የታሪኩ አብ ሞተር ነው፡፡
 የሚጋጩት ገፀባህሪያት ተመጣጣኝ መሆን አለባቸው፡፡
 ግጭቱ በእዉኑ አለም ሊያጋጥም የሚችልና ታማኒ መሆን ይኖርበታል፡፡
 ግጭት ሂደቱን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡

የግጭት አይነቶች፡-

 ሰው ከራሱ ጋር፣
 ሰው ከሰው ጋር፣
 ሰው ከማህበረሰቡ ጋር
 ሰው ከፈጣሪው ጋር
 ሰው ከእንስሳት ጋር
፭. ትልም/ሴራ፡- በምክንያትና ውጤት የተሳሰሩ ድርጊቶች ቅደም ተከተል ነው፡፡
 የልቦለዱ ምሳሶ ነው፡፡
፮. ጭብጥ፡- በልቦለዱ ሊተላለፍ የተፈለገው ዋነኛ መልዕክት ነው፡፡
 የልቦለዱ ፍሬነገር ነው፡፡
 ማዕከላዊ ትኩረት ነው፡፡
 ማንኛውም ልቦለድ የሚፃፍበት ዓላማ ነው፡፡
፯. የትረካ አንፃር፡- ደራሲው ታሪኩን የሚያቀርብበት የትረካ አቅጣጫ ነው፡፡
-ወሬ ነጋሪ ነው፡፡

የልቦለድ ዘዴዎች

 የልብወለድ ዘዴዎች የሚባሉት የልብወለዱ አላባውያን ተቀናጅተው ልብወለዱን እንዲፈጥሩ


የሚያደርጉ ስልቶች ናቸው፡፡የልብወለድ አላባውያን በተናጠል ልብወለዱን ህይወት ሊዘሩበት
አይችሉም፡፡የልብወለድ ፍሬነገሮች በውህደት ሙሉ የሆነውን ልብወለድ ማሳየት የሚችሉት በእነዚህ
ዘዴዎች አማካይነት ነው፡፡
 ስለዚህ የልብወለድ ዘዴዎች ለአንድ ልብወለድ ስኬታማነት ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታሉ፡፡ ከእነዚህ
የልብወለድ ዘዴዎች መካከል ምልልስ ፣ ምልሰት፣ንግርና ገለፃን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

የልቦለድ ማቅረቢያ ዘዴዎች 4 ናቸው፤ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩. ምልልስ፡
በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ገፀባህሪያት መካከል የሚደረግ የሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡
 ምልልስ
 የገፀባህርያቱን ማንነነትና ስነልቡና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡
 ስለሚኖሩበት አካባቢያ ላቸውን ግንዛቤ ለማወቅ ያስችላል፡፡
 የልብወለዱን ታሪክ ወደፊት ለማራመድ ይጠቅማል፡፡
፪. ገለፃ፡
የገፀባህሪያቱን መልክ፣ቁመና፣አለባበስና ስሜት መቼቱን ጨምሮ በማቂረብ አንባቢው
እንዲመለከታቸው ያስችላል፡፡

ገለፃ የሚባለው የገፀባህርያቱን መልክ፣ ቁመና፣ ስሜትና አመለካከት ፍንትው አድርጎ የሚያቀርብ
የልብወለድ ማቅረቢያ ዘዴ ነው፡፡ይህ ዘዴ የገፀባህርያቱን ውስጣዊና ውጫዊ ማንነት ለአንባቢያን
የሚስተዋውቅ ነው፡፡ከዚህም ሌላ ገፀባህርያቱ የሚንቀሳቀሱበትን አካባቢምን እንደሚመስል ቁልጭ
አድርጎ ማሳየት የሚቻልበት ስልት ነው፡፡

፫. ንግር፡ በታሪኩ ሂደት ወደፊት ለሚፈፀም ድርጊት አጋጣሚ ወይም ሁነት ፍንጭ ወይም ጥቆማ
የሚሰጥ ስልት ነው፡፡ ልብ ሰቀላ መኖር አለበት፡፡
፬. ምልሰት፡ አሁን በመተረክ ላይ ካለው ዋነኛው የታሪኩ ክፍል ወይም በትልሙ ጉዞ አስቀድሞ
የተፈፀመን ድርጊት በማስገባት የሚቀርብ የአተራረክ ዘዴ ነው፡፡
 በልቦለዱ ውስጥ ያሉ ገፀባህሪያት አሁን ላላቸው ስብዕና መነሻቸው ምን እንደነበረ ፍንጭ
ይሰጣል፡፡

አጭር ልቦለድ

ጠባብ መጠነርዕይ ያለው፣ ቁጥብ፣ የሆነ፣ የጠበቀ አንድነትና ጥድፊያ የተሞላበት ዘውግ ነው፡፡

 አጭር ልብወለድ የምንለው በእጅጉ የተጨመቀ ሃሳብን የሚያስተላልፍ የልብወለድ አይነት ነው፡፡በዚህ
የልብወለድ አይነት የሚተርኩ ወይም የሚገለፁ ወይም የሚደረጉ ክንውኖች ሁሉ እጅግ ፈጣን
ቢሆኑም ጥብቅ የሆነ ትስስር የሚታይባቸው ናቸው፡፡ በአጭር ልብወለድ ውስጥ አንድ ብቸኛ
የትኩረት ነጥብን የሚተነትን ነው፡፡

 አጭር ልብወለድ በግማሽ ሰዓት ሊነበብ የሚችል የፈጠራ ስራ ነው የሚሉ አሉ፡፡በግማሽ ሰዓት
ይነበባል ማለት የልብወለዱ መጠን አጭር ነው ለማለት እንጂ ጎደሎነትን ለመጠቆም አይደለም፡፡
አጭር ልብወለድ ከረጅም ልበወለድ የሚለየው በስፋትና በጥበት እንጂ በምሉእነትና በጎዶሎነት
አይደለም፡፡ምሁራን የሁለቱን ልዩነት ሲያብራሩ በሟሟሻ ወይም በእንጎቻ እንጀራና በዋናው እንጀራ
መካከል ያለው ልዩነት ነው የሚታይባቸው ይላሉ፡፡የእንጎቻ እንጀራ ከዋናው እንጀራ በስፋት ብቻ እንጂ
የሚለየው በቅርፅም ሆነ በአይነት ተመሳሳይ ነው፡፡

የአጭር ልቦለድ ባህሪያት፡-

 ነጠላ ውጤት
 ጥድፊያ

ረጅም ልቦለድ አጭር ልቦለድ


ተ.ቁ ደራሲ መፅሐፍ ደራሲ መፅሐፍ
1 ሀዲስ አለማየሁ ፍቅርአስከ መቃብር ተመስገን ገብሬ የጉለሌው ሰካራም
2 አቤ ጉበኛ አልወለድም አዳም ረታ ማህሌት
3 በኣሉ ግርማ ከአድማስ ባሻገር ታደሰ ሊበን መስከረም
4 ብረሃኑ ዘሪሁ የታንጉት ሚስጢር ስብሃት ገ/እግዚአሔር አምስት ስድስትሰባት-

5 ዳኛቸው ወርቁ አደፍርስ አየለተካና አብዱራህመቶ ሙሽራውና ሌሎች-


6 ይስማዕከ ወርቁ ዴርቶጋዳ ሙሉጌታ ጉደታ የአራዳ ልጆች
7 ፍቅረማርቆስ ደስታ ከቡስካ በስተጀርባ- ስብሀት ገ/እግዚአብሔር አምስት፣ስድስት፣ሰባት
8 ብርሃኑ ገበየሁ የቴዎድሮስ እንባ
 ቁጥብነት

You might also like